አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ልጩህበት !


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በጥላሁን

ስራዬን በጀመርኩ በ ሀያኛው ቀን ላይ እንደተለመደው እራቴን በልቼ ቡናዬን ጠጥቼ ከምሽቱ 3:15 ላይ ወደ ስራ ወጣሁ እስከ ምሽቱ አምስት ሰአት ድረስ ሲዝናኑ ካመሹት መሀል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ቤታቸው ከፊሉን ከመጠጥ ቤት አልጋ ወደያዙበት ሌላ ሆቴል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ሌላ መጠጥ ቤት ሳገላብጥ ቆየሁ።

ከምሽቱ 5:10 አከባቢ አንድ
ቀን ቀን ሆቴል ሆኖ ማታ ማታ ቅልጥ ወዳለ ጭፈራ ቤት ወደ ሚቀየር ሆት-ጭፈራ ቤት ከውስጥ የሚወጣ እና ትራንስፖርት መጠቀም የሚፈልግ ሰው እስኪወጣ ለመጠባበቅ ጠጋ ብዬ እንደቁምኩ አይኔ አንዲት ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሚጣል ነገር የሌላት በዛው ሰአት ሰማይ ላይ እንዳለችው ጨረቃ ደስ የሚል ውበት ያላት ልጅ መግቢያ በሩ በስተቀኝ ብርዱን ለመቋቋም ከጡቶቿ በታች እጆቿን አጠላልፋ በማጣመር ቆማለች።
ሁኔታዋ ሲታይ ግራ ግብት ያላት ትመስላለች እዛው ቆማ አንዴ ቁልቁል አንዴ ሽቅብ ትገላመጣለች ።

እድሜዋ በግምት በ 19 እና በ21 መካከል ቢሆን ነው ይቺን የመሰለች ልጅ በዚህ ሳአት ሊያውም ብቻዋን እንዴት? ትልቁ የውስጤ ጥያቄ ነበር ።
አከባቢው ለኔ አዲስ ባይሆንም ልጅቷ ግን ለአከባቢው እዲስ ሳትሆን አትቀርም ከዚህ በፊት አይቻት አላውቅም ከባጃጄ ወርጄ ምነው ብቸሽን ልበላት አልበላት እያልኩ ከፍርሀቴ ጋር ስነታረክ አንዱ ስልክ ሊያናግር ከውስጥ ወደ ውጪ ወጣና ወድያው ስልኩን አናግሮ እንደጨረሰ አብረን እንግባ ብሎ ልጅቷ ላይ ሙዝዝ አለባት ከዛ በፊት እንደማይተዋወቁ ከሁኔታዋ ተረዳሁ።

ድርቅ ሲልባት ብስጭት ብላ ውዝውዝ ቅንጥስ ብጥስ እያለች ቀጥታ ወደኔ ባጃጅ መጣች ከመድረሷ በፊት ባላየ ፊቴን ወደ ፊት ለፊት አዞርኩ።
ደርሳ " ይቅርታ ወንድም ግቢ ትወስደኛለህ? ኮንትራት "
አለች ዩንቨርስቲ ማለቷ ነው ልጅቷ የዩንቨርስቲ ተማሪ እንደሆነች ለማወቅ ግዜ አላጠፋሁም ዩንቨርስቲው ደግሞ ከከተማው ትንሽ ወጣ ይላል
200 ብር ትከፍያለሽ አልኳት
ግማሽ ፊቷ ላይ ዘንፈል ብሎ ጋደም ያለውን ፀጉሯን በቀኝ እጃ ሁለት ጣቶች ወደ ጀርባዋ ብትን አደረገችና
"200 ብር ለተማሪ አይበዛም ወንድሜ ቤተሰብ በወር የሚልክልኝ እኮ 300 ብር ነው !" አለችኝ

መጀመሪያ አሳዘነችኝ !

ቆይቼ ደግሞ ታድያ አርፈሽ ትምህርትሽን አታጠኝም በዚህ ሰአት እዚህ ምን ትሰሪያለሽ ?!ልላት ፈለኩና እሷን እንዲህ ለማለት ምንም አይነት መብት እንደሌለኝ ቶሎ በማስታወሴ ምላሴን ሰበሰብኩ።

"እ ምናልክ " አለችኝ ።

በደንብ ተመለከትኳት። ውስጤ ተላወሰ ።
እሺ ግቢ እንሂድ አልኳት
"በስንት?" አለችኝ
ደስ ያለሽን ትከፍያለሽ ዘላ ገባች ። ትንሽ በዝምታ እንደተጓዝን ድንገት ዘወር አልኩና•••
•••ሂሳብም አስቀንሰሽ ዝምም ብለሽ አያዋጣኝም !
"ኦኬ እእእእእ ግን ይቅርታ በናትህ ከሚከብዱኝ ነገሮች አንዱ ጫወታ ቀድሞ መጀመር ነው" አለች እየተቁነጠነጠች
ምን አይነት ጫወታ ? አልኳት
"ያው ወሬ ነዋ ሌላ ምን አለ?"
ኧረ ብዙ አይነት ጫወታ አለ ተጫውተሽ አታውቂም እንዴ?
"እንዴ ! ክክክክክ እሱማ ብዙ አይነት ጫወታ አለ እኔ ለማለት የፈለኩት ግን ወሬውን ነው"
ሳቋ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳቅ ደስ የሚል ለዛ አለው ።
ምን አይነት ጫወታ ይቀልሻል? ወይም ትወጃለሽ?
"እቃቃና እኩኩሉ ልበልህ "
ተሳሳቅን ሳቋን ወደድኩት።
ወደ ዩንቨርስቲው እየተቃረብን ነው።
እሺ እኔ ጫወታ በመጀመር ላግዝሻ?
"ከዚህ በላይ እሄው ጀመርከው እኮ! አለችኝ
እኔ ግን ጥያቄ ነበረኝ
የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆነሽ በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ ወይ ገብተሽ አልተዝናናሽ
በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም •••
አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ!
ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ።
​​#ልጩህበት !


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በጥላሁን

...በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም •••
አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ!
ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች••
••••
እንደፈራች ገባኝ
እኔ ሽምቅቅ ልበልልሽ አልኩ በሆዴ
ዝም ብዬ ሳያት ሳቋ መጣ ፍርሀት የተቀላቀለበት ሳቅ ሳቀች

የፈለከውን አርገኝ ስትይ?

"በቃ ብዙ ሳናወራና ሳንቀራረብ ልንገርህ ብዬ ነው "

እኮ የፈለከውን አርገኝ ስትይ ምን ለማለት ነው?

"እየተጫናነኩኝ ነበረ እኮ እይታይክም እንዴ በቃ ሲጨንቀኝ ነው እንጂ አንተ ባጃጅ ውስጥ የገባሁት ምንም ብር የለኝም ለዛ እኮ ነው ጨንቆኝ እኮ ነው ዝም ብዬ ግንቡን ተደግፌ ስቆም የነበረው"
ከጥያቄዬ እየሸሸች ስትቀበጣጥር የኔም ሳቅ መጣ ቢሆንም ለሶስተኛ ግዜ ጥያቄዬን ሰነዘርኩ
በዚህ መሀል መልሷን በጉጉት እየጠበኩ
አንድ ሰካራም ለሱ ያቆምኩ መስሎት ነው መሰለኝ ኬት መጣ ሳይባል ግራ ቀኝ እየተጋጨ ከውሃላ ገብቶ አጠገቧ ተቀመጠ።

ድንገት ስለገባ ደንግጣ •••

"እማ"

ብላ እየተጣራች ከነበረችበት መሀል ወደ ጥግ ተጠጋች ከሰውየው ራቅ ለማለት።
እሱም መደንገጧን አይቶ ዘወር አለና ወደሷ •••
በመሀል በመሀል ስቅ እያለው•••

"አይዞሽ የኔ ቆንጆ አስደነገጥኩሽ አደል ይቅርታ አንቺኮ - ሀበሻ ሴት ስለሆንሽ ብቻ በጭለማ ውስጥ ያለሽ የ-የ-የ-የ የብርሀን ጭላንጭል ነሽ አይገርምሽም"
አይገርማትም አሁን ባጃጁን ያቆምኩት ላንተ አይደለምና ውረድ አልኩት ድንገት በንዴት!።
ለኔ ንዴት ቦታም አልሰጠው •••
"ለኔማ ነው ያቆምከው! ለሌላ የቆምክ መስሎህ ነው እንዴ?
እኔን እኮ ነው እዛ ጋር ቆሜ ያየከኝ። ሌላ ሰው ቢኖር ለምን እስካሁን አልመጣም? ይልቅ አንተ ስራህን ስራ ከልጅቷ ጋር ላውራበት" ብሎ ሲመልስልኝ ልጅቷ ሳቋን ለቀቀችው።

ሰካራሙ ሰውዬ አንገቱን ከኔ ላይ መንጭቆ በፍጥነት ወደሷ ዞረና•••
"ምን ምን ምን ምን እስቲ በናትሽ ሳቅሽን ድገሚው የተኮረኮረ ህፃን ልጅ እኮ ነው እምትመስይው !
ወይኔ ልጄ ለምን እንደምጠጣ ታውቂያለሽ የልጄን ናፍቆት ለመርሳት !
ልጅ በልጅነት ሲሉ ሰምቼ ምንም ሳይኖረኝ ወልጄ ፍቅረኛዬ እኔ ላይ ጥላብኝ ስትሄድ እኔ ደግሞ አሮጊቷ እናቴ ላይ ጥየባት መጣሁ።

እናቴ ግን መጣያም ቢኖራት የሚጥል አንጀት የላትም እና እኔን ፍዳዋን በልታ ያሳደገችኝ እንዳይበቃት ላስርፋት ሲገባኝ እረፍት እምትነሳ የአንድ አመት ህፃን ልጅ ጥየባት ከመጣሁ ስድስት አመት ሞላኝ አንዴ ብቻ ነው ልጄን ያየሁዋት!!
ግን ግን በናትሽ ካላስቸገርኩሽ ያሁኑን ሳቅ አንዴ ድገሚልኝ !"

ተበሳጨሁ።

ስማ የሷ ሳቅ ስትጋት ያመሸከው ጠጅ መሰለህ እንዴ እሚደገመው አሁን እምትወርድ ከሆነ በፀባይ ውረድልኝ? አልኩት።
"ጠጅ አልጠጣሁን አረቄ ነው ጠጅ ስጠጣ አይተሀል? ነበርክ? ደሞ ሳቅ እንጂ ሌላ ነገር ድገሚኝ አላልኳት ምን አቃጠለክ ኪኪኪኪ " ብሎ ሳቀና ደሞ ወደሷ ዞሮ
"እኔኮ ተሳፋሪ መስለሽኛል ! ፍቅረኛሽ ነው እንዴ ለካ! በቅናት አንገበገብኩልሻ አንበሳ ነኝ አደል አንበሳ••••" እያለ ሳቁን ቀጠለው።
ትግስቴ አለቀ ጎትቼ ላወርደው ተፈናጥሬ ስወርድ•••
"በናትህ ተው እንዳትጣላ " ብላ ጮከች ልጅቷ እጇን እያውለበለበች እና እንዴ ወደኔ አንዴ ወደሱ እየተመለከተች
"አፌ ቁርጥ ይበልልሽ አንቺ ባትኖሪ ምን ይውጠኝ ነበር
ሆሆሆሆ ሊበላኝ ነው እንዴ?
እውነቴን ነው እድሜ ለሴቶች እንበል እናንተ ባትኖሩ እኮ እኛ ወንዶች እሄን ግዜ እንደ ዳይኖሰር እርስ በርስ ተበላልተን ከምድረገፅ በጠፋን ነበር!
አሁን እራሱ ኮረና ያላጠፋን ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? አታውቂም?
እንደኔ ከሆነ ኮረና ድምጥማጣችንን ያላጠፋን ኢትዮጲያዊያን ሴቶች ጨዋዎች ስለሆናችሁ ነው
እድሜ ለናንተ!
እውነቴን ነው አሁን እኔ ልሙት እንኳን ማክስ ሱሪስ እምታስወልቁን እናንተው አደላችሁ ።
እናንተ ጨዋ ባትሆኑ ማነው ማክስ አላወልቅም የሚለው እንደ ብራዚል ሴቶች ብትሆኑ ማን ይተርፋል ? አልቆልን ነበር ሙች እውነቴን ነው!
እሱ ይለፈልፋል እሷ ትስቃለች !
ሰውየው የባጥ የቋጡን እየቀባጠረ ደሜን ቢያፈላውም ለምን እንደሆነ ባላውቅም በሱ ንግግር የምትሰቀውን ልጅቷን ማየት ስላስደሰተኝ ነው መሰለኝ ሳላስበው ብዙ ታገስኩት
አሁን ትወርዳለህ አትወርድም አልኩት ወደሱ እየተጠጋሁ
"እራስህ እኮ ነህ አቁመህ የጫንከኝ !"
ላንተ አልቆምኩም አልኩህ እኮ!
"ታድያ ለማን ነው የቆምከው?"
ለሷ!
"ለሷ ካካካ እሷኮ አብራህ ነው የመጣችው••••
እሀሀሀ ልታወርዳት ነበር እንዴ የቆምከው ገባኝ !
ታድያ ምን አጣደፈህ ቀስ ብለህ አትቆምም ብቻሽንማ አትወርጂም ነይ በይ እንውረድ!"
ሲላት•••
ሳላውቀው በንዴት ውስጥ ሆኜ ሳቄ መጣብኝ እንደምንም ላለመሳቅ እየታገልኩ ኮሌታውን ይዤ ጎትቼ ላወርደው ስል•••
"እባክህ ተወው እንደዛ አታድርግ ! ቆይ የት ነው መሄድ እምትፈልገው አንተ ?!" አለችው።
"ብዙ አርቅም እኮ እሄኛው መጠጥ ቤት ስለተዘጋብኝ እቅዴ ደሞ አዳሬን መጠጣት ስለሆነ ቤት ልቀይር ነው እዛች ጋ ያለችው ግሮሰሪ ደሞ ካልታሸገች በስተቀር አትዘጋም ወደዛ ነው እምሄደው " ሲላት
"በናትህ ጣል አርገነው እንለፍ ?" እለችኝ ባይኗ እያባበለች
ምነው በሱ ምክንያት የምታመልጪ መሰለሽ እንዴ እሱን አውርጄው የጀመርነውን እንጨርሳለን እሺ አልኳት ኮስተር ልልባት እየሞከርኩ።
ባጃጁን አስነስቼ ከነፍኩ።
"ምን አርጊ ነው እምትላት እነጨርሳለን እንጫረሳለን እያልክ ታስፈራራለህ እንዴ?" አለ
እስቲ ዝምበል ስለው ጭራሽ ባሰበት•••
"ዝም አልልም እንደውም እሱን ተይው አንቺ ብቻ ፍቀጅልኝ?"
"ምን ?"
"አንዴ ልጩህ በናትሽ ?"
"እንዴ ለምን ምን ሆንክ?" አለችው ግራ ተጋብታ ሰውየው መች ያልቅበትና እኔ በማታ ስራ ብዙ ሰካራም ጭኛለሁ እንደዚህ ሰውዬ ግራ ያጋባኝ ሰው አልገጠመኝም ቀጠለ••
"አንቺ ምን ስትሆኚ ነው እምትጮሂው?"
"ምን አይነት ጩኸት?"
"እሄውልሽ እኔ ደስ ሲለኝም እጮሀለሁ ሲጨንቀኝም እጮሀለሁ በናትሽ አሁን አንዴ ልጩህ ? ፈቀድሽልኝ አለና
በጣም በሚያስፈራ ድምፅ አቀለጠው።
እሷም ደነገጠች እኔም ባጃጁን አቁሜ በደምፍላት ወደሱ ዞርኩና
አንተ ሰውዬ እብድ ነህ እንዴ?ስለው
"የፈለከውን በለኝ ግን በናትህ ልጩህበት ተወኝ ?"
እስቲ ወንድ ነህ ድገመው አልኩት። የጉድ ቀን አይመሽም አሉ ዛሬ የጉድ ለሊት አይነጋም ሆነብኝ እሷ በኔና በሱ ሁኔታ ትስቃለች ሰውየው ቀጠለ
ልጩህበት ተወኝ ተወኝ ልጩህበት
በአፌ ቢወጣ የውስጤ እንፋሎት
ለየልኝ እሄ ሰውዬ አላበዛውም እንዴ ግጥምህንም አንተንም አልፈልግም ውረድልኝ
እቺን ግጥም ሳልጨርስልህማ አልወርድም
ታድያ ልጩህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ
የገዛ ጩኸቴ ለኔ እየተሰማ
ንዴቴን
ብሶቴን
ናፍቆቴን ባከስመው
እኔ እየጮህኩኝ እኔ እራሴ ልስማው!!
••••አለ። ጨረስክ አልኩት ።አፍጦ እያየኝ•••
"አዎ ግጥሜን ጨርሻለሁ ግን አንተም ዝም ብለህ አትጩህ እሺ

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍21
​​#ልጩህበት !!


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በጥላሁን

ታድያ ልጩህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ
የገዛ ጩኸቴ ለኔ እየተሰማ
ንዴቴን
ብሶቴን
ናፍቆቴን ባከስመው
እኔ እየጮህኩኝ እኔ እራሴ ልስማው!!
••••አለ። ጨረስክ አልኩት ።አፍጦ እያየኝ•••
"አዎ ግጥሜን ጨርሻለሁ ግን አንተም ዝም ብለህ አትጩህ እሺ •••
እኔ ከባጃጅህ አልወረድኩ አንተ ግን ከገባሁ ጀምሮ ዝም ብለህ ትጮሀለህ ስማኝ የት እና መቼ እንደምትጮህ ካላወክ ዝም ብትል ይሻላል
ያለበለዚያ ሰሚ ሳይኖር ዝም ብለህ ብትጮህ የራስህ ጩኸት እራስህን ያደነቁርህ እንደሆን እንጂ ምንም አታመጣም !"
ብሎኝ ሲያበቃ ደሞ ወድያው ወደሷ ዞረና
"አንድ ግዜ ብቻ ልጩህ በናትሽ ?"
ሲላት ቀርታኝ የነበረችው እንጥፍጣፊ ትግስት ተሟጠጠች •••

አቦ ባባ ክብር ካልወደደልህ እንዴት እንደምትወርድ ላሳይሀ እንግዲህ ብዬ እጄን ለፀብ እያሰናዳሁ ወርጄ ስጠጋው
"ተው ተው ተው ቦክስ አታባክን ወጣቱ መጀመሪያውኑ እንደዚህ ወንድ ብትሆን ኖሮ አንተ ባጃጅ ውስጥ እስካሁን ማን ይቀመጥ ነበር ፈሪ ፈሪ ነገር ነህ !"
እያለ ከባጃጇ ሲወርድ ልጅቷ በሳቅ ፈነደቀች
ግራ ቀኝ እየተወዛወዘ ትንሽ ከባጃጇ ራቅ እንዳለ ዘወር አለና
"ሞት ይርሳኝ ቻው እሺ የኔ ልጅ ልጅ አልኩ እንዴ አንቺን እንኳን አላደርስም !
ቻው እሺ የኔ ልእልት አንቺን የመሰለች ልጅ ከዚህ አስቀያሚ ሹፌር ጋር በማየቴ ደንግጫለሁ !
ፍችው በናትሽ! " እላት።
"እሺ "አለችው በሳቋ መሀል
"ግን መች ትፈችዋለሽ በናትሽ! እ••• እ ••እ ንገሪኛ?" እያለ ሊመለስ ሲል እኔም እየሳኩ ወደሱ ስጠጋ ፊቱን አዙሮ ከቆምንበት በስተቀኝ መንገድ ዳር ወዳለችው የማትዘጋዋ መጠጥ ቤት አመራ።

ባጃጃን አስነስቼ ከዩንቨርስቲው በቅርብ ርቀት
ጨለማ ውስጥ አቆምኳትና ከመሪው ላይ ተነስቼ እሷ አጠገብ ተቀመጥኩ ። ፊቷ ተቀያየረ።
ካቆምንበት እንቀጥላ አልኳትና
ቅድም የፈለከውን አርገኝ ስትይ ምን ለማለት ፈልገሽ ነበር ?
"በቃ ከፈለክ ልትሰድበኝም ከፈልክ ልታወርደኝም ትችላለህ ሌላ ምንድን ነው?" አለችኝ የጭንቀቷን
ወደ ዩንቨርስቲው ዞሬ ተመለከትኩ አጠገባችን ነው ግቢው ከሩቅ ይታያል ሳቄ መጣ አብራኝ ሳቀች።
ሀይ ስትደርሺ ነው እንዴ ልታወርደኝ ትችላለህ እምትይው? ስላት•••
ጭንቅላቷን ወደ ግራ ሰበቀችና በዝምታ እጇን እያፍተለተለች አይን አይኔን ታየኝ ጀመር
የሆነ ስሜት ተሰማኝ
ታውቂያለሽ ሁለት ወንድሞች አሉኝ ግን እህት የለኝም ቢሆንም እናት አለኝ የማይሆን ቢሆንም እናትም ባይኖረኝ እራሱ አንቺ ላይ የሚጨክን አንጀት የለኝም
ምንም አልደርግሽምም አልሰድብሽምም አላወርድሽምም እሺ መጀመሪያውኑ ብር እንደሌለሽ ብትነግሪኝና በነፃ እንዳደርስሽ ብትጠይቂኝ ለስራ ብወጣም ከሰአቱ አንፃር ላውሬ ጥዬሽ አልሄድም ነበር ።

እያሰብኩ የነበረው ምናልባት መጥፎ ባህሪ ያለው የባጃጅ ሹፌር አጋጥሟት ቢሆን ኖሮስ እያልኩ ነው።
ግን ምን አጋጥሞሽ ነው ማለቴ
በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ ?ስለራስሽም ብትነግሪኝ ደስ ይለኛል
"አጋጣሚው ከብዙ ነገሮች ጋር የተያያዘ ነው ኬቱ ጋር ልጀምርልህ?
ከፈለግሽው።
"በናትህ አሁን መሽቷል ሞባይሌን ዶርም ጥዬው ወጥቼ ነው ከፈለክ ስልኬን ያዝና ነገ ወይ በሚመችህ ቀን ደውልልኝ አወራሀለሁ!"
እዚሁ ባጃጅ ውስጥ እናድራታለን እንጂ አልፋታሽም አልኳት ኮስተር ብዬ
" እያስገደድከኝ ነው ማለት ነው አለች እሷም በስሱ ከስተር ብላ
ስትስቅም ስትኮሳተርም የሚያምርባት ሴት እሷን አየሁ።

አሁን ከተለያየን ቡሀላ ልታገኝኝ ፍቃደኛ ሁኚ አትሁኝ እርግጠኛ ስላልሆንኩ አሁኑኑ እንድትነግሪኝ እየለመንኩሽ ነው! ከተጫንኩሽ ይቅር ብትነግሪኝ ግን የመጣሽበትን ሂሳብ እንደከፈልሽ እቆጥረዋለሁ አልኳትና አሁንም እኩል ሳቅን።
"ክትክትክትክት ኧረ ባክህ
እሺ ግን ባጭሩ ነው በደንብ እንድትረዳው ገባ ብዬ ብጀምርልህ ይረዝምብኛል?"
አቦ ንገሪኝኛ አታጓጊኝ!።
" እኔ
እኔ
እኔ ማለት እኔ ደሀ ከሚባል ቤተሰብ ነው የተወለድኩት ።
አባቴ አናፂ ነው እናቴ ደግሞ ሽንኩርት ቲማቲም ምናምን ነው ጉሊት ውስጥ የምትቸረችረው
ሁለቱም ፀሀይ ላይ ውለው ፊታቸው ጠቁሮ ከሚያገኙት ገቢ ውስጥ አብዛኛውን እኔን ከሰፈሬ እና ከትምህርት ቤት ጓደኛቼ እኩል ማድረግ ባይችሉ እንኳን ክፍተቱን በመጠኑ አጥብበው ብዙ ሳይሰማኝ እንዳድግ ለማድረግ አውለውታል።
ሳይለብሱ ያለብሱኛል
ለነሱ ርካሽ የተባለውን ጫማ እየተጫሙ ለኔ ውድና ሁለት ሶስት ቅያሪ ጫማ እንዲኖረኝ ለማድረግ ለነሱ የሚያስፈልጉዋቸውን ሁሉ ወደ ጎን ትተዋል !
ሳይደሰቱ እኔን ለማስደሰት የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል!
ቢኮራረፉ እኔ ፊት ይስቃሉ!
ቢያዝኑ እኔ ፊት ደስተኛ ለመምሰል ይሞክራሉ!
በአጠቃላይ ለራሳቸው ሳይኖሩ ለኔ ደክመው ለኔ ኖረው ያስተማሩኝን ቤተሰቦቼን ለማስደሰት የምችለው በትምህርቴ ስጎብዝ ነውና ምንም ነገር ሳያታልለኝ በርትቼ በመማር ወደ ዩንቨርስቲ መግቢያ የሚሆን ውጤት አምጥቼ ባስደሰትኳቸው ማግስት ነበር አባዬ እኔ ወደዚህ ለመምጣት የሚያስፈልገኝን ነገር ለሟሟላት ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ ያገኘውን ስራ በሙሉ እየሰራ ገንዘቡን እኔው ጋር ማጠራቀም የጀመረው •••"
አለችና ዝም አለች።
ምነው ቀጥይ እንጂ ስላት
"ስላባዬ ሳወራ ጨነቀኝ !
ትንሽ ዝምታ ተፈጠረ በመሀላችን።
ሲጨንቀኝ ደሞ ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ?"
ምን ትዝ አለሽ ?
አንዴ ልጩህ እሚለው የቅድሙ ሰካራም ።
አንዴ ልጩህ እንዴ?"
ስትለኝ ሁለታችንም ባንድ ግዜ ከነበርንበት ሙድ ወጥተን ከባጃጇ ጣራ በላይ ሳቅን።
በናትሽ ቀጥይልኝ ? አልኳት ሳቄን ስጨርስ። ካሳቁ መልስ ደሞ ባንዴ ፊቷን ቅጭም አርጋ ቀጠለች•••
አባዬ ድካሙና እንቅልፉ ተደራርቦበት ነበር ።
ልመጣ ሁለት ሳምንት ሲቀረኝ •••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
​​#ልጩህበት ! !


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በጥላሁን

"ስላባዬ ሳወራ ጨነቀኝ !
ትንሽ ዝምታ ተፈጠረ በመሀላችን።
ሲጨንቀኝ ደሞ ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ?"
ምን ትዝ አለሽ ?
አንዴ ልጩህ እሚለው የቅድሙ ሰካራም ።
አንዴ ልጩህ እንዴ?"
ስትለኝ ሁለታችንም ባንድ ግዜ ከነበርንበት ሙድ ወጥተን ከባጃጇ ጣራ በላይ ሳቅን።

በናትሽ ቀጥይልኝ ? አልኳት ሳቄን ስጨርስ። ካሳቁ መልስ ደሞ ባንዴ ፊቷን ቅጭም አርጋ ቀጠለች•••
አባዬ ድካሙና እንቅልፉ ተደራርቦበት ነበር ።
ልመጣ ሁለት ሳምንት ሲቀረኝ •••
••••
ልመጣ ሁለት ሳምንት ሲቀረኝ በሂወቴ እማረሳው መጥፎ አጋጣሚ ተፈጠረ ቀኑ አርብ ነበር አባዬ እንደተለመደው በለሊት ነበር ወደ ስራ የወጣው
ያን ሰሞን የሚሰራበት ቦታ ከኛ ቤት ብዙ ስለማይርቅ እንደነገ ልጀምር ማታ እማዬን በጥዋት እየተነሳሽ ምሳ አትቋጥሪልኝ ቀስ ብለሽ ስሪና አለሜ ታምጣልኝ አላት ስሜ ኤደን ቢሆንም አባ ግን አለሜ የኔአለም እያለ ነው እሚጠራኝ።

ለአራት ቀናት ምሳውን ስራ ቦታ እየወሰድኩለት እስኪበላ እያዋራሁት እምለሳለሁ በአምስተኛው ቀን ጓደኛዬ አርብ እለት ከማዬ ጋር ልብስ ይዥበት የምመጣውን ቦርሳ ለመግዛት አብረን ወጥተን ስለነበር ምሳውን ሳላደርስለት ሰአቱ ሄደብኝ በውስጡ ልጄን ምን አጋጠማት እያለ ሲጨነቅ ነበር ለካ ከቀኑ ሰባት ሰአት ተኩል ላይ ምሳውን ይዤ ከቤት ወጣሁ ከ15 ደቂቃ ቡሀላ ደረስኩ።
ቀና ስል•••
አባዬ በግምት ከመሬት አምስት ሜትር ከፍታ ላይ ተሰቅሎ ስራውን እየሰራ ነው አባ ብዬ ጮክ ብዬ ስጣራ ስቆይበት ጭንቀት ላይ የነበረው አባዬ የኔን የልጁን ድምፅ ድንገት ሲሰማ ደነገጠ መስለኝ ሳይጠነቀቅ እኔን ለማየት የያዘውን ለቆ ዞረ!
ወድያው ከላይ ቁልቁል ሲምዘገዘግ አይኔን ማመን ተሳነኝ በሂወቴ እንደዛን ቀን ደንግጬ አላውቅም ውሃ ሆንኩ ወደ ወደቀው አባቴ መጠጋት ፈርቼ በቆምኩበት ስጮህ ባከባቢው የነበሩ ሰራተኛች ከወደቀበት አንስተው አናቱ ላይ ውሀ ሲያፈሱበት ተመለከትኩ
ተርፏል አባቴ !
ተርፏል አባቴ !
እያልኩ ወደሱ በመሮጥ እያለቀስኩ አንገቱ ላይ ተጠመጠምኩበት።
እግሩና የጎን አጥንቱ ላይ ጉዳት ደረሰበት ያን ቀን አሰሪው ሀኪም ቤት ወስዶ ህክምና ተደረገለት ከዛን ቀን ቡሀላ ግን ዘወር ብሎም አላየውም
ከ አምስት ቀን ቡሀላ እኔ ጋር ያለው ለዩንቨርስቲ ጉዞዬ ብሎ ያጠራቀመው ገንዘብ ለሱ ህክምና እንዳልጠቀምበት ብሎ ሳይሻለው ተሽሎኛል ብሎ ከሀኪም ቤት ወጣና እቤታችን ተኛ
ለሊት ለሊት ሲያቃስት ስለሰማሁት አባ እሺ በለኝ እና በደንብ ታከም እኔ ጋር ባለው ብር ታክመህ ካልዳንክ ወደ ዩንቨርስቲ እንደማልሄድ እወቀው ስለው እሺ አለኝ።
አሳክሜው የተረፈችኝን ይዤ መጣሁ እዚህ ከመጣሁ አራት ወር ሊሞላኝ ነው ግን እስካሁን ስራ አልጀመረም እማዬ በምትሰራው ብቻ ስለሚኖሩ እማን ላለማጨናነቅ ብዬ ምንም ወጪ የለብኝም ብር እንዳትልኪልኝ አልኳት
እዚህ ደግሞ ብዙ ወጭዎች አሉ ኖቶችን(ሀንድ አውቶችን) ኮፒ ከማረግ ጀምሮ ብዙ ነገሮች አሉ በተለይ ሴት ልጅ ከወንድ ልጅ በባሰ ሁኔታ እጇ ላይ ሳንቲም ያስፈልጋታል ሁሉንም ፍላጎቷን ማስቀረት ብትችል የሞድየስን እና የአንዳንድ ነገር ወጪዎቿ ግድ ናቸው።
በዚህ ግቢ ማደሪያ ክፍላችን (ዶርም) ውስጥ በጣም የምቀርባቸው ሁለት ጓደኛች አሉኝ የመጣን ሰሞን ስለሂወታችን ስናወራ የሶስታችንም ቤተሰቦቻች በተቀራራቢ የድህነት ህይወት ውስጥ ያሉ እድሚያችን ፣አለባበሳችን፣ ፍላጎታችን ፣ ችግራችን ባጠቃላይ በተመሳሳይ ህይወት ውስጥ ማለፋችን ነው መሰል ቶሎ ለመቀራረብና እንደህታማቾች ለመተሳሰብ እና ለመተዛዘን ግዜ አልፈጀብንም።
እማንለያይ አንዳችን ላንዳችን የምንጨነቅ ሆንን ከቅባት ጀምሮ የሚያስፈልጉንን አዋጥተን እንገዛለን አንዳችን ያንዳችንን ልብስ ለመልበስ ፍቃድ መጠየቅ አያስፈልገንም የነሱን ባላውቅም እኔ ሁለቱንም በጣም ነው እምወዳቸው ።
ትንሽ እንደቆየን በተለይ አንዲት የሶስተኛ አመት ተማሪ ባጋጣሚ ከአንደኛዋ ጋደኛዬ ጋር ተዋውቋ ዶርማችን መጥታ ከተዋወቀችንና በየቀኑ መምጣት ከጀመረች ቡሀላ ነገሮች በፍጥነት መቀያየር ጀመሩ።
እኔ ልጅቷ የምታወራው ነገር ሁሉ ስለማይጥመኝ ብዙም አልቀርባትም ነበር ።
ከሁለቱ ጋር ግን በጣም ተቀራረበች ጭራሽ ከግቢ ውጪ አምሽተው አንዳንዴም አድረው መምጣት ጀመሩ የት ሄዳችሁ ነው? ስላቸው ከሷ ጋር እንደነበሩ ይነግሩኛል የጓደኝነቴን ትምህርታቸው ላይ እንዱያተኩሩና ከሷ ልጅ ጋር መዞሩን እንዲቀንሱ ብነግራቸውም ጭራሽ ባሰባቸው ። እንደውም እኔም አብሬያቸው ዘና እንድል በተለያየ መንገድ ሊያሳምኑኝ ይሞክሩ ጀመር።

በተዋወቋት ባጭር ግዜ ውስጥ እኔ ለፎቶ ኮፒ ተቸግሬ ፍዳዬን ሳይ እነሱ ልብስና ጫማ በየሳምንቱ መቀያየር ጀመሩ ከኔ ጋር ያላቸው ልዩነት እየሰፋ እየሰፋ መጣ የነበሩት ነገሮች በሙሉ ተለዋወጡ እንኳን ከኔ ጋር ቅባት አዋጥተው ሊገዙ እንኳን ከኔ ጋር ልብስ ሊቀያየሩ የበፊቶቹን ልብሶቻቸውን ከፈለኩ መውሰድ እንደምችል ይነግሩኝ ጀመር።
ቅባት ሻንፖ ሎሽን የመሳሰሉትን ነገሮች ገዝተው ሲሰጡኝና እና ለፎቶ ኮፒ የሚሆነኝን ገንዘብ ስፈልግ እንድጠይቃቸው ሲነግሩኝ ከምልህ በላይ ይሰማኝ ጀመር በቃ በፊት ተሰምቶኝ የማያውቅ የበታችነት ስሜት ተረጋግቼ ማጥናት እስክቸገር ድረስ መጥፎ ሁኔታ ውስጥ ከተተኝ።
በዛ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ደግሞ ያቺ ጓደኛቸው እና እነሱ እነሱን እንድመስል አብሬያቸው እንድውል እና እንዳመሽ ባገኙት አጋጣሚ ይወተውኛል ።
በቅርቡ የመጀመሪያው ሴሚስተር ፈተና ነበርና በየትምህርት አይነቱ ያሉትን ኖቶች ኮፒ ለማድረግ በጣም ሳንቲም ያስፈልገኝ ነበር።
ያቺ ጓደኛቸው ያዘነች መስላ ያንን ወጪ በነሱ በኩል
በመሸፈን በውለታ ከያዘችኝ ቡኋላ
ዶርም መጥታ ፈተና ስንጨርስ አብሬያቸው ወጣ ብዬ ለመዝናናት ፍቃደኛ እንድሆንና ቃል እንድገባላት በነሱ ፊት ጠየቀችኝ ለሶስት ሲያዋክቡኝ ግራ ገባኝ !
ደስ ባይለኝም ያቀደችልኝን ቀድሜ መረዳት አልችልም ነበርና ቃል ገባሁ።
ፈተናው ሊያልቅ አንድ ቀን ሲቀረው ጨነቀኝ
ዛሬ ጥዋት ስድስት ሰአት አከባቢ እነሱ ፈተናው በማለቁ ደስ ሲላቸው እኔን ግን ፍርሀት ፍርሀት አለኝ •••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
​​#ልጩህበት !!


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በጥላሁን

እያዋከበ ይዞኝ ከወጣ ቡሀላ
" እዛጋ ባጃጅ ታገኛለሽ ቆይ ትንሽ ላስጠጋሽ" እያለ ቁልቁል ወረድን ። እሱ እሄን ሁሉ ሲያወራ ስለደነገጥኩ ነው መሰለኝ ትንፍሽ አላልኩም በቃ ተመለስ ብዬው ቆም እንዳልን ከጀርባው ከሆቴሉ እየተምዘገዘገ የሚመጣውን ሰው ተመለከትኩና
በቆምኩበት በድን ሆንኩ ሁኔታዬ ግራ ገብቶት ሲያፈጥብኝ በጄ ወደሚመጣው ሰው እያመለከትኩ እንደምንም
ወይኔ ተከትለውን መጡ መሰለኝ አልኩት ደንግጦ ዞረ •••
•••
ወድያው መጀመሪያ እየሮጠ የወጣውን የሚያባርሩ ሁለት ወጣቶች ከጀርባው ተከታትለው ወጣ
"እንዴ የሚያባርሩት እኮ ጀለሶቼ ናቸው ምን ተፈጥሮ ነው ? ምን አርጓቸው ነው ?" አለና ድንጋይ አንስቶ ከፊት ጠበቀው።
በናትህ ተው አትጣላ አልኩት በጭንቀት።
ልጁ ግን ገና እኛ ጋር ሳይደርስ ድንገት ወደ ግራ ተኮሩቦ እግሬ አውጪኝ አለ።
ልጁ ድንገት ስልብ ያለባቸው ጓደኛቹ
"ወዴት ሄደ ?
በየቱጋ ነው የሄደው? እያሉ ልጁ በሄደባት ቀጭን እና ጨለማዋ መንገድ ሊገቡ ሲሉ
ቆይ ቆይ ወደጨለማው አትግቡ ! ቆይ ምን አድርጓችሁ ነው ? ምን ተፈጠረ ? ማነው ልጁ? አላቸው ከኔ ጋር የነበረው ልጅ ።
ሁለቱም ቁና ቁና እየተነፈሱ እኩል ማውራት ጀመሩ
••• "ያ ነዋ ጥግ ላይ ብቻውን ደቅ ብሎ ሲቀመቅም የነበረው
እንዴ እኛ የፌኩን ድብድብ ስናጧጥፈው
ማለት ብሩኬ እና እሱ ሲደባደቡ እኔ ደግሞ እማገላግል መስዬ መሀል ላይ ስወክብልሽ ድብድብ ሲያይ ዛሩ ተነስቶበት እንደቀልብ አረገው መሰለኝ ዝም ብሎ ብቻ የሚጠጣውን ቢራ አንስቶ እየተንደረደረ በመምጣት ብሩኬ አናት ላይ አያፈነዳውም ሲል የደነገጥኩት መደንገጥ !
ተጎድቷል እና እሱን እዛ ጥላችሁት መቺውን ለማባረር ሁለታችሁም ትወጣላችሁ መጠጡ ገብቶላችቹሀል ማለት ነው ቻው እሺ እህቴ በቃ ሂጅ አንቺ አለኝና ሶስቱም ተያይዘው ወደ ጭፈራው ቤት እሮጡ
ይህ ሁሉ ነገር በኔ ምክንያት መሆኑን ሳስበው ተሸማቅቄ ጤፍ አከልኩልህ በቆምኩበት እስኪገቡ ድረስ አያየሁዋቸው ጓደኛቸው የከፋ ጉዳት እንዳይደርስበት ተመኘሁ።

አምስት ሳንቲም እጄ ላይ እንደሌለ ትዝ ያለኝ ከሩቁ የምትመጣ ባጃጅ እንዳየሁ ነበር ግራ ገባኝ በግር አልመጣ ነገር ሰአቱም እርቀቱም የማይሆን ሆነብኝ ጨነቀኝ!
ለዛች አውሬ ጥለውኝ የሄዱትን ጓደኛቼን በጣም ብናደድባቸውና እና ብጠላቸውም አማራጭ አልነበረኝምና የመሳፈሪያ ብር ልቀበላቸው ሞባይል እናምጣ ብለው ወደሄዱበት መጀመሪያ ወደነበርንበት ሆቴል ሄድኩ ስደርስ ሆቴሉ ጢም ብሏል መግባት ፈራሁ እዛው ግንብ አጥሩን ተደግፌ እንደቆምኩ ያንተ ባጃጅ መጥታ ቆመች ።
ወድያው ደግሞ አንድ ሰካራም በስልክ እየተጨቃጨቀ ከሆቴሉ ወጣና ከፊት ለፊቴ ቆሞ ያወራ ጀመር አብዛኛው ንግግሩ ስድብ ነበር ቀጥራው የቀረችበትን ሴት መሰለኝ እሚሰድበው።
እንደጨረሰ ወደኔ ዘወር አለልህና
" ውይ ውይ ውይ ውይ ውይ ውይ የኔ ቆንጆ ምነው ብቻሽን እኔንም ወንድ ቀጥሮ አስደግፎኝ ነው እንዳትይኝ ብቻ በእውነት አላምንሽም ነገሩ ተይው ባለጌ ባለጌ ነው !
ሳይደግስ አይጣላም ትል ነበር አያቴ አሁን በስልክ ስሰድባት የነበረችው ልጅ እኮ እኔንም ቀጥራ አስደግፋኝ ነው ኧረ እንኳንም ቀረች የሆነች አስቀያሚ ነገር ነችኮ ሳስበው ሳስበው ግን የኔዋም ያንቺውም እዚሁ ቀጥረውን የቀሩት አብረው ሆነው ሳይሆን አይቀርም ኧረ ነው
እሄው እኔና አንቺን አገናኝቶ የጃቸውን ሰጣቸዎ
"አንተ የሰው ስታጫውት ያንተን እሚያጫውት ይልክልሀል "ትል ነበር አያቴ ኖኖኖ አጎቴ " አለና ጠጋ ብሎ "በይ ነይ እንግባ" አይለኝም አልገባም ስለው እጄን ሊይዘኝ ሲል መንጭቄው ቀጥ ብዬ ወዳንተ ባጃጅ መጣሁ"
ብላ ታሪኩን ስትቋጭልኝ ልጁን ምክንያት አድርጎ ያተረፋትን ፈጣሪን አመሰገንኩ
ልጁ ባያተርፋት ምን ሊፈጠር ይችል እንደነበር ሳስበው ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ተሰማኝ ምናልባትም ያ የምትጠጣው ቢራ ውስጥ የከተተችባት ነገር እራሷን እንድትስት የሚያደርግ ነገር ሊሆን ይችላል ከሽንት ቤት እንደተመለሰች ቢራውን ጠጥታ እራሷን ስትስትና "
አይዞሽ ምን ሆነሽ ነው አመመሽ እንዴ እያለች ደግፋ ሰውየው ወደያዘው አልጋ ክፍል አስገብታለት ትሄዳለች አበቃ ።
ወደራሷ ስትመለስ አልያም ጥዋት ስትነሷ የሚሰማትን ስሜት መገመት ይከብዳል ከዛ ቡሀላ ያለውን ሂወቷን ማሰብ ያሳምማል
እሱ ለሳሏት የአንድ ለሊት ደስታ ለሆነችው ትንሽ ስእል የሷን የሂወት ግብ የሆነውን ትልቁን ስእል ሲያጠፋባት ያድራል!
ኤዱዬ ፈጣሪሽን አመስግኝው አየሽ ክፉዎች የሚመጡበት መንገድ የተለያየ ነው አንዳንድ ክፉዎች የክፋት መርዛቸውን በቀጥታ ሊያበሉን ይሞክራሉ በጣም የከፉት ክፉዎች ግን የክፋት መርዛቸውን በስኳር ለውሰው ሊያበሉን የሚሞክሩት ናቸው
አንዱ መንገዳቸው ለኛ ያዘኑ ወይም ጥሩ መስለው በመቅረብ ሲሆን ሌላው መንገዳቸው ደግሞ በደካማ ጎናችን በመግባት በውለታ ጠፍረው በዩልኝታ ተይዘን ወደ ቆፈሩልን ገደል እንድንገባላቸው የሚገፋፉን ናቸው ታድያ ያኔ የፈለገ ውለታ የዋለልን ሰው ቢሆን በማንፈልገው መስመር እንድንጓዝ ሲገፋፋን ያደረገልንን ነገር ሳይሆን ባደረገልን ነገር ምክንያት እየተጫነን መሆኑን አስበን ምንም ሳያደርግልን በዛ ሁኔታ ውስጥ እንድናልፍ ከሚጠይቀን ሰው የበለጠ ሊያናድድን ሲገባ ውለታውን እያሰብን በጭራሽ ገደል መግባት የለብንም ለፎቶ ኮፒ ገንዘብ ስለሰጠችሽ ማድረግም መሆንም ወደማትፈልጊው መንገድ እንድትገቢላት ቃል ስታስገባሽ እሺ ማለት አልነበረብሽም እያልኩሽ ነው
ከቤተሰቦችሽ ጀምሮ ያለውን ሁኔታ በግልፅ ስለነገርሽኝ አመሰግናለሁ
ካሁን ቡሀላ እኔም ተቀጥሬ የምሰራ ካንቺ ቤተሰብ ቡዙ የማይርቅ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ያደኩኝ ቢሆንም በዚህ ሰአት ቢያንስ ካንቺ እሻላለሁና በትምህርት ሂወትሽ የሚያስፈልጉሽን ማለት ከትምህርትሽ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወጪዎች እኔ ብሸፍንልሽ ደስ ይለኛል
የሚያስፈልግሽን በግልፅ ልትጠይቂኝ ፍቃደኛ ነሽ ኤዱ ስላት
አይኖቿ እምባ አቀረሩ። መልስ ሳትሰጠኝ አቀረቀረች •••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
​​#ልጩህበት !!


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በጥላሁን

ከቤተሰቦችሽ ጀምሮ ያለውን ሁኔታ በግልፅ ስለነገርሽኝ አመሰግናለሁ
ካሁን ቡሀላ እኔም ተቀጥሬ የምሰራ ካንቺ ቤተሰብ ቡዙ የማይርቅ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ያደኩኝ ቢሆንም በዚህ ሰአት ቢያንስ ካንቺ እሻላለሁና በትምህርት ሂወትሽ የሚያስፈልጉሽን ማለት ከትምህርትሽ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወጪዎች እኔ ብሸፍንልሽ ደስ ይለኛል
የሚያስፈልግሽን በግልፅ ልትጠይቂኝ ፍቃደኛ ነሽ ኤዱ ስላት
አይኖቿ እምባ አቀረሩ። መልስ ሳትሰጠኝ አቀረቀረች ••
•••
ምነው ?ስላት•••
"አይ ምንም እንዲሁ ገርሞኝ ነው!"
ምኑ?
"እኔና አንተ በብዙ ኪሎ ሜትር ተራርቀን የኖርን ነን አታውቀኝም አላውቅህም አደረከውም አላደረከውም ግን እንዲህ ስትለኝ ከሚያስፈልጋቸው በላይ እያላቸው የጓዳችንን ችግር እያዩ የቅርብ እሩቅ ሆነው ህመማችን የማያማቸው ችግራችን ያራቃቸውን በደና ኑሮ ውስጥ ያሉ የናቴንም ያባቴንም ዘመዶች አስታወስከኝ እማዬ በጣም የዋህ ነች ምንም ባያደርጉላትም ካለቻት ላይ ቀንሳ የሆነ ነገር ገዝታ ሄዳ ትጠይቃቸዋለች እነሱ እሚጠያየቁትም እሚረዳዱትም በንሮ ከሚመስሏቸው ሌሎች ዘመዶቻችን ጋር ነበር።

እያደኩ እና እሄን እያስተዋልኩ ስመጣ እማዬ "ልጠይቃቸው ልሄድ ነው "ስትለኝ በሷ እራሱ መናደድና ባትሄድ ደስ እንደሚለኝ ፊት ለፊት መናገር ጀመርኩ።
እሷ ግን
"ተይ ልጄ ክፉ መስለውሽ እንጂ ክፉ አደሉም ቢሆኑም ደግሞ ሰው ክፉ ሆነ ተብሎ ክፉ አይኮንም ፈጣሪ ሁሉንም እንደየስራው ይስጠው እኔ ግን ሄጄ ሰላም መሆናቸውን አይቼ መምጣት እረፍት ይሰጠኛል እና መጠየቄን አላቋርጥም" ነበር የሁልግዜ መልሷ።
ቢሆንም ግን •••
ከልጅነቴ ጀምሮ አባዬ እና እማዬ ሲከፋቸው በነሱ ሲበሳጩ እኔን በማይገባኝ መንገድ የውስጣቸውን ቁስል እርስ በርስ ለማውራት ሲሞክሩ እኔ በደንብ ይገባኝ ነበር በዛ ምክንያት ዘመዶቻችንን አልወዳቸውም።
እንደውም ስለነሱ ሳስብ ሰው ሁሉ ክፉ ነበር የሚመስለኝ ነገር ግን •••
ለሰው ችግር ደርሰው ሰው በነሱ ደስ ሲለው ሲያዩ በደስታ አለም የምትሞቃቸው ሰው አዝኖ ሲመለከቱ አለም የምትጨልምባቸው ደጋግ ጎሮቤቶቻችን ከክፍ ሰዎች ይልቅ ደግ ሰዎች በቁጥር እንደሚበልጡ አስተማሩኝ ሁሌም በመንገዴ በማላውቃቸው መሀል እንኳን ብገኝ ካሉት ውስጥ እኔን ከሚጎዳኝ ይልቅ እኔን የሚወደኝ እና ከጉዳት የሚታደገኝ ሰው ቁጥሩ የበዛ እንደሆነ እንዳምንና እንዳልፈራ ያደረጉኝ እነዛ ደጋግ የማዬ ጎረቤቶች ናቸው ።

ዛሬ አንተ እንዲህ ስትለኝ እነሱ ትዝ አሉኝና እምባ ተናነቀኝ !!" አለችኝ ።
ቅድም ህይወቷንና ያጋጠማትን ነገር ስትነግረኝ ከተሰማኝ ሀዘን በላይ ይህ ንግግሯ ውስጤን ሲፈነቃቅለው ተሰማኝ ።
ከዛ ሁኔታ ውስጥ ቶሎ መውጣት ፈለኩ••
ሰአቴን አየት አደረኩና ከለሊቱ ሰባት ሰአት ተኩል ሊሆን ነው ኤዱ በቃ በዚህ ሰአት ወደ ግቢ መግባቱ ጥሩ አይመስለኝም
ችግር እንኳን ባያጋጥምሽ የሆነ የሚያውቅሽ ሰው ባጋጣሚ በዚህ ሰአት ስትገቢ ቢያይሽ ስላንቺ ያለው አመለካከት ጥሩ ካለመሆኑም በላይ ነገ ባየሽ ቁጥር አጠገቡ ላሉት እቺ ልጅ እኩለ ለሊት ከደጅ ስትገባ አየሁዋት እያለ ስምሽን ሊያጠፋው ባጠቃላይ በዚህ ሰአት መግባቱ በተለይ ለሴት ሌላ ስም ነው እሚያሰጣት የነበርሽበትን ሁኔታ ማንም አይረዳም ስላት ትከሻዋን ሰበቀችው
"ታድያ ምን ላድርግ " ይመስላል የሰበቃው ትርጉም።
ለምን አልጋ ይዘሽ አታድሪምና ጥዋት አትገቢም?
"አይ ልግባ ባክህ አንተንም ከዚህ በላይ ላስቸግርህ አልፈልግም !"ስትለኝ በግድ አሳመንኳትና አልጋ ፍለጋ ወደ ከተማ ተመለስን
ትንሽ መንገድ በፀጥታ እንደተጓዝን ዝም ስትል እንደፈራች ስለገባኝ እኔ ማውራት ጀመርኩ
ቅድም ስለአንቺ ስለጓደኛችሽ እና ስለዛች ልጅ ስለ መሲ ስታወሪልኝ አንድ ጓደኛዬ ከአመት በፊት ያወርልኝ ነገር ነው ትዝ ያለኝ
"ምን አውርቶልህ ነበር እኔ ካወራሁልህ ጋር የሚመሳሰል ነው?"
ልጁ ቀደም ብሎ ነው በባጃጅ ሹፍርና ስራ የጀመረው አንድ ቀን ካፍቴርያ ቁጭ ብለን ማኪያቶ እየጠጣን •••
የሆነ ሰው እኛ ወዳለንበት ካፌ ገባና ከኛ ራቅ ብሎ ፊት ለፊት ተቀመጠ
"እሄን ሰውዬ ታውቀዋለህ ?አለኝ
ኧረ አላውቀውም ስለው
"እስቲ በደንብ እየው"
በደንብ አየሁት ደነገጥኩ ሰውየውን አፈር አይኳኝ ሲል አውቀዋለሁ
አዎ አንተ አውቀዋለሁ ምን ሆኖ ነው እንደዚህ አይጥ የበላው እስፖንጅ የመሰለው ደሞ በጣም ከስቷል ጆከሩን ስቦ ነው እንዴ ? ስለው
"እኔ በቀላሉ እምታገኘው ብር አንተንም አቅልሎህ እንደሚሄድ ያረጋገጥኩት በዚህ ሰውዬ ነው " ሲለኝ እንዴት? አልኩት
በቃ በቀላሉ ስታገኝ በቀላሉ ታጠፋዋለህ እሱ ደግሞ ብቻውን አይጠፋም አጥፍቶ ጠፉ በለው
ማለት ? አልኩት የተሸፋፈነውን ታሪክ ገላልጦ እንዲነግረኝ •••
"እሄውልህ ሰውየው ደሞዙ ትዝ አይለውም ከደሞዙ ብዙ እጅ በቀላሉ የሚያገኝባቸው ፕሮጀክቶች ነበሩት
ታድያ ብሩም በቀላሉ ይመጣል እሱም በቀላሉ ይረጨዋል ።

ብሩም ብቻውን አልተበተነማ እሱንም በትኖት ሄደ
እኔ በባጃጅ ስራ በደንብ አውቀዋለሁ።
በየቀኑ ጥዋት መጠጣት ይጀምራል ፣ከሰአት በርጫ ይቀመጣል፣ ማታ ጨብሲውን ይቀጥላል ፣
ያለ ስጋ አይበላም ፣አንዴ አብሯት የወጣውን ሴት አይደግምም ፣ በየቀኑ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ያድራል እሄን ብር እያሳየ ስንት የግቢ ልጆች እንደቀጠፈ አትጠይቀኝ
እሄው አሁን ብሩ ሳያልቅ እሱን ጨረሰው ያለበትን በሽታ ከምነግርህ የሌለበትን ብጠራ ይቀለኛል
በስኳር ላይ ኮልስትሮል በክልስትሮል ላይ ደምብዛት በደምብዛቱ ላይ ኮብራውንም ሳይስበው አይቀርም
ታድያ ከ ብር በላይ አጥፍቶ ጠፊ የታለ? አታየውም እንዴ ማቆ ብሎኑ እንደላላ አልጋ እየተንቃቃ እኮ ነው እሚሄደው ! አለኝ ሰውየው ከዘራውን እየተደገፈ ተነስቶ ሲወጣ ።
አየሽ ኤዱ ፈጣሪ ሁሉንም ነገር በልኩ
እንድንጠቀም ነው የፈቀደልን በየቤቱ ሰው ኑሮ ከልክ ከልክ በታች እያኖረ ያሸዋል
ሰዎች ግን ሰው ከመርዳት ይልቅ ባገኙት ወይ ባላቸው ብር ከልክ በላይ ለመሆን ይሞክራሉ
ከልክ በላይ የሆነ ነገር ሁሉ ደግሞ ከበሽታ ወይ ከጭንቀት ያለፈ ነገር አያስገኝም እያልኳት እግረ መንገዴን በአይኔ ክፍት የሆነ ሆቴል እየፈለኩ ነበርና የምንሄደው አብዛኛዎቹ ዝግ በመሆናቸው መጀመሪያ ወደተገናኘንበት አከባቢ እየተቃረብን መጣን
"እንዴ ያገኘከኝ ቦታ ልትመልሰኝ ነው እንዴ አንተ ልጅ መሲ ይዘካት ና ብላህ ነው እንዴ?
እያለችኝ እየተሳሳቅን ጠጋ እንዳልን እዛ አከባቢ ካሉት ጭፈራ ቤቶች ከአንደኛው የፀብ የሚመስል ጫጫታ ከሩቅ ተሰማን እና
"ምንድን ነው? ፀብ ነው መሰለኝ እየተባባልን ጠጋ እንዳልን
ቀውጢ ሆኗል መስታወት ሲሰበር ጠርሙዝ ሲፈነዷ ሴቶች ሲጮሁ ይሰማል
እባክህ ብዙ አትጠጋ እያለችኝ ባጃጄን እያቀዘቀዝኩ በቀስታ ስጠጋ ከጭፈራ ቤቱ እየተሯሯጡ መውጣት ጀመሩ ከነዛ መሀል በደም የተጨማለቀችው ቀይ ረጅም ሴት የኤደን ጓደኛ መሆኗን ያወኩት ኤዱ
"ወይይይይይኔ ጉዴ ያቺ እኮ ጋደኛዬ ነች ብላ ስትጮህ ነበር ልብሷም ፊቷም ደም ለብሷል እጇን እያወራጨችና ደሟን ከአይኗ ላይ ለመጥረግ እየሞከረች እየተደነቃቀፈች ወጣችና አቅም አንሷት ወደቀች
የቷ!? አልኳት ደንግጬ ;
ያቺ ያቺ የወደቀችው እኮ ጋደኛዬ ረዱ ነች እያለች ከባጃጄ ላይ ተፈናጥራ በመውረድ ወደ ልጅቷ እያለቀሰች ስትሮጥ
እኔም ተከተልኳት••••••••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#ልጩህበት!!


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በጥላሁን

...በቀስታ ስጠጋ ከጭፈራ ቤቱ
እየተሯሯጡ መውጣት ጀመሩ ከነዛ መሀል በደም የተጨማለቀችው ቀይ ረጅም ሴት የኤደን ጓደኛ መሆኗን ያወኩት ኤዱ •••
"ወይይይይይኔ ጉዴ ያቺ እኮ ጋደኛዬ ነች ብላ ስትጮህ ነበር ልብሷም ፊቷም ደም ለብሷል እጇን እያወራጨችና ደሟን ከአይኗ ላይ ለመጥረግ እየሞከረች እየተደነቃቀፈች ወጣችና አቅም አንሷት ወደቀች
የቷ!? አልኳት ደንግጬ ;
ያቺ ያቺ የወደቀችው እኮ ጋደኛዬ ረዱ ነች እያለች ከባጃጄ ላይ ተፈናጥራ በመውረድ ወደ ልጅቷ እያለቀሰች ስትሮጥ
እኔም ተከተልኳት•••••
•••
ተከታትለን ደረስን። መሬት የተዘረረችውን ጓደኛዋን አነሳናትና ወደ ባጃጇ ወሰድናት ። ልጅቷ ኤደንን ስታያት ከዱላው በላይ ቢዥ አለባት ። ግራ ተጋባች።
ግንባሯ አከባቢ ተፈንክታለች ። በቅርብ ርቀት ያለው ሆስፒታል ድል ጮራ ነው ። ወደ ድል ጬራ ድንገተኛ ክፍል ይዣቸው በረርኩ ።
እንደገባን ወድያው እርዳታ ተደረገላት ምናልባት የፈሰሳት ደምና ድንጋጤዉ እንጂ ፍንክቱ ያን ያህል የከፋ አልነበረም።
ከለሊቱ ስምንት ሰአት ተኩል ሆኗል።
" በቃ ደና ነች አይዟችሁ የሰጠሁዋትን አንድ ግልኮስ እንደጨረሰች ትሄዳላችሁ እስከዛው ደጅ ሁኑ አለችን ሌላ የተጎዳ ሰው ወደ ድንገተኛ ክፍሉ ስለመጣ ክፍሉ እንዳይጣበብ።
እኔና ኤደን ወጣንና ግቢ ውስጥ ካለው ቴሌቭዥን ፊት ለፊት ተቀመጥን።
ኤዱ ! አልኳት በዝምታችን መሀል ከድንጋጤዋ እንደተረጋጋች በአተነፋፈሷ እንደተረዳሁ።

ወዬ ዳኒ ! አለችኝ ለኔ የሚጨነቅ የሚመስለውን ገፅታዋን ወደኔ ዞራ እያሳየችኝ።
በጣም ገርመሽኛል ! በእውነት የዋህ ልጅ ነሽ እናትሽ•••
" ሰው ክፉ የሆበበትን ሰው በክፋት ሳይሆን በደግነት የሚረታበት አጋጣሚ ከተፈጠረለት እና ከተጠቀመበት ትክክለኛ አሸናፊው እሱ እንደሆነ እየነገሩም በተግባር እያሳዩም አሳደጉሽ እሄው ዛሬ ፍሬውን እኔ አየሁት!ስላት•••
"እህህህህ በርግጥ ልክ ነህ ክፋትን በክፋት ስንመልስ ያን ሰው ለሌላ ክፋት እናዘጋጀዋለን!
ክፋትን በጥሩ ነገር ስንመልስ እኛም እናሸንፋለን ያን ሰውም ዳግም ሌላው ላይ ክፉ እንዳይሆን አድርገነው ልናልፍ እንችላለን የሚማርና የሚፀፀት ሰው ከሆነ !
እውነቱን ለመናገር እኔ ግን ረዱ እንደዛ ሆና ሳያት እሄን ሁሉ የሀሳብ ስሌት የማሰላበት ግዜ አልነበረኝም በቃ ውስጤ ያዘዘኝን ነው ያደረኩት!"
ተናደድሽባቸው እንጂ አልጠላሻቸውም ማለት ነው?! ስላት
አይ ለዛች እንዲህ እሆናለሁ ብለህ ነው እኔ እንጃ
ምን መሰለህ ይቺ የቲጂ ተከታይ ነች በቃ ቲጂ ወደመራቻት የምትጓዝ ዝም ብላ ወደ ነዷት ሁሉ የምትነዳ የዋህ አይነት ነገር ።
እኔን ወደዚህ አይነት ነገር ውስጥ ለማስገባት ያለፍላጎቴ ሲጫኑኝ ፊቷ ላይ ጭንቀት አነብ ነበር እሷ ግን ነገሮችን የማየትና የመሞከር ጉጉቷ ሀይለኛ ነው ለምን እንደሆነ አላውቅም!
ቢሆንም ከዛች ጭራቅ ጋር ሆነው አንቺን •••
ስላት ሳታስጨርሰኝ •••
"አስበው እስቲ ዳኒዬ ለመሲ እኔም ብሆን እኮ ተታልየላት ነበር ልጁ በአጋጣሚ እዛ ባይኖርና መሲ ያሰበችው ሁሉ ተሳክቶላት ቢሆን
በንጋታው ፊቴ ተቀምጣ
ካሁን ቡሀላ ሁለት አማራጮች አሉሽ አንዱ እኔ ነይ ስልሽ መምጣትና አድርጊ ያልኩሽን ማድረግ ሌላው ከኔ ጋር መጣላትና ለሊቱን ምን ስታደርጊ እንዳደርሽ ሚስጥርሽን በፎቶ አስደግፌ እንድበትንልሽ መፍቀድ ብትለኝ ምን ይውጠኝ ነበር ምንስ አማራጭ አለኝ
ወይ የሷ ለማዳ ውሻ መሆን ያለበለዚያ እራሴን ማጥፋት!"
ስትለኝ ከግር እስከራሴ ውርርር ሲያደርገኝ ታወቀኝ
አቦ የዚች መሲ እምትሏትን ልጅ ፎቶ ስጪኝ በናትሽ ካሁን ቡሀላ ፀቧ ከኔ ጋር ነው
"ኧረ ባባባ ሞት እዚህ ነገር ውስጥ አትግባ በቃ ሁሉም አለፈኮ ካሁን በኋላ የት ታገኘኛለች "
ስትለኝ ዝም ብለሽ ስጭኝ በናትሽ አልኳት
"እኔ ጋር የሷ ፎቶ ምን ያደርጋል ረዱ ሞባይል ግን አለ ግን ምንም አያደርግልህም።"
በዚህ መሀል የረድኤት ቤተሰቦች ብላ ተጣራች ነርሷ። ተነስተን ኤዱ ከፊት እኔ ከኌላ በመሆን ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ጭንቅላቷ ዙርያውን በነጭ ፋሻ የታሰረው ረድኤት ተነስታ ቁጭ ብላለች ኤዱን ስታያት አለቀሰች ኤዱም ተንደርድራ አቀፈቻት።
"እሄውልህ እነዚህን መድሀኒቶች ግዙላት እሺ" አለችና የሀኪም ማዘዣ ወረቀቱን ሰጠችኝ ነርሷ።
ካራ ማራ አከባቢ ፔንስዮን (የምኝታ ብቻ) አገልግሎት የሚሰጥ ቤት መኖሩ ትዝ አለኝና ወደዛው ይዣቸው ልሄድ አሰብኩ ገና ከሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ወጣ እንዳልን ኤዱ ረድኤትን በጥያቄ ታጣድፋት ጀመር•••
ምንድን ነው የተፈጠረው?
ማን ነው የመታሽ ?
ቆይ ከማን ጋር ነበርሽ?
ማን እንደመታኝ አላውቅም ከኔ ጋር የነበረው ልጅ ፍቅረኛ ነበረው ለካ!
አብረን እየደነስን ድንገት መጥታ ስታንቀውና ሲወረውራት አብረዋት ይምጡ አይምጡ አላውቅም ወረሩት አብሮኝ ስለነበር ሲወሩት ጮህኩ ብቻ ምናባሽ ትጮሂያለሽ የሚል ወፍራም የሴት ድምፅ ተሰምቶኝ ዘወር ከማለቴ ግንባሬ ላይ የቢራ ጠርሙሱን ስታፈነዳው ትዝ ይለኛል ከዛ በኋላ እንዴት እንደወጣሁ እራሱ አላስታውስም
ማነች እሷ የመታችሽ ፍቅረኛው
ኧረ እሷ እኔን ዞራም አላየችኝ እዛው የምትሰራ ሴተኛ አዳሪ ሳትሆን አትቀርም የመታችኝ ከዚህ በፊት ሳይተዋወቁ አይቀሩም ከገባን ጀምሮ ስትመነቃቀርብኝ ነበር ሳስበው ለፍቅረኛው እሷ ሳትሆን አትቀርም የደወለችላት በመሀል ስልኩን ተውሳው ነበር
ቆይ አንቺ እሱን መች ነው የተዋወቅሽው
ረድኤት "በቀደም መሲ ናት ያስተዋወቀችኝ •• ብላ ገና ወሬዋን ሳትጨርስ•••
አስተዋወቀችኝ አትበይ ረዱ ሸጠችኝ በይ ልጅቷ እኮ ምንም የማያውቁ ፍሬሾችን ከወንዶች ጋር እያገናኘች ቢዝነስ የምትሰራ ጭራቅ ነች እሄን ታውቂያለሽ በናንተ እየተጠቀመች ነው "!
እኔ ነኝ ባለጌዋ ኤዱ እኔ የማረባ ሴት ነኝ ላንቺ ጓደኝነት እንኳን የማልመጥን ተራ ሴት ሆኜ አንቺ ግን ••••
በቃ እራስሽን አትውቀሺ ያቺ ቲጂ ነች አንቺን እዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ የከተተችሽ
አይደለም ኤዱ ማንንም ጥፋተኝ ማረግ አልፈልግም ስለኔ የማታውቂው ነገር አለ!
አልጋ አግኝተን ይዣቸው እንደገባሁ
"ምንድን ነው እሱ ስላንቺ የማላውቀው ?" አለቻት ኤዱ ገብተን ቁጭ እንዳልን
••• "ታውቂያለሽ አባቴ በጣም ሀይለኛ ነበር ታላቅ ወንድሜ ደግሞ ቁጭ አባቴን በሱ ነው የወጣው እናቴ ደግሞ በተቃራኒው ልጅን ክፉና ደጉን በመንገር እና በመምከር እንጂ የትወጣሽ የት ገባሽ ከማን ጋር አወራሽ ከማን ጋር ታየሽ ማለታቸውን ሁሌ የምትቃወም እናት ነበረች ግን አይሰሟትም
ወንድም እና አባቴ በኔ ላይ አምባገነን የሚለው ቃል አይገልፃቸውም እንኳን የወንድ የሴት ጓደኛዬ እነሱ ቀልባቸው ካልወደዳት ከኔ ጋር አትቀጥልም ምን ልበላችሁ አባቴ በቤት ታላቅ ወንድሜ በሰፈር እና በትምህርት ቤት መፈናፈኛ አሳጥተው ነው ያሳደጉኝ።
ትምህርት ቤት በጋራ የሚሰሩ የቤት ስራዎች ከወንዶች ጋር ከተደለደልኩ አወቁ አላወቁ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ነው የክፍል ልጆች ግን ስለሚረዱኝ ነይ እንስራ ብለው ብዙም አይጫኑኝም ነበር!
ግን አባቴና ወንድሜ እንዳሰቡት በቁጥጥር ብዛት ስነስርዓት ያላት ሴት ሳይሆን በቁጥጥራቸው ብዛት አጋጣሚውን ስታገኝ ለመፈንዳት ሳይሄን ለመፈነዳዳት የተጠመደች ቦንብ አድርገውኝ አረፉት።

ዩንቨርስቲ ለመመደብ የድልድል ፎርም ስሞላ እንኳን ሆን ብዬ እራቅ እራቅ ያሉ ዩንቨርስቲዎችን ነበር በምርጫዬ ውስጥ የሞላሁት ከነሱ ለመራቅ ስል።
ቁጥጥራቸው ከመብዛቱ የተነሳ ምርር ስላለኝ ለኔ ብለው ነው ብዬ ከማሰብ ፈንታ እነሱን የምጎዳ መስሎኝ እልህ ውስጥ ገባሁ ግን ወድጄ አልነበ
👍1
​​#ልጩህበት !!


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በጥላሁን

የሷ ሚስጥር አልገባኝም ነበርና እኔ ከምፈልገው ደስ ካለኝ ወንድ ጋር ለመሆን ስሞክር ታጣጥልብኝ ነበር አንድ ሁለቴ በሀሳቧ ተስማማሁና ተውኩላት በሶስተኛው አንድ ቀን ግቢ ከተወወኩት ልጅ ጋር ኦቨር ማለት አብረን ጭፈራ ወጣን በመሀል ስትደውል አላነሳሁላትም እንዴት እንዳወቀች እንጃ ብቻ ያለንበት ድረስ ቀጥ ብላ መጣችና •••••
ስትጠራኝ ከጀርባዬ ስለነበረች አለየኋትምም አልሰማኋትምም ነበር አብሮኝ ያለው ልጅ •••
"እንዴ ከዚች የሴት ነጋዴ ጋር ደግሞ የት ነው የምትተዋወቁት በይ ሂጂ እየጠራችሽ ነው ! ልታጫርትብሽ ሳይሆን አይቀርም እኔማ በምን አቅሜ እጫረታለሁ"
ሲለኝ አባባሉ ግራ እየገባኝ ዘወር አልኩ ፊቷን ምን አስመስላው እንደቆመች አትጠይቂኝ ።

እንዴት እንደተናደድኩ ከናባዬ ተገላገልኩ ስል እቺን ደሞ ማነው የላከብኝ አልኩ በውስጤ !
አልመጣም ልላት ሁላ ፈልጌ ነበር ።
ልጁን አንዴ አናግሪያት ብመለስ ቅር አይልህም አደል? ስለው•••
"ኧረ በጭራሽ እንደውም ባታናግሪያት ነው እሚሸክከኝ ይልቅ አፍጥኚው ወደዚህ ሳትመጣ!" አለኝ።
ሄድኩ ። ገና አጠገቧ እንደደረስኩ•••
"ስሚ ከኔ እና እኔ እኔ ከማውቃቸው የተከበሩ ሰዎች ጋር አንዴ ከታየሽ ከእንደዚህ አይነቱ መናጢ ተማሪ ጋር መታየት እንዳልነበረብሽ ሳልነግርሽ ማወቅ ነበረብሽ እኮ?!" ስትለኝ የእውነት ደሜ ፈላ
በምናቸው ነው የተከበሩት እሱ ከነሱ በምን ያንሳል?!
"በብራቸው ነዋ በብራቸው ብርርርር ታውቂያለሽ አደል ስንቱን እንደሚያበር ስንቱን እንደሚያስከብር እሄውልሽ እሄ ልጅ ምናልባት መልኩና ወጣትነቱ ያምር ይሆናል ግን ባዶ ነው ባዶ ታውቂያለሽ ለኔ በብዙ ደሀዎች መካከል ያለ አንድ ባለ ብር ለምን ሰላሳ ሁለት ጥርሱ ረግፎ በድዱ አይስቅም ለኔ ቆንጆው እሱ ነው !"
ለኔ ግን አይደለም አንቺም ቆንጆሽ ጋር ሂጂ እኔንም ከቆንጆዬ ጋር ተይኝ ብያት ጥያት ወደ ተማሪው ስመለስ ቤት በኩል እንደወጣ ድራሹ የለም ! አመዴ ቡን አለ!።
ሹክክ ብዬ ስመለስ ሲወጣ ትየው ወይ እንደሚወጣ ቀድማ ትወቅ ብቻ ቀድማ ነበር እየሳቀች የጠበቀችኝ "
አለችና በረጅሙ ተንፍሳ ጭንቅላቷን እየነካካች
"የሷ ጉድ መች ያልቃል እራሴን ሲሻለኝ አወራሻለሁ ። ግን እሄ ልጅ ማነው ኤዱ ?" አለች በአገጯ ወደኔ እያመለከተች። ሁለቱ አልጋ ላይ እኔ ደግሞ ከፊት ለፊታቸው ክፍሉ ውስጥ መስኮት ስር ባለችው አንዲት ወንበር ላይ ተቀምጫለሁ።
"ወንድሜ ነው! ያንቺዋ መሲ ሳታስበው የሰጠችኝ ምርጥ ወንድሜ!"አለቻት ።
ኤደን ስትናገር በጥልቀት እያየችኝ ነበር ንግግሯም ከልቧ ስለመሆኑ ቃናው ያስታውቃል።
"!?" እንዴት አለች ረድኤት ግራ ተጋብታ ።
በዚህ መሀል ጣልቃ ገባሁና እሱን እንቅልፍ እስኪወስዳችሁ ድረስ ታወራላችሁ እኔ ልሂድ አልኳቸው እና የመሲን ፎቶ በግድ ድርቅ ብዬ ከረድኤት ሞባይል ላይ ወደኔ ከላኩ በኋላ ኤዱን ነይ አንዴ ብያት ከክፍሉ ወጣሁ ።
ተከትላኝ እንደወጣች እሄን ለግዜው ያዥው ብዬ የተወሰነ ሳንቲም ሰጥቻት ስልኳን ወስጄ ደና እደሩ ነገ እደውልልሻለሁ ብያት ልሄድ ስል •••
ከአንደበቷ ቃል እንዳይወጣ ሰንጎ ከያዛት ሲቃ ጋር እየታገለች •••
"አመሰግናለሁ እሺ" አለችኝ ።
እንደተለየኋት ሰአቴን ስመለከት ዘጠኝ ተኩል ሆኗል።
ሁልግዜም ቢሆን በማታ ስራ ከዚህ ሰአት በፊት ገብቼ አላውቅም አንዳንዴ እስከ አስር ተኩልም ሰራለሁ። ቀጥታ ወደቤቴ አመራሁ። በንጋታው ከእንቅልፌ ስነቃ ከቀኑ ሰባት ሰአት ተኩልን አለፍ ብሏል። እዛው መኝታዬ ላይ ሆኜ ስልኳ ላይ ደወልኩ። ስልኳ ጥሪ አይቀበልም ግቢ ሄደዉም ተኝተዋል ማለት ነው አልኩና ትንሽ ተገላብጬ ተነሳው ተጣጥቤ ቀማምሼ ወጣ እንዳልኩ ነበር ጆሲ ስልክ ላይ የደወልኩት ዮሴፍ ይባላል በጣም የምወደው ጓደኛዬ ነው ።

ከስራ ወጥቼ እየመጣሁ ነው ስደርስ እደውላለሁ አለኝና ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ደርሶ ደወለልኝ ። እንደተገናኘን ማታ ያጋጠመኝን ነገር ንግግራችንን ሳይቀር አንድ በአንድ ነገርኩት።
በመሲ በጣም ተናዶ ለነኤዱ በጣም አዘነ እና እኔን ግን ከባድ ጥያቄ ጠየቀኝ•••
"ዳኒዬ ለልጅቷ ማለት ለ ኤደን ያልካትና ውስጥህ ያለው ስሜት አይጋጭም አደለ!?" አለኝ።
ምን ለማለት ፈልገህ ነው!? አልኩት ቢገባኝም እንዳልገባኝ ሆኜ ለማሰቢያ የሚሆነኝ አየር ለመያዝ
"ማለት እኔ አሁን በነገርከኝ በነኤደን አጋጣሚ ውስጥ የነበረውን ዳንኤልን አላውቀውም"
የቱን ነበር የምታውቀው? አልኩት አሁንም ባስብም ለአጥጋቢ መልስ ጠብ የሚል ሀሳብ ሲደርቅብኝ ግራ ተጋብቼ!
"ሰዎች ውልታ ውለውልሽ ከመንገድሽ ውጪ እንድትሄጂ ከጠየቁሽ ጥያቸው ብሎ እየመከረ ውለታ ለመዋል ቃል የገባው ጋደኛዬ ዳኒ ኋላ የራሱ ቃል ጠልፎ እንዳይጥለው ፈራሁለት! "አለኝ
አልገባኝም ስለው
" ባክህ ገብቶሀል አታድርቀኝ !" አለኝ
አዎ ገብቶኛል ጆሲዬ ግንኮ አንዳንዴ በንፁህ እህትነት ብቻ የምንቀርባቸው ሴቶች ያስፈልጉናል ቢያንስ አንድ እሷም እንደወንድሟ አንተም እንደህትህ የምታያት ሴት እንድትኖርህ አስበህ አታውቅም ?!ስለው•••
"አላውቅም!" አለኝ ፈርጠም ብሎ
ለምን ?
"የለም ማለቴ አደለም ግን መጨረሻው አያምርም!" አለኝ አሁንም ቁምጭጭ ብሎ
ጆሲዬ መጨረሻውን እያሰብን ነገሮችን የምናጣጥም ከሆነማ መጨረሻችን ሞት መሆኑን እያስታወስን ምንም እንዳይጥመን፣ ምንም እንዳይደንቀን፣ ምንም እንዳይሞቀን ፣ሆነን መኖራችን ነውኮ ስለው
እሱማ መታደል ነዎ የሰው ልእልና ጫፍ ላይ መድረስ ነገ መሞታችንን ሁሌ ካስታወስን ክፋት ይሸሸን ነበርኮ ዳኒዬ
ክርክር ከጀመረ አያቋርጥም ።
አቦ ተወኝ እንግዲህ ይልቅ ባለፈው ያልከውን ሀሳብ ተውከው እንዴ? አልኩት
"የቱን?"
ስራ እንደጀመርኩ አከባቢ ለሁለት አንዲት ክፍል ተከራይተን ለምን ከቤተሰቦቻችን ቤት አንወጣም ያልከኝን ስለው ሳቁን ለቀቀው
ምን ያስቅሀል አልኩት ተናድጄ!
"መከራየቱን አልተስማማህም ነበር እኮ አሁን ምን አዲስ ነገር ተገኘ አየህ ውስጥህ እና ለሷ ያልካት ነገር እንዳይጋጭ ያልኩህ ለዚህ ነው!"ሲለኝ•••
ባክህ ለዛ አደለም ለሊት ለሊት ከስራ ስገባ እየረበሽኳቸው ስለሆነ ነው አልኩት።
"ይሁንልህ" አለኝ አሁንም እየሳቀ።
ማታም ስልኳ ላይ ስሞክር ጥሪ አይቀበልም ዝም ብዬ ወደ ምትማርበት ዩንቨርስቲ ሄድኩና ትናንት አብረን የነበርንበት አከባቢ ጭለማ ውስጥ የባጃጄን መብራት በማጥፋት ስላሳ ደቂቃ ያህል ግቢ ውስጥ ውር ውር ከሚሉት ተማሪዎች በተጨማሪ ከግቢ የሚወጡትን እና የሚገቡትን በአይኔ ስሸኝና ሳስገባ ቆየሁ።
ኤዱን ግን አላየኋትም ። መሄዴን ለጆሲም አልነገርኩትም።
በንጋታው በደላላ አፈላልጌ ከሰፈር ብዙም በማይርቅ በአንድ ትልቅ ግቢ ውስጥ ስፋቷ አራት ባአራት የሆነች ሰርቪስ ቤት አገኘሁ ለጆሲ ደውዬ ማግኘቴን ስነግረው እየሳቀ በል እሺ ኪራዩን ክፈል ከስራ ስወጣ ብር አወጣና ፍራሽ ምናምኑን እንገዛዛለን አለኝ።
ቤታችንን ማብሰያም መቀቀያም የለላት ምርጥ የወንደላጤዎች ቤት አደረግናት በየፍራሻችን ላይ ጋደም እንዳልን ስልኬን አውጥቼ የኤዱ ስልክ ላይ ስሞክር ጠራ ፍንጥር ብዬ ስነሳ •••
"ምን ሆንክ!? " አለኝ ደንግጦ ከፍራሹ ላይ ቀና እያለ!
እየጠራ ነው ስለው
"ማነው እሱ!? አለኝ
የኤዱ ስልክ ነዎ ስለው •••
"ካካካካካካ ••••!" የጆሲ ሳቅ ነበር•••

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
1👎1
#ልጩህበት!!


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በጥላሁን

የኤዱ ስልክ ላይ ስሞክር ጠራ ፍንጥር ብዬ ስነሳ •••
"ምን ሆንክ!? " አለኝ ደንግጦ ከፍራሹ ላይ ቀና እያለ!
እየጠራ ነው ስለው
"ማነው እሱ!? አለኝ
የኤዱ ስልክ ነዎ ስለው •••
"ካካካካካካ ••••!" የጆሲ ሳቅ ነበር•••
እስቲ ላውራበት የሚል መልክት የያዘ ግልምጫ ገላመጥኩት ኤዱ ስልኩን ያነሳችው መስሎት ሳቁን ባጭሩ ቀጨው።
የኤዱ ስልክ ግን አልተነሳም አሁንም እየጠራ ነው •••" ጢርርርርር•••••ጢርርርርርር••••ጢርርርርርርር•••!"
ጥሪው አለቀና ሴትዮዋ "የደወሉላቸው ደንበኛ ስልክ አይመልስም"! ብላ የማውቀውን እውነት ለመድገም ከመድከሟ በፊት "የ!" እንዳለች አቋረጥኳትና በዝግታ ወደ ፍራሼ ተመለስኩ።
ሽቅብ እያየኝ የነበረው ጆሲ•••
"ምነው? አላነሳችልህም እንዴ?"ሲለኝ •••
አይ "ቤተ መፃህፍት ውስጥ ነኝ ስወጣ እደውልልሀለሁ!" አለችኝ አልኩት።
"ለዚሁ ነው ሳቄን ያቋረጥከኝ ምናለ እስቲ ብስቅበት!"
ካቆምክበት ቀጥላ ! አልኩት በሽቄ።
ዳንዬ የምስቀው አንተን ለማናደድ ቢሆን ኖሮ ካቆምኩበት እቀጥል ነበር እኔ የሳኩት ግን የእውነት ሁኔታህ አስቆኝ ስለሆነ ከቆምኩበት መቀጠል አልችልም"
ባንድ ጉዳይ ላይ ካንድ ግዜ በላይ መሳቅ አይቻልም እያልከኝ ነው?
"አላልኩም እሱ እንደሁኔታው ይወሰናል መቼም ግን ባንድ ጉዳይ የመጀመሪያውን ሳቅ ደግመህ መሳቅም ሆነ ከቆምክበት መቀጠል አትችልም!
ለምሳሌ•••!"
ብሎ ሊቀጥል ሲል
በቃ! በቃ ! ጆሲ በቃህ በናትህ ! ምንድን ነው ነገር እንደዚህ ማስፋት! ያ ፍቅሩ የተባለ ጋደኛህ ግን መጥፎ ልማድ እያለማመደህ ነው!
"ስትል ? እንዴት?" አለኝ ግንባሩን ቋጥሮ
ምን እንዴት አለው ከሱ ጋር ስትገናኙ በቃ የሆነች ርእስ ካገኛችሁ ቀኑን ሙሉ ስትከራከሩባት አደል እንዴ የምትውሉት የሱ ባህሪ ባይጋባብህ ኖሮ ድንገት ተነስተህ
ሳቅ ይደገማል ? አይደገምም ?
በሚል ርእስ ከኔ ጋር ልትከራከር ባልሞከርክ ነበራ?
ቆይ ያ ጓደኛህ ግን እሚያነበው ለመከራከር ነው? ወይስ ለማወቅ? አልኩት•••
"እምትከራከረው እኮ ስታውቅ ነው አለኝ ገልበጥ ብሎ በጀርባው እየተንጋለለ
እማትከራከረው ስለማታውቅ ነው እያልከኝ ነው ? ስለው
"ሰው ያውቃል እሚባለው ምን ያህል ሲያውቅ ነው ? ቆይ የማወቅ መለኪያው ምንድን ነው መቼስ ሰርተፍኬት ነው አትለኝም እንደዛ ቢሆን ሀገራችን ውስጥ •••"
ብሎ ሊቀጥል ሲል ለሁለተኛ ግዜ አቋረጥኩትና•••
ደሞ ጀመርክ እሄን ፖለቲካህን!
ስለፖለቲካ ማውራት አልፈልግም ይልቅ የጠየኩህን መልስልኝ አልኩት•••
"ዳንዬ የሚከራከር ሁሉ ያውቃል ማለት አይደለም እንደውም ሀገራችን ውስጥ የማያውቀው ነው ሁሉንም ነገር ተቆጣጥሮት እሚንጫጫው የሚያውቀው የተሻለው ዝምምምምምምምምምም ብሏል ለምን ይመስልሃል?"
በናትህ እሄን ርእስ ከዛ ከፍቅሩ ጋር ተዳረቅበት ከፈለክ ደውዬ ልጥራልህ እኔን ግን ተወኝ ! አልኩት ኮስተር ብዬ•••
" ወይ ፎንቃ••••• እና እሺ ስለምን እናውራ ቆይ አንተ እምትፈልገው ስለኤደን ብቻ እንድናወራ ነው?"
በናትህ ጆሲ እንዲህ አትበለኝ እኔ እማ ትሙት ኤዱን በጣም እምሳሳላት እህቴ እንደሆነች ነው የሚሰማኝ በሌላ በምንም ነገር አላሰብኳትም! ስለው ፍጥጥ ብሎ ለሰከንዶች አየኝና•••
"በእውነት! አመንኩህ በቃ ካሁን ቡሀላ እንደዚህ አልልህም!" አለኝ ከልቡ ነበር።
በማላውቀው ቁጥር ስልኬ ላይ ተደወለ እንደዋዛ አነሳሁትና •••
ሀሉ ስል•••
" ሄሎ ዳንዬ የኔ ውድ ወንድም እንዴት ነህልኝ ይቅርታ እሺ ረዱን ትንሽ አሟት ስለነበረ እሄን ሁለት ቀን ችግር ላይ ነበርን !"
የሚለውን የኤዱን ድምፅ ሰማሁ!•••
ለምን ደውለሽ አልነገርሽኝም ስላት እየተንተባተበች እኔን ከዛ በላይ ላለማስቸገር አስባ እንጂ ሳላስፈልጋት ቀርቼ እንዳልሆነ ልታስረዳኝ ሞከረች።
በቃ ከዛን ቀን ቡሀላ ቢያንስ በየሁለት ቀኑ በስልክ ቢያንስ በየሁለት ሳምንቱ ደግሞ በአካል እየተገናኘን እናወራለን ሻይ ቡና እንባባላለን ማታ ማታ ከነበረው ስራዬ ቀንም ማታም እስከተወሰነ ሰአት ወደ መስራት ከተሸጋገርኩ ቡኋላ አንዳንዴ ቀን ወደነሱ ግቢ ሰው ይዤ ከሄድኩ ሳላገኛት አልመለስም ።

ብዙ ግዜ እኔ ጋር ስትመጣ ረዱን ይዛት ትመጣለች ትግስት ስለምትባለው ጓደኛቸው ስጠይቃቸው ሁለቱም እየተጋገዙ "እሷ ከመሲ ጋር ተጣብቃ ቀረችኮ!
ዶርምም ለቃለች !
ማንበቡንም ጭራሽ ትታዋለች !
ክላስ እራሱ ብዙ የምትገባ አይመስለኝም!" በማለት ነግረውኛል እነሱ ግን መሲ ባለፈችበት መንገድ እንኳን አንደማያልፉ አውቃለሁ።
በዚህ መልኩ ቅርርባችን ቀጠለ። ከተዋወቅን አራት ወር ከሁለት ሳምንት ሆነን።
ከዛሬ ሶስት ሳምንት በፊት አንድ ጥያቄ ጠይቂያት ነበር መቼ ነው የተከራየኋት ቤት ውስጥ አንቺና ጓደኛሽ ቡና እምታፈሉባት? ብዬ የሁለተኛው መንፈቅ ፈተና መድረሱን ነግራኝ ፈተናውን እንደጨረሱ እንደምትመጣ ቃል ገባችልኝ ። እኔም ፈተናዋን ተፈትና እስክትጨርስ እየደወልኩ እንደማረብሻት ቃል ገባሁላት ። ችግር የለውም ደውል ብትለኝም ደውዬ አላውቅም ዛሬ አርብ ነው በነገረችኝ መሰረት ከሆነ ዛሬ ፈተናው ያልቃል። ስልኳን ስጠባበቅ ነው የዋልኩት እስካሁን ግን አልደወለችም ።
አመሻሹ ላይ ስራ ላይ ሆኜ ስልኬ ጠራ እየነዳሁ ነበርና ባጃጄን ጥግ አስይዤ ስልኬን ከኪሴ አውጥቼ ስመለከተው ኤዱ ነች ሰላምታ ከተለዋወጥን
ቡሀላ የነበረችበት ቦታ የሙዚቃ እና የሰው ጫጫታ ስለነበር የት ነሽ? አልኳት ግቢ ካፌ ውስጥ እንደሆነች ከነገረችኝ
ቡሀላ ነገ ማለት ቅዳሜ ስምንት ሰአት ላይ እንደምትመጣ ነገረችኝ እኔ እራሴ ግቢ ሄጄ እንደምውስዳት ነግሪያት ስራዬን ቀጠልኩ ልክ ከምሽቱ አራት ተኩል ላይ በቃ አቦ ደክሞኛል ልግባ ብዬ እያሰብኩ ስልኬ ጠራ በቋሚነት ስልክ ተቀያይረን ሲፈልጉ እየደወሉ ኮንትራት ከሚይዙኝና ደና ብር ከሚከፍሉኝ ሰዎች መሀከል ቀዳሚው ነበር የደወለው የማይታለፍ ስልክ አልኩ ገና ስልኩን እንዳየሁት።
እሄን ሰውዬ ሳስበው ነገረ ስራው ሁሉ ይገርመኛል የሆነ ድብቅ ማንነት ያለው ሰው ነው ኑሮው ድሬ ዳዋ አይደለም አልፎ አልፎ ነው ከጅግጅጋ ወደ ድሬ የሚመጣው ሁሌም እንደነገ ሊመጣ እንደዛሬ ይደውልልኝና ነገ መጣለሁ የተለመደው ቦታ አልጋ ያዝልኝና ውሃ አስገባልኝ ይለኛል ። ትዛዜን ተቀብዬ ክፍል ይዝለትና እሽግ ውሃውን በብዛት አስገብቼ እጠብቀዋለሁ ። ድሬ ሲቃረብ ይደውላል መግቢያው ላይ ጠብቄ ወደያዝኩለት ክፍል እወስደዋለሁ ።
ጥዋት ቁርስ ምሳ ሰአት ላይ ምሳና ኪሎ ጫቱን እንዲሁም ሌሎች የሚያስፈልጉትን ሁሉ ሴተኛ አዳሪን ጨምሮ አስገባለታለሁ ለሁለት ወይም ለሶስት ሳምንት በዚህ መልኩ ከያዝኩለት ክፍል ሳይወጣ ይቆይና ይሄዳል።
አሁን ከመጣ ስምንት ቀን አልፎታል ።
አንዳንዴ በቆይታው መሀል ቢበዛ አንድ ወይም ሁለት ቀን ወጣ ማለት ካስፈልገው ብቻ በዚህ ሰአት ይደውላል ዛሬም መውጣት ፈልጎ ይሆን እንዴ? እያልኩ ስልኩን አንስቼ ሳናግረው እንደጠረጠርኩት •••
"አቢቲ ዛሬ ወጣ ማለት አስኝቶኛል ትመጣልኝ?" አለኝ ባጃጄን አዙሬ ወዳለበት ከነፍኩ።
ሰው ወደማይበዛበት እና ሁሉም ነገር ወደድ ወዳለበት ጭፈራ ቤት አድርሼው ስመለስ ከኋላዬ የተሳፋሪ መቀመጫው ላይ ስልክ ሲጮህ ስልኩን ጥሎ መውረዱ ገባኝ አንስቼ ሄሎ ስል•••
" አቢቲ ስልኬን ባጃጅህ ውስጥ ጥያት ወረድኩ ታቀብለኝ?" አለኝ።
ጭፈራ ቤቱ ውስጠኛው ክፍል ውስጥ ገብቼ ስልኩን ሰጥቼው ልወጣ ሁለት እርምጃ እንደተራመድኩ ድንገት ወደ ቀኝ ገልመጥ ሳደርግ
ሁለት ሴቶችና አንድ የሰፈራችን ሀብታም ነጋዴ
2
#ልጩህበት!


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በጥላሁን

ጭፈራ ቤቱ ውስጠኛው ክፍል ውስጥ ገብቼ ስልኩን ሰጥቼው ልወጣ ሁለት እርምጃ እንደተራመድኩ ድንገት ወደ ቀኝ ገልመጥ ሳደርግ
ሁለት ሴቶችና አንድ የሰፈራችን ሀብታም ነጋዴ የተቀመጡበት ሶፋ ላይ አይኔ ተተክሎ ቀረ።
ደነገጥኩ!
ሰውየው የኤች አይ ቪ ኤድስ ተሻካሚ የሆነና ሚስቱ በዚሁ በሽታ የሞተችበት ሰው ነው ።

•••ሁለቱ ሴቶች ደግሞ አንዷ ጭራቋ ስትሆን አንዷ ደግሞ ምናልባት የነኤዱ ጓደኛ ሳትሆን አትቀርም ወይኔ ቲጂ እንዲህ አንድፍሬ ልጅ ነሽ ቆይ ኧረ •••
አልኩና እየተጣደፍኩ ከጭፈራ ቤቱ በመውጣት ሞባይሌን ከኪሴ አውጥቼ ፎቶ ማህደሩን ከፈትኩ አልተሳሳትኩም መሲ እራሷ ነች ከንፈሮቼን በሶስት ጣቶቼ ተጭኜ የመሲ ፎቶ ላይ እንዳፈጠጥኩ ወደ ባጃጄ ውስጥ ገብቼ ተቀመጥኩ ።
መደበኛ ስራዎ እሄ መሆኑን አውቃለሁ እኔን ያስደነገጠኝ አገር ምድሩ ሚስቱ በምን እንደሞተችና እሱም ምን እንዳለበት ከሚያውቀው ከዚህ ህሊና ቢስ ቀበጥ ጋር መተዋወቋ ነው።
ምንም የማያውቁ ከየቦታው የሚመጡ ፍሬሽ ተማሪዎችን እያቀረበችለት ሲጫወትባቸው ታየኝ እሷና እሱን ከዚህ ውጪ ምንም ሊያገናኛቸው እንደማይችል ግልፅ ነው ።

ሰውየው እንደሆነ ከመጨረሻዋ ልጅ እኩዮች ጋር ለመጋደም ፈሪሀ ህሊንም ሆነ ፈሪሀ ፈጣሪ ያልፈጠረበት አረመኔ መሆኑን እንኳን እኔ በታክሲ ስራ ምክንያት ከተማ ውስጥ ስቅበዘበዝ የምውል ከቤት የማይወጣ የሰፈራችን ሰው ቢኖር እንኳን ስለዚህ ሰውዬ ለመስማት መጠየቅ አይጠበቅበትም ስለሰፈራችን ሀብታሞች ከተወራ የሚወራ ብዙ ነገር ያለው እሱ ነው።
ባጠቃላይ ሰባት ልጆች አሉት። እናት አባቶቻችን ስለሱ ሲያወሩ•••
" ሀብታም የሆነው አንድ ልጁን ለሰይጣን ገብሮ ነውኮ ልጁ መፍዙዝ ሆኖ ግቢያቸው ውስጥ ካለች አንድ ክፍል ውስጥ ጫቱን ሲደፈልቅ ውሎ ነው እሚያድረው ወደውጪ ሳሰማይወጣ ሰው አያውቀውም!" ሲሉ ሰምቻለሁ
ለሀብት ሲል የገዛ ልጁን እንደዛ ያረገ ሰው ደግሞ ለምድር ቆይታው በቀሩት የተገባደዱ ቀሪ እንጥፍጣፊ አመታት የልጁ ታናሽ እና እኩያ የሚሆኑ ሴት እህቶቻችንን በገንዘብ ሀይል ጨርሶ ለማለቅ ባይሽቀዳደም ነበር እሚገርመኝ!።
ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ ስለዚህ ሰው ማንነት እያወኩ ቢሳካም ባይሳካም ልጅቷን ከሱ ለማስጣል ሳልሞክር ወደቤቴ ብሄድ የሰላም እንቅልፍ እንደማይወሰደኝ ምናልባትም እስክረሳው እና ባስታወስኩት ቁጥር የጥፋተኝነት ስሜት እንደሚለበልበኝ አውቀዋለሁ ።

የሆነ ነገር መሞከር አለብኝ አልኩ ለራሴ ሞክሬ ካቅሜ በላይ ሆኖ ባይሳካ እንኳን ከህሊና ክስ እተርፋለሁ!
አካሄዴን ከማጣራት መጀመር እንዳለብኝ አስብኩ ምክንያቱም መሲ የዚህ አገር ልጅ ስለሆነች ዘመዱ ብትሆንስ አብራቸው ያለችው ልጅ ደግሞ የነ ኤዱ ጓደኛ ትግስት ባትሆንስ?
እዛው ባጃጄ ውስጥ እንዳለሁ ኤዱ ጋር ደወልኩ
አነሳችው። ግዜ ሳላጠፋ ቀጥታ ወደገደለው ገባሁ•••
ኤዱ የጓደኛሽን የትግስትን ፎቶ በቴሌግራም ላኪሊኝ
"ለምን ? ምነው? በሰላም ነው?"
አዎ በሰላም ነው አፍጥኚው!
ላከችልኝ። ትግስት ናት ብላ ኤዱ የላከችው ፎቶና አሁን በዚህ ሰአት ከነመሲ ጋር ያለችው ልጅ ጭራሽ አይገናኝም!
ሌላ ነች ማለት ነው? የግቢ ልጅ ትሆን ? በራሴ ጥያቄዎች ስወዛገብ ኤዱ ደወለች•••
ወዬ ኤዱ
"ምንድን ነው እሱ?" አለችኝ ያየሁትን ነገርኳት
"እስቲ የልጅቷን መልክ ንገረን "አለች።
ከረዱ ጋር አብረው እንደሆኑ ገባኝ ምናልባትም ስልኳን ድምፅ ማጉያ ላይ አድርጋው ለሁለት እየሰሙኝ ነው።
የልጅታን መልክ ማብራራቴን ጀመርኩ•••
ልጅቷማ ደስ የሚል ቅጥነት ያላት! ፀጉሯን ብራውን የተቀባች በጣም ቀይ ! አፍንጫዋ •••
እያልኩ ከአናቷ ጀምሬ ቁልቁል ልወርድላት ስል ካንገቷ ሳልሻገር ልጅቷን አወቋት መሰለኝ ቆይ ቆይ አንዴ ቴሌግራም ላይ ገባና ጠብቀኝ ብላ መልሴን ሳትሰማ ስልኩን ጠረቀመችው።
የላከችው ፎቶ ቴሌግራሜ ላይ እንደገባ በፍጥነት በረገድኩት እሚገርመው ልጅቷ እሄን ፎቶ ከለቀቀች ቡሀላ ፎቶው ላይ ያለውን ልብሷን ሳትቀይር ነው ወደጭፈራ ቤቱ የመጣችው ምናልባትም ወደዚህ አምሮባት ስትመጣ ተነስታ ቴሌግራሟ ላይ ለቃው ይሆናል።
ኤዱ እሄን ፎቶ ኬት ነው ያገኘሽው?
"ዛሬ ቀን ዘጠኝ ሰአት አከባቢ ነው የፌስ ቡክ ፕሮፋይል ፒክቸሯን የቀየረችው ከዛ ላይ እስክሪን ሹት አድርጌ ነው የላኩልህ ምነው ልጅቷ እራሷ ነች እንዴ ዳንዬ!?
አዎ እሷ ናት ስላቸው ሁለቱም ጮሁ!!
ምንድን ነው ምንሆናችሁ ኤዱ?
ቆይ እሷ ትንገርህ እንቺ ብላ ስልኩን ለረድኤት ሰጠቻት •••
" መሲ በመጨረሻም ተሳክቶላት እቺን ልጅ ወጥመዷ ውስጥ ጣለቻት እኔ አላምንም! "
ማለት? አልኳት።
ግራ ገብቶኝ አንቺ ኤዱ እና ትግስትስ በወጥመዷ ውስጥ ገብታችሁ የለ እንዴ
የሚለውን ሀሳብ ለራሴ እያወራሁት ቀጠለች•••
"አንድ ቀን ልጅቷ ባጠገባችን ስታልፍ መሲ ልጅቷን በክፉ አይን ስታያት አየሁና ምነው? ስላት•••
እቺ ልጅ ለጓደኛዋ ድንግል ነኝ የጀመርኩት ነገር የለም ማለቷን ሰምቼ ላጠምዳት ብሞክርም ገገማ አሳ ሆነችብኝ!።
ጋደኛዋ በኔ ቀመር እየተሽቀረቀረች ልታስቀናት ብትሞክርም ልጅቷ አልሞቅ አልደንቅ እንዳላት ነገረችኝ አሁን ሳያት ታስጠላኛለች !
" ብላ ስትነግረኝ •••
ምነው የኔ አይን አርፎባት! ለሆነ ቢዝነስ አቀባብያት ! ሳልተኩሳት የምትክሽፍብኝ ሴት የለችም ስትይ አልነበር እንዴ ታድያ እቺ እንዴት ከሸፈችብሽ ? ስላት
ኮሚሽን ሼር ሳላደርግ ለብቻዬ ማጣጣም ስለፈለኩ እንጂ እኔ መሲ እልህ ውስጥ ከገባሁ የትኛዎም የግቢ ሴት በዘረጋሁላት መረብ ላይ መወዘፏ የማይቀር ነው! "
ኮሚሽን ሼር ላለማረግ ስትል ምን ለማለት ፈልጋ እንደሆነ ጠየኳት እንዲህ አለች•••
እቺ ልጅ ጋደኛዋ ብትሽቀረቀር ብትብለጨለጭ ብልጭ አይልባትም አደል ስለዚህ እቺን በብልጭልጭ ነገር ማጥመድ አይቻልም ለእንደዚህ አይነት ሴቴች ደግሞ እቅድ ሁለት (ፕላን ቢን) እጠቀማለሁ የቱንም ፈተና ብትቋቋም ያንን መቋቋም ይከብዳታል።
እንደዚች አይነቷን በሴት ሳይሆን በወንድ ታጠምጃታለሽ እንኳን የሷን የድንጋይን ልብ የሚያቀልጥ ስንት የድሬ ልጅ ሞልቷል እሄን ያህል እከፍልሀለሁ በግር በጇ ብለህ አጥምዳት ብለው ሁለት ሳምንት ባልሞላ ግዜ ውስጥ አምጣት ያልኩት ቦታ እያክለፈለፈ ያመጣልኛል ግን ከልጅቷ ሽያጭ ግማሹ የሱ ነው ያንን ነው ኮሚሽን ያልኩሽ ብላኝ ነበር ይገርማል በዛ መንገድ ሸውዳ እጇ አስገባቻት ማለት ነው!?"
ስትለኝ እልህ አንቀጠቀጠኝ !
በፍፁም አታስገባትም! ኡልኩና ስልኩን ዘጋሁባት!
ምናልባት ሰውየው በአይን ሊያውቀኝ ስለሚችል ባጃጄ ውስጥ ያለውን ጥቁር ኮፍያ አደረኩና እስከ ግንባሬ ዝቅ አድርጌ አጎበጥኩት !
ሰተት ብዬ ወደ ጭፈራ ቤቱ ገባሁና ከነሱ ትይዩ ኮርነር ላይ ተቀምጬ መጠጥ አዘዝኩ።
መሀላቸው ጎልተው ግራ እንዳጋቧት የሚቅበዘበዘው ፊቷ ይመስክራል ። ምናልባቷ አጥምዶ ያስረከባት ልጅ መጣሁ ብሎ በመውጣት በዛው ቀርቶባት ይሆን አስሬ ዘወር ዘወር እያለች እምታየው? አንጀቴን በላችኝ !!
እየጠጣሁ ሁለቱን አውሬዎች ባየኋቸው ቁጥር ንዴቴ እየጨመረ መጣ!
ሰውየው ያንን በድሜ ብዛት ቶሎ ቶሎ ኩበት እየሆነ የሚያስቸግረውን ከንፈሩን በምራቁ ለማውዛት እየመጠጠ ያቺን አንድ ፍሬ ልጅ ለማሽኮርመም ሲታገል ስመለከተው አለም አስጠላችኝ !
ተነስተህ በባክስ ወደ ጀርባው ዘርረውና ልጅቷን ይዘካት ውጣ ውጣ አለኝ።
መሲ ተነስታ ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ ከጀርባ ተከተልኳት ! እሷ ከፊት እኔ ከውኋላ ወደ ሽንት ቤት እምትወስደው ቀጭና መንገድ መሀል ላይ እንደደረስን
👍1