አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
511 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
​​አለብሽ..ምንም አይነት የዓላማ መዛናፍ..ምንም አይነት በህይወት የሚከሰት ሀዘን ሊሰብርሽና በጀርባሽ ሊዘርርሽ አይገባም፡፡››
‹‹እሺ…እየታገልኩ ነው፡፡ያለፈ ቆሻሻ ማንነቴን ከላዬ ላይ አውልቄ ጥዬ አዲሷን ሳባ ከውስጤ አብቅዬ ማሳደግና ከእሷ ጋር ስምምነት በመፍጠር በአዲስ አይነት የህይወት መስመር አዲስ አይነት ህይወት ለመኖር ነው እቅዴ…››
‹‹ድንቅ እቅድ ነው..አየሽ አዲስ ሰው ለመሆን የምንፈልግ ከሆነ መጀመሪያ ልክ እንደምንፈልገው አይነት አዲስ ሰው በምናባችን ቀርፀን ያንን ሰው እንደሆን ፊል በማድረግ በምናብ ደጋግሞ ማሰላሰል ይጠበቅብናል፡፡ንቁ የሆነው የአእምሮ ክፍል ሀሳብ የሚፈልቅበት ፤የሚተነተንበትና ፤ተመዝኖ ውሳኔ የሚሰጥበና በከፊል ንቁ ወደሆነው የአእምሮችን ክፍል የሚተላለፍበት ስፍራ ነው፡፡በከፊል ንቁ የሆነው የአእምሮ ክፍል የተቀበለውን ሀሳብ ያለምንም ጥያቄና ያለምንም እርማት እንዳለ ተቀብሎ(ልክ እንደ ወታደር) ተግባራዊ የሚያደርግበትን መንገድ ማውጠንጠን ይጀምራል፡፡ንቁ ያልሆነው አእምሮችን ክፍል ተመሳሳይ አይነት ነገር ደጋግመን ስንጭንበት ያንን እውን እንዲያደርግ የሚያስችለውን ኃያል እንዲያጎለብት እያደረግነው ነው፡፡ስልዚህ ይሄንን ቅዱስ የሆነ እቅድሽን ደጋግመሽ ለአእምሮሽ ንገሪው…ከዛ በእርግጠኝነት ይሳካል፡፡››
እንደዚህ ሲያወሩ ቆዩና በማግስቱ ሀኪም ቢት በመሄድ ያቆረጠችውን መደበኛ ህክምና ለመቀጠል ተስማምታ ተለያዩ፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8012🤔3🥰1
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ስድስት ፡ ፡ #ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ባለፋ ሶስት ወር ውስጥ ተሰምቷት የማያውቅ ደስ የሚልና የሚያፅናና ስሜት ተሰማት…..እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነቷን ለመታጠብ ወደ ሻወር ቤት ገባች፡፡ግዙፉ መስታወት ፊት ቆማ የለበስችውን ቢጃማ በቁሟ አወለቀችና እዛው ከእግሯ በታች ወለሉ  ላይ  ረገጠችው…መላ  እሷነቷን  በፅሞና  ተመለከተች…. ፀጉሯ በዛ ርዝመቱና ብዛቱ ጭብርር…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ለ15 ቀን ያህል በሶስት ቀን አንዴ እየተመላለሰች ህክምናዋን መከታተልና የታዘዘላትን መድሀኒት በመጠቀም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ከጀመረች በኃላ... ቀናውና ሳባ እሷ መኝታ ቤት አንድ አልጋ ላይ ጎን ለጎን ተኝተው እያወሩ ነው።

‹‹እንግዲህ አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነሽ ...ቀጣይ  እቅድሽ ምንድነው?›› "ቀጣይ እቅዴ አንተን ማግባት"አለችው ፍርጥ ብላ
"እውነቴን እኮ ነው"

""ወደአሰላ እመለሳለሁ...እዛ የእንጀራ እናቴ የጀመረችልኝ በጣም እስፔሻል የሆነ ስራ አለ …እሱን በሰፊው መስራት ነው የምፈልገው።››

"ምንድነው ስራው?"

"ልነግርህ አልችልም...የዛሬ ሳምንት አብረን እንሄዳለን ..የምወዳት እናቴን አስተዋውቅሀለው..ትንሹ      ወንድሜም      እርግጠኛ      ነኝ      ይወድሀል... እናም የምወዳትን እትብቴ የተቀበረባትን ከተማዬን አስጎበኝሀለው...ከዛም የምሰራውን ስራ አሳይሀለው።››

"በጣም ደስ ይለኝ ነበር...ግን እኮ የዛሬ ሳምንት የምበርበት ቀን ነው፡፡"

"ምን?"ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቁጭ አለች።
ጭራሽ ትዝ ብሏት አስባበት የማታውቀው ነገር ነው፡፡

ቅዝዝ እና ክፍት ብሏት፡፡"የእውነት ጥለኸኝ ልትሄድ ነው...?."ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን ማድረግ እችላለሁ...?እሺ ብትይኝማ ወደአሜሪካ ብወስድሽ ደስ ይለኛል  "

‹‹እንደዛማ ማድረግ አልችልም...ለስንድ ቃል ገብቼላታለሁ....አባቴን የሚያስደስት ስራ መስራት ነው የምፈልገው፡፡ሀገሬን ለቆ የመሄድ እቅድ የለኝም"

"ይገባኛል....ግን የእኛ ነገርስ?"

"እኳ አትሂድ ምልህ እኮ ለእኛ ብዬ ነው።...አሜሪካ ምን አለህ ?ገንዘብ ብቻ ነው ያለህ። እዚህ ለዛውም አሰላ ለመኖር ያንተ ብር አያስፈልገንም።እኔ ሁሉንም ነገር አስተካክላዎለው።ይሄንን ቤት እንሸጥና ጥሩ  ብር  እናገኛለን፡፡  ከዛ   አሪፍ የሆነ ገቢ ሚያስገባ ድርጅት እናቋቁማለን..፡፡››

"መሄድ እኳ የምፈልገው ለገንዘብ አይደለም...የካትሪንና የሱዛና ስም ከስሞ እንዲጠፋ ስለማልፈልግ ነው።በካምፓኒው አመታዊ ትርፍ የሚንቀሳቀስ ካትሪን ኤንድ ሱዛና ፋውንዴሽን የሚባል የእርዳታ ድርጅት ለማቋቋም አስቤ ነበር።

"የሚገርምና ደስ የሚል ሀሳብ ነው።.....ግን ፍውንዴሽኑ ምን ላይ ነው የሚሰራው..?ሀሳብህ እንዴት ነው?።››

"እሱን  ገና  አልወሰንኩም...ይሄን  አይነት  ሀሳብ   እራሱ   ወደ   አእምሮዬ የመጣው እኮ አሁን በቅርብ እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ነው።"

"አትለኝም...እየቀለድክ መሆን አለበት?"

"የእውነቴን ነው፡፡ ወደ ኢትዬጰያ ስመጣ የምኖርበት   የህይወት   አላማ   የሚኖር ከሆነ በስክነትና በመረጋጋት ውስጥ ሆኜ ለመፈለግ ነበረ...እና የዛሬ ወር አካባቢ
እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ሳውጠነጥን ነው ሀሳብ የመጣልኝ። ስለዚህ ዝርዝሩን ገና አሜሪካ ከሄድኩ በኃላ ነው የተወሰኑ ጥናቶችን በማድረግ የምወስነው።"

‹‹እሺ ገባኝ ..ግን ለእኔ ስትል አንድ ነገር አድርግ...››

‹‹ጠይቂኝ".

‹‹ ..ወደአሜሪካ የመሄድ ቀንህን በአንድ ወር አራዝመው..."

የተወሰነ እንደማሰብ አለና‹‹ጥሩ እሺ አራዝመዋለሁ...እና ለአንድ ወር እንዴት አድርገሽ ልትንከባከቢኝ ነው ያሰብሽው?››

‹‹እርግጠኛ ሁን …አሪፍ የሚባል ጊዜ እንድታሳልፍ አደርጋለሁ…››

‹‹እኮ እንዴት እንዴት አድርገሽ..?››

‹‹በመጀመሪያ አሰላ ወስድሀለሁ...ከምወዳት እንጀራ እናቴና ከወንድሜ ጋር አስተዋውቅሀለው...ቀጥሎ ደሴ እንሄዳለን?"

የደሴን ድምፅ ሲሰማ ደነገጠ "ምን  ..?ደሴ? ምን ለመስራት?"

"ቤተሠቦችህን ሳታይ በምንም አይነት  መንገድ  መሄድ  የለብህም..እነሱ  በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ የቀሩህ የቅርብህ  የሆኑ  ሰዎች  ናቸው።እንዳልከው  እነሱን ማግኘት የማትፈልገው የሚጠይቁህን ጥያቄ መመለስ ፈርተህ  ብቻ አይመስለኝም?"

በገረሜታ አፍጥጦ እያያት ‹‹›.እና ለምን ይመስልሻል?"

"ዳግመኛ የእኔ የምትላቸውን ሰዎች ስትነጠቅ ላለማየት ከለህ ፍራቻ ነው። ጨለማውን እየሸሸህ ነው።በጭለማው ሰንጥቀህ ካላለፍክ ደግሞ ብርሀን የሚባል ነገር አታይም…"

"ዋው...የስነ-ልቦና ባለሞያዎችን ታስንቂ የለ እንዴ?"

"አዎ... በበሽታዬ የተነሳ ከእነሡ ጋር አመታትን አሳለፍኩ እኮ ..አሁን  አሁን እንደእነሡ ማሰብ ጀምሬለሁ።"

‹‹..እሱን በደንብ እያየሁ ነው…ግን ነገሩ እንዳልሽው ቀላል አይደለም.."

‹‹ይሄውልህ ቀናው እኔ ካንተ አላውቅም… አንድ ጓደኛዬ ‹ሁሉም ድርጊቶች የአምላክን ፍቃድ ያገኙ  ናቸው::››የሚል እምነት ነበረወ…  ይሄ  ጓደኛዬ  ሀይማኖተኛ አይደለም…ማለቴ ማንኛውንም ሀይማኖት አይከተልም….ግን በእግዚያብሄር ያምናል..መንፈሳዊ ሰው እንደሆነም ይናገራል፡፡እና እሱ እኛ የሰው ልጆች የእግዚያብሄር ህልውና አንድ  ቅንጣት  ሴሎች  ነን፡፡ከመወለዳችን  በፊት  የእግሩ ሴል ከሆንን ከተወለድን በኃላ ምን አልባት የእጆቹ ሴል ሆነን ሊሆን  ይችላል.. ከሞትን በኃላ ደግሞ የጭንቅላቱ ወይም የፀጉሩ አንድ ቅንጣት ሴል ነው የምንሆነው…ስለዚህ ለእግዚያብሄር ከመወለዳችን በፊትም በተወለድን ጊዜም ሆነ ከሞታችን በኃላም ተመሳሳይ ዋጋ  ነው  ያለን…  ቦታችን  እንቅስቃሴ  ላይ መሆናቸን ካልሆነ በስተቀር ምንም የሚቀየር ነገር የለም…››
‹‹ይመስለኛል ጓደኛሽ ለማለት የፈለገው…ሞት   በእግዚያብሄር   ዘንድ   ያለው ትርጉም እኛ እንደምናስበው አይደለም ለማለት መሰለኝ››
‹‹በትክክል….በቃ አሁን እንተኛ"

‹‹እሺ… ከመተኛታችን በፊት ግን አንድ ጥያቄ መልሺልኝ?›› "ምንድነው?"
"እናትሽ..ማለቴ እንጀራ እናትሽ ላንቺ ብላ የጀመረችውን ስራ ምንድነው?እስቲ ንገሪኝ"

"ምነው ሄደህ እስክታየው መጠበቅ አቃተህ..?እኔስ እንደሰርፕራይዝ እንዲታይልኝ ፈልጌ ነበር...ያው ከዚህ በፊት ታሪኬን ስተርክልህ ስለአባቴ አደጋ ነግሬህ ነበረ.. በመኪና አደጋ ሁለቱም እጀግሮቹን አጥቶ በዊልቸር ለአመታት ሲገፍ ኖሮ እንደሞተ...እና ድንቋ እናቴ ስንድ በተለያየ ምክንያት  አደጋ  ደርሷባቸው  አካል ጉዳት ላይ የወደቁ ግን ደግሞ ለመታከምና ለማገገም የፋይናንስ አቅም የሌላቸውን ጉዳተኞች እቤት በመከራየት ተንከባካቢ ቀጥራ ሀኪም ቤት እያመላለሰች ትንከባከባቸዋለች ፡፡ሙሉ በሙሉ ድነው ህክምና የማይፈልጉበት  ደረጃ  ላይ ሲደርሱ የተሻለ ነገር ካገኙ መርቀዋትና  ተሰናብተዋት  ይሄዳሉ። እርግጥ  ካላት አቅም አንፃር ለጊዜው አስር  የሚሆኑ  ሰዎችን  ነው  የያዘችው..እኔ  አቅሜን አጠናክሬ ስሄድ እስከመቶ ሰው መቀበልና መንከባከብ ምችል ይመስለኛል..በሂደት ደግሞ ፈንድ በማፈላለግ…እያስፋፋሁት ሄዳለሁ…..ያን በማድረጌ ምን አልባት ባለፉት አስር አመታት ውስጥ የሰራዋቸውን ቆሻሻ ስራዎች  እግዚያብሄር  ይቅር ይለኝ ይሆናል፡፡በዛ ላይ ደግሞ ከአባቴ የሙት መንፈስ ጋር ያለኝን ቀረቤታ
አጠብቅበታለሁ…እያንዳንዱን አካል ጉዳተኛ ስንከባከብ አባቴን እንደተንከባከቡኩ ነው ሚሰማኝ..እሱም ባለበት ሰማይ ቤት ሆኖ ይደሰትብኝ ይሆናል፡፡››

‹‹የሚገርም ነው..ምን አልባት እኔና አንቺ  መገናኘታችን  እንዲሁ  በዘፈቀደ  የሆነ ነገር አይመስለኝም…የሆነ ታላቅ ህይወት ምስጢራዊ ተልዕኮ ያለው ሊሆን ይችላል፡፡››

‹‹አልገባኝም››
👍1067👎1😁1
‹‹እኔ ላቋቁመው ያሰብኩት ፋውንዴሽንና ያንቺን ፋውንዴሽን አሰብሽው….?በጥምረት እኮ በጣም ሰፊ ስራ መስራት ይችላል፡፡የእኔ ፋውንዴሽን ጥሩ የሚባል የገናዘብ አቅም  አለው…አንቺና  እናትሽ  ደግሞ  ኦረዲ  የተጀመረ ስራ፤ ጥልቅ የሆነ መነሻ ምክንያትና አላማ ያለው ነው፡፡እና…››

ፊቷ በደስታ በራ‹‹እና ምን…?››
‹‹አብረን ልንሰራ እንችላለና…..የሁለቱ ፋውንዴሽን መጣመር እግረመንገዱን የእኔ እና  የአንቺን  መጣመር  ያፈጥነው  ይሆናል…አሰላ  እስክትወስጂኝና  ከብልኋ እናትሽ ጋር እስክታስተዋውቂኝ ቸኮልኩ››
‹‹በጣም ነው ደስ ያለኝ…››አለች ሳባ፡፡

ቀናውም ‹‹እኔም ደስ ብሎኛል..ደስ ስላለኝ ደግሞ ሞቀኝ እና ሰውነቴን ልለቃለቅ…››ብሎ ከጎኗ ተነሳና ወደሻወር ቤት ገባ፡፡
የሻወር ቤቱን በራፍ ሳይዘጋ ልብሱን አወለቀና  የሻወሩን ውሀ ከፍተ.. ሰውነቱን በውሀ ያስመታ ጀመር…

ሳባ ድንገት ስሜቷ ገፋትና  ከተኛበት  አልጋ  ተነሳ  ስሊፐር  በማጥለቅ  ወደሻወር ቤት ተራመደች፡፡ቀናው ፊቱን በተቃራኒው አቅጣጫ አዙሮ ጀርባዋን ለበራፉ በመስጠት ተገትሮ ቆሟል… ከላይ ከቧንቧው እየተስፈነጠረ ከግንባሩ ላይ በመላተም ወደ ጠቅላላ ሰውነቱ እየተንቆረቆረ በሚወርደው ውሃ ሰውነቱን እያቀዘቀዘው ነው፡፡ሳባ በአንድ ሜትር ርቀት ቆማ እርቃን ሰውነቱን በፍዘት እና በተመስጦ እያስተዋለች ነው፡፡ ይህ ፊት ለፊቷ ያለው ወንድ ከምታውቃቸው ከአብዛኞቹ የኢትዮጵያ  ወንዶች  ይለይበታል፡፡  ብዙዎቹ  በተለይ  ደህና  ህይወት ላይ ያሉ በማሳጅ  ቤት  ህይወቷ  የምታውቃቸው  ወንዶች….  ከመቀመጫቸው ሰፋ፤ ከሆዳቸው ገፋ ያሉ ወጣ ገባ የሰውነት ቅርጽ  ያላቸው  ናቸው፡፡ሸንቃጣ መስለው የሚታዩ ወንዶች እንኳን ልብሳቸውን አውልቀው እርቃን ሲቆሙ የላላና የተንዘለዘለ ነገር አያጣቸውም፡፡ ቀናው ግን የሰውነቱ ቅርጽ የአትሌቶችን አይነት ነው፤ ቁመናው የተስተካለ ፤ጡንቻው የፈረጠመ፡፡ይህን ቅርጹን ደግሞ ከልብስ ውጭ እንዲህ እርቃኑን ሆኖ ለዛውም  እንዲህ  እንደሳባ  በፍቅር  አይን ከተመለከቱት የሚያደነዝዝ መሆኑ ብዙም አያስገርምም፡፡
ከተገተረችበት እንደመባን አለችና ተንቀሳቀሰች፡፡ከሳሙና  ማስቀመጫው ሳሙናውን  አነሳችና  ከኃላ  ተጠጋችው  …ሳሙና  የያዘ  እጇን  ጀርባው  ላይ አሳርፋ አካባቢውን ማዳረስ ጀመረች፡፡ቀናው በመመሰጥ ውስጥ ካለበት ስሜት ወጣና ፊቱን አዙሮ በትኩረት ተመለከታ…ገረመው፤
በዝምታ ለምታደርገው ነገር ተባባሪ ነበር፤የአምስት አመት ህጻን የልጇን ሰውነት እንደምታጥብ እንስፍስፍ እናት ከፀጉሩ አንስታ እስከ እግር ጥፍሮቹ ድረስ እሽት አድርጋ አጠበችው፡፡እሱ እንዳደረገችው ነው የሆነላት… ሰውነቱንም መንፈሱም በከፍተኛ ደረጃ ተነቃቃ ፡፡
ሳባ ከእዚህ ሁሉ ማጥና ደባቴ ወጥታ ይሄንን   የመሰለ ዕድል በማግኘቷ ተደሰተች፡፡ የምትወደውን ሰው እያንዳንዱን የሰውነት ክፍሉን መዳሰስ ስለቻለች

እሱን ማገዝ..እሱን መንከባከብ ስለቻለች …ከእሱ ጋር  ፍቅር  የመስራን  ያህል ስሜት ሰጥቷታል፡፡ግን ከዚህ አልፋ መሄድ አልሞከረችም፤ለዛሬ ይሄ ይበቃታል
..ምክንያቱም ያንን ማድረግ እንደምትችል እርግጠኛ  አይደለችም..ለዛ  ገና  ቡዙ ቡዙ ማገገም አለባት፡፡
ነገ ተነገ ወዲያ  ደግሞ  ሌሎች  ከእሱ  ጋር  የሚያቆራኟትን  አጋጣሚዎች እየጠነከሩና እየፋፉ ሲሄዱ ምን አልባት ያኔ በቀላሉ ማድረግ ትችል ይሆናል፡፡መታጠቡን ጨርሶ ፎጣ አገልድሞ በግማሽ እርቃን አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ… ከጎኑ በተቀመጠችበት አትኩራ አየችው…፡፡
‹‹ምነው ጮኸሽ አየሺኝ?››

‹‹እኔ እንጃ… ማሳጅ ላድርግህ እንዴ?››ከአፏ አመለጣት፡፡

‹‹እንዴ ተገኝቶ ነው…..በአንድ አፍ…››

‹‹ምን ነካኝ..አሁን ማሳጅ ብዬ ስሜቴን ተቆጣጥሬ ማሳጅ አድርጌ ብቻ ተወዋለሁ?››ስትል በውስጧ አሰበችናኝ በራሷ ተበሳጨች፡፡
አንዴ ከአፏ ስለወጣ ከተቀመጠችበት ተነሳች…የተወሰኑ የማሳጅ መሳሪያዎችን ለማግኘት ለወራቶች በተለይ ፋሲል ከሞተ በኃላ ዞር ብላ አይታ የማታውቀውን የቁም ሳጥኑን የታችኛውን መሳቢያ ከፈተች….ፍዝዝና ቅዝዝ ብላ እዛው ቀረች፡፡ስትቆይበት ግራ ገባው‹‹ምነው ቆየሽ? ካልተመቸሽ ተይው….ሌላ ቀን እናደረርገዋለን፡፡››
ምንም ሳትናገር አንድ አነስተኛ ጥቁር የቆዳ ቦርሳ አነሳችና ወደእሱ መጣች…አልጋው ላይ አሰቀመጠቸና ከፈተችው፤ውስጡ ያለውን ብረታ ብረቶች ላስቲኮች፤ ሰንሰለቶች፤ ካቴናዎች….ዘረገፈች
ግራ ገባው…‹‹.ሳቢ ምንድነው?››

‹‹ማወቅ አለብህ ..ይሄ የበሽታዬ እንዱ ክፍል ነው..እኔ በኖርማል ወሲብ አይደለም የምረካው.. አንተ አሜሪካ ስለኖርክ በተወሰነ መንገድ ልትረዳኝ ትችላለህ… ወደኖርማል ግንኙነት ለመግባት ምን አልባት አመታት ሊወስድብኝ ይችላል…››
የዘረገፈችውን እቃዎች አንድ በአንድ ወደ ቦርሳው ከተተችና መልሳ ዚፕን በመዝገት‹‹..ከዛሬ ወዲህ እንዚህን ነገሮች ስለማያስፈልጉኝ ነገ የሆነ ቦታ ውሰድና ቅበራቸው ወይም ጣልልኝ፡፡››አለችው
ይሄ ሰው ከዶክተሯ በተሻለ ሀኪሞ እየሆነ  እንደሆነ  ከገባት  ቆይቷል፡፡በእሱ መታከም ማለት ግን አእምሮውን ገልብጦ ለእሱ ማስፈተሸ ነው፡፡መላ ታሪክን መዘክዘክና ሀጥያትንም ሆነ የነፍስ መቆሸስን መናዘዝ ነው፡፡ያ ደግሞ በጣም ለሚያፈቅሩት ሰው ሲሆን በጣም ከባድ ነው፡፡ለሚወዱት ሰው የአካል እርቃንን ማሳየት የአእምሮን እርቃን ከማሳየት በጣም  ከባድ  ነው፡፡ይህንን  እውነት የደረሰበት ነው የሚያውቀው፡፡እሷ ግን ቀስ በቀስ ..እለት በእለት ሳትወድ በግዷ እያደረገችው ነው፡፡
ወደራሱ ጎተተና  ተጠመጠመባት…ጭምቅ  አድርጎ  አቀፋት…ግማሽ  እርቃን ሰውነቱ ላይ ተለጠፈች…ግንባሯና አይኖቾን ሳመና‹‹ሳቢ አይዞሽ …ጊዜ ሁሉንም ቁስሎቻችንን ይፈውሳል …ለጊዜ እድሉን ስጪው››አላት፡፡
እሷም እንባዋን ጀርባው ላይ እያንጠባጠበች…‹‹እኔ ተስፋዬን በጊዜ ላይ አይደለም የምጥለው…ቁስሌን ያክምልኝና ያድነኛል ብዬ ተስፋዬን የጣልኩት በአንተ ላይ ነው…በል አሁን ቃል እንደገባሁልህ ማሳጅ ላድርግህ፡፡››
‹‹እሺ ከዛ በፊት ግን አለና ከእቅፉ አወጣትና ትኩር ብሎ  አያት…  አይኖቾ ተርገበገቡ.. ወደእሷ ከንፈሩን አሞጥሙጦ ተጠጋት..ከፋታ ጠበቀችው.. ጎረሳት….ከእግር ጥፍሯ አንስቶ ወደላይ የሚነጉድ ንዝረት በሰውነቷ ተቀጣጠለ፡፡

ተፈፀመ

በቅርብ በአዲስ ድርሰት እንገናኛለን

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍15927👏1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

#ፔሩ_ሊማ

ኑሀሚ 26 አመት ላይ ያለች ማራኪ ገፅታና ሳቢ ውበት ያላት ንቁ ወጣት ናት፡፡

ከመደበኛው ትምህርት በላይ ከህይወት ብዙ የተማረችና በብዙ ፈተናና ውጣ ውረድ የበሰለች ወጣት ነች፡፡ኢትዬጳያ ውስጥ በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ በሚንቀሳቀስ አለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ መስራት ከጀመረች አራት አመት አልፏታል፡፡ እዚህ ድርጅት ውስጥ ከመስራቷ በፊት በሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ከ12 ዓመቷ ጀምሮ ተመልምላ ለረጅም አመት ስልጠና ከወሰደች በኃላ በተለያዩ የሽፋን ስራዎችና ተልዕኮዎች ላይ ተሳትፋ ድንቅ የተባሉ ስኬቷችን ያስመዘገበች የተዋጣላት ሰላይ ነበረች፡፡ለውጡን ተከትሎ በመስሪያ ቤቱ በተካሄደው ሪፎርም የ10 አመት የግዳጅ የአገልግሎት ዘመኗንም አጠናቀ ስለነበር..በራሷ ፍቃድ ከስራው ለቃ አሁን የምትሰራበት መስሪያ ቤት ተቀጠረች፡፡

እርግጥ አሁንም አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ እሷ ብቻ የምትሰራቸው ስራዎች ሲያጋጥሙ በኮንትራት ሰራተኝነት ተልዕኮ ይሰጣታል፡፡ እሷም ስራውን ስለምትወደው ያለማንገራገር ተቀብላ ትሰራለች፡፡

አሁን በምትሰራው ስራም ደስተኛ ነች..ምክንያቱም ደሞዟ በዶላር ነው፡፡ጥሩ ኑሮ እንድትኖር ምክንያት ሆኗታል፡፡ በዛ ላይ ብዙ ነገር አውቃበታለች፤ብዙ ነገር ተምራበታለች፡፡አሁን በዚህ ሰዓት ከአለም አቀፍ ሀገሮች ከተውጣጡ መሰል ኤክስፐርቶች ጋር የ3ወር ስልጣና ለመውሰድ ሰሜን አሜሪካ በምትገኘው ሀገረ ፔሩ ዋና ከከተማ የሆነችው ሊማ ከከተመች አንድ ወር አልፏታል፡፡

በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ ለሚካሄደው አለም አቀፍ ሴሚናር ፔሩና ብራዚል በጥምረት ነው አስተናጋጅ ሆነው የተመረጡት፡፡የዚህም ምክንያት ሁለቱም ሀገሮች በተፈጥሮ ሀብት ክምችታቸው ምድራዊ ገነት ስለሆኑ ነው፡፡ብራዚል 60 ፐርሰንት የሆነው የአማዞን ደን ባለቤት ስትሆን ፔሩ ደግሞ 13 ፐርሰንት የሚሆን ድርሻ አላት፡፡፡፡የአለም አንደኛውና ግዙፉ የአማዞን ወንዝ እየተጠማዘዘ የሚፈስበት እና ለአለም ህልውና መሰረት የሚሆነው ካርቦንዳይኦክሳይድ የሚመረትበትና ለመላው አለም በአምላክ እስትንፋስ ሀምሳያ የሚበተንባቸው ሀገሮች ናቸው፡፡አማዞን ወንዝ አንዴ ሸንቃጣ ጅረት እየመሰለ ደስ ሲለው ደግሞ ጋሻ መሬት ላይ ተኝቶ ሀይቅ እየፈጠረ በሁለቱም ሀገራት ምድር ላይ እንዳሻው እየተጠማዘዘና እየደነሳ ይጋልብበታል፡፡እና አለምን ከጥፋትና ከውድመት ለመታደግ የተፈጥሮ ሀብትና ደንን የባዬ-ዳይቨርሲቲ ጥበቃ እና እንክብካቤ በሙሉ አቅም ለማስተግበር ከምር ስራው መጀመር ካለበት መነሻ ቦታው ደቡብ አሜሪካ መሆን እንዳለበት የአለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ ድርጅት ብቻ ሳይሆን እሷም በግል በተለይ መጥታ አካባቢውን በጥቂቱም ቢሆን ካየችና የአንድ ወር ስልጠናውን ከወሰደች በኃላ አምናበታለች ፡፡
ኑሀሚ ይሄንን እድል አግኝታ ወደደቡብ አሜሪካ ከመምጣቷ በፊት ስለብራዚልና አርጀንቲና ካልሆነ ስለፔሩና ሌሎች የአህጉሪቷ ሀገሮች ከስማቸው ውጭ የምታውቀው ምንም ነገር አልነበራትም፡፡ለምስሌ ስለብራዚል ባህላቸውንና የሳንባ ዳንሳቸውን ብዙ የዶክመንተሪ ፊልሞችና በተደጋጋሚ ጊዜ አይታለች፡፡ከሁሉም በላይ ደግሞ የእግርኳስ አፍቃሪ የሆነው ብቸኛ መንትያ ወንድሟ የብራዚሎች አድናቂ ነው፡፡በተለይ የአለም ዋንጫ ኖሮ የእግር ኳስ ጫወታ በሚኖርበት ጊዜ ገና ህፃን ሆነው ጀምር የብራዚሎች ደጋፊ ነበር..ለብራዚል ተጫዋቾች ያለው ፍቅር እብድ የሚያስብለው አይነት ነው፡፡ሮናልዶ..ሮናልዲኒዬ…ሮቤርቶ ካርሎስ….ሪቫልዶ….  ኒይማር  ..ገብርኤል  ጀሱስ….ማርቲሊኒ…በእሱ  እድሜ  ሙሉ የተጫወቱትን ዘርዝሮ አይጨርስም፡፡ በየጫወታቸው የሚያሳዩትን አብዶ እንደ ህጻን ልጅ ቁጭ ብድግ በማለት ማየት የዘወትር ድርጊቱ ነው፡፡እና እሷም ይሄንን ባየች ቁጥር ይገርማት ነበር፡፡ከዛ የሚያየውን አይታ በእነሱ መደመምና ትኩረት መስጠት ጀመረች፡፡ ከዛም ተጋባባት ከብሄራዊ ብድን የብራዚል… ከክለብ ደግሞ የአርሴናል ደጋፊ ሆና እራሷን በእግርኳስ አፋቃሪዎች መዝገብ ላይ አሰፈረች፡፡እና በዚህ የተነሳ የብራዚል አድናቂ ነች፡፡ታዲያ ወደደቡብ አሜሪካ እንደምትሄድ ዜናውን ስትሰማ ፔሩን ሳይሆን ብራዚልን ለማየት ነበር የጓጓችው… እንደአጋጣሚ ደግሞ ፕሮግራሙ ከፔሩ ስለተጀመረ… እስከአሁን ብራዚልን የማየት ጉጉቷ ባለበት እንዲቆይ ሆኗል፡፡

እዚህ ፔሩ ባሳለፈችበት አንድ ወር ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ጥብቅ በሆነ ስልጠና እና ትምህርታዊ ሴሚናር ያሳለፈች ቢሆንም አልፎ አልፎ ወጣ ብላ ዞር ዞር በማለት የመዝናናት እድሉ አጋጥሟታል፡፡ሊማ  የፓስፊክ ውቅያኖስን በአንድ ጎኗ ታካ የተመሠረተች ጥንታዊውንና ዘመናዊውን ስልጣኔን ጎን ለጎን አቻችላ የላቲኒንና የዬሮፖዎችን ባህልና ቋንቋ ቀይጣ የተመሰረተች የፔሩ ዋና ከተማ ነች።ኑሀሚ ከተማዋን ገና እንዳየቻት ነው የወደደቻት።እርግጥ የመጣችው ለጉብኝት ሳይሆን ለትምህርታዊ ሴሚናር ነው።በዛም ምክንያት የቀኑን የበዛ ጊዜዎን በትምህርታዊ ሴሚናሮችና የወርክሾፕ ስልሰጠናዎች ላይ ነው የምታሣልፈው።ግን ባገኘችው ጥቂት ጊዜም ቢሆን በተለይ ምሽቱ ላይ እዛው ከተዋወቀቻቸው የሀገሬው ተወላጅ ሠልጣኝ ጋር ሹልክ ብላ ትወጣለች።
ሊማ ከተማን እንደታዘበቻት ከሆነ ከወገብ በላይ ውብና ዘመናዊ ከወገብ በታች ጎስቋላና ቆሻሻ ሆና ስላገኘቻት በጣም ተደምማበታለች፡፡በጉብኝቷ ወቅት እጅግ ካስገረሟትና አይኗንም ቀልቧንም ከተቆጣጠሯት ብዙ ነገሮች መካከል ጥቂቱ
1)  ካቴድራል ዲ ሊማ የተባለ በጥንታዊ የአውሮፓዎች የህንፃ ዲዛይን የተሠራ ግዙፍና ውብ ሙዚዬም ነው።ሙዚዬሙ በረቀቀ ጥበባቸው ልብን ስልብ በሚያደርጉ በተለያየ የስዕል
ክምችቶች የተሞላ ነው።ከዛም በተጨማሪ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ቅርሶች፤ ልዩ ልዩ አይነት መስቀሎች፤ሀውልቶችና .. ታሪካቸውንና ጀግንነታቸውን የሚዘክሩበት በሰው የራስ ቅል ክምችቶች የተሞላ ነው።
2)  ልላው ፕላዛ ዳ ራና የሚባለው አካባቢ ነው።ይሄ የሀገሬው መንግስት ቤተመንግስት የሚገኝበት እና የሊማ ዋና አደባባይ ያለበት እንደ ዳውን ታውን የሚታይ የከተማዋ ማእከላዊ ስፍራ ነው።በዚህ አደባባይ ላይ ከእድሜ ጠገቦቹ ህንፃዎች ፊት ለፊት ለቀቅ ብሎ በተንጣለለው ሰፊ የኮንክሪት ሜዳ ላይ በእርግባች እና በቱሪስቶች መካከል በመረጋጋት እና በስክነት የተሞላ ጫወታን ማየት ልዩ ደስታን ለልብ ይሰጣል።ቱሪስቶች ለወፎቹ ጥራጥሬና ምግብ ሲበትኑላቸው..ወፎቹ ግር ብለው መጥተው አካባቢውን ሲወሩትና ምግቡን ከወለሉ ላይ ሲለቅሙ ማየት ልዩ አይነት ስሜት ይፈጥራል፡፡

3/ፓርክ ኬኔዲ…በአካባቢው ያለው የህንፃዎች ውበት ፤የአበቦችና የአረንጓዴ ዛፎች እይታ አካባቢውን የሚያላብሰው ውበት እንዳለ ሆኖ የዚህ ፓርክ ድንቁ ነገር ድመቶች ናቸው።ፓርኩ ጠቅላላ በድመቶች የተሞላ ነው ማለት ይቻላል።ደግሞ አንድ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ከአስር በላይ የድመት ዝርያ መመልከት ይቻላል፡፡ሲንቀሳቀሱ ደግሞ ሌላ አይነት።በአለም ላይ የሚገኙትን የድመት ዝርያዎች በጠቅላላ ከየቦታው እየለቀሙ በማማምጣት እዚህ የበተኗቸው ነው የሚመስለው.፡፡ይንን ሁሉ የድመት ዝርያ በአንድ ቦታ አይቶ ማንም የማይደመም ሰው አይኖርም።በዛ ላይ ስለ ድመት የማውቀው ብሎ አስጎብኚዋ የነገራት ነገሮች በጣም ነው ያስገረማት፡፡ለምሳሌ ድመት ማረጥ የሚባል ነገር እንደማታውቅና እድሜ ልኳን መውለድ እንደምትችል ነግሯታል፡፡አንድ ድመት የሆነ ቀዳዳ ለመሹለክ ከመሞከሯ በፊት መጀመሪያ ቀዳዳው እንደሚያሾልካት ለክታ እርግጠኛ ስትሆን ብቻ እንደምታደርገው
👍15511👏4😁3🔥1
ነግሯት አስገርሟታል፡፡ሌላው ድመት ሰው በአካባቢዋ ከሌለ በስተቀር
‹‹ሚያው›› የሚል ድምፅ እንደማታሰማና ‹‹ሚያው›› የሚለው ድምፅ ድመት ከድመት የሚግባቡበት ቃል ሳይሆን ድመት ከሰው የሚግባቡበት ቃል እንደሆነ እንድታውቅ አድርጓታል፡፡
4)በቀጣይ የጎበኘችው ኤልማሊኮን ፓርክን ነው፡፡ ይሄ የፓስፊክ ሀይቅን ታኮ ያለ ፓርክ ሲሆን ልዪ ልዩ ካፌዎችና የመዝናኛ ስፍራዎች ያሉበት ነው።ከዚህ ስፍራ በጣም አስደማሚው ነገር ሠአት ጠብቆ በመሄድ የፀሀይን መውጣትና መጥለቅን መመልከት ነው።ፀሀይ ወደምድር ስትመጣም ሆነ የቀን ተግባሯን አጠናቃ ተመልሳ ስትሄድ ከሀይቁ ጋር ባላት ሚስጥራዊ ተራክቦ የምትበትናቸው አስማታዊ ቀለማትና ነፀብራቆች ቀጥታ ልብን በደስታ ቅልጥልጥ ነው የሚያደርጉት።በዛ ላይ በእግር ወክ ማድረግ..በሞተር ሳይክል የሀይቁን ጥግ እየታከኩ መንሸራሸር..ሰርፈር በተባለው ጃንጥላ መሰል ነገር ልክ እንደባለክንፍ መለአክ በአየር ላይ የአካባቢውን ውበት እና የውቅያኖሱን ግርማ ሞገስ ከላይ ወደታች እየተመለከቱ በፍራቻና በጀግንነት መካከል በተንጠለጠለ ስሜት በሰማይ ላይ በመብረር የእድሜ ልክ የህይወት ልምድ መቃሰም..ከዛ ሲወርድ ከሆቴልና ከካፌዎች ጋር ሲወዳደር ዋጋቸው በጣም እርካሽ የሆኑ ግን ደግሞ ይበልጥ ሀገርኛ እና ይበልጥ ባህላዊ የሆኑ የመንገድ ላይ ምግብ ቤቶች ጎራ ብሎ አይን የፈቀደውንና ልብ የተመኘውን ምግብ መመገብ መጠጡንም መጎንጨት ልዩ ስሜት አለው።
ኑሀሚ እንዲህ በሊማ ውበትና የኪነ-ህንፃ ምጥቀት ስትደነቅና የእሷም አዲስአባ አንድ ቀን እንዲህ እንደሊማ ፍፅም ንፁህ እንድትሆን በምትመኝበት ቅፅበት እግሯ ሊማ ከረገጠ ከ20 ቀን በኋላ ነበር ያ መደበኛ አስጎብኚዋ እስከዛሬ ካየሽው የተለየ ቦታ ልውሰድሽ ብሎ በህልሟ እንኳን አየዋለው ብላ ያላሰበች ቦታ የወሰዳት።ወደእዛኛው የከተማው ክፍል ለማለፍ የሲኦሉ ግንብ የሚሉትን ማለፍ ይጠይቃል።ልክ ከሁለተኛ የአለም ጦርነት በኋላ ጀርመን ለሁለት ስትሰነጠቅ የበርሊንን ከተማ ለሁለት እንዲከፍል እንደታነፀው የበርሊን ግንብ ሊማ ከተማም  ኑዎሪዎቾ  የሲኦሉ  ግንብ  እያሉ  በሚጠሩት  አስፈሪ  አይነት  የግንብ  አጥር ከተማዎንም ኑዋሪዎቾንም ሁለት ቦታ እንዳይተያዩ እና እንዳይደራረሱ አድርጎ ከፍሏቸዋል።አንድ ሰው በህይወት እያለ ሲኦልና ገነትን በአይኖቹ ማየት ከፈለገ ሊማን መጎብኘትና ከግንቡ ወዲህ ማዶና ወዲያ ማዶ ያሉትን ሁለት ፅንፍ የረገጠ የኑሮ ልዩነት ያላቸው የአንድ ሀገር ዜጎችን በማየት መረዳት ይችላል።ከግንብ ወዲህና ወዲያ ለመተላለፍ ጥብቅ የሆነ የደህንነት ፍተሻ ማለፍ የግድ ይላል።
በተለይ እሷ ከላችበት ከውቧ የሊማ ከተማ ወደዛኛው የጉዝቁልና መንደር ለመሻገር ቀላል ቢሆንም ከዛኛው ወደዚህ ወደሀብታሞቹ መንደር ለማለፍ ግን ከአካላዊ ፍተሻ ጀመሮ ለምን ምክንያት ወደከታማዋ እንደሚገባ ማስረዳትና የጸጥታ አካላቱን ማሳመን ይጠይቃል፡፡በዛ ከተማ ፍፅም ያረጁ፤ የጠቆሩና የተበጫጨቁ ቆርቆሮዎች የለበሱ፤ ለአይን እይታ በጣም የሚያስጠሉ ከከተማነት ይልቅ ሰፊ የስደተኞች ጣቢያ የሚመስሉ የፈራረሱ ቤቶች የታጨቀበት ነው፡፡ቤት አሰራሮቹ እራሱ ተራራ ላይ… ትንሽ ሲሄዱ የሆነ ሸለቆ ውስጥ… ደግሞ የቆሻሻ ክምር ላይ፡፡
‹‹ሁለቱም ከተማ ግን በአንድ ከንቲባ ነው የሚተዳደረው?›› ብላ ነበር አስጎብኚዋን የጠየቀችው፡፡እንዳዛ አይነት ጥያቄ ለመጠየቅ የተገደደችው ከተማው እንዴት አንድ የአስፓልት መንገድ እንኳን አይኖረውም…?እንዴት አንድ የአይን  ማረፈያ የሚሆን ደህና ፎቅ ይጠፋዋል…?ኑዋሪዎቹን ስታያቸው…የተጎሳቆሉ ብቻ ብሎ ለመግለፅ እራሱ ይከብዳል…ታዲያ ያን ሁሉ ካየች በኃላ እንደዛ አይነት ጥያቄ ብትጠይቅ ምን ይገርማል፡፡በዛች የሊማ ከተማው አካል በሆነው ስፈር ሲዞሩ ቢውሉ የአዲሰአበባውን ቆሼ ሰፈር ከሚመስል እይታ ውጭ ሌላ ነገር ማየት አይችልም ..አስቡት በስፋት አዳማን ከተማ የሚበልጥ የዋና ከተማ አካል የሆነ ከተማ ሙሉ ቆሼ ሰፈርን ሲመስል ፡፡በህይወቷ እንዲህ ደሀና ሀብታሞች ጥርት ባለ ሁኔታ ተለይተውና በግንብ አንዱ ወደሌላው እንዳያልፍ ተደርጎ የሚኖርበት ቦታ ይኖራል ብላ በህልም እንኳን አስባ አታውቅም፡፡በዋናነት ከሄደችበት ትምህርታዊ ሴሜናር ጎን ለጎን እነዚህን የመሳሰሉት አስደማሚና አስደናቂ…አስደሳችና፣አሳዛኝ የህይወት ልምዶችን ቀስማ የስልጠናውን 50 ፐርሰንት አጠናቃ ለሁለተኛ ዙር ስልጠና ወደሚካሄድባት እሷም ለማየት ወደጓጓቻት ብራዚል ለመጓዝ ዝግጁ ሆነች፡፡


ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
47👍41
አትሮኖስ pinned «#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ ( በአመዞን ደን ውስጥ) ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ #ፔሩ_ሊማ ኑሀሚ 26 አመት ላይ ያለች ማራኪ ገፅታና ሳቢ ውበት ያላት ንቁ ወጣት ናት፡፡ ከመደበኛው ትምህርት በላይ ከህይወት ብዙ የተማረችና በብዙ ፈተናና ውጣ ውረድ የበሰለች ወጣት ነች፡፡ኢትዬጳያ ውስጥ በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ በሚንቀሳቀስ አለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ መስራት ከጀመረች አራት አመት…»
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)

#ምዕራፍ_ሁለት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ፔሩ/ኢኩኢቶስ

አሁን ኑሀሚ ከሊማ ወደብራዚሊያ በሚወስደው የሊማ አለምአቀፍ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 102 ላይ ነች፡ከጉዞው በፊት የጀመራት የራስ ምታት እረፍት ነስቷታል…በዛ ላይ ከጎኗ ያለው ጎልማሳ ሰው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገብቶ እያንኳራፋ ነው፡፡አውሮፕላኑ ውስጥ ስትገባ እንኳን ቀድሟት ወንበሩን ይዞ መተኛት ጀመሮ ነበር፡፡ሁኔታውን ስታየው ምን አልባት ለሳምንታት እንቅልፍ ሚባል ነገር በአይኑ እንዳልዞረ ገመተች፡፡የሰውነቱ ቀለም በቀይና ነጭ መሀከል የሚዋልል ነው፡፡ጸጉሩ ሉጫ ከመሆኑ በተጨማሪ ወርቃማ የሚባል ሆኖ እንደልጃገረድ ፀጉር ረጅም ሆኖ ጀርባው ላይ ተኝቷል፡፡…ፈረንጅ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነች፡፡ምን አልባት ብራዚላዊ ወይም ኮሎምቢያዊ ብቻ እዛ አካባቢ ዜጋ ሊሆን እንደሚችል ገምታለች፡፡
ከእንቅልፉ ተነስቶ ቢያዋራት ደስ ይላት ነበር፡፡ከሰው ጋር ስታወራ የሚወቅራት የራስ ህመሟ ስቃይ ይቀንስላት ወይም ጥሏት ይሄድ ይሆናል፡፡ይህ የእሷ ግምት ነው…፡፡ሰውዬው እኮ ትንፋሽ በውስጡ መኖሩን እስክትጠራጠር ድረስ ፀጥ እንዳለ ቀጠለ ፡፡የአንድ ሰዓት ጉዞ ከተጓዘ በኃላ ድንገት ከጎኗ ያለው ሰውዬ ተንቀሳቀሰ ..አላመነችም፡፡ነቃና አይኖቹን ገለጠ፡፡ዙሪያ ገባውን በመገረምና በድንጋጤ ቃኘ፡፡እሷንም ደጋግሞ ተመለከታት…የሆነ ያልጠበቀው ነገር እንደየ አይነት ነው፡፡
‹‹Where I am?››

‹‹ጥያቄው አስገረማት፡፡ ግን …በስተመጨረሻም ቢሆን የምትፈልገውን ወሬ ስላገኘች ትመልስለት ጀመር፡፡ ከፔሩ ወደብራዚል እየተጓዝን ነው፡፡ ….ከአንድ ሰዓት በላይ ስለተኛህ ከየት ተነስተህ ወደየት እየሄድክ እንደሆነ ዘነጋኸው አይደል?››ጥያቄው እዚህ ጋር ያቆማል ብላ ጠብቃ ነበር ፡፡እሱ ግን ሌላ ግራ አጋቢ ጥያቄ ጠየቃት ፡፡
‹‹Who I am?››

‹‹እርፍ!! ››አለች፡፡ስለሱ ሰምታችሁም ሆነ መልኩን እንኳን ከዚህ ቀደም አይታችሁት የማታውቁት ሰው ድንገት ፊታችሁ ተጋርጦ እኔ ማን ነኝ? ብሎ ሲጠይቃችሁ ምን አይነት ስሜት ነው ሚሰማችሁ?፡፡አንድ የተሳሳተ ነገር እንዳለ ወዲያው ማሰባችሁ አይቀርም….ኑሀሚም እንደዛ ነው ግራ የተጋባችው፡፡ ቀልድም መስሏት ፈገግ ልትልለትም ቃጥቷት  ነበር…ግን  ፊቱን  ስታይ  ምንም  የመቀለድ  አፒታይት  ያለው  ሰው  ሆኖ አላገኘችውም፡፡፡እሷ ደግሞ በበፊት ስራዋና ስልጠናዋ ጋር ተያይዞ የሰውን ስሜትና ፍላጎት መተንበይ እና መገመት ችሎታዋ የተዋጣለት የሚባል ነው፡፡እና እየቀለደ እንዳልሆነ እርግጠኛ ሆናለች፡፡ይሁን እንጂ ይበልጥ እንዲያወራ ለማድረግና ከወሬው ደግሞ ተጫማሪ ፍንጭ ባገኝ ብላ ጥያቄዋን ቀጠለች፡፡
‹‹አር ዩ ኪዲንግ ሚ(እየቀለድክ ነው)?››

‹‹አይ እውነቴን ነው …፡፡እኔ ማን ነኝ..?ወደብራዚል ለምድነው የምሄደው? ፡፡››

‹‹እሱን ልመልስልህ አልችልም…ኪስህ ውስጥ ግባና ፓስፖርትህን እይ፡፡››የሚል ምክረ-ሀሳብ ሰጠችው፡፡

‹‹ፓስፖርት ምንድነው?››

‹‹እንዲህ አእምሮ የለቀቀ ሰው ብቻውን እንዴት ይጓዛል ?››ስትል አሰበችና ይበልጥ የታሪኩን መጨረሻ ለማወቅ ጓጓች፡፡
አወጣችና የእሷን ፓስፖርት ሰጠችው‹‹ፓስፖርት ማለት ስለአንተ ማንነት..  ስምህን፤ዕድሜህን፤ ዜግነትህን የመሳሰሉትን ዋና ዋና መረጃዎች የያዘ ሰነድ ነው…ከአንድ ሀገር ወደሌላ ሀገር ለመግባትና በነፃነት ተንቀሳቅሶ የሄዱበትን ጉዳይ ለመከወን ይሄንን ፓስፖርት የተባለ መታወቂያ መሳይ አለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰነድ መያዝ የግድ ነው፡፡›› ስትል አብራራችለት፡፡
ተቀበላትና አየው፡፡የእሷን ፓስፖርት መለሰላትና ወደኪሶቹ እጁን ሰደደ፡፡ንግግሯን ከምር ወስዶ ኪሱን መፈተሸ ጀመረ ፡፡የተወሰኑ ዶላሮች ..እናም የተወሰኑ የብራዚል ብር ከፔሩ ወደብራልዚል የመብራሪያ አየር ትኬት በቃ…በኪሱ ያሉ ዕቃዎች እነዛ ናቸው፡፡ ፓስፖርት የሚባለው ነገር የለውም፡፡
ትናንሽ አይኖቹን እያቁለጨለጨባት ‹‹የለኝም…፡፡››አላት፡፡

አሁን እየቀለደ እንዳልሆነ እየተሰማት ነው…‹‹እስቲ ዙሪያህን ተመልከት… የምታውቀው ሰው የለም….?ምን አልባት አብሮህ ያለ ዘመድ ወይም ጓደኛ ፕሌኑ ውስጥ ሊኖር ይችላል?››የሚል ምክር ሰጠችው፡፡ቆመና መቀመጫውን ለቆ ተነሳ ፡፡ወደፊት ሄደና ከመጀመሪው ወንበር አንስቶ ወደኃላ እየተጓዘ ሚያውቀውን ፊት እንዳለ ወይም አውቋት ሚያናግረው ሰው ይኖር ይሆን በሚል ስሌት ፈተሸ….ተስፋ ሲቆርጥ ተመልሶ ተቀመጠ፡፡
‹‹እ…አገኘህ?››

‹‹አይ ..ምንም የማውቀው ፊት የለም፡፡››

‹‹እስኪ ተረጋጋ …ምን አልባት ሻንጣ ውስጥ የሆነ መረጃ ታገኝ ይሆናል?››

‹‹ሻንጣ…?››

‹‹አዎ ሻንጣህ?››

‹‹ሻንጣ አለኝ እንዴ ?››መልሶ እሷኑ ጠየቃት፡፡
‹‹ካለህ ብዬ ነዋ፡፡ሁሉም ሰው የሆነ ሻንጣ ይኖረዋል፡፡ለማንኛውም እስኪ ጥቂት ተረጋጋና ለማስታወስ ሞክር፡፡››
‹‹እሺ ››አለና ፀጥ አለ፡፡3…4…5..10 ደቂቃ ሞከረ..ምንም ሚያስታውሰው ነገር የለም…፡፡
በዚህ ጊዜ ከአብራሪው ክፍል አቅጣጫ በድምጽ ማጉያ ቀጭን ቃጭል የሆነ የሴት ድምፅ መሰማት ጀመረ ‹‹ደንበኞቻችን ከፍተኛ እይታ ሚጋርድ ጥቅጥቅ ጉም ከፊታችን መንገዳችንን ስለሸፈነ እና የአየር ፀባዩ አስተማማኝ ለሆነ ጉዞ ምቹ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት ወደመዳረሻችንን መጓዝ አልቻልንም…በዚህ ምክንያት በቅርብ የሚገኝ የኢኩኢቶስ አየር መንገድ ፍቃድ እንዳገኘን እናርፍና የአየሩ ፀባዩ እንደተስተካከለ እንቀጥላለን፡፡አሁን ሁላችሁም  ቀበቷችሁን እንድታደርጉና ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክ
መገልገያዎችን እንድታጠፉ በትህትና እንጠይቃለን የሚል መመሪያ አስተላለፈችና ንግግሯን አጠናቀቀች፡፡
በፕሌኑ ውስጥ ያሉ መንገደኞች ውስጥ ጉርምሩምታና ትርምስ ተሰማ…. ሁሉም ቀበቷቸውን እንዲያስሩን የኤሌክተትሮኒክ መሳሪያዎቻቸውን እንዲያጠፉ ትእዛዝ ተሰጠ፡፡
‹‹ኢኩኢቶስ የት ነው የምትገኘው?›› ጠየቀችው ፡፡ ለማስታወስ ሙከራ አደረገ..አልተሳካለትም፡፡
አሳዘናትና ‹‹የትም ቢሆን ችግር የለውም ..ተወው አትጨነቅ፡፡አይዞህ የሆነ ነገር እናደርጋለን…አሁን ቀበቶህን እሰር አለችው፡፡››

‹‹እሺ አመሰግናለሁ፡፡›› አለና እንዳለችው አደረገ፡፡
ከደቂቃዎች በኃላ አውሮፕላኑ የተወሰና መንገጫገጭ አሰማና ተረጋግቶ አረፈ፡፡ጉዞው የአየር ፀባዩ ከተስተካከለ በማግስቱ እንደሚደረግ ስለተነገረ ተጓዦች ሻንጣቸውን ከተሰቀለበት እያወረዱ ወደመውጫቸው መጓዝ ጀመሩ፡፡እሱ በተቀመጠበት ቦታ ሆኖ እየተቁለጨለጨ ነበር….፡፡
‹‹ተነስ›› አለችው..ተነሳና ግራ በመጋባት ተከተላት፡፡ሻንጣዋን አወረደችና በእጇ በመያዝ የእሱን ትከሻ ያዘችና አቆመችው፡፡
‹‹ምነው አንወጣም እንዴ?››ግራ በመጋባት ጠየቃት፡፡
‹‹ቆይ… ሁሉም ሰው ወጥቶ ይለቅ…መጨረሻ መቅረት አለብን፡፡››አለችው፡፡
እንደዛ ያለችበትን ምክንያት ባይረዳም..ግን እሷ ምትለውን ከመቀበል በስተቀር ምርጫ ስለልነበረው እንዳለችው አደረገ፡፡ሁሉም ወጥቶ ካለቀ በኃላ ቀጥታ ወደዕቃ ማሳቀመጫው መደርደሪያ ተንጠራራች፡፡ የተንጠራራችው የቀረውን አንድ ላፕቶፕ የያዘ ሻንጣና አንዴ ሌላ ሻንጣ በድፍረት አወረደች…የላፕቶፑን ሻንጣ ኪስ ከፈተችና ስትፈትሽ ፓስፖርት አገኘች፡፡ አወጣችና አየችው፡፡
‹‹ ዳግላስ ዲያሲስ ሞሬራ›› ይላል ..ፎቶ የራሱ ነው፡፡ሰጠችው፡፡
‹‹ምንድነው?››
👍776🔥2👏2😁1
‹‹ዳግላስ ነህ..ማለቴ ስምህ ዳግላስ ዲያሲስ ሞሬራ ይባላል፡፡››ስትል የገዛ ስሙን ለራሱ አስተዋወቀችው፡፡
‹‹አነስተኛ ሻንጣውንና ላፕቶፕኑ አስያዘችውና‹‹ በል ና እንውጣ …፡፡››አለችው፡፡
አየር ማረፊያው መለሰተኛ ነው…ከፕሌኑ ወርደው እግራቸው መሬት ሲረግጠጥ ልዩ አይነት ስሜት ሰውነቷን ነዘራት፡፡…ሰማይ እንደዛ ቅርብ የሆነበት ቦታ ከዛ በፊት አጋጥሟት አያውቅም፡፡ …ሰማይ ትክክለኛ የምድር ክዳን ነው የሚመስለው፡፡ በተትጎለጎለ ነጭ የተባዘተ ጥጥ በሚመስል ደመና ተሸፍኖ በቅርብ ርቀት ከሚገኙ ተራሮች ጋር ሄዶ የሚገጥም ነው የሚመስለው…፡፡ደግሞ ፀሀዮ በሁለት ተረሮች መካከል ሾልካ ልታመልጥ በሳምሶማ ሩጫ ወደማደሪያዋ እየተጓዘች ነው የምትመስለው፡፡ በዛ ላይ ከምትጠልቀው ፀሀይ የሚወጣው ነፀብራቅ ከተማዋን ከከበባት የውሀ አካል ላይ ሲያርፍ የሆነ ልብን ስውር ሚያደርግ ቀለማማ ጨረር ያንፀባርቅና በአከባቢወው ያለውን የሰው ልጅ ሁሉ በአድናቆት አጃኢብ እንዲል ያስገድዳል፡፡
ይ ሁሉ መገረምና መደነቅ ግን ለኑሀሚ እንጂ ለዳግላስ አልነበረም..እሱ በአካባቢውም ሆነ በዙሪያው እየሆነ ላለው ነገር ብዙም ቁብ ያለው አይመስልም፡፡ከዛ ይልቅ ‹‹እኔ ማን ነኝ ?›› በሚለው የማንነት ጥያቄ እሩሱን እንዳጨናነቀ ነው፡፡የአየር ማረፊያውን ግቢ ለቀው ከመውጣታቸው በፊት ስልኳን ከኪሶ አወጣችና ኢንተርኔት ከፍታ ስለከተማዋ ጥቂት ለማወቅ ጎግል ማድረግ ጀመረች፡፡ከጎግል ያገኘችው ውጤት ከታማዋን በፍጥነት እንድታያት ሚያጓጓና የሚያስደንቅ ሆና ነው ያገኘችው፡ ፡
ኢኩኢቶስ  ከሌሎች ከተሞች ጋር ምንም ዓይነት የመሬት ግንኙነት የሌላት 200ሺ ኑዋሪዎች በላይ የሚኖሩባት በዓለም ላይ ሙሉ በሙሉ በውሀ ተከባ የምትገኝ ትልቋ ከተማ መሆኗ አስገርሟታል። ማንም ሰው ወደ ኢኩኢቶስ  ውበቷን ለማየት መምጣት ከፈለገ ያለው ምርጫ ሁለት ብቻ ነው፡፡አንድም እንሱ እንዳደረጉት በአየር ትራንስፖርት መጠቀም አለበት፤ካልሆነ ደግሞ በውሃ ትራንስፖርቶች ማለት በባህላዊና ዘመናዊ ጀልባዎች መጠቀም የግድ ይለዋል፡፡
ከተማዋ በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ማደግ የጀመረችው የጎማ ምርት ማምረት  በጀመሩ እንግሊዛዊያን አማካይነት ወደ እድገት ጓዳና የተመነደገች እንደሆነች ይነገራል፡፡ የጎማ ፋብሪካዎች የነበራቸው ባለሀብቶች አሁንም ለከተማዋ የላይኛው መደብ ኑዋሪዎችና ቅንጡ መኖሪያ ቤቶችን ባለቤት ናቸው፡፡
ከኢኩኢቶስ Iquitos ከተማና ያጠሯት የውሀ አካላትን በጀልባ ተሸግረው ቀጥታ የአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ መግባት መቻሉም ሌላው ከታማዋን ድንቅና በቱሪስቶች ተመራጭ እንደሚያደርጋትና በጫካው ውስጥ ደግሞ ጥንታዊ ኑዋሪ የሆኑ ነገዶችንን እስከ ጥብቅ ባህላቸው ማግኘትና መደመም እንደሚቻል መረዳት ችላለች፡፡
ተያይዘው የአየር መንገዱን ማረፊያ ለቀው መውጣት ጀመሩ፡፡ኑሀሚ የመጀመሪያ እቅዷ እሱን ወደሚፈልገው ሆቴል በተክሲ አሳፍራ በመሸኘት እሷ ደግሞ ወደሌላ ሆቴል መሄድ ነበር፡፡ያልገባት ሰውዬው እያጭበረበራት ቢሆንስ…?በማታውቀውና በእንግድነት በመጣችበት የባእድ ምድር የሆነ ነገር ቢያደርጋትስ….?ፍራቻ የጎበኘው ጥርጣሬ በአእምሮው ተሰነቀረ….ግን መልሳ ተወችው…‹‹.በምን ምክንያት እኔን ታርጌት ያደርጋል? ››ስትል አሰበች፡፡እቅዷን ቀየረችና ምርጫውን ለራሱ አቀረበችለት፡፡
‹‹አሁንስ አስታወስክ..?ማለቴ ዳግላስ ማነው?››መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹ምንም ያስታወስኩት ነገር የለም…….አስቸገርኩሽ አይደል ?››አላት፡፡
‹‹አይ አትሳቀቅ፡፡ ሁሉ ነገር ይስተካከላል፡፡..አሁን ወደከተማ እንሂድና ሆቴል ፈልገን አረፍ እንበል እና ከዛ የሚሆነውን አብረን እናያለን፡፡››አለችው፡፡
ፈገግ ብሎ ከልቡ እንደሆነ በሚያረጋግጥ ጠንከር ያለ ቃል ‹‹አመሰግናለሁ፡፡››አላት ፡፡
በዚህ ጊዜ የአየር ማረፊያውን ሙሉ በሙሉ ለቀው ወጥተው ነበር፡፡ ወደከታማው መሀከል እንግዶችን ሚያጓጉዙ ኡበሮች፤ ታክሲዎችና ሁለት ሰው የሚያሳፍሩ ባለሞተር ባጃጆች በየቦታቸው ተሰልፈው ሲጠብቁ ተመለከቱ …ምክንያት ባይኖራትም እየጎተተች ወደ ባለ ሶስት ጎማዎቹ ሞተር ሳይክል ይዛው ሄደች፡፡
‹‹ጥሩ የተባለ ሆቴል ውሰደን›› አለችው፡፡

ስለዋጋው ለፈለፈላት..አልገባትም፡፡እሷ የምታወራው በእንግሊዘኛ እሱ የሚመልስላት በእስፓኒሽ ሆነና መግባባቱ ቀላል አልሆናቸውም….ያው ፔሩ ብሄራዊ ቋንቋ እስፓኒሽ እንደሆነ በሊማ ባሳለፈችው አንድ ወር ስለተረዳች ብዙ አልገራትም፡፡ዝም ብላ ሻንጣዋን አስቀድማ ገባች….ዳግላስም ተከተላት፡፡
ወደከተማው እየዘለቁ ሲሄዱ ደስ የሚል ስሜት እየተሰማት መጣ፡፡ስለዚህች ኢኩኢቶስ የተባለች ጥንታዊ ከተማ ከኢንተርኔት በወሰደችው መረጃ መነሻነት የመንገዷን ግራና ቀኝ እየተመለከተች ደስ የሚለውንና ያልተበከለውን ንፅህ አየሯን እየማገች እየተጓዘች ነው፡፡መኪናው የከተማው መሀከል ወሰደና ጣላቸው፡፡በቀኛቸው ሆቴል አለ፡፡ በግራቸው ደግሞ የአዲስአበባን አትክልት ተራ የሚመስል ገበያ ተመለከተችና ሻንጣዋን በእጇ እንዳንጠለጠለች ወደእዛው አመራች፡፡ በመደዳ በተሰሩ ትናንሽ ጉልት መሳይ ሱቆች የአትክልትና የፍራፍሬ አይነቶች ተደርድረውና ተሰቅለው ይታዬታል፡፡ አብዛኞቹ ፍራፍሬዎቹም ሆነ አትክልቶች በሀገሯ በኢትዬጵያ ጭምር የሚገኙ ናቸው፡፡ሙዝ ፤መንደሪን፤ፓፓዬ ፤ሎሚ ብዙ ብዙ አለ…የገረማት ግን እነሱ ሎሚ ብለው ለገበያ ያቀረቡት ከሀገሯ ብርቱካን የበለጠ መጠን እንዳለው ማየቷና የድንች አይነታቸው ደግሞ ከቁጥር በላይ ሆኖ በማግኘቷ ነው፡፡ሌላው ለገባያ ዝግጁ ሆነው ገዢን የሚጠብቁት ከባህር የወጡ የዓሳ ዝርያዎችን ናቸው፡፡ ለእሷ አዲስ እውቀት ነው፡፡ሙዝና መንደሪን ገዙና መንገዱን ተሻግረው ወደሆቴሉ ገቡ፡፡
እሷንም ባልገባት ምክንያ ሁለት አልጋ ያለበት አንድ ክፍል ተከራየችና እሱን አስከትላ ይዛው ገባች፡፡ሻንጣቸውንና ሌሎች ዕቃዎቻቸውን አስቀመጡና በየአልጋቸው ላይ አረፍ አሉ፡፡
‹‹ምትፈልገው ነገር አለ? ››ግራ ተጋብቶ ጭንቀት ላይ ያለውን እንግዳ ሰውዬ ጠየቀችው፡፡
‹‹ማለት…ምን ልፈልግ ችላለሁ?››

‹‹ሻወር መውሰድ…ወይም ምግብ ነገር…››

‹‹አይ ምንም አልፈልግም?››

‹‹እንግዲያው ወጣ ብለን ከተማዋን ዞር ዞር ብለን እንያት››የሚል ግብዣ አቀረበችለት፡፡
‹‹አዎ…ይቻላል፡፡››አለና ተያይዘው ወጡ፡፡ልክ አካባቢውን ሊጎበኝ እንደመጣ ፍቅረኛሞች ጎን ለጎን ሆነው በውቧ ከተማ አስፓልት ጠርዝ በዝግታ እየተጓዙ መጎብኘታቸውን ቀጠሉ፡፡ለእሷ ሁሉ ነገር አዲስና አስደማሚ ስለሆነ እሱ ስላለበት ሁኔታ ለጊዜው ዘንግታ‹‹ አየህ ያንን ውሀ…አየህ ፀሀዬ ደስ ስትል?..አየህ ድመቶችን…››እያለች በምታየው ነገር ሁሉ ስትፈነጥዝ….እሱ በተቃራኒው የሚያየው ነገር ሁሉ መንገዶች፤ ህንፃዎቹ ሳይቀር የሚያቃቸውና ከዚህ በፊት ደጋግሞ ያያቸው እንደሆኑ ደመነፍሱ እየነገረው ቢሆን ጥርት ያለ ምስልና ትውስታ ሊመጣለት አልቻለም፡፡ቢሆንም ግን በውስጡ የሚብሰለሰለውን ጭንቀት ለራሱ ቀብሮ ከጎኑ ያለችውን ውብ ፤ደግና ፤ተወዳጅ የሆነች ሴትን ሙድ ላለማበላሸት በምታወራው ወሬ ላይ ምጥን አስተያየት እየሰጠ..ስትፈግ እየፈገገ…ስትስቅ ደግሞ እየሳቀ..በሞባይሏ ፎቶ ስታነሳው እየተነሳ…ሰልፊ ስትለው እንደፍቃዷ እየሆነላት.. ደስ የሚል የጉብኝት ጊዜ አሳለፉና ጨለምለም ሲል ወደሆቴላቸው ተመለሱ፡፡እዛው ሆቴል እራታቸውን በልተው ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲሆን ወደመኝታቸው ተመልሰው ገቡ፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe
👍1079👎1😁1
👍9👎1
አትሮኖስ pinned «#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ ( በአመዞን ደን ውስጥ) #ምዕራፍ_ሁለት #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፔሩ/ኢኩኢቶስ አሁን ኑሀሚ ከሊማ ወደብራዚሊያ በሚወስደው የሊማ አለምአቀፍ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 102 ላይ ነች፡ከጉዞው በፊት የጀመራት የራስ ምታት እረፍት ነስቷታል…በዛ ላይ ከጎኗ ያለው ጎልማሳ ሰው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገብቶ እያንኳራፋ ነው፡፡አውሮፕላኑ ውስጥ ስትገባ እንኳን ቀድሟት ወንበሩን ይዞ መተኛት…»
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሁለት ሰዓት ሲሆን ወደመኝታቸው ተመልሰው ገቡ፡፡
‹‹እንግዲያው መተኛት እንችላለን..››አለችና ሙሉ በሙሉ አልጋው ላይ ወጣች፡፡ የአልጋው ጠርዝ ላይ እንደተቀመጠ ‹‹አይ ግን እንቅልፌ አልመጣም››አላት፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ እኔም እንቅልፌ አልመጣም…››አለችና መልሳ ከአልጋው ወረደችና ‹‹ቆይ የሚጠጣ ነገር ትፈልጋህ?››ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹የሚጠጣ ..እኔ እንጃ ?››ነበር መልሱ
ዝም አለችና ክፍል ውስጥ ወዳለው ፍሪጅ ተንቀሳቀሰች ፤ከፈተችው…..፡፡ሁለት በቆርቆሮ የታሸጉ የአልኮል መጠጦች አወጣችና ወደ እሱ ተመልሳ ከጎኑ ተቀመጠች…አንዱን አቀበለችው፡፡ከፈተችና ተጎነጨችለት ….እንዳደረገችው አደረገ…አልተመቸውም ፤ ግሽግሽ አለ፡፡
‹‹ምነው? አልኮል ጠጥተህ አታውቅም እንዴ?››

‹‹እንግዲህ አላውቅም ማለት ነዋ…ባውቅ እንዲህ ግሽግሽ አይለኝም ነበር?››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ምን አድርገሀቸው ይሆን እንዲህ ትናንትህን ከአእምሮህ እጥብ ያደረጉት? ›› ስትል በውስጧ ስለእሱ አሰበች፡፡የሰላይነት ህይወቷ ሰው በሰው ላይ ብዙ ነገር እንደሚደረግና የሰው ልጅ በገዛ ስህተቱ ሆነ በማያውቀው እና በማይመለከተው ምክንያት ብዙ መከራና ስቃይ ሊደርስበትና ህይወቱን እስከማጣት የሚያደርስ መከራ እንደሚያጋጥም በተግባር ደጋግሞ አሳይቷታል፡፡ይህ ፊት ለፊቷ የተቀመጠው ሰውዬ ግን በህይወት እያለ ህይወቱን ያጣ ሆኖ ነው ያገኘችው…ይሄ ደግሞ ነፍስን እስከወዲያኛው ከማጣትም የከፋ ነው፡፡እንዲህ አይነቱ ግራ የገባው ነገር የመጀመሪያ ጊዜ ገጠመኟ ነው፡፡ለዛውም ጥሩ ነገር ብቻ አይበታለው ብላ በመጣችበት በባአድ ሀገር ፡፡ ድንገታዊ ሀሳብ በአእምሮዋ ብልጭ አለባት፡፡
‹‹ግን እንዴት ስልክ ሳይኖርህ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹እኔ እንጃ ምን አልባት ጥዬው ሊሆን ይችላል?››

‹‹ሊሆን ይችላል ..ሞባይልህ ኖሮ ቢሆን ኖሮ የተደዋወልካቸውን ቁጥሮች እዛ ላይ ተመዝግቦ ስለምናገኘ ደውለን የሚያውቁህን ሰዎች ወይም ቤተሰቦችህን በቀላሉ ማግኘት እንችል ነበር፡፡››
‹‹እና አሁን ማንነቴን ለማወቅ ምንም ተስፋ የለኝም ማለት ነው?››

‹‹አይ እንደዛማ እንዴት ይሆናል..?አይዞህ ብራዚል እስክንደርስ ምንም ትዝ የሚልህ ነገር ከሌለ ሀኪም እንዲያይህ ማድረግ እችላለሁ… ያንቀላፋውን የማስታወስ ችሎታህን የሚቀሰቅስ የሆነ መድሀኒት አያጡም፡፡››
‹‹ለምን ግን እንዲህ ደግ ሆንሺልኝ?››ሲል ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡

‹‹የሰው ልጅ ስለሆንኩ ነዋ…አንተም እኮ እኔን በዚህ ሁኔታ ላይ አግኝተኸኝ ቢሆን ከዚህ በላይ የሆነ ነገር ነው የምታደርግልኝ…እንዴ ላፕቶፕህ?››ስትል ወደእሱ አፍጥጣ ጮኸች፡፡
በመብረቃዊ ንግግሯ ተገርሞ ‹‹ላፕቶፑ ምን?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ማወቅ የምትፈልጋው.. ማለት ስለማንነትህ የሚያወሩ መረጃዎች ላፕቶፕህ ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ..አዎ እርግጠኛ ነኝ የሆነ ነገር ይገኛል፡፡››
ከተቀመጠበት ተነሳና ለፕቶፑን በማንሳት ሄዶ ከጎኗ ተቀመጠ ፡፡‹‹እንዴት ነው የሚከፈተው?›› ጠየቃት፡፡ተቀበለችውና በቀይ ቀለም የደመቀውን በተን ተጫነችው፡፡ ጥቁር የነበረው የላፕቶፕ አስክሪን ቀስ እያለ በራ….ፓስወርድ ይጠይቃል፡፡
‹‹ወይኔ ፓስወርድህን መቼስ አታስታውስም…..?ስምህን የረሳህ ሰው ፓስወርድህን እንዴት ልታስታውስ ትችላለህ?››
‹‹ቆይ እስኪ›› አለና ተቀበላት… ዝም ብሎ በደመነፍስ በሚመስል ሁኔታ የተወሰኑ ፊደሎቹንና ቁጥሮችን ሲጫን ኮምፒተሩ ተከፈተ፡፡
በደስታ እየተፍለቀለቀች‹‹ከፈትከው….ፓስወርዱን አስታውሰህ ነው ?››ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ ..ዝም ብዬ ነበር የነካካሁት፡፡››

‹‹ግድ የለም ..ዋናው መከፈቱ ነው፡፡››

ፎልደሮችን እየከፈቱ ማየት ጀመሩ፡፡የሚገርምና ጭራሽ ግራ ሚያጋባ ፍይልነው እየተመለከቱ ያሉት፡፡ጥቅጥቅ የአማዞን ደን….ጥቅጥቅ ደን ውስጥ የታነፁ ቢላ ቢቶች…አስፈሪ መሳሪያ  የታጠቁ አውሬ መሳይ ሽፍቶች ….…. ብዛት ያላቸው ሰዎች የሚተረማምሱባቸው ነጭ ለባሽ ሰዎች የሞሉባቸው ላባራቶሪ፡፡
‹‹ቆይ ቆይ እስቲ አቁመው…››
  አቆመው..
‹‹ወደ ኃላ ትንሽ መልሰው››ሌላ ትእዛዝ፡፡
‹‹ይሄ አየኸው እራስህ ነህ፡፡ሳይንቲስት ነህ፡፡እዛ ጥቅጥቅ የአማዞን ደን ውስጥ በሚገኝ ላባራቶሪ ውስጥ ከአነዛ አደገኛ መሳሪያ የታጠቁ አስፈሪ ሰዎች ጋር አብረህ የምትሰራ ሳይንቲስት ነህ፡፡››
እንደዛ ትበል እንጂ እዚህ ስሯ ቁጭ ብሎ ማንነቱን ማወቅ እንኳን አቅቶት ልክ እንደደነበረ አውሬ መግቢያ አጥቶ የሚቁለጨለጨውን ሚስኪንና አሳዛኝ ሰው ከሽፍቶችና ገዳዬች ጋር አገናኝቶ ማሰብ ምንም ሊዋጥላት አልቻለም…ቢሆንም በህይወት አይሆንም ተብሎ ድምዳሜ ሚደረስባቸው ነገሮች በኃላ ሆነው ሲገኙ ብዙ ጊዜ ስለታዘበች የሚሆነውን ለማየት ወሰነች፡፡
‹‹ምንድነው የምሰራው….?››ጠየቃት፡፡
‹‹እኔ እንጃ…እስቲ ማጫወቱን ቀጥል፡፡››

እንዳለችው አደረገ፡፡ሀሺሽ ፕሮሰስ ሲደረግ …በየአንድ ኪሎ እተጠቀለለ ሲታሸግ ..ሌላ ቦታ ደግሞ በኪኒን መልክ ሲዘጋጅ…..ብዙ ብዙ ነገር ይታያል፡፡
‹‹አንተ ምንድነው ይሄ ጉድ….?››ሰውነቷ ሁሉ ይንቀጠቀጥባት ጀመር…በጣም ፈራችው፡፡
‹‹እንዴት ግን እዛ ልገኝ ቻልኩ…?.ምን አልባት አስገድደውኝ ይሆን?ማለት በመሳሪያ አስፈራርተውኝና አግተውኝ፡፡››
አሰበች‹‹ምን አልባት ሊሆን ይችላል..ግን እንደዛ ከሆነ ፔሩ ሊማ ምን ስትሰራ ነበር…?እዛ ፕሌን ውስጥ እንዴት ልትገባ ቻልክ…?እንዴት አንድ ጠባቂ እንኳን ሳይኖርህ? ወደብራዚሊያስ ምን ለትሰራ ነው የምትሄደው?እንዴት ሁሉን ነገር ልትረሳ ቻልክ?››ጥያቄዎችን አዣጎደጎደችበት፡፡
‹‹ለዚህ ሁሉ ጥያቄዎችሽ መልስ ኖሮኝ ብመልስልሽ በጣም ደስ ይለኝ ነበር፡፡››አለና ላፕቶፑን ከጎኑ አስቀምጦ ተነሳ ……ወደቦርሳው ሄደና ከወለል ላይ አንስቶ አልጋው ላይ አስቀመጠው፡፡ ከዛ ከፈተው…ከላይ ጀኬት አለው…አወጣና አስቀመጠው፡፡ከዛ የተወሰኑ መፅሀፎች አሉበት
..ከዛ ..ከዛ የሚያስደነግጥ ነገር ነው…ሙሉ ዶላር ነው፡፡››

በድንጋጤና በመገረም አፏን ከፍታ ‹‹አንተ ይሄ ሁሉ ብር ምንድነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እኔ እንጃ?››

‹‹አንተ ከእኔ እንጃ በስተቀር ሌላ መልስ የለህም እንዴ?››በብስጭት አፈጠጠችበት፡፡
‹‹እኔ እንጃ …የለኝም መሰለኝ፡፡››

‹‹ቆይ እስኪ ሌላ ነገር የለውም.?.››አለችና የኪሱን ዚፕ ከፈተች፡፡ውስጡን ፈተሸች፡፡በትናንሽ ላስቲኮች የታሸገ ነጭ ዱቄት፡፡አወጣችና አልጋው ላይ ዘረገፈችው፡፡‹‹አየህ..ይሄን ሁሉ ኮኬይን..እንዴት ፕሌን ውስጥ ይዘህ ገባህ…?እንዴት ፍተሻውን አለፍክ..?አንተ ማን ነህ….?ይመስላኛል አንተ እዛ ላባራቶሪ ውስጥ ታግተህ ሳይሆን እራስህ በፍቃደኝነት የእነሱ አንድ አባል ወይም ቅጥረኛ ሆነህ እየሰራህ ያለህ ሰው ነህ ..የዛ የኮኬይን ማምረቻና ማቀነባበሪያ ላብ ውስጥ ወሳኙ ሰውም ልትሆን ትችላለህ …ወደሊማ ወጣ ያልከው ምን አልባት ዘና ልትልና ከከተማዋ ቆነጃጅቶች ጋር ልትዝናና ፈልገህ ሊሆን ይችላል…፡፡ምን አልባትም ደግሞ ከተረካቢዎችህ ጋር የስራ ድርድር ለማድረግም ወክለውህም ሊሆን ይችላል፡፡አሁን ስራህን ጨርሰህ ወይም ተልኮህን አጠናቀህ ወደ ምሽግህ እየተመለስክ ሊሆን ይችላል፡፡ወደብራዚል እየተጓዝክ ያለህበት ዋናው ምክንያት ምን አልባት ይሄ ላባራቶሪህና ምሽጋችሁ የሚገኘው የብራዚል ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ሰለሆነም ሊሆን
👍807👏3
የችላል፡፡ምን አልባት ሁሉንም ነገር አውቀህ እኔን ለሆነ ተልዕኮ መጠቀሚያ ልታደርገኝ አስበህ ሊሆን ይችላል?››ስትል ጥርጣሬዋን ሁሉ ያለምንም ይሉኝታና ፍራቻ ዘረገፈችለት፡፡
‹‹አልገባኝም..እኔ ያልሽውን ሁሉ ሆንኩ ልበል ፡፡አንቺ ምን ትጥቅሚኛለሽ…?እንደነገርሺኝ ከሆነ ባህር አቋርጠሸ ከአፍሪካ ምድር የመጣሽ ነሽ፡፡ስለአካባቢውም ሆነ ስለዚህ ስራ ምንም አይነት እውቀት ያለሽ አይመስለኝም…እና ምን ትጠቅሚኛለሽ?ነው ወይስ ስለሀሺሽ ምርትና አለምአቀፍ ስርጭት የምታውቂው ነገር አለ?››ሲል ያላሳበችውን ሞጋች ጥያቄ ጠየቃት፡፡በቀላሉ ልትመልስለት አልቻለችም፡
‹‹እኔም የገረመኝና እያስፈራኝ ያለው ይሄ ነው…?ታዲያ እንዴት ሆኖ ሁሉን ነገር ላታስታውስ ትችላለህ….?ምን አይነት መድሀኒት አቅምሰውህ ነው?››
‹‹በቃ በዚህ አይነት ውይይት ምንም ጠቀሚ መረጃ ላይ አንደርስም… አሁን አንቺ ተነሺና ተኚ ፡፡እኔ በረንዳ ላይ ልውጣና እዚህ ላፕቶፕ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ መልሼ በእርጋታ ልይ..እና ነገሮችን እንዴት እንዲህ እንደሆኑ ላስብበት…ከዛ ጥዋት በጉዳዩ ላይ በድጋሚ እንነጋገራበታለን…ምን አልባት የዛኔ ተጨማሪ ስለራሴ የምነግርሽ ነገር አገኝ ይሆናል፡፡››
አሰበችና ባቀረበው ሀሳብ ተስማማች፡፡አልጋዋ ላይ መሉ በሙሉ ወጣችና ከነልብሷ ብርድልብሱን ገልጣ ገባች፡፡እሱ የተዘረገፈውን ብር ወደሻንጣው መለሰ፡፡ሀሺሹንም አንድ እሽግ አስቀረና የተቀረውን የሻንጣው ኪስ ውስጥ ጨመረ .. ፡፡ያስቀረውን እሽግ ከፈተው፡፡በጣቱ ቆነጠረና ወደአፍንጫው ወሰደና ሳበው፡፡ ፊቱን ቁጥርጥር አደረገ ፡፡ደገመና ሳበ፡፡ ላፕቶፑን ይዞ ወደበረንዳው ወጣና በራፉን ዘጋላት፡፡ቁጭ ብሎ ላፕቶፑን ከፍቶ በትዕግስት መመልከት ጀመረ፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍6811
አትሮኖስ pinned «#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ ( በአመዞን ደን ውስጥ) ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ሁለት ሰዓት ሲሆን ወደመኝታቸው ተመልሰው ገቡ፡፡ ‹‹እንግዲያው መተኛት እንችላለን..››አለችና ሙሉ በሙሉ አልጋው ላይ ወጣች፡፡ የአልጋው ጠርዝ ላይ እንደተቀመጠ ‹‹አይ ግን እንቅልፌ አልመጣም››አላት፡፡ ‹‹እንደዛ ከሆነ እኔም እንቅልፌ አልመጣም…››አለችና መልሳ ከአልጋው ወረደችና ‹‹ቆይ የሚጠጣ ነገር ትፈልጋህ?››ስትል…»
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
:
:
#ክፍል_አራት
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ፔሩ/ኢኩኤቶስ

ኑሀሚ በተኛችበት አጨንቁራ በመስታወቱ አሻግራ እያየችው ነው፡፡የህይወት አዙሪት ከየት ወስዶ የት ላይ እንደወረወራት አሰበችና እጅግ ተገረመች፡፡ስለእሱ እና ስለገጠመኞቾ እያመላለሰች በማሰብ ላይ ሳለች ድንገት ወደሀገር ቤት የሚያበር የሀሳብ ሀዲድ በአእምሮዋ ተዘረጋ….ጭንቅሏቷን ትራሷ ላይ አመቻቸችና በተዝናኖት ተኝታ በተዘረጋው ሀዲድ ወደሀገር ቤት በትዝታ ፍስስ አለች፡፡ ኑሀሚ የተደላደለ እና የተረጋጋ የሚባል ህይወት የኖረችው እስከ 9 ዓመቷ ድረስ ብቻ ነበር፡፡ ከዛ በጥምቀት ሰሞን በእለተ ከተራ የዘጠኝ አመቷን የልደት በአል ሊከበርላት ድግስ ተደግሶ፤ ኬክ ታዞ፤ ሻማ ተገዝቶና ፤እቤቱ በዲኮሬሽን አሸብርቆ ባለበት ቀን እናትና አባቷ ተቃቅፈው በተኙበት ሞተው ተገኙ፡፡በምትወዳት የልደት ቀኗ በጥምቀት ቀን ጥር 11 በህይወቷ በጣም ልብ ሰባሪው ሀዘን ደረሰባት፡፡ከዛ በኃላ ህይወት ለእሷ ቀላል ሆና አታውቅም፡፡ከዛ በኃላ በአለም ላይ በ10 ደቂቃ ታላቋ ከሆነ ከመንትያ ወንድሟ በስተቀር ምንም ነገር አልነበራትም….ከዛ በኋላ አመት በመጣ ቁጥር በጥምቀት ወቅት ህዝበ- ክርስቲያኑ በየጎዳናው ተቦት ተከትለው ሲዘምሩና ሲጨፍሩ የወላጆቾን ሬሳ ተከትለው ሙሾ የሚያወርዱ ለቀስተኞች ነው የሚመስሏት…በቃ ከዛ በኃላ ሕይወት በአጠቃላይ ሁሉ ነገር አስከፊ ሁሉ ነገር አስጠዩ ነበር የሆነባት፡፡ይህ በጥልቅ ሀዘንና ብቸኝነት አጥንት የሚሰነጣጥቅ ችግር ለእሷ ብቻ ሳይሆን ለወንድሟም ጭምር ነበር፡፡ስለወንድሟ ትዝ ሲላት ከተጋደመችበት ተስፈንጥራ ተነሳችና ስልኳን በማንሳት ወደ ሀገር ቤት ደወለች…ወንድሟ ጋር፡፡
‹‹ሄሎ ናኦል…እንዴት ነህ?››

‹‹አለሁልሽ እህቴ…እንዴት ነሽ…?.ሁሉ ነገር አሪፍ ነው?፡፡››

‹‹ሰላም ነኝ.. ዛሬ ከፔሩ አንተ ወደምትወዳት ብራዚል እየበረርኩ ነበር… ግን የአየር ፀባዩ ተበላሸና ሳንደርስ አንድ የምታምር ለብራዚል ድንበር ቅርብ የሆነች የፔሩ ከተማ ለማረፍ ተገደድን፡፡››
ወንድሟ በሰማው ዜና በጣም ደነገጠ‹‹እንዴት ….?ምን አይነት ቦታ ነው ያረፋችሁት ..?ፕሌኑ ሰላም ነው?››

‹‹አረ ሁሉ ነገር አሪፍ ነው…፡፡››

‹‹እና እንዴት ልትሆኑ ነው?››

‹‹በቃ ምን እንሆናለን..አሁን ቤርጎ ይዤ አረፍ ብዬ ነው እየደወልኩልህ ያለሁት፡፡ነገ የአየር ፀባዩ ከተሻሻለ እንቀጥላለን፡፡ከለበለዚያ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በሚሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የምናደርገውን እናያለን፡፡››
‹‹አህቴ እራስሽን ጠብቂ ደግሞ በጣም ናፍቀሺኛል….ጨርሰሽ እስክትመጪ ቸኩያለሁ፡፡..ሶስት ወር እንደዚህ ረጂም መሆኑን አላውቅም ነበር››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹ለምን ይዋሻል..ከዚህ በፊት እኮ ሶስት አመት ሙሉ ተለያይተን ነበር››

‹‹የዛን ጊዜ እኮ እኔ ራሴ ሀይለኛ ወከባ ላይ ነበርኩ…የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት አለ..በዛ ላይ በምታውቂው ስራ ሀለቃችን ምስራቅ ከወዲህ ወዲያ ታሽከረክረኝ ነበር…ከዚህ ሁሉ መዋከብ በተረፈቺኝ ብጣቂ ጊዜ ብቻ ነበር አንቺን መናፈቅ የምችለው፡፡አሁን ግን ስለአንቺ ከማሰብ ውጭ ሌላ ምን ስራ አለኝ?››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹ስለናፈቅኩህ ደሰስ ብሎኛ፤ቻለው ከአንድ ወር በታች ነው የቀረኝ…እና ደግሞ እንዲህ ዞር ስል የምናፍቅህ ከሆነ ስርህ እያለው አታበሳጨኝም ማለት ነው፡፡››
‹‹አረ አንቺ ብቻ ነይልኝ እንጂ ቀና ብዬም አላይሽም፡፡››ሲል ቃል ገባላት፡፡

‹‹ነግሬሀለው… አሁን የተናገርከውን ሪከርድ አድርጌዋለው፡፡››

‹‹ችግር የለውም እውነቴ ነው፡፡››

‹‹ምስራቅ ደህና ነች..?››ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

‹‹ያው ታውቂያለሽ ..እሷ ካልፈለገች አላገኛትም..ግን ደህና መሆኗን አውቃለሁ፡፡››ሲል እሷ ብቻ ሳትሆን ምስራቅም እንደናፈቀችው በሚያሳብቅ የድምፅ ቅላፄ መለሰላት፡፡ምስራቅ ማለት በሁለቱም ህይወት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያላት…የደህንነት መስራቤት ውስጥ የምትሰራ ሲኒዬር ሰላይና ለአመታት ሀለቃቸው የነበረች የ43 ዓመት ሴት ነች፡፡
‹‹በል ቸው ..ልተኛ ደክሞኛል ነገ ደውልልሀለው፡፡››አለችው፡፡
‹‹ቸው እህቴ …ውድድ ነው የማደርግሽ››ስልኩ ተዘጋ፡፡
አልጋውን ለቃ ወረደችና ወደ ፍሪጁ በመሄድ ሌላ የቆርቆሮ መጠጥ አወጣችና ከፍታ እየተጎነጨች ወደውጭ ወጣች፡፡ዳግላስ አሁንም ላፕቶፑ ላይ አቀርቅሮ ውዝግብ ውስጥ እንደገባ ነው፡፡የአማዞን ወንዝ ከበረንዳው አሻግረው ሲያያዩ  እንደእባብ ተጠምዝዞ ሽብልል እያለ ሲፈስ ይታያል፡፡ትኩረቷን ወደዳግላስ መለሰችና‹‹እሺ አዲስ ነገር አለ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹የተወሰነ ነገር እየገባኝ ነው፡፡ሳይንቲስት ነኝ፡፡አዎ ኬሚስት ነኝ፡፡እዚህ አማዞን ጫካ ውስጥ በሚገኝ የኮኬይ መቀመሚያ ላብ ውስጥ እሰራ ነበር፡፡አሁንም እንዴት እንደሚቀመም ፕሮሰሱን ሁሉም ትዝ ብሎኛል፡፡ግን ከዛ በፊት የት ነበርኩ..?የት ነው የተማርኩት? ቤተሰቦቼ የት ናቸው…?ሚስትና ልጆች አሉኝ…?እንዴት እዚህ ነገር ውስጥ ልገባ ቻልኩ?አሁንስ ፔሩ ምን ስሰራ ነበር..?የተሸከምኩትን ሻንጣ ሙሉ ዶላር ከየት አመጣሁት? ለምንስ ተሸከምኩት?አሁንስ ወደብራዚል ለምንድነው እየሄድኩ ያለሁት?ቀደም ብለሽ አንቺ ለጠይቅሺኝ ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ሚሆን መልስ ግን እስከአሁን አላገኘሁም፡፡››
‹‹በቃ ላፕቶፑን ዝጋና ተነስ… ወደ ውስጥ እንግባ …ምን አልባት ለጠየቅካቸው ጥያቄዎች ሁሉ የሚሆኑ መልሶችን አረፍ ብለህ እንቅልፍ ከተኛህ በኃላ ትዝ ሊሉህ ይችላሉ፡፡ዶላሩ ላልከው ግን ምን አልባት ለአመታት ለሰራህላቸው ስራ የከፈሉህ ደሞዝ ሊሆን ይችላል፡፡ምን አልባት ከእነሱ ጋር በሰላም ተለያይተህ ሰላማዊና ኖርማል ህይወት ለመኖር ወደ ሀገርህና ቤተሰቦች በመጓዝ ላይ ትሆናለህ፡፡በል አሁን እኩለ ለሊት ሆነ ፤አረፍ እንበልና ነገ ከነገወዲያ የሚሆነውን እናያለን..ምን አልባትም እኮ ለእነዚህ ሁሉ ጥቄዎችህ መልስ የሚሰጥህ ሰው አየር ማረፊያ ቆሞ እየጠበቀህ ሊሆንም ይችላል፡፡››
‹‹አዎ እኔም ተስፋ ማደርገው እንደዛ ነው፡፡››አለና እንዳለችው ላፕቶፑን በመዝጋት መቀመጫውን ለቆ ተነሳ፡፡ ..ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡን ወደበረንዳ የሚያስወጣውን በራፍ በመዝጋት በየአልጋቸው ላይ ተቀመጡ፡፡
‹‹ታውቂያለሽ ከሌላ ፕላኔት ድንገት ተንሸራትቼ የወደቅኩና ያለቦታዬ ከማላውቃቸውና ከማይመስሉኝ ፍጡሮች ጋር የተቀላቀልኩ እየመሰለኝ ነው፡፡››አላት
በንግግሩ አሳዘናት‹‹አይዞኝ…..እንዳልኩህ አሁን መጨነቁን አቁምና ለማረፍ ሞክር…ጥዋት የሚሆነውን እናደርጋለን፡፡›› ብላ አልጋዋ ላይ ወጣችና ተሸፋፍና ለመተኛት መከረች፡፡ፈፅሞ እንቅልፍ ይወስደኛል ብላ አላሰበችም ነበር፡፡ግን ወዲያው ነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰዳት፡፡ማለዳ 12፡40 አካባቢ ከእንቅልፏ ባና አይኗን ስትገልጥ ዳግላስ ስትተኛ ተቀምጦበት በነበረበት ቦታ ተቀምጦ ነው ያገኘችው፡፡
‹‹ምነው አልተኛህም እንዴ?››ስትል በመገረም ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ አልተኛሁም፡››

‹‹እና እዛው የተቀመጥክበት ቦታ አነጋኸው …. ?››
👍878
እሱም የተቀመጠበት ቦታ ማንጋቱን ገና አሁን እሷ ስትጠይቀው ልብ ያለው መሆኑን በሚያሳብቅ ግራ የመጋባት ስሜት፡፡‹‹አዎ ..እንደዛ መሰለኝ፡፡››አላት፡፡
ተነሳችና ከሻንጣዋ ውስጥ የምትቀይራቸውን ልብሶች መርጣ በመያዝ ወደ ሻወር ቤት ሄደች፡፡ሻወር ወስዳ..ሰውነቷን አደራርቃ ልብሷን ቀያየረችና ያወለቀቻቸውን ልብሶች ይዛ ተመለሰች፡፡ስልኳን አወጣችን አየር መንገድ ደወለች፡፡የአየሩ ፀባይ እየተስተካከለ ስለሆነ ሶስት ሰዓት በረራው ይደረጋል ብለው ነገሯት፡፡
‹‹በል እቃህን አዘጋጅና እንውረድ፡፡በረራ ሶስት ሰዓት ስለሆነ ቁርስ በልተን በዛው እንሄዳለን፡፡››
ያለምንም ንግግር እንዳለችው ዕቃውን መሰብሰብ ጀመረ…ከሻንጣው ውስጥ ሁለት እስር ዶላር አወጣና ወደእሷ አልጋ በመወርወር የሻንጣውን ዚብ ዘጋው፡፡
ግራ ገባትና‹‹ምን እያደረክ ነው?››

‹‹አየር ማረፊያ ምን እንደሚያጋጥመን አይታወቅም፡፡በድንገት እንደተገናኘን ሳናስበው በድንገት ልንለያይ እንችላለን፡፡››
‹‹እና? ››

‹‹እናማ ምንም ሳታውቂኝ ላደረግሸልኝ ትብብር እንደምስጋና ይሁንልኝ…፡፡.››

‹‹ሀያ ሺ ዶላር ….ብዙ ብር እኮ ነው››

‹‹ችግር የለውም…ከዋልሽልኝ ውለታ አንፃር እዚህ ግባ የሚባል ብር አይደለም..ባይሆን እንዳይረደፍድብን እንውጣ፡፡››
‹‹ቆይ ከመሄዳችን በፊት ለማስታወሻ ፎቶ እንነሳ…አለችና ፎቶዋን ይዛ ወደእሱ ተጠጋች፡፡ተለጠፈችበትና ሰልፊ ማንሰት ጀመረች…ከዛ ቪዲዬ ላይ አደረገችና ማውራት ጀመረች፡፡
‹‹ዳግላስ ላለፉት ሀያ ምናምነ ሰዓታት ሳንለያይ አብረን አሳልፈናል፡፡የተገናኘነው ድንገት ነው፡፡ ምንአልባትም የምንለያውም በድንገት ይሆናል፡፡ግን ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል፡፡በጣም የሚግባቡ የረጅም ጊዜ ጓደኛሞች የሆን መስሎ ይሰማኛል፡፡.አመሰግናለው ፡፡››
አለችና ተንጠራተርታ ጉንጩን ሳመችው፡፡
‹‹በእውነት በዚህ ማንነቴና ማወቅ ባልቻልኩበት አስቸጋሪ ጊዜያቶች ማንነት ሆነሺኛል፡፡ልክ እንደልብ ጓደኛ ከጎኔ ሆነሽ ተንከባክበሺኛል….ውለታሽን መቼም አረሳውም..እድል ቀንቶኝ  አንድ ቀን መክፈል ብችል ደስ ይለኛል፡፡ለማንኛውም በጣም አመሰግናለው፡፡አንቺ በጣም ትልቅ ልብ ያለሽ ጠይም መላአክ ነሽ፡፡››
ብሎ  ልክ እሷ እንዳደረገችው ጎንበስ አለና ጉንጯን ሳማት …የቀዳችውን ቪዲዬን ሴፍ አደረገችውና ለመሄድ ዝግጁ ሆነች፡፡
‹‹ይሄ የማስታወሻ ፎቶና ቪዲዬ እኔም ቢኖረኝ ደስ ይለኛል፡፡››አላት፡፡
‹‹ይቻላል እኮ ..ትናንትና ኮምፒተርህን ስትከፍት ኢሜል አድርሻህን አይቼ በቃል ሸምድጄዋለው፡፡ እልክልሀለው፡፡››
በጣም ደስ አለው….‹‹ይሄኛው ደግሞ ሌላh ውለታ ነው፡፡››አለና ሻንጣውን ይዞ እና ላፕቶፑን አንጠልጥሎ ቀድሟት ከክፍሉ ወጣ፡፡እሷም ብሩን የእጅ ቦርሳዋ ውስጥ ከስር ወሸቀችና መልሳ ዘግታ የልብስ ሸንጣዋን እየጎተተች ተከተለችው፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12123👏3👎2
አትሮኖስ pinned «#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ ( በአመዞን ደን ውስጥ) : : #ክፍል_አራት : : #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፔሩ/ኢኩኤቶስ ኑሀሚ በተኛችበት አጨንቁራ በመስታወቱ አሻግራ እያየችው ነው፡፡የህይወት አዙሪት ከየት ወስዶ የት ላይ እንደወረወራት አሰበችና እጅግ ተገረመች፡፡ስለእሱ እና ስለገጠመኞቾ እያመላለሰች በማሰብ ላይ ሳለች ድንገት ወደሀገር ቤት የሚያበር የሀሳብ ሀዲድ በአእምሮዋ ተዘረጋ….ጭንቅሏቷን ትራሷ ላይ አመቻቸችና…»
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ፔሩ/አማዞን ወንዝ ላይ
ደግላስ እና ኑሀሚ እታች ወርደው ካፌ ቁጭ ብለው ያዘዙት ቁርስ እስኪመጠ ያነሳቸውን ፎቶና ቪዲዬ ትናንት ከተማውን እየዞሩ ሲጎበኙ የተነሱትንም ጭምር በኢሜሉ ላከችለት፡፡ሁለት ሰዓት ሲሆን ቁርሳቸውን በልተው ጨርሰው ወደ ኤርፖርት ለመሄድ ዝግጁ ሆነው ነበር፡፡እርግጥ ኤርፖርቱ ካረፉበት ሆቴል 15 ደቂቃ ያህል ብቻ ነው የሚርቀው፡፡ቢሆንም ቀድመው ሄደው እዛው ለመጠበቅ ተስማሙና ለሆቴሉ አስተናጋጅ ታክሲ እንዲጠራላቸው ነገሩት፡፡በአምስት ደቂቃ ውስጥ የፈለጉት ታክሲ መጣና ጫናቸው፡፡ሁለቱም ከኋላ ወንበር ተጠጋግተው ተቀምጠው በፀጥታ ጉዞቸውን ጀመሩ፡፡ሹፌሩ ታክሲ ከሚነዳ ይልቅ ቱርቦ ወይም ግዙፍ ተሳቢ መኪና ቢነዳ ከአቋሙ ጋር ይሄድ ነበር…እጆቹና አንገቱ ጠቅላላ በንቅሳት የተዝጎረጎረ.. ግዙፍ ግን ባለ አስፈሪ ጡንቻ ባለቤት የሆነ ሰው ነው፡፡የከተማውን ግራና ቀኝ ፎቆች እና የንግድ ተቋሞችን እየተመለከቱ ለ15 ደቂቃ ከተጓዙ በኃላ ሹፌሩ ወደኃላ በመዞር…‹‹ካላስቸገርኳችሁ እዚህ ፊት ለፊታችን ካለው ቅያስ ጋር የምቀበለው እቃ ነበረኝ..ሁለት ደቂቃ ባዘገያችሁ ነው››ሲል በተሰባበረ እንግሊዘኛ ፍቃድ ጠየቃቸው፡፡
ቢያንስ ከ30 ደቂቃ በላይ ትርፍ ሰዓት ስላላቸው እና ከዛ ላይ አንድ 5 ደቂቃ ቢለግሱት የሚጎዳቸው መስሎ ስላልተሰማቸው አልተቃወሙትም፡፡
‹‹..ችግር የለም.. እንችላለን፡፡››ስትል ሁለቱንም ወክላ ፍቃዱን የሰጠችው ኑሀሚ ነች፡፡ እንዳለውም በመጀመሪያው ቅያስ ወደግራ ታጠፈና ጠባብ የድንጋይ ንጣፍ የሆነ መንገድ ውስጥ ገባ፡፡ጭር ያለ መንገድ ነው፡፡ሁለት መቶ ሜትር ያህል ከተጓዘ በኃላ ጥግ አሲይዞ መኪናውን አቋመና ፡፡‹‹መጣሁ ሁለት ደቂቃ›› በማለት ሞተሩን ሳያጠፋ ታክሲዋን ለቀቀና ወጥቶ አንድ የብረት በር ግቢ ገፋ አድርጎ ገባ ፡፡ሁለቱም አይናቸውን እሱ የገባበት ግቢ ላይ ተክለው ከአሁን አሁን ወጣ እያሉ ሲጠብቁ በቅፅበት ከግራና ከቀኝ ያለው በራፍ ተከፈተና ጭንብል ያጠለቁና ሽጉጥ የደቀኑ ሰዎች የመኪናውን በራፍ ከፍተው ገቡና ሁለቱን አንድ ላይ አጣብቀው ከመሀላቸው በመክተት በሽንጣቸው አቅጣጫ ሽጉጣቸውን ደቀኑባቸው፡፡ ኑሀሚም ሆነች ዳግላስ በድንጋጤ ትንፋሽ አጠራቸው፡፡ ልክ ቀድመው እንደገቡት ጭንብል ያጠለቀ ሌላ ሰው ከፊት ለፊት የሹፌሩን ቦታ ያዘና መኪናውን አንቀሳቀሳት፡፡ቀጥታ ወደፊት ለፊቱ ነው እየነዳ ያለው፡፡ከ10 ደቂቃ በኃላ ሙሉ በሙሉ ከከተማ ወጡና ረግረግ የሆነና ግራና ቀኙ በደን በተሸፈነ ከዛም አልፎ በጭቃ የላቆጠ ወጣ ገባ መንገድ ውስጥ ገቡ፡፡

‹‹ምንድነው የምትፈልጉት….?ገንዘብ ነው…?››ኑሀሚ ነች ጠያቂው፡፡
አንደኛው መናገር ጀመረ፡፡ኑሀሚ ግን ምንም እየገባት አይደለም፡፡ቋንቋው እስፓኒሽ ነው፡፡እሷ ደግሞ ከእንግሊዘኛ ውጭ ሌላ የውጭ ቋንቋ አታውቅም፡፡ እርግጥ ራሺኛ ትችላለች..ያ ግን እዚህ አካባቢ እርባን ያለው መስሎ አልተሰማትም፡፡አጠገቧ ወዳለው ዳግላስ ዞረችና አፍጥጣ አየችው‹‹አፍሽን ዝጊ ነው የሚሉት፡፡››ሲል ተረጓመላት፡፡
‹‹ቋንቋውን ትችላለህ እንዴ?››

‹‹የሚሉትን መስማት የቻልኩት ብችል ነዋ››ሲል መለሰላት፡፡

አስር ደቂቃ በኋላ ጫካና ቁጥቆጦ እያቆራረጡ ከተጓዙ በኃላ መኪናዋ ቆመች፡፡ግራና ቀኛቸው ተቀምጠው ሽጉጥ የደቀኑባቸው ሰዎች አንዳንዳቸውን ይዘው ከታክሲዋ ወረዱ፡፡ሹፌሩም የታክሲዋን ሞተር አጥፍቶ ወረደ ፡፡

መኪናዋን ሲሾፍር የነበረው..ከጃኬቱ ኪስ ውስጥ እነሱ የለበሱትን አይነት ጥቁር የፊት ጭንብል አወጣና ተራ በተራ አጠለቀባቸው፡፡፡ከዛ ሌላ ጥቁር ጨርቅ አወጣና በአይናቸው ዙሪያ በማሽከርከር አሰረና ሙሉ በሙሉ እንዳያዩ አደረጋቸው፡፡ከዛ እየጎተቱና እያመናጨቁ በእግር ይዘዋቸው መጓዝ ጀመሩ፡፡ኑሀሚ በጣም ተረበሸች፡፡በቀልቃላነቷም እራሷን በጣም ወቀሰች፡፡‹‹እንዴት ሰው በማያውቀው ሀገር የማያውቀውን ሰው ለመርዳት ይሄን ሁሉ ርቀት ይጓዛል ?ለዛውም ምን እንደሆነ እና ማን መሆኑን ለማያውቅ ሰው?ከእኔ እንደዚህ አይነት ስህተት ፈፅሞ አይጠበቅም፡፡››ስትል አሰበች፡፡
.እርግጥ ኑሀሚ በህይወቷ ከህፃንነቷ ጀምሮ ብዙ ይሄንን መሰል አደጋዎችና አሳልፋለች፡፡ሞትኩ በቃ አበቃልኝ ካለች በኋላ ባልተጠበቀ ቅፅበታዊ ገጠመኝ ከመከራውም ወጥታ ህይወቷንም ያተረፈችበት አጋጣሚ በርካታ ናቸው፡፡ግን ያን ሁሉ ፈተና ያን ሁሉ ተስፋ መቁረጥ አጋጥሟት የነበረው በገዛ ሀገሯ በገዛ ህዝቦቾ ውስጥ ነው፡፡በሀገር ውስጥ በገዛ ምድር ላይ እየተራመዱ ተስፋ መቁረጥ በሰው ሀገር ውስጥ የሰው ምድር ላይ እየተራመዱ ተስፋ ከመቁረጥ ፍፁም የተለየ ነው፡፡በገዛ ሀገር ሆኖ ተስፋ መቁረጥ ማለት ሁል ጊዜ የተደበቀች ተስፋ ትኖራለች፡፡ያቺ ተስፋ ከእናት የምትገኝ ወይ ከአባት የምትቸር ወይም ወንድም የሚለኩሳት..ወይ ደግሞ እህት የምታበራት የአይዞህ ባይነት ተስፋና አለውልህ የሚል ማፅናኛ ነች፡፡ያ ቃል ደግሞ የተገነዘ ተስፋን ከሞት የሚያስነሳ ይሆናል፡፡በሰው ሀገር ተስፋ ሲቆረጥ ግን እነዚህ ሁሉ የሉም፡፡
እየተደናበሩና እየተገፋፉ 15 ደቂቃ ከተጓዙ በኃላ ተረጋጉ፡፡ከአይናቸው ላይ የታሰረው ጥቁር ጨርቅም  ሆነ  ጭንብል  ተነሳላቸው፡፡ከጀርባቸው  ጥቅጥቅ  ጫካ  …ከፊት  ለፊታቸው የተንጣለለ የአማዞን ወንዝ ነው የሚታየው፡፡እነሱ ከቆሙበት በሁለት ሜትር ርቀት መለስተኛ የሞተር ጀልባ መልህቋን ጥላ ቆማለች፡፡አንዱ እጇን ያዛትና እየጎተተ ወሰዳት እና አንደኛው ጀልባ ላይ ጫናት…ልክ እንደእሷ ሁሉ ዳግላስንም አምጥተው ከጎኔ ያስቀምጡታል ብላ ስትጠብቅ..በተቃራኒው ወሰዱና ሌለኛው ጀልባ ላይ ጫኑት፡፡
‹‹ለምንድነው የምትለያዩን..?ወዴት ነው የምትወስዱን ..?እኔ እኮ ምንም አላውቅም፡፡ከእሱ ጋር የተገናኘሁት ትናንትና ነው፡፡ምንም ማውቀው ነገር የለኝም…?››ኑሀሚ ለፈለፈች፡፡ቁብ ሰጥቶ እያዳመጣት ያለ ሰው የለም፡፡እሷ ራሱ ያንን ሁሉ ስትለፈለፍ የነበረው በአማርኛ ነበርና ያ ትዝ ሲላት የምሬት ፈገግታ ፈገግ አለች፡፡ሁለት ሽጉጥ የደቀኑ አጋቾች በአንድ ሜትር ከእሷ ፈንጠር ብለው ሁለት ሌላ መሳሪያ የታጠቁ ደግሞ ከጀርባዋ ተቀመጡ፡፡ጀልባዋ አስደንጋጭ የሞተር ጩሀት ድምፅ አሰማችና ወደባህሩ መሀከል ተፈተለከች፡፡…ወንድሟ ትዝ አላት…፡፡እህቴ ከዛሬ ነገ ትመጣለች እያለ ሲጠብቅ…..መኖር መሞቷን እንኳን ማረጋገጥ ሳይችል በስቃይ ሲኖር አሰበችና ስቅጥጥ አላት ..አይኖቾን አሻግራ ላከችና ዳግላስ የተጫነበትን ጀልባ ለማየት ሞከረች፡፡እነሱ እየተጓዙ ካሉበት አቅጣጫ በተቃራኒው ነው ይዘውት እየሄዱ ያሉት፡፡በቃ መቼም እንደማይገናኙ አሰበች…..እሷ እራሷ አሳዛኝ ሁኔታ ላይ ብትሆንም ለእሱ ከማዘን እራሷን ማቀብ አልቻለችም፡፡

ፔሩና/ኮሎምቢ ድንበር
በአለም ላይ በውሀ ከተከበብት ከተሞች መካከል ግዙፍ የሆነችውንና እስከ 200 ሺ ህዝብ በላይ ከሚኖርባትን የኢኩኢቶስ ከተማ ነጥቀው በአማዞን ወንዝ ላይ እያንሳፈፉ አርቀው ወሰዷትና አማዞን ደን ውስጥ ከተቷት።ከጀልባው ወርዳ መሬት ላይ ስታርፍ ይዛዋት የመጡት አራት ሰዎች በመጡበት ጀልባ ወደኃላ ሲመለሱ …መሬት ላይ ቆመው ሲጠብቋት የነበሩ ከነዛኞቹ በላይ አስፈሪ የሆኑ በቁጥር 9 አካባቢ ሰዎች ነበሩ የተቀበሏት፡፡‹‹በዚህ ሁሉ ትጥቅና አጀብ የሚቀበሉኝ ማነች ብለው ነገሯቸው ይሆን?›› ስትል በውስጧ አልጎመጎች፡፡አራቱ ከኃላዋ አራቱ ደግሞ ከፊት አንዱ ከመሀከላቸው በአቋሙ ቀጠን የሚል በአለባበሱ ስርአት ያለውና ..ለስላሳ ቢጤ የሆነ ሰው ወደእሷ ቀረበና
👍834🤔3👎2🤩1
እራሱን ከእሷ ጋር አንድ ሜትር ርዝመት ባለው ቀለል ባለ ሰንሰለት በማቆራኘት ከኃላዋ ሆኖ መራመድ ጀመረ፡፡አሁን እሷን በመሀከል አድርገው አማዞን ደን ውስጥ ልክ እንደጉንዳን ሰራዊት ሰልፍ ገብተው ይዘዋት እየተጓዙ ነው።በደን ውስጥ እየተጓዙበት ያለው መንገድ እጅግ ቀጭንና ግራና ቀኝ በተቆላለፉ ሀረጎችና የዛፍ ቅርንጫፎች የተጠላለፈ ስለሆነ አስቸጋሪና በተለይ ለእሷ አስፈሪ ነበር።
በህይወቷ እሷ እራሱ እስኪገርማት ድረስ ከህፃንነቷ የጓዳና ላይ ኑሮዋ ጀምሮ እጅግ አስቸጋሪ አስፈሪና በአደጋ የታጠሩ ብዙ ቀናቶችንና ወራቶችን አሳልፍለች፡፡ወደፊትም ህይወቷ ከአደጋ የፀዳና ከችግር የራቀ እንደማይሆን ታውቃለች፡፡ግን መቼም ቢሆን በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ደም የጠማቸው እንደሆነ በሚያስታውቁ ወጠምሻ ጋንግስተሮች እንደከብት እየተነዳች ወደማታውቀው ስፍራ እንደምትወሰድ ፈፅሞ በስህተት እንኳን አስባው አታውቅም ነበር፡፡በዛም ምክንያት አሁን እራሷን ለማዳን ምን ማድረግ እንዳለባት እንኳን ምንም አይነት ሀሰብም ሆነ ዕቅድ ወደ አእምሮዋ እየመጣላት አይደለም። ባላት ወታደራዊ ስልጠና እና የመስክ ላይ ተሞክሮ እየነዷት ካሉት የተወሱንትን ቆልፋ የተወሰኑትን ሰባብራ ልታመልጣቸው ትችል ይሆናል።ከዛስ...?ከዚህ ደን እንዴት ትወጣለች...? የጫካው ነገስታት የሆኑትን አደገኛ አውሬዎችን እንዴት ተፍልማ እንዴት ታሸንፋቸዋለች? በህይወት ጉዞዋ ከሰው ጋር እንዴት መፋለም አንዳለባት እንጂ በጥቅጥቅ ደን ውስጥ ከሚኖሩ ድንብር አውሬዎች ጋር እንዴት መፋለም እንዳለባት የወሰደችው ምንም አይነት ስልጣናም ሆነ የህይወት ተሞክሮ የላትም፡፡ስለዚህ በአደገኛ እንሸላሊት ተነድፍ መንገድ ብትቀርስ..?መርዛም እንቁራሪት ቢነድፏትስ?ከአማዞን ወንዝ ዘሎ የወጣ አዞ በመጋዝ ጥርሶቹ ቢዘነጣጥላትስ? ይሄንና የመሳሰሉትን መአት አስከፊ ሊገጥሙ የሚችሉ ከፊቷ ያሉ መከራዎች አሰበችና አጋቾቻን ለመተናኮል ያላትን ምኞት ለጊዜውም ቢሆን ተወችው፡፡እናም ደግሞ ስለዳግላስ አሰበች…‹‹ይሄኔ እንዴት ሆኖ ይሆን?"
ግራ የተጋባ ማንነቱና ለእሷ የነበረው ደግነት ትዝ አላት፡፡ጥዋት የሠጣትን የ20 ሺ ዶላር ስጦታ አስታወሰች ..ልብሷን የያዘ ሻንጣዋን ከኋላ ካሉት አጓቾቾ መካከል አንዱ ይዞታል፡፡ብሩንና ፓስፖርቶ ያለበትን የእጅ ቦርሳዋን ደግሞ እራሱን በሰንሰለት ከእርሷ ጋር አቆራኝቶ ከኋላዋ ያለው የእሷ እኩያ የሆነ ወጣት ትከሻው ላይ ተንጠልጥሏል።
ከአራት ሰዓት አድካሚ የእግር ጉዞ በኃላ አንድ ሰው አልባ ጎጆ ያለበት ስፍራ ሲደርሱ ርምጃቸው ተገታ።ልጁ ከኪሱ ቁልፍ አወጣና ከእሷ ጋር ሚያገኛኘውን ሰንሰለት በመፍታት ለቀቀው…እሷ እጅ ላይ የታሰረው እንዳለ ስለሆነ ቀሪው መሬት ላይ ይጎተት ጀመር…ከዛ ከመሀከላቸው አለቃ መሳዩ ሰው ገፈታተረና ወደጎጆ ውስጥ አስገብቶ ከውጭ ዘጋባት..፡፡ጎጆዋ ዕቃ አልባ ባዶ ነች።በጣም ደክሟትና ሰውነቷ ዝሎ ስለነበረ ወለሉ ላይ ተዘረፈጠችና ግድግዳውን ተደግፋ ትንፋሽ መሳብ ጀመረች።ከላይ የለበሰችው ሹራብ ጨጎጊት በመሰል ነገሮች ተጠቅጥቆበት ተነጫጭቷል፡፡አወለቀችውና በጡት ማስያዣ ብቻ ሆና ሹራብን በተቻላት መጠን ለማፅዳትና ከተጠቀጠቀበት ጨጎጊት ለማስለቀቀ ትጥር ጀመር።ስትጨርስ ባዶ ወለል ላይ መልሳ ጋደም አለች፡፡ብዙም ሳይቆይ ሳታስበው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት፡፡
ኑሀሚ ለምን ያህል ጊዜ እንደተኛች አታውቅም፡፡ስትነሳ ግን አስፈሪ ሁኔታ ላይ ነበረች፡፡ወደ አፍንጫዋ የሞት ሽታ እየተመሰገ ነው፡፡ጉሮሮዋ ላይ መላከ-ሞት የተቀረቀረ መስሎ እየተሰማት ነው...እታች ሆዷ ውስጥ አፉን የከፈተ የመቃብር ጉድጓድ እየታያት ነው።ግን እንደዛም ሆኖ እየፈራች አይደለም። አለመፍራቷ ደግሞ አስደንግጦታል ፡፡ብቸኛ የሚያሳሰባት ነገር የወንድሟ ነገር ነው ፡፡እሷን ማጣቱ በምን ፅናትና ብርታት ይቋቋመዋል?ይሄንን በእርግጠኝነት መመለስ አትችልም፡፡ያው ለእሷ ብቻዋን እንደማትሞት ታውቃለች ፡፡ቢያንስ ቢያንስ ሁለት ሶስት ሰው ይዛ ትወድቃለች፡፡ከሞተች በኃላ ደግሞ የትም ብትሞት የትም ብትቀበር ሀጃዋ አይደለም፡፡እሷ ስኖር ኢትዬጳያዊ ስሞት ኢትዬጵያ ልሁን ከሚሉት መካከል አይደለችም፡፡ለሀገሯ ያላትን ፍቅር እና ለሀገር ያላትን ትርጉም እንጥፍጥፍ አድረገው የተቀበረው ገና ድሮ በልጅነቷ ነው፡፡ቤተሰቦቾ ሲሞቱና ያንን ተከትሎ ቤታቸውም ሆነ ንብረታቸው በብልጣብልጥ ከሀዲዎች ተዘርፎ ጎዳና ተዳዳሪ ሲሆኑ፡፡ሳታስበው ቀስ በቀስ ወደሀገሯ ምድር ወደልጅነቷ በትዝታ ተጓዘች፡፡

ትዝ ይላታል የዛሬ 16  አመት በፊት
ኑሀሚ እና ወንድሟ ናኦል ወላጆቻቸው ሞተው እቤታቸውም ከተወረሰ በኃላ ቀጥታ ሰበታ የሚገኝ ህፃናት ማሳደጊያ ተቋም ነበር የገቡት፡፡እዛ የወላጆቻቸው ናፍቆት ቢኖርባቸውም ያን ያህል የከፋ የሚባል ህይወት አልነበረም ያላቸው፡፡ ግራ መጋባትና ፍራቻ ውስጣቸውን የተቆጣጠረው ጨለማ ስሜት ቢሆንም በአንፃራዊ የተሻለ የተባለ እንክብካቤ እየተደረገላቸውና ትምህርታቸውንም እየተማሩ ከመሰልና እኩያ ወላጅ አልባ ህጻናት ጋር አንድ አመት በተስፋ መኖር ችለው ነበር፡፡በኋላ ግን ነገሮች መስመር የያዙና የሰከኑ በመሰሉ ጊዜ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ፡፡አንድ ቀን ኑሀሚ ክፍል ውስጥ ከእኩዬቾ ጋር እየተማረች ሳለች…በህፃናት ማሳደጊያው አስተዳደር ተጠራችና ከክፍል ወጥታ ወደተጠራችበት ቢሮ ሄደች፡፡ቀጥታ ወደዋናው የተቋሙ ዋና አስተዳዳሪ ቢሮ ገባች፡፡ ሽበታሙ አዛውንት አስተዳዳሪ ፊት ለፊት ተቀመጠች ..ኑሀሚ እኚህን ሰውዬ ትፈራቸው ነበር፡፡ ሁልጊዜ ፊታቸው እንደተቋጠረና ሽበት የወረረው አፍሮ ፀጉራቸው እንደተንጨፈረረ ነው፡፡
ድንገት ‹‹ኑኃሚ በቀለ፡፡››ሲሉ ጠሯት

ጭል ጭል በምትል ድምፅ ‹‹አቤት ጋሼ…››አለቻቸው፡፡

ፊት ለፊታቸው ያለውን የዴስክቶፕ ኮምፒተር እስኪሪን እያስተካክሉ…‹‹በዛ ዞረሽ ወደእኔ ነይ፡፡››ነበር ያሏት፡፡

በወቅቱ በጣም ነበር ግራ የገባት…፡፡እኚ ሰው ከሩቅ የሚገፋተር እንጂ እንደዛ በፍቅር የሚያቀርብ ፍላጎት አሳይተዋት አያውቁም፡፡ቢሆንም ትዕዛዛቸውን የማክበር ግዴታ እንዳለባት ታውቃለች፡፡ሁል ጊዜ እሳቸውን ላለማበሳጨትና ላለማስቆጣት እንደጣረች ነበር፡፡በእሷ ግንዛቤ እሳቸው የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከሉ ባለቤት ነው የሚመስሏት፡፡በዛም የተነሳ እሳቸውን ድንገት አስቀይማ እሷንና ወንድሟን ከዚያ ብዙ ልጆች ካሉበት ቤታቸው እንዳያባርሯቸው ትሰጋ ነበር፡፡ፈራ ተባ እያለች እንዳሏት አደረገች፡፡ ግዙፉን ጠረጴዛ ዞራ ስራቸው ቀረበች፡፡ ወደራሳቸው ጎተተዋት የተዝረከረከ አለባበሷን አስተካከሉ፡፡የጫረተ ፀጉሯን ወደኃላ እያስተኙ ለማስተካከል ሞከሩ፡፡:እንደዚያ የሚያደርግላት አባቷ ነበር፡፡በወቅቱ እዛ ተቋም ከገባች አመት ልትደፍን አንድ ወር ብቻ ነበር የቀራት፡፡ቢሆንም የሰውዬው መዳፍ ሰውነቷ ላይ ሲያርፍ የዛን ቀን የመጀመሪያ ቀን ገጠመኟ ነበር‹‹….ምን ተገኘ?››በትንሽ ጭንቅላቷ የተፈጠረ ትልቅ ጥያቄ ነበር፡፡

ከዛ ሰውዬው ላፕቶፕን ከፈቱና የተወሰኑ ቁልፎች ተጭነው መጠበቅ ጀመሩ፡፡ከዛ በእስክሪኑ ሁለት ነጭ ፈረንጃ ወንድና ሴት ተጋርጠው ታዮት… ባልና ሚስቶች እንደሆኑ ጠረጠረች፡፡በወቅቱ ለምን እንደዛ እንደመሰላት አታውቅም፡፡ሰዎቹ ማውራት ጀመሩ,፡፡….ቋንቋው እንግሊዘኛ ቢሆንም ስለእሷ እያወሩ እንደሆነ ገብቷታል፡፡ ውይይቱ ለሰላሳ  ደቂቃ  ቀጠለ፡፡ካዛ  እየተሳሳቁ  በመግባባትና  በምስጋና  ውይይታቸውን  ዘጉት፡፡ሽበታሙ አስተዳዳሪ ዴስክቶፓቸውን እጥፍተው…ወደ ኑሀሚ ዞሩና ‹‹…እንኳን ደስ ያለሽ የእኔ ልጅ፡፡››ነበር ያሏት፡፡በወቅቱ ለምን እንደዛ እንዳሏት አልገባትም
👍608😁1
ነበር..ፍጥጥ ብላ አየቻቸው፡፡

በተዝናኖት ያብራሩላት ጀመር….‹‹ልጄ አሁን ያየሻቸው ባልና ሚስቶች ሲዎዲናዊ ናቸው፡፡አስር አመት ያስቆጠረ ትዳር ቢኖራቸውም ልጅ ግን መውለድ አልቻሉም..እና እንደራሳቸው ልጅ የሚያሳድጉት ቆንጆ ሴት ልጅ ይፈልጉ ነበር…እና አንቺን ወስደው እንደራሳቸው ልጅ ተቀብለው ለማሳደግና ለማስተማር በደስታ ተስማምተዋል፡፡ባልና ሚስቶቹ ትንሽ የጤና ችግር ስላለባቸው በጣም ህፃን የሆነች ልጅ ለመውሰድና ለመንከባከብ አልፈለጉም፡፡ለዛ ነው ይሄን እድል ያገኘሽው፡፡ብዙውን ጊዜ በአንቺ ዕድሜ ያለች ልጅ አሳዳጊ ለዛውም
ሲውዲንን ከመሰለች አገር ለማገኘት የማይታሰብ ነገር ነው፡፡..አንቺ ግን ይሄው እድለኛ ሆንሽ፡፡ከነገ ጀምሮ ፕሮሰሶቹ ይጀመራሉ፡፡ከወር ባልበለጠው ጊዜ ውስጥ ወደእነሱ ትሄጂያለሽ፡፡እዛ በቪዲዬው ያየሽው የተንጣለለ ቤት ውስጥ እየኖርሽ እዛ ግዙፍ የመዋኛ ገንዳ ውስጥ እየዋኘሽ ጥሩ ትምርት ቤት እየተማርሽ የምቾን ኑሮ ትኖሪያለሽ››ሰውዬው ሲያወሩ
‹እኔንም በማደጎ ወስደው በጦሩኝ› የሚል ምስጢራዊ ጉጉት የሚነበብባቸው ይመስል ነበር፡፡

እሷ  ግን  በወቅቱ  እንደእሳቸው  በገጠማት  እድል  አልተደሰተችም…
‹‹እንዴ..ወንድሜስ?››ክፉኛ የሚያሳስባትን ነገር በድንጋጤ ጠየቀች፡፡
‹‹ወንድምሽ ምን ሆነ?››ግራ በመጋባት መልሰው ጠየቋት፡፡
‹‹ወንድሜን ትቼ ወደየትም አልሄድም..››ፍርጥም ብላ ነበር የመለሰችላቸው፡፡
ሰውዬው ያረጀ ፊታቸውን አጨማደው አንቧረቁባት‹‹ትቀልጂያለሽ..ወንድምሽ ምን ይሆናል..?፡፡እንደአንቺ እድለኛ ከሆነ ሌላ አሳዳጊ እናገኝለትና እሱንም እንልከዋለን፡፡ካልሆነም እዚህ አሁን እንደሚኖረው ይኖራል፡፡ወደፊት ትልቅ ስትሆኚ መጥተሸ ትወስጂዋለሽ…ደግሞ እኮ እሱ ወንድ ነው …እራሱን መቻያ ጊዜው እየደረሰ ነው፡፡››በማለት ሊያባብሏትና ሊያግባቧት ሞከሩ፡፡
‹‹አይ አልፈልግም..ወንድሜን ካለእኔ መኖር ስለማይችል ጥዬው የትም አልሄድም፡፡››ውሳኔዋን በድጋሜ አሳወቀቻቸው፡፡
ሊሰሟት አልፈቀዱም‹‹እሱ ነው ያላንቺ መኖር የማይችለው ወይስ አንቺ ነሽ ያለእሱ መኖር የሚያቅትሽ?››እስከዛን ጊዜ ድረስ መለየት ያልቻለችውን ጥያቄ ጠየቋት፡፡በወቅቱ አፏ ላይ አንደመጣላት‹‹ሁለቱም ያው ነው፡፡››ብላ ነበር የመለሰችላቸው፡፡
የእሷን ተቃውሞ ከቁም ነገር ሳይቆጥሩ ‹‹በይ ውጪ…..ይሄንን ዕድል ለአንቺ ለማግኘት ስንት ውጣ ውረድ እንዳሳለፍን አታውቂም፡፡ ደግሞ ቢከሽፍ ያንቺ ዕድል ብቻ አይደለም…እኛም በዚህ ሰበብ ምናገኘው ስንት ዶላር ገደል ገባ ማለት ነው…፡፡በይ አሁን ውጪ፡፡››ብለው ነበር በብስጭት ከቢሮቸው ያባረሯት፡፡ብዙም ጊዜ ሳያባክኑ በሁለተኛው ቀን ነበር እሷን ከባህር ማዶ ለመላክ እንቅስቀሳሴና ፕሮሰስ የጀመሩት..በሶስተኛው ቀን ለወንድሟ እየሆነ ያለውን ነገር ነገረችው፡፡ በመጀመሪያ ሲሰማ በጣም ነበር የደነገጠው….ከመደንገጥም አልፎ እንባ አውጥቶ አልቅሶ ነበር፡፡ቀስ ብሎ ሲያስበው ግን ለእህቱ ጥሩ እድል እንደሆነ አመነ እና እንድትሄድ ይወተውታት ጀመር፡፡ለእሷ ግን በወቅቱ የማደጓ ቤቱ አስተዳዳሪ ሆነ የገዛ ወንድሟ ስለሚያወሩት ሎቶሪ መሰል እድልና የተንደላቀቀ ኑሮ ምንም ሊታያት አልቻለም….በእሷ ሚዛን ገነትም ቢሆን ወንድሟ ከሌለበት ከሲኦል የተለየ ቦታ አድርጋ አትወስደውም፡፡በዛም ምክንያት የወንድሟን ምክር አልሰማችም፡፡
በሳምንቱ ወንድሟንና ቅያሪ ልብሷን በፔስታል ቋጥራ ከግቢውን ለቃ ጠፋች፡፡ምንም ሳንቲም ባይኖራቸውም ከሰበታ ወደአዲስ አበባ የሚወስደው አንበሳ ባስ ውስጥ ሰተት ብለው ገቡ..በተጠቀጠቀ ህዝብ መካከል ተሸጉጠው ምንም ሳይከፍሉ ቀጥታ ለገሀር ድረስ ነበር የሄዱት…ከዛ እግራቸው ወደአመራቸው ወደቦሌ መስመር ተጓዙ፡፡ ከዛ ለአንድ ወር ያህል ምቹ ያሉትን ቦታ እየመረጡ እዚህም እዛም ባሉ የአዲስአበባ ጎዳናዎች ሲዘዋወሩ ከቆዩ በኃላ በመጨረሻ የተሻለ መስሎ በተሰማቸውና በጋራ በተስማሙበት 22 አካባቢ ባለ አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት የግንብ አጥር ስር በቋሚነት ተጠግተው መኖር ጀመሩ፡፡
በወቅቱ እዛ አካባቢ እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች በእነሱ ዕድሜም ከእነሱ በጣም የሚተልቁ ሴቶችና ወንዶችም ይኖሩ ነበር፡፡እርግጥ መጀመሪያ ሰሞን ሊተናኮሏቸው ጀምረው ነበር፡፡በኃላ ግን ቀስ በቀስ እየለመዶቸው ሲመጡ ተቀበሎቸውና ከጫና ውጭ አደረጎቸው፡፡ ከዛም መኪና እየወለወሉም …እየለመኑም…ከሆቴልና ከምግብ ቤት እንደቢጤዎቻቸው ተመላሽ እየለመኑም ልክ ሁለት አፍ እንዳላት አንድ ወፍ..ያገኙትን እየተካፈሉና እየተቆደሱ ለአንድ አመት ያህል ለዘላለም የመሰለ ተደጋጋሚ ተስፋ ቢስ አይነት ኑሮ መኖር ቀጠሉ…፡፡
በወቅቱ በዚህ ሁኔታ እስከመቼ እንደሚቀጥሉ እና ማብቂያው የት ጋር እንደሆነ ሁለቱም አያውቁም ነበር፡፡ ግን ተስፋ ነበራቸው፡፡የሰው ልጅ ያለፈ ትዝታውን ካልረሳ እና የነገ ተስፋውን ካላጠ …በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆን መኖሩ በራሱ ዋጋ አለው ፡፡ነገም ባይሆን ተነገወዲያ የሚቀየር እና ሚለወጥ ነገር አይጠፋም ፡፡በዛ ስሌት ነበር ጎዳና ወጥተው የመከራ ህይወትን በፅናት መቋቋም ችለው የነበረው፡፡እንዳሉትም አቅጣጫዋ የማይታወቅ የተስፋ ፀሀይ ድንገት በህይወታው አንፀባረቀች..ከጎዳና በተአምር ተነሱ..ትምህርታቸውን ተማሩ ስራ ያዙ ብዙ ብዙ የህይወት ውጣ ውረድ አሳለፉ..አሁን ያን ሁሉ የዘመን ልፋታቸውንና ውጣ ውረዳቸውን ጣፋጭ ምርት እያጨዱና እሼቱን በፍቅር አየተመገቡ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ይሄው ጥልቅ በሆነው የአማዞን ደን ከረስ ውስጥ በተቀየሰች አንድ የወንጀለኞች ምን አልባትም የሽብርተኞች ጎጆ ውስጥ ታግታ የምትገኘው ፡፡ከዛ ሁሉ መከራና ከዛ ሁሉ ስቃይ አልፋ ሌላ ስቃይ ሌላ መከራ ላይ….በጣም ከመበሳጨቷ የተነሳ ሳቋ አመለጣት፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8111🥰10👏5👎2