አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሁቱትሲ


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#ምዕራፍ_ሁለት

#ከመቀመጫችን_ሲያስነሡን

‹‹ቱትሲዎች ከመቀመጫችሁ ተነሡ!››
አንድ ቀን አራተኛ ክፍል ሆኜ እማርበት በነበረው መማሪያ ክፍል ውስጥ ስድስት ልጆች ከመቀመጫቸው ተስፈንጥረው ሲቆሙ ግማሽ ደርዘን ወንበሮች ወደ ኋላ ተንጓጉ፡፡ ከዚያ በፊት ሁልጊዜ እናቴ በምታስተምርበት አነስተኛ ትምህርት ቤት ውስጥ እማር ስለነበር ምን እየተከሰተ እንደነበር ልገምት አልቻልኩም፡፡ በዚያን ወቅት አሥር አመቴ ስለነበርና ትንሽ አደግ ላሉ ልጆች የሚሆን ትምህርት ቤት ውስጥ ስማር የመጀመሪያ ቀኔ በመሆኑ የልጆቹ መራበሽ ግራ አጋብቶኛል፡፡ ከዚያ በፊት አስተማሪ የዘውግ ጥሪ ሲያካሂድ በፍጹም አይቼ አላውቅም፡፡
‹‹ቱትሲዎች በሙሉ ከመቀመጫችሁ ተነሡ!›› መምህራችን፣ ቡሆሮ፣ አምባረቀ፡፡ በትልቅ እርሳስ ከዝርዝሩ ላይ ከተማሪዎች ስም አጠገብ ምልክት እያደረገ ነበር፡፡ ከዚያም አቆመና በቀጥታ እኔ ላይ አፈጠጠ፡፡
‹‹ኢማኪዩሌ፣ ሁቱ ስል አልተነሣሽም፤ ትዋ ስል አልተነሣሽም፤ አሁንም ቱትሲ ብል ልትነሺ አልቻልሽም፡፡ ለምንድነው?›› ቦሆሮ ፈገግ እያለ ቢሆንም ድምጹ ግን ክፋቱን ያሳብቅበታል፡፡
‹‹አላውቅም መምህር፡፡››
‹‹ምን ዘውግ ነሽ?››
‹‹የት አውቃለሁ፣ መምህር?››
‹‹ሁቱ ነሽ ቱትሲ?››
‹‹እኔ - እኔ አላውቅም፡፡››
‹‹ካላወቅሽ ውጪያ! ከዚህ ክፍል ውጪ፤ እና ምን እንደሆንሽ ሳታውቂ ተመልሰሽ አትምጪ!››
መጻሕፍቴን ሰበሰብኩና በሃፍረት አንገቴን ደፍቼ ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ፡፡ ገና ያልታወቀኝ ቢሆንም በሩዋንዳ የዘውግ ክፍፍል ላይ የመጀመሪያዋን ትምህርቴን
ተማርኩ፤ ይህም ክው ነበር ያደረገኝ፡፡
ወደ ትምህርት ቤቱ ጓሮ ሮጬ ወንድሜ ዳማሲን የዕለቱን ትምህርት እስኪጨርስ ድረስ ከቁጥቋጦ ጀርባ ተደብቄ መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ እንባዬን ማቆም ተስኖኝ ሰማያዊ የትምህርት ቤት የደንብ ልብሴ እስኪረጥብ ድረስ ነፈረቅሁ፡፡ ምን እንደተከሰተ ስላልገባኝ ወደ ክፍል ሄጄ የቅርብ ጓደኛዬን ዣኔትን ጉዳዩን ታብራራልኝ ዘንድ ለመጠየቅ በጣም ፈለግሁ፡፡ መምህሩ ሁቱ የሚለውን ስም ሲጠራ ተነሥታለች - ምን አልባትም መምህሩ ለምን እንዳመናጨቀኝ ታውቅ ይሆናል፡፡ በቁጥቋጦው ውስጥ ተኮራምቼ ዳማሲን እዚያ እስኪያገኘኝ ድረስ እንባዬን ሳዘራ ቆየሁ፡፡
‹‹ማን መታሽ ኢማኪዩሌ?›› ሲል ታላቅ ወንድሜ ባለችው የ13 ዓመት ሥልጣን ጠየቀኝ፡፡ አለኝታዬ ዳማሲን አንድ ሰው ጫፌን ከነካኝ ለመፋለም የተዘጋጀ ልጅ ነው፡፡ ቡሆሮ ያለኝን ነገርኩት፡፡
‹‹ቡሆሮ ጥሩ ሰው አይደለም›› አለ ወንድሜ፡፡ ‹‹ቢሆንም አትጨነቂለት፡፡ ሌላ ቀን ስም ሲጠራ እኔ የማደርገውን አድርጊ፤ ከጓደኞችሽ ጋር ተነሺ፡፡ ጓደኛሽ ዣኔት ስትነሳ ተነሺ፡፡››
‹‹ዣኔት ሁቱ ብሎ ሲጠራ ነበር የተነሣችው፡፡››
‹‹በቃ እንደዚያ ከሆነ ሁቱ ሲሉ ተነሺ፡፡ ጓደኞቻችን የሆኑት ያንን ከሆነ መቼም እኛም የምንሆነው እንደዚያው መሆን አለበት፡፡ ሁላችንም አንድ ሕዝብ ነን፣ አይደል?››
በዚያን ወቅት የማውቅበት መንገድ አልነበረኝም፤ ዳማሲንም እንደኔው በሩዋንዳ ስለነበረው ዘውገኝነት ግንዛቤ አልነበረውም… ይህም በአካባቢው በጥሩ ሁኔታ ይማሩ ከነበሩት ልጆች ውስጥ ከመመደባችን አንጻር እንግዳ ነገር ነው፡፡ በየዕለቱ ከትምህርት መልስ ወንድሞቼና እኔ ወደ ቤታችን በእናታችን ተቆጣጣሪነት የቤት ሥራችንን እንድንሠራ ከመጠራታችን በፊት የ90 ደቂቃ የእረፍት ጊዜ ነበረን፡፡ አባታችን ከራት በፊት የትምህርት ቤታችንን ሰሌዳዎች የምታክል ጥቁር ሰሌዳ በቤታችን መካከል አድርጎ ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ ያስጠናናል፡፡ የሒሳብ፣ ሰዋስውና መልክዓምድር ጥናት ጠመኔ እየሰጠ ያለማምደናል፡፡
ይሁን እንጂ ወላጆቻችን ስለራሳችን ታሪክ አላስተማሩንም፡፡ ሩዋንዳ የሦስት ዘውጎች፣ ማለትም የሚበዛው ሁቱ፣ አናሳ ቱትሲዎችና በጣም ትንሽ ቁጥር ያላቸው በጫካ ውስጥ የሚኖሩት ትዋዎች ስብስብ እንደሆነች አላስገነዘቡንም፡፡ የጀርመን ቅኝ ገዥዎችና ከእነርሱ በኋላ የመጡት ቤልጅየሞች የሩዋንዳን ነባር ማኅበራዊ አወቃቀር ማለትም ሩዋንዳን ለምዕተ-ዓመታት ሰላምና ስምምነት የሰጣት ቱትሲ ንጉሥ የሚመሩትን ዘውዳዊውን ሥርዓት በአግላይ ዘውግ-ተኮር የመደብ ሥርዓት ቀይረውት እንደነበር አልተማርንም፡፡ ቤልጅየማውያኑ የቱትሲውን ገዥ መደብ ደግፈውና በመሪነት ደረጃ ያለውን አስተዋፅኦም ተቀብለው፣ አገሪቱን በተሻለ መንገድ ለማስተዳደርና ለቤልጅየማውያኑ ከፍተኛ ትርፍ ለማስገኘት ያግዝ ዘንድ ቱትሲዎች የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ አድርገዋል፡፡ ቤልጅየሞች በሁቱና ቱትሲ መካከል ፈጥረውት የነበረውን ክፍተት በማባባስ ሁለቱን ዘውጎች በቀላሉ ለመለየት የዘውግ መታወቂያ ደብተር አስተዋውቀዋል፡፡ እነዚያ የማይረቡ ስህተቶችም በሁቱዎች ዘንድ ዘላቂ ቁጭት በመፍጠር ለዘር ጭፍጨፋ መሠረት ለመጣል አገዙ፡፡ ቱትሲዎች የተሻለ ነጻነት በጠየቁ ጊዜ ቤልጅየማውያኑ በጠላትነት አዩአቸው፡፡ በ1959 ደም-አፋሳሽ የሁቱ አመፅን ደግፈው ዘውዳዊው ሥርዓት እንዲገረሰስ አደረጉ፡፡ ከ100 000 በላይ ቱትሲዎች በበቀል በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ተገደሉ፡፡ በ1962 ቤልጅዬም ከሩዋንዳ ለቃ ስትወጣ የሁቱ መንግሥት አንቀጥቅጦ በመግዛት ላይ ሲሆን ቱትሲዎችም በሁቱ አክራሪዎች ማሳደድ፣ ሽብርና ግድያ የሚፈጸምባቸው ሁለተኛ ዜጎች ለመሆን በቁ፡፡ በብዙ አሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ቱትሲዎች ግድያዎች የዕለት ከዕለት ክስተት በነበሩባቸው አሥርት ዓመታት ውስጥ ሞቱ፡፡ የሽብር ዑደቱ ተጧጡፎ መድሎ መፈጸሙ ቀጠለ፡፡ የሁቱው መንግሥት ከቤልጅየሞች የአገዛዝ ዘመናት የወሰደው የዘውግ መታወቂያ ደብተር አሠራር መድሎውን የበለጠ ይፋና ቀላል አደረገው፡፡
ወላጆቻችን እኔና ወንድሞቼ ቢያንስ በልጅነታችን እንዳንማራቸው ያልፈለጓቸው የታሪክ ትምህርቶች እነዚህ ነበሩ፡፡ ስለ መድሎም ሆነ ስለ ግድያ ዘመቻዎቹ፣ ስለ ዘር ማጽዳቱም ሆነ የዘር መታወቂያ ካርዶቹ አላወሩንም - እነዚህ ነገሮች ፈጽሞ የልጅነቴ አካል አልነበሩም፡፡
ዘርን፣ ሃይማኖትን ወይንም ዘውግን ከግምት ውስጥ ሳናስገባ በቤታችን ማንንም ሰው በደስታ እንቀበላለን፡፡ ወላጆቼ የእርስዎን ሁቱ ወይንም ቱትሲ መሆን ከስብዕናዎ ጋር አያገናኙትም፡፡ ጥሩ ጸባይ ካለዎትና ገራገር ከሆኑ እጆቻቸውን ዘርግተው ሰላምታ ያቀርቡልዎታል፡፡ ወላጆቼ ራሳቸው ግን በሁቱ ጽንፈኞች የደረሱባቸው የተወሰኑ አሰቃቂ ችግሮች ነበሩ … እንዲያውም አንደኛውን ትንሽ ትንሽ አስታውሳለሁ፡፡ ያኔ የሦስት ዓመት ልጅ ነኝ፡፡ ነፍስ ባለማወቄ ምን እየተከሰተ እንደነበር አልገባኝም፡፡ የምሽቱን ሰማይ እሳት ሲንቦገቦግበት፣ እናቴም በእጆቿ ጥብቅ አድርጋ ታቅፋኝ ከቤታችን ስትሮጥ ይታወሰኛል፡፡ ይህ የሆነው ብዙ ቱትሲዎች በተሳደዱበት፣ ከቤቶቻቸው በተነዱበትና በየመንገዱ በተገደሉበት የ1973ቱ መፈንቅለ-መንግሥት ወቅት መሆኑ ነው፡፡ በኛ ክፍለሀገር ሁቱ ጽንፈኞች የቱትሲዎችን ቤቶች በየተራ አቃጥለዋል፡፡ እሳቱ ወደኛ ሽቅብ ሲገሰግስ መላው ቤተሰቤ አብሮ ቆሞ ወደ ኪቩ ሐይቅ ቁልቁል በማስተዋል ላይ ነበረ፡፡ ሩታካሚዜ ወደተባለው ጥሩ ሁቱ ወዳጅ ጎረቤታችን ቤት ሸሸን፡፡ እርሱም ግድያዎቹና ቃጠሎው እስኪያቆሙ ድረስ ሸሸገን፡፡ ወደ ቤታችን ስንመለስ የሚጫጫስ
👍2
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)

#ምዕራፍ_ሁለት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ፔሩ/ኢኩኢቶስ

አሁን ኑሀሚ ከሊማ ወደብራዚሊያ በሚወስደው የሊማ አለምአቀፍ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 102 ላይ ነች፡ከጉዞው በፊት የጀመራት የራስ ምታት እረፍት ነስቷታል…በዛ ላይ ከጎኗ ያለው ጎልማሳ ሰው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገብቶ እያንኳራፋ ነው፡፡አውሮፕላኑ ውስጥ ስትገባ እንኳን ቀድሟት ወንበሩን ይዞ መተኛት ጀመሮ ነበር፡፡ሁኔታውን ስታየው ምን አልባት ለሳምንታት እንቅልፍ ሚባል ነገር በአይኑ እንዳልዞረ ገመተች፡፡የሰውነቱ ቀለም በቀይና ነጭ መሀከል የሚዋልል ነው፡፡ጸጉሩ ሉጫ ከመሆኑ በተጨማሪ ወርቃማ የሚባል ሆኖ እንደልጃገረድ ፀጉር ረጅም ሆኖ ጀርባው ላይ ተኝቷል፡፡…ፈረንጅ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነች፡፡ምን አልባት ብራዚላዊ ወይም ኮሎምቢያዊ ብቻ እዛ አካባቢ ዜጋ ሊሆን እንደሚችል ገምታለች፡፡
ከእንቅልፉ ተነስቶ ቢያዋራት ደስ ይላት ነበር፡፡ከሰው ጋር ስታወራ የሚወቅራት የራስ ህመሟ ስቃይ ይቀንስላት ወይም ጥሏት ይሄድ ይሆናል፡፡ይህ የእሷ ግምት ነው…፡፡ሰውዬው እኮ ትንፋሽ በውስጡ መኖሩን እስክትጠራጠር ድረስ ፀጥ እንዳለ ቀጠለ ፡፡የአንድ ሰዓት ጉዞ ከተጓዘ በኃላ ድንገት ከጎኗ ያለው ሰውዬ ተንቀሳቀሰ ..አላመነችም፡፡ነቃና አይኖቹን ገለጠ፡፡ዙሪያ ገባውን በመገረምና በድንጋጤ ቃኘ፡፡እሷንም ደጋግሞ ተመለከታት…የሆነ ያልጠበቀው ነገር እንደየ አይነት ነው፡፡
‹‹Where I am?››

‹‹ጥያቄው አስገረማት፡፡ ግን …በስተመጨረሻም ቢሆን የምትፈልገውን ወሬ ስላገኘች ትመልስለት ጀመር፡፡ ከፔሩ ወደብራዚል እየተጓዝን ነው፡፡ ….ከአንድ ሰዓት በላይ ስለተኛህ ከየት ተነስተህ ወደየት እየሄድክ እንደሆነ ዘነጋኸው አይደል?››ጥያቄው እዚህ ጋር ያቆማል ብላ ጠብቃ ነበር ፡፡እሱ ግን ሌላ ግራ አጋቢ ጥያቄ ጠየቃት ፡፡
‹‹Who I am?››

‹‹እርፍ!! ››አለች፡፡ስለሱ ሰምታችሁም ሆነ መልኩን እንኳን ከዚህ ቀደም አይታችሁት የማታውቁት ሰው ድንገት ፊታችሁ ተጋርጦ እኔ ማን ነኝ? ብሎ ሲጠይቃችሁ ምን አይነት ስሜት ነው ሚሰማችሁ?፡፡አንድ የተሳሳተ ነገር እንዳለ ወዲያው ማሰባችሁ አይቀርም….ኑሀሚም እንደዛ ነው ግራ የተጋባችው፡፡ ቀልድም መስሏት ፈገግ ልትልለትም ቃጥቷት  ነበር…ግን  ፊቱን  ስታይ  ምንም  የመቀለድ  አፒታይት  ያለው  ሰው  ሆኖ አላገኘችውም፡፡፡እሷ ደግሞ በበፊት ስራዋና ስልጠናዋ ጋር ተያይዞ የሰውን ስሜትና ፍላጎት መተንበይ እና መገመት ችሎታዋ የተዋጣለት የሚባል ነው፡፡እና እየቀለደ እንዳልሆነ እርግጠኛ ሆናለች፡፡ይሁን እንጂ ይበልጥ እንዲያወራ ለማድረግና ከወሬው ደግሞ ተጫማሪ ፍንጭ ባገኝ ብላ ጥያቄዋን ቀጠለች፡፡
‹‹አር ዩ ኪዲንግ ሚ(እየቀለድክ ነው)?››

‹‹አይ እውነቴን ነው …፡፡እኔ ማን ነኝ..?ወደብራዚል ለምድነው የምሄደው? ፡፡››

‹‹እሱን ልመልስልህ አልችልም…ኪስህ ውስጥ ግባና ፓስፖርትህን እይ፡፡››የሚል ምክረ-ሀሳብ ሰጠችው፡፡

‹‹ፓስፖርት ምንድነው?››

‹‹እንዲህ አእምሮ የለቀቀ ሰው ብቻውን እንዴት ይጓዛል ?››ስትል አሰበችና ይበልጥ የታሪኩን መጨረሻ ለማወቅ ጓጓች፡፡
አወጣችና የእሷን ፓስፖርት ሰጠችው‹‹ፓስፖርት ማለት ስለአንተ ማንነት..  ስምህን፤ዕድሜህን፤ ዜግነትህን የመሳሰሉትን ዋና ዋና መረጃዎች የያዘ ሰነድ ነው…ከአንድ ሀገር ወደሌላ ሀገር ለመግባትና በነፃነት ተንቀሳቅሶ የሄዱበትን ጉዳይ ለመከወን ይሄንን ፓስፖርት የተባለ መታወቂያ መሳይ አለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰነድ መያዝ የግድ ነው፡፡›› ስትል አብራራችለት፡፡
ተቀበላትና አየው፡፡የእሷን ፓስፖርት መለሰላትና ወደኪሶቹ እጁን ሰደደ፡፡ንግግሯን ከምር ወስዶ ኪሱን መፈተሸ ጀመረ ፡፡የተወሰኑ ዶላሮች ..እናም የተወሰኑ የብራዚል ብር ከፔሩ ወደብራልዚል የመብራሪያ አየር ትኬት በቃ…በኪሱ ያሉ ዕቃዎች እነዛ ናቸው፡፡ ፓስፖርት የሚባለው ነገር የለውም፡፡
ትናንሽ አይኖቹን እያቁለጨለጨባት ‹‹የለኝም…፡፡››አላት፡፡

አሁን እየቀለደ እንዳልሆነ እየተሰማት ነው…‹‹እስቲ ዙሪያህን ተመልከት… የምታውቀው ሰው የለም….?ምን አልባት አብሮህ ያለ ዘመድ ወይም ጓደኛ ፕሌኑ ውስጥ ሊኖር ይችላል?››የሚል ምክር ሰጠችው፡፡ቆመና መቀመጫውን ለቆ ተነሳ ፡፡ወደፊት ሄደና ከመጀመሪው ወንበር አንስቶ ወደኃላ እየተጓዘ ሚያውቀውን ፊት እንዳለ ወይም አውቋት ሚያናግረው ሰው ይኖር ይሆን በሚል ስሌት ፈተሸ….ተስፋ ሲቆርጥ ተመልሶ ተቀመጠ፡፡
‹‹እ…አገኘህ?››

‹‹አይ ..ምንም የማውቀው ፊት የለም፡፡››

‹‹እስኪ ተረጋጋ …ምን አልባት ሻንጣ ውስጥ የሆነ መረጃ ታገኝ ይሆናል?››

‹‹ሻንጣ…?››

‹‹አዎ ሻንጣህ?››

‹‹ሻንጣ አለኝ እንዴ ?››መልሶ እሷኑ ጠየቃት፡፡
‹‹ካለህ ብዬ ነዋ፡፡ሁሉም ሰው የሆነ ሻንጣ ይኖረዋል፡፡ለማንኛውም እስኪ ጥቂት ተረጋጋና ለማስታወስ ሞክር፡፡››
‹‹እሺ ››አለና ፀጥ አለ፡፡3…4…5..10 ደቂቃ ሞከረ..ምንም ሚያስታውሰው ነገር የለም…፡፡
በዚህ ጊዜ ከአብራሪው ክፍል አቅጣጫ በድምጽ ማጉያ ቀጭን ቃጭል የሆነ የሴት ድምፅ መሰማት ጀመረ ‹‹ደንበኞቻችን ከፍተኛ እይታ ሚጋርድ ጥቅጥቅ ጉም ከፊታችን መንገዳችንን ስለሸፈነ እና የአየር ፀባዩ አስተማማኝ ለሆነ ጉዞ ምቹ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት ወደመዳረሻችንን መጓዝ አልቻልንም…በዚህ ምክንያት በቅርብ የሚገኝ የኢኩኢቶስ አየር መንገድ ፍቃድ እንዳገኘን እናርፍና የአየሩ ፀባዩ እንደተስተካከለ እንቀጥላለን፡፡አሁን ሁላችሁም  ቀበቷችሁን እንድታደርጉና ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክ
መገልገያዎችን እንድታጠፉ በትህትና እንጠይቃለን የሚል መመሪያ አስተላለፈችና ንግግሯን አጠናቀቀች፡፡
በፕሌኑ ውስጥ ያሉ መንገደኞች ውስጥ ጉርምሩምታና ትርምስ ተሰማ…. ሁሉም ቀበቷቸውን እንዲያስሩን የኤሌክተትሮኒክ መሳሪያዎቻቸውን እንዲያጠፉ ትእዛዝ ተሰጠ፡፡
‹‹ኢኩኢቶስ የት ነው የምትገኘው?›› ጠየቀችው ፡፡ ለማስታወስ ሙከራ አደረገ..አልተሳካለትም፡፡
አሳዘናትና ‹‹የትም ቢሆን ችግር የለውም ..ተወው አትጨነቅ፡፡አይዞህ የሆነ ነገር እናደርጋለን…አሁን ቀበቶህን እሰር አለችው፡፡››

‹‹እሺ አመሰግናለሁ፡፡›› አለና እንዳለችው አደረገ፡፡
ከደቂቃዎች በኃላ አውሮፕላኑ የተወሰና መንገጫገጭ አሰማና ተረጋግቶ አረፈ፡፡ጉዞው የአየር ፀባዩ ከተስተካከለ በማግስቱ እንደሚደረግ ስለተነገረ ተጓዦች ሻንጣቸውን ከተሰቀለበት እያወረዱ ወደመውጫቸው መጓዝ ጀመሩ፡፡እሱ በተቀመጠበት ቦታ ሆኖ እየተቁለጨለጨ ነበር….፡፡
‹‹ተነስ›› አለችው..ተነሳና ግራ በመጋባት ተከተላት፡፡ሻንጣዋን አወረደችና በእጇ በመያዝ የእሱን ትከሻ ያዘችና አቆመችው፡፡
‹‹ምነው አንወጣም እንዴ?››ግራ በመጋባት ጠየቃት፡፡
‹‹ቆይ… ሁሉም ሰው ወጥቶ ይለቅ…መጨረሻ መቅረት አለብን፡፡››አለችው፡፡
እንደዛ ያለችበትን ምክንያት ባይረዳም..ግን እሷ ምትለውን ከመቀበል በስተቀር ምርጫ ስለልነበረው እንዳለችው አደረገ፡፡ሁሉም ወጥቶ ካለቀ በኃላ ቀጥታ ወደዕቃ ማሳቀመጫው መደርደሪያ ተንጠራራች፡፡ የተንጠራራችው የቀረውን አንድ ላፕቶፕ የያዘ ሻንጣና አንዴ ሌላ ሻንጣ በድፍረት አወረደች…የላፕቶፑን ሻንጣ ኪስ ከፈተችና ስትፈትሽ ፓስፖርት አገኘች፡፡ አወጣችና አየችው፡፡
‹‹ ዳግላስ ዲያሲስ ሞሬራ›› ይላል ..ፎቶ የራሱ ነው፡፡ሰጠችው፡፡
‹‹ምንድነው?››
👍776🔥2👏2😁1