አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
480 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

#ፔሩ_ሊማ

ኑሀሚ 26 አመት ላይ ያለች ማራኪ ገፅታና ሳቢ ውበት ያላት ንቁ ወጣት ናት፡፡

ከመደበኛው ትምህርት በላይ ከህይወት ብዙ የተማረችና በብዙ ፈተናና ውጣ ውረድ የበሰለች ወጣት ነች፡፡ኢትዬጳያ ውስጥ በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ በሚንቀሳቀስ አለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ መስራት ከጀመረች አራት አመት አልፏታል፡፡ እዚህ ድርጅት ውስጥ ከመስራቷ በፊት በሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ከ12 ዓመቷ ጀምሮ ተመልምላ ለረጅም አመት ስልጠና ከወሰደች በኃላ በተለያዩ የሽፋን ስራዎችና ተልዕኮዎች ላይ ተሳትፋ ድንቅ የተባሉ ስኬቷችን ያስመዘገበች የተዋጣላት ሰላይ ነበረች፡፡ለውጡን ተከትሎ በመስሪያ ቤቱ በተካሄደው ሪፎርም የ10 አመት የግዳጅ የአገልግሎት ዘመኗንም አጠናቀ ስለነበር..በራሷ ፍቃድ ከስራው ለቃ አሁን የምትሰራበት መስሪያ ቤት ተቀጠረች፡፡

እርግጥ አሁንም አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ እሷ ብቻ የምትሰራቸው ስራዎች ሲያጋጥሙ በኮንትራት ሰራተኝነት ተልዕኮ ይሰጣታል፡፡ እሷም ስራውን ስለምትወደው ያለማንገራገር ተቀብላ ትሰራለች፡፡

አሁን በምትሰራው ስራም ደስተኛ ነች..ምክንያቱም ደሞዟ በዶላር ነው፡፡ጥሩ ኑሮ እንድትኖር ምክንያት ሆኗታል፡፡ በዛ ላይ ብዙ ነገር አውቃበታለች፤ብዙ ነገር ተምራበታለች፡፡አሁን በዚህ ሰዓት ከአለም አቀፍ ሀገሮች ከተውጣጡ መሰል ኤክስፐርቶች ጋር የ3ወር ስልጣና ለመውሰድ ሰሜን አሜሪካ በምትገኘው ሀገረ ፔሩ ዋና ከከተማ የሆነችው ሊማ ከከተመች አንድ ወር አልፏታል፡፡

በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ ለሚካሄደው አለም አቀፍ ሴሚናር ፔሩና ብራዚል በጥምረት ነው አስተናጋጅ ሆነው የተመረጡት፡፡የዚህም ምክንያት ሁለቱም ሀገሮች በተፈጥሮ ሀብት ክምችታቸው ምድራዊ ገነት ስለሆኑ ነው፡፡ብራዚል 60 ፐርሰንት የሆነው የአማዞን ደን ባለቤት ስትሆን ፔሩ ደግሞ 13 ፐርሰንት የሚሆን ድርሻ አላት፡፡፡፡የአለም አንደኛውና ግዙፉ የአማዞን ወንዝ እየተጠማዘዘ የሚፈስበት እና ለአለም ህልውና መሰረት የሚሆነው ካርቦንዳይኦክሳይድ የሚመረትበትና ለመላው አለም በአምላክ እስትንፋስ ሀምሳያ የሚበተንባቸው ሀገሮች ናቸው፡፡አማዞን ወንዝ አንዴ ሸንቃጣ ጅረት እየመሰለ ደስ ሲለው ደግሞ ጋሻ መሬት ላይ ተኝቶ ሀይቅ እየፈጠረ በሁለቱም ሀገራት ምድር ላይ እንዳሻው እየተጠማዘዘና እየደነሳ ይጋልብበታል፡፡እና አለምን ከጥፋትና ከውድመት ለመታደግ የተፈጥሮ ሀብትና ደንን የባዬ-ዳይቨርሲቲ ጥበቃ እና እንክብካቤ በሙሉ አቅም ለማስተግበር ከምር ስራው መጀመር ካለበት መነሻ ቦታው ደቡብ አሜሪካ መሆን እንዳለበት የአለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ ድርጅት ብቻ ሳይሆን እሷም በግል በተለይ መጥታ አካባቢውን በጥቂቱም ቢሆን ካየችና የአንድ ወር ስልጠናውን ከወሰደች በኃላ አምናበታለች ፡፡
ኑሀሚ ይሄንን እድል አግኝታ ወደደቡብ አሜሪካ ከመምጣቷ በፊት ስለብራዚልና አርጀንቲና ካልሆነ ስለፔሩና ሌሎች የአህጉሪቷ ሀገሮች ከስማቸው ውጭ የምታውቀው ምንም ነገር አልነበራትም፡፡ለምስሌ ስለብራዚል ባህላቸውንና የሳንባ ዳንሳቸውን ብዙ የዶክመንተሪ ፊልሞችና በተደጋጋሚ ጊዜ አይታለች፡፡ከሁሉም በላይ ደግሞ የእግርኳስ አፍቃሪ የሆነው ብቸኛ መንትያ ወንድሟ የብራዚሎች አድናቂ ነው፡፡በተለይ የአለም ዋንጫ ኖሮ የእግር ኳስ ጫወታ በሚኖርበት ጊዜ ገና ህፃን ሆነው ጀምር የብራዚሎች ደጋፊ ነበር..ለብራዚል ተጫዋቾች ያለው ፍቅር እብድ የሚያስብለው አይነት ነው፡፡ሮናልዶ..ሮናልዲኒዬ…ሮቤርቶ ካርሎስ….ሪቫልዶ….  ኒይማር  ..ገብርኤል  ጀሱስ….ማርቲሊኒ…በእሱ  እድሜ  ሙሉ የተጫወቱትን ዘርዝሮ አይጨርስም፡፡ በየጫወታቸው የሚያሳዩትን አብዶ እንደ ህጻን ልጅ ቁጭ ብድግ በማለት ማየት የዘወትር ድርጊቱ ነው፡፡እና እሷም ይሄንን ባየች ቁጥር ይገርማት ነበር፡፡ከዛ የሚያየውን አይታ በእነሱ መደመምና ትኩረት መስጠት ጀመረች፡፡ ከዛም ተጋባባት ከብሄራዊ ብድን የብራዚል… ከክለብ ደግሞ የአርሴናል ደጋፊ ሆና እራሷን በእግርኳስ አፋቃሪዎች መዝገብ ላይ አሰፈረች፡፡እና በዚህ የተነሳ የብራዚል አድናቂ ነች፡፡ታዲያ ወደደቡብ አሜሪካ እንደምትሄድ ዜናውን ስትሰማ ፔሩን ሳይሆን ብራዚልን ለማየት ነበር የጓጓችው… እንደአጋጣሚ ደግሞ ፕሮግራሙ ከፔሩ ስለተጀመረ… እስከአሁን ብራዚልን የማየት ጉጉቷ ባለበት እንዲቆይ ሆኗል፡፡

እዚህ ፔሩ ባሳለፈችበት አንድ ወር ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ጥብቅ በሆነ ስልጠና እና ትምህርታዊ ሴሚናር ያሳለፈች ቢሆንም አልፎ አልፎ ወጣ ብላ ዞር ዞር በማለት የመዝናናት እድሉ አጋጥሟታል፡፡ሊማ  የፓስፊክ ውቅያኖስን በአንድ ጎኗ ታካ የተመሠረተች ጥንታዊውንና ዘመናዊውን ስልጣኔን ጎን ለጎን አቻችላ የላቲኒንና የዬሮፖዎችን ባህልና ቋንቋ ቀይጣ የተመሰረተች የፔሩ ዋና ከተማ ነች።ኑሀሚ ከተማዋን ገና እንዳየቻት ነው የወደደቻት።እርግጥ የመጣችው ለጉብኝት ሳይሆን ለትምህርታዊ ሴሚናር ነው።በዛም ምክንያት የቀኑን የበዛ ጊዜዎን በትምህርታዊ ሴሚናሮችና የወርክሾፕ ስልሰጠናዎች ላይ ነው የምታሣልፈው።ግን ባገኘችው ጥቂት ጊዜም ቢሆን በተለይ ምሽቱ ላይ እዛው ከተዋወቀቻቸው የሀገሬው ተወላጅ ሠልጣኝ ጋር ሹልክ ብላ ትወጣለች።
ሊማ ከተማን እንደታዘበቻት ከሆነ ከወገብ በላይ ውብና ዘመናዊ ከወገብ በታች ጎስቋላና ቆሻሻ ሆና ስላገኘቻት በጣም ተደምማበታለች፡፡በጉብኝቷ ወቅት እጅግ ካስገረሟትና አይኗንም ቀልቧንም ከተቆጣጠሯት ብዙ ነገሮች መካከል ጥቂቱ
1)  ካቴድራል ዲ ሊማ የተባለ በጥንታዊ የአውሮፓዎች የህንፃ ዲዛይን የተሠራ ግዙፍና ውብ ሙዚዬም ነው።ሙዚዬሙ በረቀቀ ጥበባቸው ልብን ስልብ በሚያደርጉ በተለያየ የስዕል
ክምችቶች የተሞላ ነው።ከዛም በተጨማሪ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ቅርሶች፤ ልዩ ልዩ አይነት መስቀሎች፤ሀውልቶችና .. ታሪካቸውንና ጀግንነታቸውን የሚዘክሩበት በሰው የራስ ቅል ክምችቶች የተሞላ ነው።
2)  ልላው ፕላዛ ዳ ራና የሚባለው አካባቢ ነው።ይሄ የሀገሬው መንግስት ቤተመንግስት የሚገኝበት እና የሊማ ዋና አደባባይ ያለበት እንደ ዳውን ታውን የሚታይ የከተማዋ ማእከላዊ ስፍራ ነው።በዚህ አደባባይ ላይ ከእድሜ ጠገቦቹ ህንፃዎች ፊት ለፊት ለቀቅ ብሎ በተንጣለለው ሰፊ የኮንክሪት ሜዳ ላይ በእርግባች እና በቱሪስቶች መካከል በመረጋጋት እና በስክነት የተሞላ ጫወታን ማየት ልዩ ደስታን ለልብ ይሰጣል።ቱሪስቶች ለወፎቹ ጥራጥሬና ምግብ ሲበትኑላቸው..ወፎቹ ግር ብለው መጥተው አካባቢውን ሲወሩትና ምግቡን ከወለሉ ላይ ሲለቅሙ ማየት ልዩ አይነት ስሜት ይፈጥራል፡፡

3/ፓርክ ኬኔዲ…በአካባቢው ያለው የህንፃዎች ውበት ፤የአበቦችና የአረንጓዴ ዛፎች እይታ አካባቢውን የሚያላብሰው ውበት እንዳለ ሆኖ የዚህ ፓርክ ድንቁ ነገር ድመቶች ናቸው።ፓርኩ ጠቅላላ በድመቶች የተሞላ ነው ማለት ይቻላል።ደግሞ አንድ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ከአስር በላይ የድመት ዝርያ መመልከት ይቻላል፡፡ሲንቀሳቀሱ ደግሞ ሌላ አይነት።በአለም ላይ የሚገኙትን የድመት ዝርያዎች በጠቅላላ ከየቦታው እየለቀሙ በማማምጣት እዚህ የበተኗቸው ነው የሚመስለው.፡፡ይንን ሁሉ የድመት ዝርያ በአንድ ቦታ አይቶ ማንም የማይደመም ሰው አይኖርም።በዛ ላይ ስለ ድመት የማውቀው ብሎ አስጎብኚዋ የነገራት ነገሮች በጣም ነው ያስገረማት፡፡ለምሳሌ ድመት ማረጥ የሚባል ነገር እንደማታውቅና እድሜ ልኳን መውለድ እንደምትችል ነግሯታል፡፡አንድ ድመት የሆነ ቀዳዳ ለመሹለክ ከመሞከሯ በፊት መጀመሪያ ቀዳዳው እንደሚያሾልካት ለክታ እርግጠኛ ስትሆን ብቻ እንደምታደርገው
👍15510👏4😁3🔥1