አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_አስራ_አንድ


...ደግመን ልንበድላት አይገባም የዱላን ፍቅር አሳይዋት እሷም ተተወሰነ ጊዜ በኋላ ፍርሃቱ ይወጣላታል!"

"እእ! እሽ ዛሬስ እኛም አስበናታል ና እንጂ አንተስ
ተጫዋት?"

አለሁ የት እሄዳለሁ  አዳሬ ተዚሁ ነው" ብሎ ደልቲ
ከበርኮታው ላይ ተነሳ ጎረምሳው ደግሞ የባራዛ አርጩሜውን ወደ
ደበቁበት ጉቶ ሄዶ ሶስት ለበቆችን አነሳ ደልቲም ከወንዶች ግማሽ ክብ ሰልፍ ገብቶ ወገብ ለወገብ ተያያዘ

አንዱ ጎረምሳ አንደ መፎከሪያ በርኮታውን በቀኝ እጁ ይዞ የመፎከሪያ በሬውን ጥንካሬና ውበት የጓደኝነታቸውን ምሥጢር
ሲደረድር ሁለት ልጃገረዶች አንባራቸውን እያፋጩ: ከፊት ለፊቱ ቆመው ሲያሞጋግሱት ቆይቶ እያቀነቀነ መዝለልና መጨፈር ጀመረ
ከዚያ የእድሜ ጓደኞቹ ተቃቅፈው ሄደው በቃህ ብለው በትህትና
ጠይቀው አጅበው ተሰልፉ አስገቡት ወዲያው ግን
ጧ ጧ፥ጣጣ.ጣ… የሚል ግርፊያ ተሰማና ልጃገረዶች እያውካኩ፥ ብትን ብለው ሲስቁ ቀጭን የሲቃ ልቅሶ ከመካከላቸው ተሰማ"

ያች ባለጌ ናት! አለ ደልቲ ንድድ እያለው"

ኮቶ ምን አደረኩት ..." ካርለት እንባዋ እየረገፈ ሰውነቷ
እየተንቀጠቀጠ፥ ኮቶን ተጠምጥማ ጠየቀቻት ለበለባት የተገረፈችው
ቦታ ሰንበሩ ጀርባዋ ላይ እንደ እባብ ተጋድሞ ቆጠቆጣት እንባዋ
እርግፍ እርግፍ አለ

"ኮቶ ለምን ገረፉኝ ..." አለቻት ህቅ ብላ እያለቀሰች,

"ይእ! ካርለቴ ደንብ ነው ብየሽ! ዘመድሽኮ ነው፤ “ለምን ተኔ ጋር አትደንሽም ብሎ ነው የመታሽ ሄደሽ አብረሽው ደንሽ
ይልቅ  ታለበለዚያ ይደግምሻል"" ስትላት ካርለት ቦታውን ለቃ
ልትሄድ አሰበች ህሊናዋ ተሟገተ

"ኮቶ ለምን እገረፋለሁ!- እኔ'ኮ መመታት አለመድሁም?" ብላ
በቀላው ዐይኗ ትክ ብላ አየቻት

"ይእ!  ስንወለድ እኮ እኛም አለመድነውም ትርጉሙን
ስናውቅ ማድረግ ያለብን ነው ብለን ስናምን ልባችን ደንድኖ ለመድነው አንችስ ሰው መስለሽኝ ስትመጭ የካሮ አፈር  ፈጭተሽ መች ትቀቢ ነበር ቆዳ መልበስ:
በእግር መሄድ እንጨት
መልቀም የተማርሽው እዚህ አይደል ግርፊያም የሚለመደው ስትደፍሪ ነው
የፍቅር ማባያ ይሆንሻል
የተማርሽው እዚህ አይደል
ስትገረፊ መጀመሪያ እንደቃሪያ ያቃጥልሻል ቀጥሎ የፍቅር ማባያ ይሆንሻል በመጨረሻ ደግሞ የሚለበልበው ቃሪያ
ያምርሻል! አይዞሽ የኔ እህት ያን ጊዜ እንደ ሱስ በልቦናሽ
ውል እያለ አምጭ አምጭ' እያለ ተሐመር አንበሶች ክርን ስር ያልወሰውስሻል
ከዚያ ትለምጅዋለሽ" ብላ ደረቷ ላይ አስጠግታ አግባባቻት,

"እሽ ኮቶ ካርለት በጽሞና ስታዳምጣት ቆይታ እንባና ሳቋ ተቀላቀለባት

"እሽ! ዓላማ ታውቂያለሽ ኮቶ" አለቻት  ትክ ብላ በጨረቃ  ብርሃን እያየቻት

"ይእ! ኢላማ ማለትሽ ነው  ማነጣጠሪያ የዓልሞ ተኳሽ
መለያ ነው ኢላማ ተሆነ "

"ልክ ነሽ! የአነጣጠርኩት: ዓልሜ የምመታው ኢላማ አለኝ ኮቶ! ስለዚህ

"ይእ! አይ ካርለቴ መቼም የአንች ነገር እንደ እርጎ ዝንብ ወንዶች መዋያ ጥብሉቅ ማለት ስትወጂ  እስቲ እንደ ሴት ኢላማሽ
ልጅ መውለድ: ለባል ታዛዥ ለመሆን ይሁን የአባት ደንብ ለማክበር ይሁን ኢላማሽ!"

"እንደንስ ኮቶ!  ዳንስ አማረኝ ግርፊያ ፈለግሁኝ... ንኪው ልቤን የፍርሃት እርግጫውን አቆመ
አደፋፈርሽው አስተማርሽው ህዋን የሰው ልጅ በእግሩ ሲረግጥ እኔም በጭንቅላቴ
የመሬትን እንብርት  እነካዋለሁ…ቃሪያውን እየበላሁ ጥቅምና
ጉዳቱን ለሌላው አሳያለሁ  እነ ዲያና ፎሲ ከጉሬላ ጋር ቅጠል በልተውስ ኖረው የለ

"ይእ!- ካርለቴ!" ወዘወዘቻት ትከሻዋን"

"ደህና ነኝ ኮቶ"

"እየቃዠሽ! ቢጫ ሐሞት እንደሚያስተፋ ወባ እንደያዘው ሰው

"የለም ደህና ነኝ ቃል ኪዳን ነው ኮቶ ሰው ለመሆን፥
ጠንካራ ሰው!... በተሰጠኝ የሰውነት ክፍል ሁሉ ተጠቅሜ ከቦርጆ
ወቀሳ ለመዳን ባህሉ ተጠየቀኝ ለዓላማዬ ስል እኔም የእባብንም
አንገት አንቄ ጥርሶቹን ላይ መርዛም ነው የሚባለውን እባብ ጥቅምና
ጉዳቱን ጉሮሮውን ፈልቅቄ ላይ ተገርፌ፥ አልቅሼ: ቧጥጬ ባህሌን ጥሼ ባህል ላሳውቅ ኮቶ!"

"ይእ!  መንደር እንሂድ ካርለቴ?"z

"ተይኝ!  ትንሽ ጊዜ ብቻዬን ተይኝ!  እሽ?"

"ይእ! እሽ " ኮቶ ሄደች ዝምታ ፀጥታ ህሊናን
እንዳይደነብር  እንደሚያረጋጋ ተከብቶች ከአባቷ ከመንደሯ…
ተምራለችና ሄደች
ካርለት ራሷን ከፈተችው... ወደ ራሷ ገባች ... የላላውን
አጠባበቀች የተወጠረውን አላላች የአበጠውን አፈረጠች የቆሸሸውን አፀዳች ካርለት እንደ አዳኝ ውሻ ዐይኗን ጠበብ አድርጋ ደልቲን አየችው አያያትም" ወደ ዳንሱም ልትጋብዘው አትችልም፤ ዳንሱ
እንደገና ተጋጋለ

"ይእ! ካርለቴ ነይ ጋብዥው የገረፈሽን?" ብላ ኮቶ ጠራቻት ወገባቸውን ተቃቀፉ ከዚያ በቄንጥ እንደ ፔንዱለም ፊትና ኋላ
ተወዛወዙና ሶሰት ጊዜ ዘለል: ወዝወዝ… ብለው ሾረው ሄደው ሁለት
ጎረምሶችን ጋበዙ"

የገረፋት ጎረምሳ ካርለት ስትጋብዘው እየሰገረ ሄዶ የካርለትን ጭኖች እንደ መሮ እየሰረሰረ ገብቶ: በእጆቹ ቀጭኑን ወገቧን
ጨምድዶ አሻት ጎረምሳው ሳያቋርጥ እየሰረሰራት ጭኖችዋን በስቶ
ገባ "የት ሊደርስ ነው?" እያለች ሸሸችው እሱ ግን
ወገቧን የጨመደደበትን እጁን እየወጠረ ሲጠጋት ቆየና ከገለዋ ተጣበቀ
የሚታሸው አካሏ የአምቦ ውሃ እንደጠጣ ሰው አስገሳት እሷም
ሰረሰረችው፥ ወዘወዘችው.

ካርለት ያላየች መስላ ደልቲን አየችው ደስ ብሎታል እሷም ደስ አላት ደልቲ አልቀናም ቅናት ባህል እንጂ ተፈጥሯዊ
እንዳልሆነ አሰበች ጭፈራው ቀጠለ ጨዋታው ደመቀ።

"ኮቶ!"

"ዬ ሳቀች ከትከት ብላ ቀጣዩ ዳንስ እስኪጀመር
ቦታቸው ሲመለሱ

"ምን ሆንሽ ካርለቴ?" አለቻት

ሃሣቧን ሳትጨርስው  ደልቲ እጅዋን ያዝ አድርጎ
ከሴቶች መሐል ጠራት የሆነ ነገር እንደ ፍላፃ ተወርውሮ ስሜቷን
አጋጋለው" ፈገግ አለችለት ለስሜቷ-ለደልቲ…

ከዚያ በኋላ ብዙ አልተነጋገሩም ቀስ ቀስ እያሉ ፈንጠር ፈንጠር ብለው ጨረቃን አሹፈውባት ሰማይ ይግቡ መሬት ጠፉ….የኢቫንጋዲ ጭፈራው ግን ቀጥሏል ወደፊትም ለቀናት: ለዓመታት ይቀጥል ይሆናል ከዚያ ግን ይሸነቆራል
ወይንም ለዘመናት
ጥቅም፥ ገንዘብ‥ የተባለው ቆሻሻ ስልክልክ ብሎ ገብቶ ይበክለዋል ደስታም ጥቁር ከል ለብሳ: ተስፋ ቆርጣ: መባዘኗን ትጀምራለች
ካልያም አንድዬ አንች ከርታታ ተዛሬ ጀምሮ መባዘንሽ ያቆማል'
ብሎ ይጠራታል… እግዚኦ ያች ቀን ምናለ ባትደርስ! እግዚኦ!…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ቀትር ነው፤ የፀሐይዋ ሙቀት አሸዋው ላይ ነጥሮ እንደ ሐይቅ
ማዕበል እየተንቀሳቀሰ ከርቀት ጀምሮ ይታያል በዚያ አይነቱ ሐሩር የዛፍ ጥላ ህይወት አዳኝ ነው" የሐመር ወንዶች በእንዲህ ዓይነቱ ሙቀት ወቅት ዛፍ ጥላ ሥር ይሄዱና ሲጫወቱ: ሲወያዩ
ቆይተው አሸዋውን ይደለድሉና በበርኮታቸው ጭንቅላታቸውን ደገፍ
አድርገው እረፍት መውሰድ የተለመደ ነው

የሐመር ህይወት የሆነው ከስኬ ወንዝ ከጥም አርኪነቱ ሌላ ከለላ ችግርን መፍቻ በከብት ዝላይ ወቅት የልጃገረዶች መገረፊያ
መጋጌጫ… ማረፊያ ነው ለሰውም ለከብቱም ጫርጫር ሲደረግ ውስጡ ውኃ ይፈልቃል ላዩ መኝታ ይሆናል መወያያ መድረክም  ነው ሐመሮች የከስኬ ናቸው ከስኬም የነሱ ነው ያጌጡበታል
👍25🔥1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
.እንሂድ ወዳላት ቦታ ለመሄድ ብዙም ደስተኛ እንዳልሆነች በመገመት‹‹አዎ ምነው…?አባቴ እዛ ነው የሚኖረው ..በየሳምንቱ በዚህን ሰአት ይጠብቀኛል..ባይሆን ከዛ መልስ አንቺ የፈለግሽው ቦታ እንሄዳለን፡፡›አላት፡፡
‹‹አረ ችግር የለውም..እንዲሁ ያልጠበቅኩት ቦታ ስለሆነ ነው››ብላ በምትሄድበት ቦታ እንዳልተከፋች ተናገረች…እውነታው ግን እንደዛ አልነበረም፡፡
ከዛ በመሀላቸው ዝምታ ሰፈነ›…የሆነ ነገር ይናገራል ብላ ብትጠብቅም ለረጂም ደቂቃ ዝም አለ፡፡እሱ በጥልቀት ስለእሷ እያሰበ ነው…እሷ ከጠበቀችውና ከምታውቃቸው ወንዶች ሁሉ የተለየ ሆኖ እንዳገኘችውና በዛም እየተደመመችበት ሁሉ አሱም እጅግ ገራሚ ሴት ሆና አግቷታል…..የሌብነት ታሪኳ ግራ አጋብቶት ሳያበቃ አሁን መኝታ ቤቱ ገብታ የሰራችው ስራ ከግምቱ ውጭ ነው የሆነበት ‹‹ይህቺ ልጅ በህይወቴ የተከሰተችው በድንገgትና በአጋጣሚ ነው ወይስ ሆነ ተልዕኮ ኖራት አቅዳና አልማ?››ሲል እራሱን ጠየቀ..ቃል የተመረቀው በኮምፒተር ኢንጂነሪንግ ነው፡፡በስራው በጣም የተመሰገነ እና ፕሮፌሽናል ባለሞያ ነው፡፡ስልኩ ላይ አንድ እራሱ የሰራው አፕ አለ..ባለበት በ10 ሜትር ያለ ካሜራ መኖሩን ምልክት የሚሰጥ አፕ ነው…ለረጅም ጊዜ የለፋበትና ሚኮራበት ስራው ነው…ከስድስት ወራ በላይ ሙከራ ላይ የቆየና መቶ ፐርሰንት ሙከራውን አልፎ አሁን ለሽያጭ ሊያቀርበው ድርድር ላይ ይገኛል፡፡እና ልዩ መኝታ ቤቱ ከገባችበት ከደቂቃዎች በኃላ ይሄ አፕ ካንቀላፋበት ነቅቶ ድምፅ ሲያሰማው ማመን አቅቶት ክፉኛ የደነገጠው ለዛ ነው፡እዛ እሱ ቤትም ሆነ በጊቢው ምንም አይነት የካሜራ ዘር አንደሌለ እና ኖሮም እንደማያውቅ እርግጠኛ ነው፡፡ለማንኛውም ወደቤቱ ሲመለስ ያረጋግጣል .ለምን አለማ እንዳስቀመጠችውና እሱስ ምን እንደሚያደረግ ያስብበታል.
‹‹ምነው ዝም አልክ ፈራህ እንዴ ?››ስትለው ነበር ከሀሳቡ የባነነው፡
‹‹ለምንድነው የምፈራው?››
‹‹አይ…ምን አልባት የተሰረቀ  መኪና ውስጥ ያስገባሁህ መስሎህ …እንዳልታሰር ብለህ ፈርተህ እንደይሆን ?››
የማሪያምን ብቅል የበላ ይለፈልፋል ነው የሚባለው አይደል..የራሷ ክፉ ስራ ደጋግሞ ያስለፈልፋት ጀመር.
‹‹በፍፅም እንደዛ አላሰብኩም….››አለ ፍርጥም ብሎ፡
‹‹ብታስብም እኮ በቂ ምክንያት አለህ..ግን ማረጋግጥልህ መኪናዋ የራሴው ነች .. ማለቴ የእኔ እንኳን አይደለችም የእናቴ ነች፡፡››
‹‹ገባኝ….››
‹‹ግን ትገርማለህ…እንዴት ነው ስሜትህን እንደዚህ ማመቅ የምትችለው?›› አለችው፡፡
‹‹እኔ ስሜቴን ማመቅ..?እንዴት እንዳዛ ልትይ ቻልሽ…?››አላት በውስጡ‹‹እኔም በአንቺ ሚስጥራዊ ደርጊቶች ተገርሜያለሁ››ሲል አሰበ
‹‹እኔን በተመለከተ እስከአሁን ያየሀቸው ነገሮች ድርጊቶቼ  የተለመዱ እና ዝም ብለህ የምታልፋቸው ናቸው ማለት  ነው…? ምንም አያስደንቁህም…? የማወቅ ጉጉትህን አይቀሰቅሱም..? እና ምንም ጥያቄ የለህም….?››
‹‹ስለአንቺ  በጥልቀት  ለማወቅ ሁኔታዎችን እየገመገምኩ ነው..ማለት እንዳልሽው ከድርጊቶችሸ በፍቃድሽ ከምታደረጊያቸው ነገሮች በመነሳትና   እነሱን በመገጣጠም…ግን ጥያቄ ልጠይቅሸ አለሰብኩም.. ማለት ምንም ጥያቄ የለኝም››እውነቱን ነገራት፡፡
‹‹ማለት ጥያቄ ካልጠየቅከኝ እንዴት ታውቀኛለህ?››
‹‹ጥያቄ በመጠየቅ የሆነ ስውን በጥልቀት መረዳት እኮ አድከሚው መንገድ ነው…አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽ ለዛ መልስ ትሰጪኛለሽ…ግን ደግሞ መልስሽ ውስጥ ተደብቀው የሚወለዱ ሌሎች ጥያቄዎች ይፈልቃሉ…. መልስ ጥያቄ ..መልስ… ነገሩ ሁሉ  አዙሪት ነው የሚሆነው…..››አለ….ወደቤቱ ሲመለስ ሰለሚጠብቀው እሱን ለመሰል ስለተደበቀ ካሜራ እያሰበ፡፡
‹‹እሺ እራሴ እየጠቅኩ እራሴ ልመልስ..?›››
ዝም አላት.እሷ ማውራቷን ቀጠለች፡፡
‹‹ለምን ሌባ ሆንኩ…?መስረቅ ስለሚያስደስተኝ  ወይ  የመስረቅ በሽታ ስላለብኝ…መልሱ ሁለተኛው ነው፡፡የስርቆት በሽታ አለብኝ፡፡አስቂኝ ነው አይደል?፡፡ግን በሚገርም ሁኔታ  ይሄን በሽታ ደበሪ ነው፡ አወቃላሁ ደባሪነቱ የሚገለፅልኝ ግን  ካደረኩት በኃላ ነው ፤እንደ መጠጥ ወይም ሲጋራ ሱስ በለው..አንድ የሀሺሽ ሱሰኛ ፊት ለፊቱ ሀሺሽ ሲያይ እንደሚያቅበጠብጠው ሁሉ እኔም የሚሰረቅ ነገር በአቅራቢያዬ ካለ እንደዛ ነው ሚያደርገኝ፡፡ ምንም ያህል ብጥር እራሴን ወደኃላ መግታት አልችልም፡ ሆን ብዬ እኮ አይደለም ማለቴ እቅድ ወጥቼ ልስረቅ ብዬ በፍፅም ሰርቄ አላውቅም፡፡ የማደርጋቸው ነገሮች በሁኔታዎች ውስጥ ነው የሚከሰቱት፡፡ለምሳሌ ፀጉር ቤት ፀጉሬን ለመሰራት ሄጄ ተሰርቼ ከጨረስኩ በኃላ  ሂሳብ 200 ብር ከሆነ ሀምሳ ብር ጨምሬበት 250 ብር ከፍልን ባለሞያዎ ስትፍነከነክ አዘናግቼ የ25 ብር ማበጠሪያ ሰርቄ ቦርሳዬ ውስጥ ደብቄ ወጣለሁ፡፡››
‹‹እንደዛ ካደረግሽ በኃላ ምን ይሰማሻል?›ሲል የትዝብት ሳይሆን የሀዘኔታ በሆነ ድምፅ ጠየቃት፡፡ንግግሯን ከስሜቷ ጋር አንድ ላይ አጣምሮ ሲመዝነው ምንም አይነት ውሸት የሚመስል ነገር ሊያገኝበት አልቻለም…
እሷ ቀጠለች‹‹በወቅቱማ  አሷ ዞር እስክትል መጠበቁ…. .ማዘናጋቱ …ሌሎች ተስተናጋጆች እንዳያዩኝ መጠንቁ ከዛ ፐርፌክት በሆነ ታይሚንግ ማበጠሪያውን ባርሳዬ ውሰጥ ከትቼ ምንም እንዳልተፈጠረ በፈገግታ ሁሉንም ተሰናብቼ መውጣቱ በጣም ደስ የሚል እርከታ ነው የሚሰጠኝ..ችግሩ አካባቢውን ለቅቄ ትንሽ ራቅ ካልኩ በኃላ ነው.፡፡
ስሜቴ ሁኑ በአንዴ ዘጭ ይላል፡፡.ለምንድነው እንዲህ ያደረኩት.?አሁን ይሄ ማበጠሪያ ምን ይረባኛል..?ብያዝስ ምንድነበር የምለው.?እኚህንና ሌሎች መሰል ጥቄዎችን እየጠየቅኩ በጣም አዝናለሁ፡፡ አንዳንዴም ስቀስቅ ብዬ አለቅሳለሁ፡፡ .እራሴን እጠየፋለሁ፡፡ ለምሳሌ እንዳልኩህ የሰረቅኩት ማበጠሪያ ከሆነ ፀጉሯ የተንጨፈረረ የጎዳና ለማኝ ፈልግና የመኪናዬን መሰኮት ዝቅ አድርጌ ወረውርላታለሁ….ካልሆነም ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ እጥለዋለሁ…ስልክ ከሆነ ደግሞ  ብዙውን ጊዜ መልሰው ስለሚደውሉ የሆነ ቦታ አስቀምጥላቸዋለሁ.ሄደው ይወስዳሉ.. አንዳንዱ ደግሞ  ሊሳደብ ሲፎክር እልክ ይይዘኝና ዝም ብዬ ለአንዱ የሰፈር ጎረመሳ ሸልመዋለሁ...ብቻ አንድም ቀን የሰረቅኩት ነገር ትንሽ እንኳን አጓጉቶኝ ተጠቅሜበት አላውቅም…. ምክንያም ምሰርቃቸው ነገሮች ሁለ ቤቴን ያጨናንቁ ተራ ቁሶች ናቸው.ቢሆንም ግን እቃዎቹን አለመጠቀሜ እኔን ንፁህና ስራዬንም ልክ አያደርገውም፡፡...ያው ሰርቃለሁ ማለት ሌባ ነኝ..ሌላ ምንም ማስተባበያ ሊሰጥበት የሚችል ጉዳይ አይደለም…፡፡
‹‹ግን ተይዘሽ አታውቂም.?››
‹‹አንድ አራቴ››
‹‹ታዲያ እንዴት ተወጣሽው.?››
‹‹ሶስቱን ከተሰራቂዎቹ ጋር ተደራድሬ ብር ሰጥቼያቸው ለቁኝ፣አንዱ ግን ፖሊስ ጣቢያ ወስዶ አንድ ቀን አሳደረኝ፡፡›
‹‹እንዴት ?ልትደራደሪው አልቻልሽም ነበር?››
‹‹እንደውም መስረቄ ሳይሆን ለመደራደር ሞከሬ ነበር ይበልጥ ያበሳጨው... ሰውዬው ለካ ፖሊስ ነበር››
‹‹‹በተሰቀለው..ታዲያ በመጨረሻ እንዴት ሆንሸ?›
👍10711🔥2🥰2👏2👎1😱1
#ህያብ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በኤርሚ



#ከጊዜያት_በኋላ

"ንገሪኝ እስኪ ህያብ ሀኪም እንዲያይሽ ባትፈልጊም ህመምሽን ለኔ ንገሪኝ ዝምምም ብዬ እሰማሻለሁ። ስለ ልጅሽ ስለ ዮኒ ስለተፈጠረው ሁሉንም ንገሪኝ" ሶስት ወራትን በዝምታ ስለዚህ ነገር ሳያነሳብኝ ሳላወራው በየጊዜው የአእምሮ ህመሜ እየተነሳ ከኔው እኩል ሲሰቃይ አሳልፈናል። ትዕግስቱ እንክብካቤው ፍቅሩ ድሮ ከማውቀው የበለጠ ተወዳጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ግን ምን ዋጋ አለው ፍቅር አንዳንዴ ፍትሀዊ አይደለም ቢሆንማ ኖሮ የማፈቅረው ዮኒን ሳይሆን ቢኒን ነበር። ወደ መኝታ ቤት ሄድኩ... ተከተለኝ... በሩን ከፍቼ ገባሁና ቤቴ ሄደን ካመጣናቸው እቃዎች መሀል አነስተኛውን ሻንጣዬን አወረድኩት... ከፈትኩት... ውስጡ ያለው ሁሉም የልጄ ማስታወሻ ነው። ለአዲስ አመት የሳለችልኝን አበባ አገኘሁት... እሱን አቅፌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ

"የኔ ልጅ... የኔ እንቁ... ናፈቅሽኝ እኮ" ቢኒ አጠገቤ ብርክክ ብሎ ትከሻዬን ያዘኝ ከዛም ወደራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ። ህመሜ ሳይነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሴን አረጋጋሁና ከእቅፉ ወጥቼ ከመፅሀፍ መሀል አጣጥፌ ያስቀመጥኩትን ደብዳቤ አወጣሁት... ከባዱን መርዶ ያረዳኝን... መራራውን እውነታ የጋተኝን ደብዳቤ አወጣሁና ለቢኒ ሰጠሁት። ግራ በተጋባ ፊት ካየኝ በኋላ ከፈተው... ደጋግሜ ከማንበቤ የተነሳ እያንዳንዱን ቃል እንደ ውዳሴ ማርያም የሸመደድኩትን ደብዳቤ እሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያነበው ከፈተው... እንዲህ ነው የሚለው...

"ማሚ ከበደል ሁሉ የቱ እንደሚከፋ ታውቂያለሽ... አባቴ የምትይው ሰው በስሜት ጦዞ ጭንሽን ሊከፍት ሲታገል ማየቱ...... ማም እውነቱ ይገልሻል አውቃለሁ ...ግን እንደዛ ጠንካራ ስነ ልቦና እንዲኖራት አድርገሽ ያሳደግሻት ልጅሽ ለምን ራሷን አጠፋች? የሚለው ጥያቄም ይገልሻል። ማም እውነቱን እወቂው..... መጀመሪያ የውሸት ቆይቶ ደግሞ የእውነት አባት የሆነኝ ዮኒ የውሸት አባቴ እያለ አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ደፍሮኛል። ታስታውሻለሽ ያኔ ፔሬድ አሞኝ ነው ብዬሽ የተኛሁ ጊዜ... ለመጀመሪያ ጊዜ የደፈረኝ ቀን ነበር። አንቺ ውስጥ እያለሽ ሊጠይቀኝ ሲመጣ ፊቴን አዙሬበት ነበር አይደል? ከዛ አንቺ ወጣሽ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ 'በሶስተኛው ቀን መድገም አለብን ካላዛ ተደፍነሽ ትቀሪያለሽ' አለኝ። እናም በሶስተኛው ቀን መኝታ ቤቴ ድረስ መጣ... መከላከል ደከመኝ እና በዝምታ አየሁት ሳይራራልኝ እላዬ ላይ ጨፍሮ ሄደ... ያንኑ ድርጊቱን የአባትነት እውነታው እስከሚታወቅ ድረስ ደጋገመው። በተለይ ፊልድ መውጣትሽ ለሱ ምቹ ሁኔታ ለኔ ደግሞ ስቃይን ፈጠረ

ካንቺ ፊት ላይ የየሁትን ደስታ እኔ ጋር ፈልጌ አጣሁት። ማም እንዴት ልደሰት... አባቴን አገኘሁ ብዬ እንዴት ደስ ይበለኝ...? አባትነቱን እኮ ጭኔ መሀል ቆፍሮ ቀብሮታል። እናም አባቴ አይደለም ሊሆንም አይችልም ብዬ በዝምታ ተሸብቤ ቁጭ ብዬ እያለ ሌላ ክስተት ተፈጠረ። በየጊዜው እየመጣ ይቅርታ ብሎኝ 'አደራ ለናትሽ እንዳትነግሪያት' ከሚለኝ ከህሊናቢሱ አባቴ የስምንት ሳምንት ነብሰ ጡር እንደሆንኩ ሆስፒታል አረጋገጥኩ። ያኔ በራሴ ላይ ወሰንኩ... ታሪክ ራሱን አይደግምም... ማም አንቺ አባት እንደሌለኝ እያሰብሽ ወልደሽ እሳደግሺኝ... የኔ ልጅ አባት ግን አባቴ ነው... እናም በራሴ ላይ እና ባልወለድኩት የአባቴ ልጅ ላይ የሞት ፍርድ ወሰንኩ።

ማሚዬ ለኔ ስትይ ጠንክረሽ ኑሪ እወድሻለሁ።
እድለቢሷ ልጅሽ"

ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ ቢቆይም እንባ ከአይኖቹ እየወረደ ፍዝዝ ብሎ ተቀምጧል።

"ይህን ደብዳቤ ሳገኘው ቢኒ ጊዜው ረፍዷል... የልጄ ገዳይ አጠገቤ አልነበረም... ትቶኝ ሄዶ ነበር... ፈለኩት በየሆስፒታሉ በየሆቴሉ ግን አጣሁት... ባገኘው በአደባባይ ስጋውም ዘልዝዬ ለአሞራ እሰጠው ነበር"። እያለቀሰ መጥቶ አቀፈኝ ረጅም ሰአት ተቃቅፈን ተላቀስን...።

"እባክሽ አንድ ነገር እሺ በይኝ የስነልቦና ሀኪም ይይሽ እባክሽ ለኔ ስትይ" ለብዙ ጊዜ ደጋግሞ ቢጨቀጭቀኝም እምቢ ነበር መልሴ

"እሺ ደስ ያለህ ሀኪም ጋ ውሰደኝ"

።።።።። ።።።።። ።።።። ።።።።። ።።።

የስነ ልቦና ህክምናዬን ከጀመርኩ አንድ ሳምንት ቢያልፈኝም ለዶክተሬ ምንም የነገርኩት ነገር አልነበረም። የሆነ ቀን ግን ልክ ከዚህ በፊት ያለውን ታሪክ እንደሚያውቀው ሁሉ

"ዮኒን ብቻ ጥፋተኛ አድርጌ እንዳልፈርድ የሚያደርገኝ እንደዚህ ያሳመመኝ ብዙ ፀፀት ውስጤ አለ። ብዙ ቢሆን ኖሮ.... ብዙ.... ብዙ....

•ከመጀመሪያው ታሪኬን ነግሬው ቢሆን ኖሮ

•ስራ ስራ ማለቴን ትቼ ለልጄ ጊዜ ሰጥቻት ቢሆን ኖሮ

•እንደዛ ሆና እያየኋት ትንሽ እንኳን ለምን አልተጠራጠርኩም... አሁን እኔ ዶክተር እባላለሁ...

ከሁሉም በላይ ፀፀቱ በልቶ ጨረሰኝ... መገጣጠሚያ አጥንቴ እስከሚታይ ከሳሁ... ጠቆርኩ... ታመምኩ... አበድኩ ...ግን ትርጉም አልነበረውም... እኝህ ሁሉ የኔን እንቁ አይመልሱልኝም ባዶ... አንተስ የኔን እንቁ ትመልስልኛለህ? አየህ እዚህ መጥቼ መፋጠጣችንም ትርጉም የለውም ባዶ..." አልኩት። ዝምምም ብሎ ካየኝ በኋላ ከወንበሩ ተነስቶ መጥቶ ፊት ለፊቴ ሶፋ ላይ ተቀመጠ

ከስድስት ወራት ያላሰለሰ የህክምና ክትትል በኋላ ወደራሴ ተመለስኩ ወደ ስራየም ጭምር። ከቢኒ ጋር ደስ የሚል የፍቅር ግንኙነት ጀመርኩ... ህይወት ድጋሚ ቀጠለች። ያለፈው ባይረሳም ህመሙ ቀንሷል... የልቤ በልቤ ተቀብሮ መሳቅ ቻልኩ።

ከቢኒ ጋ ልንጋባ ነው ማለትም ከሁለት ወር በኋላ እንጋባለን። ለፊርማው እንጂ የምንኖረው አንድ ቤት የምንተኛው አንድ አልጋ ላይ ከተጋባን ቆይተናል ለማለት ነው። ልንጋባ መሆኑን ያወቀው ሀብታሙ ካለበት ሀገረ አሜሪካ የሚያምር ቬሎና ሱፍ ልኮልናል። ለቢኒ ሚዜ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ።

የሆነኛው ሌሊት ላይ ተኝቼ ልጄን በህልሜ አየኋት... ብቻዋን አይደለም ዮኒ ሲደፍራት "ድረሽልኝ" እያለች ስትጮህ... ጮኬ ከእንቅልፌ ነቃሁ... አጠገቤ የተኛው ቢኒ ጩኸቴ አስደንግጦት

"ምንድነው ፍቅር አይዞሽ ቅዠት ነው" አለና እቅፉ ውስት ከተተኝ... እኔ ግን የበቀል ጥሜ ድጋሚ አንሰራራ... እፈልገዋለሁ እናም እገለዋለሁ... እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።

ለቀናት በሀሳብ ተብሰከሰኩ እናም ወሰንኩ ይህን ነገር ከስሩ መንግዬ መጣል ይኖርብኛል። ተቆርጦ ባቆጠቆጠ ቁጥር ህመሙ እየባሰ ነው የሚሄደው ስለዚህ እ ገ ለ ዋ ለ ው

#አሁን

ትቼው ልሄድ ነው። በቃ ልሄድ ነው የመጨረሻ ውሳኔዬን ወስኛለሁ የምሄደው እንደ ሌላው ጊዜ ጥላቻንና ክህደትን ሽሽት አይደለም... ፍቅርን እንጂ።
እናም በሀሳብ እየዋዠኩ ደብዳቤ ልፅፍለት ወሰንኩ ቢያንስ ምክንያቴን ማሳወቅ አለብኝ አይደል... ደግሞ ጠፋች ብሎ ሀገር ምድሩን ነው የሚያምሰው...

መፃፍ ጀመርኩ

"አንዳንዴ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ይሆንብኛል። ፍቅርህ፣ ስስትህ፣ እንክብካቤህ፣ አንተን ትተህ ለኔ ደስታ መድከምህ፣ ከቃላት ጋጋታ ይልቅ በተግባር የምታሳየኝ መውደድህ በአጠቃላይ ሁሉም ነገርህን መቋቋም ያቅተኛል።
👍7414🔥2😁1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ያ ማለት ታዲያ ኬድሮን ሁሌ መልካም ስራና የሚያስመርቅ ተግባር ብቻ ትሰራለች ማለት አይደለም፡፡ሲመጣባትና በተለይ እንድትበሳጭ ካደረጓት ሰይጣን እንኳን ሊያስበው የማይችል ክፉ ስራና አስደናጋጨ ተንኮል ባለቤት ነች፡፡

የእሷ እኩዮች ሆኑ በዕድሜም ሆነ በአካል ዘለግ የሚሉ ልጆች ጋር ተጣልታ እጇን ሰንዝራ በጥፊ ከመታቻቸው የሆነ ነገራቸው ለሳምንት ይጣመማል…በዛ የተነሳ የማንኛውም ወላጅ ቀዳሚ ምክር ‹‹እባካቹ ከዛች ግማሽ ጋንኤል ከሆነች ልጅ  ጋር አትጋጩ›› የሚል ነው፡፡ትልልቅ ሰዎችንም ካበሳጯት የሆነ ነገር አድርጋ ሳትበቀላቸው በምህረት የምታለፈው ነገር አይኖራትም፡፡ ስትበሳጭ የሰውነቷ የቆዳ ቀለምና ከአይኖቾ የሚፈልቁት ብርሀን የተለዩና አስፈሪ ይሆናሉ፡፡
10   አመቷ ላይ ነው፡፡ከምሸቱ 12 ሰዓት አካባቢ ከብቶቾን ከፊት እየነዳች ወደ ሰፈር እንደደረሰች ወደ ቤታቸው መጠምዘዣ  ኩርባ ላይ  ባለ አንድ የግንድ ጉማጅ ላይ አንድ ልጅ ተቀምጦ አንገቱን አቀርቅሮ እንባውን ወደምድር ያንጠባጥባል…ልጁ በዕድሜ በሁለት አመት ቢበልጣትም ጓደኛዋና የሰፈሯ ልጅ  ነው፡፡ድባለ  ይባላል፡፡ገና ከሩቅ እንዳየችው ነው ሰላም እንዳልሆነ የተረዳችው… በእጇ አንጣልጥላ የያዘቻቸውን አምስት የሚሆኑ አንድ ላይ የታሰሩ አሳዎችን እያማታች ከብቶቹን ወደቤታቸው እንዲገቡ መንገዱን አስያዛቻቸው ወደ እሱ አመራች..ደርሳ  ከጎኑ ተቀመጠች፡፡እና ሳታስበው እንባ አውጥታ አብራው ማልቀስ ጀመረች..ገልመጥ ብሎ አያትና

‹‹አንቺ ደግሞ ምን ሆነሽ ነው?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ምንም አልሆንኩ ላግዝህ ብዬ ነው››

‹‹ምን ማለት ነው… በለቅሶ ማገዝ አለ እንዴ?››

‹‹ታዲያ በምን ላግዝህ?

‹‹በምንም .. ማንም ሊያግዘኝ አይችልም…››

‹‹እሺ ምን እንደሆንከ ንገረኝ?››

‹ምን ያደርግልሻል፤እዚህ እየጠበቅኩ ያለሁት አንቺ እስክትመጪ ነበር…ነገ ወይም ተነገወዲያ ልንሄድ ነው…..ጓደኛዬ ስለሆንሽ ልሰናበትሽ ነው›

ደንግጣ..‹‹እንዴ ወዴየት ነው ምትሄደው?››

‹‹ጊንር አካባቢ ወደሚገኝ ገጠር …አያቶቼ ጋር››

‹‹ለምን? ትምህርትስ?››

‹‹እኔም ወንድሞቼም አቋርጠን ነው የምንሄደው››

‹‹ቤተሰቡ ጠቅላላ ነው የሚሄደው እንዴ?››

‹‹አዎ… ከአባቴ በስተቀር…››

‹‹ከአባቴ በስተቀር ማለት ? አባትህስ ለምን?››

‹‹እሱ ሌላ ሚስት እዚህ አግብቷል…ጥሎን ከቤት ከወጣ ብዙ ቀን ሆነው ..ብንጠብቀው ብንጠብቀው ሊመጣ አልቻለም…እናቴ እናንተን የማኖርበት ገንዘብ የለኝም..ስራም ማግኘት ስለማልችል.ወደ ቤተሰቦቼ ይዣችሁ እሄዳለሁ ›› አለችኝ፡

‹‹እና በጣም አዝነሀል?›

‹‹በጣም እንጂ ..እኔ እዛ ገጠር ክረምት  ቤት ሲዘጋ ለተወሰነ ጊዜ መሄድ ነው ደስ የሚለኘ እንጂ ሁሌ እዛ መኖር አልፈልግም..እኔ እዚህ መኖር ነው የምፈልገው..አንቺ ትናፍቂኛለሽ›አላት እየነፈረቀ…፡፡

‹‹አንቺ ትንፋቂኛለሽ›› ሲላት ትኩር ብላ አይኖቹን አየቻቸው… ሀዘኑን ከውስጡ ማንበብ ስለቻለች…ልትገልፀው የማትችለው ስሜት ተሰማት… ከተቀመጠችበት ግንድ መቀመጫ ዘላ በመውረድ..‹‹ና እንሂድ›› አለችው…፡፡

‹‹ወደ የት?››

‹‹ወደ እናንተ ቤት››

‹‹ምን እንሰራለን …በጣም እኮ ነው የሚደብረው ..እማዬ የቤት እቃዎቻችንን ለጎረቤት እየሸጠች ነው..ይዘን የምንሄደውን ደግሞ እያሳሰረች ነው…››

‹‹እዚህ መቅረት ምትፈልግ ከሆነ ተከተለኝ›› አለችውና እርምጃዋን ወደእነሱ ቤት አስተካክላ እርምጃዋን ቀጠለች...እያቅማማ ተከተላት... እንደደረሱ እውነትም እቤቱ በኮተታ ኮተት ተሞልቶ ተተረማምሶል .. ሁለት ወንድሞቹ በሀዘን ኩርምትምት ብለው በቤቱ አንድ ጥግ ከላ አግዳሚ ወንበር ላይ ሲቀመጡ… እናትዬው ፈንጠር ብላ ኩርሲ ላይ ተቀምጣ ትተክዛለች፡፡

ኬድሮን ዝም ብላ በራፉን አልፋ ወደ ውስጥ ገባችና ወደ ድብአለ  እናት ተጠጋች… በእጇ ያንጠለጠለችውን አምስት አሳዎች ዘረጋችላት፡፡ሴትዬዋ ግራ ገብቷት አንዴ አሳዎቹን አንዴ   ኬድሮንን እያየች ለደቂቃዎች ቆየች፡፡

‹‹ተቀበይኝና ለልጆችሽ ጥበሺላቸው…ደግሞ ድብአለ  ወደ ጊንር መሄድ ሰለማይፈልግ እኔ እንድትሄዱ አልፈቅድላችሁም››
የድባአለ  እናት ፊቷ የቆመችው የ10 አመት ልጅ ዝም ብላ ልጅ ብትሆን ኖሮ በዚህ ንግግሯ በጥፊ ጆሮ ግንዷን አቅልጣ ከቤቷ  ገፍትራ ታባርራት ነበር….አረ የ10 አመት ብቻ ሳይሆን አንድ የ19 ዓመት የጎረቤት ልጅ እንዲህ ብስጭትጭት ባለችበት ጊዜ በዚህ አይነት ድፍረት  እየተውረገረገች መጥታ አሁን እሷ ያለችውን ብትላት ጉሮሮዋን አንቃ ከልጆቾ ጋር በመተባበርም ቢሆን  ንዴቷን እንደምትወጣበት እርግጠኛ ነች….ኬድሮንን ግን እንደዛ ልተደፍራት አልፈለገችም ..አላደረገችውም፡፡

‹‹ኬድርዬ ያልገባሽ ነገር አለ፡፡››

‹‹አስረጂኛ..››

ምን ብላ ትንገራት…. አንዴ እሷን አንዴ ልጆቹን  እያየች ግራ ስትጋባ…ልክ ከእኩያው ጋር ሚስጥር ማውራት እንደፈለገ ትልቅ ሰው‹‹ልጆችሸን ከቤት አስወጪያቸው.. ምን ይሰራሉ?›› አለቻት ፡፡

‹‹ልጆች ተነሱ ውጨ ተጫወቱ አንዴ ላውራት››ትዕዛዞን ተቀብላ አስተላለፈች፡፡

ድባአለን  ጨምሮ የሰባት አመትና የ10 አመት  ወንድሞቹ  እቤቱን ለእናታቸውና ለኬድሮን ጥለው ወጡ የእናቷ እኩያ የሆነችውን ትልቋን ሴትዬ ፊት ለፊት እያየቻት፡ኬድሮን እነሱ በለቀቁበት ቦታ ተቀመጠችና‹እሺ ንገሪኝ ›አለቻት፡፡
ምን መሰለሽ ኬድርዬ…እዚህ ሀገር ይዞኝ የመጣው ባለቤቴ ነው…አሁን ደግሞ እሱ ከእኛ ጋር የለም ፤ስለዚህ እዚህ ሆኜ ደግሞ ልጆቼን ማስተዳደር አልችልም››

‹‹የድባአለ  አባት ለምን ጥሎሽ ሄደ?››

‹‹እንዴት ብዬ ልንገርሽ የትልቅ ሰው ጉዳይ ነው፡፡››

‹‹ሌላ ሴት ወሽሞ ጥሎኝ ሄደ ላለማለት አፍረሽ ነው..የትልቅ ሰው ወሬ ምትይው?››

ሴትዬዋ አንገቷን በእፍረት አቀረቀረችና‹አዎ ምን ታርጊዋለሽ ..እኔ ልጆቼንና ትዳሬን እያልኩ ጉስቁል አልኩበትና  ጠላኝ መሰለኝ ሌላ ወዶ ሄደ››

‹‹ግን ብዙ ጊዜ ስትጨቀጭቂውና ስታበሳጪው አይቼለሁ››

‹‹ብጨቀጭቀውስ ለኑሮችን መሻሻል ብዬ ነው…እንዲህ ከሶስት ልጆቹ ጋር እርግፍ አድርጎ ጥሎኝ ይሄዳል፡፡15 ዓመት በትዳር ማሳለፍ እንዲህ ቀልድ ነው…?››

‹‹እኔ እንዲመለስ አደርጋለሁ…አንቺ ግን ፀባይሽን ታስተካክያለሽ… እርምጥምጥ የምትይውን ነገርም ታስተካክልሽ›› 

‹‹አይ ያከተመ ነገር እኮ ነው… እሺ አይልሽም እኔም ደግሞ እቃዎቼን ሁሉ እኮ ግማሹን ሸጬያለሁ፡፡››
እሱን ለእኔ ተይልኝ…እንቺ ወይም ባልሽ አሳዝናችሁኝ አይደለም… ለጓደኛዬ ለድብአለ  ብዬ ነው…
ብዙም ሳይመሳላት ‹‹ካልሽ እሺ ሞክሪ ›አለቻት፡፡

ቀጥታ ወደቤቷ ሄዳ እናቷን ካገኘችና ከብቶቹ ወደበረትና በጎቹንም ወደጉሮኗቸው መግባታቸውን ካረጋገጠች በኃላ ልክ አንድ ሰዓት ከሩብ አካባቢ ሹልክ ብላ ድብአለ  አባት ገብቶበታል ወደተባለው ቤት ነው ያመራችው…ስትሄድ ምን እንደምታደርግና እንዴት አድርጋ ከአዲሷ ሚስቱ አለያይታ ወደቤቱ እንዲመለስ እንደምታሳምነው ወይም እንደምታስገድደው ምንም አይነት እቅድ አልነበራትም፡፡
👍1019👏1
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ለሁለት ወራት ድምፅዋን አልሠማም፡፡ አልደወለችለትም፡፡ ምንም አይነት አዲስ ጽሁፍም አላከችለትም፡፡ እሷ ልታገኘው ካልፈለገች እሱ ሊያገኛት የሚችልበት ምንም መንገድ የለውም፡፡ ይሄ ሁኔታ ሁሴንን እጅግ ሲያስጨንቀውና ሲያበሳጨው ነው የከረመው፡፡ ዛሬ ግን በሀሳብ የሚያባክነው ጊዜ አላገኘም፤ውጥረት ላይ ነው ያለው፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ በዋቤ ሸበሌ ሆቴል የሚስጥር የግጥምና የአጫጭር ልብ ወለድ መጽሐፍ ይመረቃል፡፡

ሁሴን፣ሠሎሞን እና ትዕንግርት ነገሮችን ሁሉ በታቀደላቸው ዕቅድ መሠረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከወዲህ ወዲያ ይሯሯጣሉ፡፡

‹‹አሁን ምን ቀረ?›› ሠሎሞን ነው የጠየቀው፡፡

‹‹ምንም ... የእንግዶቹ መምጣት ብቻ..፡፡›› ሁሴን መለሰ፡፡

‹‹የሚዲያ ሠዎችስ .. ያረፍዱ ይሆን?›

‹‹ኧረ ደርሰዋል...ሆቴል ሻይ ቡና እያሉ ናቸው፡፡››

‹‹በትክክልም መድረስ አለባቸው፡፡ ይሄን የመሠለ ግራ የገባው ታሪክ ለመዘገብ የማይጓጓ የወሬ ሠው የት ይገኛል ብለህ ነው?››ሰሎሞን ነው ተናጋሪው፡፡

‹‹እስቲ ዛሬ እንኳን ስድብህን ዋጠው፡፡›› አለው ሁሴን እንደመበሳጨት ብሎ

<እንዴ  ቁጭ ብላችሁ ታወራላችሁ እንዴ......? እንግዶች እኮ መምጣት ጀምረዋል፡፡ ውጭ ናቸው›› ትንግርት ነች በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ እየገባች የምታወራው፡፡

‹‹በቃ የቀረን ነገር የለም ... ዝግጅታችንን አጠናቀናል፡፡ ዘና የሚያደርጉን ሙዚቃኞች ከነ ሙዚቃ መሳሪያቸው መጥተዋል፡፡ ዝግጅቱን በንግግር የሚከፍቱልን የክብር እንግዳችን የደራሲን ማህበር ፕሬዘዳንትም በሠዓቱ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ሠጥተውናል፡፡
ለእድምተኞች ከመጽሐፍ በመቀንጨብ የሚያነቡ ሠዎችም ተመድበዋል፡፡ ያው እንደተነጋገርነው በመጀመሪያ አንቺ ታነቢያለሽ ሌላውን እኔ ጨምራለሁ፡፡ ይሄ ቀፈታም
ኢንጂነር እንደሆነ አይኖቹ ብር ላይ የሚገኝ ቁጥር እንጂ ፊደል ማንበብ ካቆሙ ዘመናት አልፈዋል፡፡ ስለዚህ የእሱ ኃላፊነት እንግዶች በስርዓት መስተናገዳቸውን መቆጣጠር ነው፡፡›› ንግግሩን ገታ አደረገና አይኖቹን ሠሎሞን ላይ ተክሎ ንግግሩን ቀጠለ ‹‹ደግሞ ዛሬ እንዴት ነው አለባበስህ? ሚስትህን ጥለህ ከቤት ስትኮበልል ወጣት የሆንክ መሰለህ
እንዴ?>>

‹‹ሰውዬ እንደውም ዛሬ ከዕድምተኞቹ ውስጥ አንዷን ምርጥ ካገኘሁ መጥበሴ አይቀርም፡፡›› አለው ሠሎሞን፡፡

‹‹ምን አልባት ከአስተናጋጆቹ መካከል ከሆነ እስማማለሁ፡፡ ዝግጅቱን ለመታደም ከሚመጡት ውስጥ ግን ላንተ ነፍስ የምትስማማ የምትኖር አይመስለኝም፡፡ ደራሲ ወይም ገጣሚ አፍቅረህ ልታብድ ነው...እስቲ በእኔ ይብቃ››ተሳሳቁ!!

‹‹ግን ዛሬም አትመጣም ማለት ነው?! >> ትንግርት ነበረች ጠያቂዋ፡፡ መልሱን ከሁሴን አንደበት ለመስማት በጉጉት ስሜት አይኖቿን እያቁለጨለጨች፡፡

‹‹በቃ ስለ እሷ እያወራችሁ ስሜቴን አታደፍርሱት፡፡ እንዲያውም ሠዓቱ ደርሷል በራፉን ክፈቱና እንግዶችን ወደ ውስጥ አስገቧቸው፡፡››

ሠሎሞን ተንደርድሮ በሩን ከፈተና ውጭ የተጠራቀሙትን እንግዶች ወደ ውስጥ እንዲገቡ ይጋብዛቸው ጀመር፡፡ ጋዜጠኞችም ከካሜራ ባለሞያቸው ጋር እየተንጋጉ ገቡ፡፡ በ3ዐ ደቂቃ ውስጥ ከተጠሩት ሠዎች
አብዛኞቹ ስለተገኙ ፕሮግራሙን ለማስጀመር ሁሴን ወደ መድረኩ ማይኩን በቀኝ እጁ የተወሰኑ ወረቀቶችንና በእለቱ ለምረቃ የተዘጋጀውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ በግራ እጁ ይዞ ወጣ፡፡መድረኩ ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ከሩቅ እንዲነበብ ታስቦ በባነር ላይ የተጻፈ ፅሁፍ ተለጥፏል፡፡ እንዲህ ይነበባል፡፡

የመፅሀፍ ምረቃ በዓል

የመፅሀፍ አይነት፦ የግጥምና አጫጭር ልቦለድ መድብል

ርዕስ፦ የጨረቃ ፍካት

ደራሲ፦ ምስጢር በለጠ

አሳታሚ፦ ፍካት ማተሚያ ቤት

የታተመበት ቀን፦ ሠኔ 2ዐ ቀን 2007 ዓ.ም.

ሁሴን ከአትሮኖሱ ጀርባ ቆሞ ጉሮሮውን ጠራረገና ንግግሩን ጀመረ፡፡ ከተለያዩ መጽሔት፣ ጋዜጣ፣ ሬዲዬና ቴሌቪዥን ጣቢያ የመጡ ጋዜጠኞች ካሜራቸውንና መቅረፀ ድምጻቸውን በዙሪያው ቀሠሩ፡፡

‹‹ክቡራንና ክብርት የጥበብ አፍቃሪዎች

በመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ ከጥበብ ማዕዱ ለመቋደስና የደስታችን ተካፋይ
ለመሆን እዚህ ስለተገኛችሁ በደራሲዋ እና በራሴ ስም የከበረ ምስጋናዬን ለማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡በማስከተልም ስለደራሲዋ
አንዳንድ ያልተለመዱ ነገሮች መናገር እፈልጋለሁ›› መጽሀፉን አነሳና ወደ ታዳሚው
በማሳየት ንግግሩን ቀጠለ፡፡

‹‹ይሄ መጽሐፍ
ሠባት አጫጭር ልብ ወለድ እና ሠላሳ የተመረጡ ግጥሞች የተካተቱበት ባለ ሁለት መቶ ሃያ ገጽ መጽሐፍ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል አራቱ አጭር ልብ ወለዶች እና ሃያ የሚሆኑት ግጥሞች በተለያየ ጊዜ በፍኖተ ጥበብ ጋዜጣ ላይ ለህትመት የበቁና በአንባቢ
ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙ ናቸው፡፡ለዚህም
የጋዜጣው አንባቢ የሆናችሁ መመስከር ትችላላችሁ፡፡ ሌሎቹ ግን በደራሲዋ የቀረቡ ከዚህ በፊት ያልተነቡ አዳዲሶች ናቸው፡፡

የመሸጫ ዋጋው ሰላሳ ሁለት ብር ነው፡፡ ዋጋው ካለው የወረቀት ውድነትና ይሄን ተከትሎ አሳታሚ ድርጅቶች ከሚጠይቁት ዋጋ አንፃር ተሠልቶ የተተመነ ስለሆነ ተመጣጣኝ ነው ብለን እናስባለን፤ ስለ መጽሐፉ ይሄን ያህል ካልኩ ስለ ደራሲዋ ደግሞ ጥቂት ነገር ማለት ያለብኝ ይመስለኛል፡፡ደራሲዋ አሁን በመሀከላችን... >> ንግግሩን አቋረጠና ወደ ውስጡ ትንፋሹን ደጋግሞ ሳበ፡፡ እንደ ማሳል አለና በተንቀረፈፈ ሁኔታ ንግግሩን ቀጠለ ፡፡

‹‹...አሁን በመሀከላችን የለችም፡፡ ማለቴ እዚህ ዝግጅት ላይ እንድትታደምና የድካሞን ውጤት፤ የዘራችውን ዘር ፍሬ እንድታጣጥም ማድረግ አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም በአካል አላውቃትም፤ መኖሪያ ቤቷን፣ ስልኳን፣ ፖስታ ሳጥን ቁጥሯን አላውቅም፡፡ ላውቅ ያልቻልኩትም እኔ ማወቅ ስላልፈለግኩ ሳይሆን እሷ እንዳውቅ ስላልፈለገች ነው፡፡››

ከእድምተኞች አካባቢ ጉምጉምታ በዛ፣ የጋዜጠኞች ጆሮ ይበልጥ ተቀሠረ፣ካሜራዎቻቸውን ከወዲያ ወዲህ በፍጥነት ማሽከርከር ቀጠሉ፡፡ ብዛት ያላቸው ሠዎች በተንቀሳቃሽ ሞባይል ስልካቸው ሳይቀር ንግግሩንም ሆነ የዝግጅቱን ድባብ በተቻላቸው መጠን በመቅረፅ ላይ ናቸው፡፡‹‹... ያው እንዳልኳችሁ ምስጢር ከሁለት ዓመት ለበለጠ ጊዜ የፍኖት ጥበብ ጋዜጣ ቋሚ አምደኛ ነች፡፡ ጽሁፎችን የምትልከው በፖስታ ቤት በኩል ሲሆን አድራሻዋን ግን አትፅፍም፡፡ ጽሁፎቿ በጣም ማራኪ ብስለት ያልተለያቸውና ዘና የማድረግ ደረጃቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ዛሬም ድረስ የእሷ አድናቂ እንድሆን ተገድጄያለሁ፡፡ በነገራችን ላይ በግል ስልኬም ትደውልልኛለች፤ እውነቴን ነው የምላችሁ መፃፍ ብቻም ሳይሆን ማውራትም ትችልበታለች፡፡ የምትጠቀመው ስልክ የሕዝብ ነው አንድ ቀን ከልደታ፣ በሌላ ሳምንት
ከመገናኛ፣ ሲያሰኛት ከሳሪስ አካባቢ ባለ የሕዝብ ስልክ ነው የምትደውልልኝ፡፡ ከምታስቡት በላይ ግራ አጋቢ የሆነች ፍጡር ነች፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ ላገኛት እንደምፈልግ ነግሬያት ብማፀናትም ጥያቄዬን ልትቀበል አልቻለችም፡፡

በመጨረሻ እሷን ከተደበቀችበት ጉድጓድ እንዴት አድርጌ ለማውጣት እችላለሁ? ብዬ ሳስብ የፃፈቻቸውን ፅሁፎች የማሳተም ሃሳብ በአዕምሮዬ ተሠነቀረና አማከርኳት፤ ነገሩ ግን እንደገመትኩት አልሆነም፡፡ ጽሁፎቿን የማሳተም ፍላጎት እንደሌላትና እኔ ማሳተም ከፈለኩ ግን እንደማትቃወመኝ እናም ውክልናውንም እንደምትሠጠኝ ነግራኝ ከዛ አልፎ ግን ከእኔ ጋር ለመገናኘት ለጊዜው ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት አረዳችኝ፡፡ እንዳለችውም ውክልናውን በፖስታ ቤት ላከችልኝ..
👍8710🥰1👏1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ማታ ቤት ገብታም ስለሴትዬዋ ማሰቧን አላቋረጠችም ነበር፡፡ ወንድ ብትሆን "ፍቅር ያዘኝ እንዴ?ብላ ራሷን መጠራጠር ትጀምር ነበር...ሴትዬዋ የማሳጅ ቤት ባለቤት መሆኗን ከቢዝነስ ካርዷ ብትረዳም ‹‹የፈለገችኝ ለሌላ ስራ ቢሆንስ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮዋ ብልጭ አለባት።

እንደምንም ራሷን   ተቆጣጠረችና አራት ቀን በመቆየት በአምስተኛው ቀን ደወለችላት፡፡

"ሳባ  እባላለሁ...በቀደም  ለታ  ቢዝነስ  ካርድሽን  ሰጥተሽኝ  ነበር..."ብላ.ቦታውንና ሁኔታውን ልትዘረዘርላት ስትጀምር አቋረጠቻት

"አውቄሻለሁ...ስለደወልሽ ደስ ብሎኛል..." የሚል መልስ ሰጠቻት
ትብለጥ፡

"አመሰግናለሁ"

"እሺ.ተገናኝተን.እናውራ፡

"ይቻላል"

"መቼ ይመችሻል?"

"ያው ያንቺን አላውቅም እንጂ እኔ ዛሬ እሁድ ስለሆነ  ይመቸኛል...ካልሆነ ግን በማንኛውም ቀን ከ11.30 በኃላ መሆን ይችላል።››

"ግድ የለም ይመቸኛል...ሰፈርሽ የት ነው፡፡"

"ላንቻ....ግሎባል አካባቢ፡፡"

‹‹በቃ ስምንት ሰዓት መኪና ልክልሻለሁ...ቁጥርሽን እሰጠዋለሁ… ይደውልልሻል።"
‹‹እረ  አያስፈልግም  ቦታውን  ንገሪኝና  በላዳ  መጣለሁ፡፡"አለቻት  ያልጠበቀችውን ነገር በመስማቷ ግራ ተጋብታ፡፡

"አይ እሱ  አሳሳቢ ጉዳይ አይደለም...ቻው በቃ፡፡ ስምንት ሰአት ይመጣልሻል፡፡ በኃላ እንገናኝ።››ስልኩ ተዘጋ።

ይበልጥ ገረማት። ለእሷ እቤት  ድረስ  መኪና? መደመም  ውስጥ  የሚከት  ነው፡፡ቢሮዋ እንኳን ጉዳይ እንድታስፈፅም የሆነ ቦታ ሲልካት..አለቃዋ ቀብረር ብሎ‹‹እስከ እዛ በታክሲ ሄደሽ ..ከዛ በእግር ተሻግረሽ ወደዚህ ተጠምዝዘሽ ከዛ ሌላ ታክሲ ተሳፍረሽ....›› ብሎ ነው የሚያዛት። አሁን ግን መኪና ከሹፌር ጋር ለዛውም ቤቷ ድረስ?ለዛውም ለራሷ ጉዳይ፡፡

‹‹ይሄ  ነገር  የእውነት  ህይወቴን   የሚቀይር   አጋጣሚ   ይሆን   እንዴ?..›› ስትል አሰበችና ሰዓቷን ተመለከተች …5 ሰዓት ሆኗል።ፒጃማዋን አውልቃ ልብስ ቀየረችና ቦርሳዎን ይዛ አንድ ክፍል  ቤቷን  ቆልፋ  ግቢውን  ለቃ  ወጣች። ያመራችው እዛው ሰፈር ወደሚገኝ አንድ ፀጉር ቤት ነው።‹‹አዎ የተለየ ሰው ጋር ለተለየ አገጣሚ የተለየ ሆኜ መሄድ አለብኝ፡፡"ብላ ወስናለች፡፡ባላት ሶስት ሰዓት ወስጥ በተቻላት እና አቅሟ በፈቀደላት መጠን አምራና ዘንጣ የሚላክላትን ሹፌር መጠበቅ እንዳለባት ተሰምቷታል። ዝግጅቷን ጨርሳ 10  ደቂቃ  ያህል  እንኳን ሳታርፍ ነበር ስልኳ ያንጫረረው። ስልኳ እጇ ላይ ስለነበረ ፈጥና አነሳችው።

‹‹ሄሎ፡፡››

‹‹የእኔ እመቤት ጤና ይስጥልኝ፡፡ ደምሳሽ እባላለሁ፤አንቺን ወደ ቤት ለመውሰድ ተልኬ ነበር?››

‹‹ወደ ቤት?›› አለች ደንግጣ...የደነገጠችበት ምክንያት ፈፅሞ ቤት  የሚባል በምናቧ ስላልነበረ ነው... የጠበቀችው ሆቴል ወይም ካፌ..ወይም የሆነ  መዝናኛ ቦታ ነበር፡፡"

ደዋዩ  ፀጥ  ስትልበት  ግራ  ተጋብቶ "ምነው  እመቤቴ  ችግር  አለ.እንዴ?"ሲል ጠየቃት።
"እረ ምንም ችግር የለም...በቃ እየወጣሁ ነው"
"ግሎባል ጋር ቆሚያለሁ አቅጣጫውን ንገሪኝና ልቅረብልሽ"

"ቅርብ ነኝ ...እዛው እመጣለሁ"ብላ ስልኩን አቋረጠችና ቤቱን በመዝጋት ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡ እንግዳና የማይገመቱ ነገሮች ናቸው እየገጠሟት የነበረው፡፡ ደግሞ የሹፌሩ ትህትና "ማን ነች ብላ ብትነግረው ነው እንዲህ እመቤቴ እያለ ቅንጥስጥስ የሚለው?" በማለት እያጉረመረመች ዋናው አስፓልት ላይ ወጣች። ወደ ግሎባል ተጠጋች፡፡ ወዲህ ማዶም ሆነ ወዲያ ማዶ ምንም መኪና አይታያትም...ስልኳን አወጣችና ደወለች፤ከአጠገቧ ከ5 ሜትር ርቀት አካባቢ በእጅ ምልክት ሲሰጣት አየችው፡፡ሰውዬውን ከዚህ በፊት አይታዋለች፤ በቀደም ከሴትዬዋ ጋር የእሷ ጋርድ ሆኖ ቢሮዋ ድረስ መጥቶ ነበር፡፡ የመኪና በራፍ ይዞ ቆሟል፡፡መጥታ እስክትገባ እየጠበቀ ነው፡፡ ትህትናው ከሰውነት ግዝፈቱና ከመወጣጠሩ ጋር ፈፅሞ አብሮ የማይሄድ ነው የሆነባት።መኪናዋ እጅግ ዘመናዊ ከመሆኗ የተነሳ ከዚህ በፊት እንኳን ልትቀመጥበት በአስፓልቱ ላይ እራሱ ሲነዳ የምታየው በጣም አልፎ አልፎ ነው።ለዛ ነው ገና ከቤቷ ቅያስ ወጥታ አስፓልቱን እንደያዘች አይኗ የገባው የመጀመሪያው መኪና ቢሆንም  ለእኔ የተላከ ይሆናል ብላ ስላልገመተች ትኩረት ያልሰጠቸው፡፡ እየፈለገች የነበረው ሌላ ቪታራ ወይም ቪትስ አይነት መኪና ነበር።

በደመነፍስ እየተንሳፈፈች ሄደችና ተጠጋችው፡፡በአንድ እጅ የመኪናውን በራፍ እንደያዘ ጎንበስ ብሎ በሌላ እጅ ወደውስጥ እንድትገባ አመለከታት.. ገባች። የመኪናው መቀመጫ ራሱ የተለየ ነው። ሁሉ ነገሩ የተሟላለት የሀብታም ወንደላጤ ሳሎን ነው የሚመስለው፡፡ ዙሪያውን የተገጠገጠው በሚያብረቀርቅ ቡኒ ቆዳ የተለበጠው ምቹ መቀመጫ ፊት ለፊት የሚታየው አነስተኛ ፍሪጅ፤ ከዛ ከፍ ብሎ ዘመነኛ የፈረንጅ ክሊፕ እያጫወተ ያለ ቲቪ...ሁሉም  ያምራል።‹‹አሁን ይሄን ያለው ሰው ቤት ምን ያደርግለታል?››። ስትል  በውስጧ እያልጎመጎመች ፈራ ተባ በሚል ስሜት ኮርነር ላይ ሄደችና ተቀመጠች።

ሹፌሩም ‹‹እመቤቴ የሚጠጣ ነገር ከፈለግሽ ፍሪጅ ውስጥ አለልሽ ፤ሌላ የሚያስፈልግ ነገር ካለ ጠይቂኝ›› አለና በራፉን ዘግቶ በፊት ለፊት ዞሮ ሄደና የሹፌሩን ቦታ ይዞ ማሽከርከር ጀመረ፡፡...ትንሽ  እንደተጓዙ  በእሷ  እና  በእሱ መካከል  ያለውን  ክፍተት  በተንሸራታች ጥቁር መስታወት  ዘጋው። ተንፈስ  አለች.. የተሻለ ነፃነት ተሰማት፡፡ ከ20 ደቂቃ በሀሳብ የሚያናውዝ ጉዞ በኋላ ካዛንቺስ ደረሱ፡፡ ከስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ቢሮ ቀጥሎ ባለው ቅያስ ተጠምዝዞ ገባና የተወሰነ ደቂቃ ከተጓዘ በኋላ አንድ ግዙፍ ግቢ ውስጥ ይዟት በመግባት ጋራዥ  አቁሞ በፍጥነት ዞሮ በመምጣት በክብር እንዳስገባት በክብር እጇን ይዞ አወረዳት፡፡ እየመራት ወደ ግዙፉ ቪላ ቤት ይዟት ገባ። በእውነት መኖሪያ  ቤት  ሳይሆን የነገስታት የእልፍኝ አዳራሽ  ነው ሚመስለው፡፡ድባቡ ያስፈራል፤ በራፉን አልፈው ወደውስጥ አንድ ሶስት እርምጃ ዘልቀው እንደገቡ  የሆኑ  ደልደል  ያለች ነጭ ሽርጥ ያደረገች ሴትዬ  ከግራ  በኩል  ካለው  ኮሪደር  ድንገት ወጣችና.

.."እመቤቴ እንኳንም በሰላም መጣሽ"በሚል ቃል የታጀበ በሞቀ ፈገግታ ካመጣት ሹፌር ተቀብላት ወደ ውስጥ ይዛት ዘለቀች፡፡ሹፌሩ ቀኝ  ኃላ ዞሮ ተመልሶ ወጣ፡፡

ሴትዬዋ እየመራች ወስዳ ግዙፉ እና ባለግርማ ሞገሱ ሶፋ ላይ እንድትቀመጥ ካደረገች በኋላ"የሚጠጣ ምን ላምጣ?"ስትል ከአንገቷ ጎንበስ ብላ በትህትና ጠየቀቻት፡፡

‹‹አይ ግድ የለም…ምንም አያስፈልግም፡፡››ስትል መለሰችላት፡፡

‹‹አንድ ነገርማ ያዢ"

‹‹እንግዲያው ውሀ ይሁንልኝ›› አለች።እውነት ውሀ ጠምቷት ሳይሆን በህይወቷ እንዲህ አይነት ግራ የገባው ነገር ገጥሟት ስለማያውቅ በደመነፍስ  ነው ያዘዘችው።
//
ከ10 ደቂቃ ጥበቃ በኋላ ሴትዬዋ በቀደም ካየቻት የተለየች ሆና መጣች፡፡ የሆነ የደቡብ አፍሪካ ወይም የታንዛኒያ የባህል አምባሳደር ነው የምትመስለው…ከላይ ከሻሽ አስተሳሰሯ እስከ ተጫማችው ጫማ ልዩ ኦሪጅናል አፍሪካዊ መስላ ነው የጠበቀቻት፡፡ ያው የሴትየዋ አለባበስ ለሳባ አዲስ ሆነባት እንጂ ለእሷ የተለመደና በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ቀን የምትጠቀምበት ነው፡፡፡የሞቀና የጋለ ሰላምታ ሰጥታት ከተቀመጠችበት ሶፋ ላይ ልክ ለረጅም አመት እንደምታውቃት ታላቅ እህቷ አንድ እጇን ትከሻዋ ላይ ጥላ በፍቅርና በፈገግታ   እያወራቻት ወደሚቀጥለው ክፍል
👍776🔥1😁1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

አማዞን ደን ኮሎንቢያ ግዛት
ጫካውን እየሰነጠቁ ከአውሬውና ከነፋሳት ጋር እየተጋፉ መጓዝ በጀመሩ አራት ቀን ሆኗቸዋል፡
በጉዞቸው ከዛፍ ዛፍ ሲንጠለጠል አንድ ገራሚ እንስሳ አየች፡፡ትንሽ ነው፡፡ ድመት ነው የሚመስለው፡፡ ግን ጸጉር የለበሰ በመሆኑ ከመጠኑ ገዝፎ እንዲታይ እረድቶታል፡፡ ዝንጀሮም አንበሳም ይመስላል፡፡ከዚህ በፊት በምስል ላይ ፎቶውን እንኳን አይታ አታውቅም፡፡
‹‹ምንድነው ይሄ እንስሳት?››ቁራኛዋን ካርሎስን ጠየቀችው፡፡
‹‹እ ታማሪን ወይም ሮሳሊያ ይባላል፡፡ወይም በቀላሉ ወርቃማው አንበሳ ይሉታል፡፡››

‹‹አዎ እውነትም ወርቃማው አንበሳ፡፡ፀጉሩ እኮ ወርቅ መሳይና አብረቅራቂ ነው…ትክክለኛ ስሙ ይሄኛው ነው፡፡››
‹‹አዎ ዝርያው የዝንጀሮ ቢሆንም እንደምታይው ግን አንበሳ ነው የሚመስለው፡፡የዚህ ፕሪሜት ልዩ ቀለም ምናልባትም በጠንካራ የፀሐይ ብርሃን ጥምረት እና በአመጋገቡ ውስጥ በሚገኙ የካሮቲኖይዶች ብዛት ላይ የተመሠረተ ነው የሚል መላምት አለ።እንደምታይው አስደናቂ ገጽታ አለው: ወፍራም፤ ለስላሳ፤ ደማቅ ቀይ ፀጉር፤እንዲሁም ጥቁር ፊት እና ትልቅ ቡናማ አይኖች ያሉት አስደማሚ ፍጡር ነው››
‹‹ስላየሁት ደስ ብሎኛል፡፡የማልሞት ቢሆን ኖሮ እዚህ መጥቼ ስላየሁት እያንዳንዳንዱ ድንቅ እና አስደሳች ነገር… ስለእንስሳቱና ስለጥቅጥቁ ዳን… ስለሚንዠቀዠቀው የአማዞን ወንዝ ለወንድሜም ለጓደኞቼም በደስታ እንግራቸው ነበር..ግን ምን ዋጋ አለው….››ከገባችበት ጊዜያዊ የደስታ ስሜት ወጣችና ሀዘን ውስጥ ገባች፡፡
‹‹አይዞሽ …እሰክአሁን በህይወት አለሽ ..ለጊዜው ያ በቂ ነው፡፡››አላት፡፡

‹‹እንዳልክ ይሁንልህ››አለችውና ዝምታ ውስጥ ገባች፡፡
እኩለ ቀን ላይ ኣማዞን ወንዝን ታካ የተመሰረተች የደቡብ ኮለምቢያ የጠረፍ ከተማ ከሆነችውና 35 ሺ ኑዋሪዎች ከሚኖሩባት ላቲሲያ ከተማ ደረሱ፡፡ይህቺ ከታማ ሶስት ሀገሮች ማለት ፔሩ ኮሎቢያን ብራዚል የሚገናኙባት ነጥብ ከሆነችው ትሬስ ፎረንቴራስ ትንሽ ወደላይ ፈቅ ብላ ምትገኝ በዓሳ ምርቷ የታወቀች እጥር ምጥን ያለች ከተማ ነች፡፡የኮሎምቢያ መንግስት ግዙፍ የሆነ የዓሳ ምርቱን ከአካባቢው እየሰበሰበ በጀልባ በመጫን ወደ ማአከላዊ የሀገሪቱ ስፋራዎች የሚጫንባት ወሳኝ ከተማ ነች፡፡ከታማዋን በሩቅ ሲያዮት እና ጉዞቸውንም በዛ አቅጣጫ ሲያቀና ቀጥታ ወደከታማው ዘልቀው ሚገቡ መስሏት ተደስታ ነበር፡፡የዛም ምክንያቱ ህዝብ ያለበትና የመንግስት ተቋማት ሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ላይ ከደረሰች በተቻላት መጠን ለማምለጠ ትሞክራለች፤ያ ከሆነ ደግሞ ጥረቷ የመሳካት እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ስሌቱን ስለሰራች ነው፡፡ይሁን እንጂ አጋቾቻ
የገመተቻቸውን ያህል ጥንቃቄ አልባ አልነበሩም፤በዛም ምክንያት ወደከታማዋ አልገቡም፡፡ይልቅስ ከተማዋን በቅርብ ርቀት ታካ አማዞን ጉያ ውስጥ ተወሽቃ ከምትገኝ ነባር ጎሳዎች ወደሚኖሩባት ወደአንድ መንደር ነው ጎራ ያሉት፡፡

‹‹እርግጠኛ ነኝ ይሄ የመጨረሻ የጉዞ መዳረሻችን ነው፡፡››ካርሎስን ነው የምትጠይቀው፡፡
‹‹አይመስለኝም..ግን የተወሰኑ ቀናትን እዚህ የምናርፍ ይመስለኛል››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹በሩቅ ወደምትታየው ከተማ ምንገባ መስሎኝ ነበር››
‹‹እ..ወደ ላቲሲያ ማለትሽ ነው..ወደእዛ አለመግባታችን ጥሩ ነው…ለአንቺ ምንም ሚጠቅም ነገር አይገኝበትም…ከኑዋሪዎቹ ከግማሽ በላይ የእኛ ሰውዬ ሰዎች ናቸው››

ተስፋ ቆረጠችና… ዝም አለች፡፡..የቡድኑ ሰዎችን ለመቀበል ሶስት የሆኑ የመንደሩ ሰዎች መጡና አወሯቸው፡፡ ከተወሰኑት ጋር የሞቀ ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡ አንድ ወለሉ በአየር ላይ የተንጠለለ በስሩ ውሀ የሞላበት በጣውላ እርብራብ የተሰራ የሳር ክዳን ቤት ከፊት ለፊታቸው ይታያል፡፡ወደዛው መጓዝ ጀመሩ፡፡ቤቱ ሰፋ ያለ ግን ደግሞ እቃ አልባ ነበር፡፡ቁራኛዋ ሰንሰለቱን ከላዩ ላይ አላቀቀና ለብቻዋ ተወላት፡፡ሁሉም በተርታ መቀመጫ ይዘው ተቀመጡ…ምግብ ቀረበላቸው፡፡ ሁሉም ተርበው ስለነበር የምግብ አይነቱ ሳያስጨንቃቸው በፍቅር በሉ ፡፡የሚጠጣ ነገር ቀረበላቸው…ጠንከር ያለ የአልኮል መጠጥ ነው፡፡እሷ መጠጣት አልፈቀደችም፡፡፡ውሀ ቀረበላት፤እሱን ጠጣች፡፡የምግብ ስርአቱ ካለቀ በኃላ እሷን እዛው ቤት ውስጥ ተዋትና ከውጭ ቆልፈውባት ወጥተው ሄዱ፡፡

ቤቱን ክፍት ትተውት ቢሄዱም ወደምትሄድበት ቦታ የላትም፡፡መቼስ በቃ ተመልሰሽ ሂጂ ቢሏት እንኳን የአራት ቀን መንገድ በእንደዛ አይነት ጥቅጥቅ የአማዞን ደን ከጇጓርና ከአናኮንዳ ጋር እየታገለች…አረንጎዴ መርዛማ እንቁራሪቶችና ሰውነት ላይ ከተጣበቁ ማይላቀቁ ጉንዳኖችን ተቋቁማ ወደኃላ ተመልሳ ፔሩ ገባለው የሚል ግምት የላትም፡፡እርግጥ ወደፊት ቀጥላ በአምስት ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ ከምትታየው ላቲሲያ ከተማ ልትሄድ ትችላለች፡፡ግን ሙሉ ከተማው የራሳቸው የጋንግስተሮቹ ግዛት እንደሆነ ካርሎስ በግልፅ ነግሯታል...ምክሩን ችላ ብላ ብትሄድና ምንም አይነት የመንግስት ተቋም ሆነ የሚታደጋት ተቋም በቦታው ባይኖርስ…?፡፡ጠቅለል አድርጋ ስታስበው ከዚህ አሁን ካለችበት ስፍራ አምልጦ ነፃ መውጣት የማይተገበር ምኞት ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡
ደክሞት ስለነበረ እቤቱ ውስጥ ያለች አንድ መተኛ ፍራሽ ነገር ላይ ሄዳ ጋደም አለች፡፡፡ሰውነቷን በቀላሉ እንዳሳረፈችው አእምሮዋን ልታሳርፍ አልቻለችም፡፡ በእነዚህ ሰዎች እጅ ከገባች ቀን ጀምሮ እንዲህ ለብቻዋ በመሆን ጥቂት ሳዕታትን ባገኘች ቁጥር ወዲያውኑ ሀሳቧ በሮ ወንድሟ ጋ ነው የሚሄደው፡፡የትናንት ትዝታዋ ጋር ነው የሚለጠፈው፡፡ናኦል ይሄኔ ለአራት ቀን ድምፆ ሲጠፈበት እና ስልኳም አልሰራ ሲለው የሚያደርገው ጠፍቶት መስሪያ ቤቷ ሄዶ እህቴን ውለዱ እያለ እያስጨነቃቸው አንደሚሆን ገመተች..ብቻ በዛ ችኩል ባህሪው የሆነ ሰውን ውለዷት ብሎ አፍንጫ እንዳይሰብር ነው የሰጋችው፡፡ምን አልባትም ምስራቅ ጋር ሊሄድ እንደሚችል ገመተች፡፡እንዲህ አይነት ጭንቅ ውስጥ ሲገባ ከምስራቅ ቀድሞ ወደአእምሮ የሚመጣ ሌላ የተሻለ የሚቀርባቸውና የሚረዳቸው ሰው እንደሌለ ታውቃለች፡፡እሷም በእሱ ቦታ ብትሆን እንደዛ ነው የምታደርገው፡፡

ከምስራቅ ጋር በወዳጅነት መቀራረብ ብቻ ሳይሆን የስራ ባለደረባም ሆነው እንደሀለቃና ምንዝር ለረጅም አመት ሰርተዋል፡፡ለዛውም በሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት፡፡እርግጥ እሷም ሆነች ወንድሟ ቀጥታ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ተወዳድረው አይደለም የተቀጠሩት፡፡በወቅቱ ለእዛ የሚያበቃ እድሜ ላይም ሆነ ሁኔታ ላይ አልነበሩም፡፡ ..የእዛ መስሪያ ቤት አባል የሆኑት በእሷ በኩል ተመልምለው ..በእሷ ጥረት ወደስልጠና እንዲገቡ ተደርገው…በእሷ በኩል ተልዕኮ እየተሰጣቸው ነው፡፡ከዛ ብዙ ብዙ የሚባል ተልዕኮዎችን ተወጥተዋል…ለሀገር የሚጠቅሙ አንዳንዴም የተሳሳቱ ሰራዎችን ሰርተዋል፡፡ ያኔ እዛ በረንዳ ላይ ረዳት አልባ በነበሩበት ጊዜ ካገኘቻቸው በኋላ እንዴት እንደመለመለቻቸው ትዝ አላት፡፡
ኢትዬጵያ/አዲስ አበባ
አንድ ቀን አስራሁለተኛ አመታቸው ላይ ከምስራቅ ጋር በተዋወቁ በሁለተኛው ቀን በየእለቱ ለደምበኞች ጫት የማመላለስ ስራ ሰርተው ከጨረሱ በኃላ ምስራቅ እመጣለሁ ብላቸው ስለነበረች ቦታቸው ላይ ቁጭ ብለው እየጠበቋት ነበር፡፡ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ ምስራቅ እንዳለችው መጣች፡፡ ከመቀመጫቸው ተነስተው በፈገግታ ተቀበሏት፡፡ይዛ የሄደችው አንድ ፔስታል ቢሆንም አሁን ግን ሌላ አንድ ጥብሰቅ ያለ እቃ የታጨቀበት ፔስታል ይዛ መጥታለች፡፡
👍6214
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ይህቺን ፀሀፊ ልጅ ወዶታል…እሷ እራሷ የመጀመሪያ ደንበኛው ከመሆኗም በላይ ሌላ ደንበኛ አገኝታለታለች፡፡ስልኩን አወጣና ደወለ……አስቴር ጋር…

‹‹እሺ ወንድሜ ደህና ነህ?››

‹‹አለሁልሽ…የላክሻት ልጅ መታለች ልልሽ ነው፡፡››

‹‹እንዴት ነው …ተስማማችሁ?››

‹‹አዎ ጎበዝ ልጅ ትመስላለች››

‹‹ጎበዝ?››

‹‹አዎ ምነው?››

‹‹አይ በአንድ ቀን እንዴት ጎበዝ መሆኗን አወቅክ ?ብዬ ገርሞኝ ነዋ››

‹‹ማለቴ እንዲሁ  ሳያት ተግባቢና ቀልጣፍ ነገር ነች ልልሽ ነው››

‹‹ወንድሜ ፍቅር እንዳይዝህና እንዳትጎዳብኝ…ልጅቷ ፍቀረኛ አላት››

‹‹አይዞሽ አታስቢ አውቃለው፣በዛ ላይ እኔ ማፈቀሪያ ጭንቅላቴ የተበላሸብኝ ሰው ነኝ….››

‹‹ምኑ ነው ምታውቀው?››

‹‹እንዳላት ነዋ››

‹‹ከምኔው?››

‹‹ውይ ኪያ ደግሞ ….በቃ ቻው ማታ ቤት እንገናኝ››

‹‹እሺ ቻው ወንድሜ››በተንከትካች ሳቅ አጅባ ስልኩን ዘጋችው፡፡

////
ወላጇቾ ብቻ ሳይሆኑ ያደገችበትና የእድሜዋን ግማሽ የኖረችበት እቤቷም ጭምር ናፈቃት‹‹ ቤት ማለት..ግን ምን ማለት ነው?ስትል እራሷን ጠየቀችና መልሱን ከአእምሮዋ ውስጥ በርብራ ለማግኘት አይኖቾን ጨፍና ማሰላሰል ጀመረች

‹‹አዎ እቤት ከድንጋይ ወይም ከእንጨት የሚታነፅ የሰው ልጅ መጠለያ ነው።ያንን ህንፃ ከመጠለያነት ወደ ቤትነት የሚቀይረው ግን የታነፀበት ማቴሪያል ጥራትና ውበት አይደለም...ውስጡ ያሉት  ዘመናዊ የቤት እቃዎች እና ውድነትም አይደለም። ህንፃው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነትና የፍቅር ትስስር መጠን ነው ህንፃውን እቤት የሚያደርገው።ለዚህ ነው ከኖርኩበት የተንጣለለ ቪላ ይልቅ አሁን እየኖርኩበት ያለሁት ባለ ሁለት ክፍል ጎስቋላ ቤት የተሻለ የሚሞቀውና የሚደምቀው
››መልሱን ለራሷ ሰጠች፡፡ ቀኑን እንዲሁ በሀሳብና በትካዜ ጊዜውን ብታሳልፍም ሲመሽ ግን ሁሉ ነገር የተለየ ሆነ፡፡

ማታ የቤተሰቡ አባል ጠቅላላ ተሰብስበው በሞቅ ደስታ ከወትሮ በተለየ ድግስ መሰል እራት ቀርቦ በመጎራረስ ከበሉና ቡናም ተጠጥቶ ከተነሳ በኃላ በፀሎት ሽንት ቤት ለመሄድ እንድምትፈልግ ለለሊሴ ነገረቻት…ያሰበችው እሷ ደግፋ እንድትወስዳት ነበር…በተቀራራቢ እድሜ ስለሚገኙ እቤት ውስጥ ካሉ ሰዎች ሁሉ እሷን ማዘዝ ወይም ትብብር መጠየቅ ቀላል ይላታል፡ ….ለሊሴ ግን እንዳሰበችው አላደረገችም….
‹‹ወንድሜ በፀሎትን ሽንት ቤት ትወስዳታላህ?››ብላ ስትጠይቀው ክው ነበር ያለችው….እሱ አንደበት አውጥቶ ፍቃደኝነቱን ሳይናገር በቀጥታ ከተቀመጠበት ተፈናጥሮ ተነሳና ወደእሷ በመሄድ ልክ ትናንት ለሊት እንዳደረገው ከስር ሰቅስቆ ልክ እንደህፃን ልጅ አቀፋት….እንዲህ አይነት ሁኔታ በህይወቷ ገጥሞት ስለማያውቅ መደንገጥ ብቻ ሳይሆን እፍረትም ተሰማት…‹‹.ወላጆቹ እንዲህ ሲያቅፈኝ ምን ይላሉ ?››የሚለው ሀሳብ አእምሮዋ ተሰነቀረና ያንን ለማጣራት እይታዋን በቤቱ ዙሪያ ስትሽከረከር ሁሉም በራሳቸው ጫወታ ተመስጠው እርስ በርስ እያወሩ እየተሳሳቁ ነው……አንከብክቦ እንዳቀፋት ይዟት ወጣ
..ቀጥታ ሽንት ቤት ወሰዳና ወደውስጥ አስገብቶ አቆማት…ልክ እንደሌሊቱ ውሀ በሀይላንድ ከቧንቧው ቀድቶ አመጣላትና የሽንት ቤቱን መጋረጃ ወደታች መልሶ ‹‹ስትጨርሺ ጥሪኝ
››ብሎ ከአካባቢው ዞር አለ፡፡

የሽንት ቤት ጣጣዋን ከጨረሰች በኋላ ቀጥታ ወደቤት አይደለም ይዞት የገባው፡፡ልክ እንደለሊቱ ወንበር አመቻችቶ ስለነበር ተሸክሞ ወስዶ አስቀመጣት….‹‹ቀኑን ሙሉ ተኝተሸ ስለዋልሽ አሁን ትንሽ ንፍስ ይንካሽ››

‹‹አዎ ትክክል ነህ፣በዛ ላይ ጨረቃዋም ናፍቃኝ ነበር፡፡››
እሱም ለራሱ መቀመጫ አምቻችቶ ከፊት ለፊቷ እየተቀመጠ‹‹ከጨራቃዋ ጋር ወዳጅ ናችሁ እንዴ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አዎ ለዛውም የእድሜ ልክ››

‹‹ያን ያህል ብቸኛ ነሽ ማለት ነው?››

‹‹እንዴት ከጨረቃ ጋር ለመወዳጀጀት ብቸኛ መሆን የግድ ነው እንዴ?››

‹‹አይ የግድ ባይሆንም ከልምዴ ስነሳ ብዙውን ጊዜ ከጨረቃዋ ጋር ለረጅም ጊዜ የማውጋት ልምድ ያላችው እንቅልፍ አልባ ብቸኛ ሰዎች ናቸው……በተለይ በፍቅር የተሰበሩ››

‹‹እንዴ በፍቅር የተሰበሩ ነው ያልከው..አይ እንደዛ እንኳን አይደለም…..ባይሆን እንዳልከው ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ በሚፈጠር ብቸኝነት ብንለው የተሻለ ነው..የፍቅር ጉዳይማ ቢሆን በምን እድሌ..ፍቅር እኮ በጣም ምርጥ ነገር ነው፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ… ፍቅር በጣም ወሳኝ ስሜት ነው….አንድ ሰው ሩሚን ‹‹ፍቅር ምንድነው?››ብሎ ጠየቀ።ሩሚም ..‹‹ፍቅር ምን እንደሆነ ትክክለኛ ትርጉሙን ልታውቅ የምትችለው ውስጡ መጥፋት ስትችል ነው።›› ብሎ መለሰለት…..፡፡

‹‹አዎ ትክክለኛ አባባል ይመስለኛል….ፍቅር የምትተነትነውና የምታወራው ነገር አይደለም፣ፍቅር ኖረህ የምታጣጥመው የተቀደሰ ስሜት ነው….በፍቅር መጥፋት ጥሩ አባባል ነው››

‹‹አይ ጥሩ…ለማንኛውም ለደቂቃም ቢሆን እስቲ ከጨረቃዋ ጋር ብቻችሁን ልተዋችሁ…. መጣሁ›› ብሎ ተነስቶ ወደቤት ገባ..እሷ አይኖቾን ወደላይ አንጋጠጠች…ሰማዩ ጥርት ብሎ ይታያል ፡፡ጨረቃዋ ሙሉ ክብ ሆና ደፍናለች..ዙሪያዋን የተበተኑና ከዋክብቶች ብልጭ ድርግም እያሉ ይታያሉ…አናትና አባቷ ትዝ አሏት..ይሄኔ የእሷን መጥፋት ምክንያት በማድረግ የመጨረሻውን ጥል እየተጣሉና የመጨረሻ የተባለውን አንጀት በጣሽ ስድብ
እየተደሰዳደብ እንደሆነ በምናቧ አሰበችና ሙሉ ሰውነቷ ሽምቅቅ አለባት..ሰውነቷ ሲሸማቀቅ ደግሞ የእግሯ ሆነ የፊቷ ጥዝጣዜ ህመም ተቀሰቀሰባት….
ድንገት የሰማችው ድምፅ ነው ከሀሳቧ ያባነናት…..ያልገመተችውን ነገር ነው እያየች ያለችው..ፊራኦል ፊት ለፊቷ ቅድም የነበረበት ቦታ ቁጭ ብሎ ክራር እየከረከረ የሙሀመድ አህመድን የትዝታ ሙዚቃ ያንቆረቁራል….ፍዝዝ ብላ በፍፁም ተመስጦ ታዳምጠው ጀመር፡፡
ስንቱን አስታወስኩት…ስንቱን አስብኩት ልቤን በትዝታ ወዲያ እየላኩት
አንዴ በመከራ …አንዴ በደስታዬ ስንቱን ያሳየኛል ..ይሄ ትዝታዬ

በድምፁ ድንዝዝ ብላ ጠፋች………… የትናንቱ ፍቅር ….ጣሙ ቁም ነገሩ ምነው ያስተዋሉት ያዩት በነገሩ
ሁሉም እንደገና ኑሮን ቢያሰላስል አይገኝም ጊዜ ያኔን የሚመስል፡፡

ዘፈኑን ሲጨርስ‹‹አንተ..አንድ ሺ አመት በዚህ ምድር ላይ ኖረህ ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ያለውን ጊዜ ናፍቀህ የምትተክዝ እድሜ ጠገብ አዛውንት ነው የምትመስለው፡፡››የሚል አስተያየት ሰጠችው፡፡

‹‹ያን ያህል?››

‹‹አዎ …ድምፅህ በጣም ግሩም ነው….ሙዚቃ ትሰራለህ እንዴ?››

‹‹አይ ያን ያህል እንኳን ሰራለሁ ማለት አልችልም …በፊት በፊት ቀበሌ ኪነት ከጓደኞቼ ጋር እሞክር ነበር አሁን ከህይወት ሩጫ ጋር አብሮ አልሄድ አለኝና ተውኩት፣እንዲህ አንደዛሬው ጨረቃዋ ሙሉ ስትሆን እንዲህ እቀመጥና ለእሷ አዜምለታለው፡፡››

‹‹እንዴ..ለእኔ የዘፈንክልኝ መስሎኝ ውስጤ በደስታ ተፍነክንኮ ነበር ..ለካ ለጨረቃዋ የተዘፈነውን ዘፈን ነው ሳይፈቀድልኝ የሰማሁት…..››

‹‹አይ እንደዛ አንኳን ለማለት አልችልም…የዛሬው ዘፈን ቀጥታ ላንቺ ነው..ምስጋናና ይቅርታ ለመጠየቅ፡ ብዬ ነው የዘፈንኩት፡፡››

‹‹አልገባኝም..ይቅርታውስ ለምን ?ምስጋናውስ?፡፡››

‹‹ይቅርታው ገና ስትመጪ ጀምሮ በሙሉ ልቤ ስላልተቀበልኩሽና ለእኔም ሆነ ለቤተሰቦቼ እንደሸክም ስለቆጠርኩሽ…ምስጋናው ዛሬ እናቴንም ሆና መላ ቤተሰብን አንበሽብሸሽ በማስደሰትሽ…..››
👍7918😱1
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

"አንች ጠጭ ጠጭ ምንም አይልሽም ብለሽኝ አሁን እኮ አዞረኝ" አለች፡፡ ለጓደኛዋ መቅደስ፡፡

"አንዱን ቢራ ጨረሽው እንዴ? ትገርሚያለሽ እንደለስላሳ ነው ስልሽ እንደለስላሳ ጨለጥሽው፡፡ በይ አሁን ቀስ ብለሽ አንድ ድገሚና ከዚያ በኋላ ይበቃሻል፡፡ ለነገሩ ቢራ አንድ ስለማይጠጣ ነው እንጅ በአንድ ቢበቃሽ ጥሩ ነበር፡፡

"አሁን አመመኝ እያልኩሽ ድገሚና ጠጭ ትይኛለሽ ? ብላ ብትኮሳተርም መድገሟ አልቀረም ሁለተኛ ቢራዋን አስከፈተች፡፡

በስካር መንፈስ ምሽቱ ወደ ቀን ተቀይሮበታል፡፡ አይመሽም እንዴ? ሆቴሉ አይዘጋም? ይላል ፤ ተመስን በውስጡ ፡፡

"ከአሁን በፊት ከሴት ጋር ተኝተህ ታውቃለህ"? እንዴ አለው ያሬድ፡፡

"ከሴት ጋር መተኛት አይደለም ለመተኛትም አውርቼ አላውቅም፡፡ ዛሬ ግን ብተኛ ምን እሆናለሁ፡፡

"እና የትኛዋ ትሻልሃለች"?፡፡

"የሽሃረግ ትሻለኛለች ፤ እሽ ካለች፡፡

"እሽ ፤ እንጠይቃታለን ግን እንደ ገጠር ሴት ዝም ብለው እሽ አይሉም፡፡ ገንዘብ ይጠይቃሉ፡፡

"ለብር ችግር የለም፡፡ ብቻ እሽ አሰኝልኝ ፡፡

ያሬድ መቅደስን ለብቻዋ ጠርቶ ለማነጋገር ፈልጓል፡፡ ከመቀመጫው ተነሳ፡፡ መቅደስን ጠራት፡፡ ከሰው ጋር እንዴ? ብሎ ጠየቃት፡፡

"እኔ ከሰው ጋር ነኝ፡፡ የሽሃረግ ደግሞ እንደዚ አይነት ስራ ሰርታ ስለማታቅ አትወጣም አለችው፡፡

ደግሞ የከተማ ሴት እንደ ገጠር ነው እንዴ? በገንዘብ እሽ አትልም? ፡፡

"እሱማ ልክ ነህ ፤ እሷ ግን ስለማትሰራ ነው፡፡

ጓደኛየ ከአሁን በፊት ከሴት ጋር ተኝቶ አያውቅም፡፡ ዛሬ ምን እንደነካው እንጃ በየሽሃረግ አብዷል አላት፡፡

ብቻ ከእሷ ለመስማት እሽ ካለች እጠይቃታለሁ፡፡ ብላ ልጠይቃት እየፈራች ቢሆንም ተጠጋቻት፡፡ የሽሃረግ የጠጣችው የሐረር ቢራ አስክሯታል፡፡ ወደ ኋላ ያሰረችውን ሐር የሚመስለውን ፀጉሯን ለቃዋለች፡፡

ታዲያ አይኗን ሸፍኖት ትንሽ ትንሽ ነበር ፊቷ የሚታየው፡፡

መቅደስ የጠጣችው ቢራ እሷንም ሞቅ አድርጓት ስለነበር የሽሃረግን ሳትፈራ ስሟን አቆላምጣ የሺዬ ያሰውዬ ፎንቅቄያለሁ እያለ ነው አለቻት፡፡

"የቱ ነው"? አለች፡፡ ፀጉሯን ከፊቷ ላይ ገለጥ እያደረገች፡፡

ቢራ ከጋበዙሽ አንደኛው ፡፡ ያ የፂሙ አሪዝ የሚያምረው ሰውዬ፡፡ ደግሞ ሴት የሚባል አውጥቶ አያውቅም፡፡ ቢራ እራሱ የተማከራችሁ ይመስል እንደ አንችው ዛሬ ነው ፤ የጀመረው አለቻት፡፡

"አንች በምን አወቅሽ ዛሬ ቢራ መጀመሩን ?፡፡

አብሮት ያለው ጓደኛው ነው የነገረኝ፡፡

"እኔ እንደዚህ አይነት ስራ እንደማልሰራ እያወቅሽ ፤ ለምን ትጠይቂኛለሽ"? አለች፡፡ ውስጧ ፍራት ፍራት እየተሰማት፡፡

እሱንማ አውቃለሁ፡፡ ግን አንች እስከመቼ ድረስ ነው? ወንድ የማትፈልጊው ፤ የጠየቀሽን ሁሉ አልፈልግም እያልሽ፡፡ ላይፍሽን በአሁን ሰዓት ካልተጠቀምሽበት መቼ ልትጠቀሚበት ነው?፡፡ ደግሞ ጊዜሽ ካለፈ ወዲያ ማንም ሊጠይቅሽ አይደለም ዞር ብሎ የሚያይሽ አታገኝም፡፡ ይልቁንም ዛሬ እትዬም ስለሌለች አብረሽው እደሪ አለቻት፡፡

እሳትን በእሳት እንደ ሚባለው ሴትን በሴት አሳምኖ በቁጥጥር ስር ማድረግ በሴቶች የተለመደ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡

ጊዜሽ ካለፈ ዞር ብሎ የሚያይሽ አታገኝም፡፡ ያለቻት ህሊናዋን በመርፌ የተወጋች ያህል ተሰማት፡፡ በትካዜ ተዋጠች፡፡ መጀመሪያም ልቧን በአይን አፋርነቱና በጉንጩ ላይ መስመር ሰርቶ በወረደው አሪዛም ፂሙ አሸፍቶ የወሰደባት ተመስገን እንኳን ለሴት ልጅ ለወንድ ልጅ ያማልል ነበር፡፡

"እትየ ስትመጣ ካልነገርሽብኝ እኔም ወድጀዋለሁ"፡፡ አለቻት የልብ ትርታዋ ከመጠን አልፎ ቁና ቁና እያስተነፈሳት፡፡

አልነግርብሽም፡፡ ደግሞ እኔ የምናግረው ጣቱን የሚጠባ ህፃን አደረግሽኝ እንዴ ብላት "በይ አሁን
ሰውም ስለሌለ እንዘጋጋና እኔም ሰው እየጠበቀኝ ነው እንተኛ አለቻት፡፡

"እምቢ ሳትል አትቀርም አለ ፤ ያሬድ፡፡

የከተማ ሴት ገንዘብ ነው የሚፈልጉት አላልከኝም" እንዴ አለ ፤ ተመስገን፡፡

የዚች የተለየ ነው እባክህ ብሎ ሌላም ደግሞ ሳይናገር መቅደስ ጠጡና ተነሱ ልንዘጋ ነው አለች፡፡

ተመስገን መሸ እንዴ? አለ፡፡

አልታወቀህም እንዴ? ከመምሸቱም ሊነጋ ተቃርቧል፡፡ እንዴውም የእኛ ብቻ ነው፡፡

ያልተዘጋው እንጅ የሁሉም ሆቴሎች ተዘግተዋል አለች ፤ መቅደስ፡፡

"እሽ ፤ እንነሳለን ግን የሽሃረግ ምን አለችሽ"? አለ

መቅደስ በስንት ልመና እሽ አስብያታለሁ፡፡ አሁንም እየፈራች ስለሆነ እናንተ ተነሱና አልጋ ቤት ጠብቁኝ፡፡ እኔ ይዣት እመጣለሁ አለች፡፡

ተንገዳገደ፡፡ ደግፎት ወደ መኝታ ቤት ገቡ፡፡

መቅደስ ሆቴሉን ዘጋግታ ከጨረሰች በኋላ፤ የሽሃረግን የሆቴሉ ዘበኛ እንዳያያት ወደ ሽንት ቤት የሚሄዱ አስመስላ ወደ እነ ያሬድ አልጋ ቤት አስገባቻት፡፡ ያሬድ ለሚተኛበት ሌላ አልጋ ከፍታለት አብሯት ወደ ሚያድረው ሰው ጋር ተመለሰች ፡፡

ለተመስገን ችግር የሚያጋጥምህ ከሆነ እዚህኛው አልጋ ቤት ነው የምተኛው፡፡ ነገ በጥዋት ወደ አቶ ላንቻ ቤት እንሄዳለን ብሎት ሁለተኛ ወደ ያዘው አልጋ ሄዶ ተኛ፡፡

የመኝታው በር ተዘጋ፡፡ ልብሳቸውን አወላለቁ፡፡ ከአሁን በፊት እንደሚተዋወቁ ፍቅረኛ ተቃቀፉ፡፡ ታምሪያለሽ ፤ አንተም ታምራለህ፡፡ ብቻ የሚል ቃል ተነጋግረው በለበሱት ብርድልብስ ውስጥ ከንፈር ለከንፈር ተፈላልገው ተገናኙ፡፡

የሁለቱም የሰውነት ሙቀት ጨመረ፡፡ ሳይታወቃቸው የተመስገን እግሮች በየሻረግ እግሮች ውስጥ ተጠላለፉ፡፡ በስካር መንፈስ ጉዳያቸውን ከፈፀሙ በኋላ ሁለቱም እራሳቸውን ሳቱ፡፡ መተቃቀፉና መሳሳሙ ቀረ፡፡ ድጋሜም አልተገናኙም፡፡ የለሊቱ ጨለማ ለቆ የቀኑ ብርሃን ተተካ፡፡

ያሬድ እሱም በስካር መንፈስ የመኝታ በሩን ከፍቶ እንደ ገባ ጫማውን እንኳን አላወለቀም፡፡ የወደቀበትን አያውቀም፡፡ ስካርና እንቅልፉን አሳልፎ ከተኛበት መኝታ ላይ ባነነ፡፡ ጫማውን ሳያወልቅ በመተኛቱ ተገረመ፡፡እንደዚህ እራሴን እስከምስት ድረስ ሰክሬ ኖሯል፡፡ ወይ ነዶ የሰውዬው ልጅ እያለ ተነሳ፡፡ በሩን ከፈተ፡፡ ሌሊቱ ነግቶ ቀን ቀን እየሸተተ ነው፡፡

የስካር ፊቱን ታጠበ፡፡ ልቡ አቶ ላንቻ ጋር ለመሄድ ተቻኩሏል፡፡ የአልጋው በር አልተዘጋም፡፡ ገርበብ ብሏል፡፡ ሳይዘጉት ይሆን እንዴ? የተኙት እያለ ገርበብ ያለውን በር ከፈት አድርጎ ገባ፡፡

የሽሃረግ ከተኛችበት ስትነሳ ከማታውቀው ሰው ጋር ተኝታ የንፅህና ክብሯን በመስጠቷ የሞት ያህል ተሰምቷታል፡፡ በሁለት እጆቿ እራሷን ደግፋ ከአንገቷ ወደ መሬት አቀርቅራ ከመኝታው ላይ ተቀምጣለች፡፡ የተፈጠረውንና ያደረገችውን ሁሉ ለማስታወስ እየሞከረች ከህሊናዋ ጋር እየተሟገተች ሳለ ያሬድ በር ከፍቶ ገባ፡፡ ካቀረቀረችበት ቀና አለች፡፡ ከያሬድ ጋር አይን ለአይን ተጋጩ፡፡ ያሬድ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡ ድንጋጤ ተሰማው፡፡

የሽሃረግን ደጋግሞ አትኩሮ ተመለከታት፡፡ ማታ በዲም ላይትና በፌር ቅባት ህንዳዊ መስላ የታየችው የፊት ላይ ቅባት ተወግዶ የኢትዮጵያዊነት ደም ግባቷ ተመልሷል፡፡ የጠይም ለግላጋ ቆንጆ መሆኗን በደንብ ይታያል፡፡ የሚያውቃት የሚያውቃት መሰለው፡፡

ተመስገን የት እንደ ሄደ እንኳን አልጠየቃትም፡፡ ወደ ተቀመጠችበት መኝታ ተጠጋ፡፡

ምነው? የማውቅሽ መሰለኝ፡፡ ግን ስምሽ ትክክለኛ የሽሃረግ ነው? አላት፡፡

የሽሃረግ ጭንቅላቷን በመጥረቢያ እንደተመታች ያህል ባለችበት ክው ብላ ቀረች፡፡ ያሬድን አፍጣ ፣ ደግማ ፣ ደጋግማ አየችው፡፡

"የየየየየየየየየየየየየ..ታ...ውቀኛለህ"?  አለች፡፡ አፏ እየተንተባተበ፡፡
👍693
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================

ሁሴን ወደዩኒቨርሲቲው  ከተመለሰ ከአስራ አምስት ቀን በኋላ…
አላዛር እንደተለመደው  ስራ ውሎ ቤት እንደገባ  በራፉ ከልክ በላይ ተቆረቆረ..በድንጋጤ ሄደና ከፈተው፡፡ሰሎሜ ነች..፡፡አይኖቾ በለቅሶ ብዛት ደም ለብሰዋል፡፡በዛ ላይ አባብጣለች፡፡ወደውስጥ ጎትቶ አስገባትና በራፉን መልሶ ዘግቶ ‹‹ምን ሆንሽ?››ሲል ጠያቃት..ልትመልስለት ሞከረች ግን ሳግ እየተናነቃት ማውራት አልቻለችም፡፡ተንደርድራ ሄዳ ሶፋው ላይ ወጥታ እጥፍጥፍ ብላ ተኛች፡፡ለምን እንደዚህ እንደሆነች በደንብ ያውቃል፡፡ቢሆንም አሳዘነችው፡፡ቢቻለው ይሄንን ጉዳይ እሷን ቅንጣትም ሳያሳዝን በፀጥታ ማጠናቀቅ ነበር ምኞቱ…ግን እንደዛ ማድረግ አይችልም‹‹ካለመስዋዕትነት የሚገኝ ውጤት የለም››ብሎ በማሰብ እራሱን ለማፅናናት ሞከረ፡፡በጣም አሳዘነችው፡፡በዝግታ ሄዶ ፈራ ተባ እያለ ስሯ ተቀመጠ፡፡

‹‹ሶል ምን ሆንሽ?››

‹‹ያ ደደብ..ቺት ሲያደርግብኝ ነበር ለካ፡፡››

‹‹እንዴ ማን?›

‹‹እስራኤል ነዋ.. ሌላ ማን ይሆናል?››

‹‹እንዴ ገና ከመጀመሪያችሁ..አረ የተሳሳተ ወሬ ደርሶሽ እንዳይሆን?››ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን  እውነተኛ ሙሉ  ታሪኩን  ቢያውቅም በማስመሰሉ ቀጠለበት፡፡

‹‹ኸረ ባክህ…››አለችና ከተጋደመችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከጃኬቷ ኪስ ውስጥ ፎቶዎችን አወጣችና ጠረጴዛው ላይ ዘረገፈችለት፡፡

ልክ ፎቶውን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየው በማስመሰል በመደነቅና  በመገረም እያቀያየረ ይመለከታቸው ጀመር፡፡

‹‹ልጅም አለው ማለት ነው?›

‹‹አይገርምም..ምን አይነት ጅል ኖሪያለው?››

‹‹እንዴ አንቺ እንዴት ልታውቂ ትችያለሽ?››

‹‹አይደል …ልስልስ ብሎሰ ሲቅለሰለስ እኮ መላአክ ነው የሚመስለው፡፡.

ፎቶውን እንዴት እንዳገኘችው በደንብ እያወቀ‹‹ለመሆኑ ይሄን መረጃ እንዴት አገኘሽው?››ሲል ጠየቃት፡፡

..ካፌ አስተናጋጅነት ስራ ጀምሬለሁ አላልኩህም…ሽፍቴን ጨርሼ ወደቤት ለመምጣት ታክሲ እየጠበቅኩ ሳለሁ ነው የሆነ ህፃን ልጅ  የሰጠኝ…የሆነች ሴት ነች የላከችልሽ››ነው ያለኝ…በወቅቱ ግራ ተጋብቼ ስለነበር ከዛ በላይ ማጣራት አልቻልኩም፡፡››

‹‹እራሷ ሚስቱ ትሆናለች፡፡››

‹‹አዎ መሰለኝ ከፎቶው ጋር አብሮት የሆነ ማስታወሻ ነበረበት

..‹እባክሽ የልጄ አባት ባሌን ተይልኝ……ትዳራችንን አትበጥብጪ› ይላል››

‹‹ይገርማል…ታዲያ እሱን አላናገርሽውም?››

‹‹ምን አባቱና ነው የማናግረው…..ወዲያውኑ ነው ስልኩን ብላክ ሊስት ውስጥ የጨመርኩት ፣  ብቻ እግዜር ነው የተፋኝ፡፡››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹ምን እንዴት አለው..?አንድ ተጨማሪ ወር ቆይተን ቢሆን ኖሮ ሌላ ነገር ውስጥ ልንገባ እንችል ነበር››

‹‹ሌላ ነገር ማለት?››

‹‹አንተ ደግሞ በረዶ ነጭ ነው ካለሉህ አይገባህም….››አለችው በብስጭት፡፡
በረጅሙ ተነፈሰ….‹‹አለመነካካታችሁም አንድ ነገር ነው…አይዞሽ ቀስ እያልሽ ትረሺዋለሽ››ሲል ሊያፅናናት ሞከረ፡፡

‹‹አይ አካላችን አለመነካካቱን አትይ …ልባችን ተነካክቶ ነበር..በተለይ ልቤ ልቡ ላይ ተለጥፎ ነበር….ልብን ከተለጠፈበት መንጭቀህ ስታላቅቀው ደግሞ ተቦጭቆ የሚቀር ነገር አለ..የሚቆስልና የሚቆጠቁጥ…ያማል…..››
ጭንቅላቷን እያሻሸ‹‹አይዞሽ…!!.››አላት፡፡

‹‹አላዛር››ስትል ድንገት ጠራችው፡፡

‹‹ወዬ ሰሎሜ››

‹‹ቆይ እኔ አስጠላለሁ እንዴ?››

‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው?››

‹‹ጓደኛዬ ከሆንክ በታማኝነት መልስልኝ..እኔ አስጠላለሁ ወይ?››

‹‹አንቺ ማለት ድቅድቅና ጭለማ በሆነ  አለም ውስጥ ቦግ ብለሽ በድምቀት የምታበሪ ጨረቃ ነሽ…አንቺ ውብ ካልሆንሽ..ውብ ሚባል ነገር ጭራሽ በዚህ አለም የለም ማለት ነው››አላት ከአንጀቱ፡

‹‹አንተ ደግሞ ከፊክሽን ያነበብከውን ውብ የፍቅር ውዳሴ አሰማኝ አላልኩህም እኮ….ንፅህ ስሜትህን ነው የጠየቅኩህ››

‹‹እኔም የነገርኩሽ ስለአንቺ የሚሰማኝን ነው..ፊክሽን ማንበብ እንደማልወድ ደግሞ ታውቂያለሽ፡፡››

‹‹ታዲያ እንደምትለው ከሆነ ..ለምን ፍቅርን በተመለከተ ስኬታማ መሆን አቃተኝ..?››

‹‹አንቺ ብቻ እኮ አይደለሽም ..እኛም ጓደኞችሽ እስከአሁን ይሄነው የሚባል የፍቅር ታሪክ የለንም፡፡ያ ማለት ወደፊት አይኖረንም ማለት አይደለም….ከፊታችን ገና ብዙ ብሩህ እድሎችና ተስፋዎች እንዳሉን አምናለው፡፡ደግሞ እንዳትረሺ ውቧች ሁሉ  ሁሌ  በፍቅር ውጤታማ መሆን አለባቸው የሚል ህግ የለም ፡፡ .››

‹‹ይሁን እስኪ እንደአፍህ ያድርግልን…..ምን አልባት ሁለችንም ጓደኛሞች ልጆች ሆነን ጀምሮ ተንኮል ስንሰራ ስላደግን የሆነ ሰው ‹ፍቅር  በልባችሁ አይደር…ካደረም አይሰንብት› ብሎ እረግሞን ይሆናል….›› ብላ  ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቆመች፡፡

‹‹ምነው ልትሄጄ ነው እንዴ?››

‹‹እና ልደር?››

‹‹ምን ችግር አለው…?

‹‹በል ይሄን ያህል ካለቃቀስኩብህ ይበቃኛል ..አመሰግናለው..ትንሽ ቀለል ብሎኛል››

‹‹በይ እሺ ደህና እደሪ››አለና በራፉ ድረስ ሸኛት፡፡በራፉን እንደከፈተ ቆሞ በራፏን ከፍታ እስክትገባ  ተመለከታት…ከዛ በእፎይታ እና በእርካታ በራፉን ዘጋና ወደመኝታው አመራ፡፡
////
አላዛር እና ሰሎሜ ለሁሴን ምርቃት ለመሄድ እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ያልገመቱት አስደንጋጭ እና ያልተጠበቀ ግን ደግሞ አስደሳች ተብሎ ሊታሰብ የሚችል ዜና ደረሳቸው፡፡
መጀመሪያ ለአላዛር  ነው መልእክት የተላከለት፡፡
ሰሎሜ እና አላዛር ወንድሜ እኔን ለማስመረቅ ወደእኔ ለመምጣት ምታደርጉትን ዝግጅት አቁሙ..አስፈላጊ አይደለም፡፡ልትልክልኝ ያሰብከውን  ገንዘብም አትላክልኝ …እስከዛሬ ከበቂ በላይ ረድተኸኛል…አመሰግናለሁ፡፡ለምን እንደዛ እንዳልኩህ  ዝርዝር ምክንያቱን ሰሞኑን ኢሜል አደርግልሀለው፡፡››ይላል፡፡
ገና ሰሞኑን ጠብቆ ኢሜል እስኪልክለት መጠበቅ አልችልም.፡፡ለምን እንደዛ እንዳላቸው ለማወቅ..ስልክ ደወለለት …አይነሳም፡፡ደጋግሞ መከረ…፡፡በማግስቱ እንደውም ጭሩሱን ስልኩ አይሰራም ፡፡ጥሪ አይቀበልም ይላል፡፡
ለሰሎሜም ሁኔታውን ነግሯት አብረው መጨነቅ ጀመሩ፡፡
እሷም ከእሱ በላይ ተጨንቃ

‹‹ታዲያ ምን ይሻላል ትላለህ?››ስትል ጠየቀችው ፡፡

‹‹እኔ እንጃ …ምን አልባት እኛን ማስቸገር ከብዷት እንዳይሆን››

‹‹ይመስለኛል…ማለቴ አንተን ማስቸገር ከብዶት ነው የሚሆነው››ስትል በሀሳቡ ተስማማች፡፡

‹‹ምን ማለት ነው..?ጓደኛቹ አይደለን እንዴ..?በእንደዚህ አይነት ጊዜ ከጎኑ ካልሆን ጥቅማችን ምኑ ላይ ነው፡፡››ተበሳጨ፡፡
‹‹ያው ሁሉም ጓደኛ እኮ አንተ እንደምታደርገው አያደርግም››

‹‹እንዴት? ››

‹‹እኛ እርስ በርስ ጓደኛሞች ብቻ አይደለንም የእድሜ ልክ ትስስር ያለን ወንድምአማቾች ነን››

‹‹ይሄ ገለፃ አሌክስንም ያጠቃልላል?››ሲል መልሶ ሌላ ጥያቄ ጠየቃት፡፡

ፊቷ ቅይርይር አለ…አሌክስ የሚባለውን ስም መስማት የማትፈልገው ስም ከሆነ ከራርሟል ፡፡መኮሰታተሯን አይቶ‹‹እሺ አትበሳጪ..እንዳልሺው ሊሆን ይችላል፡፡አሁን ዋናው ነገር  ምን እናድርግ የሚለው ነው?›› ሲል ምክረ ሀሳቧን ጠየቀ፡፡

‹‹እኔም ግራ ገባኝ እኮ…፡፡›

‹‹ዝም ብለን  ወደ ጎንደር እንሂድ እባክሽ››ሲል ቅፅበታዊ ውሳኔውን ነገራት፡፡

‹‹መቼ….?››

‹‹በቃ ነገ እንዘገጃጅና ተነገ ወዲያ እንሂድ፡፡››

‹‹ግን አውቀሀል… ለምርቃቱ ገና አስር ቀን ይቀረዋል…ደርሰን እንመለሳለን ወይስ  እንዴት እናደርጋለን?››
👍504
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////

ሚካኤል ከኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊ ጋር ሚስጥራዊ ስብስባ እያደረገ ነው፡፡እኚን ባለስልጣን ለማግኘትና ለማናገር በጣም ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፏል …በጣም ብዙ ገንዘብም ከስክሷል፡፡

‹‹እሺ አቶ ሚካኤል እንዳገኝህ ያሳመነን ወዳጄ ትልቅ ባለውለታዬ ነው ..ምን እንዳደርግልህ ነው የምትፈልገው?፡፡››ሲል ቦርጫቸውን እሻሹ ጠየቁት፡፡

‹‹ያው ጫፉን ያውቁታል ስለአባቴ ጉዳይ ነው››

‹‹እሱን ሰምቼለው…አባትህ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ሰው ነው፡፡ምን እንድረዳህ እንደፈለክም ያልገባኝ ለዛ ነው፡፡ታውቃለህ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ፍርደኛ ቀጥታ ፋይሉ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ጋር ነው ሚላከው..እሳቸው ሲፈርሙበት የሞት ቅጣቱ ተፈጻሚ ይሆናል…እስከዛው በእስር ይቆያል…ማንም ሰው ምንም ማድረግ አይችልም፡፡››

‹‹አውቃለው…..የእኔ ፍላጎት የሞት ፍርድ ተፈፃሚ እስኪሆንበት ያለው የማረሚያ ቤቱ አያያዝ እንዲሻሻልለት ለመጠየቅ ነው፡፡››

‹‹አዎ አንተን ለማግኘት ከመምጣቴ በፊት ስለአባትህ አጠቃላይ ሁኔታ በመጠኑ ለማጣራት ሞክሬ ነበር፡፡አሁን የታሰረው ጥብቅ በሆነ  ጥበቃ ለብቻው መሆኑን ገልፀውልኛል፡፡››አሉን ፊትለፊታቸው የተቀመጠውን የውስኪ ብርጭቆ አንስተው ተጎነጩና መልሰው አስቀመጡት፡፡

ሚካኤልም ‹‹አዎ ያስጨነቀኝ እኮ ያ ነው፡፡››ሲል መለሰላቸው፡፡

‹‹ያ ለምን እንደሆነ መቼስ ታውቃለህ፡፡አባትህ ከሌሎች በእስር ቤት ካሉ ታራሚሆች ጋር በማሰር ከማረሚያ ቤቱ ለማምለጥ ሞክሮ አንድ የፖሊስ አባልና ሁለት እስረኛ ሞተዋል፡፡የዛ ኦፕሬሽን ዋናው ማስተር ማይንድ እና መሪ ደግሞ አባትህ ነበር…ያ ውሳኔ የተወሰነበት ከዛ ክስተት በኋላ ነው፡፡ለፖሊስ መገደል ምክንያት መሆን ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት አይከብድህም››

‹‹አዎ አውቃለው…ግን እኮ በጣም ተቀጣ..እዛ ጨለማ ክፍል በሰንሰለት ተጠፍሮ መኖር ከጀመረ ስድስት ወር አለፈው፡፡እሺ ብቻውን ይታሰር….ቢያንስ ከጨለማ ክፍል የሚወጣበትና  ከሰንሰለት እስርም የሚገላገልበት እድል ቢኖር፡፡ዋናው ከሰው እንዳይቀላቀልና ተመሳሳይ አይነት የማምለጥ ሙከራ እንዳይሞክር አይደል››ሲል በንግግሩ ቃናም በአይኖቹም ተማፀናቸው፡፡

‹‹ይመስለኛል ..ያም ብቻ አይደለም..በእሱ ምክንያት የሞተው ፖሊስ በወህኒ ቤት ውስጥ በፖሊስችም ሆነ በእስረኞች በጣም ተወዳጅ ስለነበረ….በጓደኞቹ ዘንድ ከፍተኛ ብስጭት ፈጥሯል….እና አንድም በጣም እንዲቀጣ ይፈልጋሉ በሌላ ጎኑም በተግባሩ በተበሳጩ ሰዎች ጥቃት እንዳይደርስበትም ስጋት ስላለ መጠበቅ ይፈልጋሉ፡፡››

‹‹‹አውቃለሁ…ያ ጉዳይ በመፈፀሙ እኔም ከፍተኛ ልብ ስብራት ደርሶብኛል ፣ የሞች ፖሊስ ቤተሰቦች አግኝቼ ለማነጋገር ሞክሬለው፡፡ባለቤቱንና አንድ ልጁን ወዲው ነበር ያገኘዋቸው….እና ምንም እንኳን እሱን መልሼ ላመጣላቸው ባልችልም በኑሮ ግን እንዳይቸገሩ የተቻለኝን እያደረኩ ነው፡፡ለሚስቱ ስራ እንድታገኝ አድርጌለው….የልጁንም ትምህርት ቤት ክፍያ  እና አንዳንድ ወጪዎች እየከፈልኩ ነው….ምንም ሆነ ምንም ወደፊትም ያንን ማድረጌን አላቋርጥም፣እባኮት እርሶ በተቻሎት መጠን ይርዱኝ…ምንም አይነት ቤተሰብ እንዳይጠይቀውም ስለተከለከለ እኔ እንኳን ካየሁት ስድስት ወር አልፎኛል…››

‹‹በእውነት እያደረከው ስላለ ነገር ምስጋና ይገባሀል..ትልቅ ሰው ነህ!!እንግዲህ እንዲህ እናድርግ….አንድ አስር ቀን ስጠኝ  እና ሁኔታውን በተሻለ ሁኔታ ላጥና..ከዛ ሌሎች ጓደኞቼንም ቢሆን አስቸግሬ ማድረግ የምችለውን ነገር ላስብበትና መልሰን እናውራበት››

‹‹በእውነት በጣም ነው የማመሰግነው…..ምን አልባት ጓደኞቾትን ሲያስቸግሩ የሚያስፈልግ ነገር ካለ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አሟላለሁ…፡፡››ሲል ቃል ገባ፡፡

‹‹ችግር የለም… የሚስፈልግ ነገር ካለ አሳውቅሀለው….እነደነገርኩህ አንተን እንድረዳህ የጠየቀኝ ሰው በጣም ወዳጄና ባለውለታዬ ነው…..እና በእኔ አቅም ማድረግ የምችለውን ነገር ሁሉ እንደማደርግና የአባትህን በእስር ቤት ውስጥ ያለውን አያያዝ ለማሻሻል ጥረት እንደማደረግ ልገልጽልህ አፈልጋለው…በተለይ አባትህን የመጠየቅ  መብትህን መልሰህ እንድታገኝ ማድረግ ምችል ይመስለኛል፡፡››

‹‹አመሰግናለው..ስልኮትን በጉጉት ጠብቃለው፡፡›› በዛው ተለያዩ
////
ፀአዳ  በአራተኛው ቀን ስሜቷን አብርዳ….መረበሿን አረጋግታ ልጇን ይዛ መጣች፡፡ከዶዶላ ተመልሳ አዳማ እስክትገባ ስልኳን አልከፈተችም ነበር፡፡ቤቷ ደርሳ አረፍ እንዳለች ከፈተችና ለአዲስ አለም ደወለችላት፡፡

አዲስአለም ከሰላምታ ሳይሆን ከስድብ ነው የጀመረችው‹‹አንቺ ቅሌታም…..ጤነኛ ነሽ ግን?››

‹‹ቀስ …ይሄ ሁሉ ቁጣ ናፍቆት ነው ወይስ ሌላ ምክያት አለው?፡፡››

በስድቧ ገፋችበት ‹‹ወሬኛ ነሽ እሺ…..ለመሆኑ አሁን የት ነሽ?››

‹‹ቤቴ ነኛ››

‹‹ማለት እዚህ አዳማ?››

‹‹አዎ..ምነው ሌላ ቦታ ቤት አለኝ እንዴ?››

‹‹እኔ ምን አውቅልሻለው….ግን ሳስበው በቅርብ አዲስአበባ ላይ ቤት የሚኖርሽ ይመስለኛል….በቃ ጠብቂኝ አሁኑኑ መጣሁ…፡፡››

‹‹ኸረ እኔ ራሴ መጣለሁ…፡፡››

‹‹መጣው እኮ አልኩሽ፡፡››ስልኩን ጠረቀመችባት፡፡

‹‹ዛሬ ልትደበድበኝ ሁሉ ትችላለች››ስትል አሰበችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ቤቱን ማስተካከል ጀመረች ..ተዘግቶ ስለከረመ እምክ እምክ ይላል…መስኮቱን ከፋፈተች…ሰንደል ለኮሶችና በየኮርነሩ ላይ ሰካካች… ቡና ለማፍላት ሲኔ ደረደረች፣ከሰል በማቀጣጠል ላይ እያለች አዲስ አለም መጣች፡፡

ጠየቀቻት ካሰበችው ጊዜ በጣም ፈጥና በመምጠቷ ተገርማ‹‹እንዴ ..!!ስትደውይልኝ መንገድ ላይ ነበርሽ እንዴ?››ስትል ….፡፡
ልትስማት ስትጠጋት ወደኃ ሸሸቻትና ገፍትራት ወደቤት ገባች….ፀአዳማ እያቀጣጠለች የነበረውን ከሰል ትታ ከኃላ ተከተለቻት፡፡

‹‹ምስር የታለች?››

‹‹ጎረቤት ልትጫወት ሄዳለች››

‹‹ቆይ አንቺ ግን ያምሻል..?እንዴት አንድ ነር ሳትነግሪኝ ብን ብለሽ ትሔጃለሽ…እሺ መሄዱንስ ሂጂ እንዴትሰ ስልክሽን ትዘጊያለሽ?››

‹‹ስልኬ እኮ ተበላቶብኝ ነው››

‹‹አረ ባክሽ..አሁን እኔን የምትሸውጂኝ ይመስልሻል?››

‹‹‹እሺ በቃ ማንንም ለማውራት ጥሩ ሁኔታ ላይ አልነበርኩም…በፀጥታ ማሰብ ነበር የፈለኩት..በዛ ላይ አንቺ የሰርግና የመልስ ግርግር ላይ ስለሆንሽ ልረብሽሽ አልፈለኩም››

‹‹ወይ ረበሺኝ እኮ..እኔን ብቻ ሳይሆን ባሌንም ጭምር ነው በደንብ የረበሺን፡፡››

‹‹እንግዲህ አዝናለው…..በጣም ይቅርታ›

‹‹ደግሞ ሰውዬሽ..አብዶልሻል….››

‹‹የቱ ሰውዬ?››ግራ በመጋባት ጠየቀች፡፡

‹‹ስንት ሰውዬ ነው ያለሽ…?ዘሚካኤል ነዋ..ከደበቅሺበት  ውለጂያት ብሎ ሊያንቀኝ››

‹‹እንዴ ደወለልሽ እንዴ?››
ምን ይደውልልኛል…በዛን ቀን ልክ ያንቺ መልእክት ደርሶኝ እሱን ከሚካኤል ጋር አንብበን እየተገረምን ሳለ ቤት ድረስ መኪናውን እያከነፈ መጣና ሰፈሩን በመኪናው ክላክስ አደበላለቀው…ምን ሆኖ ነው ብዬ ስወጣ መኪና ውስጥ አስገባኝና ከሰፈር ይዞኝ ሄደ….››ብላ የዛን ቀን የሆነውን በዝርዝር ተረከችላት፡፡›

ፀአዳ በሰማችው ነገር በጣም ተገረመች‹‹ፈፅሞ እንደዛ ያደርጋል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር…ግፋ ቢል ደውሎ የሆነ ነገር ይልሻል ብዬ ነው ያሰብኩት፡፡››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..?ልጁ እኮ ጨርቁን ጥሎልሻል››

‹‹ማለት?››

‹‹አፍቅሯሻል እያልኩሽ ነው››

‹‹እኔ ፍቅር አልፈልግም››

‹‹እና ወሲብ ነው ምትፈልጊው?
👍7119
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
_
__
///
‹‹ነይ የኔ ማር፣ ዝም በይ፣ ላደርቅልሽ እፈልጋለሁ።››ራሄል ትሁትን ከመታጠቢያ ገንዳው ውስጥ አውጥታ በፎጣው  ጠቀለለቻት።

ወደ ምትሄድበት የስብሰባ ቦታ ፀጋን መውሰድ እንዳለባት ወስናለች፡፡  ህጻኗን ዛሬ ከሰአት በኋላ  ለረጅም ሰዓት እንቅልፍ እንድትተኛ አድርጋ ስለነበር  ማታ ከሶስት ሰዓት በፊት   እንደማትተኛ ታውቃለች። ልብስ ልታለብሳት እየተዘጋጀች ሳለ ሕፃኗ ከንፈሯ ላይ በጥፊ  መታቻት። ትልቅ ሰው በጥፊ ያጠናገራት ነው የመሰላት‹‹አንቺ ትንሽ ድርዬ›› ብላ አጉተመተመች፡፡ ‹‹ምን ፈልገሽ ነው የምትደባደቢው?›› ጠየቀቻት፡፡

  በዛው ቅፅበት  የበሩ ደወል ጮኸ። ለመክፈት ፊቷን ስታዞር የራሄል እግር ይዛ  ታገለቻት ሳትወድ በግዷ ጎንበስ ብላ አቀፈቻት፡፡ አሁንም በፎጣው ተጠቅልላለች። ራሄል በረዥሙ ኮሪዶር ላይ ወርዳ የራሷን ክፍል አልፋ ወደ መግቢያ በር ቀረበች። መጥሪያው ከእንደገና ጮኸ…

‹‹መጣሁ፣ መጣሁ››ስትል ራሄል አጉተመተመች፣ አሁንም በደረጃው ላይ ነች።ከታች ስትደርስ የእብነበረድ ወለሉ ቅዝቃዜ በባዶ እግሯ ዘልቆ ተሰማት ፡፡በሩን በዝግታ ከፈተችው።ዶ/ር  ኤልያስ ነበረ፡፡

ወደ ውስጥ ስትጋብዘው ተንደርድራ ጉንጩ ላይ ተጣብቃ ልትስመው ፈልጋ ነበር…እንደምንም እራሷን ተቆጣጠረች፡፡
እሱ የፀጋ ሐኪም ብቻ ነው። እሱ የእህቷን ደህንነትን ሊቆጣጠር እናሊከታተል ብቻ ነው ወደቤታቸው የሚመላለሰው ። በማለት እራሷን ለማረጋጋት ጣረች፡፡ የዔሊ ሞቃታማ ሰማያዊ አይኖች ቀና ብላ ስትመለከት፣ውስጧ ተናወጠባት፡፡
‹‹ኤሊ ውሰደኝ…››ትሁት ጮኸች፣
ራሄል እህቷን ችላ ብላ ከኤልያስ ጋር ማውራቷን ቀጠለች፡፡‹‹አንዲት ብዙ ገንዘብ ለፋውንዴሽናችን የምትለግስ ሴት ማግኘት አለብኝ እና ምርጫ ስለሌለኝ ፀጋን ይዣት ልሄድ ነበር ያሰብኩት…ምን ትላለህ?››

‹‹ማታስቸግርሽ ከሆነ ምንም ችግር የለውም….››አላት

‹‹ እሱ የእኔም ስጋት ነው….ድፍረት ካልሆነብኝ ልትረዳኝ ትችላለህ?››

‹‹ለምን አይሆንም?እዚህ ሆኜ እንድጠብቅልሽ ነው የምትፈልጊው?››

‹‹ኮስተር አለችበት‹‹እሱም ይቻላል..ግን አብረኸን ብትሄድና እዛ ሴትዬዋ ጋር በምነጋርበት ሰዓት አንተ ፀጋን ታጫውትልኛለህ ብዬነበር ያሰብኩት…እኔም እንዲህ ሆና ይሆን ከሚል ስጋት ተገላግዬ በተረጋጋ መንፈስ ከሴትዬዋ ጋራ አወራለው››አለችው፡፡

ሳቀባት…….
በሳቁ ግራ ተጋባች‹‹ምነው ያልሆነ ነገር ተናገርኩ እንዴ?››

‹‹አይ…አሁን ኦርጂናል እናት እየሆንሽ እንደሆነ ስለታዘብኩ ነው…እዚህ ለእኔ እንኳን ቢሆን አምነሽ ጥለሻት ልትሄጂ አልፈቀድሽም…በእውነት ደስ ብሎኛል…አብሬችሁ እሄዳለው››

‹‹እሺ ይህችን ልጅ  ላልብሳት እና እኔም ለብሼ መጣን ….አስር ደቂቃ ታገሰን››

‹‹ችግር የለም..ሂዱ›› ፈቀደላቸው…ሄለን ፀጋን እንዳቀፈች ወደመኝታ ቤት አመራች፡፡ፀጋን ካለበሰች በኃላ የራሷን ልብስ ቀየረችና መስታወት ፊት ስትቆም ቅድም ፀጋ የመታቻት ከንፈሯ ቀልቶ እና አብጦ ተመለከተች….፡፡
ወደፀጋ ዞራ ልንቦጯን ዘርግታ እያሳየቻት ‹‹ውይ አንቺ ልጅ ….እይው እስኪ ያደረግሺኝን››
ፀጋ እየተመለከተቻት ሳቀችባት፡፡ራሄል ከፍሬጅ ውስጥ በረዶ አወጣችና ያዘችበት፡፡ከዛ ቀይ ሊፒስቲክ አወጣችና በስሱ በመቀባት የቀላውን ከንፈሯን ከሌላው ክፍል ጋር አመሳሰለችው፡፡
ከዛ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ከተረዳች በኃላ ቦርሳዋን ይዛ በአንድ እጆ  የፀጋን እጅ ጨብጣ ወደሳሎን ሄደች፡፡ተያይዘው ከቤት ወጡ፡፡

ራሄል ከንፈሯን አስጨነቀች፣ ጸጋና መሀከላቸው አድርገው ወደ  ራሄል መኪና ሲያቀኑ ልክ በቅርብ የተጋቡ ባልና ሚስቶች ይመስሉ ነበር፡፡ፀጋን ከኋላ በስርዓቱ ቀበቶዋን አሰሩላትና እነሱ ገቢና ጎን ለጎን ተቀመጡ..መኪናውን የምታሽከረክረው ራሄል ነበረች፡፡
ለተወሰነ ደቂቃ በዝምታ ነበር የተጓዙት ያሉት፡፡በፋውንዴሽኑ ውስጥ ስላሏት ችግሮች ለአንድ ሰው መንገር ፈልጋ ነበር። የሮቤል ሚስጥራዊነት አሳስቧታል።ትናንት ማታ  አነጋግራዋለች። ለምን ጥሪዋን እንዳልመለሰላት ስትጠይቀው ሞባይሉን ቤቱ ረስቶ እንደነበር  ነው የነገራት።በበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ያገኘኛቸውን መረጃዋች በማጠናከር ላይ ተጠምዷ ስለነበር ጊዜ አልነበረውም .. እሱ የሚፈልገው አንድ ነገር እንዳለ በግልፅ ነግሯታል….እሷም ልታምነው ፈለገች ነገር ግን አልቻለችም እና ዛሬ ከሰአት በኋላ በፋውንዴሽን ከኮምፒውተሯ ጋር ስትገናኝ፣ ሌላ ሰው የቢሮውን ኮምፒውተር ላይ እንደገባ አስተዋለች። መረጃዋን የሚበረብር ማን እንደሆነ ግራ ተጋብታለች፡፡

የአእምሮዋን ፍጭት ያነበበ ይመስል‹‹የምታናግሪው ሰው አለ?›› ስል ጠየቃት። ራሄል ወደ
‹‹ስለዚህ ነገር በተለምዶ ከአባቴ ጋር ነበር የምንነጋገረው፣ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ እንደምታውቀው በእናቴ ጉዳይ በጣም የተጠመደ ነው እና እሱን ማስቸገር አልፈልግም።››

‹‹የፋውንዴሽኑ ቦርድ እንዴት ነው? አይረዳዱሽም እንዴ?››

ራሄል አንገቷን በአሉታ ነቀነቀች። ‹‹አይ አሁን ያጋጠመን … ውስጣዊ ችግር ነው እነሱን ወደዚህ ጎትቼ ማስገባት አልፈልግም….እኔ በራሴ በምችለውን መንገድ መፍትሄ መፈለግ አለብኝ››

‹‹ሁሉንም ነገር በራስሽ ብቻ ማድረግ የለብሽም››ኤሊ ተቃወማት ።በዚህ ጊዜ የሚሄዱበት ቦታ ደርሰው መኪናዋን እያቆመች ነበር፡፡
ትንሽ ሳቅ ብላ‹‹በቅርብ ጊዜ ሁሉንም ነገር በራሴ የማደርገው ይመስላል››ስትል ቦርሳዋን አንጠልጥላ ከመኪናዋ ወረደች፡፡ራሄል ከመኪናው ጎን በመጣችበት ጊዜ ኤሊያስ ፀጋን ከታሰረችበት ቀበቶ እየፈታት ነበር። የዳይፐር ቦርሳውን ለራሔል ሰጣት እና በሩን ዘጋው።  ራሄል ወደ ወ.ሮ ላምሮት መግቢያ ደረጃ ሲወጡ‹‹ልክ  እንደ ትንሽ ቤተሰብ እንመስላለን››ስትል አሰበች።

መግቢያ በራፉ ላይ ደረሱና ደወሉን ተጫኑት፡፡ ‹‹ማግባት ምን አይነት ጣዕም ሊኖረው  ይችላል?››እራሷን ጠየቀች፡፡ ጋብቻ ከኪሩቤል  በኃላ ያልተጠቀመችበት ቃል ነበር።የስሙ ትዝታ የደስታ ስሜት እንዲሰማት አደረጋት፣ ከዚያም የታማኝነት መጉደል ውስጧን ሲያንቀጠቅጣት ተሰማት። እንዲህ ያሉ የቀን ህልሞችን እንድታልም ስውር ኃይል የነበረው ኪሩቤል ብቻ ነበረች። ከዚህ በፊት ወይም በኋላ ማንም ሌላ ሰው ያንን  ስሜት ሊቀሰቅስባት አልቻለም ።
ራሄል ድጋሚ ደወሉን ልትደውል ስትል በሩ በራሱ ተከፈተ። ራሄል ወደ አንድ ትልቅ አዳራሽ መሳይ ሳሎን ውስጥ ገባች ወዲያው ጥርት ያለ ሰማያዊ ቀሚስ የለበሰች ሴት ተቀበለቻት።

‹‹ወ/ሮ ላምሮት ከኋላ ባለው አትክልት ስፍራ እየጠበቀችሽ ነው።››በማለት ዘወር ብላ ወደ ሌላ በር መራቻቸው፡፡ ወደ ዔሊ ተጠግታ በሹክሹክታ  ‹‹ፀጋ ከስርህ እንድትርቅ አትፍቀድላት። ››ስትል ተናገረች፡፡ፈገግ አለላት….በፊት ፀጋን በተመለከተ እንዲህ አድርጊላት… ይሄንን ተጠንቀቂላት… እያለ የሚያጨናንቃት እሱ ነበር..አሁን ግን ይሄው በተቃራኒው ለእሱ መመሪያ እየሰጠችው ነው፡፡እያሳየች ባለችው ለውጥ በውስጡ እርካታ ተሰማው፡፡
ወ.ሮዋ ከተቀመጠችበት መድረክ መሳይ ውብ ቦታ ባሻገር በሁለት በኩል በጡብ ግድግዳ የተከበበ አበባ ሞልቶ ነበር። ወ.ሮ ላምሮት በትልቅ ዣንጥላ በተከለለ የመስታወት ጠረጴዛ ጎን ከተቀመጠችበት ልዩ ወንበር ተነስታ ‹‹ ጤና ይስጥልኝ ራሄል …በድጋሚ እንኳን ደህና መጣሽ ›› አለቻት ፡፡
60👍3😱2👏1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///

ፀሀፊዋ አለምን አቁማ ወደዳኛው ቢሮ ተራማዳ በራፉን በጥንቃቄ አንኳኳች እና ወደውስጥ ገባች…ብዙ ሳተቆይ ተመልሳ ወጣችና ወደአለም ቀርባ …በአጭሩ

‹‹ሊያይሽ ተስማምቷል ››አለቻት፡፡

"አመሰግናለሁ።" አለችና እሷን አልፋ ወደ ክፍሉ ገባች።

"ወ.ሮ አለም …በዚህ ጊዜ ስለምንድነው የምታናግሪኝ?" ዳኛ ዋልልኝ ኮቱን ከመስቀያው ላይ እየጎተተ ነበር የሚያናግራት። "ያለ ቀጠሮ ሰው ቢሮ የመግባት መጥፎ ልማድ ያለሽ ይመስላል። እንደምታየው እኔ ልወጣ ነው። ልጄ ስርጉት ያለ እኔ እራት መብላት አትወድም እና እሷን ማስጠበቅ ለእኔ አሳፋሪ ነው።"

"ሁለታችሁንም ይቅርታ እጠይቃለሁ ክቡር ዳኛ… ለፀሀፊዎ እንደነገርኩት ጉዳዬ በጣም አስቸኳይ ስለሆነብኝ ነው ።"

"እሺ…ልስማው?"

"መቀመጥ እንችላለን?"

" ቆሜ መስማት እችላለሁ …ምን ልትነግሪኝ ፈልገሽ ነው?"

"የእናቴ አስከሬን ተቆፍሮ እንዲወጣ እና  ዳግም የፎረንስክ ምርመራ እንዲደረግበት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲሰጡልኝ እፈልጋለሁ."

ዳኛው ቀስ ብሎ ወንበሩ ላይ ተቀመጠ። አለም ግልፅ የሆነ ጭንቀት ተመለከተችበት።

"ይቅርታ፣ ምን አልሺኝ?፧"

"ክቡር ዳኛ  ያልኩትን እንደሰሙኝ አምናለሁ፣ ግን ጥያቄዬን መድገም አስፈላጊ ከሆነ፣ አደርገዋለሁ።"

ዳኛው  እጁን አወዛወዘ። "አይ. ቸሩ ጌታ አይሆንም. አንድ ጊዜ መስማት በቂ ነው…ለምን እንዲህ አይነት አስቀያሚ ነገር ማድረግ ፈለግሽ?"

"የመፈለግ ጉዳይ ሳይሆን ግድ ሆኖብኝ ነው, በጣም  አስፈላጊ ነው ብዬ ባላምን ኖሮ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልጠይቅም ነበር."

"አስቲ ተቀመጪና…  ምክንያቶችሽን አስረጂኝ።››

"እናቴ ላይ ወንጀል ተፈጽሟል ፣ነገር ግን ትክክለኛው ፍርድ ተገኝቷል ብዬ አላምንም ።"

"እንደዛ ማድረግ አትችዬም " ብሎ ጮኸ።
"አልሰማሽም።ከአመታት በኃላ ድንገት ከመሀከላችን ተገኘሽ፣ ወዲያው መሠረተ ቢስ ውንጀላ ይዘሽ ትረብሺኝ ያዝሽ፣ ለበቀል ቆርጠሻል።"

"ይህ እውነት አይደለም" ስትል ለመከላከል ሞከረች ፡፡ " ለመሆኑ ሀለቃሽ ግርማ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል?"

"አሱ ለጊዜው የለም ..ለጥቂት ቀናት እረፍት ወሰዶ ወደ አዲስአበባ የሄደ ይመስኛል።›› ዳኛው ተናደደ።

" ለማንኛውም ጥያቄሽ … ጥሩ ሀሳብ አይመስለኝም››

" ክቡር ዳኛ ማስረጃ እንድፈልግ ይፈቅዱልኛል?"

"ምንም ማስረጃ አታገኚም" ሲል አፅንዖት ተናገረ፡፡

"ከእናቴ አስከሬን የተወሰነ መነሻ ሚሆነን መረጃ ልናገኝ እንችላለን."

" የተገደለችውና ሬሳዋ የተገኘው እኮ ከዛሬ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ነበር ።"
"በዚያን ጊዜ ለሬሳ ምርመራ ለማድረግ ቴክኖሎጂዎች አልነበሩም… ..በአሁኑ ጊዜ ግን ነገሮች የተለዩ ናቸው፡፡እኔ በግሌ ጎበዝ የተባለ የፎረንሲክ ስፔሻሊስት አውቃለሁ።አሁን ለሚከሰቱ የወንጀል ድርጊቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ከእሱ ጋር የመስራት እድል ነበረኝ …እሱና ጎደኞቹ በጣም ውጤታማ ናቸው ..በዛን ወቅት ባለው ቴክኖሎጂ ሊገኝ ያልቻለ የሆነ ነገር ሊያገኝልን እንደሚችል ዋስትና እሰጥዎታለሁ።››

"ጥያቄሽን እንደጥያቄ እወስደዋለሁ።››

"መልሱ ለዛሬ ማታ ቢደርስልኝ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው ።"

" ይቅርታ ወ/ሪት አለም ማድረግ የምችለው በአንድ ጀምበር አስብበት እና በጠዋት መልሱን እሰጥሻለው።እስከዛው ሀሳብሽን ለውጠሽ ጥያቄውን እንደምትሰርዢ ተስፋ አደርጋለሁ።"

"አላደርገውም።››

ዳኛው ከተቀመጠበት ተነሳ። "ደክሞኛል፣ በዛ ላይ ርቦኛል፣ እናም በዚህ የማይመች ቦታ ላይ ስላስቀመጥሺኝ ተበሳጫችቻለሁ።" የክስ አመልካች ጣት አነጣጥሮባት። "እኔ እንደህ አይነት የተጨመላለቀ ነገር አልወድም."አላት፡፡

" ይህ በጣም አስፈላጊ ባይሆን እኔም አላደርገውም ነበር."

"አስፈላጊ አይደለም."

"እኔ ደግሞ እንደሆነ አምናለሁ" ስትል በግትርነት መለሰች።

" አሁን፣ በቂ ጊዜዬን ወስደሻል። ይሄኔ ልጄ ስርጉት ተጨንቃለች።››

‹‹ ደህና ይሁኑ ብላ ።"ከክፍሉ ወጣች።
///
አለም ቀጥታ  ወደመኪናዋ አመራችና ወደቤቷ ነው የነዳችው… መንገድ በትራፊክ ስለተጨናነቀ ወደቤቷ ለመመለስ ረጅም ጊዜ ነበር የወሰደባት፡፡

ክፍሏ ገብታ አልጋዋ ላይ ተዘርራ ትንሽ እረፍት ለመውሰድ ሞከረች…ከዛ ተነሳች….ማስታወሻዎቿን እንደገና ለመገምገም ሞከረች….ወዲያው ሰለቻት፡፡ ቴሌቪዥኑን ለመክፈት ወሰነች። ሪሞቷን አነሳችና ከፈተች፡፡ፊልም ላይ አደረገችውና ሰውነቷን ለመለቃለቅ ልብሷን አወላልቃ ወደሻወር ቤት ሄደችና መታጠብ ጀመረች……ታጥባ ከመጨረሷ በፊት አንድ ሰው በሯን ሲያንኳኳ ሰማች… እርጥብ ፀጉሯን በፎጣ ጠቅልላለች። ረጅምና ነጭ ካባዋን አደረገችና እና ወገቧ ላይ ያለውን መቀነት ለማሰር እያስተካከለች ወደሳሎን ሄደችና በበራፉ ቀዳዳ በማጮለቅ ማንነቱን ለማረጋገጥ ሞከረች፡፡

የሰንሰለት መቆለፊያው እስከሚፈቅደው ድረስ በሩን ከፈተችው "እንኳን ደህና መጣህ ኩማንደር ምነው በሰላም?"

ኮስተር ብሎ"በሩን ክፈቺ" አላት

"ለምን?"

" ካንቺ ጋር መነጋገር አለብኝ።"

"ስለ ምን?"

‹‹ወደ ውስጥ ካስገባሺኝ እነግርሻለሁ።
አለም  አልተንቀሳቀሰችም."በሩን  ልክፈት  ወይስ  ምን?"እለች  ከራሷ  ጋር  ሙግት ገባች፡፡ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለውን ሰዓት ተመለከተች….ለሶስት እሩብ ጉዳይ ይላል፡፡
"እዚያው ሆነህ ላናግርህ እችላለሁ።"

"በሩን ክፈቺ" ብሎ ጮኸ።

‹‹ሰውነቴን እየታጠብኩ ነበር."አለም ሰንሰለቱን አላቀቀችና በሩን ከፍታ ወደ ጎን ቆመች።

"አንድ ሰው እየጠበቅሽ ነበር?"

"አይደለም."

ኮፍያውን ከጭንቅላቱ አወለቀና ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ … ወደ ወንበር ሄዶ ተቀመጠ እና ወደ ቴሌቭዥን ስክሪን ተመለከተ፣ ልብስ ያልለበሱ ጥንዶች ተቆላልፈው ይሳሳማሉ ። ካሜራው የወንዱ ከንፈር ከሴቷ ጡት ጋር ሲጣበቅ እያሳየ ነው፡፡

"ስለአቋረጥኩሽ መናደድሽ አይገርምም።››አላት ሪሞቱን አነሳችና አጠፋችው "አያየሁት አልነበር."
"በራፍሽን ለሚያንኳኳ ሰው ሁል ጊዜ በርሽን ትከፍቺያለሽ?"

"በዚህ ከተማ ውስጥ ከፍተኛው የህግ አስከባሪ የፖሊስ መኮንን ነህ። አንተን ማመን ካልቻልኩ ማንን ማመን እችላለሁ?ይልቅ በዚህ ማታ ለምን መጣህ? እስከ ጠዋት ድረስ መጠበቅ አልቻልክም?"

"ዳኛ ዋልልኝ ደውሎልኝ ስለጠየቅሽው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነገረኝ.››

በንዴት ሲመታ የነበረው ልቧ በፍጥነት ቀዘቀዘ፣ "በዚህ ከተማ ውስጥ የግል የሚባል ነገር የለም ማለት ነው?"ብላ ጠየቀች፡፡

"ብዙ አይደለም"

"በከተማው ክልል ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው የእናንተ ቡድን ሳይፈቅድለት ማስነጠስ የሚችል አይመስለኝም።"

"እንደፈለግሽ ተርጉሚው …አንቺ ዙሪያችን እየተሸከረከርሽ ጉድጓዳችንን ስትቆፍሪ ምን እንድናደርግ ጠብቀሽ ነበር?"

"የእናቴን መቃብር እንዲከፈት ማድረግ ትክክለኛ የግድያዋን መንሴ ለማወቅ ወሳኝ እርምጃ ነው ብዬ ባላስብ ኖሮ የምረበሻት ይመስላችኋል?" ሞቅ ባለ ስሜት ጠየቀች ።

‹‹አንቺ ቋሚንም ሆን ሟችን ከመረበሽ ውጭ ምን ስራ አለሽ?››

"አምላኬ ሆይ ጥያቄውን ማቅረብ እንኳን ቀላል ብሎኝ ያደረኩት ይመስልሃል? እና ዳኛው ከ አንተ እና ከሰዎች ሁሉ ጋር መማከር ለምን አስፈለገው?"

‹‹ለምን ብለሽ ትጠይቂያለሽ እንዴ?… ተጠርጣሪ ስለሆንኩ ነዋ?"

"ዳኛው በዚህ ጉዳይ ከአንተ ጋር መወያየቱ ሞያዊ ሥነ ምግባር የጎደለው ሽማግሌ መሆኑን ነው የሚያሳየው "

"እኔ እኮ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ነኝ፣ አስታውሺ?"
39👍4