አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ጎይቲ አንተነህ ከሎ ሆራ አጎት ቤት እንደ መጣች ፈጽሞ መንፈሷ ሊረጋጋላት ባለመቻሉ ካርለት የምታደርገውን አጣች" ጎይቲ ጽጕሯን ስትላጭ ካርለት ብቸኝነት እንዳይሰማት አብራት ተላጨች በከሰልና በቅቤ የተለወሰውንም ቅባት መላ ሰውነቷን ስትቀባ ካርለትም አብራት ተቀባች"

ጎይቲ አንተነህና ካርለት አልፈርድ ቆጥ ላይ ከተደበቁ በኋላ ካርለት ጎይቲን ለማጽናናትና ለማደፋፈር ብትጣጣርም አልሳካልሽ አላት ጎይቲ እንዲያውም ፊቷን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዞረችባት
ካርለት ሁኔታው አስደንጋጭ መሆኑን ብታውቅም ሦስት ወር  እስኪሞላቸው ድረስ ቆጡ ላይ መቆየት ነበረባቸውና እስከዚያ ድረስ
በመካከላቸው እርቀ ሰላም እንደሚወርድ ተመኘች"

ቀኑንና ምሽቱን ቆጥ ላይ ከቆዩ በኋላ ለአንድ አፍታ ወረድ ብለው ከሎ ከመምጣቱ በፊት ለመናፈስ ወጡ" ጎይቲ አነተነህ ቆጥ ላይ መውጣቱ አልዋጥልሽ ብሏታል።

«አሁን እሱ የወንድ ልብ አግኝቶ እኔን ሊመታኝ? በየትኛው ወኔውና ጀግንነቱ፤ ወይ ሲያየኝ እሱ ራሱ ባልተርበተበተ አይደል?
ወይኔ ጎይቲ የወንድ ልጅ ዱላም ይናፍቃል ለካ?» አለች ለካርለት ይሁን ለማን እንደተናገረች ሳይታወቅ።

ወደ ጎጇቸው ሲመለሱ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ከከሎ ሆራ ጋር ፊት ለፊት ተገናኙ" ከሎ ሆራ ሁለቱንም ሲያይ ደንገጥ ብሎ ቆመ!
ካርለት በዓይኗ ጠቅሳ እንዲመታት ልትነግረው ፈልጋ ነበር። ለእሱ
«ና ምታት» ብላ በዓይን ለማመልከት እንዴት እንደምታደርግ ስከታስብ ግን እሱ ከቆመበት ደረሱ። ከሎ ሆራ መንገዱን ለቆ
አሳለፋቸው። ካለፉ በኋላ ግን ተሰማው፤ በባህሉ መሠረት እንዳያት ደህና አድርጎ መግረፍ ነበረበት። ያን ሲያስብ የብሽቀት ስሜት ታየበት፤ ጎይቲ አንተነህን ይወዳታል፣ ባህሉንም ያከብራል
ቅሬታና ቂም የሚይዝ ከሆነ አካል በማይጎድልበት መንገድ መምታቱ
የሚያመጣው ችግር የለም።

«ወደፊት ግን ይህን ጥፋት መድገም የለብኝም" በመምታቴ ጎይቲ አንተነህን የሚሰማት ነገር የለም። እንዲያውም እሷን ባለመደብደቤ ቅሬታ ሊያድርባት ይችል ይሆናል» እያለ፣ ራሱን ወቅሷል"
ካርለትም በበኩሏ ትንሽ በሽቋታል። ከሎ ሆራ ጎይቲ አንተነህን ፊት ለፊት ባገኛት ጊዜ ሁሉ እንዲገርፋት ተመካክረዋል። ጎይቲ
አንተነህ ደግሞ የከሎን የፍቅር ፍርሃት ባለመረዳት ሲርበተበት ስታየው ባሕርይው ያስጠላታል። ከሎ ወንድ ወንድ አልሸትሽ
ብሏታል። «ከሎ ትክክል አልሠራም። እሱ ጎይቲን ልክ ከተማ እንዳየው
ብዙ ሕይወቱን እንዳሳለፈበት በጠባይ ሊያግባባት፣ ሊያቀርባት
ፍቅሩን ሊገልጽላት ይፈልጋል" ጎይቲ ግን ወንድ ልጅ በቅድሚያ የምትፈልገው ኰስታራነት ነው ኵሩ ወንድ፣ ሸንቆጥ የሚያደርግ ወንድ፣ እሷን በፍቅር ገርቶ፣ በፍቅር አብሯት መጋለብ ይችላል
ሴት ልጅ ዱላ ሲያርፍባት የሴትነት ፍላጎቷ ከአሸለበበት ይቃል»
አምጭ አምጭ የሚላት፣ ፍቅር የሚናፍቃት፣ ድሪያ የሚታወሳት ያኔ ነው፤ ከሎ ደግሞ ይህን አልተረዳውም። እንግዳ ነገር ሆኖበታል ሕጉን እያወቀ በተግባር ግን አያከብርም። ይህ ደግሞ ስሕተቱ ነው ካርለት በእንግሊዝኛ ለጎይቲ ነገረቻት። ጎይቲ አንተነህ ግን ያለችው  በጭራሽ አልገባትም እንግሊዝኛ ደግሞ የት አውቃ

ጎይቲ አንተነህ አጠገቧ ያለችው ቀውስ ብቻዋን ስትለፈልፍ ብትደነቅም፣ እሷም ተመሳሳዩን ፈጸመች።

«ይኸዋ ይህ ቦቅቧቃ! እንኳንስ ሲያየኝ እንደ ወንዶቹ ሊገርፈ
ይቅርና መንገድ ለቆ አሳለፈኝ" ባል እኔ ነኛ! እሱ ሚስት ነው እንዴት ሆኜ ከዚህ ሴት ጋር እኖራለሁ? ምነው ያን ቀን ደልቲ
ገልዲን ብዬ ባልሄድሁ ኖሮ፤ እሱን ብዬ በመሄዴ ቀናው እንጂ የታባቱ ያገኘኝ ነበር ይህ ሴት" ሴት ልጅ የባሏ ዱላ ሕይወቷ ፍቅሯ ነው" ታዲያ ይህ ሰው እኔንኮ ሕይወቴን እያጠፋ ነው" እሽ
የኔስ ነገር ይቅር ነገር ግን የሚወለዱት የሁለት ሴት ልጆች መባላቸው አይደል? ወይኔ ያልታደሉት" ወይኔ ወይኔ» እያለች፣ እንባዋ
ታወርደው ጀመር"
ካርለት ትንሿን ቴፕ ከፍታ የምትለውን እየቀዳች በማስታወሻ ደግሞ የሚሰማትን ትከትባለች» ካርለት በአንዳንድ ሁኔታ ላይ እሷም ራሷ እየተስማማች መጣች» በአገሯም፣ አንዳንድ እውቅ ሴቶች ስለ ወንድ ፍቅረኛቸውና ከእሱ ስለሚጠብቁት ባሕርይ ሲያወሱ ነካ አድርገው የሚያልፉት ነገር አለ፣ «ከፍቅረኛዩ ጋር ስንላፋ
ስንታገል፣ የፍቅር ዱላ ገላዬ ላይ ሲያርፍ ልቤ እስኪጠፋ ድረስ ራሴን እሰጠውና የሱን ደግሞ ለመውሰድ ሙሉ ፍላጎት አሳያለሁ ከዚያ በኋላ የምንሠራው የፍቅር ጨዋታ ሁሉ እንደ አይስhሬም እየጣፈጠኝ፣ መላ አካሌ ከጸጕር እስከ እግር ጥፍሬ በርካታ
ሲንበሸበሽ ይሰማኛል" እንደዚህ አድርገው ከኔ ጋር የተጫወቱ ወዶች የፍቅር ዙፋኑን ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም» ብለው
የተለያዩ ሴቶች አስተያየት ሲሰጡ ሰምታለች።

እሷም ቢሆን አንዳንድ ልምዶችን አሳልፋለች" አንድ ጊዜ፣ ስሜ ጃክ ነው ብሎ የተዋወቃት አሜሪካዊ፣ ማንችስተር ውስጥ
ለጉዳይ መጥቶ አንድ የምሽት ዳንስ ላይ ይተዋወቃሉ“ ካርለት
በእርግጥ ወደ ዳንሱ ቦታ የሄደችው ከወንድ ጓደኛዋ ከዴቪድ ጋር ነው ታዲያ አሜሪካዊው አንድ ሁለት ጊዜ በትእዛዝ መልክ ዳንስ
ጋበዛትና ሰውነቷን በጠንካራ እጆቹ ጠበቅ አድርጎ እያሸ፣
አሳመማት። ቀደም ብላ ባሳለፈችው ሕይወቷ ወንዶች እንደዚያ ሰው
አድርገዋት አያውቁም" ሰውነቷን የሚደባብሱት ቀስና ላላ አድርገው
ነው። ሰውዬው ግን መሞረዱ አንሶ በረጅም እጁ መቀመጫዋን ደህና አድርጎ ቸብ ቸብ አደረገላት «ተው» ማለት እየፈለገች፣ ቃሉ ግን
ከጕሮሮዋ አልወጣልሽ አላት" በእርግጥ፣ ዴቪድም ከሌላ ሴት ጋር እየደነሰ ስለነበር እነሱን ልብ አላላቸውም።

አሜሪካዊው ፍጹም በማታውቀው መንገድ ሰውነቷን እየመታ፣ እየሞረደ፣ ልቧን ስልቱን አስቀየረው ከንፈሯን እንኳን
ሲስማት የንከሻ ያህል ሆኖባት እግሯን አንሥታ ለመጮህ ትንሽ ቀርቷት ነበር ግን አልጮኸችም" ዳንሱ አብቅቶ ሲለያዩ ካለልብ ወደ ቦታዋ ተመለሰች እንደ ምንም ታግሣ ሁለት ጨዋታዎችን
አሳልፋ ልቧን ወደ ቦታው ለመመለስ ወደ አሜሪካዊው ሰው ሄደች።
ቆንጅት እንደምትመጪ አውቅ ነበር...» ብሎ አሜሪካዊው ተመጻድቆባታል" ግን ፊቷን አዙራ አልተመለሰችም፤ ተመልሳ ካቴና እጆቹ መሃል ወደቀች ሞራርዶ፤ ቸባችቦ፤ ብድግ አድርጎ ተሸክሟት ወደ አንድ ክፍል ሲገባ፣ እግሮቿ አልተፈራገጡም"
እጆቿ አልተወራጩም፤ አፏም አልቀባጠረም።

ካርለት ይህንን አሜሪካዊ እስከ አሁን ድረስ በዚያች ለሰዓታት ብቻ በዘለቀች የፍቅር ጨዋታ የማትረሳው ትዝታ አስታቅፏት ነግዷላ" ያንን ሰው ለብዙ ጊዜ የተካው ወንድ አልነበረም። ኖራ ኖራ ግን ሐመር ላይ ተመሳሳዩን አገኘች" የሷም ብቻ ሳይሆን የጎይቲም የሆነው ሰው በእርግጥ ለየት ያለ በመሆኑ ሳይወዱ በግድ ሌላ ወንድ ቢያስንቃቸው አይፈረድባቸውም"
ካርለት ቆጥ ላይ እንዳሉ እንዲህ በሐሳብ ተዘፍቃ ቆየችና እናቷ ትዝአሏት" ስለዚህ፣ ደብዳቤ ለመጻፍ ብዕርና ወረቀቷን
አስተካከለችና መጻፍ ጀመረች።

ውድ እናቴ፣

ምን ጊዜም እንደማፈቅርሽ፤ እንደማልምሽ የምትዘነጊ
👍23🤔1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


“…ሶራ- የባህል ትንሽ ትልቅ አለው ብዬ ላነፃፀር
አልሻም። ልምዴና እውቀቴ ገና ውስን ነው: የባህል ልዩነት ግን አኗኗር ልዩነት እንደሚያመጣ አውቃለሁ፡፡

“ሁሉም ሰው ያለበትን አካባቢ ከሌላው በተሻለ ያውቃል! ይጠቀማል አያቴም ከለመደው ባህል ወጥቶ ካለፍላጎቱ ወደ
አለመደው ባህል ከመጣ በኋላ አስተሳሰቡ ከዘመነው ህብረተሰብ አንፃር ያነሰ ቢሆንም ከዚህኛው ህብረተሰብ የተሻለ ትዕግስትና ጨዋነት የነበረው ከዚህኛው የነበረው በመሆኑ ሴት አያቴን አስባውና
አልማው ያልነበረውን በጥቁር ፍቅር እንድትንቦራችና አያቴ ከዚህ
ዓለም በሞት ከተለየ በኋላም ፍቅሩ ጥቁር ድመት አቅፋ እንድትውል አድርጓታል፡

“ወንድ አያትሽን በመልክ ታውቂያቸዋለሽ? ሶራ ጠየቃት:

“ልጅ ነበርኩ እንጂ አስታውሰዋለሁ። ከእንጨት ጠርቦ የሰራት ትንሽና ልዩ በርጩማው ላይ ቁጭ አንዳንዴም ጋደም ብሎ
ይንተራስና ሽቅብ ሽቅብ እያየ ሰማዩ ላይ ማፍጠጥ ይወዳል:

“እኔም ከሌሎች ጋር ስሆን መዝለልና መጫወት
እንደማልወድ ሁሉ እሱ ደረት ወይ ትከሻ ላይ ሆኜ ግን ለረጅም ጊዜ
ከሚቆዝመው ጥቁርና ልዩው አያቴ ጋር ፀጥ ስለምል ሴት አያቴ፡-

“ሎካዬ! ካንተ ጋር ስትሆን ለምን ዝም እንደምትል
ታውቃለህ?" ስትለው  ዘወር ብሎ ወይም አይኖቹን ከሰማዩ ላይ መልሶ ያያታል።

“ስለምትፈራህ ነው አንተ ስ
ለህፃንም ለአዋቂም ዝግ ነህ አዕምሮህ የዕድሜ ልዩነትን አይገምትም! መሣቅ መጫወት ለልጆች
ምን ያህል ጠቃሚ መሆኑን አታስብም…” ትለውና ለመውሲድ እጅዋን ስትዘረጋልኝ በእንቢታ ደረቱ ውስጥ ድብቅ እላለሁ፡

“ወለላዬ! ሂጂ፤ አብረሽኝ መሆንሽን እየዘነጋሁ በዝምታ እኔ የምፈራው አንሶኝ አንችንም አስፈራሁሽ ውሰጃት :ኜስ
ላጫውታት አልታደልሁም" ይላታል። ያን ጊዜ በትናንሽ እጆቼና እግሮቼ ቁልፍ አድርጌ እይዘውና “አልሄድም' እላለሁ

“ያኔ ሴት አያቴ ትኩር ብላ ታየንና ቀስ ብላ መጥታ
ትከሻውን ተደግፋ! …ሎካዬ ለምን ደስተኛ አትሆንም እወድሃለሁ እኮ መሣቅ መጫወት ግን ልትለምድልኝ አልቻልክም: ለምን
ታሳቅቀናለህ! ስትለው ዝም ብሏት ይቆይና፡-

"አኜስ  እባክሽ ተይኝ" ይላታል:

ከኔ በላይ የሚቀርብህ ማን ሊመጣ ይችላል፡፡ ጭንቀትህ ውስጣዊ ብሶትህ ጊዜ የማይሽረው ዝምታህ ምንድነው?” ስትለው፡-

“የአባቴ  ልማድና ወግ  ከብቶቼ…"ሃሳቡን ሳይጨርስ
አይኖቹን ይጨፍናል

“የአንተ አገር ከብቶች ከኛ ይለያሉ?"

“እንዴታ! ይለያሉ እንጂ።"

“በምን?”

“በማእረግ ፧ አኜስ!  ከብት ከስጋና ወተቱ ይልቅ ቅሩ
ያጠግባል። በምላሱ ሲልስሽ በሽንቱ ስትታጠቢ እነሱ እያገሱ አንች
እያንጎራጎርሽ ስትከተያቸው
ስትውይ የሆዳቸውን
ጩኸት እያዳመጥሽ
ትንፋሻቸውን እየሞቅሽ
አብረሻቸው ስትተኝ…
የህይወት ቁርኝቱ የተፈጥሮ ሰንሰለቱ በፍቅር የተገመደ ነውር ።

“እዚህ ግን ከብቶችና እኔ አረም ነን። የምግብ ክምር
ይሰጠንና ታስረን የምንውል  ማግሳትና ማንጎራጎር የማንችል…"ሲላት ሴት አያቴ በወንድ አዬቴና ላይ ያለ የሌለ እርግማን ታወርድበታለች፡፡

“ምንም ሳይመልስላት አይኖቹን አድማስ ላይ ይተክላል። የእጅ ጣቶቹ ግን የሰራ አካላቴን ሳይታክቱ
ስለሚደባብሱኝ የመጨረሻውን ሳላውቅ እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ይወስደኛል፡፡

“እና! የሴት አያቴ ዘመዶች ሴት አያቴን፡

“አፍሪካዊው ሎካዬን በማግባቷ ብዙ ነር ጎድሏታል እያሉ
ኢያቴን ለምን አብራው እንደምትኖር ሲጠይቋት-

ዝምታው ልቤን በፍቅር የባህር ጨው አድርጎታል::
የፍቅር ነፃነቴም ያስደስተኛል ሎካዬን እንለያይ ብለው እሺ እህትና ወንድም እንሁን 'እንዳልሽ' ከማለት ሌላ ታቃውሞ ግዴታዬ መለማመጥ ፍርሃት ስለማላይበት ከእሱ መለየት የማይታሰብ ነው ብላ አፋቸውን ታሲዛቸዋለች:

“ወንድ አያቴ ሎካዬ በግር መጓዝም ይወዳል! በተለይ
በረፍት ቀኑ ከተማው መሃል ካለው መናፈሻ የተወራረደ ሰው ሄዶ አያጣውም እፅዋት ስር ይገባና አላፊ
አግዳሚውን ሳያይ እንደ ስነ
ፍጥረት ተመራማሪ አይኑን ሰማዩ ላይ ሰክቶ በርጋታ ለብዙ ጊዜ ይቀመጣል።

ሶራ ወንድ አያቴ ማንም ሊረዳው ከሚችለው በላይ ውስጡ ናፍቆት ትዝታ የቦረቦረው ነበር ዘመናዊነት ደስታን ሊፈጥርለት አልቻለም በረጅሙ ህይወቱ ካገኘው ልምድ ይልቅ
የልጅነት ዘመነ ትዝታ እሱነቱን ሽፍኖለታል: ድሮ ስለ አያቴ ባሰብኩ ቁጥር የሱን ትውልድ ቦታ እንደ ገነት እቆጥረው ነበር።
እናቴ ግን አፍሪካ ድህነት ችግር….የተከመረባት ሰዎቹም እርስ በርሳቸው የሚበላሉ እንደሆኑና ሲኦል እንጂ ገነት እንደሊለባት
ስትነግረኝ ሌላ ሃሳብ በአእምሮዬ መፈጠር ጀምሮ ነበር። ይህች አለም ጥቁርና ነጭ አምላክ ያላት ሁለት ገነት የሚገኝባት ሆና
አንዱ የሌላው ጠላት እንደሆነ ይስማኝ ነበር፡፡

"አያቴ ስለ ወንድ አያቴ ሁለት ተቃራኒ እምነቶች ነበሯት በአንድ በኩል ዝምታውንና ጅንነቱን የምትወድለት ቢሆንም በሌላ በኩል ደግሞ አብረው ለመዝናናት ለመወያየት ስለማይችሉ ፀጉሯን እየነጨች ትበሳጫለች ያም ሆኖ ግን እናቴ እንደነገረችኝ ከሆነ
አያቴ ለወንድ አያቴ በተደጋጋሚ በፍቅር ስትናዘዝለት ሰምታታስች
ለምሳሌ እንድ ቀን አያቴ ከሁዌልቫ በስተምእራብ አስራ  አምስት ኪሎሜትር ላይ ከሚገኘው የብርቱካን ማሳቸው አያቴን ይዛት
ትሄዳለች እዚያ ሲደርሱ ግን ወንድ አያቴ አልነበረም፡

“ስለዚህ እናቴ ከሪና ሁሌም እንደምታደርገው ወደ ብርቱካን ማሳው ገባ ብላ ብርቱኳን እየላጠች ስትበላ የቀሚሷ ጫፍ እየያዘች
ስትዘፍንና ስትዝናና ቆይታ አያቴን ወደተለየችበት ቦታ ስትመጣ አያቴን ታጣታለች።

“ደጋግማ ተጣርታ ወይ የሚላት ሲጠፋ የትም አትሄድም በሚል እራሷን አረጋግታ አያቴን አኜስን ስትፈልጋት እመስኖው
ውሃ ቦይ ትደርስና ውስጡ
ገብታ እየተንቦጫረቀች ስትሄድ የመስኖውን ውሃ ከሚስበው ሞተር ቤት ደረሰች፡፡

የሰው ድምፅ የሰማች መስሏት ፀጥ ስትል ድምፁ
ጠፋባት፡ ልትጣራ ፈለገች
ከመጣራቷ በፊት ግን ቀርቦ የራቃት ድምጽ ተመልሶ መጣ! ከሞተሩ ቤት የሚመጣውን ድምጽ በጆሮዋ ያዘችው። የሚያቃስት ሰው ድምጽ ነው  የእናቷ! ደነገጠች ወደ
ሞተሩ ቤት ሄዳ በፍርሃት በጭላንጭል አየች እናቴን ከእግር ጥፍሯ እስከ ጸጉሯ አንዳች ነገር ነዘራት፡፡ ድምፁ እንደገና ቀሰቀሳት
አያቴ አኜስ ናት! ድምፅዋ ቁርጥርጥ እንደሚቀጣ ህፃን ትንፋሽዋን በሲቃ ውጥር ይልና ደሞ ይጠፋባታል፤
በመጨረሻ ድምፁ
መጠኑን ጨምሮ መጣ
የሁለት ሰው ድምፅ የሉካዬና አኜስ ጨመረ ድምፁ እናቴ ተጨነቀች። ልትሮጥ ዘወር ስትል
የፎይታ ድምጽ ሰማች። ከዚያ አያቴ ተረጋግታ ስትናገር ሰማቻት፡

“አመሰግናለሁ ሎካዬ የልቤን ነው ያደረስከው ከከሪና ጋር ወደ አንተ ስገሰግስ እንዲህ አንጀቴን እንደምታርሰው እርግጠኛ
ነበርሁ። የውጭ በግ…
የልጋ ላይ ግን አንበሳ ነህ. ብላ ስትናዘዝላት እናቴ አያቴን ሰምታታለች።

“ይህ ደግሞ ሴት አያቴ
ወንድ አያቴን የምታፈቅረው
በዲፕሎማሲያዊ አነጋገር በዝምታው ነው ትበል እንጂ ጌታውን እንዳዬ ውሻ እግሩ ስር የሚያልወሰውሳት ሚስጥሩ ሴላ ነው፡፡
ሶራ የሚገርምህ ግን እናቴ ያችን ቀን ፆታዬን
ያወቅሁበትና ረሃቤን ለማዳመጥ ትእግስት የጎደለኝና የተመኘሁትን
ያጣሁበት ቀን ናት' ብላ ታስታውሳለች፡፡

ይህ በሆነ ከአምስት ዓመት በኋላ ግን እናቴ ከአባቴ
ከፍራንሲስኮ ፔሶ ቤኒ ጋር ከሁዌልቫ ወደ ሊዝበን ለጉብኝት ስትሄድ
ተዋውቀው ግንኙነታቸውና መግባባታቸው እየጨመረ ሲሄድ የብርቱካን ማሳቸውን ልታሳየው ቀጠረችው፡፡
👍32
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹አያቴ ዛሬ በጣም አዝኛለሁ…››

‹አይ አንተ ልጅ ..መቼ ነው ዛሬ ተደስቼያለሁ የምትለው….ደግሞ ምን ሆንክ?››

‹‹ስለልጅቷ ነግሬዎታለሁ አይደል?›

‹‹ሥለየቷ… ስለልጅህ እናት››

‹‹እማይደል… እኛ ሆቴል ስለምትመጣው››

‹‹እ. ጄኔራል ውሽማ አላት ያልከኝ››

‹‹አዎ…›

‹‹ምነው? ተተናኮላት እንዴ?››

‹‹አይ ነገሩ ወዲህ ነው…›

‹‹እንዴት..››

‹‹በቀደም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማዕረግ እድገት ከሰጣቸው ጀኔራሎች መካከል አንዷ እሷ ነበረች››

‹‹ምን?››

‹‹አዎ ወታደር መሆኗን ሳላውቅ ..ጄኔራል ሆና አገኘኋት››

‹‹እርግጠኛ ነህ..በመልክ መመሳሰል ወይም መንታ እህት ኖሯት ይሆናል››

‹‹አይ አያቴ እንደዛ አይደለም..ማታ እቤት ከገባኁ ቡኃላ ሳይሰሙኝ ቀስ ብዬ ወጥቼ ወደሆቴል ሂጄ ነበር›

‹‹አንተ ቀልማዳ ምን ለመፍጠር…›

‹‹ቤርጎ ይዛ ስለነበረ አግኝቼ ልጠይቃት..እና እውነት መሆኑን አረጋጣልኛለች፡፡››

‹‹ታዲያ ይሄ ይደንቃል እንጂ ምኑ ያሳዝናል….እርግጥ ይገባኛል…አንተ የምታስበው ፍቅር እውን የመሆን እድል የለውም ብለህ ልታስብ ትችላለህ..እንደዘ ብታስብ አይገርምም፡፡ ማንም ባንተ ቦታ ቢሆን በተለየ መልኩ ሊያስብ አይችልም..ግን ማወቅ ያለብህ መቼም ቢሆን ፍቅር ምክንያታዊ ሆኖ አለማወቁን ነው፡፡እና በፍቅርና በጦርነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው›› የሚባለው ለምን ይመስልሀል፡፡ምንም ያልተገመተ እና ያልታቀደ ነገር መከሰት በፍቅርና በጦርነት ውስጥ ተደጋሞ የሚስተዋል እውነት ስለሆነ ነው፡፡

‹‹አያቴ ትክክል ኗት፤ እሱ እንዳለ ሆኖ እኔ ያዘንኩት ግን በአሁኑ ጦርነት ክፉኛ ተጎድታ ለሶስት ወር ሆስፒታል እንደነበረች ነገረችኝ…..››

‹‹ያሳዝናል….ድሮስ ከጦርነት ምን መልካም ዜና ይሰማል.››

‹‹አዎ እንደነገረችን ከሆነ ለአንድ ወር ሙሉ እራሷን አታውቅም ነበር..ከተንቤን በረሀ ተጭና አዲስ አበባ እስክትመጣ ..ኦፕራሲዬን ሲሰራላት ሁሉንም አታስተውስም…ጓደኞቾ እንደነገሯት አንጃቷ ሙሉ በሙሉ ተዘርገፎ ከተዝረከረከበት ተፋሶ ወደውስጥ ተመልሶ ነው ልትተርፍ የቻለችው  …

ጠባሳዋ ከእንብርቷ ከፍ ብሎ ወደታች  ከ20 ሴ.ሜትር በላይ ይረዝማል…እንደተነገራት ከሆነ ማህፀኗም ተቆርጦ ስለወጣ ከአሁን ወዲህ መውለድ አትችለም….. ለሀገሯ ደሞን ማፍስ ብቻ ሳይሆን …..››

‹‹በቃ በቃ ልጄ…በህይወት መትረፎም አንድ ተአምር ነው….ሌላው በሂደት የሚታይ ነው፡፡››

‹‹አያቴ እንዲህ መስዋዕት የሚከፈልላት ሀገር የምትባለው ጣኦት ግን ማን ናት?;›

ይህቺን ጥያቄ ለእሷ ብታቀርብላት እርግጠና ነኝ በእንባ ባቀረሩ አይነቾ በሞቀና በደመቀ ስሜት የሚያንሳፍፍ አይነት መልስ ልትሰጥህ ትችል ነበር፡፡እኔ ግን የተለመደው አይነት ቀና መልስ ልሰጥህ አልችልም ፡፡፡ልጄ እንደእኔ ሀገር ሀሳብ ወለድ ፅንሰ ሀሳብ ነው።ቋሚ እውነት አይደለም..ይጠባል ይሰፋል...ይለማል ፤ይፈርሳል ። ቢሆንም ከስነልቧናችን ጋር  ስር የሰደደ ትስስር አለው፤ምክንያቱም ዘሬ ምንለውን መንጋ ህዝብ አዝሎ የሚያኖርልን .. ሀይማኖቴ የምንለውን መንፈሳዊ ተቋም የሚያቅፍልን ...መከታዬ ብለን የምንመካበትን ወታደርና ፓሊስ    የሚያስገኝልን ….ተወልደን ያደግንበት ስፍራ ብቻ ሳይሆን ወልደንም የምናሳድግበት. .ዘርተን የምናጭድበት…ሞተንም የምንቀበርበት፤መታወቂያ እንጂ ፓስፖርት የማንጠየቅበት ስፍራ ነው፡፡
ሀገር በህይወት ጉዞችን በኑሮ ውጣ ውረዳችን ቀላል ትርጉም የለውም።ከሀገር በላይ ለእውነት የቀረበው  እቤታችን ነው..፡፡ .አዎ ሚስታችን የምታስተዳድረው...ልጇቻችን የሚያደምቁት .. የልባችን የመጨረሻ ማረፊያ የአካላችን የየእለት መገኛ ..አዎ ሀገርን እንደ እንቁላል ውሰዷት ...ቅርፊቱ የአገር የመጨረሻው ድንበር ማለት ነው ...፡፡ጠላት በቀላሉ የሚበረቅሰው የመጀመሪያው ከለላ...ከዛ የመሀሉ ነጭ ክፍል የመሀል ሀገር ..ወይም ዋና ከተማ በለው...አስኳሉ ግን እቤትህ ነው ...ሚስትና ልጇችህ ወይም እናትና አባትህ እናም ቤተሠብህ የሚኖርበት ቢላ ቤትም ሆነ ደሳሳ ጎጇ።ግን አጥቂ ጠላት ሲመጣ ገና ከሩቅ ቅርፊቱን እንዳይሸነቁር ነፍስህን አሲዘህ ትፋለማለህ...ደምህን ታፈሳለህ ከዛም ከጨከነ ህይወትህንም ትሰጣለህ...ምክንያቱም ከቅርፊት መሸንቆር በኃላ እንቁላሉ ነጭ ክፍል መዝረክረኩ አስኳሉም መፍረሱ አይቀሬ ነውና...እና ለሀገሬ ብለን ስንፍለም አውቀንም ሆነ ሳናውቅ የምንለፋበት ዋናው ምክንያት ለገዛ  ቤታችን ደህንነት ነው...ለሚስታችንና ልጆቻችንን ለመታደግ ነው።
እስቲ የሀግርህን ሰው ተመልከት ቤት የሚሰራበት መሬት ሲመራ ቀድሞ አጥር ነው የሚያጥረው፡፡ ይህን የሚያደርገው  በቀላሉ ሰው ያለእሱ ፍቃድ አልፎ የማይገባበትን..እንስሳ ሳይቀሩ የማይደፍሩትን የግል ይዞታን ለመፍጠር ነው፡፡እቤቱ ቀስ ብሎ ይደርሳል ዋናው ግን ግዛትን ማስከበር ነው የሚል ሳያውቀው በውርስ ያዳበረው እውነት አለው፡፡
ተረታችን እንኳን ባለቤቱን ካናቁ አጥሩን አይነቀንቁ፡፡››የአንድን ኢትዬጵያዊ ግለሰብ አጥር ሄደህ መነቅነቅ ቀጥታ ሰውዬውን በዱላ ከመዠለጥ የተለየ ትርጉም አይሰጠውም…ህግ የመጣስ ሳይሆን  የክብር ጉዳይ ነው፡፡እና የሀገር ስሜት እንዲህ ከማንነታችን የተጋመደና የተወሳሰበ እሳቤ ነው፡፡እውነት ሆነ ሀሰባ ወለድ እሱ ብዙም ትርጉም የለውም፡፡ምክንያቱም አብዛኛው የሰው ልጅ የህይወት ፍልስፍና የተቃኘው በእውነት ላይ ሳይሆን በሚያማልሉ አፈታሪኮች ላይ ነው፡፡
‹‹ጋሼ…እሷም ከዚህ በላይ አታስረዳኝም…ግን ዋናው አሁን ምን ላድርግ ?አሳዝናኛለች››
‹‹አይ ልጄ…..ፍታ ያልኩህን ችግሮች ሳትፈታ ሌላ የተወሳሰበ ችግር ውስጥ ተጎትተህ እየገባህ ነው፡፡ቢሆንም ይቅርብህ አደጋ ስላለው ሸሽተህ አምልጥ አልልህም….ህይወትን በመጋፈጠ እንጂ ሸሽቶ በማምለጥ ምንም የምታተርፈው ነገር የለም…ግን አንድ ነገር ልመክርህ እችላለሁ፡፡
‹‹ምን አያቴ …?››
‹‹ስራህ ቀይር››
‹‹ምን አያቴ?››
‹‹አዎ ከዚህ በላይ አስተኛጋጅ ሆነህ መቀጠልህ ህይወትህን ማባከን ነው የሚሆነው..ደግሞም አስተናጋጅ ሆነህ በቀጣይ እየመጣብህ  ያለውን የህይወት ፈተና ተታግለህ ለማሸነፍ ትቸገራለህ፡፡›
‹‹ትክክል ነህ አያቴ..ግን?››
‹‹ግን ምን?››
‹‹ሁለት ችግር አለብኝ..አንድ የሂሳብ ደብተሬ ውስጥ ያለው 70 ሺ ብር ብቻ ነው..በዛ ብር ደግሞ እራሴን ችዬ ምን አይነት ስራ መጀመር እንደምችል አላውቅም…?››.
‹‹ሁለተኛውስ?››
‹‹ሁለተኛውም..ጋሼ ነው….ጋሼ ለእኔ በጣም ባለውለታዬ ነው….እሱ ጎትቶ ባያወጣኝ ዛሬም እዛ ጎዳና ትኬት መኪና ላይ እየለጠፍኩ ነበር ምገኘው…በዛ ላይ አያቴ ከእርሶ መለየትም ዝግጁ አይደለሁም…››
‹‹እኔም ካንተ ለመለየት ዝግጁ አይደለሁም…ለዛውስ ስራ ቀይር አልኩህ እንጂ እቤቱን ለቀህ ወጥተህ ተንዘላዘል ወጣኝ….?.››
‹‹አይ ማለቴ?››
ይሄውልህ ስማኝ..ጋሼ ውለታ ምናምን የምትለውን እርሳው እኔ ነገረዋለሁ…ማለቴ ካለፍላጎትህ እንድትለቅ የፈለኩት እኔ እንደሆንኩ እነግረዋለው…ይሄውልህ ስማኝ እኔ እንደምታየኝ ሽማግሌ ነኝ…ለዛውም የከተማ ባህታዊ ሆኜ ባህት  የዘጋሁ…ምን ለማለት ነው ምንም ስራ የመስራት ፍላጎት የለኝም…ግን የተወሰነ ብር ደብተሬ ውስጥ አለ…እና አንተ ደስ የሚልህን ቢዝነስ አጥናና አምጣ እኔ ገንዘብ እሰጥሀለሁ…የጋራ ቢዝነስ እንመስርታለን ማለት ነው፡፡›
👍65👏3😁3🔥1
#ባል_አስይ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከቃል ምክር በኃላ ልዩ የሌብነት መነሻዋ ከየት ነው? የሚለውን ጥያቄ  ደጋግማ  ከመጠየቅ እራሷን መግታት አልቻለችም። ትዝ ይላታል …ኤለመንተሪ ተማሪ ሆና ነው፤ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ክፍል እያለች ጀምሮ ነው ፡፡ አያቷ  ጠጅ በጣም ይወዳሉ ….አባባ ትልቁ ነው የምትላቸው..ምክንያቱም በወቅቱ ብዙ  አባባ የሚባሉ ሰዎች ግቢያቸው ውስጥ ስለነበሩ ነው ዘበኛው ..አትክልተኛው ወዘተ)፡፡

ማታ ሞቅ ብሏቸው  ወደ ቤት ሲመጡ ጠብቃ  ተከትላቸው መኝታ ቤታቸው በመግባት  የድሮ ታሪክ ወይም ተረት ንገሩኝ ትላቸዋለች።ደስ ይላቸውና አልጋቸው ላይ ወጥተው ጋደም በማለት ማውራት ይጀምራሉ...ግን ብዙውን ጊዜ አውርተው ከመጨረሳቸው በፊት እንቅልፍ ይዟቸው ጥርግ ይላል..."እና መተኛታቸውን ስታረጋግጥ ብርድ ልብሳቸውን ሙሉ በሙሉ ወደ ላይ ስባ ሸፍና ታለብሳቸዋለች...››እንደዛ ስታደርግ የሚያያት ሰው አያቷን እየተንከባከበች መስሏቸው ይመርቋት ይሆናል…እሷ ግን  ድንገት አይናቸውን ገልጠው የምትሰራውን እንዳያዩባት ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ  ነበር...

ከዛ ኪሳቸውን መበርበር ትጀምራለች...አ10 ብርም ሆነ 50 ብርም መዛ ኪሷ ትከትና ሌላውን ትመልሳለች። የምትሰርቀውን የብር መጠን የሚወስነው ኪሳቸው በምትገባ ወቅት ባገኘችው የብር መጠን ነው።

አያቷ የእናቷ አባት….ባላንብራስ  አይተንፍሱ ይርገጤ ይባላሉ።በጣም ቆፍጣና ግትርና ወግ አጥባቂ ሰው ነበሩ።እናቷን ጨምሮ የቤቱ ሰው ሁሉ ይንቀጠቀጡላቸዋል...‹‹እኔ ፊት አውራሪ አይተንፍሱ›› ብለው ከዘራቸውን ከወዘወዙ ማንም ፊታቸው አይቆምም...እሷ ግን አትሰማቸውም.. እሳቸው እሷ ሲቆጧት እልክ ይይዘትና እጇን አጣምራ አይኖቾን አፍጥጣ ፊታቸው ትገተራለች...፡፡

ቅሬታቸውንና ኩራታቸውን ደባልቆ በሚገልፅ ስሜት"ምን ዋጋ አለው በዚህ ጀግንነትሽ ወንድ ብትሆኚ ..?."ብለው ይሉና ቁጣቸውን አብርደው ወደራሳቸው ስበው ጭንቅላቷን በመዳበስ ያሞጋግሷታል...እንደዛ ሲሆን ደግሞ የልብ ልብ ይሰማታል።እና ወደኃላ ተመልሳ  ትናንቷን ስትቆፍር የስርቆት ታሪኳ የሚጀምረው አያቷን ደጋግሞ ከመስረቅ ሆኖ ነው ያገኘችው ...ለምን እሷቸውን ብቻ ነጥላ ትሰርቃቸው እንደነበረ  አታውቅም ።ከረሜላና ቸኮሌት መግዣ ገንዘብ አስፈልጓት ነው እንዳይባል እናቷ ከመጠየቋ በፊት ነው መዥረጥ አድርጋ የምትገዛላት። ለመስረቅም ከሆነ ደግሞ ከአያቷ ይልቅ እናቷን መስረቅ ለእሷ በጣም ቀላል ነው። እናቷ መኝታ ቤት መሳቢያዎ ውስጥ ሆነ ቦርሳዎቾ   ሁሌ በብር እንደተሞሉ ነው...፡፡የፈለገችውን ያህል ብር እናቷ  እያየች  መዛ ብትወስድ ፈገግ ከማለት ያለፈ ትኩረት ሰጥታ  አትናገራትም። ይሄንን ደግሞ ከጨቅላነቷ ጀምሮ በደንብ ታውቃለች፡፡

አይገርምም በህይወታችሁ የከወናችኋቸውን አንዳንድ ነገሮች ወደኃላ መለስ ብላችሁ በትኩረት ካልመረመራችሁ እንዴትና ለምን የሚለውን ጥያቄ መልስ ሳታውቁ ዕድሜያችሁ ያከትምለታል…. እሷም  ዕድሜ ለቃል አሁን ነው  በዛን የልጅነት ወቅት አያቷን ብቻ ለይታ ትሰርቅ እንደነበር በመገረም ያስተዋለችው፤ ለምን አያቷን ብቻ?አሁንም መልሱን አታውቅም።ግን ከአያቷ ላይ ገንዘብ በሰረቀችው በእያንዳንዷ ቀን ትልቅ ደስታና የድል ስሜት ይሰማት እንደነበረ  አሁንም ድረስ ታስታውሳለች። ይሄንን ተግባሯን እስከሰባተኛ ክፍል ቀጥላበት ነበር...ከዛ አቆመች።

ያቆመችው ማቆም ፈልጋ ሳይሆን አያቷ ድንገት ስለሞቱባት ነበር። በእውነት በመሞታቸው ከእሷ እኩል የደነገጠም ያዘነም ሰው አልነበረም።ያዘነችበት ዋና ምክንያት ግን "ከአሁን በኃላ ማንን ነው የምሰርቀው ?››የሚል ስጋት ስላደረባት ነበር፡፡

ይሄንን ግራ አጋቢ ስሜቴን ማንም አያውቅም ነበር ፤እናቷን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች ሁሉ ለአያቷ ካላት የተለየ ቅርበት እና  ፍቅር የተነሳ እንደሆነ በማመን  እንድትፅናና የተቻላቸውን እንክብካቤ ሲያደርጉላት ከረሙ...በእውነት እሷም  በቀላሉ ልትፅናና አልቻለችም ነበር።በኋላ ግን ትምህርት ቤት ሄዳ ከጓደኞቾ  እስኪሪብቶና ደብተር መስረቅ ስትጀምር አያቷን  ቀስ በቀስ እየረሳቻቸው  መጣች፡፡

..ስርቆቱ ግን እያደገ እያደገ ሄዶ  አብሯት ኖሮ እንሆ እዚህ አድርሷታል…እና  ልጅነቷን እንዲህ ስትፈትሽ ሌባ እንድትሆን ያስገደዳት ምክንያት ምንድነው?በመሞላቀቅ ሰበብ በህፃንነቷ ሳንቲም ስለለመደች ይሆን?ታዲያ ስርቆቱን ሳንቲም በመስረቅ ጀመረች እንጂ  እያደረ ትርኪ ምርኪ ቁሳቁስ  ነበር ስትሰርቅ የኖረችው...ልጅ ሆና እንኳን የ50 ብር የሚያምር ብዕር ቦርሳዋ ውስጥ እያለ የአንድ ብር ተራ እስኪሪብቶ ከጓደኞቾ ትሰርቅ ነበር...ለምን..?‹‹ሌባ ለአመሉ ዳቦ ይልሳል›› ተብሎ የተተረተው በትክክል የእሷን ሁኔታ ይገልፃል፡፡አይገርምም አሁን በዚህ ሰዓት እንኳን ለምን እንደሆነ አታውቅም፡፡

መኝታ ቤቷን ለቀቀችና ወደ እናቷ መኝታ ቤት ሄደች..አንኳኳች፡፡

‹‹ማነው?››

‹‹እኔ ነኝ እማ?››

‹‹ግቢ››

ከፈተችና ወደ ውስጥ ገባች

‹‹የእኔ ቆንጆ ምነው..?እስከአሁን አልተኛሽም እንዴ?›› አለቻት. ከተኛችበት ግዙፍ አልጋ ትራሷን ከፍ አድርጋ ከአንገቷ ቀና በማለት፡፡‹‹እንቅልፍ እምቢ አለኝ .ከአንቺ ጋር መተኛት ፈለጌ ነው፡፡››አለቻቸው፡፡

‹‹በሩን ዝጊውና ነይ….››ብርድልብስና አንሶላውን እየገለጡላት
እንዳሏት በራፉን ዘጋችና  ወደእናቷ አልጋ ሄዳ በተገለጠላት አንሶላ ውስጥ ገብታ ልክ እሳቸው እንዳደረጉት ትራሱን ከፋ አደረገችና ፊቷን ወደእናቷ አዞረች›

እንዲህ የማታደርገው የሆነ ነገር ከእናቷ ስትፈልግ እንደሆነ ከልምድ ይታወቃል…እና የምትለውን ለመስማት እናቷም ነቃ ብለው ተዘጋጀተዋል፡፡

‹‹እማዬ›አለቻቸው፡፡

‹‹ወዬ የእኔ ማር››

‹‹ከእዚህ በሽታዬ የእውነት እንድፈወስ ትፈልጊያለሽ"

ያልጠበቁትን ርዕስ እንዳነሳችባቸው ከፊታቸው  መለዋወጥ መረዳት ይቻላል፡

‹‹ከየትኛው በሽታሽ?››

‹‹ከሌብነቴ ነዋ››

"ምን ማለት ነው የእኔ ልጅ...?እንዴት እንዲህ አይነት ጥያቄ ትጠይቂኛለሽ..?››.

"እንድድን ከምር የምትፈልጊ ከሆነ አሁን የምጠይቅሽን  ጥያቄዎች ትመልሺልኛለሽ?››

‹‹እንዴ… አንቺ ዳኚልኝ እንጂ የፈለግሺውን ጠይቂኝ"

"እርግጠኛ ነሽ?"

"ምን ነካሽ...አንቺን ለመፈወስ የሚያግዝ ከሆነ የማላደርገው ነገር የለም"

"እሺ ስለአባቴ ንገሪኝ?"በጣም የምትፈራውን ጥያቄ አናቷን ጠየቀቻቸው፡፡

"ምን አስደነገጠሽ?እንድትድኚ እፈልጋለሁ አላልሽም እንዴ?"

"እሱማ እፈልጋለሁ...ስለአባትሽ መጠየቅና ከችግርሽ መፈወስ ምን እንደሚያገናኛቸው ስላልገባኝ ነው።"

"በደንብ ይገናኛል..እንዴት እንደሚገናኝ በሂደት ምንደርስበት ይሆናል። አባዬ ምን አይነት ሰው ነው?።

"ያው ፎቶውን ታይው የለ፤ ሸጋ ፤መልከመልካም ሰው ነበር።›› በራሳቸው ገለፃ እንደልጃገረድነት ጊዜያቸው ተሸኮረመሙ፡

"እሱንማ አውቃለሁ...ደግሞ እኳ ያየሁት የአምስት አመት ህፃን ሳለሁ ቢሆንም ትንሽ ትንሽ እንደ ህልም  ትዝ ይለኛል።እሽኮኮ አድርጎኝ ጊቢውን ሲዞር...ኪወክስ ወስዶ ከረሜላ ሲገዛልኝ...ወድቄ ሳለቅስ ተንደርድሮ አንስቶኝ ጉያው ሸጉጦ ሲያባብለኝ...አዎ እኚን የመሳሰሉ ብጥቅጣቂ  ምስሎች  በእምሮዬ ተቀርፀው ቀርተዋል፡፡››

"እኮ ከዚህ በላይ ምን ለማወቅ ነው የፈለግሽው?"

"ምን አይነት ሰው ነበር ...?ምን አይነት ፀባይ ነበረው?"

"ያው እንዳንቺ ነው"
👍7915🔥2🥰2😁2👏1😢1🤩1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

ይሄ ነገር በጣም ነው የከነከናት….‹‹እንዴት ነው ከቤቴ በጉያዬ አቅፌው የወጣሁት ንስር እኔን ምታህል ግዙፍ ልጅ በቀላሉ እንደላባ በማንጠልጠል እንዲህ ዘና ብሎ ሚበረው..ደግሞ እንደዚህ አይነት ግዙፍ ክንፍ ከምኑ ውስጥ ነው መዞ የሚያወጣው፤እሱ ወደአየር ሲወጣ ስለሚገዝፍ ነው ወይስ እኔ ክብደት እልባ እየሆንኩ ስለምሄድ ነው?›ብላ በአእምሮዋ ብታብሰለስልም መልስ አላገኘችም..ንስሯ ወደላይ ሳይሆን ቀጥታ ወደ ጎን   ይዟት ይነጉድ ጀመር…ሽው የሚለው ንፍስና ቀዝቃዛው አየር ፊቷን እየገረፋት ግን ደግሞ በፍፅም ደስታ ቁልቁል እያየች  መደመሟን ቀጠለች…ሙሉ ጥቅጥቅ ጫካ ራቅ ብሎ ሰንሰለታማ የተቀጣጣሉ ተራሮች ይታዬታል….በስተሰሜን በኩል ነው እየወሰዳት ያለው…ወደየት እየወሰደኝ ነው ብላ በውስጧ ጥያቄ ቢጫርም ፍርሀት ግን አልተሰማትም..ጎሮሮዋ እስኪሰነጠቅ ጮሀ ‹‹.አባዬ ንስሬን ስለመለስክልኝ አመሰግናለሁ››  አለችው፡፡

በንስሯ ወይም ጀርባዋ ላይ ተለጥፋ በሚርገበገበው ክንፍ  እየተመራ ለ30 ደቂቃ ያህል ዙሪያ ጥምዝ ጥቅጥቅ ደኑን ዞረች.. እክሮባት አይነት እያሰራት መልሶ ከተነሳችበት ከብቶቾ መካከል አስቀመጣትና ከጀርባዋ ተላቆ ከስሯ አረፈ..
ስትቆዝምና ስትተክዝ የነበረው ስሜቷ አገገመ፡፡ ከዛን ቀን በኃላ ንስሯ ከእሷ ተነጥሎ ወደየትም  ሄዶ አያውቅም..በሂደት እንደውም አእምሮውን ማንበብ ጀመረች…ከንፈር ሳያነቃንቁና ፤ቃላት ሳይለዋወጡ አንዳቸው የሌላቸውን አእምሮ በማንበብ ብቻ በአስደናቂ ሁኔታ መግባባትና ሀሳብ መለዋወጥ ችለዋል፤የምትፈልገውን ነገር ማዘዝና ወደምትፈልገው ቦታ እንዲወስዳት ስትጠይቀው ያለማዛነፍ ይከውንላት ጀመር፤ ይህ ደግሞ በፊት በነበራት ጥንካሬና በሚያውቋት ሰዎች ዘንድ የነበራት ተፈሪነትና ክብር በእጥፍ ጨመረ…የእሷም ስለነገሮች ያላት አተያይ ተቀየረ....ከብት ጥበቃውን ቀስ በቀስ በመተው ከሀገር ሀገር እየተዘዋወሩ ምድርንና በውስጧ ያሉትን ሚስጥሮችን እየበረበሩ መዋል ላይ አተኮረች… መጀመሪያ በአካባቢ በቅርብ ርቀት በሚገኙ ከተሞች መዳወላቦ፤ ነጌሌ ቦረና ፤በርበሬ ፤ሰወይና፤ራይቱ፤ ጊንር ፤ ጎባ፤  ዶዶላ አንጌቱ የመሳሰሉት ከተሞች በንስሯ ክንፍ ተዞዙራ በመሄድ እዛ ውላና ተዝናንታ መምጣት ጀመረች…ቀጥሎ ለምን ከሀገር አልወጣም …ብላ የሱማሌ ድንበርን አቆርጣ ሀርጌሳ ፤ሞቃ ዲሾ፤ሱማሌላንድ ድረስ ዘልቃ በመሄድ ውላ መምጣት በሌላ ጊዜ ደግሞ በሞያሌ በኩል የኬኒያን ድንበር አቋርጣ ውላ መግባት ጀመረች፡፡:
ከዛ አስደናቂ ምትሀታዊና ልብ ሰባሪ ገጠመኝ ከሞት የታደጋት ንስር የልብ ጓደኛዋ ጠባቂ መላአኳ ሆኖ እንደ አንድ ቤተሰቡ አባል አብሯት እየበላ አብሯት እየጠጣ አብሯት አንድ ብርድልብስ እየተጋፈፋት መኖር ጀመረ፡:በዚህ የተነሳ ስለንስር ተፈጥሮአዊ ባህሪ በጥልቀትና በዝርዝር ማወቅ ቻለች፡በዛም መደነቆ የትየለሌ ሆነ .
የእሷው ንስር ሳይሆን ስለ ጠቅላላ ንስር ስለሚባሉት ዝርያዎች ጥቂት ነገር ላጫውታችሁ

‹‹ንስር የጥንካሬ ምልክት ነው፡፡››
ንስር ስትወልድ የምትወልድበት ስፋራ በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው የሚዘጋጀው…ብዙውን ጊዜ የተራራ ጫፍ ላይ ሌሎች አጥቂዎች ማይደርሱበት ቦታ ተመርጦ ነው፡፡ጎጆውን የመስራቱን ኃላፊነት የወንዱ ነው፡፡ጎጆውም ከማንኛውም አደጋ እና ጥቃት ልጆቹን መጠበቅ የሚችል ተደርጎ ነው የሚሰራው….እሾህ..ለስላሳ  እንጨት (ገለባ ነገር)..ከዛ ደግሞ ሌላ እሾህ…በሾሁ ላይ  ለስላሳ ገለባ… እያለ  በተመሳሳይ ቅደም ተከተል በስድስት እርብራብ በወንድዬው አመካይነት ይሰራል
ታዲያ በዚህ በታነፀ ቤት ውስጥ አንድ ንስር እናት ልጆቾን  ከወለደች በኋላ ለተወሰነ ቀን ብቻ ነው የምትንከባከባቸው፡፡ከዛ ታወጣና አለቱ ላይ ትጥላቸዋለች፡፡ልጆቾ በመደናገጥ..ምን ጉድ ተፈጠረ..? በሚል  ስጋት  ተመልሰው ወደማደሪያቸው ሲመለሱ..እናት ንስር ሆዬ መልሳ አውጥታ ትጥላቸዋለች..እነሱም ይመለሳሉ ..በዚህ አይነት ሁኔታ የተወሰነ ካለማመደቻቸው እና  ከፍራቻ ጋር እንዲታረቁ ካደረገች በኃላ ታወጣቸውና ወደአለቱ ከጣለቻቸው በኃላ የላይኛውን ለስላሳ ሳር(ገለባ) ታነሳባቸዋለች.. ልጆቹ ሀገር ሰላማ ነው ብለው ተመልሰው ወደጎጆቸው ሲገቡ እሾሁ ላይ ያርፋሉ ….ባልጠነከረ ለስላሳ ገላቸው እሾሁ ይቀረቀርባቸዋል ይቆስላሉ …ይደማሉ..፡፡
ከዛ እሾሁን ሽሽት ወደአለቱ ጫፍ በራሳቸው ጊዜ ይወጣሉ ፡፡….እናት አሁንም አትታዋቸውም ከአለቱ ላይ ገፍታ ትጥላቸዋለች …. በእናታቸው ጭካኔ እየተገረሙ በፈጣሪም ዝም ማለት ግራ እየተጋቡ ወደጥልቁ ገደል አበቃልን በሚል ተስፋ መቁረጥ እየተምዘገዘጉ ሲሰምጡ አባት አየሩን ሰንጥቆ በመምጣት  ይቀልባቸውና በጀርባው አዝሎ ወደ ተራራው ጫፍ ይመልሳቸዋል….እናት አሁንስ መች ትራራለች… መልሳ ትገፈትራቸዋለች.. አባት እንደፈረደበት ከአየር ላይ ይቀልባል…በሂደት ልጆቹ ከውስጣቸው ያለው ፍርሀት እየከሰመ..ልል የነበረው ጡንቻቸው እየጠነከረ…ክንፋቸውም መብረርን እየተማረ ይመጣና ያንን መከራ እና ስቃይ እንደጫወታና መዝናኛ መቁጠር ይጀምራሉ…፡፡ፍርሀታቸው ወደ ድፍረት…..መማረራቸው ወደ መዝናናት ይቀየራል….፡፡እናታቸውን በተራገሙበትን አንደበታቸውን መልሰው ያመሰግናሉ….ገና በጨቅላነታቸው በወላጆቻቸው ጥበብ ህይወትን በጥረት እና በብቃት ለማሸነፍ ሙሉ የራስ መተማመን ይጎናፀፋሉ..እንደሰው ልጅ እናት ጉያ ውስጥ ሀያ አመት ሙሉ መሻጎጥ በንስር አለም አይታሰብም….


ይቀጥላል
👍134😱1413🥰3👏1😁1
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹዋቤ

ከለሊቱ ስድስት ሠዓት አልፏል፡፡እንቅልፍ አልወስደው ብሎ አልጋው ላይ ተጋድሞ እየተገላበጠ ሳለ ድንገት ተንቀሳቃሽ ስልኩ ድምፅ አሠማ፡፡ አነሳና ቁጥሩን አየው፡፡ ያልተመዘገበ ቁጥር ነው፡፡ አያውቀውም፡፡ ግራ በመጋባባት አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ ማን ልበል?››

‹‹ይቅርታ ከእንቅልፍ ቀሠቀስኩህ?››

ብድግ ብሎ ቁጭ አለ፡፡ ያልጠበቀው ስልክ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በሞባይል የደወለችለት ሚስጥር!፡፡

‹‹ኧረ አልቀሰቀሽኝም.. እንቅልፍ እና እኔ ከተጣላን እኮ ሰነባበትን

‹‹ኦ! ምን ምቀኛ በመሃላችሁ ገባ እቴ›› በማለት በስሱ ሳቋን ለቀቀች፡፡

‹‹ይሄ ሞባይል ቁጥር ያንቺ ነው?›› ጠየቃት፡፡

‹‹ኧረ ተመስገን ነው፤በፈለኩ ጊዜ ብደውልልሽ አገኝሻለኋ?››

‹‹አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ሁል ጊዜ አልከፍተውም፤በተለይ ቀን ቀን አይሠራም፤ማታ ከአራት ሠዓት በኋላ ግን ክፍት ነው፡፡››

‹‹ኧረ ይሁን እሱንስ ማን አየበት…፡፡››

‹‹አሁን የደወልኩት ውሳኔህን እንድትነግረኝ ነው፡፡››

<<የቱን ውሳኔ?>>

‹‹በቀደም የተነጋገርነውን ነዋ፤ልታገኝኝ ከፈለክ አግባኝ ያልኩህን ?››

‹‹ግን እኮ በጣም ከባድ ነገር ነው፡፡››

‹‹ከባድ ከሆነማ ልታገኘኝ አትፈልግም ማለት ነው?ስለዚ እንደ ከዚህ ቀደሙ ግንኙነታችንን በስልክ ብቻ እንቀጥላለን፡፡››

‹‹ኖ... እሱማ አይሆንም፤ከባድ ነው እኮ ያልኩት አንቺን ማግባቱ አይደለም፡፡››

‹‹እና ምኑን ነው?››

‹‹ሠርግ ምናምን የሚባለውን ነገር ነዋ፡፡ አየሽ እኔ ለሠርግዐያለኝ አመለካከት በጣም የወረደ ነው:: እንኳንም ሠርግ
መደገስ ሠርግ ስጠራ እንኳን መሄድ አልፈልግም፡፡ በዚህ ፀባዬ ከስንት ወዳጆቼ ተጣልቻለሁ መሠለሽ ... ለምን ዝም ብለን አንጋባም ፤ አሁን በዚህችው ደቂቃ እንኳን ብትፈቅጂልኝ ያለሽበት ድረስ በርሬ መጥቼ አገባሽ ነበር፡፡››

‹‹እና ታዲያ ምን ይሻላል?እኔም እኮ ሠርግ ወድጄ አይደለም፡፡ ግን አንተ አይተኸኝ እንድትተወኝ በፍፁም አልፈልግም፡፡ ካገባኸኝ በኋላ ካልተስማማሁህ ብትፈታኝ ይሻለኛል…በወሩም ቢሆን፡፡ ይሄንኑ ማረጋገጥ ስለምፈልግ ነው ይሄንን ዘዴ የቀየስኩት...፡፡››

‹‹ሚስጥር እኔ በጣም ከምትገምቺው በላይ አፈቅርሻለሁ፡፡ ስለማፈቅርሽም አንቺ እምቢ ብትይኝ እንኳን በህግ ልጠየቅ እንጂ ጠልፌም ቢሆን አደርገዋለሁ፡፡ እኔ የሚያስጠላኝ ቀለበት ሠርግ የሚባለው የድግስ ጋጋታ ነው፡፡ ፍቅሬን ከተጠራጠርሽ ሌላ የምታረጋግጭበት ዘዴ ወይም ፈተና አቅርቢልኝ፡፡››

‹‹ቆይ ላስብበትና ልደውልልህ››

‹‹መቼ ነው የምትደውይልኝ?››

‹‹ዛሬውኑ...ከ3ዐ ደቂቃ በኋላ፡፡››

‹‹እጠብቅሻለሁ፡፡››

ስልኩ ከተዘጋ ገና አስር ደቂቃ ብቻ ያለፈው ቢሆንም የአስር ቀን ያህል ረዘመበት፡፡ ምን አይነት ተቀያሪ ሀሳብ እንደምታቀርብለት መተንበይ አልቻለም፡፡ መንጎራደድ የእሷን የሃሳብ መስመር ሹክ የሚለው ይመስል መኝታ ቤቱን ተሸከረከረ፡፡ ሲደክመው መልሶ አልጋው ጫፍ ላይ በመቀመጥ አንገቱን አቀርቅሮ ወደ ትካዜው ገባ፡፡‹‹እንደምታገባኝ እርግጠኛ የምሆንበት ሌላ ዘዴ ስለሌለኝ መደገስህ የግድ ነው ብትለኝ ምን አደርጋለሁ? እሺ እላታለሁ ወይንስ አይሆንም እላታለሁ?›› ግራ ገባው፡፡ በአሁኑ ሰዓት እርግጠኛ የሆነበት አንድ ነገር ቢኖር እሷን በአካል ማግኘት ካልቻለ ትክክለኛ ሠው ሆኖ ስራውን ማከናወንም ሆነ ህይወቱን መምራት እደሚያስቸግረው ነው፡፡‹‹እና ምን ይሻለኛል?›› እራሱን ጠየቀ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለለት፡፡ ማንነቷን ለማወቅ አንድ እድል አለው፡፡ በሞባይል ቁጥሯ በመመራት ከቴሌ አድራሻዋን ማፈላለግ፡፡

‹‹በራሷ ስም ካላወጣችስ?›› አፍራሽ የሆነ ሌላ ጥያቄ ተሠነቀረበት፡፡

‹‹ቢሆንም ቁጥሩን ከቴሌ በስሙ የወሰደውን ሠው ብከታተለው ወደ እሷ ሊመራኝ ይችላል፡፡ >> ይሄን ዕድል ለመሞከር ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ስልኩ ጮኸ፡፡ በአንድ ጥሪ ነበር ያነሳው፡፡

‹‹አልተኛህም.. እየጠበቅከኝ ነው?››

‹‹ምኑን ተኛሁ .. ምን ወሰንሽ?››

‹‹ሌላ ተቀያሪ ጨዋታ እንጫወታ፡፡››

‹‹ምን አይነት ጨዋታ?››

‹‹ሌባና ፖሊስ አይነት ነገር፡፡››

‹‹በናትሽ እስቲ ዘርዘር አድርጊልኝ?››

‹‹እንግዲህ አፈቅርሻለሁ ብለኸኛል››

<<በትክክል::>>

‹‹የምታፈቅረኝ ደግሞ ነፍሴን ነው››

‹‹አሁንም ትክክል ነሽ››

‹‹እንግዲህ እንደዛ ከሆነ ነፍስህ ነፍሴን ታውቃታለች ማለት ነው፤ስለዚህ እኔ ማን እንደሆንኩ ለማወቅ ነፍስህ ትረዳሀለች ብዬ አስባለሁ፡፡››

<<እየገባኝ ያለ አይመስለኝም …፡፡››

‹‹በዝግታ ተከታተለኝ እያስረዳሁህ እኮ ነው፡፡››

« .. እሺ ቀጥይ...::>>

‹‹እንግዲያው ከላይ የጠቀስካቸው ሁኔታዎች እውነት ከሆኑ የሦስት ቀን ጨዋታ እንጫወታለን፡፡ ቦታው የትም ሊሆን ይችላል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥም ሆነ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ማንኛውም ከተማ ..ያ ያንተ ምርጫ ነው፡፡ ፈልገህ ካገኘኸኝ በቃ አገኘኸኝ ማለት ነው፡፡››

‹‹እንዴት ነው የምፈልግሽ?››

‹‹በተመቸህ ሳምንት ጨዋታውን እንጀምራለን፡፡ የመጀመሪያው ቀን ግን አርብ ሆኖ ማብቂያው ደግሞ እሁድ ይሆናል፡፡ የትኛው አርብ እንደሚሆን ከወሰንክ በኋላ ትነግረኛለህ፡፡››ሁሴን ይበልጥ እየተገረመና ነገሮች እየተወሳሰቡበት ነው፡፡ በእሷ ላይ ያለው ገረሜታና አድናቆት ይበልጥ በውስጡ እየገዘፈ መጣ፡፡

‹‹እሺ ቀጥይ እየተከታተልኩሽ ነው፡፡››

‹‹በተወሰኑት ቀናቶች ከ1ዐ-12 መሀከል ባሉት ሰዓቶች በተስማማንበት አካበባቢ እገኛለሁ፡፡ በአካባቢህ ካሉት ሴቶች መካከል እኔ የትኛዋ እንደሆንኩ የመለየት ስራው ግን የአንተ ይሆናል፡፡››

‹‹ነገሩን እንዲሁ አወሳሰብሽው እንጂ አንቺን ማግኘት ቀላል ነው፡፡››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹ያው ትንሽ ፍንጭ ሰጥተሺኝ ነበር እኮ..ረሳሽው እንዴ ?>>

‹‹ኦ .. እሱ ባክህ የመጀመሪያው ጊዜ የቀረበልህ ቀላል ፈተና ነው፤እኔ አይናማ ነኝ፡፡››

‹‹ለመሆኑ ምን ዓይነት ሠው ነሽ ?... ቤተሠቦችሽ እንዴት አድርገው ነው ያሳደጉሽ?››

‹‹እንቆቅልሽ እያስተማሩ፡፡››

‹‹ከለየሁሽ ቀጥታ መጥቼ አነጋግርሻለሁ ማለት ነዋ››

‹‹አይደለም አበባ ትሠጠኛለህ፡፡አበባው ላይ የሚለጠፍ ሦስት ካርድ እንቆቅልሽ የሚል ፅሁፍ ያለበት በፖስታ ቤት ልክልሀለው፡፡ ሦስቱም ላይ ፊርማዬ ያርፍበታል፡፡ አበባው እጄ ሲደርስ ለአሸናፊነትህ ያዘጋጀሁልህ የወርቅ ሀብል ስላለ እሱን አንገትህ ላይ አንጠለጥልልሀለሁ…ሀብሉ ልብ ቅርፅ ነው፡፡››

‹‹በጣም ጥሩ›› አለ ሁሴን ሳይታሠሰበው ድምፅ አውጥቶ፡፡ እሷን የሚለይበት አንድ ምልክት ስለሰጠችው ‹‹በድምፅህ ላይ አንድ ነገር ተረዳው›› አለችው፡፡

<<ምን??>>

‹‹ሀብሉን ከአንገቴ ላይ አውልቄ አይደለም የማጠልቅልህ ፤ከቦርሳዬ ውስጥ አውጥቼ ነው፡፡ ብቻ የልብ ቅርፅ የተሠራና በልብ መሀከል ያንተ ስም የመጀመሪያ ፊደል ያለበት ነው፡፡››

‹‹እሺ ይሁን>> አለ፤ የጭንቀት ትንፋሽ በመተንፈስ፡፡

‹‹እንግዲህ አስታውስ ያሉህ የሦስት ቀናት መጫወቻ ካርታዎች ብቻ ናቸው፡፡ በአንዱ ቀን አንዱን ካርታ ብቻ ነው መጠቀም የምትችለው፡፡ በነገራችን ላይ ጨዋታውን ለምን ቢሾፍቱ አናደርገውም፡፡››

‹‹ቢሾፍቱ .. ደብረዘይት?››

‹‹ምነው? አሪፍ ነው፡፡እንዲያውም ጨዋታችንን ለየት ያደርገዋል፡፡ በዛውም አብዛኞቹን ሀይቆች መጎብኘት እንችላለን፡፡››

‹‹እኔ እኮ በደንብ አላውቃትም››
👍7318
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ዛሬ ላይ

ሳባ  ሊቱን  ሙሉ  በትዝታ  ከወዲህ  ወዲያ  ስትዋዥቅ  ነው  ያደረችው…ለሰከንድ እንኳን እንቅልፍ በአይኗ አልዞረም…አሁን የትዝታ ጉዞዋን መሀከል ላይ ሳትቆጭ
ያቆመችው ታናሽ ወንድሟ ራጂ የተኛችበት ክፍል ደረስ መጥቶ በእናቱና በእሷ መካከል ሰርስሮ መሀከላቸው ሲገባ ነው፡፡

‹‹አንተ ጓረምሳ ሴቶች ክፍል ምን ትሰራለህ?››

‹‹እህቴ ናፍቃኝ ነዋ››

‹‹ወደራሷ ልጥፍ አድርጋ በማቀፍ  ግንበሩን ሳመችው፡፡››

‹‹እህቴ ዛሬም ታድሪያለሽ አይደል?›

‹‹ማደር አላድርም …ግን አሁን እንነሳና ከተማህን ዞር ዞር አድርገህ አሳየኝ..ከዛ ትንሽ ዘና ብለን ከሰአት በኃላ እሄዳለሁ፡፡››
ስንዱ(እማሆይ  አፀደ)  ከአልጋዋ  እየወረደች‹‹  ምነው  ዛሬ  አድረሽ  ነገ  በጥዋቱ     -ብትሄጂ አይሻልም?››ስትል ሀሳብ አቀረበችላት፡፡
‹‹አይ..  ቢያንስ  ነገ  በጥዋት  ሀኪሜ  ጋር  ተመልሼ  በመሄድ  ስላቋረጥኩት  -መድሀኒት ነገሬው የሚለኝን መስማት አለብኝ፡፡››

‹‹በቃ እንደዛ ከሆነ ተነሱ እስከዛ እኔ ቁርስ ልስራ፡፡››

‹‹አይ አንቺም ተነሺና አብረን ውጭ ነው ቁርስ ምንበላው፡፡››

‹‹ባይሆን እናንተው ሂዱና  ስትመለሱ  ከእኔ  ጋር  ሆነን  የሆነ  ቦታ እንሄዳለን፡፡ ማለቴ ብዙም ጊዜ የሚፈጅ አይደለም፡፡እዚሁ ቅርብ ነው፡፡15 ደቂቃ ቢወስድብን ነው፡፡››

‹‹ሳባም …እሺ በቃ›› ብላ ለባብሳ ከወንድሟ ጋር ተያይዘው ከግቢ ወጡ፡፡ቀጥታ የሄዱት ሻለቃ ደራርቱ  ቱሉ  ሆቴል  ነው፡፡  እዛ  እየተዝናኑና  ቁርስ  እየበሉ እተጫወቱ   አራት ሰዓት  ሆነ ፡፡ ከዛ ወጡና ወደስጦታ መሸጫ ሱቅ እየሄዱ ሳለ ስልኳ ጠራ፡፡አየችው ..በጣም የምትፈልገው ስልክ ነው፡፡አነሳችው፡
‹‹እሺ ደራሲ ጳውሎስ እንዴት ነህ?››
‹‹አለሁ.. ሰላም ነኝ››
‹‹እሺ እንዴት እየሆነልህ ነው…?›
‹‹ጨርሼለሁ..ዛሬ ወደአዲስአባ ልንመጣ ነው…ከመነሳቴ በፊት ልደውልልሽ ብዬ ነው፡፡››
‹‹በእውነት  በጣም  አስደሳች  ዜና  ነው  የነገርከኝ…በቃ  እኔም  አሁን  አሰላ ነኝ…ከሰአት እነሳለሁ..ነገ እንገናኛለን፡፡››
‹‹እሺ በቃ ቸው››
‹‹ደግሞ የጉዞውም ነገር መስመር ይዞል..በአስራአምስት ቀን ውስጥ የሚጠናቀቅ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ደስ ይላል፡፡በቃ ነገ አንገናኝ፡፡››ብሏት   ስልኩን   ዘጋው፡፡እሷም   ስልኳን   ወደኪሷ መልሳ በደስታ ፈጋ ወንድሟን እንዳቀፈች ወደ ሱቅ ገባች፡፡ ትኩስ አበባ ከገዙ በኃላ ቀጥታ ወደቤተክርስትያን ነው ተያያዘው የሄዱት፡፡ ሁለቱም አባታቸው መቃብር ላይ የያዙትን አበባ አስቀመጡና ሀውልቱ ስር ጎን ለጎን ቁጭ አሉ፡፡ ሁለቱም በዝምታ ተሸብበው በየራሳቸው ትዝታ መዳከር ጀመሩ፡፡ሳባ ትዝ ይላታል፡፡የዛሬ ሰባት አመት በፊት የአባቷ አሟሟት፡፡ 
አዎ   ሙሉ   በሙሉ በእሷ ጣጣ እንደሞተ ነው የምታምነው፡፡በዛ ምክንያት ደግሞ በቀል በውስጧ በቅሎ ሰው እስከመግደል ደርሳለች፡፡እርግጥ ቀጥታ የሽጉጥ ቃታ ስባ…ወይም ጩቤ በሰው ልብ ሰክታ አልነበረም ግድያውን የፈፀመችው፡፡ግን የአባቴ ዋነኛ ገዳይ ነች የምትላትን ሴት ያላትን ሁሉ አንድ በአንድ እንድታጣ አድርጋ ባዶዋን በማስቀረት በራሷ እጅ አንገቷን ገመድ ውስጥ አስገብታ ከዚህች አለም ህይወት እራሷን እንድትገላግል አድርጋለች፡፡አሁን ሌላ አንድ ትቀራታለች….ለእሷም የመጨረሻውን ቦንብ አጥምዳ ወደማጠናቀቁ ላይ ነች…ከዛ የሴትዬዋ እግሮች ቦንቦቹን ረግጠው ሲነሱ ሁሉ ነገሯ ቡም ብሎ ይበታተናል... ያ ወጥመድ….ደራሲ ጳውሎስ ፅፎ ያጠናቀቀው መፅፈህ ነው፡፡ያ መፅሀፍ ቦንብ ሆኖ ቀሪዋንና ኃያሏን ሴት ያስወግዳታል..‹‹አባዬ አይዞህ ..አንድ በአንድ እበቀላቸዋለሁ››አለች ሳባ፡፡
‹‹ምን አልሽ እህቴ …?አናገርሺኝ?››አላት ታናሽ ወንድሟ፡፡
‹‹አይ…. ከአባዬ  ጋር  እያወራሁ  ነበር፡፡››አለች  ደንግጣ፡፡ ራጂም ‹‹እህቴ …አባዬ እኮ በጣም ነው የሚናፍቀኝ፡፡›› አላት፡፡
‹‹እኔም በጣም ነው የሚናፍቀኝ…..በየጊዜው እናንተ ጋር የማልደውለው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ ?እንተን ሳወራ አባዬ ትዝ ስለሚለኝና እሱ ትዝ ሲለኝ ደግሞ ሀዘን ውስጤን ስለሚሸረካክተው ነው፡፡አባዬ በጣም ጀግናና ስማርት የሆነ አባት ነበር… ሲሞት አንተ ልጅ ስለነበርክ በደንብ ልብ ላትለው ትችችለህ…በተለይ ከአደጋው በፊት ሮጦ ልረፍ የማይል፤ ሰርቶ ደከማኝ የማያውቅ፤ ለቤቱ  ድንቅ አባወራ ለእኔና ለአንተ ድንቅ አባት ፤ለሰፈርና በቄሄው የተከበረ ልዩ ሰው ነበር…አባዬን ሳስብ ሁል ጊዜ ከአደጋው በፊት ስለነበረው ሁኔታ ነው ማሰብ የምፈልገው…››
‹‹እህቴ እኔ አንቺ ከምታስቢው በላይ አባዬን  አውቀዋለሁ.እርግጥ አምስት  አመቴ ላይ ነው የሞተው…ቢሆንም አምስት አመት  ሙሉ እኔን ከማሳደግ ውጭ ሌላ ስራም ሆነ ፍላጎት እልነበረውም…እማዬ  እናቴ  መሆኗን  በትክክል  ያወቅኩት እንኳን   እሱን   በሞት   ካጣሁ   በኃላ   ነው፡፡ከዛ   በፊት   ምተኛው   ከእሱ   ጋር
፤የሚያጥበኝ እሱ፤ ምግብ እራሱ የሚያጎርሰኝ እሱ ነበር..እስኪሞት ድረስ በእጆቼ ምግብ ቆርሼ መጉረስ አልችልም ነበር ፡፡እሰከዛ ድረስ በእሱ እጅ ካልሆነ ምግብ ወደአፌ አይገባም ነበር…በየቀኑ የሚነግረኝ ተረቶች የሚያነብልኝ መፅሀፎች ትዝታው  ዛሬ  የተከወነ  ያህል  ነው የማስታውሰው    ፡፡አንድ አይነት ተረት በቀን
ለ10 ጊዜ ደጋግመህ ንገረኘኝ ስለው አይሰለችም…በደስታ ያደርገዋል፡የአባዬ ጣፋጭ ድምፅ ዛሬም በጆሮቼ ውስጥ ሲንቆረቆር ማደመጥ እችላለሁ፡››
በታናሽ ወንድሟ ልብ የሚነካ ንግግር እንባዋ በጉንጮቾ ተንኳለለ፡፡
ወንድሟ ቀጠለ‹‹…እህቴ የዛን ያህል እያስታወስኩት በዛ መጠን እየናፈቀኝ እንኳን ለምን አንዳማላማርር ታውቂያለሽ?››
መልሱን ለመስማት ተነቃቃች‹‹ለምንድን ነው?››
‹‹አንቺ ስላለሺኝ ነዋ…አንቺ እኮ ልክ እንደአባቴ ነሽ..አይደለም አሁን ላለሁበት ለወደፊት ህይወቴ እንኳን ትጨነቂያለሽ…ጀግና እህት ስላለኝ በአንቺ እፅናናለሁ..አባዬ ሲናፍቀኝ እዚህ እመጣና አንቺ ለእኔ  እና  ለእናቴ  ምታድርጊልን ነገር ሁሉ እነግረዋለሁ…ከዛ ደስ ሲለው አይቼ ወደቤቴ እምለሳለሁ.፡››
ከተቀመጠችበት ተንደርድራ ሄዳ አቀፈችው …ጭምቅ አድርጋ አቀፈችው.. እያገላበጠች ሳመችው…እሱ በእሷ ላይ ያለውን መመካት እሩብን   ያህል   እሷ በራሷ ላይ ኖሯት ቢሆን እጅግ ደስ ይላት ነበር፡፡ግን እሷ በውስጧ ትንሽነት ነው የነገሰው.. ፤ባዶነት ነው ልቧን የሞላው ፤ስጋት ነው እየናጣት   ያለው፤ተስፋ መቁረጥ ነው ዙሪያዋን የከበባት፣
እህትና ወንድም ተመልሰው  እቤት  ሲደርሱ  ስድስት  ሰዓት  አልፎ  ነበር… እናትየው ምርጥ  የተባለ  ምሳ  ሰርታ  ቡና  አፍልታ  ፤እቤቱን  አሟሙቃና አጫጭሳ ነበር የጠበቀቻቸው…የተዘጋጀውን ምግብ ከበሉና ከቡናውም አቦሉን ከጠጡ በኃላ ስንዱና ሳባ በተራቸው ተያይዘው ወጡ..
‹‹ስንድ የት እንደምትወስጂኝ ለማወቅ ጓጉቼያለሁ?››
‹‹ትንሽ ታገሽ ደግሞ አስደሳች ቦታ የምወስድሽ እንዳይመስልሽ››
‹‹እናስ..?››
‹‹ያው አስፈላጊ ቦታ ነው…. በተለይ ለእኔ?››
‹ለነገሩ ዝም ብዬ ነው የጠየቅኩሽ…መቼስ መዝናኛ ቦታ ይዘሽኝ ትሄጃለሽ ብዬ አላስብም…›
👍7911🔥1😁1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ደቡብ ኮሎምቢያ/የአማዞን ደን
ዳግላስ አንድ ወር ከራቀበት የግል ግዛቱ ሲመለስ ፍፁም የሆነ ደስታ ነው የተሰማው፡፡ከመኪናው ወረዶ የቅፅር ግቢውን አፈር እንደረገጠ በውስጡ ጎድሎ የነበረው ኀያልነቱ መልሶ ሲሰርግበት ተሰማው፡፡አፉን በደንብ ከፈተና አየሩን ወደውስጥ ምጎ በመሳብ በአፍንጫው አስወጣው፡፡.አሁን ያለበት የግል ግዛቱ የሆነው እንደቤተመንግስቱ የሚያየው ስፍራ አስር ሺ ካሬ ላይ ያረፈ ቅፅር ግቢ…ወደ ሰሜን አቅጣጨ ጠጋ ብሎ በአንድ ሺ ካሬ ሜር ላይ ያረፈ ግዙፍ ባለአንድ ፎቅ ህንፃ ሲኖር.. ህንፃው….ከመሬት በታች አንደርግራውንድ ቤት ሲኖረው ሙሉ በሙሉ መግቢያው በጀርበ በኩል ሚስጥራዊ መሹለኪ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ በውስጡ ሀያ የሚሆኑ ሳይንቲስቶች ከነረዳቶቻቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያለእረፍት ይሰሩባታል፡፡ ምን አልባትም በአለም ግዙፍ የተባለው የኮኬይን ቅመማ የሚካሄድበት የተሞላ የላባራቶሪ እቀዎች የተተከሉበት….በየወሩ አንድ 100 ኩንታል ኮኬይን ተቀምሞ፤ ተመርቶና በተለያየ መጠን በጥንቃቄ ታሽጎ በኮሎምቢያ …ፓናማና… ሚክሲኮን በመሸገር በአሜሪካ የሚገባበትና የሚሰራጭበት እስከአውሮፓ የሚዘልቅ  ሰንሰለት ያለው ውስብስብ ስራ ነው፡፡
ኮኬይኑ እዛ ደርሶ ከተሰራጨ በኃላ ከሽያጩ ሚሰበሰበው ረብጣ ዶላል ለሁሉም ተወናዬች የየድርሻቸውን በማክፋፈል የቀረውን ዳጎስ የለ ድርሻ ለዳግላስ ተመልሶ የሚመጣበት አሰራር ነው ያለው፡፡ዳግለስ ለዚህ የኮከዬን ምርት ሚሆነውን የኮካ ዛፍ ምርት የሚያገኘው እዚሁ አሁን ካለበት ተያይዞ ካለ መቶ ሺ  ካሬ ሜትር የእርሻ መሬት ነው፡፡ቀሪውን 60 ፐርሰንት ግን ከአካባቢው በቅርብ ርቀት ላይ በአማዘን ደን ወስጥ ሆነ ከዛ ውጭ ተበትነው በሚገኙ ከግለሰብ ሆነ ከብድን እምራቾች ጋር በፈጠረው የንግድ ስምምነት ይሰበስብና ጉድለቱን ያሟላል፡፡
ይሄን ጥሬ እቃውን ከእርሻ ቦታም ሆነ በክፍያ ከሚሰበሰብበት ቦታ የሚሰበበስቡ እንዲሁም የቢዝነሱን ሆነ የእሱን ድህነንት የሚጠብቁ…ግደሉ ሲላቸው የሚገድሉ፤ ሙቱልኝ ሲላቸው የሚሞቱላት በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች አሉት፡፡የህንፃው ግራውንድ ላይ ደግሞ እታች ቤዝመንት ውስጥ ለሚሰሩት ሳይንቲቶችና ዋና ዋና የታጣቂ አዛዦች መኖሪያነት ያገለግለል፡፡ከላይ ያለው የመጀመሪያው ፍሎር ግን ለደግላስ የግል ቤተመንግስቱ ነው፡፡አንድ ግዙፍ ሳሎን፤30 የሚሆኑ መኝታ ቤቶች፤ከአምስት በላይ ቢሮዎችና በአጠቃላይ ከ50 በላይ ክፍሎች ከነቅንጡ እቀዎች ያሉበት ዘመናዊ ቤት ነው፡፡እዛው ቤት ውስጥ ደግላስና አንድ ወንድ እና ሁለት ሴት አገልጋዬቹ ብቻ ናቸው የሚኖሩበት፡፡ከዛ ውጭ እሱ ኖረም አልኖረም ሳይፈቅለድት ወደ እዛ ህንፃ ለመውጣት የሚደፍር ሰው የለም፤ካለም በደግላስ ጥይት ወይ ግንባሩ ይፈረከሳል ወይ ደግሞ ደረቱ ይነዳላል፡፡
ሌላው የህንፃ ጣሪያ ከላይ እይታ እንዳይስብ  አረንጓዴ ሳርና ቋጥኝ መሰል ተክሎች እንዲለብስ ተደርጎ ሙሉ በሙሉ እይታው ከአማዞን ደን ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎል፡፡
የዳግላስን ወደቤቱ መምጡት አስመልክተው በስልፍ ሆነው የእንኳን በሳላም መጣህ አቀባበል ሊያደርጉለት እየጠበቅ ያሉትን ታጣቂዎችና ሌሎች ሰረተኞችን ቀላል እና አጭር ሰላምታ ሰጠና ቀጥታ አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ሔደ፡፡ከዛ ወደዋናኛ መኝታ ቤቱ ነው የገባው፡፡አሁንም ያቺ ጠፋች የተባለችው ኢትዬጵያዊት ሴት በአእምሮው እየተመላለሰች ነው፡፡እሷን እንዳገኞት እስክያበስሯት ድረስ ተረጋግቶ ስራውን በስርአት መስራት እንደማይችል ገብቶታል፡፡ደህንነቱ የተጠበቀ የመገናኛ ስልኩን አወጣና መልሶ ላንቲኒያ ወደሚገኙ የእሱ ሰዎች ደወለ ‹‹እሺ አዲስ ነገር አለ?››
‹‹ሁሉንም ሰው አስማሪቼለው..እስከአሁን አዲስ ነገር አላገኘንም፡፡››

‹የልጅቷ እቃዎች አሉ?››ሲል ያልጠበቀውን ጥያቄ ጠየቀው፡፡
‹‹የእጅ ቦርሰዋን ይዛ ነው  የሄደችው… የልብስ ሻንጣዋ ግን አሁንም ከእኛ ጋር ነው፡፡››
‹‹ውስጡ ምን አለ?››

‹‹እኔ እንጀ! እስከአሁን ከፍተን አላየነውም፡፡››

‹‹ክፈተው››

‹‹እሺ…››

ከተወሰነ ደቂቃ ዝምታና መተረማመስ በኃላ…‹‹ሻንጣው ተቆልፏል እንዴት ላድርግ?››የሚል ቃል ተሰማ፡፡
‹‹አንተ ጀዝባ …ስረህ አልመሆኔ በጀህ እንጂ በዚህ ጥያቄህ ግንባርህን ነበር የመነድልልህ…በጩቤ ዘንጥለህ ክፈተው››አንቦረቀበት፡፡
እንዳለው ከጎኑ የሻጠውን ጩቤ አወጣና የኑሀሚ ሻንጣ ከጉን በኩል ቦትርፎ ከፈተው፡፡ ውስጥ ያለውን እቃ እንዳለ ወለሉ ላይ ዘረገፈ…ቀሚሶች..ጅንስ ሱሪ…ፓንቶች…ጡት ማስያዣ… ማስተወሻ ደብተር……በቀ ይሄው ነው ያለው፡፡››
‹‹በቃ..››በብስጭት ጠየቀ
‹‹አዎ ..ቆይ…ሌላ አንድ አይፓድ አለ፡››

‹‹አዎ እንደእሱ አይነት እቃ ነው የምፈልገው…ክፈተው፡፡››

‹‹እ››ብሎ ለመክፈት ማከረ..ግን አልሆነለትም፡
‹‹አበራሁት …ግን ልከፍተው አልቻልኩም… ፓስ ወርድ አለው››

‹‹በቃ..በቃ አሁኑኑ..ተነስና ለሊቱንም ተጉዘህ ወደእኔ ይዘኸው ና…..ጥዋት ከእንቅልፌ ስነሳ አይፓዱን ካላገኘው..በቃ ሟች ነህ››አለና ስልኩን ዘጋው፡፡
ታጣቂው ወዲያው ነበር ጊዜ ሳያባክን አይባዱን እና የቦተረፈውን ሻንጣ መልሶ ከፍቶ እቃዎችን ወደውስጥ በመመለስ ይዞ ከአካባቢ ገበሬ አንድ ፈረስ ተውሶ ዳግለስ ወደሚገኝበት ሳንቹዋሪ ሽምጥ መጋለብ የጀመረው፡፡
ዳግላስ ጥዋት በጠበቀው ሰዓት አይፓዱ ደረሰው፡፡ እዛው የእሱ ሰረተኛ በሆነ የኮምፒተር ባለሞያ ሀክ አስደርጎ ፓወርዱን ካሰበረ በኃላ ውስጡን ማየት ጀመረ፡፡
የፎቶ አይነት ..እርቃኗን የተናሳችውን ጭመር ..ቪዲዬዎች..፡፡አብዛኛዋቹ ፎቶዎቸና ቪዲዬዎቸ በእሷ አድሜ አካባቢ ካለ ወጣት ጋር አብራ ስትስቅ ..አልያም እላዩ ላይ ተንጠልጥላበት..አዝላው ወይም አዝሏት የተነሱት ወይም የተቀረፁት ነው፡፡ፍቅረኛዋ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነ፡፡አይፓዱን ከኢተርኔት ጋር አገናኘና የተላኩላትን ብዙ መልእክቶች ተመለከተ፡፡ግን በማያውቀው ቋንቋ ስለሆነ መረዳት አልቻለም፡፡ወደጎግል ገበና የኢትዬጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ምን እንደሆነ ጠየቀ፡፡አማርኛ የሚል መልስ አገኘ፡፡አማርኛ የሚባል ቋንቋ መኖሩን እራሱ አያውቅም ነበር፡፡የሀገሬው ቋንቋ እንደሆነ ተረድቷል፡፡ በጣም ነው የተገረመው፡፡በደቡብ አሜሪካ ያሉትን ሀገሮች አሰበ…ፔሩ ፤ኮሎምብያ፤ አርጀንቲና ብሄራዊ ቋንቋቸው እስፓኒሽ ነው..ብራዚል በፖርቹጊዝ ቋንቋ ነው የምትገለገለው፤ኢጎና እንግሊዘኛ ነው ..እንደዛ እያለ ይቀጥላል፡፡ቢያስብ ቢያስብ አንድም ሀገር የራሱን ቋንቋ ብሄራዊ ቋንቋው አድርጎ የሚጠቀም ሊያስታውስ አልቻም፡፡ሀሳቡን ተወና ጎግል ትራንስሌት ከፍቶ መልእክቶቹን ኮፒ ፔስት እያደረገ ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ በመቀየር ለመረዳት ሞከረ፡፡በጣም ነው የተገረመው፡፡ያ ሁሉ መልእክት ከወንድሟ እንደነበረ..እና እሷ በመጥፋቷና አድረሻዋን ሊያገኝ እንዳልቻለ በመጨነቅ በተደጋገሚ ጊዜ የላከላት መልእክት ነው፡፡…ፍቅረኛዋ ነው ብሎ ያሰበው ወንድሟ መሆኑን ሲያውቅ ደስ አለው፡፡በዚህ መጠን የሚተሳሰቡና የሚወደዱ ወንድም እና እህት  መኖራቸውን  ተጠራጠረ…የእሱን  የራሱን  ወንድምና   እህቶች   አሰበና በመሀከላቸው ያለውን መግባባትና ፍቅር መዝኖ ፈገግ አለ፡፡በዘ ቅፅበት ያላሰበው ተንኳል በአእምሮ ብልጭ አለበት፡፡ይህቺ ሴት አምልጣ የመንግስት ተቋም ያለበት አካባቢ በህይወት መድረስ ብትችል እንኳን
👍7415😁2🥰1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

በሰሎሜ ላይ እየሆነ ያለው ግን ተቃራኒው ነው፡፡ወሲብን ሊሰጣት ያልቻለው እሱ ነው፡፡ግን ደግሞ ቢያንስ እስከአሁን ጥላው አልሄደችም፤ቢሆንም በውስጧ የፈጠረባትን ስለልቦናዊ ቀውስ ልትቋቋመው ከምትችለው በላይ እየሆነባት ነው፡፡እንደማንኛውም ሴት በእሷ አረዳድ‹ ከእኔ ጋር ወሲብ የማይፈፅመው  ወሲብ የማድረግ ፍላጎት ሳይኖረው ቀርቶ ሳይሆን እኔን ስለማያፍቅረኝ ቢሆንስ?› የሚለው ሀሳብ ሁሌ ነው በአእምሮዋ እየተሰነቀረ የሚያስጨንቃት፡፡
ከወራት በፊት ግን ይሄንን ለማረጋገጥ አንድ ነገር አድርጋ ነበር፡፡‹‹እንዴት አድርጌ የእውነት እንደሚያፈቅረኝ አውቃለሁ?ከእኔ ጋር ወሲብ ማይፈጽመው ሌላ ቦታ በድብቅ የሚሄድባት ሴት ብትኖስ?››በወቅቱ ዋና አላማዋ እነዚህን በእምሮዋ ይጉላሉ የነበሩ ጥያቄዎችን በተግባር ማረጋገጥና ውጤቱን ተከትሎ የራሷን ውሳኔ ለመወሰን ነበር፡፡
ከብዙ መብሰልሰልና መብከንከን በኃላ ምርጥ ያለችውን እቅድ አወጣች፡፡ ለዚህ ተልዕኮ ልትረዳት የምትችል አንድ ጓደኛዋ ትዝ አለቻት፡፡ሀይስኩል አብራት የተማረቻና ስታገባም  ሚዜዋ የነበረችውን  ሂሩትን ደውላ ቀጠረቻት፡፡
ሂሩት ሰሎሜን ብቻ ሳይሆን አላዛርንም በደንብ ታውቃዋላቸው ….አብረው በመማራቸው የቀረቤታቸው መጠን ይለያይ እንጂ ለሁለቱም ጓደኛ ነች ማለት ይቻላል፡፡ እንደውም ሂሩት ዘጠነኛ ክፍል እያሉ በተወሰነ መልኩ ወደግሩፑ የተቀላቀለችው ለአላዛር ከነባራት የተለየ ፍቅር የተነሳ ነበር፡፡በወቅቱ አማልዬ የራሴ አደርገዋለው የሚል ፅኑ እምነት ነበራት፡፡ለዛም ይረዳት ዘንድ የግሩፑ ብቸኛ ሴት የነበረችውን ሰሎሜን በተለየ ሁኔታ ቀረበቻት፡፡ በኃላ ግን የአላዛር ጉዳይ እንዳሰበችው ባይሳካላትም ከሰሎሜ ጋር ያላትን ጓደኝነት እንደውም ካሰበችው በላይ በጠበቀ ሁኔታ ማስቀጠል ችላለች፡፡ሂሩት ከሰሎሜ ጋር  ስትነፃፀር በጣም ልቅም ያለች ቆንጆ ልጅ ነች፡፡በዛ ላይ በጣም ተጫዋችና ቀልጣፋ፡፡
የተቀጣጠሩበት ሆቴል እንደተገናኙ ለወሬ የቸኮለችው ሂሩት ገና በቅጡ ተቀምጠው ያዘዙት መጠጥ እንኳን ሳይቀርብላቸው ‹‹በፈጣሪ… እንዲህ አንገብግበሽ የጠራሺኝ ምን ልትነግሪኝ ነው?፡፡›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ቆይ ተረጋጊ …ነግርሻለው፡፡››
‹‹የጠረጠርኩት ብቻ እንዳይሆን?››
ሰሎሜ ደንግጣ ‹‹ምንድነው የጠረጠርሽው?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ክርስትና እናት ልትሆኚ ነው እንዳትይኝ?››
ሰሎሜ የሄሩትን ያልተጠበቀ ወሬ ስትሰማ ዘወትር ‹‹መቼ ነው አያት የምታደርጊኝ ?››የሚለው የእናቷ ንዝንዝ ትዝ አላት፡፡
‹‹እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?››
‹‹አንቺ ደግሞ መቼስ እኔ እያለሁ ልጅሽን ለሌላ ሰው ክርስትና አትሰጪያትም!!››
‹‹የምን ልጅ?››
‹‹ተይ ባክሽ…!!!ገና እንገናኝ ስትይኝ ነው የጠረጠርኩት ..አርግዣለሁ ልትይኝ ነው አይደል…?ስንት ወር ሆነሽ…?መቼስ እናትሽ በአንድ እግራቸው ቆመው ደንሰዋል?››
‹‹ፅድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ ››አለች እቴቴ፡፡
‹‹ያንቺ እናት ደግሞ ሁሌ የማይገባ ተረት ነው የሚተርቱት…ምን ማለት ነው?፡፡››
ሰሎሜ በማይረባ የጓደኛዋ ግምት ተበሳጨች‹‹አሁን በፅሞና አድምጪኝ …መጀመሪያ አሁን የምነግርሽን  ነገር ለማንም እንዳትናገሪ…እንደው ብንጣላ እንኳን ሚስጥር አድርገሽ እስከወዲያኛው በውስጥሽ እንድትቀብሪው እፈልጋለው፡፡››
ሂሩት  ፈራች‹‹አረ ችግር የለውም አታውቂኝም እንዴ…?.››
‹‹በእናትሽ ማይልኝ፡፡››
‹‹ይሄን ያህል ምን ቢሆን ነው..?ሰው ገድለሽ ቀብረሽ ነው እንዴ..?ነው ወይስ እንዳቃብርሽ ልትለምኚኝ ነው?በእማሚ ሞት እኔ እንዲህ አይነት ነገር ፈራለሁ፡፡››
‹‹አትቀልጂ!!!... ወይ ማይልኝ ካለበለዚያ  አልነግርሽም፡፡›› ኮስተርተር አለቻባት፡፡
‹‹እሺ እማዬ ትሙት…ለማንም አልናገርም፡፡››
‹‹የባልና ሚስቶች ጉዳይ ነው…››
‹‹ማለት..?››
‹‹የእኔ እና የአላዛር ጉዳይ..››
‹‹አንቺና አላዛር ምን ሆናችሁ?››
‹‹እንዴት ብዬ ልንገርሽ …አሳፋሪ ነው፡፡››
‹‹እንደፈለግሽ አድርገሽ ንገሪኝ፡፡ምንድነው እኔ ጓደኛሽ ነኝ እኮ ..በእኛ መካከል መተፋፈር አለ እንዴ..?ለዛውም ካስማልሺን በኃላ ትቅለሸለሻለሽ?ግፋ ቢል ሰረቅኩበት ልትይኝ ነው፡፡›› በማለት ቅድሚያ ወደአእምሮዋ የመጣላትን ሀሳብ ሰነዘረች፡፡
‹‹በስመአብ….አንቺ …አታውቂኝም ማለት ነው..?እንዴት በባሌ ላይ ሰርቃለሁ?››
‹‹ያልሆነ ነገር እንድገምት ካልፈለግሽ… ንገሪኛ፡፡››
‹‹ወሲብን በተመለከተ ነው፡፡››
ሂሩት ይበልጥ ተነቃቃች..‹‹ወሲብ ምን ?አደገኛ ሆኖ አሰቃየሽ….?ምን…. ኩላሊትሽን እያመመሽ ነው?››
ሰሎሜ ከት ብላ ሳቀች..የመገረም ሳቅ…የንዴትና የብስጭት ሳቅ፡፡
አምጣ..አምጣ ‹‹ወሲብ ማድረግ ካቆምን በጣም ቆየን …››ስትል ጉዳዩን አፈረጠችው፡፡
‹‹ቆየን ማለት…?አምስት ቀን….አንድ ሳምንት..ወይስ አንድ ወር?››
በተጎተተ ንግግር ‹‹ስድስት ሰባት ወር አለፈን…..››አለቻት…፡፡
‹ጭራሽ አድርገን አናውቅም እሰከዛሬ ድንግል ነኝ ›› ብላ ልትነግራት አቅም ማግኘት አልቻለችም….እንዴት ከገባሁ አንድ አመት ቢያልፈኝም ባሌ እስከዛሬ ነክቶኝ አያውቅም..  ብላ ከአንደበቷ  አውጥታ ትናገር.. ለዚህ ነው ከፊል እውነትና ከፊል ውሸት ደባልቃ ነግራት መፍትሄ ያለችውን ሀሳብ አቅርባላት እንድትተባበራት ለመጠየቅ የፈለገችው፡፡
‹‹ሰባት ወር…!!ምነው ?እናንተ ባለትዳሮች እኮ አንዴ በእጃችሁ አስገብታችሁ እና የራሳችሁ መሆኑኑ ካረጋገጣችሁ  በኃላ ችላ የምትሉት ነገር አለ፤እምቢ ብለሽው ነው አይደል?››
‹‹አይ …አኔ አይደለሁም፤እሱ ነው እምቢ ያለኝ፡፡››
‹‹እኔ አላምንም..እንዲሁ አይን አይንሽን አፍጥጦ እያየ ..አፍ አውጥቶ አምቢ እልፈልግም ጠግቤያለሁ..አለሽ?››
‹‹ያው አፍ አውጥቶ እምቢ ባይልም…እናድርግ ብሎኝ ግን ጠይቆኝ አያውቅም፡፡››
‹‹እንዴ ባልሽ አይደለ እንዴ…?እሱ ተዘናግቶ መጠየቅ ካቆመ አንቺ አትጠይቂውም?ብዙ ጊዜ እኮ ብር የሚያሳድዱ የቢዝነስ ሰዎች እንዲህ ናቸው….ሚስታቸውና እና ብራቸውን መለየት ይከብዳቸዋል ፡፡ስለዚህ እሱ ዝም ካለ አንቺ መጠየቅ ነበረብሽ››
‹‹እንዴት ብዬ? ምን ነካሽ ሴት እኮ ነኝ?››
‹‹እንዴ ባልሽን…?ወይኔ እኔ በሆንኩ… ከስር አስተኝቼ ነበር ….በግድ የምደፍረው››
‹‹ባክሽ አትቀልጂ…ወንድ ልጅን ደግሞ እንዴት አድርገሽ ነው የምትደፍሪው?፡፡››
‹‹ለምን አልደፍረውም ..ምነው ጉልበተኛ ስለሆኑ..?እነሱ ጉልበተኛ ቢሆኑም እኛ ደግሞ ከእነሱ የተሻልን ጥበበኞች ነን››
‹‹የጉልበቱ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ …እንዴት አድርገሽ ታቆሚዋለሽ››አላቻት እያፈረች፡፡
‹‹ባክሽ ዘዴ አይጠፋም…አሽቼም ሆነ አልቤ እንዲቆም ማድረግ አያቅተኝም፡፡››
‹‹ይሁንልሽ… አሁን  ይሄንን ጉዳይ እንድፈታ እንድታግዢኝ ነው  የምፈልገው፡፡››
‹‹እንዴት አድርጌ …?በማቆም ነው በመድፈር…?ምን? እጅና እግሩን እንድይዝልሽ ትፈልጊያለሽ?››
‹‹እኔ ተጨንቄ ምሆነው ጠፍቶኛል አንቺ ትቀልጂብኛለሽ አይደል…?በቃ ተይው ተነሽ እንሂድ››ሰሎሜ ተበሳጨች፡፡
‹‹በቃ እሺ ይቅርታ….ንገሪኝ እሺ ምን እንዳግዝሽ ነው የምትፈልጊው?፡፡››
‹‹ምን አልባት ከእኔ ጋር ወሲብ መፈፀም ያቆመው ጠልቶኝ ማለቴ ፍቅሩ አልቆ ይመስለኛል..ያንን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ፡፡››
‹‹አረጋግጠሸስ?››
👍678
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
===================

አላዛር አልጋ ላይ ተጋድሞ በጥልቀት እያሰበ ነው፡፡ሰሎሜ ቀን ከሂሩት ጋር ያወራችውንና የዶለተችውን ነገር መልሳ በደንብ እያመዛዘነች ስለሆነ ፈጥና ወደመኝታ ቤት ለመግባት አልፈለገችም፡፡ሳሎን ሶፋ ላይ ተዘርግታ አይኖቾን የተከፈተው ቲቪ ላይ በመሰካት በሀሳብ ግን ነጉዳለች፡፡

በተመሳሳይ አላዛርም የባለቤቱን የከረረ የስሜት መለዋወጥ በእራት ሰዓት ስላስተዋለ ጥልቅ ትካዜ ውስጥ ገብቷል፡፡ ‹‹እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምቀጥለው?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ሚስቱን ያፈቅራታል..፡፡በጣም ነው የሚያፈቅራት፡፡ለመጀመሪያ ቀን ካገባት ቀን ጀምሮ በሙሉ ልቡ እየተንከባከባት ነው፡፡ግን ምንም ያህል ቢጥር ደስተኛ ሊያደርጋት አልቻለም፡፡እስከአሁን እንደወንድሟ ነው አብሯት እየኖረ ያለው፡፡መሆን የሚገባው  የሚጠበቅበትም ግን እንደባሏ መሆን ነበር፡፡እንደዛ ቢሆን ልክ እንደተመኘው ሙሉ ደስተኛና ፍልቅልቅ ትሆንለት ነበር፡፡ ያንን ማድረግ ግን አልቻለም…፡፡በጣም እያስጨነቀው ያለው ደግሞ እስከአሁን አለመቻሉ አይደለም..፤ መቼ ሊችል እንደሚችል ፍፁም አለማወቁ ነው፡፡እጅን አንቀሳቀሰ እና ወደቢጃማ ኪሱ ሰደደ..ስልኩን አወጣና ጎግል ከፈተ፡፡ ስንፈተ ወሲብ ብሎ  ሰርች ሲያደርግ ብዙ ምርጫዎች መጡለት፡፡

ከመካከላቸው በደመነፍስ መረጠና አንዱን ከፈተው፡፡ትራሱን ቀና አድርጎ አስተካከለና  የሆነ የሚጠቅም ነገር ባገኝ በሚል ተስፋ ማንበብ ጀመረ፡፡

ርእሱ ‹‹የስንፈተ ወሲብ አይነቶች ፤ምክንያቶችና መፍትሄዎቹ›› ይላል፡፡

በወንዶች ላይ የሚታዩት የስንፈተ ወሲብ ችግሮችን በሶስት መልኩ ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ አንደኛው የብልት መነሳት ችግር ወይም በሌላ አገላለፅ ስንፈተ ወሲብ እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡ ሁለተኛው እርካታ ደረጃ ሳይደርስ የዘር ፈሳሽ ማውጣት ወይም ገና አካባቢው ጋር እንደደረሱ  መርጨት   ሲሆን ሶስተኛው  ደግሞ የወሲብ ስሜት አልባነት ወይንም ጭሩሱኑ ወሲብ  ለማድረግ  ፍላጎት ማጣት ናቸው፡፡
አላዛር ንባቡን ገታ አደረገና ስላነበበው ነገር ማሰላሰል ጀመረ..‹‹ከእነዚህ ሶስት ምክንያቶች መካከል የእኔ ችግር የትኛው ላይ ነው የሚያርፈው?››ሲል እራሱን ጠየቀና

ማሰላሰል ጀመረ፡፡የእሱ ችግር ሙሉ በሙሉ የወሲብ ስሜት ማጣት እንደሆነ ተረዳ፡፡እና ንባቡን ካቆመበት ቀጠለ፡፡
የመጀመሪያውን ስንመለከት የብልት መነሳት ችግር ያለባቸው ሰዎችን በብዛት እናገኛለን፡፡ ይሄ አይነት የወሲብ ችግር በተለያየ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ላይ የሚከሰት ቢሆንም  በተደጋጋሚ ወደ ህክምና የሚመጡት ግን ዕድሜያቸው ከስልሳ ዓመት በላይ የሆኑት ሰዎች ናቸው ፡፡ አንዳንድ ወጣቶችም አልፎ አልፎም ቢሆን የዚህ ጉዳይ ተጠቂዎች መሆናቸውን ሪፖርት ሲያደርጉ ይታያል፡፡

ችግሩ ከየት ይነሳል? ብለን ስንመለከት ሁለት አይነት ምክንያቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ከስነ ልቦና  ጋር የተያያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተለያዩ በሽታዎች  በሚፈጥሩ የጎንዬሽ ተፅዕኖ ምክንያት ይከሰታል፡፡ ዋነኛው የስንፈተ ወሲብ መንስኤ ተብሎ የሚጠቀሰው የስነ-ልቦና ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአዕምሮ ውጥረት ፤ ጭንቀት እና የተለያዩ ሀሳቦች ለስንፈተ ወሲብ ችግር ያጋልጡናል፡፡  የአካል ድካም እና መዛልም ሌለኛው ምክንያት ነው፡፡ ለምሳሌ አካሉ በብዙ ስራ ሲንገላታ የዋለ ሰው በግንኙነት ወቅት የብልት መነሳት፣ ስሜት ማጣት አሊያም ለወሲብ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሊገኝ ይችላል፡፡
አንድ ሰው የሀሳብ መደራረቦች በአእምሮው እንደታጨቀ ወሲብ ለማድረግ በሚሞክርበት ጊዜ  ብልት ትክክለኛው ጥልቀት ላይ ደርሶ ተገቢውን እንቅስቃሴ ከማድረጉ በፊት   አስቀድሞ ጥንካሬውን የሚያጣበት ሁኔታ ይከሰታል ፡፡ ይህን በምሳሌ ብንመለከት ከፍቅር ጓደኛው ጋር ወሲብ በሚፈፅምበት ወቅት ነጋዴ ከሆነ ስለተጋረጠበት የንግድ ችግር የመስሪያ ቤት ኃላፊ ከሆነ ስላልተሳኩ የድርጅቱ እቅዶች ካለው ኃላፊነት ጫና የተነሳ በአዕምሮው ሊመላለሱበት ይችላሉ፡፡ ይህም ጥሩ ያልሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳይከውን ምክንያት ይሆነዋል፡፡ግብረስጋ ግንኙነት ደግሞ በባህሪው ሙሉ ለሙሉ ትኩረት የሚሻ የስሜት ተራክቦ ነው፡፡ ሌላው በባልና በሚስት መካከል አለመግባባት እና ቅሬታ በሚኖርበት ጊዜ ተነሳሽነቱ በሁለቱም ወገን ይቀንሳል፡፡……..
እስከአሁን ያነበባቸው የስንፈተ ወሲብ ችግር የሚያጋልጡ ምክንያቶች ለጠቅላላ እውቀት ጥሩ ግንዛቤ የሰጡት ቢሆንም ቀጥታ የእሱን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል መፍትሔ ሚጠቁሙ ሆነው አላገኛቸውም..ቢሆንም ግን ተስፋ ቆርጦ ንባቡን ማቋረጥ አልፈለገም…ትንፋሹን ሰበሰበና ማንበቡን ቀጠለ፡፡
የአንድሮጂን ሆርሞን መመረት ወንዶች ላይ ብዛት ያለው  የደም ፍሰት ወደ ብልት እንዲዘዋወር በማድረግ ብልት እንዲነሳ ያደርጋል፡፡ ከላይ የጠቀስናቸው እንደ ጭንቀት፤በስራ መዛል ወዘተ አይነት  ምክንያቶች ይህን ሆርሞን በተገቢው መንገድ እንዳይመረት ያደርጋል፡፡በዛም ምክንያት ወደብልት የሚፈሰው የደም መጠን አናሳ ስለሚሆን የብልት በተገቢው ጥንካሬ የመቆም ችግር ያጋጥመዋል፡፡ይሄን ለማካካስ ሲባል በተለይ በወጣቶች የወሲብ  ፊልሞች ለማየት ወደመነሳሳት  ያዘነብላሉ፣ ይሄም  በጫና፣ በሃዘን እና በድካም ላይ ሆነንም የወሲብ ስሜታችን እንዲነሳሳ ያደርጋል፡፡ያ ደግሞ በተለይ ለብልት መነሳሳት አና ለፍላጎት መጨመር ጊዜያዊ መፍትሄ ሆኖ ቢያገለግልም በቆይታ ግን የራሱ የሆነ የጎንዬሽ ጉዳት ማስከተሉ አይቀርም፡፡የፊልም ኢንደስትሪው ሚያመነጫቸው የወሲብ ፊልሞች በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከዛም አልፎ በጎልማሶች ዘንድ በደንብ የሚታዩ ናቸው፡፡እንዚህ ወሲብ ፊልሞች ከላይ ሲታዩ እጅግ ማሪኪ ስሜት ቀስቃሽና መንፈስ አነቃቂ መስለው ቢታዩም በሚያየው ወጣት ላይ የሚያስከትሉት ስነልቦናው ቀውስ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡አንደኛ ወጣቱ የአካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ዝግጅት ሳያደርግ ወጣ ያሉ አፈንጋጭ ወሲባዊ ተራክቦ እንዲያደርግ ይወሰውስታል፡፡ያ ደግሞ ለቋሚ  የጤና ችግርና  ወሲባዊ ችግር ይዳርገዋል፡፡ሁለተኛ በፊልሞቹ የሚደረጉ ወሲባዊ ተራክቦዎች ከሰውኛ ይልቅ ሜካኒካል ገፅታ ያላቸው ከ30 ደቂቃ አስከአንድ ሰዓት የሚዘልቁ አይነቶች ናቸው፡፡

እርግጥ አንድ ሰው በውሲብ ግንኙነት ያንን ያህል ሊቆይ አይችልም ለማለት አይደለም….ግን ከሺ ጥንዶች በአንዶቹ የሚከሰት ነገርን  እንደኖርማልና የተለመደ አድርጎ ማቅረብ በአብዛኛው ላይ የሚፈጥረው ስነልቦናዊ ውዥንብር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ለምሳሌ በስንፈተወሲብ ችግር የሚመደበው ቀድሞ መርጨት ችግር የሚባለው አንድ ሰው ወሲብ ጀምሮ ከአንድ ደቂቃ በታች በሆነ የጊዜ ርዝመት ውስጥ የዘርፍሬውን ካፈሰሰ ነው፡፡እንግዲህ ሁለትም ሶስትም አምስትም ደቂቃ ኖርማልና በብዙ ውንዶች የሚከሰት ነው ማለት ነው፡፡ይሄንን ሀቅ ወንዱም ሆነ ሴቷ ማወቅ አለባቸው፡፡ሀያ ..ሰላሳ ደቂቃ መቆየት የቻለም እንደዛው ያንን እንደጀግንነት ማውራት ትርጉመ ቢስ ነው፡፡ዋናው ምን ያህል የጊዜ ርዝመት ቆየ ሳይሆን በቅፅበት ውስጥም ቢሆን ምን ያህል ፍፃማዊ ደስታ ተቀያይረናል…ምን ያህል በአየር ላይ ተንሳፈን ነበር…?ምን ያህልስ ሰዓት አንዳችን  በሌላችን ውስጥ ጠፍተን ነበር…?የሚለውን ነው መመዘኛ መሆን ያለበት… እና አንድ ሰው በተቻለው መጠን እነዚህን የምራባዊያን የወሲብ ፊልሞችን ከማየት እራሱን
👍5310
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

አዲስ አለም በራሷ መኪና ግን ሹፌር እየነዳላት  ከአዳማ ወደአዲስ አበባ እየተጓዘች ነው፡፡

የተቀመጠችው ከኋላ ወንበር ላይ ሲሆን ከግራዋ የራሷ ልጅ ቅዱስ ሲኖር ከግራዋ ደግሞ የፀአዳ ልጅ ምሰር ትገኛለች፡፡

አዲስአለም ወደአዲስ አበባ የምትሄደው እናቷን ለመጠየቅ ነው፡፡ይሄ ቤተሰቦቾ አዳማ ለቀው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ  በወር ወይም በሁለት ወር አንዴ የምታርገው ነገር ስለሆነ ማንም ለምን እንዴት ብሎ የሚጠይቃት የለም፡፡ምስርን በምን ሰበብ አስፈቅዳ ከእሷ ጋር ይዛት እንደምትመጣ ግን ግራ ገብቷት ነበር፡፡ማታ ነበር ፀአዳ ጋር የደወለች፡፡

‹‹እሺ ጓደኛዬ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ ምነው ቀን ተገናኝተን ነበር እኮ..በዚህ መሀከል ምን ትሆናለች ብለሽ አሰብሽ?››.

‹‹አንቺ ደግሞ ከአፍሽ ቀና ነገር ቢወጣ ምን አለበት?››

‹‹በይ አሁን ምን ፈልገሽ ነው ወደገደለው ግቢ….››

‹‹በእናትሽ ነገ እነማዬ ጋር አብረን እንሂድ››

‹‹ነገ ››

‹‹አዎ ነገ››

‹‹ያምሻል እንዴ…?ስንት ስራ እንዳለብኝ  ስነግርሽ ውዬ እንዴት የማልችለውን ነገር ትጠይቂኛለሽ?››

‹‹ውይ ለካ ስራ አለብሽ..ብቻዬን መሄድ እኮ ደብሮኝ ነው››

ብቻሽን መሄድ ከደበረሽ  ታዛዥ እና ጣፋጭ የሆነ ምርጥ ባል አለሽ እሱን አስከትለሽ ሂጂ››

‹‹አንቺ እየሰማሽ እኮ ነው››

‹‹ላውድ ላይ አድርሽ ነው እንዴት የምታወሪኝ… አንቺ እኮ ቅሌታም ነሽ….ለነገሩ ሚኪን በተመለከተ መጥፎ ነገር እንደማልናገር እርግጠኛ ስለሆንኩ እንደፈልገሽ››

‹‹መጥፎ ነገር እንደማትናገሪ እኔም ምስክር ነኝ … ውሸት ግን ትናገሪያለሽ..ምን አልባት እንዳልሺው ጣፋጭ ሊሆን ይችላል ታዛዣ ግን አይደለም..ልክ እንደአንቺው ስራ አለኝ አልችልም የሚል መልስ ነው የሰጠኝ››

‹‹በቃ ከልጅሽ ጋር ሒጂ››

‹‹ወይ እንደውም ተውት ከልጆቼ ጋ ሄዳለው…ምስርን ቆንጆ አድርገሽ አሳምሪያትና ወደስራ ስትሄጂ ይዘሻት ውጭ.. በዛው መጥቼ ወስዳታለው››

‹‹ምን እያልሽ ነው?››ፀአዳ እንደመበሳጨት አለች፡፡

‹‹የራስሽው ምክር እኮ ነው፡፡ልጆቹን ይዤ ሄድና ዘና እንላለን…እናንተም ካለልጆቻችሁ ይድላችሁ…እሁድ ማታ ተመልሰን እንመጣለን፡፡››

‹‹አንቺ እኮ የሆነ መዠገር ነገር ነሽ…እኔ ለራሴ ስንት ስራ አለብኝ..?ገና አሁን እሷን ሰውነቷን ሳጥብ..ፀጉሯን ሰሰራ….››

አላስጨረሰቻትም፡፡‹‹በቃ…ጥዋት ሁለት ተኩል አካባቢ ስራ ቦታሽ እመጣና ወስዳታለው..ደህና እደሪ..እወድሻለው፡፡››ብላት ስልኳን ዘጋችው፡፡እንዳለችውም ጥዋት ስትሄድ ፀአዳ ከነንጭንጯ ልጇን ምስርን አስባና አሳምራ ነበር የጠበቀቻት፡፡

‹‹ውይ ጎደኛዬ ንዴት እንደሸወድኩሽ ስታውቂ እንዴት ትናደጂ ይሆን?›› ብላ አሰበችና ብቻዋን ፈገግ አለች፡፡

ሹፌሩ ጎሮ አካባቢ የሚገኘው የቤተሰቦቾ ቤት ካደረሳት በኃላ  ሚካኤል እንዲገዛለት ያዘዘው ዕቃዎች ስለሉ ወደመርካቶ ለመሄድ ተዘጋጀ….

‹‹በቃ ነገ አስር ሰዓት አካባቢ እዚህ ድረስ ››አለችው አዲስ፡፡

‹‹እዚህ የምትንቀሳቀሺበት አይቸግርሽም?››

‹‹ችግር የለውም..የትም የመውጣት እቅድ የለኝም…ምን አልባት የምወጣም ከሆነ ራይድ እጠቀማለው››አለችና ሸኘችው፡፡

ከዛ ልጆቹን ወደቤት አስገብታ እናቷን በቅጡ እንኳን ሰላም ሳትል ነው ወደጓሮ ሄዳ ስልክ የደወለችው፡፡ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ‹‹እንዴት ነህ ዘሚካኤል?››

‹‹ሰላም ነኝ..ግን አልተሳካልኝም ብለሽ እንዳታበሳጪኝ››

‹‹አረ ተሳክቶልኛል…መጥተናል እማዬ ቤት ነው ያለነው፡፡››

‹‹በጣም ጎበዝ…..በቃ ጎሮ አካባቢ ነው ያልሺኝ፡፡››

‹‹አዎ… ትክክለኛ አድራሻውን በሚሴጅ ልክልሀለው››

‹‹በቃ..በአንድ ሰዓት ውስጥ እመጣለው››

‹‹ጥሩ ነው..እኛም ገና አሁን መድረሳችን ስለሆነ እስከዛ ከእማዬ ጋ እንጫወታለን…በል ቻው››

‹‹አዲስ በጣም አመሰግናለው…ቻው››

ስልኩ ተዘጋ ፣፣እሷ ግን ፈዛ ቀረች…ከዘሚካኤል ጋር በዚህ መጠን መቀራረብ መቻሏ የተአምር ያህል ነው….ለዘመናት ስታልመውና ስትመኘው የነበረ ነገር ነው፡፡ግን በዚህ መንገድ ይሆናል ብላ ፈፅሞ ሀሳብ አልነበራትም..እሱ የእሷን የልብ ጓደኛ አፍቅሮ እሷ ደግሞ እሱን ከሚያፈቅራት ልጅ ጋር ለማቀራረብ ስትጥር….በራሷ ድርጊት ፈገግ አለች፡፡

‹‹ምን አለበት…. ለሚያፈቅሩት ሰው የሚያፈቅረውን ነገር እዲያገኝ መርዳት ትንሽ ህመም ቢኖረውም ግን ደግሞ ደስ የሚል ስሜት አለው፡፡››አለችና ለስሜቷ ድጋፍ ለመስጠት ሞከረች…የባሏ ሚካኤል ምስል በድንገት መጥቶ አየሩን ሞላው‹‹ፍቅሬ ምን እያሰብሽ ነው…?የገዛ ወንድሜን!!!››ብሎ በሀዘን በተሰበረ ስሜት ሲወቅሳት አየች፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ይሄ እኮ ያለፈ ታሪክ ነው….ታውቃለህ እሱን ለማግኘት ስትጥር ነበር ከአንተ ጋር የተቀራረብኩት…ከዛ እሱም ሀገር ጥሎ ጠፋ አንተም ለእኔ ምርጥና ተወዳጅ ሆንክልኝ..እናም  በሙሉ ልቤም ወድጄ አገባሁህ››

‹‹ግን ስታገቢኝ…ወደሽ ነው..ወይስ አፍቅረሺኝ?››

‹‹አይ አንተ ደግሞ ምን ቃላት ትመነዝራለህ….ለማንኛውም..የእሱ ያለፈ የአፍላ የወጣትነት ስሜት ነው..አሁን እየቀረብኩትና እየረዳሁት ያለሁት ያንተ ወንድም ስለሆነ ብቻ ነው››

‹‹እንዴ…!!ምንድነው  ጓሮ ተደብቀሽ ብቻሽን ምታወሪው?››የእናትዬው የመገረም ንግግር ነበር ከገባችበት ቅዠት መሰል ሀሳብ አባኖ ያወጣት፡፡

‹‹አይ እማዬ ..ምንም አይደል ..የሆነ ነገር እያሰብኩ ነበር››

‹‹የሆነ ነገር..ምነው ከሚካኤል ጋር ተጣላችሁ እንዴ?››

‹‹ወይ እማዬ ምንድነው የምታወሪው..?ከሚካኤል ጋር ለምንድነው የምጣለው?››

‹‹ባልና ሚስት ለምንድነው የሚጣሉት?››

‹‹እኔ እንጃ..እኔና ሚኪ ስንጣለ አይተሸን ታውቂያለሽ?››

‹‹እሱ መልካምና ታጋሽ ባል ስለሆነ ነዋ…እንጂማ እንደአንቺ መመነጫጨቅ ቢሆን… ››እናትዬው ነግግሯን ሳታገባድድ አንጠልጥላ ተወችው፡፡

‹‹እማዬ ደግሞ… የእኔ እናት ነሽ  የእሱ?››

‹‹የሁለታችሁም…ባሌ ነው ብለሽ አምጥተሸ ካስተዋወቅሺኝ ቀን ጀምሮ እኮ ልክ እንደአንቺ እሱም ልጄ ሆኗል…በዛ ላይ አሁን ወርቅ የሆነ የልጅ ልጅ ሰጥቶኛል…በይ አሁን ነይ ግቢ ቁርስ ቀርቧል…››አሏትና ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ፡፡ 

ዘሚካኤል እንዳለውም ከአንድ ሰዓት በኃላ በራፍ ላይ ደርሶ ደወለላቸው፡፡ተዘጋጅታ ስትጠብቀው ስለነበረ ወዲያውኑ ነው ልጆቹን ይዛ የወጣችው፡፡ከግዙፉ ሀመር መኪናው ወርዶ በራፍን ከፍቶ ቆሞ እየጠበቃቸው ነበር…የስድስት አመቷ ምስር እንዳየችው ደነገጠች…..መጀመሪያ የት እንደምታውቀው ነበር ግራ የገባት..ከዛ የምትወደው ዘፋኝና ተዋናይ መሆኑን ስታውቅ ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት እየተንደረደረች ወደ እሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ከቆመበት እጆቹን ዘርግቶ ወደእሷ ተንቀሳቀሰ…እቅፉ ውስጥ ወደቀች.. ጭምቅ አድርጎ አቀፋትና በአየር ላይ አንጠለጠላት..የምስርን ድርጊት ያየው ቅዱስ እጆቹን ከእናቱ እጅ አስለቅቆ ኩስ ኩስ እያለ ምስር እንዳደረገችው ወደዘሚካኤል ሮጠ….አዲስአለም በልጆቹ ያልተጠበቀ ድርጊት  በድንጋጤ አፏን ከፈተች ….ሚካኤል ቅዱስ ስሩ ሲደርስ ምስርን ወደአንዱ እጁ አዘዋወራትና ጎንበስ ብሎ ቅዱስን አቅፎ ወደላይ አነሳውና ጉንጮቹን እያገላበጠ ሳመው…..በዚህ ጊዜ አዲስ አለም ከመደነቅ ሳትወጣ ስራቸው ደርሳ ነበር፡፡

‹‹ቆይ ከእነዚህ ልጆች ጋር ከዚህ በፊት ትተዋወቁ ነበር እንዴ?››

ጉንጮቾን እያገላበጠ ሰማት..ትንፋሹ ልክ ሰው ፊት ላይ እደሚበትን አደንዛዥ ዕፅ ኃይል አለው…
👍6617
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////
ራሄል ዶ/ር ኤልያስን ማግኘት ስለፈለገች ስልኳን አንስታ መጀመሪያ ሞባዩሉ ላይ ደወለች….ዝግ ነው፡፡ከዛ ሆስፒታል ደወለች፡፡ከተወሰነ ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡

‹‹ሄሎ እባኮት ዶ/ር ኤልስን ማግኘት እችላለው?››

‹‹ይቅርታ የእኔ እመቤት ዶ/ሩ ዛሬ ስራ ››
‹‹ነገር ግን ዶክተር ኤልያስ የግድ ማግኘት  አለብኝ››አለች ኮስተር ብላ፡፡… ራሄል የረጠበ ጨርቅ በፀጋ ፊት ላይ እያስቀመጠች የሰውነቷን ሙቀት ለማስተካከል በመጣር ስልኩን እያወራች ነው። ከሁለት ቀናት በፊት ከቤታቸው ከተከናወናው የበጎ አድራጎት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት  ጀምሮ፣ ፀጋ ተለዋዋጭ በሆነ የጤና ችግር እየተሰቃየች ነው፡፡ 
በዛን ቀን ከሌንሳ መንታ ልጆች ጋር አብራ ስትጫወት ነበር ፡፡ምን አልባት ከእነሱ የሆነ ጉንፋን አይነት በሽታ ወስዳ ሊሆን እንደሚችል ጠረጠረች። ሌንሳ ትናንት ለራሄል ደውላ አንደኛዋ ልጇ ትንሽ ንፍጥ እና ትኩሳት እንዳለባት ነግራት ነበር። ለፀጋ በጣም  ተጨነቀች፣ እና አሁን ጭንቀቷ ትክክል የሆነ ይመስላል።

በስልክ መስመር ላይ ያለችው የዶክተሩ ፀሐፊ ‹‹ይህን ተረድቻለሁ ግን የሱን ቀጠሮዎች በሙሉ ወደሌላ ቀን ለማዘዋወር በሂደት ላይ ነኝ። ይቅርታ፣…. በቤተሰብ  ላይ ባጋጠመው ድንገተኛ ችግር ምክንያት ለአንድ ሳምንት ያህል ወደስራ መግባት አይችልም፡፡››

ራሄል ሴትዮዋን አመሰገነች እና ስልኩን ዘጋችው‹‹ ዔሊ ምን አይነት የቤተሰብ ችግር ነው ያጋጠመው?››ፍርሀት ሰውነቷን ወረራት፡፡ባለፈው ምርጥ ጊዜ አሳልፈው በመጥፎ ሁኔታ እንደተለያዩ አሰበችና እራሷን ወቀሰች፡፡ስለ ፀጋ  ምን ማድረግ እንዳለባት መወሰን አልቻለችም፡፡
ፀጋ አይኖቿን በእጆቿ እያሻሸች‹‹መጠጣት እፈልጋለሁ›› አለቻት ።ራሄል አንድ ብርጭቆ ጭማቂ  ሰጠቻት፣ከዚያም አብራት በኩሽና ወንበር ላይ ተቀምጣ አቀፈቻት ።ራሄል ብርጭቆውን  ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች እና ፀጋን በእርጋታ እያወዛወዘች ለስለስ ያለ ዘፈን ትዘፍንላት ጀመር። ሌላ ምን ማድረግ እንዳለባት አላወቀችም።ፀጋ ጧዋት ሙሉውን ጊዜ ስትበሳጭ ነው ያረፈደችው፣ እና የሙቀት መጠኑ በጣም ከፍተኛ ባይሆንም ራሄል መጨነቋን ማቆም አልቻለችም ።ራሄል የእህቷን ጭንቅላት በስሱ ሳመቻት፡፡

‹‹ኤሊ የት ነው ያለኸው?›› ብላ በሹክሹክታ ተናገረች፡፡
ነገሮች እንዴት በፍጥነት እንደተቀየሩ አስቂኝ ሆነውባታል። እሷ በዚህ መጠን  እሱን ማነጋገር መፈለጓ በጣም የሚገርም ነው…. የዚያን የዝግጅት ቀን ምን እንደተሰማት ለማስረዳት ፈልጋለች። በሁለቱ መካከል ስላለው ነገር  በጥንቃቄ ማስረዳት ፈልጋለች፣ ግን ይህን ማድረግ በእሱ እይታ  ምን ያህል የተጋለጠች እንደሚያደርጋት ፍራቻ አድሮባታል። ፀጋን መልሳ ወደ አልጋው ወስዳ አስተኛቻት… ፀጋ አልተቃወመችም… ይህም ለራሄል ልጅቷ ምን ያህል እንደታመመች እንድትረዳ አደረጋት። ከሰአታት ስቃይ በኋላ ተኛች። እሷን  ሊያሳስብ  በሚችል ጸጥ ባለ ጽናት ነው የተኛችው።ትንሽ ተጨማሪ ጉልበት እንድታሳይ ፈለገች። ለብዙ ደቃቂ  ስሯ ከተቀመጠች በኃላ በጸጥታ ክፍሉን ለቃ ወደ ቢሮዋ ሄደች። ከፋውንዴሽኑ የፋይናንስ ክፍል የቀረበውን ዘገባ አነበበች፣ ሮቤል እንዲከታተል የሚያሳስብ ጥቂት ማስታወሻዎችን አዘጋጅታ ጥቂት የስልክ ጥሪዎችን አደረገች።ከዛ  ለዔሊያስ ለመደወል ሞከረች… ነገር ግን  ያገኘችው የመልስ ማዳመጫ ማሽኑን  ድምፅ ብቻ ነው.፡፡

ራሄል ብቸኝነት ተሰማት።ወደ ፀጋ ክፍል ስትመለስ  ኮሪደር ላይ  አለምን አገኘቻት።

‹‹ራሄል የደከመሽ ትመስያለሽ…ለምን ለትንሽ ጊዜ ወጣ ብለሽ አትመለሺም?ጸጋን እኔ ልከታተልሽ። ››አለቻት፡፡

‹‹ፀጋ አሁንም መተኛቷን ለማረጋገጥ  ወደክፍሏ ዘልቃ ገባችና ተመለከተቻት።ተኝታለች ፣ተመልሳ ወጣችና በራፍ ላይ ካለችው አለም ጋር ማውራቷን ቀጠለች፡፡

‹‹ በጣም ፈታኝ ይመስላል…አለም››

‹‹ግድየለሽም …ሞባይልሽን ይዘሽ መውጣት አለብሽ… ፀጋ ተኝታለች፣ ደህና ትሆናለች..ችግር ካለ ወዲያው ደውልልሻለው።››የሚል ሀሳብ አቀረበችላት፡፡

‹‹ራሄል አለም ትክክል እንደሆነች ታውቃለች። ከገቢ ማሰባሳቢያው ቀን ጀምሮ፣ ስለ ዔሊያስ መርሳት አልቻለችም። በምትኩ እራሷን ወደ ስራ እና ፀጋን በመንከባከብ ውስጥ አስገብታ ነበር። ዓይኖቿ እስኪቃጠሉ ድረስ የቢሮዋን ስራ በቤቷ ውስጥ ሠርታለች፣  ነገር ግን እራሷን ስለእሱ እንዳታስብ ለማድረግ የወሰደችው እርምጃ ሙሉ በሙሉ አልሰራላትም። ከሁሉም በላይ ዔሊያስን የሳመችበት ክፍል ውስጥ መገኘቱ ትዝታውን ደጋግሞ እንዲቀሰቀስባት አድርጎታል። በአእምሮዋ ውስጥ ሌሎች ሀሳቦችን ለማስቀመጥ ፤ለጊዜውም ቢሆን ያንን ክፍል ለቃ መውጣት አለባት።ሞባይሎን እና የመኪናዋን ቁልፍ ይዛ ‹‹እሺ ከአንድ ሰአት በኋላ እመለሳለሁ››ብላ ወጣች…. መኪናዋን አስነሳችና ተንቀሳቀሰች፡፡
   ከአርባ ደቂቃ ጉዞ በኃላ   ራሔል በድንገት የ ዔሊያስ አዲሱ ቤት   በሚገኝበት ጎዳና ላይ እራሷን አገኘችው፡፡  የመኪናውን ፍጥነቱን አቀዘቀዘች። እሷ በዚህ መንገድ ለመምጣት አላሰበችም ነበር፡ በእውነቱ የጉዞው ምክንያት ስለ ዔሊ ለመርሳት  ነበር። ሳታስበው ግን እሱ ቤት ፊት ለፊት ተገኝታለች፡፡ፀሐፊው የቤተሰብ ችግር አጋጥሞት ከከተማ እንደወጣ ነበር የነገረቻት ነገር ግን የዔሊ ሞተር ሳይክል ከቤቱ ፊት ለፊት  ዛፍ ጥላ ስር ቆሞ ነበር።
‹‹ርቆ ቢሄድ ኖሮ  ሞተር ሳይክሉን ከእሱ ውጭ ሌላ ሰው መኖር ባልጀመረበት ቤት በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ጥሎ አይሄድም ነበር..››ስትል አሰበች
በውስጧ ሲጉላላ የከረመውን በእሱና በእሷ መካከል ስላለው ነገር  ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስተካከል አለባት።እሷ ዔሊን መንከባከብ ትፈልጋለች, እሱ እንደሚያስብላት ታውቃለች…እሷም በጣም ታስብለታለች…ትጨነቅለታለች፡፡ግን ደግሞ በልቧ ውስጥ ፍራቻ ሚረጭባትን ስሜት  ለእሱ መንገር እንዳለባት ታውቃለች፡፡ወደእሱ ለመቅረብ ታመነታ ነበር …አዎ፣ ወደ ሌላ ግንኙነት ለመግባት ፈርታለች። ቀድሞውንም ይሄንን ብታብራራለት ይረዳት ነበር። ሁለቱም ትልልቅ ሰዎች ናቸው። በመሀከላቸው ያለው ነገር  ቀላል መሆን አለበት…. መኪናዋን ከሞተር ሞተሩ አጠገብ አቆመችና የቤቱን ደረጃ ወጣች ። የቤቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ገጽታ ውስጡን ለማየት እንድትጓጓ አድርጓታል። የቤቱ ውጫዊ ክፍል በቅርብ ጊዜ የሚጠናቀቅ አይነት ቢሆንም ግቢው ተጨማሪ ሥራ እንደሚያስፈልገው አስተዋለች። ጠርዝ ላይ ባለው የአበባ አልጋ ላይ ምን ዓይነት ተክሎች መቀመጥ እንዳለባቸው በምናቧ እየቀረጸች አሰላሰለች, በሩ ተከፈተ። ዔሊ ከፊት ለፊቷ ቆመ፣ ያልተላጨ ፂሙ፣  ክፍት ሸሚዙ፣ መላ ቁመናውን  በሰከንድ ሽርፍራፊ አስተዋለች።
‹‹ሄይ… ራሄል ምን አመጣሽ?››
ፊቱ ላይ ምንም አይነት የተለየ ስሜት ማንበብ አልቻለችም ፡፡ ‹‹ትንሽ አየር ልውስድ  ብዬ በመኪና ወጥቼ ነበር፣ድንገት በዚህ ሳልፍ  የሞተር ሳይክልህን አየሁና ፣ እናም...››
በእጁ  አንድ ወረቀት ይዟል..እጇቹ እየተንቀጠቀጡ መስሎ ተሰማት፡፡   ፎቶ መሆኑን ለየች ፣ወዲያው ከእጁ አመለጠውና ወደቀበት… ራሄል ልታነሳለት ጎንበስ ስትል ኤሊያስ እጁን  በፍጥነት ዘረጋና ለቀም አደረጋት።አስደነገጣት፡፡
በሻከረ ድምጹ‹‹ተይው እኔ አነሳዋለው፣ቆሻሻ ነው ›› አላት ፡፡
56👍1🔥1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////

‹‹ለፈረሶች የምታሳየውን ፍቅር ግማሹ ለሰው ብታሳይ እንዴት ጥሩ ነበር….ፈረሶችህን በትህትና ስታናግር ከቆየህ በኋላ ከሰው ጋር ማውራት ስትጀምር ቶንህ ወዲያው ይቀየርና ተናዳፊ ትሆናልህ››

የምፀት ፈገግታ ፈገግ አለና‹‹ለፈረሶችም ሆነ ለሰዎች የሚገባቸውን ነው ማደርገው….››አለና አጥሩ ላይ የተንጠለጠለውን ኮርቻ በማንሳት ፈረሱ ጀርባ ላይ አድርጎ አሳሰረውና የፈረሱን ሉጋም ይዞ ወደመውጫው መሄድ ጀመረ፡፡
ግራ ተጋብታ

"ወዴት ትሄዳለህ?"ስትል ጠየቀችው

" ትንሽ መጋለብ ፈልጋለው"

ከንዴቷ አንፃር ማልቀስ አማራት ‹‹ላናግርህ እፈልጋለሁ..ለምን እንደመጣሁ እያወቅክ ጥለኸኝ ልትሄድ ነው..?›› አለችው

ፈረሱ ላይ ወጣና ወደእሷ ቀረበ…እጁን ዘረጋላት….ግራ ተጋብትና በቆመችበት አይኖቾን አቁለጨለጨች….

‹‹እጅሽን ስጪኝ››አላት…..ዝምብላ ቀኝ እጇን ወደላይ ሰቀለችለት.. አጥብቆ ያዛትና ወደላይ ጎተታት…ጥንካሬው አስገረማት….እርካብ ላይ እግሯና አኖረችና እንጣጥ ብላ በመውጣት ከጀርባው ፈረሱ ላይ ተፈናጠጠች፡፡ከዛ ለፈረሱ ሉጋሙን ለቀቅ ሲያደርግለት ፈረሱ እየሰገረ ወደፊት ተስፈነጠረ ፡፡በፍራቻ ወገቡን አጥብቃ አቀፈችው….የኮረኮንች መንገዱን ይዞ ወደ ከተማዋ መውጫ ሽምጥ መጋለብ ጀመሩ….፡፡
"ትላንትና ማታ በቡና ቤት ውስጥ ከማን ጋር ነበር የተገናኘሽው?"

"ይሄ የኔ ጉዳይ ነው ኩማንደር …ለምን ተከተልከኝ?"ልትጠይቀው የምትፈልገው ብዙ ጥያቄዎች ነበራት፣ ነገር ግን በእያንዳንዱ የፈረስ እንቅስቃሴ ከተቀመጠችበት እንጣጥ ብላ ጀርባው ላይ ስትለጠፍበት ስለነበር አእምሮዋን በጀመረው ሀሳብ ላይ ፀንቶ እንዲቆይ ማድረግ ከባድ ሆነባት። እንደምንም ወደ አእምሯዋ የመጣውን የመጀመሪያ ጥያቄ ጠየቀችው።

"አንተ እና እናቴ እንዴት የቅርብ ጓደኛሞች ሆናችሁ?"

"አብረን ነው ያደግነው" አለ በንቀት። ተንፋሽ ወሰደና ቀጠለ"ት/ቤት መጫወቻ ሜዳ ላይ ተጀምሮ በእድሜ እየገፋን ስንሄድ ተሻሻለ"

"አስቸጋሪ ሆኖ አያውቅም?"

"አይ አንዳችን ከሌላችን የምደብቀው ምንም ምስጢር አልነበረንም. እንዲያውም ያንቺን ካሳየሺኝ የእኔንም አሳይሻለው እያልን እንጫወት ነበር."አለና ፈገግ አለ።‹‹በአጠቃላይ በእኔ እና እሷ መካከል አይነኬ የተባለ የውይይት ርዕስ አልነበረም ።››ሲል አከለበት፡፡

"ያ አንድ ሴት ልጅ ከሌላ ሴት ጋር የሚኖራት አይነት ግንኙነት አይደለምን?"

‹‹ብዙውን ጊዜ ግን ሰሎሜ ብዙ የሴት ጓደኞች አልነበራትም, አብዛኛዎቹ ልጃገረዶች በእሷ ይቀኑ ነበር."

"ለምን፧"

አለም መልሱን ቀድሞውንም ብታውቅም ከእሱ አንደበት መስማት ፈለገች፡፡ "በአንተ ምክንያት ነበር አይደል? ካንተ ጋር የነበራት ወዳጅነት?"
"ምናልባት ሊሆን ይችላል, ዋናው ጉዳይ ግን እሷ በጣም ቆንጆ ነበረች…በዙሪያዋ ያሉ አብዛኞቹ ልጃገረዶች እንደ አጋር ሳይሆን እንደ ተቀናቃኝ ነበር የሚቆጥሯት፡፡….ቆይ አንዴ።›› ፈረሱን አቅጣጫ ከመቀየሩ በፊት አስጠነቀቃት እና ፈረሱ ጓድጓዳ አካባቢ ሲረግጥ ወደ ፊት ገፋት፣ እሱ ላይ ተለጠፈች። በደመ ነፍስ ወገቡን አጥብቃ አቀፈችው።

"ፈረስ ቁልቁል ሲወርድ ወደፊት መንሸራተቱ የሚጠበቅ ነው….››
ስትረጋጋ“እናቴ ሁሉንም ሚስጥሮቾን እያመጣች ለአንተ ትዘረግፍ እንደነበረ እየነገርከኝ ነው?›› ብላ ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ, እንደዛ ነበር የምታደርገው…እሷ እንደአንቺ አይነት ውስብስብ ሴት አልበረችም…ለምሳሌ አንድ ቀን ምንም ሳትነግረኝ ከትምህር ቤት ቀረች እና የሆነ ችግር እንዳለ አውቄ ነበር...ተጨንቄ ስለነበር በእረፍት ወደ ቤቷ ሄድኩ. አያትሽ በሥራ ላይ ስለነበሩ ሰሎሜን ብቻዋን እያለቀሰች ነበር ያገኘዋት…ፈርቼ ምን እንደሆነች እስክትነግረኝ ድረስ ጨቀጨቅኳት።"

‹‹ጉዳዩ ምን ነበር?"

‹‹ የወር አበባዋን ለመጀመሪያ ጊዜ መቶባት ነበር….አያትሽ የወር አበባን በተመለከተ የሀጥያት ፍሬ እና እርግማን እንደሆነ የሚተርኩ አስፈሪ ታሪኮች ነግረዋት ስለነበር በጣም አዝና ነበር ያገኘኋት ፡፡ እንዴት ነው አያትሽ ለአንቺም እንደዛ አይነት አስፈሪ ታሪኮችን ይነግሩሽ ነበር?››
አለም ወገቡን ሳትለቅ አንገቷን እንደምንም ቀና አደረገችና‹‹ያን ያህል የሚረብሹ አይነት ታሪኮችን ነግራኝ አታውቀኝም… ምናልባት አያቴ እኔን ማሳደግ በጀመረችበት ጊዜ ተሻሽላ ሊሆን ይችላል።ለአቅመ አዳም በደረስኩበት ጊዜ በቀላሉ ነው የተቀበልኩት።››

ፈረሱ ግልቢያውን እስኪያቆም ድረስ አለም ያሉበትን ቦታ አላስተዋለችም ነበር፡፡መኖሪያ ቤቱ ደርሶ ነበር ያቆመው፡፡

" ከዛስ እንዴት ሆነ?"

‹‹አፅናናኋት እና የወርአበባ ማለት ሴትነቷ በይፋ የታወጀበት ድንቅ ቀን እንደሆነ እና መደስት እንጂ ማልቀስ እንደማይገባት ነገርኳት።››

"ሰራ ታዲያ?"

"እንደምገምተው አዎ። ማልቀሷን አቆመች"
'እና...?'' አለም የታሪኩን በጣም አስፈላጊ ክፍል እንዳልነገራ ስላወቀች  እንዲቀጥል አነሳሳችው።
"ከዛማ.. በቃ ።››አለና ቀድሞ ከፈረሱ ላይ በቀላሉ በመውረድ ‹‹ እግርሽን አንሺው።" አለና እሷን ለማውረድ እጁን ዘርግቶ በጠንካራ እጁ ወገቡ ላይ አቀፋትና ወደ መሬት አወረዳት።

ከእናቷ ጋር ሲሳሳም ሚያሳየውን ፎቶ መመልከቷን አስታወሰች ። "ለቅሶዋን ካቆመች በኃላ ሳምካት አይደል?"

በትከሻው የማይመች እንቅስቃሴ አደረገ። "ከዚያን ቀን በፊትም ስሜያት ነበር።" "ግን ያ የመጀመሪያው እውነተኛ መሳም ነበር አይደል?"
እሷን በጥልቀት ተመለከታትና ወደ ቤቱ  በረንዳ ወጥቶ በሩን ገፋው ። ወደኃላ ዞር አለና

‹‹መግባትም ሆነ አለመግባት የአንቺ ጉዳይ ነው።››አለና ክፍት አድርጎ ተወው… ወደ ውስጥ ገብቶ ጠፋ, ተስፋ የቆረጠች ቢሆንም ግን ደግሞ ተጫማሪ የማወቅ ጉጉት ስላላት ተከተለችው።
መየፊት ለፊት በር በቀጥታ ወደ ሳሎን ተከፈተ። በግራዋ በኩል ባለው በር በኩል የመመገቢያ ቦታ እና ኩሽና ማየት ችላለች። በተቃራኒው በኩል ያለው የመተላለፊያ መንገድ ወደ መኝታ ክፍል ይወስዳል፣ እሱም ሲያወራ ትሰማለች። የሳሎኑን በር ዘጋች፣ መነጽርዋን አውልቃ ዙሪያዋን ተመለከተች።ቤቱ የወንደላጤነት ወዝ ነበረው …ፈሪኒቸሮቹ መጠነኛና ቅልብጭ ያሉ ናቸው፡፡በግራ ግድግዳ ያለው መደርደሪያ ላይ ያሉት መጻሕፍቶች የተዘበራረቁ ነበሩ፣ ፡፡

"ቡና ትፈልጊያለሽ?"

"ባገኝ ደስ ይለኛል።››

ወደ ኩሽና ገባ። የቀዘቀዙ እግሮቿ የደም ዝውውር እንዲስተካከል እያፍታታች በክፍሉ ውስጥ መዞሯን ቀጠለች። ከመጽሐፍ መደርደሪያው በላይ ወደተቀመጠው አንድ ረጅም ዋንጫ ቀልቧ ተሳበ። በላዩ ላይ የኩማንዱሩ ስም እና ቀኑ በግልፅ ፊደላት ተቀርጾበታል።
"ይህ ትክክለኛው ቀለም ነው?" ዘወር ስትል አንድ ኩባያ ቡና ይዞላት ወደ እሷ እየቀረበ ነበር።

"አመሰግናለሁ።" ብላ ተቀበለችውና …ጭንቅላቷን ወደ ዋንጫው በማዘንበል "ይሄ ያንተ ምርጡ አመት አይደል?"ስትል ጠየቀችው፡፡

"ምን አልባት"

"ምነው ?እርግጠኛ አይደለህም?"

ወደ ወንበሩ ሄደና ተቀመጠ ፡፡ "ያኔ እንደዛ ተሰምቶኝ ነበር እና አሁንም ድረስ በወቅቱ የሚደግፈኝ ጥሩ ቡድን እንደነበረኝ ይሰማኛል።ሌሎች በእጩነት የቀረቡት ተጫዋቾችም እንደኔ ዋጋ ያላቸው ነበሩ።"

"ለምሳሌ ጁኒየር?"

"አዎ እሱም ከነሱ አንዱ ነበር " ሲል መለሰ፣

‹‹ሽልማቱን ያሸነፍከው አንተ እንጂ ጁኒየር አይደለም።››ዓይኖቹ ወደሷ አፍጠጠ፡፡
"ውድ አቃቢህግ ከእኔ ጋር የጀመርሽውን ጫወታ አቁሚ እና በአእምሮሽ ያለውን ነገር ቀጥታ ተናገሪ።"
40👍4🔥1