አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_አስይ_ቁማር


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ከቃል ምክር በኃላ ልዩ የሌብነት መነሻዋ ከየት ነው? የሚለውን ጥያቄ  ደጋግማ  ከመጠየቅ እራሷን መግታት አልቻለችም። ትዝ ይላታል …ኤለመንተሪ ተማሪ ሆና ነው፤ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ክፍል እያለች ጀምሮ ነው ፡፡ አያቷ  ጠጅ በጣም ይወዳሉ ….አባባ ትልቁ ነው የምትላቸው..ምክንያቱም በወቅቱ ብዙ  አባባ የሚባሉ ሰዎች ግቢያቸው ውስጥ ስለነበሩ ነው ዘበኛው ..አትክልተኛው ወዘተ)፡፡

ማታ ሞቅ ብሏቸው  ወደ ቤት ሲመጡ ጠብቃ  ተከትላቸው መኝታ ቤታቸው በመግባት  የድሮ ታሪክ ወይም ተረት ንገሩኝ ትላቸዋለች።ደስ ይላቸውና አልጋቸው ላይ ወጥተው ጋደም በማለት ማውራት ይጀምራሉ...ግን ብዙውን ጊዜ አውርተው ከመጨረሳቸው በፊት እንቅልፍ ይዟቸው ጥርግ ይላል..."እና መተኛታቸውን ስታረጋግጥ ብርድ ልብሳቸውን ሙሉ በሙሉ ወደ ላይ ስባ ሸፍና ታለብሳቸዋለች...››እንደዛ ስታደርግ የሚያያት ሰው አያቷን እየተንከባከበች መስሏቸው ይመርቋት ይሆናል…እሷ ግን  ድንገት አይናቸውን ገልጠው የምትሰራውን እንዳያዩባት ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ  ነበር...

ከዛ ኪሳቸውን መበርበር ትጀምራለች...አ10 ብርም ሆነ 50 ብርም መዛ ኪሷ ትከትና ሌላውን ትመልሳለች። የምትሰርቀውን የብር መጠን የሚወስነው ኪሳቸው በምትገባ ወቅት ባገኘችው የብር መጠን ነው።

አያቷ የእናቷ አባት….ባላንብራስ  አይተንፍሱ ይርገጤ ይባላሉ።በጣም ቆፍጣና ግትርና ወግ አጥባቂ ሰው ነበሩ።እናቷን ጨምሮ የቤቱ ሰው ሁሉ ይንቀጠቀጡላቸዋል...‹‹እኔ ፊት አውራሪ አይተንፍሱ›› ብለው ከዘራቸውን ከወዘወዙ ማንም ፊታቸው አይቆምም...እሷ ግን አትሰማቸውም.. እሳቸው እሷ ሲቆጧት እልክ ይይዘትና እጇን አጣምራ አይኖቾን አፍጥጣ ፊታቸው ትገተራለች...፡፡

ቅሬታቸውንና ኩራታቸውን ደባልቆ በሚገልፅ ስሜት"ምን ዋጋ አለው በዚህ ጀግንነትሽ ወንድ ብትሆኚ ..?."ብለው ይሉና ቁጣቸውን አብርደው ወደራሳቸው ስበው ጭንቅላቷን በመዳበስ ያሞጋግሷታል...እንደዛ ሲሆን ደግሞ የልብ ልብ ይሰማታል።እና ወደኃላ ተመልሳ  ትናንቷን ስትቆፍር የስርቆት ታሪኳ የሚጀምረው አያቷን ደጋግሞ ከመስረቅ ሆኖ ነው ያገኘችው ...ለምን እሷቸውን ብቻ ነጥላ ትሰርቃቸው እንደነበረ  አታውቅም ።ከረሜላና ቸኮሌት መግዣ ገንዘብ አስፈልጓት ነው እንዳይባል እናቷ ከመጠየቋ በፊት ነው መዥረጥ አድርጋ የምትገዛላት። ለመስረቅም ከሆነ ደግሞ ከአያቷ ይልቅ እናቷን መስረቅ ለእሷ በጣም ቀላል ነው። እናቷ መኝታ ቤት መሳቢያዎ ውስጥ ሆነ ቦርሳዎቾ   ሁሌ በብር እንደተሞሉ ነው...፡፡የፈለገችውን ያህል ብር እናቷ  እያየች  መዛ ብትወስድ ፈገግ ከማለት ያለፈ ትኩረት ሰጥታ  አትናገራትም። ይሄንን ደግሞ ከጨቅላነቷ ጀምሮ በደንብ ታውቃለች፡፡

አይገርምም በህይወታችሁ የከወናችኋቸውን አንዳንድ ነገሮች ወደኃላ መለስ ብላችሁ በትኩረት ካልመረመራችሁ እንዴትና ለምን የሚለውን ጥያቄ መልስ ሳታውቁ ዕድሜያችሁ ያከትምለታል…. እሷም  ዕድሜ ለቃል አሁን ነው  በዛን የልጅነት ወቅት አያቷን ብቻ ለይታ ትሰርቅ እንደነበር በመገረም ያስተዋለችው፤ ለምን አያቷን ብቻ?አሁንም መልሱን አታውቅም።ግን ከአያቷ ላይ ገንዘብ በሰረቀችው በእያንዳንዷ ቀን ትልቅ ደስታና የድል ስሜት ይሰማት እንደነበረ  አሁንም ድረስ ታስታውሳለች። ይሄንን ተግባሯን እስከሰባተኛ ክፍል ቀጥላበት ነበር...ከዛ አቆመች።

ያቆመችው ማቆም ፈልጋ ሳይሆን አያቷ ድንገት ስለሞቱባት ነበር። በእውነት በመሞታቸው ከእሷ እኩል የደነገጠም ያዘነም ሰው አልነበረም።ያዘነችበት ዋና ምክንያት ግን "ከአሁን በኃላ ማንን ነው የምሰርቀው ?››የሚል ስጋት ስላደረባት ነበር፡፡

ይሄንን ግራ አጋቢ ስሜቴን ማንም አያውቅም ነበር ፤እናቷን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች ሁሉ ለአያቷ ካላት የተለየ ቅርበት እና  ፍቅር የተነሳ እንደሆነ በማመን  እንድትፅናና የተቻላቸውን እንክብካቤ ሲያደርጉላት ከረሙ...በእውነት እሷም  በቀላሉ ልትፅናና አልቻለችም ነበር።በኋላ ግን ትምህርት ቤት ሄዳ ከጓደኞቾ  እስኪሪብቶና ደብተር መስረቅ ስትጀምር አያቷን  ቀስ በቀስ እየረሳቻቸው  መጣች፡፡

..ስርቆቱ ግን እያደገ እያደገ ሄዶ  አብሯት ኖሮ እንሆ እዚህ አድርሷታል…እና  ልጅነቷን እንዲህ ስትፈትሽ ሌባ እንድትሆን ያስገደዳት ምክንያት ምንድነው?በመሞላቀቅ ሰበብ በህፃንነቷ ሳንቲም ስለለመደች ይሆን?ታዲያ ስርቆቱን ሳንቲም በመስረቅ ጀመረች እንጂ  እያደረ ትርኪ ምርኪ ቁሳቁስ  ነበር ስትሰርቅ የኖረችው...ልጅ ሆና እንኳን የ50 ብር የሚያምር ብዕር ቦርሳዋ ውስጥ እያለ የአንድ ብር ተራ እስኪሪብቶ ከጓደኞቾ ትሰርቅ ነበር...ለምን..?‹‹ሌባ ለአመሉ ዳቦ ይልሳል›› ተብሎ የተተረተው በትክክል የእሷን ሁኔታ ይገልፃል፡፡አይገርምም አሁን በዚህ ሰዓት እንኳን ለምን እንደሆነ አታውቅም፡፡

መኝታ ቤቷን ለቀቀችና ወደ እናቷ መኝታ ቤት ሄደች..አንኳኳች፡፡

‹‹ማነው?››

‹‹እኔ ነኝ እማ?››

‹‹ግቢ››

ከፈተችና ወደ ውስጥ ገባች

‹‹የእኔ ቆንጆ ምነው..?እስከአሁን አልተኛሽም እንዴ?›› አለቻት. ከተኛችበት ግዙፍ አልጋ ትራሷን ከፍ አድርጋ ከአንገቷ ቀና በማለት፡፡‹‹እንቅልፍ እምቢ አለኝ .ከአንቺ ጋር መተኛት ፈለጌ ነው፡፡››አለቻቸው፡፡

‹‹በሩን ዝጊውና ነይ….››ብርድልብስና አንሶላውን እየገለጡላት
እንዳሏት በራፉን ዘጋችና  ወደእናቷ አልጋ ሄዳ በተገለጠላት አንሶላ ውስጥ ገብታ ልክ እሳቸው እንዳደረጉት ትራሱን ከፋ አደረገችና ፊቷን ወደእናቷ አዞረች›

እንዲህ የማታደርገው የሆነ ነገር ከእናቷ ስትፈልግ እንደሆነ ከልምድ ይታወቃል…እና የምትለውን ለመስማት እናቷም ነቃ ብለው ተዘጋጀተዋል፡፡

‹‹እማዬ›አለቻቸው፡፡

‹‹ወዬ የእኔ ማር››

‹‹ከእዚህ በሽታዬ የእውነት እንድፈወስ ትፈልጊያለሽ"

ያልጠበቁትን ርዕስ እንዳነሳችባቸው ከፊታቸው  መለዋወጥ መረዳት ይቻላል፡

‹‹ከየትኛው በሽታሽ?››

‹‹ከሌብነቴ ነዋ››

"ምን ማለት ነው የእኔ ልጅ...?እንዴት እንዲህ አይነት ጥያቄ ትጠይቂኛለሽ..?››.

"እንድድን ከምር የምትፈልጊ ከሆነ አሁን የምጠይቅሽን  ጥያቄዎች ትመልሺልኛለሽ?››

‹‹እንዴ… አንቺ ዳኚልኝ እንጂ የፈለግሺውን ጠይቂኝ"

"እርግጠኛ ነሽ?"

"ምን ነካሽ...አንቺን ለመፈወስ የሚያግዝ ከሆነ የማላደርገው ነገር የለም"

"እሺ ስለአባቴ ንገሪኝ?"በጣም የምትፈራውን ጥያቄ አናቷን ጠየቀቻቸው፡፡

"ምን አስደነገጠሽ?እንድትድኚ እፈልጋለሁ አላልሽም እንዴ?"

"እሱማ እፈልጋለሁ...ስለአባትሽ መጠየቅና ከችግርሽ መፈወስ ምን እንደሚያገናኛቸው ስላልገባኝ ነው።"

"በደንብ ይገናኛል..እንዴት እንደሚገናኝ በሂደት ምንደርስበት ይሆናል። አባዬ ምን አይነት ሰው ነው?።

"ያው ፎቶውን ታይው የለ፤ ሸጋ ፤መልከመልካም ሰው ነበር።›› በራሳቸው ገለፃ እንደልጃገረድነት ጊዜያቸው ተሸኮረመሙ፡

"እሱንማ አውቃለሁ...ደግሞ እኳ ያየሁት የአምስት አመት ህፃን ሳለሁ ቢሆንም ትንሽ ትንሽ እንደ ህልም  ትዝ ይለኛል።እሽኮኮ አድርጎኝ ጊቢውን ሲዞር...ኪወክስ ወስዶ ከረሜላ ሲገዛልኝ...ወድቄ ሳለቅስ ተንደርድሮ አንስቶኝ ጉያው ሸጉጦ ሲያባብለኝ...አዎ እኚን የመሳሰሉ ብጥቅጣቂ  ምስሎች  በእምሮዬ ተቀርፀው ቀርተዋል፡፡››

"እኮ ከዚህ በላይ ምን ለማወቅ ነው የፈለግሽው?"

"ምን አይነት ሰው ነበር ...?ምን አይነት ፀባይ ነበረው?"

"ያው እንዳንቺ ነው"
👍7915🔥2🥰2😁2👏1😢1🤩1