#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹዋቤ
የውብዳርስ?››
‹‹እኔ እንጃላት፡፡››
‹‹እንዴት እኔ እንጃላት ... ?ወንዶች ስትባሉ በቃ ሁላችሁም አንድ አይነት ናችሁ? ሴትን ልጅ ቀምሳችሁ... ልሳችሁ ጣዕሟን ከጨረሳችሁ በኋላ ተፍታችሁ ከአፈር ስትደባልቁ ጥቂት እንኳን ፀፀት አይሠማችሁም? ግርም የሚለኝ እግኢአብሔር ለምን እናንተን እንደፈጠራችሁ ነው>>
‹‹የፈጠረንማ አንደኛ አቶ ሁሴን እንደሚለው መልኩን በእኛ በኩል ለማየት ነው፤ምክንያቱም እኛ እሱን እንመስላለን፡፡ ሁለተኛው ምድርን እንድናስተዳድርለት ነው፤ሦስተኛው እንድናመሰግነው ይመስለኛል፡፡ እንደ እኔ ሦስተኛው ብዙም የተሳካ አይመስለኝም፡፡ እናንተን ከፈጠረ በኋላ አይናችንን ወደ ፈጣሪ እንዳናነሳ እንቅፋት እንደሆናችሁን ነው የምረዳው፡፡›› ሁለቱም ምግቡን ስላቆሙ አስተናጋጅ መጥቶ መአዱን አነሳና ጠረጴዛውን አፀዳዳው፡፡...
‹‹ግን እውነት ደህና ነች?›› ጠየቀችው
‹‹እኔም እውነቴን እኮ ነው ..አላውቅም፡፡››
‹‹ምን ማለት ነው?››
‹‹ተፋተናል፡፡››
‹‹ምን?›› በድንጋጤ አፏን በእጇ ሸፍና ከመቀመጫዋ ተነሳችና መልሳ ቁጭ አለች፡፡
‹‹አዋ አራት ወር አለፈን፡፡››
‹‹እንዴት ሳልሰማ? ምን አለበት ደውለህ እንኳ ብትነግረኝ?››
‹‹ምን የሚነገር ነገር አለው? ለሰርጉም ጠርቼሽ ለፍቺውም ጠርቼሽ እችላለሁ... ? ድግስና ጥሪ ለጋብቻ ብቻ ነው ብዬ ነው፡፡››
‹‹ለምን የለውም? የዛሬን አያድርገውና ስንት ጥሩና መጥፎውን ነገር አብረን አሳልፈናል እኮ …ቆይ እናንተን ሀይ የሚላችሁ ሠውም የለ እንዴ? ዳሩ ከእብድ ጋር የሚውል ምን ጤና ይኖረዋል?ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር...> እንደሚባለው ቢጤ እኮ ነው፡፡››
‹‹እንደምታስቢው እኔ ጠልቻት ወይም ሌላ አፍቅሬ እንዳይመስልሽ፡፡››
‹‹እና እንዴት ሆኖ ነው?››
‹‹ሠለቸኋት ... ድብብቆሽ ጨዋታ ውስጥ ገባች...እጅ ከፍንጅ ያዝኳት .. በቃ ይሄው ነው፡፡››
‹‹እኔ አላምንም ... የውብዳር ከሌላ ወንድ ጋር... ምቀኛ በመሀከላችሁ ገብቶ እንዳይሆን?››
‹‹አመንሽም አላመንሽም በወሬ ወይ በጥርጣሬ እንዳይመስልሽ፤እራሷም ባመነችበት አሳማኝ ማስረጃ ነው፡፡››
‹‹ወይ ጉድ!›› አለች ኤደን ግራ ገብቷት፡፡
ሠሎሞን ብርጭቆውን አነሳና ውስጥ ያለውን ጅው አድርጎ በመጨለጥ ጠርሙሱ ውስጥ የነበረውን ለሁለቱም ቀድቶ ሌላ እንዲጨምርላቸው ለአስተናጋጁ በምልክት ትዕዛዝ በማስተላለፍ ንግግሩን ቀጠለ፡፡ ‹‹አየሽ ኤደን ምን አልባት አንቺ ነገሮችን ከራስሽ አንፃር ስትገመግሚያቸው በወንድ በደል ደርሶብኛል ወይም ተገፍቼያለሁ ብለሽ ስለምታስቢ ጠቅላላ ወንዶች ላይ ያለሽ ግንዛቤ አሉታዊ ጎኑ ስለሚያመዝን ወንዶች ሁሉ በዳይ ሴቶች ደግሞ ተበዳይ ሆነው ሊታዩሽ ይችላሉ፡፡ ሀቁ ግን እንደዛ አይደለም ስንት መሠሪና አለሌ ሴቶችም አሉ ፡፡ እና ምን መሠለሽ ...››ንግግሩን የስልኩ መጮህ አቋረጠው፡፡ ከኪሱ አወጣና ደዋዩ ማን እንደሆነ አየው፡፡ ሁሴን ነበር፡፡ አነሳው፡፡
‹‹እሺ ጌታው፡፡››
<አለሁ ባክህ ... ሰርጉ እንዴት ነበር?>>ሁሴን
‹‹አሪፍ ነው፡፡ አሁን ወጥቼያለሁ፡፡ ፍንድቅድቅ ያልክ ትመስላለህ ደግሞ ምን አገኘህ?››
<ደወለች እባክህ::››
<<ማን?>>
ሁሴን ተበሳጨ ‹‹ማን ትላለህ እንዴ? ማን እንድልህ ትፈልጋለህ?››
‹‹ይቅርታ እሺ ደራሲዋ?››
ኤደን ሁሴን እንደደወለ አወቀች፡፡ ሌላ ነገር የምታስብ መስላ ከወይኑ እየተጎነጨች በጽሞና ቃለ ምልልሳቸውን እያዳመጠች ነው፡፡
‹‹ትክክል ነህ፤እሷን ለማግኘት ማድረግ የሚገባኝን ነገረችኝ፡፡››
‹‹አትለኝም ምን አለችህ?››
<<አግባኝ>>
‹‹በተሠቀለው ንጉስ አግባኝ? የምሯን ነው!››
‹‹አዎ ከምሯ ነው፡፡››
‹‹ታዲያ ምን ችግር አለው እሺ በላታ፤ከዛም አግኛትና ካልተመቸችህ ቃልህን ታጥፋለህ፤ቃል ማጠፍ እንደሆነ ላንተ የሚከብድ አይመስለኝም››
የኤደን ስሜት ይበልጥ እየተነቃቃ ውስጧ በቁጣና በቅናት እየነደደ መጣ፡፡ ትቼዋለሁ ወጥቶልኛል ብላ ከሁሴን አጠገብ ከራቀችና እሱን ማግኘት ከተወች ስድስት ወር ቢያልፋትም ውስጧ ግን ዛሬም ይራበዋል፡፡ መሸነፍ ልቧን ያቆስለዋል፡፡
ንግግራቸው ቀጥሏል፡-‹‹ባክህ የዋዛ እንዳትመስልህ የእውነት ከወደድከኝ ቆማጣም ሆንኩ ሸፋፋ የማትተወኝ ከሆነ እና ልታገባኝ ከወሠንክ በመጀመሪያ ሠርግ ደግስ ለምታውቃቸው ሠዎች ሁሉ የሠርግ ጥሪ በትን ከዛ በሠርጉ ቀን ሽማግሌዎችህን ሚዜዎችህንና አጃቢዎችህን አዘጋጅ ልክ
በሠዓቱ እደውልልሀለሁ ያለሁበት ትመጣና ይዘኸኝ ትሄዳለህ፡፡››አለችኝ፡፡
‹‹እንዲህ ነችና ... ልጅቷ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ፊልም እየሠራች ነው እንዴ ...? እኔ ይሄንን ጉዳይ ከዚህ በላይ በስልክ ማውራት አልፈልግም ነገ ጥዋት እቢሮ እመጣለሁ፤ ታወራኛለህ፡፡››
እጠብቅካለው....ለማኝማውም ሚዜ ለመሆን ተዘጋጅ፡፡››
‹‹እሱን እናያለን .. ለማንኛውም አሁን ከኤደን ጋር ነኝ፡፡ሰርግ ቤት ተገናኘን፡፡ ሠላም እያለችህ ነው፡፡››
ኤደን በተቃውሞ ፊቷን አኮሳተረች፡፡
‹‹ተመችቶኃላ .. ላናግራት›› አለ ሁሴን ሠሎሞን ሞባይሉን ዘረጋላት .. ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ ‹‹በል ቻው፡፡ በአየር ላይ ሠላም ብላሀለች፡፡›› በማለት ስልኩን ዘጋው፡፡
‹‹በቃ አሁንም ስለዛች ደራሲ የቀን ህልም እያለመ ነው?››
‹‹ባክሽ እኔም ግራ ገብቶኛል፡፡››
‹‹እኔ እኮ የሚገርመኝ ቆይ ማን ትሆን እንዲህ የምትጫወትበት?››
‹‹እሱ አይደል እንቆቅልሹ፡፡ አሁን እኮ የሚለኝ ልታየኝ ከፈለክ ድግስ ደግስና አግባኝ አለችኝ ነው >>
‹‹በቃ በቃ እኔ እንዲህ አይነት ቅራቅንቦ መስማት አልፈልግም፡፡ እንደውም መጠጣት ሁሉን መርሳት እፈልጋለሁ፤ ሞቅ ያለ ቤት ውሠደኝ፡፡›› አለችው፡፡
‹‹ኧረ እስማማለሁ፡፡›› በማለት ሂሳቡን ከፍሎ ቀጫጭን የእጆቿን ጣቶች በፈርጣማው ጣቶቹ አቆላልፎ በመያዝ ወደ ጭፈራ ቤት ይዟት ለመሄድ መኪናው ውስጥ ይዟት ገባ፡፡ መኪናውን ከማንቀሳቀሱ በፊት ግን የሞባይል ስልኩን ካስቀመጠበት ኪሱ አውጥቶ የጹሁፍ መልክት ለሁሴን ላከ ‹‹ኤደን ጭፈራ ቤት ውሠደኝ እያለችኝ ነው፡፡ ባንተ የተበሳጨች ይመስለኛል፡፡ ስሰክር ማስተዋሌ እንደሚቀንስ ታውቃለህ፡፡ ምን አልባት አንተን የማያስደስት ነገር በእኔና በእሷ መሀከል ይፈጠር ይሆን? ብዬ ፈራሁ፡፡ ምን ትመክረኛለህ?››መልዕክቱን ላከና የመኪናውን ሞተር አስነስቶ መንዳት ጀመረ፡፡ ወዴት እንደሚሄዱ አያውቅም፡፡ ከሁሴን መልስ እስኪመጣለት ጊዜ ለማግኘት እየጣረ ነው ፡፡ ሠዓቱ 3፡45 ሆኗል፡፡ ከዚህ ሠዓት በኋላ ለብታን ወደ ስካር ለማሸጋገር፤ ለዛውም ከሴት ጋር ጭፈራ ቤት መግባት መጨረሻውን መገመት አዳጋች ነው፡፡ ሞባይሉ ምልክት አሳየው፡፡ መኪናውን ጥግ ይዞ አቆመና የመጣለትን መልስ ከፍቶ ማንበብ ጀመረ፡፡
‹‹ቀሽም አትሁን…ምንም ቅር የሚያሰኝ ነገር የለም፡፡ ግን አደራ በቦርጭህ ሙሉ ተከምረህባት እንዳታፈነዳት፡፡ በል ይመቻችሁ፡፡ በጥዋት ቢሮ ና፡፡ ባይሆን የአልጋ መውረጃ ደህና ቁርስ ጋብዝሀለሁ፡፡››ይላል፡፡አንብቦ ሲጨርስ ፈገግ አለና መኪናውን አስነስቶ ተፈተለከ .....ወደ ጭፈራ ቤት፡፡ እሷ ግን በዝምታዋ ውስጥ እንደሰመጠች ነው፡፡
✨ይቀጥላል✨
የዛሬው ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ የማድረግ እንቅስቃሴ ጥሩ ነው ይልመድባችሁ👍 አሁንም እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍124❤12🥰2😁2
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹዋቤ
ከለሊቱ ስድስት ሠዓት አልፏል፡፡እንቅልፍ አልወስደው ብሎ አልጋው ላይ ተጋድሞ እየተገላበጠ ሳለ ድንገት ተንቀሳቃሽ ስልኩ ድምፅ አሠማ፡፡ አነሳና ቁጥሩን አየው፡፡ ያልተመዘገበ ቁጥር ነው፡፡ አያውቀውም፡፡ ግራ በመጋባባት አነሳው፡፡
‹‹ሄሎ ማን ልበል?››
‹‹ይቅርታ ከእንቅልፍ ቀሠቀስኩህ?››
ብድግ ብሎ ቁጭ አለ፡፡ ያልጠበቀው ስልክ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በሞባይል የደወለችለት ሚስጥር!፡፡
‹‹ኧረ አልቀሰቀሽኝም.. እንቅልፍ እና እኔ ከተጣላን እኮ ሰነባበትን
‹‹ኦ! ምን ምቀኛ በመሃላችሁ ገባ እቴ›› በማለት በስሱ ሳቋን ለቀቀች፡፡
‹‹ይሄ ሞባይል ቁጥር ያንቺ ነው?›› ጠየቃት፡፡
‹‹ኧረ ተመስገን ነው፤በፈለኩ ጊዜ ብደውልልሽ አገኝሻለኋ?››
‹‹አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ሁል ጊዜ አልከፍተውም፤በተለይ ቀን ቀን አይሠራም፤ማታ ከአራት ሠዓት በኋላ ግን ክፍት ነው፡፡››
‹‹ኧረ ይሁን እሱንስ ማን አየበት…፡፡››
‹‹አሁን የደወልኩት ውሳኔህን እንድትነግረኝ ነው፡፡››
<<የቱን ውሳኔ?>>
‹‹በቀደም የተነጋገርነውን ነዋ፤ልታገኝኝ ከፈለክ አግባኝ ያልኩህን ?››
‹‹ግን እኮ በጣም ከባድ ነገር ነው፡፡››
‹‹ከባድ ከሆነማ ልታገኘኝ አትፈልግም ማለት ነው?ስለዚ እንደ ከዚህ ቀደሙ ግንኙነታችንን በስልክ ብቻ እንቀጥላለን፡፡››
‹‹ኖ... እሱማ አይሆንም፤ከባድ ነው እኮ ያልኩት አንቺን ማግባቱ አይደለም፡፡››
‹‹እና ምኑን ነው?››
‹‹ሠርግ ምናምን የሚባለውን ነገር ነዋ፡፡ አየሽ እኔ ለሠርግዐያለኝ አመለካከት በጣም የወረደ ነው:: እንኳንም ሠርግ
መደገስ ሠርግ ስጠራ እንኳን መሄድ አልፈልግም፡፡ በዚህ ፀባዬ ከስንት ወዳጆቼ ተጣልቻለሁ መሠለሽ ... ለምን ዝም ብለን አንጋባም ፤ አሁን በዚህችው ደቂቃ እንኳን ብትፈቅጂልኝ ያለሽበት ድረስ በርሬ መጥቼ አገባሽ ነበር፡፡››
‹‹እና ታዲያ ምን ይሻላል?እኔም እኮ ሠርግ ወድጄ አይደለም፡፡ ግን አንተ አይተኸኝ እንድትተወኝ በፍፁም አልፈልግም፡፡ ካገባኸኝ በኋላ ካልተስማማሁህ ብትፈታኝ ይሻለኛል…በወሩም ቢሆን፡፡ ይሄንኑ ማረጋገጥ ስለምፈልግ ነው ይሄንን ዘዴ የቀየስኩት...፡፡››
‹‹ሚስጥር እኔ በጣም ከምትገምቺው በላይ አፈቅርሻለሁ፡፡ ስለማፈቅርሽም አንቺ እምቢ ብትይኝ እንኳን በህግ ልጠየቅ እንጂ ጠልፌም ቢሆን አደርገዋለሁ፡፡ እኔ የሚያስጠላኝ ቀለበት ሠርግ የሚባለው የድግስ ጋጋታ ነው፡፡ ፍቅሬን ከተጠራጠርሽ ሌላ የምታረጋግጭበት ዘዴ ወይም ፈተና አቅርቢልኝ፡፡››
‹‹ቆይ ላስብበትና ልደውልልህ››
‹‹መቼ ነው የምትደውይልኝ?››
‹‹ዛሬውኑ...ከ3ዐ ደቂቃ በኋላ፡፡››
‹‹እጠብቅሻለሁ፡፡››
ስልኩ ከተዘጋ ገና አስር ደቂቃ ብቻ ያለፈው ቢሆንም የአስር ቀን ያህል ረዘመበት፡፡ ምን አይነት ተቀያሪ ሀሳብ እንደምታቀርብለት መተንበይ አልቻለም፡፡ መንጎራደድ የእሷን የሃሳብ መስመር ሹክ የሚለው ይመስል መኝታ ቤቱን ተሸከረከረ፡፡ ሲደክመው መልሶ አልጋው ጫፍ ላይ በመቀመጥ አንገቱን አቀርቅሮ ወደ ትካዜው ገባ፡፡‹‹እንደምታገባኝ እርግጠኛ የምሆንበት ሌላ ዘዴ ስለሌለኝ መደገስህ የግድ ነው ብትለኝ ምን አደርጋለሁ? እሺ እላታለሁ ወይንስ አይሆንም እላታለሁ?›› ግራ ገባው፡፡ በአሁኑ ሰዓት እርግጠኛ የሆነበት አንድ ነገር ቢኖር እሷን በአካል ማግኘት ካልቻለ ትክክለኛ ሠው ሆኖ ስራውን ማከናወንም ሆነ ህይወቱን መምራት እደሚያስቸግረው ነው፡፡‹‹እና ምን ይሻለኛል?›› እራሱን ጠየቀ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለለት፡፡ ማንነቷን ለማወቅ አንድ እድል አለው፡፡ በሞባይል ቁጥሯ በመመራት ከቴሌ አድራሻዋን ማፈላለግ፡፡
‹‹በራሷ ስም ካላወጣችስ?›› አፍራሽ የሆነ ሌላ ጥያቄ ተሠነቀረበት፡፡
‹‹ቢሆንም ቁጥሩን ከቴሌ በስሙ የወሰደውን ሠው ብከታተለው ወደ እሷ ሊመራኝ ይችላል፡፡ >> ይሄን ዕድል ለመሞከር ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ስልኩ ጮኸ፡፡ በአንድ ጥሪ ነበር ያነሳው፡፡
‹‹አልተኛህም.. እየጠበቅከኝ ነው?››
‹‹ምኑን ተኛሁ .. ምን ወሰንሽ?››
‹‹ሌላ ተቀያሪ ጨዋታ እንጫወታ፡፡››
‹‹ምን አይነት ጨዋታ?››
‹‹ሌባና ፖሊስ አይነት ነገር፡፡››
‹‹በናትሽ እስቲ ዘርዘር አድርጊልኝ?››
‹‹እንግዲህ አፈቅርሻለሁ ብለኸኛል››
<<በትክክል::>>
‹‹የምታፈቅረኝ ደግሞ ነፍሴን ነው››
‹‹አሁንም ትክክል ነሽ››
‹‹እንግዲህ እንደዛ ከሆነ ነፍስህ ነፍሴን ታውቃታለች ማለት ነው፤ስለዚህ እኔ ማን እንደሆንኩ ለማወቅ ነፍስህ ትረዳሀለች ብዬ አስባለሁ፡፡››
<<እየገባኝ ያለ አይመስለኝም …፡፡››
‹‹በዝግታ ተከታተለኝ እያስረዳሁህ እኮ ነው፡፡››
« .. እሺ ቀጥይ...::>>
‹‹እንግዲያው ከላይ የጠቀስካቸው ሁኔታዎች እውነት ከሆኑ የሦስት ቀን ጨዋታ እንጫወታለን፡፡ ቦታው የትም ሊሆን ይችላል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥም ሆነ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ማንኛውም ከተማ ..ያ ያንተ ምርጫ ነው፡፡ ፈልገህ ካገኘኸኝ በቃ አገኘኸኝ ማለት ነው፡፡››
‹‹እንዴት ነው የምፈልግሽ?››
‹‹በተመቸህ ሳምንት ጨዋታውን እንጀምራለን፡፡ የመጀመሪያው ቀን ግን አርብ ሆኖ ማብቂያው ደግሞ እሁድ ይሆናል፡፡ የትኛው አርብ እንደሚሆን ከወሰንክ በኋላ ትነግረኛለህ፡፡››ሁሴን ይበልጥ እየተገረመና ነገሮች እየተወሳሰቡበት ነው፡፡ በእሷ ላይ ያለው ገረሜታና አድናቆት ይበልጥ በውስጡ እየገዘፈ መጣ፡፡
‹‹እሺ ቀጥይ እየተከታተልኩሽ ነው፡፡››
‹‹በተወሰኑት ቀናቶች ከ1ዐ-12 መሀከል ባሉት ሰዓቶች በተስማማንበት አካበባቢ እገኛለሁ፡፡ በአካባቢህ ካሉት ሴቶች መካከል እኔ የትኛዋ እንደሆንኩ የመለየት ስራው ግን የአንተ ይሆናል፡፡››
‹‹ነገሩን እንዲሁ አወሳሰብሽው እንጂ አንቺን ማግኘት ቀላል ነው፡፡››
‹‹እንዴት ማለት?››
‹‹ያው ትንሽ ፍንጭ ሰጥተሺኝ ነበር እኮ..ረሳሽው እንዴ ?>>
‹‹ኦ .. እሱ ባክህ የመጀመሪያው ጊዜ የቀረበልህ ቀላል ፈተና ነው፤እኔ አይናማ ነኝ፡፡››
‹‹ለመሆኑ ምን ዓይነት ሠው ነሽ ?... ቤተሠቦችሽ እንዴት አድርገው ነው ያሳደጉሽ?››
‹‹እንቆቅልሽ እያስተማሩ፡፡››
‹‹ከለየሁሽ ቀጥታ መጥቼ አነጋግርሻለሁ ማለት ነዋ››
‹‹አይደለም አበባ ትሠጠኛለህ፡፡አበባው ላይ የሚለጠፍ ሦስት ካርድ እንቆቅልሽ የሚል ፅሁፍ ያለበት በፖስታ ቤት ልክልሀለው፡፡ ሦስቱም ላይ ፊርማዬ ያርፍበታል፡፡ አበባው እጄ ሲደርስ ለአሸናፊነትህ ያዘጋጀሁልህ የወርቅ ሀብል ስላለ እሱን አንገትህ ላይ አንጠለጥልልሀለሁ…ሀብሉ ልብ ቅርፅ ነው፡፡››
‹‹በጣም ጥሩ›› አለ ሁሴን ሳይታሠሰበው ድምፅ አውጥቶ፡፡ እሷን የሚለይበት አንድ ምልክት ስለሰጠችው ‹‹በድምፅህ ላይ አንድ ነገር ተረዳው›› አለችው፡፡
<<ምን??>>
‹‹ሀብሉን ከአንገቴ ላይ አውልቄ አይደለም የማጠልቅልህ ፤ከቦርሳዬ ውስጥ አውጥቼ ነው፡፡ ብቻ የልብ ቅርፅ የተሠራና በልብ መሀከል ያንተ ስም የመጀመሪያ ፊደል ያለበት ነው፡፡››
‹‹እሺ ይሁን>> አለ፤ የጭንቀት ትንፋሽ በመተንፈስ፡፡
‹‹እንግዲህ አስታውስ ያሉህ የሦስት ቀናት መጫወቻ ካርታዎች ብቻ ናቸው፡፡ በአንዱ ቀን አንዱን ካርታ ብቻ ነው መጠቀም የምትችለው፡፡ በነገራችን ላይ ጨዋታውን ለምን ቢሾፍቱ አናደርገውም፡፡››
‹‹ቢሾፍቱ .. ደብረዘይት?››
‹‹ምነው? አሪፍ ነው፡፡እንዲያውም ጨዋታችንን ለየት ያደርገዋል፡፡ በዛውም አብዛኞቹን ሀይቆች መጎብኘት እንችላለን፡፡››
‹‹እኔ እኮ በደንብ አላውቃትም››

👍72❤18
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹዋቤ
ሁሴን ትንግርትን እንደያዘ ቤቱ ሲገባ የገጠመው ከገመተው በላይ የሆነ ዝግጅት ነው፡፡ ለወር ያህል የታሠበበት ይመስል ሁሉ
ነገር ደምቋል፡፡ ሳሎኑ በዲኮሬሽን አሸብርቋል፡፡
ቤቱ ውስጥ ያሉ ሠዎች የጎደሉ ነገሮችን ለሟሟላት ከወዲህ ወዲያ ውር ውር ይላሉ፡፡
የሳሎኑን በር ዘልቀው ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ግን የቤቱ ድባብ ሙሉ በሙሉ ነበር የተቀየረው፡፡ ሁሉም በያለበት ደንዝዘው ቆሙ፡፡ ፎዚያ፣ ኤደን፣ ሠሎሞን፣ የሠለሞን ሁለት መንታ ልጆች፣ አንድ የጎረቤት አሮጊት፣ እቤቱ ውስጥ የጠበቁት ሠዎች ናቸው፡፡ ሁሉም ፈዞ እንደቆመ ሁሴን የትንግርትን እጆቿን ይዞ
እየጎተተ ወደ ሶፋው ወስዶ አስቀመጣትና ወደ መኝታ ክፍሉ አመራ፡፡
‹‹አልተሳካም ማለት ነው?›› ሠሎሞን ነበር ከደብረ ዘይት ጀምሮ አንደበቷን ተቆልፎ የደነዘዘችውን ትንግርትን የጠየቃት፡፡ሌሎችም መልሱን ለመስማት ወደ እሷ ተጠግተው ቆመዋል፡፡
‹‹ምን ነካችሁ? ምን ተፈጠረ?›› መልስ ስታጣ ዳግመኛ የጠየቀችው ፎዚያ ነች፡፡ከድንዛዜዋ ሳትወጣ ‹‹ባካችሁ ተውኝ እሱኑ ጠይቁት፤ እኔ ምንም አላውቅም፡፡››ብላ መለሰችላቸው፡፡
‹‹አብረሽው አልነበርሽ እንዴ?›› ኤደን ነች ጣልቃ የገባችው፡፡ ትንግርት ቀና ብላ አየቻት፡፡ እስከአሁን መኖሯን አላወቀችም ነበር፡፡
‹‹ነበርኩ.. ግን ለምን እራሱን አትጠይቁትም›› ተበሳጨች፡፡
‹‹ተዋት በቃ.... ለማንኛውም ተረጋጉ መጣሁ፡፡›› በማለት ወደ መኝታ ክፍል ፈራ ተባ እያለ አመራ፤ሰሎሞን፡፡ ዘልቆ ሲገባ ያልጠበቀው ነገር ነው ያየው፡፡ሁሴን በፈገግታ ተጥለቅልቆ.. ለብሶ የመጣውን ልብስ አውልቆ
ቡኒ ከለር ያለውን የጣሊያን ሱፉን እየለበሠ ነበር::
‹‹ምን እየተከናወነ ነው?›› ሠሎሞን በገረሜታ ጠየቀው፡፡
‹‹ሙሽራ አይደለሁ… እየተዘጋጀሁ ነዋ!!››
‹‹አግኝተሀታል ማለት ነው?››
<አግኝቻታለሁ ግን ይዣት አልመጣሁም .. አላናገርኳትም፤ እዛው ጥያት ነው የመጣሁት፡፡
‹‹አንተ ሠውዬ ጭራሽ ለይቶልሀል ማለት ነው?›› ይሄን ሁሉ ጊዜ ቁም ስቅላችንን ስታሳየን ከርመህ አንተም ይሄን ያህል ተሠቃይተህ ካገኘሀት በኋላ ጥያት መጣሁ ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው?››
‹‹ባክህ አትነጫነጭ .. ድግሳችሁ አይከስርም አንድ እቅድ አለኝ ሂድና ንገራቸው.. ሁሉም ለእራት ዝግጁ ይሁኑ፤ አስር ደቂቃ አይፈጅብኝም መጣሁ፡፡››
‹‹ለነገሩ እውነትህን ነው... የለፋንበትን እራትማ መሬት ላይ ደፍተን አንሄድም፡፡ ሁለተኛ ግን ካንተ ጋር አብሮ የሚያብድ ሠው የምታገኝ አይምሰልህ፡፡ደግሞ ልጆቼን አንከርፍፌ መምጣቴ፡፡›› በማለት እየተበሳጨ ወደ ሳሎን ተመለሠ፡፡
ሁሉም መቀመጫቸውን ይዘው የእራት ድግሱን ለመቋደስ ሲዘጋጁ ሠዓቱ ሁለት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ እንዳንዱ ቤት ውስጥ ካሉት መጠጦች የሚስማማውን እየመረጠ ይዟል፡፡ የሁሴን ፊት በፈገግታ መጥለቅለቅ የቤቱን የቀድሞ ድባብ በተወሠነ ደረጃም ቢሆን አሻሽሎታል፡፡ ትንግርት ግን አሁንም እንደደነዘዘች ነው፡፡
ከጎኑ ብትቀመጥም ሩቅ ኪሎ ሜትሮች በሀሳብ ርቃ ሄዳለች፡፡ ፎዚያ ወደ እራት ዝግጅቱ ለማምራት ፈራ ተባ በምትልበት ቅጽበት ሁሴን እጁን በማጨብጨብ መናገር የሚፈልገው ነገር እንዳለ ሲናገር ሁሉም
በታላቅ ፀጥታ ውስጥ ገባ፡፡ ፎዚያም ክፍት ወንበር ፈልጋ ተቀመጠች፡፡ ሁሉም በአዕምሮአቸው የሚያጉላሉትን ጥያቄዎች መልስ ከንግግሩ ለማግኘት ጓጉቷል፡፡
‹‹ወደ እራት ፕሮግራሙ እንደዚህ በተጨናነቀና በታፈነ ድባብ እንድንገባ አልፈለኩም፡፡ በመጀመሪያ ኤደን ምን አልባት ጥሪዬን አትቀበይም ብዬ አስቤ ነበር ስለተገኘሽ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ መንታዎቹ ዕፀ - ህይወት እና ዕፀ - ፍቅርም ስለተገኛችሁ በጣም አስደስታችሁኛል፡፡ እናታችሁ ብትመጣም ደስ ይለኝ ነበር ግን ምንም አይደል…›› ንግግሩን ገታ አደረገና እጁን ወደ ኪሱ ከቶ አበባ እና ቀለበት ይዞ መጥቶ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው፡፡
‹‹እንግዲህ የሦስት ቀን ተልዕኮዬን አጠናቅቄ መጥቻለሁ፤ እናንተም ይሄንን በማስመልከት በሞቀ ዝግጅት ተቀብላችሁኛል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ የጠበቃችሁት ነገር ማለት የፈለጋችሁት ሠው ለማየት አልቻላችሁም፡፡ የዚህንም
ምክንያት እንዳብራራላችሁ የምትፈልጉ ይመስለኛል፡፡መቶ ፐርሰንት እርግጠኛ ባልሆንም ለሁለት ዓመታት በማይጨበጥ ፍቅር ያሠቃየችኝን ደራሲ ዛሬ ያገኘኋት መስሎኛል ፤ነገር ግን ላናግራት ወይንም በተስማማነው መሠረት ይሄንን እንቡጥ አበባ ላበረክትላት፤ ይሄንን ቀለበትም ላጠልቅላት አልቻልኩም፡፡ እንዲህ ስላችሁ የማትሆን ሴት ሆና ስላገኘኋት እንዳይመስላችሁ ፤እንዳውም ከጠበኳት በላይ ቆንጆ፤ ከአሠብኳት በላይ ውብ ነች፡፡ ጠይም የሆነ ኢትዮጵያዊ የቆዳ ቀለም፤ሞዴሊስት ለመሆን የሚያስችላት የሠውነት ቅርጽ፤ገና ያልተነካ እንቡጥ ወጣትነት፤በቃ አሟልቶ የፈጠራት የምትባል ዓይነት ነበረች፡፡››
‹‹እና መጨረሻው ምን ሆነ?›› ትዕግስት አጥታ ጣልቃ የገባችው ኤደን ነበረች፡፡ ከስምንት ወር በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ከእሱ ጋር ስትቀመጥ ዛሬ የመጀመሪያዋ ነው፡፡አሁንም ታፈቅረዋለች፤ግን በበፊቱ መልክ አይደለም፡፡ ከእሱ ጋር የነበራትን አብሮነት ሙሉ በሙሉ በጥሳዋለች፡፡ሌላ ሕይወት ሌላ የፍቅር መንገድ ውስጥ ገብታለች፡፡ እንዲያም ሆና ታፈቅረዋለች፡፡ስለምታፈቅረውም… ያፈቀራትን፤ለረጅም ጊዜ የተጎዳባትን፤ከእሷ ጋርም የተለያየባትን ልጅ አግኝቶ ጥሩ የፍቅር ስኬት ቢያጋጥመው በዚህን ወቅት ደስተኛ ትሆን ነበር፡፡ አሁን ግን ምኞቷ ሁሉ በመክሸፉ ግራ መጋባት ውስጥ ገብታለች፡፡
ሁሴን ንግግሩን ቀጠለ <<....መጨረሻም ሀሳቤን ቀየርኩ፡፡ ሳስበውና ውስጤን በጥልቀት ሳዳምጠው፤ ከእሷ በላይ ማጣት ማልፈልጋት፤ ከእሷ በላይ የማፈቅራት ልጅ ልቤ ውስጥ አገኘሁ፡፡››
‹‹ማነች?›› ከሦስት ሠው አፍ ነበር የወጣው፡፡
ሠሎሞን፣ ፎዚያ እና ኤደን፤ እንደተማከረ ሠው
በአንዴ አፋቸውን ከፈቱ፡፡ ትንግርት በመጠኑ
እንደመነቃቃት ብላ አይኖቿን አፍጣ
ታስተውለው ጀመር፡፡
ምን እየተካሄደ እንደሆነ ብዙም ያልገባቸው ከጎረቤት የተገኙት አሮጊትና መንታዎቹ የሠሎሞን ልጆች በዝምታ ይቁለጨለጫሉ፡፡
‹‹ማንነቷን ልነግራችሁ አይደል…፡፡›› አበባውን አነሳ ፊቱን ከጎኑ ወደ ተቀመጠችው ትንግርት አዞረ ...‹‹እነሆ ይሄ የሦስተኛና የመጨረሻ ዕድሌን የምሞክርበት የፍቅር መግለጫ አበባ ነው፡፡ ትንግርት አንቺን ከምስጢር በላይ እንደማፈቅርሽ ዛሬ በደንብ ነው የገባኝ፡፡ ዛሬውኑ ላገባሽ እፈልጋለሁ፤ እባክሽ አታሳፍሪኝ፡፡››
የቤቱ ሠው ሁሉ የሚካሄደውን ትዕይንት ማመን አልቻለም፡፡ አንደ ትንግርት ግን ሁሉም ነገር ቅዠት የሆነበት የለም፡፡ ሁሴን አበባውን እንድትቀበለው እጆቹን ለልመና እንደዘረጋ ነው፡፡ እሷ ግን መንቀሳቀስ አልቻለችም፤ ወንበሩን ወደ ኋላ አንፏቆ ክፍት ቦታ ካገኘ በኋላ በጉልበቱ ተንበረከከና አንገቱን በትህትና ወደ መሬት ደፍቶ ‹‹እባክሽ ተቀበይኝ፡፡›› አላት፡፡
‹‹ተቀበይው›› ሠሎሞን ነበር፡፡
<ተቀበይው ተቀበይው ሁሉም...» በመቀባበል ጮኹባት፡፡በደመነፍስ እጇን ዘርግታ ተቀበለችው፡፡ እቤቱ በጭብጨባ ደመቀ፡፡ በማስከተልም ጠረጴዛ ላይ ያለውን ቀለበት አንስቶ ጣቷ ላይ አጠለቀላት፡፡ዳግመኛ ደማቅ ጭብጨባ በቤቱ ተስተጋባ፡፡ የትንግር፦ ጉንጮች በእንባ ራሱ…፡፡ ቀስ ብላ አጠገቧ ያለውን ቦርሳዋን አነሳችና የጎን ኪሱን ከፈተችው፡፡ እጇን ሠደደችና የልብ ቅርፅ ኖሮት መሀከሉ የእሱ ስም የመጀመሪያ ፊደል ያለበት ሀብል መዛ አወጣችና አንገቱ ላይ አጠለቀችለት፡፡ አሁን ደግሞ ግራ

👍106❤14👎2👏1