አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰው_ሁን_በይኝ

በቀደም ለት ጉንጬ መሐል
በከንፈሯ ብትዳብሰኝ፣
ሙት አካሌ ፊት እንዳለኝ አስታወሰኝ፣

ደሞ ድንገት ቀልድ ነግራኝ
ስቄ ስቄ እንዳባራሁ ፤
"ጥርስህ ሲያምር" ስላለችኝ
ዘላለሜን ማልቀስ ፈራሁ ፤

ተካተትኩኝ ከተፈጥሮ
እፍ ...አልሸብኝ ድብቅ ውበት፤
እስቲ ባክሽ አሁን ደሞ
'ሰው ሁን ብለሽ ሹሚኝና
ሰው መሆኔን ልመንበት ፤

ሰው ተብዬ ልጠራበት።

🔘አስታወሰኝ ረጋሳ🔘
👍44🥰5🔥43👏1
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በታደለ_አያሌው

...የጃሪም አወጣጥ በኃይል እየቆረቆረኝ ቢሆንም፣ ደስታዬ ግን ጢም እንዳለ ነዉ።

የመሠረት ድንጋዩ በጳጳሳቱ እና ሌሎች ታላላቅ ስዎች ተቀምጦ ከአበቃና የጉባዔዉ አጋፋሪ ‹ሂዱ በሰላም› ካለን ከብዙ ደቂቃዎች በኋላም ቢሆን፣ ችዬ መነሳት አልቻልሁም ነበር፡ ልጄ ቱናት የተኛችበትን አልጋ ወደ
ተቀመጠዉ የመሠረት ድንጋይ አስጠግቼ፣ በደስታ እንባዬን ሳወርድ ብዙ ቆየሁ፡ ሁኔታዬን ሁሉ እመዋ በሩቁ ስትመለከት ኖሯል መሰለኝ፣ ከእንግዳዉ ጋር መዉጣቷን ትታ ወደ'ኔ መጣች፡

“ደስ እለሽ ዉብዬዋ?” አለችኝ፣ ወደ እቅፏ እየሳበችኝ፡፡

“በጣም!” አልኋት፣ እንባዬን በቀሚሷ እያበስሁ

“እሰይ! እንኳ ንም ደስ አለሽ ልጄ”

“እንደ ዛሬዉም ደስ ብሎኝ አያዉቅ”

“እኔም” አለችኝ፣ ወደ አንገቷ ሥር ጠበቅ አድርጋ እየሳበችኝ ቀና ብዬ
ሳያት፣ እዉነትም ተጫጭኗት የነበረዉን እርጅና ሳይቀር ድል ነስታዉ ታየችኝ: ግንባሯ ላይ በተደረደሩ መስመሮች ሁሉ ደስታ ሲፈስ አየሁ በጣም ደስ ብሏታል። ይኼ ደስታዋ የኔንም ደስታ የትና የት አደረሰዉ።

“የቱናት እናት” አለ ባልቻ፣ እንግዳዉ ቀለል እስከሚልለት ድረስ ሲሸኝ ቆይቶ ወደ እኛ እየመጣ፡ የእሱም ፊት ከእኛ በሚስተካከል ደስታ ተጥለቅልቋል ቱናትን ከነአልጋዋ አቅፎ አነሳትና የመሠረት ድንጋዩ አናት ላይ ጉብ አደረጋት: “ይኼን ወደ መሰለ ሥፍራ ስጠራት እንዲያ
እንዳልተግደረደረች፣ ደስታ እንዴት እንደሚያደርጋት አየሽልኝ አይደል
ይቺን እናትሽ?” አላት፣ ቱናትን በስስት እየተመለከታት

የመሠረት ድንጋዩ ላይ ከነአልጋዋ ያደረግናትን ቱናትን ለረዥም ጊዜ
ከብበን ከቆየንና፣ ለዚሁ ደስታችንም ወሰን ልናበጅለት ከሞከርን በኋላ እኔና ባልቻ ቱናት የተኛችበትን አልጋ ከግራ እና ከቀኝ ይዘን ወደ ባልቻ
መኪና ተሳፈርን

“በሉ እንግዲህ” አለችን እመዋ፣ ከሀገር ርቀን የምንጓዝ ይመስል አቅፋ እየተሰናበተችን፡

“አብረሽን አትሄጅም ወይ እመዋ? ዉቤ እኮ ወደ ሲራክ እየተመለሰች
ያለችዉ ከዓመት በኋላ ነዉ። መቼም በዚህ አንድ ዓመት ዉስጥ
በማዕከላችን የተለዋወጠዉ ነገር ሁሉ እያየች እንደ ጀማሪ ጎብኚ
ይኼ ደግሞ ምንድነዉ እያለች በጥያቄ ማስቸገሯ አይቀርም: ብቻዬን እችላታለሁ ብለሽ ነዉ?” አለ ዓይኖቹን በእኔ፣ በእመዋ እና በቱናት ላይ እያንከባለለ፡፡

“ወደ ሲራክ ነዉ እንዴ የምንሄደዉ?”

“አዎ ምነዉ?” አሉኝ እኩል፣ ድንግጥ ብለዉ፡ ደግሞ ልትለመንብን ነዉ› ብለዉ ነዉ መሰለኝ፣ በቅጽበት አመዳቸዉ ቡንን አለ

“እሺ”

“እኮ! እንዳንቺም በሕጋችን የቀለደበት ሰዉ የለም: እንዲያዉ የቱናት እናት መሆንሽ አተረፈሽ እጂ፣ አንቺስ ደህና አድር ገዉ ቢቀጡሽ ሁሉ የምታጸድቂ ወንጀለኛ ነሽ” አለኝ፣ እንደ መሳቅም በእፎይታ እንደ
መተንፈስም ብሎ፡

“ታዲያ እኔ እምቢ ብዬ ነወይ? ልብ ካላችሁ መቅጣት ነበራ” አልሁት፣ የቱናትን ልብስ እያስተካከልሁ

“ይቀርልሽ መስሎሻል!”

“ቆይ ምን አጥፍቼ ነዉ ግን?”
ያልሰማኝ መስሎ ፊቱን አዞረብኝና፣ እመዋን እንደገና ተሰናበታት፡ እኔም እንደ'ሱ የመኪናዉን መስታዎት ዝቅ አድርጌ ልሰናበታት ስል፣ ሆነ ብሎ
መኪናዉን አንቀሳቀሰብኝ፡፡

“ አየሽልኝ አይደል ምቀኝነቱን እመዋ?” አልኋት፣ ልክ እንደ በባቡር ተጓዥ እጄን እያዉለበለብሁላት፡

እሷን ተለይተን መንገድ ከጀመርን በኋላ፣ ቅድም ያልሰማ መስሎ
ያለፈብኝን ጥያቄዬን እንደገና አነሳሁበት

“እ፣ በል ገረኛ”

“ምኑን?”

“ብቀጣበት የምትጸድቁበትን ጥፋቴን ነዋ”

ፍርጥም ብሎ ጥርሶቹን ገለጠልኝ፡

“እዉነት ጥፋትሽ ጠፍቶሽ ነዉ አንቺ? ሌላዉ ቢቀር፣ አንዲት የሲራክ አባል ብትወልድም እንኳን ፈቃዷ ምን ያህል እንደሆነ አጥተሽዉ ነዉ?”

“ወይ ጉድ… እኔስ አሁንም ወደ ሲራክ እየሄድሁ መሆኑ ደንቆኛል”

ቱናትን ከወለድሁ፣ በተለይም ኋላ በሕክምናዎቿ ጊዜ ያለፈችበትን አበሳ ካየሁ በኋላ፣ ወደ ሲራክ ፯ እመለሳለሁ አላልሁም ነበር፡ እንኳንስ እስከዚህ ድረስ፣ ገዳሜን ከገደምሁበት የእመዋ ቤት አንድም ርምጃ ንቅንቅ የምል አይመስለኝም ነበር፡ ዛሬ ግን ባልቻ ገና ‹እንሂድ› ሲለኝ፣
‹እሺ› ብዬ ከመከተል በቀር ምንም ያሳሰብኝ ነገር የለም፡

በዚህ ሁኔታ ከዋናዉ የማኅበራችን ሕንጻ ደርሰን፣ ጥብቁን እና ረዥሙን የሲራክ ፯ መንገድም አልፈን ከመጨረሻዉ በራፍ አጠገብ ስንደርስ ድንገት ቆመ፡፡ ጭራሽ እንደ መቅለስለስ ብሎ አየኝ፡፡ ይኼ አስተያየቱ
ነበር ቀድሞዉንም እኔን እና እሱን በሌላ ያስጠረጥረን የነበረዉ፡፡ ግራ ገብቶኝ አየሁት፡ በሩ ደግሞ ሲጠም፣ እኛ መሆናችንን አዉቆ በራሱ ጊዜ እንደ ቀድሞዉ ይከፈትልናል ብዬ ብጠባበቀዉም፣ ክርችም እንዳለ ቀረ፡

ምነዉ” አልሁት፣ ዓይን ቢያበዛብኝ፡ “ኧረ አባትዮ፣ እንዴት እንዴት እየሆንህ እንደሆነ ታዉቆሃል ግ?”

“እንዴት እንዴት ሆንሁ?”

“ለራስህ አይታወቀህም?''
መቅለስለሱን ተከትሎ፣ በዚያዉ ሐሳብ ገባዉና፣ ቁዝም ብሎ ቆየብኝ፡

“ምንድነዉ ጉዱ፣ የማትነግረኝ?”
“እንዳትቆጪኝ ፈራሁ እንጂ”

“እንዳትቆጪኝ?”ፈራሁ

“ለእሷ የምትሆኚዉን ሳይ፣ ትንሽ ፈራሁ”

“ማናት ደሞ እሷ?”

ልጅሽ፣ ቱናት” አለኝ፣ የቱናትን አልጋ የያዘ እጄን እያስለቀቀብኝ፡ እሱዐበአንደኛዉ ጎን፣ እኔ ደግሞ በሌላኛዉ ጎን ሆነን ነበር በየእጃችን የያዝናት አሁን ግን የመፈልቀቅ ያህል እጄን አስለቅቆ ለብቻዉ ወደ እቅፉ ወሰዳት አድራጎቱ ሊገባኝ ባይችልም፣ ባልቻ ነዉና ሰዉየዉ ልጄን አትንካብኝ ብዬ ልከላከለዉ አልቻልሁም፡ ትንፋሼን ዉጬ
መጨረሻዉን ጠበቅሁት፡፡ በእርግጥ፣ ደግሞ ሌላ የምሥራች
የተዘጋጀልኝም መስሎኝ ራሴን ለደስታ እያመቻቸሁ ነበር የለመደች ጦጣ አሉ!

“በቃ ዉቤ፤ በቃ ቱናትን ወስጄብሻለሁ” አለ፣ ስለ ራሱ ንግግር ራሱ ሐፍረት እየተሰማዉ፡፡

"እ" አልሁት፣ በግንባሬ፡ ብቻ ያንን የመሰለ ደስታ እንዳይከስምብኝ፡
ዓይኔን በልጥጬ በግርታ አየሁት፡

“አዎ”

“ኧረ አባትዮዉ ተዉ አታስቀኝ” ብዬ፣ እንደ ምንም ጥርሴን ለመግለጥ ሞከርሁ: ሳቄን የሚጋራኝ መስሎኝ ሳቅ ብርቃቸዉ የሆኑት ጥርሶቹ እስኪገለጡ ብጠብቅም፣ እሱ ግን ክርችም እንዳለ ነዉ አሁንም:

“እየቀለድህብኝማ አይደለም: ነዉ እንዴ?”

“በፍጹም! ከእሽቴ ጋርም ተመካክረበታል: ለማኅበራች
ሊቀመንበርም አወያይቼዋለሁ:: ያዉ እመዋንም ቢሆን ጫፍ ጫፏ
አጫዉቻታለሁ: ሁላችንም ጋ ያለዉ ሐሳብ ተመሳሳይ ነዉ''

“ቆይ ቆይ”

“ተዪ ዉቤ: በቃሽ: እዲያዉም ግልጹን ንገረኝ ካልሽኝ፣ ቱናት በዚህ መልኩ የምትጠቅሚያት አይመስለኝም” አለ፣ ቆምጨጭ ብሎ፡ ጭጭ ብዬ ከማዳመጥ በቀር የምሆነዉን እንጃልኝ፡፡

“ስለዚህ ቱናት እየወሰድሁብሽ ነዉ። ከእንግዲህ ቱናትን ለብቻሽ ቤት ዘግተሽባት የብቻሽ ማድረግሽ ይቀርና፣ የሁላችንም ልጅ አድር ገንእናሳድጋታለን። አንቺም ቱናት የምታገኛት እንደ ማናችም አልፎ አልፎ እና ከሥራ ዉጪ ይሆናል ማለት ነዉ። በማኅበራችን የሕጻናት መዋያ ዉስጥ እናስገባት እና እንደ ማንኛዉም ልጅ ጨዋታ እና ግበረ ሕጻናት እየፈጸመች ታድጋለች”

“እንደ ማንኛዉም ልጅ?”
👍27
“ይገባኛል። ይገባኛል፣ከማንኛዉም ልጅ ደግሞ እሷ ተጨ ማሪ
እ ክብካቤ ትፈልጋለች: ለዚያም ቢሆን እኮ ታዲያ ትክክለኛ ቦታዋ
የማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት ነዉ: ከሰዉ ጋር ነዉ ማደግ ያለባት እንጂ በጠባብ ክፍል ከሰዉ ተሽሽጋ አይደለም: በዚያ ላይ ማኅበራችን ዘንግቶት
የነበረዉን የእሷን ዓይነት ልጆች የማገዝ ኃላፊነቱ እንዲወጣ ዓይኑን የገለጠችለትን ቱናትን ለዉለታዋ የሚሆ ነገር እዲያደርግላት ዕድል
መስጠት ያለብሽ ይመስለኛል”።

እመር ብዬ ልጄን ከእጁ መንጠቅ ፈለግሁ

“ግድ የለሽም፤ አሁ ነግሬሽ አሁኑኑ አልወስድብሽም: ግን ልብ
አድርገሽ አስቢበት። አንቺንም እኮ አጣንሽ ዉቤ? ለዚህ ማዕከል፣ ለዚህ ማኅበር ይልቁንም ለቤተ ክርስቲያናችን ምን ያህል አስፈላጊ ሰዉ እንደ ሆንሽ ላንቺ ላይታወቅሽ ይችላል: ግን አንቺም ልጅሽም እስካሁ በቆያችሁበት መንገድ ከሰዉ የምትነጠሉ ከሆነ፣ የሚጎድለዉ እንዲህ ነዉ ተብሎ የሚነገርም አይሆም: ግድ የለሽም አስቢበት''

ምንም መግባባት የቻልን አልመሰለኝም፡ እኔ በአርምሞ ተሞልቼ፣ ልጄንም ገዳሜ አድርጌ ገዳማዊ ሕይወት እየኖርሁ ነኝ ስል፣ እሱ ግን ሰዉ ጠልቼ ከሰዉ የተደበቅሁ ሳይመስለዉ አልቀረም፡

“በይ እባክሽ፤ ወደ ቀልብሽ ተመለሺና በቅጡ አስቢበት: እርግጠ ነኝ ለመቼም ፣ እስከ ማታ እሺ የሚል መልስ ከልብሽ አገኛለሁ” አለኝና፣ ወደ
ፊት ቀደም አለ፡፡ የበሩ እስካሁን አለመከፈት ገርሞኝ ነበር፡ ለካንስ እኔ ስለ ቀደምሁ እና በየሳምንቱ መታደስ የነበረበት የይለፍ ፈቃዴ ከቋቶች ሁሉ ስለ ተሰረዘ ኖሯል ክርችም እንዳለ የቆየዉ፡ ልክ ባልቻ እኔን አልፎ፣ ከፊት ከመሆኑ ወለል ብሎ ተከፈተልን
እዉነትም ቅድም ባልቻ እንዳለዉ፣ የማዕከሉ የዉስጠኛዉ ክፍል
ልዉጥዉጥ ብሏል፡ በዚህ የነበረዉ ወደዚያ፣ በወዲያ የነበረዉ ደግሞ በሌላ በኩል ቦታ ተቀያይሯል፡ እዚህ ዉስጥ የሚሠሩትን አብዛኛዉን
የማዕከሉን አባላት የሚይዘዉን ሰፊዉን ክፍል አልፎ ይገኝ የነበረዉ የዋና ዳይሬክተሩ ቢሮ ሳይቀር ወደ በሩ አጠገብ መጥቷል

“ማን ናፈቀሽ?” አለኝ ባልቻ፣ ቱናትን ይዞ ወደ ቢሮዉ እየወሰደኝ

“ማንም”

“ዉሽታም! ማንም ማንም?”

“ማን ይናፍቀኛል ብለህ ነዉ ከቱናት በቀር? እሷ ብቻ ናት እቅፌ ላይ ሆና ጭምር አብራኝ እንዳለች የማላምናት። ሌላ ማንም”

“እነሱ ግን ‹ናፈቀችን ናፈቀችን እያሉ ትንፋሽ አሳጥረዉኛል”
“እነማናቸዉ እነሱ?”

“ኧረ ስንቱ! አንቺንና እኔን አብረዉ የሚያዉቁን ሁሉ። በተለይ እዚህ
የሚሠሩት የሲራክ አባላትማ አይወራም: አንቺ ግን ያ ሁሉ ለሰዉ የነበረሽ ስስት ቀርቶ፣ አሁን የናፈቀኝ የለም, ብትዪኝ ደንቆኛል። ለነገሩ አላምንሽም: እንዴት ግን?”

እዉነት አለዉ እኮ የናፈቀኝ የለም እዉነት? የባልቻን አግራሞት ተከትዬ እንደገና ባስበዉ፣ እኔንም ገረመኝ፡ ሌላዉ ቢቀር ወንድሞቼና እህቶቼ አልናፈቁኝም ወይ? እመዋ ቤት ባለኝ ክፍል ተወስኜ ከቱናት ጋር ብቻ ከተቀመጥሁ በኋላ፣ ሲወጡ ሲገቡ ዳናቸዉን በሩቁ እሰማቸዋለሁ እንጂ
ዓይን ለዓይን ከተያየን ስንት ጊዜያችን! እመዋንስ እሺ በቀን አንድ ጊዜም ቢሆን፣ መቁነን ስለምታቀርብልኝ እና አልፎ አልፎ ደግሞ ለቱናት የሚሆኑትን ነገሮች በገፍ አስገዝታ ስለምታቀብለኝ ሳንተያይ አድረን አናዉቅም፡ እነ ጃሪም ግን ከናፋቂ ልቤ እንዴት ሊወጡ ቻሉ? በእንቅልፍ
ልቤ እንኳን ባጣቸዉ የምሞት ሲመስለኝ ኖሬ፣ አሁን ግን እንዴት የእናቴ ልጆች አይናፍቁኝም?
እንዴት?....

ይቀጥላል
👍205👏2🔥1
#ሳቤላ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...የሚስተር ኬን የሙዚቃ ትርዒት ሀሙስ ታይቶ ሲያበቃ ሎርድ ማውንት ስቨርን ቅዳሜውን ከኢስት ሊን ጓዙን ጠቅልሎ ለመነሳት አቀደ የጉዞው ዝግጅትም አስቀድሞ ተጀመረ ነግር ግን ቀኑ ከይረሰ በኋላ ያ ሁሉ የመነሳት ዝግጅት ለሁለተኛ ጊዜ እንዳይሰናከል አጠራጣሪ መስሎ ታየ ገና ሲነጋ ቤቱ ተሸበረ ከዌስትሊን ቀዶ ጠጋኝ ሐኪም ሚስተር ዌይን ራይት ተጠርቶሰ ከኧፕርሎ መኝታ ቤት
ገባ " ኧሮሎ አሁንም በሽታው እንደገና ክፉኛ ተቀሰቀሰበትና በጣም ተበሳጨ።

« በዚህ ዐይነት ገና ሳምንት ሁለት ሳምንት ወይም አንድ ወር እዚህ እቆይ ይሆናል » አላት ለሳቤላ ።

« በጣም አዝናለሁ... አባባ ኤስት ሊንን በጣም ስልችኸዋል " »

« መሰልቸት ይደለም ። ከኢስትሊን እንድወጣ የምፈልግበት ሌሎች ምክንያቶች አሉኝ አሁን ኮ አንቺም ወደ ሙዚቃ ትርዒት መሔድ ላትችይ ነው »

ሳቤላ ፊቷ ቀላ ። ምነው አባባ ? ላትችይ ነው አልከኝ?»

«አዎን ማን ይዞሽ ይሔዳል ? እኔ እንደ ሆንኩ ከመኝታዬ እንኳን መነሣት አልቻልኩም »

« መገኘት አለብኝ . . . አባባ " አለዚያማ እንግኛለን ብለን አስወርተን ብንቀር ዱሮውንም እንደማናደርገው አወቀን ያስወራነው ይመስልብናል " ደግሞ እንደምታውቀው ከዱሲ ቤተሰብ ጋር እዚያ ለመናኘት †ቃጥረናል " ባይሆን ሠረገላው እዚያው ያድርሰኝና እኔ ከነሱ ጋር እገባለሁ" »

« በይ እሺ ላንቺ ደስ እንዲለሽ እኔ እንኳን የምትቀሪበትን ስበብ ካገኘሽ እንዳጋጣ ቀርተሽ የምትጠቀሚበት መስሎኝ ነበር » አላት "

« በጭራሽ ! እኔ ሚስተር ኬንን ከነሙዚቃው የማልንቀው መሆኔን ዌስት ሊን እንዲያይ እፈልጋለሁ » አለች ሳቤላ እየሣቀች ።

ቀን ላይ የዊልያም ቬን በሽታ በጣም ከሚያሳስብ ደረጃ ላይ ደረሰ " ስቃዩ በጣም የሚያሰቅቅና የሚያስጨንቅ ነበር ከክፍሉ እንዳትገባ የተደረገችው ሳቤላ
ስለ በሽታው መባባስ ምንም አላወቀችም " ያን ያህል ሲያቃስት እንኳን ምንም ድምፅ ከጆሮዋ አልደረሰም » ስለዚህ ያለምንም ሐሳብና ጥርጣሬ እየሣቀችና
እየተጫወተች ደንገጡሯ ማርቨል እየረዳቻት መልበስ ጀመረች ማርቨል እመቤቷ የመረጠችውን ልብስና ጌጥ ሳትወደው እየከፋት አልብሳት አበቃች » ሳቤላ ልዩ ሁና
አጊጣና ለብሳ ወደ አባቷ ክፍል ገባች እንግዲህ ልሒድ አባባ ? » አለችው።

እሱም አዘብዝበው ያበጡትን ያይኑን ቆቦችና ደም የለበሰው ፊቱን ገለጥ አድርጎ” ሲያይ በትክክል ምን እንደምትመስል ባያረጋግጥም የምታምር ንግሥት የምታበራ መንፈስ መስላ ታየችው "ነጭ ዳንቴል ሥራ ቀሚስ ለብሳ አልማዟን በጸጉሯ ባንገቷና በክንዷ አድርጋለች " ቀሚሱ በጣም ምርጥ ከሆነ ጨርቅ የተስፋ ነበር " አልማዞቹ ከመልካሙ አንገቷና ከሚያሳሱት ክንዶቿ ላይ ሲብለጨለጩ ጫፉ
ቅልብስ ቅልብስ ብሎ የተበጠረ ከትከሻዋና ከደረቷ ወርዶ ከተኛው ጸጉሯ ጋር ልዩ ሁነው አምሮባት ነበር።

ኧርሉ ሲያያት በጣም ገረመውና ትክ ብሎ ካስተዋላት በኋላ «እንዴት ለአንድ የሙዚቃ ትርዒት እንደዚህ ሆነሽ ትለብሻለሽ ? አብደሽ ነው በጤናሽ ? » አላት

« ማርልም እንዳንተ አለችኝ » አለችው አሁንም በደስታ እየተፍነከነከች "
«እንዲያውም ልብሱንም አላቀርብም ብላኝ በግድ ነው ያስጣኋት እኔ ግን አባባ የሚስተር ኬንን ዝግጅት በደንብ ለብሰው ሊያዩት የሚገባ ትልቅ ትሮዒት
መሆኑን እነዚህ ዌስት ሊኖች እንዲያውቁት አስቤና ሆነ ብዬ ነው ያደረግሁት " »

« በአዳራሹ ያለው ሕዝብ በሙሉ እንደ ጉድ ይመለከትሻል »

« ግድ የለኝም " የፈለገ አፉን ከፍቶ ሲያየኝ ያምሽ ውጤቱን ይዠልህ እመጣለሁ " »

« ቀጣፊ በሰበቡ ለመታየት ፈልገሽ ነው እንጂ እንደዚህ የለበስሺው ግን ሳቤላ ...ኡ ኡኡ ! ኡህ ! ኡህ ! »

ሳቤላ እንደ ቆመች ድንግጥ አለች አባቷ ሲያቃስት ሰሚውን ያስጨንቅ ነበር
«ክፉ ልክፍት ! ልጄ . . . በይ ሒጂ ስናገር ይብስብኛል " »

« አባባ ልቅርና አጠገብህ ልሁንልህ ? » አለችው ኮስተር ብላ " ከማንኛውም ሐሳብና ሥራ በሽታ ይቀድማል " እንድቀር ከፈለግኸኝ ወይም የማደርግልህ ነገር
ቢኖር ልቅር " »

« እንዲያውም መሔድሺን እፈልገዋለሁ " ልታደርጊልኝ የምትችይው አንድም ምድራዊ ነገር ስለሌለ ሒጂ ይልቅስ ሚስተር ካርላይልን ያገኘሽው እንደሆነ ነገ ላነጋግረው እንደምፈልገው ንገሪው »

ማርቨል አንድ ካባ በትከሻዋ ላይ ጣል አዶረገችላትና ተዘጋጅቶ ሲጠብቅ ወደነበረው ሠረገላ ሔዳ ገባች።

የሙዚቃው ትርዒት ከገበያው ላይ ከነበረውና የከተማ አዳራሽ እየተባለ ከሚጠራው ከፍርድ ችሎት አዳራሽ ውስጥ ነበር " ድምፅ ለማስተጋባት የተመቸ
አዳራሽ ነበር ከዌስት ሊን የበለጡ በጣም የታወቁ ከተሞች እንኳን ይህን የሚያህል የሚመኩበት አዳራሽ አልነበራቸውም " ሚስተር ኬን ችሎታው በፈቀደለት መጠን ትርዒቱን ለማሳመር ሞከረ አንዲት በአራተኛ ደረጃ ልትመደብ
የምትችል ተጫወተች ከለንደን ቀጥሮ አምጥቶ ሌሎች አጃቢዎችም ከአካባቢው
አሟላ።

ባርባራ ሔርም የፈለገው ነገር ይምጣ እንጂ ትርዒቱን ሳታየው እንዶማትቀር አሳውቃ ነበር እናቷ ሚስዝ ሔር ግን ፍላጐቱም ጤንነቱም አልነበራትም" ስለዚህ
ሚስተር ሔርና ባርባራ ከሚስ እና ከሚስተር ካርላይል ጋር አብረው ለመሔድ ተነጋግረው ነበር ስለዚህ ቀደም ብለው በቡና ሰዓትላይ ለመድረስ ወደ ሚስ ካርላይል ቤት ሔዱ ከተገናኙ በኋላ በሠረገላ የመሔድ ነገር ሲነሣ ቦታው ቅርብ የምሽቱ
አየር ጥሩ ስለነበር ሚስ ካርላይል « እግሮቻችን ምን ሆኑና ነው ? » ብላ ተቃወመች " ባርባራም ከሚስተር ካርላይል ጋር እየተጫወተች በእግር መሔዱን አልጠላችውም " እነሆ ዳኛው ሔርና ሚስ ካርላይል ፊት ፊት እየተጫወቱ ሲሐዱ ባርባራና ሚስተር ካርላይል ቀረት ብለው እያወጉ ከኋላ ይከተሉ ነበር "

« እንዴት ነው አሁንስ ጠፋህሳ ? » አለችው ባርባራ "
«ሎርድ ዊልም ቬን ብቸኝነት እተሰማቸው ሲቸግሩ አየሁዋቸውና በየቀኑ ኢስት ሊን እተሻገርኩ አብሪአቸው ስለማመሽ ነው " ከእንግዲህ ግን ቅዳሜ ስለሚሔዱ በቂ ጊዜ ይኖረኛል።

« ትናንት ከደብሩ አለቃ ቤት ትመጣለህ ተብለህ ስትጠበቅ ነበር አኛም ማምሻውን ስንፈልግህ አመሸን»

« አለቃው ሚስተር ሊትልና ባለቤታቸው እንኳን የጠበቁኝ አልመሰለኝም ኢስት ሊን የራት ቀጠሮ እንደ ነበረኝ ነግሬአቸው ነበር »

« ኧረ ካልክስ አንዳንዶቹ ይህን ያህል ከዚያ ቤት የሚያመላልስህ ጉዳይ ምን እንደሆነ ይርማቸዋል " አጠቃሌለህ ኢስት ሊን ሳትግባ አትቀርም እየተባልክ ነው " እንዲያውም ሳቤላ ቬን እመቤት ሳቤላ ባትሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ምልልስ እሷን ፍለጋ ነው ተብለህ ትታማ ነበር " »

ስለኔ ይህን ያህል በማሰባቸው አመሰግናለሁ የሚሰማኝ ደስታና የምቆጥርላቸው ውለታ እመቤት ሳቤላ ቬን ከሚሰማትና ከምትቈጥርላቸው የላቀ ሊሆን ይችላል " እኔን የገረመኝ ግን ባርባራ....አንቺም ይህን የማይረባ ወሬ ከቁም ነገር ቆጥረሽ ስትደግሚው ነው " »

« ሰው እኮ ነው እንዲህ የሚለው እኔ አላልኩ » አለችውና ነገሯን በመቀጠል! «ወይዘሮ ሳቤላ ድምፀ መልካም ናት የሚሏት እውነት ነው ? መቸም ያንጐራረች እንደሆነ የድምጿ ቃና ከሰማይ የወረደ እንጂ ከሰው አንደበት የወጣ አይመስልም አሉ።

« በይ ይህን አባባልሽን እኔ እንደ ሰማሁሽ ኮርሊያ እንዳትሰማሽ " ፊቷ የመልአክ ፊት ይመስላል » ስል ስምታኝ የቁጣ መዓት እንዳወረደችብኝ እንዳታወርድብሽ» አላት እየሣቀ።
👍221
ባርባራ ፡ ፊቷን ወደሱ ምልስ አድርጋ አየችውኛ «ግን እውነት መልአክ ትመሰላለች ? አንተስ እንደዚህ ብለህ ተናግረሃል ? » አለችው

« የተናገርኩ ይመስለኛል ብቻ ኮርኒሊያ ካፌ ስለ ነጠቀችኝ እርግጠኛ አይደለሁም " ኧረ ስሚ እስኪ ... ስለ ሪቻርድ እስከዛሬ ምንም ወሬ የለም ? »

«የለም ሁልጊዜም አንተና እማማ ናችሁ ይጽፋል የምትሉ " እኔ ግን ምነም እንኳን እሱ እጽፋለሁ ብሎን ቢሔድም ስለሚፈራ ይጽፋል ብዬ ተስፋ አላደርግም""
« በሌላ ስም አድርጎ ቢልክልኝ ምንም አያሠጋም " ለሚስዝ ሔርም ትልቅ እፎይታ ነበር »

«የሪቻርድን ፍራት ታውቀዋለህ ኦትዌይ ቤተል እኮ ተመለሰ" ሲመለስ እንደምትጠይቀው ነግረኸኝ ነበር ... አርኪባልድ»

« ጠየቅሁትና ምንም እንደማያውቅ ነገረኝ » ጥፋቱን ሁሉ በሪቻርድ ላይ ነው
ያላከከው»

«እኔስ ይህ ቶርን የሚባል ምን ዐይነት ሰው እንደሆነ ጨንቆኛል»
« ይገርምሻል ኮ በስዌንሰን በኩል ባጠያይቅም ምንም ፍንጭ አላገኘሁም "

በዚያን ጊዜ በዚሀ ስም የሚጠራ ሰው በዚያ አካባቢ እንዳልነበረ ተረድቻለሁ እንግዲህ ጊዜ የራሱን መብራት ይዞ መጥቶ የቶርንን ማንነትና የትነት እስኪያሳየን ድረስ በተስፋ መጠበቅ እንጂ ሌላ የምናደርገው የለም»
ባርባራና ካርላይል፡ስለዚህ እየተጫወቱ ከከተማው አዳራሽ ደረሱ - ከበሩ ብዙ ሰው ነበር " እንግዶቹ ትርዒቱን ለማየት ሲገቡ ብዙ ሕዝብ ደግሞ ከውጭ
ሆና ገቢዎቹን ይመለከት ነበር " የሎርድ ማውንት እስቨርን ሠረገላ ለሌሎች እንግዶች ሠረገላዎች መንገድ እንዳይዘጋ ጥግ ይዞ ቆመ "

« እመቤት ሳቤላ ቬንም ያቻትና እዚያ ተቀምጣለች » አለች ባርባራ

"ሚስተር ካርላይል ድንግጥ አለ " ምን ትጠብቃለች ? አባቷ የት ይሆኑ ? ጥርጣሬ ተሰማው " ምን እንደሆነ መለየት ባይችልም , አንድ የሆነ ነገር እንደነበረ
ጠረጠረ

« ይቅርታ አድርጊልኝ . . . ባርባራ " አንድ ጊዜ እስካነጋግራት ድረስ ልለይሽ ነው » አላትና መልሱን ሳይጠብቅ ሔዶ ሳቤላን አነጋገራት

«ሚስዝ ዲሲን እየጠበቅሁ ነው ... ሚስተር ካርላይል " ብቻዬን መግባቱ ደስ አላለኝም " የሚስዝ ዲሲ ሠረገላ ሲመጣ እወርድና ከሷ ጋር እገባለሁ » አለችው

« ጌቶችሳ ? »

« አዬ ለካ አልሰማህም ? እንደገና ታመመ "

« አሁንም እንዶገና ? »

«አዎን በጣም ታሟል ሚስተር ዌይንራይት ከሌሊቱ በዐሥራ አንድ ሰዓት ተልኮበት መጥቶ አብሮት እንደዋለ ነው " አባባ አን†ንም ነገ ሊያነጋግርህ እንደሚፈልግ ንግሪው ብሎኛል»

ሚስተር ካርላይል ወደ ባርባራ ተመለሰና ከአዳራሹ ገብተው በደረጃዎቹ ሲወጡ አንድ ሌላ ያማረ ሠረገላ ደረሰ " ባርባራ ዞር ብትል የሚስዝ ዲሲ ሠረገላ
መሆኑን አየች "

አዳራሹ ሞልቶ ነበር " ሚስዝ ዱሲ ከሁለት ሴት ልጆቿና ከሳቤላ ቬን ጋር ሆና ስትገባ ሚስተር ኬን አስቀድሞ ከኦርኬስትራው አጠገብ ይዞላቸው ወዶ ነበረው
ከፍተኛ ቦታ እየመራ ወሰዳቸው " ቀደም ሲል ሎርድ ማውንት እስቨርንን ያስገረመው የሳቤላ ቬን አለባበስና ጌጥ በአዳራሹ ሞልቶ የነበረው ሕዝብንም አስገረመው "
የሚስዝ ዲሲ ልጆች አፍንጫቸውን ነፍተው ሲመለከቷት እናቲቱም ብትሆን በጣም ያዘነች ትመስል ነበር «ተዉ ልጆች አትፍረዱባት ይህች እናት የሌላት ምስኪን ልጅ የሚያስከፋባትን የሚያስቅባትን ነገር ገልጾና ለይቶ የሚነግራት
የሚመክራት ሁነኛ ሰው የላትም ። አሁን እንዶምታይዋት አሻንጉሊት መስላ ለብሳ እንድትመጣ ያደረገቻት ማርቨል ናት » አለቻቸው "

ሚስ ካርላይል ሔርና ባርባራም ከኦርኬስትራው ጥግ ቦታ ተይዞላቸው ነበር "ሚስ ካርላይል በዌስት ሊን ከሁሉ ቀድማ የምትታይ እንጂ ከሌሎች በስተጀርባ የምትሸሸግ ሰው አልነበረችም ሚስተር ካርላይል ግን አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው
ከነበሩት ሰዎች ጋር ተደባልቆ በአካባቢው መቆሙን ስለፈለገ ከነሱ ተለየ " በአዳራሹ ውስጥ የእግር መቆሚያ ቦታ እንኳን አልነበረም " ለሚስተር ኬን ይህን ሁሉ ሕዝብ የሰበሰበለት የሱ ሙያ ተወዳጅነትና ችሎታ ሳይሆን የሳቤላ ጥረት እንደሆነ
በማወቁ እንደ መለኮት ቢሰግድላትም በወደደ ነበር ።

እንደ ማንኛውም የገጠር ዝግጅት ሁሉ የሙዚቃው ትርዒት ሪጂም ነበር " ከወታው ሩብ ያህል እንደ ተገባደዶ የሽቶ ዱቄት የተነሰነሰበት ጭንቅላት ከበራፉ አጠገብ ከነበሩት ሰዎች በስተኋላ በደረጃዎቹ ሲወርድ የሎርድ ማውንት አስቨርን አሽከር መሆኑ ሙሉ በሉ ከዘለቀ በኋላ ታወቀ " ሰውየው በዚያ ጭንቅላቱ
ግራና ቀኝ እየተገመጠ ወደ ሰዎቹ ተጠግቶ ተመልካቾችን በማስቸገሩ ይቅርታ የመጠየቅ ያህል ዝቅ ብሎ እጅ ነሣ "

ሰውየው የደነገጠና ግራ የተጋባ ይመስል ነበር ።ዐይኖቹን ከመአዘን ማእዘን እያቅበዘበዘ ፈለገና ሚስተር ካርላይልን ድንገት ሲያየው ቅልል አለው

« ይቅርታ ያድርጉልኝ ጌታዬ እመቤቲቱ የት እንዳለች ሊያሳዩኝ ይችላሉ
« ከመድረኩ አጠግብ ነው ያለች "

« ታዲያ እንዴት አድርጌ ከዚያ መድረስ እችላለሁ ? » አለ ሰውየው ከራሱ ጋር የሚነጋገር መስሎ ድምፁን ዝቅ በማድረግ
አዳራሹ እንደዚህ ሞልቶ እያለ
ይህን ሁሉ ሕዝብ ጥሎ ማለፉ ደስ አይለኝም ጌቶች በጣም ደክመውበን ነው አለው ለሚስተር ካርላይል « ሁኔታቸው በጣም የሚያሰጋ ነው »

ሚስተር ካርላይልም ሲሰማ በጣም ደነገጠ "

« ሲያቃስቱ ሲጓጉሩ በጣም ነው የሚስጮንቁት ሚስተር ዌይን ራይትና አንድ ሌላ ሐኪም አብረዋቸው አሉ " በተጨማሪም ሌሎች ሐኪሞች ለማምጣት
ወደ ሊንበራ ባስቸኳይ ተልኳል አሁን ሚስዝ ሚዞን እመቤት ሳቤላን እንድጠራት ስለ ነገረችን ሠረገላ ይዘን መጥተን ነበር " »

« ደኅና እኔ እጠራታለሁ » አለና ሚስተር ካርላይል በዚያ ግጥም ብሎ በሞላው ሕዝብ መኻል ዐልፎ ሔደ " በዚያ ሰዓት አንዲቷ የለንደን ተጫዋች አሳዛኝ
ዘፈን ስትዘፍን ስለነበር ተመልካቹ ሁሉም ሚስተር ካርላይልን በክፉ ዐይን ዐየው የሰውን መከፋት ችላ ብሎ አለፈና ከሳቤላ ፊት ቆመ።

💫ይቀጥላል💫
👍186
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በታደለ_አያሌው


“እንዴት? ተለዉጫለሁ ማለት ነዉ በቃ?” እያልሁ፣ ከራሴ ጋር
ስተዛዘብ ቆየሁ።

እንዲያዉ ራሴንም ጭምር ስዋሸዉ የናፈቀኝ የለም አልሁ እንጂ፣ እንዴት ነዉ የማይኖረዉ? የጎዳናዉን ሰዉ ሁሉ የልቤ ሰዉ ማድረግ ይሆንልኝ የነበርሁት እኔ ዉብርስት፣የእናቴን ልጆች ከልቤ ችዬ ላስወጣ? አይሆንም፡ የናፈቀኝ የለም ያለ አፌን ይዤ እንኳንስ በባልቻ ፊት፣ በራሴ ኅሊናም ሚዛን ላይ ለመቆም ተሸማቀቅሁ።

አፈርሁ።

“ወዴት ነዉ ታዲያ?” አለኝ ባልቻ፣ ቱናት ያለችበትን አልጋ እየሳብሁ
ወደ መዉጫዉ ስራመድ አይቶኝ፡

“ወደ በረሃ”

“ወዴት?”

“ገዳሜን ወደ ገደምሁበት ወደ በረሃዬ። ወደ እመዋ ቤት!”

“ቅድም ምን ተባብለ'? ተይ እንጂ በማርያም: ይልቅ ቱናትን ይዘሽ
የማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት እየጎበኛችሁት፣ ቅድም ያልሁሽን
አታስቢበትም?”

“እኔ የፈለገዉን ያህል ባስበዉ፣ የሚሆን የሚሆን መስሎ አልታኝም”

“ግድ የለሽም፣ እስከማታ ጊዜ አለሽ: ደጋግመሽ አስቢበት”

“እስኪ ይሁን። እሺ። መኪናህን አታዉሰኝም ታዲያ? ለማሰቡም ቢሆን እኮ የከረምሁባት በረሃዬ ትሻለኛለች: ወደ እመዋ ቤት መሄድ አለብኝ ትክ ብሎ ሲያየኝ ቆየና አንገቱን በይሁንታ ነቅንቆ፣ ቀድሞኝ ወደ በሩ አመራ፡ ዝም ብዬ ኖሯል እንጂ ቀደም ቀደም ያልሁት፣ ቀድሞ የነበሩኝ
የትለፍ ፈቃዶች ሁሉ መልሰዉ ካልታደሱልኝ በቀር ያለ'ሱ ወደ ሲራክ ፯ መግባትም ሆነ ከማዕከሉ መውጣት
አልችልም:: ስለሆነም
ጠመዝማዛዉን እና ባለ ብዙ በሩን ሲራክ ፯ አሳልፎኝ መኪናዉ
እስከቆመበት ድረስ ቱናትን ከነአልጋዋ አቅፎ አደረሰልኝ፡፡
“በይ እንግዲህ። ማታ፣ ልክ አንድ ሰዓት ሲሆን እደዉልልሻለሁ” አለኝ፣ የጠየቅሁትን የመኪናዉን ቁልፍና ያልጠየቅሁትን አንድ የእጅ ስልክ ጭምር አዉጥቶ እያቀበለኝ፡፡ እሺም፣ እምቢም፣ ቻዉም ሳልለዉ፣ ቱናትን ጭኜ የመኪናዉን ሞተር አስነሳሁ፡ እንደ ድሮዉ በችኮላ ሳይሆን፣ የመኪና መሪ ከነካሁ ቢያንስ መንፈቅ እንዳለፈኝ እና ከአጠገቤ
የጫንኋትም ሰዉ ገዳሜ ቱናት መሆኗን በማሰብ ወደ እመዋ ቤት
የሚወስደኝን ጎዳና በዝግታ አሽከረከርሁበት እንደ ደረስሁ፣ የግቢዉን በር ራሴዉ ለመክፈት ቀልጠፍ ብዬ ወረድሁ።
ስሞክረዉ ግን አልከፈትልሽ አለኝ፡፡ ለወትሮዉ ማናችንም የቤተሰቡ አባላት አድርሶን በመጣን ጊዜ እንዳንቸገር በሚል፣ ግቢያችን ተቆልፎብን
አያዉቅም: እንዲሁ በዉስጥ በኩል ይሸነጎርና፣ መሸንጎሪያዋን
የምንስብባት ደግሞ እኛ ብቻ የምናዉቃት አልባሌ ገመድ አለችልን፡አሁን ግን ይቺ ገመድ በሩን ልትከፍትልኝ አልቻለችም፡፡ እንዲያዉም እጄ ላይ ስለቀለለችብኝ፣ ሳብ ሳደርጋት ጭራሽ ምዝዝ ብላ ወጣች ገመዷ
ተበጥሳለች::

ቆይ፣ ገመዳችንን የበጠሰብን ማነዉ? ምንድነዉ?

“ኤጭ!” አልሁኝ፣ ንድድ ብሎኝ፡ በዚያ ላይ ልጄ ቱናት ምግብ
ከቀመሰች ቆይታለች፡፡ እንዲያዉም ለመንገድ ብዬ ይዤላት የነበረዉ
ምግብ ስለ ቀዘቀዘባት፣ እዚህ ደርሼ ትኩስ ምግብ እስከማጎርሳት ነበር
ችኮላዬ::
“ቆይ፤ ገመዳችንን ማነዉ የበጠሰብን?” አልሁኝ፣ እጄ ላይ ያለዉን የገመድ ቁራጭ ጨብጬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ቢገባኝ፡

“እኔ” አለኝ፣ ከዉስጥ በኩል።

“አሃ፣አላችሁ እንዴ? በሉ ክፈቱልኝ' አልሁኝ በደፈናዉ፣ ማን
እንዳናገረኝ ስላላወቅሁት

“ምን ልትሆኚ?” አለኝ አሁን በድምፁ ለየሁት፡ ጃሪም ነዉ፡

“ክፈትልኝ”

“እንዳታስቢዉ!”

“ኧረ ባክህ አትቀልድብኝ። ለራሴ ልጄን ርቦብኛል። በል ክፈተዉ ይልቅ”

“አይ እግዲህ! በቋንቋሽ መሰለኝ ያናገርሁሽ!''

“ምን መሆንህ ነዉ፣ ክፈትልኝ እኮ ነዉ የምልህ”

“ሴትዮ! ምናለበት ባትፈታተኚኝ? ነገርሁሽ፤ ከዛሬ በኋላ እዚህ ግቢ ላይሽ አልፈልግም”

“እኔ ተናግሪያለሁ ጃሪም! ክፈተዉ ልጄን ርቧታል። አላበዛኸዉም እንዴ ?
ብለህ ብለህ ደግሞ ወደ እናቴ ቤት እንዳልገባ ልትከለክለኝም ያምርሃል ጭራሽ?” እልህ እየመጣ ጉሮሮዬን ተናነቀኝ፡፡

“ዉነት የእናትሽ ቤት እንግዲያዉስ እርምሽን አዉጪ። ሰማይ ዝቅ
ቢል ይቺን ግቢ ደግመሽ አትረግጫትም: በጭራሽ! ለአንቺም ሆነ ለእናትሽ፣ በቂ ጊዜ ሰጥቻችሁ ነበር: የማያልቅ መስሏችሁ ስትቀልዱበት
ያለቀባችሁ እንደሆነ፣ እኔ ጃሪም ምን እዳዬ? ከዚህ በቀር ምን
ላድርጋችሁ? የራሳችሁ ችግር ነዉ፣ ሥራችሁ ያዉጣችሁ: ከደጄ ግን ፈቀቅ! ያቺ ቆዳ እናትሽ መቼም ልብ የላትም፣ ያልኋትን ረስታ ድርሽ እንዳትልብኝ ብቻ!"
ይኼን ሁሉ ስንባባል፣ ጎረቤት እና አላፊ አግዳሚዉ ሁሉ በግላጭ
እየሰማና እያየኝ ነዉ አንዳንዱ ለእኔ አዛኝ መስሎ ጠጋ ይልና፣ ‹እንዲህ በይዉ› ብሎ ይመክረኛል የተረፈዉ ደግሞ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንደ'ሱ ልክ ልኳን ንገራት ጃሪምን
ይመክረዋል አንዳንዱ እንዳትከፍትላት፣ ደግ አደረግህ!» ይለዋል እሱን፣ ሌላዉ ደግሞ ምን አለማመነሽ? ፈሪ ነሽ እንዴ? መኪና ይዘሽ የለ? ዝም ብለሽ ደርምሰሽዉ የማትገቢ! ይለኛል እኔን፡ አልደነቀኝም ምክራቸዉን ሰምቼ የእናቴን
አጥር ብደረምሰዉ እና ቢፈርስ፣ እኛ እንጂ እነሱ አይጎዱም፡

መካሪ እና ግርግሩ መብዛቱን ሳይ፣ ለመሸሽ መረጥሁ: ምስስ ብዬ ወደ መኪናዉ ገባሁና፣ ቆይቼ ብመለስ
አልፎለት እንደሚጠብቀኝ
በመተማመን፣ እሱን ትቼ እመዋን ፍለጋ ወደ ኋላ መንዳት ጀመርሁ።

እሺ ጎረቤት እና አልፎ ሂያጅስ የእኛን ነገር ያባብስብን ግድየለም፣ የቀሩት
እህትና ወንድሞቼን ድምፅ አለመስማቴ ግን ደነቀኝ፡፡ መቼም በግቢዉ
ዉስጥ ያለዉ ጃሪም ብቻዉን አይመስለኝም: ያም ብቻ ሳይሆን፣ እኔን
ከብቦ እኔንም ግፊ፣ እሱንም ግፋ ይል ከነበረዉ ሰዉ መሀል አንደኛዋ
እህቴ ጭጭ ብላ፣ ልክ እንደሌላዉ ሰዉ ስትታዘበን አይቻታለሁ የሆነዉ ሆኖ በቅቶኛል፡ እየተንገሸገሽሁ ከመንደራችን ራቅ እንዳልሁ፣ መኪናዉን ዳር አስይዤ
አቆምሁትና፣ አብሮ በሚዞረዉ አልጋዋ ላይ ከኋላዬ ያስተኛኋትን ልጄን
ዳበስኋት፡ ቱናትን፡ ትራፊ ምግብ አላበላትም ብዬ የመብያ ሰዓቷን
በጣም አሳልፌባታለሁ፡ አሁን ግን አማራጭ ስለ ሌለኝ፣ ቅድም
ቀማምሳለት የተረፈዉን ቀዝቃዛ ፍትፍትም ቢሆን ማብላት አለብኝ በተጨማሪም እንደ ልማዴ ዓይኔን ጨፍኜ እየተንሰፈሰፍሁ፣ ትንሿን ጣቴን በፊንጢጣዋ በኩል ሰድጄ ካካ ማስባል አለብኝ፡ ይኼንንም በየሦስት
ሰዓቱ ማድረግ ሲጠበቅብኝ፣ ዛሬ ግን አሳልፌባታለሁ በዚያም ላይ
ከጠዋት ጀምሬ ወዲያ ወዲህ ስላልኋት ነዉ መሰለኝ፣ እነዚያ ቁልቁል
የሰረጉ ዓይኖቿ ይበልጡኑ ቡዝዝ ብለዉ ታዩኝ፡

ቱናትን እንደ ነገሩ አቀማመስኋትና፣ ሌላ ሌላዋንም እንደሚሆን እንደሚሆን አድርጌላት ስጨርስ፣ ወደ ነበረችበት መልሼ አስተኛኋት። ከዚያ፣ እመዋን ፍለጋ ወደ ታዕካ ነገሥት ገዳም ማሽከርhር ጀመርሁ።
ምን እየተደረገ እንደሆነ እመዋን መጠየቅ አለብኝ፡፡ መቼም እሷ መልስ
አታጣልንም አሁኑኑ አግኝቻት እስከዛሬ እየናቅሁ ያለፍሁትን ጥያቄ
ሁሉ መጠየቅ አለብኝ፡ ምን እስኪፈጠር ነዉ ከዚህ በላይ? አይበቃም? ኧረ በቃ በቃኝ...

“እመዋን አይተዋታል አባ?” አልኋቸዉ ቄሰ ገበዙን፣ በሥዕል ቤት ኪዳነምሕረ እና ታዕካ ነገሥት በዓታ መካከል ባለዉ ሰፊ አደባባይ አግኝቻቸዉ፡

“እግዚአብሔር ይመስገን: ደህና ዉለዋል?” አሉኝ፣ መንገዳቸዉን ገታ አድርገዉ አቤት ትሕትና! እኔን እኮ ነዉ አንቱ ያሉኝ፡ መቼም ትሕትና ከገዳም ሌላ መኖሪያም የላት! ያልኋቸዉን ባይሰሙኝም፣ ሰላምታ እንዳቀረብሁላቸዉ ገምተዋል።

“እመዋን አይተዋት ይሆን?” ስል አቻኮልኋቸዉ አሁንም፣ ሰላምታቸዉ ጊዜ የሚወስድብኝ ስለመለሰኝ፡፡
👍22
“አላወቅኋቸዉም፣ ማናቸዉ?” አሉኝ፣ አዉቅሻለሁ አላውቅሽም በሚል ግርታ ትኩር ብለዉ እየተመለከቱኝ፡ “አሃ ፍቅርተ ማርያም፣ አንቺ አይደለሽም ወይ?” አሉኝ፣ የክርስትና ስሜን ጠርተዉ “እኔ ነኝ:
እመዋ አላይዋትም ከቀትር በኋላ?” “ዛሬ ወዲህ ባይመጡ መሰለኝ ጨርሶም አላየኋቸዉ: ምነዉ ደህናም አይደሉ?”

“አይ” ብዬ፣ በቆሙበት ትቻቸዉ ወደ ግቢ ገብርኤል ተፈተለክሁ
እዚያም አጣኋት፡ ትኖርበታለች ብዬ በገመትሁበት ቦታ ሁሉ፣ ወደ
ላይም ወደ ታችም ብዬ ብፈልጋት ላገኛት አልቻልሁም፡ ተስፋ ስቆርጥ፣ ቱናትን ለብቻዋ ትቼበት ወደ ሄድሁበት መኪና ተመለስሁ
የቀረኝ አማራጭ፣ ወደ ባልቻ መደወል ነዉ፡ ቅድም እሱ የሰጠኝ ስልክ እንዳለኝ አስታወስሁና፣ ደወልሁለት

“ኅሽ! አሰብሽበት?” አለኝ፣ ስልኩን ከማንሳቱ፡ ቱናትን ወደ ማኅበራችን
መዋእለ ሕጻናት ለማስገባት እና እኔም ወደ ቀድሞዉ የሲራክ፯
አገልግሎቴ ለመመለስ እንዳስብበት ነግሮኝ ስለነበር፣ መስማማቴን ልገልጽ የደወልሁለት መስሎታል፡ እኔ ግን እመዋ የት እንዳለች እንዲነግረኝ ነበር አደዋወሌ፡ መቼም ያለችበትን እንደሚያዉቅ ጥርጥር
የለኝም::

“አሰብሽበት አይደል?” አለኝ፣ ትንሽ እየተንተባተብሁ ስለ ቆየሁበት።

“አዎ” አልሁት፣ እንኳንስ ጨክኜ ወደ መዋእለ ሕጻናቱ ላስገባት
ይቅርና፣ ትንፋሿን ለቅጽበት የተለየሁት እንደሆነ የምሞት መሆኔን ሊያዉቀዉ እንደሚገባ ልነግረዉ በልቤ ወስኜ፡፡

“ንገሪኝ”

“አዎ፣ አሰብሁበት”

“አላልሁሽም? አሁን እኮ እንዲያዉም፣ እመዋ እና እሸቴ ወደ ማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት ሄደዉ አስፈላጊ ፈቃዶችን እና ለቱናት መሠረታዊ የሆኑ
ነገሮችን አሟልተዉ መጨረሳቸዉን እየነገሩኝ ሳለ ነዉ የደወልሽልኝ''

“እመዋ?”

“በይ አሁኑኑ ቱናትን እዚያዉ ዉሰጃት''

“ቆይ ቆይ… እመዋ አጠገብህ አለች እንዴ አሁን?''

“ ኧረ ስሚኝ እስኪ ቱናትን ወደ መዋእለ ሕጻናቱ አድርሻት መጀመሪያ እስኪ ለማንኛዉም” አለኝ፣ ስልኩን ለመዝጋት የተቻኮለ መሆኑን በሚገልጽ ሁኔታ ቅድም ወደ ቤት ስሄድ የሆነብኝን ሁሉ ሳያዉቅ እንደማይቀር በመገመት ሐሳቡን ለመቀበል አመነታሁ

“ዉሰጃት”

“እሺ”

“ከዚያ ስትመለሺ ደዉዪልኝ''

“እሺ፤ ግን እመዋን እዚያዉ አገኛታለሁ አይደል?”

“ደዉዪልኝ አልኩሽ እኮ: በይ ስትጨርሺ ደዉዪልኝ''

አሁን ገና ነዉ በቅጡ ያሰብሁበት ስልኩን ከዘጋሁት በኋላ፣ ቱናትን
ወደ ማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት ማስገባት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሀ ብዬ አሰብሁበት በእርግጥ መንፈቅ ያልሞላቸዉ ጨቅላዎች ሳይቀር የሚዉሉበት ቤት መሆኑን አዉቃለሁ በዚያ የሚያገለግሉት ሠራተኞች፣ ልባቸዉ ለሕጻናት የተመቸ መሆኑም ይገባኛል፡

ለቱናት ግን የሚሆን ነዉ? እኔስ እሷን መለየቱ ይሆንልኛል ወይ?

ስፍስፍ አልሁላት።

ቢሆንም ሌላ ምርጫ አጣሁ ሁሉም ነገር የሞት የሽረት ጉዳይ እየሆነ መጥቶብኛል። ምርር ላለብኝ ነገር ሁሉ ምርር ማለት አለብኝ የቤተሰባችንን መጨረሻ እስከማየዉ ድረስ፣ ለጊዜዉም ቢሆን ለቱናት ማቆያ ያስፈልጋታል እንደ ምንም፣ ጨክኜ መጨከን አለብኝ፡

ሰዓቴን ተመለከትሁ

ቀትሩ አልፏል።

ጥርሴን ነክሼ የመኪናዉን ሞተር ቀሰቀስሁት እንዲችዉ ሆዴ እንደ
ተንቦጫቦጨብኝ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አልፎ ከምስካየ ኅዙናን
መድኃኔዓለም ገዳም ማዶ ባለዉ ቅያስ ገባ ብሎ ወደሚገኘዉ የማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት አሽከረከርሁ። ልጄን በየቅጽበቱ እየዞርሁ እያየኋት፣ እንደ ጀማሪ አሽከርካሪ መኪናዉን ወዲያ ወዲህ እያወላገድሁ ነዳሁት፡
ዞሬ ባየኋት ቁጥር ደግሞ፣ እንዲህ ነዉ የማይሉት ድንጋጤ ጥብስቅ
እያደረገ ይወጋኛል። በኃይል ተሸበርሁ።
ለአንዳፍታም ቢሆን እንኳን ቱናትን መለየት ያሸብራል፡ መቼስ እንዲህ
የሚያደርገኝ ልጅነቷ ወይም መላመዳችን ወይ ደግሞ ገዳሜ ስለሆነች ብቻ አይመስለኝም፡ ታዲያ ምንድነዉ? ብቻ ክብድ ብሎኛል፡...

ይቀጥላል
👍3212👏3
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በታደለ_አያሌው

...ለአንዳፍታም ቢሆን እንኳን ቱናትን መለየት ያሸብራል፡ መቼስ እንዲህ የሚያደርገኝ ልጅነቷ ወይም መላመዳችን ወይ ደግሞ ገዳሜ ስለሆነች ብቻ አይመስለኝም፡ ታዲያ ምንድነዉ?
ብቻ ክብድ ብሎኛል፡

ደረስሁ።

ከጨዋታ ይልቅ ለዝምታ የሚያመቸዉን በትላልቅ ሀገር በቀል ዛፎች የተሞላዉን ግቢ፣ በተለያየ ዕድሜ የሚገኙት ሕጻናት ይቦርቁበታል። አንዳንዶች ክብ ሠርተዉ፣ አንዳንዶች በመስመር ሆነዉ፣ ሌሎች ዝብርቅርቅ ብለዉ የልባቸዉን ይጫወቱበታል፡ አለፍ ብሎ ባለዉ ሜዳ ላይ ሰፊ ምንጣፍ ተነጥፎላቸዉ ጨቅላዎች ይንከባለላሉ ከእነሱ በወራት
ዕድሜ ከፍ ያሉት ደግሞ ራሳቸዉን ችለዉ ለመቆም ይዉተረተራሉ
የሕጻናቱ ተንከባካቢዎች እንደየምድባቸዉ የሚቆሙት ቆመዉ፣ ያቀፉት ደግሞ ተቀምጠዉ በየትዕይንቱ ይደሰታሉ።

መሥራትስ እንደ እነሱ ነዉ› አልሁኝ፣ በቅናት።

ሆኖም ሥጋቴ ሊያልፍልኝ አልቻለም: እንዲሁ ከመኪናዬ ወረድሁና ቱናትን ከአልጋዋ አንስቼ አቀፍኋትና፣ የግቢዉ አማካይ የሚሆን ሥፍራ ላይ ቆምሁ፡፡ በየትኛዉ ቢሮ የትኛዉን ሰዉ ማናገር እንዳለብኝ በዓይኖቼ
ወዲያ ወዲህ ስል አንዲት በልተት ያሉ ሴትዮ ቀረቡኝ፡

“እንኳን በደህና መጣችሁ” አሉ፣ ልብ በሚሞላ ፈገግታ እኔንም
ቱናትንም አይተዉ ይበልጥ እየቀረቡን፡፡

“እንኳን ደህና አገኘኋችሁ” አልሁ፣ አንገቴን ወደ ጉልበታቸዉ
በመስበር ለትሕትናቸዉ ጭምር አክብሮት እየሰጠሁት፡
እዉነትም እነ እመዋ ነገሮችን ጨራርሰዉልኝ ኖሮ፣ ማነሽ የሚለኝ ሰዉ ቀርቶ ቅጽ እንድሞላ እንኳን የጠየቀኝ ሰዉ የለም፡ ቀድሜ ያገኘኋቸዉ ሴትዮ ለቱናት የተመደበላትን ማደሪያ ክፍል፣ ክፍሉን የሚጋሯትን
ሕጻናት፣ ያለማስታጎል እንዲከታተላት የተመደበላትን ነርስ፣ የምግቦቿን ዝርዝር መርሐ ግብር፣ልብሶቿን እና ሌሎች ነገሮችን በዚያዉ በማይለዋወጥ ትሕትናቸዉ ከገለጹልኝ በኋላ፣ ሥጋት ወይም አስታያየት
ይኖረኝ እንደሆነ ጠየቁኝ፡፡

“እንግዲያዉ መዋእለ ሕጻናት ብቻ አይደለማ ይኼማ?” አልኋቸዉ:
“ትክክል። ያዉ እንደምታዉቂዉ” አሉ፣ ደጋገሜ አንቺ እንዲሉኝ
የለመንኋቸዉን እንደ ምንም ተስማምተዉልኝ፡ “ያዉ እንደምታዉቂዉ አብዛኛዉ የማኅበራች አገልጋዮች ሌት ከቀ ሥራ ላይ ናቸዉ። በዚህም
የተነሳ ለልጆቻቸዉ በቂ እክብካቤ ለማድረግ ይቸገራሉ። ይኼ የሕጻናት መዋያ ከተከፈተ ወዲህ ግን እንደየአገልግሎት ጸባያቸዉ፣ ሙሉ ኃላፊነቱን ለእኛ ለመተዉ የተፈቀደላቸዉ አገልጋዮች አሉ: ሥራቸዉ ፋታ የሚሰጣቸዉ ያሉ እንደሆነ ግን ኃላፊነት የም ወስድላቸዉ ወይ ቀኑን ወይ ማታዉን ብቻ ይሆናል ማለት ነዉ” አሉኝ፣ ቱናትን ባዘጋጁላት
አልጋዋ ላይ እያሳረፏት፡
“ታዲያ” አልሁኝ፣ ከሁሉም ቅድሚያ ለቱናት የሚበላ እንዲሰጡልኝ ለመጠየቅ እንደገና እየዳዳሁ የአንገት ሰላምታ በርቀት ሰጥተዉኝ ከነበሩት ሴቶች አንደኛዋ፣ የልቤን አዉቃልኝ ይሁን የቱናትን ቡዝዝ ማለት አይታ እንደሆነ እንጃ፣ ትኩስ የሥጋ ፍትፍት አመጣችላት። ደቀቅ
ያለዉን የሥጋ አመታሮ በቀይ እንጀራ ፈትፍታ አምጥታ ስታጎርሳት እኔ ምራቄን ብዉጥም፣ቱናት ግን እምቢ አለች: ለማጫወት ብትሞክራት ሁሉ ለማልቀስ ተነፋነፈች።

“ግድ የለም” አሉ፣ ባልቴቷ። “ግድየለም፤ እንግድነት ተሰምቷት ነዉ። ትንሽ ትፋሽ ትዉሰድና እኔ አጫዉቼ አበላታለሁ”

“አይ አልሁኝ፣ ሥጋቴን መደበቅ እያቃተኝ፡

“ግድ የለሽም”

“እንዲያዉ ዛሬ እምብዛም ሳትበላ ነዉ የዋለችዉ”

“ሐሳብ አይግባሽ፤ አጫዉቼ አበላታለሁ”

“እንግዲህ ምን እላለሁ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ከማለት በቀር አልኋቸዉ ኹለቱንም፣ ስለ በጎ አድራጎታቸዉ፡
"ተዪ ተዪ: እኛ ነን ማመስገን ያለብን: እንኳንም እግዚአብሔር ልዩ አድርጎ የሰጠሽ ልጅሽ እንድናገለግላት ዕድሉን ሰጠሸን”

“አይ… እንዲያዉ ወድጄ እንኳን አይደለም ያመጣኋት: ልጄ ከብዳኝ ወይ ደግሞ ከእሷ የሚበልጥብኝ ሥራ ኖሮብኝም አይደለም”

“ይገባኛል”

“የሆነዉ ሆኖ እንግዲህ ከኹለት ወይ ከሦስት ሰዓት በላይ
አላስቸግራችሁም”

“ማስቸገር? የለም የለም: ለእሷ ከምናደርግላት ይልቅ፣ እሷ ለእኛ
የምታደርግልን ይበልጥብናል። ከባሪዎቹ እኛዉ ነን''

“ይሁን” ብዬ፣ ወጣሁ።

ለቅሶዋን ከኋላዬ እየሰማሁ፣ እንደ ምንም ጨክኜ ወጣሁ ወደ ጦር ሜዳ እየኼድሁ እንደሆነ ነዉ የሚሰማኝ፡ ከወንድሞቼ እና
ከእህቶቼ፣ በተለይም ከጃሪም ጋር ፊት ለፊት እስከምገጥም ቸኩያለሁ።እሱም ቢሆን ሌላ ምንም ምርጫ አልተዉልኝም፡፡

‹ምን ይሉት ፍርጃ ነዉ ግን? ኧረ እንደ ዋዛ የት ነዉ የደረስነዉ
በማርያም? እያልሁ እንዲችዉ እንደ ተብሰለሰልሁ፣ በአዲስ አበባ
ዩኒቨርስቲ ዋናዉ ግቢ በኩል ባለዉ ቁልቁለት ወረድሁ።

ለነገሩ ለምን በእነሱ ብቻ እፈርዳለሁ? ጥፋቱ የራሴም ጭምር አይደል?እነሱ ሆኑብኝና ተለማመጥኋቸዉ፡ የእኔ በሕይወት መኖር በእነሱ ፈቃድ እስኪመስል ድረስ ግፊያቸዉን ሁሉ ቻልሁላቸዉ᎓ የጃሪም ወንድምነት
ቢቀርብኝ እሞት ይመስል፣ ያለ ጥፋቴ ጭምር ማረኝ ማረኝ አልሁት።

ቆይ፤ እዉነት ግን አልሞትም? ያለ ጃሪም ወንድምነት፣ ያለ እህቶቼ
እህትነት ምንድን ነኝ እኔ?

ወደ ማኅበራችን ሕንጻ የሚያደርሰኝን መንገድ እንደ ተያያዝሁት፣ የዛፍ እና የንብ ሽርክና በልቡናዬ ክችች አለብኝ፡፡
ሠራተኛዋ ንብ ለማኅበረ ንቧ የሚሆነዉን ምግብ ለመቅሰም አበባ ወዳለው ዛፍ ታርፋለች:: ከአበባዉ ላይ የምታገኘዉን ዕጩ ማር ከቀሰመች በኋላ ተጨማሪ ፍለጋ ወደ ሌላ ባለ አበባ ዛፍ ትሄዳለች: ነገር ግን ከዛፋ
በምትነሳበት ጊዜ፣ የአበባዉ ወንዴ ዘር በጸጉራም አካሏ ላይ ተሳፍሮ ይከተላታል። ወደ ቀጣዩ የአበባ ዛፍ በምታርፍ ጊዜም፣ ያ ከዚያኛዉ ዛፍ ያመጣችዉ ወንዴ ዘር፣ እዚህኛዉ ዘንድ ካለዉ የአበባዉ ሴቴ ዘር ጋር ይገናኛል፡ በዚህም ምክንያት፣ ንቧ ምግቧን ፍለጋ ከዛፍ ዛፍ ባረፈች
ቁጥር፣ የአበባ ዛፎች እንዲራቡ ታደርጋለች ማለት ነዉ ንብ ያለ አበባ ማለት እንግዲህ ያለ ምግብ፤ አበባም ያለ ንብ ማለት ደግሞ ያለ መራባት ስለሆነ ተከላክለዉ አያዉቁም:: እርስ በእርስ ቢከላከሉ፣ አንዳቸዉም መኖር እንደማይችሉ ኹለቱም ጠንቅቀዉ ያዉቁታል።

ስለዚህ ንብ እና አበባ አይለማመኑም:: አለመለማመን ብቻም ሳይሆን፣ ነፍሳቸዉ እስኪገባ ድረስ ይዋደዳሉ
እንደ እዉነቱ፣ እኔና ጃሪምም ሆንን ከሌሎች እህትና ወንድሞቻችንም
ጋር ግን፣ አበባና ንብ ብቻ አይደለንም፡፡ ወይ ንብ እና ንብ፣ ወይ አበባና አበባ ነን፡ ያዉም ወይ የአንድ እናት ንብ እናት አበቦች ነን፡፡ እንዲያዉ እሱም አጉል ሆኖ ቢፈርስ ግን፣ ቢያንስ ንቦች፣ ወይ ደግሞ የአንድ እንደ አበባና ንብ እንኳን መሆን እንዴት ያቅተናል?

የእኔም እጅ አለበት፡፡

አዎ፣ አለበት!

እኔ ያለ እነሱ መኖር እንደማልችል ብቻ እንጂ፣ እነሱም ያለ እኔ መኖር
እንደማይችሉ ነግሪያቸዉ አላዉቅም አበባ የንብን ጥቅም ባያዉቅ ኖሮ አያከብረዉም: የማያከብረዉን ደግሞ የሚወድ የለም፡ መናቅን እንጂ፣በእጄ ነሽ፣ ብለቅሽ ያልቅልሻል፣ ተሸከምሁሽ፣ በደልሽኝ ማለትን እንጂ
እንደ'ኔ ማለትን ያስተዋል፡፡ እህትነቴ እንዲተናነቃቸዉ፣ እነ ጃሪም እዚህ እንዲደርሱ የእኔም ሚና አለበት፡፡

“የት ናት?” አልሁት ባልቻን፣ ከራሴ ጋር እንዲህ እየተዋቀስሁ ወደ
ሲራክ ፯ ማዕከል ደርሼ ቢሮዉ ዉስጥ ያገኘሁት ከኹለት ሰዎች ጋር እየተነጋገረ ቢሆንም፣ ምንም ሳይመስለኝ፡
👍31👏2
“ከእንግዶች ጋር እኮ ነኝ” አለኝ፣ በቁጣ ጥርሱን ነክሶብኝ፡፡
ይኼን እንዳወቅሁ ድንግጥ ብዬ መመለስ ቢኖርብኝም፣ ምንም ግድ ሳይሰጠኝ፣ እንዲያዉም እኔን አስቀድሞ እንዲያናግረኝ አፍጥጬ ቀረሁበት፡ እሱም፣ ምርር ማለቴን ሲያይ እንግዶቹን ለአንድ አፍታ ይቅርታ ጠይቆ፣ እኔ ወደ ቆምሁበት ወደ በሩ አቅራቢያ መጣልኝ፡

“እመዋስ?”

“እቤቷ”

“በማርያም! እንዳትቀልድብኝ። ልጄን ጥዬ ነዉ የመጣሁት። እመዋ የት ናት?”

“እየነገርሁሽ?”

“እቤቷ?” አልሁት፣ ለማመን እየተቸገርሁ፡ አላመንሁትም ግን ደግሞ ከማመን ዉጪ ምንም ምርጫ የለኝም እየተጠራጠርሁ ቢሆንም በቆመበት ትቼዉ ወደ ቤት ለመሄድ፣ ስጠቀምበት የቆየሁትን የራሱን የባልቻን መኪና ካቆምሁበት አስነስቼ
አሽከረከርሁ፡ እዉነት ባልቻ እንዳለዉ እመዋ በዚህ ጊዜ በቤቷ ከሆነች፣ ቅድም ጃሪም በሯን ዘግቶ ፈጥሮት የነበረዉ አምባጓሮ ላይ አዲስ ነገር ተፈጥሯል ማለት ነዉ።

እስከምደርስ ቸኮልሁ።

እንዳይደርሱት የለም ፍርሃት እንደ ሞላብኝ፣ እልህ እንደ ቀላቀለብኝ ወደ ሰፈር ደረስሁ ቅድም እየተገፋፉ ግርግሩን ታድመዉ ያየኋቸዉን ሰዎች አሁን አላገኘኋቸዉም: ይኼ በራሱ በጎ ነገር ቢሆንም፣ ለእኔ ግን
ጭንቀቴን ነዉ የጨመረብኝ፡፡ በዚያ ላይ የግቢዉ አጥር ወደ ዉጪ ዘመም ያለ መሰለኝ፡፡
ምንድነዉ የተፈጠረዉ?
መኪናዬን ወደ በሩ ጠጋ አድርጌ አቆምኋትና በድቅድቅ ጨለማ ወንዝ እንደሚሻገር ሰዉ እየተንቀጠቀጥሁ በሩን ቀስ አድርጌ ገፋሁት᎓ በዉስጥ
በኩል ስላልተሸነጎረ፣ ስገፋዉ በቀላሉ ተገፍቶ ተከፈተልኝ፡ ወደ ግቢዉ
ዉስጥ ዘልቄ ዋናዉን የእመዋ ቤት ስመለከት እረጭ ብሏል፡ ከራሴ
የእርምጃ ድምፅ እና የልብ ምት በቀር ምንም አይሰማኝም:

ወደ ሳሎን የሚያስገባዉን በር ቀስ አድርጌ ስከረፍደዉ፣ እመዋን በሳሎኑ
በኩል ባለዉ የጃሪም ክፍል መግቢያ አጠገብ ተቀምጣ አገኘኋት᎓
ምንጊዜም ከትከሻዋ ወርዶ አይቼዉ የማላዉቀዉ ነጠላዋ፣ እንደ መቀደድ
ብሎ ከወገቧ አልፎ ወርዷል።

እጥፍ ብላ ሳያት፣ ሁኔታዋ ነፍሴን ነዉ ያሳጣኝ፡፡ ብቻ እንዲሁ “እመዋ”
ብዬ ተብረክርኬ እግሯ ሥር ወደቅሁ ምኗን ልዳብሳት? እንባዋን
እንዳላብስላት ዓይኖቿ ድርቅ እንዳሉ ናቸዉ፡፡ ጠብታ እንኳን
አልፈሰሰባቸዉም፡ ወደ ዉስጧ ነዉ ያለቀሰችዉ: ጃሪም እናትነቷን
ከተጠራጠራት ጀምሮ ሐሜቱን እና ወሬዉን ሁሉ በሆዷ ይዛዉ እንደ
ኖረች፣ አሁንም ወደ ሆዷ ነዉ የምታለቅሰዉ፡

“እመዋ” አልኋት፣ አቤት ብትለኝ የምላት ምንም ሳይኖረኝ፡፡

ዝም አለችኝ፡፡ ዘወር ስል በሳሎኑ የግራ ጠርዝ በኩል አንደኛዋ እህቴ
እና ሌሎች ኹለት ወንድሞቼ ፈንጠር ፈንጠር ብለዉ ተቀምጠዋል።
ምንም እንዳልተፈጠረ ቆጥረዉ ሞባይል ይነካካሉ፣ እርስበእርስ ይተያያሉ፣ አልፎ አልፎ ደግሞ ወደ እኛ ሰረቅ እያደረጉ አይተዉ ፈገግ ይላሉ፡ ኧረ ምን ያለዉን ልብ ነዉ ያገኙት? እሺ፣ የቀሩት እህትና
ወንድሞቼስ የት ይሆኑ?

“እምዬ”

ዘወር እንኳን ሳትልልኝ ዝም ብላ መሬት መሬቱን እያየች ቆየችብኝ፡
እኔም የሆነዉን እንድትነግረኝ ዓይን ዓይኗን እያየሁ በመጠባበቅ ላይ
ሳለሁ፣ በሳሎኑ በኩል ያለዉ የጃሪም ክፍል በር ሲጢጥ ሲል ሰማሁት።
ዓይኔን ለበስ አድርጌ ቀና አልሁ
ዓይኔን እንደ ነገሩ ብገልጠዉም ጭልምልም ብሎብኛል፡ ብቻ እንደ
ተቀመጥሁ፣ ይኼንኑ ቡዝዝ ያለ ዓይኔን በተከፈተዉ በር ትክክል አየ ወዲያዉ ነዉ ዓይኖቼ ቦግ ያሉት፡ በጃሪም ጉልበቶች መካከል ዓይኔ ስወረዉረዉ፣ በሩን በከፈተዉ ሰዉ እግሮች መሀል አልፎ አንድ ልጅ አየ ወዲያው ነው አይኖቼ ቦግ ያሉት። በጃሪም ጉልበቶች መካከል ዐይኔ
ዉስጥ የገባዉ ሰዉ፣ እንደ ራሴ የማምነዉ ቢራራ ነዉ፡ የሲራክ ፯ቱ
ቢራራ! ዓይኔን ልመነዉ? ስለ ሲራክ ፯ መረጃ እያሾለከ ለጃሪም ያቀብለዉ
የነበረዉ ሰዉ ቢራራ ነዉ?

ሰአሊ ለነ ማርያም!

ሽንፈትም፣ መከዳትም፣ ወንድምን ያህል ሰዉ ጨርሶ ማጣትም፣ መተንፈሻ ሳይቀር መቀማትም በየነበልባሉ ለመጠጠኝ፡ በላኝ፡ በጣም በላኝ፡፡ እንዲህ ነዉ፣ እዚህ ጋ ነዉ የማልለዉን አካሌን እከኪዉ እከኪዉ የሚል ስሜት ዕረፍት ነሳኝ፡ በኃይል መከፋት፣ አሟጦ ተስፋ ማጣት፣
የእናትን የተሰበረ አንገት ማየት እና ከእናት ልጅ ጋር አንገት ለአንገት ለመተናነቅ የሚያጣድፍ ስሜትን መግለጽ እንደሚከብድ ያለ መከራ
መኖሩን አላዉቅም፡

እንደ ጃሪም ሁኔታ፣ ከእንግዲህ እሱን ከተለማመጥሁም የምለማመጠዉ
ወንድምነቱን ብቻ ላይሆን ነዉ ማለት ነዉ፡ የገዛ ትንፋሼን ጭምር ነዉ፡
አየሩን ሁሉ! እመዋን አየኋት ፤ እንደዚያዉ ናት፡ በስሕተት እንኳን ዓይኗን
አታርገበግበዉም: በሳሎን የተቀመጡትን እህትና ወንድሞቼንም አየቸዉ፣ እነሱም እንደ ነበሩት ናቸዉ፡፡

“እመዋ?” አልኋት፣ ሳግ ይሁን እልህ ጉሮሮዬ ላይ እንደ ያዘኝ፡

ዝም፡፡

“እመዋ፣ አናግሪኝ''

ዝም:

“አናግሪኝ!” አልኋት፣ በገዛ እናቴ ላይ እጄን ለማንሳት ጭምር እየቃጣኝ፡ “ንገሪኝ!” አልኋት እንደገና፣ ጮኼ፡ የምትሰማኝ መሆኗን ሁሉ እንጃ፣ አሁንም ዝም እንዳለችብኝ ቀረች:

ስቅስቅ ብዬ አለቀስሁ፡ እንባዬ እንዴት እንደሚያቃጥል! እየለመጠጠኝ
በአካላቴ ፈሰሰ፡ ያም ሆኖ ግን ሊወጣልኝ አልቻለም፡

“እመዋ በማር ያም!” አልኋት፣ አልቅሼ አልቅሼ ባይበርድልኝም::
“ንገሪኛ! ጃሪም ነዉ ልክ ወይስ እኔ? ምንም እዉነት የለኝም እኔ? በል
በል ብለዉ እዚህ ያደረሱት መካሪዎቹ ናቸዉ እዉነት ያላቸዉ? እዉነት
ወንድም አለኝ? የለኝም? እህትስ? በእዉነትም ከእኛ መሀል አንቺ እናት
ያልሆንሽው ልጅ አለሽ?

ዝም።

“ጃሪም የሆነ ጊዜ ጥሩ ጥያቄ ጠይቆኝ ነበር፤ የእኔና የእሱ ልደት በእኩል ቀን ይከበርልን የነበረዉ ለምን እንደሆነ: (መንታ ነን ወይ ሲለኝ አይደለንም አልሁት። እንግዲያዉ ታላቅና ታናሽ ሆነን በተለያየ ዓመት ግን በአንድ ዓይነት ቀን ተወልደ ነወይ> ሲለኝም አይደለም አልሁት:አሁን ሳስበዉ ግን የማላዉቀዉን ነበር የመለስሁለት ያኔ። ንገሪኝ፣
ለምንድነዉ ልደታችን በአንድ ቀ ይከበርል የነበረዉ? ቢያንስ ይቺን ብቻ ንገሪኝ''

ክስል ያለ ጥርሷን ለአንድ አፍታ አሳየችኝ፡፡

ቁርጤን ልትነግረኝ ነዉ ብዬ ለማዳመጥ ትንፋሼን ስዉጥ፣ ቀስ ብላ
እግሮቿን ዘረጋች: ከዚያ ግራና ቀኝ በእጆቿ ተመርኩዛ ከመቀመጫዋ
ሸርተት ብላ ተንጋለለች ቀጥላ፣ ወደ ቀኝ ጎኗ ገልበጥ አለችና፣ በጃሪም
ክፍል ትይዩ ጋደም አለች::

“እመዋ!”

ወይ ፍንክች! ዝም፡

መለስ እያደረጉ ፈንጠር ፈንጠር ብለዉ ምኑም እንደማይመለከታቸዉ
“እሺ እናንተስ?” አልኋቸዉ፣ ልክ እንደ ሌላ ሰዉ ትኩረታቸዉን ወሰድ
መስለዉ ወደሚመለከቱን ወንድም እና እህቶቼ ቀረብ ብዬ፡ “በቃ?
እንዲህ ይሁን እንኳን አትሉም?''

ዝም።

“በቃ?”

ጭጭ፡

እነሱ ከጃሪም የሚለዩት ምናልባትም የሚወላዉል እንጥፍጣፊ ልብ
ያላቸዉ እንደሆነ ብቻ ነዉ፡ ምናልባት ነዉ ያዉም ምናልባት ወደ ዉስጤ ብቻ ተነፈስሁ ከዚያ ዓይኔን ጨፈንሁና ወደ ልቤ አዳራሽ ዘለቅሁ፡ ጨከን ያለ ዉሳኔ ለመወሰን ከራሴ ጋር ተሰበሰብሁ፡ በልቤ
አዳራሽ ዉስጥ ራሴን ከራሴ ጋር ስበሰባ አስቀመጥሁበት፡፡
👍30
‹ብቻ አትቀደሚ! አንዴ አይቅደሙሽ እንጂ፣
ከተቀደምሽ አንቺን ለመድፈቅ የማይበረታ የለም ሳር
ቅጠሉ ይነሳብሻል፡ ምናምንቴዉ ሁሉ ጎሮሮሽ ላይ ይቆማል፡ እንኳንስ የኔ ነዉ የምትዪዉ ይቅርና፣
ራሳቸዉ ያንቺ ነዉ ያሉሽን እንኳን ይወስዱብሻል።
ጭራሽ ባዶሽን ማስቀረታቸዉም አልበቃ ብሏቸዉ፣
ወሰደችብን ብለዉ ያዋክቡሻል፡ መልሰዉ ደግሞ ይዘባበቱብሻል። ይሸልሉብሻል ግድየለም እነሱን ራሳቸዉን እንኳን አጥቻቸዉ የለ ብለሽ እንኳን
ትንፋሽ የሚባል እንዳትጽናኝ፣ የመጽናኛ
አያስቀሩልሽም አንቺን በፍህም ያዉም በሹል ሚስማር ላይ አቁመዉሽ፣ ያሽኩብሻል። ልንገርሽ?
በፍጹም እንዳትቀደሚ፡ ወደ አንቺ የተዘረጋዉ እጅ ለፍቅርም ይሁን ለጸብ፣ እንዳመጣጡ አፈፍ አድርጊዉ
እንጂ አትቀደሚ ለምንም ነገር፣ ማንም አይቅደምሽ! የፈለገ ብትሸሸጊዉ ዉጊያዉ እንደሆነ አይቀርልሽም እንግዲህ! ይልቁንስ ምረጪ። መዋጋት
ያለብሽ ራስሽን ለማዳን ነዉ ወይስ ራሱን የሚዋጋሽን ቤተሰብ ለማትረፍ? ወጣ ወረደ፣ እንዳትቀደሚ!

አመጽሁ: በራሴ ላይ ራሴ ተነሳሁ፡ ይኼን የራሴን ከራሴ ጋር ያደረግሁትን ስብሰባ ጨርሼዉ ተነሳሁና፣ ጃሪም ወደ ክፍሌ ገባሁ ከዚያ፣ ሲራክ ፯ን በዋና አባልነት የተቀላቀልሁ ጊዜ ለማዕከሉ ተልእኮ
ብቻ እንድጠቀምበት የተሰጠኝን ሽጉጥ ከደበቅሁበት አወጣሁት ሽጉጡን ይዤ በጎኗ ወደተኛችዋ እመዋ ተመለስሁና፣ ዘርፈፍ ብሎ የተረፈዉ የቀሚሷ ጥለት ላይ ተቀመጥሁ እያንጎራጎርሁ፡ ያዉም፣ አንድ ጊዜ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የሩስያዉን የሐኪም ልዑክ እራት የጋበዘ ዕለት
አንጎራጉሬዉ፣ ትንቢቱ ገብቶት ይሁን ሳይገባዉ እንጃ፣ ብቻ አምባሳደሩ ሳይቀር አጀብ አጀብ ካለልኝ እንጉርጉሮ መካከል፡፡ አሁን እንደ ልማዴ ክራር ሳይሆን ሽጉጥ ቢሆንም በእጄ የጨበጥሁት፣ የዚያን ጊዜዉን ስሜት ግን ጨርሼ አላጣሁትም፡

የማታ መንገድ የሚያልቅ መስሎት
የፀሐይን ዓይን እፍ እፍ አለበት።
እፍ ፍታዉ ላይ ባልኖርበትም፣
የመጣዉ ይምጣ
ዓይኔን አልከድንም፣
አ ል ቀ ደ ም ም!


አልቋል


ቀጣዩን ክፍል በቅርብ ያደርስንላን ብለን ተስፋ እናደርጋለን
👍49🥰5😁1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አንድ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


ደሃና ሁን አባዬ

የእኛ ህይወት የተጀመረው ደስ በሚል አይነት ስለነበረ፣ በጣም ትንሽ ልጅ ሳለሁ ጀምሮ ህይወት ሁሉ እንደ አንድ ደስ የሚል ረጅም ብሩህ ቀን እንደሆነ አድርጌ አምን ነበር። የልጅነታችንን ጊዜ በተመለከተ በጣም ጥሩ
ጊዜ ነበር ከማለት በስተቀር ልለው የምችለው እምብዛም የሆነ ነገር የለም በኑሯችን ሀብታምም፣ ደሀም አልነበርንም፧ እኛ ያሉንን ነገሮች ሌሎች ካሏቸው ጋር ሳወዳድር፣ አስፈልጎን ያጣነውንም ሆነ በቅንጦት ያገኘነውን ነገር አላስታውስም:: በዚያ ላይ በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች በሚኖሩበት በእኛ አካባቢ ማንም ሰው ብዙም ሆነ ትንሽ አልነበረውም በሌላ አነጋገር፣ ተራና የተለየ ነገር ያልነበረን ልጆች ነበርን።

አባታችን በፔንሲልቫንያ፣ ግላድስተን ውስጥ በሚገኝ 12,602 ሰዎች ባሉበት
ግዙፍ የኮምፒውተር ማምረቻ ውስጥ የህዝብ ግንኙነት ሰራተኛ ሆኖ ይሰራ ነበር የአባታችን አለቃ አብዛኛውን ጊዜ ከእኛ ጋር እራት ይበላ ስለነበርና አባታችንን “ክሪስ በዚህ ማራኪ ባህርይህና በመልከ መልካም ፊትህ ማን አስተዋይ ሰው ሊቋቋምህ ይችላል?” እያለ ያደንቀው ስለነበር በአባታችን
ደስተኞች ነበርን።

በዚህ አባባሉ እኔም ከልቤ እስማማለሁ አባታችን እንከን የለሽ ነው: ዘንካታ ቁመና ያለው ሲሆን ከቁመቱ ጋርም ተመጣጣኝ ውፍረት ታድሏል። ፀጉሩ
ጥቅጥቅ ያለና ወርቃማ ነው፡ ሰማያዊ አይኖቹ ለመኖርና ለመደሰት ያለውን ትልቅ ፍቅር የሚያንፀባርቁ ናቸው። አፍንጫው ቀጥ ያለና ረጅምም አጭርም
ያልሆነ… ተመጥኖ የተሰጠው ነው። ቴኒስና ጎልፍ መጫወትና መዋኘት ይወዳል፡ ሁልጊዜ እኛን ከእናታችን ጋር ትቶን ለስራ ጉዳይ ከካሊፎርኒያ ወደ ፍሎሪዳ ወይም ወደ ሌላ ውጪ ሀገር ይሄድና በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ይመለሳል ዘወትር አርብ ከሰዓት በኋላ ወደ ቤት መጥቶ በፊት ለፊቱ በር በመግባት ደስ የሚል ትልቅ ፈገግታውን ፈገግ ሲልልን ስናይ፣ ዝናብ ቢጥልም ሆነ በረዶ ቢዘንብ ለእኛ ግን ፀሀይ ይሆንልን ነበር ሻንጣውን ወለሉ ላይ ጣል አድርጎ ሰላምታ ይጀምራል። “የሚወደኝ መጥቶ ይሳመኝ::
ይለናል።

ልክ ይህንን ሲናገር እኔና ወንድሜ ከተደበቅንበት ወንበር ወይም ሶፋ ስር እየሮጥን ወጥተን እቅፉ ውስጥ እንወድቃለን፡ እሱም አጥብቆ ያቅፈንና ጉንጮቻችንን ጥብቅ አድርጎ በመሳም ያሞቀናል። አርብ ሁልጊዜ አባታችንን መልሶ ወደ እኛ ስለሚያመጣልን ከሁሉም ቀናት የበለጠ ምርጥ ቀናችን
ነበር፡

አባታችን በመጣ ቁጥር በኪሱ ውስጥ ይዞልን የሚመጣውን ትንንሽ ስጦታዎች ከሰጠን በኋላ ሻንጣው ውስጥ ያሉትን ትልልቆቹን ስጦታዎች ለመቀበል
ደግሞ እኛ ሰላምታችንን እስክንጨርስ ድረስ በትዕግስት የምትጠብቀውን እናታችንን ሰላም ብሎ እስኪጨርስ እንጠብቃለን
እኔና ክሪስቶፈር ኪሱ ውስጥ የያዛቸውን ትንንሽ ስጦታዎች ካገኘን በኋላ፣እናታችን የአባታችንን አይኖች እንዲያበሩ የሚያደርገውን የእንኳን ደህና
መጣህ ፈገግታዋን ተላብሳ ወደ እሱ በቀስታ ስትራመድ እንመለከታታለን፡

አባታችንም እጆቹን ዘርግቶ ያቅፋትና ቢያንስ ለዓመት ያህል ያላያት በሚመስል ሁኔታ ፍዝዝ ብሎ ቁልቁል በናፍቆት ይመለከታታል።

እናታችን ዘወትር አርብ ሽቶ ባለው የመታጠቢያ ዘይት በተቀላቀለበት ውሀ ገላዋን ስትታጠብ፣ ጸጉሯን ስትሰራና ጥፍሮቿን ስታሳምር ነው ግማሹን ቀን የምታሳልፈው። እኔም እስክትጨርስ ድረስ በመልበሻ ክፍሏ ውስጥ ቁጭ ብዬ በጉጉት እጠብቃለሁ። ራሷን ከቆንጆ ሴት እጅግ ውብና እውን ወደማትመስል ሴት ስትቀይር የምታደርገውን እያንዳንዷን ነገር በጉጉት አስተውላለሁ።

የሚገርመኝ ነገር አባታችን በተፈጥሮ አስደናቂ ውበት እንዳላትና ፊቷን ምንም እንደማትቀባባ ማሰቡ ነው።

እኛ ቤት ከመጠን በላይ የሚደመጥ ቃል ቢኖር ፍቅር የሚለው ቃል ነው።
“እኔ በጣም አፈቅርሻለሁ አንቺስ ታፈቅሪኛለሽ? ናፍቄሽ ነበር? ቤት
በመምጣቴ ደስ ብሎሻል? እዚህ የሌለሁ ጊዜ ስለእኔ ታስቢ ነበር? በየምሽቱ እየተገላበጥሽ አጠገብሽ ሆኜ እንዳቅፍሽ ተመኝተሸ ነበር? እንደዚያ ካልሆነ
ካሪን… የእውነት ብሞት ይሻለኛል።” ይላታል። እናታችን ለእንደዚህ አይነት ጥያቄዎች እንዴት በአይኖቿ በለስላሳ
ሹክሹክታዋና በመሳም መመለስ እንዳለባት በትክክል ታውቅ ነበር።

በአንድ ክረምት ላይ እኔና ክሪስቶፈር ከትምህርት ቤት ወደ ቤት ተመልሰን እየተቻኮልን በፊት ለፊቱ በር ገባን፡ እናታችን ሳሎን ውስጥ ከምድጃው ፊት ለፊት ተቀምጣ ለአሻንጉሊት የሚሆን ነጭ ሹራብ እየሰፋች ነበር።
ከአሻንጉሊቶቼ ለአንዷ የሚሆን የገና ስጦታ እንደሆነ አስቤ ደስ አለኝ በተቀመጠችበት ሆና “ወደዚህ ከመግባታችሁ በፊት ጫማችሁን በሩ ጋ አውልቁና አስቀምጡት!” አለችን፡

ቦት ጫማዎቻችንና ወፍራም ኮቶቻችንን እንዲሁም ኮፍያችንን አስቀምጠን በካልሲ ብቻ በመሆን ነጭ ምንጣፍ ወደተነጠፈበት ክፍል አመራን አብዛኛውን ጊዜ ነጭ ምንጣፍ በተነጠፈበት ክፍል በሚያማምሩት ሶፋዎችና
ወንበሮች ላይ እንደልባችን ለመሆን ስለማይፈቀድልን የተዋበው የእናታችን ክፍል ለእኛ ምርጫችን አይደለም የአባታችን ክፍል ግን ጠቆር ያለ ቀለም
ያለው በመሆኑና ምንም ነገር እናበላሻለን ብለን ስለማንሳቀቅ ጠንካራው ሶፋ ላይ እንደልባችን መላፋትና መታገል ስለምንችል ክፍሉን በጣም እንወደው
ነበር።

እግሯ ስር ተቀምጬ እንዲሞቀኝ እግሮቼን ወደ እሳቱ እየዘረጋሁ “እማዬ… ሳይክሎቻችንን እየነዳን ወደ ቤት ስንመጣ ዛፎቹ ሁሉ በበረዶ ተሸፍነው ሲታዩ እንዴት ደስ እንደሚሉ ብታይ። ደሞ እማዬ ውጪውን ብታይው ተረት ተረት ላይ ያለውን ቦታ ነው የሚመስለው: ግን ብርዱ አይቻልም ያም ሆኖ ደስ ይላል እኔ በበኩሌ መቼም ቢሆን በረዶ የማይጥልበት ደቡብ አካባቢ መኖር አልፈልግም” አልኳት።

ክሪስቶፈር ሁለት ዓመት ከአምስት ወር ስለሚበልጠኝና ሁልጊዜ ከእኔ የተሻለ ብልህ መሆኑን ማሳየት ስለሚፈልግ ስለ አየር ሁኔታውና በረዶው ስለፈጠረው
ውበት ምንም አልተናገረም ልክ እንደኔ የቀዘቀዘውን እግሩን በእሳት እያሞቀ በጭንቀት ተኮሳትሮ የእናታችንን ፊት አፍጥጦ እየተመለከተ ነበር እንደዚያ አይነት ጭንቀት እንዲሰማው ያደረገው ምን አይቶ እንደሆነ ለማወቅ ፈልጌ እኔም ቀና ብዬ አየኋት᎓

“እማዬ ደህና ነሽ?” ሲል ጠየቃት።

ስስና ደስ የሚል ፈገግታ እያሳየችው “አዎ በጣም ደህና ነኝ” ብላ መለሰችለት።

“የደከመሽ ትመስይኛለሽ” አላት።

የምትሰራውን ትንሽ ሹራብ ወደጎን አስቀመጠችና የክሪስቶፈርን ፅጌረዳ
የሚመስሉ ቀዝቃዛ ጉንጮች ለመዳበስ ወደፊት ዘንበል ብላ “ዛሬ ሀኪም ቤት
ሄጄ ነበር” አለች:

“አሞሻል እንዴ እማዬ?” ሲል በድንጋጤ ጮኸ፡

በስሱ ሳቅ አለችና ጥቅጥቅ ያለውን ወርቃማ ጸጉሩን ቀጫጭንና ረጃጅም
በሆኑ ጣቶቿ እያሻሸች “ክሪስቶፈር ዶላንጋንገር፣ የሆነ ነገር ጠርጥረህ
እያሰብክ ነው አይደል? መቼም ምን ሆኜ እንደሆነ ሳትገምት አትቀርም አለችው ከዚያ እጁን ያዘችና የእኔንም አንዱን እጄን ጎትታ ሁለቱንም ሆዷ ላይ አስቀመጠቻቸው

ሚስጥራዊና ደስ የሚል አስተያየት ፊቷ ላይ እየተነበበ “የሆነ ነገር
አልተሰማችሁም?” ስትል ጠየቀችን፡
ክሪስቶፈር በፍጥነት እጁን መነጨቃት እኔ ግን ምን እንደሆነ በመጠበቅ
እጄን እዚያው ላይ ተውኩት።

“ምን ተሰማሽ ካቲ?”
👍62🥰21
በመዳፌ ስር ሆዷ ውስጥ በትንሹ የሚሰማ እንቅስቃሴ አለ እጅግ ተገርሜ
ጭንቅላቴን ቀና አድርጌ ፊቷን አየሁት ምን ያህል ተአምር ሆኖብኝ
እንደነበር ዛሬም አስታውሰዋለሁ።
“እማዬ የበላሽው ምሳ ሆድሽ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ነው” አልኳት።
ሰማያዊ አይኖቿ በሳቅ እያንፀባረቁ እንደገና እንድገምት ነገረችኝ።
ከዚያ ዜናውን ስትነግረን ድምጿ ጣፋጭ ሆኖ ነበር። “ውዶቼ፣ ግንቦት መጀመሪያ ላይ አዲስ ልጅ ይኖረኛል። በእርግጥ ዛሬ ሀኪሙ ሁለት የልብ ትርታዎች መስማቱን ነግሮኛል ይህ ማለት ልጆቹ መንታ ናቸው ማለት ነው እግዚአብሔር አያድርገውና ምናልባት ሶስትም ሊሆኑ ይችላሉ። ይህንን ዜና አባታችሁ ገና ስላልሰማ ከእኔ ቀድማችሁ እንዳትነግሩት” አለችን፡፡

በሰማሁት ነገር ደንግጬ ክሪስቶፈር ምን እንደተሰማው ለማወቅ አይኖቼን
ወደሱ ወረወርኩ። ያፈረ ግን ደግሞ የተደሰተ ይመስላል እንደገና በእሳቱ
ብርሃን የሚያበራውን የእናቴን ቆንጆ ፊት ተመለከትኩ። ከዚያ ፍንጥር ብዬ
ተነሳሁና እየሮጥኩ ወደ ክፍሌ ሄድኩ
አልጋዬ ላይ በደረቴ ተወረወርኩና ፊቴን ትራሱ ውስጥ ቀብሬ አለቀስኩ።
ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ህፃናት ሊመጡ! ህፃኗ እኔ ነኝ! የሆኑ ነጭናጫና
አልቃሻ ፍጡራን መጥተው የእኔን ቦታ እንዲወስዱ አልፈልግም ስቅስቅ
ብዬ እያለቀስኩ የሆነ ሰው መጉዳት ባልችል እንኳን የሆነ ነገር መጉዳት
ስለፈለግኩ እጆቼን ጨብጬ ትራሱን በቡጢ ቀጠቀጥኩት አልቅሼ ሲወጣልኝ
ቀና ብዬ ተቀመጥኩና ጠፍቶ ስለመሄድ ማሰብ ጀመርኩ።

እናቴ የተቆለፈው በሬ ላይ ሆኖ እየጠራችኝ ነው። "ካቲ” አለች እናቴ: “አንድ ጊዜ ገብቼ መነጋገር እንችላለን?” ስትል ጠየቀችኝ።

“ሂጂልኝ!” ስል ጮህኩ። “ልጆችሽን ገና ከአሁኑ ጠልቻቸዋለሁ።"

መካከለኛ ለሆንኩት ለእኔ በግዴለሽ ወላጆቼ ምን እንደተደገሰልኝ አውቄያለሁ።
በቃ ከዚህ በኋላ ልረሳ ነው የአርብ ስጦታዎች የሚባሉ ነገሮች አይኖሩም
አባቴም ቢሆን ከአሁን በኋላ ስለ እናቴ፣ ስለ ክሪስቶፈርና ከቦታዬ ስላስነሱኝ
የሚያስጠሉ ህፃናት ብቻ ነው የሚያስበው።

የዚያን ቀን ምሽት አባቴ ቤት እንደገባ ብዙም ሳይቆይ ወደኔ ክፍል መጣ።
ሊያየኝ ከመጣ ብዬ በሩን ከፍቼው ነበር፡ በጣም ስለምወደው ቀስ ብዬ ፊቱን
አየት አደረግኩት ያዘነ ይመስላል፡ በዛ ላይ ተለቅ ያለ ብራማ ቀለም ባለው
ካርቶን ውስጥ የታሸገ ነገር ይዟል።
“የኔ ካቲ እንዴት ናት?” ሲል በለሆሳስ ጠየቀ፡፡ በደረቴ ተኝቼ በክንዴ ስር
አጮልቄ እያየሁት ነው፡ “ቤት ስገባ ሰላም ልትይኝ ሮጠሽ አልመጣሽም !
አሁንም እዚህ ስመጣ ሰላም አላልሽኝም ሌላው ቀርቶ ቀና ብለሽ እንኳን
አላየሽኝም: ካቲ፣ እየሮጥሽ ወደ እቅፌ ስላልመጣሽና ስላልሳምሽኝ አዝኛለሁ”
ምንም አልመለስኩለትም ግን አልጋው ላይ እንዳለሁ በጀርባዬ ሆንኩና
አፈጠጥኩበት፡ እሱና እናቴ ለምን ሌሎች ልጆች ፈለጉ? ሁለት አይበቃም
ነበር? በህይወቱ ሙሉ ተወዳጅ መሆን ያለብኝ ሴት ልጁ እኔ ብቻ መሆን
እንዳለብኝ አያውቅም እንዴ?
በረጀሙ ተነፈሰ፡ ከዚያ ቀረብ ብሎ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡ “አንድ
ነገር ታውቂያለሽ? በእንደዚህ አይነት አስተያየት ስታይኝ ለመጀመሪያ ጊዜ
ነው እየሮጥሽ እቅፌ ውስጥ ያልገባሽበት የመጀመሪያ አርብ ነው: ላታምኒኝ
ትችያለሽ ግን አርብ ደርሶ ቤት እስክመጣና አንቺን እስካይሽ ድረስ ህያውነት አይሰማኝም መሸነፍ አልፈለግኩም ከአሁን በኋላ አይፈልገኝም ትልቁ ልጁ አለ አሁን ደግሞ ሌሎች አልቃሻ ልጆች እየመጡለት ነው። በመሃሉ እረሳለሁ:

“ሌላም ነገር ልንገርሸ?” ሲል ጀመረ። ...

ይቀጥላል
👍54🤩16🥰1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሁለት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

..."ሌላም ነገር ልንገርሽ?" ሲል ጀመረ።በቅርበት እየተመለከተኝ ነው፡ “አርብ አርብ ወደ ቤት ስመጣ ላንቺም ሆነ ለወንድምሽም ምንም ስጦታዎች
ባላመጣላችሁ እንኳን… ሁለታችሁም በመምጣቴ ብቻ ተደስታችሁ እንደ እብድ እየሮጣችሁ እንደምታቅፉኝና እኔን እንጂ ስጦታዎቹን እንደማታስበልጡ አምን ነበር እናታችሁና እኔ በደርዘን የሚቆጠሩ ልጆች ቢኖሩንም እንኳን ሁልጊዜም በልቤ ውስጥ ትልቅ ቦታ እንዳለሽ የምታውቂና ጥሩ አባት በመሆኔ ትወጂኛለሽ ብዬ አስብ ነበር ለካ ተሳስቻለሁ አለ: ከዚያ መናገሩን ቆም አደረገና እንደገና በረጅሙ ተነፈሰ: ሰማያዊ አይኖቹ ደፈረሱ፡ “የእኔ
ካቲ የመጀመሪያ ሴት ልጄ በመሆኗ አሁንም ለእኔ የተለየች እንደሆነች የምታውቅ ይመስለኝ ነበር :"

በተቆጣና በተጎዳ አስተያት አየሁት ከዚያ ሳግ አነቀኝ “ግን እማዬ ሌላ ሴት ልጅ ሲኖራት ለሷም ተመሳሳይ ነገር ትላታለህ” አልኩት።

“እላታለሁ?”

“አዎና” ከመቅናቴ የተነሳ ተንሰቅስቄ ጮህኩ፡ “ትንሽና ቆንጅዬ ስለምትሆን እኔን ከምትወደኝ የበለጠ ትወዳታለህ”
“በጣም ልወዳት እችላለሁ ግን hአንቺ የበለጠ አይሆንም” አለና ክንዶቹን ዘረጋ ከዚህ የበለጠ መቋቋም አልቻልኩም: ከተጋደምኩበት ብድግ ብዬ ደረቱ
ላይ ልጥፍ አልኩና አጥብቄ አቀፍኩት። እቅፉ ውስጥ እንዳለሁ ማልቀሴን እንዳቆም አባበለኝ “አታልቅሺ ካቲ… ቅናት አይሰማሽ፡ የምወድሽ በፍጹም ከእነርሱ ባነሰ አይሆንም: ደግሞ ካቲ፣ እውነተኛ ህፃናት ከአሻንጉሊቶች
የበለጠ ደስ ይላሉ ታያለሽ ትወጃቸዋለሽ፡ እናትሽ ልትይዛቸው ከምትችላቸው በላይ ልጆች ስለሚኖሯት የአንቺን እርዳታ መፈለጓ የማይቀር ነው እኔ ቤት
በማልኖርባቸው ጊዜያት እናትሽ የሁላችንንም ህይወት ቀላል የምታደርግ ውድ ልጅ እንዳለቻት ማወቄ በራሱ ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ ያደርገኛል” አለኝና
ሞቃት ከንፈሮቹ በእንባ የራሰ ጉንጬ ላይ አረፉ። “ነይ አሁን ስጦታሽን ክፈቺና ውስጡ ስላለው ነገር ምን እንደምታስቢ ንገሪኝ አለ።

ስጦታውን ከመክፈቴ በፊት አይኖቹ ውስጥ ላስቀመጥኩት ሀዘን ማካካሻ ፊቱን በሙሉ በመሳም አዳረስኩትና የበለጠ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት።
በሚያምረው ካርቶን ውስጥ ኢንግላንድ ውስጥ የተሰራ ብርማ ቀለም ያለው ቀ የሙዚቃ ሳጥን ነበረበት። ሙዚቃው ሲጫወት ሮዝ ቀለም ያለው ቀሚስ
የለበሰች አሻንጉሊት መስታወት ፊት እየተሸከረከረች ትደንሳለች።

“የሙዚቃ ሳጥን ብቻ ሳይሆን የጌጥ መያዣም ነው” አለና ካርቶኑ ውስጥ ከነበረች ማስቀመጫ ውስጥ ቀይ ፈርጥ ያለባት የወርቅ ቀለበት አውጥቶ
ጣቴ ላይ አጠለቀልኝ። “ገና ካርቶኑን ሳየው ልገዛልሽ እንደሚገባኝ አወቅኩ።እና በዚህ ቀለበት የኔዋን ካቲ ለዘለዓለም እንደምወዳት ቃል እገባለሁ" አለ።

አባታችን ህፃናቱ እስኪወለዱ ለመጠበቅ ለሁለት ሳምንት ያህል ቤት ነበር።ሁልጊዜ እናትና አባታችን ከባልና ሚስትነት ይልቅ ወንድምና እህት ይመስላሉ
ብላ የምትናገረው ጎረቤት የምትኖረው ወይዘሮ ቤርታ ሲምሰን ወጥ ቤት ውስጥ ሆና ምግብ እያዘጋጀችልን ነበር።

አራት ሰዓት አካባቢ አባታችን ወደምንመገብበት ክፍል እየተጣደፈ ገባና ለእኔና ለክሪስቶፈር እናታችንን ሆስፒታል ይዟት ሊሄድ እንደሆነ ነገረን
“አትጨነቁ፣ ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል፡ ወይዘሮ ሲምሰንን እንዳታስቸግሯት የቤት ስራዎቻችሁን ስሩ። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወንድሞች፣ እህቶች ወይም ደግሞ ወንድምና እህት ማግኘታችሁን ታውቃላችሁ።” አለን በማግስቱ ጠዋት አባታችን ከሆስፒታል ሲመለስ ፂሙን ሳይላጨው ልብሱም ተጨማድዶ በጣም የደከመው ቢመስልም በደስታ እየሳቀ “ገምቱ! ወንዶች
ወይስ ሴቶች?” አለን። “ወንዶች!” አለ ኳስ መጫወት የሚያስተምራቸው ወንድሞች የሚፈልገው ክሪስቶፈር፡ እኔም የምፈልገው ወንዶች እንዲሆኑ
ነው የአባቴን ፍቅር የሚነጥቁን ሴቶች ልጆች አልፈልግም:

“ወንድና ሴት ናቸው:: አለ አባታችን በኩራት: “እስከዛሬ አይቻቸው የማላውቃቸው አይነት የሚያማምሩ ፍጥረታት ናቸው: ራሳችሁ እንድታዩዋቸው ኑ ልብሶቻችሁን ልበሱና ልውሰዳችሁ ”

እንዳኮረፍኩ ነው አባታችን ህጻናቱ የተኙበት ክፍል ውስጥ እንዳሉ ማየት እንድችል ወደ መስኮቱ ከፍ አድርጎ ሲያቅፈኝ እንኳን ነርሷ ያቀፈቻቸውን ሁለት ሚጢጢ ህፃናት ለመመልከት እያመነታሁ ነበር በጣም ትንንሾች
ናቸው! ጭንቅላታቸው ከአፕል አይበልጥም: ትንንሽ እጆቻቸው በአየር ላይ ይወናጨፋሉ፤ አንደኛው ደግሞ ልክ በመርፌ እንደተወጋ አይነት ይጮሃል።
አባታችን ጉንጬን እየሳመና ጥብቅ አድርጎ እያቀፈኝ “እፎይ… እግዚአብሔር እንዴት መልካም ነው! ልክ እንደመጀመሪያዎቹ ልጆቼ እንከን የለሽ የሆኑ
ሌላ ወንድና ሌላ ሴት ልጅ ሰጠኝ።” አለ። ሁለቱንም እንደምጠላቸው አስቤ ነበር። በተለይ ኮሪ ተብሎ ከተሰየመ
ዝምተኛ ልጅ በአስር እጥፍ ጯሂ የሆነችውን ኬሪ ተብሎ ስም የወጣላትዐልወዳት እንደማልችል አስብ ነበር። ሁለቱ ከእኔ ክፍል ባሻገር ያለው ክፍብ ውስጥ ከሆኑ ፀጥ ያለ መኝታ የማይታሰብ ነው: ሆኖም ከፍ ብለው ፈገግ ማለት ሲጀምሩና እኔ ስመጣ ወይም ሳቅፋቸው አይኖቻቸው ላይ ያለውን ደስታ ስመለከት የቅናት ስሜቴን ሞቃትና ደስ የሚል የእናትነት ስሜት ሲተካው ታወቀኝ፡ የትምህርት ሰዓት እንዳለቀ እነሱን ለማየት፣ ከእነሱ ጋር ለመጫወት፣ የሽንት ጨርቃቸውን ለመቀየር፣ ጡጧቸውን ለመያዝና እነሱን
ለማቀፍ ወደቤት እጣደፍ ጀመር። እውነትም ለካ ከአሻንጉሊቶች የበለጠ ደስታ የሚሰጡ ናቸው።

እኔ ሁለቱንም ለመውደድ ልቤ ውስጥ ቦታ እንዳለኝ ሲገባኝ፣ ወላጆችም ልባቸው ውስጥ ቁጥራቸው ከሁለት በላይ ለሆኑ ልጆች የሚሆን በቂ ቦታ
እንዳላቸው ተረዳሁ

ትንሽ ጠየም ከሚለው ከአባታችን በስተቀር ሁላችንም ተመሳሳይ የሚያምር የቆዳ ቀለምና ወርቃማ ፀጉር ስላለን፣ የአባታችን የልብ ጓደኛ ጂም ጆንስተን
“የድሬስደን አሻንጉሊቶች” በሚል ቅጽል ስም ይጠራን ነበር እሱን የሰሙ ጎረቤቶቻችንም የሚጠሩን በዚህ ስም ነበር።

መንትዮቹ አራት አመት ሲሆናቸው ክሪስቶፈር አስራ አራት አመት ሞላው"እኔም አስራ ሁለተኛዬን ይዣለሁ። ለየት ያለው አርብ መጣ የአባታችን ሰላሳ ስድስተኛ አመት የልደት ቀን ነው: ድንገት ልናስገርመው ግብዣ አዘጋጅተናል። እናታችን ተጣጥባና ተቆነጃጅታ ተረት ተረት ላይ ያለችውን ልዕልት መስላለች የምግብ ቤቱ ጠረጴዛ በምግቦች ተሞልቶ አሸብርቋል።
ስጦታዎቹ ሁሉ ተደርድረዋል ለቅርብ ወዳጆቻችንና ለቤተሰብ ብቻ የተዘጋጀ ግብዣ ነበር፡

ሁላችንም አምሮብንና ተውበን አባታችን እስኪመጣ መጠበቅ ጀመርን፡አስራ አንድ ሰዓት አለፈ እየጠበቅነው ነው:: የአባታችን አረንጓዴ ካዲላክ መኪና ግን እስካሁን አልመጣም: እናታችን በጭንቀት ክፍሉ ውስጥ
እየተንጎራደደች ነው: የተጠሩት እንግዶች እያወሩ ነው አባታችን በተለምዶ አስር ሰዓት ላይ ይመጣ ነበር፡ አረ እንዲያውም አንዳንዴ ከዚያም ሁሉ ቀደም ይላል። ዛሬ ግን ያለወትሮው በጣም ዘግይቷል።

አንድ ሰዓት ሆነ፤ አባታችን እስካሁን ብቅ አላለም።

እናታችን ረጅም ሰዓት ወስዶባት ያዘጋጀቻቸው ምግቦች ማሞቂያው ውስጥ ብዙ በመቆየታቸው ምክንያት ደረቁ አንድ ሰዓት የመንትዮቹ የመኝታ ሰዓት በመሆኑ እንቅልፋችው መጥቶ እንኳን ሳያዩት ላለመተኛት አስር ጊዜ “አባባ የሚመጣው መቼ ነው?” እያሉ መጠየቅ ጀምረዋል።

እናታችን ወዲያ ወዲህ እየተመላለሰች ደጋግማ በሰፊው መስኮት ወደ ውጪ
ትመለከታለች።

ድንገት የሆነ መኪና ወደ እኛ ግቢ ሲታጠፍ ተመለከትኩና “አባታችን መጣ!” ብዬ ጮህኩ።
👍591
በራፋችን ላይ መጥቶ የቆመው ግን የአባታችን አረንጓዴ ካዲላክ ሳይሆን ፖሊስ የሚል የተጻፈበት ነጭ መኪና ነበር።

ሁለት የደንብ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች ወደ በሩ ቀርበው የበሩን ደወል ሲጫኑ እናታችን በድንጋጤ ደርቃ ቀረች። እጇን አንገቷ ላይ አድርጋ፣ የደነዘዘች መስላና አይኖቿ ጠቁረው ስመለከታት ልቤ ውስጥ የሆነ የሚስፈራ ነገር
ሲራወጥ ተሰማኝ።

በሩን የከፈተው የአባታችን ጓደኛ ጂም ጆንስተን ነበር።በእድሜ ጠና ያለው ፖሊስ እይታውን ከአንደኛዋ ሴት ወደ ሌላኛዋ እያንከራተተ “ወይዘሮ ክሪስቶፈር ዶላንጋንገር?” ሲል ጠየቀ
እናታችን በዝግታ ጭንቅላቷን ነቀነቀች። ወደሷ ጠጋ አልኩ፤ ከሪስቶፈርም እንደዚያው አደረገ፡ መንትዮቹ ግን የፖሊሶቹ መምጣት ምንም ግድ ሳይሰጣቸው ወለሉ ላይ ተቀምጠው በትናንሽ መኪኖቻቸው እየተጫወቱ ነው
ሌላኛው ፖሊስ ወደ እናታችን ጠጋ አለና “ወይዘሮ ዶላንጋንገር፣ በጣም እናዝናለን፡ በግሪንፊልድ አውራጎዳና ላይ አደጋ ደርሶ ነበር አደጋው ውስጥ ባለቤትሽም ነበረበት” አለ

ከእናታችን የታፈነ ጉሮሮ ድንገተኛ ሳግ ተሰምቶ ተንገዳገደች: እኔና ክሪስ አጠገቧ ሆነን ባንደግፋት ኖሮ ትወድቅ ነበር።

“አደጋውን በተመለከተ የአይን ምስክር አነጋግረን ነበር፤ የባለቤትሽ ጥፋት አልነበረም::” ሲል ያለምንም ስሜት ቀጠለ፡፡ “እንደ መረጃው ከሆነ ሰማያዊ
ፎርድ መኪና ይነዳ የነበረ የሰከረ ሰው የባለቤትሽን መኪና ለመግጨት እየተጠጋ ነበር። ባለቤትሽ አደጋ እየመጣ መሆኑን በማወቁ ላለመጋጨት
መንገዱን ሲለቅ ሌላ መኪና ላይ የነበረ ማሽን መኪናው ላይ ወደቀበትና የባለቤትሽ መኪና ተገለባበጠ፡ ያም ሆኖ ሊተርፍ ይችል ነበር. ነገር ግን እየመጣ ያለ ሌላ የጭነት መኪና መቆም ባለመቻሉ የባለቤትሽን መኪና
በሃይል ሲገጨው የባለቤትሽ መኪና እንደገና ተገለባበጠና ... በእሳት ተያያዘ

"የኔ ባለቤት?” እናታችን በሹክሹክታ ተናገረች: ድምጿ በጣም የደከመና ለመስማት የሚያስቸግር ነበር፡ “አልሞተም… አይ…ሞትም” አለች:

“እመቤቴ፣” አለ ፖሊሱ በፊኛዎችና በመብራት የደመቀውን ክፍል እየተመለከተ። “በዚህ ልዩ በሚመስል ቀን እንደዚህ አይነት መጥፎ ዜና ይዤ
በመምጣቴ ይቅርታ: አዝናለሁ እመቤቴ ሁሉም ሰው እሱን ለማትረፍ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል: ግን ዶክተሩ እንደነገረን ህይወቱ ያለፈው ወዲያውኑ ነበር”

ሶፋ ላይ ከተቀመጡት መሀል የሆነ ሰው ጩኸቱን አቀለጠው
እናታችን አልጮኸችም: አይኗ ላይ ግን ከባድ ሀዘን ይታያል። ፊቷ ላይ
የነበረው የሚያምር ቀለም የሞት ጭንብል መሰለ ይህ ሁሉ ነገር እውነት ሊሆን እንደማይችል በአይኖቼ ልነግራት በመሞhር አይነት ቀና ብዬ አተኩሬ
ተመለከትኳት።

አባቴ አይሆንም! የእኔ አባት አይሆንም! እሱ ሊሞት አይችልም... ሊሆን አይችልም! የሚሞቱት ያረጁና የታመሙ ሰዎች እንጂ የሚፈለግ፣ የሚወደድና ወጣት የሆነ ሰው አይደለም።

ሆኖም እናቴ ፊቷ ገርጥቶ፣ አይኗ ፈዞና እጆቿ እርጥብ መሀረብ እያፍተለተሉ ቆማለች፡ በምመለከታት በእያንዳንዱ ሰከንድ አይኖቿ ወደ ውስጥ እየጎደጎዱ የሚሄዱ ይመስሉ ነበር።

ማልቀስ ጀመርኩ። ፖሊሱ “እመቤት፣ በመጀመሪያው ግጭት ወቅት ከመኪናው ውስጥ የወደቁ
የተወሰኑ እቃዎቹን አግኝተናል: ለማትረፍ የቻልነውን ያህልም ሞከረናል አለ።

“ሂድ ከዚህ! ውጣ! የኔ አባት አልሞተም: እሱ አልሞተም! መንገድ ላይ አይስክሬም ለመግዛት ቆሞ ነው አውቃለሁ በየትኛውም ደቂቃ ይመጣል!
ውጣ ከዚህ!” እያልኩ ፖሊሱ ላይ ጮህኩበት: ፖሊሱን ለመምታት ወደፊት ተንደረድሬ ያዝኩት ሊያላቅቀኝ እየሞከረ ሳለ ክሪስቶፈር መጣና ጎትቶ
ወሰደኝ።

“እባካችሁ አንዳችሁ ይህችን ልጅ እርዷት” አለ።

የእናቴ እጆች ትከሻዬን ይዘው ወደ እሷ አስጠጉኝ፡ ቤት ውስጥ ያሉት ሰዎች በደነገጠ ድምፅና በሹክሹክታ ያልጎመጉማሉ። በሞቀው መጋገሪያ ውስጥ
የነበረው ምግብ ተቃጥሎ መሽተት ጀመረ።

የሆነ ሰው መጥቶ እጄን ይዞኝ እግዚአብሔር እንደ አባቴ ያለ ሰው ህይወት በጭራሽ እንደማይወስድ እንዲነግረኝ ጠበቅኩ። ግን ማንም አልመጣም።

ክሪስቶፈር ብቻ እጁን ወገቤ ላይ አደረገ፡ ሶስታችንም ተቃቀፍን-ዘ እኔ፣ እናቴና ክሪስቶፈር።

በመጨረሻ እንግዳ በሆነ ሻካራ ድምፅ መናገር የመጀረው ክሪስቶፈር ነበር።
“አባታችን ለመሆኑ እርግጠኞች ናችሁ? በእሳት የተያያዘው አረንጓዴ ካዲላክ ።መኪና ውስጥ የነበረው ሰው የደረሰበት ከባድ ቃጠሎ ከነበረ ማንነቱን እንዴት
ታውቃላችሁ? የእኛ አባት አይሆንም ምናልባት ሌላ ሰው ሊሆን ይችላል አለ።

እናታችን ከአይኖቿ እምባ ባይወርድም ከጉሮሮዋ ውስጥ የተቆራረጠ ጥልቅ መንሰቅሰቅ ይሰማ ነበር አምናለች እነዚያ ሁለት ሰዎች እውነቱን እየተናገሩ
እንደሚሆን አምናለች!
ልደት ለማክበር ዘንጠው የመጡት እንግዶች ሁሉ አሁን በዙሪያችን ተሰብስበው ለተፈጠረው ነገር ማጽናኛ የሚሉትን ቃል እየነገሩን ነው።

“በጣም እናዝናለን ኮሪን፣ እውነት በጣም አስደንጋጭ ...አሳዛኝ ... "

“ምስኪን ክሪስ ... ምን አይነት ከባድ መከራ ደረሰበት”

“ቀናችን የተቆጠረ ነው
ሁልጊዜም እንዲህ ነው፣ ከተወለድንበት ጊዜ ጀምሮ ቀናችን የተቆጠረ ነው።"

ቀጠለ ቀጠለ እናም ልክ ውሀ ኮንክሪት ውስጥ እንደሚሰርግ አይነት ነገሩ በውስጣችን በቀስታ ሰረገ: አባታችን ሞቷል። ከዚያ በኋላ መቼም በህይወት
አናየውም ልናየው የምንችለው በሳጥን ውስጥ ሆኖ ከዚያ መሬት ውስጥ ሲገባና ስሙ፣ የተወለደበትና የሞተበት ቀን የተፃፈበት ድንጋይ ላይ ነው።
እኔ እንደተሰማኝ ሊሰማቸው የማይገባ ስለሆነ መንትዮቹ እንዴት እንደሆኑ ለማወቅ ዞሬ ተመለከትኩ።

ይቀጥላል
👍31😢174🎉1
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ ..."ሌላም ነገር ልንገርሽ?" ሲል ጀመረ።በቅርበት እየተመለከተኝ ነው፡ “አርብ አርብ ወደ ቤት ስመጣ ላንቺም ሆነ ለወንድምሽም ምንም ስጦታዎች ባላመጣላችሁ እንኳን… ሁለታችሁም በመምጣቴ ብቻ ተደስታችሁ እንደ እብድ እየሮጣችሁ እንደምታቅፉኝና እኔን እንጂ ስጦታዎቹን እንደማታስበልጡ አምን ነበር እናታችሁና እኔ በደርዘን የሚቆጠሩ…»
#ሳቤላ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...«ደኅና እኔ እጠራታለሁ » አለና ሚስተር ካርላይል በዚያ ግጥም ብሎ በሞላው ሕዝብ መኻል ዐልፎ ሔደ " በዚያ ሰዓት አንዲቷ የለንደን ተጫዋች አሳዛኝ
ዘፈን ስትዘፍን ስለነበር ተመልካቹ ሁሉም ሚስተር ካርላይልን በክፉ ዐይን ዐየው የሰውን መከፋት ችላ ብሎ አለፈና ከሳቤላ ፊት ቆመ።

"እኔ ደሞ ዛሬ ማታ ወደኔ ትመጣለህ ብዬ አላሰብኰም - በጣም ግሩም ዝግጅት አይዶለም ? እኔን መቸም እንዴት አስደሰተኝ መሰለህ » አለችው .

« እዎን በጣም ደስ የሚል ነው » አላት ፊቱን ጥቁርቁር እያደረገ
« አሁን ግን ስቤላ ( ሎርድ ማውንት እስቨርን እምብዛም ደኅንነት የተሰማቸው አልመሰለኝም " ስለዚህ ሠረገላውን ልከውልሻል »

« ምን ! አባባ ደኅና አይዶለም !! » አለች ከመናገሩ ቀጠል አድርጋ።

«ሳያማቸው አልቀረም ግን እስከዚሀም አይመስለኝም " ሆኖም ወደቤት እንድትመጭ ይፈልጉሻል : እየመራሁ ላሳልፍሽ ? »

«አየ አባባ ... ሁልጊዜ እንዳሰበልኝ አሁንኮ እንዳይሰለቸኝ ስለሠጋ ቀደም ብሎ ሊያላቅቀኝ ፈልጎ ነው " አመሰግናለሁ ... ሚስተር ካርላይል " እስከ ዝግጅቱ መጨረሻ እቆያለሁ »

« የለም የለም ሳቤላ ... እሱማ ስለ ባሰባቸው ነው የላኩብሽ» መልኳ ልውጥ ግንባሯ ቁጥር አለ ግን አልደነገጠችም « እሺ ጥሩ አሁን አዳራሹን አንዳንረብሽ ይህ የተጀመረው ዘፈን ያብቃና እወጣለሁ »

« ጊዜ ባታባክኝ ይሻላል ስለ አዳራሹና ስለ ሕዝቡ ምንም አታስቢ»

ወዲያው ተነሥታ ክንዷን ከሚስተር ካርላይል ክንድ ጣል አደረገች » እሱም ነገሩን ለሚስዝ ዲሊ ገጸላትና ሳቤላን እየመራ ይዟት ወጣ ተመልካቹ በግድ
በመጨነቅ መንገድ እየሰጠ አሳለፋቸው " ብዙ ሕዝብም በዐይኑ ተከተላቸው ከሁሉ የበለጠ የተቅበጠበጠችውና ለማወቅ የጓጓችው ግን ባርባራ ነበረች "
የት ሊወስዳት ነው ? » አለች ሳታስበው
« እኔ ምን ዐውቃለሁ ? » አለቻት ኮርነሊያ « ባርባራ ... ዛሬ ማታ መቁነጥነጥ አበዛሽሳ? ምን ነካሽ? ሰዎችወደዚህ የሚመጡት እኮ ሊያዳምጡ ሊመለከቱ
እንጂ እንደዚህ ሊቅበጠበጡ አይደለም »

የሳቤላ ካባ ከተቀለበት ወርዶ ተደረበላትና ደረጃውን ከሚስተር ካርላይል ጋር ወረደች " ሠረገላው እስከ በሩ ተጠጋላት ። ሠረገላ ነጂው መንገድ ለመጀመር
ልጓሙን ሳብ አድርጎ ተዘጋጅቶ ጠበቃት አንድ ሌላ አሽከር እመቤቲቱን ገና ሲያያት የሠረገላውን በር ከፈተላት ሰውየው ገና ሥነ ሥርዓት ያልተማረ አዲስ ገብ ገጠሬ ብጤ ነበር " ክንዷን ከሚስተር ካርላይል ክንድ አስለቅቃ ወዶ ሠረገላው ልትገባ ስትል ሰውየውን እያየች ትንሽ ቆም አለችና « አባባ በጣም አሞታል እንዴ ? » አለችው "

« አዎን እመቤቴ ሲያቃስቱ ለሰማቸው ያሳዝናሉ " አዩ አንጀት ሲበሉ ! ሰዎችማ ምናልባት ዛሬን ቢያድሩ ነው እንጂ አይተርፉም ይላሉ » አላት።

ምርር ብላ ጮኸችና ከመደንገጧ የተነሣ ልትወድቅ ስትል የካርላይልን ክንድ ግጥም አድርጋ በመያዝ ተረፈች ሚስተር ካርላይል ሰውየውን በቁጣ ገፈተረው ።ከዚያ ድንጋይ ንጥፍ መሬት ላይ በቁመቱ ቢዘርረውም አይረካም ነበር " በጣም
ተናድዶበታል "

«ምነው ሚስተር ካርላይል ለምን አልነገርከኝም ? » አለችው እየተንቀጠቀጠች "

« እኔስ አሁን በመናገርሽም በጣም አዝኛለሁ አሁንም አትደንግጪ ! ሁል ጊዜም እንዴት እንደሚነሣባቸው ታውቂያለሽ " የተለመደው በሽታ ተነሣባቸው
እንጂ ሌላ ምን ይሆናሉ ብለሽ ነው » በይ ይልቅ አሁን ግቢና እንሒድ ምንም ክፉ ነገር እንደማይጠብቀን አምናለሁ»

« አንተም አብረኸኝ ልትመጣ ነው ? »

«አዎን ብቻሽን እንዴት እሰድሻለሁ?» አላት እንዲቀመጥ ፈቀቅ አለችለት "

« ግድ የለም ተይው እኔ ከውጭ እቀመጣለሁ » አላትና በሩ ከተዘጋ በኋላ ከነጂው ጐን ተቀመጠ አሽከሮቼ ከኋላ ተቀመጡ " ሠረገላው ገሠገሠ " ሳቤላ
ከአንድ ጥግ ሽብልል ብላ ተቀምጣ ትንሠቀሠቅ ጀመር "

« ለፈረሶቹ አትዘንላቸው ቶሎ ቶሎ ንዳ አለበለዚያ ሳቤላ በሐሳብ ብቻ ትታመማለች » አለ ሚስተር ካርላይል

« ምስኪን ልጅ መከራዋ አላለቀላትም " ሌሊቱ ከመንጋቱ በፊት ከዚህ የከፋ ነገር ይጠብቃታል " እኔ ከዚህ ቤት ዐሥራ አምስት ዓመቴ ነው ። እሷን ገና ሕፃን ሳለች ጀምሬ ነው የማውቃት »

« ግን ኧርሉን በጣም የሚያሠጋቸው ነው ? »

« አዎን በጣም ታመዋል ሚስተር ዌይን ራይት በሽታው ወደ ልባቸው ተሸጋግሯል ሲሉ ሰምቻለሁ »
« ወትሮምኮ በሺታው ሲነሣባቸው እንዶዚህ ኃይለኛ ነው »

« ዐውቃለሁ የዛሬው ግን የተለየ ነው » ከዚህ ሌላ ዶግሞ » አለ ሠረግላ ነጅው በምስጢር አነጋገር « የሌሊት ወፎቹም በከንቱ አይዶለም የመጡት »

« የሌሊት ወፎቹ ? » አለ ሚስተር ካርላይል "

« አዎን " የነሱ መምጣት ሞት ሰተት ብሎ ወዶቤት መግባት መሆኑን የማያወላውል ምልክት ነው»
« ስለ ምንድን ነው የምታወራው ሚስተር ዌልስ?» አለው ሚስተር ካርላይል
« ዛሬ ቤቱን የሌሊት ወፎች ሲዞሩት አመሹ የት አባታቸው አስቀያሚዎች ናቸው " እኔማ አልወዳቸውም "

« የሌሊት ወፎች ኮ ሌሊት የትም መብረር ይወዳሉ ተፈጥሯአቸው ነው . . .

« ተፈጥሮአቸው ቢሆንም በመንጋ ሁነው እየበረሩ በመስኮት አይገቡም ዛሩ ማታ እመቤቴን ከሙዚቃው ትርዒት አድርሼ ተመለስኩ " ከዚያ ሚስዝ ሜሰን
እንደምትፈልገኝ ነገሩኝና እሷ ወደ ነበረችበት ወደ ቤተ መጻሕፍቱ ስገባ ከተከፈተው መስኮት ቁማ አገኘኋት » ብርድ ስለነበር ለምን መስኮት ከፍታ እንደ ቆመች ጠየቅኳት እሷም ቀረብ ብዬ
እንድመለከት ጠራችኝ እኔም ወደ መስኳቱ ጠጋ ብዬ ብመለከት
ብመለከት በሕይወቴ አይቸው የማላውቀው ጉድ አየሁ" በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የሌሊት ወፎች ዳመና መስለው ክንፎቻቸውን እያማቱ መጡብን ወደ ኋላችን ሸሸት ባንል ኖሮ ፊታችንን ይመቱን ነበር " ከየት እንደ ተጠራቀሙ አላውቅም ከአንድ ደቂቃ በፊት ከደጅ ሳለሁ ለምልክት እንኳን አልነበሩም "

እነዚህ የለሊት ወፎች ምን ነካችው ይህን የሚያህል ክምችት ባንድ ላይ ሆነው አይተህ ታውቃለህ ... ዌልስ ? አለችኝ ሚስዝ ሜሰን “ እኔም ኧረ የለም ደግሞ እንደዚህ ከሰው ሲጠጉም አይቸ አላውቅም እንደዚህ ሆነው ባያቸውም ደስ አይለኝም " ገዱ ደግ አይደለም የክፉ ነገር ምልክት ነው አልኳት ለካስ እሷም በምልክቶችና በሕልመች ከሚስቁት አንዷ ሆናለች በሳቅ ልትፈርስ
እርሶዎም እንደሚያውቁት እሷ እመቤት ሳቤላን ከድሮ ጀምራ ስታስተምር የኖረች ናት እነዚህ የተማሩ ሰዎች በምልክት በሕልም በቀላሉ አያምኑም »

ሚስተር ካርላይል አንገቱን ነቀነቀ

« እንዶዚህ በብዛት መምጣታቸው የምን ምልክት ነው ትላለሀ ... ዌልስ አለችኝ ሚስዝ ሚዞን እያሾፈችብኝ „ “ እኔ እንደዚህ ግጥም ብለው በብዛት ሲመጡ
አይቻለሁ አላልኩም ግን የሌሊት ወፎች እንደዚህ በብዛት ሆነው ወደ ቤት ሲገቡ ብዙ ጊዜ መታየታቸውንና ከገቡበት ቤትም ሰው እንደሚሞት የማያብል
የታወቀ ምልክት መሆኑን ሲነገር ሰምቻለሁ ' አልኳት “ ኧረ ሞትስ በዚህ ቤት አይምጣ” እያለች መስኮቱን ዘጋችው የጌቶች ነገር በሐሳቧ መጣባት መስኮቱ እንደ
ተዘጋ እነዚያ አስቀያሚ ፍጡሮች መስኮቱን በክንፋቸው ይጠፈጥፉት ጀመር ከዚያ ሚስዝ ሜሰን ለአንድ ሦስት ደቂቃ ያህል ስለሌላ ጉዳይ ስታነጋግረኝ ቆየችና ስታበቃ ወደ መስኮቱ ዞር ብዬ ብመለከት አንድም የሌሊት ወፍ አልነበረም“

« ደግሞ ካንዱ ቤት መስኮት ክንፎቻቸውን ሊያርገበግቡ ሔደው ይሆናላ» አለ ሚስተር ካርላይል በነግሩ ባለማመን ።
👍27
« ከዚያ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ቤቱ ተበጠበጠ ጌቶች በጣረ ሞት መያዛቸው ተሰማ " በሽታው ከሆዳቸው መግባቱን ወደ
ልባቸውም ሊሸጋገር ይችላል ብሎ ሚስተር ዌይን ራይት መናሩን ወሬው በአንድ ጊዜ በመላ ቤተሰቡ ዘንድ ተዳራሰ“ ዶኔስ ሐኪሞችን ፍለጋ ወደ ሊንበራ ተላከ እኔም እመቤት ሳቤላን ለማምጣት ወደ ሙዚቃው አዳራሽ መጣሁ " »

«መቸም በሽታው ቢጠናባቸውም የሌት ወፎቹም በረው ቢመጡም መልስው በጎ እንደሚሆኑ ተስፋ አለኝ » አለ ሚስተር ካርላይል "
ሠረገላ ነጂው ( ራሱን በአሉታ ነቀነቀና ፈረሶቹን ገረፋቸው እየጋለቡ መጥተው በሩን ዐልፈው ከቤት ደረሱ "

የቤቱ ጠባቂ የሆነችው ሚስዝ ሜዞን ከበራፉ ቁማ ስትጠብቃት ነበር " ሚስተር ካርላይል ደግፎ ከሠረገላው አወረዳት ሳቤላ ስላባቷ ለመጠየቅ ፈራች " ዝም
ለማለትም አልቻለችም " ተጨነቀች ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ « በጎ ነው ? ከክፍሉ ገብቼ ላየው እችላለሁ ? » አለች።

በርግጥ መሻል ይባል እንደሆነ እንጃ እንጂ አባቷ ነፍሱን ስለሳተ ከዚያ ሁሉ ማቃሰትና መጓጐር ዐርፎ ጸጥ ብሎ ነበር ሳቤላ ወደ እሱ ክፍል ስትግባ ካርላይል
ቤት ጠባቂዋን ወደኋላ ሳብ አደረጋት "

« የመትረፍ ተስፋ አላቸው ? » አላት "
« ምንም ተስፋ የላቸውም መሞታቸው ነው " »

ኧርሉ ማንንም አይለይም" ሥቃዩ ለጊዜው ተግ ብሎለት አልጋው ላይ ጸጥ ብሎ ተኝቶ ነበር ፊቱ ግን የሞት ጥላ ነበረበት " ሳቤላም ፊቱን አይታ ደነገጠች ቢሆንም ምንም ሳትጮህ ከመንቀጥቀጧ ጸጥ ብላ ቆች " « ቶሎ የሚሻለው ነው?»አለችው አጠገቧ ቆሞ ለነበረው ለሚስተር ዌይንራይት

« መቸም ... ተስፋ አለመቁረጥ ነው » አለ።

« ግን ፊቱ ግርጥት ብሎ ጢስ የመሰለው ለምንድነው ? እንደዚህ ሲሆን አይቸው አላውቅም " »

« በጣም ከባድ ሥቃይ ላይ ነበሩ . . እመቤት ሥቃይ ደግሞ ምልክቱን መልክ ላይ ይተዋል »

ሚስተር ካርላይልም ገብቶ ከሐኪሙ ጐን ቆመና እሱም የኧርሎን ፊት አይቶ ደነገጠ ሐኪሙን ለብቻው ሊያነጋግረው ፈልጎ በእጁ ነካ አድርጐት ሲወጣ ሳቤላ ደግሞ ካርላይልን ሲወጣ አይታ በእጅዋ ጠቀሰችው "

« ወጥተህ እንዳትሔድ . . . ሚስተር ካርላይል ሲነቃ ካጠገቡ ያየህ እንደሆነ ደስ ይለዋል አባባ አንተን ሲወድህ ለብቻው ነው " »

« የለም አልሔድም " የመሔድ አሳብም የለኝም " »

ከሊንበራ ሦስት ሐኪሞች ደረሱ - እነሱ ሲገቡ ኧርሎ ጣሩ እንደና ተነሥቶበት ከምትተናነቀው ነፍሱ ጋር ሲጠራሞት በበዓል ልብስና በሚያንጸባርቁ ጌጦች ያሸበረቀችው ቆንጆ ከጐኑ ቆማ ስትመለከተው አገኛት » ከአንድ ድግስ ላይ በድንገት ተጠርታ እንደ መጣች እነሱም ገምተው ነበር "
ሐኪሞቹ ቀረብ ብለው አዩት ትርታውን አዳመጡት ልቡን ዳስሱት " ለራሳቸው እንጂ ለሌላ የማይሰሙ ቃላት ተለዋጡ " እነሱ ልብ ያላሏት ቢመስሉም እስከ መጨረሻ ያደርጉት የነበረውን ሁሉ ስትከታተል የነበረች ሳቤላ ወዶ
ነሱ ጠጋ ብላ' « የምትረዱት ነገር ይኖራል ? ይድናል ? እባካችሁ እውነቱን ንገሩኝ » አላወቃችሁኝም እኔ እኮ አንዲት ልጁ ነኝ " ማንም የሌለኝ ብቸኛ ነኝ " »

ታላቁ ለውጥ ስለታቀረበ ነፍስና ሥጋ ሲለያዩ የሚኖረውን ከባድ መወራጨትና መጠራሞት እንዳታይ ከክፍሉ ሊያስወጧት ፈለጉ " እሷ ግን ከአባቷ ትራስ
ተደፍታ ተስፋ በመቁረጥ እየተንሰቀሰቀች አልወጣም ብላ አስቸገረች "

« አንዴ መውጣት አለባት » አለ አንዱ ሐኪም ቆጣ ብሎ « ስሙ እሜቴ » አላት ወዶ ሚስዝ ሚዞን እያየ «ምነው ይህችን ልጅ ነግሮ የሚያሰማ ዘመድ ከቤት
ውስጥ የለም? »
«ማን አላት?አሁን ያለነዉ ብቻችን ነን " ከነጭራሹም የቅርብ ዘመድ የላትም የኧርሎ ሁኔታ በየደቂቃው እየከፋ መወራጨቱም አየጨመረ መምጣቭን የተመለከተው ሚስተር ካርላይል የነገሩን አሳሳቢነት ተገንዝቦ ወደሷ ጠጋ ብሎ ሁላችንም ላባትሽ ደህንነት እየተጨነቅን ነው ። ግን ካንቺ መጨነቅ ጋር ልናወዳድረው አንችልም ። ኢምንት ነው " »

«አዎን ! ኢምት ነው ! አረ እንዴት ልሁነው እናን† ! ኧረ የት ልድረስ!ልቤ ፈሰሰ » አለች

« ስለዚህ የሐኪሞችን ትአዛዝ መቀበል አለብሽ በሽተኛውን ብቻቸውን ሆነው ሊያክሟቸው ይፈልጋሉ ጊዜ ዶግሞ በከንቱ እየባከነ ነው . .

« እና የኔ መውጣት አስፈላጊ ነው?ለአባቴ ይጠቅመዋል ? »

« አስፈላጊ ነው አመቤት ፍጹም አስፈላጊ ነው » »

ምንም ቃል ሳትጨምር ቀደም ብለው የሌሊት ወፎች ሲንጋጉበት ወደ ነበረው መጻሕፍት ቤት ገባች ከመሞቂያው ምድጃ እሳቱ ይንቀለቀል ነበር " ወደዚያው
ተጠጋችና ከምድጃው ላይኛ ጠርዝ ሔዳ በእጅዋና በራሷ ተደገፈች "

« ሚስተር ካርላይል » አለችው ቀና ሳትል "
« አለሁ ምን ላድርግልሽ ? » አላት ተከትሎ መጥቶ ነበርና ።

« ይኸውልህ ወጣሁ ተመልሸ አስክገባ ድረስ ሁኔታውን ቶሎ ቶሎ ትነግረኛለህ ? »

« አምን እነግርሻለሁ » ብሏት እንደ ወጣ ደንገጡሯ ማርቨል እየሰፈፈች ገባች

« እሜቴ ልብስሽን ብትለውጭውስ ? » አለቻት "

« አይ ተይኝ... አውልቄ እንዳበቃሁ ወደ አባቴ ቢጠሩኝስ ? »

« ግን እኮ እሜቴ እንዳሁኑ በመሰለ የመከራ ሰዓት እንዶዚህ ያለ ልብስ አይለበስም »
ሚስዝ ሜሰን አልማዟን አወለቀችላትና ገና ትንቀጠቀጥ ስለ ነበር አንድ ወፍራም መደረቢያ ትከሻዋ ላይ ጣል አዶረገችላት "

ሚስተር ዌይን ራይት ሲቀር ሌሎች ሐኪሞች ሔዱ " ለሎርድ ማውንት እስቨርን አንድም ነገር ሊደረግለት አልተቻለም " ጣሩ ረጅምና አስፈሪ ሆነ " የሞት
ጣሩ ጠናበት " መጓጐሩ • ማቃሰቱ መፈራገጡ መወራጮቱ የሚስቀጥጥ ነበር "

ሊነጋጋ ሲል ሳቤላ ትዕግሥቷ አለቀ " ሚስተር ካርላይል ያባቷን እውነተኛ ሁኔታ እያለሳለሰ ቶሎ ቶሎ ይነግራት ነበር ። እሷ ግን እንዳታየው የተደሪገበት ምክንያት ሊገባት ስላልቻለ ካርላይል አስቆጥቷት ነበር ሚስተር ካርላይል ጀርባውን ለበሩ ስጥቶ ከፊቷ ቆመና'«ይቅርታ አድርጊልኝ ሳቤሳ ... አላስገባሽም » አላት
እሱም ሁኔታዋን አይቶ አንጀቱ በኀዘን እንዶ ተላወሰ በፊቱ ላይ ያስታውቅ ነበር።

አምቃ ይዛው የነበረችው ለቅሶ ጥሶ መጣ ጦሽ ብላ አለቀሰች ወደ እሳቱ ይዟት ተመለሰና አብሯት ቆመ ።

« የምወዴው አባቴኮ ነው " በዚህ ዓለም ያለኝ እሱ ብቻ ነው»

« ዐውቃለሁ ብሶትሽ ስሜትሽ ሁሉ ለኔም ይሰማኛል »

«በል እስቲ ለምን እንዳላየው ተከለከልኩ ? በቂ ምክንያት ከሰጠኸኝ እቀበላለሁ እታዛለሁ ግን አባቴ እንዳይረበሽ ነው አትበለኝ አላምንህም" ውሸት
ነው። »

« በጣም ከባድ በሆነ ጣር ላይ ነው ያሉት « አሁን ያሉበትን ሥቃይ ያንቺዐአንጀት አይችለውም " አሁን እምቢ ብለሽ ብትገቢ የምታይው አስቃቂ ሁኔታ ዘለዓለም አዲስ እንዶ ሆነብሽ ይኖራል " ስለዚህ ምክሬን ተቀ0ዪ » »

« መሞቱ ነው ? »

ሚስተር ካርላይል እመነታ " እንደ ሐኪሞቹ ገልጾ ለመናገር ቢያስብ ልቡ አልቻለም መናገር እንዴሌለበት የሚገፋፋ ከባድ ስሜት ተናነቀው "

« እንደማታታልለኝ አምንሃለሁ » አለችው "

« ወዶዚያው ናቸው ብዬ እሠጋለሁ " የሚተርፉ አይመስሎም»

ብድግ አለች » በመጣባት ድንገተኛ ፍራት ተወርውራ ክንዱን ጭምድድ አድርጋ ያዘችውና ዐውቀህ ነው ሙቷል » አለችው "

« የለም አላታለልኩሽም ሳቤላ ገና አልሞቱም » ግን ብዙ ላይቆዩ ይችላሉ »

ከሶፋው መከዳ ድፍት አለች » «አባቴ ... እስከ ዘለዓለሙ ከኔ ጋር ልንለያይ ላንተያይ ! ለዘለዓለም !

ሚስተር ካርላይል... ለአንድ ደቂቃ ልየው! ልሰናበተው
እባክህን አንድ ጊዜ ልየው»
👍24
« እስኪ ፊት እኔ ልያቸው " አንቺ ግን ከዚህ ዝም ብለሽ ቆይ ! እንዳትመጪ»ብሏት ነገሩ ተስፋ እንደሌለው እያወቀ ወጣና ወደ በሽተኛው ክፍል ገብቶ ወዲያው
ተመለሰ "

« አበቃ » አላት ለሚስዝ ሜሰን በሹክታ ከኮሪደሩ አገኛትና ሚስተር ዌይን ራይት ይፈልግሻል

« ቶሎ ተመለስክሳ ? » አለችው ሳቤላ « ልግባ ? »

ተቀመጠና እጅዋን ያዛት » «አንቺን ማጽናናት ብችል ደስ ይለኝ ነበር» አላት ጥልቅ በሆነ ስሜት ሲቃ እየተናነቀው
« ንገረኝ » አለችው እየቃተተች » «ኧረ ጉዴን ንገረኝ »

« እኔም ከመራራው መርዶ በቀር የምነግርሽ የለኝም » የተወደድሽ እመቤት ሳቤላ ... ብርታቱን ይስጥሽ » አላት "

ጢስ የመሰለው ንጋት ተመልሶ በዓለም ላይ ወግግ አለ " በሕይወት ጉዞ ላይ አዲስ ውጣ ውረድ አዲስ ሸብ ረብ ተጀመረ የዊልያም ቬን ነፍስ ግን ከዓለም ለዘለዓለም ተለየች - ወደ ሰማይ መጠቀች።"....

💫ይቀጥላል💫
👍10😱1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሶስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


....እኔ እንደተሰማኝ ሊሰማቸው የማይገባ ስለሆነ መንትዮቹ እንዴት እንደሆኑ ለማወቅ ዞሬ ተመለከትኩ።አንድ መልካም ሰው ወደ ወጥ ቤት ወስዷቸው
ከመተኛታቸው በፊት ቀለል ያለ ምግብ እያዘጋጀላቸው ነበር። አይኔ ከክሪስቶፈር አይን ጋር ተጋጨ ልክ እንደኔ በዚህ ቅዠት ውስጥ እንደተያዘ ያስታውቃል። ፊቱ የገረጣና የደነገጠ ይመስላል። አይኖቹ ሀዘን አጥልቶባቸው ጠቁረዋል።

አንደኛው ፖሊስ ወደ መኪናው ተመልሶ የታሰሩ ነገሮች ይዞ መጣና በጥንቃቄ ጠረጴዛ ላይ ዘረገፋቸው አባቴ ኪሱ ውስጥ የሚያስቀምጣቸው ነገሮች
ነበሩ እናታችን ለገና በስጦታ የሰጠችው የኪስ ቦርሳ፣ የማስታወሻ ደብተሩ፣ የእጁን ሰዓትና የጋብቻ ቀለበቱን ስመለከት በቆምኩበት ደረቅኩ። ሁሉም ነገር ጠቁሯል። በጭስና በእሳት አርሯል።

በመጨረሻ የመጡት የመኪናው የእቃ ማስቀመጫ ሲመታ ከሻንጣው ውስጥ የተበተኑት የአባቴ ልብሶችና ለኮሪና ኬሪ የተገዙላቸው ባለቀለም አሻንጉሊቶች ነበሩ። ባለ ቀይ ፊቱ ፖሊስ ሲናገር ሁሉም የተገኙት መንገዱ ላይ ተበትነው ነበር።

እነዚያን ልብሶች አውቃቸዋለሁ: እነዚያን ሸሚዞች፣ ከረባቶችና ካልሲዎች...ሁሉንም አውቃቸዋለሁ ከልብሶቹ መሀል ላለፈው ልደቱ ሰጥቼው የነበረው ከረባት ነበረበት።

“አስከሬኑ የእሱ መሆኑን የሚለይልን አንድ ሰው እንፈልጋለን፡” አለ ፖሊሱ።

አሁን በእርግጠኝነት አወቅኩ እውነት ነው: አባታችን… በራሱ የልደት ቀን እንኳን ሳይቀር ስጦታ ይዞልን የሚመጣው አባታችን ሞቷል!!

ከዚያ ክፍል ሮጬ ወጣሁ! ልቤን ከሚያደሙትና እስከዛሬ ከተሰሙኝ ህመሞች ሁሉ በከፋ ሁኔታ ካሳመሙኝ ከተዘረገፉት ዕቃዎች ሸሽቼ ሮጥኩ። ከቤት
ወጥቼ ከጀርባ ያለው የአትክልት ቦታ ሄድኩና አሮጌውን የማፕል ዛፍ በጡጫ ቀጠቀጥኩት እስኪያመኝና እጄ ደም በደም እስኪሆን ድረስ ቀጠቀጥኩት።
ከዚያ ሳሩ ላይ ዘጭ ብዬ ወድቄ አምርሬ አነባሁ በህይወት መቆየት ይገባው ስለነበረው አባቴ አለቀስኩ። ያለ እርሱ ህይወታችንን ለምንገፋው ለእኛ አነባሁ እናም ምን ያህል መልካም አባት እንደሆነና እንደነበረ የማወቅ
እድል ላላገኙት መንታ እህትና ወንድሜ አለቀስኩ። እምባዬ አልቆ አይኖቼ አብጠው ደም መስለው እየቆጠቆጡኝ ባለሁበት ቅፅበት የእግር ኮቴ ወደኔ ሲመጣ ሰማሁ። እናቴ ነበረች:

ሳሩ ላይ አጠገቤ ተቀመጠችና እጄን በእጆቿ ያዘች ሰማዩ ላይ ግማሽ ጨረቃ በሚሊየን በሚቆጠሩ ከዋክብት ታጅባ ወጥታለች አዲስ ከተወለደው ከፀደዩ ሽታ ጋር ንፋሱ ደስ የሚል ነበር። በመካከላችን የነበረው ዝምታ ማብቂያ የሌለው በሚመስል ሁኔታ ለረጅም ደቂቃዎች ቀጠለ፡ በመጨረሻ እናቴ “ካቲ አባትሽ ከላይ ከሰማይ ሆኖ እያየሽ ነው፡ ጎበዝ እንድትሆኚ እንደሚፈልግ
ታውቂያለሽ አይደል?” አለችኝ።

“አልሞተም እማዬ!” ላለማመን ፈለግኩ።

“እዚህ ቦታ ብዙ ቆይተሻል። ምናልባት አላስተዋልሽ ይሆናል እንጂ አራት ሰዓት ሆኗል። አንድ ሰው የአባትሽን አስከሬን መለየት ነበረበት ለዚህ ደግሞ
ጂም ጆንስተን እንደሚሄድ ነገሮኝ ነበር። እኔ ግን ራሴ ማየት ስፈለግኩ ሄጄ አየሁት። አየሽ እኔም ለማመን ከብዶኝ ነበር አባትሽ ሞቷል ካቲ። ክሪስቶፈር አልጋው ላይ ሆኖ እያለቀሰ ነው፡ መንትዮቹ ተኝተዋል። መሞት
ምን እንደሆነ ገና በደንብ አልገባቸውም:”

አቅፋኝ ጭንቅላቴን ትከሻዋ ላይ አሳረፈችው።

ከዚያ ተነሳችና ከእሷ ጋር እንድነሳ ክንዷን ወገቤ ላይ አድርጋ እየጎተተችኝ “ነይ… እንደዚህ አዝነሽ ብቻሽን መሆንሽ ጥሩ አይደለም: ሀዘንሽን ውስጥሽ
ከምትቀብሪው ይልቅ ሀዘንሽን ከሚጋሩሽ ሰዎች ጋር መሆን የተሻለ ነው:"

ይህንን ስትነግረኝ አንዲት ዘለላ እምባ እንኳን አይኖቿ ላይ አልነበረም ነገር ግን በውስጧ እያለቀሰችና እየጮኸች እንደሆነ ከድምጽዋና አይኖቿ ላይ
ከሚታየው ጥልቅ ሀዘን መናገር ይቻላል።

ከአባታችን ሞት ጋር ተያይዞ ቀኖቻችንን ቅዠት ያጠላባቸው ጀመር᎓ እናቴን ያለማቋረጥ አተኩሬ እያየኋት ለእንደዚህ አይነት ነገር አስቀድማ ልታዘጋጀን
ይገባ እንደነበር አሰብኩ የሆነ ነገር በሞት ማጣት ምን እንደሚመስል
እንድናውቅ የራሳችን የሆነ ውሻ ወይም ድመት እንዲኖረን ፈቅዳልን
አታውቅም ያንን ብታደርግ ኖሮ ድንገት ሲሞቱብን ሞት ምን ማለት
እንደሆነ በጥቂቱም ቢሆን ማወቅ እንችል የነበረ ይመስለኛል የሆነ ሰው፣ትልቅ ስው፣ መልከ መልካሞችም፣ ወጣቶችም፣ በጣም አስፈላጊ ሰዎችም
ሊሞቱ እንደሚችሉ ሊያስጠነቅቀን ይገባ ነበር።

ዕጣ ፋንታ በሆነ ቀዳዳ ውስጥ እየጎተታት ቀጭንና ስስ ላደረጋት እናት እንዴት እንደዚህ አይነት ነገር ሊባል ይችላል? መናገር ወይም መብላት ወይም ፀጉሯን ማበጠር ወይም ሳጥኗን የሞሉትን የሚያማምሩ ልብሶች መልበስ ለማትፈልግ ሴት እንዴት እንዲህ አይነት ነገር በግልፅ መናገር
ይቻላል? ሌላው ቀርቶ እኛ የሚያስፈልገንን ነገር እንኳ ማየት አትችልም ነበር። ደጋግ የጎረቤቶቻችን ሴቶች መጥተው የሚወስዱን መሆናቸው
ቤታቸው ያዘጋጁትን ምግብ የሚያመጡልን መሆኑ መልካም ሆኖልን ነበር ቤታችንም በአበቦችና ጎረቤቶች ሰርተው በሚያመጡት ምግብ የተሞላ ነበር።

አባታችንን የሚወዱት፣ የሚያደንቁትና የሚያከብሩት ብዙ ሰዎች ሁለ ይመጡ ስለነበር አባታችን ይህን ያህል ታዋቂ በመሆኑ ተገረምኩ። ሆኖም
የሆነ ሰው እንዴት እንደሞተ ጠይቆ ስንት ጥቅም የሌለው መሞት ያለበት ለማህበረሰቡ ሸክም የሆነ ሰው እያለ እንደሱ አይነት ወጣት መሞቱ አሳዛኝ
ነገር እንደሆነ በተናገረ ቁጥር ሞቱ ይበልጥ ያሳምመኝ ነበር።

ከሰማኋቸው ነገሮች የተነሳ ዕጣ ፋንታ የሚባለው ነገር ክፉና ለሚወደድና ለሚፈለግ ሰው እንኳን ክብር የሌለው አሰቃቂ ነገር እንደሆነ አወቅኩ።

የፀደይ ቀናት እያለፉ ወደ በጋ ተጠጋ። ምንም ያህል ለቅሶውን ለማስተናገድ ቢሞhርም ሀዘን እየደበዘዘ የሚመጣበት የራሱ መንገድ አለው። እናም
በህይወት ውስጥ በጣም ተወዳጅ የነበረ ሰው ሳይቀር የደበዘዘና ከትኩረታችን ወጣ ያለ ጥላ እየሆነ ይመጣል።

አንድ ቀን እናታችን ፈገግ ማለት እንዴት እንደሆነ የረሳች በሚመስል ሁኔታ ፊቷ ተከፍቶ ተቀምጣ ነበር ሀዘኗን ላስረሳት በመጣር “እማዬ… አባታችን
በህይወት እንዳለ ቁጠሪውና ለሌላ የስራ ጉዞ እንደሄደና እንደሚመለስ፣ ከዚያ "
በበሩ ገብቶ ልክ ድሮ እንደሚያደርገው ተጣርቶ “የሚወደኝ መጥቶ ይሳመኝ
ሲል አይታይሽም? እማዬ ለሁላችንም እንደዚህ ብናስብ ይሻለናል ሁላችንም የሆነ እኛ የማናየው ቦታ እየኖረ እንደሆነና ድንገት እንደሚመጣ መጠበቅ እንችላለን" አልኳት።

“አይሆንም ካቲ፣ እውነቱን መቀበል አለብሽ፡ በማስመሰል ውስጥ መደበቂያ መፈለግ የለብሽም ሰምተሸኛል? አባትሽ ሞቷል። ነፍሱ ወደ መንግስተሰማይ ሄዳለች እናም በአንቺ እድሜ ማንም ሰው ከሰማይ ተመልሶ እንደማይመጣ
መረዳት አለብሽ፡ እኛ ካለእሱ የምንችለውን እናደርጋለን፡ ያ ማለት ግን እውነታን ባለመጋፈጥ ማምለጥ ማለት አይደለም” አለችኝ በቁጣ።

ከዚያ ከተቀመጠችበት ወንበር ላይ ተነስታ ቁርስ ለመስራት ከማቀዝቀዣው ውስጥ የሆኑ ነገሮች ስታወጣ አየኋት።
እንደገና እንዳትቆጣኝ እየተጠነቀቅኩ “እማዬ ካለሱ የምትችይ ይመስልሻል?
አልኳት።

“በህይወት እንድንቆይ የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ” አለች ስሜት በማይሰጥ ድምፅ።

“አሁን እንደ ወይዘሮ ጆንስተን ስራ መሄድ አለብሽ ማለት ነው?”
👍345👏3👎1
“ምናልባት አዎ። ካቲ… ህይወት ብዙ አስገራሚ ነገሮች አሏት አንዳንዶቹ ደስ አይሉም፤ ዋናው ነገር ግን ለአስራ ሁለት አመታት አካባቢ ሁልጊዜ አንቺ እጅግ ልዩ እንደሆንሽ የሚያስብ አባት ስለነበረሽ የተባረክሽ ልጅ እንደሆንሽ አስታውሺ።”

ከፍሪጁ እቃ እያወጣች ዞር ብላ ተመለከተችኝ። “ካቲ ከዚህ በፊት ነግሬሽ የማላውቀውን አንድ ነገር አሁን እነግርሻለሁ። በመልክ እኔ አንቺ እድሜ ላይ እያለሁ የምመስለውን ነው የምትመስይው! በባህሪሽ ግን እኔን አትመስይም፡ አንቺ በጣም ቁጡና ቆራጥ ነሽ፤ አባትሽ እናቱን እንደምትመስይ ይናገር
ነበር። እሱም እናቱን በጣም ይወድ ነበር:”

“ሁሉም ሰው እናቱን ይወድ የለ እንዴ?”

“አይ እንድትወጃቸው ስለማይፈልጉ ልትወጃቸው የማትችይ አንዳንድ እናቶች
አሉ።” አለች በሚያስገርም አገላለጽ። ከዚያ ወደኔ ዞራ አቀፈችኝና “የምወድሽ ካቲ አንቺና አባትሽ በጣም ልዩና የቀረበ ግንኙነት ነበራችሁ: በዚያ ምክንያት ከክሪስቶፈርና ከመንትዮቹ በተለየ በጣም ናፍቀሽዋል ብዬ እገምታለሁ:”

ትከሻዋን ተደግፌ አነባሁ። እሱን ስለወሰደብኝ እግዚአብሔርን እጠላዋለሁ! እስኪያረጅ መኖር ነበረበት። እኔ ዳንሰኛ፣ ክሪስቶፈር ደግሞ ዶክተር ሲሆን እሱ አይኖርም። እሱ ስለሄደ አሁን ሁሉም ነገር ምንም ስሜት አይሰጥም ስል ተነፋረቅኩ።

“አንዳንድ ጊዜ ሞት እንደምታስቢው መጥፎ አይደለም በጭንቅላትሸ ውስጥ አባትሽ አያረጅም ሁልጊዜም ወጣት ሆኖ ይቆያል። አንቺም ሁልጊዜ
የምታስታውሺው ወጣት፣ መልከመልካምና ጠንካራ እንደሆነ ነው። ከዚህ በላይ አታልቅሺ ካቲ። አባትሽ ሁልጊዜ ይለው እንደነበረ ለሁሉም ነገር ምክንያት፣ ለሁሉም ችግር መፍትሄ አለው ከዚህ በመነሳት እኔም ጥሩ ነው
ብዬ የማስበውን ለማድረግ በጣም እየሞከርኩ ነው" አለች:

በሀዘንና በማጣት ውስጥ የተሰበሰብን አራት ልጆች ነበርን። ጓሮ ያለው አትክልት ቦታ ውስጥ እንጫወታለን፡፡ ህይወት ድንገት በአስከፊና ድንገተኛ ሁኔታ እንደሚለወጥና “ጓሮ” እና “የአትክልት ቦታ" የሚባሉት ነገሮች
አንድ ቀን ለእኛ የመንግስተ ሰማይ ስያሜ እንደሚሆኑ ባለማወቃችን ከፀሀዩዋ ብርሀን ውስጥ መፅናናትን ለማግኘት እየሞከርን ነበር።

ከአባታችን ቀብር በኋላ ባለ አንድ ከሰዓት በኋላ እኔ፣ ክሪስቶፈርና መንታዎቹ ጓሮ እየተጫወትን ነው ኮሪና ኬሪ መልካቸው የማይመሳሰል መንትዮች
ቢሆኑም ልክ እንደ አንድ ሆነው እየተጫወቱ ነው አንዳቸው በሌላኛቸ ይረካሉ አንዳቸው ለአንዳቸው እስካሉ ድረስ በቂ ነበር።

እናታችን ሳትጠራን የእራት ሰዓት አለፈ ቀስ እያለ ምግብ ከቤታችን ሊጠፋ እንደሚችል ሁሉ መፍራት ጀምረናል። ስለዚህ ለእራት ባንጠራም እንኳን የመንትዮቹን እጆች ይዘን ወደ ቤት ገባን እናታችን የአባታችን ትልቅ ጠረጴዛ
ኋላ ተቀምጣ አስቸጋሪ የሆነባት የሚመስለውን ደብዳቤ እየፃፈች አገኘናት::ኮስተር እንዳለች ለረጅም ደቂቃዎች ትፅፍና ቆም አድርጋ ጭንቅላቷን ቀና በማድረግ ባዶ ግድግዳ ላይ ታፈጣለች።

“እማዬ አስራ ሁለት ሰዓት ሊሆን ነው: መንትዮቹ እርቧቸዋል” አልኳት።

“መጣሁ… መጣሁ” አለች እናቴ ለመምጣት በተዘጋጀ አይነት። “ቨርጂኒያ ለሚኖሩት አያቶቻችሁ ደብዳቤ እየፃፍኩ ነው፡ ጎረቤቶቻችን ለሳምንት
የሚበቃ ምግብ አምጥተውልናል። አንደኛውን ወደ ማሞቂያው ማስገባት ትችያለሽ ካቲ።" አለችኝ
ማዘጋጀቱ ላይ የተሳተፍኩበት የመጀመሪያ ምግብ ነበር እናቴ ልታግዘኝ ስትመጣ ጠረጴዛው ተስተካክሎ፣ ምግቡ ሞቆና ወተቱ ተቀድቶ ነበር።

አባታችን ከሞተ ጀምሮ እናታችን ብዙ ጊዜ ደብዳቤ ትፅፋለች። በዚያ ላይ አብዝታ የምትሄድበት ቦታ ስለሚኖራት እኛን ጎረቤት ትተወን ነበር። ሲመሽ ደግሞ የአባታችን ጠረጴዛ ጋር ትቀመጥና አረንጓዴ የማስታወሻ ደብተር
አውጥታ የተከመሩ ደረሰኞች ታገላብጣለች ሁሉም ነገር ምንም ደስ የሚል ስሜት አይሰጥም: አሁን አሁን አብዛኛውን ጊዜ መንትዮቹን የምናጥበው፣
የሌሊት ልብሶቻቸውን የምናለብሰውና ወደመኝታቸው የምንወስደው እኔና ወንድሜ ነን፡ ከዚያ ክሪስቶፈር ወደ ክፍሉ ሄዶ ለማጥናት ሲጣደፍ ደግሞ እንደገና ደስታ ወደ አይኖቼ የመመለሻ መንገድ ለመፈለግ ወደ እናቴ እሄዳለሁ።

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ እናቴ ለወላጆቿ ለፃፈቻቸው ደብዳቤዎች ምላሽ መጣላት። ፖስታውን እንዳገኘች ሁላችንንም ጓሮ ከምንጫወትበት ጠራችንና
ሳሎን ሶፋ ላይ እንድንቀመጥ አደረገች። እናቴ ወፍራሙን ፖስታ ሳትከፍተው ገና ማልቀስ ጀመረች....

ይቀጥላል
👍331👎1