አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሳቤላ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


በማውንት እስቨርን ኧርል ዕረፍትና ቀብር መካከል የነበረው ጋዜ ውስጥ ሁኔታዎች ቶሎ ቶሎ ተከታተሉ " አንባቢ ከነዚህ ሁኔታዎች አንዱን ከእውነተኛ
ሕይወት ጋር የማይዛመድና መሠረት የሌለው ነገር ነው ይል ይሆናል ካለ ስሕተት ነው " ሁኔታዎቹ ደርሰው ታይተዋል "

ዊልያም ቬን ዓርብ ጥዋት ንጋት ላይ ዐረፈ " ወሬው ወዲያው ተዛመተ ትልቅ ሰው ሲሞት ምን ጊዜም ይኸው ነው የዚያኑለት ለንደን ላይ ተሰማ " ስለዚ ሟቹ በሕይወት ቢኖር ኖሮ «መንቻኮች» ይላቸው የነበሩት ብዙ ሰዎች ኢስት ሊንን ለመክበብ ቅዳሜ ማለዳ ደረሱ የጥቂት ገንዘብ ባለዕዳዎችም የብዙ ገንዘብ ባለዕዳዎችም ነበሩባቸው " ከአምስት እስከ ዐሥር ፓውንድ የሚጠይቁ ' ከአምስት እስከ አሥር ሺ የሚፈልጉም ሁሉ ነበሩባቸው አንዳንዶቹ ሰላማዊ ሰዎች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ትዕግሥት የሌላቸው አንዳንዶቹ ለፍላፊዎች ሥነ ሥርዓት
የሌላቸውና ቁጡዎች ሌሎች ደግሞ እዚያው ላይ እርምጃ ለመውሰድ አንዳንዶቹ አስከሬኑን በቁጥጥራቸው ሥር ለማድረግ የመጡ ነበሩ።

የመጨረሻው ድርጊት በዘዴ ነበር የተፈጸመው " ሁለት አፍንጫ ቈልማማ ሰዎች ከግርግሩና ከሽብሩ ሹልክ ብለው በጓሮ በር አለፉና ሲደውሉ አንዲት የማድ ቤት ሠራተኛ ከፈተችላቸው።

« የሬሳው ሳጥን ገና አልመጣም እንዴ ? » አሉ
« የሬሳ ሳጥን ? የለም ሚስተር ጆንስ ከሦስት በፊት እመጣለሁ አላለም "አሁን ገና ሁለት ሰዓት እንኳን አልሞላም » አለቻቸው።

« እሱስ አሁን ይዶርሳል እመንገድ ላይ ነው " ስለዚህ ወደ ክቡርነታቸው ክፍል አቅንተን አስከሬኑን እያዘጋጀን እንቆያለን » አሏት ሠራተኛዋ የቢት አዛዡን ጠርታ « ከቀብር አስፈጻሚው ከጆንስ ዘንድ የመጡ ሁለት ሰዎች ሳጥኑ እስኪደርስ ከላይ ወጥው ሬሳውን አሰናድተው ለመቆየት ይፈልጋሉ » አለችው ።

አዛዡም ሰዎቹን እየመራ ወስዶ አስከሬኑ ከነበረበት ክፍል ካስገባቸው በኋላ
« ይበቃሃል » አሉት አብሮ ለመግባት ሲል «እዚህ በመቆየት አናስቸግርህም » ሲሉት ምንም ሳይጠረጥር ወጣላቸው ። እነሱም ክፍሉን ዘግተው ከሬሳው ግራና
ቀኝ ተቀምጠው ሲያበቁ ጥያቄያቸው ካልተሟላ በቀር ሬሳውን እንዶማይለቁ አስ
ታወቁ ከአንድ ሰዓት በኋላ ( ሳቤላ ከክፍሏ ወጥታ ምንም ድምፅ ሳታሰማ ያባቷ ሬሳ ካረፈበት ክፍል ስትገባ ሁለት የማይታወቁና የሚቀፉ ሰዎች ባጠገቡ ተቀምጠው ስታገኛቸው ጊዜ ክው ብላ ደነገጠች "

መጀመሪያ ነገሩ ተገቢ ባይሆንም እንኳን'ለወሬ የቸኮሉና ሁኔታውን ለማየት የጓጉ የመንደር ሰዎች መስለዋት ነበር " ቢሆንም ትክክለኛውን ነገር ከነሱ አግኝታ ለማረጋገጥ ፈለገችና « እዚህ የምትፈልጉት ነገር አላችሁ ? » አለቻቸው "

« ስለ ጠየቅሺን እናመሰግናለን " እመቤት ) ደኅና ነን ምንም አትቸገሪ » አሏት " ሥራቸውም አነጋገራቸውም ፍጹም ያልተለመደና ያልተጠበቀ ሆነባት
ጨነቃት » ይህን ተናግረው ቢደነግጡም የወግ ነበር ከዚያ ገብተው ቁጭ ለማለት መብትና ሥልጣን ያገኙ ይመስል ተደላድለው እንደ ተቀመጡ ዝም አሉ።

« እዚሀ ምን አመጣችሁ ? ምን እያደረጋችሁ ነው ? » አለቻቸው።

« እንደ መሰለን አንች ልጃቸው ነሽ ብንነግርሺም ግድ የለንም » አላት
አንደኛው በግራ አውራ ጣቱ በስተኋላው ወደነበረው አስከሬን የኋሊት እያመለከተ"
« ባጠገባቸው ሌላ የቅርብ ዘመድ እንዶሌላቸው ስምተናል አሁን እኛ እዚህ የመጣነው በጣም ብዙ ዕዳ ስለ ነበረባቸው ገንዘባቸውን ያላገኙ አበዳሪዎቻቸው መሞታቸውን ሲሰሙ ሬሳውን በዕዳ መያዣ እንድናስከብር ቀጥረው ልከውን ነው » አላት

ድንጋጤና ፍርሃት በአስጨናቂው መከራዋ ላይ ተደምረው የምትለውን አስጠፋት » እንደዚያ ያለ ጉድ ሰምታ አታውቅም » ብታውቅም አታምንም ነበር "
ሬሳን በእስረኝነት መያዝ ? ምን ለማድረግ » ቁና ቁና እየተነፈሰች ከክፍሉ ወጥታ ስትወርድ ሚሲዝ ሜዞንን ከደረጃው ስታልፍ አኘቻትና በሁለት እጆቿ ጥምጥም
አድርጋ ይዛ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ራሷን መቈጣጠር አልቻለችም አስተካክላ መናገርም አልሆነላትም።

« እነዚያ ሰዎች እዚያ ! » አለች እየቃተተች "
« የምን ሰዎች ናቸው . . . የኔ እመቤት ? »
« ኧረ እኔስ እንጃ ! ኧረ እኔስ እንጃ ! ከዚያ የሚወጡም አልመሰሉኝም አባባን በዕዳ ይዘነዋል ይላሉ። የቤት ጠባቂዋም ነገሩ አስገርሟት ዝም ብላ ከቆየች በኋላ ሁኔታውን በዐይኗ ለማየት ሔደች " ሳቤላ ግን ከዚያ ለመነቃነቅ ፈራች ሰውነቷ ዛለባት ከደረጃው መደገፊያዎች ላይ ተደግፋ ብቻዋን ቀረች ሁኔታው ደስ
የማይል ሌላ ብጥብጥ በምድር ቤት በኩል ሰማች » ማንነታቸው ያልታወቁ እንዲያውም ከማያገባቸው ገብተው ነገር የሚያዳንቁ ሰዎች ከምድር ቤቱ አዳራሽ ዘልቀው ሲያማርሩ ' ሲፎክሩ ሲደነፉ ተሰማት ፍራቷ እየጨመረ መጣ " በደንብ ለማዳመጥ ትንፋሿን ያዝ አደረገች።

« ይህች ልጅ ከናንተ ፊት ብትቀርብ ጥቅማችሁ ምንድነው ? እሷ ስለ አባቷ
ጉዳዮች ምን ታውቃለች ? አሁን ለራሷ በከባድ ኀዘን ላይ እያለች በተጨማሪ ባታስጨንቋት ምናለበት ? » እያለ የቤት አዛዡ ሲያነጋግራቸው ከጆሮዋ ገባ "

« የፈለገው ይምጣ እሷን ማየት አለብኝ » ይላል አንድ ችክ ያለ ድምፅ «እዚሀ ድረስ ወርዳ አንድ ሁለት ጥያቄዎች ለመመለስ ክብሯ የሚዋረድ ከሆነ
ካለችበት ድረስ በግድ እገባለሁ " ገንዘባችን የተጭበረበረብን ምስኪኖች ከዚች ልጅ በቀር ልናነጋግረው የምንችል ማንም እንደሌለ እየተነገረን ከነሷው ደግሞ አታስቸግሯት ለምን ትሉናላችሁ ? ገንዘባችንን ለማጫረስ አባቷን ስትረዳ ግን አልተቸገረችም " እዚህ ድረስ መጥታ ልታነጋግረን ካልፈቀደች የሴት ወይዘሮ ስሜትም
ክብርም የላትም »

ስሜቷን አምቃ ይዛ ደረጃዎቹን ወረዶችና የቤቱን አዛዥ ወደሷ ጠራችው "

« ምንድነው ይህ ሁሉ ሽብር ? ማወቅ እፈልጋለሁ " »

« ተይ እመቤቴ አትሒጂ " ሥነ ሥርዓት የላቸውም ያንቺ ከመኻከላቸው መገኘት የሚያስታግሣቸው አይደሉም ። እኔ ለሚስተር ካርላይል ስለ ላክሁባቸው አሁን ይመጣሉ ስለዚህ አንቺ እነዚህ ሰዎች ሳያዩሽ ግቢ » አላት።

« ግን አባባ ከነዚህ ሁሉ ገንዘብ ወስዷል ማለት ነው? »

« አዎን ሳይወስዱ የቀሩ አይመስለኝም » አላት።

ሳቤላ ቀጥታ ወደነሱ ሔዴች ከመተላለፊያው ተበታትነው የነበሩትን 0ልፋ ብዙዎቹ ተሰብስበው ከቆሙበት ጩኸትና ጫጫታ ከበዛበት ከምግብ ቤት
ገባች " ሁሉም ሲያዩዋት ጸጥ አሉ የሚያምር የጧት ልብስ ለብሳ፡ ቆንጆው ፊቷ በተዘናፈለው ጸጉሯ ተጋርዶ ሲያዩዋት በዚያ ሁኔታቸው ከነሱ ጋር መልስ ልትለዋወጥ
ቀርቶ ጕዳዬም ሊገባት የማይችል ምንም ነግር የማታውቅ ገና ልጅ አድርገው ገመቷት " በደላቸውን የብሶታቸውን ያሀል በመዘርዘር ፋንታ ሁሉም ጸጥ አሉ።

« አንድ ሰው እኔን ለማየት እንደሚፈልግ ሲናገር ስምቸ ነበር» አለች ንግግሯ እየተቆራረጠ « ከኔ ምን ትፈልጋላችሁ? » ሁሉም ረጋ ባለ አነጋግር የየራሱን ጉዳይ ሰነዘረ ። እስኪያጥወለሡላት ድረስ በጥምና አዳመጠቻቸው " ብዙ የከፍተኛ ገንዘብ ጥያቄዎች ቀረቡ ። በተወሰነ ጊዜ
የሚመለስ የብድር ሰነዶች ባለዕዳነት መተማመኛዎች የጊዜ ገደባቸው ያለፈና ያልደረሰ ሒሳቦች ፡ በጠቅላላው ለቤት ጣጣ ለአሽከች የደንብ ልብስ ለውጭ ከትልቅ እስከ ትንሽ ይህ ነው የማይባል ብዙ ብዙ ዕዳ
አሽከሮች ደሞዝ ተዘረዘረ ።
👍21🔥1👏1😁1
ሳቤላ የምትሰጣቸው ተስፋ የምትጠይቃቸው ይቅርታ : የምትመልስላቸው አልነበራትም ዐይኖቿን ከአንዱ ወደሌላው አመልካች እያንከራተተች
በኀዘን እንደ ተሸማቀቀች ዝም አለች።

« ሰማሽ እመቤት . ... » አለ አንድ ሲያዬት ከበድ ያለ ሰው ፡ « እኛ እዚህ ድረስ መጥተንም ባላስቸገርንሽ ነበር ዕረፍታቸውን እንደ ሰማን ብዙዎቻችን
ወደ ወኪሎቻቸው ወደ ዋርበርተንና ዌር ብንሔድ ምናልት ከቤት ዕቃ ካልሆነ በቀር አንዲት ሺልንግ እንኳን እንደማናገኝ ነገሩን እኔም ቀድሞ የመጣ ቀድሞ
ያግኛል ነውና ጎህ ሲቀድ መጥቼ ዕቃውን ያዝኩ … »

« አልሰሜ ካንተ በፊት የተያዘውን» አለ በአፍንጫው ቆልማማነት የነዚያ አስከሬኑን የያዙት ሰዎች ወንድም የመስለ አንድ ስውዬ
« ግን ያስ ቢሆን ይህ ዕቃ እኛ ከምንጠይቀው ገንዘብ ጋር ብናስተያየው ከምናችን ይደርሳል ? በውነቱ አንድ ቅምጫና ውሃ ከቴምዝ ወንዝ ቢቀዳ ወይ ቢጨመር ምን ያህል ይለውጠዋል ?የኛም እንደዚሁ ነው » አለ።

« አሁን ምን ማድረግ እችላለሁ?» አለች ሳቤላ እየተንቀጠቀጠች » « ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ ? የምሰጣችሁ ገንዘብ የለኝም " እኔ . . . »

« የለም እመቤት » አለ አንድ ግርጥት ያለና የረጋ ሰውዬ
« የሚባለው እውነት ከሆነ አንቺም ከኛ የበለጠ ጉዳት ደርሶብሻል ያንገት ማስገቢያ ጣራና የኔ ነው
የምትይው አንድ ቤት እንኳን እንደሌለሽ ይነገራል »

«ሰውየው ወሮበላ ነበር » አለ አንድ የተናደደ ድምፅ« ብዙ ሺ ሕዝብ አቀለጠ።

በዚህ መኻከል ሚስተር ካርላይል ደረሰ በጭንቀት የተለዋወጠው ፊቷንና ሲንቀጠቀጡ የነበሩት እጆን ዐይቶ የመጨረሻውን ተናጋሪ አቋረጠው።

« ምንድነው ይኸ ሁሎ ? ምን ፈልጋችሁ ነው ? » አላቸው በሥልጣን አነጋገር "
«ጌታዬ . . . የሟቹ ወዳጅ ከሆንክ የምንፈልገውን ማወቅ ነበረብህ " እኛ ገንዘባችን እንዲከፈለን ብቻ ነው የምንፈልገው »

« ታድያ ወደ ዋርበርተንና ዌር ሒዱ እንጂ እዚህ ብትንጋጉ ምን ታግኛላችሁ?»
« እነሱማ ማናችንም ምንም ገንዘብ እንደማናገኝ ነግረውናል»

« እንግዲያውስ ከዚህም ምንም ስለማታገኙ ፡ አሁኑኑ ትወጡ ዘንድ በፍቅር እለምናችኋለሁ »

እነሱ ግን ጥያቄውን እንደማይቀበሉት ነገሩት "

« ይህ ቤት የሎርድ ማውንት እስቨርን ንብረት አይዶለም ። ከሸጡት ሰንብቷል ስለዚህ እናንተም የሌላ ሰው ንብረት በመድፈር ላይ ነው ያላችሁትና እምቢታችሁ ሌላ መዘዝ እንዳያመጣ ላስጠነቅቃችሁ እፈልጋለሁ »

እነሱ ግን እሱ ከሚነግራቸው የበለጠ እንደሚያውቁ በማመን የሱን ንግግር ጊዜ ያለፈበት ማታለያ በመሆኑ እንደማይቀበሉት ነገሩት "

« ስሙኝ ወንድሞቼ. . . ንብረቱ ሲመረመር በግልጽ የሚታወቀውን ነገር ለማለባበስ መሞከር የዋህነት ነው " ይህ ቤትና በውስጡ ያለውንም ንብረት ከሎርድ ማውንት ስቨርን እጅ በሕግ ወደሌላ የተዛወረው ከብዙ ወሮች በፊት ነው እሳቸው ከዚህ የሰነበቱት በባለቤቱ ፈቃድና ስምምነት እንጂ በባለቤትነታቸው
አልነበረም ። ከተጠራጠራችሁ ከወኪሎቻቸው ዘንድ ሔዳችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ »

« ማን ገዛው ? »

« የዌስት ሊኑ ካርላይል ገዝቶታል " ያም ሰው እኔ ነኝ " ኢስት ሊንን በሕግ ተዋውዬ ገዝቼ ገንዘቡን ባለፌው ሰኔ ወር ነው ጨርሽ የከፈልኩ ” እኔ ራሴ የሕግ ሰው እንደ መሆኔ መጠን ገንዘቤን ያለውል የምበትን አልምሰላችሁ " እሳቸው ከኔ ጋር ተስማምተን ጥቂት ቀኖች ሰንብተው ሊሔዱ ሲሉ በሽታቸው እየተነሣባቸው እስከዛሬ ሰነበቱ” ሰሞኑንም ለመሔድ ሲዘጋጁ ሰንብተው እነሆ ዛሬ ሊነሡ በቀጠሩበት ቀን እንደዚህ ሆኑ " አሁን ይህ ቤት ከፈረሶቹና ከሠረገላው በቀር ከነ
ዕቃው የኔ ነው »

« ወይ ማውንት እስቨርን ! እንዴት ያለው ወሮበላ ኖሯል ? »

« እሳቸው የፈለጋቸውን ዐይነት ሰው ቢሆኑም'እናንተ ልጃቸውን የማስቸገር መብት የላችሁም በተለይ በእንግሊዛዊነቱ የሚኮራ ሰው እንደዚህ ያለውን አስፈሪ
ድርጊት አይፈጽምም ነይ ሳቤላ » አላት እጅዋን ይዞ ሊያስወጣት በማሰብ "

« ጉዳዩን እኔ እከታተለዋለሁ » ሲላት አመነታች » አባቷ የሠራው በደል ተሰማትና ስሜቷን ልትገልጽላቸው ፈለገች " በአካልም በመንፈስም ተጨነቀች ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ አስቸገራት "

« በጣም አዝናለሁ » አለች በግድ እየተንተባተበችና ዕንባዋም ከቁጥጥሯ ውጭ ዝርግፍግፍ እያለ " « እኔ ይኸን ሁሉ አላውቅም አባቴ የሚሠራውን ሁሉ ነግሮኝ አያውቅም አሁን እንደምስማው ከሆነ ምንም ሀብት የለኝም " ቢኖረኝም በምችለው መጠን እያመጣጠንኩ እከፍላችሁ ነበር " አሁንም ወደፊት ንዘብ ማግኘትከቻልኩ ገንዘባችሁን አከፍላችኋለሁ »

እሷ « ሁሉ » ብላ ስትናገር አባቷ ከነበረበት ዕዳ መጠን ጋር አገናዝባ አልተረዳችውም " ሚስተር ካርላይል ከዚያ ክፍል ይዟት ወጣ " በሩን በሰዎቹ ላይ ዘጋባቸው በኋላ ዕንባዋ ገንፍሎ መጣ " ሕሊናዋን እስክትስት ድሬስ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች »

« በጣም አዝናለሁ እኔ አንደዚህ ያለ ጭቅጭቅ እንደሚደርስብሽ ባውቅ ኖሮ መቸ በቀላሉ ትገኝላቸው ነበር " አሁን ብቻሽን ወደ ፎቅ መውጣት ትችያለሽ ወይስ ሚሲሲስ ሜዞንን ልጥራት?"

« ብቻዬን እወጣለሁ ፍራትና የሆድ ብሶት እንጂ ሕወም የለብኝም ደሞም ጉዱ በዚህ አላበቃም » አለችው እየተንቀጠጠች " " ከላይ ከፎቅ ደግሞ ከአባባ ጋር ሁለት ሰዎች አሉ »

« እላይ አባባ ጋር » ሚስተር ካርይል ግራ ገባው " እሷ ከፌቱ እንደቆመች ከእግር እስከ ራሷ ስትንዘፈዘፍ አያት "

« እኔ ነገሩ ሊገባኝ አልቻለም እንዲያውም አስደነገጠኝ ካባባ አስከሬን አጠገብ ተቀምጠው በቁጥጥራቸው ሥር እንዳደረጉት ይናገራሉ "

« እነዚህን ካስወጣሁ በኋላ» አላት ወደ ምግብ ቤቴ እያመለከተ
« ወደፎቁ እመጣለሁ "

« ሁለት ወመኔዎች » አለች ሳቤላ « ከቀብር አስፈጻሚው የተላኩ በመምሰል አታለው ከገቡ በኋላ አስከሬኑን ይዘው ወርም ቢሆን ይቀመጣል እንጂ የጠየቁትን ገንዘብ እስካላገኙ ድረስ ሬሳውን እንደማይለቁና እንደማያስቀብሩት ተናግረዋል »

ሚስተር ካርላይል በመጀመሪያ ወደ ምግብ ቤት ተመልሶ እነዚያ የተበደሉና የተናደዱ ሰዎች በሟቹ ላይ ያወረዱትን የምሬትና የቁጭት ንግግር በትዕግስት አዳመጠ " ሆኖም ከነገራቸው መልስ የተለየ ተስፋ እንደማያኙ በማወቅና
እንዳላቸውም ንብረቱ በሕጋዊ መንገድ ለሌላ ተዛውሮ ከተገኘ ዕዳው ከማይመከተው ሰው ጋር መጣላት ምንም ፋይዳ እንዴሌለው በመገንዘብ አንድ ባንድ እየወጡ ሔዱ።

እነዚያ አስከሬን አጋችዎች ግን ሊወጡ አልቻሉም " ሚስተር ካርላይል አስከሬኑ ወዶ ነበረበት ክፍል ገብቶ ማንነታቸውንና በምን መብታቸው እንደዚያ ማድረግ እንደቻሉ ጠየቀ መረመረ እንደዚህ ያለ ድፍረት በሕይወቱ ዘመን አይቶ አያውቅም " ብቻ ዱሮ አንድ የቤተ ክህነት ባለሥልጣን የሆነ ሰው እንደዚሁ በከባድ ዕዳ እንደ ተዘፈቀ ሞተና አስከሬኑ ሊቀበር ቤተ ክርስቲያን እንዶ ደረሰ እንደዚሁ ባለዕዳዎች ይዘውት እንደነበር አባቱ ያጫወተውን ያስታውሳል " አሁንም እነዚህ ሰዎች የጠየቁትን ከባድ ገንዘብ ካልተከፈላቸው ሚስተር ቬን ተተኪው የማውንት እስቨርን ኧርል ከካስል ማርሊንግ እስኪደርስ ድረስ ሬሳውን መልቀቅ
እንዶማይችሉ አስታወቁ "....

💫ይቀጥላል💫
👍251😁1
Forwarded from Yared😊 buttons

📌 በሀዘን😔
በደስታ😀
💻 በስራ ቦታ
💺 የእረፍት ጊዜ ለይ

የሚደመጡ ዝማሬዎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇
👍12
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አራት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...ሳሎን ሶፋ ላይ እንድንቀመጥ አደረገች። እናቴ ወፍራሙን ፖስታ ሳትከፍተው ገና ማልቀስ ጀመረች ከዚያ በዝግታ የደብዳቤ መክፈቻ አመጣችና በሚንቀጠቀጡ እጆቿ ሦስት ወረቀቶችን ከፖስታ ውስጥ አውጥታ ደጋግማ አነበበቻቸው: እያነበበች እያለ እምባዋ የተቀባችውን ሜካፕ እያበለሻሸ ቀስ እያለ በጉንጮቿ ይወርድ ነበር።

እያየኋት ለስላሳና ማራኪ ገፅታዋ ወዲያው ወደሚያስፈራ ኮስታራነት
እየተቀየረ አፈጠጠችብን፡ ያኔም ቀዝቃዛ ብርድ ታች አከርካሪዬ ድረስ ደርሶ አንቀጠቀጠኝ ከዚያ ልክ ደብዳቤው ላይ ለተፃፈ የሆነ ጥያቄ መልስ የምትሰጥ ይመስል በሚንቀጠቀጡ እጆቿ ወደያዘቻቸው ወረቀቶች እንደገና
ደግሞ ወደ መስኮቱ ተመለከተች

እናታችን እንግዳ የሆነ ፀባይ እያሳየችን በመሆኑ ስለተደናገርን ባልተለመደ ሁኔታ ዝም አልን፡ የእናታችንን ምላስ የቆለፈና አይኖቿን ያደነደነው ባለሶስት ገፅ ደብዳቤ ሳይጨመር እንኳን አባት የሌለበት ቤታችን በበቂ ሁኔታ
አስፈራርቶን ነበር ለምን ይሆን እንደዚህ እንግዳ በሆነ አይን የምትመለከተን?

በመጨረሻ ጉሮሮዋን አፀዳችና በተለመደው ለስላሳና ሞቃት ድምፅ ሳይሆን የእሷ በማይመስል ቀዝቃዛ ድምፅ መናገር ጀመረች: “አያታችሁ በመጨረሻ
ለደብዳቤዬ መልስ ፅፋልኛለች: የፃፍኩላት እነዚያ ሁሉ ደብዳቤዎች ላይ...በቃ ተስማምታለች: ሄደን ከእሷ ጋር እንድንኖር ተስማምታለች” አለች።

መልካሙን ዜና ለመስማት ስንጠብቀው የነበረ በመሆኑ ልንደሰት ይገባን ነበር ግን አልተደሰትንም: እናታችን በድጋሚ ወደዚያ ዝምታዋ ተመለሰችና
እዚያው እንደተቀመጠች እኛ ላይ ማፍጠጥ ቀጠለች ምን ሆና ነው? የልብስ ማስጫ ገመድ ላይ የተቀመጡ ወፎች የምንመስል አራት እንግዳ ፍጥረታት
አይደለንም፧ የእሷ ልጆች እንደሆንን አታውቅም?
“ክሪስቶፈር፣ ካቲ፣ አስራ አራትና አስራ ሁለት ዓመት ዕድሜ ላይ ስለሆናችሁ የምለውን ለመረዳት፣ ለመተባበርና እናታችሁን ካለችበት ተስፋ መቁረጥ ለማውጣት በቂ እድሜ ላይ ናችሁ።” መናገሯን ቆም አድርጋ ጣቷን ጉሮሮዋ
ላይ አድረገችና በጭንቀት በከባዱ ተነፈሰች: ለማልቀስ የደረሰች ትመስላለች
ባል የሌላት ምስኪኗ እናቴ በጣም፣ እጅግ በጣም አሳዘነችኝ፡፡

“እማዬ ሁሉም መልካም ነው? አልኳት።

“አዎ ውዴ ሁሉ መልካም” ብላ ፈገግ ለማለት ሞከረች: “ነፍሱን ይማረውና አባትሽ ረጅም እድሜ እንደሚኖርና በቂ የሆነ ንብረት እንደሚያጠራቅም ያስብ ነበር፡ ገንዘብ እንዴት መስራት እንደሚቻል ከሚያውቁ ሰዎች መሀል ስለመጣ እድሜ ቢሰጠው ኖሮ ያቀደውን በትክክል እንደሚፈፅም ምንም
ጥርጣሬ አልነበረኝም ሰዎች ሁልጊዜ መጥፎ ነገሮች ሌሎች ሰዎች ላይ እንጂ እነርሱ ላይ እንደማይደርስ አድርገው የሚያምኑበት መንገድ አላቸው
አደጋዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አንገምትም። በወጣትነት መሞት እንዳለ አንጠብቅም አባታችሁና እኔ አብረን እንደምናረጅ እናስብ ነበር። በአንድ ቀን አብረን ከመሞታችን በፊትም የልጅ ልጆቻችንን እንደምናይ ተስፋ ነበረን::አንደኛችንም፣ ብቻችንን ቀርተን በሌላኛችን ሞት እናዝናለን ብለን አስበን አናውቅም ነበር።

እንደገና በጭንቀት ተነፈሰች “ከዛሬ ቀድመን እየኖርን እንደነበር መናገርh እፈልጋለሁ። ማለቴ ከወደፊታችን ላይ እንኳን ገንዘብ እንበደር ነበር፧ ከማግኘታችን በፊት እናጠፋ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ እሱን እንዳትወቅሱት: ስለ ድህነት በደንብ ያውቅ ነበር። እኔ ግን ስለ ድህነት ብዙም ስለማላውቅ
ጥፋቱ የኔ ነበር። እንዴት ያሞላቅቀኝ እንደነበር ታውቃላችሁ። ይህንን ቤት
ስንገዛ እንኳን የሚያስፈልጉን ሶስት መኝታ ክፍሎች ያሉት ቤት ነው ብሎኝ ነበር። እኔ ግን አራት ካልሆኑ አልኩት። አራትም በቂ አይመስለኝም ነበር።

“ተመልከቱ፣ ይህ ቤት የሰላሳ ዓመት የባንክ ዕዳ አለበት። ውስጡ ያሉት የትኞቹም ዕቃዎች የእኛ አይደሉም መኪኖቹም፣ ወጥቤት ያሉት ዕቃዎችም
ሆኑ የልብስ ማጠቢያው ክፍል ውስጥ ያሉት የትኞቹም ነገሮች ሙሉ ዋጋ የተከፈለባቸው አይደሉም”

ፈራን… ደነገጥን፡ ፊቷ ቀልቶ መናገሯን ቆም አደረገችና አይኖቿ የእሷ ውበት አምሳያ የሆነውን የሚያምረውን ክፍል መቃኘት ጀመሩ የሚያምሩት ቅንድቦቿ በመጓጓት አይነት ተኮሳተሩ። “አባታችሁ ተይ እንዳይለኝ ይወደኝ
ነበር ስለሚወደኝም ያሞላቅቀኝ ነበር። እኔም እንዴት ላሳምነው እንደምችል አውቅ ነበር። በመጨረሻ እነዚያ የቅንጦት ነገሮች አስፈላጊዎቻችን እየሆኑ
መጡና እጅ ሰጠ፡ ሁለታችንም ፍላጎቶቻችንን ለማሳካት መንገዶች ነበሩን።

እንግዳ በሆነ ድምጿ የምትናገረውን ከመቀጠሏ በፊት ፊቷ ከባዶ ትዝታዎቿ በአንዱ የተዋጠ መሰለ፡ “አሁን ሁሉም ውብ ነገሮቻችን ተወስደዋል። በህግ ቋንቋ ሁኔታው መውረስ ይባላል የገዛችሁትን ነገር ዋጋውን ከፍላችሁ ለመጨረስ በቂ ገንዘብ ከሌላችሁ እነሱ እንደዚያ ነው የሚደረጉት። ለምሳሌ ያንን ሶፋ ውሰዱ፤ ከሶስት ዓመት በፊት ዋጋው ስምንት መቶ ዶላር ነበር።
ሁሉንም ከፍለን የቀረን አንድ መቶ ዶላር ብቻ ነው: ግን በቃ ይወስዱታል።

ሁሉም ነገር ላይ የከፈልነውን ጭምር እናጣለን ይሄ ደግሞ ህጋዊ አሰራር ነው። የምናጣው እቃዎቹንና ቤቱን ብቻ አይደለም መኪናቹንም ጭምር ነው። ከልብሶቻችንና ከአሻንጉሊቶቻችሁ በስተቀር ሁሉንም እናጣለን ማለት
ነው። የጋብቻ ቀለበቴን እንድወሰደው ፈቅደውልኛል። እኔ ደግሞ ስንተጫጭ የሰጠኝን የአልማዝ ቀለበት ደብቄዋለሁ ስለዚህ እነሱ ለማረጋገጥ ሲመጡ
ለአንደኛቸውም እንኳን የቃልኪዳን ቀለበት እንዳለኝ እንዳትናገሩ፡"

“እነሱ” ማን እንደሆኑ ማናችንም አልጠየቅንም መጠየቅም አልመጣልኝም። ካለፈ በኋላ ደግሞ አስፈላጊ አልነበረም።

ከክሪስቶፈር ጋር ተያየን: ለመረዳት በመፈለግ ውስጥ እንዳልሰምጥ
እየታገልኩ ነበር። እውነታው ግን በትልልቅ ሰዎች የሞትና የዕዳ አለም ውስጥ እየሰመጥኩ መሆኑ ነው። ወንድሜ እጁን ዘርግቶ ያዘኝና ባልተለመደ ወንድማዊ የማረጋገጫ ምልክት ጣቶቼን ጨመቅ አደረጋቸው።

ለማንበብ ቀላል የሆንኩ የንፋስ መጥረጊያ ነኝ አንዴ ዋና አጥቂዬ የሆነው ወንድሜ እንኳን ሊያፅናናኝ የሚፈልገው? ምን ያህል ትልቅ ሰው እንደሆንኩ
ለማረጋገጥና እነሱ ሁሉንም ነገር በመውሰዳቸው ምክንያት የተሰማኝን ፍርሀትና ደካማነት ላለማሳየት ፈገግ ለማለት ሞከርኩ። የትኛዋም ትንሽ
ልጅ በእኔ ክፍል ውስጥ እንድትኖርም ሆነ እኔ አልጋ ላይ እንድትተኛና እኔ በምወዳቸው ነገሮች እንድትጫወት፣ አሻንጉሊቶቼን እንድትነካም ሆነ
በሙዚቃ ሳጥኔ እንድትጫወት አልፈልግም እነዚያንም ይወስዱብኝ ይሆን?

እናቴ የእኔንና የወንድሜን ሁኔታ በቅርበት እየተመለከተች ነበር። ከዚያ እንደገና በቀድሞው ጣፋጭ አነጋገሯ “ልባችሁ አይሰበር፤ እኔ ስነግራችሁ
እንደሚመስለው ያህል መጥፎ አይደለም: አሁንም ገና ትንንሽ ልጆች መሆናችሁን ረስቼ ሀሳብ የለሽ በመሆኔ ይቅር በሉኝ። መጥፎውን ዜና በመጀመሪያ የነገርኳችሁ ጥሩውን ወደ ኋላ አስቀርቼ ነው አሁን ትንፋሻችሁን
ያዙ! ወላጆቼ እጅግ ሀብታሞች እንደሆኑ ስነግራችሁ አታምኑኝም: መካከለኛ ኑሮ የሚኖሩ ሀብታሞች እንዳይመስሏችሁ፤ በማይታመን አይነት በጣም በጣም ሀብታሞች ናቸው! ቨርጂኒያ ውስጥ በሚገኝ ግዙፍ ቤት ውስጥ ነው የሚኖሩት። እንደዚያ አይነት ቤት ከዚህ በፊት አይታችሁ አታውቁም
የተወለድኩትና ያደግኩት እዚያ ነው ያንን ቤ ትዚህ ጋር ስታነፃፅሩት ይሄኛው እንደ ትንሽ ጎጆ ነው
👍391🥰1
እዚያ ልንኖር ነው: ከእናቴና ከአባቴ ጋር ልንኖር ነው ብዬ አልነገርኳችሁም አይደል?”
ይህንን ዜና በደካማና በአታላይ ፈገግታ አስውባ ብታቀርበውም እኔን ግን እሷ በነገረችን ነገር ከገባሁበት ጥርጣሬና ግራ መጋባት ሊያስወጣኝ አልቻለም
አይኖቿን ለማየት ስሞክር በጥፋተኝነት ስሜት እኔን ላለማየት የሚያደርጉት ሽሽት አልወደድኩትም: የሆነ ነገር የደበቀችን መስሎኛል።

ግን እናቴ ናት።

አባቴ ደግሞ ሞቷል!

ኬሪን አንስቼ ጭኔ ላይ አስቀመጥኳትና የሚሞቅ ሰውነቷን ወደእኔ አስጠግቼ
ግንባሯ ላይ ድፍት ያለውን ወርቃማ ፀጉሯን ሳም አደረግኩት። የአይኔ ቅንድቦች ተከድነዋል ከንፈሯ በመጠኑ ከፈት ብሏል። ወደ ኮሪ ስመለከት
ክሪስቶፈር ላይ ጋደም ብሏል፡ “መንትዮቹ ደክሟቸዋል፡ ራታቸውን ይፈልጋሉ፡”

“ለእራት የሚሆን በቂ ጊዜ አለን:" ስትል ትዕግስት በማጣት ተነፈሰች “እቅድ ማውጣት አለብን፡ ልብሶቻችንን ማዘጋጀት አለብን፡ ዛሬ ማታ በባቡር
መሳፈር አለብን፡ ልጆቹ እኛ ዕቃ በምናሽግበት ጊዜ ራታቸውን ሊበሉ ይችላሉ::አራታችሁም የምትለብሷቸው ልብሶች በሁለት ሻንጣዎች ውስጥ ብቻ መሆን "
አለባቸው አራት የምትመርጧቸውን ልብሶችና ልትተዋቸው የማትችሏውን ትንንሽ አሻንጉሊቶች ብቻ መያዝ አለባችሁ: ሌላ አያስፈልግም፤ እዚያ ከደረስን በኋላ እኔ ብዙ መጫወቻዎች እገዛላችኋለሁ: ካቲ፣ አንቺ መንትዮቹ በጣም ይወዷቸዋል ብለሽ የምታስቢያቸውን ጥቂት ልብሶችና አሻንጉሊቶች ምረጪላቸው: በአጠቃላይ ከአራት ሻንጣ በላይ መያዝ አንችልም። እኔ የራሴን ዕቃዎች ለመያዝ ሁለት ሻንጣዎች ያስፈልጉኛል” አለች።

የአምላክ ያለህ! እውነት ነው! ሁሉንም ነገር ትተን መሄድ ሊኖርብን ነው፡ ወንድሞቼና እህቴ በሚጋሩኝ ሁለት ሻንጣዎች ውስጥ ሁሉንም ነገር መክተት
አለብኝ፡ የምወዳት አንዷ አሻንጉሊቴ ራሷ የአንዱን ሻንጣ ግማሽ ትይዛለች።ታዲያ አባቴ ገና የሶስት ዓመት ልጅ ሳለሁ የሰጠኝን በጣም የምወዳትን ምርጥ አሻንጉሊቴን እንዴት ነው የምተዋት? ተንሰቀሰቅኩ
በደነገጠ ፊት እናታችን ላይ እንዳፈጠጥን ተቀምጠናል ለሷም ቀላል አላደረግንላትምና ከተቀመጠችበት ዘላ ተነስታ ክፍሉ ውስጥ መንጎራደድ ጀመረች:

“አስቀድሜ እንደነገርኳችሁ ወላጆቼ ሀብታሞች ናቸው" እኔንና ክሪስቶፈርን አየት አድርጋን ወዲያውኑ ፊቷን ለመደበቅ ዞረች።
“እማዬ ችግር አለ?” አለ ክሪስቶፈር።

ሁሉም ነገር የሆነ ችግር እንዳለበት ግልፅ ሆኖ ሳለ እንዲህ አይነት ጥያቄ መጠየቁ አስደነቀኝ። ስትራመድ የሚያምሩት እግሮቿ በለበሰችው ጥቁር ስስ ገዋን የፊት ለፊት ተካፋች ውስጥ ይታዩ ነበር በሀዘን ውስጥ ሆና ጥቁር ለብሳና አይኖቿ ችግር እየተንፀባረቀባቸው እንኳን በጣም ቆንጆ ነች: በጣም
ደስ የምትል ናት እና እወዳታለሁ። እንዴት እንደምወዳት!

የዚያን ጊዜ ሁላችንም እንዴት እንደምንወዳት!

“ውዶቼ… በሚያምረው በወላጆቼ ቤት ውስጥ መኖር ምን ችግር ሊኖረው ይችላል? ወደ ትምህርት ቤት ከተላኩባቸው አመታት በስተቀር የተወለድኩትና
ያደግኩት እዚያው ነው ትልቅና የሚያምር ቤት ነው፡: በዚያ ላይ በየጊዜው አዳዲስ ክፍሎች ይጨምሩበታል። ስለዚህ በቂ ክፍሎች እንደሚኖሩት የታወቀ
ነው።"

ፈገግ አለች። ነገር ግን ፈገግታዋ የሆነ ነገሩ የውሸት ይመስላል: “ግን ከአባቴ ማለትም ከአያታችሁ ጋር ከመገናኘታችሁ በፊት ልነግራችሁ የሚያስፈልግ
አንድ ትንሽ ነገር አለ” አለችና እንደገና ያንን ፈገግታዋን አሳየችን፡ “ከአመታት በፊት ገና የአስራ ስምንት ዓመት ልጅ ሳለሁ፣ አባቴ የተቃወመው እናቴም ያልደገፈችውን አንድ ከባድ ነገር አደረግኩ። ባደረግኩት ነገር ምክንያት አባቴ ከውርስ እንድሰረዝ አደረገኝ ስለዚህ አሁን ከውርስ ውጪ ነኝ።

“ሁልጊዜ ከሁሉም ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር የሚያወጣው አባታችሁ ይህንን ጉዳይ ከፀጋ መውደቅ ብሎ ይጠራውና ምንም ችግር እንደሌለው ይነግረኝ ነበር”
“ከፀጋ መውደቅ" ትርጉሙ ምንም ይሁን ምን እናቴ ምን አይነት መጥፎ ነገር ብትሰራ እንደሆነ አባቷ ሊጣላትና የሚገባትን ነገር ሁሉ ሊወስድባት የቻለው
ማሰብ አልቻልኩም።

“እሺ እማዬ ምን ማለትሽ እንደሆነ በትክክል ገብቶኛል።" አለ ክሪስቶፈር “በኑዛዜው ውስጥ ተካተትሽ የነበረ ቢሆንም፣ አባትሽ ያልፈቀደውን ነገር በማድረግሽ እሱ ደግሞ ነገሩን በደንብ ከማሰብ ይልቅ ጠበቃውን አንቺን ከውርስ ውጪ አድርጎ እንዲፅፍ ስላደረገው፣ አሁን የትኛውንም ንብረቱን አትወርሺም ማለት ነው።” ከእኔ የበለጠ የሚያውቅ በመሆኑ በራሱ በመኩራራት ፈገግ
አለ: ሁልጊዜ ስለሁሉም ነገር መልስ ነበረው። ቤት ውስጥ ካለ አፍንጫው መፅሀፍ ውስጥ ነው። ከቤት ውጪ ከጓደኞቹ ጋር ሲሆን ደግሞ አካባቢው ላይ እንደሚኖሩት እንደሌሎች እኩዮቹ ነው። ቤት ውስጥ ግን ከቴሌቪዥን የራቀ መፅሀፍ አንባቢ ነው ትልቁ ወንድሜ!

ትክክል ነበር።

“አዎ ክሪስቶፈር፣ አያታችሁ በሞተ ጊዜ ወደኔ የሚመጣ ከእኔም ወደናንተ የሚያልፍ ምንም ውርስ የለም፡ ለዚያ ነው እናቴ መልስ አልሰጥ ስትለኝ እነዚያን ሁሉ ደብዳቤዎች መፃፍ የቀጠልኩት: እንደገና ፈገግ አለች የአሁኑ ደግሞ መራራ ነበር።

“አሁን ያለሁት ወራሽ እኔ ብቻ ስለሆንኩ፣ የእሱን ስምምነት እንደማገኝ ተስፋ አለኝ አያችሁ ሁለት ወንድሞች ነበሩኝ: አሁን ግን ሁለቱም በአደጋ ምክንያት ሞተዋል፡ እና አሁን ለመውረስ የቀረሁት ብቸኛ ልጅ እኔ ነኝ: "
የመወራጨት ፍጥነቷ ቀነሰ። እጇ አፏን ለመሸፈን ከፍ አለ ጭንቅላቷን ነቀነቀችና በአዲስ በቀቀን መሳይ ድምፅ “ሌላም ነገር ብነግራችሁ የተሻለ
ነው እውነተኛ የአባታችሁ ስም ዶላንጋንገር ሳይሆን ፎክስወርዝ ነው። ፎክስወርዝ ደግሞ ቨርጂኒያ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ስም ነው።

በድንጋጤ ውስጥ እንዳለሁ “እማዬ ያንን የውሸት ስም የልደት ሰርተፊኬት ላይ ማፃፍ ህጋዊ ነው?” ስል ጠየቅኳት።

ድምጽዋ ትዕግስት አልባ ነበር። “ስለ እግዚአብሔር ካቲ ሰዎች ስማችውን በህጋዊ መንገድ መቀየር ይችላሉ'ኮ እና ዶላንጋንገር አነሰም በዛ የኛ ስም ነው: አባታችሁ ያንን ስም ከድሮ ዝርያዎቹ ተውሶት ነው አስቂኝ የቀልድ ስም እንደሆነ ያስብ ነበር። እናም በበቂ ሁኔታ ተገልግሎበታል።"

“በምን ዓይነት በቂ ሁኔታ? ለምንድነው አባዬ ፎክስወርዝ የሚለውን ለመፃፍ ቀላል የሆነ ስሙን በህጋዊ መንገድ ዶላንጋንገር ወደሚል ረጅምና አስቸጋሪ ስም የለወጠው?” ብዬ ጠየቅኩ።

“ካቲ ደክሞኛል” አለችና አጠገቧ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጠች። “ገና የምሰራው ብዙ ነገር አለ፤ ብዙ የህግ ዝርዝሮች አሉ። ሁሉንም ነገር በቅርቡ ስለምናውቅ
እነግራችኋለሁ: እውነቱን ብቻ እንደምነግራችሁ እምላለሁ። ግን እባካችሁ " አሁን ትንፋሼን ልሰብስብ:” አለች።

ምን አይነት ቀን ነው: መጀመሪያ ሚስጥራዊዎቹ “እነሱ” መጥተው ሁሉንም ነገራችንን ቤታችንን ሳይቀር እንደሚወስዱብን ሰማን ከዚያ ደሞ የአባታችን
ስም እንኳን ሳይቀር የእኛ እንዳልሆነ አወቅን።
መንትዮቹ በጭኖቻችን ላይ ጋደም ብለው እያንቀላፉ ነው: የሆነውን ሁሉ ለመረዳት ገና ትንንሾች ናቸው። እኔም የአስራ ሁለት ዓመት ትልቅ ሴት ሆኜ እንኳን እናቴ ለአስራ አምስት ዓመታት አይታቸው የማታውቃቸውን
ወላጆቿን እንደገና የማየቷ ነገር ለምን እንዳላስደሰታት መረዳት አልቻልኩም። ሚስጥራዊ አያቶቻችንን እስከ አባታችን ቀብር ማለፍ ድረስ እንደሞቱ
እያሰብን ነበር። በአደጋ የሞቱ ሁለት አጎቶች እንዳሉን የሰማነው ገና ዛሬ ነው። ወላጆቻችን ልጆች ከመውለዳቸው በፊት እንኳን የተሟላ ህይወት
እንዳልነበራቸውና እኛም ያን ያህል አስፈላጊ እንዳልሆንን በማሰብ ቅሬታ ተሰማኝ።
👍38🤔21
ክሪስቶፈር “እማዬ ቨርጂኒያ ያለው ትልቁ ቤትሽ አሪፍ ይመስላል፤ ግን
ለእኛ እዚህ ይሻለናል። ጓደኞቻችን ሁሉ ያሉት እዚህ ነው፡ ሁሉም ሰዎች ይወዱናል፣ ያውቁናል። እኔ ከዚህ መሄድ እንደማልፈልግ አውቃለሁ። የአባዬን ጠበቃ አግኝተሽ እዚህ መቆየት እንድንችል የሚረዳንን መንገድ
እንዲፈልግ ማድረግ አትችይም?” አለ በቀስታ።

“አዎ እማዬ እባክሽ እዚሁ እንሁን” ብዬ ለመንኳት።

ወዲያውኑ እናቴ ከወንበሯ ላይ ተነስታ ወደኛ መጣች። ከዚያ ፊት ለፊታችን በጉልበቷ ተንበረከከችና አይኖቿን ከእኛ አይኖች ትይዩ አደረገች። የእኔንና የወንድሜን እጆች ይዛ በጣቶቿ ላይ አደረገችና “አሁን አዳምጡኝ. እዚህ መቆየት እንዴት እንደምንችል ብዙ ጊዜ አስቤ ነበር። ግን ምንም መንገድ
የለም: ምንም! ምክንያቱም በየወሩ የሚጠበቁብንን ክፍያዎች ለመክፈል በቂ ገንዘብ የለንም አራት ልጆችና ራሴን ለመደገፍ የሚያስችል በቂ ደሞዝ
የሚያስገኝ ስራ ለመስራትም እውቀት የለኝም:"

እጆቿን ወደጎን ዘረጋችና “ተመልከቱኝ እስቲ…. እኔ ምን እንደሆንኩ ታውቃላችሁ? ቆንጆ ነኝ ግን ሁልጊዜም የሚንከባከባት ባል እንዳላት የምታምን
ጥቅም አልባ ጌጥ ነኝ፡ ምንም ነገር እንዴት እንደሚሰራ አላውቅም የፅህፈት መኪና ተጠቅሜ መፃፍ እንኳን አልችልም: በሂሳብ ጥሩ አይደለሁም: ጥሩ
ግን እንደዚህ የሆነ በመርፌ የሚሰራ ጥልፍ መጥለፍ ብቻ እችላለሁ ግን እንደዚህ
አይነት ስራ በቂ ገንዘብ አያስገኝም: ያለ ገንዘብ ደግሞ መኖር አትችሉም።አለምን የሚያሽከረክራት ፍቅር አይደለም ገንዘብ ነው: አባቴ ስልሳ ስድስት
ዓመቱ ነው! በዚያ ላይ በልብ በሽታ ምክንያት ተዳክሟል እናቴ በፃፈችው ደብዳቤ ላይ አያታችሁ ግፋ ቢል ከሁለት ወይም ከሶስት ወር በላይ በህይወት አይቆይም ግን ምን እንደሚሰራበት ከሚያውቀው በላይ ብዙ ገንዘብ አለው።በህይወት ያለች አንዲት ወራሽ ልጁ እኔ ብቻ ነኝ: በዚህ ሁኔታ ላይ የእሱን ፍቅር መልሶ ማግኘት ከባድ አይሆንብኝም ከዚያ ጠበቃውን በአዲ
ኑዛዜ ውስጥ እንዲያካትተኝ ይነግረውና ሁሉንም እወርሳለሁ: ከዚያ ሲሞት ንብረቱ ሁሉ የእኔ፣ የእኛ ይሆናል፡ ከገንዘብ ማጣት ጭንቀት ለዘለዓለም ነፃ
እንሆናለን፡፡ የፈለግንበት ለመሄድም ሆነ የምንፈልገውን ለማድረግ እንዲሁም ልባችን የተመኘውን ለመግዛት ጭምር ነፃ እንሆናለን፡ የምነግራችሁ ስለ
አንድ ወይም ሁለት ሚሊየን ሳይሆን ስለ ብዙ… በጣም ብዙ ሚሊየኖች ምናልባትም ቢሊየኖች ነው: አያታችሁ አሁን ለመሞት ጫፍ ደርሶ እንኳን ገንዘብ መስራት ላይ ጎበዝ ነው: የነካው ሁሉ ወደ ወርቅ ይቀየራል:"

ሰማያዊ አይኖቿ አንፀባረቁ:: በዋጋ ከሚተመን በላይ ሀብታም መሰለች::እማዬ አባታችን ከሞተ በኋላ ይህ ሁሉ እንዴት መጣ?

“ክሪስቶፈር፣ ካቲ... እየሰማችሁኝ ነው? እያሰባችሁ ነው? ብዙ መጠን ያለው ገንዘብ ምን መስራት እንደሚችል አስተዋላችሁ? ዓለምና በውስጧ ያለው ሁሉ የእናንተ ይሆናል! ኃይል፣ ተፅዕኖና ክብር ይኖራችኋል። እመኑኝ በፍጥነት የአባቴን ልብ መልሼ አሸንፋለሁ። ገና ሲያየኝ ወዲያውኑ ተለያይተን
የቆየንባቸው እነዚያ አስራ አምስት አመታት የባከኑ እንደነበሩ ያስተውላል አሁን እሱ ነርሶች ቀንና ሌሊት እየተንከባከቡት ከቤተ መፃህፍቱ ባሻገር ባለች
ትንሽ ክፍል ውስጥ ነው ያለው አርጅቷል፣ ታሟል... ሊሞት ነው" አለች።....

ይቀጥላል
👍4414🥰2😢1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


ወደ ሀብታምነት ጉዞ

እናታችን እቃዎቿን ስታሽግ እኔና ክሪስቶፈር ደግሞ ልብሶቻችንን ከጥቂት አሻንጉሊቶችና ከአንድ መጫወቻ ጋር በሁለት ሻንጣዎች ውስጥ ማጨቅ ጀመርን: በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ አንድ ጓደኛችንን እንኳን ሳንሰናበት ታክሲ መጥቶ ወደ ባቡር ጣቢያ ወሰደን፡ እናታችን ማንንም ሳንሰናበት
በሚስጥር ሹልክ ብለን እንድንሄድ የግድ ያለችን ለምን እንደሆነ አልገባኝም።

ባቡሩ ብዙ ከተሞችና መንደሮች እንዲሁም እርሻ ቦታ ላይ ያሉ ቤቶችን እያቆራረጠ ወደ ቨርጂኒያ ግዛት ሲያመራ እኔና ወንድሜ አንድም ነገር እንዳያመልጠን ብለን መተኛት አልፈለግንም በዚያ ላይ ብዙ የምናወራችው
ነገሮች ነበሩን፡ ወሬያችን በአብዛኛው ስለዛ ትልቅ የሀብታም ቤት፣ ተንደላቀን ስለመኖር፣በወርቅ ሳህን ስለመመገብና የሚያምር ልብስ በለበሰ ሰራተኛ
ስለመስተናገድ ነበር ልብሶቼን የምታጣጥፍ፣ የገላ ውሀ የምታዘጋጅ፣ ፀጉሬን
የምታበጥርልኝና ባዘዝኳት ቁጥር ከች የምትል የግል ሠራተኛ እንደምትኖረኝ አሰብኩ ግን በጣም ክፉ አልሆንባትም በጣም የምወደውን ዕቃ ካልሰበረችብኝ
በስተቀር ሠራተኞች ሁሉ የሚመኟት አይነት ደግ እመቤት ነው የምሆንላት መቼም የማልወዳቸውንና የማልፈልጋቸውን ነገሮች መጣሌ ስለማይቀር በደንብ ነው የምከፍላት፡

በዚያ ምሽት ባቡሩ ውስጥ እያለን ጨለማውን ወደ ኋላ ስመለከት ምሽቱ ማደግና መፈላሰፍ የጀመርኩበት የመጀመሪያ ምሽት እንደሆነ አስተዋልኩ ሁሉንም ለማግኘት የሆነ ነገር ማጣት ስላለ እኔም የሚመጣውን ልለምደው
እና በጣም ጥሩ ላደርገው ያስፈልጋል እኔና ወንድሜ ገንዘቡ እጃችን ውስጥ ሲገባ በምን እንደምናጠፋው እየተነጋገርን
እያለ ፀጉሩ በመመለጥ ላይ ያለ የባቡሩ ሠራተኛ ወዳለንበት መጣ። የመጣበት ከመናገሩ በፊት እናታችንን በአድናቆት ከእግር እስከራሷ ተመለከታት። ከዚ
“ወ/ሮ ፓተርስን፣ በአስራ አምስት ደቂቃ ውስጥ መውረጃሽ ጋር እንደርሳለን አላት።

አሁን ደግሞ ለምንድነው “ወ/ሮ ፓተርሰን” ብሎ የጠራት? ግራ ገባኝ፡ ክሪስቶፈርን በጥያቄ አይን ተመለከትኩት እሱም ግራ የተጋባ ይመስላል።

ድንገት ስትነቃ የት እንዳለች ግር በመሰኘቷ የእናታችን አይኖች በሀይል ተከፈቱና ትኩረቷ ወደ ባቡሩ ሠራተኛ፣ ቀጥሎ ወደ እኔና ክሪስቶፈር ከዚያ ደግሞ ተስፋ በመቁረጥ እንቅልፍ ውስጥ ወዳሉት መንትዮች ተሻገረ። ወዲያው እምባዋ መጣና ከቦርሳዋ ውስጥ መሀረብ አውጥታ አይኖቿን ጠረገች። ሀዘን
በተሞላበት አይነት በከባዱ ስትተነፍስ ልቤ በሽብር መምታት ጀመረ።

አሁንም ቆሞ በአድናቆት እየተመለከታት ላለው የባቡሩ ሠራተኛ እሺ አመሰግናለሁ አትስጋ፣ ለመውረድ ተዘጋጅተናል” አለችው: የኪስ ስዓቱን ተመለከተና የጭንቀት እይታውን ወደ እኔና ክሪስቶፈር ከዚያ ደግሞ ወደ የተኙት መንትዮች አደረገ። ከዚያ “እመቤቴ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ነው ስትወርዱ የሚጠብቃችሁ ሰው አለ?” አላት።

“ችግር የለም” ስትል እናቴ አረጋገጠችለት።

“እመቤቴ በጣም ጨለማ እኮ ነው”

“የቤቴን መንገድ በእንቅልፍ ልቤ እንኳን አውቀዋለሁ።”

የአያት አይነት ባህርይ ያለው የባቡሩ ሠራተኛ የተናገረችው ነገር አላረካውም። “እመቤት፣ ቻርለትስቪል ከመውረጃችሁ የአንድ ሰዓት መንገድ ነው: አንቺንና ልጆቹን የምናወርዳችሁ ቤት የሚባል ነገር በማይታይበት ቦታ ላይ ነው አላት።

እናቴ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ላለመፍቀድ በጣም ትዕቢት በተሞላበት አነጋገር
“የሆነ ሰው ይጠብቀናል” አለችው ባንድ ጊዜ እንዴት እንደዚህ ያለ ባህርይ ልታመጣና ወዲያው ደግሞ ልክ እንደ ኮፍያ በቀላሉ ልታወልቀው እንደቻለች ማየት ያስገርማል።

እውነትም ምንም ነገር በሌለበት ቦታ ደረስን ከባቡሩ ወረድን፡ ከባቡር ስንወርድ ሙሉ በሙሉ ጨለማ ቢሆንም ማንም የጠበቀን አልነበረም: የባቡሩ ሠራተኛ እንዳስጠነቀቀን አንድም የሚታይ ቤት የለም። በጨለማ ብቻችንን
የሰው ፍጥረት በማይታይበት ቆም ብለን የባቡሩ ደረጃ ላይ ለቆመው የባቡሩ ሠራተኛ የስንብት እጃችንን አውለበለብንለት ከገፅታው እንደተረዳሁት “ወ/ሮ ፓተርሰንን” ፦ሤከአራት እያንቀላፉ ካሉ ልጆቿ ጋር ትቶ መሄዱ ደስ አላሰኘውም።
ዙሪያውን ስመለከት ማየት የቻልኩት በአራት የእንጨት ምሰሶዎች የተደገፈ የዛገ የቆርቆሮ ጣራና አረንጓዴ አግዳሚ ወንበር ብቻ ነው፡ የባቡር ጣቢያው
መሆኑ ነው። ባቡሩ በጨለማው ውስጥ እስኪሰወርና መልካም ዕድል እየተመኘልን የሚመስል አንድ አሳዛኝ የጥሩምባ ድምፁን እስክንሰማ ድረስ ቆመን እያየነው ነበር።

በሜዳና በመስኮች ተከበናል ከባቡር መውረጃው ጀርባ ካለው ጫካ ውስጥ የሆነ የተለየ ድምፅ ስሰማ በድንጋጤ ዘለልኩና ምንነቱን ለማወቅ ዙሪያውን
ረስመለከት ክሪስቶፈር ሳቀብኝ።“ጉጉት እኮ ናት! ጣረሞት መስሎሽ ነበር?”
አለኝ።
እናታችን “አሁን ማንም የለም: በሹክሹክታ መናገር የለባችሁም: ይህ የእርሻ ሀገር ነው በአብዛኛው ያሉት የወተት ላሞች ናቸው። ዙሪያውን ተመልከቱ። የስንዴና የአጃ እንዲሁም የገብስ መሬቶች ናቸው። እዚህ ያሉት ገበሬዎች ናቸው ኮረብታው ላይ ለሚኖሩት ሀብታሞች ምርቶቻቸውን በትኩሱ
የሚያቀርቡት”

ተቀጣጥለው የቆሙ በጣም ብዙ ኮረብታዎች ሲኖሩ ኮረብቶቹ ላይ በንፋስ ላይና ታች የሚሉ በርካታ ዛፎችም ተደርድረዋል። የምሽት ዘበኞች ብዬ ጠራኋቸው። እናታችን ግን ተደርድረው የተተከሉት በርካታ ዛፎች ከባዱን
ነፋስ ለመከላከልና ከባድ በረዶ ሲመጣ እንዲይዙ መሆኑን ነገረችን። ንፋስና በረዶ ክሪስቶፈርን የማረኩት ትክክለኛ ቃላት ነበሩ። ምክንያቱም በበረዶ
የሚደረጉ ሁሉንም አይነት የክረምት ስፖርቶች ይወዳል። እና እንደ ቨርጂያ ያለ የደቡብ ክፍል ከባድ በረዶ ይኖረዋል ብሎ አላሰበም።

“እዚህም በረዶ ይጥላል” አለች እናቴ: “ያለነውኮ ከብሉሪች ተራራዎች ስር ነው: ልክ እንደ ግላድስተን እዚህም ብርድ አለ። በበጋ ቀኑ በጣም ይሞቃል፤
ምሽቱ ግን ሁልጊዜም ቢያንስ አንድ ብርድ ልብስ ብቻ የሚያስለብስ ቅዝቃዜ አለው አሁን ፀሀዩዋ ብትወጣ ኖሮ ውብ የሆነውን ገጠር ማየት ትችሉ ነበር።በዓለም ላይ የዚህን ያህል የሚያምር ቦታ የለም አሁን በጣም መፍጠን አለብን ቤት ለመድረስ በጣም ረጅም መንገድ ይጠብቀናል። ከመንጋቱና
ሠራተኞቹ ከመነሳታቸው በፊት መድረስ አለብን፡” አለችን፡።
በጣም ይገርማል፡ “ሰራተኞቹ ከመነሳታቸው በፊት? ለምን? የባቡሩ ሠራተኛ ወ/ሮ ፓተርሰን ብሎ የጠራሽ ለምንድነው?” ብዬ ጠየቅኳት፡፡

"ካቲ አሁን ለአንቺ የማብራራበት ጊዜ የለኝም:: እየፈጠንን መራመድ አለብን አለችና ሁለቱን ከባባድ ሻንጣዎች አንስታ ጠንhር ባለ ድምፅ እንድንከተላት
አዘዘችን፡ እኔና ክሪስቶፈር እንቅልፋቸው ከመምጣቱ የተነሳ ለመራመድ ሙከራ ማድረግ ያልቻሉትን መንትዮቹን ለመሸከም ተገደድን።

ትንሽ እንደተራመድን “እማዬ የባቡሩ ሠራተኛ የአንቺን ሁለት ሻንጣዎጆ ሳይሰጠን ረስቶታል” አልኳት።

“ምንም አይደል ካቲ፤ ሻንጣዎቹን ወስዶ ሻንጣ ክፍል ውስጥ እንዲያደርግልኝ ነገ እንደምወስደው ነግሬዋለሁ” አለችኝ: የያዘቻቸው ሁለት ሻንጣዎች ጥንካሬዋን እንደቀነሱት ሁሉ ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ነበር

“ለምንድነው እንደዚያ ያደረግሽው?” ሲል ጠየቃት ክሪስቶፈር።
👍33🥰41
“አንደኛ አራት ሻንጣዎች መሸከም ስለማልችል ነው፤ እችላለሁ እንዴ?
ሌላው ደግሞ አባቴ ስለ ልጆቼ ከማወቁ በፊት ከእሱ ጋር የመነጋገር እድል እፈልጋለሁ ለአስራ አምስት አመታት ከጠፋሁ በኋላ ድንገት በሌሊት ወደቤት
መምጣቴ ትክክል አይመስልም፤ ይመስላል?" አለች: ሀሳቧ ምክንያታዊ ይመስላል። መንትዮቹ መራመድ እምቢ ስላሉ የምንችለውን እያደረግን ነው።
ጋሬጣ ልብሳችንን እየያዘው ባልተስተካከለ መሬት ላይ በአለቶችና በዛፎች መሀል ቀጭን መንገድ ተከትለን ከእናታችን ኋላ ኋላ እየሄድን ነው። በጣም ረጅም መንገድ ስለተጓዝን እኔና ክሪስቶፈር ደከመን። መንትዮቹም እየከበዱንው መጡ፤ ክንዶቻችን በመታመማቸው አጉረመረምን፡ ተጨቃጨቅን፡ ትንሽ ተቀምጠን እረፍት ለማድረግ በመፈለግ እግሮቻችንን እየጎተትን መራመድ
ጀመርን፡ ከማናውቀው ብዙ ሠራተኞች ካሉበት ትልቅ ቤትና ከማናውቃቸው አያቶቻችን ጋር ከመሆን ወደ ግላድስተን ተመልሰን አልጋዎቻችን ውስጥ መግባትና በምንወዳቸው እቃዎች መከበብ እጅግ የተሻለ ይሆን ነበር።

“መንትዮቹን ቀስቅሷቸው! በእግሮቻቸው እንዲቆሙ አድርጉና በእግራቸው እንዲሄዱ አስገድዷቸው፡ ፈለጉም አልፈለጉም በእግራቸው ይሂዱ አለች እና ትዕግስት ባጣ ሁኔታ። ከዚያ ከጃኬቷ ኮሌታ ስር ለፈጣን ጆሮዎቼ በትንሹ በሚሰማ ቀስ ባለ ድምፅ አሁን ውጪ ሆነው መራመድ በሚችሉበት ጊዜ ወይ
ቢራመዱ ይሻላቸዋል' ስትል አጉረመረመች: ይህንን ስስማ መጪውን የመፍራት ማዕበል አከርካሪዬ ድረስ ተሰማኝ ታላቅ ወንድሜ ሰምቶ እንደሆነ
ለማረጋገጥ ዞር ብዬ ሳየው እሱም ዞር ብሎ አየኝ፡ ፈገግ ሲልልኝ እኔም በምላሹ ፈገግ አልኩለት
ነገ እናታችን በታክሲ ተሳፍራ በትክክለኛው ሰዓት ትደርስና ወደታመመው አያታችን ገብታ ደስ በሚል ፈገግታ ታነጋግረዋለች: የሚያምረውን ፊቷን
አንድ ጊዜ ሲመለከትና ከሚያምረው ለስላሳ ድምፅዋ አንድ ቃል ሲሰማ እጆቹን ይዘረጋላታል እናም ከፀጋ በመውደቅ የሰራችውን ስህተት ሁሉ ይቅር ይላታል። ታሸንፋለች!!

ስልሳ ስድስት አመት ለእኔ እጅግ በጣም የሸመገለ ነው በሞት አፋፍ ላይ ያለ ሽማግሌ ሰው በፊት እጅግ በጣም ይወዳት በነበረች ልጁ ላይ ቂም ቋጥሮ
ሊሄድ አይችልም። ይቅርታ ሊያደርግላት ይገባል፡ ምክንያቱም ትክክለኛ ነገር እንዳደረገ አውቆ በሰላም ወደ መቃብሩ መሄድ አለበት ከዚያ አንዴ እንዲወዳት
ካደረገችው በኋላ ከመኝታ ክፍል ታስወጣንና ሽክ ብለን ለብሰንና ቆንጆ ሆነን ወደ እሱ እንሄዳለን፡ ከዚያ አስቀያሚዎች አለመሆናችን ወይም መጥፎ
አለመሆናችንን ያውቃል፡ በዚያ ላይ ማንም ልብ ያለው ሰው መንትዮቹን አይቶ አለመውደድ አይችልም: ወደ ሱቅ ስንሄድ የሚያዩዋቸው ሰዎች
እንኳን፣ ሳይዳስሷቸውና ለእናታችንም ቆንጆ ልጆች እንዳሏት ሳይነግሯት
አያልፉም ለነገሩ አያታችን የክሪስቶፈርን ጉብዝና እንዲያውቅ ማድረግ ብቻ ይበቃል። እኔ የማጠናውን ያህል በደንብ ሳያጠና እንኳን የደረጃ ተማሪ ነው
ለእሱ ሁሉም ነገር በቀላሉ ነው የሚመጣለት: አይኖቹ አንድን ገፅ አንዴ ወይም ሁለቴ ከተመለከቱ እዚያ ገፅ ላይ የተፃፈው ነገር በሙሉ አእምሮው
ውስጥ ይቀመጣል። አይረሳም በዚህ ተሰጥኦው እንዴት እንደምቀና!

የእኔ ተሰጥኦ ደግሞ እንደ ክሪስቶፈር ብሩህና የሚያበራ ሳንቲም አይነት ሳይሆን
የሚያንፀባርቀውን ሁሉ ትቼ ደብዛዛውን የመፈለግ ነው፡ ስለማናውቀው አያታችን በለቃቀምናቸው የተወሰኑ መረጃዎች መሰረት ስናስበው በቀላሉ ይቅር የሚል አይነት ሰው እንዳልሆነ ገብቶናል በፊት ይወዳት የነበረች ልጁን ለአስራ አምስት አመታት ሲክዳት እንኳን ቅር አላለውም: ሆኖም ግን
ሊታይ የሚገባውን የእናታችንን ልምምጥ መቋቋም መቻሉን እጠራጠራለሁ።

እናታችን አባታችንን በገንዘብ ጉዳይ ስትለማመጠው አይቼም ሰምቼም አውቃለሁ ሁልጊዜም የሚሸነፈው አባታችን ነበር፡ ልትስመው፣ ልታቅፈው
ወይም ለስለስ አድርጋ ልትዳብሰው ትችላለች ብቻ በቅፅበት ውሀ ታደርገውና
በራሷ መንገድ ታሸንፈዋለች:
አባታችንም በደስታ ፈገግ ይልና ለምትገዛቸው ውድ ነገሮች ሁሉ መክፈል የሚችልበትን መንገድ ለማስተካከል ይስማማል።

“ካቲ ጭንቀትን ከፊትሽ ላይ ዞር አድርጊ፡ እግዚአብሔር ሰዎች እንዲያረጁና እንዲታመሙ በመጨረሻም እንዲሞቱ ባያደርግ ኖሮ ሰዎች ልጆች መውለድ
እንዲቀጥሉ አይፈቅድም ነበር” አለኝ ክሪስቶፈር።

ክሪስቶፈር ልክ የማስበውን የሚያነብ መስሎ እስኪሰማኝ ድረስ አፍጥጦ እያየኝ ስለነበር ደነገጥኩ። በደስታ ፈገግ አለ፡ ብልጣ ብልጥና መልካም
ነገሮች እንደሆኑ የሚጠብቅ እንጂ እኔ በአብዛኛው እንደሆንኩት አይነት አኩራፊ፣ ተጠራጣሪ ወይም ተለዋዋጭ ስሜት ያለው ሰው አይደለም፡

የእናታችንን ምክር ተከትለን መንትዮቹን ቀሰቀስናቸው: በእግሮቻቸው አቆምናቸውና ደከማቸውም አልደከማቸውም ለመራመድ ጥረት እንዲያደርጉ
ነገርናቸው: ባለመፈለግ እየተነጫነጩ ቢያለቅሱም እየጎተትናቸው መራመድ
ቀጠልን ኬሪ እያለቀሰች “የትም መሄድ አልፈልግም” አለች።
ኮሪም እያለቀሰ ነበር። ኬሪ ትንሽዬ እጇን ከእኔ ለመንጠቅ እየሞከረች “ሲመሽ በጫካ ውስጥ መሄድ
አልወድም… ቤቴ እሄዳለሁ! ልሂድ ካቲ ልሂድ!” እያለች ጮኸች።
ኮሪ ጮክ ብሎ ማልቀስ ጀመረ።
ኬሪን እንደገና አንስቼ ላቅፋት ፈለግኩ። ነገር ግን ክንዶቼ ዝለው ማድረግ አልቻልኩም: ክሪስቶፈር የኮሪን እጅ ለቀቀና ሁለት ከባባድ ሻንጣዎች የተሸከመችውን እናታችንን ለማገዝ ወደፊት ሮጠ። መራመድ የማይፈልጉ ሁለት እምቢተኛ ልጆች እየጎተትኩ በጨለማው ለመራመድ ሞከርኩ።

አየሩ ቀዝቃዛና ሽታ ያለው ነበር። እናታችን ይህንን ኮረብታማ ሀገር ብላ ብትጠራውም ለእኔ ግን እነዚያ ከሩቅ የሚታዩት ትልልቅ ጥላ ያላቸው ኮረብቶች የሚታዩኝ ተራራ መስለው ነበር ቀና ብዬ ሰማዩን ስመለከት በኮከብ ከደመቀ ሰማይ ይልቅ በሚያንፀባርቁ የበረዶ ፍንጣቂዎች የደመቀ ጠቆር ያለ ትልቅ ሰማያዊ ሳህን ይመስል ነበር፡ ኮከቦቹ ወደ ፊት ሳለቅስ
የሚወርዱ የበረዶ እምባዎች የሆኑ ይመስል በሀዘኔታ ወደታች ሲመለከቱኝ እንደ ጉንዳን ያነስኩ፣ ደካማና ፍፁም ጥቅም የሌለኝ መሆኔ እንዲሰማኝ የሚያደርጉ የሚመስለኝ ለምንድነው? ያ ሰማይ በጣም የሚያምር ነው፡ ታዲያ እንግዳ በሆነ ሁኔታ መጪው ጊዜ ጥሩ ያለመሆኑ
ትልቅና እጅግ እንዲሰማኝ በሚያደርግ ስሜት የሚሞላኝ ለምንድነው?

በዳገታማው ኮረብታ ላይ የተደረደሩ በርካታ የሚያማምሩ ትልልቅ ቤቶች ያሉበት አካባቢ ደረስን፡ ተራራው ላይ ካሉ ቤቶች በላይ በጣም ትልቅ ወደ
ሆነው ቤት በቀስታ ተጠጋን፡ እናታችን ይህ የዝርያዎቿ መኖሪያ ቤት የፎክስወርዝ አዳራሽ ተብሎ እንደሚጠራና ከሁለት መቶ አመት በላይ እድሜ ያለው መሆኑን በሹክሹክታ ነገረችን፡

ክሪስቶፈር ኮረብታማውን አካባቢ በትኩረት እየተመለከተ “ብዙ ዛፎችና አለቶች ስላሉት ለበረዶ ሸርተቴ አሪፍ ሀገር ነው: ግን የበረዶ ሸርተቴ መጫወቻና ለዋና የሚሆን ሀይቅ አለው?” ሲል ጠየቀ እናታችን በእጇ ሀይቁ ሊገኝበት የሚችልበትን አቅጣጫ እያመለከተች “አዎ ሩብ ማይል ርቀት ላይ ትንሽዬ ሀይቅ አለ” አለችው።

በጣቶቻችን ጫፍ እየተራመድን ያንን ትልቅ ቤት ዞርነው:: ከዚያ አንዲት ጠና ያለች ሴት በኋለኛው በር በኩል አስገባችን፡ ማንኳኳት እንኳን ሳይጠበቅብን በሩን የከፈተችልን በፍጥነት ነበር እየጠበቀችን መሆን አለበት እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት እንኳን ቃል አልተነፈሰችም: እኛም በሌሊት እንደሚመጡ ሌቦች ድምፃችንን አጥፍተን ወደ ውስጥ ገባን፡ ከሰራተኞቹ አንዷ ትሆን
👍335👏1
ይሆን? አልኩ በልቤ ወዲያውኑ የሆነ ጨለማ ቤት ውስጥ ገባንና ፋታ ሳትሰጠን ጠባብና ዳገታማ
በሆነ ደረጃ እንድንወጣ አጣደፈችን፡ ዙሪያውን ለመቃኘትና ትልልቆቹን ክፍሎች ለማየት አንድ በአንድ እድል እንኳን ሳትሰጠን ፀጥ ባለው መተላለፊያ ወጣንና ብዙ አዳራሾችንና በርካታ የተዘጉ ክፍሎችን አልፈን በመጨረሻ ጥግ ላይ ያለ አንድ ክፍል ጋ ደረስን፡ ከዚያ በሩን ከፈተችና ወደ ውስጥ እንድንገባ በእጇ አመለከተችን የገባነው አንዲት መብራት ብቻ በበራበት ትልቅ ክፍል ውስጥ ቢሆንም ረጅሙ የሌሊት ጉዟችን በማለቁ እፎይታ ተሰማኝ ክፍሉ ሁለት ረጃጅም መስኮቶቹን የሸፈኑ ግዙፍ መጋረጃዎች አሉት በሩ ላይ
ያስገባችን ግራጫ ቀሚስ የለበሰችው አሮጊት ሴት ወደኛ ዞራ ተመለከተችንና ወደ አዳራሹ የሚያወጣውን ከባዱን በር ዘግታ ተደገፈችው ስትናገር ድንግጥ
አልኩ፡ “ኮሪን… ልክ እንዳልሽው ልጆችሽ ቆንጆዎች ናቸው”

የሰጠቸው አስተያየት ልባችንን ሊያሞቅ የሚገባው ቢሆንም የእኔን ልብ ግን ድምጽዋ ቀዝቃዛና ግድ የለሽ ነበር፡ በእሷ የውሸት አስተያየት በቀላሉ የምንታለልና አለመደሰቷን የሚረዳ አእምሮ የሌለን አድርጋ ቆጥራናለች ማለት ነው! ብዬ እያሰብኩ ሳለ ቀጥሎ የተናገረቻቸው ቃላት
የሀሳቤን ትክክለኛነት አረጋገጡልኝ፡....

ይቀጥላል
👍168🥰1👏1
#ሳቤላ


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...እነዚያ አስከሬን አጋችዎች ግን ሊወጡ አልቻሉም " ሚስተር ካርላይል አስከሬኑ ወዶ ነበረበት ክፍል ገብቶ ማንነታቸውንና በምን መብታቸው እንደዚያ ማድረግ እንደቻሉ ጠየቀ መረመረ እንደዚህ ያለ ድፍረት በሕይወቱ ዘመን አይቶ አያውቅም " ብቻ ዱሮ አንድ የቤተ ክህነት ባለሥልጣን የሆነ ሰው እንደዚሁ በከባድ ዕዳ እንደ ተዘፈቀ ሞተና አስከሬኑ ሊቀበር ቤተ ክርስቲያን እንዶ ደረሰ እንደዚሁ ባለዕዳዎች ይዘውት እንደነበር አባቱ ያጫወተውን ያስታውሳል " አሁንም እነዚህ ሰዎች የጠየቁትን ከባድ ገንዘብ ካልተከፈላቸው ሚስተር ቬን ተተኪው የማውንት እስቨርን ኧርል ከካስል ማርሊንግ እስኪደርስ ድረስ ሬሳውን መልቀቅ
እንደማይችሉ አስታወቁ "

በበነጋው ጠዋት እሁድ ሚስተር ካርላይል ከቤቱ ዌስትሊን አድሮ ወደ ኢስት ሊን ቢመጣ ማንም አልደረሰም። ሳቤላ ከቁርስ ክፍል ተቀምጣ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል የቀረበውን ምግብ አልነካችውም መልኳ ሁሉ የበሽተኛ መስሏል ሚስተር ካርላይል ሁኔታዋንና የበሽተኛ መስሏል ሚስተር ካርላይል ሁኔታዋንና የበሽተኛ ገፅታዋን አይቶ ዝም ሊል ስላልቻለ ጠየቃት።

"አልተኛሁም በጣም በርዶኛል" በጣም ከመፍራቴ የተነሳ ዓይኔን ላመል ያህል እንኳን ሳልከድን እንዲችሁ እንዳለሁ ነገ።

"ምኑ ነው ያስፈራሽ?"
እነዚህ ሬሳውን የያዙት ሰዎች አለችው ሹክ ብላ የሚስተር ቬን አልመድረስም ገርሞኛል።

« ፖስታ አልመጣም ? » አላት "

« እንጃ እስካሁን የደረሰኝ ነገር የለም »

ገና ተናግራ ከማብቃቷ የቤቱ ዋና አሽከር አንድ ማቅረቢያ ሙሉ ደብጓቤዎች ይዞ ገባ " ብዙዎቹ ለሳቤላ የተላኩ የኀዘን መግለጫዎች ነበሩ " አንድ የማርሊንግ ከተማ ማኅተም የነበረበትን ደብዳቤ መርጣ አነሣችና • « ይኸ የሚስዝ ቬን ጽሕፈት ነው » አለችው ለሚስተር ካርላይል "

« ካስል ማርሊንግ ቅዳሜ »

« ለምወድሽ ለሳቤላ በጀልባው ሽርሽር ስለ ሔደ እኔ ከፍቸ የያዘውን መልዕክት ባየሁት ጊዜ በጣም አዘንሁ እሱ ግን ባሁኑ ስዓት ያለበትን ቦታ በትክክል አላውቅም ነገር ግን እሑድ
እንደሚመለስ ነግሮኛል " ብዙውን ጊዜም ቃሉን በመጠበቅ ረገድ ጠንቃቃ ስለ ሆነ በተስፋ እጠብቀዋለሁ " ከደረሰ ደግሞ ወዲያው ወደ ኢስት ሊን እንደሚመጣ አትጠራጠሪ

« ስለ አንቺ የተሰማኝን ኀዘን መግለጽ አልቻልኩም " በጣም ከመረበሼ የተነሣም ከዚህ በላይ መጻፍ አልሆነልኝም " መንፈስሽን ላለመጣልና ራስሽን በራስሽ ለማበረታታት ሞክሪ እያልኩ ልባዊ ኀዘኔን እገልጻለሁ " ያንቺው ታማኝ

"ኤማ ማውንት እስቨርን"

ሳቤላ ፊርማዋን ስታነብ ፊቷ ልውጥ አለ " « ራሷ ከጻፈችው ኤማ ቬን ብላ መፈረም ነበረባት ብላ አሰበች « አዬ አለመታደል » ብላ ወረቀቱን ለሚስተር ካርላይል ሰጠችው "

እሱም የሚስዝ ቬን ሙጭርጭር ጽሕፈት በፈቀደለት ፍጥነት መጠን ተመልክቶ ከፊርማው ሲዶርስ ከንፈሮቹን ሞጥሞጥ አደረገ " ለሳቤላ የተሰማት ለሱም ተሰምቶት ይሆናል "

«ቁም ነገር ያላት ሰው ብትሆን ኖሮ ብቸኝነትሽን ተገንዝባ እሷው እራሷ ገሥግሣ ትመጣ ነበር » አለ ሚስተር ካርላይል ግልፍ አለውና

ሳቤላ እጅዋን ራሷ ላይ አስደገፈች ከፊቷ የተደቀኑት ችግሮች መከማቸት ጀመሩ " ስለቀብሩ ሥነ ሥርዓት የተሰጠ ትእዛዝ አልነበረም » እሷም ብትሆን ለማዘዝ መብት ያላት መስሎ አልታያትም " የማውንት እስቨርን ኧርሎች ሁሉ የተቀበሩት ማውንት እስቨርን ላይ ነበር " ግን የአባቷን አስከሬን እዚያ ድረስ ለማጓዝ ከፍ
ተኛ ወጭ ይጠይቃል ተተኪው ኧርልስ በነገሩ ይስማማ ይሆን ? ካለፈው ጧት ጀምሮ በተጫናት የሐሳብ ክብደት ያረጀች መሰለች " ሐሳቦችዋ ተለወጡ " አስተሳሰቡዋ ቈልምም ብሎ አቅጣጫወን ለወጠ " ክብር ሀብትና ማዕረግ የነበራት ወጣት
እመቤት አሁን ሁኔታዋን ስታስበው ምናምን የሌላት ለማኝ በኖረችበት ቤት ቀላዋጭ መሆኗ ታያት " በፍቅርና በጀብድ ታሪኮች ውስጥ ወጣት እመቤቶችን መልከ መልካሞችና ማራኪዎች ከሆኑ የዕለት ጭንቀትና የአስፈላጊ ነገሮች ችግር የማይታያቸው ረሃብን ጥማትን ብርድንና እርዛትን አስከትሎ ስለሚመጣው
ስለድህነት ጭራሽ ግድ የሌላቸው አድርጐ ማቅረቡ የተለመደ ነገር ሆኗል " በእውነተኛ ኑሮ ውስጥ ግን ነገሩ እንደዚህ አይደለም " ሳቤላ ቬን አባቷን በሌሎች ዘንድ
የተባለ ቢባል ከልቧ ታከብረውና ትወደው ስለነበር በመሞቱ እርር ብላ አዝና ነበር
ይሁን እንጂ በዚህ ኀዘንና ያባቷ ሞት ባስከተላቸው ልዬ በሆኑ ችግሮች መካከል ተወጥራ እያለችም ስለ ወደፊት ዕድሏ ማሰቧን አልተወችም አስተማማኝ ያለመሆኑና ገና አስቀድመው በግልጽ መታየት የጀመሩት ችግርቿ በኀዘኗ ጣልቃ እየግቡ
ይደቀኑባት ጀመር ። ያ ነገሩ ግልጽ የነበረው ባለዕዳ ፡ « አንገትሽን የምታስገቢበት ጣራ የኔ ነው የምትይው አንድ ብር እንኳን የለሽም » ብሎ የተናገራት ከዚያ ወዲህ ከልቧ አልጠፋም በዕዝነ ልቦና ያለማቋረጥ ትሰማዋለች » እስከ ጊዜው ሚስተር ካርላይል ቤት ቆየች ከዚያ በኋላስ የት ነው የምትደርሰው ከማን ጋር ነው የምትኖረው ? አሽከሮቹ ሁሉ ያገለገሉበትን ደመወዛቸውን ይፈልጋሉ " ከየት አምጥታ ትከፍላቸዋለች ? ይህ ሁሉ ጥያቄ በአእምሮዋ እየተመላለስ አስጨነቃት »

« ሚስተር ካርላይል ይህ ቤት ያንተ ከሆነ ምን ያህል ጊዜ ሆነው ? » አለችው ሁለቱም ዝም ብለው ከቆዩ በኋላ ።

« ግዥው የተፈጸመው ባለፈው ሰኔ ወር ነበር ግን ለኔ እንደ ሸጡት አባትሽ አልነገሩሽም ? »

« ምንም አልነገረኝም " አሁን ይኸ ሁሉ ያንተ ነው ማለት ነው ? » አለችው የክፍሉን ዙሪያ በዐይኗ እየቃኘች።

« ወንበርና ጠረጴዛ የመሳሰሉት ሁሉ አብረው ተሽጠዋል “ ልብስና እንዲሁም እንደ ሰሀን የመሳስሉት የቤት ዕቃዎች ግን ከሽያጬ ዝርዝ አልገቡም »

« እንግዲያውማ እነዚያ ትናንት ገንዘባቸው እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ የነበሩት ሰዎች ሳይሸጥ በቀረው ዕቃ ላይ መብት ይኖራቸዋል ማለት ነው? »

« እንጃ ለኔ እንደሚመስለኝ እንኳን እንደ ሰሀን 'እንደ ጌጥ ዕቃዎች የመሰሉ ሁሉ ሥልጣኑን የሚወርሰው ሰው ነው የሚረከባቸው »

« ልብሶቼስ የኔ ናቸው ? »

ሚስተር ካርላይል በሳቤላ አጠያየቅ ሣቅ አለና ለማንም ሊሆኑ እንደማይችሉ ነገራት "

« እኔ ምን ላድርግ ? ነገሩ ሁሉ ሊገባኝ አልቻለም " በዚህ የአንድና የሁለት ቀን ጊዜ ውስጥ እንኳን ብዙ ሊገቡኝ ያልቻሉ ነገሮች ተፈጽመዋል " ለመሆኑ አባቴ ካንተም ገንዘብ ወስዶብህ ነበር?

« የለም እሳቸው ከኔ ገንዘብ ተበድረው አያውቁም ። »

« አሁን አንተ ኢስት ሊንን ግዝተኸዋል " የራሴም ሁኔታ ምን እንዶሚመስል እየታየኝ ነው» አለችው ወዲያው ዕንባዋ በዐይኖችዋ ሞላ « መቸም ራሴን መደገፍ እስካልቻልኩ ድረስ በመጠጊያ ረገድ አንተን ማስቸገሬ አይቀርም »

« ሳቤላ . . . ምንም ዐይነት ሰቀቀን ሳይሰማሽ እስከ ፈለግሽበት ድረስ መቀመጥ ትችያለሽ »

« እግዚአብሔር ይስጥልኝ » ለጥቂት ቀኖች ነው " ምን ማድረግ እንዳለብኝ
እስካስብ ድረስ ከዚህ እሰነብታለሁ " ለመሆኑ ሚስተር ካርላይል ... ያባቴ ዕዳ
ትናንት የሰማነውን ያህል ይመስልሃል የተረፈ ገንዘብ አይኖረውም ? »
👍151😁1
ሚስተር ካርላይል እሷን ለማጽናናት ሲል ብዙ የተረፈ ተቀማጭ ሊኖረው እንደሚችል ሊነግራት ይችል ነበር ግን እሷ እሱን ምን ያህል እንደምታምነው
እያወቀ ሊያታልላት ቢሞክር በራሱ ላይ የማይጠፋ ጸጸት መትከል መሆኑን ተገነዘበና « ሁኔታው እንደምናየው ተስፋ የሚጣልበት አይደለም " ምናልባት ግን አንቺ
የማታውቂው ኑዛዜ ትተዉልሽ ይሆናል " ስለዚህ ወርበተንና ዌርን ... »

« አይ . . . ኑዛዜ የሚባል ነገር እንኳን አልሰማሁም እንደማይኖርም እርግጠኛ ነኝ " የኔም ነገር በግልጽ እየታየ ነው " ቤት የለኝም ! ገንዘብ የለኝም ይህም ቤት ያንተ ው » የከተማው ቤትና ማውንት ስቨርን ለአዲሱ የኧርል ለሚስተር ቬን ይተላለፋሉ " እኔ ምንም ነገር የለኝም»

« አንቺ ወደ ድሮው ቤትሽ ለመመለስ ከፈለግሽ ሚስተር ቬን በጣም ነው ደስ የሚላቸው »

« ምን ? እኔ ከነሱ ጋር ልቀመጥ ማለት ? ምን እያልክ ነው ...
ይል ? እኔ ምንም ቢሆን ከሚስዝ ቬን ጋር አብሬ መቀመጥ አልችልም »

ሚስተር ካርላይል ከዚያ በላይ በመቆየት የሚረዳው ነገር አለመኖሩን በመገንዘብ ለመሔድ ሲነሳ እሷን ደግሞ የሚያነጋግራት ሰው እንደሚያስፈልግ አሰበና
ሚስዝ ዲሲ ብትመጣላት እንደሚሻል ነገራት "

ሳቤላ ራሷን ነቀነቀች » « ያባባ አስከሬን እንደዚህ እንዶ ተያዘ የውጭ ሰው ባይመጣብኝ ይሻላል " ስለ አስከሬኑ መያዝና የመሳሰለ ጉዳይ ሁሉ ማንም እንዲጠይቀኝ አልፈልግም እኔ ከዚህ ሁሉ ብቻዬን ብሆን እመርጣለሁ » አለችውና በዚህ
ተለያይተው ሲወጣ ሚስዝ ሚዞን አገኘችው" ስለ መጡት ደብዳቤዎችና በተለይም
ከካስል ማርሊንግ ስለ መጣው ምን ወሬ እንዳለው ጠየቀችው ከደብዳቤ የተነበበውን ነገራት "

« ታዲያ ሚስተር ቬን ቢቀርም ሳጥኑ በደንብ መታሸግ አለበት » አለችው "
« እሱስ ዶህና ሚስተር ቬን ባይኖሩም ይታሸጋል » አላት

«እሱማ ባይመጡም ይታሸጋል ችግሩ እሱ አይዴለም " ግን ሬሳውን የያዙት ሰዎች እሺ ይላሉ ወይ?ማለዳ ቀብር አስፈጻሚዎቹ ቢመጡ ሬሳው ከዐይናችን
እንዲለይ አንፈቅድም አሏቸው " ለመሆኑ አናሳሽግም ከሳጥን አናስግባም የማለት መብት አላቸው ? » አለችው "

« ከዚህ በፊት እንደዚህ ያለ ነገር ስላልተፈጸመ በሕግ በኩል እንዴት እንደሚታይ አላውቅም » የሆነ ሆኖ ይሆን ሥጋት ለሳቤላ አትንገሪያት " እንግዲህ ሚስተር
ቬን ሎርድ ማውት እስቨርን ማለቴ ነው እንደ መጡ ላኪብኝ » ብሏት ሔደ።
እሑድ ከቀትር በኋላ አንድ ፈጣን የሕዝብ ማመላለሻ ሠረገላ አውራውን መንገድ ይዞ ሽቅብ
እየከነፈ መጣ ሰረገላው አዲሱን የማውንት እስቨርን ኧርል ሎርድ ቬንን አሳፍሮ ነበር። ከካስል ማርሊንግ በባቡር መጥቶ ዌስት ሊን ሊግባ ስምንት ሜትር ሲቀረው ወርዶ በኪራይ ሠረገላ ተሣፍሮ ደረሰ ጥቂት ቆይቶ ሚስትር ካርላይል መጣ " ሚስተር ዋርበርትም ተከታትሎ ከለንደን ገባና መደረግ ስለሚገባው
ንግግር ተጀመረ አዲሱ ኧርል ከሱ በፊት የነበረው ኧርል ብዙ ዕዳ እንደ ነበረበት ይወቅ እንጂ ስለ ክፋቱ መጠን ግን እንደዘያ ይሆናል ብሎ አላሰበም "እስከዚህ
የቀረበ ወዳጅነት ስላልነበራቸው ይኸን ያህልም አይገናኙም ነበር " አሁን ግን ገንዘቡን ሁሉ አስፈላጊ ባልሆነ ነገር ማባከኑን አሰቃቂ ውድቀቱን ለሳቤላም ምንም
ነገር ያላሰበላትና ያስቀመጠላት አንዳችም ሀብት ያለመኖሩን በዝርዝር ሲነግረው እጅግ ከመገረሙ የተነሣ በድን ሆነ
«ሚስተር ቬን አዲሱ የማውንት እስቨርል የዊልያም ቬን ወራሽ ገጽታው ኮስተር ጠባዩ ቀዝቀዝ ጥላው ከበድ ያለ ቁመቱ ረጅም ሰውነቱ ሙሉ የሆነ ያርባ ሦስት ዓመት ጐልማሳ ነበር "

« እኔ ይህን የመሰለ ግፍ ሰምቸ አላውቅም » አላቸው ለሁለቱም ጠበቆች «ከግድየለሽ ደደቦች ሁሉ ማውንት እስቨርን የባሰ ነበር ማለት ነው»

« በተለይ ለልጃቸው ምንም ነገር ባለማሰባቸው ያደረሱባት በደል ይቅርታ የሚያስደርግ አይደለም » አሉት።

« አሳበ ቢስነት ! ፍጹም ዕብደት ነው እንጂ እስኪ ማን ጤነኛ አእምሮ ያ ሰው አንዲት ልጁን ዓለም እንደ ፈለገ ያድርጋት ብሎ ያለምንም ተስፋና ጥግ የትም
ይጥላል ? አሁን አንዲት ሺልንግ እንኳን በጂዋ የላትም እሷ እንደ ነገረችኝ ሲሞት ኻያ አምስት ፓውንድ ያልሞላ ገንዘብ ብቻ ነበር ከቤት የተገኘው " እሱ ለቤት ወጭ ለሜዞን ለቃቅማ ሰጠቻት እንደዚህ ያለ ጉድ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም »

« ትክክል ነው ጌታዬ» አለ ሚስተር ወርበርተን «በውርስ የተላለፈው ርስት ምን ጊዜም ለርስዎ ነው ከዚህ የተረፈ ልቅምቃሚ ነገር ቢገኝም ባለዕዳዎች የሚቀራመቱት ነው "

« ኢስት ሊን ያንተ መሆኑን ሳቤላ ነገረችኝ » አለ ወደ ሚስተር ካርላይል እያየ

« አዎን . . . ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ ነው የኔ የሆነው " ክቡርነታቸው ግን ነገሩን ምስጤር አድርገው ሳይዙት አልቀሩም " »
« በምስጢር የያዙት'ኮ ወደው አልነበረም » ይህማ ባይሆን ኖሮ ከሽያጮ ገንዘብ ውስጥ አንድ ሳንቲም እንኳን ከእጃቸው ሳይገባ ባለዕዳዎቻቸው ይቀራመቱት ነበር ስለዚህ ከኛና ከሚስተር ካርላይል ወኪሎች በቀር ለማንም አልተግለጸም ነበር » አለ ሚስተር ዋርበርተን "

« ግን ልጂቱ ካባቷ የምትጠብቀውን የሀብት መብት ጉዳይ ልታሳስቡትና ልትወተወቱት ስትችሉ ምንም ነገር አለማድረጋችሁ በጣም ገርሞኛል "የሱን አያያዝና አዝማሚያ እያወቃችሁ እንዴት ዝም አላችሁ ?» አለው ሚስተር ዋርበርተንን "

« እኛም ይዞታቸውን እንደ ተመለከትነው መወትወቱ ጠቃሚ ሆኖ አልታየንም ለልጃቸው አንድ ነገር ሊያቆዩላት የሚችሉበትን ጊዜ በዋዛ አሳለፉት " ይኸን
የማድረግ አቅማቸው ገና ዱሮ ነው ያመለጣቸው " እኔ እንኩዋን አንድ ሁለት ጊዜ አነሣሁባቸው አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው በርግጥ ይሰማቸው ነበር » ግን
አልፈጸሙትም ስለሷ አያስቡም ነበር ለማለት አልችልም " በሕይወት እያሉ ጥሩ ትዳር ትመሠርታለች የሚል ተስፋ ነበራቸው መቸም እሳቸው በቶሎ የሚሞቱ አልመሰላቸውም»

« እንዴት ካቅሙ በላይ ነው ትለኛለህ ? ሌላው ቢቀር የሕይወት ዋስትና በጥቂት ሺ ፓውንድ ሊገቡላት ይችሉ ነበር " አሁን ኮ ምናምን የላትም . . . ይገባሃል? »

« እሱስ በደንብ ይገባኛል ። ግን ክቡርነትዎ በሎርድ ማውንት እስቨርን ወድቆ የነበረን ሸክም የተረዱት አይመስለኝም » የዕዳቸው ወለድ ብቻ ሲሰሙት ያስርገምዎታል ። በዚያው ላይ ደግሞ እየተበደሩ ከመጨመር የሚገታቸው ነገር አልነበረም " እንዲያውም መበደር እንደ ሱስ ሆኖባቸው ነበር " »

« በውነቱ ይህን ያህል ገንዘብ የሚያስወጣ እስከዚህ ድረስ ዕዳ የሚያስግባ ችግር አልነበረውም " በሉ እስኪ ወደ ዋናው ነገር እንመለስና ሚስተር ዋርበርተን ... ከባንክ ምን ያህል ገንዘብ እንዳለ ብትነግረን » አለ ኧርሎ

« ምንም የለም የዛሬ ሁለት ሳምንት አንድ አስቸኳይ ዕዳ ልንከፍልላቸው ገንዘቡን ስናወጣው ጥቂት አስቀረን " በርግጥ አንድና ሁለት ሳምንት ቢቆዩ ኖሮ የዚህ ወር ኪራይ ይገባ ነበር ያም ቢሆን ከመግባቱ ከፍሎ ያልቅ ነበር » አለ ጠበቃው "

« ጥቂት ማስቀረታችሁም ኧረ በጣም ደስ የሚል ነው ። ለመሆኑ ስንት ነው ? »
« ጌታዬ » አለ ወርበርተን ራሱን በቅሬታ እየነቀነቀ" ያስቀረነው ገንዘብ እኛ ከኪሳችን ስናወጣው የነበረውን ገንዘብ ግማሹን እንኳን አይሸፍንም »

« እንዴ ታዲያ አሁን ለቀብሩ ማስፈጸሚያ አአሽከሮች ደሞዝ ለሌላውም ወጭ ሁሉ የሚያስፈልው ንዘብ ከየት ሊመጣ ነው ? » አለ ኧርሎ "

« ከየትም ሊመጣ አይችልም » መለሰ ዋርበርተን
👍15😱1
« የተረገመ " አሳብ የለሽነት » አሳፋሪ ብኩንነት ጨካኝ ልበ ድንጋይ ወስላታ ሆኖ መኖር ለማኝ ሆኖ መሞት ' ሴት ልጁን ከባዕዳን እጅ መጣል ! » እያለ ምርር ብሎ አዘነ አዲሱ ኧርል ።

« የሷ ነገር መቸ በዚህ ያበቃል ? » አለ ሚስተር ካርላይል » «ስለ መኖሪያዋስ ምን ይሻላታል ? »

« ሌላ ምን ታደርጋለች ? ከኔ ጋር ትቀመጣለች እንጂ ለሷም ሳይሻላት አይቀርም " ምክንያቱም ይህን ሁሉ ዕዳና የዕዳ ሰነድ ተሸክሞ የሎርድ ማውንት እስቨርን ቤት ጽጌረዳ አበባ የተጐዘጐዘበት ምቹ ሊሆንላት አይችልም ነበር »

«ስለ ነበረው ሁኔታ ስለ አባቷ በዕዳ መወጠር ልጂቱ የምታውቅ አልመሰለኝም »

ሚስተር ካርላይል እውነቱን ነው " እሷ ምንም አታውቅም ምንም ችግር አላየችም " የኢስት ሊን ሽያጭም ብዙ ነገሮችን ሸፍኗል " ለጊዜው ከብዙ ችግር አድኗል " አሁን ግን ደንታ ቢስነታቸው ሁሉ አክትሟል » አለ ወርበርተን
«ምን ያከትማል ! መዘዙ አስካሁን እየተጎተተ ገንዘባቸው የተወሰደባቸው ሰዎች ትናንት እዚህ ድረስ መጥተው ነበር አሉ »

« እሱንማ ኢስት ሊንና ወንበር ጠረጴዛ የመሳሰሎት የቤት ዕቃዎች ሁሉ የኔ መሆናቸውን በስንት መከራ አግባብቼ ሳስረዳቸው አሁን ከፎቅ ላይ ራሴውን ይዘው አንለቅም የሚሉትን ሁለት ሰዎች ብቻ ማስወጣት አቃቶኝ »

ኧርሎ ትክ ብሎ ተመለከተው የምትለው አልገባኝም » አለው

« እሬሳው በዕዳ መያዙን አላወቁም እንዴ ? ሁለት ሰዎች ከሬሳው አጠገብ ተቀምጠው አንለቅም ብለው ይኸው ከትናንት ጧት ጀምረው አሉ " ሁለቱን ከ
ተራ የሚያፈራርቅና ምሳ እስኪበሉ የሚጠብቅ አንድ ሌላም ሶስተኛ ሰውም አላቸው . .

«ሚስተር ካርላይል የምትለው በትክክል ገብቶኛል ? የሟቹ ኧርል አስክሬን በእዳ ተያዘ ? የሞተ ሰው መያዝ ? »

« መቼም ይኸው አድርገዋል " መጀመሪያ በዘዴ ወደ ክፍሉ ገቡና አንለቅም አሉ።

« ለመሆኑ እንዶዚህ ያለ አሳፋሪ ሥራ በሕጋችን ይፈቀዳል ? የሞተ ሰው መያዝ ? እኔ እንዲህ ያለ ጉድ ሰምቸ አላውቅም " ምን ለማድረግ ነውኮ ? ልንቀብረውም
አንችልም ማለት ነው?ብዬ እሠጋለሁ "
እንዲያውም ሳጥኑንም አናሳሽግም ብለዋል አሉ ስለዚህ እሽጋቱ ቢፋጠን ይሻላል »

« እንደዚህ የሚያደርው ማነው ? አውቃችሁታል ? » አለ ዋርበርተን

« አንድ አንበተይ የተባለ ሰው ነው ሁኔታዎችን ለመረዳት ከዚያው ክፍል ገብቸ ነበር " እነሱ እንዲሰጣቸው የጠየቁት | ሦስት ሺ ፓውንድ ያህል ነው "አለ
ሚስተር ካርላይል “

« አንስተይ ከሆነስ የኧርሉ ትክክለኛ የግል ዕዳ ነው " ይኸን ዘዴ ምን ሲል አሰበ ? ተንኮለኛ ሰው ነው » አለ ወርበርተን
« ይኸ ትንሽ እንኳን ኃፍረት የማይሰማው ወራዳ ሰው ነው» አለ ሎርድ ማውንት አስቨርን «መቸስ ግሩም ብሎ ዝም ነው እንጂ ሌላ ምን ይደረጋል " ሰውየው ግን ጥቂት እንኳን ይሉኝታ ያልፈጠረበት ወራዳ ነው» አለ ሎርድ ማውንት
እስቨርን "

አነሱ በዚህ ጉይ ምን ማድረግ እንዳለባቸ ሲመካከሩ ፡ ሳቤላ በኀዘንና በሐሳብ ተውጣ ሰማይ ተደፍቶባት ተቀምጣለች ሎርድ ማውንት እስቨርን ከእርሱና ከሚስቱ ጋር አብራ መኖር እንዳለባት ነግሯታል ላፏ ብታመሰግነውም እሱ
ሲወጣ ዕንባዋ ዐይኗ እስኪፈርጥ ይወርድ ጀመር " « ከሚስዝ ቬን ጋር ከመኖር ለምን ለአንዱ ግርድና ተቀጥሬ ፍርፋሪ በልቸ ውሃ ጠጥቸ አልኖርም ከሏ ጋር ከመኖር መሞት ይሻላል » ይህ የወጣት ሴቶች ጠባይ ነው " የማይሆነው ሐሳብ ሁሉ ሲመጣላቸው የሚሆን ይመስላቸዋል " በተለይ ሳቤላ ደግሞ ታበዛዋለች " ከሰው ቤት ገብቶ እየሠሩ መኖር ሲያስቡት ቀላል ነገር ሊመስል ይችላል ነገር ግን ሐሳብና ተግባር የጨለማና የብርሃን ያህል የሚፈራራቁበት ጊዜ አለ " ደግነቱ አማራጭ አግኝታለች " ሎርድ ማውንት እስቨረን የሰጣትን ጥግኝነት ተቀብላ ከሚስ ሼን ጋር መኖር ነበረባት " እንዲያውም እሱስ ወዲያው አሳፍሮ ወደ ካስል ማርሊንግ ሊልካት ነበር » እሷ አይሆንም አለችና ከቀብሩ በኋላ እንድትሔድ ተወሰነ" ለጊዜው ስታስበው አንግፈግፋት - ነገር ግን የብሶቷን ያህል ብዙ ብትናገርም ከዛያ የተሻለ ዕድል እንዶሌላት ተንዝባ ለመሔድ ተስማማች "...

💫ይቀጥላል💫
👍15
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ስድስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...የሰጠቸው አስተያየት ልባችንን ሊያሞቅ የሚገባው ቢሆንም የእኔን ልብ ግን ድምጽዋ ቀዝቃዛና ግድ የለሽ ነበር፡ በእሷ የውሸት አስተያየት በቀላሉ የምንታለልና አለመደሰቷን የሚረዳ አእምሮ የሌለን አድርጋ ቆጥራናለች ማለት ነው! ብዬ እያሰብኩ ሳለ ቀጥሎ የተናገረቻቸው ቃላት
የሀሳቤን ትክክለኛነት አረጋገጡልኝ፡....

“ጭንቅላታቸው እንደሚሰራ እርግጠኛ ነሽ? ሌላ በአይን የማይታይ የሆነ ጉድለት የለባቸውም?” እናቴ ልክ እንደ እኔ ንዴቷን ውጣ “ምንም እንከን
የለባቸውም እንደምታይው ልጆቼ በአካልም ሆነ በአእምሮ ፍፁም
ጤነኛ ናቸው” አለች ከዚያ ያችን ግራጫ የለበሰች አሮጊት አተኩራ ተመለከተቻትና ከመራመድ ብዛት እግሯ ያበጠባትን የኬሪን ልብስ ልትቀይር ዞራ ተረከዟ ላይ ቁጢጥ አለች እኔም ኮሪ ፊት ለፊት በርከክ ብዬ የጃኬቱን ቁልፍ መፍታት
ጀመርኩ። ክሪስቶፈር ደግሞ አንደኛውን ሻንጣ ከፈተና ሁለት ትናንሽ ቢጫ የሌሊት ልብሶች አወጣ።

ኬሪ የሌሊት ልብሱን እንዲቀይር እያገዝኩት አሮጊቷን አየት አደረግኳት ከሁኔታው ይህች ረጅምና ግዙፍ ሴት አያታችን እንደሆነች ገመትኩ
አሻግሬ እየተመለከትኳት ፊቷ ላይ የተጨማደደ ቆዳ ለማየት ብፈልግም መጀመሪያ የገመትኩትን ያህል አሮጊት እንዳልሆነች አወቅኩ። ፀጉሯ ደስ
በማይል አይነት ከፊቷ ወደ ኋላ በመሰብሰቡ አይኖቿን የፈጠጡና የድመት አስመስሏቸዋል። እያንዳንዱ የፀጉሯ ዘለላ እንዴት ቆዳዋን እንደጎተተው ማየት ይቻላል።

አፍንጫዋ የአሞራ መንቆር ይመስላል፤ ትከሻዋ ሰፊ ሲሆን ከንፈሯ ስስ ሆኖ አፏ በቢላ የተሰነጠቀ ጭረት መሰል ነበር። ቀሚሷ ግራጫ ሆኖ ጠበብ
ካለው አንገትጌው ላይ የአልማዝ ጌጥ አለበት፡ አንዱም ነገሯ ለስላሳና ማራኪ አይደለም፡ ጡቶቿ ሳይቀሩ መንታ ኮረብታዎች የሚመስሉ ናቸው:
ከእናታችንና ከአባታችን ጋር እንደምንጫወተው ከእሷ ጋር ቀልድ የማይታሰብ ነው።

አልወደድኳትም። ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ። ቤቴ መሄድ ፈለግኩ። እንደገና አባቴ በህይወት እንዲኖር ፈለግኩ፡ እንደዚች አይነት ሴት እንዴት እንደ
እናታችን አይነት ተወዳጅና ጣፋጭ ሴት ልትወልድ ቻለች? እናቴ ቁንጅናዋንና ለዛዋን ከማን ወርሳ ነው? እየተንቀጠቀጥኩ በአይኖቼ የሞሉት እምባዎቼ እንዳይወርዱ ሞከርኩ። እናታችን ወንድ አያታችን ለሰው ፍቅር
የሌለው፣ ግድ የለሽና ተቆጪ እንደሆነ አስቀድማ በመንገር አዘጋጅታን ነበር።ነገር ግን መምጣታችንን ያመቻቸችው ሴት አያታችንም መጥፎ የመሆኗ
ነገር አስገራሚ ነበር፡

ደንግጦ የነበረው ክሪስቶፈር አይቶኝ በኋላ እንዳይቀልድብኝ አይኖቼን በማርገብገብ እምባዎቼን መለስኳቸው: እናታችን ግን ሁሉ መልካም የሚሆን
ለመሆኑ ማረጋገጫ እንዲሆነን ኮሪን ትልቁ አልጋ ላይ ስታስተኛው በደስታ ፈገግ ብላ ነበር ከዚያ ኬሪንም ከእሱ አጠገብ አስተኛች እዚያ አልጋ ላይ ሮዝ ጉንጭ ያላቸው ትልቅ አሻንጉሊቶች መስለው ተኝተው ሲታዩ እንዴት
እንደሚያምሩ። እናታችን የመንትዮቹን ጎንጮች ሳመችና በእጆቿ ግንባራቸው ላይ የተኛውን ፀጉራቸውን በእጇ ወደ ኋላ መለሰችላቸው: ከዚያ የአልጋ
ልብሱን ወደ አገጫቸው ከፍ አድርጋ ሁላችንም በምናውቀው ጣፋጭ ድምፅዋ
“ደህና እደሩ የኔ ውዶች" ስትል አንሾካሾከች መንትዮቹ አልሰሟትም፡ ገና ድሮ እንቅልፍ ወስዷቸው ነበር።

እንደተተከለ ዛፍ ቀጥ ብላ ቆማ መንትዮቹ ሲተኙ እንዲሁም እኔና ክሪስቶፈር ተጠጋግተን ስንቀመጥ እያየች የነበረችው አያታችን ደስ እንዳላት በግልፅ ያስታውቃል በጣም ስለደከመን ተደጋግፈን ተቀምጠናል። እንደ ድንጋይ
ከጠነከሩት አይኖቿ ውስጥ የሚነበበው ነገር ደስ አይልም ያልተስማማት አንድ ነገር እንዳለ ከአስተያየቷ መረዳት ይቻላል፡ ፊቷን አጨፍግጋ ዘልቆ
የሚገባ በሚመስል አስተያየት እያየችን የመሆኑ ነገር ለእናቴ የሰጣት የሆነ መልእክት ያለ ይመስላል፡ ወዲያው “ሁለቱ ያደጉት ልጆችሽ አንድ አልጋ ላይ
መተኛት አይችሉም” ስትላት እናቴ ፊቷ በንዴት ደም መሰለ።

እናታችን ባልተለመደ ኃይለኝነት “ገና ልጆች እኮ ናቸው። እማዬ ትንሽ እንኳን አልተቀየርሽም አይደል? አሁንም አስቀያሚ ተጠራጣሪ አእምሮ ነው
ያለሽ፡ ክሪስቶፈርና ካቲ ምንም አያውቁም” አለች።

“ምንም አያውቁም!?” በቁጣ መለሰች፡ የክፋት አስተያየቷ ደም የሚያፈስ ስለት ይመስል ነበር። “እኔና አባትሽም ስለአንቺና ስለ አጎትሽ ሁልጊዜም የምናስበው እንደዚያ ነበር።”

አይኖቼ በሰፊው ተከፍተው ከአንደኛቸው ወደ ሌላኛቸው ተንከራተቱ፡ ወደ ወንድሜ ሳማትር ከእድሜው ላይ አመታት የተቀነሱ ይመስል ልክ እንደ ስድስትና ሰባት አመት ህፃን ረዳት አልባ መስሏል። ከእኔ የበለጠ እንዳልገባው ያስታውቃል።

የሚፋጅ ቁጣ የእናታችንን ቀለም ለዋወጠው “እንደዚያ ካሰብሽ የተለያየ ክፍልና የተለያየ አልጋ ስጫቸዋ! እዚህ ቤት ውስጥ በቂ ክፍል እንዳለ የታወቀ ነው”

“ያ የማይቻል ነው! አጠገቡ መታጠቢያ ያለውና ወዲያ ወዲህ ሲሉ ወይም የሽንት ቤት ውሀ ሲለቁ ባለቤቴ የማይሰማበት ብቸኛ ክፍል ይሄ ብቻ ነው፡ የተለያየ ክፍል ውስጥ ከሆኑ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ድምፃቸው ወይም ጩኸታቸውን ይሰማል ሰራተኞቹም ሊሰሙ ይችላሉ። ይህንን ክፍል ያመቻቸሁት ብዙ ካሰብኩበት በኋላ ነው ደህንነቱ የተጠበቀ ብቸኛው ክፍል
ይህ ብቻ ነው:" አለች አያታችን እንደ በረዶ በቀዘቀዘ ድምፅዋ።

“ደህንነቱ የተጠበቀ?” ሀያ፣ ሰላሳ፣ አርባ ክፍሎች ባሉበት ትልቅ ቤት ውስጥ ሁላችንም በአንድ ክፍል ውስጥ ታጭቀን እያደርን? በአንድ ክፍል ውስጥ እየኖርን? ቢሆንም ግን አሁን ሳስበው በዚህ ግዙፍ ቤት ብቻዬን አንድ ክፍል
ውስጥ መሆን አልፈልግም
“ሁለቱን ሴቶች አንዱ አልጋ ላይ፣ ሁለቱን ወንዶች ደግሞ ሌላኛው አልጋ ላይ አስተኚ” ስትል አዘዘች
እናታችን ኮሪን አንስታ ሌላኛው አልጋ ላይ አስተኛችው ከያ በኋላ ቀስ በቀስ ሁሉም ነገር አያትየው እንዲሆን እንደምትፈልገው ሆነ። ወንዶቹ ለመታጠቢያ ቤቱ ቅርብ የሆነው አልጋ ላይ፣ እኔና ኬሪ ደግሞ መስኮቱ አጠገብ ያለው አልጋ ላይ ሆንን።

አሮጊቷ እይታዋን መጀመሪያ ወደ እኔ ከዚያ ደግሞ ወደ ክሪስቶፈር አደረገች ከዚያ ልክ እንደ አዛዥ ወታደር መናገር ጀመረች። “ስሙ! ትንንሾቹን ልጆች ፀጥ እንዲሉ ማድረግን የእናንተን የትልልቆቹ ሀላፊነት ይሆናል፤ ከማወጣቸው
ህሃጎች አንዱንም እንዳትጥሱ የምለውን በጥንቃቄ በአእምሯችሁ ያዙ።
ክፍሉንና መታጠቢያ ቤቱን ልክ ሰው የማይኖርበት በሚመስል አይነት በንፅህና መያዝ ይጠበቅባችኋል። ፀጥ ማለት ግዴታ ነው! መጮህ፣ ማልቀስ ወይም መሮጥ አይቻልም ከዚህ ክፍል ወጥታችሁ መሄድ ስለማይፈቀድና በምንም
ምክንያት ወደ ቤቱ ሌላኛው አካባቢ እንድትሄዱም ስለማልፈልግ እናታችሁና
እኔ አሁን ከዚህ ስንወጣ በሩን ከውጪ እቀረቅረዋለሁ። ወንድ አያታችሁ እዚህ መኖራችሁን ካወቀ በህይወት በመኖራችሁ ብቻ በአስከፊ ሁኔታ ከቀጣችሁ በኋላ አንዲት ሳንቲም ሳይሰጣችሁ አስወጥቶ ይወረውራችኋል!
ስለዚህ እሱ እስከሚሞት ድረስ እዚህ ትቆያላችሁ: ግን እዚህ እንደሌላችሁ ትቆጠራላችሁ”
👍324
ወይኔ አምላኬ! አይኔን ወደ እናቴ ወረወርኩ፡ እውነት ሊሆን አይችልም!እየዋሸች ነው አይደል? እንደዚህ የምትለን ልታስፈራራን ነው ወደ ክሪስቶፈር ተጠግቼ ጎኑ ላይ ልጥፍ አልኩ፡ ብርድ ተሰምቶኝ እየተንቀጠቀጥኩ ነበር።አያታችን ቷን ስትከሰክስ ቶሎ ብዬ ራቅ አልኩ እናቴን ለማየት ስሞክር ጀርባዋን አዙራና ጭንቅላቷን ዝቅ አድርጋ እያለቀሰች እንደሆነ በሚያስታውቅ
ሁኔታ ትከሻዋ ሲነቃነቅ ይታያል
በፍርሀት ተሞላሁ: ምስጋና ለሚያጠጋጉን ክንዶቿና ፀጉራችንንና ጀርባችንን
ለሚዳብሱን እጆቿ ይሁንና እናታችን ወደ እኛ ዞራ አልጋው ላይ ባትቀመጥና ለእኔና ለክሪስቶፈር ክንዶቿን ባትዘረጋልን ኖሮ መጮኼ አይቀርም ነበር።

ወደ እሷ ሮጥን፡ “አይዟችሁ እዚህ የምትሆኑት ለአንድ ምሽት ብቻ ነው እመኑኝ አባቴ ቤቱ እንድትኖሩ ይቀበላችኋል፡ ከዚያ የአትክልት ስፍራውን ሳይቀር ሁሉንም እንደራሳችሁ ቤት እንድትጠቀሙበት ይፈቅድላችኋል:" አለች:

ከዚያ በጣም ረጅም፣ በጣም ግትርና ሁሉንም ከልካይ ወደሆነችው እናቷ ዞረች፡ “እማዬ ለልጆቼ ትንሽ ሀዘኔታ ይኑርሽ የአንቺ ስጋና ደም ናቸው።
ጥሩ ልጆች ናቸው፡ እንደማንኛውም ልጅ መጫወት፣ መሮጥና መጮህ ያስፈልጋቸዋል እንዴት በሹክሹክታ እንዲነጋገሩ ትጠብቂያለሽ? በዛ ላይ አዳራሹ መጨረሻ ላይ ያለውን በር ከቆለፍሽው ስለሚበቃ የዚህን ክፍል በር መቆለፍ አያስፈልግሽም ለዚህ አሮጌ ክፍል ብዙም ግድ እንደሌለሽ አውቃለሁ ታዲያ በዚህ በቀኝ በኩል ያሉትን ክፍሎች ለምን እንደራሳቸው አድርገው እንዲጠቀሙበት አትፈቅጂላቸውም?” አለቻት፡

አያትየው ባለመስማማት ጭንቅላቷ ነቀነቀች። “ኮሪን… እዚህ ቤት ውሳኔ የማስተላልፈው እኔ እንጂ አንቺ አይደለሽም! በዚህ በኩል ያለውን በር ብቻ
ስዘጋ ሰራተኞቹ ለምን ብለው አያስቡም ብለሽ ትጠብቂያለሽ? አይሆንም! ሁሉም ነገር እንደነበረ ይቆያል፡ ወደ ጠባቡ መንገድ የሚያወጣው ደረጃ በዚህ
በኩል ስለሆነ ይህንን ክፍል በተለየ ለምን እንደምቆልፍ ይገባቸዋል። ልጆችሽ
መሆን በማይገባቸው ቦታ እንዲሆኑ አልፈልግም። በጣም በማለዳ ምግብ አብሳዩዋና ሠራተኞቹ ወደ ወጥ ቤት ከመግባታቸው በፊት ምግብና ወተት አመጣላቸዋለሁ። ይህ የሰሜኑ የቤቱ ክፍል በእያንዳንዱ ወር የመጨረሻ አርብ ላይ ለማፅዳት ካልሆነ በስተቀር ሰው አይገባበትም፡ በነዚያ ቀናት
ሠራተኞቹ ፅዳት እስኪጨርሱ ድረስ ልጆቹ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ መደበቅ አለባቸው: ሠራተኞቹ ሊያፀዱ ከመግባታቸው በፊት ደግሞ እኔ ራሴ እዚህ መኖራቸውን የሚያሳይ ምንም ነገር አለመተዋቸውንና በእርግጥም መደበቃቸውን አረጋግጣለሁ”

እናታችን ተቃወመች: “የማይሆን ነገር ነው! ቢያንስ ወደ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል እንዲሄዱ ምልክት ስጫቸው: እና ደግሞ እማዬ… እባክሽ አዳራሹ
መጨረሻ ላይ ያለውን በር ብቻ ቆልፊ!”

አያትየው ጥርሷ ነከሰች። “ኮሪን ጊዜ ስጪኝ! ሠራተኞቹ ወደዚህ ክፍል ለማፅዳትም ቢሆን እንኳን ለምን መግባት እንደሌለባቸው ምክንያት ለማዘጋጀት ጊዜ ያስፈልገኛል። ጥርጣሬ እንዳያስነሳ በጥንቃቄ ማሰብ አለብኝ:: ሰራተኞቹ እኔን አይወዱኝም፡ ስለዚህ አባትሽ ሽልማት እንደሚሰጣቸው
ተስፋ በማድረግ ሄደው ያልሆነ ነገር ሊነግሩት ይችላሉ የዚህኛው የቤቱ ክፍል በር ከተዘጋ ግን ማንም ከአንቺ መመለስ ጋር የሚያገናኘው የለም

እናታችን በመሸነፍ ጭንቅላቷን ነቀነቀች እሷና አያትየው ሲመካከሩ እኔና ክሪስቶፈር እያንቀላፋን ነበር። የማያልቅ የሚመስል ቀን ነበር። ከኬሪ ጎን
አልጋ ውስጥ መግባትና ችግሮች ወደሌሉበት ጣፋጭ እንቅልፍ ውስጥ መግባት ፈልጌያለሁ።

በመጨረሻ አታስተውለውም ብዬ ተስፋ በቆረጥኩበት ጊዜ እናታችን
ክሪስቶፈርና እኔ ምን ያህል እንደደከመን አስተዋለችና ልብሳችንን መታጠቢያ
ቤት ውስጥ ሆነን እንድንቀይር ተፈቀደልን፡ በመጨረሻ አልጋችን ውስጥ ገባን።

እናታችን አይኖቿ ፈዝዘው የደከማትና የተጨነቀች መስላ ወደ እኔ መጣችና በሞቃት ከንፈሮቿ ግንባሬ ላይ ሳመችኝ። አይኖቿ ጠርዝ ላይ እምባ ተመለከትኩ። የተቀባችው ማስካራ እንባዋን ወደ ጥላሸት ቀይሮታል።ለምንድነው በድጋሚ የምታለቅሰው?

“ተኚ…” አለችኝ በሽካራ ድምፅ። “አሁን ለሰማሽው ነገር ትኩረት አትስጪ። አባቴ ይቅር ሲለኝ እጆቹን ከፍቶ የልጅ ልጆቹን ይቀበላል። ለረጅም ጊዜ
ሳያያቸው የቆየውን የልጅ ልጆቹን ያያል”

ኮስተር ብዬ “እማዬ ለምንድነው ዝም ብለሽ የምታለቅሽው?” አልኳት።

ፈጠን ብላ እምባዋን ጠራረገችና ፈገግ ለማለት ሞከረች። ካቲ... የአባቴን ይቅርታና ፍቅር ለማግኘት ብዙ ጊዜ ሊወስድብኝ ይችላል ብዬ ስለፈራሁ ነው" አለችኝ፡

“ብዙ?”

“ምናልባት ሳምንት ግን ከዚያ በላይ አይሆንም: እንዲያውም ከዚያ ባነሰ ይሆናል: እውነቱን ለመናገር በትክክል አላውቀውም. ግን ብዙ እንደማይሆን ላረጋግጥልሽ እወዳለሁ” ለስላሳ እጆቿ ፀጉሬን እየዳሰሱኝ ነበር። “የኔ ውድ ካቲ… አባትሽ በጣም ይወድሽ ነበር፤ እኔም እወድሻለሁ:” ከዚያ ወደ ክሪስቶፈር ሄዳ ግንባሩን ሳመችውና ፀጉሩን ዳሰሰችው። በሹክሹክታ የነገረችውን ግን መስማት አልቻልኩም

በሩ ጋ ስትደርስ ዞር አለችና “መልካም የሌሊት ዕረፍት ይሁንላችሁ!በቻልኩት ፍጥነት ቶሎ እመጣለሁ፡ እቅዴን እንደምታውቁት መጀመሪያ
ወደ ባቡር ጣቢያው ሄጄ ወደ ቻርለትቪል የሚሄደውን ባቡር እይዛለሁ።እዚያ እንደደረስኩም ሁለቱን ሻንጣዎቼን ይዤ በጠዋት በታክሲ እመለስና በተቻለኝ መጠን እናንተን ለማግኘት እሞክራለሁ” አለችን።

አያትየው እናታችን እንድትወጣ ፈልጋ በጭካኔ ወደ ውጪ ጎተተቻት።እናታችን ግን ፊቷን ወደኛ መልሳ በትከሻዋ በኩል እየተመለከተችን “እባካችሁ
ጥሩ ልጆች ሁኑ። ፀባያችሁን አሳምሩ አያታችሁንና ያወጣቻቸውን ህጎች አክብሩ። በተቻለ መጠን እናንተን ለመቅጣት የሚያስችል ምንም አይነት ምክንያት እንዳትሰጧት ተጠንቀቁ እባካችሁ… መንትዮቹም በስርአት እንዲታዘዙ አድርጉ፡ እንዳያለቅሱና እኔንም ብዙ እንዳይናፍቁኝ የተቻላችሁን
አድርጉ: አሁን ያላችሁበትን ሁኔታ እንደ ጨዋታ ቁጠሩት፤ አሻንጉሊቶችና መጫወቻዎች ይዤላችሁ እስክመለስ ድረስ መንትዮቹን ለማዝናናትም
የተቻላችሁን አድርጉ፡ ነገ እመለሳለሁ። በሄድኩበት ሁሉ በየሰከንዱ አስባችኋሁ እፀልይላችኋለሁ እወዳችኋለሁ።” አለች።

እንደ መልአክ ታዛዥና የተጣለብንን ህግ ሁሉ አክባሪ ለመሆን ቃል ገባን ለመንትዮቹ የተቻለንን እናደርጋለን። እኔ ደግሞ አይኖቿ ላይ ያለውን ሀዘን
ለማጥፋት ምንም ነገር አደርጋለሁ። ምንም ነገር እሆናለሁ። ሁለታችንም
“ደህና እደሪ እማዬ” አልን፡ “ስለእኛ አትጨነቂ ደህና እንሆናለን፡ ለመንትዮቹ
ምን ማድረግ እንዳለብንና ራሳችንን እንዴት እንደምናዝናና እናውቃለን ከአሁን በኋላ ትንንሽ ልጆች አይደለንም:" ይህንን ሁሉ ያለው ወንድሜ ነበር።

አያትየው “ነገ በማለዳ ታገኙኛላችሁ" አለችና እናታችንን ወደ አዳራሹ ገፋቻትና በሩን ቆለፈችው ልጆች በመሆናችንና ብቻችንን ስለተቆለፈብን ፈራን፡፡ እሳት ቢነሳስ? ስለ እሳትና
እንዴት እንደምናመልጥ እያሰብኩ ነው: እዚሁ እንደተቆለፈብን ለእርዳታ ብንጮህ እንኳን ማንም አይሰማንም: በዚህ በተረሳና ሰው እንዳይደርስበት በተhለከለ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ባለ በወር አንዴ በመጨረሻው አርብ ብቻ ሰው
በሚመጣበት ክፍል ውስጥ ሆነን ማን ይሰማናል?
👍19
ለአንድ ምሽት ብቻ በመሆኑ እግዚአብሔር ይመስገን: ነገ እናታችን እየሞተ ያለውን አያታችንን ታሳምነዋለች:
አሁን ብቻችንን ነን፡ ተቆልፎብናል። መብራቶቹ ሁሉ ጠፍተዋል። ይህ
ትልቅ ቤት አፉ ውስጥ ባሉ ሹል ጥርሶቹ የያዘንና ከተንቀሳቀስን፣ ካወራን ወይም በሀይል ከተነፈስን የሚበላንና የሚውጠን ጭራቅ ይመስል ነበር።

በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ጭንቅላቴ ትራስ ላይ አርፎ ቶሎ እንቅልፍ ሳይወስደኝ ቀረ። እንደተጋደምኩ የፈለግኩት እንቅልፍ እንጂ በማያልቅ ሁኔታ
የተዘረጋ ረጅም ፀጥታ አልነበረም። ክሪስቶፈር ግን ፀጥታውን ሰበረውና ስለ
ሁኔታው በሹክሹክታ መወያየት ጀመርን።

አይኖቹ ላይ ያለው እርጥበት በድንግዝግዙ ብርሃን ያንፀባርቃል። “ያቺ አያት
የተባለችው ሴት የምትመስለውን ያህል ክፉ ልትሆን አትችልም:" አለ
በቀስታ።

“አሮጊቷ ጥሩ እንደሆነች አላስብም እያልክ ነው?”

“አዎ ልክ ነሽ”

“ግን እንዴት ትልቅ ናት! ቁመቷ ስንት ይመስልሀል?”

“መገመት ይከብዳል ምናልባት ስድስት ጫማና ሁለት መቶ ፓውንድ።”

“ሰባት ጫማ! አምስት መቶ ፓውንድ”

“ካቲ አንድ ነገር መማር አለብሽ፤ ትንንሽ ነገሮችን ትልቅ ማድረግና ማጋነን አቁሚ! አሁን ያለንበትን ሁኔታ በደንብ ተመልከቺ እናታችን ተመልሳ እስክትመጣ ድረስ አንድ ምሽት እዚህ ማሳለፋችን ግድ ነው ስለዚህ ይሄ አንድ ትልቅ ቤት ውስጥ ያለ ክፍል እንጂ በጭራሽ የሚያስፈራ ነገር አለመሆኑን አስተውይ" አለኝ፡

“ክሪስቶፈር፣ አያትየው አጎት ስላለችው ነገር ሰምተሀል? ምን ማለቷ እንደሆነስ ገብቶሀል?”

“አልገባኝም፡ ግን እማዬ ስትመጣ ሁሉንም ነገር ታስረዳናለች። አሁን ተኚ። ደግሞ ፀልዩ! ማድረግ የምንችለው ይህንን ብቻ ነው አይደል?”

ከአልጋ ውስጥ ወጥቼ ተንበረከኩና እጆቼን አጣጥፌ አገጬ ስር አደረግኩ
ከዚያ አይኖቼን ጨፍኜ እግዚአብሔር እናታችንን የምትወደድና አሸናፊ
እንዲያደርጋት ፀለይኩ፡ “እና እግዚአብሔር እባክህ ወንድ አያትየው እንደሚስቱ በጥላቻ የተሞላና ክፉ እንዲሆን አታድርግ” አልኩ።

ከዚያ በሃሳቦቼ ውስጥ ሰጥሜና ተዳክሜ ወደ አልጋዬ ተመለስኩና ኬሪን ወደ ደረቴ አስጠግቼ አቀፍኳት ወዲያው ልክ እንደፈለግለኩት ህልም ውስጥ ወደቅኩ።

ይቀጥላል
👍35🤔2
#ላባቴ

የማትንበረከክ
የማትርመጠመጥ
ከባለጌ ዙፋን
በርጩማ የማትመርጥ፡፡
ያለ ባህር ሰርጓጅ ያለ ሙሴ በትር
በመታገስ ብቻ ፣ባህር የምትመትር፡፡

ካዘልከኝ ጀምሮ ፣እንኮኮ ጫንቃህ ላይ
ከፍታውን እንጅ፣ ዝቅታውን እንዳላይ
እንደ ንሥር መጠቅሁ፣ እንደ ምስራቅ በራሁ
የገዛ ክንፎቼን ፣እንደ ዳንቴል ሠራሁ፡፡
በርግጥ ደሀ ነበርህ…
ከሰላምታ በቀር የማታበረክት
ነጠላህ መናኛ፣ሰውነትህ የክት
በርግጥ ድሀ ነበርህ
የነጣህ፣ የጠራህ
ከጦርሜዳ ይልቅ ገበያ ሚያስፈራህ፡፡
ቤሳ ባታወርሰኝ አወረስከኝ ትግል
የትም እንዳይጥለኝ ፣ሕይወት እንደ ፈንግል፡፡
አባየ ብርሀን
አባ የምስራቅ በር
ገመና ሸሻጊ፣እንደ ካባ ገበር
አባቴ ባትሆን ይጸጽተኝ ነበር፡፡

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
34👍18
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰባት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የአያቶቻችን ቤት

ቀኑ እንዳንከፍት ከተከለከልነው መስኮትና ሙሉ በሙሉ ከሸፈነው ከባድና ትልልቅ መጋረጃዎች ጀርባ ደብዛዛ ብርሃኑን በማሳየት መንጋቱን እየነገረን ነው: ክሪስቶፈር እያዛጋና እየተንጠራራ አልጋው ላይ በመቀመጥ ወደ እኔ
እየተመለከተ “ሰላም ጨብራሪት” አለኝ፡ የእሱም ፀጉር ከእኔ በባሰ ተንጨባሮ ነበር ፀጉሩ ያምራል፡ እግዚአብሔር ለእኔና ለኬሪ ቀጥ ያለ ፀጉር ሰጥቶን ለኮሪና ለእሱ እንደዚህ አይነት የሚጠቀለል ጸጉር ለምን ሊሰጣቸው እንደመረጠ አልገባኝም: ድሮ የተጠቀለለውን ፀጉሩን ሲያበጥር አጠገቡ ተቀምጬ ፀጉሩ
ከእሱ ላይ ተነቅሎ እኔ ጭንቅላት ላይ እንዲሆን እመኝ ነበር።

ከተኛሁበት ተነስቼ ተቀመጥኩና ምናልባት አስራ ስድስት በአስራ ስድስት የሚሆነውን ክፍል ዙሪያውን ተመለከትኩት። ውስጡ ሁለት ትልልቅ አልጋዎች፣ ሰፊ የልብሰ ማስቀመጫ መሳቢያ፣ ትልቅ የልብስ ማስቀመጫ
ቁምሳጥን፣ ሁለት ትልልቅ ወንበሮች፣ በሁለቱ መስኮቶች መካከል ከትንሽ ወንበር
ጋር የተቀመጠ የመልበሻ ጠረጴዛ፣ በተጨማሪም በዙሪያው አራት ወንበሮች የተደረጉለት ትልቅ ጠረጴዛ ተጠቅጥቀውበት ክፍሉን ትንሽ አስመስለውታል።
በሁለቱ ትልልቅ አልጋዎች መካከልም መብራት የተቀመጠበት ሌላ ጠረጴዛ
አለ: በክፍሉ ውስጥ አራት መብራቶች አሉ ካረጁት ጥቋቁር ቁሳቁሶች ስር ድሮ በጣም የሚያምር እንደነበረ የሚያስታውቅ ወርቃማ መስመር ያለው ቀለሙ የደበዘዘ አሮጌ ቀይ ምንጣፍ ተነጥፏል። የአልጋ ልብሶቹ ወርቃማ ቀለም ያላቸው ወፍራሞች ናቸው: ግድግዳዎቹ ደብዛዛ ቢጫ የግድግዳ ወረቀት የተለጠፈባቸው ሲሆን ሶስት ስዕሎችም ተሰቅለውባቸዋል። ከስዕሎቹ መሃል ሰይጣኖች ምስኪን ነፍሳትን ሲበሉ የሚያሳየው አንደኛው ስዕል ልብ
ያስደነግጣል። ሰይጣኖቹ ራቁታቸውን የሆኑ ሰዎችን ሲያባርሩ ያለበት የስዕሉ
ክፍል ደማቅ ቀይ ቀለም ተቀብቷል። ነፍሳቱ እግራቸውን እያንፈራገጡ ቢሆንም በረጃጅም አንፀባራቂና ሹል ጥርሶች ከተሞላው የሰይጣናቱ አፍ
ማምለጥ አልቻሉም
ስዕሉን እየተመለከትኩ ሳለ ወንድሜ “ሲኦል ላይ እያፈጠጥሽ ነው? ይህንን ስዕል የሰቀለችው መልአክ የሆነችው አያታችን ራሷ መሆን አለባት አልታዘዝ
ካልን የሚጠብቀን ምን እንደሆነ ልታሳየን ፈልጋ ሳይሆን አይቀርም” አለ ወንድሜ የእውነትም ሁሉን ነገር ሳያውቅ አይቀርም ዶክተር ከመሆን ቀጥሎ የሚፈልገው አርቲስት መሆን ነው የውሀና የዘይት ቀለም በመጠቀም ሲስል እጅግ በጣም ጎበዝ ነው።

ከብዙ መገላበጥ በኋላ ኬሪና ኮሪ አንድ ላይ ነቅተው ማዛጋት ጀመሩ። አይኖቻቸውን አሸት አሸት አደረጉና እንቅልፍ ባልለቀቀው አይናቸው አካባቢውን ቃኙ፡ ከዚያ ኬሪ “እዚህ መሆን አልፈልግም” አለች።

አላስገረመኝም: ኬሪ አፍ ከመፍታቷ በፊትም እንኳን ሀሳቧን መግለፅ የምትወድ ናት አፏንም የፈታችው በዘጠኝ ወሯ ነበር፡ የምትወደውንና የምትጠላውን ታውቃለች: ለኬሪ መሀከል ላይ ብሎ ነገር የለም: ወይ ታች
ነው አለዚያም ላይ ነው፡ ላይ ሰማይ ጥግ፡ ስትደሰት በጣም የሚያምር የትንሽዬ ወፍ የሚመስል ድምፅ አላት፡ ችግሩ እንቅልፍ ካልወሰዳት በስተቀር ስትዘምር መዋሏ ነው። በዚያ ላይ ከአሻንጉሊቶቿ፣ ከሻይ ስኒዎቹና
ከሌሎችም ነገሮች ጋር ታወራለች ምርጫዋ ዝም ብሎ የተቀመጠና መልስ የማይሰጣትን ነገር ማዋራት ነው።

ኮሪ የተለየ ነው። ኬሪ ዝም ብላ ስትለፈልፍ እሱ ቁጭ ብሎ በእርጋታ ያዳምጣታል ወ/ሮ ሲምሰን ኮሪን “ቀስ እያለ ወደ ውስጥ የሚሰርግ የረጋ ውሀ
ነው" ስትለው ትዝ ይለኛል። ይህንን ስትል ምን ለማለት ፈልጋ እንደሆነ አሁንም አይገባኝም: ምናልባት ዝምተኛ ሰዎች ሌሎችን የሚያስገርምና ከላይ ከሚታየው ነገር ስር የሚገኝ ሚስጥራዊ አስተሳሰብ አላቸው ለማለት
ይመስለኛል፡
“ካቲ እዚህ መሆን አልፈልግም ስል ሰምተሸኛል?" አለችኝ ትንሽዋ እህቴ።ኮሪ ይህንን ሲሰማ ከአልጋው ላይ ዘሎ ወረደና ሮጦ ወደ እኛ መጣ ከዚያ
በፍርሃት አይኖቹን አፍጥጦ መንትያ እህቱን እቅፍ አደረጋት ከዚያ ረጋ ብሎ “እዚህ እንዴት መጣን?” ብሎ ጠየቀ፡
“ትናንት ማታ በባቡር ነው የመጣነው አታስታውስም?”
“አይ አላስታውስም”
“በጨረቃ በጫካ ውስጥ እየተራመድን ነበር፡ በጣም ያምር ነበር‥”

“ፀሀዩዋ የታለች? አልነጋም?”

ፀሀዩዋ ከመጋረጃዎቹ ጀርባ ተደብቃለች ያንን ለኮሪ ብነግረው በእርግጠኝነት መጋረጃውን ከፍቶ ወደ ውጪ ይመለከታል አንድ ጊዜ ውጪውን ካየ ደግሞ ውጪ መውጣት ይፈልጋል፡ ምን ማለት እንዳለብኝ አላወቅኩም።

የበሩን ቁልፍ ለመክፈት የሚሞክር የሆነ ሰው መልስ ከመስጠት አተረፈኝ። አያታችን በነጭ ፎጣ የተሸፈነ በምግብ የተሞላ ትልቅ ትሪ ይዛ ወደ ክፍሉ እየገባች ነበር። ትልልቅ ትሪዎችን እየተሸከመች ቀኑን ሙሉ ደረጃውን
ወደላይና ወደታች ስትወጣ እንደማትውል ኮስተር ባለ አነጋገር አስታወቀችን በተደጋጋሚ ከመጣች ሠራተኞቹ ሊያዩዋት ስለሚችሉ ምግብ የምታመጣልን
በቀን አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ተናገረች።

ትሪውን ትንሽዋ ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጠች “ሳስበው hአሁን በኋላ የሽርሽር ቅርጫት እጠቀማለሁ” አለችን፡፡ የምግቡ ሀላፊነት የእኔ እንደሆነ ሁሉ ዞር ብላ ተመለከተችኝና “ይህንን ምግብ ቀኑን ሙሉ እንዲቆይ አድርጊ።ምግቡን ለሶስት ጊዜ ማለትም ለቁርስ፣ ለምሳና ለእራት እንዲሆን አድርገሽ
ከፋፍይ፡ ፍራፍሬዎቹን ደግሞ ከምግብ በኋላ መብላት ትችላላችሁ። እስከ ቀኑ መጨረሻ ድረስ ፀጥተኛና ጥሩ ልጆች ከሆናችሁ አይስክሬምና ኩኪስ
ወይም ኬክ አመጣላችሁ ይሆናል። ከረሜላ ግን በጭራሽ አይታሰብም።
አያታችሁ ካልሞተ በስተቀር ወደ ጥርስ ሀኪም መሄድ የማይታሰብ ስለሆነ ጥርሳችሁ እንዲቦረቦር ልናደርግ አንችልም:”

ክሪስቶፈር ልብሱን ለባብሶ ከመታጠቢያ ቤት ወጣና ምንም ሀዘን ሳይሰማት የባሏን ሞት ቀለል አድርጋ የምታወራውን አያታችንን አፍጥጦ እየተመለከታት
ነበር። ስለባሏ ሳይሆን ቻይና ውስጥ ባለ አንድ የአሳ ማርቢያ ውስጥ እየሞተ ስላለ አሳ የምታወራ ነው የምትመስለው: “ከበላችሁ በኋላ ደግሞ ጥርሳችሁን አጽዱ” ቀጠለች “ፀጉራችሁን በደንብ ማበጠር፣ ሰውነታችሁን ንፁህ ማድረግና ልብሳችሁንም በንፅህና መልበስ አለባቸሁ ፊታቸውና እጃቸው
የቆሸሸና ንፍጣም ልጆች አልወድም”

ይህንን ስትል የኮሪን አፍንጫ የመፀዳጃ ወረቀት በመጠቀም በጥድፊያ ጠረግኩለት ምስኪን ኮሪ አብዛኛውን ጊዜ ሀይለኛ ጉንፋን ስላለበት ንፍጡ
ይዝረበረባል እሷ ደግሞ አፍንጫው ላይ ንፍጥ የሚታይበት ልጅ አትወድም
“መታጠቢያ ቤቱን ስትጠቀሙ ስርዓት መያዝ አለባችሁ: ወንዶችና ሴቶች አንድ ላይ መታጠቢያ ቤት መጠቀም አይችሉም” አለች። ይህንን ስትናገር በተለይ እኔንና የመታጠቢያ ቤቱን የበር ጠርዝ ተደግፎ የቆመውን ክሪስቶፈርን
እየተመለከተች ነበር።

ጉንጮቼ ሲግሉ ታወቀኝ! ምን አይነት ልጆች እንደሆንን ነው የምታስበው?ቀጥሎ ከዚህ በኋላ ደጋግመን የምንሰማውን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ነገረችን፡
“አስታውሱ እግዚአብሔር ሁሉንም ያያል፡ ከጀርባዬ የምትሰሩትን ክፉ ነገር ሁሉ ይመለከታል! እኔ ባልቀጣችሁ እግዚአብሔር ይቀጣችኋል”

ከቀሚሷ ኪስ ወረቀት አወጣችና “በዚህ ወረቀት ላይ እኔ ቤት ውስጥ እስካላችሁ ድረስ ልትከተሏቸው የሚገባችሁ ህጎች ሁሉ ተጽፈዋል። አለች ከዚያ ወረቀቱን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ እንድናነባቸውና በቃላችን እንድናጠናቸው እንደሚገባ አዝዛን ፊቷን አዙራ ልትሄድ ካለች በኋላ...
ተመልሳ ገና ወዳልከፈትነው ልብስ ማስቀመጫ ሳጥን አመራች።
👍321🥰1
“ከዚህ ጀርባ በቁምሳጥኑ ጥግ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል የሚያስወጣ ደረጃ አለ። እዚያ ክፍል ውስጥ ልትሮጡበት፣ ልትጫወቱበትና ልትጮኹበት
የምትችሉበት በቂ የሆነ ቦታ አለ ነገር ግን ከአራት ሰዓት በፊት ሠራተኞቹ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ስራ ስለሚሰሩ ስትሯሯጡ ሊሰሙ ይችላሉ። ከአራት ሰዓት በኋላ ግን ሠራተኞቹ ሁለተኛ ፎቅ ላይ መድረስ ስለማይችሉ ወደዛ
መሄድ ትችላላችሁ። ሁልጊዜም ግን በጣም ከጮሃችሁ ታች ልትሰሙ እንደምትችሉ አስቡ። እዚህ ቤት ውስጥ የራሳችንን ህግ የምናወጣውም ሆነ ቅጣት የምንሰጠው እኛው ነን፡ ትናንት ማታ እንዳልኩት በእያንዳንዱ ወር
የመጨረሻው አርብ፣ በጠዋት ጣሪያው ስር ወደሚገኘው ክፍል ትሄዱና ሳታወሩና በእግራችሁ ጭምር ድምፅ ሳታሰሙ በፀጥታ ትቀመጣላችሁ።ገባችሁ?” ሁላችንንም ተራ በተራ ተመለከተችን፡ በክፉና በአስፈሪ አይኖቿ ቃላቶቿን መረዳታችንን አረጋገጠች: እኔና ክሪስቶፈር መረዳታችንን ለማሳየት ጭንቅላታችንን ነቀነቅን፡ መንትዮቹ እንግዳ በሆነ ወደ ፍርሀት በተጠጋ አክብሮት ዝም ብለው ይመለከቷት ነበር። በተጨማሪ በዚያ አርብ
ስለ መኖራችን የሚጠቁም ምንም አይነት ምልክት አለመተዋችንን ክፍሉንና መታጠቢያ ቤቱን በማየት ራሷ እንደምታረጋግጥ ነገረችን፡

ሁሉን ብላ ጨርሳ እንደገና ቆልፋብን ሄደች: አሁን መተንፈስ እንችላለን ይህንን ጉዳይ ወደ ጨዋታ ለመለወጥ አሰብኩ። “ክሪስቶፈር አንተ አባት ትሆናለህ" አልኩት ሳቀና በማላገጥ አይነት “ወንድ ስለሆንኩ የቤቱ ራስ
ነኝ፡ እንደንጉስ እጅና እግሬን አጣምሬ መጠበቅ ብቻ ነው ሚስትየዋ ደግሞ የበታችና ባሪያዬ ስለሆነች ጠረጴዛ ማስተካከል፣ ምግቡን መስራትና ለጌታዋ
ማቅረብ አለባት ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ወንድምሽ ሳልሆን ጌታሽ ነኝ::የፈለኩትን ታደርጊያለሽ ያልኩትን ሁሉ"

“አንተ ያልከውን ካላደረግኩ ቀጥሎ ምን ታደርጋለህ ጌታዬ?”

“አነጋገርሽን አልወደድኩትም እኔን ስታናግሪ በአክብሮት መሆን አለበት:”

“አንተን በአክብሮት የማናግርህ የእኔ አክብሮት የሚገባህ ቀን ነው: ያ ቀን ደግሞ ቁመትህ ሶስት ሜትር ሲሆንና ጨረቃ ቀን ላይ መውጣት ስትችል ነው፡” አልኩትና የኬሪን ትንሽ እጅ ይዤ እየመራኋት በተራችን ለመታጠብ፣ ለመልበስና ፀጉራችንን ለማበጠር ወደ መታጠቢያ ቤት ለመግባት በመፈለግ እየተጣራ ያለውን ምስኪኑን ኮሪ ቀድመን ተያይዘን ገባን።

ብታምኑም ባታምኑም ከመታጠቢያ ቤት ስንወጣ ክሪስቶፈር ኮሪን አለባብሶት
ጨርሶ ነበር! በጣም የሚያስደነግጠው ነገር ደግሞ አሁን ኮሪ መታጠቢያ ቤት
መጠቀም አላስፈለገውም:

“ለምን? አልጋው ላይ ተጠቀምኩ እንዳትለኝ ብቻ!”

ኮሪ በፀጥታ አበባ ያልተቀመጠበት ትልቅ ሰማያዊ የአበባ ማስቀመጫ አመለከተኝ

ክሪስቶፈር በራሱ በመደሰት የልብስ ማስቀመጫውን ተደግፎ እጁን ደረቱ ላይ አመሳቅሎ ቆሞ “ይሄ የተቸገሩ ወንዶችን ችላ ማለት ምን እንደሚያስከትል
ያስተምርሻል፡ እኛ ወንዶች እንደ እናንተ አይደለንም: ትንሽዋም ነገር በአስቸኳይ መፈፀም አለባት” አለኝ።

ቁርስ መብላት እንዲጀምሩ ከመፍቀዴ በፊት ሰማያዊውን የአበባ ማስቀመጫ
መድፋትና በደንብ ማጠብ ነበረብኝ ለማንኛውም የአበባ ማስቀመጫውን ኮሪ
የሚተኛበት አጠገብ ማድረግ እውነትም ጥሩ ሀሳብ ነው።

መስኮቶቹ አጠገብ ለካርታ መጫወቻ የሚሆን ትንሽ ጠረጴዛ አዘጋጀን መንትዮቹ የሚበሉትን ማየት እንዲችሉ ትራስ ደራርበን አስቀመጥናቸው።አራቱም መብራቶች የበሩ ቢሆንም አሁንም ግን ድንግዝግዝ ባለ ብርሀን ቁርስ መብላት በጣም ደባሪ ነበር
“አይዞሽ ነቃ በይ… እየቀለድኩ ነው:: የእኔ ባሪያ መሆን አያስፈልግሽም ስትናደጂ የምትናገሪው ነገር ደስ ስለሚለኝ ነው" አለኝና የማያስብና ማዘዝ
ብቻ ደስ የሚለው አለመሆኑን ለማሳየት ወተት በመቅዳት አገዘኝ: ባያግዘኝ ኖሮ ያንን ከሚያክል ፔርሙዝ ወተቱ ሳይፈስብኝ መቅዳት የማይቻል ነበር
ኬሪ ገና የተጠበሰውን እንቁላል ስትመለከት “እኛ እንቁላል አንወድም የምንወደው ቀዝቃዛ ሲሪያል ነው! ትኩስ ከሆነ ደግሞ አንበላም ዘቢብ ያለበት ቀዝቃዛ ሲሪያል እንፈልጋለን!” እያለች ጮኸች:

አዲሱ ትንሹ አባታቸው ኮስተር ብሎ “አዳምጡኝ… ይሄ ፊታችሁ የቀረበላችሁ ምግብ ትኩስ አይደለም የቀዘቀዘ ነው ማማረር፣ መጮህ፣ ማልቀስ የለም!
አርፋችሁ ብሉ! ሰማችሁ?” አለ።

እነዚያ መንትዮች ወዲያውኑ እኔን ባልገባኝ በሆነ ምክንያት ያለምንም ማጉረምረም ቁርሳቸውን ጥርግ አድርገው በሉ፡ በጉልበተኛ ታላቅ ወንድማቸው ሳይገረሙ አልቀሩም ቁርስ አልቆ ሳህኖቹን በንፅህና ወደ ትሪው ስመልስ ስንበላ ያለማመስገናችን ትዝ አለኝና በጥድፊያ በጠረጴዛው ዙሪያ ተቀምጠን አንገቶቻችንን ዝቅ በማድረግ እጅ ለእጅ ተያያዝን፡

“ጌታ ሆይ ያንተን ፈቃድ ሳንጠይቅ በመመገባችን ይቅር በለን፡ እባክህ አያትየው እንዳታውቅ እርዳን፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ በትክክል እንደምናደርገው
ቃል እንገባለን አሜን፡” ስንጨርስ አያትየው ማድረግ ያለባችሁና የሌለባችሁ ብላ ዝርዝር ነገሮች የተፃፈችበትን ወረቀት ለክሪስቶፈር ሰጠሁት ፅሁፉ ለመረዳት የማንችል ደደብ የሆንን ይመስል በትልልቁ ተፅፏል።

ትናንትና ማታ እያንቀላፉ ስለነበር ያልተረዱትን ሁኔታችንን አሁን ወንድሜ ከላይኛው ጀምሮ የተዘረዘሩትን መተላለፍ የሌለብንን ህጎች ሲያነብ ሙሉ በሙሉ የገቡበትን ሁኔታ ተረዱ
በመጀመሪያ የአያትየውን በጥላቻ የተሞላ አነጋገር በማስመሰል አፉን እሷ እንደምታደርገው አደረገና ጀመረ፤

“አንድ” ሲል በቀዝቃዛና ስሜት በማይሰጥ ድምፅ ማንበብ ቀጠለ፡ “ሁልጊዜም በደንብ መልበስ አለባችሁ:

“ሁለት የእግዚአብሔርን ስም አላግባብ መጥራት አይቻልም፤ በእያንዳንዱ የምግብ ሰዓት ላይ ከመመገባችሁ በፊት ፀሎት ማድረግ አለባችሁ።እኔ ክፍላችሁ ውስጥ ሆኜ ይህንን ማድረጋችሁን ባላይም ከላይ ያለው እንደሚሰማና እንደሚያይ እርግጠኞች መሆን አለባችሁ

“ሶስት መጋረጃዎቹን በፍፁም መክፈት አይፈቀድም አጮልቆ ለማየትም ቢሆን

“አራት አስቀድሜ እኔ ካላናገርኳችሁ በስተቀር እኔን ማናገር አይፈቀድም::

“አምስት ይህንን ክፍል በንፅህናና በስርዓት መያዝ አለባችሁ፤ ሁልጊዜ አልጋው መነጠፍ አለበት።

“ስድስት ስራ ፈትታችሁ መቀመጥ አይቻልም በየቀኑ ለአምስት ሰዓታት ያህል ማጥናት አለባችሁ: የቀረውን ሰዓት ደግሞ ችሎታችሁን በሆነ ትርጉም ባለው መንገድ ማዳበር አለባችሁ የሆነ ክህሎት ወይም ችሎታ ወይም ተሰጥኦ ካላችሁ፣ እሱን ለማሻሻል መትጋት አለባችሁ ምንም አይነት ክህሎት፣ ችሎታ ወይም ተሰጥኦ ከሌላችሁ ደግሞ መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ
ይጠበቅባችኋል። ማንበብ የማትችሉ ከሆነ እንኳን ቁጭ ብላችሁ መፅሀፍ ቅዱሱን ትኩር ብላችሁ በማየት ሀሳባችሁን ለማጥራት የእግዚአብሔርንና
የእሱን መንገዶች ለመያዝ መሞከር ይጠበቅባችኋል።

“ሰባት ጥርሶቻችሁን ጠዋት ከቁርስ በኋላና ማታ ከመኝታችሁ በፊት መፋቅ አለባችሁ:

“ስምንት ወንዶችና ሴቶች አንድ ላይ መታጠቢያ ቤት ስትጠቀሙ ከያዝኳችሁ ያለምንም ምህረት የጀርባችሁን ቆዳ እገሸልጠዋለሁ:
ልቤ የወደቀች መሰለኝ አምላኬ ሆይ ምን አይነት አያት ነው ያለን?

“ዘጠኝ አራታችሁም በአረማመድ፣ በንግግርና በሀሳብም ጭምር ሁልጊዜም ጨዋና ጥንቁቅ መሆን አለባችሁ:

“አስር የመራቢያ አካላቶቻችሁን መንካት፣ በእነርሱ መጫወት፣ በመስተዋት መመልከት፣ የሰውነታችሁን ክፍሎች ስታፀዱም ቢሆን እንኳን ስለነሱ ማሰብ
የተከለከለ ነው”አይኖቹ ላይ ትንሽዬ አስቂኝ የእፍረት ጭላንጭል እየታየ የአያታችንን አነጋገር በማስመሰል ማንበቡን ቀጠለ፡፡
👍336
“አስራ አንድ በአእምሯችሁ ውስጥ ክፉ የኃጢአት ወይም ፆታዊ ፍላጎት ላይ ያተኮሩ ሀሳቦችን ማሰብ የተከለከለ ነው ሀሳቦቻችሁን ንፁህና ፅዱ ማድረግና ስነምግባራችሁን ከሚያበላሹ ክፉ ርዕሶች መራቅ አለባችሁ:

“አስራ ሁለት በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ተቃራኒ ፆታ የሆኑ የቤተሰቡን አባላት ከማየት መቆጠብ አለባችሁ።

“አስራ ሶስት ማንበብ የምትችሉት ሁለታችሁ... ትንንሾቹ ልጆች
ከእግዚአብሔር ቃል ትምህርት መጠቀም እንዲችሉ በቀን አንድ ሰዓት ተራ በተራ ከመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ቢያንስ አንድ ገፅ ከፍ ባለ ድምጽ ማንበብ አለባችሁ

“አስራ አራት እያንዳንዳችሁ በየቀኑ መታጠብና የመታጠቢያ ቤቱን ልክ እንዳገኛችሁት እንከን በሌለው ሁኔታ ማፅዳት ይጠበቅባችኋል

“አስራ አምስት እያንዳንዳችሁ… መንትዮቹን ጨምሮ… ቢያንስ በቀን አንድ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ መማር አለባችሁ ያነበባችሁትን የመፅሀፍ ቅዱስ
ክፍል ማወቅ እንድችል እኔ በጠየቅኳችሁ ጊዜ ሁሉ ያጠናችሁትን ጥቅስ
መናገር ይጠበቅባችኋል።

“አስራ ስድስት የማመጣላችሁን ምግብ ሁሉ ጨርሳችሁ መብላት አለባችሁ።
አለም ላይ ብዙዎች ተርበው ባሉበት ሁኔታ ጥሩ የሆነን ምግብ ማባከን ኃጢአት ስለሆነ ትንሽም ቢሆን ማባከን፣ መወርወር ወይም መደበቅ አይፈቀድም።

“አስራ ሰባት ከአልጋችሁ ወደ መታጠቢያ ቤት ወይም ከመታጠቢያ ቤት ወደ አልጋ የምትሄዱ ቢሆንም እንኳን የሌሊት ልብሶቻችሁን ብቻ ለብሳችሁ
በክፍሉ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ማለት አይፈቀድም የመታጠቢያ ቤቱን ለሌላ ልጅ በአስቸኳይ መልቀቅ ቢኖርባችሁ እንኳን ሁልጊዜ በሌሊት ልብሶቻችሁ
ወይም በውስጥ ልብሶቻችሁ ላይ ጋዋን መደረብ ይኖርባችኋል። በዚህ ጣራ ስር የሚኖር ማንኛውም ሰው በሁሉም ነገርና በሁሉም መንገድ ጨዋና
ጥንቁቅ መሆን ይኖርበታል።

“አስራ ስምንት እኔ ወደ ክፍሉ ስገባ ሁላችሁም መነሳትና እጆቻችሁን ወደታች አድርጋችሁ መቆም አለባችሁ እጆቻችሁን አፋችሁ ላይ ማድረግም
ሆነ አይኖቼን ማየት አይፈቀድላችሁም ለእኔ የፍቅር ፊት ማሳየትም ሆነ ከእኔ ጋር ወዳጅነት እንዲኖራችሁ ተስፋ ማድረግ አይፈቀድም: ወንድ
አያታችሁም ሆነ እኔ ግብረገባዊ ያልሆነ የትኛውም ነገር ስሜት እንዲያሳድርብን ስለማንፈቅድ የእኔን ሀዘኔታም ሆነ ፍቅር ለማግኘት መሞከር አይፈቀድም

እ እንዴት የሚያሳምሙ ቃላት ናቸው! ክሪስቶፈር ማንበቡን አቋረጠና ተስፋ በመቁረጥ ፊቱን ጣለው አይኖቻችን ሲገጣጠሙ ሁሉንም ተወና ኬሪ እንድትስቅ መኮርኮር ጀመረ ከዚያ ኮሪም እንዲስቅ ብሎ አፍንጫውን ጎተት
አደረገው

“ክሪስቶፈር… አያትየው የምትናገረው ሁሉ እውነቷን ከሆነ፣ እናታች በምንም መንገድ ቢሆን የአባቷን ፍቅር በጭራሽ መልሳ የማግኘት ተስፋ
አይኖራትም ግን አያታችን በአይኑ እንኳን ሊያየን የማይፈልገው ለምንድነው ምን አደረግን? እናታችን አባቷ ከውርስ እንዲሰርዛት የሚያደርግ ጥፋት
ሰርታ ከፀጋ ስትወድቅ እዚህ አልነበርን! ያን ጊዜ ገና አልተወለድን! ታዲያ
ለምንድነው እንደዚህ የጠሉን?” ብዬ ጮህኩ።

“ተረጋጊ” አለ አይኖቹ ረጅሙን ዝርዝር እያጠኑ “እዚህ ላይ የፃፈቻቸውን አንዳቸውንም በቁም ነገር አትውሰጃቸው እብድ ናት መቼም እንደ ወንድ
አያታችን ያለ አስተዋይ ሰው እንደ ሴት አያታችን አይነት የደደብ አስተሳሰ አይኖረውም: እንደዚያ ቢሆን ኖሮ እንዴት በሚሊየን የሚቆጠሩ ዶላሮች
መስራት ይችል ነበር?”

“ምናልባት ገንዘቡን ሠርቶት ሳይሆን ወርሶት ሊሆን ይችላል”

“አዎ፡ እማዬ የተወሰነውን በውርስ እንዳገኘው ነግራናለች ነገር ግን መቶ እጥፍ አሳድጎታል፡ ያን ለማድረግ ጭንቅላቱ ውስጥ ትንሽ አእምሮ ሳይኖረው አይቀርም ምናልባት ዛፍ ከምታክለው ሚስቱ እብደት ተጋብቶበት ካልሆነ
በስተቀር” ፈገግ ብሎ ህጎቹን ማንበቡን ቀጠለ።

“አስራ ዘጠኝ ወተትና ምግብ ልሰጣችሁ ወደ ክፍላችሁ ስመጣ ክብር በማያሳይ መልኩ እንድታዩኝ፣ እንድታናግሩኝ ወይም ስለኔ እንድታስቡ አይፈቀድም: ወንድ አያታችሁንም በንቀት ማሰብ የተከለከለ ነው፡ በሰማይ
ያለው እግዚአብሔር አእምሯችሁን ማንበብ ስለሚችል ማንም በምንም መንገድ ባለቤቴን በዚያ መንገድ እንዲያስበው አይፈቀድም:: የዶክተርና
የነርስ ሰራዊት ስላሉት የሚያስፈልገውን አድርገው የማይሰሩትን የሰውነት
ክፍሎቹን እንዲሰሩ የሚያደርግ ማሽን ገጥመው ያድኑታል ከብረት የተሰራ ሰው የደከመ ልብ ስላለው ብቻ ሊወድቅ አይችልም:”

ዋው! እውነትም ከብረት የተሰራው ሰውዬ ከሚስቱ ኋላ ቆሟል የእሱም አይን ብረት የመሰለ ግራጫ መሆን አለበት: የራሳችን እናትና አባት እንዳረጋገጡልን ተመሳሳዮች ይሳሳቡ የለ፡

“ሀያ” ክሪስቶፈር እያነበበ ነው፡ “መዝለል፣ መጮህና ማንኳኳት የተከለከለ ነው፡ ጠንካራ ሶል ያለው ጫማ ማድረግ የተከለከለ ነው: ማድረግ የምትችሉት
ስኒከር ብቻ ነው።

“ሀያ አንድ የመፀዳጃ ቤት ወረቀት ወይም ሳሙና ማባከን የተhለከለ
ነው: መፀዳጃ ቤት ከተጠቀማችሁ በኋላ ውሀ መልቀቅ ብትረሱ hዚህ
እስከምትሄዱበት ጊዜ ድረስ እንደዚያው ይቆያል: እናንተም ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ፖፖ ትጠቀማላችሁ፡ ፖፖውንም እናታችሁ
እንድትደፋ ይደረጋል።

“ሀያ ሁለት ወንዶቹም ሆኑ ሴቶቹ የራሳቸውን ልብስ ማጠብ አለባቸው። አንሶላውንና ፎጣዎቹን እናታችሁ ታጥባለች: የፍራሹ ጨርቅ በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ይቀየራል ህፃናቱ ድንገት ካበላሹት እናታችሁ የላስቲክ አንሶላ
እንድትጠቀሙ እንድታደርግና በአግባቡ የመፀዳዳት ትምህርት ያልተሰጠውን ልጅ እንድትቀጣ ይደረጋል።

ይህንን ሲሰማ ደንግጦ ላዬ ላይ ልጥፍ ያለውን ኮሪን አቀፍኩትና “ሽሽሽ! አትፍራ የሰራኸውን አታውቅም እኛ እንከላከልልሀለን” አልኩት። ክሪስ ማንበቡን ቀጠለ፡፡

“ማጠቃለያ” ይህኛው አድርጉ አታድርጉ ሳይሆን ማስጠንቀቂያ ነው፡ “እኔ ምንም ነገር የማያመልጠኝ አስተዋይ ሴት ነኝ፡
ልታታልሉኝ፣ ልትቀልዱብኝ ወይም ልትጫወቱብኝ ብትሞክሩ ቅጣታችሁ የከፋ ከመሆኑ የተነሳ ቆዳችሁና ጭንቅላታችሁ የዘለዓለም ጠባሳ እንዲኖራቸው
ይሆናሉ፡ ክብራችሁና ኩራታችሁ በቋሚ ሽንፈት የተዋረደ ይሆናል ከአሁን ጀምሮ እኔ ባለሁበት የአባታችሁን ስም ወይም የእሱን ጉዳይ በሆነ መንገድ መጥቀስ የተከለከለ ነው: እኔም ራሴ በጣም እሱን የሚመስለውን ልጅ
ከማየት የተቆጠብኩ እሆናለሁ።” አለቀ። ክሪስቶፈርን በጥያቄ አስተያየት አየሁት እኔ የጠረጠርኩትን ጠርጥሮ ይሆን? የመጨረሻው ዓረፍተ ነገር
ምንን ያመለክታል? በሆነ ምክንያት ለእናታችን ከውርስ መውጣትና በወላጆቿ
መጠላት ምክንያቱ አባታችን ይሆን እንዴ?

እኔ እንደገመትኩት እዚህ ውስጥ በጣም ለረጅም ጊዜ እንደሚቆለፍብን ገምቶ
ይሆን?
“አምላኬ… አምላኬ! ለአንድ ሳምንት እንኳን መቋቋም አልችልም!”
“ካቲ” አለ ወንድሜ ደካማ ፈገግታ ከንፈሩ ላይ እየታየ። መንትዮቹ እንፈራ፣እንደሰት ወይም እንጮህ እንደሆነ በመጠበቅ ተራ በተራ ይመለከቱናል
“እናታችንንና አባታችንን እኛ በማናውቀው ምክንያት እንደምትጠላቸው በግልፅ ያስታውቃል፡ ግን እኛስ? ያን ያህል አስቀያሚና የማንወደድ ነን
እንዴ? አንዱም ነገር እውነቷን አይሆንም፡ ውሸታምና አጭበርባሪ ናት”
ከዚያ ወረቀቱን አጣጥፎ ወደ ልብስ ሳጥኑ ወረወረው። “ማመን የሚገባን እንደዚህች አይነቷን አሮጊት ሳይሆን የምትወደንንና የምናውቃትን ሴት ነው:
እናታችን ትንከባከበናለች ምን እንደምታደርግ ስለምታውቅ በሷ መተማመን እንችላለን፡፡”

አዎ ትክክል ነው: መታመን ያለባት እናታችን እንጂ ይህች የጥይት ተኩስ አይነት አስተያየትና የቢላዋ ስንጥቅ የመሰለ አፍ ያላት ግትር አሮጊት አይደለችም::
👍378
በአጭር ጊዜ ውስጥ ምድር ቤት ያለው ወንድ አያታችን በእናታችን ውበትና ማራኪነት ይደሰትና ዝንጥ ብለን በደስታ ፈገግ እንዳልን እሱ ወዳለበት በደረጃው እንወርዳለን፡ ምናልባት ሲያየንም ለልጅ ልጆቹ የሚሰጠው ትንሽ ፍቅር ሊኖረው ይችላል ማን ያውቃል?....

ይቀጥላል
👍2412