አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...ዛሬ ግን ሲልቪ አላዘነችም፡
የተለመደው ሳቋ አይኖቿን እየደጋገመ ያበራቸዋል፣ ከንፈሮቿን
ያለማቋረጥ ይከፋፍታቸዋል። እራት ላይ ሁለት ጠርሙስ ወይን
ጠጥተን ነበር፣ አሁን ሁለት ጠርሙስ ቢራ ስንቀላቅልበት ጊዜ ወሬአችን ሞቀ.
«አቤት እንዴት ነው ያማርሽኝ!» አልኳት
«ሱሪ ስለለበስኩ ነው?»
«ግማሽ»
«ግማሽስ?»
«ከስሩ ሙታንቲ ስላላረግሽ ነው። ለምን ሙታንቲ
አልለበስሽም?»
«ለምን ይመስልሀል?» አይኖቿኸ ውስጥ ያ የሚያሰክረኝ ቅንዝር
ይታያል
«እኔ እንጃ፡፡ ለምንድነው?»
«ግማሹ አንተ እንዳሁን እንድትመኘኝ ነው»
«ግማሹስ?»
«አይ! አይነገርም፡፡ በብርሀን አይነገርም፡፡» የአፏ አከፋፈት!
«ንገሪኝ። ንገሪኝ፡፡ ለምንድነው ሙታንቲ ሳትለብሺ
የመጣሽው?»
«ልንገርህ?»
«ንገሪኝ!»
«ተው ይቆጭሀል!»
«ንገሪኝ!»
«ሱሪው ጠባብ ነው:: ያለሙታንቲ ስለብሰው ቂጤ የበለጠ
አያምርም? የበለጠ አያስጐመጅም?»
«ያንገበግባል»
«እና ስራመድ ወንዶቹ እንዴት እንደሚያዩኝ አላየህም?»
ቅናቱ ጀመረኝ
«አላየሁም» አልኳት
«ያዩኝ ነበር። ይታወቀኛል'ኮ፡፡ ስራመድ ከኋላዬ ሆነው
ሲያዩኝ፣ አይናቸው ከዳሌዬ ጋር ሲንከራተት ይታወቀኛል፡፡»
«እና ምን ይሰማሻል?»
«ደስ ይለኛል፣ ዛሬ በሀይል አላምርም?»
«ታምሪያለሽ፡፡ ግን ከሌላ ጊዜ ይበልጥ እንደምታምሪ እንዴት
አወቅሽ?»
«ይታወቀኛላ»
«እንዴት ይታወቅሻል?»
«ውስጤ ይሰማኛል፡፡ አየህ፣ ዛሬ ወንድ አምሮኛል። በሀይል
አምሮኛል። ስለዚህ፣ ፊቴ፣ ገላዬ፣ አረማመዴ ሁሉ ወንድ ሊስብ
ይፈልጋል። ስለዚህ በሀይል አምራለሁ።»
የትላንቱ ሌሊት አይነት ቅናት ውስጤ መንቀሳቀስ ጀመረ
«እንዴት ነው የምታየኝ አንተ!?»
«እንዴት ነው?»
«አማርኩህ መሰለኝ»
«በጣም አምረሽኛል»
«እኔም አምረኸኛል። ግን ዛሬስ ልታጠግበኝ የምትችል
ኣይመስ ለኝም፡፡ ዛሬ የያዘኝ ምኞት እንደ እሳት ነው:: ለማጥፋት
ብዙ ብዙ ውሀ ይፈልጋል፡፡ አንተ ብቻህን ልታጠፋልኝ መቻልህን
እንጃ የትላንቱ ሌሊት ቅናት እንቅ አደረገኝ፣ ሌላ
ወንድ እንዲያምራት ተመኘሁ
«እና ምን ትፈልጊያለሽ? ንገሪኝ እስቲ»
«ትቆጣለሁ!»
«ይልቅ ንገሪኝ»
«ንገሪኝ፡፡ ምን ያምርሻል?»
«ወንድ ያምረኛል። ሶስት አራት ቆንጆ ቆንጆ ወንድ ባጎኝ
እፈቅዳለሁ፡፡
«እንድ አይበቃሽም?»
«አይበቃኝም። አልጠግብም፡፡ ዛሬስ አንተ እንኳ ብትሆን
እታጠግበኝም፡፡»
እና ምን ይሻላል?»
«አንተ ባትኖር መፍትሄ ነበረው»
«እኔ ባልኖር እንዲህ አይነት ስሜት ሲመጣብሽ ምን ታረጊያለሽ?»
ጠረጴዛ ላይ ያለውን ጥቁር ቦርሳዋን መታ እያደረገች
«ማስታወሻ ደብተሬ ውስጥ የቴሌፎን ቁጥሮች አሉኝ»

«የወንዶችሽ?»

ጭንቅላቷን በኣዎንታ ነቀነቀች
«አሁንም ልትደውይሳቸው ትችያለሽ' ኮ»– ደነገጠኩ፡፡ እንዲህ ማለት መቼ ፈለግኩና? በጭራሽ አልፈለግኩም፡፡ ምን ነካኝ? እስቲ
አሁን እንዲህ ይባላል? ምን አይነት ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት!?
እጇን ቶሎ ሰዳ እጄን በሀይል ጨበጠች። አይኖቿ ውብ ብርሀን
ለበሱ፣ ቀያይ ከንፈሮቿን በምላሷ አረጠበች፣ ከውስጥ ወተት መሳይ
ጥርሶቿ ይብለጨለጫሉ፡፡ ማማሯ ማስጐምጀቷ ስሜት ባፈነው
ወፍራም ድምፅዋ
«ትፈቅድልኛለህ? ልደውልላቸው? አትጠላኝም? በኋላ
አታባርረኝም? ልደውልላቸው? አንተን ነው የምወደው:: ግን በሽተኛ ነኝ። መሄድ አለብኝ። ግን የምትጠላኝ ከሆነ አልሄድም፡፡ ልደውል?
ልሂድ? ትፈቅዳለህ?»
አቅበጠበጣት፡፡ አሳዘነችኝ፡፡ ደሞ በሀይል አማረችኝ፡፡ እንደዛሬ
አምራኝ አታውቅም፡፡ ግን አሁን ላገኛት ኣልፈለግኩም፡፡
ከሆነልኝና ወደ ሌሎቹ ከሄደችልኝ፣ ከሌላ ጋር መሆኗን እያሰብኩ
መሰቃየት አማረኝ፡፡ እሷ ወንዶች ያማሯትን ያህል እኔ መሰቃየት
አማረኝ፣ መቅናት፣ መቃጠል አሰኘኝ፡፡ ራሲንም ለማወቅ ተጠማሁ፡፡ማን ነኝ? ፍቅር ይዞኛል? እና ፍቅር ምንድነው? ቅናትስ? የሁለቱስ ዝምድና እንዴት ያለ ነው የሚያፈቅሩዋት ሴት ጥብቅ ያለ ሱሪ ለብሳ ሌላ ወንድ ፍለጋ ስትሄድ ማየት፣ ሄዳ ስትመለስ፣ ቢያንስ ቢያንስ ሶስት ወንድ በየተራ ሲደሰትባት፣ ሲስማት፣ ሲልሳት፣ ሲያለፋት ከቆየ በኋላ፣ ከዚያ ተቀብለው ይህን ሁሉ እያወቁ ያችን የሚወዷትን ሴት ማቀፍ፣
መሳም፣ መላስ፣ በቅናት እየነደዱ ሴትዮዋን መተኛት
ይሄ ደሞ ከሁሉ የጠለቀ፣ ከሁሉ የላቀ፣ ከሁሉ የደመቀ ከሁሉ የጨለመ፣ የሚያቃጥል፣ የሚበርድ፣ የሚያስደስት፣ የሚያበሳጭ፣ የሚገድል፣
የሚያድን፤ ከስሜት በላይ የሆነ ስሜት ይሰጥ ይሆን?

«ልሂድ ትፈቅዳለህ?» አለችኝ
«ብኋላ የት አገኝሻለሁ?» አልኳት፡፡ ድምፁ የኔው አይመስልም
ሆቴላችን»
«ከስንት ሰአት በኋላ?»
ሰአቷን አየች
«ከአምስት ሰአት በኋላ፡፡ ልክ በሰባት» አለችኝ
በጠረጴዛው ተንጠራርታ ግምባሬን ሳመችኝ
«አግባኝ፡፡ እባክህን አግባኝ! ይቅር እሺ። ይቅር፡፡ “nous nous
reverons bientôt'' (“አሁን አሁን እንገናኛለን») ብላ እጄን ስማኝ ተነስታ ከካፌው ወጣች። ስትሄድ ረዥም አንገቷን እያወዛወዘችው፣
ወደኋላዋ የተለቀቀው ፀጉሯ ዥዋዥዌ ይጫወታል። ከቀጭን ወገቧ ስር ወፍራም ዳሌዋ ይወዛወዛል፣ ስትራመድ ጠባቡ ሱሪዋ የቂጧን ውብ ቅርፅ ያሳያል ከውስጥ ሙታንቲ አልለበሰችም!!
ከጥቂት ደቂቃ በኋላ፣ ከካፌው ወጥቼ ሲኒማ ገባሁ
እንደ አጋጣሚ ኢንግግር በርግማን የተባለው ገናና የስዊድን ፊልም አዘጋጅ የፈጠረው «ሰባተኛው ማህተም» የተባለው እጅግ የተመሰገነ ፊልም ነበር አንድ የጥንት ስዊድናዊ አርበኛ፣ ከኢየሩሳሌም የመስቀል ዘመቻ ሲመለስ፣ ልክ የክርስትያን ኢውርፓን መሬት እንደረገጠ፣ ሞት የተራ ሰው መልክ ለብሶ ይመጣና
«ልወስድህ መጥቻለሁ» ይለዋል
አርበኛው
«አሁን ካንተ ጋር መምጣት አይሆንልኝም፡፡
ላደርጋቸው የሚገባኝ፣ ግን ገና ያልፈጸምኳቸው፣ አንድ ሁለት ጉዳዮች አሉ» ይለዋል
ሞት «ልወስዳቸው ስመጣ ሰዎች ሁሉ ይህንኑ ነው የሚሉኝ ይለዋል

አርበኛው «እኔ ግን እውነቴን ነው:: ላደርጋቸው የሚገባኝ
ነገሮች አሉ፡፡ . . . በቼስ ጨዋታ የሚችልህ የለም ይባላል» ይለዋል
«እውነት ነው»
አርበኛው «እኔ ግን የምችልህ ይመስለኛል። ይዋጣልን እስቲ።
ምን ቸገረህ? በመጨረሻ ማሸነፍህ አይቀር» ይለዋል
“እሺ እንጫወት»
“እስክሽነፍ ድረስ ልኑር ፍቀድልኝና፣ እኔን ለማሸነፍ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድብህ እናያለን
«እሺ»
ጨዋታቸውን ይጀምራሉ
እንደሱ ያለ አስደናቂ ፊልም አይቼ አላውቅም።
እጭለማው ውስጥ ሲልቪን አንድ አምስት ጊዜ ብቻ በድንገት
እያስታወስኳት በሀይል ድንግጥ አልኩ:: ግን ያኔውኑ ፊልሙ ከሀሳቢ ያባርራታል። ግሩም ፊልም ነበር። ሲያልቅ ደገምኩት፡፡ በጭራሽ አልጠገብኩትም፡፡ ግን ሶስተኛ ላየው አልቻልኩም፡፡ ሲኒማ ቤቱ ተዘጋ፡፡ ወጥቼ ስለፊልሙ እያሰላሰልኩ ስራመድ ሰአቴን አየሁ። ሰባት ከሩብ ልቤ በሀይል መምታት ጀመረ፡፡ ባለሁበት ቆምኩ።ሲልቪ እንዴት እስካሁን የሷ ሀሳብ አላስጨነቀኝም? ይሄ
ኢንግማር በርግማን እንዴት ያለ ፍፁም አርቲስት ቢሆን ነው?!
እስካሁን ከሱ ጋር ነበርኩ። ከሱ ጋር ስለሞትና ስለህይወት ሳስብ፣
👍24
ስጨነቅ ቆየሁ፡፡ ከሲልቪ መንጭቆ ወስዶ ስለዋናው መሰረታዊ አጣዳፊ ጥያቄ፣ ሞት ስለሚባለው ጥያቄ አዋየኝ፡፡ ሞት ምንድነው? ህይወትስ? ግን ሲልቪን ያስረሳኝ እንደማር በርግማን ብቻውን እንዳልሆነ ገባኝ። እኔም ራሴ ልረሳት ፈልጌ ኖሯል። አልታወቀኝም እንጂ፣ ስለሷና ስለወንዶቿ “ማሰብ ስላስፈራኝ፣ ሸሽቼ ኢንግማር
በርግማንን የሙጥኝ ማለቴ ኖሯል፡፡ በርግማን ከስንት ጨካኝ ስቃይ ከለለኝ! ስንት የላቀ ሀሳብ እሳተፈኝ! አሁን ታድያ፣ በርግማን የሚባለው ግድብ ተነሳ፡ የሲልቪ ሀሳብ በሀይል ጎርፎ መጥቶ አፈነኝ፡፡ ተንገበገብኩ። ላያት ላቅፋት ተንዝገበገብኩ፡፡ አቶቡስ ለመጠበቅ ወይም የሜትሮ ባቡር በዚህ ሰአትም ይሰራ እንደሆነ ለመሞከር ትእግስት አጣሁ:: ታክሲ ተሳፈርኩ፡፡ ሆቴላችን ገባሁ። የክፍላችንን ቁልፍ ሆቴል ጠባቂው (coracierge) ሰጠኝ፡፡ ሲልቪ ገና አልመጣችም ማለት ነው። ሰአቲን አየሁ፡፡ ለስምንት ሩብ ጉዳይ። እመጣለሁ ያለችው በሰባት ነበር:: ንዴቱ ውስጤ እየገነፈለ ወደ ክፍላችን ገባሁ
ንዴቴ ለመጠራቀም ጊዜ አላገኘም። ያኔውኑ በሩ ተንኳኳ።
ሲልቪ በቀስታ እርምጃ ገባች፡፡ በሩን ቆለፈችው:: ተወርውራ እግሬ
ስር ተምበረከከች። እቅፍ አርጋኝ ፊቷን እጭኖቼ መጋጠሚያ ሰፈር
ደበቀች። ማናችንም ቃል አልተናገርንም። ትንሽ ጭንቅላቷን
ከዳበስኩ በኋላ ቀስ አድርጌ አነሳኋትና አቀፍኳት። ትንሽ ቆይቼ
ለቀቅኳትና ልብሴን ማውለቅ ጀመርኩ። እሷም ልብሷን ማውለቅ
ጀመረች። ሁሉን ነገር ስትስራ በዝግታ ነው፡፡ እንደመጠውለግ
ብሳለች፣ አይኖቿ ውስጥ የነበረው የፍትወት እሳት ተዳፍኗል
ሸሚዟን ስታወልቅ ነጭ እንገቷ ላይ አንድ ቀይ ነገር ታየኝ፣
ጠጋ አርጌ አየሁት፣ ተነክሳ ነው። ሳላስበው! በድንገት ሳብ አድርጌ
አፏ ላይ ሳምኳት። ማልቀስ ጀመረች፡፡ እየደባበስኩ
አይዞሽ አይዞሽ አልኳት
«አፈርኩ፣ በሀይል አፈርኩ። እንዴት ቆሻሻ ነኝ! እባክህን
መብራቱን አጥፋው» አጠፋሁት። ሱሪዋን በጭለማው አወለቅኩላት።
አቀፍኳት። ጠረኗ ሌላ ነው፣ ጎረምሳ ጎረምሳ ትሽታለች። ራሲ
ዞረብኝ ላብድ ይታወቀኝ ነበር፤ ግን እብደቱን ለመከላከል
አልቻልኩም፣ አልሞከርኩምም
የት ነበርሽ? የት ነበርሽ? ንገሪኝ! ሳልሞት ንገሪኝ! ሳልፈነዳ
ንገሪኝ!» አልኳት
«እሺ' እሺ የኔ ቢራቢሮ፣ እሺ' እሺ»
«ንገሪኛ!» አልኳት፡ አፏን እየላስኩ፣ ወደ ገላዋ እየተጠጋሁ።
እያቀፈች እየተቀበለችኝ
«ከነሱ ጋር ነበርኩ። በሰባት ልመጣ ነበር፣ የመጨረሻው አልጠግብ ብሉ አልለቅ አለኝ
የመጨረሻው?»
«አዎን»
«ስንተኛው?»
«አራተኛው»
«እውነት? ከተለየሁሽ ጀምሮ አራት ወንድ ተኝቶሻል?»
«አዎን»
«አላምንሽም»
በውብ ፈረንሳይኛዋ፣ በደከመ የጭለማ ድምፅዋ፣ በሹክሹክታ
«ለምን አታምነኝም? አይታወቅህም? አያስታውቅም?» አለችኝ
«ኡ . ዉ! ንገሪኝ፣ ንገሪኝ!»

ነገረችኝ፡፡ የሳሙዋትን፣ የላሱዋትን፣ የነከሱዋትን፣ ሁሉን አንድ በአንድ ነገረችኝ። የስሜቱ እዲስነት፣ ብዛት፣ ጥልቀትና ሀይል
ካሰብኩት በላይ ሆነ፡፡ መጨረሻ ላይ ከስሜት ብዛት ስጮህ በእጂ
አፌን አፈነችኝ። በብዙ ለስላሳ ቃላት «አይዞህ ያንተ ነኝ» እያለች
አባበለችኝ፡፡ ገና ከላይዋ ላይ ሳልወርድ እንቅልፍ ወሰደኝ
እንደ መሞት ነበር እንደዚህ አድርጋ ሲልቪ የግል ገንዘቧ አደረገችኝ፡፡ እንደ ልቧ
ትገዛኝ ጀመር። ሲያሰኛት ትሄዳለች፣ ደሞ በቀን በቀን ያሰኛታል።
በቅርቡ የፈነዳች አበባ መስላ ትሄዳለች፡ ጠውልጋ ደክማ
ትመለሳለች፡ በዝግታ ልብሷን ታወልቅና፣ በተሳመ አፏ
ትስመኛለች፣ በታሽ በለፋ ገላዋ ታቅፈኛለች፣ የረጠበ ነበልባል
ውስጥ ታስገባኛለች ስላቀፏት ወንዶች ትነግረኛለች፣ በዚያ
በልስልስ ፈረንሳይኛዋ «መኖር እንዴት ጥሩ ነው! ውብ ኮረዳ
መሆንና ቆንጆ ጎረምሳ እያቀያየሩ መደሰት እንዴት ጥሩ ነው!
ከዚያ ሁሉ መጥቶ ደሞ አንተ እቅፍ ውስጥ መግባት እንዴት ያለ
ገነት ነው!» ትለኛለች፡፡ መጨረሻ ላይ ልጮህ ስል አፌን
ታፍናለች። «አይዞህ የኔ ቆንጆ፣ አይዞህ ያንተው ነኝ፣ የኔ ቢራቢሮ
አይዞህ፤ አይዞህ፡፡ ሌሎቹን ከምንም አልቆጥራቸው፤ መጫወቻዬ ናቸው፤ አንተን ብቻ ነው የምወደው! በፈለግክ ጊዜ አትሄጂ በለኝ፣
እርግፍ አርጌ እተዋቸዋለሁ፡ እሺ? አይዞህ የኔ ፍቅር የኔ ጣኦት፣
አይዞህ ተኛልኝ፣ እኔ እጠብቅሀለሁ፤ አይዞህ፤ እዚሁ ነኝ ተኛ፡

ኑሮዋችን እንደዚህ ቀጠለ፡፡ አውቀን ይሁን ሳናውቅ እንጃ፣
አንድ ፕሮግራም ብጤ መከተል ጀመርን። ከአልጋ ለምሳ እንነሳለን።ከዚያው ፓሪስን በእግርና በኦቶቡስ እንዞራለን፡፡ አንዳንዴ ሉቭርን ወይም ሚዩዚየም እንጐበኛለን። እራት ከበላን በኋላ እንለያያለን፡፡ እኔ ሲኒማ እገባለሁ፡፡ ስንት ግሩም ፊልም አየሁ! እሷ ወደ ወንዶቿ ትሄዳለች

ሰባት ወይ ስምንት ሰእት ሲሆን ሆቴላችን እንገናኛለን፡፡
ድክም ጥውልግ ባለው ውብ ገላዋ ታቅፈኛለች፣ ወባ እንደያዘው
እስክንቀጠቀጥ ታስቀናኛለች፣ እስክጮህ ታስደስተኛለች፤ ማእበሉ ሲያልፍልኝ ታባብለኝና ታስተኛኛለች። ለምሳ ከአልጋ እንነሳለን እንዲህ ስንል ብዙ ቀናት አለፉ

አንድ ማታ ከእራት በኋላ ካፌ ቁጭ ብለን ስናወራ
«ከበሽታዬ አዳንከኝ'ኮ» አለችኝ
«በአንዱ ወንድ ገላ ሌላውን ወንድ ማቀፍ ተውኩ፡፡»
«እንዴት አርገሽ ተውሽ?»
«እኔ እንጃ፡፡ አንተ እየፈቀድክልኝ እስኪወጣልኝ ጠገብኩ
መሰለኝ። ብቻ ድኛለሁ። አድነኸኛል»
«እኔ ያዳንኩሽ አይመስለኝም፡፡ ራስሽ ነሽ የዳንሽው»
«አንተ ባትኖር አልድንም ነበር»
«ጥሩ። አንቺ ዳንሽ። እኔ ደሞ ታመምኩ»
«ምነው?» አለችኝ በስጋት ድምፅ
«እያወቅሽው:: ሌሊት ሌሊት እንዴት ነው የምሆነው?»
«ታድያ ሰው ሆንክ ማለት ነው እንጂ፣ እሱ ምን በሽታ ነው?»
«ከሉ የባሰ ምን በሽታ ትፈልጊያለሽ? ካንቺ ጋር ፍቅር
ይዞኛል። ለብቻዬ ሳረግሽ መሞከር ይገባኛል፤ ግን ሌሎች ወንዶች
ሲተኙሽና ከነሱ ተቀብዬ ስተኛሽ በሀይል ደስ ይለኛል፡፡ ይሄ በሽታ
አይደለም?
«እሺ። ይሄ በሽታ ያልከው እንዴት ነው የሚያረግህ?»
«እርግጠኛ አይደለሁም?»
ቢሆንም ንገረኝ። ምን ቸገረህ?»
«እሺ፡፡ እንዲህ ይመስለኛል፡፡ አየሽ፣ እወድሻለሁ፡፡ ከልቤ
እወድሻለሁ፡፡ ያላንቺ አንድ ቀንም መኖር የምችል አይመስለኝም።
አንቺን ሌላ ሰው ቢወስድብኝ፣ ላንድ ሰአት ብቻ እንኳ ቢሆን
አልችልም፣ አንቺን ቢቀሙኝ እንደ ሞት ክፉና አስፈሪ ሆኖ ይታየኛል።
አና እንደማይቀሙኝ እርግጠኛ ለመሆን አልችልም ይወስዱብኝ
ይሆን?' እያሉ ማሰብ ብቻ አንድ ራሱን የቻለ ገሀነብ ነው»

«ግን ሲወስዱኝ ደስ ይልሀል?»

«ቆይ' ኮ። እምነት ቢኖረኝ ጥሩ ነበር። ግን ላምንሽ አልችልም፡፡
ማንንም ማመን አልችልም፡፡ ፍጥረቴ ነው። ቆንጆ ነሽ፣ አፍሽ
ይስቃል፣ አይኖችሽ ይጣራሉ፣ ዳሌሽ ምኞት ይቀሰቅሳል ማንም
ወንድ ቢያገኝሽ አይምርሽም፣ አንቺ በበኩልሽ ግብረ ስጋ
ትወጂያለሽ። ቆንጆ ወንዶች ትወጂያለሽ፡ እነሱ ደሞ ክፋታቸው
በየቦታው ይበቅላሉ፡፡ ስለዚህ፣ በሆነ ሰአት እኔን ትተሽ ከሌላ ወንድ ጋር ልትተኚ ትችያለሽ። ይሄ ደሞ ለኔ ሆዴን በቀዝቃዛ ጩቤ
እንደ መውጋት ነው! በሀይል ያስፈራኛል፡ አይታይሽም?»

«ቀጥል»
👍251
«አንቺንም ማመን አልችልም ወንዶቹም ይምሩልኛል ብዬ
ማሰብ አልችል። ልከለክልሽ ደሞ አልችልም፡ ነፃ ሰው ነሽ።
ልከለክልሽ ብችልም፣ ወንዶቹ እንዳይተኙሽ ለመጠበቅ እችል
"ንደሆነ ነው : ንጂ፣ አንቺ እንዳትመኚያቸው ለመከልከል በጭራሽ አልችልም። ውስጡን ከተመኘሻቸው ደሞ፣ እነሱ አይወቁት እንጂ ቀምተውኛል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አንቺን የመነጠቅ ፍርሀቱ አንቺን
ከማግኘት ጋር የተሳሰረ ነው፣ ሊለይ አይችልም፡፡ እኔ ካገኘሽ
ሌላም ሊያገኝሽ ይችላል። ስለዚህ ሁልጊዜ እንደፈራሁ፣ ውስጡን እንደተንቀጠቀጥኩ ነው:: ሁልጊዜ!»

«እህ»

«ምንም መውጫ የለኝ፡፡ እዚህ ፍርሀት ውስጥ መኖር ለብዙ
ጊዜ ኣይቻልም ... ትንሽ ቆይቶ ያሳብዳል። እኔም አበድኩ፡፡»
«አበድክ? እንዴት?»
«ማበድ ማለት እንዴት ነው? የሆነውን ነገር እንዳልሆነ አድርጎ
ማየት ወይም መቁጠር፡ ይኸው ነው ማበድ ማለት አይደለም?
አሁን ኣንዱ ተነስቶ ናፖሊዮን ነኝ ቢል አበደ እንላለን፡፡
ምክንያቱም፣ የሆነውን (እሱን ራሱን) እንደ ሌላ ሰው (እንደ
ናፖሊዮን) አርጎ ስለሚያይ ብቻ ነው»
«እሺ እንተ እንዴት አበድክ?
«ቆይ። ሰው የሚያብደው ለምንድነው? ምን እየነካው ነው?
በዙሪያው የሚታየው እውነት (relite) በጣም ከመጨከኑ ማስፈራቱ ወይም ከማስቀየሙ የተነሳ፣ ይሄ ሰው ይህን እውነት ሊቀበለው አይችልም፡ ይክደዋል “ይሄ እውነት አይደለም፣ እውነት ሊሆን አይችልም ይላል። ይሄ እውነት ካልሆነ፣ እንግዲያው እውነተኛው እውነት ሌላ ነው:: እዚህ ላይ ለሱ የሚስማማውን 'እውነት' ይመርጣል፡፡ ገብቶሻል።»
ገብቶኛል። አሁን ወዳንት ንምጣ»
«ይኸው መጣን፡፡ ለአንድ ደቂቃም ቢሆን ስላንቺ ነገር
እርግጠኛ ልሆን አልቻልኩም፡፡ ይሄ መጠራጠር ከመጠን በላይ
ስለሚያሰቃየኝ፣ ልቀበለው አልቻልኩም፡፡ ስለዚህ ካድኩት፡፡»
«እንዴት?»
«እኔ እዚህ አንቺን ይዤ ሌሉቹ ሊነጥቁኝ አልነበረም?
መከላከያ በፍፁም አላጣሁም? ስለዚህ በውስጤ በድብቅ (ህሊናዬ ደብቄ) እንዲህ አልኩ 'እነሱም ሰዎች እኔም ሰው:: ስለዚህ ወስደው ሲደሰቱባት ምናለበት? ያው እንደኔው ናቸው። እኔና እነሱ ያው ነን። እኔ እነሱ ነኝ፣ እነሱ አኔ ናቸው : አልኩ። አየሽ፡ እንዲህ ከሆነ መስጋትም የለብኝ፡ መፍራትም አያስፈልገኝ፡፡ በዚህ አኳኋን እውነተኛውን እውነት ክጄ፡ በሱ ቦታ የሚመቸኝን እውነት ተካሁ፡፡

«ስለነሱ ስትነግሪኝ ለምን ልቤ እንደሚጠፋ ልንገርሽ»....

💫ይቀጥላል💫
👍15
#ሚስቴን_አከሸፏት


#አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም


"አብርሃም!”

“አቤት!”

"እ..ለዚች ተልካሻ ምክንያት ብለህ ነው ሚስቴን ልፍታ የምትለው ?” ስትል ዳኛዋ ጠየቀችኝ። እዩት
እንግዲህ ክብርት ዳኛ ቋጥኝ ሴትነቷ ተንዶ ሕዝብና መንግሥት በአደራ የሰጣትን የዳኝነት ኃላፊነቷን ሲጫንባት! እስቲ አሁን ችሎት ላይ የቀረበን የአመልካችን ብሶት ተልካሻ? ብሎ ማጣጣል ተገቢ ነው? አይ መብቴማ ሊከበር ይገባል! ያ..ሌባ ትዝ አለኝ። አንዱ ልማደኛ ሌባ ነው አሉ። ለሠባተኛ ጊዜ ስልክ ነጥቆ ሊያመልጥ ሲሞክር ተይዞ ፍርድ ቤት ይቀርባል…፤ ታዲያ ዳኛው በብስጭት፣

“አንተ ልክስክስ ዛሬም እንደገና ሰርቀህ መጣህ ?” ሲሉት ሌባው ኮስተር ብሎ፣

“ክቡር ዳኛ… እንዲህማ አይዝለፉኝ…ደንበኛ ክቡር ነው!” አለ አሉ።

እውነቱን ነው ደንበኛ መከበር አለበት። የግድ ጉዳዬ እንዲካበድ ሚስቴን ከሌላ ወንድ ጋር አልጋ ላይ ማግኘት አልያም በገጀራ ጨፍጭፌያት ፍርድ ቤት መቆም ነበረብኝ እንዴ ? ለምን ምክንያታችንን ያናንቃሉ…?ምክንያቴን ያቀል ዘንድ የማንን ምክንያት ማን በትከሻው ተሸክሞ መዝኖታል? ደግሞ ስንት ጊዜ ነው ለዚህች ዳኛ ስለጉዳዩ የምነግራት? ከዚህ በፊትም ደጋግማ ጠይቃኝ ደጋግሜ መልሻለሁ…።

“አይ ምክንያቱ ለእኔ ከበቂ በላይ ነው ክብርት ዳኛ ስል በትህትና 'ተልካሻ ብላ ያናናቀችውን
ምክንያት ሚስቴን ለመፍታት በቂ መሆኑን ለማረጋገጥ ሞከርኩ። (ክብርት የሚለው ቃል ከብረት
የተሠራ ይመስል አፌ ላይ ከበደኝ።)

እኮ ሚስቴ ካለፍቃዴ ፀጉሯን ተቆረጠች ብለህ የፍች ጥያቄ ይዘህ ፍርድ ቤት ድረስ መጣህ?” አለች ዳኛዋ አሁንም ተገርማ። ምን አስገረማት?

እዎ ስል ኮስተር ብዬ መለስኩ። ዳኛዋም ዝም ! ችሎቱም ዝም ! ሁሉም ሰው እንደ እብድ
እየተመለከተኝ ነበረ። ዳኛዋ እንደዳኛ ብቻ ሳይሆን እንደሴት መናገር ጀመረች (ፆታዋን ወግና)፤
ስልችት ያለኝን ዝባዝንኬ የሞራል ወግ…

“ስማ አብርሃም ! ባለቤትህ እኮ ሕፃን ልጅ አይደለችም። የሚጠቅምና የሚጎዳትን ነገር በሚገባ ራሷ ታውቃለች። ስትቆም ስትቀመጥ አንተን ማስፈቀድ የለባትም። ምንም እንኳን ባሏ ብትሆንም ያገባሀት በባርነት ልትገዛት እና የአንተን ብቻ ፍላጎት ልትጭንባት አይደለም። ይህ ዘመናዊ አስተሳሰብም
አይደለም። አንተ ወጣት ነህ፣ የተማርክ የከተማ ልጅ ነህ። በመቻቻልና በመተሳሰብ እንዲሁም አንድኛችሁ የአንድኛችሁን ፍላጎት በመረዳት ትዳራችሁን አክብራችሁ…” በለው! ሰውነቷ በእልህ እየተንቀጠቀጠ ምክር ይሁን ግሳፄ ያልለየለት ንግግሯን አንተረተረችው።

አሁን ክብርት ዳኛ የተናገሩት ነገር እንዲሁ ከላይ ሲታይ ትክክል ይመስላል። ግን ይሄ ሁሉ ዝባዝንኬ በፍትሐብሔርም፣ በወንጀለኛም፣ በቤተሰብ ሕግም ላይ በቀጥታ የሰፈረ አይመስለኝም ችሎት ውስጥ
ሳይሆን የእኛ ሰፈር የሴቶች እድር ውስጥ የቆምኩ መሰለኝ። ለነገሩ ዳኛዋ ሴት በመሆኗ ሲጀመርም
ፈርቼ ነበር። በኋላ ሳስበው ሙያ መቼስ ፆታ የለውም፣ ሴት ዳኛ እንጂ ሴት ዳኝነት የለም፣ ሴት ሐኪም እንጂ ሴት ሕክምና የለም። ቢሆንም ፆታው ሙያው ላይ የሚያሳርፈው የራሱ ተፅዕኖ ይኖራል፤ ልክ እንደዚች ዳኛ! ደግሞ ሚስትህ ሕፃን አይደለችም” ትላለች እንዴ፤ ምነው ችሎቱን የሕፃን ችሎት
አደረገችው !

“ሴት በዛ ጎመን ጠነዛ ብዬ ተረትኩ። የተረቱ አንድምታ እኮ ስለሴት አይደለም። ብዙ አዋቂ ሲበዛ ሁሉም ጉዳዩን በራሱ እውቀት ልክ እየጎተተ በቀላሉ ሊሠራ የሚችለውን ነገር ማክረም ይከተላል ለማለት ነው። እንኳንም ተረትኩ። ችሎቱን የሞሉት ሴቶች ናቸው፤ ሚስቴን ጨምሮ (ሚስቴ ስል እንዴት እንደሚቀፈኝ…።)

እስቲ አሁን ባለቤትህ እኮ ሕፃን ልጅ አይደለችም፣ የሚጠቅምና የሚጎዳትን ነገር በሚገባ ራሷ
ታውቃለች… ማለት ይሄ ምን የሚሉት ከንቱ ንግግር ነው። አንዲት ሴት ለራሷ ይጠቅመኛል ያለችውን ማወቅ በቃ ሙሉነት ይመስላቸዋል። ይሄ እኮ ነው የዘመኑ ችግር። ለራሴ አውቃለሁ! የሚሉት የማይረባ መኮፈስ። 'ለራሴ የሚጠቅመኝን እኔ አውቃለሁ' ማለት የትዳር አጋርን ፍላጎት ካላገናዘበ ምኑን ትዳር ሆነው ?!

'ሕፃን ልጅ አይደለሁም፤ የሚጠቅመኝን እኔ አውቃለሁ' ብዬ የፈለግኩበት ባድር ሚስቴ ደስ ይላታል?የሚጠቅመኝን እኔ አውቃለሁ' ብዬ ፀጉሬን ሳላበጥር፣ ጥርሴን ሳልቦርሽ ብወጣ ሚስቴ ዝም ትላለች? የሚጠቅመኝን እኔ አውቃለሁ' ብዬ የጨርቅ ሱሪዬን እንደጌሾ ካልሲዬ ውስጥ ጠቅጥቄው ብወጣ ሚስቴ ዝም ትላለች ? በተራ እሽኮለሌና የሞራል ጩኸት ፍቅር ፀንቶ የሚቆም ሊያስመስሉ ሲቀባጥሩ
ይገርሙኛል።

ይሄ እኮ ሁሉም ሴቶች ከሰውነት መንበር የተገፈተሩ ሲመስላቸው ጨምድደው እንዳይወድቁ
የሚንጠለጠሉበት የተረት ገመድ ነው ! ትዳር ማለት ራስን ማወቅ ብቻ አይደለም፤ የትዳር አጋርንም
ጠንቅቆ ለማወቅ መሞከር ነው። የራስን ፍላጎት ብቻ አንጠልጥሎ ትዳር የለም። እንደዛማ ከሆነ
ሁሉም በየራሱ የእውቀትና የፍላጎት አጥር ውስጥ ከመሸገ ምን አብሮነት አስፈለገ።
ይሄው ነው እውነቱ !!
“ክብርት ዳኛ ያሉት ነገር ከእኔ ጉዳይ ጋር አይገናኝም። እኔ ሚስቴ ፀጉሯን በአጭሩ ስለተቆረጠች ሕፃን ናት አልወጣኝም! እኔ ፀጉሯን በመቆረጧ መፋታት እፈልጋለሁ፣ ከእርሷ ጋር መኖር አልፈልግም ነው እያልኩ ያለሁት። ቀድሜ ፀጉሯን እንዳትቆረጥ ነግሬያት ነበር። የራሷን ምርጫ ተከትላለች። እኔም የራሴን ምርጫ እከተላለሁ !! ደግሞስ የቤተሰብ ሕጉ ሚስትን ለመፍታት የግድ ምክንያት መቅረብ አለበት ይላል ? አይልም !! አንድ ሰው መፋታት ከፈለገ በቃ ይፋታል። ስለዚህ ክቡር ፍርድ ቤቱ
ጥያቄዬን በመቀበል ፍቺውን እንዲያፀድቅልኝ በማክበር እጠይቃለሁ!!” አልኩ።

“ለመሆኑ ስትፋቱ ያላችሁን ንብረት እኩል እንደምትካፈሉ ገብቶሃል ?”

“ኧረ በሙሉ ትውሰድ ... ብቻ እንፋታ” አልኩ በምሬት እየተንገሸገሽኩ። ሚስቴ ፌቨን ከኋላ ስታለቅስ (ስትነፋረቅ ነው እንጂ..) ይሰማኛል። ጩኸቴን ቀማችኝ፤ ማልቀስ የሚያምርብኝስ እኔ ! ነጋቸውን
የፍቅር እና መከባበር ባሕር ከፊታቸው ተዘርግቶ መለቃለቅን ይንቁና እንዲህ ነገር ከእጃቸው
ሲያፈተልክ በራሳቸው እንባ የጨው ባሕር ሠርተው ነፍሳቸውን ይዘፈዝፋሉ። እንባቸውን ገድበው
ቁጭት ያመንጩበት እዛው። እንዴት እንደጠላኋት! የአባቴንም ገዳይ እንዲህ አልጠላ።

ዳኛዋ በትኩረት ተመለከተችኝ፤ እኔም በትኩረት ተመለከትኳት። ፀጉሯ ባጭሩ ተቆርጦ ደማቅ
ወርቃማ ቀለም ተቀብቷል፤ ልክ እንደሚስቴ። ወርቃማ ቀለም ውስጥ ነክረው ያወጡት ቡርሽ ነው የሚመስለው፤ ችፍርግ! ፊቷ ላይ ልክ የሌለው ጥላቻ ይንቀለቀላል። ጠላች አልጠላች በሕግ እንጂ በፍቅር አትፈርድ ድሮስ !ሕግ አይጥላኝ። ጠረጴዛው ላይ በተቀመጠው መዶሻ አናቴን ብትፈጠርቀው
ደስታዋ…። ኧረ ጎበዝ እኔ ስለሚስቴ ፀጉር ማጠር ሳወራ ለካስ ዳኛዋ ስለራሷም ፀጉር ነው
የምትሟገተኝ። ግን ሕግ ነውና እንደምንም ብስጭቷን ዋጥ አድርጋ ጉዳዩን በሌላ ጊዜ ለማየት ቀጠሮ ሰጠችን። ሦስተኛ ቀጠሮ መሆኑ ነው። ቆይ ይቺ ሴትዮ በቀጠሮ ብዛት የሚስቴ ፀጉር የሚያድግና ሐሳቤን የምቀይር መስሏት ይሆን እንዴ ? መክሸፍ አይገባትም ... በቃ ሚስቴ ለእኔ ከሽፋለች !!
👍40😁51👏1
ከችሎት ስንወጣ ሚስቴ ከእናቷ (እኔም ማሚ ነበር የምላቸው) እና ታናሽ ወንድሟ ጋር በር ላይ
ቆመው ነበር። እናቷን ሄጄ ሰላም አልኳቸው፤ ለእኔ እናት ማለት ናቸው።ወንድሟ በጉርምስና ደም
ፍላት ፊጥ ፊጥ ይላል። ከጥንቱም ነገረ ሥራው አያምረኝም፤ ዘመናዊ ወልጋዳ። እኔን ሰላም ላለማለት
ሸፈፍ ሸፈፍ እያለ ራቅ ብሎ ሄደ። ለምን እህቱን አስከትሎ እስከምድር ዋልታ አይሄድም። መንደር ለመንደር ከመዋል ይሻለዋል። ሚስቴ ፌቨን ዓይኗ እንባ ተሞልቶ ፍዝዝ ብላ ታየኛለች። እኔ ደግሞ በተቻለኝ አቅም ሁሉ እሷን ላለማየት እሞክራለሁ። ፀጉሯን ከተቆረጠች ጀምሮ ሚስቴ ሳትሆን የሆነ
የተወለድኩበት፣ ያደግኩበት፣ ብዙ ጣፋጭ ትዝታ ያሳለፍኩበትን ሰፈሬን በግሬደር ካፈራረሱት በኋላ የማየው የፍርስራሽ ቁልል መስላ ነው የምትሰማኝ !

ፌቨን በሥልጣኔ ግሬደር፣ በፋሽን ትራክተር ዳግም ላትሠራ ፈራርሳለች !! መፍረስ ቃሉ ያማል !
እቃቃው ፈረሰ ! ዳቦው ተቆረሰ” ሲባል የልጅ ነገር አይደለም ለካ። ድፍን ዳቦ ላይ ያለው ግርማ ሞገስ፣ ምራቅ የሚያስውጥ ጉምዠቱ ሲቆረስ ከሚኖረው ጋር እኩል አይደለም። ያም ዳቦ ይሄም ዳቦ ማለት የዋህነት ነው። ያ ዳቦ፣ ይሄንኛው ሙሉነቱን የሚሸነሽን ስለት ያረፈበት የዳቦ ቁራሽ፣ የዳቦ ፍርፋሪ።ፌሽን የፈራረሰ ሰፈር፣ የተቆራረሰ ዳቦ ሆናለች ለእኔ። የጎኔ ሽራፊ ሳትሆን ከሙሉነት ጎን የተሸረፈች የዳቦ ሽራፊ። እጠላታለሁ? አዎ ! ቆንጆና በአበባ የተዋበ ግቢውን በግዴለሽነት ያፈራረሰበትን ሰው ማን ይወዳል ?! ፌቨንን በማፈቅራት ልክ ጠላኋት በቃ!

“ማናባቱ ያዘኛል ምን የጎበረበት፣

በገዛ ትዳሬ ውኃ ብደፋበት” ብላለች ዘፋኝዋ!....

ይቀጥላል
👍173
አትሮኖስ pinned «#ሚስቴን_አከሸፏት ፡ ፡ #አንድ ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም "አብርሃም!” “አቤት!” "እ..ለዚች ተልካሻ ምክንያት ብለህ ነው ሚስቴን ልፍታ የምትለው ?” ስትል ዳኛዋ ጠየቀችኝ። እዩት እንግዲህ ክብርት ዳኛ ቋጥኝ ሴትነቷ ተንዶ ሕዝብና መንግሥት በአደራ የሰጣትን የዳኝነት ኃላፊነቷን ሲጫንባት! እስቲ አሁን ችሎት ላይ የቀረበን የአመልካችን ብሶት ተልካሻ? ብሎ ማጣጣል ተገቢ ነው? አይ መብቴማ ሊከበር…»
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

...ስለነሱ ስትነግሪኝ ለምን ልቤ እንደሚጠፋ ልንገርሽ»

«ለምንድነው?»
«ከነገርሽኝ ነገሩን አወቅኩት ማለት ነው። ካወቅኩት ደሞ
አያስፈራኝም፡፡ ጭለማ ሲሆን፣ ምን ይመጣብኝ ይሆን? በማለት
እፈራለሁ እንጂ፡ በብርሀን ካየሁት ማንም ሰው ቢሆን አያስፈራኝም፡፡ ማለቴ ሳላውቀው አንድ ሰው ይተኛሽ ይሆን? ብዬ እፈራለሁ እንጂ፣ እያወቅኩ ከሆነ፣ አስር ሰው ቢተኛሽም አልፈራም፡፡
እያወቅኩት ከተደረገ ድርጊቱ የኔ ሆነ ማለት ነው፡፡ የኔ ከሆነ
ሊጎዳኝ አይችልም .. እንዴት እንደተኙሽ ስትነግሪኝ፣ እኔ እነሱን
ሆኜ ተኛሁሽ፣ ተወስዶብኝ የነበረውን ገላሽን፣ ቃላትን መለሱልኝ ማለት ነው። ... ስለዚህ ነው የተኙሽ ወንዶች ቁጥር እንደመብዛቱ መጠን የኔ ደስታ የሚበዛው፡፡»

«አልገባኝም»
«አየሽ፣ ማንም አልተኛሽም ማለት ያስፈራኛል፡፡ ጭለማ ውስጥ
ነኝ ማለት ነው። .. አንድ ሰው ተኝቶኛል ብትይ፡ ትንሽ ይሻለኛል። ግን አሁንም አንድ ሰው ደብቀሽኝ ሊሆን ይችላል። አራት ወንድ ተኛኝ ብትይ የበለጠ ይሻላል። ምክንያቱም የደበቅሽኝ ነገር
የለም ማለት ነው። ስለዚህ መፍራት አያስፈልገኝም፤ ምክንያቱም የተወሰደብኝ ሁሉ ተመልሶልኝ አቅፌዋለሁ ማለት ነው፡፡»

«ገባኝ። አንድ ጥያቄ፡፡»
«ምን?»
«እኔም እነሱም ያው ነን ካልክ፣ ምን እንዳረጉኝ ባታውቅስ ምን
ልዩነት ያመጣል?»
«ይህን አትጠይቂኝ። ላስረዳሽ አልችልም፡፡ እኔም ራሴ
አይገባኝም፡፡ ምናልባት እኔም እነሱም ያው ለመሆን የምንችለው፣ እነሱ ያረጉትን ካወቅኩ ብቻ ይሆናል፡፡»
ዝም ዝም ሆነ፡፡ ታችኛ ከንፈሯን እየነከለች ስታስብ ቆየች
«ልንገርህ?» አለች
«ምን?»
«እኔ በበኩሌ ሌላ ሆኖ ነው የሚታየኝ»
እንዴት ሆኖ ነው ሚታይሽ?»
“በጭራሽ በሽታ አልያዘህም፡፡ እንደሌላ ወንድ ነህ»
ሌሎች ወንዶች ከሌላ ጋር ተኝተሽ ነይልኝ ይሉሻል?»
« አይሉኝም
እኔም የሚሉሽ አልመሰለኝም
«ስማኝ እንግዲህ:: ክርክሩን ተውና አድምጠኝ። በግብረ ስጋ
በኩል ስለሴቶች ታውቃለህ እንጂ፣ በጥቅሉ ስለ ሴቶች ምን
ታውቃለህ? እነሱ ካልነገሩሀ ስለነሱ ለማወቅ አትችልም፡፡ እነሱ ደሞ የውስጡን አይነግሩህም። ለምሳሌ፣ አንተ እኔን ከሌሎች እየተቀበልክ እንደምትደሰትብኝ ለሰው ትነግራለህ ይመስልሀል? ለማንም አትናገርም። ሌሎችም ወንዶች ውስጣዊውን ምስጢር አይነግሩህም፡፡
ስለዚህ ሴት ካልሆንክ ወንዶችን በዚህ በኩል ልታውቃቸው
አትችልም። እኔ ልንገርህ

“ብዙ ጋብቻዎች መቀዝቀዝ ሲጀምሩ፣ ሴትዮዋ ተስፋ
ትቆርጥና ውሽማ ትይዛለች። ባልየው ሲያውቅ ምን እንደሚያደርግ ታውቃለህ? ለጊዜው ይናደዳል፣ ይደበድባታል፣ እንፋታ ይላል።
በኋላ ግን ታርቀው ይቅርታ ያደርግላትና፣ በጣም ሊወዳት
ይጀምራል። ቀዝቅዞ የነበረው ጋብቻ ይሞቃል፣ ይታደሳል። ለምን? ሴትዮዋ ሌላ ወንድ ጋ ስለሄደች ነው

መንገድ ዳር ውጣና ጎረምሶቹን ሴት ሲያድኑ እያቸው።
ሴትዮዋ በጣም ጨዋ ከመሰለቻቸው፣ ምንም ቆንጆ ብትሆን አይከተሏትም፡፡ ትንሽ በመጠኑ ስድ ብጤ ከሆነች ግን
አስተያየቷ፣ አረማመዷ፣ ወይም አለባበሷ በቂ ልቅነት ካሳየ
ጎረምሶቹ ይሻሟታል። በቀላሉ ሊያገኙዋት ስለሚችሉ ብቻ
እንዳይመስልህ፡፡ ዋናው ምክንያት ሌላ ነው። ባለጌ ከመሰለች፣
እንግዲያው ብዙ ወንድ ኣውቃለች ማለት ነው:: ለዚህ ነው
የሚሻሟት
«እየው፣ የሰው ልጅ ፍጥረቱ እንደዚህ ነው:: አንድ የለመድከው ሰው ሊለይህ የሆነ እንደሆነ ልትወደው ትጀምራለህ።
ለህይወትህ የሚያስፈራ በሽታ የያዘህ የመሰለህ እንደሆነ፣ በፊት
ከምንም የማትቆጥራትን ህይወትህን በሀይል ልትወዳት ትጀምራለህ

ሀኪም ጨው እንዳትበላ ያዘዘህ : እንደሆነ፣ ጨው ምንኛ ግሩም
ቅመም እንደሆነ ትገነዘባለህ ሴትህ ወደሌላ የሄደችብህ
እንደሆነ፣ እንዴት ቆንጆ እንደሆነች እንደ አዲስ ሊታይህ ይጀምራል
በራሲ የሚያጋጥመኝን ለምን አልነግርህም? በዚህ ሰሞን
ከማያቸው ወንዶች ሁለቱ እንዴት እንደሚሆኑ ላጫውትህ፡፡ ሁለቱም
ያው ናቸው። ስለዚህ ስለአንዱ ልንገርህ፡፡ ማርሴል ይባላል። በጣም ቆንጆ ነው። ብዙ ሴት ያወቀ ወጣት ነው። ማታ ከእራት በኋላ ካንተ እንደተለየሁ፣ በቀጥታ ወደሱ የሄድኩ እንደሆነ፣ ንፁህ ነኝ፣ የማንም ላብ አልነካኝም፣ ጠረኔ የራሴ ነው፡፡ ልብሴን አስወልቆ ያቅፈኛል! በደምብ ያስደስተኛል፡፡ አንዳንዴ ታድያ፣ ካንተ እንደትለየሁ በቀጥታ ወደሱ እልሄድም፡፡ በፊት ሌላጋ እደርሳለሁ። እና እሱጋ ስሄድ የሌላ ወንድ ላብ ነክቶኛል፣ ጠረኔ የብቻዬ ሳይሆን ከጎረምሳ ጠረን ጋር ተቀላቅሏል። አሁንም ልብሴን ያስወልቀኝና ያቅፈኛል፤ ግን እንደነብር ይሆናል፣ ይጨፈልቀኛል፣ ይነክሰኛል።
ስለሌላ ወንድ አንነጋገርም ግን ሌላጋ እንደነበርኩ በማወቁ የበለጠ እንደሚጣፍጠው ግልፅ ነው፡፡ ይታይሀል?"

«በሚገባ! እና እኔ እንዲህ የምሆንበት ምክንያቱ ምን
ይመስልሻል?» ቀላል ነው። አንደኛ፣ ሌላ ወንድ ከተኛኝ ቆንጆ ነኝ ማለት ነው። ብዙዎች ከተኙኝ እጅግ በጣም ቆንጆ ነኝ፡፡ ስለዚህ የቀለጠ ትፈልገኛለህ፡፡ ሁለተኛ፣ ሌላው ተኝቶኝ አንተ ቀጥለህ ከተኛኸኝ፣ ከሱ ቀምተህ ወሰድከኝ ማለት ነው:: እኔ በሀይል ቆንጆ ሆኜ ከሌሎቹ ሁሉ ቀምተህ ከወሰድከኝ፣ ከሌሎቹ ሁሉ የበለጠ ወንድ ነህ።በወንድነት ከሁሉ በላይ ሆንክ፣ ስለዚህ ደስ ይልሀል፡፡ በጣም ደስ ይልሀል። ወንዶች ሁላችሁም እንደሱ ናችሁ። ግን አየችኝ..

«ግን ምን?» አልኳት
አብዛኛዎቹ ወንዶች ውጪውን ጎበዝ ቢመስሉም ውስጡን ፈሪ
ናቸው፡፡ የውስጥ ስሜታቸውን አይተው መቀበል ይፈራሉ። ስለዚህ ከራሳቸው ይደብቁታል። ሁሉም ወንድ አብዛኛው ወንድ ልበል የራሱን ሴት ሌሎች ሲቀምሱበትና እሱ ነጥቋቸው መልሶ የራሱ ሲያረጋት፣ የበለጠ ወንድነት ይሰማዋል። በሀይል ደስ ይለዋል። ግን ይህን እንደ ጉድ አርጎ ስለሚቆጥረውና ስለሚያፍርበት፣ እያየውም
አውቆ አይኑን ይጨፍናል። ስለዚህ ያስመስላል፤ ያስመስላል፡
ያስመስላል። አቤት ስንት ማስመሰል አለ!

«እዚህ ላይ ነው አንተን ከልቤ የማደንቅህ፡፡ እቺን
ያህል አትፈራም። ወደነብስህ ውስጥ አትኩረህ ትመለከታለህ፡፡ እዚያ ውስጥ ምንም ቀፋፊ ነገር ብታይ አይንህን አትጨፍንም፡፡ ስለዚህ ያለማስመሰል ትኖራለህ ውስጣዊውን ኑሮ ማለቴ ነው። እንግዲህ ወደ ውስጥህ ተመለከትክ፣ ውስጥህ እኔን ሌሎች ቢተኙኝ ከነሱ
ቀምተህ ስትተኛኝ ደስ እንደሚለው ነገረህ። ስለዚህ እኔን 'ሂጂ ወንዶችሽ ጋ አልከኝ። ሄድኩ፡፡ ተመለስኩ። ተደሰትክብኝ፡፡ ወንድ
ነህ። አንተ እውነተኛ ወንድ የሆንከውን ያህል እኔ እውነተኛ ሴት ሆኜ እንደሆነ እጅግ ኩራት ይሰማኛል።»

«አንቺ እንደምትይኝ ከሆንኩ፣ አንቺም እንደኔ አይነት ነሽ።
ልክ እንደኔ አይነት! አብዛኛዎቹ ሴቶች፣ ፍቅር ከያዘኝ ወንድ ጋር
ብቻ ነው ግብረ ስጋ ደስ የሚለኝ ይላሉ። ይህም ማስመሰል፣
ማስመሰል፣ ማስመሰል ነው። አንቺ ግን ለራስሽ አትዋሺም። ቆንጆ ወጣት ሆኖ ቆንጆ ወንድ እያቀያየሩ መደሰት እንዴት ያለ ገነት ነው!' ትያለሽ። እኔኮ አልችልም፣ ቆንጆ ወንድ ሳይ አያስችለኝም፣ቁንጅናውን መንካት መዳሰስ አለብኝ፣ በወጣትነቱ መደሰት አለብኝ ትያለሽ

“አንድ ቀን አንድ ነገር አልሽኝ። አስከመቼም አልረሳውም፡፡»

«ምን አልኩህ?»
👍23👎1
«ሰክረን ሳይሆን ሞቅ ብሎን ነበር፡፡ እና ስለስነ ጽሑፍ ስናወራ
ቆይተን ወደ ግብረ ስጋ ወሬ ተሸጋገርንና፣ እንዲህ አልሽ ሴት
መሆንን የመሰለ ነገር የለም፡፡ አምላክ ከመሆን ይበልጣል። ያንን
ሽንቅጥ ጎልማሳ ታየዋለህ? መልከ ቀና ነው፡፡ ጤነኛ ነው። ኩሩ
ነው። የትኛው አምላክ ነው ይህን ጎልማሳ ለራሱ ለማድረግ
የሚችል? እኔ ግን በአይኔ ልጠራው እችላለሁ፡፡ በደስታ
ይታዘዘኛል። የግል የውስጥ ፍሬውን ለኔ ይሰጠኛል
ምክንያቱም ሴት ነኛ! ቆንጆ ሴት ነኝ፡ ቆንጆ ወጣት ሴት
እስከሆንኩ ድረስ ከአማልክት በላይ ነኝ፡ የግማሹ አለም ጣኦት ነኝ።
« 'ወንዶቹን እያቸው። አለባበሳቸው፣አረማመዳቸው"
አስተያየታቸው ግሩም አይደለም? ይሄ ሁሉ የተደረገው ለኔ ነው:: ለኔ ለራሴ! ለሚቀጥሉት አስር አስራ አምስት አመታት፣የአለም ንግስት ነኝ፡፡ ሁሉ የኔ ነው:: ሁሉ ስልህ፣ የአለም ባንክና የኒው ዮርክ ፎቆች፣ የፓሪስ ሻንዜሊዜ ጎዳና ማለቴ አይደለም፡፡ እሱ
የሱ ምን ዋጋ አለው? ምን ሊያረግልኝ ይችላል? ሁሉ የኔ ነው
ስልህ፣ ዋጋ ያለው ሁሉ የኔ ነው ማለቴ ነው። የጎረምሶቹ ኩሩ
አረማመድ፣ የጋለ አስተያየት የኔ ነው። የተገማመደ፣ የተወጣጠረ
ጡንቻቸውና ከሻኔል ሽቶ ይበልጥ የሚሰርፀው መአዛዊ ጠረናቸው
የኔ ነው:: ወጣትነት የገተረው ወንድነታቸው ለኔ ነው:: ይገባሀል
የምልህ? የኔ ናቸው። እያንዳንዱ ጎረምሳ አንድ ራሱን የቻለ የተለየ
አለም ነው። አዲስ ወንድ ልብሱን አውልቆ በጡንቸኛ ፀጉራም እጁ
ባቀፈኝ ቁጥር፣ አንድ አዲስ አለም ውስጥ ነኝ። ታውቃለህ፣
እስካሁን ስንትና ስንት ወንድ አቅፎኛል፡፡ ታድያ ላይ ላዩን እንደሆነ ነው እንጂ፣ አንዱም አንደሌላው አያቅፈኝም። እያንዳንዱ ከሌሎቹ ልዩ የሆነ ግለኛ ወንድ ነው:: እኔም በበኩሌ እንዱንም እንኳ እንደሌላው አድርጊ እቅፌ አላውቅም፡፡ ከልዩ ልዩ ወንድ ጋር ልዩ ልዩ ሴት ነኝ። ካንዱ ጋር አይናፋር ነኝ፤ ከሌላው ጋር አይናውጣ ነኝ፡ ካንዱ ጋር የተቀጣሁ ጨዋ ነኝ ከሌላው ጋር ስድ ባለጌ ነኝ፣ ከሌላው ጋር ሳቂታ ነኝ ከሌላው ጋር ትራጂክ ነኝ። ብቻ ምን ልበልህ፣ ብዙ ሴቶች ነኝ። ብዙ ቆንጆ ሴቶች ነኝ። ታድያ ይሄ ሁሉ እኔ ራሴ ነኝ፡፡ እና ግሩም ድንቅ ነው። መኖር የማይደገም ትልቅ ተአምር ነው። ወጣት ሴት ሆኖ ልዩ ልዩ ወጣት ወንድን ማቀፍ
ደሞ የተእምር ተአምር ነው፡፡»

« ለምን ዘለአለም ወጣት ሆነን አንኖርም ግን!?” አልሽና
ድንገት ቦርሳሽን እያነሳሽ 'እንሂድ' አልሽኝ። የት? አልኩሽ።
ሆቴላችን እንሂድ። አምሮኛል አልሽኝ። ሄድንና እጅግ በጣም
ተደሰትን።»

«ይህን ሁሉ ታስታውሳለህ?»

«ኧረ ስንት ሌላ ነገር አስታውሳለሁ፡፡ ስላንቺ ምንም ነገር ልረሳ የምችል አይመስለኝም ልጅ ሳለሁ አባቴ ከቤታችን ጓሮ አትክልት ይተከሉ ነበር። ለኔ ትንሽዬ 'ርስት' ሰጡኝና በቆሉ ዘሪሁባት። በቀን አስር ጊዜ እየተመላለስኩ በቆሎዎቼ በቅለው " እንደሆነ አይ ነበር። ከሶስት ቀን በኋላ አንዷ ብቅ አለች። አቤት እንዴት ነው ደስ ያለኝ አረንጓዴ ነበረች፤ ህይወት ነበረች። እየሮጥኩ ሄጄ እናቴን ጎትቼ አመጣኋትና በቆሎን አሳየኋት። አባቴ ከእርሻ ሲመጡ ጉትቼ ወስጀ በቆሉዩን አሳየኋቸው። 'ርስቴ' ላይ አብረው
የተዘሩት ሌሎች በቆሎዎችም በቀሉ። ግን እኔ ያችን የመጀመሪያዋን ነበር " ምወደው። በየቀኑ 'የሄድኩ አያታለሁ፡፡ እያደገች ስትሄድ በየቀኑ ትንሽ ልዩነት አገኝባታለሁ፣ ማለት ሁልጊዜ አዲስ ነበረች፣ ግን ሁልጊዜ ያችው በቆሎዬ ነበረች፡፡ እስካሁን አልረሳኋትም። እስክሞትም አልረሳትም «ያኔ ሲልቪ፣ አንቺም ለኔ እንደዚያች በቆሎዬ ነሽ፣ የጎልማሳነቴ ልዩ ፍቅር ነሽ። በየቀኑ የበለጠ እያወቅኩሽ ስሄድ፣ በየቀኑ የበለጠ እየወደድኩሽ እሄዳለሁ።»
እጇን የያዘ እጄን እያሻሻች
«እኔም እወድሀለሁ። እንዳንት ያለ ወንድ አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡
«አሁን ሰአትሽ አልደረሰም? አልኳት ሰአቷን እያየች
ደርሷል አለች። «ይድረስ፡፡ Je m'en fouts! ዛሬ ካንተ ጋር
ነው የማመሸው:: ደሞ ከንግዲህ ሌሎቹን አልፈልጋቸውም፡፡ ይህን
ሰሞን ካንተ መለየት አልፈልግም፡፡
«አዳዲስ አለሞችን ማየት ይቀርብሻላ»
«ያንተ አለም ከሀያ አዳዲስ አለም ይበልጥ ያስደስተኛል' ኮ።
አታውቅም?
«አውቃለሁ እንጂ» አልኳት እየሳቅኩ
«አቤት ትእቢት! ትንሽ መግደርደርም የለ?» አለችኝ በጉልህ ሰማያዊ አይኖቿ እያየችኝ፣ በሰፊ ውብ አፏ እየሳቀችብኝ፡ እየወደደችኝ
ድንገት ሳቁን እየተወች አንድ ነገር ልነግርህ እፈልግ ነበር»
አለችኝ ንገሪኝ
እንዳትቆጣ፡፡ ወንድ ሆነህ አትስማኝ፡ ደራሲ ሆነህ አዳምጠኝ..

💫ይቀጥላል💫
👍19👎2
#ሚስቴን_አከሸፏት


#ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

...ፌቨን የፈራረሰ ሰፈር፣ የተቆራረሰ ዳቦ ሆናለች ለእኔ። የጎኔ ሽራፊ ሳትሆን ከሙሉነት ጎን የተሸረፈች የዳቦ ሽራፊ። እጠላታለሁ? አዎ ! ቆንጆና በአበባ የተዋበ ግቢውን በግዴለሽነት ያፈራረሰበትን ሰው ማን ይወዳል ?! ፌቨንን በማፈቅራት ልክ ጠላኋት በቃ!

“ማናባቱ ያዘኛል ምን የጎበረበት፣

በገዛ ትዳሬ ውኃ ብደፋበት” ብላለች ዘፋኝዋ!

አራት ዓመት በፍቅር ቆይተናል፤ ከፌቨን ጋር። እድለኞች ነበርን፤ ለድፍን አራት ዓመት ያልቀዘቀዘ
ፍቅር ነበረን። አስር ደቂቃ አብረን ለመቆየት የአንድ ሰዓት መንገድ አቆራርጠን እንገናኛለን። “ዓይንህን ልየው ብዬ ነው የመጣሁት፤ በጣም እቸኩላለሁ” ብላኝ ላባችን ሳይደርቅ ወደየመጣንበት። ላገባት
እፈልግ ነበር። እርሷ ደግሞ አገባኋት አላገባኋት አያሳስባትም። ቀልቧ የትም እንደማልሄድ ነግሯታል። ቀልቧ ታዲያልክ ነበር። ደግሞ ሌላው የእድለኝነታችን ገፅ ሁለታችንም የሚታይ ለውጥ በሕይወታችን እየተከሰተ በሁሉም ነገር ስናድግ ነበር። ፌቨን አካውንቲንግ ተምራ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ሥራ አገኘች። እኔም ልክ ተመርቄ እንደወጣሁ ሥራ ያዝኩ። ትዳር ሲታሰብ አንዳች ኃይል ነገሮችን
ያገጣጥማቸዋል (እግዜር እንዳልል የዛሬውን ፍች ሳስብ ፈርቼ ነው)፤ እናም እንዲህ አልኳት፣

“ፌቪ!”
“ወይዬ” ሁልጊዜ ስጠራት ከዓይኗ ብርሃን ይረጫል። ስሟ ላይ የጨመርኩበት አንዳች ነገር ያለ
ይመስል፣

“ላገባሽ ነው”

“እኔ ... አላምንም… አብረን ልናድር ነው?” ብላ ተጠመጠመችብኝ። አቤት ደስታዋ።በእርግጥ ለሌላ ሰው ይህ አባባሏ ሳያስቀው አይቀርም። ለእኔ ግን የሆነ አስደሳች እና በስሜት የሚንጥ
ነገር ነበረው። አብረን ውለን
“በቃ ልሂድ” ስትል እንዴት ይቀፈኝ እንደነበረ የማውቀው እኔ ነኛ።
አብሮ ማደር የቀለለባቸው ይሄ ተራ ነገር ይመስላቸዋል። ፌቨን ከእቅፌ ውስጥ ቅር እያላት ስትወጣ የዓለም ቅዝቃዜ ሁሉ ወደኔ ይጋልብና አንጀቴ ውስጥ ገብቶ ያንዘፈዝፈኛል። ሸኝቻት ወደቤት ስመለስ ቤቱ ቤት አይመስለኝም፤ በረንዳ።

ለአራት ዓመት በፍቅር ስንቆይ እንኳን ማደር ምሽቱ ምን እንደሚመስል አብረን አይተነው አናውቅም። የፌቨን እናት ናቸው ምክንያታችን ... የሚገርሙ ሴትዮ … ልጆቻቸውን አታምሹ አይሉም፡፡ ግን የእናትነት የፍቅር መብታቸውን በትክክል ተጠቅመውበታል። ልክ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ፌቨን
ቡና ታፈላላቸዋለች (የቤቱ ደንብ ነው)፣ ሁለት ሰዓት ራት ይበላሉ…ልጆቹ ካልተሟሉ ራት አይበሉም
እንደውም ሰዓቱ ካለፈ ልጆቻቸው ቢሟሉም ራት ሳይበሉ ነው የሚያድሩት። ፌቨን ታዲያ ይሄው
ነገር ተከትሏት መጥቶ እኔ ቤት ካልገባሁ እህል በአፉ አይዞርም፤ እንግዲህ ፌቨን ርሃብ እንደማትችል አውቃለሁ። ከራባት እንስፍስፍ ነው የምትለው፤ ዓይኗን እንኳን መግለጥ ያቅታታል!(አቤት ስታሳዝነኝ እንደነበር) ታዲያ እንዴት አባቴ ብዬ ለእራት እዘገያለሁ በጊዜ ወደ ቤቴ ጥድፊያ ነው ! የፌሽን
እናት በእነዚህ የማይዛነፉ ሕጎች ልጆቹን የማይዛነፍ የቤት መግቢያ ሰዓት ድንበር አስምረውላቸዋል።
ካለአባት ስላሳደጓቸው እናታቸውን እንደ አባትም እንደ እናትም ነው የሚያይዋቸው።

ተጋባን ! ትዳራችን በሚያሰክር ፍቅር የተሞላ ነበር ! እድለኛ ነኝ ያልኩት ለዚህ ነው። ልክ እንደ ፍቅረኛ ነበር የምንኖረው። ከቤታችን መውጣት አንፈልግም። ሰውም ወደቤታችን ባይመጣ
ደስታችን.እውነቴን እኮ ነው። ክፉ ሆነን ሳይሆን ፍቅር የሚባለው ስካር አልሰከነልንም ነበር። ሰዓት
አይበቃንም። ቅድም ነግቶ ቁርስ በልተን ምን እንዳወራን ምን እንደሰራን እንኳን ሳናውቀው
እንዳንዴ እንዲያውም ምሳ ሰዓት ሁሉ በየት እንዳለፈ ሳይገባን ብቅ ስንል ማታ ሆኗል። በቃ! እንዲህ
ነበርን እኔና ፌቨን ! “ሁሉም ሲጀምረው እንዲሁ ነው” ይባል ይሆናል፤ ግን ለድፍን ሦስት ዓመት
ስንኖር ደስታችን ሳይሸረፍ፣ ሳቃችን ሳይከስም ፍፁም ደስተኞች ሆነን ነበር።

ደግሞ አማረብን እንጂ !ፌቨን ድሮም ቆንጆ ናት ጭራሽ አበባ መስላ አረፈች። እኔ እንኳን አንድ ሁለት ተብሎ አጥንቴ የሚቆጠር ፍጥረት ትንሽ የተገለበጠች ጎድጓዳ ሰሃን የምታህል ቦርጭ ተከሰተችብኝ ! እንደ አዳምና ሄዋን የቀደመ ሕይወትም ትዝታም ሳይኖረን እዚሁ ቤት በዚሁ እድሜ የተወለድን ይመስል ያለፈውን ዓለም፣ ቤተሰብ፣ ጓደኛ ምናምን ሁሉ ሁለታችንም ረሳነው። የፌቨን እናት ይደውሉና፣ “ኧረ እናንተ ልጆች ድምጣችሁ ጠፋ .በደህናችሁ ነው ?” ይሉናል።

እኔና ፌቪ ታዲያ ልክ ስልኩ ሲዘጋ፣ “በደህናችን ነው ግን ?” ተባብለን እንሳሳቃለን። ከዛ ፕሮግራም እናወጣለን። በቀጣዩ ቅዳሜ የፌቪ እናት ጋር፣ በዛንኛው ደግሞ እኔ ቤተሰቦች ጋር፣ እንዴ ከሰው ተለየንኮ እንባባልና፤ በቀጣዩ ቅዳሜና እሁድ ወፍ የለም !! እንደውም ቅዳሜና እሁድ ማለፉን የምናስታውሰው ሰኞ ነው! እኛ ሌላ ዓለም ውስጥ ነን!

ቢጨንቃቸው የፌቨን እናት ራሳቸው መጥተው ጠየቁን፤ እና መከሩን፣

“ታፍናችሁ አትዋሉ፣ ወጣ እያላችሁ ይንፈስባችሁ ፊታችሁ ፈረንጅ የመሰለው ጠሃይ እጦት እኮ ነው ምቾት እንዳይመስላችሁ።” ምን ያደርጋል ምክራቸው ራሱ ነፈሰበት። ምናባቴ ላድርግ እኔ ራሱ ከቤት
( ስወጣ ገና ትላንት ከገጠር እንደመጣ ሰው እደናበራለሁ። ቤቴ ይናፍቀኛል .ፌቪ ትናፍቀኛለች። ሩቅ አገር የሄድኩ፣ የማልመለስ ይመስለኛል። ት ና ፍ ቀ ኛ ለ ች እንዲህ ዓይነት ትዳር ከመቶው አንድ ነው አሉ። ለምን ግማሽ አይሆንም። የበረከቱ ተካፋዮች እኔና ፌቨን ነበርን።
ሳወራው ያመኛል። ሰዎች የበለጠ በተፋቀሩ ቁጥር እንደስስት መስተዋት ራሳቸውን ከቀላልም
ከከባድም ግጭት መጠበቅ ይኖርባቸዋል። አንዱ ቸልተኛ ሆኖ ሳት ካለው ፍቅር ሲንኮታኮት
ያሰቅቃል። ደግሞ ብቻውን አይንኮታኮትም፤ ጣፋጭ ትዝታንም ይዞ ነው አፈር ድሜ የሚበላው።የጨነገፈ ፍቅርን እንደማሰብ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ምን ሰቆቃ አለ…?

ፌቨንን እወዳት ነበር፣ አከብራት ነበር፣ አፈቅራት ነበር። ትንሽ ነገር፣ ይሄ ነው የማይባል ምክንያት
በውስጤ እሳተ ገሞራ የሚያህል ቅያሜ አፈነዳ። “አሁን ይሄ ምኑ ይካበዳል ? እንኳን ለፍች ተራ
ኩርፊያም አያበቃምኮ” ይባል ይሆናል። “ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል” አሉ።ይሄ ትንሽ የተባለው
ምክንያት ለተመልካች ትንሽ ይምሰል እንጂ ፌቨንን ዓይኗን ማየት ድምፅዋን መስማት የጠላሁት በዚሁ ምክንያት ነው።
ፍቺ ፈለግኩ። ምክንያቱም ፌቨን ፀጉሯን በአጭሩ በመቆረጧ ነበር ...!! በቃ ይሄው ብቻ ነው ምክንያቱ ሚስቴ ፀጉሯን በአጭሩ መቆረጧ። የፌቨን ፀጉር ምን ቢሆን ነው እንዲህ ጉድያ ፈላው፣ ጎጇችንንስ በጭንቅላቱ ያቆመው ?

ፌቨን” አልኳት ሚስቴ ፀጉሯን ተቆርጣ የመጣች ቀን፣

“አቤት”አላለችኝም!!እንደ ወትሮዋ “ወይዬ” አላለችም። ፊቴ ላይ የነበረው ጥላቻ ቅስሟን ሰብሮታል። እንዲህ ሙሉ ስሟን ደግሞ ጠርቻት አላውቅም። ሙሉ ስሟን ከምጠራት ሙልጭ አድርጌ ብሰድባት ይሻላታል። በምርጥ ፍቅረኞች መሀል እኮ በሙሉ ስም ከመጥራት የበለጠ ስድብ የለም።በአገራችን
አቶ፣ ወይዘሮ ምናምን ከሚባሉት ተቀፅላዎች ይልቅ ስማችን ሲቀናጣ ሐሴት ማድረጋችን ሳይታለም የተፈታ ነው። አቶ ጉልማው ከመባል ጉሌ፣ “ጉልዬ” ብንባልም ደስ ነው የሚለን መቼስ። ፍቅረ ቅንጦት !
👍362👎1
ፌቨን ነገሮች ወዴት እየሄዱ እንደሆነ ገብቷታል። ገና በሰላሙ ጊዜ፣ “አብርሽ አንተ ከምትጠላቸው ሰዎች አንዷ ከምሆን ሞቴን እመርጣለሁ” ትል ነበር። ታውቃለች ስወድም ስጠላም ልክ እንደሌለኝ።
ታውቃለች ሳፈቅር ሁሉንም ነገሬን ሰጥቻት የምትረግጠውን የእግሯን ጫማ፣ ከአናቷ በላይ
የምትዘረጋውን ዣንጥላ እንደምሆንላት። ስወዳት በምድር ላይ የዕይታዬ አልፋና ኦሜጋ እሷ ብቻ እንደምትሆን ታውቅ ነበር፤ በቃ ፀባዬ ነው። ላፈቀርኩት እኔን ራሴን ጥቅልል አድርጌ እንደምሰጥ። አንዳንዱ ሰው “በአምላኬማ አትምጡብኝ ይላል። እኔ ግን ፌቨንን ሳፈቅራት ከእግዚአብሔርና ከሷ ቢሉኝ ርሷን ነበር የምመርጠው። እንደውም እግዜርን ራሱን በፌቪንዬማ አትምጣብኝ ባልለው ነው። እግዜር በዚህ ተቆጥቶ ሲያሻው ምድሩን በመብረቅ ይረሰው፣ ከፈለገ ዲን እሳት ያውርድ እንጂ
ካፈቀርኩ እውነቱ ይሄው ነው።

ቤቴን ከሩቅ ስመለከተው የሚንቀዥቀዥ መንፈሴ ደብር እንዳየ አማኝ ይረጋጋል። እዛ ደብር ውስጥ የነፍሴ ፅላት ነበረች ፌቨን !

ፌቨን ሥርዓት ያላት ትሁት ልጅ ነበረች። ደግሞ ስርዓቷ ሰው አለ የለም ብለው ግራና ቀኝ ዓይተው
በአሻንጉሊት ሞራል፣ በአስመሳይ ጨዋነት እንደሚስለመለሙ ሴቶች አልነበረም (ኤዲያ ነበር ለማለት በቃን)። አንዳንዴ እንዲህ ትለኛለች፣ “ታውቃለህ.! ካንተ ጋር ስሆን ተጨማለቂ ተጨማለቂ
ይለኛል ሂሂሂሂ። እንዲህ ነኝ ሳፈቅር። ራሴን ላፈቀርኩት የደስታ ማቅረቢያ ሰሐን አድርጌ የምሰጥ።እና ሳፈቅር ጆሮዬ ዓለምን አይሰማም፡ ድምፅ ሁሉ እሷን ነበር የሚመስለኝ። ብቻዋን ያለች ያህል እስኪሰማት ልክ የሌለው ነፃነት ነበራት ፌቨን፤ እናም ጓደኛዋ (ያች ናዚላ ጓደኛዋ) እንዲህ ትላታለች፣

እናትዬ አንቺን ጉዝጓዙ ላይ ጥሎሻል።በደስታ ለሽሽ ብለሽ የፍቅር እንቅልፍሽን ለጥጭ ሂሂሂሂሂሂሂሂሂ”። ስታወራ ዓይኗ ውስጥ መርዘኛ ቅናት አለ። ሳቋ ቡና ቤት በር ላይ ደንበኛ ለመጥራት እንደሚጮኹ
የቡና ቤት ሴቶች ዓይነት ሳቅ ነው፤ ምኗም አያምረኝም።

ስለ ጓደኛዋ….

የፌቨንን ጓደኛ አልወዳትም። በቃ ሲታይ የሚኮሰኩስ ሰው የለም ? እንደዛ ናት። አባጨጓሬ መንፈስ
የከበባት ነገር ! ድምፅዋ ራሱ ይኮሰኩሳል። ንግግሯ ከቃል ሳይሆን ከአባጨጓሬ የተሠራ ነው
የሚመስለው። በተለይ ሳቋ እንደዚህች ልጅ ሳቅ የሚቀፍ፣ እንደዚህች ልጅ ወሬ የሚያቅለሸልሽ ነገር በምድር ላይ ያለ አይመስለኝም። የሆነ ከዓይኗ የሚወጣው የውድቀት ጨረር ሰላም ይነሳል። እሷንለማየት ትልቅ የትዕግስት መነፅር ያሻል!

“ማሜ ነው ስሟ። እንደው ሳስበው የሆነ ክብ ስም ይመስለኛል፤ ተመልሶ እዛው ዓይነት።ለማያድግና ስንዝር እልፍ ለማይል ስብዕና የተሰጠ ሽክርክሪት። ሽክርክሪት የሚያስደስታቸው ሕፃናት ብቻ ናቸው። ያደገ ሰው እልፍ ማለት ያስፈልገዋል። ዞሮ ሲመለከት ከትላንትናው ትንሽ እልፍ ማለት አለበት። ትላንትም …ትላንት ላይ፣ ዛሬም ትላንት ላይ፣ ነገም ትላንት ላይ የሚቆም ሰው ሌላው ቢቀር ትንሹ ነገር ትዝታ እንኳን በውስጡ የሻገተበት ይሆናል።

ትላንት የሆነ ወንድ ጋር ሶደሬ፣ ዛሬ የሆነ ወንድ ጋር ላንጋኖ፣ ነገ የሆነ ሰውዬጋ ምንትስ ሆቴል ራት
ዛሬ እንትና ሰርግ ላይ ሚዜ .. ከነገ ወዲያ እከሊት ቀለበት ላይ አጃቢ ጠዋት ሳውና፣ ስቲም ገለመሌ … ከሰዓት ፀጉር ቤት፤ ከውስጥ የቆሸሸ ሥጋ እንደዶሮ በሙቅ ውሃ ተዘፍዝፈው ስለዋሉ
ይጠራ ይመስል። ሕይወቷ እንደዛ ነው። በዛ ሄዳ በዚህ ወጥታ ተመልሳ እዛው። እንዲሁ እንደዞረባት፤ ሳታስበው የእድሜ ሰዓቷ ዞሮ ዞሮ ሠላሳ ስምንት ሆነ ! ዕድሜ በየትኛውም ደረጃ መጥፎ አይደለም።እንደ ዕድሜ ካለመሆን በላይ በሽታ ግን ምን አለ። ሰው በዕድሜው ገንዘብ፣ ፍቅር፣ ዘመድ፣ ጓደኛ በተለያየ ምክንያት ላያፈራ ይችላል። ግን ለዕድሜው የሚገባ ጥሩ ባህሪ መኖር ማንን ገደለ? አሁንም ቦርሳዋን አንጠልጥላ መንደር ለመንደር ከመዞር ሌላ ሥራ የላትም። አንዳንዴ ሳስባት የሰላሳ
ስምንት ዓመት ሰይጣን ትመስለኛለች። ዝናብ ጠራራ ሳይል ኮሲ ለኮሲ ሲዞር የሚውል ሰይጣን !

በዚህ እድሜም የሚገርም አቋም ነው ያላት። ወንዶቹን እንደ ለማዳ ውሻ ነው የምታስከትላቸው።
ሕይወቷም ይሄው ነው፤ ወንድ ማስከተል፣ ወንድ መከተል በቃ ! ሰውነቷ ከብዙ ወንዶች ኪስ
በተዋጣ ቁርጥራጭ ሥጋ የተገነባ ነው የሚመስለኝ። የየድርሻቸውን ቢያነሱ 'ማሜ' የምትባል ሴትዮ በምድር የማትኖር ዓይነት !

እንግዲህ የዚህች ዋጋ ቢስ ፍጥረት የልብ ጓደኛ ናት፤ ሚስቴ ፌቨን ! እዚህች ሴትዮ ጋር ተይ
ይቅርብሽ አላልኳትም። ቤታችን ስትመጣ ፊት አልነሳኋትም። ቤቱ “ሽቶ” በምትለው ቅርናታም ነገር
ሲታፈን፣ ስማቸው ተጠርቶ በማያልቅ መንጋ ወንዶች ተረት ጆሮዬ ሲደነቁር ፊት አልነሳኋትም።
ለምን…የምወዳት ሚስቴ ጓደኛ ስለሆነች ! በዛ ላይ ፌቨንን እንደምትቀናባት አውቃለሁ። አስተያየቷ ይነግረኛል። የፌቨንን ፀጉር በእጇ እየነካካች፣ “እኔኮ የሚገርመኝ ከርዝመቱ ብዛቱ ትላታለች።

የፌቨንን ሰውነት ስትነካ ይቀፈኛል። አብራቸው በየሥርቻው የወደቀቻቸው ወንዶች መንፈስ ሁሉ ሚስቴ ላይ የሰፈረ ነው የሚመስለኝ።

የሚስቴን ለስላሳና ጠይም ጉንጭ እየነካች፣ “እስቲ አንድ ቀን ስቲም እንግባ፤ እኔ እጋብዝሻለሁ ፌቭዬ!
አፈር ስሆን…” ስትላት ትንፋሽ ያጥረኛል። አፈር መሆን ከፈለገች ለምን ብቻዋን አፈር አትሆንም
የኔ ሚስት ስቲም ስላልገባች….።

ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ግን ወሬዋ ..! ወይኔ ወሬዋ ! ሰው እንዴት በቅሌቱ አንቱ ለመባል ይጥራል በእግዚአብሔር። እኔ ጥሎብኝ ዋው! እሷ እኮ ተጫዋች ምናምን.. ለመባል ብሎ የሚቀባጥር ሰው ያስመርረኛል።...

ይቀጥላል
👍24😁2
አትሮኖስ pinned «#ሚስቴን_አከሸፏት ፡ ፡ #ሁለት ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ...ፌቨን የፈራረሰ ሰፈር፣ የተቆራረሰ ዳቦ ሆናለች ለእኔ። የጎኔ ሽራፊ ሳትሆን ከሙሉነት ጎን የተሸረፈች የዳቦ ሽራፊ። እጠላታለሁ? አዎ ! ቆንጆና በአበባ የተዋበ ግቢውን በግዴለሽነት ያፈራረሰበትን ሰው ማን ይወዳል ?! ፌቨንን በማፈቅራት ልክ ጠላኋት በቃ! “ማናባቱ ያዘኛል ምን የጎበረበት፣ በገዛ ትዳሬ ውኃ ብደፋበት” ብላለች ዘፋኝዋ!…»
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

በሰፊ ውብ አፏ እየሳቀችብኝ፡ እየወደደችኝ ድንገት ሳቁን እየተወች አንድ ነገር ልነግርህ እፈልግ ነበር» አለችኝ ንገሪኝ
እንዳትቆጣ፡፡ ወንድ ሆነህ አትስማኝ፡ ደራሲ ሆነህ አዳምጠኝ እንጂ
«እሺ»
"Parole d'honneur?"
"Parole d'honneur!"
«አንተን እወድሀለሁ። ከልቤ አፈቅርሀለሁ፡፡ ግን ፖልን ልረሳው
አልችልም። የመጀመሪያዬ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ ሳልጠግበው
ስለሄደብኝ ጭምር ይመስለኛል። «ይገባሀል?»
«ይገባኛል»
«እና አንድንድ ጊዜ ይናፍቀኛል፡፡ ይመስለኛል፣ በውስጤ
የልጃገረድነቴ ጊዜያት ከሱ ጋር ተዋህዷል፡፡ እና ያ ጊዜያት
ሲናፍቀኝ፣ ፖል ይናፍቀኛል። ከልቤ ላወጣው ልረሳው እሞክራለሁ።
ግን የምችል አይመስለኝም፡፡ የምልህ ይገባሀል?»
«ይመስለኛል»
«ስለዚህ ፖልን የሚመስል ሰው ሁሉ ደስ ይለኛል፤ ይስበኛል።
... እና ስለ ባህራም ልነግርህ እፈልጋለሁ፡፡»
ይናገራል ብላ ዝም አለች። መናገሩ እየከበዳት ሄዷል። ዝም
ብዬ ሳያት ቀጠለች
«አንተ ነህ ባህራምን እንድወደው ያረግከኝ፡፡ ስለሱ ብዙ ብዙ
አወራህልኝ። አራት ወር ሙሉ አወራህልኝ፡፡ ከወሬህ እንዳየሁት፣
በጣም በጣም ታከብረዋለህ። ግን እንደማውቅህ አንተ ማንንም
አታከብርም፡፡ ስለዚህ፣ ይሄ ባህራም እንዴት ያለ ሰው ቢሆን ነው? አልኩ። አንዲት ሴት እንዲህ ካለች ደሞ መመለሻ የላትም። ይህን ያባሰው ምንድነው? ከወሬህ እንደተገነዘብኩት ባህራም እንደ ፖል ያለ ሰው ነው። እንደሌላው ሰው ከተራ ጭቃ ተጠፍጥፎ አልተሰራም፡፡ ጀግናዎቹ ከሚሰሩበት ከልዩ ጭቃ ተቀርፆ፣ በልዩ ንፁህ እሳት ውስጥ ነው የተጠበሰው። ባህራምን እንደዚህ አድርገህ
ነው ያሳየኸኝ
«አንተ ያንን ያህል እያከበርከው፣ ከፖል ጋር ያንን ያህል
እየተመሳሰለ፣ እንዴት ላይለኝ ይችላል? እኔ ደሞ
እንደምታውቀኝ ነኝ:: እንዴት ላልመኘው እችላለሁ?»
«ፍቅር ይዞሻል?»
ራሷን በሀይል
እየነቀነቀች፡ ከኋላዋ ጥቁር ሀር ፀጉሯ እየተወዛወዘ፣ የደስታ ሳይሆን የመሰቃየትና የመደናገር ፈገግታ ውብ አፏን እየሸመቀቀው

እኔ እንጂ! እኔ እንጃ! እኔ እንጃ!» አለችና ራሷን ጠረጴዛው ላይ
ደፋች
ረዥም ፀጥታ
እጄን ሰድጄ ራሷ ላይ አሳረፍኩት። ቀና ብላ አየችኝ፡፡ እምባዋ
ይወርዳል
«ሶስት ፍቅር አንድ ላይ ሊይዝ ይችላል?» አለችኝ
“ሴትዮዋ ተራ ከሆነች አይችልም» አልኳት
ጠረጴዛው ላይ የነበረ እጄን ወስዳ ከጎንጯ ጋር እያተሻሸት፣
በእምባዋ እጄን እያረጠበች፡ በተጨነቀ ድምፅ
«ብዙ ጎዳሁህ፣ የኔ ቢራቢሮ?» አለችኝ
ግድ የለሽም አልኳት
«አለኝ እንጂ። ላንተ ብዙ ግድ አለኝ፡፡ ለዚህ እኮ ነው
የምነግርህ፡፡»
«አውቃለሁ»
ለኔ እንዴት ጥሩ ነህ! አሁን ምን ይሻለኛል?»
ቆንጆ ነሽ። ተወዳጅ ነሽ፡፡ ለምን አትወጂውም?»
በመሀረቤ እምባዋን እየጠረገች
«አንተስ? አትቀየምም?»
ሌሎች ጋ ትሂጂ የለ? ስለዚህ ለኔ ያው ነው»
ውይ! እንዴት ደግ ነህ!?»
«ለምን?»
ውሸትክን ነዋ» ተናፈጠች
እኔ እንድደሰት ብለህ
ትሰቃያለህ፡፡»
«የምን ስቃይ?»
መሀረቤን አጥፋ እየመለሰችልኝ
«እንግዲህ አትዋሽ። ይበቃሀል። አውቅሀለሁ'ኮ። ከምትገምተው
በላይ አውቅሀለሁ፡፡ ፊትህ ላይና አይኖችህ ውስጥ ስንትና ስንት ነገር ይታየኛል መስለህ።»
«ምን ይታይሻል?»
«ስለባህራም ስነግርህ በብዙ ነው ያዘንከው::
«ላንቺ ነዋ ያዘንኩልሽ፡፡
«እሱም ታይቶኛል። ግን ለራስህም በሀይል በመሰቃየት ላይ ነህ፡፡ እና በጣም አዝናለሁ፡፡ እንዲህ በመሆኔ በጣም አዝናለሁ፡፡»
«በማዘን የትም አይደረስም፡፡»
አውቃለሁ የኔ ቆንጆ:: ግን ማዘን አይቀርም፡፡»
ዝም ዝም ሆነ
«በኔ ብቻ ሳይሆን በባህራምም ጭምር ነው ያዘንከው። ልክ
ዝም አልኳት
«እንግዲህ ልንገርህ፡፡ እውነቱን ብታውቅ ይሻላል። ልንገርህ?»
«እሺ፡፡»
«ያን እለት ማታ ያ ሰውዬ ባህራምን ሊገድለው አልመጣም?
እና አንተ ኒኮልን ይዘህ ማርዕይ አልሄድክም? ከኒኮል ጋር
ምንም አልሰራችሁም? እውነት ተናገር፡፡»
«ምንም አልሰራንም፡፡ ይልቅ ቀጥዪ።»
«እና ሰውየውን ሲገድለው አላየሁም? እሱን ነግሬሀለሁ። እና
ከዚያ ወደ ቤት ሄድን፡፡ ባህራም ልክ ምንም እንዳልስራ በእርጋታ
ሶፋ ላይ ተቀመጠ። እኔ መጠጥ ሰጠሁትና ሶፋው ላይ አልጋ ብጤ
አነጠፍኩለት፡፡ አንጥፌ ስጨርስ 'እንግዲህ እዚህ ውስጥ ይተኛል።
ነብስ ገድሏል፤ ግን እዚህ ውስጥ ይተኛል። ከጀግና ጋር ነው'ኮ
ያለሁት። ከነብሰ ገዳይ ጋር ነው ያለሁት ብዬ አሰብኩ፡፡ ዘወር ብዬ
አየሁት። አንተ እንደ ነገርከኝ ነው። ዝም ሲል የኢራንን ሻህ
ይመስላል። ግን ማን ያውቃል? ጀግና ስለሆነ አንድ ቀን የኢራንን
ሻህ ይገድለው ይሆናል'ኮ!' ብዬ አሰብኩ
«እና በሀይል ተመኘሁት፡፡ ፍትወት ያንን ያህል አንቆ ይዞኝ
አያውቅም፡፡ ራሴን 'ተይ እንደሱ አታርጊ! - ተይ!'
እያልኩ
ከተቀመጠበት ሄድኩና እግሩ አጠገብ ተምበርክኬ ወደላይ አየሁት።
እንደ ቄስ እጁን ራሴ ላይ አሳረፈና
«ምን ሆነሻል?» አለኝ
ቀስ ብዬ ተነሳሁና አፉ ላይ ሳምኩት
አሁንም «ምን ሆነሻል?» አለኝ። ግን ገብቶታል
«ፈልጌሀለሁ» አልኩት
«እኔ አልፈልግሽም» አለ
«አውቃለሁ ትፈልገኛለህ፡፡ ትፈልገኝ የለ?»
«አዎን፡፡ ካየሁሽ ጀምሮ እንደፈለግኩሽ ነው::»
«ይኸዋ፡፡ አለሁልህ!»
«አይሆንም!»
«ለምን አይሆንም?»
«ምክንያቱን መቼ አጣሽው» አንተን ማለቱ ነው
«እሱ ንደሆነ ግድ የለውም» ኣልኩት
«እኔ ግድ አለኝ!»
«ለምን?»
«ጓደኛዬ ነው:: እፈልግሻለሁ፡፡ ግን እሺ አልልሽም። ስለዚህ
እርሺው!»
«አልረሳውም፡፡ ልረሳው አልችልም፡፡ ልረሳው አልፈልግም።
ሌሊት እመጣለሁ!» አልኩትና ሄጄ አልጋዬ ውስጥ ገባሁ፡፡ ልተወው
ቆረጥኩ። ምናልባት አንድ ሰአት ያህል ቆየሁ። ከዚያ በላይ ግን
ልቆይ አልቻልኩም፡፡ እንደዚህ አላስችል ያለኝ እሱ ስለሆነ ብቻ
ነበር፣ ወይስ ሰው ሲገድል ስላየሁት ነበር? አላውቅም፡፡ የሆነ ሆኖ፣ እሱ እዚያ ተጋድሞ እኔ እዚህ ሆኜ ልታገስ አልቻልኩም
ራቁቴን ወጣሁ፡፡ ሽቶ ተቀባሁ፡፡ ከመኝታዬ ወጣሁ፡፡ የንግዳ
ቤቱን መብራት አበራሁ። እንቅልፍ አልወሰደውም ነበር። በቀጥታ
ሄድኩና ከበላዩ ቆምኩ፡፡ ወደላይ አየኝ፡፡ ሲያየኝ ብዙ ጊዜ ቆየ፡፡
እጁን ሰደደ። ጭኔን ይዞ ወደታች ጎተተኝ
ካሸነፈኩት በኋላ ወደ አልጋዬ ሄድን፡፡»
ዝም አለች፡፡ ያችን ሌሊት እንደምታስታውስ ያስታውቃል፡፡
እንዴት ያለች ሌሊት ነበረች ይሆን? ብጠይቃት እንደማትነግረኝ
እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ስለሌሎቹ ወንዶች በሰፊው ትንገረኝ እንጂ፣
ስለነሱ ጥቃቅኑን ስጋዊ ተግባር ሳይቀር ትዘርዝርልኝ እንጂ፣
ስለፖልና ስለ ባሀራም አትነግረኝም፡፡ እኔም ስለነሱ መጠየቅ ልክ አልመሰለኝም፡፡ ዝም አልኩ። ቀጠለች

«ስለሌሊቱ ልንገርህ እንዴ?» አለችኝ
«ልትነግሪኝ ትፈልጊያለሽ?»
«አልፈልግም። ከፈለግክ ግን እነግርሀለሁ።»
ይህን ያለችኝ «ሳትፈልጊ ብትነግሪኝ ደስ አይለኝም»
እንደምላት አውቃ ነው እንጂ፡ ንገሪኝ ብላትም እንደማትነግረኝ
አውቃለሁ
«ሳትፈልጊ ብትነግሪኝ ደስ አይለኝም» አልኳት
👍16🤔3
ዝም አለች። እኔም ዝም አልኩ
«እንግዲያው ከአልጋ ውጪ የሆነውን ልንገርህ፡፡»
«ባሀራም ጧት ተነስቶ ገላውን ታጥቦ ቁርስ ከበላን በኋላ
«አንድ ነገር ላስረዳሽ እፈልጋለሁ። ፍቀጂልኝ አለኝ
ምንድነው?» አልኩት
«በጣም ቆንጆ ሴትዮ ነሽ፡፡ ማንንም ወንድ ማዘዝ ትችያለሽ፡፡
ባንቺ መገዛት በጣም እፈልግ ነበር። ግን ትላንት ሌሊት
የመጨረሻችን ሌሊት መሆኑን እወቂ» አለኝ
«ለምን?» ብለው
«እያወቅሽ አትጠይቂኝ። የሱን ስም እዚህ ባላነሳ ፈቃዴ ነው።
ትላንትም ነግሬሽ ነበር። ትላንት ልታሸንፊኝ ቻልሽ። ከንግዲህ
ወዲያ ግን በጭራሽ እንዳትጠጊኝ። አደራሽን። ስለሌሊቱ በጣም አመሰግንሻለሁ፡፡ ግን በጣም በጣም ይቆጨኛል!» አለኝ
«እኔ ነኝ ሊቆጨኝ የሚገባው:: ግን ፈፅሞ አልቆጭም አልኩት
«አውቃለሁ፡፡ የተለያየን አይነት ሰዎች ነን። አየሽ፣ እኔ በሰው
ልጆች ብዙ እምነት ኣለኝ። ለምሳሌ፣ እሱ ኒኮልን ቢፈልጋትም ለኔ ብሎ እንደሚተዋት እርግጠኛ ነኝ፡፡ ስለዚህ፤ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ታውቂ የለ?»
«አላውቅም አረ፡፡ ምን ማድረግ አለብህ?»
የበደልኩትን ጓደኛዬን ሂጄ ይቅርታ መለመን አለብኝ»
«ምን?»
«ሄጄ ይቅርታ እለምነዋለሁ። ትላንት ማታ የሰራሁትን
እነግረዋለሁ»
“ይቅርታ ባያረግልህስ?»
«ያረግልኛል»
ባያረግልህስ?»
«እሱ እንግዲህ የራሱ ፋንታ ነው»
«ጓደኝነታችሁ አበቃ ማለት አይደለም?»
«ጓደኝነታችን በውሽት ተደግፎ ከሚቀጥል ቢያበቃ ይሻላል።»
«ይህን ስትነግረው እሱ ይጎዳ የለም?»
«ጠንካራ ነው። ምንም ነገር ሊጎዳው አይችልም። ወንድ ነው»
አለኝ፡፡ አየህ፤ እኔ ብቻ አይደለሁም የብረት ሰው ሆነህ የምትታየኝ»
«ቀጥይ» አልኳት
« እና የኔንስ ነገር እንዴት ታረጋለህ? ብትነግረው ይተወኛል።
እኔ ደሞ እወደዋለሁ። ታድያ፣ ተደስተህብኝ ስታበቃ፣ ለጓደኝነትህ
ንፅህና ስትል የኔን ፍቅር ታፈርስብኛለህ?' አልኩት፡፡»
« ያምነኛል' አለኝ “አንቺ አማርሽኝና በጉልበት ተኛሁሽ
ብል፣ ማንም ወንድ ያምነኛል
ሊሄድ ሲል « አአንድ ነገር ልለምንህ 'ባክህን' አልኩት»
ምን?»
«እኔ ራሴ እንድነግረው ፍቀድልኝ»
«እኔ ብነግረው ይሻልሻል» አለኝ
«ግድ የለህም አልኩት
«እሺ» አለኝ
«ግን እውነቷን ነው የምነግረው» አልኩት
«ለምን?» አለኝ
«ጓደኝነት ብቻ ነው በእውነት ውስጥ መኖር ያለበት? ፍቅርስ
እውነት ኣይወድለትም?» አልኩት
ሳቅ አለ። «ይቅርታ አርጊልኝ፡፡ እንዲህ አይነት ፍቅር
አልመሰለኝም ነበር። እንግዲያው አንቺ ብትነግሪው ይሻላል» አለኝ
«እና እንዲህ ሲለኝ የባሰውን ወደድኩት። ምን ይሻለኛል?»
አለችና፣ እንደገና ራሷን ጠረጴዛው ላይ ደፋች ዝም አልኳት። እንደዚህ ሆነን ረዥም ጊዜ ቆየን። እንደተደፋች
ቦዩ መጥቶ ከኋላዋ ቆመና ይገላምጠኝ ጀመር፡፡ ባለ ፀጉራም እጅ ጎረምሳ ነው። ምናልባት ሊደበድበኝ የሞከረ እንደሆነ ለመከላከል
ያህል ቢራ የሞላ ብርጭቆዬን ጨበጥኩ። በልቤ «አብሾዋም
ፈረንሳይ!» አልኩ
ሲልቪ ቀና አለች። አሁንም እምባዋ ይወርዳል። መሀረቤን
ሰጠኋት፡፡ እምባዋን ስትጠርግ ቦዩ እሷ ልታየው ወደምትችልበት
ቦታ (ወደኔ አጠገብ) ራመድ አለና፣ እኔን ቀሚቆጣ፣ ግን እሷን
በሚያባብል ድምፅ
“Mademoiselle a besoin de u፡elue chose?” አለ («ማድሟዜል
የሚያስፈልጋቸው ነገር አለ?»)
ወደሱ ተመለከተች። የተጨበጠ ፀጉራም እጁ ታያት። ገባት።
“Merci, monsieur , je suis avec un ami” («እግዜር ይስጥልኝ መስዬ፣ ከጓደኛዬ ጋር ነኝ») አለችና፣ በብሩህ ፈገግታ እጇን ሰዳ እጄን እየያዘች “un tr cher ami” አለች። («በጣም ውድ የሆነ ጓደኛ»)
ቦዩ በለዘበ ድምፅ “Pardon momsieur” አለኝና ሄደ፡፡ አንዳንዶቹ ፈረንሳዮች ግሩም የሆነ ጠባይና አስተዳደግ አላቸው
ሲልቪ ፈገግታዋ እየጠፋ
«ምን ይሻለኝ ይመስልሀል?» አለችኝ
«በሱ በኩል ተስፋ የለሽም፡፡ ተይው» አልኳት
«ከዚህ ውሰደኝና ውድድ አርገኝ 'እስቲ። ትችላለህ?»
«ለምን አልችልም?»
«ይህን ሁሉ ከነገርኩህ በኋላ?»
«አሁንም እወድሻለሁ፡፡»
«አውቃለሁ፡፡ እኔም እወድሀለሁ፡፡»
ከፍለን ስንወጣ የቦዩ ፈገግታ ሸንን ፍቅራችንን ወዶልናል...

💫ይቀጥላል💫
👍22👎3
#ሚስቴን_አከሸፏት


#ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም

...ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ግን ወሬዋ ..! ወይኔ ወሬዋ ! ሰው እንዴት በቅሌቱ አንቱ ለመባል ይጥራል በእግዚአብሔር። እኔ ጥሎብኝ ዋው! እሷ እኮ ተጫዋች ምናምን.. ለመባል ብሎ የሚቀባጥር ሰው ያስመርረኛል።

“ዋው እንትናዬ ! እንዴት አባቱ የሚጥም ተጨዋች መሰለሽ ...! ሙድ ያለው ጨዋታው ብትይ፣
የሚወስደኝ ቦታ ብትይ፣ በዛ ላይ አልጋ ላይ ሂሂሂሂሂሂሂሂሂ” አፏን እስከመጨረሻው ከፍታ
ታሽካካለት…። ይህቺን ሴትዮ ሳስባት ከእናትና ከአባት ሳይሆን እንደሙጃ ሕይወት ይሉት ዝናብ
ዘንቦባት ድንገት ሜዳ ላይ ቱግ ብላ የበቀለች አረም ነው የምትመስለኝ የሰው አራሙቻ !

ከፌቨን ጋር የተዋወቁት በአንድ የግል ድርጅት ሲሠሩ ነበር።
“ኦ ማሜ ማለትኮ እናት ማለት
ትላታለች ሚስቴ ይህቺን ሴት ስታደንቃት .. !ይታያችሁ እናት !ለነገሩ እናት” ናት።

"ፌቪዬ የኔ ማር…! ይሄን ሽንኩርት የሚባል ነገር እየከተፍሽ ቆንጅዬ እጅሽን ልታበላሽው ነው…።”
ትላታለች። ፌቨን ልታስተናግዳት ጉድ ጉድ ስትል እኮ ነው፤ ምክሯ ሁሉ ግራ ነው የሚያጋባው።

አንዳንዴ ደግሞ እኔና ፌቨንን እየተመለከተች፣ “እንዴ እናንተ ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ፤ የምን እንጀራ መጠፍጠፍ ነው .. የቀን ሠራተኛ ቅጠሪና ወጥ ምናምን ሠርታ ፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ፣ እንጀራ ከሱቅ ገዛ አድርገሽ መጠቀም፤ እንደው አበሻ ጓዳ ገብቶ ፍዳውን ካልበላ ካላቦካ፣ ካልተጨማለቀ እሳት ላይ ካልተጠበሰ የበላ አይመስለውም፤ ... አይደል እንዴ አብርሽ? ሂሂሂሂሂሂ …ይህቺን የመሰለች ማር የሆነች ልጅማ ሽንኩርት አታስከትፋት…።”

ፌቨን ምሳ ሠርታ ይህቺ መካሪ በደንብ እያጣጣመች ከበላች በኋላ መልሳ እንዲህ ትላለች፣

“ላለለት ሰውማ ማን እንደ ቤት ምግብ እናቴ ትሙት (እናቴ ትሙት ብሎ መሐላ አይቀፍም?) ... ውይ
እንዴት ርቦኝ ነበር። ጥሞኝ በላሁ። ፌቪዬ ከአልጫዋ ትንሽ ጨምሪልኝ ትላለች። እውነቱን ለመናገር
እንደዚህ ስትል ታሳዝነኛለች። ሴት ራበኝ ስትል አልወድም። በዛላይ አንዲት ሴት ያውም ኢትዮጵያዊት
ሴት የፈለገ የሞራል ውድቀት ውስጥ ብትገባ የዚህ ዓይነት አኗኗር የምትመርጥ አይመስለኝም። አንድ
ከሕይወቷ መጽሐፍ የተገነጠለ የኑሮ ገጽ ይኖራል፣ ወይም አንዱ ደደብ የሕያውነት አንቀጿን በክፋት
ሰርዞታል። ወዶ አይደለም ወሬዋ የሚምታታው..

በጣም ቆንጆ ናት። ያውም ውብ የሚባል ዓይነት። ላግባ ብትል እግሯ ላይ ወድቆ የሚያገባት ሺ
ከሚሊየን ነው (በዚህ ዕድሜዋ እንኳን ላግባ ብትል የሚሻማባት ጎረምሳ ብዙ ይመስለኛል…) ግን
ከርታታ ናት። በቃ እዛ ስታድር፣ እዚህ ስትውል፣ ሽሽቷን ልታዘምነው አንዴ ትልልቅ ሆቴሎች፣ ሌላ ጊዜ ሌላ የመዝናኛ ቦታዎች ብትንከራተትም ዓይኗ ላይ እንደሩቅ አገር እሳት ቢል ቢል ሲል የሚታየው አምሮት … እፎይ ማያ ጎጆ መናፈቋ ነው!!
እናም ፌቨንን ፊቴ እንዲህ አለቻት፣ ፌቪ ማር…!ይሄ እንቁላል ቅርፅ ያለው ፊትሽ በዚህ ፀጉርሽ
ባይሸፈን ኖሮ መልክሽ የሚያሳብድ ይሆን ነበር። ብዙ ሳይሆን ትንሽ አጠር …፤ ምን አሁን እኮ ፀጉር ጀርባ ላይ ለቅቆ አንበሳ መምሰል ትንሽ ጊዜው አልፎበታል። ዳሩ አንቺ ወጣ ብለሽ አታይ፤ እዚህ ባልሽ ጋር ታፍነሽ እየዋልሽ ሂሂሂሂሂሂ። ቀልድ አልብሳ መርዟን ረጨችው።

ማታ እንደተኛን ፌቨን ድንገት ከጎኔ ቀጥ ብላ ደረቴ ላይ አገጯን አስደገፈች። ጥቁር ፀጉሯ ፊቴ ላይ
ተነሰነሰ።ዓይኖቼን ጨፍኜ የፀጉሯን ዝናብ ተጠመቅኩት በደስታ … እንደ ሩፋኤል ፀበል።

“አብርሽዬ…”

“እ!”

“ዓይንህን ግለጣ” አለች፤ ገለጥኩ። ከጥቁር ደመና ውስጥ ብቅ ያለች ጠይም ፀሐይ ከበላዬ።

“ማሜ ያለችው ነገር ግን አልገረመህም፤ እንዴት እስከዛሬ አላሰብኩትም…?”

“ምኑን?” አሁን እኔም ነቃ አልኩ።
“ፀጉሬን ባሳጥረው እንደሚያምርብኝ ፀጉር የምትሠራኝ ልጅም ደጋግማ ነግራኛለች” ፊቷ ላይ ያለው
ስሜት የመጠየቅ ሳይሆን ፀጉሯን የምትቆርጥበት መቀስ እንዳቀብላት የመጠየቅ ዓይነት ያበቃለት መርዶ ነበር። ሁሉም ነገር ቅድሚያ የሚቆረጠውም የሚቀጠለውም ልብ ላይ ነው።

“ፀጉርሽን እንድትቆረጭ አልፈልግም። እንኳን መቆረጥ ፀጉርሽን ስታበጥሪ ማበጠሪያው ላይየሚቀሩት የፀጉር ዘለላዎችሽ ያሳዝኑኛል። እና ለእኔ የምታምሪኝ እንደዚህ ስትሆኝ ነው። ፀጉርሽን ከዓይኖችሽ፣ ከአፍንጫሽ እና ከእነዚህ ውብ እጅና እግሮችሽ እኩል እወደዋለሁ፤ እንደ አንድ የሰውነትሽ ክፍል ነው
የማየው” አልኳት ጣቶቼን ፀጉሯ ውስጥ እያርመሰመስኩ።

“እንደዚህ አንበሳ ስመስል ነው የምትወደኝ?” ብላ በማሾፍ ከተናገረች በኋላ ፀጉሯን በጣቷ
መነጨረችውና ከንፈሬን ስማኝ ደረቴ ላይ ልጥፍ ብላ ተኛች። (ይሄ መሳም ቃሌን መስማት ይሁን
ወይስ ስሞ መሸጥ ዓይነት ይሁዳዊ መሳም አልገባኝም)። አተኛኘቷን ሳየው የልብ ምቴን የምታደምጥ ነበር የምትመስለው እንቅልፍ ወሰዳት።ስንተኛ ፀጉሯን ስለማታስይዘው እንዲሁ ነው የምትተኛው።በእንቅልፍ ልቧ በተንቀሳቀሰች ቁጥር የፀጉር መዓበል ትራሱ ላይ ሲነሳ ከትራሱ ላይ እየተንሸራተተ ፍራሹ ላይ ሲርመሰመስ ነፍሴ ሐሴት ታደርጋለች።

ፀጉር እኮ መንፈስ ነው። በተለይ የሴት ልጅ ፀጉር። የቅዱሳን ሥዕልላይ ከራሳቸው በላይ እንደሚታየው የብርሃን አምድ …. የሴት ልጅ ፀጉርም ባፈቀራት ወንድ ብቻ የመንፈስ ዓይን የሚታይ የውበት አምድ
ነው ! የሴት ልጅ ሰውነት በማይታይ የክብር ብርሃን የተከበበ ሕያው ቅድስና ነው። ትልቁ ችግር የብዙ ሴቶች ፍላጎት ለብዙኃኑ ቆንጆ ሆኖ የመታየት መሆኑ ነው። ብዙኃኑ አድናቂ ነው። ብዙኃኑ ጤዛ የሆነ አብሮነቱ ከዓይን ሲርቁ አብሮ ይከስማል። ብዙኃኑን የኔ ከምንለው ሰው ጋር በአንድ ሚዛን ልናስቀምጠው አይገባም። ለብዙኃኑ ብዙ ሆኖ መገኘት በመፈለጋቸው አንዱንም ሳይዙት ምንም ሆነው እንዲቀሩ ያደረጋቸው ብዙ ናቸው።

ፌቨን ተኛች። ስትተኛ የተመጠነ አተነፋፈስና ሰላም ያለው እረፍት ፊቷ ላይ ይረብባታል። የፌቨን
እንቅልፍ ሰላም ባለው ሰፊ ባሕር ላይ ያለ ምንም እንቅስቃሴ በጀልባ እንደመንሳፈፍ ይመስለኛል።ተኝታ ሳያት ታሳሳኛለች። እና ቀስቅሳት ቀስቅሳት ይለኛል። ለብቻዬ ትታኝ ወደሆነ ሰላም ወዳለው ዓለም የሄደች ይመስለኛል፤ እኔ ግን በሐሳብ ነጎድኩ። ወደኋላ … ፌቨንን ዓይቻት ፍቅር የጀማመረኝ
ሰሞን ከሩቅ ስመለከታት የሚገርመኝ ፀጉሯ ነበር። ድብን ያለ ጥቁርና ጠንካራ ፀጉር። ከርዝመቱ ብዛቱ። ከተዋወቅንና ከተቀራረብን በኋላ ደግሞ ፀጉሯ መሐል ጣቶቼ ጠፉ ማለት ዘበት ነው። አንገቷን ወደግራ ዘንበል ስታደርግ ፀጉሯ ወደ ግራ ይናድና በግራ ትከሻዋ አልፎ እየተርመሰመሰ የግራ ጡቷን
ይሸፍነዋል።

ፀጉር ቤት ቆይታ ስትመለስ የሆነ የተቃጠለ ፀጉር ሽታ አፍንጫዬን ያውደዋል። ያንን ሽታ እወደዋለሁ።
እንደውም በሴቶች ፀጉር ቤት ሳልፍ ይሄ የተቃጠለ የፀጉር ሽታ ሲሸተኝ ፀጉር ቤቱ ውስጥ ፌቨን ያለች ይመስለኛል። ፀጉር መተኮስ ማለት እኮ ለውበት አምላክ የሚቃጠል የፀጉር መስዋዕት እንደማቅረብ ነው። (የመረረ የፋሽን ጥላቻ ኖሮብኝ ሳይሆን ውበት ዋጋ እንደሚያስከፍል ለመግለፅ)

ጠዋት ከእንቅልፌ የቀሰቀሰችኝ ፌቨን ናት ቁርስ ሰርታ ሁልጊዜም እንዲሁ ነች። ቁርስ እየበላን
ድንገት ፍርፍሩ ውስጥ አልያም እንቁላል ጥብሱ ውስጥ የፀጉር ዘለላ ማግኘቴ አይቀርም። ዛሬም
ይሄው አንድ ቢመዘዝ የማያልቅ የፌቪን ፀጉር አገኘሁ።

ተሳሳቅን።

የግራ እጄን ጣቶች ወደ ዓይኗ አስጠግታ እየተመለከተች እንዲህ አለች፣ “ይሄ ሽንኩርት እጄን

"አሻከረው”።

ዝም አልኩ።

ዝም ተባባልን።
👍37
የዛች ዋጋ ቢስ ፍጥረት መንፈስ ቃል በቃል በመካከላችን ሥራውን እየሠራ ነው።

ማታ ከሥራ ስመለስ ፌቨን ፊቷ በሳቅ ተጥለቅልቆ ሶፋ ላይ ተቀምጣለች። ቤቱ በእጣን ታፍኖ ቡና ቀራርቧል። ፀጉሯን ተቆርጣ ወደ ቢጫ የሚያደላ ወርቃማ ቀለም ተቀብታዋለች። ዙሪያውን ጆሮዋ አካባቢ ተቀልብሶ ሲታይ ወርቃማ ኮፍያ ያጠለቀች ነበር የሚመስለው። ፈፅሞ አላማረባትም። የሆነ ነገሯ ተገፍፎ እርቃን ነገር ሆናለች። አንገቷ ወደ ላይ የተመዘዘ ይመስል ረዝሟል (የዚህች ልጅ አንገት እንዲህ የመሞቻዋን ቀን እንዳወቀች ወፍ የሰለለ ነበር እንዴ?)። ትከሻዋ የሆነ የተራቆተ ተራራ መስሏል። ትላንት ገና ዛፉ የተቆረጠ …። ፌቨን ነፍስ ይማር! ዘጋኝ። ማየት ዘጋኝ፤ መሳቅ ዘጋኝ፤ መኖር
ራሱ ዘጋኝ !

ጉዳዩ የፀጉር አይደለም..

“እሺ አሁንስ እንደሚያምርብኝ አመንክ…?” አለችኝ ድንገት ቆማ ወገቧን በመያዝ አንዴ ወደፊት አንዴ ወደኋላ እየዞረች በመውረግረግ ... ውበቷን ለማሳየት። እጄን ልኬ ፀጉሯን ነካሁት፤ ማረጋገጥ ፈልጌ
ነበር። እንደው የሆነ ተዓምር ነገር ሆኖ ጥቁር ፀጉሯ ከወርቃማው ኮፍያ ውስጥ ቁልቁል እንዲዘንብ
በልቤ እየፀለይኩ። የፌቨን ፀጉር በቦታው የለም። በቃ የለም። ፀጉሯ ናፈቀኝ። ፌቨን ናፈቀችኝ። የኔ
ፌቨን ከነጥቁር የፀጉር መጋረጃዋ በእጇ ወደ ኋላዋ መለስ የምታደርገው ጥቁር ዘንፋላ ፀጉሯ ጠፋ ...ተገለጠች ! ተገላለጠች። እናም ልዩነቷን አስቆርጣ ጥላ መንገድ ለመንገድ ትርፍርፍ ያሉትን ሁሉንም ሴቶች ሆነች ! ሁሉንም ለመሆን ወደ መንጋው ለመቀላቀል ነበር ይሄ ሁሉ ሩጫ ! እኔና ሁሉም ባለቀለም ፀጉሮች አንድ ቤት ያለን መሰለኝ። ቢሮ … ሱፐር ማርኬት … ካፌ ውስጥ ... ታክሲ ውስጥ .. ቡና ቤት ውስጥ ..የዘፈን ክሊፖች ውስጥ ስልችት ያሉኝ ሴቶች ቤቴም !! ቤቴ አደባባይ የሆነ መሰለኝ!
አካባጅ ሆኜ ነው ?… አይደለም !

“ተቆረጥሽው!” አልኳት፤ጥያቄ አልነበረም።

“አብርሽዬ ፀጉር ቤት የሚሰሩኝ ልጆች እንዴት እንደተገረሙ። ይሄን ያህል የሚያምርብሽ አልመሰለንም ነበር አሉ…።” አሉ አሉ አሉ አሉ አሉ … የፀጉር ቤት ሰራተኞች ብዙዎቹ ለሚሠሯቸው ሴቶች የሚሉት ተመሳሳይ ነገር፣ “ከምሠራቸው ሴቶች ፀጉር ያንቺ ይለያል ለተፈለገው ስታይል የሚሆን ምርጥ ፀጉር
… ምናምን” ሴቶቹ ደግሞ ያምናሉ። ይገርመኛል። እናም ፌቨንን ዝም ብዬ ስመለከታት ድንግልናዋን ሆነ ሌላ ሰው የገሰሰው ዓይነት ስሜት ተሰማኝ። ድንግልና ማለት የእኔ የግሌ ብለን የምናምንበት ጉዳይ እንደሆነ የገባኝ አሁን ነው።

ድንግልና የሥጋ ጉዳይ አይደለም። ማንም ሴት እድሜ ልኳን የምታስቀምጠው የቃል ድንግልና አለ።ለባሏ ብቻ፣ የኔ ላለችው ሰው ብቻ የምትናገረው። ደግሞም የውበት ድንግልና አለ። ፋሽንም ዘመንም የማይገስሰው። የኔ ለምንለው ሰው ብቻ ርካታ የተፈጠረ። ያንን ድንግልና ነው አስረክባ የመጣችው።
አካባጅ አይደለሁም። ፌቨን ራሷ ምስክር ናት። ስንቱን ጉድ፣ ወሳኝ የሕይወት ስንክሳር በቸልታ
ሳልፈው ታውቀኛለች። ይሄ ግን… ከዛ ቀን ጀምሮ ዘጋኝ ! ሁሉም ነገር ዘጋኝ።

“አዝናለሁ” አልኳት። የፊቴ መቀያየር አስደንግጧታል። ድንጋጤዋ ደደብ መስላ እንድትታየኝ አደረገኝ። ሚስቴ ደደብ ከመሰለችኝ ቃሉን በማሰቤ ራሱ ወይ እኔ በቁሜ ሞቻለሁ፣ አልያም የሚስቴ ሕልውና በውስጤ አክትሟል። የሆነ ዓለም ግማሽ ጎኗ የተሸረፈ መሰለኝ። ክብር ራሱ ግማሹ ተሸርፎ
በንቀትና በጥላቻ ምድር ላይ የተከሰከስ

“አብርሽ አልወደድከውም?” አለችኝ ግራ ገብቷት እንደቆመች። እንዴት ነው አንገቷ ተመዝዞ የሆነ
ቆቅ ነገር የመሰለችው፣ በእግዚአብሔር። ወደሷ ማየት ቀፈፈኝ። መኝታ ቤቴ ገብቼ ተኛሁ። ልክ እንደብርሃን በሆነ ቀዳዳ ገብታ ፊቴ የምትቆም ይመስል ጥቅልል ብዬ ዓየር እንኳን እንዳይገባ ታፍኜ ተኛሁ። ግን ምን ያደርጋል በጨለማው ውስጥ ወርቃማ ፀጉሯ እያብረቀረቀ አእምሮዬን ሞላው!

እንዴ ራት አንበላም እንዴ?” አለች፤ እንባ እየተናነቃት ነበር ድምፅዋ ያሳብቃል። አብረን በትዳር
በቆየንባቸው ጊዜያት ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር እንዲህ መጥፎ ፊት ያሳየኋት። በቀጥታ መጥታ
የለበስኩትን የአልጋ ልብስ ገፍፋ ወደዛ ጣለችው። አራስ ነበር ሆና ነበር። “አንተ ራስህን በምን ሒሳብ
ነው የምታስበው፣ ማንኛዋም ሴት የምታደርገው ተራ ነገር ነው ይሄ፣ ለምን ታሳቅቀኛለህ…”

ይሄው “ማንኛዋም ሴት ሆነች ሚስቴ !

ያልወደድከው ነገር ካለ መናገር ትችላለህ። ምን ተፈጥሮ ነው እንዲህ የሚቀያይርህ?”በእልህ ዓይኗን ጎልጉላ ነበር የምትናገረው። እንዲህ ጮኻ ስትናገር ሰምቻት አላውቅም።ግን ምን ዋጋ አለው፤ ጩኸትም ቁጣም የሚያስደነግጠው ለካ ለተቆጪው ባለን ክብርና ፍቅር ልክ ነው። ይሄ ባንዴ ከውስጤ የተነነው የፌቨን ነገር ግርማ ሞገሷንም ድራሹን አጥፍቶት ይሄን ሁሉ ጩኸቷ በሰፈራችን
እያለፈ “ቁራሌ” ከሚል ሰው ጩኸት እንኳን ለይቼ አላየሁትም።

ድንገት ውስጤን ፈንቅሎ በወጣ ጩኸት፣ “አስቀያሚ” አልኳት። በድንጋጤ ሽምቅቅ አለች። አቤት
ብልግና። ከየት አባቴ ነው እንዲህ መዥረጥ አድርጌ ያወጣሁት! ለካ ጨዋ የምንሆነው በትርፍ
ጊዜያችን ነው። ወደ ዋናው እኛነታችን በቁጣ አልያም በደስታ ስንዘፈቅ ብልግናችን እንዲህ እርቃኑን ይቆማል። ፌቨን የጨው አምድ ሆና ቀረች። የአልጋ ልብሱን ገፍፌ እየጎተትኩ ወደ ሳሎን ሄድኩና ሶፋ ላይ ተኛሁ። አልተከተለችኝም። እንኳን ያልተከተለችኝ። ተቀያይሬ ነበር። የሆነ ነገር ባደርጋት ደስታዬ
ነበር። ከሆነ ረዥም ሕንፃ ላይ ብገፈትራት ነገር (ጭካኔ ይመስላል አይደል … ግን ቦታው ላይ ካልሆኑ ስሜቱ አይገባም … ለካ ሰው ሚስቱን በገጀራ አንገቷን አላት ምናምን የሚባለው በእንዲህ ዓይነቱ አጋጣሚ ነው .… ትህትና፣ ዘመናዊነት፣ ሴትን ማክበር ቅብርጥስ የሚባሉት ጣጣዎች ለካ አልገቡንም
.. ገና አልዘመንንም ለካ !)
ከዛ በኋላ ፌቨን ትኑር ትሙት አላውቅም። ሶፋ ላይ አድሬ ጠዋት ወደ ሥራ እሄዳለሁ።ማታ ጓደኞቼ ጋር አምሽቼ እኩለ ሌሊት አካባቢ ወደ ቤት እመለሳለሁ። አልጠጣም፤ ግን ፌቨንን ላለማየት ያለኝ አማራጭ እጅግ በጣም የምጠላቸው መጠጥ ቤቶች ለስላሳ ይዤ መጎለትና ለዛ ቢሱን የሰካራሞች መለፋደድ ማዳመጥ ነበር። እኔ ሚስቴ አበሳጨችኝ ብዬ መጠጥ የምጋት ሰው አይደለሁም። ስወድም
በራሴ አዕምሮ፣ ስጠላም በንፁህ አዕምሮዬ መጥላት እፈልጋለሁ። ከሚስቴ ጋር ተጣላሁ፣ ፍቅረኛዬ
ካደችኝ፣ ቅብርጥስ በሚል ሰበብ የጠርሙስ አንገት አንቀው የሚጨማለቁ ሰዎች በራሳቸው ሕይወት ላይ ድራማ የሚሰሩ ይመስለኛል።

አንድ ቀን የፌቨን እናት ደወሉና በጥብቅ እንደሚፈልጉኝ ነገሩኝ። አከብራቸዋለሁ ግን በቀጠሩኝ ሰዓት ሳልሄድ ቀረሁ። በቀጣዩ ቀን አምሽቼ ቤት ስገባ የፌቨንን እናት ቤት መጥተው አገኘኋቸው። ፌቨን
ጎናቸው ተቀምጣለች። ፀጉሯን በጥቁር ሻሽ አስራዋለች። እንዲህ ግራ ከመጋባት … አስቀያሚ !
“አብርሽ ምንስ ቢሆን እናትህ አልነበርኩም” ብለው ወቀሱኝ እናቷ። ከልቤ አዘንኩ። ግን ስለፌቨን ማውራት አልፈለግኩም። “የሆነውን ሁሉ ሰምቻለሁ፣ ልጅ ናት ሴቶቹ የሚያደርጉት ነገር ያምራታል።
በዕርግጥ ተይ ስትላት መስማት መመካከር ደግ ነበር፤ ግን አንዴውኑ ሆነ። ሁለተኛ እንዳይደገም መመካከር እንጂ እዚህም የሚያደርስ አልነበረም”ብለው ነገሩን ቀለል ሊያደርጉት ሞከሩ። አልገባቸውም

ማዘር። ማንም የእኔ ጉዳት አይገባውም። ማንም የእኔ ጥልቅ ስሜትና ሐዘን አልገባውም።

“ማዘር በጣም የማከብርዎት ሰው ነዎት። ልጅዎትንም አክብረው ሰጥተውኛል። እኔም አንድ ነገር
አስቀይሜያት አላውቅም”
👍24
"አውቃለሁ አብርሽ” አሉ ፊታቸው ላይ ሐዘን ነበር።

“አሁን ግን ከፌቨን ጋር አብሬ መኖር አልፈልግም። ዓይኗን ማየት አልፈልግም። መፋታት ነው
የምፈልገው” አልኳቸው። ፌቨን ያቃሰተች መሰለኝ። እናቷ በድንጋጤ ወደ ፌቨን ዞረው አፈጠጡባት።

አስተያየታቸው፣ “አንቺ ሌላ ያደረግሽው ነገር አለ እንዴ” የሚሉ ይመስላል። እውነቴን ነው ፌቨንን
መፍታት ብቻ ነው የምፈልገው። ለሞተው ትላንታችን ፍቺ የቀብር ስነስርዓቱ ነው ለእኔ! ምን ያደርጋል የበከተ የፍቅር ሬሳ ተሸክሞ ማንዘፋዘፍ። ወደዛ ቀብሮ እርም ማውጣት ነው እንጂ። እርሜን ማውጣት
እፈልጋለሁ። አካባጅ እባላለሁ አውቀዋለሁ። ግትር እንደምባል አውቀዋለሁ። በዘመነው ዘመን ኋላ ቀር እንደምባል አውቃለሁ። ዘመናዊ ለመባል ግን ስሜቴን ማፈን አልፈልግም .…. ፍቺ ፍቺ ፍቺ !!

እዚህ ምድር ላይ መናቅ፣ መገፋት የበዛብን እኛ ቢያንስ ቤተሰባችን ያልነው ካልሰማን፣ ተንቆ ከመኖር፣
ፍላጎታችንን ሲቆርጡ ሲገነጥሉ፣ እኛነታችንን ማንነታችንን ያልሆነ ቀለም ቀብተው አሳመርንላችሁ”
ሲሉን “ገደል ግቡ አንፈልግም” እንል ዘንድ ቢያንስ በትዳራችን ላይ ሥልጣን ሊኖረን ይገባል !! ገደል
ትግባ ፌቨን የምትባል ደነዝ ! እሷን ብሎ ሚስት። የትዳር አጋር ክቡር ቃል ነው። ቃሌ ከመንደርተኛ ቃል ካልተሻለ፣ እኔ ተራ ጎረቤቷ እንጂ ባሏ አይደለሁም። ገደል ትግባ ! ገደል ትግባ … ገደል ትግባ ! ባዶ አድርጋኛለች። አንዲት ሚስት የባሏን ስሜት መረዳት ካቃታት፣ ያውም ሺ ጊዜ የነገራትን … ወጥ
መወጥወጥና ቀለበት ሰክቶ መንከርፈፍ ትዳር ነው ያለው ማነው ... የማትረባ !! እኔ ቁጡ ነበርኩ ? አልነበርኩም !! እና ሳቄን ማን አከሰመው፣ በውስጤ ማን ቁጣ ዘራ ....…. ራሷ ፌቨን።

ይቀጥላል
👍94
አትሮኖስ pinned «#ሚስቴን_አከሸፏት ፡ ፡ #ሶስት ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም ...ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ግን ወሬዋ ..! ወይኔ ወሬዋ ! ሰው እንዴት በቅሌቱ አንቱ ለመባል ይጥራል በእግዚአብሔር። እኔ ጥሎብኝ ዋው! እሷ እኮ ተጫዋች ምናምን.. ለመባል ብሎ የሚቀባጥር ሰው ያስመርረኛል። “ዋው እንትናዬ ! እንዴት አባቱ የሚጥም ተጨዋች መሰለሽ ...! ሙድ ያለው ጨዋታው ብትይ፣ የሚወስደኝ ቦታ ብትይ፣ በዛ ላይ አልጋ…»
#ትኩሳት


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

የሞት ጥሪ

አማንዳ

ወደ ኤክስ ልንመለስ ሶስት ቀን ሲቀረን ሲልቪ ቤቶቿን ለመሰናበት ሄደች። ጊዜው ንፁህ ብርህንና ለስላሳ ሙቀት በዝግተኛው ነፋስ የሚንሳፈፉበት ውብ የፀደይ ቀን ነበር። የፓሪስ ሴቶች ወደ ሰፊው ስመ ጥሩ ጎዳና ወደ ሻንዜሊዜ እንደሚጎርፉ ታወቀኝ፡፡ በሜትሮ ወደዚያው ሄድኩ ሱቆቹ የፀደይ ሞድ ልብሶቻቸውን መስኮቶቻቸው ላይ ዘርግተዋል፤ ካፌዎቹ ጠረጴዛ ወምበሮቻቸውን ወደ መንገዱ
አውጥተው ከአብዛኛዎቹ ጠረጴዛዎች በላይ በልዩ ልዩ ቀለማት ያጌጡ ሰፋፊ ጃንጥላዎችን ዘርግተዋል። ሰዉ ይንጋጋል፤ ትራፊኩ ይፈሳል። አንዱ ካፈ ውጪ ሰዉ የሚተላለፍበት ቦታ አንዲት ትንሽ ጠረጴዛ አጠገብ ተቀመጥኩ

በፀደይ ቀን ሻንዚሊዜ ጎዳናው ዳር ቁጭ ብሎ ቢራ እየጠጡ
አላፊ አግዳሚዋን ፈረንሳዊት እና የስንትና ስንት ሌላ አገር ሴት
መቃኘት። ከዚህ የበለጠ ምን ደስታ ይገኛል? ሴቶቹ የፀደዩን
ብርሀንና ነፋስ ለመቀበል የፈነዱ አበባዎች ይመስላሉ፡፡ የወፍ ቋንቋ
መሳይ ፈረንሳይኛቸውን በልዝብ ድምፃቸው እንደዘፈን እየተቀባበሉ፣የተነጠፈውን ድንጋይ በረዥም ተረከዛቸው ኳ! ኳ! እያረጉ፤ ውብ ዳሌያቸውን እያወዛወዙ ወደላይና ወደታች ይተላለፋሉ፡፡ አይኔ
አብሯቸው ይመላለሳል
ቀስ እያለ አይኔ ሰከረ፡፡ ውበት በዛበት። የአንዷን ኩሩ አረማመድ ሳደንቅ ትንሽ እንደ ተራመደችልኝ፡ ህዝቡ መሀል ገብታ ትጠፋለች፡፡ የሌላዋ ግሩም ቅርፅ አይኔን ይስባል፡ ከዳሌዋና ከባት ከተረከዟ የቱን እንደምመርጥ ገና ሳልወስን ህዝቡ ይውጣታል። ደሞ
የአንዷ ፀጉርና አንገት ልቤን ይወስደዋል። የምትቀጥለዋ ወጣት ነጭ ጥብቅ ያለ ሱሪ ለብሳ ስታልፍ አይኔ በዳሌዋ እንቅስቃሴ ላይ ይተከላል። እሷንም ሚንጋጋው ህዝብ ይውጣታል። ሌላ ወበት ሌላ ሴት ላይ ተጭኖ ሲሄድ አይኔን ይስባል። እንደዚህ ሰል አይኔ ሰከረ

የቢራዩን ሂሳብ ከፍዬ ወደ ፕላስ ደ ሌትዋል በኩል ስራመድ
የአንዷ ፀጉር አይኔን ማረካው:: ሴትዮዋ ከኋላ ሲያዩዋት ምንም
አትል አረ ሻንለዚ ስላየሁዋት ነው እንጂ ሌላ ቦታ ባያት በጣም ደስ ትላለች። አጠር ያለች ወጣት ናት። ቀይ ቦርሳ አንጠልጥላለች። ገላዋን እቀፍ አርጎ የሚሸፍን፣ ነጭ ባለ ሽንሽን የፀደይ
ቀሚስ ለብሳለች። ወገቧን ሰፊ ቀይ ቀበቶ አቅፎታል። ቀይ
ባለረዥም ተረከዝ ጫማ የረገጡት እግሮቿ ወፈር ብለው፣ ቀለማቸው ወደ ቡናማ የሚያደላ ነው። ወፍራም ዳሌዋ ከነጭ ልብሷ
ስር ሲመዛዝ ያስታውቃል፣ ምኞት ይቀሰቅሳል። ግን ዋናው ውበቷ
ፀጉሯ ነው:: ይሄ ንፁህ ነጭ ፀጉሯ ወደኋላዋ ትከሻዋ ድረስ ተለቆ፣
ፀሀዩ ውስጥ ይብለጨለጫል። የረጋ የጨረቃ ብርህን የሚመስል
ንፁህ ፀጉር ከዚህ በፊት የት ነው ያየሁት? የት? መቼ? የት?
ሴትዮዋ ወደ ቀኝ በኩል ተጠምዛ ከሻንዜሊዜ ወጥታ፣ አንድ
ሌላ መንገድ ይዛ ወደሳይ በኩል መራመድ ጀመረች። ለምን
ተከተልኳት? አላውቅም
መንገዱ ዳር ብዙ መኪናዎች ቆመው ነበር፡ እሷ አንድ ጥቁር
ጃጉዋር ስፖርት መኪና ውስጥ ገባች። አልፌያት ወደ ላይ በኩል
መንገዴን ስቀጥል፣

“Hi there!” አለችኝ። ባለሁበት ቆምኩ፡፡ የአማንዳ፥ ድምፅ!
ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም፡፡ ግን ፀጉሩ የሷ ነው። አሁንም
አስታወስኩ። ወደሷ ዞርኩ፡፡ ከመኪናዋ ወጥታ እየሮጠች መጣችና ተጠመጠመችብኝ። ሽቶዋ በጣም ደስ ይላል።
“አማንዳ ነሽ እውነት?
«እዎን»
«ታድያ ያ ሁሉ ጮማ የት ሄደ?»
«ሸጥኩት» አለችና ትንሽ ከኔ ራቅ ብላ አንድ ሁለት ጊዜ
እየተሽከረከረች ምን ይመስልሀል?» አለችኝ
«ተአምር ነው፡፡ በአይኔ ባላይሽ ኖሮ አላምንም ነበር»
"Thank you"
«እውነቴን ነው:: አሁንኮ ማን እንደሆንሽ ሳላውቅ ከኋላሽ
በኩል ሳይሽ የማናት ቆንጆ ፈረንሳይ? እያልኩ ስከተልሽ ነበር»
«አንዲት ሴት ምን መስማት እንደምትወድ ብጥር አርገህ
ታውቃለህ መቸስ፡»
«እውነቴን ነው ኧረ!»
«ደስ ካልኩህ አብረኸኝ ምሳ ብላ እስቲ»
«ጥሩ»
ወደ ቆንጆ ጥቁር መኪናዋ ገባን፡፡ አማንዳ ድሮ ቁምቡርስ
ነበረች፣ አሁን ግን ቢራቢሮ ሆናለች። ትርፍ እገጯ ጠፍቷል፣
አንገቷ ዙርያ ተጠፍጥፎ የነበረው ጯማ ረግፏል። ፊቷ ሙሉ ነው፡
ግን ደስ ይላል፡፡ ከንፈሮቿ ሮዝ ብጤ ቀለም ተቀብተው፣ ሰማያዊ
አይኖቿ በጥንቃቄ ተኩለው፣ ቀይ ጉትቻዋ ከነጭ ፀጉሯ አጠገብ
ሲታይ በረዶ አጠገብ የተንጠለጠለ እንጆሪ ይመስላል።
ከአስቀያሚዎቹ ሴቶች ማህበር ወጥታ፣ ቆንጆዎቹ ማህበር
ገብታለች፡፡ ድምፅዋ ሳይቀር ተለውጧል። ድሮ አልቃሻ ብጤ ነበር፤አሁን ግን ልስልስ ያለ ቆንጆ ድምፅ ነው
«ንገሪኝ እስቲ፡ ምን እንደዚህ ለወጠሽ?» አልኳት
«አንድ ሰካራም አለችኝ
«ምን?»
«ሉን ተሰናብቼ ወደ አገሬ ስሄድ፡ ኤሮፕላኑ ውስጥ አንድ
ሰውዬ አጠገብ ተቀመጥኩ፡፡ ሰውየው ሰክሮ ነበር። ሉ ትዝ እያለኝ ለብቻዬ ሳለቅስ
« ምን ያስለቅስሻል? የወደድሽው ሰውዬ እምቢ አለሽ? ደግ አረገ! በዚህ እድሜሽ ምን እንዲህ አወፈረሽ? አለኝና ያኔውኑ
ረሳኝ፣ እንቅልፍ ወሰደው
«እኔ ግን ቃላቱን እስከ መቼም አልረሳቸውም። ለመጀመርያ
ጊዜ አንድ እውነት ተገለፀልኝ። ይኸውም፣ ጅል ሆኜ ነው እንጂ፣
ውፍረቴን እንደ ጭነት ተሸክሜ መዞር የለብኝም፡፡ ጭነቱን አውርጄ ልጥለው እችላለሁ። ልጥለው ቆረጥኩ። ሳን ፍራንሲስኮ ሄጄ ሙያቸው ክብደት መቀነስ ከሆነ ሰዎች ጋር አራት ወር ሙሉ ሰራሁ። ውጤቱን አንተም አመሰገንክልኝ አለች። ሳቋ ውስጥ ወጣትነትና የህይወት ድል አድራጊነት ይጨፍራል!

ባለ አራት ኮከብ (ማለት ከሁሉ ይበልጥ ምቾት ያለበት) ሆቴሏ
ወሰደችኝ። ክፍሏ ሆነን በቴሌፎን ሁለት ምሳ አዘዘች። አሁንም
አስደነቀችኝ። ኤክስ ሳውቃት ፈረንሳይኛውን በአስቀያሚ የአሜሪካን ቅላፄ ነበር የምታዜመው፣ አሁን ግን የፓሪስ ፈረንሳይኛ ሊሆን ምንም አልቀረው:: እያየችኝ ስትስቅ
“እንደዚህ የሚያስደስት ለውጥ አይቼ አላውቅም።

"Thank you, you re really sweet" አለችኝ

ከምሳ በኋላ «ፓሪስ ምን ትሰራለህ?» አለችኝ፡፡ ነገርኳት፡፡
«አንቺስ?» አልኳት።
«ከኒው ዮርክ የዛሬ ሳምንት መጣሁ፡፡ ይሄ ጃጉዋር ከኢንግላንድ እስኪመጣልኝ ነበር " ምጠብቀው። ነገ ወይም ተነገ ወድያ ወደ ኤክስ መሄዴ ነው:: . . ሉን ማግኘት አለብኝ፡፡ ደህና ነው? አሁንስ የሚፈልገኝ ይመስልሀል? ለጊዜው ሴት አልያዘ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ይዞ እንደሆነ፣ ነጥቄ መውሰድ ይኖርብኛል።»

«ምን?»
«ነጥቄ እወስደዋለሁ። ምነው ገረመህ? የድሮዋ አማንዳ
መስዬህለሁ እንዴ? ተለውጫለሁኮ:: ተዘጋጅቼ ነው የመጣሁት፡፡ ቢያንስ አርባ የሳይኮሎጂ መፅሀፍ አንብቤያለሁ። ደሞ ሉን
አውቀዋለሁ፡፡ ግብረ ስጋ በጣም ይወዳል። ለሱም ተዘጋጅቻለሁ፡፡»

«እንዴት?»
«ለሌላ ሰው ቢሆን ይህን አልነግረውም። አንተ ግን
ትወደኛለህ። ወፍራም ሳለሁም ትወደኝ ነበር፡፡ ለኔ ግድ ነበረህ፡፡
የተሻልኩ ሰው ሆኜ ስላየኸኝ ደሞ በጣም ደስ ብሎሀል። ይሄ ለኔ
ትልቅ ስጦታ ነው። በጣም ተወዳጅ ነህ፡፡ እና ለምን እንደሆነ
ሳላውቅ በጣም አምንሀለሁ፡፡ ለምንድነው እማምንህ?»
👍14🤔2
«ምክንያት የለውም፡ ምክንያት አያስፈልገውም።»
«እውነትክን ነው፡፡ ብልህ ነህ፡፡ እውነቴን ነው፣ ብልህ ነህ፡፡
አገሬ ሆኜ ብዙ ሳስብህ ነበር። ኤክስ ሆነህም እወድህ ነበር፤ ግን ያኔ ስሜቴን ለመናገር እፈራ ነበር። ድፍረት መስሎ ይታየኝ ነበር።
አሁን ግን ሳልፈራ ስሜቴን ልናገር እችላለሁ። ተለውጫለሁ፡፡ ጤነኛ
ሆኛለሁ። ስለዚህ ልንገርህ። በጣም ነው የምወድህ፡፡ ፂምህን ስትላጭ በጣም ታምራለህ፡፡ ቆንጆ ስለሆንክና ስለምወድህ ልስምህ እፈልጋለሁ፡፡ ትፈቅድልኛለህ?» አለችና ፈት ለፊቴ ከተቀመጠችበት
ሶፋ ተነስታ በዝግታ እፌ ላይ ስማኝ ተመልሳ ቁጭ አለች፡፡
እያየችኝ ሳቀች

ግራ ስለገባኝ አሁን አታረሳሺኝ፡፡ ለግብረ ስጋ ተዘጋጅቻለሁ
ስትዪ ምን ማለትሽ ነው?» አልኳት
ቀላል ነው፡፡ ሳላስበው ከአንድ የሰላሳ ሰባት አመት ህንድ ጋር
ገጠምኩ፡፡ ፒ-ኤች-ዲ ያለው ሊቅ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ጎብኚ
መምህር ነው:: እሱ ስለ ግብረ ስጋ ያስተማረኝን ብነግርህ ልታምነኝ አትችልም፡፡ ልነግርህም አልችልም። ቃላቱን አላውቀውም፡፡ ግን ስራውን በሀይል እችልበታለሁ፡፡ ፕሮፌሰሩ ገና ገና ቀሽም ነሽ ይለኛል፡፡ እውነቱን ነው፣ ከህንዶቹ ጋር ስተያይ ቀሽም ነኝ። ግን ሉን ሄጄ አንድ ሌሊት ከኔ ጋር ሳሳድረው እብድ እንደሚሆንልኝ
እርግጠኛ ነኝ፡፡»

«ከዚያስ?»
«ከዚያ እንጃ፡፡ ሉ ከፈለገ አሜሪካ እንሄዳለን። ካልፈለገም ኤክስ
እንቀራለን፡፡ ወይ ፓሪስ እንመጣለን። ካንድ ሶስት አመት በኋላ፣ ሀሳቤን ያልለወጥኩ እንደሆነ፣ እንጋባለን፡፡»

«እምቢ አላገባሽም ያለሽ እንደሆነስ?»
«እሱንም አስቤበታለሁ። ተዘጋጅቻለሁ።»
አየሁዋት። ትችላለች። የፈለገችውን ለማግኘት ትችላለች

በሶስተኛው ቀን አማንዳ፣ ሲልቪ፡ እኔ በአማንዳ ጃጉዋር ወደ
ማርሰይ አመራን። ኤክስ ስንደርስ አርብ ማታ ነበር። ሉልሰገድ
ከጀምሺድ ጋር ሞንቴ ካርሉ ሄዷል። እንግዲህ አማንዳ እስከ ሰኞ ጧት መታገስ ይኖርባታል።
እኔ ፓሪስ ሄጀ ቅናት ውስጥ ስንፈላሰስ ኤክስ ውስጥ ምን ምን
ተደረገ? ከባህራም፣ ከተካና ከኒኮል የሰማሁትን ሳገጣጥመው እንደ እሚከተለው ሆነ፡-...

💫ይቀጥላል💫
👍167
#ሚስቴን_አከሸፏት


#አራት


#በአሌክስ_አብርሃም

....የፌቨን እናት ተቀየሙኝ። ሊያስታርቁን መጥተው፣ “ልጅዎትን ከዚህ በኋላ ማየት አልፈልግም ስላልኳቸው ተቀየሙ። ማንም ወላጅ ቢሆን ይሰማዋል። በደካማ አቅማቸው ከየትና የት ድረስ መጥተው ለማስታረቅ ሲሞክሩ እንቢ አይለኝም ብለው ነበር ያሰቡት። የእኔ ፌቨንን መጥላት ...
ርሳቸውን መናቅ መሰላቸው “አንዲት ሴት ፀጉሯን መቆረጧ ትዳር እስከማፍረስ ካደረሰ ከፍቺው ኋላ ፀጉር ብቻ ሳይሆን ሌላ ምክንያት አለ ማለት ነው” ብለው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። እውነት ነው

ከፌቨን ፀጉር ኋላ ሚሊየን ምክንያቶች ነበሩ፤ ሁሉም ምክንያቶች ግን መነሻቸው ፍቅር ነበር።

“ፍቅር ይታገሳል” ይሉኛል ጉዳዩን የሰሙ ሁሉ፣

ሰው በሰላሙ ቀን እግዜሩንም መጽሐፉንም አሽቀንጥሮ አሸሼ ሲል ይከርምና የቁርጥ ቀን ሲመጣ በየሥርቻው የጣለውን የሕይወት መጽሐፍ አቧራውን አራግፎ እያነሳ ሁሉም ሰባኪ፣ ሁሉም ቃል አጣቃሽ ካልሆንኩ ይላል።

“ፍቅር ይታገሳል”ይለኛል መካሪ። እንዲህ ሲሉኝ ተናገር ተናገር ጩህ ጩህ ይለኛል። “እስቲ እንዲህ
ለነፍስህ ያደርክ ከሆንክ ቃሉ እንደሚለው አታመንዝር ! አዎ አንተ ራስህ ይሄን የምትመክረኝ …
እስቲ በየስርቻው ራሳቸውን ነጥቀህ በቀለም የምታዥጎረጉራቸውን የወሲብ እቃዎችህን እንደሰው ቁጠር ! እዚህች አገር እንደ ሴት መጫወቻ የሆነ ፍጥረት አለ ... ? የማንም ወጠጤ መጥቶ የብልግና
ብሩሹን አንከርፍፎ መንገድ ላይ እንደተሰጣ ሸራ ሴቶችህ ላይ ብልግናውን ሲስል የት ነበርክ…” ማለት ያምረኛል።

አዎ ውስጤ በቁጣ ይሞላል፣ “ላንት 'መብታቸው ነው እያልክ በየመጠጥና ጫት ቤቱ እንደ ጥራጊ ማንም ሲረግጣቸው የነበሩ ሴቶችህን ስታልፍ .… ዛሬ ሴተኛ አዳሪነት፣ወሲብን አቃልሎ ማየት፣ በፋሽን ሥም ሴትነትን መንገድ ዳር አቅርቦ መቸብቸብ ሰተት ብሎ ጓዳህ ገባ! ሴቶች በጓዳ አይቅሩ አደባባይ
ይውጡ ከሚለው የሚበዛው ለሴቶች መጨቆን ያዘነ እንዳይመስልህ። በአደባባይ እንደ ፋሲካ በግ ዳሌና ሽንጥ በዓይኑ እየመተረ ለመምረጥ ነው! ምነው የሚመች ጓዳ፣ ክብር ያለው ጎጆ አግኝተው ሴቶች ጓዳቸው ውስጥ አርፈው በተቀመጡ። ግን ባትለውም ኑሮ ራሱ እየመዘዘ አደባባይ ያሰጣቸዋል።
ያውም የኛ ኑሮ…” ብዬ በአደባባይ ድፍን የአበሻ ወንድ ላይ መጮህ መደንፋት ያምረኛል።

“ለመሆኑ የሴቶችን ልብስና ጫማዎች ታዝበሃል ? ለተረት የሚመች አይደለም ሁሉም። ሴት ልጅ ከቤቷ ወጥታ ወደ መኪናዋ ከመኪና ወደ ሥራ ረጋ ያለ ሕይወት እና እንቅስቃሴ እድትኖር ታስበው የተሰሩ ናቸው። እንዳንተ ስኒከር፣ ሸራ ጫማ፣ ከስክስ አይደለም የሴቶች ጫማ ! ሴቶችህ ራሳቸው ለአደባባይ ማንነት “መብት” የሚል ሽፋን ይሰጡታል እንጂ በብዙሃኑ የከተማ ሴት አዕምሮ ውስጥ
ያለው እውነት ጥሩ ሥራ አግኝቶ ወይም አንዱን ኃብታም አግብቶ “
እርፍ” የሚል ሕልም ነው !
(ይሄ አንዳንዶችን ያበሳጫል ግን ምን ይደረግ እውነት ነው። ከተማውን ከሰኞ እስከ አርብ የዘነጠ ሽቅርቅር ትውልድ ሲሞላው ሥራ አጥነት ጣራ እንደነካ አስተውል። የታደሉ ዜጎች የቆሸሸ እጅ፣የሥራ ቱታ የለበሱ ሰውነቶች የታደሉ ናቸው። ከሰኞ እስከ አርብ መዘነጥ ከሰኞ እስከ አርብ አዕምሮም ሰውነትም ሥራ መፍታቱን የሚያሳይ የውድቀት ባንዲራ ነው !” እንዲህ ብዬ የሚሞግተኝን ሁሉ መሞገት ያሻኛል። ምክራቸው መከራ ከመጨመር ውጪ ወንዝ የማያሻግር እንቶፈንቶ ይሆንብኛልና ሁሉም መጽሐፉ እንደሚለው “የሚያደክሙ አፅናኞች” ናቸው።

በሚስቴ ሰርጥ አልፌ ወደ ሰፊው የሴትነት ባሕር ስመለከት ሴቶች ባሕሉ ብቻ ሳይሆን ልብስና
ጫማቸው ሳይቀር ካቴና ሆኖባቸው ይታየኛል።ፋሽን ነፃነታቸውን ነጥቆ፣ ምቾታቸውን ቀምቶ፣ ወንዱ ፊት የእይታ አምሮት እንዲያሳረፍ ይደረድራቸዋል። እነሱም ፍልቅልቅ እያሉ በካቴናቸው ይኮራሉ ..
ፋሽን ነዋ። እንደውም ትክክለኛው ዘመቻ መሆን ያለበት ሴቶች አደባባይ ይውጡ ሳይሆን ወደ ጓዳ ይመለሱ ነው ! ጓዳቸው ምቹ ይሁን ነው !! እግሯ እስኪቀጥን ከተማውን የምታካልል ቆንጆ የሆነ
ቀን እፎይ ዙረት ሰለቸኝ” ስትል ትሰማታለህ ..ዙረት የሴት ልጅ ተፈጥሮ አይደለማ ! በተሰጣቸው
የተፈጥሮ ፀጋ ልጆችን ሊያሳድጉ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። ልጅን ለማሳደግ እግርን ሰብስቦ ቤት
ውስጥ መቀመጥ፣ ደስታን አሳልፎ መስጠት ይጠይቃል። ልጅ ጭፈራ ቤት ውስጥ አያድግም። ይሄ የዘመናችን አጉል ዘመናዊነት እንዲህ ተጣምሞ ካደገ፣ ልጆቻቸውን በጋሪ እየገፉ በደረቅ ሌሊት ጭፈራ
ቤት የሚሰየሙ እናቶችን መፍጠሩ አይቀሬ ነው።

ደግሞ እንደ ደንቃራ በመብት ስም ስለእንዝላልነት ልትሞግተኝ ፊቴ የምትደቀን እንስት ብስጭቴን
ጣራ ታስነካዋለች። “አንቺ ራስሽ እስቲ ራስሽን ተመልከች፣ ለምንድነው ፀጉርሽን ቀለም የተቀባሽው ከፊትሽ ከለር ጋር እንደሚሄድ' ባለሞያዎቹ ነግረውሽ …. ወይስ እንዲሁ ሲያደርጉ አይተሽ …. ሞኝ ነገር ነሽ … ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አጠቃላይ የፀጉር ሞያተኞች ስንት ይሆኑ በሙያው ጥልቅ እውቀት
ያላቸው። ጥቂቶች በጣም ጥቂቶች። ሌላው የተከበረ ፊትና ፀጉርሽን ቤተ ሙከራ የሚያደርግ
የልምድ አዋላጅ' ነው ! እንግዲህ ይሄ መደዴ ፀጉር ተኳሽ ነው የፊትሽ ቅርፅ፣ የቆዳሽ ልስላሴ፣ ይሄን ቀለም ተቀቢ፣ ያንኛውን ሜካፕ ተለቅላቂ እያለ ቅዠቱን የሚመክርሽ !

እየውልሽ የፀጉር ፍሸናው አንቺን አጥፍቶ የሆነች ሌላ ሴት ማስመሰል እንጂ፣ ያለሽን ውበት ማጉላት አለመሆኑ የሚገባሽ የፍሸናውን ስም ስትሰሚ ነው፣

ቢዮንሴ ሹርባ፣

ሪሃና ቁርጥ፣

ዊትኒ ስታይል..

አንቺ ግን ስምሽ አረጋሽ ነው፣ ወላ ነጃት፣ ወላ ነፊሳ፣ ሄለን፣ ሲቲ፣ ቲቲ ሁኝ ብትፈልጊ…። ካናትሽ
ላይ ቆሞ ፀጉርሽን የሚሰራ የሚመስልሽ የፀጉር ባለሞያ በካውያው ፀጉርሽን እየተኮሰ በማያባራ ለፋፊ አንደበቱ ግን አዕምሮሽን ነው በጋለ የውበት እና ፋሽን ካውያው የሚተኩስሽ ! አንቺነትሽን ሊያተን ነው። ከዛ ምንም ከሌሎቹ ሴቶች የተለየ ውበት አይጨምርልሽም። መጨረሻ ላይ እንደሌሎች
ሴቶች ትሆኛለሽ። በቃ ይሄው ነው። ደግሞ ወንዱ ባንቺ ውበት ይደነቃል ብለሽ አትድከሚ። ወንዱ
በሚጎረጉረው ስልኩ መለዓክ የመሰሉ ሴቶች ፎቶ ላይ አፍጥጦ ነው የሚውለው፤ ምንም ብትሆኝ
አይደንቀውም፡፡ ጉዳዩ ከሰውነትሽ ነው። ከስልኩ ወዲያ አምሮት የቀሰቀሰበትን ገላ ሲያጣ አጠገቡ
ያለሽውን አንቺን እንደማስታገሻ ከማይረባ የፍቅር ዲስኩር ጋር ይወስድሻል ! የአንቺን ሥጋ አቅፎ
መንፈሱ በተመለከተው ገላ ላይ ነው የሚቃዠው…” ብቻዬን ተቀምጬ እንዲህ ነው የማስበው።ሴት ወንዱ በሽተኛ የሆነ ይመስለኛል። ለክርክር የሚያሞጠሙጠው አፉ ለምን ራሱን ለመጠየቅ
እንደማይጠቀመው ግራ ይገባኛል።

“እንደ ኳስ መካሪው ወደ ፋሽን …. ፋሽኑ ወደ ወንድ፣ ወንዱ ወደ አልጋ፣ አልጋው ወደ ተዘባረቀ ሕይወት እየተቀባበለ በሴት ልጅ ሕይወት ጨዋታውን ያሞቀ ዘመን እንደዚህ ዘመን ከቶ አልተከሰተም።ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነውና ዘመኑ ራሱን 'የሰለጠነ የሚል ስም አከናንቦታል ከክንብንቡ ስር … በስልጣኔ መዳፍ አፋቸውን የታፈኑ 'ስልጡን የፋሽን ባሮች ዓየር አጥሯቸው ይወራጫሉ። ለዚህ መፍትሄው ራስን መሆን ነው። በዚህ ዘመን በትክክል የሚያስፈልገው “ራስሽን ሁኚ” የሚል መካሪ ነው። ልድገመው ራስሽን ሁኚ ! የነፈሰው ንፋስ ጋር ልንፈስ ካልሽ እብድ የበላው በሶ ሆነሽ ትቀሪያለሽ... የኔን ሚስት አታያትም … ይቺን አስቀያሚ ! በክብር ካኖርኩባት ዙፋን ላይ ፀቁልቁል በአናቷ ወርዳ
👍291🔥1😁1