አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሚስቴን_አከሸፏት


#አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም


"አብርሃም!”

“አቤት!”

"እ..ለዚች ተልካሻ ምክንያት ብለህ ነው ሚስቴን ልፍታ የምትለው ?” ስትል ዳኛዋ ጠየቀችኝ። እዩት
እንግዲህ ክብርት ዳኛ ቋጥኝ ሴትነቷ ተንዶ ሕዝብና መንግሥት በአደራ የሰጣትን የዳኝነት ኃላፊነቷን ሲጫንባት! እስቲ አሁን ችሎት ላይ የቀረበን የአመልካችን ብሶት ተልካሻ? ብሎ ማጣጣል ተገቢ ነው? አይ መብቴማ ሊከበር ይገባል! ያ..ሌባ ትዝ አለኝ። አንዱ ልማደኛ ሌባ ነው አሉ። ለሠባተኛ ጊዜ ስልክ ነጥቆ ሊያመልጥ ሲሞክር ተይዞ ፍርድ ቤት ይቀርባል…፤ ታዲያ ዳኛው በብስጭት፣

“አንተ ልክስክስ ዛሬም እንደገና ሰርቀህ መጣህ ?” ሲሉት ሌባው ኮስተር ብሎ፣

“ክቡር ዳኛ… እንዲህማ አይዝለፉኝ…ደንበኛ ክቡር ነው!” አለ አሉ።

እውነቱን ነው ደንበኛ መከበር አለበት። የግድ ጉዳዬ እንዲካበድ ሚስቴን ከሌላ ወንድ ጋር አልጋ ላይ ማግኘት አልያም በገጀራ ጨፍጭፌያት ፍርድ ቤት መቆም ነበረብኝ እንዴ ? ለምን ምክንያታችንን ያናንቃሉ…?ምክንያቴን ያቀል ዘንድ የማንን ምክንያት ማን በትከሻው ተሸክሞ መዝኖታል? ደግሞ ስንት ጊዜ ነው ለዚህች ዳኛ ስለጉዳዩ የምነግራት? ከዚህ በፊትም ደጋግማ ጠይቃኝ ደጋግሜ መልሻለሁ…።

“አይ ምክንያቱ ለእኔ ከበቂ በላይ ነው ክብርት ዳኛ ስል በትህትና 'ተልካሻ ብላ ያናናቀችውን
ምክንያት ሚስቴን ለመፍታት በቂ መሆኑን ለማረጋገጥ ሞከርኩ። (ክብርት የሚለው ቃል ከብረት
የተሠራ ይመስል አፌ ላይ ከበደኝ።)

እኮ ሚስቴ ካለፍቃዴ ፀጉሯን ተቆረጠች ብለህ የፍች ጥያቄ ይዘህ ፍርድ ቤት ድረስ መጣህ?” አለች ዳኛዋ አሁንም ተገርማ። ምን አስገረማት?

እዎ ስል ኮስተር ብዬ መለስኩ። ዳኛዋም ዝም ! ችሎቱም ዝም ! ሁሉም ሰው እንደ እብድ
እየተመለከተኝ ነበረ። ዳኛዋ እንደዳኛ ብቻ ሳይሆን እንደሴት መናገር ጀመረች (ፆታዋን ወግና)፤
ስልችት ያለኝን ዝባዝንኬ የሞራል ወግ…

“ስማ አብርሃም ! ባለቤትህ እኮ ሕፃን ልጅ አይደለችም። የሚጠቅምና የሚጎዳትን ነገር በሚገባ ራሷ ታውቃለች። ስትቆም ስትቀመጥ አንተን ማስፈቀድ የለባትም። ምንም እንኳን ባሏ ብትሆንም ያገባሀት በባርነት ልትገዛት እና የአንተን ብቻ ፍላጎት ልትጭንባት አይደለም። ይህ ዘመናዊ አስተሳሰብም
አይደለም። አንተ ወጣት ነህ፣ የተማርክ የከተማ ልጅ ነህ። በመቻቻልና በመተሳሰብ እንዲሁም አንድኛችሁ የአንድኛችሁን ፍላጎት በመረዳት ትዳራችሁን አክብራችሁ…” በለው! ሰውነቷ በእልህ እየተንቀጠቀጠ ምክር ይሁን ግሳፄ ያልለየለት ንግግሯን አንተረተረችው።

አሁን ክብርት ዳኛ የተናገሩት ነገር እንዲሁ ከላይ ሲታይ ትክክል ይመስላል። ግን ይሄ ሁሉ ዝባዝንኬ በፍትሐብሔርም፣ በወንጀለኛም፣ በቤተሰብ ሕግም ላይ በቀጥታ የሰፈረ አይመስለኝም ችሎት ውስጥ
ሳይሆን የእኛ ሰፈር የሴቶች እድር ውስጥ የቆምኩ መሰለኝ። ለነገሩ ዳኛዋ ሴት በመሆኗ ሲጀመርም
ፈርቼ ነበር። በኋላ ሳስበው ሙያ መቼስ ፆታ የለውም፣ ሴት ዳኛ እንጂ ሴት ዳኝነት የለም፣ ሴት ሐኪም እንጂ ሴት ሕክምና የለም። ቢሆንም ፆታው ሙያው ላይ የሚያሳርፈው የራሱ ተፅዕኖ ይኖራል፤ ልክ እንደዚች ዳኛ! ደግሞ ሚስትህ ሕፃን አይደለችም” ትላለች እንዴ፤ ምነው ችሎቱን የሕፃን ችሎት
አደረገችው !

“ሴት በዛ ጎመን ጠነዛ ብዬ ተረትኩ። የተረቱ አንድምታ እኮ ስለሴት አይደለም። ብዙ አዋቂ ሲበዛ ሁሉም ጉዳዩን በራሱ እውቀት ልክ እየጎተተ በቀላሉ ሊሠራ የሚችለውን ነገር ማክረም ይከተላል ለማለት ነው። እንኳንም ተረትኩ። ችሎቱን የሞሉት ሴቶች ናቸው፤ ሚስቴን ጨምሮ (ሚስቴ ስል እንዴት እንደሚቀፈኝ…።)

እስቲ አሁን ባለቤትህ እኮ ሕፃን ልጅ አይደለችም፣ የሚጠቅምና የሚጎዳትን ነገር በሚገባ ራሷ
ታውቃለች… ማለት ይሄ ምን የሚሉት ከንቱ ንግግር ነው። አንዲት ሴት ለራሷ ይጠቅመኛል ያለችውን ማወቅ በቃ ሙሉነት ይመስላቸዋል። ይሄ እኮ ነው የዘመኑ ችግር። ለራሴ አውቃለሁ! የሚሉት የማይረባ መኮፈስ። 'ለራሴ የሚጠቅመኝን እኔ አውቃለሁ' ማለት የትዳር አጋርን ፍላጎት ካላገናዘበ ምኑን ትዳር ሆነው ?!

'ሕፃን ልጅ አይደለሁም፤ የሚጠቅመኝን እኔ አውቃለሁ' ብዬ የፈለግኩበት ባድር ሚስቴ ደስ ይላታል?የሚጠቅመኝን እኔ አውቃለሁ' ብዬ ፀጉሬን ሳላበጥር፣ ጥርሴን ሳልቦርሽ ብወጣ ሚስቴ ዝም ትላለች? የሚጠቅመኝን እኔ አውቃለሁ' ብዬ የጨርቅ ሱሪዬን እንደጌሾ ካልሲዬ ውስጥ ጠቅጥቄው ብወጣ ሚስቴ ዝም ትላለች ? በተራ እሽኮለሌና የሞራል ጩኸት ፍቅር ፀንቶ የሚቆም ሊያስመስሉ ሲቀባጥሩ
ይገርሙኛል።

ይሄ እኮ ሁሉም ሴቶች ከሰውነት መንበር የተገፈተሩ ሲመስላቸው ጨምድደው እንዳይወድቁ
የሚንጠለጠሉበት የተረት ገመድ ነው ! ትዳር ማለት ራስን ማወቅ ብቻ አይደለም፤ የትዳር አጋርንም
ጠንቅቆ ለማወቅ መሞከር ነው። የራስን ፍላጎት ብቻ አንጠልጥሎ ትዳር የለም። እንደዛማ ከሆነ
ሁሉም በየራሱ የእውቀትና የፍላጎት አጥር ውስጥ ከመሸገ ምን አብሮነት አስፈለገ።
ይሄው ነው እውነቱ !!
“ክብርት ዳኛ ያሉት ነገር ከእኔ ጉዳይ ጋር አይገናኝም። እኔ ሚስቴ ፀጉሯን በአጭሩ ስለተቆረጠች ሕፃን ናት አልወጣኝም! እኔ ፀጉሯን በመቆረጧ መፋታት እፈልጋለሁ፣ ከእርሷ ጋር መኖር አልፈልግም ነው እያልኩ ያለሁት። ቀድሜ ፀጉሯን እንዳትቆረጥ ነግሬያት ነበር። የራሷን ምርጫ ተከትላለች። እኔም የራሴን ምርጫ እከተላለሁ !! ደግሞስ የቤተሰብ ሕጉ ሚስትን ለመፍታት የግድ ምክንያት መቅረብ አለበት ይላል ? አይልም !! አንድ ሰው መፋታት ከፈለገ በቃ ይፋታል። ስለዚህ ክቡር ፍርድ ቤቱ
ጥያቄዬን በመቀበል ፍቺውን እንዲያፀድቅልኝ በማክበር እጠይቃለሁ!!” አልኩ።

“ለመሆኑ ስትፋቱ ያላችሁን ንብረት እኩል እንደምትካፈሉ ገብቶሃል ?”

“ኧረ በሙሉ ትውሰድ ... ብቻ እንፋታ” አልኩ በምሬት እየተንገሸገሽኩ። ሚስቴ ፌቨን ከኋላ ስታለቅስ (ስትነፋረቅ ነው እንጂ..) ይሰማኛል። ጩኸቴን ቀማችኝ፤ ማልቀስ የሚያምርብኝስ እኔ ! ነጋቸውን
የፍቅር እና መከባበር ባሕር ከፊታቸው ተዘርግቶ መለቃለቅን ይንቁና እንዲህ ነገር ከእጃቸው
ሲያፈተልክ በራሳቸው እንባ የጨው ባሕር ሠርተው ነፍሳቸውን ይዘፈዝፋሉ። እንባቸውን ገድበው
ቁጭት ያመንጩበት እዛው። እንዴት እንደጠላኋት! የአባቴንም ገዳይ እንዲህ አልጠላ።

ዳኛዋ በትኩረት ተመለከተችኝ፤ እኔም በትኩረት ተመለከትኳት። ፀጉሯ ባጭሩ ተቆርጦ ደማቅ
ወርቃማ ቀለም ተቀብቷል፤ ልክ እንደሚስቴ። ወርቃማ ቀለም ውስጥ ነክረው ያወጡት ቡርሽ ነው የሚመስለው፤ ችፍርግ! ፊቷ ላይ ልክ የሌለው ጥላቻ ይንቀለቀላል። ጠላች አልጠላች በሕግ እንጂ በፍቅር አትፈርድ ድሮስ !ሕግ አይጥላኝ። ጠረጴዛው ላይ በተቀመጠው መዶሻ አናቴን ብትፈጠርቀው
ደስታዋ…። ኧረ ጎበዝ እኔ ስለሚስቴ ፀጉር ማጠር ሳወራ ለካስ ዳኛዋ ስለራሷም ፀጉር ነው
የምትሟገተኝ። ግን ሕግ ነውና እንደምንም ብስጭቷን ዋጥ አድርጋ ጉዳዩን በሌላ ጊዜ ለማየት ቀጠሮ ሰጠችን። ሦስተኛ ቀጠሮ መሆኑ ነው። ቆይ ይቺ ሴትዮ በቀጠሮ ብዛት የሚስቴ ፀጉር የሚያድግና ሐሳቤን የምቀይር መስሏት ይሆን እንዴ ? መክሸፍ አይገባትም ... በቃ ሚስቴ ለእኔ ከሽፋለች !!
👍40😁51👏1
#ሚስቴን_አከሸፏት


#ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

...ፌቨን የፈራረሰ ሰፈር፣ የተቆራረሰ ዳቦ ሆናለች ለእኔ። የጎኔ ሽራፊ ሳትሆን ከሙሉነት ጎን የተሸረፈች የዳቦ ሽራፊ። እጠላታለሁ? አዎ ! ቆንጆና በአበባ የተዋበ ግቢውን በግዴለሽነት ያፈራረሰበትን ሰው ማን ይወዳል ?! ፌቨንን በማፈቅራት ልክ ጠላኋት በቃ!

“ማናባቱ ያዘኛል ምን የጎበረበት፣

በገዛ ትዳሬ ውኃ ብደፋበት” ብላለች ዘፋኝዋ!

አራት ዓመት በፍቅር ቆይተናል፤ ከፌቨን ጋር። እድለኞች ነበርን፤ ለድፍን አራት ዓመት ያልቀዘቀዘ
ፍቅር ነበረን። አስር ደቂቃ አብረን ለመቆየት የአንድ ሰዓት መንገድ አቆራርጠን እንገናኛለን። “ዓይንህን ልየው ብዬ ነው የመጣሁት፤ በጣም እቸኩላለሁ” ብላኝ ላባችን ሳይደርቅ ወደየመጣንበት። ላገባት
እፈልግ ነበር። እርሷ ደግሞ አገባኋት አላገባኋት አያሳስባትም። ቀልቧ የትም እንደማልሄድ ነግሯታል። ቀልቧ ታዲያልክ ነበር። ደግሞ ሌላው የእድለኝነታችን ገፅ ሁለታችንም የሚታይ ለውጥ በሕይወታችን እየተከሰተ በሁሉም ነገር ስናድግ ነበር። ፌቨን አካውንቲንግ ተምራ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ሥራ አገኘች። እኔም ልክ ተመርቄ እንደወጣሁ ሥራ ያዝኩ። ትዳር ሲታሰብ አንዳች ኃይል ነገሮችን
ያገጣጥማቸዋል (እግዜር እንዳልል የዛሬውን ፍች ሳስብ ፈርቼ ነው)፤ እናም እንዲህ አልኳት፣

“ፌቪ!”
“ወይዬ” ሁልጊዜ ስጠራት ከዓይኗ ብርሃን ይረጫል። ስሟ ላይ የጨመርኩበት አንዳች ነገር ያለ
ይመስል፣

“ላገባሽ ነው”

“እኔ ... አላምንም… አብረን ልናድር ነው?” ብላ ተጠመጠመችብኝ። አቤት ደስታዋ።በእርግጥ ለሌላ ሰው ይህ አባባሏ ሳያስቀው አይቀርም። ለእኔ ግን የሆነ አስደሳች እና በስሜት የሚንጥ
ነገር ነበረው። አብረን ውለን
“በቃ ልሂድ” ስትል እንዴት ይቀፈኝ እንደነበረ የማውቀው እኔ ነኛ።
አብሮ ማደር የቀለለባቸው ይሄ ተራ ነገር ይመስላቸዋል። ፌቨን ከእቅፌ ውስጥ ቅር እያላት ስትወጣ የዓለም ቅዝቃዜ ሁሉ ወደኔ ይጋልብና አንጀቴ ውስጥ ገብቶ ያንዘፈዝፈኛል። ሸኝቻት ወደቤት ስመለስ ቤቱ ቤት አይመስለኝም፤ በረንዳ።

ለአራት ዓመት በፍቅር ስንቆይ እንኳን ማደር ምሽቱ ምን እንደሚመስል አብረን አይተነው አናውቅም። የፌቨን እናት ናቸው ምክንያታችን ... የሚገርሙ ሴትዮ … ልጆቻቸውን አታምሹ አይሉም፡፡ ግን የእናትነት የፍቅር መብታቸውን በትክክል ተጠቅመውበታል። ልክ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ፌቨን
ቡና ታፈላላቸዋለች (የቤቱ ደንብ ነው)፣ ሁለት ሰዓት ራት ይበላሉ…ልጆቹ ካልተሟሉ ራት አይበሉም
እንደውም ሰዓቱ ካለፈ ልጆቻቸው ቢሟሉም ራት ሳይበሉ ነው የሚያድሩት። ፌቨን ታዲያ ይሄው
ነገር ተከትሏት መጥቶ እኔ ቤት ካልገባሁ እህል በአፉ አይዞርም፤ እንግዲህ ፌቨን ርሃብ እንደማትችል አውቃለሁ። ከራባት እንስፍስፍ ነው የምትለው፤ ዓይኗን እንኳን መግለጥ ያቅታታል!(አቤት ስታሳዝነኝ እንደነበር) ታዲያ እንዴት አባቴ ብዬ ለእራት እዘገያለሁ በጊዜ ወደ ቤቴ ጥድፊያ ነው ! የፌሽን
እናት በእነዚህ የማይዛነፉ ሕጎች ልጆቹን የማይዛነፍ የቤት መግቢያ ሰዓት ድንበር አስምረውላቸዋል።
ካለአባት ስላሳደጓቸው እናታቸውን እንደ አባትም እንደ እናትም ነው የሚያይዋቸው።

ተጋባን ! ትዳራችን በሚያሰክር ፍቅር የተሞላ ነበር ! እድለኛ ነኝ ያልኩት ለዚህ ነው። ልክ እንደ ፍቅረኛ ነበር የምንኖረው። ከቤታችን መውጣት አንፈልግም። ሰውም ወደቤታችን ባይመጣ
ደስታችን.እውነቴን እኮ ነው። ክፉ ሆነን ሳይሆን ፍቅር የሚባለው ስካር አልሰከነልንም ነበር። ሰዓት
አይበቃንም። ቅድም ነግቶ ቁርስ በልተን ምን እንዳወራን ምን እንደሰራን እንኳን ሳናውቀው
እንዳንዴ እንዲያውም ምሳ ሰዓት ሁሉ በየት እንዳለፈ ሳይገባን ብቅ ስንል ማታ ሆኗል። በቃ! እንዲህ
ነበርን እኔና ፌቨን ! “ሁሉም ሲጀምረው እንዲሁ ነው” ይባል ይሆናል፤ ግን ለድፍን ሦስት ዓመት
ስንኖር ደስታችን ሳይሸረፍ፣ ሳቃችን ሳይከስም ፍፁም ደስተኞች ሆነን ነበር።

ደግሞ አማረብን እንጂ !ፌቨን ድሮም ቆንጆ ናት ጭራሽ አበባ መስላ አረፈች። እኔ እንኳን አንድ ሁለት ተብሎ አጥንቴ የሚቆጠር ፍጥረት ትንሽ የተገለበጠች ጎድጓዳ ሰሃን የምታህል ቦርጭ ተከሰተችብኝ ! እንደ አዳምና ሄዋን የቀደመ ሕይወትም ትዝታም ሳይኖረን እዚሁ ቤት በዚሁ እድሜ የተወለድን ይመስል ያለፈውን ዓለም፣ ቤተሰብ፣ ጓደኛ ምናምን ሁሉ ሁለታችንም ረሳነው። የፌቨን እናት ይደውሉና፣ “ኧረ እናንተ ልጆች ድምጣችሁ ጠፋ .በደህናችሁ ነው ?” ይሉናል።

እኔና ፌቪ ታዲያ ልክ ስልኩ ሲዘጋ፣ “በደህናችን ነው ግን ?” ተባብለን እንሳሳቃለን። ከዛ ፕሮግራም እናወጣለን። በቀጣዩ ቅዳሜ የፌቪ እናት ጋር፣ በዛንኛው ደግሞ እኔ ቤተሰቦች ጋር፣ እንዴ ከሰው ተለየንኮ እንባባልና፤ በቀጣዩ ቅዳሜና እሁድ ወፍ የለም !! እንደውም ቅዳሜና እሁድ ማለፉን የምናስታውሰው ሰኞ ነው! እኛ ሌላ ዓለም ውስጥ ነን!

ቢጨንቃቸው የፌቨን እናት ራሳቸው መጥተው ጠየቁን፤ እና መከሩን፣

“ታፍናችሁ አትዋሉ፣ ወጣ እያላችሁ ይንፈስባችሁ ፊታችሁ ፈረንጅ የመሰለው ጠሃይ እጦት እኮ ነው ምቾት እንዳይመስላችሁ።” ምን ያደርጋል ምክራቸው ራሱ ነፈሰበት። ምናባቴ ላድርግ እኔ ራሱ ከቤት
( ስወጣ ገና ትላንት ከገጠር እንደመጣ ሰው እደናበራለሁ። ቤቴ ይናፍቀኛል .ፌቪ ትናፍቀኛለች። ሩቅ አገር የሄድኩ፣ የማልመለስ ይመስለኛል። ት ና ፍ ቀ ኛ ለ ች እንዲህ ዓይነት ትዳር ከመቶው አንድ ነው አሉ። ለምን ግማሽ አይሆንም። የበረከቱ ተካፋዮች እኔና ፌቨን ነበርን።
ሳወራው ያመኛል። ሰዎች የበለጠ በተፋቀሩ ቁጥር እንደስስት መስተዋት ራሳቸውን ከቀላልም
ከከባድም ግጭት መጠበቅ ይኖርባቸዋል። አንዱ ቸልተኛ ሆኖ ሳት ካለው ፍቅር ሲንኮታኮት
ያሰቅቃል። ደግሞ ብቻውን አይንኮታኮትም፤ ጣፋጭ ትዝታንም ይዞ ነው አፈር ድሜ የሚበላው።የጨነገፈ ፍቅርን እንደማሰብ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ምን ሰቆቃ አለ…?

ፌቨንን እወዳት ነበር፣ አከብራት ነበር፣ አፈቅራት ነበር። ትንሽ ነገር፣ ይሄ ነው የማይባል ምክንያት
በውስጤ እሳተ ገሞራ የሚያህል ቅያሜ አፈነዳ። “አሁን ይሄ ምኑ ይካበዳል ? እንኳን ለፍች ተራ
ኩርፊያም አያበቃምኮ” ይባል ይሆናል። “ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል” አሉ።ይሄ ትንሽ የተባለው
ምክንያት ለተመልካች ትንሽ ይምሰል እንጂ ፌቨንን ዓይኗን ማየት ድምፅዋን መስማት የጠላሁት በዚሁ ምክንያት ነው።
ፍቺ ፈለግኩ። ምክንያቱም ፌቨን ፀጉሯን በአጭሩ በመቆረጧ ነበር ...!! በቃ ይሄው ብቻ ነው ምክንያቱ ሚስቴ ፀጉሯን በአጭሩ መቆረጧ። የፌቨን ፀጉር ምን ቢሆን ነው እንዲህ ጉድያ ፈላው፣ ጎጇችንንስ በጭንቅላቱ ያቆመው ?

ፌቨን” አልኳት ሚስቴ ፀጉሯን ተቆርጣ የመጣች ቀን፣

“አቤት”አላለችኝም!!እንደ ወትሮዋ “ወይዬ” አላለችም። ፊቴ ላይ የነበረው ጥላቻ ቅስሟን ሰብሮታል። እንዲህ ሙሉ ስሟን ደግሞ ጠርቻት አላውቅም። ሙሉ ስሟን ከምጠራት ሙልጭ አድርጌ ብሰድባት ይሻላታል። በምርጥ ፍቅረኞች መሀል እኮ በሙሉ ስም ከመጥራት የበለጠ ስድብ የለም።በአገራችን
አቶ፣ ወይዘሮ ምናምን ከሚባሉት ተቀፅላዎች ይልቅ ስማችን ሲቀናጣ ሐሴት ማድረጋችን ሳይታለም የተፈታ ነው። አቶ ጉልማው ከመባል ጉሌ፣ “ጉልዬ” ብንባልም ደስ ነው የሚለን መቼስ። ፍቅረ ቅንጦት !
👍361👎1
#ሚስቴን_አከሸፏት


#ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም

...ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ግን ወሬዋ ..! ወይኔ ወሬዋ ! ሰው እንዴት በቅሌቱ አንቱ ለመባል ይጥራል በእግዚአብሔር። እኔ ጥሎብኝ ዋው! እሷ እኮ ተጫዋች ምናምን.. ለመባል ብሎ የሚቀባጥር ሰው ያስመርረኛል።

“ዋው እንትናዬ ! እንዴት አባቱ የሚጥም ተጨዋች መሰለሽ ...! ሙድ ያለው ጨዋታው ብትይ፣
የሚወስደኝ ቦታ ብትይ፣ በዛ ላይ አልጋ ላይ ሂሂሂሂሂሂሂሂሂ” አፏን እስከመጨረሻው ከፍታ
ታሽካካለት…። ይህቺን ሴትዮ ሳስባት ከእናትና ከአባት ሳይሆን እንደሙጃ ሕይወት ይሉት ዝናብ
ዘንቦባት ድንገት ሜዳ ላይ ቱግ ብላ የበቀለች አረም ነው የምትመስለኝ የሰው አራሙቻ !

ከፌቨን ጋር የተዋወቁት በአንድ የግል ድርጅት ሲሠሩ ነበር።
“ኦ ማሜ ማለትኮ እናት ማለት
ትላታለች ሚስቴ ይህቺን ሴት ስታደንቃት .. !ይታያችሁ እናት !ለነገሩ እናት” ናት።

"ፌቪዬ የኔ ማር…! ይሄን ሽንኩርት የሚባል ነገር እየከተፍሽ ቆንጅዬ እጅሽን ልታበላሽው ነው…።”
ትላታለች። ፌቨን ልታስተናግዳት ጉድ ጉድ ስትል እኮ ነው፤ ምክሯ ሁሉ ግራ ነው የሚያጋባው።

አንዳንዴ ደግሞ እኔና ፌቨንን እየተመለከተች፣ “እንዴ እናንተ ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ፤ የምን እንጀራ መጠፍጠፍ ነው .. የቀን ሠራተኛ ቅጠሪና ወጥ ምናምን ሠርታ ፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ፣ እንጀራ ከሱቅ ገዛ አድርገሽ መጠቀም፤ እንደው አበሻ ጓዳ ገብቶ ፍዳውን ካልበላ ካላቦካ፣ ካልተጨማለቀ እሳት ላይ ካልተጠበሰ የበላ አይመስለውም፤ ... አይደል እንዴ አብርሽ? ሂሂሂሂሂሂ …ይህቺን የመሰለች ማር የሆነች ልጅማ ሽንኩርት አታስከትፋት…።”

ፌቨን ምሳ ሠርታ ይህቺ መካሪ በደንብ እያጣጣመች ከበላች በኋላ መልሳ እንዲህ ትላለች፣

“ላለለት ሰውማ ማን እንደ ቤት ምግብ እናቴ ትሙት (እናቴ ትሙት ብሎ መሐላ አይቀፍም?) ... ውይ
እንዴት ርቦኝ ነበር። ጥሞኝ በላሁ። ፌቪዬ ከአልጫዋ ትንሽ ጨምሪልኝ ትላለች። እውነቱን ለመናገር
እንደዚህ ስትል ታሳዝነኛለች። ሴት ራበኝ ስትል አልወድም። በዛላይ አንዲት ሴት ያውም ኢትዮጵያዊት
ሴት የፈለገ የሞራል ውድቀት ውስጥ ብትገባ የዚህ ዓይነት አኗኗር የምትመርጥ አይመስለኝም። አንድ
ከሕይወቷ መጽሐፍ የተገነጠለ የኑሮ ገጽ ይኖራል፣ ወይም አንዱ ደደብ የሕያውነት አንቀጿን በክፋት
ሰርዞታል። ወዶ አይደለም ወሬዋ የሚምታታው..

በጣም ቆንጆ ናት። ያውም ውብ የሚባል ዓይነት። ላግባ ብትል እግሯ ላይ ወድቆ የሚያገባት ሺ
ከሚሊየን ነው (በዚህ ዕድሜዋ እንኳን ላግባ ብትል የሚሻማባት ጎረምሳ ብዙ ይመስለኛል…) ግን
ከርታታ ናት። በቃ እዛ ስታድር፣ እዚህ ስትውል፣ ሽሽቷን ልታዘምነው አንዴ ትልልቅ ሆቴሎች፣ ሌላ ጊዜ ሌላ የመዝናኛ ቦታዎች ብትንከራተትም ዓይኗ ላይ እንደሩቅ አገር እሳት ቢል ቢል ሲል የሚታየው አምሮት … እፎይ ማያ ጎጆ መናፈቋ ነው!!
እናም ፌቨንን ፊቴ እንዲህ አለቻት፣ ፌቪ ማር…!ይሄ እንቁላል ቅርፅ ያለው ፊትሽ በዚህ ፀጉርሽ
ባይሸፈን ኖሮ መልክሽ የሚያሳብድ ይሆን ነበር። ብዙ ሳይሆን ትንሽ አጠር …፤ ምን አሁን እኮ ፀጉር ጀርባ ላይ ለቅቆ አንበሳ መምሰል ትንሽ ጊዜው አልፎበታል። ዳሩ አንቺ ወጣ ብለሽ አታይ፤ እዚህ ባልሽ ጋር ታፍነሽ እየዋልሽ ሂሂሂሂሂሂ። ቀልድ አልብሳ መርዟን ረጨችው።

ማታ እንደተኛን ፌቨን ድንገት ከጎኔ ቀጥ ብላ ደረቴ ላይ አገጯን አስደገፈች። ጥቁር ፀጉሯ ፊቴ ላይ
ተነሰነሰ።ዓይኖቼን ጨፍኜ የፀጉሯን ዝናብ ተጠመቅኩት በደስታ … እንደ ሩፋኤል ፀበል።

“አብርሽዬ…”

“እ!”

“ዓይንህን ግለጣ” አለች፤ ገለጥኩ። ከጥቁር ደመና ውስጥ ብቅ ያለች ጠይም ፀሐይ ከበላዬ።

“ማሜ ያለችው ነገር ግን አልገረመህም፤ እንዴት እስከዛሬ አላሰብኩትም…?”

“ምኑን?” አሁን እኔም ነቃ አልኩ።
“ፀጉሬን ባሳጥረው እንደሚያምርብኝ ፀጉር የምትሠራኝ ልጅም ደጋግማ ነግራኛለች” ፊቷ ላይ ያለው
ስሜት የመጠየቅ ሳይሆን ፀጉሯን የምትቆርጥበት መቀስ እንዳቀብላት የመጠየቅ ዓይነት ያበቃለት መርዶ ነበር። ሁሉም ነገር ቅድሚያ የሚቆረጠውም የሚቀጠለውም ልብ ላይ ነው።

“ፀጉርሽን እንድትቆረጭ አልፈልግም። እንኳን መቆረጥ ፀጉርሽን ስታበጥሪ ማበጠሪያው ላይየሚቀሩት የፀጉር ዘለላዎችሽ ያሳዝኑኛል። እና ለእኔ የምታምሪኝ እንደዚህ ስትሆኝ ነው። ፀጉርሽን ከዓይኖችሽ፣ ከአፍንጫሽ እና ከእነዚህ ውብ እጅና እግሮችሽ እኩል እወደዋለሁ፤ እንደ አንድ የሰውነትሽ ክፍል ነው
የማየው” አልኳት ጣቶቼን ፀጉሯ ውስጥ እያርመሰመስኩ።

“እንደዚህ አንበሳ ስመስል ነው የምትወደኝ?” ብላ በማሾፍ ከተናገረች በኋላ ፀጉሯን በጣቷ
መነጨረችውና ከንፈሬን ስማኝ ደረቴ ላይ ልጥፍ ብላ ተኛች። (ይሄ መሳም ቃሌን መስማት ይሁን
ወይስ ስሞ መሸጥ ዓይነት ይሁዳዊ መሳም አልገባኝም)። አተኛኘቷን ሳየው የልብ ምቴን የምታደምጥ ነበር የምትመስለው እንቅልፍ ወሰዳት።ስንተኛ ፀጉሯን ስለማታስይዘው እንዲሁ ነው የምትተኛው።በእንቅልፍ ልቧ በተንቀሳቀሰች ቁጥር የፀጉር መዓበል ትራሱ ላይ ሲነሳ ከትራሱ ላይ እየተንሸራተተ ፍራሹ ላይ ሲርመሰመስ ነፍሴ ሐሴት ታደርጋለች።

ፀጉር እኮ መንፈስ ነው። በተለይ የሴት ልጅ ፀጉር። የቅዱሳን ሥዕልላይ ከራሳቸው በላይ እንደሚታየው የብርሃን አምድ …. የሴት ልጅ ፀጉርም ባፈቀራት ወንድ ብቻ የመንፈስ ዓይን የሚታይ የውበት አምድ
ነው ! የሴት ልጅ ሰውነት በማይታይ የክብር ብርሃን የተከበበ ሕያው ቅድስና ነው። ትልቁ ችግር የብዙ ሴቶች ፍላጎት ለብዙኃኑ ቆንጆ ሆኖ የመታየት መሆኑ ነው። ብዙኃኑ አድናቂ ነው። ብዙኃኑ ጤዛ የሆነ አብሮነቱ ከዓይን ሲርቁ አብሮ ይከስማል። ብዙኃኑን የኔ ከምንለው ሰው ጋር በአንድ ሚዛን ልናስቀምጠው አይገባም። ለብዙኃኑ ብዙ ሆኖ መገኘት በመፈለጋቸው አንዱንም ሳይዙት ምንም ሆነው እንዲቀሩ ያደረጋቸው ብዙ ናቸው።

ፌቨን ተኛች። ስትተኛ የተመጠነ አተነፋፈስና ሰላም ያለው እረፍት ፊቷ ላይ ይረብባታል። የፌቨን
እንቅልፍ ሰላም ባለው ሰፊ ባሕር ላይ ያለ ምንም እንቅስቃሴ በጀልባ እንደመንሳፈፍ ይመስለኛል።ተኝታ ሳያት ታሳሳኛለች። እና ቀስቅሳት ቀስቅሳት ይለኛል። ለብቻዬ ትታኝ ወደሆነ ሰላም ወዳለው ዓለም የሄደች ይመስለኛል፤ እኔ ግን በሐሳብ ነጎድኩ። ወደኋላ … ፌቨንን ዓይቻት ፍቅር የጀማመረኝ
ሰሞን ከሩቅ ስመለከታት የሚገርመኝ ፀጉሯ ነበር። ድብን ያለ ጥቁርና ጠንካራ ፀጉር። ከርዝመቱ ብዛቱ። ከተዋወቅንና ከተቀራረብን በኋላ ደግሞ ፀጉሯ መሐል ጣቶቼ ጠፉ ማለት ዘበት ነው። አንገቷን ወደግራ ዘንበል ስታደርግ ፀጉሯ ወደ ግራ ይናድና በግራ ትከሻዋ አልፎ እየተርመሰመሰ የግራ ጡቷን
ይሸፍነዋል።

ፀጉር ቤት ቆይታ ስትመለስ የሆነ የተቃጠለ ፀጉር ሽታ አፍንጫዬን ያውደዋል። ያንን ሽታ እወደዋለሁ።
እንደውም በሴቶች ፀጉር ቤት ሳልፍ ይሄ የተቃጠለ የፀጉር ሽታ ሲሸተኝ ፀጉር ቤቱ ውስጥ ፌቨን ያለች ይመስለኛል። ፀጉር መተኮስ ማለት እኮ ለውበት አምላክ የሚቃጠል የፀጉር መስዋዕት እንደማቅረብ ነው። (የመረረ የፋሽን ጥላቻ ኖሮብኝ ሳይሆን ውበት ዋጋ እንደሚያስከፍል ለመግለፅ)

ጠዋት ከእንቅልፌ የቀሰቀሰችኝ ፌቨን ናት ቁርስ ሰርታ ሁልጊዜም እንዲሁ ነች። ቁርስ እየበላን
ድንገት ፍርፍሩ ውስጥ አልያም እንቁላል ጥብሱ ውስጥ የፀጉር ዘለላ ማግኘቴ አይቀርም። ዛሬም
ይሄው አንድ ቢመዘዝ የማያልቅ የፌቪን ፀጉር አገኘሁ።

ተሳሳቅን።

የግራ እጄን ጣቶች ወደ ዓይኗ አስጠግታ እየተመለከተች እንዲህ አለች፣ “ይሄ ሽንኩርት እጄን

"አሻከረው”።

ዝም አልኩ።

ዝም ተባባልን።
👍37
#ሚስቴን_አከሸፏት


#አራት


#በአሌክስ_አብርሃም

....የፌቨን እናት ተቀየሙኝ። ሊያስታርቁን መጥተው፣ “ልጅዎትን ከዚህ በኋላ ማየት አልፈልግም ስላልኳቸው ተቀየሙ። ማንም ወላጅ ቢሆን ይሰማዋል። በደካማ አቅማቸው ከየትና የት ድረስ መጥተው ለማስታረቅ ሲሞክሩ እንቢ አይለኝም ብለው ነበር ያሰቡት። የእኔ ፌቨንን መጥላት ...
ርሳቸውን መናቅ መሰላቸው “አንዲት ሴት ፀጉሯን መቆረጧ ትዳር እስከማፍረስ ካደረሰ ከፍቺው ኋላ ፀጉር ብቻ ሳይሆን ሌላ ምክንያት አለ ማለት ነው” ብለው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። እውነት ነው

ከፌቨን ፀጉር ኋላ ሚሊየን ምክንያቶች ነበሩ፤ ሁሉም ምክንያቶች ግን መነሻቸው ፍቅር ነበር።

“ፍቅር ይታገሳል” ይሉኛል ጉዳዩን የሰሙ ሁሉ፣

ሰው በሰላሙ ቀን እግዜሩንም መጽሐፉንም አሽቀንጥሮ አሸሼ ሲል ይከርምና የቁርጥ ቀን ሲመጣ በየሥርቻው የጣለውን የሕይወት መጽሐፍ አቧራውን አራግፎ እያነሳ ሁሉም ሰባኪ፣ ሁሉም ቃል አጣቃሽ ካልሆንኩ ይላል።

“ፍቅር ይታገሳል”ይለኛል መካሪ። እንዲህ ሲሉኝ ተናገር ተናገር ጩህ ጩህ ይለኛል። “እስቲ እንዲህ
ለነፍስህ ያደርክ ከሆንክ ቃሉ እንደሚለው አታመንዝር ! አዎ አንተ ራስህ ይሄን የምትመክረኝ …
እስቲ በየስርቻው ራሳቸውን ነጥቀህ በቀለም የምታዥጎረጉራቸውን የወሲብ እቃዎችህን እንደሰው ቁጠር ! እዚህች አገር እንደ ሴት መጫወቻ የሆነ ፍጥረት አለ ... ? የማንም ወጠጤ መጥቶ የብልግና
ብሩሹን አንከርፍፎ መንገድ ላይ እንደተሰጣ ሸራ ሴቶችህ ላይ ብልግናውን ሲስል የት ነበርክ…” ማለት ያምረኛል።

አዎ ውስጤ በቁጣ ይሞላል፣ “ላንት 'መብታቸው ነው እያልክ በየመጠጥና ጫት ቤቱ እንደ ጥራጊ ማንም ሲረግጣቸው የነበሩ ሴቶችህን ስታልፍ .… ዛሬ ሴተኛ አዳሪነት፣ወሲብን አቃልሎ ማየት፣ በፋሽን ሥም ሴትነትን መንገድ ዳር አቅርቦ መቸብቸብ ሰተት ብሎ ጓዳህ ገባ! ሴቶች በጓዳ አይቅሩ አደባባይ
ይውጡ ከሚለው የሚበዛው ለሴቶች መጨቆን ያዘነ እንዳይመስልህ። በአደባባይ እንደ ፋሲካ በግ ዳሌና ሽንጥ በዓይኑ እየመተረ ለመምረጥ ነው! ምነው የሚመች ጓዳ፣ ክብር ያለው ጎጆ አግኝተው ሴቶች ጓዳቸው ውስጥ አርፈው በተቀመጡ። ግን ባትለውም ኑሮ ራሱ እየመዘዘ አደባባይ ያሰጣቸዋል።
ያውም የኛ ኑሮ…” ብዬ በአደባባይ ድፍን የአበሻ ወንድ ላይ መጮህ መደንፋት ያምረኛል።

“ለመሆኑ የሴቶችን ልብስና ጫማዎች ታዝበሃል ? ለተረት የሚመች አይደለም ሁሉም። ሴት ልጅ ከቤቷ ወጥታ ወደ መኪናዋ ከመኪና ወደ ሥራ ረጋ ያለ ሕይወት እና እንቅስቃሴ እድትኖር ታስበው የተሰሩ ናቸው። እንዳንተ ስኒከር፣ ሸራ ጫማ፣ ከስክስ አይደለም የሴቶች ጫማ ! ሴቶችህ ራሳቸው ለአደባባይ ማንነት “መብት” የሚል ሽፋን ይሰጡታል እንጂ በብዙሃኑ የከተማ ሴት አዕምሮ ውስጥ
ያለው እውነት ጥሩ ሥራ አግኝቶ ወይም አንዱን ኃብታም አግብቶ “
እርፍ” የሚል ሕልም ነው !
(ይሄ አንዳንዶችን ያበሳጫል ግን ምን ይደረግ እውነት ነው። ከተማውን ከሰኞ እስከ አርብ የዘነጠ ሽቅርቅር ትውልድ ሲሞላው ሥራ አጥነት ጣራ እንደነካ አስተውል። የታደሉ ዜጎች የቆሸሸ እጅ፣የሥራ ቱታ የለበሱ ሰውነቶች የታደሉ ናቸው። ከሰኞ እስከ አርብ መዘነጥ ከሰኞ እስከ አርብ አዕምሮም ሰውነትም ሥራ መፍታቱን የሚያሳይ የውድቀት ባንዲራ ነው !” እንዲህ ብዬ የሚሞግተኝን ሁሉ መሞገት ያሻኛል። ምክራቸው መከራ ከመጨመር ውጪ ወንዝ የማያሻግር እንቶፈንቶ ይሆንብኛልና ሁሉም መጽሐፉ እንደሚለው “የሚያደክሙ አፅናኞች” ናቸው።

በሚስቴ ሰርጥ አልፌ ወደ ሰፊው የሴትነት ባሕር ስመለከት ሴቶች ባሕሉ ብቻ ሳይሆን ልብስና
ጫማቸው ሳይቀር ካቴና ሆኖባቸው ይታየኛል።ፋሽን ነፃነታቸውን ነጥቆ፣ ምቾታቸውን ቀምቶ፣ ወንዱ ፊት የእይታ አምሮት እንዲያሳረፍ ይደረድራቸዋል። እነሱም ፍልቅልቅ እያሉ በካቴናቸው ይኮራሉ ..
ፋሽን ነዋ። እንደውም ትክክለኛው ዘመቻ መሆን ያለበት ሴቶች አደባባይ ይውጡ ሳይሆን ወደ ጓዳ ይመለሱ ነው ! ጓዳቸው ምቹ ይሁን ነው !! እግሯ እስኪቀጥን ከተማውን የምታካልል ቆንጆ የሆነ
ቀን እፎይ ዙረት ሰለቸኝ” ስትል ትሰማታለህ ..ዙረት የሴት ልጅ ተፈጥሮ አይደለማ ! በተሰጣቸው
የተፈጥሮ ፀጋ ልጆችን ሊያሳድጉ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። ልጅን ለማሳደግ እግርን ሰብስቦ ቤት
ውስጥ መቀመጥ፣ ደስታን አሳልፎ መስጠት ይጠይቃል። ልጅ ጭፈራ ቤት ውስጥ አያድግም። ይሄ የዘመናችን አጉል ዘመናዊነት እንዲህ ተጣምሞ ካደገ፣ ልጆቻቸውን በጋሪ እየገፉ በደረቅ ሌሊት ጭፈራ
ቤት የሚሰየሙ እናቶችን መፍጠሩ አይቀሬ ነው።

ደግሞ እንደ ደንቃራ በመብት ስም ስለእንዝላልነት ልትሞግተኝ ፊቴ የምትደቀን እንስት ብስጭቴን
ጣራ ታስነካዋለች። “አንቺ ራስሽ እስቲ ራስሽን ተመልከች፣ ለምንድነው ፀጉርሽን ቀለም የተቀባሽው ከፊትሽ ከለር ጋር እንደሚሄድ' ባለሞያዎቹ ነግረውሽ …. ወይስ እንዲሁ ሲያደርጉ አይተሽ …. ሞኝ ነገር ነሽ … ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አጠቃላይ የፀጉር ሞያተኞች ስንት ይሆኑ በሙያው ጥልቅ እውቀት
ያላቸው። ጥቂቶች በጣም ጥቂቶች። ሌላው የተከበረ ፊትና ፀጉርሽን ቤተ ሙከራ የሚያደርግ
የልምድ አዋላጅ' ነው ! እንግዲህ ይሄ መደዴ ፀጉር ተኳሽ ነው የፊትሽ ቅርፅ፣ የቆዳሽ ልስላሴ፣ ይሄን ቀለም ተቀቢ፣ ያንኛውን ሜካፕ ተለቅላቂ እያለ ቅዠቱን የሚመክርሽ !

እየውልሽ የፀጉር ፍሸናው አንቺን አጥፍቶ የሆነች ሌላ ሴት ማስመሰል እንጂ፣ ያለሽን ውበት ማጉላት አለመሆኑ የሚገባሽ የፍሸናውን ስም ስትሰሚ ነው፣

ቢዮንሴ ሹርባ፣

ሪሃና ቁርጥ፣

ዊትኒ ስታይል..

አንቺ ግን ስምሽ አረጋሽ ነው፣ ወላ ነጃት፣ ወላ ነፊሳ፣ ሄለን፣ ሲቲ፣ ቲቲ ሁኝ ብትፈልጊ…። ካናትሽ
ላይ ቆሞ ፀጉርሽን የሚሰራ የሚመስልሽ የፀጉር ባለሞያ በካውያው ፀጉርሽን እየተኮሰ በማያባራ ለፋፊ አንደበቱ ግን አዕምሮሽን ነው በጋለ የውበት እና ፋሽን ካውያው የሚተኩስሽ ! አንቺነትሽን ሊያተን ነው። ከዛ ምንም ከሌሎቹ ሴቶች የተለየ ውበት አይጨምርልሽም። መጨረሻ ላይ እንደሌሎች
ሴቶች ትሆኛለሽ። በቃ ይሄው ነው። ደግሞ ወንዱ ባንቺ ውበት ይደነቃል ብለሽ አትድከሚ። ወንዱ
በሚጎረጉረው ስልኩ መለዓክ የመሰሉ ሴቶች ፎቶ ላይ አፍጥጦ ነው የሚውለው፤ ምንም ብትሆኝ
አይደንቀውም፡፡ ጉዳዩ ከሰውነትሽ ነው። ከስልኩ ወዲያ አምሮት የቀሰቀሰበትን ገላ ሲያጣ አጠገቡ
ያለሽውን አንቺን እንደማስታገሻ ከማይረባ የፍቅር ዲስኩር ጋር ይወስድሻል ! የአንቺን ሥጋ አቅፎ
መንፈሱ በተመለከተው ገላ ላይ ነው የሚቃዠው…” ብቻዬን ተቀምጬ እንዲህ ነው የማስበው።ሴት ወንዱ በሽተኛ የሆነ ይመስለኛል። ለክርክር የሚያሞጠሙጠው አፉ ለምን ራሱን ለመጠየቅ
እንደማይጠቀመው ግራ ይገባኛል።

“እንደ ኳስ መካሪው ወደ ፋሽን …. ፋሽኑ ወደ ወንድ፣ ወንዱ ወደ አልጋ፣ አልጋው ወደ ተዘባረቀ ሕይወት እየተቀባበለ በሴት ልጅ ሕይወት ጨዋታውን ያሞቀ ዘመን እንደዚህ ዘመን ከቶ አልተከሰተም።ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነውና ዘመኑ ራሱን 'የሰለጠነ የሚል ስም አከናንቦታል ከክንብንቡ ስር … በስልጣኔ መዳፍ አፋቸውን የታፈኑ 'ስልጡን የፋሽን ባሮች ዓየር አጥሯቸው ይወራጫሉ። ለዚህ መፍትሄው ራስን መሆን ነው። በዚህ ዘመን በትክክል የሚያስፈልገው “ራስሽን ሁኚ” የሚል መካሪ ነው። ልድገመው ራስሽን ሁኚ ! የነፈሰው ንፋስ ጋር ልንፈስ ካልሽ እብድ የበላው በሶ ሆነሽ ትቀሪያለሽ... የኔን ሚስት አታያትም … ይቺን አስቀያሚ ! በክብር ካኖርኩባት ዙፋን ላይ ፀቁልቁል በአናቷ ወርዳ
👍291🔥1😁1
#ሚስቴን_አከሸፏት


#አምስት (መጨረሻው)


#በአሌክስ_አብርሃም

...ፌቨን ከዛ ቀን በኋለ የፀጉሩ ነገር እንዳበቃለት ሲገባት ያማልለኛል ያለችውን ነገር ሁሉ እያሳየች የተንኮታኮተ ፍቅሬን ልትመልሰው ተፍገመገመች። አንዴ አጭር ቀሚስ ለብሳ እግሯን እስከታፋዋ ታሳየኛለች፤ (እግርሽ ያምራል እላት ነበር ድሮ እንደዛሬው እያንቀዠቀዠ አልባሌ ቦታ ሳይወስዳት በፊት) የእጇን ጣቶች ብታወናጭፍ፣ ዓይኗን ብታፈጥ፣ከንፈሯን ብታሞጠሙጥ... ውሉን ቆርጣ ጥላ ትርፍራፊ ውበቷን ብታግተለትል ወይ ፍንክች። እንደውም የባሰ አስጠላችኝ። አይናገረውም እንጂ ሁሉም አፍቃሪ ለዘላለሙ የሚያመልከው የሚያፈቅረው ሰው ላይ በየቀኑ ዓይኑ የሚፈልገው የውበት አማካይ ቦታ አለው። ሌላው ሁሉ ካለዚህ ነጥብ ባዶ ነው። ለእኔ የፌቨን አማካይ የውበት ቦታ ፀጉሯ ነበር። ፌቨንን እንደከተማ ብመለከታት መሐል አደባባይዋ ፈርሷል። አንጋፋ ፍቅር አዲስ ከተማ ላይ መኖር ያንገሸግሸዋል።

የዘመናዊው ፋሽን ትልቅ ችግር የሴቶችን ፀጉር የሚያደንቅ ተፈጥሯችንን በግድ ጠምዝዞ ሴቶች ዳሌ ላይ ለማሳረፍ መጣሩ ነው። ሴቶች እግር ላይ ሴቶች ጡት ላይ ዓይናችንን በግድ ማስተከል። እንቢ ማየት
አንፈልግም ስንል ውበት የማይገባን ገገማዎች መሆናችንን በማሳመን ስልጡን አይደላችሁም ይለናል ሞላ ያለች ሴት እይታችንን ትስበው ይሆናል። ፋሽን ተብዬው ግን የትከሻዋ አጥንት ካልተሰረጎደ
ሴት ምኑን ሴት ሆነች ብሎ ሊያሳምነን ይጥራል። ፋሽን ጉልበተኛ ነው። በተለይ ሴቶች ላይ ክንዱ ይበረታል። ዛሬ ፋሽን ለመከተል ፀጉሯን የቆረጠች ሴት ነገ የላይኛውን የፊት ጥርስ አስነቅሎ በባዶ ድድ መገልፈጥ ያምርብሻል ብትባል ጥርሷን ከማራገፍ አትመለስም፡፡ የተጋነነ ይመስላል እንጂ ባለፉት
አስር ዓመታት በአገራችን አይሆኑም ያልናቸው ጉዳዮች ዛሬ ላይ ለትውልዱ ተራ ጉዳዮች ሆነዋል።ደግሞ ፍጥነታችን

የፌቨንን ፀጉር መቆረጥ ከሴት ልጅ ግርዛት ለይቼ አላየውም። ልዩነቱ የሴት ልጅ ግርዛት በሴቷ ስሚት ላይ መቀለድ ሲሆን ይሄንኛው በእኔ ፍላጎትና ስሜት ላይ መጫወት መሆኑ ነው። እናም ፌቨንን እፈታታለሁ !! እሷን ብሎ ሚስት። የፍርድ ቤት ቀጠሮዬ ነገ ነው። ፌቨን እናቷ ጋር ከሄደች ሃያ ቀናቶች አልፈዋል፡፡ አልናፈቀችኝም። እንደውም የተሰማኝ ሰላም ልክ አልነበረውም። ትንሽ የተሰማኝ ፌቨንንም ሆነ እናቷን በገንዘብ የምረዳቸው እኔ ነበርኩ በዚህኛው ወር ግን ምንም አልሰጠኋቸውም። ከፌሽን
ጋር ስለተጣላሁ ሳይሆን ብሩን ብልክላቸው ፌቨንን የመፈለግ ስሜት ያደረብኝ እንዳይመስላቸው
በማሰብ ብቻ ነው….

ከፌቨን ጋር ከተለያየን በኋላ ብዙዎች እንዳሰቡት ስትናፍቀኝ “ማሪኝ” ብዬ ቤቷም አልሄድኩ።
ስልክም አልደወልኩም። እንደውም አንዳንዶች፣ “ሚስቴ ቤቱን ጥላልኝ ስትሄድ ቤቱ ሊበላኝ ደረሰ፣ ጭር አለ ኦና ሆነ” ምናምን የሚሉት ነገር ለምን እንደሚባል ገረመኝ። በጣም ነው ቤቱ የተስማማኝ ገነት ነው የሆነብኝ ! ምግብ ራሴ አበስላለሁ፣ ቤቴን በደንብ አፀዳለሁ፣ አነባለሁ፣ ፊልም አያለሁ
(እንደውም ከዚያ ፌቨን ከምትከፍተው አሰልቺ የቴሌቪዥን ድራማ ተገላገልኩ) እና ደግሞ ሰላም ሆንኩ!! እንደውም ባልና ሚስት የፈለገ ቢፋቀሩ፣ ትንሽ መለያየት፣ ራሳቸውን የሚያደምጡባት
“ሱባዔ” መሰል ብቸኝነት ታስፈልጋቸዋለች ብዬ አሰብኩ።

ፌቨንን ለራሴ እንኳን ስሟን በውስጤ መጥራት ይቀፈኛል። በቃ በተፈጥሮዬ ወግ አጥባቂ ነገር ነኝ ማለት ነው ብዬ አሰብኩ። እና እንዴት ይሄን ሁሉ ዓመት አብራኝ የኖረች ሴት ያውም በፍቅር ተነስታ ስትሄድ ምንም ሳይመስለኝ ቀረ። ለደቂቃ መኝታ ቤታችን ውስጥ ስትበር የነበረች ትንኝ
እንኳ በሆነ ሽንቁር ስትወጣ የሚናፍቅ ነገር አላት። አይ ጤነኛ አይደለሁም ማለት ነው። ወይስ የሆነ ውስጣችን ሳያውቀው የሚሰለቸው አብሮነት አለ ... ምክንያት ፈልጎ የሚፈነዳ ... ፌቨንን ሳላስበው ውስጤ ሰልችቷት ይሆን ? ዓይቷት የማይቋምጥ ወንድ የለም … ቁንጅናዋ እንግዳ ነገር ነው ..
መኝታ ቤት ገብታ ወደ ሳሎን ስትመለስ እንኳ አዲስ ቆንጆ ሴት እንዳየ ጎረምሳ ልቤ ይደነግጥላት
ነበር ... እና እንዴት ነው ነገሩ ... እንዲህ ልክ የሌለው ግዴለሽነት የሞላኝ ወይስ እየቆየ እንደተዳፈነ
እሳት ሊያንገበግበኝ ይሆን ...

ለነገሩ ቆንጆ ሴቶች ቶሎ ነው የሚሰለቹት ይባላል። በጥናት ባይረጋገጥም የሆነ እውነት እንዳለው በብዙ ቆንጆ ፍቅረኛ ባላቸው ጓደኞቼ ታዝቤያለሁ። በተለይ ከተጋቡ በኋላ ቆንጆ ሚስቶች ለውጭ ተመልካች እንጂ ለባሎቻቸው ያን ያህል አስገራሚም አስደሳችም ነገር የላቸውም እየተባለ ከፉኛ
ይታማል ሚስቶቹም ራሳቸው ይሄ ነገር ግራ ይገባቸዋል አንድ ጓደኛዬ እንዳለኝ ከሆነ እንደውም
ቃል በቃል፣ ለዛ ቢስ ናቸው !!” ነበር ያለው እንግዲህ ከሰፊ የብሶት ምክሩ የተወሰነውን ሳስታውስ (ያኔ እንኳ ችላ ብዬው ነበር) ቁንጅናቸው ይስብሃል፣ ቁንጅናቸውን ትፈልጋለህ፣ ታገኘዋለህ፣ ቁንጅናቸው መጋረጃ ሆኖ ስለሚጋርድህ ከማግኘት ቀጥሎ ያለውን ሕይወት አታስበውም። መጋረጃውን ስታልፍ ግን ጭው ያለ በረሃ ይጠብቀሃል.. ሰሐራ ! ምንም አይኖርም ወላ ሃንቲ !! ሁሉም ነገራቸው ወዲያው ነው
የሚሰለችህ... እንደውም እነሱን ለማግኘት የደከምከው ድካም ከንቱ ሆኖ ስለሚታይህ ነጭናጫ
ትሆናለህ ድሮ ይቺን ሚስትህን አፍቅረህ ስትንከራተት ፊት የነሳሃት በፍቅር ዓይን ስትስለመለምልህ
የነበረች ጎራዳ ሽቦ ፀጉር ልጅ ሁሉ ትናፍቅሃለች ! ለዛ ነው ብዙውን ጊዜ “ልዕልት የመሰለች ሚስት
አስቀምጦ ሰራተኛው ጋር…” ምናምን ሲባል የምትሰማው እንጅማ ሚስትህ ልዕልት ባትመስልም ሌላ ሴት ጋር ሂድ የሚል ፍርድ የለም መቼስ።” የጓደኛዬ ምክር ይከሰትልኝ ይጀምራል። የበላኝን
እንደሚያክልኝ ሁሉ ንግግሩን የራሱ ልምድና አመለካከት አድርጌ ከማድመጥ በላይ ዓለምአቀፍ
የሴቶች ባህሪ አድርጌ ልቀበለው ይዳዳኛል። ማንም ሰው በጋራ ብሶት ውስጥ ሲኖር በአዕምሮው ልክ ሳይሆን በብሶቱ ልክ ያስባልና።

“ሴትን ልጅ ለማየት ይሄ ደካማ ሥጋዊ ዓይን በቂ አይደለም ድፍን የስሜት ሕዋሳቶችህ፣ በአካባቢህ ያለው እውነታ፣ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ኃይማኖት፣ አስተዳደግህ፣ የትምሕርት ደረጃህ ሁሉ “ተቀናጅቶ” መሥራት ይኖርበታል። በደመ ነፍስ ዘለህ ከገባህ በደም ግፊት ዘለህ መቃብር ጉድጓድህ ውስጥ ነው
የምትገባው ያውም በጭንቅላትህ። ፍቅር ላይ ያለህ ነገር ከተበላሸ በምድር ላይ ያለህ ማንኛውም ነገር እንደተበላሸ ቁጠረው። ሌላው ቢቀር እየቆየ የሚያገረሽ የተበላሸ ትዝታ ይኖርሃል። ልብህን ለፍቅር
ስትሰጥ ወሲብ ያዞረው ናላህን አሽቀንጥረህ መጣል አለብህ። እሱ ነው እንደጋሪ ፈረስ ሸብቦ አንድ ነገር ብቻ እንድታይ የሚነዳህ። ለምን እቅጩን አልነግርህም ያኔ አንድ ቤት የሁለትዮሽ ስብሰባ ላይ ስትገናኝ
ተረከዝ አይመስጥህ፣ ዳሌ አያማልልህ፣ ከንፈር አያስጎመዥህ፣ ስርቅርቅ ድምፅ ቀልብ አያሳጣህ፣ ጉችም ይበል
ዝርግፍም ይበል ጡት ከመጤፍ አይቆጠር ሃቂቃዋ የፍቅር ዘርልብህ ውስጥ ከሌለች
አለቀልህ !”
👍453👏3👎1