አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰመመን


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

ለራሱ መቼ ይናገርና ! እንዳይናገር የማለው ገና ሻንጣውን ይዞ እዚህ ግቢ ሲመጣ ነው ። ደሞ ማርታ የባጡን የቆጡን ስትለፈልፍ የሌሎቹ ማጋነን ፥ የሌሎቹ አብሮ ከበሮ መደለቅ ምን ይባላል ? ... “ ጥሩ ጭንቅላት አለው ... ሌክቸረሮቹን ቻሌንጅ ያደርጋል . . . ከአራት ጂ.ፒ.ኤ. ስለወረደ ሊሰቀል ነበር . ” ቅብጥርሴ ። ይሰቀላ ከፈለገ ! አለሱ
ጎበዝ ተማሪ የለም እንዴ ? ! ደሞስ በቀደም ዕለት 'አዜብና አሰገደች ፥ ማርታ ስታወራላቸው ግማሽ ሰዓት ሙሉ አፋች
ውን ከፍተው ከማዳመጥ ይልቅ ፡ አሳይሜንታቸውን አይሠሩም ነበር ? አሰገደች የማስረከቢያውን ቀን አሳልፋ ጋሼ ኤርምያስ አልቀበልም አላት ። እሱ ለራሱ ሴሪየስ ነው አዜብ ግን ተስፋ የላትም ። ከአባት ጦሮች ጋር ፀሐይ እየሞቀች ማን ያውራላት ? ማርታስ ብትሆን መቼ ከነሰ ትሻላለች?እሷ እምታውቀው አቤልን ማድነቅ ብቻ!ጎበዝ ተማሪ ማድነቅ ጎበዝ የሚያደርግ ይመስል ። ኦፍ ኮርስ ብራሊየንት
ነው ። እሱ የታወቀ ነው ... ግን ነገሩን ሲያስቡት ደሞ “አቤል ብሎ ሲኒየር፥ የመጽሐፍ ብሪሊያንት ! አቤል ብሎ
ወጣት ! ስሙ ራሱ ደስ አይልም !!...”

ትዕግሥት ወደሚዘፍኑት ሴቶች ተመለከተች፡፡ በሆዷ ለራሰ እምታወራውን የሰማት ይመስል-ግራና ቀኝ ወዳሉት
ሰዎች አማተረች ። አንዳንዶቹ ወዲያ ወዲህ ይላሉ ።አንዳንዶቹ እያጨበጨቡ ዘፈኑን ከሩቅ ያደምቃሉ ። ዐልፎ ዐልፎ እጅዋን ለኮፍ ማድረጓ ባይዘነጋትም፡እነማርታን ስታይ በወጉ ማጨብጨብ ጀመረች ። ቤተልሔምና ማርታ ጥቂት
ቆይተው ከሁለት ወንዶች ጋር ፈጠን ፈጠን እያሉ ሲያልፉ አየቻቸው ። ወደሷ ቀረብ ሲሉ ፥ ከማርታ ጋር እሚያወራው
ቀጠን ያለ ወጣት ላይ ዐይኗ ዐረፈ ። “ ማርታ ከሰው ጋር የመግባባት ችሎታ አላት ፥ በተለይ ከወንዶች ጋር ስትል
አሰበች ። ማርታ ፡ “ ወንድ ደስ እሚለኝ ቀጠን ሲል ነው ” እያለች ብዙ ጊዜ እምትናገረው ነገር በሐሳብዋ እየደጋገመ
ተሰማት ። ወዲያው በድንገት አቤል ከፊቷ ላይ ድቅን አለባት ። «መልኩ መስሎ በምናቧ መንቀሳቀስ ጀመረ ። አቤል ጠይም ነው ቀጠን ዘለግ ያለ ። ከሲታ ሳይሆን ፡ ሁሌ እሚለብሰው ጃኬቱ ጠባቃ ባያደርገው ፥ በአቋቋሙ ሚዛኑን የጠበቀ ነው ። አረማመዱ ኮራ ያለ ዐይነት ነው እሷን ሲያይ መርግጫውን እማያውቅ ከመምሰሉ በስተቀር ። አቤል ዐይኖቹ ተለቅ ተለቅ ያሉ ናቸው ። ሰልካካ አፍንጫው የተመጠነ አወራረድና ለግንባሩ ገጥታ ተስማሚ አቀማመጥ አለው ዞማ ጠጉሩ በደንብ ተበጥሮ እሚያውቅ አይመስልም ። ይሁን
እንጂ ለራስ ቅሉ እንደ ቆብ በልክ እንደ ተስፋ ሁሌ ክርክም ያለ ዐይነት ሆኖ ድምቀቱ ከጥቁር ከፋይ ይወዳደራል ! እስካሁን ጥርሶቹን በደንብ ለማየት አልቻለችም ። አቤል መች ይሥቃል ? ! እንዳይሥቅ ተገዝቶ ነው ካምፓስ የመጣው።እንዳውም እራት ዓመት ሙሉ በጭራሽ ሥቆ አያውቅም ።ጨፍጋጋ !ጨፍጋጋ ፊት ! እስቲ ምን ይባላል ፥ በጨፍጋጋ ሰው መታማት ? ! ቢሆንም ግን ላመል ፈገግ ሲል በጨረፍታ ኣ
አይታዋለች አንድ ቀን ከእስክንድር ጋር ቆሞ ሲያወራ ። ከዛም በፊት ሳታየው አትቀርም ፡ ማስታወሱ ይቸግራል እንጂ ። ስንቱ ነገር ይታወሳል ? አቤል ዝርዝር ያሉት ናቸው ጥርሶቹ በጠይም ፊቱ ላይ እንደ ወተት ነጭ መሆናቸው ነው ዐይን እሚስበው ። ድምፁ ግን ምን ዐይነት ነው
የአቤል? መቼም በዚህ ጥርስ አቀማመጥ በትንሿ ኮልተፍ ቢል ሳያምርበት አይቀርም ! ግን በየት በኩል ? እሱ ለራሱ ዲዳ ነው አይናገር አይጋገር ። ይቺ ማርታ ግን ዋና ናት
ጥርሰ ፍንጭት ነው እያለች ማውራቷ ። ቀድሞ ነገር የት ታውቀውና ያው እንደኔ ነው ከሩቅ የምታየዉ ..

ትዕግሥት ይሄን ስታስብ ቆይታ እስቲ በደንብ አየዋለሁ” አለች በልቧ ። ግን ደሞ ወዲያው ፥ እስክስታው ላይ ተተክሎ የነበረው ዐይኗ ቦዘዝ ብሎ ወደ ካምፓስ አዘገመ

ለምንድነው ጠዋት እንደዚያ የተቆጣው ? ” ስትል አሰበች ። አቤል ከደረጃ ወርዶ ፊት ለፊት በተገጣጠሙበት ሰዓት ከፊቱ ላይ ያየችው ቁጣ እንደ ገና ታያት ። የሱ መቆጣት ብቻ ሳይሆን ፥ የራሷም መሸማቀቅ ነበር ያስገረማት ።ንግግር የለ ! ሰላምታ መለዋወጥ የለ! ተቀራርቦ መጨዋወት የለ እንዲያውም እንደ ዲዳ እንደ ደንቆሮ በዐይን ብቻ መገናኘት ምንድነው ?

ዕንቆቅልሽ ሆነባት ። ዓይኗን ከድንኳኑ አሻግራ ወደ ማዶ ወረወረችው ፤እጅዋ ቀስ ቀስ እያለ ማጨብጨቡን አቋረጠ
ትምህርቷን መከታ አድርጋ ልትሽሽ የምትታገለው የዐይን ፍቅር እንደ ውሃ ጠብታ ቀስ ቀስ እያራሳት መሆኑ
ተሰማት መጨረሻዉ ናፍቋት ።

“ እሺ እንግዲህ መቼ ነው ታዲያ አፍ አውጥቶ የሚያናግረኝ ወይም አፍ አውጥቼ የማናግረው?” ስትል ሜሰቧን
ቀጠለች ። “ ዛሬ ያናግረኛል” ብላ ያሰበችበት የአንድ ቀኑ ጥሩ አጋጣሚ ታወሳት ።

የትምህርት ቀን ነበር። ነገር ግን ቀትር ሰዓት ላይ ስለሆነ የሚነቃነቅ ሰው አልነበረም ። አብዛኛው ምሳ በልቶ
በየክፍሉ ጋደም ብሎአል ። ጥቂቱ መጻሕፍት ቤት ገብቶ ያንኑ መጽሐፍ የሙጥኝ ብሏል ። ትዕግሥትን ከደብረ ዘይት የመጣ ዘመድ አስጠርቶአት ወደ ውጭው በር ስትሔድ አቤል ቡና ጠጥቶ ከውጭ ሲመጣ ተገጣጠሙ ። እሷ ፈጥና ነበር የምትራመደው። እሱም እሷን ባየ ጊዜ፥እጆቹን ከኪሱ አዉጥቶ ፈጠን አለ ። የተገጣጠሙበት መንገድ ወደ ግራም ወደ ቀኝም መታጠፊያ አልነበረውም ። ሊቀራረቡ ጥቂት
እርምጃ ሲቀራቸው የሁለቱም ልብ ትርታ ጨመረ ። ትዕግሥት ወደ ግራዋ ሰረቅ አርጋ አየችው ። እሱ መሬት መሬቱን
ነው የሚያየው።አጠገቡ ስትደርስ ገልመጥ አረገችው ፤ግልምጫዋ ለክፋት ያለችው አልነበረም ። ምናልባት አቤል
ለሰላምታ ጭንቅላቱን ሰብሮላት ፈገግ ብሎላት ወይም በግንባሩ ምልክት ሰጥቷት እንደሆን አጠፌታውን ልትመ
ልስለት ነበር ። አቤል ግን አጠገቧ ሲደርስ በልቡ እንዳልከጀላት ፈጽሞ እንዳልፈለጋት ፥ ጭራሽ እንደማያቃቃት
ፀይነት አንገቱን ደፍቶ ግንባሩን አኮማትሮ ቅርቅር አድርጓት አለፈ ።

ሁኔታው ትዕግሥትን ረበሻት ። በተለይ ችግሩን አስልታ ከትምህርቱ ጋር በተመለከተችው ጊዜ ዓይኗ እንባ
አቀረረ ። እንቅፋት ነው እንቅፋት!” ስትል ለራሷ ተነፈሰች ። ከዚያ ቀን በኋላ ከአቤል ዐይን ለመሸሽ ሞከረች
ግን ለማንም እላማከረችም ። በዕለቱ ከደብረ ዘይት ድረስ የመጣውን ዘመዷን እንኳ ፥ በቅጡ ሳታጫውተው ነበር የተለየችው .....

“ታዲያ ከዚያ ቀን የበለጠ አጋጣሚ ከየት ይገኛል? ”ብላ በሐሳብ ስትወራጭ የድንኳኑ ግርግር አባነናት ። ከውጭ ተከታታይ የመኪና ጥሩንባ ስለ ተሰማ ። በድንኳኑ የተሰበሰበው ተጋባዥ ሁሉ ሙሽራውን ለማየት የመቻኮል ስሜት ይታይበታል ። የቤተ ዘመድ ሽር ጉድ ማለትና መንጫጫት ግሏል ።

ማርታ ወደ ዘፋኞቹ ስትንደረደር መጥታ የትዬ ሙቀጫን ትከሻ ነካ ነካ አረገችና ። “ እትዬ ሙቀጫ ፥ ከበሮውን ይዛችሁ ውጡ እንጂ ! ሙሽራው እኮ መጥቷል ። ቶሎ በሉ እንጂ! ” አለቻቸው ።

ዘፋኞቹ ወደ በሩ ግልብጥ ብለው ሔደው ከበሮውን ሞቅ አድርገው እየመቱ ይዘፍኑ ጀመር ።

“አናስገባም በሩን ፡ ሰርገኛውን
በሩን ..
ሰርገኛውን ....
አናስገባም ሠርገኛ እደጅ ይተኛ
ሰርገኛ እደጅ ይተኛ ... ”

ማርታ ደስ አላት ። በሙሽራው ላይ እልኋን እንደ ተመጣች ሁሉ ፥ ብሽቀቷ በርዶላት ፊቷ ፈክቶ " ዳር ሆና ታጨበጭብ ጀመር።ሙሽራው ገብቶ ብፌ በሚዘረፍበት ሰዓት ቤተልሔም አንድ ሰው አየች።ለማ ካብትይመር ነበር።ከግርግሩ መሀል ለይታ እንድታየው ያስቻላት
👍3
ጸጉሩ ሸሽቶት የተጋለጠው ግንባሩ ነው ። ልክ እንዳየችው በደስታ ደነገጠች ። ብፌውን
ዘርፎ ወደ ቦታው ሔዶ እስኪቀመጥ ድረስ በዐይኗ ተከተለችው ። በሙሽሮቹ መደዳ ትንሽ ራቅ ብሎ ነበር የተቀመጠው።

አጃቢ ይሆን?” ስትል አሰበች ፥ “ እንዲያማ ቢሆን መታደል ነበር” አለች | የግንኙነት ጊዜው እንደሚረዝም በመገመት ።

ብዙም ሳትቆይ እሱ በተቀመጠበት አካባቢ ዐለፈች እንዲያያት ፈልጋ ነበር ። እሱ ግን ምግቡ ላይ አቀርቅሮ ስለ ነበረ ቀና ብሎ አላያትም ። እንዴት ሰላም እንደምትለው ግራ ገብቶታል ። የቀድሞ ግንኙነታቸው ያው የአሰተማሪና የተማሪ ስለሆነ ፥ ከአንገት ሰላምታ አላለፈም ። ስለሆነም አሁን ፊት ለፊት ሔዳ ሰላምታ መስጠት አልደፈረችም ።

ብሉ እስቲ ፥ ምን ጎደለ ? ” እያለች በሱ መደዳ ላሉት ሰዎች ፥ ድምጿን ከፍ አድርጋ ።

ለማ ቀና ሲል አያት ። ተማሪው መሆኗን አያት። እሷም በዝግታ ዐይኗን ቀልሳ አየችውና ሰላም የማለት ያህል ፈገግ
ብላ አንገቷን ሰበር አደረገች። ምላሹን ሰጣትና የሚጠጣውን ነገር ከጠርሙሱ ወደ ብርጭቆው ማንደቅደቅ ጀመረ ።

ቤተ ልሔም በልቧ እንደ መብሸቅ አለች።የሰላምታው ምላሽ የጠበቀችውን ያህል ሞቅታ ኣልነበረውም ።

ድርቅ ብላ ከፊቱ ቆመችና ፥ “ ምን ጎደለ ታዲያ? ምን ላምጣ ? ” አለችው ፡ ከአስተናጋጅነት ይልቅ ቅርብነት
በጎላበት ጣፋጭ አነጋገር ። በጎልማሳነት ክልል ውስጥ ቢሆንም ። ከዚህ በፊት ቀርባ አነጋግራው ስለማታውቅ። አንተ
ወይም አንቱ ለማለት ቸግሮአታል ። ነገር ግን ለማጥመድ ያሰበችውን ሰው አንተ ማለት የሚያስከትለውን ውጤት
ታውቃለች ። ኋላ አባትና ልጅ ወይም ወንድምና እኅት ሆኖ ቁጭ ነው ። እናም ደፍራ ኣንተ ለማለት ወሰነች ።

ሁሉም አለ። ግሩም ነው አላት ለማ ።

“እውነቴን ነው ፥ የምትመርጠውን ነገር ላምጣልህ ” አለችው ፡ በዐይኗ ከሰሐኑ ላይ የተቀመጠውን የምግብ ዐይነት እየፈለገች ። “ ጭኮዋን ወደሃታል አይደል?! እሷን ላምጣልህ” አለችውና ከእሱ መልስ ሳትጠብቅ ልታመጣለት
ሔደች ።

ለማ የዶሮ ወጡን እንቁላል እየፈረከሰ ቤተ ልሔምን ከኃላዋ ቃኛት ። ሰፋ ያሉ ጃፖኒ ቀሚስ ነበር የለበሰችው ። ውፍረቷ
ያንኑ መጠነኛ ቁመቷን ቢውጥባትም ለጊዜው በረዥም ታኮ ጫማ ተነሥታለች ስትራመድ ዳሌዋ ግራ ቀኝ ይረግጣል ።
የሚዛኗ አጠባበቅ ብዙ ልምምድ እንደ ተደረገበት ያስታውቃል ቤተልሔም የጭኮውን ሰሐን ብፌው ከተዘረጋበት ጠረጴዛ ላይ ስታነሣ ማርታ ተመለከተቻት እንደ ደንቡ ከሆነ ለድጋሚ ዙር የምግቡ ዐይነት ከተዘረጋበት ጠረጴን ተነሥቶ
በየገበታው የሚዞረው ተጋባዡ ሁሉ ብፌ ዘርፎ ከጨረሰ በኋላ ነው ። ቤተልሔም የጭኮውን ሰሐን ስታነሣ ግን ገና ብፌ ዘረፋው አልተጠናቀቀም ። ስለዚህም ማርታ ልቧ የሆነ ነገር ጠርጥሮ በዐይኗ ተከተለቻት ፤ ጭኮውን ወስዳ ለማ ሰሐን ላይ ስትዘረግፍለት በቅናት ስሜት ተመለከተቻት ።

“ኧረ በቃ!በቃ!” አለ ለማ የምትጨልፍበት እጅዋን ለማስጣል በግራ እጁ ይዞ

“ እሺ ፡ በል ያመጣሁልህን ብላ ” አለችና ዐይኗን አስለምልማ አየችው ። ሳያስበው የእሽታ ፈገግታ ሰጣት ።ፈገግታው ካመለጠው በኋላ በቅልጥፍናዋ ተደነቀ ።

እሷም እይታዋን አልደገመችውም ተቀባይ ልብ ላለው ሰው የአንዴው በቂ እንደሆን ታውቃለች ። በምላሽ ፈገግታው
ረክታ ነገሩን ለማድበስበስ ያህል በአቅራቢያው ላሉትም ብሉ እንጂ” እያለች ከጭቆው ጨመረችላቸው ።

ለማ ጸጉር በከዳው ግንባሩ በኩል ላብ ሲንቸረፈፍ ተሰማው ። ወንድነቱ “ ዘራፍ” እያለ መጣበት ። ምግቡ ላይ እንዳቀረቀረ ቤተልሔምን በልቡ ተመለከታት ጉሮሮ
ውን ምንም ነገር ሳይኮሰኩሰው ፡ ጣለ ፡ ለአፍታ ያህል ትንፋሹን አምቆ ቆየና በረዥሙ ተነፈሰ ። በድንገት የሚስተር
ራህማን ምስል ከፊቱ ተደቀነበት

ሚስተር ራህማን ለለማ የሥራ ባልደረባው ናቸው እሱ ተመርቆ ዩኒቨርስቲ ማስተማር ከጀመረ ገና አራተኛ
ዓመቱ ነው ። ሚስተር ራህማን ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ዩኒቨርስቲ ሲያስተምሩ ዘጠኝ ዓመት አላቸው ። ነገር ግን ሰማቸው። በዩኒቨርስቲው ውስጥ የዚያኑ ያህል ጠፍቷል በሴት ጉዳይ ተማሪው ብቻ ሳይሆን መምህራኑም ጭምር ያሟቸዋል ። የትም ይሁኑ የትም ዐይናቸው ከሴት ላይ አይነቀልም
ቆንጆ ልጅ ታክሲ ውስጥ ካጋጠመቻቸው ካልከፈልኩልሽ በማለት ብቻ አይመለሱም “ አይቲንክ አይ ኖው ዩ ሳምዌር ”ብለው ወሬ መክፈት ልማዳቸው ነው።

💥ይቀጥላል💥
👍2
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

ጉዞ ወደ አርባምንጭ፤በጥዋት ተነስተን በሚኒ ባስ ተሳፍረን ጉዞ ጀመርን፡፡ሃኒ ከአዲስ አበባ ስንነሳ ጀምሮ መኪናው አልተመቻትም፤ ስትንቆራጠጥ ነው ሻሸመኔ ደረስን አደርን፡፡ ከሻሸመኔ ደግሞ ቅጥቅጥ አይሱዙ ተሳፍረን፣ በወላይታ
ሶዶ አድርገን፣ ጉዞ ወደ አርባ ምንጭ፡፡ መኪናው እላይ አድርሶ ያፈርጠናል፡፡ ደጋግሜ አይዞሽ እላታለሁ፡፡ በእርግጥ እንደዛ ከማለት ውጪ፣ ምንም ማድረግ ምችለው ነገርም የለም፡፡

“መዝናናት ሳይሆን መጉላላት ሆነብሽ?” አልኳት የሚሰማትን ማውቅ ፈልጌ፡፡

“ለምንድነው ግን፣ በቱር መኪና ያልመጣነው?” አለች፡፡

“አቅም ነዋ ሃኒዬ፣ አቅም..! በጣም ውድኮ ነው፡፡ በቀን ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር፣ አይከብድም...?”

“ኖ...! እንደሱ ሳይሆን፣ ኮስትር በጋራ ከሌላ ጎብኒዎች ጋር ሆነን ማለቴ ነው፡፡”

“እንደዛ አይነት ፓኬጅ ያለ አይመስለኝም፡፡ ሰምቼ አላውቅም፡፡
ሙሉ ኮስትር ግን ይባስ ውድ ነው፡፡”
“ለምን እንከራየዋለን? እንደኛ አርባ ምንጭን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጓዦችን አሰባስቦ የሚሄድ፣ የአስጎብኚ ድርጅቱ ጋር ሁለት ትኬት ገዝተን ብንሄድ ነው ምልህ፡፡ እንደውም፣ አስጎብኚ ስለሚኖር ብዙ ነገሮችን ማየት እንችላለን፡፡”

“እንደምትዪው አይነት ጉዞ ሰምቼ አላውቅም፡፡ በአስጎብኚዎች የሚዘጋጅ፣ የግሩፕ የጉብኝት ጉዞ እድል ያለው፣ ወደ እስራኤልና ሲሸል ለማስጎብኘት ሲሆን፣እንጂ ሀገራችን አልተለመደም፡፡ ሀገራችንን ለማየት፣ ያለን አማራጭ፣ በቀን ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር ከፍሎ፣ ላንድክሩዘር መከራየት ይጠይቃል ወይም
እንደዚህ በተለመደው የህዝብ ትራንስፖርት ተሳፍረሽ፣ ለመዝናናት
እየተጉላላሽ መሄድ ነው፡፡ የግሩፕ ጉዞ ቢኖር ኖሮማ፣ይሄኔ ሀገሬን ከሰሜን እስከደቡብ፣ ከምስራቅ እስከምዕራብ ማየት እችል ነበር፡፡”

“እንዴ ይኼ እኮ አሪፍ ቢዝነስ ነው፡፡ እና ወደ አርባ ምንጭም ሆነ፣ ወደተለያዩ የሀገራችን ተፈጥሯዊና ባህላዊ መስህብ ያላቸውን ቦታዎች በተደራጀ መልኩ፣ ቅስቀሳ አድርገው፣ በተመጣጣኝ ዋጋ
የማስጎብኘት ስራ የሚሰሩ ድርጀቶች የሉም እያልከኝ ነው?”

“በእርግጥ፣ ይሄ አካሄድ ገዳማትን ለማስጎብኘት በየታክሲው፣በከተማዋ ግድግዳዎችና የስልክ ቋሚዎች ላይ በሚለጠፉ ቅስቀሳዎች፣ፍላጎቱ ያላቸውን ሰዎችን አሰባስበው በማደራጀት በተመጣጣኝ ዋጋ ጉብኝቶችን ሲያዘጋጁ አይቻለሁ፡፡ ነገር ግን ይህን አካሄድ፣ በጥቂቱ አዘምነው፣ ሀይማኖታዊ ላልሆኑትም ለሌሎች የሀገሪቱ መስህቦችን ለማስጎብኘት ብንጠቀምበት፣ ማህበረሰቡን በተመጣጣኝ ዋጋ የተለዩ የሀገራችንን መስህቦች ለማስጎብኘት እድል ይሰጣል፡፡ በሂደቱም፣ ለብዙ ሰዎች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ፣ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ ነገርግን፣ ይህ የተለመደ ባለመሆኑ፣ ላሊበላን፣
አክሱምን፣ የጀጎል ግንብን፣ የባሌ ብሄራዊ ፓርክን፣ ነጭሳር ፓርክን
እና ሌሎች ልዩ እና ድንቅ የሆኑ የሀገራችን ውበቶችና ኩራቶች ከዜጎቻችን ይልቅ በውጪ ቱሪስቶች ይጎበኛሉ፡፡ ትውልዱም ሀገሩን የማወቅ እድል ስለሌለው፣ በሀገሩ መኩራት ሲገባው፣ ባለማወቁ ፀምክንያት ያፍርባታል፡፡”

“ይኸውልህ ያቡ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ ያለው ውጣ ውረድ አድካሚ እና የሚያጉላላ ከመሆኑም በተጨማሪ በየቦታው የሚገኙ መስህቦችን ቆም ብሎ ለማየት፣ ለማድነቅና ፎቶ ለማንሳት አይመችም፡፡በመሆኑም ጉብኝቱን የተሟላ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ እንደምትነግረኝ ከሆነ፣ የአስጎብኚ ድርጅቶች አደረጃጀት የውጪ ዜጎችንና ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን ሰዎች ብቻ ያማከለ ይመስላል፡፡ ይህም የመጎብኘት
ባህላችን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ጉብኝትን እንደቅንጦት እንዲቆጠር
ያደርጋል፡፡ እራስን አድሶ ለቀጣይ ስራ እራስን ከማዘጋጀትም በላይ፣
በመጎብኘት ውስጥ በጣም ብዙ አዲስ እውቀት፣ የፈጠራ ሀሳቦችና የልምድ ልውውጦች አሉ፡፡”

“ትክክል ብለሻል ሃኒዬ፡፡ እንደማህበረሰብ የመጎብኘት ባህላችን መሻሻል አለበት። እንዳልሺው መጎብኘት ከመዝናናት በዘለለ ብዙ ፋይዳዎች አሉት፡፡ አንዱ ማህበረሰብ ውስጥ ያየሽውን ባህልና እሴት ቀምረሽ፣ በህይወት ለሌሎች ችግሮችም እንደ መፍትሄ ልትጠቀሚበት
ትችያለሽ፡፡ ነገር ግን እንዳለ መታደል ሆኖ፣ በማህበረሰባችን መጎብኘትን
እንደቅንጦት፣ ለመጎብኘት የሚያወጣን ወጪ እንደ ማባከን የሚቆጥረው
ቁጥሩ ቀላል ሚባሉ አይደሉም፡፡”

እየተጫወትን ለመርሳት የመኪናውን እንግልት እንዲህ ሞከርን፡፡ ሲደክማት ጋደም እያለችብኝ፣ አስር ሰአት አርባ ምንጭ ከተማ ገባን፡፡ እንደደረስን ቱሪስት ሆቴል አልጋ ያዝን፡፡ ቢደክመንም፣ ሃኒ
ከተማውን ለማየት ካላት ጉጉት የተነሳ፣ ሳናርፍ ሻወር ወስደን ወጣን፡፡በቅርብ የተሰራ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ ለከተማዋ አዲስ ውበት ሰጥቷል፡፡ አርባ ምንጭ ግርግር ያልበዛበት ደርባባ ከተማ ነች፡፡ በባጃጅ ተዘዋውረን ከተማዋን ለማየት ሞከርን፡፡ ከተማዋ ሁለት ጫፎች አሏት፡፡የዩኒቨርስቲውን መስፋፋት ተከትሎ የተመሰረተውና የቀደመው መንደር ደረጃውን በጠበቀ የአስፓልት መንገድ በቅርብ እንደተገናኘ ያስታውቃል፡፡
አስፓልቱ ሳይሰራ ከተማዋን አሰብኳት፡፡ የአባይና ጫሞ ትልልቅ ሀይቆች ሀገር፣ የነጭ ሳር ፓርክ፤ የአዞ ገበያ፣ የሙዝና የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ የቱሪስት መናኸሪያ ሀገር፣ አርባ ምንጭ የረባ የአስፓልት
መንገድ ለዓመታት ብርቋ ነበር፡፡

ለዐይን ያዝ ሲያደርግ ወክ እያደረግን ወደ ቱሪስት ሆቴል ተመለስን፡፡ ወደ ሆቴሉ እንደገባን ረሃብ ስሜት ተሰማኝ፡፡ እራት
ለመብላት ዞርዞር ብለን ቦታ መፈለግ ጀመርን፡፡ አንድ ጥግ ላይ ክፍት ቦታ አገኘንና ተቀመጥን፡፡ አስተናጋጅ እየጠበቅን፣ ግቢውን ቃኘነው፡፡

“ግማሽ በግማሽ ፈረንጅ አይደል እንዴ?” አለች ሃኒ፡፡

“ያው ቱሪስት ሆቴል አይደል፡፡”

“ኪ.ኪ.ኪ..፣ እና ለዛ ነው?”

ማለቴ አርባ ምንጭ እኮ ምድራዊ ገነት ናት፡፡” አስተናጋጁ መጥቶ “ምን ልታዘዝ!” አለን፡፡

“ምን እንብላ ሃኒዬ?”

“እንዴ! አርባ ምንጭ መጥተንማ፣ ከአሳ ውጪ መብላት...”

“እሺ! አንድ ለብለብ አንድ ጉላሽ ይሁን?”

“እሺ፣አሪፍ ነው፡፡”

“የሚጠጣ ሁለት ጊዮርጊስ ቢራ፡፡”

አስተናጋጁ እየተዋከበ ከአጠገባችን ሄደ፡፡ ግቢውን በዐይኔ ቃኘሁት፡፡ በግቢው የመዝናናት መንፈስ ሰፍኗል፡፡ ሰው ይበላል፤ ይጠጣል፡፡ ይጫወታል፡፡ ከሃኒ ጀርባ የተቀመጡ ሁለት ነጭ ሴቶችን አየሁ፡፡ ከኔ ትይዩ ያለችው ፈረንጅ
👍3
ልከኛ ሰውነት ያላት ቆንጆ ነች። አብራት ያለችው፣ ጀርባዋ ብቻ ቢታየኝም፣ ግዝፍዝፍ ያለች ወፍራም እንደሆነች ታስታውቃለች።ቆንጅዬዋ ታወራለች። ወፍራሟ ታዳምጣለች፡፡ የአንድ አገር ሰው
አይመስሉም፡፡ የየት ሀገር ሰው ይሆኑ ብዬ አሰብኩ፡፡ በውስጤ ፀለመገመት እየሞከርኩ ነው፡፡

ነገ ምንድ ነው ፕሮግራማችን?” ብላ ሃኒ ከሄድኩበት ሃሳብ አወጣችኝ፡፡

“ነገማ አርባዎቹንም ምንጮች
እናያቸዋለና።”

“እንዴ! የምር አርባ ናቸው እንዴ?”

“ኧረ ስቀልድሽ ነው፡፡ ማን ቆጠራቸውና፡፡”
ከነጯ ጋር ደጋግመን ዐይን ለዐይን ተጋጨን፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ልተዋወቃት ፈልጊያለሁ፡፡ ወደ ሽንት ቤት ወይም እጇን ልትታጠብ ከተነሳች ተከትያት ለመሄድ ወስኛለሁ፡፡ በየመሃሉ በሃኒ ላይ አሻግሬ እመለከታታለሁ። ሃኒ ምን እንደማይ ለማየት፣ አንድ ሁለቴ
ዞራ ተመለከተች፡፡ ሃኒ ሌላ ደስ ሚል ባህሪዋ፣ ብዙ ጨቅጫቃ አየደለችም፡፡ አይታ እንዳላየ አለፈችኝ፡፡ የኛ ምግብ መጥቶ እየበላን እነሱ ታጥበው፣ ከፍለው እየወጡ ነው፡፡ በተቻለኝ መጠን ትኩረቴን
እንደሳበችኝ እንድታውቅ ደጋግሜ አየኋት። ሲወጡም፣ በዐይኔ ሸኘኋቸው፡፡
በሚቀጥለው ቀን የመንገዱ ድካም እስኪለቀን፣ ከተማዋን እያየን፣ እዛው ያሉ ሎጆችን እየጎበኝን ስንዝናና አመሸተን፣ ወደ ክፍላችን ስንገባ ትናንት እራት ላይ ያየናቸው ነጮች ወደ ክፍላቸው ሲገቡ በር ላይ ተገናኘን፡፡ እነሱም ቱሪስት ሆቴል ነው አልጋ የያዙት፡፡
ሳላስበው፤

ሄይ ሃው አር ዩ?” አልኳቸው፡፡ እነሱም ሰላምታ ሰጥተውን ተዋወቅን፡፡ ደስ ያለችኝ ኢቫ ትባላለች፡፡ የወፍራሟን ስም እዛው
እረሳሁት፡፡

“ሲ ዩ፡፡” ብለውን ገቡ፡፡ እኛም ወደ ክፍላችን ገባን፡፡ ሳላስበው ከነጮቹ ጋር ባደረኩት አፍሪያለሁ፡፡ ሃኒ ምን ተሰምቷት ይሆን? ግን ምን መሆኔ ነው? ፈረንጅ ብርቁ እንደሆነ ሰው፣ እንደዛ መሆን
አልነበረብኝም፡፡ በራሴ ተናደድኩ፡፡ ልንተኛ ልብስ እየቀየርን፤

“ነገስ የት ነው ምንሄደው?” አለችኝ ሃኒ፡፡ ምንም የመናደድ ምልክት አይታይባትም፡፡

“ነገ የት እንደምንሄድ አልወሰንኩም፤ እንዴት እንደምንሄድም አላውቅም፤ ግን የዶርዜ ሎጅን ብናይ ደስ ይለኛል፡፡”

“እንዴት ነው እዛ ሚኬደው?

ታውቀዋለኽ?”

“አይ፣ አላውቀውም፡፡ ጥዋት ስው እንጠይቃለን፡፡”

አልጋችን ውስጥ ገብተን ተኛን፡፡ እንቅልፍ ቶሎ አልወሰደኝም፡፡ከነጮቹ ጋር ያደረኩት ስሜታዊ ድርጊት ምን እንደሆነ ማስብ ጀመርኩ፡፡

እንዴት ማሂ እያለች እንደዚህ አይነት ስሜት ይሰማኛል? እንዴት ቢያንስ ማሂ ፊት ስሜቴን መደበቅ አቃተኝ? ከማሂ ጋር ተኝቼ ውስጤ ኢቫን ሰወሲባዊ ስሜት ያስባል፡፡ ምን አይነት እብደት ነው?፡፡ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍2
#ሰመመን


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

.... " ቆንጆ ልጅ ታክሲ ውስጥ ካጋጠመቻቸው ካልከፈልኩልሽ በማለት ብቻ አይመለሱም “ አይቲንክ አይ ኖው ዩ ሳምዌር ” ብለው ወሬ መክፈት ልማዳቸው ነው።የመኖሪያ ቤታቸውን እቅጣጫ እየዘረዘሩ ቀጠሮ መለዋወጥ
ከጀመሩ ግን ፥ ከታክሲ ነጂው ጋር መጣላታቸው አይቀርም ።ሚስተር ራህማን በወሲብ ፍላጎታቸው ራሳቸውን መቆጣጠር አይችሉም ። ለምሳሌ ካምፓስ አካባቢ ከሴት ጋር ቆመው
ሲያወሩ ቢታዩ፥ ሠራተኛ ለመቅጠር እየተነጋገሩ ነው ማለት አይደለም። ወይም አማርኛ እየተለመማዱ ነው ብሎ እሚያስብ ተሳስቷል ። ሚስተር ራህማን በዚያን ሰዓት ያጠኗቸውንም ያላጠኗቸውንም ውበት ማድነቂያ ቃላት አንድ ባንድ እየቦረቦሩ በማዥጎድጎድ ላይ እንደሚሆኑ አይጠረጠርም እንዳውም በል ካላቸው የሴትዮዋን እጅ በጃቸው ጥርቅም አርገው እንደ ያዙ ፡ አደባባይ በመዞር ላይ ያሉ የሞላ ታክሲ
ወዲያውኑ ካላስቆምኩ ሊሉ ይችላሉ ።

የሚያወጧቸው ሴቶች አያወሩባቸውም ። “ A ” በእጃቸው እንደ ገባች አረጋግጠው ድምፃቸውን አጥፍተው ቁጭ ነው ።ነገር ግን የራህማንን ጥያቄ የማይቀበሉ ጥቂት
ጠንካራ ሴቶች ያጋጥማሉ።እኒህኞቹ ለቅርብ ጓደኞቻቸው ።አንቺዬ ይሄ ሽማግሌ ሕንድኮ ላውጣሽ እለኝ አያፍር
እንዴ በናትሽ ? ምን ቅሌታም ነው!” ሲሉ ይሰማል ። ወሬው እንዲህ እያለ ይራባል ወንዶች ይህን “ ዕድል” ባይታደ
ሉትም ፡ አንዳንዶቹ በአገናኝነት በማገልገል የበኩላቸውን ሚና ይጫወታሉ እየተባለ ይወራል ...

“ ከዚህ አድነኝ ! ” በማለት ዐይነት ለማ ግንባሩን ቋጥሮ ራሱን ነቀነቀ ። ከራሱ ጋር ቅራኔ ውስጥ ገባ ።

ቤተልሔም የጭኮውን ሰሐን ከጠረጴዛው ላይ መልሳ እየተፍነከነከች ሙሽራዋ ስትለባብስ ወደ ቆየችበት ክፍል ሔደች። ማርታም አይጥ እንዳየች ድመት በዐይኗ ስትከታተላት ቆይታ { ወደ ገባችበት ክፍል ዘው ብላ ገባች ።

«ዉይ ! ኮቴሽን ሳልሰማ ። እንዴት አስደነገጥሽ !አለች ቤተልሔም በደስታ የሚሥቁ ዐይኖቿን ማርታ ላይ ተክላ ። በቁም ሳጥኑ መስታወት እያየች ጸጉሯን ስታስተካክል ነበር የደረሰችባት ።

“ አለ ነገር ! ” አለች ማርታ ከፊል ቀልድ ከፊል ቅናት በተደባለቀበት ሞዛዛ አነጋገር “ ከግብዣ መሐል አስነሥቶ ጸጉር የሚያስበጥር ፡ አለ ነገር! አለ ነገር ! ”

“ መች አጣሽው ማርትዬ ፡ አለ እንጂ ጥብቅ ነገር ! ሠርግና ምላሽ መሐል ከመምህሬ ጋር ስገጣጠም ” አለች "
ዜማ ቀረሽ በሆነ ድምፅ ።

መምህርሽ ነው እንዴ?” ስትል በቁም ነገር ቃና ጠየቀቻት ።

“ አይተሽዋል እንዴ ? ” ስትል ፥ ቤተልሔም ጥያቄውን በጥያቄ መለሰች

አይቼዋለሁ ። ያ ራሰ በራሽን ሰመውዬ አይደለም? ”ጸጉሩ የሸሽው በዘር ሊሆን ይችላል እንጂ " እሱስ ገና ወጣት ነው

“ ማለቴ " ምልክቱን ነው እንጂ • ስለ ዕድሜው መግለጼ አይደለም ።

“ አዎ እሱ ነው ። ግን ከምኔው አየሽው ? አይ አንቺ !”አለችና በምስጢር ዐይነት ድምጿን ዝቅ አድርጋ “ አንድ ኮርስ ያስተምረኛል ” አለቻት ።

“ ታዲያ እንዴት ነው ? ” አለች ማርታ ከንፈሯን ነከስ አድርጋ ።

“ እንዴት ይመስልሻል ? ” አለችና ቤተልሔም የግራ ጎን ዳሌዋን በመስታወቱ ውስጥ እየተመለከተች ፡
ጠብ ነዋ ! ” አለቻት ።

ለማንኛውም ነገር ዕድልና አጋጣሚ ያስፈልጋል ? አለች ማርታ በልቧ ፥ “ አሁን ምናለበት ፈጣሪዬ አንዱን
መምህሬን ኣምጥቶ እዚህ ሰርግ ላይ ቢጥልልኝ !

ፊት ለፊት ቆማ ፥ በጎን በኩል ሆና ፥ ከኋላ በኩል አንግቷን አዙራ ፥ ባለችበት ራመድ ራመድ እያለች ቤተልሔም ራሷን መስታወት ውስጥ ተመለከተችና ፥ምን ይወጣልኛል ! ” በማለት ዐይነት በኩራት ፈገግ አለች።

ውፍረቷ አያስጠላባትም ። በአለባበስ ትሸፍነዋለች ።የትኛው ልብስ ከየትኛው ጫማና ሹራብ ጋር እንደሚሔድ
ጠንቅቃ ታውቀዋለች ። ሱሪ አታዘወትርም ከሰውነቷ ሁኔታ ጋር አዛምዳ ነው የምትለብሰው ። ገንጮቿ የተላጠ
ብርቱካን ነው የሚመስሉት ። ነገር ግን በምቾት አበጥ ስላሉ ጓደኞቿ “ ለጉንጮችሽ የጡት መያዣ ያስፈልጋቸዋል እያሉ ይቀልዱባታል ። ፎርሟን ለማስተካከልና ውፍረቷን
ለመቀንስ እንዳንድ ሰሞን ቁርስ መብላት ትተዋለች ። ነገር ግን ምሳ ላይ ደርሳ ነው የምትበላው ። የዩኒቨርስቲው ምሳ
አይስማማትም ። እንዲያው ነካ አድርጋ ነው የምትተወው ።ከዚያ በጓሮ በር የምትግባባቸው ቤቶች አሏት ። የሆድ ነገር ከሆነ የቅርብ ጓደኛዋንም አታስጠጋ ሹልክ ብላ ነው የምትሔደው ።

በቃሽ እንግዲህ ኤፍ ! ደሞ ለአስተማሪ ይህን ያህል ! ”አለች ማርታ በመሰላቸት አይነት ።

ቤተልሔም በልቧ " ባይሳካልሽ ነው” አለችና ሽቶ ከቦርሳዋ አውጥታ ጡቶቿ መሐል አርከፈከፈች ።ከነጋ አራተኛ ዜዊዋ መሆኑ ኔው ።

ተያይዘው ወደ ድንኳኑ ሲወጡ ቤተልሑም እንደ ልማዷ ወደ ሽንት ቤት ሔደች ። ማርታ አገሩ ገባትና ሣቅ አለች።

ከዚህ ሁሉ ትርኢት ርቃ ከዘፈኑ አካባቢ የቆየችው ትዕግሥት ፥ ማርታን ፈልጋት መጣችና ፤

“ አንቺ ማርታ " እረ እንሔድ ” አለቻት ። ።
“ የት ? ” አለች ማርታ ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር እንደ ጠየቀቻት ሁሉ ተደናግጣ ።

“ ወደ ካምፓስ ነዋ ! ምን ማለትሽ ነው? ” አለቻት ፥ የተከመረውን ጥናትና የተቃረበውን ፈተና በሚገልጽ ስሜት
ግንባሯን ኩምትር " ፊቷን ትክዝ አድርጋ ።

ትዕግሥት ሰርግ ቤት መቆየቱን አልጠላችም ። ብታድርም በወደደች ነበር ነገር ግን ሐሳቧ ተረጋግቶ መቀመጥ
አልቻለም ። እሷ ከዚህ ሙሽራ አጅባ ስታጨበጭብ ካምፓስ ውስጥ ተማሪው ጥናቱን ሲፈልጠው የታሪክ ትምህርቱን ሲለበልብው ። የፍልስፍና ትምህርቱን ሲሰነጣጥቀው የሒሳብ ትምህርቱን ሲያላምጠው በሐሳቧ ቁልጭ ብሎ እየታያት የመበለጥ ስሜት ተሰማት ። ከዚህ ሁሉ ደግሞ አቤል በምሳ ሰዓት ምግብ አዳራሽ ውስጥ በዐይኑ እንደሚፈልጋት ታውቃለች ከሄደችበት ተመልሳለች ወይስ አልተመለሰችም በሚል የቅናት ስሜት ። እና ወደ ካምፓስ መመለሷን እንዲያውቅ ራት ላይ እንኳን ልትታየው አሰበች ።

“ እሺ ቆይ ፥ ለማንኛውም ሙሽራ ይውጣ ” አለች ማርታ ። “ከዚያ መኪናም አይጠፋ ፤ካምፓስ ድረስ እንሸኝሻለን ።

ትዕግሥት እነሱ ወደ ካምፓስ እንድማይመለሱ ተረዱ ኧረ ግድየለም
እኔ በአውቶቡስ እሔዳለው አለቻት ።

“ እሺ ! ” አለች ማርታ ፡ ትዕግሥት የተናገረችውን ሳትሰማ ። ሐሳቧ ዐይኗን ተከትሎ ለማ ወደ ተቀመጠበት ሔዶ ነበር

ለማ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቤተልሔም ከዐይኑ ጠፍታበት አዳራሹን ግራ ቀኝ ሲማትር ፥ ድንገት ከጀርባው በኩል
“ ብሉ እስቲ ። ምን ጎደለ ? እዚህ አካባቢ ጠፋሁባችሁ አይደል? ” አለች ገና ከመድረሷ በሌላ መደዳ ስታልፍ የቆየች
ለማስመሰል

አብዛኛዎቹ መብላት አብቅተው ወደ መጠጡ አዘንብለው ነበር ። የተደጋገመው መስተንግዶ አስደንቆአቸው
እሷን በሙሉ ዐይናቸው ፡ እሱን ደግም በሰርቆት ተመልክተው ግብዣዋን በማመስገን ዐይነት እጅ ነሱ ።

የቤተልሔም የሙዚቃ መሳይ ድምፅ ጆሮውን ብቻ ሳይሆን ልቡን ጭምር ቢነካዉም ለማ ወደ ኋላው ዞር ብሎ
አልተመለከታትም ። መኩራቱ ሳይሆን መቆጠብ ነበር ።

ብርጭቆውን እንዳጎደለ ተመለከተችና እጅዋን በማጅራቱ በኩል አሳልፉ ከጠርሙሱ እየቀዳችለት

“ በጀርባህ በኩል በመቅዳቴ ይቅርታ ! ” አለችው ።

ምላስ እንደሌለው ሁሉ “ ምንም አይደለም በማለት ዐይነት ጭንቅላቱን ነቀነቀ ደረቷ ለአፍንጫው በጣም ሰለቀረበ የሽቶዋ መዓዛ ክፉኛ አወደው ። አሁንም ወንድነቱ የሽቶውን መዓዛ እየማገ ከእሱነቱ ውስጥ “ ዘራፍ ! ”ሲል ተሰማሁ

“ ምናባቷ
👍2🥰1
ትፈታተነኛለች ! ” አለ በልቡ ።

ብርጭቆው ቶሎ እንዳይሞላ ቀስ ብላ እየቀዳች ፡ “ ትቆያለ ወይስ ትሔዳለህ? ? ” ሰትል ሹክ አለችው ልቡ ክፉኛ ነጠረበት ለእሷ መልስ በመስጠት ፈንታ ቀስ ብሎ አጠገቡ የተቀመጠውትን ሰዎች ማትረ። እሷ ድምፅዋን ዝቅ አድርጋና ፈጥና ሌሎች እንዳይሰሙ አድርጋ ነበር የጠየቀችውኑ እሱ ቀና ሲል ከፊት ለፊቴ የተቀመጡት ሁልት ሴቶች አቀርቅረው ሲንሾካሾኩ ተመለከተ።

ምኗ ይሆን ? እንዴት ብትወደው ነው ? እያሉ ይሆናል የሚንሾካሾኩት ” ሲል አሰበ እጁ ሳይታዘዝ በራው ላይ ያቸፈቸፈውን ላብ ጠረገለት ሲያሳጣዉ ።

“ማለቴ” አለችው ቤተልሔም ፥ መልሱ ስለ ቆየባት።ጥያቄዋ ያደናገረው መስሏት ማማለቴ አጃቢ ሆነህ ነው የመጣኸው ወይስ ተጋብዘህ ? ”

ኧረ ተጋብዤ ነው አላት።

“ ቶሎ ሕያጅ ነሐ? ” ብላ መጠጡን ቀድታለት ጨርሳ ቀና ስትል ፊቷ ዕዝን ብሎ ነበር ። በዚያች ቅጽበት ዐይኗ
ውስጥ የሆነ ነገር አንብቦ “ በርታ ልቤ ! ” እያለ ግን ምን ዐይነት ዐይን ነው ያላት ! ” ሲል ተደነቀ ቤተልሔም ቆመችበት ተቁነጠነጠች ። ፊቷ ተለወጠ ። ለማ ቶሎ የሚሔድ ከሆነ የተጀመረው ነገር አሁኑኑ
ማለቅ አለበት ። ከአስተማሪነቱና ከተማሪነቱ መውጫ የሚገናኙበትን ቀጠሮ ማበጀት አለባቸው።ቤተልሔም ነገሩን በይደር መተወኑ አልፈለገችም ። ምናልባት ይህ አሁንበለማ ውስጥ ያበበው የሰሜት ተስፋ፡ ነገ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሐሜትን ፈርቶ ፥ ቁጥብነትን ፈልጎ ወይም በሌላ ምክንያት ሊጠወልግ ይችላል ። ይህ ከሆነ ደግሞ ወጥመዷ መክሸፉ ነው ። እና አሁኑኑ በአስቸኳይ ልቡ ሳያጋድል የስሜት እሳቱ ሳይበርድ ቀጠሮ ከአፉ ከወጣች ለመቼም ቢሆን ግድ የለም ። ቃሉን አጥፎ ወደ ኋላ እንደማይል ታውቃለች። ካወሩት እንዳደረጉት ይቆጠራል ። ነገሩ !እንደ ደስታዋና እንደ ድንጋጤዋ ጊዜ ሁሉ ፥ አሁንም ለጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ ለመስጠት ስሜቷ ስለ ተቁነጠነጠ ፥ ሽንቷ የመጣባት ፡ ውጥር አርጎ የያዛት መሰላትና እግሯን አኮራምታ ቆመች ።

የለማ ልብ ዐርፎ አልተቀመጠም ነበር ይንፈራንገጣል ። ከጥያቄዋና ከገጽታዋ ስሜቷን በሚገባ ተረድቷል ።አንዳች ሰይጣናዊ ስሜት ልቡን ገፋፋለትና እጅዋን ጎተት አርጎ ፡ ዝቅ ባለ ድምፅ
ልሔድ ስል አነጋግርሻለሁቻ ”አላት ።

“ እ ? ” ሳትሰማው ቀርታ ሳይሆን " ጆሮዋን ማመን አቅቷት ነበር ።

አልደገመላትም ።

ቶሎ የከፋው ልቧ ቶሉ ተደሰተ፤ እየተፍነከነከች ከሩጫ ባላነሰ እርምጃ ወደ ሽንት ቤት ሔደች ።

ጠረኗ ግን እዚያው ለማጋ ቀርቶ ነበር ። ወትዋች ህሊናው ደረቱን ገልብጦ ቡጢ ጨብጦ ግንባሩን አኮማትሮ የቤተልሔምን ጠረን ላለማሽተት አፍንጫውን ደፍኖ እሱነቱ ውስጥ ግትር ብሎ ቆሞ ተመለከተውኑ ሁለት ለማዎች!

ምንድን ነው ነውሩ ? ”መምህር የሚያስተምራትን ልጃ ገረድ ቢወድ ከሚወዳት ተማሪው ጋር ቢዳራ ምንድነው ነውሩ ?”

መውደድማ ባልከፋ ነበር ።ነገር ግን የወደደ ቸር ነው ። እና ማርክ አሰጣጥ ላይ , . . ደም የደደ ልብ ወዳጅ ሲወድቅ ዝም ብሎ አይመለከትም ።

እና ታዲያ?
እናማ ምርጫው ሁለት ነን !
"ኤጭ

💥ይቀጥላል💥
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ (MD)

አልጋችን ውስጥ ገብተን ተኛን፡፡ እንቅልፍ ቶሎ አልወሰደኝም፡፡ከነጮቹ ጋር ያደረኩት ስሜታዊ ድርጊት ምን እንደሆነ ማስብ ጀመርኩ፡፡እንዴት ማሂ እያለች እንደዚህ አይነት ስሜት ይሰማኛል? እንዴት
ቢያንስ ማሂ ፊት ስሜቴን መደበቅ አቃተኝ? ከማሂ ጋር ተኝቼ ውስጤ
ኢቫን በወሲባዊ ስሜት ያስባል፡፡ ምን አይነት እብደት ነው?፡፡ እንቅልፍ
ወሰደኝ፡፡

ጥዋት ተነስተን ተጣጠብንና ቁርስ በልተን ሁለት ሰዓት ላይ ወጣን፡፡ ባጃጅ ይዘን፣ አስጎብኚ ድርጅቶች ጋር ሄድን፡፡ የዶርዜ ሎጅ መጎብኘት እንደምንፈልግ ነገርነው፡፡

“ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ?”

“አዎ!”

“የሞላ መኪና አለ፡፡ ሂሳብ ክፈሉ።” የተጠየቅነውን ክፍያ ከፈልን፡፡ ባለድርጅቱ ከሌላ ልጅ ጋር አገናኘን፤

“ኑ፣ ፍጠኑ፡፡ እድለኛ ናችሁ፡፡”ተከተልነው።

“ከዚህ ይርቃል እንዴ?”

“ብዙም አይርቅም፡፡ ሰላሳ ኪ.ሜ. አካባቢ፡፡”

መኪናው ጋር አደረስን፡፡ እውነቱን ነበር፡፡ እንዳለው ሚኒባሱ ሞልቷል፡፡ ሁሉም በሚባል መልኩ፣ አብዛኛው ጎብኚ ፈረንጆች ናቸው።

ክፍት የነበረው የመጨረሻ ወንበር ላይ ሄደን ተቀመጥን፡፡ ወዲያው መኪናው ጉዞውን ጀመረ፡፡ የምናልፍበት ቦታ ሁሉ አረንጓዴ ነው።በየመንገዱ ማይሸጥ የፍራፍሬ አይነት የለም፡፡ ሙዝ፣ ሎሚ፣ አቡካዶ፣መንደሪንና የመሳሰሉት፡፡ የቦታው አረንጓዴነት፣ ከመሬቱ አቀማመጥ
ጋር እጅግ ውብ፣ መንፈስን የሚያድስ ነው፡፡

ሃኒ በምታየው ነገር ሁሉ፣ “ኦ... ሎርድ፣ እንዴት ያምራል!” ትላለች፡፡

“ምድራዊ ገነት ነች ያልኩሽ ዋሸሁ?”

“በፍፁም...!! እውነትም ምድራዊ ገነት፡፡ እንኳን እዚህ መጣን፡፡ሎርድ...ያቢዬ በናትህ ፎቶ ላንሳ ቦታ ቀይረኝ፤”

“እንዴ፣ እኔ አላነሳም እንዴ?”

ካሜራዬን አውጥቼ ማንሳት ጀመርኩ፡፡ ሃኒ “ዋው..፣ ይሄን ተራራ አንሳው፣ ሰማዩን አብረህ አስገባው፣ ዛፉን በከፊል...” ትላለች።

መልሳ ደግሞ፣ “ወይኔ ይሄኛው ሲያምር፣ እስቲ እኔም ላንሳ በናትህ፣” ተቁነጠነጠች፡፡ ቦታውን ቀየርኳት፤ ካሜራውን ሰጠኋት፤ ብዙ ፎቶዎችን
አነሳን፡፡ እያበላለጥን፣ እየተፎካከርን፣ እያደነቅን፣ ተደሰትን፡፡ እጅግ የሚገርም ብዙ ቅፅበታዊ ደስታዎች፡፡ በተፈጥሮ ተማርከን፤ ተዋጥን፣በደስታ ተንሳፈፍን፡፡ አስጎብኚያችን “አሁን ወደ ዶርዜ መንደር
ደርሰናል፤” ሲል ከሄድንበት የራሳችን የደስታ አለም ተመለስን፡፡አይተን፣ ተደስተን፣ አንስተን ግን፣ አልጠገብንም ነበር፡፡

ከመኪናው እንደወረድን፣ ሃኒ፣

“ዋ...ይ..!” ብላ ጮሃ ተጠምጥማብኝ፣ “እየው ያቡዬ” ትለኛለች፣ እጆቿን ወደ ፊታችን ቀስራ፡፡

“ኦ...፣ ማይ ጋድ! ምንድነው...? ሰው ነው?››

“ኖ ኖ...፣ እዚህ አሳ በብዛት ስላለ፣ አሳ ነው ሚሆነው::በአሳ ቅርፅ ነው የሰሩት፡፡ ሎርድ!”

“በጣም ግዙፍ እኮ ነው፡፡” ማንንም እየሰማን አይደለም፤ ቀስ ብለን እየተጠጋነው ነው፡፡ ምን አይነት ትልቅነት ነው? ምን አይነት ከፍታ ነው...?

“ጭንቅላት አለው፤ አፍንጫ አለው፤ አፍ አለው፤ ጆሮ አለው፤”ሃኒ በስሜት ሆና ትቆጥራለች፡፡

“ሃኒዬ ልንገርሽ? ይሄ የዝሆን ቅርፅ ነው፡፡”

“የስ..!፣ አሁን በትክክል ተመልሷል፡፡” ፈነጠዘች...!

“እስቲ ዝም ብለሽ እዪው:: ግዙፍነቱ፣ ወደ ላይ ያለው ከፍታ፣ኩንቢው፣ በረንዳው ነው:: አፉ በር ነው:: ጆሮዎቹ መስኮቶች ናቸው።
“... ፣ ሎርድ!፣ ምን አይነት ጥበብ ነው...! ምን አይነት እውቀት ነው...? ልቤ ልትቆም ሳግ ተናነቀኝ፡፡”

“ኧረ ፎቶ ሳንነሳ...!” ጮኸች ሃኒ፡፡

ውስጡ ገባን፤ እየዞርን አየነው፤ተሻሸነው፣ ታቀፍነው፣ እጅግ በጣም ብዙ ፎቶዎች ተነሳን፡፡ በተመለከትነው ኢትዮጲያዊ ድንቅ ጥበብ ነብሳችን ሃሴትን አደረገች፡፡ ፈረንጆቹ እንደ ተአምር ተደንቀው
ይመለከቱታል። ፎቶ ያነሱታል፡፡ የከተማ ህንፃዎች ለምን እንደዚህ አይነት የስነ ህንፃ ዲዛይን እንደማይጠቀሙ ገረመን፡፡ የምንችለውን ያክል ተዟዙረን አየነው:: በፎቶ ማስቀረት የቻልነውን ያክል አስቀረን፡፡ዶርዜዎች ለጥበብ የተፈጠሩ ህዝቦች ናቸው!፡፡ መመለስ ስላለብን
ተመለስን፡፡ ነብሳችን ግን እዛው ቀረች፤ አልተመለሰችም፡፡ ስላየነው ድንቅ ጥበብ ብቻ ስናወራ ተመልሰን አርባ ምንጭ ገባን፡፡ ደስታችን፣እርካታችን ቅጥ አጣ፡፡ እራት በላን፣ ከደስታችን የተነሳ የድካምም ስሜት አልተሰማንም፡፡ በየመጠጥ ቤቱና በየጭፈራ ቤቱ መዝናናት ጀመርን፡፡

እየጠጣን፣ ጨፈርን፣ ቤት እየቀያርን ተዝናናን፡፡ ደስ የሚል ልዩ ስሜት፡፡ እኩለ ለሊት እየሆነ ነው፡፡ የመጨረሻ አንድ ቤት እንይ ብለን የገባንበት ቤት፣ ደረጃውን የጠበቀና በቅርቡ እንደተከፈተ
የሚያስታውቅ፣ ሞቅ ያለ ጭፈራ ቤት ነው፡፡ ሙዚቃዉ ደርቷል፡፡በሚያምር የጭፈራ መብራቶች ታጅበው፣ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚጨፍሩ ሰዎች፣ አለባበሳቸውም ሆነ ውበታቸው አትለፉኝ፣
አትለፉኝ የሚሉ ቆነጃጂት ቤቱን ሞልተውታል፡፡ ከሃኒ ጋር እየተሽሎኮሎክን ወንበር ፈልገን ተቀመጥን፡፡ ሁለት ደብል ብላክ ሌብል አዝዘን፣ ሂሳብ በቅድሚያ ከፍለን እየጠጣን፣ ከቤቱ ጋር እስክንግባባ ወንበራችን ላይ ሆነን በቀስታ መደነስ ጀመርን፡፡ ስንገባም ሞቅ ስላለን፣ከቤቱ ጥሩ የሙዚቃ ምርጫ ጋር ተደምሮ የሞቀ ጭፈራ ጀመርን፡፡
ድንገት እነ ኢቫን ከበሩ በስተ ግራ በኩል ሆነው እንደ እብድ ሲደንሱ አየሁ፡፡ ከሃኒ ጋር እየጨፈርኩ፣ ልቤ ግን ኢቫ ጋር ሄዷል፡፡ ለምክንያት ሽንት ልሽናና ልምጣ ብዬ ወጣሁና ስመለስ ኢቫን አስደንሼያት
ተመለስኩ፡፡ ትንሽ ቆይቼ፣ ወደነሱ
ጋር ቦታ እንድንቀይርና እንድንቀላቀል አደረኩ፡፡ ደጋግሜ ኢቫን ወሲብ ቀስቃሽ ዳንስ አስደነስኳት፡፡ እያስደነስኳት እንደተማረኩባት ነገርኳት፡፡ እብደቱ
ብሶብኛል፡፡ ሃኒና ወፍራሟ ፈረንጅ ብዙ ሰዓት አብረው ይደንሳሉ፡፡ ከኢቫ
ጋር ተግባብተናል፡፡ አልጋ ይዜ ልምጣ አልኳት፡፡ አልተግደረደረችም፡፡
ይዤ መጣሁ፡፡

ውጪና ጠብቂኝ፡፡” በጆሮዋ አንሾካሾኩላት፡፡ በተራዋ ለጓደኛዋ
አንሾካሹካ ወጣች፡፡ ትንሽ ቆይቼ እኔም፣

“ሃኒዬ መጣሁ፣ ሽንት፡፡” ብያት ልወጣ ስል

“ያቡ ሰክረሀል ጠንቀቅ በል፧” አለችኝ፡፡

“ሃኒዬ፣ እኔን በዚች ሰክረሃል?”

“እሺ ለማንኛውም ጠንቀቅ በል፡፡”

“እሺ!” ብዬ ወጣሁ፡፡ እንደውጣሁ ኢቫን ወደ ያዝኩት ክፍል እያከነፍኩ ወሰድኳት፡፡ የተሰረቀ ነገር ሆኖብኝ አንገበገበኝ፡፡ በቁማችን ጀመርነው ልብሳችንን ተጋግዘን
አወልቀን፣ አልጋው ላይ ተወረወርንበት፡፡ ለዘመናት የተጠራቀም፣ የወሲብ አምሮት ያለብኝ እሰኪመስል፣ ሀይልና ስግብግብነት የተቀላቀለት ወሲብ ተዋሰብን፡፡ስንጨርስ ከውስጤ የወሲብ ሰንኮፍ ተነቅሎ የወጣ መስሎ ተሰማኝ፡፡
ስካሬ ለቀቀኝ፣ በምትኩ ሀፍረት ወረረኝ፡፡ ልብሴን በፍጥነት ለብሼ ቻው እንኳ ሳልላት ልወጣ፣ በሩን ሳብ ሳደርገው፣ አልተቆለፈም፡፡ ምን አይንት አብደት ነው፡፡ ሃኒን እንዴት ብዬ ነው ማያት፡፡ ቆይተን ይሆን? ትጠረጥረኝ ይሆን?፣ በፍጥነት ወደ ውስጥ ገባሁ፡፡

“ቆየሁ ሃኒዬ?”

“አይ ትንሽ፡፡ ደህና ነህ አይደል?”

“ደህና ነኝ፡፡ ሸንቼ ስመጣ ኢቫ ሲጋራ እያጨሰች አገኘኋት።

ንፋስ ለመውሰድ ትንሽ አወራኋት፡፡ የመጣልኝን ቀባጠርኩ፡፡

“አይ እንኳን ንፋስ ወሰድክ፡፡ አሁን ስካርህ የለቀቀህ ትመስላለህ፡፡” በአሽሙር እየተናገረችኝ መሰለኝ፡፡

“ሰከርክ ሰከርክ አትበይኝ እኔ ድሮም አልሰከርኩም፡፡” በእኔ ብሶ ኸኩኝ፡፡ ድካም ተሰምቶኛል፣ ፀፀት ተጨምሮበት እንደቅድሙ እየተጫወትኩኝ አደለም። አሁን የምፈልገው መውጣትና መሄድ ነው። ድንገት ቤቱ ውስጥ ትርምስና
1👍1
ጫጫታ ተፈጠረ። የብርጭቆ መሰበር ድምፅ ለመውጣት የሚደረግ ትርምስ ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልኩም "ኑ..ኑ...ውጡ ብዬ በሁለት እጆቼ ሶስቱንም እየገፈታተርኳቸው ወደ ውጨ ወጣን ግርግሩም ጫጫታውም ድንጋይ ውርወራውም ተከትሎን ውጪ ወጣ ከበሩ ፈቀቅ ብላ የቆመች ባጃጅ አየሁ ።

"ኑ ግቡ ኑ ግቡ ጮሁኩኝ።

ሾፌሩ የታል ሃኒ ጠየቀች። በአጠገባችን ምን የመመያክል ድንጋይ መሬት ነጥሮ አለፈ።እስካሁን አልተፈነከትንም።

ዝም ብላችሁ ግቡ ጮኽኩና ገፈታትሬ አስገባኋቸው እኔ ጋቢና ገባሁ ሹፌሩ አይቶን አልመጣም።ከአሁን አሁን ምን የሚያህል ድንጋይ አንዳችንን ሲተረክከን እየተሰማኝ ነው። ይሄ ሁሉ የኔ ሃጥያት ነው ዛሬ አይቀርልንም ብዬ አሰብኩኝ። በፍጥነት ከዚህ ቦታ መጥፋት አለብን። መሪው ላይ ቁልፍ መፈለግ ጀመርኩ። የለም ደንግጬለሁ። በፊልም ኤሌክትሪክ በጣጥሰው የቆመ መኪና አስነስተው ሚነዱት በአእምሮዬ ብልጭ አለብኝ። ጎንበስ ብዬ ገመድ መፈለግ ጀመርኩ። ከታች ብዙ ገመዶች አየሁ። የቱን ነው የምቆርጠው? ዝም ብዬ በደመነብስ ያገኘሁትን ገመድ እየጎተትኩኝ እታገላለሁ ቀና ስል ግርግሩ ቀንሷል።

“ምን እያደረክ ነው?” የሚል ድምፅ ሰምቼ ቀና ስል፣ ግዙፍ ቅልብ ጎረምሳ ፊትለፊቴ ቆሟል፡፡ ልቤ ፀጥ ልትልብኝ ነው፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍21
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“ምን እያደረክ ነው?” የሚል ድምፅ ሰምቼ ቀና ስል፣ ግዙፍ ቅልብ ጎረምሳ ፊትለፊቴ ቆሟል፡፡ ልቤ ፀጥ ልትልብኝ ነው፡፡

“ዕቃ ወድቆብኝ እየፈለኩ፡፡”

“መጀመሪውኑ ባጃጄ ውስጥ ምን ፈልገህ ገባህ ነው የምልህ?”

“ባለ ባጃጁ አንተ ነህ? ጭፈራው ቤት ነበርን፡፡ ብጥብጥ ሲነሳ ኮንትራት ፈልገን ስንመጣ የለህም፡፡ እንድታደርሰን ቁጭ ብለን እየጠበቅንህ ነው፡፡” ብዬ፣ ከሾፌሩ ወንበር ላይ ቀስ ብዬ ጠጋ አልኩና
ቦታውን ለቀኩለት። ከኋላ ዞር ብሎ ሲመለከት ብቻዬን እንዳልሆንኩ
ተገነዘበ፤

“ወዴት ናችሁ?”

“ቱሪስት ሆቴል።”

“መቶ ብር ትከፍላላችሁ፡፡”

“ችግር የለውም፡፡” ኡፈይ አልኩ በውስጤ፡፡

ቁልፉን አውጥቶ ባጃጇን ለማስነሳት ሞከረ፣ ምንም ድምፅ የለም፡፡ ደጋግሞ ሞከረ፣ ምንም የለም፡፡ ደነገጥኩ፡፡ እኔ ስጎትት ወደ የነበረበት ጎንበስ ብሎ አየ፡፡ ላብ አጠመቀኝ፡፡ ስካሬ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ገመድ በጥሼ ይሆን እንዴ? የሆነ ነገር ነካካ፡፡ መልሶ ቁልፉን ሞከረ፡፡ ባጃጇ
ተረክ ብላ ተነሳች፡፡ ተመስገን...፣ ከግንባሬ ላይ ላቤን ጠራረኩ፡፡

እንግዶች ናችሁ?”

“አዎ፡፡”

“አርባ ምንጭ ሰላማዊ ከተማ ነች፡፡ የቅድሙ ፀብ አጋጣሚ ነው፡፡ በሴት ተጣልተው ነው፡፡ አትደንግጡ፡፡ እንደዚህ ተፈጥሮ አያውቅም፡፡ ዘና በሉ፡፡ ከፈለጋችሁኝ ስልኬን ውሰዱ፡፡”
“እሺ እናመሰግናለን፡፡ ስልክ ቁጥርህን ስጠን፤” አልኩት፡፡ሆቴላችን አድርሶን፣ ሂሳብ ከፍለን ቁጥሩን ተቀብለን ወረድን፡፡ ባጃጁ ከሄደ በኋላ፣ ሦስቱም ያደረኩትን እያስታወሱ፣ ያሽኩብኝ ጀመር፡፡

“ቆይ ባጃጇን ምን ልታደረጋት ፈልገህ ነው፣ እንደዛ የተንፈራፈርከው?” ከት... ከት... ከት

“በተለይ ባጃጇ በቁልፉ አልነሳም ስትልማ የደነገጥኩት ድንጋጤ... ” ከት... ከት ከት..

“ደግሞ እኮ ተው ሲባል አይሰማም፡፡” ከት ከት...

“እኔማ ይሄ ልጅ፣ ዛሬ እስር ቤት አሳደረን እያልኩ ነበር፡፡” ከት..ከት..

የሰራሁት የእብድ ስራ መልሶ እኔንም ያስቀኝ ጀመር፡፡

አብሪያቸው እስቃለሁ፡፡ እስኪደክማቸው፣ እንባ እሰኪወጣቸው ሳቁብኝ፡፡

“ኧረ ሰዓቱን እዩት፡፡ ከለሊቱ ስምንት ሰዓት አልፏልኮ፡፡” አልኩኝ እንደደከመው ሚስቁብኝን ለማስቆም፡፡ ወደ ክፍላችን ገባን፡፡ ልንተኛ ስል፣ ቅድም ከነጮ ጋር ባደረኩት የተሰማኝ ፀፀት ጠፍቶ፣ ስሜቴ.
እንደገና ሲያገረሽ ተሰማኝ፡፡ ምክንያት ፈልጌ መውጣት ፈለኩ፡፡ ምን ብዬ እወጣለሁ፡፡ ሽንት ቤቱ እዚሁ ነው፡፡ ሌላ ምን ምክንያት እፈጥራለሁ፡፡ ኢቫም እንደኔው እያሰበችኝ ነው ብዬ ገመትኩ፡፡ ጆሮዬን አቁሜ ውጪ ያለ የተለየ እንቅስቃሴ ማዳመጥ ጀመርኩ፡፡ በር ላይ የቆመ ሰው እንዳለ ይሰማኛል፡፡ ሃኒ ተኝታለች፡፡ ቀስ ብዬ ከአልጋ ውስጥ
ወጣሁ፡፡ ከአልጋው ብድግ ስል፧ “እንቅልፍ እንቢ አለህ እንዴ ያቡ”
አለች ሃኒ፡፡ አልተኛችም፡፤

“አይ ይሄን ቢራ ልፈን ሽንቴ..”

ለይስሙላ ሽንት ቤት ደርሼ ተመልሼ ተኛሁ፡፡ በንጋታው በጣም የድካም ስሜት ተሰማን፡፡ ከአልጋችን ላይ አርፍደን ተነሳን፡፡ ቁርስ እንደነገሩ ቀማመስን፡፡ ሁለታችንም የምግብ ፍላጎት አልነበረንም፡፡ ሃኒም ከኔ እኩል ድካም ተሰምቷታል፡፡ ከሰዓት በአብዛኛው እክፍላችን ተኝተን አሳለፍነው፡፡ አስራ ሁለት ሰዓት አካባቢ ተነስተን ከክፍላችን ወጣን፡፡

“ሃኒዬ እርቦኛል፡፡”

እኔም ልልህ ነበር፡፡ የሆነ ነገር እንብላ፡፡”

“ምን እንብላ?”

“አሳ እንዳይሆን እንጂ፣ የፈለገከውን፡፡”

“ከአሳ ውጪ እንዳላልሽ፣ ሰለቸሽ?”

“ሳይሆን፣ ቅድመ ጥንቃቄ ነው፡፡”

ወጥተን ምሳችንን እንደነገሩ በላን፤ ቡና ጠጥተን ሰውነታችንን ለማፍታታት ከሆቴላችን ወጣን፡፡ ስለ ሀገሩ ለምነት እያወራን፣ በትናንትናው እብደት እየሳቅን፣ ነገ ነጭ ሳር ፓርክን ለማየት እያቀድን
የአርባ ምንጭን የምሽት ንፁህ አየር እየማግን፣ በእግራችን ብዙ
ተንቀሳቀስን፡፡
በንጋታው በጥዋት የበቀደሙ አስጎብኚ ድርጅት ጋር ሄድን፡፡

“ሄይ እንዴት ነህ አለቃ?" አልኩት፡፡

“አለሁ፤ አለሁ...፤ እንዴት ናችሁ ዘመዶች?"

“ይመስገነው! ይኸው ያንተ ናፍቆት መልሶ አመጣን”

“እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ ምን እንታዘዝ ” አለ እጆቹን እያሸሽ፡፡

ነጭ ሳር ፓርክን ማየት ፈልገን ነበር፡፡ እንዴት እንደከረመ ጠይቀነው እንምጣ?”

“ታዲያ ምን ችግር አለ፡፡ እንደ ንጉስ አስጎብኝተን እንመልሳችኋለን፡፡ በጀልባ ይሁንላችሁ በመኪና?”

“በጀልባ” አለች ሃኒ ከአፉ ነጥቃ፡፡

“በጀልባ፣ ሶስት ሺህ ብር ብቻ ያስከፍላችኋል፡፡”

እችን ትወዳለች.... እኛ አንተን ደንበኛ ብለን መርጠንህ ብንመጣ፣ ጭራሽ ታሰወድዳለህ?”

“እንደውም ደምበኝነታችሁን ብዬ ነው፡፡አልተወደደም፡፡”

“እንዴ! በጣም ውድ ነው እንጂ፣ በጣም!”
“እንደዛ ነው ዋጋው፡፡ ጀልባው አራት ሰው ነው የሚጭነው፡፡

ሁለት ሰው ካገኛችሁ ሂሳቡን ተካፍላችሁ መሄድ ትችላላችሁ፡፡”

“እኛ ሰው ከየት እናመጣለን? ባይሆን እሺ እሱን ፈልግ፡፡”

“እዛ ጋር የቆሙት ሁለቱ ነጮች፣ እንደናንተው ዋጋው በዛ ብለው ነው፣ ካልደበራችሁ አናግሯቸው፡፡” አለኝ ፈንጠር ብለው ወደ ቆሙ ሁለት ፈረንጆች እየጠቆመኝ፡፡ አውርቶ ሳይጨርስ፣ ቆመው ከነበሩት ፈረንጆች ወንድየው ወደኛ መምጣት ጀመረ፡፡ ሰላምታ
ሰጠንና፤

“ወደ ነጭ ሳር መሄድ ፈልጋችሁ ነው?” አለን በእግሊዝኛ፡፡

አዎ፡፡ ግን ዋጋው በዛብን፡፡”

“እኛም ዋጋው በዝቶብን ነው፡፡ ዋጋውን ተካፍለን አብረን ብንሄድ፣ ይስማማችኋል?”

“ጥሩ ነው፡፡ እንደዛ ይሻላል፡፡” አልኩ ሃኒን እያየሁ፡፡

መስማማቷን ጭንቅላቷን በመነቅነቅ ገለጠችልኝ፡፡

ሦስት ሺህ ብሩን እኩል አዋጥተን ትኬት ቆረጥን፡፡ ወደ ሀይቁ ለመሄድ፣ ከከተማ ለታክሲ አራት መቶ ብር ተጠየቅን፡፡ ፈረንጆቹ ቀድመው መረጃ ሰብስበዋል፡፡ በባጃጅ በሁለት መቶ ብር መሄድ
እንደሚቻል ነግረውን፣ ባጃጅ መጠበቅ ጀመርን፡፡ የከተማው ዋና መንገድ
ላይ ቆመን፣ ባጃጅ እየጠበቅን፣ በመንገድ ላይ ጫት እየቃሙ ሚያልፉ ወጣቶችን ፈረንጆቹ ተመልክተው፣

“ወጣቶቹ ሚበሉት ቅጠል ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁ፡፡

“ጫት ይባላል፤” አልኳቸው፡፡

“ያለው ጥቅም ምንድን ነው?”

“ያነቃቃል፡፡ ደስተኛ ያደርጋል፡፡”

“እንዴት ያነቃቃል?” ሰውየው አጥብቆ ጠየቀኝ፡፡

“ማለት?”

“ውስጡ ያለው ንጥረ ቅመም ምንድን ነው? ሴሮቶኒን /የደስታ ንጥረ ቅመም/ አለው?”

“ስለ ሴሮቶኒን ንጥረ ቅመም ብዙም አላውቅም፡፡ ግን ካቲን የተባለ ቅመም አለው ሲባል ሰምቻለሁ፡፡”

በተባለው ዋጋ ወደ ሃይቁ የሚያደርሰን ባጃጅ አግኝተን ጉዟችንን ጀመርን፡፡ መንገዱ በጣም ቁልቁለታማ፣ ጥምዝምዝ የበዛው፣ ግማሽ ፒስታ በሚባል ደረጃ፣ የፈራረሰና ጠባብ መንገድ ነው፡፡ ወደ ሀይቁ ስንቀርብ፣ መንገዱ ጭራሽ ጭቃ የበዛው ረግረጋማ ሆነ፡፡ ከዚህ በፊት ሰምጠው የተያዙ ተሽከርካሪዎች ጎማ ቅርፅ ይታያል፡፡

“ሌላ የተሻለ አማራጭ መንገድ የለም?” አለች፤ አብራው ያለችው ፈረንጅ፡፡

አይመስለንም፤” አልኳት።

በጭቃው መንገድ ውስጥ ትንሽ እንደሄድን፣ ባጃጁ ቆመና እዚህ
ጋር ነው መውረጃው አለን ሹፌሩ፡፡ ሀይቁ በትልልቅ ዛፎች ተከቦ ይታያል፡፡ ወደ ፓርክ እየገባን እንደሆነ ሚያሳይ፣ አንዳችም ምልክት የለም፡፡ ሂሳብ ከፍለን ወረድን፡፡
“ምልክት ሚሆን መግቢያ በር የለውም እንዴ?” አለችኝ ሃኒ፡፡

“ሌላ መግቢያ ይኖረው ይሆናል፡፡”

“እንዴ፣ ቢኖረውስ፣ ቱሪስት ሚገባበት እስከሆነ ድረስ፣ ምልክት መኖር አለበት፡፡ በዛውም
👍1
እኮ ማታወቂያ ነው::”

“እሱስ እውነትሽን ነው፡፡ ይሄን ሚያክል እድሜ ያለው ታዋቂ ፓርክ፣ ለፎቶ መነሻ እንኳን ሚሆን ምልክት ማጣት...”

ሃይቁ ላይ በሚጠብቀን የሞተር ጀልባ ተሳፍረን፣ ከጫሞ ሃይቅ የሚነሳውን፣ ነፍስን የሚያድስ ንፋስ እያጣጣምን፣ አስጎብኚያችን ስለ እግዜር ድልድይ እየነገረን፣ ጉማሬና አዞ እያሰየን፣ ሃይቁን አቋርጠን ነጭ ሳር ፓርክ ደረስን፡፡ ከጀልባው ወርደን በጫካ ውስጥ በእግር
እየተጓዝን ፓርኩን ጎበኘን፡፡ አንዳንድ እንስሳቶችን ለማየት በጫካ ውስጥ
በእግር እርቆ መጓዝ የግድ ነው፡፡ የሜዳ አህያ፣ የሜዳ ፍየል፣ ሚዳቋና ሌሎች የዱር እንስሳትን እስኪደክመን ድረስ እየተዟዟርን ጎበኝን፤ ፎቶ አነሳን፡፡ ውሃ ጥም ሊገለን ሆነ፡፡ የሚሽጥ ውሃ የፓርኩ መግቢያ ላይ ይኖራል ብለን ሳንይዝ ነው የመጣነው፡፡ ከከተማው ከወጣን በኋላ
አንድም ቡና ሚጠጣበትም ሆነ ውሃ ሚሽጥበት ሱቅ የለም፡፡ በውሃ ጥም ተቃጠልን፡፡ በስተመጨረሻ፣ እረሃቡም ተጨመረና ድካሙ ጠናብን፡፡ ወደ ጀልባችን ተመልሰን፣ ውሃውን እየቀዘፍን ወደ አርባ ምንጭ ተመለስን፡፡ በደንብ መረጃ ስላላገኘን ድካሙና ውሃ ጥሙ
ቢያስቸግረንም፣ የዱር እንስሳቱን ማየት ልዩ ስሜትን ይሰጣል፡፡መንፈስን ያድሳል፡፡ ረጅሙ የጀልባ ጉዞም ተጨማሪ የደስታ ምንጭ ነው፡፡

ከአምስት ቀናት ጉብኝት በኋላ፣ ውቢቷን አርባ ምንጭ ተሰናብተናት ጉዞ ወደ ቢሾፍቱ፡፡ ስንመለስ ያነሳናቸውን ፎቶዎች
እያየን፣ ስለ ምድራዊዋ ገነት በመደነቅ ስናወራ፣ እንዲህ ቢሆን፣ እንዲህ
ቢደረግ የበለጠ ውብ ይሆን ነበር፣ እያልን ሳይታወቀን ሻሸመኔ ደርሰን አደርን፡፡ ማታ ስንተኛ ኢቫ ትዝ አለችኝ፡፡ ያደረግኩት እብደት፣ የመዝናናቱ አንዱ ደስ ሚል ልዩ አጋጣሚ አድርጌ አሰብኩት፡፡ ሃኒን
እወዳታለሁ፡፡ ያ ስሜት እንዴት ተሰማኝ? እንዴትስ ደፍሬ አደረኩት?
አሁንስ ለምን ትዝ አለችኝ? የእርሷ ነገር አልወጣልኝም ማለት ነው?ትናንት ሊሄዱ ሲሰናበቱን፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ነበር ቻው ያልኳት፡፡በሃኒ ላይ እንዲህ ማድረግ የለብህም፧' የሚለኝ ጭንቅላቴ፣ አሁን ስልክ መለዋወጥ ነበረብህ፤ ይለኛል፡፡ ሳላስበው እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

ጥዋት ከሻሸመኔ ተነስተን ጉዞ ከጀመርን ጀምሮ፣ ሃኒ ቅዝቅዝ ብላለች፡፡ ወሬ ለመጀመር ብሞክርም በአጭሩ ትቆርጥብኛለች፡፡ ፊቷን አየሁት፤ ደብሯታል፡፡ በሃሳብ ትሄዳለች፡፡ ምን አጥፍቼ ነው? ማታ በእንቅልፍ ልቤ ኢቫ እያልኩ ቀባጥሬ፣ ሰምታኝ ይሆን እንዴ? ጉድ ፈላ፡፡ ግን እንደሱ ቢሆን ትጠይቀኝ ነበር፡፡

“ምን ሆነሽ ነው ሃኒዬ?”

“ምን ሆንኩ?”

“እንጃ፣ ከጥዋት ጀምሮ ደብሮሻል፡፡ ዝም፣ ቅዝዝ ብለሻል፡፡”


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍21
#ሰመመን


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

በገለጻው አዳራሽ የተሰበሰቡት ተማሪዎች ከትከት ብለው ሣቁ ። አቤል ግን ሌክቸረሩ የተናገረውን ቀልድ ስላላዳመጠ ለመሣቅ ዕድል አላጋጠመውም ። በአዳራሹ ሣቅ
ተኮርኩሮ ከሐሳቡ ከነቃ በኋላ አጠገቡ የነበረውን ተማሪ ስለ ሁኔታው እንዲያስረዳው ጠየቀው ።

ምንድነው? አለወ ድንግርግር ባለ ስሜት
አልሰማኸውም እንዴ ? ” ብሎ ተማሪው ቀልዱን ሊነግረው ሲሞክርም ሣቁን መግታት አልቻለም ነበር ።አቤል ደግሞ የተማሪውን ሣቅ አስጨርሶ ቀልዱን ለማዳመጥ ትዕግሥት አልነበረውም ። በተሰላቸ ስሜት ቸልብሎ ተወው ።

ሰኞን አይወደውም ብላክ መንዴይ ይለዋል ።ቅዳሜና እሑድን መንፈሱንም ባይሆን አካሉን አሳርፎ ሰኞ ደብተሩን ይዞ ወደ ትምህርት ክፍል ሲገባ አንዳች የጥላቻ ስሜት ያድርበታል ። እንዲያው ለስሜቱ ይቅርታ ለመስጠት ያህል ቀናቱን በመውደድና ባለመውደድ ይከፋፍላቸዋል
እንጂ ፥ ልቡ ውስጥ ለትዕግሥት ቦታ ከሰጣት ጊዜ ጀምሮ የመምህሮቹን ገለጻ በሙሉ ስሜት ያዳመጠበት ጊዜ የለም ።
ሐሳቡ ውጭ እየከነፈበት አካሉ ብቻ ነበር ክፍሉ ውስጥ የሚቀመጠው ።

ከሌሎቹ ሁሉ ይህን ክፍለ ጊዜ ይወደው ነበር ።የፍልስፍና ተማሪዎቹ ሳይወስዱ ያለፉትን አንድ የሳይኮሎጂ ኮርስ ከሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር የሚወስዱበት ክፍለ ጊዜ በመሆኑ ፥ ከትምህርቱ ይልቅ አዳራሹ ሞልቶ ማየቱ ያስደስተዋል ። ምክንያቱም ሌሎቹን ኮርሶች የሚወስደው ከስድስቱ ተማሪዎች ጋር ብቻ ነው ። በቁጥር ማነሳቸው ደግሞ
መምህሩ የተማሪዎቹን ስሜትና ሁኔታ በቀላሉ እንዲከታተል ይረዳዋል ። በዚያ ላይ ጥያቄ መጠየቅ አለ ።አቤል ይህን ነው ያልወደደው ፤ አካሉን ክፍል ውስጥ አሰቀምጦ በሰሜቱ ወደ ወጭ የመብረሩን ነጻነት ያሳፈዋል ፤ በቀላሉ
ይጋለጣል ።

ዛሬ ግን ሰኞ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ሌላም ስሜትን ያቁነጠነጠው ጉዳይ ነበር ። ትዕግሥትን ማየት አለበት ። የሁለት
ቀን ናፍቆት ላለበት አፍቃሪ የአንድ ሰዓት ሌክቸር በጣም ረጅም ነው ። እናም ከክፍሉ ሮጦ ለመውጣት የደወሏን
ድምፅ ነበር የሚጠባበቀው ።

ምን መስለህ ? አለው አጠገቡ የተቀመጠ ተማሪ ሣቁን እንደጨረሰ
የመምህሩን ቀልድ ለአቤል ለመንገር
ጓጉቶ ሃይማኖታዊ ቀልድ ነውኮ የተናገረው ።
እኮ ምን አለ አቤል በተሰላቸ ድምፅ ።

“ ሰዎቹ ከሞቱ በኋላ ወደ ሰማይ ቤት ሔደው መንግስት ሰማያት ለመግባት ሽሚያ ተፈጠረ ። የገነት በር ጠባብ ነበር ስለዚህ ጻድቃኖቹ ተወዳድረወ ይግቡ
ተባለና መመዘኛው በምድር ላይ ለደሃ የመጸወቱት ገንዘብ ብዛት ሆነ ። በዚህም መሠረት ለደሃ ብዙ የመጸወቱት ወደ
ገነት ሲገቡ አምስት ሳንቲም ብቻ የመጸወጡት ጻድቅ ግን አምስት ሳንቲሙ ተመልሶለት ወደ ገሀነም ይግባ ተባለ።

አቤል ቀልዱ ብዙም ስላልኮረኮረው ፥ ጥርሱን ትንሽ ብልጭ አድርጎ ሰዓትህ ስንት ትላለች ? መውጫችን አልደረሰም
እንዴ? ሲል ጠየቀው ።

ተማሪው ሰዓቱን ተመልክቶ፡ “ ሁለት ደቂቃ ይቀራል” አለው።

ሁለት ዓመት ይቀራል ያለው ይመስል አቤል ፊቱን ኮሶ አስመስሎ በልቡ ሴኮንዶቹን ሲያባርር ቆየ ።

ልክ የደወሏን ድምፅ ሲሰማ አንዳች ነገር መቀመጫውን እንደ ወጋው ሁሉ ቶሎ ብድግ አለ ። ነገር ግን አልተትኮረበትም ። ሌሎቹም ለመመገቢያ አዳራሹ ሰልፍ ለመሽቀዳደም ደውሉን ተከትለው ግልብጥ ብለው ስለተነሱ ክፍሉ ትርምሱ ወጣ ። ቀድሞ ለመውጣት በሩ ላይ ጭንቅንቅ ተፈጠረ

ምናለበት ቅድሚያ ቢሰጡኝ ? አለ አቤል በልቡ ለመውጣት እየተጋፋ “ እነሱ የራባቸው ሆዳቸውን ነው»የእኔው ግን የዐይን ረሀብ ነው ።

“ ታዲያ ከዐይን ረሀብና ከሆድ ረሀብ ለየትኛው ነው ቅድሚያ የሚሰጠው ? ” ሲል የገዛ ኅሊናው ያፋጠጠው
መሰለው።

እንደ ረሀቡ ጥንካሬ መሰለኝ ። ”
አይደለም ። ጅል አትሁን ። ሆድህ ሳይጠግብ ዐይንህ አይራብም ።

አረ አይመስለኝም ። አያድርስ ነው ። የዐይን ረሀብ ራሱ ከሆድ ረሀብ ይብሳል አያድርስ ነው ! እረ እንዲያው መቃጠል ነው !?

“ ምነው የዐይንን ረሀብ እንዲህ አጋነንከው ? የማያውቁት ዐይነ ሥውራን አሉ አይደለም እንዴ ? ”

“ ሀሀ ! እነሱም ” ኮ ጆሮአቸው የሚራብ ይመስለኛል ። ጆሮአቸው የዐይናቸውን ያህል ያገለግላቸዋል ። ለምሳሌ እኛ ዐይናማዎቹ የምንወዳትን ሴት በየጊዚው ለማየት እንደምንራበው ሁሉ ፡ እነሱም የሚወዷትን ሴት ኮቴ ወይም ድምፅ ለመስማት ጆሮአቸው የሚራብ ይመስለኛል ። ”

• ድንቅ የሆነ የመከላከያ ሐተታ ነው ። እስቲ እንግዲህ አንድ ሁለት ቀን ምግብ ሳትበላ ቆይና ፥ ከዐይንህና ከሆድህ
የትኛው ቅድሚያ እንደሚኖረው ትረዳዋለህ ። ”

አቤል ወትዋች ኅሊናውን “ ወጊድልኝ!” ብሎ የማማረር ያህል እጁን አወራጭቶ ፥ “ ሰው ኅሊናን ያህል ባላንጣ።ባይኖረው ምንኛ እንደ ልቡ በሆነ ነበር ! ” ሲል አሰበ

“ እንዴት እባክህ ? እንደ ከብት ? እንደ እንስሳ? ”እያለ ኅሊናው እንደገና ከተፍ ።

መንገዱን በምን ዐይነት ርምጃ እንደ ጨረሰው ለራሱ” እየገረመው ከመኝታ ክፍሉ ደረሰ ። ደብተሩን እልጋው ላይ ወረወረና በወጣበት ፍጥነት ተመልሶ ደረጃውን ወረደ በሩጫ ቀረሽ ርምጃ ወደ ምግብ አዳራሽ አመራ ከገለጻ ክፍሉ ለመውጣት የነበረው ችኮላ " ያ ሁሉ የዐይን ረሃብሬ የተመረኮዘ ግላዊ ሙግት ፥ ይህ ሁሉ ሩጫ ትዕግሥትን ለማየት ነው ። ትላንት ጠዋት ወደ ሰርጉ ከሔደችበት ጊዜ ጀምሮ አላያትም ። እሔደችበት አድራለች ብሎ ነው የገመተው ። እሷ ግን አውቶቡስ አጥታ አምሽታ ነበር እንጂ ካምፓስ ነው ያደረችው ። ጠዋት ደግሞ እሱ ራሱ እንቅልፍ ተጫጭኖት ስላረፈደ እንደ ወትሮው ወደ ቁርስ ክፍል ስትሔድ ወይም ወደ ትምህርት ክፍሏ ስትገባ ለማየት ዕድል አልገጠመውም ። በዚህ ምክንያት ገለጻ ክፍሉ ውስጥ ሁሉ
ነገሩን እያብላላ ሲበሽቅ ነው ያረፈደው ።

አሁንም ከምግብ አዳራሹ አካባቢ ደርሶ የምሳ ሰልፍ እንደ ያዘ ። መላ ሰውነቱ በቅናትና በእልህ ነበልባል ይንቀለቀል ነበር ። ትዕግሥት ሰልፉ ውስጥ የለችም ቀድማ ገብታ ይሆን ? ሰልፍ መጠበቁ አስመረረው ። ወደ ውስጥ ለመግባት
ቸኰል ። ነገር ግን ተራ መጠበቅ ግዴታ ነው ። በውዴታ ግዴታ የተሳሰረች ዓለም !

ተራው ደርሶ ውስጥ ከገባ በኋላ ፡ እንጀራ ሳይቀበል ወጥ ጨላፊዋ ጋ ሔዶ ትሪውን ዘረጋለት ። መሳሳቱን ያወቀው ሲሥቅበት ነው ። ድርሻውን ተቀብሎ መቀመጫ
በሚፈልግበት ጊዜም ዐይኑ አዳራሹን ዙሪያ ገብ እየማተረ ነበር ። በተለይ ሴቶች ፀየተቀመጡበትን አካባቢ እሳት
በጎረሱ ዐይኖቹ ቃኘ ።

ዛሬም አልመጣችም ማለት ነው ? ” አለ በልቡ ሳያስበው ጥርሶቹን እያንቀጫቀጨ ከኅሊናው ጋር እንደ ልቡ ለመሟገት ተናግሮ ከሚያናግር ለመሸሽ ፥ ከታዛቢ ለመራቅና ግላዊ ነጻነቱን ለማግኘት አብዛኛውን ጊዜ በምግብ አዳራሹ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ
መብላት ይመርጣል ። ሰላምን ከብቸኝነት ሊያገኛት ይጥራል ። ይህ ዐይን ፍቅር ላይ ከመውደቁ በፊትም የነበረው ጸባይ ነው ። በእርግጥ ፥ በዐይን ፍቅሩ ሳቢያ ደረጃው ከፍ ብሏል ። አሁንም ከወደ ጥግ በኩል ባዶ ጠረጴዛ ተመልክቶ
ወደዚያው ሲያመራ ትዕግሥት ተመለከተችው ። የጎረሰችው አፏ ውስጥ ተንቀዋለለባት ። ቶሎ ብላ ዐይኗን ልትሰ

ብር ስትል ማርታ ቀለበቻት ። ቤተልሔም ሁለተኛዉ ምግብ አዳራሽ ስለምትመገብ አብራቸው አልነበረችም ።

“ ኤጭ ! እንዲያው ይሄ የማሽላ እንጀራቸው!” አለች ማርታ ትዕግሥትን ላለማሳፈር ብላ ። በእርግጥም የእሑዱ
ግብዣ ገና ከውስጧ ስላልጠፋ ፡ ሽሮው አልዋጥ ብሏት እየታገለች ነበር ።

ትዕግሥት ምንም አላለችም ። ከዚያ
👍1
በኋላ ቀናም አላለች ።

አቤል መቀመጥ የፈለገበት አካባቢ ሲደርስ ድንገት አየችው ። የቅናት እሳት የሚተፉት ዐይኖቹ በድንገትኛው
አይታ ከማርታ ጋር በመገጣጠማቸው ድንግጥግጥ አለ ።እግሩ የተሳሰረ መሰለው ። ዐይኑን ሳይሰብር ከድንጋጤው ለማምለጥ ራመድ ሲል የአንዱ ወንበር እግር ጠለፈው ።
በሁለት እጁ የምግብ ትሪውን ይዞ ስለ ነበር ተንገዳግዶ ሚዛኑን ጠብቆ መዳን አልቻለም። አሳዛኝትርኢት ሆነ። እሱ
ከታች ፡ ያድነኛል ብሎ የተደገፈው ወንበር እግሩ ላይ ሲወ ድቅ የትሪው እንጀራና ወጥ ተገልብጦ ደረቱ ላይ ተደፋ ።
የትኩሱ ወጥ ፍንጣቂ የደረሰባቸው በአካባቢው የተቀመጡ ተማሪዎች ተቆጥተው እየተፈናጠሩ ቢነሡም ትርኢቱ
ቁጣቸውን ወደ ሣቅ ለወጠው ። ካካታውን ሰምቶ የአዳራሹ ተመጋቢ ሁሉግልብጥብሎ ተነሣ በአንዱ ውድቀት ሌላዉ ሊሥቅ ፡ የሳምንቱ መሣቂያና መሳሳቂያ ሆኖ የሚቆየው ወሬ ከሌላ አፍ ከመስማት ይልቅ በዐይኑ በብሌኑ ለማየት
አንዱ ባንዱ ላይ መንጠራራት ራሱ ሌላ ትርኢት ሆነ ።

እስክንድርም እንደ ሌሎቹ ተንጠራርቶ ሲያይ ተዋናዩ አቤል መሆኑን በተመለከተ ጊዜ ዐይኑን ማመን አቃተው ።ግፊያውን እየበረጋገደ ዐልፎ አጠገቡ ሲደርስ • በወጥ የተጨማለቀ ልብሱን እየጠራረገለት “ አቤል” አቤል ነው ?
ምን ነካህ ? ” አለው ።

አቤል ምንም አልመለሰለትም « ከወደቀበት ተነሥቶ ቢቆምም በድንጋጤ ክው ብሎአል ። ከዚያ አዳራሽ ተፈት
ልኮ መውጣት ነበር ፍላጎቱ ። ግን በየት በኩል? የዚያ ሁሉ ተማሪ ዐይን አንድ ርምጃም እንደማያራምደው ገመተ ።
ሆኖም እስክንድርን አጠገቡ በማግኘቱ ትንሽ ቀለል አለው ።

ትንግሥት በዚች ደቂቃ ውስጥ መሬት ቁልቁል ተሰንጥቃ ብትውጣት ምንኛ በወደደች ! ካካታውን ሰምታ ቀና
ስትልና አቤል ከያዘው ትሪ ጋር ሲወድቅ ስትመለከት ፡ ሽምቅቅ ብላ አንገቷን ጠረጴዛው ላይ እንደ ደፋች ቀረች ። የሚ
ቀጥለውን ትርኢትም ለማየት ቀና አላለችም ። ተማሪው ሁሉ ወደ ወደቀው ወጣት ሳይሆን ወደ እሷ የሚያይ መሰላት
እንባዋ ድንገት ሊመጣባት ሲል ገታችው

አቤል በምግብ አዳራሹ በር ከእስክንድር ጋር ሲወጣ ማርታ ተመለከተች ። እሷም በድንጋጤ የምትገባበት ጠፍቷታል ። ተደናግጦ ለመውደቁ ምክንያት የሆነው ከእሷ ጋር ዐይን ዐይን መገጣጠማቸው ስለ መሰላት ፥ የኃጢአተኝነት ስሜት ተሰምቷታል ።

ት... ትዕግሥት ” አለቻት ፈራ ተባ በሚል
ድምፅ።

ወዬ ! ”

እንሒድ ፥ እን ውጣ ትዕግሥት እንባዋ እንዳይመጣ እንደ ምንም እየተጠነ
ቀቀች ቀስ ብላ ቀና አለች ። እንደ ፈራችው አልሆነም እዳራሹ ውስጥ ያሉት ተማሪዎች በሁኔታው እየሳቁ ምግባቸውን ከማጣጣም በስተቀር እነትዕግሥትን ልብ ብለው አልተመለከቷቸውም ።

የበሉ!ትን ትሪ ሳያነሱ ፥ ግራ ቀኝ ሳይመለከቱ ሁለቱም አንገታቸውን እቅርቅረው ፈትለክ ብለው ወጡ ።
ከቀትር በኋላ ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ፥ እስክንድር ከመኝታ ክፍሉ ተጠራ ። አልጋው ላይ ጋደም ብሎ እያነበቀ
ነበር።

ማን ነው የፈለገኝ ? አለው : ተልኮ የመጣውን አንዲት ልጅ ናት ። ወደዚህ ስመጣ አይታኝ አንተን እንድጠራላት ጠየቀችኝ ።

“ ስሜን የምታውቅ ናት ? ”
“ እሷ፡ ስምህን ጠርታ ነው ንገርልኝ ያለችኝ

በፈጣን ርምጃ ከመኝታ ክፍሉ ወጥቶ ፥ ደረጃውን ወርዶ ወደ ውጪ ብቅ ሲል ማርታ ደመቀን ቆማ ተመለከታት »
ግር አለው ። ከአሁን በፊት ግቢው ውስጥ መታየት ካልሆነ በስተቀር ንግግር አልነበራቸውም።

ማርታ እሷ እንዳስጠራችው እንዲያውቅ ፈገግ አለችለት ። ዝብርቅርቅ ባለ ስሜት ልቡ እየነጠረ ቀረባት ።

እኔ ጋ ነው ? ” አላት የውስጥ ስሜቱን በሚገልጽ ጣፋጭ ቅላጼ ።

“አዎ! ስለ አቤል ልጠይቅህ ነው ” አለችው ዕዝን ብላ።

የአቤልንም የእኔንም ስም እንዴት አወቀች ? ” ሲል አሰበ ። ወዲያው ግን ለምን ጅል እሆናለሁ ? እኔ እራሴ
የእሷንና የትዕግሥትን ስም አጣርቼ ዐውቅ የለም እንዴ ! የእነሱ ማወቅ ያስደንቃል ? እንዲያውም ለወሬ ሴቶች ይብሳሉ ” አለ ፡ ባይነጋገሩም በዐይን እየተራረፉ የተላለፉበትን ቀን በልቡ እያስታወሰ ።

እንደ ሴትነቷ ስማቸውን ዐውቃ እንዳላወቀች ለመሆን አለመሞከሯ አስደነቀው ። አመጣጧ ብዙ ነገር ጭንቅላቱ ውስጥ አተረማመሰበት ። የተጠቀለለ ነገር ይዛለች ።

ትዕግሥት ራሷ መምጣት ፈርታ ልካት ይሆን?” ሲል አሰበ ። በምግብ አዳራሽ ውስጥ ለአቤል መውደቅ መንስኤው
ከእነሱ ጋር እንደ ተያያዜ ፈጽሞ አላወቀም ነበር ።

ምግብ ቤት ውስጥ ሲወድቅ ነበርሽ እንዴ ? ” አላትና ፥ ከእሷ መልስ ሳይጠብቅ ። የትኩሱ ወጥ ፍንጣቂ
እጁን ትንሽ ጠበሰው እንጂ ሌላ ቦታ አልተጎዳም ” አላት ።

ከንፈሯን መጠጠች

“ እምልሽ ፡ መቼም እዚያ ሁሉ ተማሪ መሐል መውደቁ ራሱ ሕመም ነው ። አለ አይደል ! የአጋጣሚ ነገር ቢሆንም ያሳፍራል ። እና በድንጋጤ ትንሽ ተረብሾ ፡ ምሳውንም ባመጣለት ሊበላ ኣልቻለም ። አሁን ተኝቷል ። ድንጋጤው ሲያልፍለትና ሁኔታው ሲረሳው ደኅና ይሆናል አላት »
እንደ ገና ከንፈሯን መጠጠችና “ ውይ በናትህ 'አወዳደቁ እንዴት ሰቀጠቅጠኝ መሰለህ ! ብቻ እንኳን ተረፈ አለችው ።

አስተዛዘኗ ልቡን ነካው ። ምነው እኔ በወደቅኩና እንዲህ ባዘንሽልኝ ! ” አለ በሐሳቡ ።

💥ይቀጥላል💥
👍31
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“አዎ፣ ወደዛ ቤት እየሄድኩ እንደሆነ ሳስብ...” ከቤተሰብ ጋር መሆን ታክቷታል፡፡

“አይዞሽ ሃኒዬ፡፡ በቃ እርሻቸው፡፡ እንደሌሉ አስቢያቸው::እንዳልሰማሽ እለፊያቸው፡፡”

“አይ ያቡ፣ እንደዛ ሳልሞክር ቀርቼ መሰለህ? የሚቻል አይደለም፡፡ ከባድ ነው፡፡ በተለይ ታላቅ እህት ተብዬዋ፣ እዛ ሆኜ ስንት ነገር እንዳላደረኩላት ዛሬ የምትናገረኝ ቅስሜን እስኪጠዘጥዘኝ ድረስ ነው፡፡ ነገሩ ልብን ይሰብራል፡፡” ስታወራ እንባዋ መጣ፡፡ ወሬውን
አስቀይሬ መቀባጠር ጀመርኩ፡፡ ሞጆን አልፈን ወደ ቢሾፍቱ ስንጠጋ፤

“ያቡዬ..?” አለችኝ ምቀባጥረውን አቋርጣኝ፡፡

“ወዬ ሃን...”

“አንተ ግን ለምን አታገባም?”

“ማለት...?” ተደናበርኩ፡፡ ያላሰብኩት ዱብዳ ነው፡፡

“ብቻህን ነው ምትኖረው፡፡ በዛ ላይ የቅርብ ሰው እንኳ ባጠገብህ የለም፡፡ ስለዚህ ለምን አንዷን አታገባም?”

“እ...፣ እሱስ እውነትሽን ነው፡፡ ግን..”

“ይኼ ምን ግን ያስፈልገዋል?” ሳይታወቃት ጮኸች፡፡

“ንሮዬን እያየሽው አይደል፡፡ ገና ለመቆም ድክ ድክ እያልኩ፡፡ባይሆን ስራው መስመር ከያዘልኝ በኋላ...”

ቁርጠኝነቱ ቢኖርህ፣ አሁን እዚህ በሳምንት ያወጣነው፣ለሁለት ሰው ንሮን ለመመስረት በቂ ነው፡፡ አቅም ሳይሆን ቁርጠኝነቱ ነው የሌለህ፡፡”

የምመልሰው አልነበረኝም፡፡ ዝም አልኩ፡፡ እርሷም ዝም አለች፡፡መናኸሪያ እስክንደርስ ምንም አላወራንም፡፡
ወደየቤታችን ከመለያየታችን በፊት አቀፍኳትና፣

“አይዞሽ የኔ ፍቅር፣ ሁሉ ነገር ይገባኛል፡፡ እረዳሻለሁኮ፡፡ ጠንከር በይ፡፡ ትንሽ ግዜ ብቻ ታገሺኝ፣” ጉንጫን ሳምኳት፡፡ ከልቤ ነበር ያልኳት። ከሷ በፊት ስለማንም ደንታ ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ ማታ እንዴት እንደሆነች ደውዬ ጠየኳት፡፡እንደተለመደው ነው አለችኝ፡፡

ከአርባምንጭ መልስ የኔ ስሜት ጥሩ ሆኗል፡፡ የሃኒ ደግሞ ጭራሽ ብሶባታል፡፡ በስልክም በአካልም መነፍረቅ አመሏ ሆኗል፡፡ ድብርቱ እንዳይጋባብኝ፣ በየቀኑ ውሎዬን ከነ ሃብትሽ ጋር አደረኩ፡፡
ዛሬም፣ ለአራተኛ ቀን ምሳ እየበላን፣ ጃምቦ እየላፍን፣ ከአርባምንጭ
የተረፈ ወሬ አየገረብን ነው፡፡ መሃል ላይ ወሬው ሲቀዘቅዝ፣ ሳሚ ትዝ አለኝ፡፡ ተጠፋፍተናል፡፡ ደወልኩለት፣

ሳሚሻ የጠፋ ሰው፣ እንዴት ነው ባክህ?” አልኩት፡፡

ጎረምሳው፣ በዚህ ፍጥነት ሰው ትረሳለህ?”

“እውነት ሳሚሻ ቢዚ ሆኜ ነው፡፡ ብረሳ፣ ብረሳ አንተን እረሳለሁ?” ተጎዘጎዝኩኝ፡፡

“እኔ ምልህ፣ የአለቃህን ነገር ሰማህ?”

“የትኛው አለቃዬ? ሼባው?”

“አዎ ሼባው፡፡”

“ኧረ ምንም አልሰማሁም፡፡ ምን ተፈጠረ?”

“ጮማ ወሬ አምልጦሃላ..?” ካ..ካ..ካ... የተለመደች ካንገት በላይ ሳቁን፡፡

“ይነገረኛ! እዛ የቀረኸኝ ዘመድ አንተ ብቻ ነህ፡፡ ማን ይነግረኛል ብለህ ነው?”

“ያቺ ጉደኛ ሜሪ፣ ሼባውን ጉድ ሰራችው፡፡ እሷን ሊያገባ ሚስቱን ፈታ::”

“ምን?” ጆሮዬን አላመንኩም፡፡

“አዎ፡፡ ፍርድ ቤት ፍቺ ጨርሰው፣ ንብረት በሽማግሌ ተካፈሉ ሲባሉ፣ ሽማግሌ ሁነኝ አይለኝም?”

“በጣም ሚገርም ነገር ነው የምትነግረኝ፡፡ ግን ቆይ፣ ሚሪ እሺ
ባትለውስ? አባቷን የሚያህል ሽማግሌ፣ ምን አጥታ ነው ምታገባው? እሺ ደግሞ ልጆቹስ?” ሁሉ ነገር ግራ ገባኝ፡፡

“ልጆቹን ምን ሊደርግ እንዳሰበ እኔ አላውቅም፡፡ ሜሪ ግን ከቤተሰቧጋ ወጥታ ተከራይቶላት ካስቀመጣት ቆየ፡፡ እሱንም
አልሰማህማ? ከብዙ መረጃዎች እርቀሃላ ወንድሜ፡፡” ካካካ...፡፡ ብዙ ከተጫወትን በኋላ፣

“በል እንደዚህ ብዙ መረጃ እንዳያመልጥህ፣ ቶሎ ቶሎ ደውል፡፡
ሲደወልልህም ደግሞ ስልክ አንሳ፤” አለኝ፡፡

“ኧረ እኔው እደውላለሁ፡፡ አዲሱን ስራ መስመር ለማስያዝ በት በት ስል እየረሳውኮ ነው፡፡ አሁን መስመር እየያዘልኝ ነው፡፡ አልጠፋም፧
እደውላለሁ፡፡”

ስልኩን ዘግቼ ለነ ሃብትሽ፣ ስለ ቀድሞ አለቃዬ ሙሉ ታሪኩን ነግሪያቸው፣ በእርሱም በሜሪም ድርጊት ስንገረም አመሸን፡፡ ማታ እቤቴ ስገባ እንደተለመደው ለሃኒ ልደውል ስልኬን ሳወጣ፣ በጣም ብዙ ግዜ ደውላ ነበር፡፡ ወሬ ይዘን አልሰማነውም፡፡ የቴክስት መልዕክት ልካልኛለች፡፡ ስለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ!” ይላል፡፡ መልሼ ደጋግሜ
ደወልኩላት፡፡ ስልኳ ዝግ ነው፡፡ እንቅልፌን ተኛሁ፡፡ ጠዋት ስነሳ እጅግ አስደንጋጭ ዜና ሰማሁ፡፡ ሃኒ ትናንት ማታ መርዝ ጠጥታ እራሷን አጠፋች፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡ አዞረኝ፡፡ በቀጥታ እቤታቸው ሄድኩኝ፡፡ ሃኒ እራሷን ማጥፋቷ እውነት ነው፡፡ ቤታቸው በለቀስተኛ
ተሞልቷል፡፡ አብዛኛው የሰፈር ሰው በጣም አዝኗል፣ ከልቡ ያለቅሳል፡፡
ማያለቅስ ለቀስተኛ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ለነገሩ ባያዝኑና ባያለቅሱ ነበር ሚገርመው፡፡ ገና በልጅነቷ ነው የተቀጨችው ፤ በዛ ላይ ምታጓጓ ቆንጅ።
ነበረች፡፡ መሞቷ፣ እራሷን ማጥፋቷ ያላስደነገጠው የለም፡፡ አልቅሺ አልወጣልህ አለኝ፡፡ ሃዘኑ ቅስሜን ሰርስሮ ገባ፡፡ ከቀብሯ ጀምሮ እስከሰልስት፣ የሚያቀኝ ሰው ባይኖርም፣ ከለቀስተኛው መሃል ሆኜ ስቅስቅ ብዬ አነባሁ፡፡ ልቤ በሃዘን ተሰበረ፡፡ ከፍተኛ ጫና እንዳለባት
አውቅ ነበር፡፡ በተለይ ታላቅ እህቷን እንደገዳይ አየኋት፡፡ ስታለቅስ አይቻት፣ ለቅሶና ሃዘኗን አስመሳይ የአዛ እንባ ሆነብኝ፡፡ ሄጄ ማነቅ አሰኘኝ፡፡ ያስጨንቋት እንደነበር ተረድቼ ነበር፡፡ እራሷን እስክታጠፋ ይደርሳል ብዬ ግን በፍፁም አልገመትኩም፡፡ ልደርስላት፣ ልከላከላት
ይገባ ነበር፡፡ ከኔ ውጪ የሚረዳት፣ ሚከላከልላት፣ ሚደርስላት ሰው
አልነበራትም፡፡ እንዳግዛት ነግራኝ ነበር፡፡ አብረን እንኑር ብላኝ ነበር፡፡አልተረዳኋትም፤ አልደረስኩላትም፡፡ ላድናት ስችል አላደረኩትም፡፡
ልረሳው የማልችለው ከባድ ሃዘን በውስጤ ነገሰብኝ፡፡

ከሞተች ሦስት ሳምንት ሙሉ በዚህ ስሜት ተሰቃየሁ። በአዕምሮዬ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎች ይዘንባሉ፡፡ ለምንድን ነው ህይወት እንዲህ ግራ የሆነችብኝ? ለምንድነው ተስፋዬ በተደጋጋሚ እየበራ ሚጠፋው? ለምንድን ነው በተደጋጋሚ ሚጨልምብኝ? ሃኒ
ደስተኛ አድርጋኝ ነበረ፡፡ የምኖርላት ምክንያቴ ሆና ነበረ፡፡ ለምን እርሷን
ይወስድብኛል? ለምን? ለምን? ለምን?! የማያባሩ ጥያቄዎች፣ ልሸከመው፣ ልቋቋመው የማልችለው የልብ ስብራት፡፡

እራሴን በአልኮል ደብቁ ለማለፍ ሞከርኩ፡፡ ጭንቀትና ድባቴው ግን እየባሰብኝ መጣ፡፡ህይወት መልሳ እንደቀድሞው ባዶና ተስፋ ቢስ ሆነችብኝ፡፡ ልቋቋመው ማልችለው ፀፀት ያላምጠኛል፡፡ ስልኩን ባነሳው ኖሮ ታተርፋት ነበር ይለኛል። በእርሷ ምክንያት፣ የተውኩት፣ የጣልኩት እራሴን የማጥፋት እቅድ፣ አቧራውን አራግፎ፣ የችግሬ የመጀመሪያ ተመራጩ መፍትሄ
ሆኖ ታየኝ፡፡ ተከተላት ይለኛል፡፡ እዕምሮዬ ሌላ ነገር ማሰብ አቁሟል፡፡ በየቀኑ፣ በየሰዐቱ፣ በየደቂቃው ይነተርከኛል፣ ይጠዘጥዘኛል፡፡ ከዚች ጭለማ ህይወት ሞት በስንት ጠዓሙ ይለኛል፡፡ በስተመጨረሻ ተሸነፍኩለት፡፡ የተውኩትን እቅዴን በድጋሜ በጥንቃቄ ለመፈፀም
መዘጋጀት ጀመርኩኝ፡፡ በእጄ ከቀረኝ ገንዘብ አብዛኛውን ለእናቴ ላኩላት፣ የዶሮ ቤቱን ለነ ሃብትሽ እንደባለፈው ሰው እንዲያመጡና እንዲከታተሉት አደረኩኝ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍3
#ሰመመን


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


አስተዛዘኗ ልቡን ነካው ። ምነው እኔ በወደቅኩና እንዲህ ባዘንሽልኝ ! ” አለ በሐሳቡ ።
ልቡ ስለተረጋጋ ዐይኖቹ ውበቷን ከላይ እስከ ታች ማስተዋል ይዘው ነበር ። አፍንጫውም ከትኩሳቷ ጋር የሚተነውን ሽቶ መቀበል ጀምሯል ። ስትናገር ትንፋሿ ራሱ ሽቶ የመሰለውን ። ከእሑድ የሠርግ አለባበሷና አካኳሷ ከፊሉ ላይዋ ላይ ቀርቶ ነበር ። በአንገተ ክፍቱ ሹራቧ በኩል የተላጠ ሽንኩርት መስለው ብቅ ያሉት ጡቶቿ ከእስክንድር ዐይን ጋር ተፋጠጡ ።ጡት መያዛ አላደረገችም ነበር ።

“ ይህንን ለአቤል ነው ያመጣሁለት ” አለችና " ይዛው የነበረውን የተጠቀለለ ነገር ሰጠችው ። ኬክ ገዝታ ለት ነበር ።

እስክንድር የባሰውን ድንግርግር አለ ። ይህን ለሚያህል ውለታ የሚያበቃ ግንኙነት ነበር ማለት ነው ? ” አለ
በልቡ ።አቤልን ጠረጠረው ። ሆኖም ከማርታ ጋር አቀራርቦ ያነጋገረውን ይህን አጋጣሚ ወደደው ።

ኬኩን ሰጥታው ጥቂት መንገድ ከሔደች በኋላ ፥ በአንዳች ግፊት ተስባ ዘወር ስትል እንዳጋጣሚ እስክንድርም የዞረባት ቅጽበት ስለ ነበረች ዐይን ለዐይን ተገጣጠሙ ።ሁለቱም ተፋፍረው ፊታቸውን ወደ መንገዳቸው መለሱ ።

እስክንድር ኬኩን ይዞ ወደ መኝታ ክፍሉ ሲመለስ “ጆኒ ለካ የዋህ ስትመስል ፥ ውስጥ ውስጡን ጉዳይዋን አጠና
ክራለች ” እያለ አቤልን በልቡ እያማው ነበር ።

ከክፍሉ እንደ ገባ አቤልን አስነሣውና ፥ “ ቀና በል እባክህን ፤ ጣፋጭ ምግብና ጣፋጭ ወሬ አምጥቼሃለሁ ”አለውና ፥ በችኮላ እሽጉን ፈትቶ አንድ ኬክ አውጥቶ
ለራሱ ገመጠ ።

አቤል ለምንም ነገር ባልጓጓ ስሜት ተወኝ እባክህ እስክንድር ፥ ምንም አልፈልግም ብተኛ ይሻለኛል ” አለው ። ፊቱን ትራሱ ላይ እንደ ደፋ ነበር

እስክንድር ሌላ ኬክ አውጥቶ ፡ ጓደኝነት በተሞላው ስሜት ፡ “ ኤጭ !አንቺ ደሞ እንዲያው በቀላል ነገር መብሸቅ ይቀናሻል ። ተደናቅፎ መውደቅ በማንም ላይ ሊደርስ የሚችል አጋጣሚ ነው ። ይልቅ ተነሽና ይህችን ነገር
ግመጭ፥” አለው

አቤል ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ዝም !
እስክንድር ነገሩን ለማቅለል ያህል ብቻ ሳይሆን በጊዜው ያስደንግጥ እንጂ በእርግጥም ቀላል ነው ብሎ ነው
የገመተው የአቤል ምላሽ ግን ጠነከረበት

ትንሽ ቆየና ፡ ዘዴ ያገኘ ወይም አቤልን ከመጥፎ ስሜቱ ያዘናጋ መስሎት ፡ እረ ሌላው ቢቀር ውቃቢዋ ያይሃል !
ይበላልኛል ብላ ደክማ አምጥታልህ ” አለና ሳይጨርስ እቤል አቋረጠው ።

“ እንዴ ኬኩን ማነው ያመጣውን ? ” አለ አበል ጉጉት ባዘለ ደካማ ድምፅ ፥ ቀስ ብሎ ፊቱን ከደፋበት ትራስ አነሣ ። ምሳውን አልበላ ስላለው ኬኩን እስክንድር ራሱ ገዝቶ ያመጣለት መስሎት ነበር ።

“ ማርታ ' ኮ ነች ያመጣችልህ ” አለ እስክንድር ስሟን ሲጠራ አንዳች ነገር ሽምቅቅ እያረገው ።

“ እ? ! ” የድንጋጤም ፡ የመገረምም ነበር

ማርታ የ...የእንትና ጓደኛ የትዕግሥትን ስም በአቤል ፊት መጥራት አልፈለገም ።
አቤል ግን ወዲያው ገባው ። ሥሮቹ ተገታትረው ዐይኑ ደም መሰለ
“ በናትህ ስሟን አትጥራብኝ ” አለው ፡ ምርር ባል አነጋገር ፡ “ እሷን ልጅ ላለማየት ስል ይህን ዩኒቨርስቲ ሳልለቅ አልቀርም ። ”

እስክንድር ነገሩ ተምታታበት ። ትዕግሥትን ወይስ ማርታን ? ማንኛቸውን ላለማየት ? ” አለ በልቡ የቀድሞም
ጥርጣሬው የተሳሳተ መሰለው ። የሚናገረው ነገር ጠፍቶት
ዝም አለ።

ክፉኛ የቀሉት የአቤል ዐይኖች የታመቀ እንባ ተዘርግፎ እዳይፈስ ትንቅንቅ መያዛቸውን እስክንድር ገመተ ግቢ ነፍስ ውጪ ነፍስ ክፉኛ አሳዘነው ። የሆነ ነገር ልደብቅ ብላ ከውስጥ የምትቃጠለው የምትብከነከነውና የምትጨሰው ሕይወቱ ውስጥ ውስጡን አምርራ ስታለቅስ
በስሜቱ ታየው ። ትካዜው ተጋባበት ። እናም ዝም ብሎ መቆየት አልቻለም ።

ስማ እቤል ልረዳህ የምችለው ነገር ካለ ስሜትህን ሳትደብቅ በንጹሕ የጓደኝነት መንፈስ ንገረኝ ። ሰትጨነቅ ማየት አልፈልግም ። የፈለገው ነገር ይሁን ፡ እሰዋልሃለው

እስክንድር ከአቤል ጋር ከተዋወቀበት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ አምርሮና በትካዜ ተመስጦ ሲናገር፥ የመጀመሪያ ጊዜው
ነበር ። ከማርታ ጋር መተዋወቄ ከትዕግሥት ጋር አስተዋውቆኝ ፥ የአቤልን ችግር እፈታለት ይሆናል የሚል እምነት
ስላደረበት እሠዋልሃለሁ” ያለው ከዚህ ተነሥቶ ነበር።

የእስክንድር ወንድማዊ የንግግር ቃና የአቤልን ልብ ክፉኛ ኮረኮረው ። በተለይ “እሠዋልሃለሁ” የምትለዋ ቃል
ከእስክንድር አፍ የወጣችው እንባ በተናነቀው ስሜት ስለ ነበር፡ የልቡን አንጀት በኀዘን ፍላጻ ወጋችው " የሆነ ነገር
ሊነግረው ፈለገ ። ግን ምን ? አፉን ከማጥፋት በስተቀር እስክንድር መፍትሔ የሚያገኝለት አልመሰለውም።

ምንም አልተናገረም መልሶ ፊቱን ከትራሱ ላይ ደፋው።

አንተ ከባድ አርገህ የወሰድከው ነገር ይሄኔ በቀላሉ የሚፈታ ይሆናል ” አለው እስክንድር ።

አቤል አልመለስም ።

“ ስማ እንጂ አቤል ! እባክህ ንገረኝ ፤ ዝም ብለህ ራስህን አታስጨንቅ። ሐሳብን ለሰው ማካፈል ራሱ ከሕመም ያድናል ፡ መጥፎ ተፈጥሮ ነው ያለህ ፡ ለምን ሁሉን ነገር በግልህ ለመወጣት ትሞክራለህ ? ሰው ያስፈልግሃል ! እንግዲያው የጓደኝነት ትርጉሙ ምንድነው ? ነገር ሆድ ውስጥ መጨነቅ መጥፎ ነው ” አለው ፥ በእርግጥም የሚያስከትለው መጥፎ ውጤት እየታየውና መምህር ዮናታን የነግ
ሩት እየታወሰው ።

ስለ እሱ ሕመም እስክንድር ይህን ያህል መጨነቁ ሆዱን ስላባባው አቤል ቀና ብሎ ተወኝ እባክህ እስክንድር ሰለ እርዳታህ አመሰግናለሁ ። የእኔ ሕሙም ግንመፍትሔ የለውም " አትድከም ” ሊለው ፈልጎ ነበር " ነገር ግን እንባው ቀድሞም ዝርግፍ ስላለ መናገር አልቻለም ።ፊቱን ትራሱ ላይ እንደ ደፋ አለቀሰ ። ትዕግሥት ከፊቱ ቆማ በንቀት ፡ “ አልቃሻ ወንድ!” የምትለው መሰለው " ማርታ በእንባው የምትቀልድበት ከት ከት ብላ የምትሥቅበት መሰለው ።

“ ስማ ፡ አቤል ...!” እስክንድር ቢቸግረው ትከሻውን ነቀነቀው ።

መልስ የለም

አቤል ...

ዝም !

እስክንድር በሽቆ ሲጋራውን አውጥቶ ለኮሰና ፥ በልቡ ቤሽቲያ ! የራስህ ጉዳይ ነው ! ” ብሎ ጥሎት ወጣ ።

አንድ የተፈጥሮ ሳይንስ ምሩቅ መምህር ለድኅረምረቃ የሚያበቃውን የጥናት ጽሑፍ መዘክር ከማቅረቡ በፊት አማካሪው ዶክተር አጥናፉ የስንዴ ተክሉን እንዲጎበኙለት ጋበዛቸው ። ፕሮጄክቱን የሚሠራው በስንዴ ተክል ነበር የተለያየ አፈር በስንዴ አበቃቀል ላይ የሚኖረውን ተጽዕኖ አጥንቶ ለማቅረብ ።

ዮናታን ጉዳዩ ባይመለከታቸው ፕሮጄክቱን አቅራቢው መምህር በግል ወዳጅነቱ እንዲ ያዩለት ስለ ጋበዛቸው ከዶክተር አጥናፉ ጋር ሔደው ነበር ። ለጥናት ተክሎች ከተሠራችው ጎጆ ውስጥ እንደገቡ በጣሳ ጉች ጉች ብለው የተቀመጡትን የስንዴ ተክሎች አትኩረው መጐብኘት ጀመሩ ። ከምስታመት ቤቷ ላይ አረንጓዴው ቀለም ሙልጭ ብሎ ስለጠፋ ቃጠሎው ሌላ ከተማ የገቡ ይመስል ነበር ።

“ ለምን የዚህች ጎጆ ስም ተቀይሮ የኋይት ሀውስ ? አይባልም !” አሉ ዮናታን በቀልድ ዐይነት ነገር ግን ወቀሳን ባዘለ አነጋገር ። አረንጓዴው ቀለም ከጠፋ በኋላ
“ ግሪን ሀውስ ” ማለቱ ትርጉመ ቢስ መሆኑን ለመጠቆም ነበር ። “ ኋይት ሀውስ” እንዳይባልማ የተክሏን ጎጆ ከአ
ሜሪካን ቤተ መንግሥት ጎን ማስቀመጥ ይሆናላ ” አሉ ዶክተር አጥናፉ፡ ቀልድን በቀልድ በመመለስ ምንም አስተያየት ሳይሰጡ ስምንት የተክል ቆርቆሮ
ዎች ማለፋቸው አስጎብኝውን ሳያበሽቀው አልቀረም ። ከጎሳ ከኋላቸው
👍3
እየተከተለ “ ግሩም ነው ! ” የሚል ድምፅ ይጠብቅ ነበር ።“
ይህ የየት አገር ዐፈር ነው ? ” አሉ ዶክተር አጥናፉ፡ ዐፈሩ በደንብ ተስማምቶአቸው ከሁሉም ፋፍተው የበቀሉትን ዐምስት ያህል የቆርቆሮ ተክሎች እየተመለከቱ

የደብረ ዘይት ዐፊር ነው ” አለ አስጎብኝው ቆርቆሮው ላይ የጻፈውን ኮድ ተመልክቶ ፣ “ ይገርምዎታል ! በአገራችን
የስነንዴ ተክል ርዝመት ውስጥ ከፍተኛውን ደረጃ ሳይዝ አይቀርም ” ብሎ ፥ የዕድገቱን ፍጥነትና ርዝመት
የላከበትን ሰነድ ፍለጋ ማኅደሩን ያገላብጥ ጀመር ።

ፎቶግራፍ አስነሥተኸዋል ? ”

“አላነሳሁትም ። የጅማው ዐፈር ላይ የተተከሉት ፍጥነትም ባይኖራቸው ዕድገታቸውን ስላላቋረጡ ትንሽ
ልጠብቃቸውና ኣንድ ላይ አስነሣቸዋለሁ ብየ ነው ” አለ አስጎውብኝ ፥ ፊተ ብቻ ሳይሆን ልቡም ፈክቶ የፎቶግራፍ
ጥያቄ ለፕሮጄክቱ ፍጻሜ መቃረቢያ ስለሆነ ዶክተር አጥናፉ ይህን ማንሣታቸው በተዘዋዋሪም ሆን በውበቱ እንደረኩ ለመገመት አስችሎታል ።

“ አሁኑኑ ብታስነሣው የሚሻል ይመስለኛል ። ካለበለዚያ የጅማውን ስትጠብቅ ዕድገቱን የጨረሰው የደብረ
ዘይቱ ሊተኛና ፍሬው ሊረግፍ ይችላል ” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጡት ።

ይህ ሁሉ ሲሆኑ ዮናታን ምንም ሳይተነፍሱ ዐይናቸውን ከአንዷ ቆርቆሮ ተክል ላይ እንደ ተከሉ ቀርተው ነበር
እያንዳንዱ ቆርቆሮ የያዘው ስምንት ፍሬ ነው ፤ የዮናታንን ዐይን የጠለፈች ቆርቆሮ ሰባቱን ፍሬዎች ጅፍ አርጋ አብቅላ አንዷን አቅጭጫ አስቀርታለች ። ዮናታን በመቀጨጭ ላይ ያለችውን የስንዴ ዘለላ አትኩረው ሲመለከቱ አቤል በሃሳባቸው መጣባቸው ስለዚህ ነበር ከአስተያየት ተቆጥበው የቆዩት አቤል እራሱ እንደ ስንዴዋ ዘለላ በመቀጨጭ ላይ ያለ ሎጋ ወጣት ነው አሉ በልባቸው።

ትንሽ ቆይተው ፡ “ ይህችን ነገር ታያታለህ ? ” አሉ ፊታቸውን ወደ ዶክተር አጥናፉ መልሰው ።

የቷን ? ”

አስጎብኝዉም “ ምን ተገኘ ? ” በሚል ስሜት ወደ ቆርቆሮ አተኮረ ።

💥ይቀጥላል💥
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

#ምዱካን_ስወራ

ለመሞት ወስኛለሁ፡፡ ግን፣ ደስተኛ የምመስላቸው ቤተሰቦቼ፣ስኬታማ እንደሆንኩ፣ በደስታ እየኖርኩ እንዳለሁ እያሰቡ እንዲቀሩ፣በጥንቃቄ ዱካዬን አጥፍቼ ነው መሞት ያለብኝ፡፡ ልክ ከህይወታችን፣ቀስ በቀስ ጠፍተው እንደተረሱ ሰዎች፣ የት እንዳሉ ምን እንደሆኑ ትዝ እንደማይሉን ሰዎች፣ ዝም፣ ጭጭ፣ ጭልጥ ብዬ መቅረት ነው
ያለብኝ::ጥሩ ደብዛ ማጥፊያ የት ይሆን የሚገኘው? የት ነው አስክሬኔ ወድቆ
ሲገኝ፣ እንደቀልድ ሳይመረመር፣ ማነው? ከየት ነው? ሳይባል ሊቀበር ሚችለው? የት ሊሆን ይችላል?

ገቢና ወጪ ሰው የሚበዛባቸው ከተሞች፣ አዲስ ሰው፣ ፀጉረ ልውጥ ሰው፣ ማነው? ከየት ነው? መቼ መጣ? ለምን መጣ? ተብሎ ትኩረት ማይስብባቸው ከተማዎች፡፡ የድንበር ከተሞች ናቸው፡፡ በየቀኑ አዳዲስ ሰዎች ሚገቡ፣ ሚወጡባቸው፡፡ ከሀገር የሚወጣ፣ የሚሰደድ የሚሰባሰቡባቸው፡፡ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ሚርመሰመሱባቸው፡፡ከነዋሪው በላይ፣ መጪና ሂያጁ ሚበዛባቸው ከተሞች፡፡ እዛነው፣ ሰው እንደዘበት ሚቀበርበት፡፡ ህይወት እርካሽ የሆነበት፡፡ አስክሬን እንደቀልድ አፈር ማስ ማስ ተደርጎ፣ ሚቀበርበት፡፡ አዎ! ወደ እዛ ሄጄ እራሴን
ማጥፋት አለብኝ፡፡

የትኛው የድንበር ከተማ ይሻለኛል? ሞያሌ? መተማ? ሑመራ? አንዳቸውንም ሄጄባቸዋው አላውቅም፡፡ የቱን ልምረጥ? ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ ወደ መተማ መሄድ የተሻለ መስሎ ተሰማኝ፡፡ እዛ ሄጄ፣
እኔነቴን የሚገልፅ መረጃዎቼን ካጠፋሁ በኋላ፣ ሀገራቸውን ተሰናብተው
እንደሚሄዱ ሰዎች፣ እኔም ተሰናብቼ እሄዳለሁ፡፡ እነሱ ይመለሱ ይሆናል፣ እኔ ግን አልመለስም፡፡ እስከ ወዲያኛው እችን አሰልቺና አታካች አለም እሰናበታታለሁ፡፡

በነጋታው ረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ፣ ከአዲስ አበባ ጎጃም በረንዳ ወደ ማርቆስ የሚሄድ አባዱላ ተሳፈርኩ፡፡ ከኋላ ወንበር አንድ የቀረው መቀመጫ ባዶ ነው፡፡ ተቀመጥኩ፡፡ ባህርዳር፣ ደ/ማርቆስ
ወያላው ይጣራል፡፡ እንደተቀመጥኩ ሞባይሌን አውጥቼ፣ የተለመደ
ፌስቡኬን መበርበር ጀመርኩኝ፡፡ እያነበብኩ ላይክና ኮሜንት አደርጋለሁ፡፡ በዚህም ሁኔታዎች ውስጥ ሆኜ፣ በማነበው ነገር ቅፅበታዊ ንዴትና ደስታ ይሰማኛል፡፡ የማወቅ ፍላጎቴም እንደዛው አለ፡፡ ዓለምን ተጠይፌ፣ ስለ ዓለም ለማወቅ ስልኬን እበረብራለሁ፡፡ ምን አይነት ግራ ነገር ነው፡፡ 'ማምሻም እድሜ ነው፣ ሆኖብኝ ይሆን፡፡ ድንገት፣ “እዚህ
ጋር ሰው አለ?” የሚል ድምፅ ተሰማኝ፡፡ ቀና አላልኩም፡፡ ጭንቅላቴን
በመወዝወዝ የለም የሚል ምልክት ሰጠሁ፡፡

የማነበው ነገር ትኩረቴን ስቦታል፡፡ ፌስቡክ የሀገራችንን የፖለቲካ መዘወሪያ መስሏል፡፡ ሰው ሁሉ ፖለቲከኛና አክቲቪስት ሆኗል፡፡ ሀገሪቷ የሚያስፈልጋት ሙያ ጋዜጠኛና ፖለቲከኛ እንደሆነ፣ ሁሉም ሙያውን ትቶ ተመራጭ ጋዜጠኛ፣ የፖለቲካ ተንታኝና
አክቲቪስት ለመሆን ይታትራሉ፡፡ ምን እየሆንን ነው?፣ ፖለቲከኛ ባልሆንም እንደመረጃ ስለዓለም ጉዳይ ባገኘሁት አጋጣሚ እከታተላለሁ፡፡ሶሻል ሚዲያ አላማው የተሻለ ተጠያቂነትና ዲሞክራሲ መገንባትና ማስፈን እንደሆነ እሰማለሁ፡፡ በጣም ጠቃሚ ፈጠራም እንደሆነ ግልፅ
ነው፡፡ ግን የተሻለ ቁጥጥር ሚፈልግ ይመስለኛል፡፡ ሶሻል ሚዲያ በዓለማችን ከተስፋፋ በኋላ፣ ዓለማችን ይበልጥ በቀውስ የተሞላች ይመስለኛል፡፡ ከቱኒዚያ የተነሳው የአረብ አብዮት፣ ሊቢያ፣ ግብፅ፣ የመን እያለ ሀገራችን ገብቷል፡፡ አሁን አሁን ሳስበው አሜሪካንና ዌስተርኖች በእርዳታና በሌላ ዲፕሎማቲክ ጫና ያስፈጽሙት የነበረው የአንጋሽነት “King Maker” ሚና ሀገራቶች ከቻይና ጋር በመተባበር በቀላሉ
አልጠመዘዝ ሲሏቸው ያመጡት አማራጭ ይመስለኛል፡፡

በእርግጥ አሁን አሁን፣ አሜሪካንም ሆነ አውሮፓውያን በአፍሪካም ሆነ በሌሎች አህጉራት ስላሉ ታዳጊ ሀገራት እድገትና
ዴሞክራሲ ይጨነቃሉ ብዬ ማመን እየከበደኝ ነው፡፡ ሀያላን ሀገራቱ፣
ዋናው የሚያስጨንቃቸው የራሳቸው ሀገራት ቋሚ ጥቅምን ማረጋጥ
ይመስላል፡፡ በሊቢያ፣ በኢራቅ፣ በየመንና በሶሪያ የተከሰተውን በዓለም
ታሪክ ታይቶ ማይታወቅ የሰበአዊ ቀውሶችን አይተው እንዳላየ መሆናቸው፣ እነዚህ ሀያላን ሀገራት አላማችን፣ ዓለምን ለሰው ልጆች ሁሉ ለኑሮ የተመቸች ማድረግ ነው' የሚለው ዲስኩር፣ ለሽፋንነት የሚደረግ ባዶ ሽንገላ እንደሆነ እንድናስብ ያስገድዳል፡፡

እንደዚህ እያሰብኩ መኪናችን ሞልቶ፣ መንገድ ጀምረን፣እንጦጦ ኬላ ለፍተሻ እንድንወርድ ታዘዝን፡፡ ከሄድኩበት ሃሳብ ባነንኩ፡፡ፍተሻውን ጨርሰን ወደ መኪናችን ተመልሰን ገባን፡፡እኔ የተቀመጥኩት
ወንበር ላይ አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ተቀምጣለች፡፡ እግሯን ዘወር አድርጋ፣
ወደቦታዬ እንድገባ አሳለፈችኝ፡፡ ቅድም “እዚህ ጋር ሰው አለው?” ያለችኝ
እርሷ ነበረች፡፡ ቀይ፣ ወጣት፣ ቆንጆ ነች፡፡ ሰሞኑን፣ በህይወቴ የመጣብኝ
ምስቅልቅሎሽ ከሴቶች ጋር በተያያዘ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ሴቶች
መጥፊያዬ ናቸው ብያለሁ፡፡ላልደርስባቸው ምያለሁ፡፡ አሁን ሰይጣን
በዚህች የቀይ ቆንጆ ሊፈትነኝ አጠገቤ አስቀምጧታል፡፡ አላደርገውም ብዬ ስልኬን መበርበሬን ቀጠልኩ፡፡ የፌስ ቡክ ወሬ እንደቅድሙ አልጥም አለኝ፡፡ ሃሳቤ ከእርሷ አልወጣ አለ፡፡ የሚሞት ሰው ይፈራል እንዴ?፣ባክህ ዝም ብለህ እድልህን ሞክር ይለኛል ውስጤ፡፡ የስልኬን ዳታ አጠፋሁት፡፡ እንደሚያድን ነብር፣ ሁሉ ነገሬን ወደ እርሷ ቀሰርኩ።
በደንብ ተመለከትኳት፡፡ ጅንስ ሱሪና ኮት ለብሳለች፡፡ እድሜዋ ቢበዛ ሃያዎቹ መጀመሪያ ቢሆን ነው፡፡ ለመተዋወቅ ወሰንኩ፡፡ እንዴት ልጀምር እያልኩ ሳስብ፣ ታፋዎቿ ላይ መፅሀፍ አየሁ፡፡ ታፋዋን ጎሸም አደረኩና፣

“ልየው?” አልኳት፣ እጄን ወደ መፅሐፉ እየጠቆምኩ፡፡

ይቻላል በሚል ጭንቅላቷን ነቀነቀችልኝ፡፡ መፅሀፉን አነሳሁት::የፊት ገፅ ሽፋኑ ላይ ጓድ ኮርኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው የተነሱት ፎቶ ይታያል፡፡ የመፅሀፉ ርዕስ ነበር
ይላል፡፡ በጣም ገረመኝ፡፡ ይህን መፅሀፍ ብዙ ጊዜ መፅሐፍ አዟሪዎች ላይ አይቼዋለሁ፡፡ አንስቼ የጀርባ ፅሁፉን ለማንበብ እንኳ ተነሳሽነቱ አልነበረኝም፡፡ የዛ ትውልድን መፅሐፍት ፈልጌ ነበር የማነበው።ይገርሙኛል፤ ያስቀኑኛል፤ ይደንቁኛልም፡፡ በመንግስት አፍንጫ ስር
የመደራጀት ጥበባቸው፣ ዲሲፕሊናቸው፣ ለድርጅታቸው ያላቸው ፍፁማዊ ታማኝነት፣ ይደንቀኛል፡፡ ስለዚህ፣ ፈልጌ አነባቸዋለሁ።የመንግስቱ ኃ/ማርያምን ጨፍጫፊነትን ይቅር የምልበት ምክንያት
ፍለጋ ግን አላነብም፡፡ ልቤ ዝግ ነው፡፡ ስለዚህ አልገዛሁትም፡፡ እንኳን መፅሐፉን ገዝቼ ላነበው፣ ሚያነበው ሰው ያለ ፀአይመስለኝም ነበር፡፡

“ያንቺ ነው?” አልኳት ተገርሜ፡፡

“አሁን አይደል ከኔ የወሰድከው?” አለችኝ፣ በፈገግታ ነጫጭ ጥርሶቿን ፍልቅቅ አድርጋ፡፡ ፈገግታዋ የልብን ምት የሚጨምር ጨረር ይረጫል፡፡

“ማለቴ ልታነቢው ነው?” በመገረም ጠየኳት፡፡

“እንዴ...! አዎ! ምነው? ችግር አለው?”

ደግማ ፈገግ እያለች፡፡

“ኢሰፓ ቤተሰብ አለሽ?”

“ኧረ የለኝም፡፡” ኪ.ኪ.ኪ...

“ግን፣ ለምን እንዲህ አልከኝ?”

“ሴት፣ የፖለቲካ መፅሀፍ፣ ደግሞ የመንስቱ ኃ/ማርያም ታሪክ፣ በጣም ደንቆኝ ነው!”

“መፅሐፉን አንብበኸዋል ግን?”

“ኧረ በጭራሽ! ሳየው ገና ያንገሸግሸኛል!”

“ብታነበው ግን፣ እርግጠኛ ነኝ እንደዚህ አትጠላውም፡፡”

“ምን ፈልጌ ነው ማነበው?

አልጨፈጨፍኩም እንዲለኝ? ወይስ
ቀይ ሽብር ፅድቅ ነው እንዲለኝ? ለማንኛውም ተይው፡፡ ወዴት ነሽ?”

“ባህርዳር፡፡ አንተስ?”

“ባህር ዳር፣ ከዛ ጎንደር
👍32
“ለስራ ነው?

“አይ እንዲሁ አገር ለማየት፡፡”

“ሀበሻ ቱሪስት ነሀ?”

“ሳይሆን እረፍት ስሆን፣ ጃምቦ ስጠጣ ከመክረም፣ መዞር እወዳለሁ፡፡”

“ጥሩ ልምድ ነው፡፡”

“አንቺስ፣ ለስራ ነው?”

“አይ ወደ ቤተሰብ፣ ወንድሜ ጋር እየሄድኩ ነው፡፡”የባጥ የቆጡን እያወራን፣ ገብረጉራቻ ደርሰን ለምሳ ቆምን፡፡
አብረን ምሳ በላን፡፡ ቡና ጠጣን፡፡ ቶሎ ተላምደናል፡፡ እየተላፋችኝ ማውራት ጀምራለች፡፡ ከምሳ ስንመለስ፣ ወሬ እያለቀብን መጣ፡፡ የወሬ ርዕስ ለመፈለግ ያክል፣ የያዘችውን መፅሀፍ ተቀበልኳትና ማንበብ ጀመርኩ ::

“በኢትዮጵያ የተደረገው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ህዝብን አስቆጣ፤ ተማሪዎች በሰልፍ ጎዳናዎችን ሞሏቸው። ዩኒቨርስቲዎች ተዘጉ፣ ይሄ ሁሉ አመፅና አብዮት አንድ አጭር፣ ቀጭንና ጥቁር ሰው ወደ ስልጣን እያመጣ እንደነበር ግን ማንም አልገመተም ነበር፡፡ አፄው፣ በመንግስቱ ኃ/ማርያም ተተኩ፡፡” መፅሀፉ ከፍተኛ የመሳብ ሀይል አለው፡፡ አጠገቤ
ከተቀመጠችው፣ ላጠምዳት መረቤን ከዘረጋሁባት ውብ በላይ፣ ስቦ ወደራሱ አሰመጠኝ፡፡ ለወሬ መጀመሪያነት የከፈትኩት መፅሀፍ፣ ሳላስበው ዋጠኝ፡፡ እርሷን እስክረሳት ድረስ አስመጠኝ፡፡ የመፅሀፉ ኪነጥበባዊ ደረጃና የመረጃዎቹ ፍሰት፣ ከሽፋን ገፁ እጅግ የላቁ ሆነው አገኘኋቸው፡፡ እጅግ ምርጥ መፅሀፍ ነው፡፡

ድንገት አጠገቤ ያለችው ቆንጆ ልጅ ትከሻዬን ደገፍ አለችብኝ፡፡ድንገጥ ብዬ አየኋት፡፡ ለመተኛት እየተመቻቸች ነው፡፡ የት እንደደረስን፣ ቀና ብዬ በመኪናው መስኮት ወደ ውጭ ተመለከትኩ፤ አባይ በረሃ ገብተናል፡፡ አይፈረድባትም፤ የበረሀው ሙቀት እንቅልፍ ይጫጫናል፡፡
እኔ ግን፣ ለብዙ ጊዜ በጠላሁት መፅሀፍ ተመስጫለሁ፡፡ ሁለት ምዕራፎችን እንደዘበት ወጣኋቸው፡፡ ግሩም መፅሀፍ ነው፡፡ ስለመፅሀፉ ተሳስቻለሁ፡፡እስከዛሬም ደጋግሜ ላነበው ይገባ ነበር፡፡ የአባይ በርሀ መንገድ ይጥመዘመዛል፡፡ መኪናው ከግራ ወደቀኝ ያላጋናል፡፡ ወደ
ዝቅተኛው ቦታ እየቀረብን ስንመጣ፣ ሙቀቱ ጨምረ፡፡ ልጅቷ ከትከሻዬ
ላይ ተንሸራታ፣ታፋዎቼ ላይ ተመቻችታ ተኛች፡፡

አሁን፣ የአባይ ወንዝ በደንብ ይታየን ጀመር፡፡ መፅሀፉን አጥፌ ትኩረቴን አባይ ላይ አደረኩ፡፡ አባይ የአገር ፍቅር የአገር ሲሳይ...፣

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1🔥1
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) #ምዱካን_ስወራ ለመሞት ወስኛለሁ፡፡ ግን፣ ደስተኛ የምመስላቸው ቤተሰቦቼ፣ስኬታማ እንደሆንኩ፣ በደስታ እየኖርኩ እንዳለሁ እያሰቡ እንዲቀሩ፣በጥንቃቄ ዱካዬን አጥፍቼ ነው መሞት ያለብኝ፡፡ ልክ ከህይወታችን፣ቀስ በቀስ ጠፍተው እንደተረሱ ሰዎች፣ የት እንዳሉ ምን እንደሆኑ ትዝ እንደማይሉን ሰዎች፣ ዝም፣ ጭጭ፣ ጭልጥ ብዬ መቅረት…»
#የማየት_ኃይል

ባገኘሁሽ ቅጽበት፥
ባየሁሽ አንዳፍታ፣
የዘመን ትብትቤ፣
ቋጠሮው ተፈታ፤

ተራገፈ ሸክሜ፥
ጠገገልኝ ቁስሌ፣
ተፈወሰ ሕመሜ፤

ገረመኝ!

የመኖር ቁም ነገር፣
የሕይወት ምስጢሩ
በቃል መሠፈሩ፥
በሴት መቋጠሩ።
አቅልለሻልና
የጨቅላውን ስቃይ
ተጋርተሻልና
የምንዱቡን ብካይ
በፃድቃን ክብር ልክ
ይቀበልሽ ሰማይ።

🔘ኢዛና መስፍን🔘
🥰1