አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)


አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞይዞራል፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ አባይ፣ አባይ ሲባል እየሰማሁ ነው ያደኩት፡፡ በውስጤ አባይ ግዙፍ ነው፡፡ ወደ ድልድዩ እየተጠጋን ነው፡፡ አሁን በደንብ ወንዙ ይታየኛል፡፡ የአለም እረጅሙን ወንዝ አባይ...፣ በሱዳን አቋርጦ፣ ግብፅን አጠጥቶ፣ ተርፎ
ሜድትራያንያን ባህር የሚገባው አባይ... ፣ በሁሉም አቅጣጫ ለማየት ሞከርኩ፣ በደንብ ተንጠራራሁ፣ አባይ እንደጠበኩት ግዙፍ አልሆንልህ አለኝ፡፡ ውስጤ አግዝፌው ስለነበር ይሆን?፣ ወይስ ገና ከዚህ ወዲያ ነው ሚገዝፈው...? ይሄን እንዴት እስከዛሬ ሳንገድብ ቆየን? እነዚህ
ሃሳቦች በውስጤ ተሯሯጡ፡፡

ልጅቷ ነቃች፡፡ ዐይኗን እያሻሸች ቀና ብላ አየችኝ፡፡

“እንቅልፋም!” አልኳት፡፡

ፈገግ ብላ፣ “ብዙ ተኛሁ እንዴ?”

“እንጃ፣ እያነበብኩ ነበር፤ አላስተዋልኩም፡፡”

“መፅሀፉ አሪፍ ነው አይደል?”

“በጣም ምርጥ ነው፡፡ ይቅርታ ተሳስቻለሁ፡፡”

“ችግር የለውም፡፡ እንኳን ተመቸህ፡፡”

“እንደውም አልሰጥሽም፤ ወስጄዋለሁ፤” አልኩኝ ፈገግ ብዬ፡፡

“ችግር የለውም፡፡ ሌላ እገዛለሁ፡፡”

“ዋጋውን ግን፣ በእጥፍ እከፍላሁ::”

“በጭራሽ አይሆንም፡፡ እንደውም ስጦታዬ ነው፡፡”

“እንዴ ለምን?፣ምን አድርጌልሽ?››

«እንደ ፍራሽ ተኝቼብህ ለመጣሁት፡፡”

“ከተማሪማ ስጦታ አልቀበልም፤” አልኩኝ ሆን ብዬ፤ ገና አሁን እንተዋወቅ ላለማለት፡፡

“ማነው ተማሪ ናት ያለህ?”

“ውይ ለካ በደንብ ሳንተዋወቅ ነው፤ ወደ ወሬ የገባነው፡፡ ያቤዝ እባላለሁ።”

“ህይወት፡፡ ስምህ ደስ ሲል፡፡ ምን ማለት ነው?”

“እ...፣ በችግር ውስጥ የተወለደና ለችግሩ መፍትሄ የሆነ ማለት
ነው ሲሉ ሰምቻለው፡፡”

“ትርጉሙም ስሙም በጣም ደስ ይላል፡፡”

“ይሆናል፡፡ እኔ ግን እስካሁን ችግር እንጂ፣ የችግር መፍትሄ ሆኜ አላውቅም፡፡”

“ወደፊት ትሆናለሃ፡፡”

ሃሃሃ...ወደፊት ትሆናለህ'፣ ወደፊቴን ላጠፋው እየሄድኩ እንደሆነ ብታውቂ..፣ በውስጤ አልጎመጎምኩ፡፡ ዳግሞ መፅሀፉን ገለጥኩት፡፡ አላባበለኝም፡፡ በፍጥነት ጭልጥ አድርጎ አስመጠኝ፡፡ ላድናት ጥፍሬን ያሾልኩለት ቆንጅዬ፣ ዳግም አጠገቤ እንደሌለች እረሳኋት፡፡
መልሳ ጋደም አለችብኝ፡፡ አሁን ቤተኛ ሆነናል፡፡ ቀጥታ ታፋዎቼ ላይ ተጋደመች፡፡ ቀይ፣ ለጋና ሰልካካ ፊቷን አየሁት፡፡ ያስጎመዣል፡፡ የሹራብ ጃኬቴን አውልቄ እንድትንተራሰው ሰጠኋት፡፡ ተቀበለችኝ፡፡ መፅሀፉ ግን ማግኔት ነው፡፡ መልሶ ወደ ራሱ ይጎትተኛል፡፡ ወታደሩ የህዝቡን አመፅ እንዴት ወደራሱ ጠምዝዞ እንደቀለበሰው፣ አተራረኩ ይገርማል፡፡ ሻለቃ መንግስቱ በደርጉ ምስረታ ስብሰባ ላይ ባደረገው ዲስኩር፣ እንዴት የሰው
ልብ እንደገዛ ማንበብ ይመስጣል፡፡ የዚያው የመጀምሪያ ቀን ዲስኩር
ማሳረጊያ 'ኢትዮጵያ ትቅደም' መፈክር፣ የሀገሪቷ የአስራ ሰባት ዓመት ቋንቋ መሆኑን ማንበብ ይደንቃል፡፡ አብዛኛውም የሃገራችን ፖለቲካ መዘወሪያ ሃሳቦች እንደዚህ ባሉ ቅፅበታዊና ስሜታዊ ሁኔታ ሚፈጠሩ ይሆን እንዴ ብዬ አሰላሰልኩ፡፡

ህይወት ትገላበጣለች፡፡ ታፋዎቼ መሀል ሞቀኝ፡፡ አሁን ትኩረቴ ሲበተን ታወቀኝ፡፡ የሚሰማኝ ሙቀት፣ ካሰመጠኝ ድንቅ መፅሀፍ፣ እየጎተተ አውጥቶ፣ ትኩረቴን ወደ እርሷ እያደረገው ነው፡፡ ስለእርሷ
ማሰብ ጀመርኩ፡፡ እያነበብኩ፣ አንድ እጄን ጭንቅላቷ ላይ ጣልኩት፡፡

ፀጉሯን መደባበስ ጀመርኩ፡፡ በስሱ ፊቷን ዳበስኩት፡፡ ያፍንጫዋን ስልካካነት ወደታች በስሱ ወረድኩት፣ እናት ልጇን እንደምትዳብሰው፤ ፍቅረኛማቾች እንደሚደባበሱት፣ የከንፈሮቿን ጠርዝ እየተከተልኩ በጣቶቼ ጫፍ ዳበስኳቸው፡፡ ዝም፣ ጭጭ፡፡ መልሼ፣ በፀጉሮቿ መሀል
ጣቶቼን ላኳቸው፡፡ አሁን፣ መፅሀፉን ለይስሙላ ነው የያዝኩት፡፡ እያነበብኩት አይደለም፡፡

ስሜቴ እየሞቀ መጥቷል፡፡ እንቅልፍ ካልወሰዳት፣ የተኛችበት ታፋዎቼ መሀከል ያለው እንቅስቃሴ፣ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ አዎ እንቅልፍ ካልወሰዳት፣ እኔ ምንም መናገር አይጠበቅብኝም፡፡ መፅሀፉን ዘግቼ አስቀመጥኩት፡፡ ትኩር ብዬ፣ ቁልቁል እንደ ፍቅረኛ እያየኋት
ነው፡፡ የሌሎች ተሳፋሪዎችን ዐይንና ቀልብ ከሳብን ቆይተናል፡፡ አብረን
የመጣን ፍቅረኛሞች፣ ባልና ሚስት እንጂ፣ በድንገት እዚሁ የተገናኘን
አንመስልም፡፡ ተሳፋሪዎች በአግራሞት እየተመለከቱን ነው፡፡ ህይወት በጣም ቀላል፣ተግባቢና መስህብ ያላት ቆንጆ ነች፡፡ በጣም የምንዋደድ ፍቅረኛሞች እንመስላለን፡፡

ትወስደዋለህ፤ እስጥሃለሁ፤ ያለችኝ ውልብ አለብኝ፡፡ አሁን ለእኔ ጊዜ ስጠኝ መፅሀፉን ሌላ ጊዜ ታነበዋለህ ማለቷ ይሆን? ስሜቴ ሲያድግ ታወቀኝ፡፡ አሁን እንኳን ማንበብ፣ ዐይኔን እንኳ ከእርሷ መንቀል አልቻልኩም፡፡ እዳብሳታለሁ፡፡ እየሰማች ከሆነ፣ ታፋዎቼ መሀከል
የተፈጠረው እሳተ ጎሞራ፣ ስሜቴን በማያወላዳ መልኩ ያሳብቅልኛል፡፡

ማስረዳት አይጠበቅብኝም፡፡ እንቅልፍ እንዳልወስዳት ማረጋገጥ አለብኝ፡፡
ስሜቴን እየሰማችው መሆን አለመሆኑን ማወቅ አለብኝ፡፡ ትኩር ብዬ አየኋት፡፡ ቁልቁል የተንሰለከከ አፍንጫዋን በጣቶቼ በፍቅር እየዳሰስኩት ወረድኩኝ፡፡ ቁልቁል ወርጄ ጫፍ ላይ ስደርስ፣ በጣቶቼ ቀስ ብዬ አፍንጫዋን ጭምቅ፣ እፍን አደረኳት፡፡ ወዲያው ቀና ብላ፣

“ልትገለኝ ነው እንዴ?” አለችኝ፡፡

ፈገግ ብዬ፣ “እና ጥለሽኝ ስትተኚ...”

“አንተስ ጥለኸኝ በመፅሃፉ ስትመሰጥ አልነበር፡፡”

“የእውነት፡፡ መፅሀፉ ውበትሽን ሚገዳደር ነው፡፡”

“ፖለቲካ ትወዳለህ ማለት ነው፡፡”

“እንደዛ ሳይሆን፣ የያ ትውልድ ታሪክ ይማርከኛል፡፡

ችሎታቸው፣ ዲሲፕሊናቸው፣ የሀገር ፍቅራቸው፣ አሁን እንኳን ሀገር እየመሩም እየተቃወሙም ያሉት እነሱ እኮ ናቸው፡፡”

“አሁን ወጣቱ ሁሉ ፖለቲከኛ አይደል እንዴ?”

“ማለቴ፣ አሁን ያለችው ኢትዮጵያ የዛ ትውልድ የአዕምሮ ውጤትና የእጅ ስራ እየሆነችኮ ነው፡፡ ያ ትውልድ መሬት ላራሹ ብሎ ፊውዳሊዝምን በታተነ፡፡ ኢትዮጵያዊ ማነው ብሎ ሞግቶ፣ የብሄር ብሄረሰብን መልክ፣ መልኬ ነው ብላ እምትቀበል ኢትዮጵያን እጇን ጠምዝዞ እየገነባ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረስብ ነች ብለው፣ መሀል አዲስ አበባ ላይ የብሄር ብሄረሰብ አደባባይ አኑረዋል፡፡ ወደድንም ጠላንም
አሻራ ያላቸው ትልቅ ትውልዶች ናቸው፡፡ እኛ በእነሱ ጥላ ተከልለን አሻራ ቢስ ሆነን ልናልፍ ነው፡፡”

“ግን ያ ትውልድ፣ ያልከው ብቻ አይደለም እኮ፡፡ አስተዋዩና ባለ ልዩ አምሮ ያልከው ያ ትውልድ፣ እርስ በርሱ ተባልቷል፡፡ ወንድም ወንድሙን ገሏል፧ ኢትዮጵያዊ ባህል ባልሆነ ጭካኔ ሀገሪቷ የደም
አኬልዳማ አድርጓታል፡፡ ዘጠና ዘጠኝ ከመቶ በላይ አማኝ በሆነ ማሀበረሰብ፣ ከማርክስ ሌኒኒስት አስተምሮ ተነስቶ፣ ሀይማኖት የቀኝ ገዢዎች የማህበረሰብ ማደንዘዣ ድሪቶ ነው፤ አውልቁና ጣሉት አለ፡፡ ማህበረሰቡን እሴት አልባ አደረገው፡፡ መሰረቅ ባህላችን ሆነ፡፡አረ ስንቱን ..::”

“የእርስ በእርስ ጦርነቱን እንኳን ተይው፣ እንደ አንድ የማህበረሰቡ ባህልና እሴት አብሮን የኖረ ነው፡፡ ግን ቆይ ቆይ፣ ሀይማኖት ማህበረሰባችን አላደነዘዘም እያልሽኝ ነው? የሆነ ችግር ሲያጋጥመው
ለመፍታት ከመጣር ይልቅ፣ ሁሉ ለበጎ ነው ብሎ ችግሩን ተላምዶ እንዲኖር ሀይማኖት አላደረገውም እያልሽኝ ነው?”

‹‹ሀይማኖታችን የሚለው ያልሰራ እርሱ አይብላ ነው፡፡››

“ኧረ..? እና ለዚህ ነው፣ ባልጠፋ ጊዜ በታህሳስ የዘራውን ሰብል እንዳይሰበስብ የሰማይ ወፎች አይዘሩም አያጭዱም የሰማይ አባታቸው ይመግባቸዋል እንጂ፤ ብሎ የሚስብክ ቤተክርስቲያን ማህበረሰብን
👍41
አላደነዘዘም፣ አላሳነፈም እያልሽኝ ነው?”

“ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ባለ ውለታ ነች፡፡ ፊደልን ቀርፃ እውቀት ያስፋፋች ሀገራችንን ከቀኝ ግዛት እንድንከላከል ያነቃች።የሀገራችንን የደን ሀብት ተጠብቆ እንዲቆይ የረዳች፡፡ ሀገር በቀል እውቀት እንዲስፋፋ ጥንስስ የሆነች፡፡ ኢትዮጵያዊ ዜማን የፈጠረች፡፡ዓለም ዜማን በፅሁፍ ማስፈር ሳያውቅ እነ ቅዱስ ያሬድ የዛሬ አንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመት ዜማን ደርሰው በፅሁፍ እንዲያሰፍሩ ኮትኩታ
ያሳደገች ቤተክርስቲያን ነች፡፡ተዉ እንጂ አወቅን ብላችሁ ቤተክርስቲያንን ውለታ ቢስ አታድርጓት፤” አለችኝ፡፡ ሥሜታዊ እየሆነች ነው፡፡

“ወዴት ወዴት..? ቤተክርስቲያን ውለታ የላትም አላልኩም፡፡ አንቺ ያልሻቸው በሙሉ እውነት ናቸው፡፡መቶ በመቶ
እስማማባቸዋለሁ፡፡ ሁሉም ነገር ጥሩ ጎን እንዳለው ሁሉ፣ መጥፎም ሊኖረው ይችላል፡፡ ቤተክርስቲያንም እንደዛው፡፡ ጥያቄው ሁሉንም በእውቀት መመርመር አለብን ነው፡፡ አይነኬ የምንላቸው ነገሮች፣
ለመመርመር የምንፈራቸው ነገሮች፣ የዘመናት ችግራችን ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡”

“ቆይ ፊደል ቆጥራ ባስተማረች፣ ቤተክርስቲያንን ተማርን ብላችሁ መልሳችሁ እርሷ ላይ የምትዘምቱት ምን ይሁን ብላችሁ ነው?

በቃ አወቅን ካላችሁ የሚጠቅም ስራ ስሩ፡፡ እጃችሁን ከቤተከርስቲያን
አንሱ!” ተንገሸገሸች፡፡

“እንዲህ የምትናደጂ ከሆነ ወሬ እንቀይር፡፡”

“ኧረ እኔ አልተናደድኩም፡፡ ምን ያናድደኛል?”

“እንዴ! ከዚህ በላይ ምን ትሆኚ? ተንጨረጨርሽ እኮ፡፡”

“ተናድጄ ሳይሆን፣ ሁሉም አወኩ ባይ ተነስቶ እጁን ቤተክርስቲያን ላይ ሲያነሳ ያበሳጨኛል፡፡”

“ሲጀመር፣ እኔ ተማርኩ ባይ አይደለሁም ሀይማኖት ሴንሲቲቭ ኢሹ' እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ግን እንደማህበረሰብ የባህል
አብዮት ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ፡፡ ለምሳሌ፤ የመስራት ባህላችን፣የሚስራን ከማበረታታት ይልቅ መንቀፍ፣ ተነጋግሮ የመግባባት ልምዳችን፣ በአጠቃላይ ማህበራዊ ባህሎቻችን መፈተሽ አለባቸው ባይ ነኝ፡፡ እኛ ሀገር ደግሞ፣ የባህላችን መነሻም፣ መንገዱም፣ መድረሻምውም ሀይማኖት ነው። እሱን ካልፈተሸን የትም አንደርስም፡፡”

“እስቲ ቆይ፣ ቤተክርስቲያ ምን እንዳደረገቻችሁ አንድ ሁለት ብለህ አስረዳኝ፡፡” ፊቷ ላይ የንዴት ነበልባል ተንቀለቀለ፡፡ አባይ በረሃን ወጥተን የደጀን ከተማን እየተጨቃጨቅን ሳናያት አለፍን፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አንድ ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞይዞራል፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ አባይ፣ አባይ ሲባል እየሰማሁ ነው ያደኩት፡፡ በውስጤ አባይ ግዙፍ ነው፡፡ ወደ ድልድዩ እየተጠጋን ነው፡፡ አሁን በደንብ ወንዙ ይታየኛል፡፡ የአለም እረጅሙን ወንዝ አባይ...፣ በሱዳን አቋርጦ፣ ግብፅን አጠጥቶ፣ ተርፎ ሜድትራያንያን ባህር የሚገባው አባይ... ፣…»
#ሰመመን


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...“ይቺ በመቀጨጭ ላይ ያለችዋ ” አሉ ዮናታን' ወደ ቆርቆሮው ውስጥ በጣታቸው እያመለከቱ።

“ እም ፡ አዎ ከእንግዲህ የምታድግ አትመስልም ”አሉ ዶክተር አጥናፉ ፥ ብዙም ባልተደነቀ ስሜት ።

“ ከምን የመጣ ይመስልሃል ? ” አሉ ዮናታን ፡ ዐይናቸውን ወደ እስጉብኝው እያሸጋገሩ ።

“ አካባቢው ኣልተስማማት ይሆናላ ! ” አሉ ዶክተር አጥናፉ ፡ በቀልድ ዐይነት ! “ ወይም ደግሞ ፍሬዋ ከጓደኞቿ ተለይታ በተለየ ዐፈር ውስጥ መብቀል ፈልጋ ይሆናል ። ”

ከት ብሎም ባይስቅ እስጐብኝው ፈገግ አለ ። ዮናታን ግን የተቋጠረው ግንባራቸው አልተፈታም " ይብሱን ነገሩን
አጠንክረው
“ የአካባቢም ተጽፏኖ ሆና የዐፈሩ አለመማማት ፥ወይም ሌላ ችግር ፡ የስንዴዋ መቀጨጭ ከአያያዝ ግድየለሽ
ነት የመጣ ነው ። ገና ከእንጭጭነት ችግሯን አስተውሉ አካባቢዋን ወይም አፈሯን መለወጥ ቢቻል ኖሮ ለዚህ አት
ደርስም ነበር ። ግን አንድ ነች ። አንድ ነገር አንድ ነውና አብዛኛውን ጊዜ አናስብበትም ። አናስተውሰውም ። ጣሳው ሙሉ ተክል ሊበላሽ ቢሆን ኖሮ ግን ወዲያው መፍትሔ በተ ፈለገለት ነበር

አስጐብኝው በድንጋጤ ክው ብሎ ቀረ አምርረዋል ወይሰ ይቀልዳሉ ? ” አለ በልቡ እሱም ። አማካሪው ዶክተር ኤጥናፉ ቸል ያሉትን ነገር ዮናታን አምርረው መያዛቸው ምክንያቱ አልገባህ አለው ። “ ምነው ባልጋበዝኳችው ! ” አለ በልቡ ፡ አነጋገራቸው ዶክተር አጥናፉን
ይላውጥብኛል ብሎ ስለፈራ ዮናታንን በጥላቻ እያያቸው

“ ይህ እኮ አብዛኛውን ጊዜ ሊደርስ የሚችል አጋጣሚ ነው ። ደግሞስ የአንዱ መቀጨጭ ምን ያህል ይጎዳል ብለህ
ነው ? የዐፈሩ ተጽዕኖ በአብዛኛው ስንዴ ዕድገት ሲለካ ይችላል ዶክተር ፡ አሁንም ለነጎሩ ክብዶት ሳይሰጠት ።

“ ይጐዳል እንጂ እንዴት አይጐዳም ?” አሉ ዮናታን አምርረው ። “ የቆርቆሮው ተክል እኮ ስምንት የምታሰኘው
ይህቺ አንዷ ስትጨርስ ነበር ስትጐድል ግን ሰባት ታረገዋለች።አንድ ሳንቲም “ ዋጋ የለውም” እንላለን ። ግን “ ዋጋ
እንዳልው የምንረዳው አራት ሳንቲም ይዘን ስንቀር ነው ”

አስጐብኝው የባሰውን በጥላቻ ገላመጣቸው ። እሳቸው ግን ልብ አላሉትም ። እሱን መጉዳታቸውም አልታወቃችውም ። ዶክተር አጥናፉ ራሳቸው፣ “ሰውዬው አበደ እንዴ?”
በማለት ዐይነት በሆዳቸው እየሣቁ ፥ ምንም ሊጠይቁ ወይም ሊናገሩ ስላልቻሉ ዝም አሉ ።

ከጥቂት ዝምታ በኋላ ዮናታን ልምጭጭ ፈገግታ እያሳዩ' በምጸታዊ አነጋገር “ አየህ የአቤልም ነገር እንዲሁ ነው ” አሏቸው ።

ዶክተር አጥናፉ የዮናታን ውስጣዊ ስሜት እንዲህ የተለዋወጠበት ምክንያት ያው ገባቸው ። ስለ አቤል ጉዳይ ደጋግመው አነጋግረዋቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ለጉዳዩ ብዙም ክብደት ወይም አትኩሮት ባለመስጠት ቸል ብለውት ስለቆዩ
አሁን ጥያቄም ይሁን መልስ ማንሣት አልፈለጉም። ሐሳባቸውን ሁሉ ወደ ተክሉ በመሰብሰብ ዐይነት ከአስጐብኝው
ጋር ሐሳብ በመለዋወጥ ዮናታን የተነሡበትን ሐሳብ ለማዘናጋት ሞከሩ ። ይሁን እንጂ ፥ ዮናታን ውስጥ የሚንቦገቦገው ሐሳብ በቀላሉ የሚበርድ አልነበረም። ጉብኝቱን ጨርሰው
ከተክሉ ቤት ሲወጡ እንደ ገና አነሡባቸው ።

“ ሁላችሁም የዚህን ልጅ ጉዳይ ቸል ማለታችሁ ነው ? ያቤልን?እንዴትነው? አሁንም አልተሻለው?” አሉ ዶክተር
አጥናፉ ሸሽተው የማያመልጡት ነገር መሆኑን ገምተው ።

ይሻለዋል ? ጉንፋን ” ኮ አይደለም ያመመው ።ይህኛው አነጋገራቸው ቁጣ ብቻ ሳይሆን ተስፋ መቁረጥም
ነበረበት ።

የዮናታን አነጋገር ዶክተር አጥናፉን አላስቆጣቸውም ።የቅርብ ጓደኝነት ስላላቸው አንዳቸው የአንዳቸውን ጸባይ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡ዮናታን ከውስጥ ሥቀው ከላይ ጥርሳቸውን ማሳየት አይችሉም ። የተማረሩበትን ወይም የበሽቁበትን ነገር ማንም ፊት ይሁን ከማንም ጋር ፊትለፊት በቁጣ ተናግረው ነው የሚወጡት ። ከዚያ ንዴቱ ቢበርድላቸው ያው ሰው አክባሪነታችው ፍቅር የተሞላበት ሰላምታችሙ
ዮናታንነታቸው ይመለሳል ። ነገር ግን የዚህ ልጅጉዳይ ይህን ያህል ለምን እንዳንገበገባቸው ዶክተር አጥናፉ ጥርት ብሎ ሊታያቸው አልቻለም ።

“ ችግሩ ኮ! ” አሉ ዶክተር አጥናፉ፥ የዮናታንን ቁጣ ማስታገሥ በሚችል ለዘብ ያለ አነጋገር ። “ ችግሩ የሁሉም አለመተባበር ነው ። ከአሁን በፊት በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዲህ ዐይነት ጉዳይ ትልቅ አትኩሮት ተሰጥቶት
ስላልተሠራ አሁንም ...

ዮናታን አላስጨረሳቸውም ።

“ እኔም እኮ የምለው ይህንኑ ነው ። ለምን አትኩሮት አይሰጠውም ? በማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ካሉት ችግሮች አንዱ
አይደለም ወይ? አየህ ! ፍቅር ሲሠምር ፥ ሲገኝ ሲያብብ ደስታ ፍሥሐ ነው ። ከመገኘቱ በፊት ወይም ተግኝቶ ሲጠፋ ኃይለኛ ጥማት ፡ ሥቃይ ሕመም ነው ፥ ” አሉና፡ ነገሩን ከውሉጋር እንደማያያዝ ትንሽ ካሰቡ በኋላ ፥ “ አዎ ! እና ፥ ምንም
ይሁን ምን የ ግለሰብን ከዓላማው ወይም ከግቡ የሚያዘናጋ ወይም ራሱን የሚያስጠላ ሁኔታ እስከሆነ ድረስ መድኃኒቱ መፈለግ አለበት አሁን አቤል በዚህ ሁኔታ ተጨናግፎ ትምህርቱን ቢያቋርጥ ወይም ተደባብሶ ቢመረቅ ፡ ሁለተኛ ወደ ትምህርትና ምርምር ዓለም ፊቱን እንደማይመልስ አታውቅም ? ”

“ እሱ እንኳን በጤናቸው የሚመረቁትም የአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ጸባይ ነው ። ሺ አስመርቀናል ፤ ነገር ግን
ምንም ተአምር የሠራ አላየንም አሉ ዶክተር አጥናፉ በንቀትና ተስፋ በቆረጠ ስሜት ።

ይህ የሚሆነው ለምን ይመስልሃል ? ! በእኔ ግምት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቶቻቸውን በፍቅር እንዲጀምሩ
ስለማናደርጋቸው ነው ።ሳያስቡት ዶክተር አጥናፉ ቢሮ ስለ ደረሱ ። በሩን ለመ
ክፈት ቁልፉን እየጠመዘዙ አሁንም በተሰላቸና ነገሩን ቶሎ ለመቁረጥ በዳዳ ስሜት • “ ብቻ ሁሉም ነገሩን እንዳንተ
ቢያስብበት ምናልባት ውጤት ያገኝ ይሆናል ። ግን እንዳየሁት ይህን ጉዳይ ብሎ ኮሚቴ ላይ አቅርቦ መፍትሔ ለመ
ፈለግ የሚሻ ሰው እንጂ ”

“ ይህ ከምን የመጣ ይመስልሃል ? ” አሉ ዮናታን ፥ ተከትለዋቸው ወደ ቢሮ ውስጥ እየገቡ ፤ ይህ ራሱ ምሁርነታችን የሚያስከትልብን በሽታ ራሳችንን በጣም ከፍ አድርገን ስለምንግምት ከኛ በኋላ ሰው የሚፈጠር አይመስለንም ። ዐይናችንን ገልጠን ከተማሪዎቻችን መሐል ታላላቅ ሰዎች ሊበቅሉ እንደሚችሉ ማየትና መገመት አለብን ።
ይህ ስሜት ሲኖረን ብቻ ነው ተማሪዎቻችን እንቅፋት እንዳይመታቸው ልንጠነቀቅላቸው የምንችለው ”

“ ስደበና! ” አሉና ዶክተር አጥናፉ በቀልድ ፡ “ ለማንኛውም እስኪ ቁጭ በል” ሲሉ ዮናታንን ጋበዟቸው ።

“ አልቀመጥም ” አሉ ዮናታን ሰዓታቸውን እየተመለከቱ። “ ኦ! እንዲያውም ሰዓት አሳለፍን ። በአሥር ሰዓት አንድ ተማሪ ቀጥሬ ነበር።

“ እሺ እስቲ እንግዲህ በሚቻለን መንገድ እንታግሳለና ! ” አሉ ዶክተር አጥናፉ " ጉዳዩ ከውስጥ ባይፈነቅላቸውም ዮናታንን ለማስደስት ያህል "

“ በውነት እንዲያው በሚቻለን መንገድ ይህንን ልጅ መርዳት አለብን ። እባክህ ቸል አትበል ” አሉ ዮናታንም ረጋ ባለ አንደበትና ረዳት በሚፈልግ ስሜት ወደ
ከዚያ ፥
ወዲያው ወጥተው በመኪናቸው ወደ ስድስት ኪሎ በረሩ ። ከቢሮአቸው ሲደርሱ እስክንድር መዝጊያን
ተደግፎ ቆሞ አገኙት።

““ ሶሪ ዘግየሁብህ አይደለም ? ” አሉት በሩን ለመክፈት እየተቻኮሉ ። ዐሥር ደቂቃ አሳልፈውበት ነበር ።ጠዋት ገለጻ ክፍላቸው ውስጥ ክፍለ ጊዜኣቸውን ጨርሰው ሲወጡ ነበር በዚህ ሰዓት እንዲያገኛቸው የቀጠሩት ። የፈለጉት ለአቤል ጉዳይ መሆኑን ፈጽሞ አልተጠራ
ጠረም ምክንያቱም አቤል ከእሳቸው ገለጻ ክፍለ ጊዜ ሦስቱን ቀን
በተከታታይ አልገባም ። ክፍል ውስጥ ቢጠይቁት እስክንድር የሰጣቸው መልስ " ራሱን ትንሽ ስላመመው ነው ”ብሎ ነበር : ነግር ግን ደጋግሞ መቅረቱ ከዚህ የከፋ ሁኔታ ቢያጋጥመው ነው ብለው ስላሰቡ ስለሱ ሊጠይቁት ነው የቀጠሩት።

“ ስለ አቤል ልጠይቅህ ነበር'ኮ” አሉት ዮናታን ገና ቁጭ ከማለታቸው ፡ “ በእርግጥ በጠናው ነው ? ”

እስክንድር የተጠየቀው ያው የጠበቀውን ነገር ቢሆንም ስለ አቤል መስማትም ሆነ መናገር የማይፈልግበት ወቅት ነበር ። ሁኔታው ያበሽቀዋል ። ምንም ግልጽ የሆነለት ነግር የለም ። እንደጓኝነቱ ቀርቦ ቢያዋየው ፡ አባትነት በተሞላው ሁኔታ ቢያስታምመውም ፥ ቢያሻሽውም ፡ ቢኮረኩረውም ከአቤል ጠብ ያለ ነገር የለም ። አቤል አይናገርም ።አቤል ታፍኖ መሞት የሚፈልግ ሰው ነው ።

ስለ እሱ ሊጠይቁኝ እንደሆነ ጎብቶኛል ” አለ እስክንድር በቀደም እለት ምግብ አዳራሽ ሲገባ የሆነ ነገር አደናቅፎት ወድቆ ነበር ። ያን ያህል ጉዳት እንኳ አላገኘውም ፤ግን እንጃ ! ክፍልም አልገባም አለ ተኝቶ ነው የሚውለው
የመንፈስ መረበሽ መሰለኝ ።

“ እህ ! እንዲያ ነው ? ” አሉ ዮናታን ነገሩ ልባቸውን ቢከብደውም ኀዝናቸውን ለመደበቅ ሞክረው ምን መንፈሱ የተጐዳ ሰው'ኮ ዕንቅፋትም ይበቃዋል ። ”

“ እንደዚያ ሆኖ ነው መሰለኝ ”

ዮናታን ለደቂቃ ያህል ዝም አሉ : ብዙ ነገር ሐሳባቸው ውስጥ ብዙ ነገር እየተተራመሰባቸው ነበር እስክንድር የዮናታን ስሜት ምን ያህል ጭንቀት እንዶ ተወጣጠረ ከገጽታቸው ላይ ማንበብ ችሏል ። “ ይህን ያህል ለአንድ ተማሪ መጨነቃችን ምንድነው ? ” ሲል አሰበ ። ነገር ግን የአቤል ሁኔታ እሱን ራሱን እንዳስጨነቀው ባሰበ ጊዜ ዮናታንም ተመሳሳይ ስሜት ሊያድርባቸው እንደሚችል ገመተ ። ሐቀኛ ምሁር ነኝ
የሚተካውን ጠንካራ ተማሪ በጥቃቅን ማኅበራዊ ችግር ተደናቅፎ ሲቀር ማየት አይፈልግም ።

የዮናታን ሁኔታ ፡ በእስክንድር ስሜት ወስጥ አንዳች ግፊት ፈጠረበት “ ማንኛውንም መሥዋዕትነት ከፍሎ አቤልን ማዳን !” ...ግን እንዴት ? መፍትሔ ከመፈለግማ እስከ አሁንም አልቦዘነም ነበር ። “ በቅርቡ ከማርታ ጋር መተዋወቁ ምናልባት ለመፍትሔው ጥርጊያ መንገድ ይሆናል ብሎ ገመተ ። በሳምንቱ ውስጥ ከማርታ ጋር በሩቅ አንገት ከመሰበር አልፈው ሞቅ ያለ ሰላምታ መለዋወጥ ጀምረዋል።እንዲያውም ፈገግታዋ እየሞቀው ዐይኗ ወንድነቱን እየተፈታተነው በዳሌዋ ላይ በልቡ ዝቶባታል ። “ በእሷስ ድርብ ሚና ነው የምጫወተው ” ብሎ አስቧል ።

ባገኘችው ቁጥር ስለ አቤል ትጠይቀዋለች ። አቅልሎ ይመልስላታል ። ትዕግሥትንም ከእሷ ጋር ስለሚያገኛት
ሰላም ይላታል ። ሰላም ትለዋለች። ስለ አቤል ግን ጠይቃውም አታውቅም። ለአፍታ ያህልም ቢሆን ከማርታ ጋር ጨዋታ ሲያነሣ እንኳ አብራቸው አትሳተፍም ። ፈንጠር ብላ ቆማ
ትጠብቃታለች ። ይሁን እንጂ እሷም ፍቅሯን አምቃ እንደምትሠቃይ እስክንድር የሰውነቷን መክሳትና መላ አኳኃኗን በማስተዋል መገመት ችሏል መጀመሪያ ላይ ዝምታዋ አሰፈራርቶት ነበር ። በኋላ ግን አቤል በማርታ ላይ ያለውን ዐይነት መጥፎ ስሜት ትዕግሥት በእሱ በእስክንድር ላይ እንደ ሌላት ከሰሳምታ አለዋወጧ ግብቶታል ።

ታዲያ እንዴት ይደርሳል ? ብዙ ገለጻ አምልጦታል ።ሳምንት ቀላል ጊዜ አይደለም ” ሲሉ ዮናታን የጸጥታውን
አየር አደፈረሱት ።

“ እሱ እንኳ እኔ የወሰድኩትን ማስታወሻ እያነበበ ከመጻሕፍት ጋር ሲያገናዝብ ይደርስብናል ” አለና እስክንድር መናገር የፈለግወን ሳይጨርስ አንድ ነገር ራሱን
መታው ። ይህን መናገር የደፈረው የቀድሞው አቤል በጭንቅላቱ ወስጥ ስለ ተቀረጸ ነው ። በርግጥም አቤል በተለይ
የቀለም ትምህርትን ለመረዳት ፈጣን ነበር ብሩህ አእምሮ ነበረው ። አሁን ግን የብሩህ አእምሮው ዐይኖች በሆነ ነገር
ተሸፍነዋል ። የብሩህ አእምሮው ልብ በሆነ ነገር ተደፍኗል እናም እስክንድር ይህ ሐሳብ ድንገት በታየው ጊዜ ለዮናታን አጉል ቃል እንዳይገባ ፈርቶ፡ “ ብቻ እንጃ” አላቸው "በሚያመነታ ስሜት ።

“ እንዴት ? ” አሉ ዮናታን "

💥ይቀጥላል💥
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“ጨዋታ እንቀይር፡፡ በሀይማኖት ተከራክሮ፣ መቀያየም ካልሆነ መተማመን ማይታሰብ ነው፡፡”

“እሺ! ደስ እንዳለህ፡፡ ግን ሳስብህ ልብህ በውጪው ባህል የሸፈተ ይመስላል፡፡ ሚስትህ ፈረንጅ ነች እንዴ...?”

“ኧረ ሚስት የለኝም፡፡”

“ሚስትም ባይሆን ፍቅረኛ፡፡”

“ፍቅረኛም የለኝም፡፡”

“እሺ፣ ፈረንጅ ጠብሰህ ታውቃለህ?” ያን ፈገግታዋን ፍልቅቅ አደረገችልኝ፡፡

“እንደሱማ፣ አንድ ሁለቴ አይጠፋም፡፡”

“እውነት..?! ምናቸው ደስ ብሎህ?

ከአበሻ እንዴት በለጡብህ?”

ፊቷን ኮሶ እንደሚጠጣ ሰው ከስክሳ አከታትላ ጠየቀችኝ፡፡

“እንደኔ እብድ ናቸው፡፡ ከፈለጉሽ እራሳቸው ይጠብሱሻል፡፡ አስር
ገሰስ አያበዙም፡፡”

“እራሳቸው ይጠብሳሉ? እንደሱ አጋጥሞህ ያውቃል? በናትህ
ንገረኝ?” እንዳወራት ፍልቅልቅ ፈገግታዋን ቀብድ ከፈለችኝ፡፡

“እሺ፡፡ አንዴ አብራኝ የምትስራ ባልደረባ
ነበረችኝ፡፡ እንቀራረባለን፡፡”

“እሺ...”

“አብረን እንሰራለን፤ አብረን እንበላለን፡፡ አንድ ቀን፣ አስቸኳይ ስራ እየሰራን፣ ምሳ ደረሰ፡፡ እራበን፡፡ ስራው አሰቸኳይ ስለነበር ላፕቶፑን ይዘን እየሰራን ምሳ ልንበላ ወጣን፡፡”

“እሺ..”

እየሰራን ምሳ መጣ፡፡ እኔ እየበላሁ ሃሳብ አዋጣለሁ፡፡ እርሷ እየፃፈች አልፎ አልፎ ትጎርሳለች፡፡ ትንሽ እንደበላን፤
'አበሻ ጥሩ ባህል አለው፤ አለችኝ ::

ምንድን ነው እሱ?” አልኳት፡፡

ሲበላ ይጎራረሳል፡፡ አለችኝ፡፡

በአሽሙሯ በጣም ተገርሜ ሳቅኩና አጎርሳት ጀመር፡፡ ሳጎርሳት ሆን ብላ፣ ጣቶቼንም በስስ ከንፈሮቿ ላሰቻቸው፡፡ ቀና ብዬ ሳያት፣በመሽኮርመም ፈገግ አለች፡፡ የሆነ አዲስ ስሜት ወረረኝ፡፡ ከስራ
ባልደረባነቷ በተለየ፣ በሌላ ስሜት አሰብኳት፡፡ ማታ አስቸኳይ ስራውን
ስለጨረስን፣ እናክብረው፣ ልጋብዝህ አለችኝና ሞቅ እስኪለን ስንጠጣ፣
ስንጫወት፣ ስንስቅ አመሸን፡፡ ሲመሽ መኪናዋ ድረስ ሸኘኋት፡፡ እንድገባ ጋበዘችኝ፡፡ ገባሁ፤ ሳታስፈቅደኝ ትስመኝ ጀመር፡፡ አለተቃወምኳትም፡፡በቃ ተጀመረ፡ ከዛ ቀን በኋላ፣ ዛሬኮ የደሞዝ ቀን ነው፣ አርብ ነው፣ ደብሮናል፣ ብዙ ስራ ሰርተናል...፣ ተያይዞ መውጣት ሆነ፡፡”

“እብድ ነህ፡፡”

“አንዳንዴ አዎ፡፡ ግን፣ ሁሌም እብድ ብሆን ደስ ይለኛል፡፡”

“ማለት?”

“ደስ ደስ የሚሉ ነገሮችን የምሰራው፣ እብድ ስሆን ነዋ፡፡ ያለበለዛ ይሰለቸኛል፤ ያስጠላኛል፤ ውስጤ ይጠወልጋል፤ የመኖር ለዛው ይጠፋብኛል፡፡”

“ሆ ...፣ ቆይ አሁን እብድ ነህ...?” ሳቀችብኝ፡፡

“ሃ...ሃ...ሃ.... በጣም አታስቂኝ፤ ልትሸሺኝ ነው?” ድንገት ንዴት ተሰማኝ፡፡

“እና...፣ አስፈራራኸኝ እኮ፡፡” ይባስ ተበሳጨሁ። የተማረች አንባቢ ብዬ አፌን የከፈትኩላት፣ ቀልድ ማይገባት እንጭጭ ነች፡፡

“አታስቢ እናቱ፣ እኔው ቀድሜ እሸሽሻለሁ፡፡”

“ኧረ ባክህ?” አለችኝ፡፡

አልመለስኩላትም፡፡ ወደ ውስጤ ተወሸኩኝ፡፡ ባወራሁላት ነገር ማንነቴን የገመተችኝ መስሎ ተሰማኝ፡፡ እየቆየ በጣም እየተናደድኩና እየተበሳጨሁ መጣሁ፡፡ በዝምታዬ ውስጥ ንዴቴ ይንቀለቀል ጀመር፡፡ዝምታዬ ያሰፈራል። ደንግጣ ፀጥ አለች፡፡ ወሬ ጠፋባት፡፡ ልጅቷ በአንዴ አስጠላችኝ፡፡ እረጅም መንገድ በፀጥታ ተጓዝን፡፡ አስራ ሁለት ሰዐት አልፎ ለዐይን ያዝ ማድረግ ጀምሯል፡፡ እንደዛ ልቤንና ውስጤን ያቆመ
ውበቷ፣ እንደጉም በኖ ጠፋ። ማርቆስ ደረስን፡፡

“እንቺ መፅሃፍሽን!” አልኳት፡፡

“ስጦታዬ ነው፣ አንብበው፡፡”

“አመሰግናለሁ! ገዝቼ አነበዋለሁ፤ ስጦታሽ አያስፈልገኝም፡፡” ብዬ መፅሃፉን ገፈተርኩላት፡፡

“ቆይ ምንድን ነው ያስቀየምኩህ?
በአንዴ እንዲህ የተለወጥከው፡፡”

“ምንም አላጠፋሽም፡፡ ፈልጌው ነው፡፡”

“ኧረ ይደብራል፡፡ እሺ ካስቀየምኩህ ይቅርታ!”

“አላስቀየምሽኝም፡፡ ይቅርታም አያስፈልግም፡፡”

መኪናው ሰው ለማውረድ ቆመ፡፡ አሳልፊኝ ብዬ፣ ገፈታትሪያት ልወርድ ስል፣ መኪናው ተመልሶ ሲንቀሳቀስ፣ በጀርባዬ ልደፋ ስል፣ ከኋላ ደገፈችኝ፡፡ መንጭቂያት፣ በራሴ እንደቆመ ሆንኩኝ፡፡

ሰዉ “ኧረ ቆይ ወራጅ አለ!” ብሎ ጮኸ፡፡

“ዐይን የለህም?፣ ወራጅ እየወረደ ምትነዳው? መሃይም” አምባረኩበት፡፡

“የወረደው ሰውዬ ነው፣ ወራጅ ያለኝ፤” አለ እረዳቱ፣ በሩን እየከፈተልኝ፡፡

“እና፣ ዞር ብለህ አታይም! ደደብ! እዚህ የማንም መሃይም ከየትም መንጃ ፍቃድ ይለቃቅምና፣ ስለሰው ደንታ የላቸውም፡፡”
እየተሳደብኩ ወረድኩ፡፡

በአንዴ፣ እንዲህ ምን እንዳበሳጨኝ እኔም እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ሰሞኑን፣ በትንሽ ነገር እናደድና ቀስ በቀስ ብስጭቴ
ከመጠን ያለፈ ይሆናል፡፡ ያናደደኝን በቅጡ ይሄ ነው ብዬ መለየት እስከማልችል ድረስ፡፡ የቀባጠርኩላት ደጋግሞ ወደ ጭንቅላቴ እየመጣ፣
ስህተት ነበርክ፤ ቀሽም ነህ፤ በነገረካት ደካማ ጎንህ አላገጠችብህ፤” እያለ
ይነዘንዘኛል፡፡ ከለቀቀኝ ብዬ አልጋ ይዤ ሻወር ወሰድኩ፡፡ ለውጥ የለም፡፡
ሃሳቦቹ እንደ ንፋስ ውልብ እያሉ መጥፎ ስሜት ይለቁብኛል፡፡ በመጠጥ
ለመደበቅ ወሰንኩኝ፡፡ እራቴን በልቼ፣ ንዴቴና ብስጭቴ እስኪጠፋ፣ እስክስክርና እስክደነዝዝ፣ ድረስ፣ መጠጦችን እየቀያርኩ ስጠጣ አደርኩ፡፡
በንጋታው አረፋፍጄ ባህር ዳር ምሳ በልቼ ጎንደር ገብቼ አደረኩ፡፡

ጉዞ ወደ መተማ ዮሀንስ

መተማ ለመሄድ፣ ከጎንደር አዘዞ መናኸሪያ ሚኒባስ ተሳፈርኩኝ፡፡ ሚኒባሱ ወደ መሙላቱ ነው፡፡ አብዛኛው መኪናው ላይ የተሳፈሩት ወጣቶች ናቸው፡፡ ከአጠገቤ የተቀመጠው ወጣት እድሜው
በግምት ስላሳ አካባቢ ይሆናል፡፡የለበሰው ልብስ ወይቧል፡፡ ከተማ ቀመስ ይመስላል በመስኮት አጠገብ ለመቀመጥ ቦታ እንዲቀይረኝ ጠየኩት።ሳያቅማማ ቦታውን ቀየረኝ፡፡ ታክሲው እስክንተፋፈግ ድረስ ትርፍ ጭኖ መንገድ ጀመረ፡፡ የያዝኩት ገንዘብ፣ በየቀኑ እየሳሳ፣ እየመነመነ፣ አሁን ያሳሰበኝ ጀምሯል፡፡ አሁን ሃሳቤን ብቀይር እንኳ፣ መልሼ መቋቋም
ማልችልበት ደረጃ ደርሻለሁ፡፡ መፍጠን አለብኝ፡፡ መተፋፈጉን ለመርሳት፣ በመኪናው መስኮት አሻግሬ ሃሳብ የሚይዝ ነገር ፍለጋ ዐይኔን ላኩት፡፡ ምንም ቀልብ ሚይዝ ሚታይ ነገር የለም፡፡

ግማሽ መንገድ እንደሄድን ታክሲው ቆመ፡፡ ሾፌሩ የአርሴማን በረከት መያዝ የምትፈልጉ ሃያ ደቂቃ ብሎ ወረደ፡፡ ተሳፋሪው በሙሉ ተከተለው፡፡ ህብስት ዳቦ፣ ብርቱካን፣ ማንጎ፣ ይዘው የሚሸጡ ወጣቶች፣
የቅድስት አርሴማ በረከት እያሉ በመስኮት በኩል ያሳዩኛል። በቀኝ በኩል ተደርድረው የተሰሩ የጭቃ ቤቶች ይታያሉ፡፡እንደሱቅና ካፍቴሪያ እየሰሩ ነው፡፡ በስተግራ በደን የተሸፈነ ተራራ ይታያል፡፡ ከተራራው ስር
ምንጮች ይፈሳሉ፡፡ ሰዎች ተሰባስበው በምንጮቹ ውሃ ልብስ ያጥባሉ፡፡
ውሃ በጀሪካን ይቀዳሉ፡፡ ተራራው ጫፍ ላይ ትልቅ የተሰቀላ መስቀል በርቀት ይታያል፡፡ ተሳፋሪዎች፣ ህብስት ዳቦ እየበሉ፣ የገዟቸውን በረከቶች በፌስታል ጠቅልለው ገቡ፡፡ ሹፌሩ የቀረ ሰው እንደሌለ ካረጋገጠ በኋላ ጉዞውን ቀጠለ፡፡

አጠገቤ የተቀመጠው ልጅ፣ “ስለቅድስት አርሴማ!” ብሎ ህብስት ዳቦ ወደ እኔ ዘረጋልኝ፡፡ትንሽ ቆንጥሬ አርሴማ ትስጥልኝ አልኩት፡፡እስካሁን እንዳያወራኝ መንገድ ስዘጋበት ነበር፡፡ ሰሞኑን ድብርቴ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል፡፡ ማንንም ማናገር አስጠልቶኛል፡፡ ምግብና መጠጥ ሳዝ
እንኳ መመላለስ ሰልችቶኛል፡፡ላለመነጋገር፣ ያዘዝኩትን እንኳ ቀይረው
ሲያመጡልኝ፣ ንዴቴን ውጩ፣ ያመጡልኝን እጠቀማለሁ፡፡ ግን አሁን የቆምንበትን ምክንያት ማወቅ ፈለኩኝ፡፡

አጠገቤ የተቀመጠውን ወጣት “ለምንድነው የቆምነው?” ብዬ
ጠየኩት፡፡
👍21
በግራ በኩል ያለው ተራራ፣ የቅድስት አርሴማ ገዳም ነው፡፡በጣም ተአምረኛ ገዳም ነው፡፡ ከበረከቱ ለመሳተፍ ነው፤” አለኝ፡፡

ስለ ቅድስት አርሴማ ሰምቼ አላውቅም፡፡ ምንድነው ታሪኳ?”

ቅድስት አርሴማ አርመናዊ ቅድስት ነች። በዚህ ምድር ያለው መከራና ስቃይ፣ ሰይጣንና እግዚአብሄር ቢታረቁ ይፈታል ብላ ስለምታምን፣ ሁለቱን ልታስታርቅ የፀለየች ቅድስት ናት፤” አለኝ፡፡

መኪናው እየሄደ ነው፡፡ በመስኮቴ ወደኋላ ዞሬ፣ ገዳሙን ከጀርባ በኩል አየሁት፡፡ ከጀርባ፣ ተራራው ቀጥ ያለ ነው፡፡ የገዳሙ ጀርባ እንደ ፊት ለፊቱ ለምለምና አረንጓዴ ሳይሆን፣ በረሀና ገደላማ ነው፡፡ ትልቁ
የብረት መስቀል አሁንም ከርቀት ይታየኛል፡፡

“የቆየ ገዳም ነው” ብዬ ጠየኩት፡፡

“አስር ዓመት አካባቢ ይሆነዋል፡፡ ግን፣ አርሴማ ፀሎት ቶሎ ስለምትሰማ ብዙ ሰው ይመጣል።”

“ጥሩ ነው፡፡”

“ከአዲስ አበባ ነህ?”

“አዎ፡፡ እንዴት አወቅክ?”

“እዚህ አካባቢ ይህን ገዳሙን ማያውቀው የለም ብዬ ነው።”

“ለስራ ነው ሁመራ የምትሄደው?” ጀመረኝ፡፡

“አዎ፡፡”...

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1🔥1
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) “ጨዋታ እንቀይር፡፡ በሀይማኖት ተከራክሮ፣ መቀያየም ካልሆነ መተማመን ማይታሰብ ነው፡፡” “እሺ! ደስ እንዳለህ፡፡ ግን ሳስብህ ልብህ በውጪው ባህል የሸፈተ ይመስላል፡፡ ሚስትህ ፈረንጅ ነች እንዴ...?” “ኧረ ሚስት የለኝም፡፡” “ሚስትም ባይሆን ፍቅረኛ፡፡” “ፍቅረኛም የለኝም፡፡” “እሺ፣ ፈረንጅ ጠብሰህ ታውቃለህ?”…»
#ሰመመን


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...ማለቴ በአሁኑ ጊዜ እንኳ ሳምንት ወደኋል የቀረባችውን የትምህርት ዐይነቶች ለማሟላት ብዙ መጽሐፍ ያገላብጣል ብዬ ቃል መግባቱ ያስፈራኛል ” አላቸው ።

ዮናታን ነገሩ ስለገባቸው ደብዛዛ ፈገግታ አሳዩ ። ግን ብዙም ሳይቆዩ ፈገግታው ጭልም ብሎ ጠፍቶ ፊታቸው ተለዋወጠ ግንባራቸው ላይ ትልቅ የደምሥር ተምዘግዝጎ ወጣ ፤ ቅጽበታዊ ውሳኔ ከአእምሮአቸው ታዞ ምላሳቸውጋ
ደርሶ ነበር ።

ቃላቱን ከመወርወራቸው በፊት ያለምክንያት መነጽ ራቸውን አወለቁ ። እንደ ወትሮአቸው ዐይናቸውን ሳያሹ
መልሰው አደረጉት ። ወደ ኋላቸው ተለጥጠው ተቀመጡ ።እናም ተነፈሱ ።
ይህን ዓመት ትምህርቱን ማቋረጥ ይኖርበታል በኔ ግምት ።

እስክንድር ግር አለው፤ዝም ብሎ እያያቸው “ እና በምን ዐይነት መንገድ ልንመክረው እንችላለን ? አለ በልቡ ።
“ ምን ዐይነትምክር ነው ትምህርትን አቋርጥ ብሎ ምክር?”

“እህሳ ምነው ዝም አልክ?” አሉት ።
ትንሽ ሲያመነታ ቆየና ። “ ግን ይህችን ዓመት እንደ ምንም ጨርሶ ቢገላገል አይሻልም ? ” አላቸው ።

“ ትምህርት የሚገላገሉት ዕዳ ነው እንዴ ? ”

ማለቴ ” አለ እስክንድር ሐሳባቸው ስለ ገባው ቶሎ ብሎ በማደናገር ዐይነት ። “ ሌላ ዓመት መጨመሩ ራሱ የበለጠ ሊረብሽው ይችላል ብዬ ነው፤ ጓደኞቹ ሥራ ይዘው ሲያይ ይሄ ጊዜያዊ ሁኔታ ነው ጊዜያዊ ችግር ነው ። እኔ የማስበው ግን ከዘላቂ ሕይወቱ አንጻር ነው ። በእኔ ግምት አቤል ከጤናማ አእምሮው ጋር መመረቅ አለበት ። ከዚያ በኋላ ሥራ ይዞ ገንዘብ ማግኘት ሳይሆን ለዓለም አንድ ነገር ማበርከት ይሆናል ሕልሙ ” አሉና ዮናታን ከመጽሐፍ መደርደሪያቸው ላይ እንድ ጥራዝ አንሥተው አቤል በድጋሚ ሠርቶ የሰጣቸው የጥናት ጽሑፍ ነበር

«« ይኸውልህ ” አሉት። የጽሑፉን መግቢያ ዐልፈው መሐል ገጾቹን እያሳዩትጨ “ ከዚህ እስከዚህ ያለው ጽሑፍ የተቀዳው “ አንቲ ዱሪንግ” ከሚለው የኤንግልስ መጽሐፍ ውስጥ ነው ። ሐሳቡን ማለቴ እንዳይመስልህ! ፤ አረፍተ ነገሩ ቀርቶ ቃላቱን እንኳ አልቀየረውም ፡ ከመሰላቸትም አልፎ ትምህርቱን የመጥላት ምልክት ነው አቤል እንዲህ ዐይነት ተማሪ አልነበረም እንዳለች ከመጽሐፍ ቀድቶ ማምጣት ቀርቶ ታላላቅ ምሁራን በደረሱዋቸው ታላላቅ ሥራዎች ላይ የሚያቀርበውን ሐሳብ ለመፍታት እንኳ ያስቸግር ነበር ። አምና በአንዲት ዲያሎግ ሽንጡን ገትሮ ይዞን አስራ አምስት ቀን ሙሉ እንዳንጫጫን ትዝ፤ አይልህም ? !እኔ ያኔ እሱ ባነሣት ጥያቄ የራሱን ምሁራዊ ብቁነት ተጠራጥሬ እንደገና መጻሕፍት ሳገላብጥ የከረምኩብት ጊዜ ነበር ።
አሁን ግን የዚያን ጊዜው አቤል አይደለም ችሎታው አለው ። ግን አንዳች ችግር ደርሶበታል ። ስለዚህ ችግሩ ከተገለጠ በኋላ ነው ትምህርቱን በሚገባ ሊያጠናቅቅ የሚችለው እንጂ አድበስብሰው ቢያሳልፉት ምንም ጥቅም
የለውም።

እስክንድር የጥናት ጽሑፉን ወረቀት እያየ ፈዞ ቀረ ።እንዳለ የመፀፉ ግልባጭ ነበር አቤል ይህን የጥናት አርስት ወስዶ እንደገና እንዲሰራ ዮናታን በመከሩት ጊዜ መልሶ ወስዶ ሲያምጥበት ዐሥራ አምስት ቀን ያህል አስቀመጠው ። በመጨረሻም ከጠቀሱት መጽሐፍ ውስጥ እንዳለ ገልብጦ ሰጣቸው አያውቁም ብሎ አልነበረም ይህን ያረገው ከእጁ እንዲወጣለት ብቻ እንጂ ።

“ እና አሁን ትምህርቱን እርም ብሎ ከመተዉ በፊት እንዲያቋርጥ በዘዴ ብንመክረው ” አሉ ዮናታን ።

ለዚህማ ምን ምክር ያስፈልገዋል ? ” አለ እስክንድር“ “ እሱ ራሱ ለመተው በቋፍ ነው ያለው ። ”

“ የለም እሱ የራሱን ውሳኔ ወስዶ ከተወማ አሁን ባለበት ሁኔታ ለእኔዴም ለሁሌም ነው የሚተወው

ጭራሽ ወደ ትምህርት ፊቱን አይመልስም ምክሩ የሚያስፈልገው ጤናማ በሆነ አመለካከት ትምህርቱን አቋርጦ አእምሮው ሲረጋጋ እንዲመለስበት ነው” አሉና ዮናታን አንድ ሐሳብ ድንገት ስለ መጣባቸው፡ “ ደግሞ አይምሰልህ
ለማቋረጥ ድፍረት የሚኖረው አይምሰልህ ማለቴ ትምህርቱን ለመተው ድፍረት ባያጣም ዩኒቨርስቲውን መልቀቅ
ድፍረት አይኖረውም አሉ።

«« አልገባኝም ” አለ እስክንድር ግር ብሎት
በዐይኑ ያፈቀራት ልጅ ያለችወታ እዚሁ ግቢ ነው አላልከኝም ? ”
“ አዎ ፥ መቼም በግምቴ ይመስለኛል ”
“ታዲያ እሷ ያለችበትን ግቢ እንዴት ችሎ ይልቃል!”
“ እ? ”
« እንዳው ስታስበው ችሎ እሚለቅ ይመስልሃል ወይ ?”
"እህ...

“ ራስ ግሪል ” የምትል ዓርማ ከደረቱ ላይ የለጠፈች አስተናጋጅ ፡ “ ምን ልታዘዝ ?” ሲል ከፊቱ መጥቶ ቆመ ።

እስቲ ቀዝቃዛ ቢራ ” አለ ለማ ሰዓቱን እየተመለከተ

ዘጠኝ ከዐሥር ሆኖ ነበር ። “ ቦታው ጠፍቷት ይሆን እንዴ ?” ሲል አሰበ ፥ ምናልባት ዋናው ራስ ሆቴል ሔዳ እንደሆን በሚል ግምት ። ነገር ግን ቀጠሮአቸውን በደንብ ያስታውሳል ። “ራስ ግሪል ፡ ቅዳሜ በዘጠኝ ሰዓት” ሲላት
ጥቂትም ግር ሳይላት ነበር ቀጠሮውን የተቀበለችው ።

“ እንዴት አባቷ ቀጠሮው ቦታ ቀድማ አትገኝም ? የሚል ትምክህት ተሰማው ። ለጊዜው ተፈላጊ በመሆኑ ዐሥር ደቂቃ አሳልፎ የመጣው ቀድማ ትጠብቀኛለች በሚል ግምት ነበር ።

አሳላፊው ቢራውን ይዞለት መጣ ።

ለማ የቢራውን ቅዝቃዜ ለመገመት ጠርሙሱን በእጁ ጠበቅ አርጎ ከጨበጠ በኋላ አስከፈተ ። ሁለቴ ተጐንጭቶ
ግማሽ ወገቡ ላይ አደረሰው ።የዕለቱ ወበቅ ሌላ ጉዳይ ነበር ።ኮቱን አወለቀ ፡ ከፊት ለፊቱ በከረባት ታንቀው የተቀመ
ጡትን ወፍራም ሰውዬ ተመልክቶ ፡ ሙቀት በመቋቋም ችሎታቸው ተደነቀ ።

ደቂቃዎቹ ወደፊት ተራመዱ ። ወፈር ያለች አጭር ልጅ ግን ብቅም ኣላለች ። አምስት ደቂቃ ሳይሆን ሙሉ ቀን የጠበቃትን ያህል ስሜቱ ተቁነጠነጠ ። ከአሁን በፊት ሁለት ጊዜ ሴቶች በቀጠሮ ቀጥተውታል ብዙ ሴቶች በመጀመሪያ ቀጠሮ ላይ እንዲህ እንደሚያረጉ ያውቃል ።ርካሽ እንዳይምስሉ የሚያደርጉት መፍጨርጨር ነው ። ይሁን እንጂ
በቤተ ልሔም ሊቀጣ አይፈልግም መቅረት ሳይሆን መዘግየቷ ራሱ ምን ሲደረግ !

ቢራውን ጭልጥ አድርጎ ተነሥቶ ሊሔድ ፈለገ ። ነገር ግን እግሩን አሳነቃነቀም ። ነገር የጠፋው የዚያች የሰርግ ዕለት ነው "አፌኝ ካጠፋሁ አይቀር ፥ ማስጨረስ አለብኝ? የሚል ስሜት አደረበት ።የቤተ ልሔም ግምት ልክ ነበር ።የተዘበራረቀ ስሜቱን ተመርኩዞ መከረኛ ኅሊናው የፌዝ
ጥርሱን እያሳየ ከተፍ አለበት ። እንደ ገና ሁለት ለማዎች ሙግት ጀመሩ ።

ምነው ቢቀርብህ ለማ?”
• ምኑ ?
• ዝቀጡ " ያለቦታህ መዋሉ !”
• መምህር የሚያሰተምራትን ኮረዳ ሲያወጣ መዝቀጥ አይደለም ። ማነው እንዲህ ያለው? ማነው እንዲህ አይነት
ሕግ የደነገገው ? አላየሁም አላነበብኩም እስካሁን ጅል ሆኜ ቆይቻለሁ ቁጥብነቴ በሕይወቴ ላይ ምን ጨመረልኝ? ፍራፍሬ ቀርቦ አትብሉ ብሎ የሚያግድ ሕግ ካለ አልቀበልም።

መታገድ ሳይሆን መቆጠብ ያስፈልጋል ።
መቆጠብ መቆጠብያ ከአመጋግብ መቆጠብ ከቃልባዊ ግንኙነት መቆጠብ ቁጥብነትን የሰውነት መለኪያ ያደረገው ማነው ? ”

“ አመዛዛኝ እንጂ ቁጥብነት ከኔ ለማ ሰልማ የሰው ልጅ ሕይወት ከእንስሶች ባልተለየ ነበር ። እንደ እንስሶች በተገናኙበት መዳራት ፡ ባገኙበት መብላት መጠጣት : በደረሱበት ወቅ
ኛት ፡ ያገኙትን ማንሣት ፡ የጠሉትን መጥላት ቢሆንማ ፥ታላቅ የስሜት ግጭት ስለሚፈጠር የሰው ልጅ እርስ በርሱ ይተላለቅ ነበር ። ቁጥብነት በስሜት ሳይጋጩ ተባብሮ መኖ
ርን በሚፈልግ ኅብረተሰብ ውስጥ ያለ ማኅበራዊ ሕግ ነው . .

እና የአካባቢውን ሕግ ብጥስ ምን ይመጣብኛል ??

መተፋት ነዋ ! በኅብረተሰብ መታፋት መናቅ
👍1
ከአውሬ ወይም ከእንስሳ መቆጠር ! መዝቀጥ?

ለማ ድንጋት ዘመር ቢል ፊቱን ከህንፃው ጋር ከተሰራው ረዥም የቁም መሰታወት ውስጥ ቀ ተመለከተ " በውን ከጠላቱ ጋር እንደሚሟገት ሰው ግንባሩ ተኮማትሮ "ፊቱ የውስጥ ስሜቱን በግልፅ ያሳይ ነበር።
ከኅሊና የበለጠ ጠላት ምን እለ?

« አዎ ! ጠላትህ ነኝ ከሰውነት ወጭ ስትሆን ገና የባሰ ጠላትህ እሆናለሁ ። ሕይወትህ የአንዱ መሆን አለበት !
የውጭያዊ አንነትህ ወይም የውስጣዊ እንተነትህ!

“ ኦፍ ! በቃኝ ሙግት አልፈልግም ? ?
“ እንዴት ? ”

• እንዲህ ነዋ ! ትዳር መመሥረት አልቻልኩም ። ምን ተይዞ ጉዞ ! ”

“ እና የአሁኑ ተግባርህ ለዚህ ሁሉ መካካሻ ነው ? !
“ ከረሜላ ካልተገዛልኝ ብርጭቆ እሰብራለሁ ” እንደሚል ሕፃን ወይም ደግሞ ፥ “ የሲኒማ ፍራንክ ካልሰጠሽኝ እናቴ አይደለሽም ! ”? ብሎ ደሀ እናቱን እንደሚያስፈራራ ጎረምሳ ሆንክ ኳ ! ነው ፡ አይደለም ? አልቤርጎ እየኖሩ ክብር
የለም ።

ምንም ሆነ ምን በቁጥብነት ራሴን አላስርም ፡ ካለመቆጠቤ የሚቀርብኝ ክብሬ...

' ለማኅበራዊ ችግር መፍትሔው : ማኅበራዊ ትግል እንጂ ካሉበት በታች ሆኖ መገኘት እይደለም!”
ኦፍ !

በቀይ እጅጌ ጉርድ ቀሚስ ደምቃ ጽጌረዳ አበባ የመሰለች ኮረዳ ወደ ምግብ ቤቱ ስትገባ በተመለከተ ጊዜ
ሲወተውተው የቆየው ኅሊናው የኋሊት ፈረጠጠለት ።
ጎሽ ፡ ገላገልሽኝ” በማለት ዐይነት ለማ በረዥሙ ተንፍሶ ተመቻችቶ ተቀመጠ ። ነገር ግን የውስጥ ስሜቱን በፈገግታ
ሊገልጽ አልፈለገም ። ቅሬታውን በሚያንጸባርቅ አስተያየት
ተቀበላት።

“ሶሪ ፤ ብዙ እስጠበቅሁህ አይደል? ” አለችው ቤተልሔም ፡ ቁና ቁና እየተነፈሰች ። “ ኦፍ አገኝሃለሁ የሚል ግምት አልነበረኝም ተስፋ ቆርጨ ነበር
እንዳለችውም ገና በሩን ስትገባ ዐይኖቿ ከወንዶቹ መሐል አነጣጥረው ለማን ባገኙት ጊዜ፥ ልቧ በደስታ ከውስጧ ዘሎ ሊወጣ ምንም አልቀረው ። በመዘግየቷ ጥፋተኝነት እየተሰማት ነበር የቀረበችው ለማ መቆጣት አልቻለም ።መላ ሰውነቷን የተርከፈከፈችው ሽቶ መዓዛ ስሜቱን አደንዝዞት ፡ ቅሬታወን እንዲውጥ አስገደደው ።

ምንም አይደለም ፥ በይ ቁጭ በይ ። ግን ምነው ? ”አላት ፥ ግንባሩን አላልቶ ሰዓቱን እያየ ። ዘጠኝ ተኩል ሆኖ ነበር ።

“ አንድ ደረቅ ባለታክሲ አጋጥሞኝ” ኮ ነው” አለች ቤተልሔም ከአቀማመጧ እየተመቻቸች ። “ እኛን ውስጥ አጉሮ ነዳጅ ለመቅዳት አይገተር መሰለህ ? ”

“ጥላችሁት በሌሳ ታክሲ አትሔዱም ነበር? ! ” አላት ! በመቆርቆር ስሜት ።

“ መጥፎ አካባቢ ነበራ ! ታክሲ እንደ ልብ የማይገኝበት

አንድ አሳላፊ መጥቶ ከፊታቸው ቆመ ።
“ የብርቱካን ጭማቂ አለ ? ” ስትል ጠየቀች ።

ምነው ? ቢራ ጠጭ እንጂ ” አላት ለማ ።
አልጠጣም ። በዚህ በፀሐይ በቢራ ራሴን ይፈልጠዋል ” አለችውና ፊቷን ወደ አሳላፊው መልሳ' “ ጭማቂውን አምጣልኝ ” ስትል አዘዘች ።

በል ለእኔም ቢራ ድግመኝ ” አለ ለማ ።

ፀሐዩን ፈርታ ሳይሆን ቢራ እጅግም ነች ። ቦርጭ ያወጣል እያሉ ጓደኞቿ ስለሚያስፈራሯት ትታዋለች ።ሌላው ችግሯ ደግሞ ቢራ ከጠጣች ሽንት ቤቱ ለእሷ ብቻ መለቀቅ አለበት ። በጉሮሮዋ ከመውረዱ ሽንቷ ይመጣባታል ። ውስኪ ሲሆን ነው ደስ ብሎአት የምትጠጣው ።

“ውይ ! ምን ዐይነት ቃጠሎ ቀን ነው?” ስትል ጨዋታ ከፈተች ። ስስ ተካፋች ሹራቧን አውልቃ ትከሻና ደረትዋን ገላልጣ ነበር የተቀመጠችው የቆዳዋ ጥራት በሞግዚት ተንከባክበው የያዙት እንጂ በዩኒቨርስቲ ትምህርት የማቀቀ
አይመስልም ።

“ ጉድ ነው እንጂ” አለና ለማ ወበቁን በማጋነን አይነት ወዲያው መለስ አርጎ ' “ እኔስ ቦታውን ወይም ቀጠሮውን ረስተሽዋል ብዬ ነበር” አላት ።

አሳላፊው ቢራውንና ጭማቂውን አቅርቦላቸው ተመለሰ።

“ እንዴ! ምን ማለትህ ነው?” አለችው ፡ ልቡ ውስጥ ገብታ ለመጐዝጐዝ ዐይኗን እያስለመለመች ። “ እንዴት
እረሳዋለሁ ?! ””

እውነትም ቤተልሔም አትረሳም ። ከዚህ ቀደም የሶስት ቦይፍሬንዶቿን ቀጠሮ እያወጣች እያወረደች ስታማርጥ
ውላ የአንድ ትልቅ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ወደ ሆነው ዘንድ ወስና ብትሔድ ፡ ግማሽ ሰዓት በመዘግየቷ ና ወፍራም ገቢ
ያስገኝልኛል ብላ የተማመነችበትን የክረምት ሥራ ሳታገኝ ቀርታለች ።

ከዚያን ዕለት ወዲህ ቤተልሔም ቀጠሮ አትረሳም እንዳውም ጥቅም ያለበት ዐይነት ከሆነ ዝግጅቷን የምትጀም
ረው ገና በዋዜማው ነው ። ልብሷንና የሽቶዋን ዐይነት ስትመራርጥ ታመሻለች አነጋገሯን ፡ ቅልጥፍናዋን ስታስብበት ታድራለች ። ባዶ የፍቅር ዜማ እያንጐራጐረ የሚጠብቃትን ወንድ አውቶቡስ ፌርማታ ጥግ ገትራ ሲኒማ ቤት የምትዝናናውን ያህል መልካም ዝና ወይም ገንዘብ ያለውን ላለማስጠበቅ በጥድፊያ ሁለት ታክሲ የምታስቆምበት ጊዜ አለ ፡ ያም ሆነ ይህ ያን “ ለታ አልያዘላትም ። ስለዚህ እማይደገም ዕድል አመለጣት ። ሰውዬውን በሌላ ቀን አገኘው ይሆናል ብላ ብታስብም ከአዲስ አበባ መንገዶች አጣችው "

ቤተልሔም ከቀጠሮ ይበልጥ የማትረሳው ሌላው ነግር የዛሬ ዓመት“ፍሬሽ ማን” ሆና የደረሰባት ነው። ፈገግታ እማይላየው አንድ ወጣት የኢኮኖሚክስ ሌክቸረር ነበር ታዲያ ትምህርቱ እየከበዳት ሒደና በሱ ኃይል ለማለፍ ፈለገች ።

💥ይቀጥላል💥
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“ወደ ዚህ ስትመጣ የመጀመሪያህ ነው?”

“አዎ።”

“ትቆያለህ?”

ሳምንት አካባቢ።”

“እዚያ ማዶ ሚታየው አፄ ዮሐንስ አንገታቸው የተቀላበት ቦታ ነው።” እጁን ከመንገዱ በላይ እየጠቆመ::

“መተማ ዮሐንስ ደረስን ማለት ነው?”

“አዎ፡፡ አሁን ገብተናል፡፡” ልቤ ድንግጥ ድንግጥ አለብኝ፡፡ ሚኒባሱ እየቆመ፣ ሰዎችን ያወርዳል። እስከዛሬ ያልተሰማኝ ፍርሀት እየተሰማኝ ነው፡፡ ዝም አልኩ፡፡ ወደ ስንብት እየተጠጋሁ ነው፡፡
የማውራትም የማወቅም ፍላጎት የለኝም፡፡ ዝም ብዬ በዐይኔ ከተማውን መፈለግ ጀምረኩ፡፡ በግራና በቀኝ የተደረደሩ የጭቃ ቤቶች፣ ጭር ያለ ከተማ ነው፡፡ እንደጠበኩት ግርግር የበዛበት ከተማ አይደለም፡፡ ሰዐቴን አየሁ፤ አስር ተኩል፡፡ አብዛኛው ሰው ወርዶ አልቋል፡፡

“መናኸሪያ ትገባለህ?” ወያላው ፊቱን አዙሮ ጠየቀኝ፡፡

“አይ አልገባም፡፡”

“ካልገባህ መጨረሻው እዚህ ነው።”

“እሺ አውርደኝ!”

በጭራሽ እንደገመትኩት አይደለም፡፡ ለማደሪያ ሚሆን አልጋ ቤት እንኳን እስካሁን አላየሁም፡፡ ከተማዋ ትሞቃለች። አስራ አንድ ሰዓት እየሆነ ቢሆንም፣ በጣም ይወብቃል፡፡ ፍርሀት ነው መሰል፣ በጣም እያላበኝ ነው። ዝም ብዬ ዋና መንገዱን ይዤ፣ አልጋ ቤት ፍለጋ
ተጓዝኩኝ፡፡ ነጋዴ የሚርመሰመስበት፣ አዲስ ሰው፣ ፀጉረ ልውጥ ሰው
ከዐይን የማይገባበት ብዬ የገመትኩት ከተማ፣ ትንሽዬ መንደር ሆና አገኘኋት፡፡ መንገድ ዳር በብሎኬት የታጠረ ሰፊ ግቢ ያለው ሆቴል አየሁ፡፡ ሰላም ሆቴል ይላል፡፡ አላንገራገርኩም፡፡ ዘው ብዬ ገባሁ፡፡ ብቻ
አልጋ በኖረ፡፡

“አልጋ አለ?”

“አለ፡፡”

“እስቲ አሳዩኝ?”

“ባለሻወር ነው፣ ያለሻወር?”

“ባለሻወር፡፡” ቁልፍ አመጣችና አሳየችኝ፡፡

“ስንት ነው?”

“አንድ መቶ ሃምሳ ብር፡፡” ብሩን ሰጠኋትና ቦርሳዬን አስቀመጥኩ።

ሻወር ቤት ገብቼ ሻወር ቼክ ሳደርግ ውሀ የለችም፡፡ ዞር ስል፣ውሀ በባልዲ ተቀምጧል፡፡ በጣም አልቦኛል፣ ተለቃለኩኝ፡፡ እራት በልቼ ቢራ መጠጣት ጀመርኩ፡፡ ሙቀት ስለሆነ ተጠጣልኝ፡፡ ማታ ጥሩ እንቅልፍ ተኝቼ አደርኩ፡፡ ቀን ወጥቼ ከተማውን ዙሪያውን ሳይ ዋልኩ፡፡
በፍፁም እኔ እንዳሰብኩት አይደለም፡፡ የከተማው ዙሪያ ለጥ ያለ ለእርሻ የሚውል ሜዳ ሲሆን፣ ዛፎች በእርቀት ነው የሚገኙት፡፡ ስዞር ውዬ አመሻሹ ላይ፣ ቢራዬን እየጠጣሁ ምን እንደሚችል ሳስብ፣ አርሴማ ገዳም የሚል ሀሳብ መጣብኝ፡፡

#ኑሮ_በገዳም

ሽቅብ ዝግዛግ ሆኖ በተሰራውን የጥረጊያ መንገድረገ፣ በግራና በቀኝ በዛፎች ተከቧል፡፡ ከፊት ለፊቴ፣ አጠር ያለ ወጣት፣ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ስዕል ያለበት ጥቁር የጨርቅ ሻንጣ በጀርባው ተሸክሞ በዝግታ ያዘግማል። እየተከታተልን ወደ ገዳሙ ዘልቀን ገባን። ከገዳሙ መግቢያ
በር ትንሽ ፈቅ ብላ ያለች የጭቃ ቤት ጋር ስንደርስ፤

“እንኳን ደህና መጣችሁ። ምዝገባ ቢጤ አለች።” አለን ፊቱ መጠጥ ያለ ጠይም ወጣት፡፡

“እሺ!” ብዬ ቆምኩኝ፡፡ ልጁን መዝግቦ ከጨርሰ በኋላ፣ ትንሽ ቆየኝ ብሎት እኔን መመዝግብ ጀመረ፡፡ ስም፣ እድሜ፣ የመጡበት አድራሻ፣ የአደጋ ግዜ ተጠሪ...፣ ሁሉንም ቀይሬ ነገርኩት፡፡

“ለስንት ግዜ ነው ሚቆዩት?”

“ለሦስት ሳምንት፡፡”

“መታወቂያ ይዘዋል?”

“አልያዝኩም፡፡” አልተጫነኝም፡፡
“እሺ፣ እንግዶቻችን፣ እኔ መልካሙ እባላለሁ፡፡ በገዳሙ አስተባባሪ ነኝ፡፡ አሁን ማደሪያ ቦታ እሰጣችኋለው፡፡ ገዳሙን
አስጎበኛችኋለው፤ ስለ ገዳሙ ታሪክ፣ መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች መረጃዎችን እነግራችኋለው፡፡ እዚህ ገዳም፣ ማንኛውም አዲስ ሱባኤተኛ ሲገባ እናንተ እንዳደረጋችሁት ተመዝግቦ ነው፡፡ ገዳሙ የአርምሞ ገዳም ነው:: ማውራት ክልክል ነው፡፡ አስገዳጅ ነገር ካላጋጠማችሁ በስተቀር፣ ማውራት አይቻልም፡፡ የግድ ማውራት ካስፈለገ እንኳ፣ ዝግ ባለ ድምፅ፣ በለሆሳስ ነው ማውራት ሚቻለው፡፡ እዚህ መዳን የሚገኘው በአርምሞ ውስጥ ነው፡፡”

ከኛ ውጪ ለሌላ ሰው እንዳይሰማ፣ በሆዱ እንደሚያወራ፣ በጣም ዝግ ባለ ድምፅ ያወራናል፡፡ በአርምሞና በለሆሳስ ማለት እንዲህ ነው' ብዬ አሰብኩ፡፡ የሚያወራው እንዲሰማን፣ አንገታችንን ወደሱ አሰገግን፡፡ እያወራን ወደ ማደሪያችን ወሰደን፡፡ እያንዳንዱ ከሁለት መቶ ምዕመን በላይ የሚይዝ፣ አራት የማደሪያ አዳራሾች አሉ፡፡ ሁለቱ የወንድ፣ ሁለቱ የሴት እንደሆነ ነገረን፡፡ ቦታ ሊሰጠን ወደ አንደኛው አዳራሽ ይዞን ገባ፡፡ በውስጡ ከመቶ ሚበልጡ ምዕመናን አሉ፡፡አሰላሁት። በግምት በገዳሙ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሱባኤያተኛ ምዕመናን
እንዳሉ ገመትኩኝ፡፡ ገዳሙ ግን ሰው ያለው አይመስልም፡፡ ዝም፣ ጭጭ፣ ያለ ነው፡፡ ሁሉም በለሆሳስ ፀሎት ላይ ነው፡፡ ሰላምታ እንኳ፣ ጎንበስ ቀና በመባባል ብቻ ነው፡፡ ምንም አይነት የሰው ድምፅ አይሰማም፡፡የወፎች ጭጭታና የዛፎች ሽው ሽውታ ብቻ ነው፡፡ በጣም ደስ ይላል፡፡መንፈስን ያድሳል፡፡ አዕምሮን ያረጋጋል፡፡ ፈውስ በመንፈስ ቅዱስ
ባይላክም እንኳ፣ የቦታው ድባብ ፈውስን ይሰጣል።

“እና ሌላው...” አለ መልካሙ ቦታችንን ሰጥቶን ከአዳራሹ ይዞን እየወጣ፣ “ማንኛውም ምእመን ወደ ገዳሙ ለሱባኤ ሲገባ፤ ፀጉሩን መላጨት፣ ንስሀ መግባትና ስግደት መውሰድ አለበት፡፡” አለን እኔን እኔን እየተመለከተ፡፡

“እሺ፡፡ ማን ነው ሚላጨን?”

“እርስ በእረስ ነው ምትለጫጩት፡፡ ፈራህ እንዴ..? አንተን እኔ ቆንጆ አድርጌ እላጭሃለው፡፡” የከተማ ልጅ መሆኔን አውቆ ነው መሰል፣ ከገባን ጀምሮ እኔን እኔን እየተመለከተ ነው ሲያወራ የነበረው፡፡

“እሺ” አልኩት፡፡ አሁን ስለራሴ ብዙም ግድ የለኝም፡፡ ምላጭ ግቢ ካለው ሱቅ ተገዝቶ ሁለታችንንም ላጨን፡፡ ነብስ ካወኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ፀጉሬን ተላጨሁ፡፡ እየላጨንም ስለ ገዳሙ መተዳደሪያ ደንብ ይነግረናል።

“በገዳሙ፣ በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ ነው የሚበላው፡፡ ጥዋት ቅዳሴ እንዳለቀና ማታ አስራ ሁለት ሰዐት። አስራ ሁለት ሰዐት ካለፈ መመገብ አይቻልም፡፡ ገዳሙ መብራት ስለሌለው፣ ማታ ማታ ሻማ ነው
ምትጠቀሙት። ሻማ ከዚህ ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ፡፡ የማታ ሦስት ሰዓት ፀሎት ካበቃ ቦሃላ ሻማ ማብራት አይቻልም፡፡ የእንቅልፍ ሰዓት ነው፡፡ እንዳያችሁት፣ የቦታ ጥበት ስላለ አንድ ሰው፣ በአንድ መዳበሪያ በታ ላይ ነው መተኛት ያለበት፡፡ የለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ፀሎት ላይ ሁሉም
ምዕመን መገኘት ግዴታ ነው፡፡” ሁለታችንንም ላጭቶ ሲጨርስ አስራ
አንድ ሰዐት ሆኖ የሰርክ ፕሮግራም ተጀመረ።

“በሉ ተነሱ እንሂድ፣ የሚቸግራችሁ ነገር ካለ እዚሁ ስላለን በፈለጋችሁት ሰዓት ጠይቁኝ ፤ ” ብሎ ፕሮግራሙ ወደ ሚካሄድበት ስፍራ ወሰደን፡፡

የገዳም ኑሮዬ ተጀመረ፡፡ ለሊት ዘጠኝ ሰዓት መነሳት በጣም ከባድ ነው፡፡ ግን፣ አማራጭ የለም፡፡ አስተባባሪዎች እየዞሩ ይቀሰቅሳሉ።ያልተነሳ ሰው ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ይረጫሉ፡፡ የመጀመሪያ ቀናቶች ላይ
በጣም ከበደኝ፡፡ ከእንቅልፍ ሳልነቃ ውሃ ሲረጩኝ እንደ ኤሌክትሪክ ይነዝረኛል፡፡ ሁለት ሦስት ቀን ሲደጋግሙኝ፣ ገና ድምፃቸውን ስሰማ መነሳት ጀመርኩ፡፡ ፀሎትና ምህላው እስከ ጥዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ይደረጋል፤ ከዛ ወደ ፀበል።

ገዳሙን ቅጥር ግቢ በደንብ ለማማወቅ እየተዟዟርኩ ማየት ጀመርኩ፡፡ የአርሴማ ገዳም በሃገራችን እንዳሉት አብዛኞቹ ገዳማት፣በተራራማ ቦታ ላይ ከየተመሰረተ ነው፡፡ የገዳሙ መስራችና አስተዳዳሪ
የሆኑት መነኩሴ፣ እድሜያቸው ሃምሳ ዓመት ቢሆን ነው፡፡ ገዳሙ በእውቀት እንዲለማ በደንብ አስበውበት እንደመሰረቱት ገዳሙ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ከመሰረቱት
1👍1
በኋላ፣ በየአመቱ ምዕመናኑን በማስተባበር ብዙ ችግኞች እንዳስተከሉ፣ በፊት የነበረዉን ረባዳማ ቦታ፣በደን ከተሞላ ቦሃላ፣ ተራራው ወደ ሞገሳምነት እንደተለወጠ ከማየውና
ከተለያዩ ሰዎች ከምሰማው መረዳት ቻልኩ፡፡ ተራራው በደን ስለተሸፈነ፣
ከታች ብዙ ምንጮች ፈልቀዋል፤ ፊት ለፊት ያሉትን ምንጮች የአካባቢው ማህበረሰብ ለተለያዩ አገልግሎቶች ይጠቀምባቸዋል፡፡በስተጀርባ በኩል ያሉት ደግሞ፣ ከሰዎች ንክኪ ተከልለው ለፀበልነት ይውላል፡፡

ሰፋፊ የሆኑ የገዳሙ በስተደቡብ፣ ለሱባኤተኛ የተሰሩ የእንጨት ቤቶች አሉ፡፡ የሴትና የወንድ ክፍሎች ለየብቻ ናቸው።ከመኖሪያ ቤቶች ጀርባ ቁልቁል ወርዶ የፀበል ቦታ አለ፡፡ በምስራቅ በኩል የገዳሙ ዋሻ አለ፡፡ ዋሻው መሬት ተቦረቡሮ የተስራ ሳይሆን፣ የትልልቅ ዛፎች ቅርንጫፍ ተገጣጥሞ በሰራው ጣራና ግርግዳ የተከለለ ክፍል ነው፡፡ ዋሻው ውስጥ ሚገቡ ሰዎች በቀን ሰባት ግዜ ፀሎትና ስግደት ማድረግ ሲጠበቅባቸው፣ በቀን ውስጥ የሚመገቡት ደግሞ አስራ ሁለት
ፍሬ ባቄላ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ከባድ የሱባኤ ወቅት፣ ቅድስት አርሴማ እራሷ በአምሳል ተገልጣ ለችግሮቻቸው መፍትሄ ትሰጣለች ይባላል፡፡ የገዳሙ ምዕራብ ክፍል በጥቅጥቅ ደኖች የተሞላ ሲሆን፣
ምዕመኑ በየዛፉ ስር ተጠልለው በአርምሞ ፀሎት ያደርጋሉ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) “ወደ ዚህ ስትመጣ የመጀመሪያህ ነው?” “አዎ።” “ትቆያለህ?” ሳምንት አካባቢ።” “እዚያ ማዶ ሚታየው አፄ ዮሐንስ አንገታቸው የተቀላበት ቦታ ነው።” እጁን ከመንገዱ በላይ እየጠቆመ:: “መተማ ዮሐንስ ደረስን ማለት ነው?” “አዎ፡፡ አሁን ገብተናል፡፡” ልቤ ድንግጥ ድንግጥ አለብኝ፡፡ ሚኒባሱ እየቆመ፣ ሰዎችን…»
#ሰመመን


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

ቤተልሔም ከቀጠሮ ይበልጥ የማትረሳው ሌላው ነገር የዛሬ አመት "ፍሬሽ ማን" ሆና የደረሰባት ነው። ፈገግታ እማይለየው አንድ ወጣት የኢኮኖሚክስ ሌክቸረር ነበር ታድያ ትምህርቱ እየከበዳት ሄደና በሱ ኀይል ለማለፍ ፈለገች።
በመጀመሪያ ተማሪዎቹን ዘፍ ብሎ እንደሚያነጋግርና ፊት እንደማይነሣ አጠናች ። ቀጠለችና ጥያቄ ሲጠየቅ መመለስ እንደማይሰለች አስተዋለች ። ከዚያ በኋላ በሙሉ ልብ ተገፋፍታ ትከታተለው ጀመር። ብቻዋን የምትሆንበትን አጋጣሚ እየፈለገች የምታወቀውንም የማታውቀውንም አስረዳኝ እያለች የልቡን ትርታ ማዳመጥ ቀጠለች ። በኋላ አንድ ቀን ሳያስበው አንዱን ቴዎሪ ሊያስረዳት ከቃላቱ ጋር ሲታገል" “እንዴት በዚህ ዕድሜህ ማስትሬት አገኘህ ? ! አለችና በጣፋጭ ዜማ አቋረጠችው።ምን እንደሚመልስላት ግራ ገባው ። እሷ ግን ከዚያን ዕለት ወዲህ ነገሩ ሠመረላትና ልቡ ጓዳ ሰተት ብላ ገባች ። አጠመድኲት ብላ ፎከረች ። ከማለፍ ጉጉቷ አልፋ “ A” በጄ ገባች ብላ ተማመነች ።

በእርግጥም ሴክቸረሩ ከዚያን ቀን ጀምሮ ለቤተልሔም ተማረከላት ። ከደንበኞቿም አንዱ ሆነ ። ይሁን እንጂ የፍቅሩን አመጣጥ በኮስታራ መንፈስ ነበር የተቀበለው ። ግና እንደ አጀማመሩ ሰሞን እንዳትከፋ በማሰብ 'ለዘብ አድርጐ
“ የሚያጠግብ ፍቅርና ትምህርት በአያያዙ ያስታውቃል እያለ እንደ ቀልድ ሲነግራት ካንጀቱ አልመሰላትም ነበር
ይልቁንም ፥ “እስቲ እንተያያለን ” እያለች ቀልዱን በቀልድ መለሰች ። በኋሳ ፥ ቀስ እያለች ፥ « ፍቅርና ትምህርት ለየብቻ
ናቸው ” ማለት ጀመረ ።አሁንም እውነት አልመሰላትም እና ወደ ሁለተኛ ዓመት ተንጠልጥላ በማስጠንቀቂያ እንድታልፍ ያደረጋት የኢኖሚክሶ "D” መሆኑን አትረሳውም ። እንዳውም “ ደርሶ ፈረንጅ ! አጉል ሲሪየስ ልሁን ባይ !” እያለች መስከረም እስኪጠባ ረግማዋለች ። “ እንደ ጂሰስ ሐቀኛ ልሁን ሲል የፕሮቤሽን መሥዋዕቱ አደረገኝ!”እያለች ስታማው ሴሚስተሩን አጋምሳለች ።

ታዲያ አንዳንዴ ያ ሁኔታ ትዝ ሲላት፡ “ ለማም እንደሱ ይሆንብኝ ይሆን ?” እያለች ዐልፎ ዐልፎ ማሰቧ አልቀረም ።

ለማ “ያንተን ቀጠሮ እንዴት እረሳዋለሁ ?” ሲባል በርግጥ ደስታ ተሰምቶታል ። ነገር ግን አንድ የሆነ ነገር እንደ ከነከነው ያስታውቅ ነበር ።

“ የምልሽ ፡ የሰርጉ ዕለት ቀጠሮ የተሰጣጠነው በግርግር መሐል ስለሆነ ሊደናገርሽ ይችላል ብይ ነው » ከዚያ
ደግሞ ክፍል ... ” አለና ሊናገር የፈለገውን ቶሎ ብሎ በውሸት ሳል ሽፋፍኖ አሳለፈው

ለማና ቤተልሔም ቀጠሮ የተሰጣጡት የሰርጉ ዕለት ነበር ።በሰባተኛ ቀናቸው መገናኘታቸው ነው ። በዚያ መሐል
በነበሩት ቀኖች ውስጥ ለማ የሚያስተምረውን የትምህርት
ዐይነት ቤተልሔም በሳምንት ሦስት ፔርየድ መከታተል ሲኖርባት፥ የሰኞውን ክፍል ጊዜ ብቻ ገብታ ሁለቱን ክፍለ ጊዜ አልገባችም ነበር ። ለማ ሊናገር ፈልጐ ከአፉ የመለሰው ይህን ጉዳይ ነበር ። ነገሩ አላማረውም ። ገና ምኑም ሳይጀመር መቅረት ካመጣችማ ፡ ግንኙነታችን ከጠበቀ ጭራሽ ላትገባ ነው የሚል ሥጋት አድሮበታል ። ሆኖም በዚች
ዕለት ያንን ችግር አንሥቶ በሁለቱም ዐይን ውስጥ የሚንቀለቀለውን የወሲብ እሳት እንዳያጠፋ ስለፈራ አደባብሶ አለፈው።

ቤተልሔም ሁለቱን ክፍለ ጊዜ ያልገባችው ሆነ ብላ ነው ።ከቀጠሮ ቀን በፊት ደጋግሞ መተያየቱ ሁኔታውን ሊያበላሽው
ይችላል የሚል ሥነ ልቡናዊ ግምት ስላደረባት ፥ አንዴ እሲኪያወጣትና ጅማሬው መልክ እስኪይዝ ድረስ ከለማ ጋር ላለመተያየት ፈልጋ ነው ። ለማ ክፍል ... ብሎ ገና ሲጀምር ነገሩ ቢገባትም ቅሉ እሷም በዚች ደቂቃ
እኔዲነሣ የማትፈልንው ጉዳይ ስለሆነ እንዳልሰማች ሆና አሳለፈችው ።

ምንስ ቢሆን ያንተን ቀጠሮ እንዴት እረሳዋለሁ ? ”አለችና ደማቅ ፈገግታ አሳይታው ዐይኖቹ ላይ ተከለቻቸው እነዚያ የሰርጉ ዕለት ምላሱን ያሳሰሩት ዐይኖችዋ አሁንም አዩት ። “ ለመሆኑ 'ኃይለኛ ዐይን እንዳላት ለእሷም
ይታወቃት ይሆን ?” ሲል ተደነቀ ። ለአስተያየቷ ግን ምንም መልስ አልሰጣትም ደካማ ፈገግታ ብቻ !

“ ስለ ዘገየሁብህ ቅሬታ ተሰምቶህ እንደሆን እክሳለሁ ” አለችው ።
ምን ዐይነት ካሣ ? ” አላት ። የልቡ ቁልፍ ፍጹም ላልቶ እየተበረገደ ።

“ ካሣ ነዋ ! የተጠየኩትን ። ”
ከአቀማመጧ ለመመቻቸት ዳሌዋን ነቅነቅ ስታረገው የእሱም ልብ አብሮ ከቦታው ተነቃነቀ ። እንደ አውሬ ተሸክሟት
ቢወጣ በወደደ ነበር ።

በድንገት አንድ ሰው ወደ ሆቴሉ ሲገባ በተመለከቱ ጊዜ ሁለቱም ተደናገጡ ። አንድ የዩኒቨርስቲ ባልደረባ ነበር ። ከለማ ጋር በዐይን ይተዋወቃሉ ። የት ክፍል እንደ ሚሠራ ግን አያውቅም ።ከሩቁ ሰላም ብሎአቸው ፥ ሰው ፈልጎ እንዳጣ ዐይነት ወደ ኋላው ተመለሰ ።

አጓጉል ቦታ እንደሆኑ ለማ የተሰማው ይህን ጊዜ ነበር" ቀጠሮው ራሱ የመዋከብ ዐይነት ስለ ነበር ነው እንጂ እንዲህ ብዙ ሰው የሚገባበት በታ ለሽምቅ ውጊያ አመቺ እንዳልሆነ
ቀድሞም አላጣውም ነበር ።

“ብንሔድ ምን ይመስልሻል ? ” እላት ፡ ያወለቀውን ኮት መልሶ እየለበሰ ።

እንሒድ እንዴ ? ” አለች : ለመቃረን አስባ ባይሆንም ፥ መልስ መስጠት ስላለባት ብቻ ።

አይመስልሽም ? ” አላት ፥ ቢራውን ለመጨረስ ከተጐነጨ በኋላ ሒሳቡ እንዲመጣለት አዞ።

እሷም ጭማቂውን ግማሹን ትታ ሹራቧን አጥልቃ ተነሣች ። ሒሳቡን ከፈለና ወጪ
ታክሲ ተሳፍረው ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ሲያመሩ ምንም ቃል አልታሰዋወጡም ። ወዴት እንደሚወስዳት አልነገራትም ። እሷም ኣልጠየቀችውም ብቻ ጸጥ ብሎ ወደ መሐል አራዳ !

“ ቤቴን ላሳይሽ ብዬ ” ኮ ነው ” አላት ከታክሲ ከወረደች በኋላ ።

በደስታ ! »”

ትንቀኛለች በሚል ፍራቻ መኖሪያው አልቤርጎ መሆኑን ሊገልጽላት አልፈለገም ነበር ። ታክሲ ውስጥ ሆኖ ሁኔታውን እስልቶታል ። ለጊዜው እንደ ተከራየው አልቤርጎ አስመስሎ ሊያስተዋውቃት አሰበ ። ነገር ግን ክፍሉ ውስጥ በርካታ የግሉ ዕቃዎች ስላሉበት የማያዋጣ ሐሳብ መሆኑ ገባው ።

በስኒማ ኢትዮጵያ ጀርባ ታጠፉ ።

“ ግን እዚህ አካባቢ ነው እንዴ ሰፈርህ ?

“ አዎን ! ”

ታድለህ ! መሐል አራዳ ! ”

መታደል አልሽው ?” አለና በልቡ ፥ “ እስቲ ገምቺ የትኛው ይመስልሻል የኔ ቤት ? ” አላት ፡ በአንድ መልኩ በቀልድ ፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ስሜቷን ለመገመት አስቦ

ግራ ቀኝ የምታየው ቡና ቤት ብቻ ነበር ።
“ እኔ እንዴት ዐውቀዋለሁ? ” አለች ፥ ይኼ ነው ለማለት ፈርታ ።

“ እንዲያው በግምትሽ ? ” ሲል አፋጠጣት ። በስተግራዋ በኩል አንድ አፓርትመንት አየችና፡ “ምና ልባት እዚህ ውስጥ ? ” አለችው ።

ሣቀና አፓርትመንቱን ዐልፎ ወደ ሌላ ግቢ ይዞአት ገባ ። በጓሮ በር ስለ ገቡ ምን ሆቴል እንደሆነ ልታውቅ አልቻለችም ።

“ ይኸውልሽ ፥ ቤት ለመከራየት ከተመዘገብኩ ሦስት ዓመት ሆነኝ ” አላት
በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ሲገቡ ።

እንደ ገባች አጠገቧ ያገኘችው ደረቅ ወንበር ላይ ልትቀመጥ ስትል ለማ ክንዷን ይዞ

“ ኧረ አልጋው ላይ ተቀመጭ ” አላት ።
“ አይ ፥ ነውር ነው ” አለች 'ለመግደርደር ያህል
“ እባክሽ ተይ ! ነውር ድሮ ቀረ ! ” አላት ፥ በልቡ ነውር ብትፈሪ መጀመሪያውኑ መቼ መኝታ ክፍሌ ድረስ ትግቢ በር ? ” እያለ።
መኝታው ላይ ተመቻችታ ከተቀመጠች በኋላ የክፍሉን ዙሪያ ገብ መማተር ጀመረች ። ግድግዳው ላይ ሦስት
ሥዕሎች ተለጥፈዋል ። ንብረቶቹ ለቁጥር አያስቸግሩም ።ሁለት ደረቅ
👍2
ወንበሮች ከአንዲት አነስተኛ ጠረጴዛ ጋር አናቱ ላይ የጉዞ ሻንጣ የተሰቀሰበት አንድ ቁም ሳጥን መኝታውና አጠገቡ ያለችው ኮሞዲኖ ፣ እንዲሁም ሙሉውን በመጻሕፍት የተገጠገጠ አንድ መደርደሪያ ናቸው ።

“ ምግብ የት ትበላለህ ? ” አለችው ከልቧ አዝና ።
ሆቴል ነዋ ! ” አላት ከአፉ አምልጦት ። ከአፉ ባያመልጠውም ሴላ መልስ አልነበረውም ።

ምንም ሳያስቀምጥ ወይም ሳያነሣ እንዲያው ክፍሉ ውስጥ በሸሚዝ፣ በመንጐራደድ ላይ ነበር ።

ቤተልሔም የቤቱን ኣኳኋን እየተመለከተችና የለማን አኗኗር በልቧ እየገመተች ኀዘን ስለ ተሰማት የወሲብ
ስሜቷ እየቀነሰ ! የእኅትነት ዐይነት አስተያየቷ እየጐላ ሔደ ፤ ብርሃን ሲረጭ የቆየው ፊቷ መዳመን ጀመረ ።

ቤተልሔም ምቾት ትፈልጋለች ። የስሜት ሕዋሳቷ ከላይ እስከ ታች የሚግሉት ምቾት ስታገኝ ብቻ ነው ። ወንድ ልጅ የሚያሸንፋት " ልቧን ጥሶ የሚገባው ምቾቷን የጠበቀላት እንደሆነ ነው ። አሁን የተሰማት ለአንገቱ ማስገቢያ እንኳ መሥራት አለመቻሉ ነው ። ግን እሷ ከለማ ቤቱን " ውበቱን ወይም ገንዘቡን አይደለም የምትፈልገው ። ከእሱ
የምትፈልገው ማርክ ብቻ ነው ። ድህነቱ ማርክ ከመስጠት አያግደውም ነገር ግን እሷ ከወላጆቿ ጋር በምትኖርበት ጊዜ አሁን ለማ ካለበት በእጥፍ ምቾት ትኖር እንደ ነበር ስታስታውስ ከልቧ አዘነችለት።

ታዲያ ምን ይምጣልን ? ” አላት ለማ ፡ የሚያቀርብላት ነገር ግራ ጎብቶት ። ለግድያው ምንም ዝግጅት አላደረገም ነበር ። ከቡና ቤቱ አልኮል ማስመጣት የታየው ገና አሁን ነው

“ ምን? ከየት ? ” አለችው ግር ብሎአት "
የሆቴሉ ቡና ቤት ኣለ'ኮ ! የምንጠጣው ነገር ላስመጣ ? ምግብም ከፈለግሽ ሊመጣ ይችላል ።”

“ አሁን ምንም አልፈልግ በኋላ ስንወጣ ይሻላል ”
“ እውነት ? ”
“ እውነት !

የመስኮቱን መስታወት ከፍቶ ዕንጨቱን ዘጋው ፤ መብራቱን አበራ ፤በሩ በቅጡ መቆለፉን አረጋጥብ ።

“ ሽንት ቤታችሁ የት ነው?” አለችው ቤተ ልሔም አዝማሚያው ሳለ ገባት ቅድመ ዝግጅቷን ለማጠናቀቅ አስባ።

“ ነይ ላሳይሽ ”አላት የተበላሸው የሆቴሉ ሽንት ቤት በሃሳቡ ታይቶት ! ልቡ እየተሸማቀቀ ። መከልከል የማይቻል ሆኖበት ነው እንጂ ፥ ከአጠገቡ እንድትነቃነቅ አልፈላገም ነበር ። በወጣችበት ሾልካ የምታመልጠው መሰለው።

ሩቅ ነው እንዴ? ” አለችው በጣቱ ወደ ሚያመለክታት አካባቢ እያየች። እሷ የገመተችው ከመኖሪያ ክፍሉ ጋር
ባይያያዝም እንኳ አጠገቡ ይሆናል ብላ ነበር ።

“ አይዞሽ ! በዚህ በኩል ሰው አይመጣም ” ብሎ አጽናንቶ ላካት።

ከሽንት ቤት እስክትመለስ ጫማና ካልሲውን አውልቆ ጠበቃት።
“ እህሳ ሰው ነበር ? ” አላት ፡ የፍርሀት ፈገግታ እያሳያት።
አልነበረም " አለችውና ፡ አልጋወ ላይ ሒዳ እንደ ሕፃን ልጅ ዘፍ አለች ። እጅዋን ይዞ ወደ ደረቱን ሳባት ። እንን አንገቷን
ጭምቅ አርጐ እቅፎ ከንፈሩን ከንፈሯ ላይ ሊያሳርፍ ሲል እምር ብላ ተስፈንጥራ አመለጠችው።

ምነው? አላት ደንግጥ ብሎ በወሲብ ግለት በራው ላብ መንቸፍቸፍ ጀምሮአል

“ ቆይ ሊፕስቲኩን ልጥረግልህ ” አለችው

እሷ ከቦርሳዋ ሶፍት አውጥታ የከንፈሯን ቀለም ስትጠርግ እሱ በነጠላ ጫማ ሔዶ በሩን ቆልፎ ተመለሰ ። የልቡ ትርታ ፍጥነት ለራሱም አስፈራው ። ትልቅ ተራራ የወጣ ያህል ነበር ሽቅብ ሽቅብ የሚነጥረው ።

ቀሚሷን ስታወልቅ ምራቁን በደረቀ አፉ አሁንም አሁንም እየዋጠ ለአፍታ ያህል በልብሶቿ ጥራት ተደነቀ ።ከጡት መያዣዋ ጀምሮ ያደረገቻቸው ልብሶቿ ሁሉ አዲስ ነበሩ ። ይሁንና ይህን በሰፊው ለማድነቅም ሆነ ለመመራመር ጊዜ አልነበረውም ።

ገና አንድ ጐኗን አልጋው ላይ እንዳሳረፈች በስሜት እሳት የጋለ ሰውነቱ ውስጥ አስገብቶ እቅፉ ውስጥ አቀለጣት።

💥ይቀጥላል💥
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

የገዳሙ ምዕራብ ክፍል በጥቅጥቅ ደኖች የተሞላ ሲሆን፣ምዕመኑ በየዛፉ ስር ተጠልለው በአርምሞ ፀሎት ያደርጋሉ፡፡ ፀበል ይጠጣሉ። ደቡባዊው ክፍሉ ደግሞ፣ ከፍተኛ ተራራ ላይ ያለ ሲሆን፣
ወደታች ያለው የሚያሰፈራ መጨረሻው ማይታይ ጥልቅ ገደል ነው።
ለገዳሙ እንደአጥር ያገለግላል፡፡ እዚህ አካባቢ የበቀሉ ትላልቅ ዛፎች ቅርንጫፍ ከግቢው አልፎ ወደ ገደሉ ይዘናፈላሉ፡፡ በዚህ አቅጣጫ ገደላማና በረሃማ ስለሆነ፣የሰው ዘር ዝር ብሎበት ሚያውቅ
አይመስልም፡፡ ገና ሳየው፣ በውስጤ እራሴን ማጠፋበት ትክክለኛው ቦታ
እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ ጠጋ ብዬ ለወራት የተዘጋጀሁበትን ሰው ሳያየኝ የምፈፅምበትን ዛፍ መምረጥ ጀመርኩ። ውስጤ ምንም አይነት ፍርሃት እየተሰማኝ አይደለም፡፡ አሁን ውስጤ የሚፈልገውን ቦታ አግኝቷል፡፡
ስህተት ላለመፍጠር፣ የግቢውን እንቅስቃሴ በደንብ ማወቅ፣ ተስማሚ
ሰዓት ለመምረጥ፣ አብዛኛውን ጊዜ እዛ አካባቢ ያሉ ዛፎች ስር ቁጭ ብዬ ሰው ጭር የሚልበትን አመቺ ሁኔታ እያጠናሁ፣ የገዛሁትን ፎጣ ለአሰብኩት አላማ እንዲመቸኝ በመቀስ እየቆረጥኩ በሚገባ
አስተካክዬዋለሁ፡፡ ከወራት በኋላ፣ የመጨረሻው መጨረሻ ደርሷል፡፡
ሰዎች እንዳይጠራጠሩኝ ምእመኑ ሚያደርጉትን ሁሉ እፈፅማለሁ፡፡ ሁሌ ሰርክ አስራ አንድ ሰአት ጀምሮ የግቢው ዋና አስተባባሪና ሰባኪ፣ ትምህርት ይሰጣል፡፡ እረጅም ቀጠን ያለ፣ ጥሩ
ተናጋሪ ጎልማሳ ነው፡፡ በስብከቱ ሰዓት ከፕሮግራሙ የሚቀር አንድም ሰው የለም፡፡ ትክክለኛው ሰዓት እንደሆነ እርግጠኛ ሆንኩ፡፡ አንድ ቀን፣የመጨረሻ ከኔ ጋር የቀሩትን የትምህርት ማስረጃዬን ጨምሮ፣ ማስራጃ ሊሆኑ ሚችሉትን፣ እንዳይገኙ ቆፍሬ ስቀብር ዋልኩ፡፡ ማታ ምዕመኑ ለጉባዔ ሲሄድ እኔ የተለመደው ቦታዬ ቁጭ ብዬ የእቅዴን መጨረሻ
ለመፈፀም አደፈጥኩ፡፡ እንደጠበኩት ፀጥ ረጭ አለ፡፡ ተነስቼ ያስተካከልኩትን ፎጣ ቼክ አድርጌ፣ ወደ መረጥኩት ዛፍ ሄድኩ፡፡ ድንገት ኬት እንደመጣ ያላስተዋልኩት አስተባባሪ፤

“እንዴት አመሸህ?” አለኝ፡፡

“እግዚአብሄር ይመስገን!” በንዴት መለስኩ፡፡

“የምሽት ጉባኤ ተጀምሯል እኮ፣ አትሄድም እንዴ?”

“እየሄድኩ ነው፡፡” ኬት ነው የመጣው ባካቹ ኮቴ ቢስ፡፡ ሄጄ የተለመደውን ስብከት ተከታተልኩ፡፡

ከጉባኤ ስመለስ መልካሙን አገኘሁት፡፡ ከገባንበት ቀን ጀምሮ ባገኘኝ ቁጥር ያወራኛል፡፡ የገባሁ ቀን ስለ ላጨኝ የተወሰነ ገንዘብ ሰጥቼዋለሁ፡፡ ሊቀርበኝ ይሞክራል፡፡ ለሻወር ውሃ ላምጣልህ ይለኛል፡፡ሲያመጣ የተወሰነ ነገር እሰጠዋለሁ፡፡ በዛ አምኖኝ ነው መሰል፣ ስለ ገዳሙ ጥሩም መጥፎም የሚሰማውን ይነግረኛል፡፡ የገዳሙ አባት
ከፍተኛ ሀይል እንዳላቸው፣ እርሳቸው ሲመጡ፣ በግቢ ውስጥ ሰይጣን
ያለበት ሁሉ እንደሚጫኽ፣ ከከፍተኛ የባለስልጣን ሚስቶች ጀምሮ የውጪ ሃገር ዜጎች እዚህ እንደሚመጡ ይነግረኛል፡፡ ወራትን የቆዩ ምዕመናን አስተባባሪ ሆነው እንደሚሾሙ፣ ግን አንዳንዶች ያልሆነ ወሬ ስለሚያወሩ መባረር እንደሚያሰጋቸው ያጫውተኛል፡፡ ቢወጡ መሄጂያ፣መጠጊያ ስለሌላቸው እዛ መሆንን እንደመረጡ፣ ተሸሎኝ ወደ መኖሪያዬ ስመለስ እንድጠይቀው፣ እዚህ ኑሮ ከባድ እንደሆነ፣ ከቤት ውጪ ሌላ
ደሞዝ እንደሌላቸው፣ እንደኔ ያሉ አንዳንድ ምዕመናን በሚያደርጉላቸው ድጎማ እንደሚኖሩ አጫወተኝ፡፡

አብዛኛው በገዳሙ የሚገኙት ምዕመናን ወጣት ናቸው፡፡ አማካኝ ዕድሜ ቢስላ ከሰላሳዎቹ መጀመሪያ አይዘልም፡፡ አብዛኞቹ ለሳምንታትና ለወራት ሚቆዩ ናቸው። ባገኘሁት አጋጣሚ ብዙኃኑ ሰው የመጣበት ምክንያት፣ ሰይጣን አለብኝ ብሎ በመጨነቅ፣ በህይወት አለመቃናት
የተከሰተ ጭንቀትና ሌሎች ዓለማዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡ በገዳሙ ሁለተኛ ሳምንት እንዳለፈኝ፣ አይታወቅምኮ እኔም ስይጣን አሞኝ ይሆናል ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ሰው እንዴት በሀገር ሰላም እራሴን ላጥፋ ብሎ፣ ይሄን ሁሉ ሀገር አቋርጦ ይመጣል? ለማንኛውም፣ ፀሎት
መድሃኒት ነው ብዬ፣ ለሱባኤ ዋሻ ገባሁ፡፡

የዋሻው አስተባባሪ መነኩሲት፣ ስለዋሻው ህግና ደንብ ትነግረኛለች፤ አፍጥጬ አያታለሁ፡፡ እጅግ ዘመናዊ የምትመስል፣ ሴት ናት፡፡ ጥርት ያለው የፊቷ ቆዳ፣ የገዳማዊ ሴት ሳይሆን፣ ሜክ አፕ
የተቀባች፣ ኑሮ የደላት፣ የከተማ ልጅ ፊት ይመስላል፡፡ ከተሸፈነችበት ነጭ ነጠላ፣ አልፎ ሚታየው ንፁህ፣ ሉጫና ደማቅ ጥቁር ፀጉሯን ሳይ መሀል አዲስ አበባ እንጂ፣ ገዳም ውስጥ ያለሁ አልመሰልህ አለኝ፡፡እያወራች ስታየኝ በሃዘኔታ የምትመለከተኝ መሰለኝ፡፡ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ስንት ጊዜ እንደምፀለይ፣ እንደሚሰገድ፣ እግዚኦ ሲባል እንዴት
ጣት እንደሚቆጠር፣ የለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ፀሎት በእርሷ እየተመራን እንደምንፀልይ አስረዳችኝ፡፡

እኔ ይህች ለጋ ሴት እዚህ ምን ትሰራለች እያልኩ በመገረም አያታለሁ፡፡ አይደለም ስግደት፣ ፆም ባለፈበት አልፋ ምታውቅ
አልመስልህ አለኝ፡፡ እኔ እዚህ ከመጣሁ፣ በሁለት ሳምንት ብቻ ብዙ እንደከሳው ታውቆኛል፡፡ የሱሪዬን ቀበቶ ቀዳዳ ሁለቴ ቀይሬያለሁ፡፡በዋሻው ሚቆየው ሦስት፣ ሰባት፣ አስራ አራት እና ሃያ አንድ ቀን ነው፡፡በሱባኤው ጊዜ፣ ለምትፀልይበት ጉዳይ አርሴማ በአምሳል ተገልጣ
መፍትሄ ትስጥሃለች አለችኝ፡፡ እንደታዘዝኩት መፀለይኩ፣ መሰገድ
ጀመርኩ፡፡ በጣም ከባድ ነው፡፡ እረሃብ አጠወለገኝ፤ ስግደቱ አወላለቀኝ፡፡
የለሊቱ ቅዝቃዜ ይጠዘጥዛል፡፡ መሬቱ በጣም የቆረቁራል፡፡ እንቅልፍ ማይታሰብ ነው፡፡ እዚህ አንዱ ቀን በጣም እረጅም ነው፡፡ ከሦስት ቀን በፊት መውጣት ቢቻል፣ ሲነጋ ውልቅ እል ነበር፡፡ በዛ ላይ ፣ትንሽ ሸለብ ሲያደርገኝ፣ ሰይጣን ክፋቱ መነኩሲቱን እያመጣብኝ ይፈትነኛል፡፡
ሦስቱን ቀን እንደምንም ጨረስኩኝ፡፡ ልወጣ ስል እንዳገባቤ መነኩሲቷ፣
አናገረችኝ::

“እንዴት ነበር ሱባኤህ?

ጥሩ ነበር አልከትና ከዋሻው ወጥቼ ወደ አዳራሼ ተመለስኩኝ፡፡ማታ እንቅልፍ አልወሰደኝም፡፡ አሁን ሁሉም ነገር ታክቶኛል። ባለፈው ያ አስተባባሪ ነው ከመንገዴ ያቆመኝ፡፡ አሁን መሳሳት የለብኝም፡፡
የባለፈውን ስህተት ላለመድገም ለሊቱን እያቀድኩ እስኪነጋልኝ ቸኮልኩኝ፡፡ እንቅልፍ በዐይኔ ሳይዞር ነጋ፡፡ አስር ሰዓት አካባቢ ሲሆን፣ ሙሉ ትጥቄን ይዤ ወጣሁ፡፡ ያቀድኩትን ለመፈፀም ገመዱን አስተካክዬ ዛፉ ላይ ካስርኩ ቦሃላ፣ እስኪጨልም ለመደበቂያነት ወዳሰብኩት
የሚያስፈራው ተራራ ጀርባ ቀስ ብዬ ለመውረድ ስል፣ አፈሩ እየተናደ ቁልቁል ሲዖል ወደ ሚመስለው ጥልቅ ገደል ይዞኝ መውረድ ጀመርኩኝ፡፡


ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
#ሰመመን


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...መብራቱን ላጥፋው ? ” አላት ፡ በጣም በደከመ “ እንዳሻህ ” በማለት ዐይነት ትከሻዋን ነቀነቀች ስሜትና ወበቅ ስሳፈኗት መተንፈስ አልቻለችም ሁለቱም በድካም ሰመመናዊ እንቅልፍ አሸለባቸው
ለማ በሰመመን በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲው ተጓዘ ።

ያ ራስ ሆቴል ተቀምጠው ያያቸው ሰውዩ ይመስለዋል በስብሰባ መሐል “ አጀንዳ ይያዝልኝ ” እያለ ደጋማም እጁን ያወጣል

“ እሺ አጀንዳህ ምንድነው? ” ይለዋል የስብሰባው ሊቀ መንበር ከልጃገረድ ተማሪዎቻቸው ጋር ስለሚቀብጡ መምህራን ጉዳይ ነው ” ይላል ሰውዬው ፥ መላ ሰውነቱን በብስጭት እያወራጨ

ለማ ፊቱ ቀልቶ ፡ በራው ላብ አንቸፍፎ ያጋለጠው ይመስለዋል "

እንድ ተማሪ ደግሞ እጁን አውጥቶ ለሰውዬው ድጋፍ ይሰጣል " ይህ ወጣት ለማ ክፍል ውስጥ በጣም የሚያደንቀውም የሚፈራውም ጠንካራ ተማሪ መሰለው ።

አዎ ! እንዲያውም ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ አጀንዳ ነው ይላል ተማሪው ገንፍሎ ።

እሺ " በል አጀንዳህን አብራራ።” ይላል ሊቀ መንበሩ ።

“ በጣም የሚያሳዝን ተግበር ነው ” ይላል ሰውዬው "
በጣም የሚያንገበግብ ነው እንጂ ፣ ” ይላል ተማሪው ተደርቦ።

“በሥነ ሥርዓት ተናገሩ” ይላል ሊቀ መንበሩ በቁጣ ሰውየው ብቻ ንግግሩን ይቀጥላል ።

“በውነቱ በዩኒቨርስቲያችን ውስጥ እንዲህ ዐይነት ድርጊት ሲፈጸም ያሳዝናል ። የዩኒቨርስቲዉን ሥርዓት ማበላሸት ነው ። አንድ መምህር የሚያስተምራትን ተማሪ አውጥቶአት ግሪል ጋብዞአት ከሲኒማ ኢትዮጵያ በስተጀርባ ከሚገኝ አንድ ስውር መኝታ ቤት ይዞአት ሲገባ እኔ ራሴ በዐይኔ በብሌኔ አይቻለሁ ። ሊቀ መንበር ፥ ይህን ጉዳይ ከግላዊ ነጻነት አኳያ አይተው እንዳያይዘጉት አደራ እላለሁ ።መታየት ያለበት በዩኒቨርስቲዉ ውስጥ ከሚያስከትለው የአሠራር ብልሽት አኳያ ነው እጅ ወዳጁ ላይ ሊሰነዘር አይደፍርም " ደካማ ተማሪውን እቅፎ መምህርያም ዐይኑ እያየ ፈተናውን አይጥላትም ። እንዲህ ከቀጠለ ደግሞ ዩኒቨርስቲዉ ውስጥ የሚያስፈልገው ጭንቅላት መሆኑ ቀርቶ ወሲብ ሊሆን ነው ።

ለማ " ላቡ በጀርባው ሲንቆረቆር እየተስማሙ ብቸኛ ላለመሆን በዐይኑ ሚስተር ራህማንን ፍለጋ አዳራሹን ያማትራል ሚስተር ራህማን የሉም ።

ተጨማሪ ያልተጠቀሰ ነጥብ እያል ተማሪዉ ጣቱን ያወጣል " ሊቀ መንበሩ እንዲናገር ይፈቅድለታል

“ አዎ ! በተጨማሪም ጒዳዩ መታየት ያለበት ከዩኒቨርስቲው የአሠራር ስልት ጋር ነው ።ዩኒቨርስቲው የተማሪዎችን የፈተና ወረቀት አርሞ ማርክ የሚሰጠው በስኬል ሲስተም ነው ። ስለሆነም አንድ መምህር የሚወዳትን ደካማ ተማሪ ከውድቀት ለማዳን የአንድ ጎበዝ ተማሪውን ዕድል እንደሚያበላሽ ፡ ምናልባት ባይጥለው እንኳ ይፈጃውን እንደሚቀንስበት አብሮ መታየት አለበት “ ”

“እሺ " እንግዲያ ! ቤቱ ይነጋገርበት” ይላል ሊቀመንበሩ ። በአዳራሹ ውስጥ ታላቅ ማዕበል የተነሣ ይመስል ሁሉም ጸጥ ረጭ ይላል “ የለማ ነፍስ በማዕበሉ ክፉኛ የተንገላታች ያህል ድምፅ የሌለው ጩኸት ትጮሀለች " ውስጥ ውስጡን ብቻዋን ትንፈራገጣለች ።

ከረዥም ጸጥታና እርስ በርስ መፋጠጥ በኋላ ፥ ከተሰበሰቡት ተሳታፊዎች አንዱ ተነሥቶ "

“ አጀንዳ ያስያዙት ግለሰብ ጥፋተኛውን ሊጠቁም ይችላሉ ? ” ሲል ይጠይቃል
በሚገባ ነዋ ! ያው መሐላችሁ ለማ
ካብት ይደመር እያለ በጣቱ ያመለክታል

“ማ? ! ” ብሎ ለማ ሲባርቅ፡ በእርግጥ ድምፅ ስላወጣ ከሰመመናዌ እንቅልፍ
ባንኖ ቤተልሔምንም አባነናት

“ውይ ምን ነካህ ?” አለች ቤተልሔም በድምፁ ደንግጣ።

“ እ ? ምንም ። ቅዠት ነው ” አላት : ሥራ ሥሮች በጭንቀት ተገታትረው ፊቱን አጨፍግጎ ።

በጭንቀት በተጨናበሰው ስሜቱ ሲያያት አጠገቡ የተኛችው ኮረዳ ሰይጣን መሰለችው ። እሷን ያቀፈበት እጁ
ዘግነነው ፤ቀስ ብሎ ክንዱን ከአንገቷ ሥር አወጣው ።

ቤተልሔም ደንግጣ " ዐይኖቿን በሚያስፈራው የለማ ፊት ላይ አንከባለለቻቸው።

“ በዚህች ደቂቃ የዐይኖቿ ውበት አልታየውም " ሁለተኛ እኔ ከማስተምርበት ክፍል አንዳትቀሪ እሺ?” አላት በመቆጣትም በማባበልም ዐይነት ምናልባት ሊያስጠረጥራቸው ከሚችሉት መንገዶች አንዱን መጥረጉ ነበር።

ቤተልሔም ምንም አልመለሰችለትም ። ለማ ዐይን ውስጥ ቀንዳቸውን አሹለው በተጠንቀቅ የቆሙ ሰይጣኖች
ተመለከተች የሴትነት ኃይሏን የተሸከሙት ዐይኖቿ እኒህን ሰይጣኖች ማሸነፍ አለባቸው ። እናም ስይጣናቱን በቆሙበት ብቸኛ መሣሪያዎቿ ዐይኖቿን ዐይኑ ላይ ማንከባለሏን ቀጠለች ። እንዲያ ሲንከባለሉ የሚታዩ እንጂ የሚያዩ አይመስሉም የዐይኖቻቸው ፍልሚያ የሁለቱንም ምላስ አሳስረው....
=========

“ ...ኧረ መላ በሉ ወዳጅ ዘመዶቼ
ዐይን አፋር ሆኛለሁ ዐይን አፋር አይቼ
ሰሳምታ አልሰጠኋት አሳነጋገርኳት
በዐይን ብቻ እያየሁ ሦስት ወር ወደድኳት

አቤል መተከዣውን ሙዚቃ በለሆሳስ እያዜመ መኝታው ላይ ጋደም እንዳለ በዐይኑ ማፍቀር የጀመረበትን ጊዜ
ርቀት ይለካ ጀመር ። ለወጉ ያህል ዐይኑን መጽሐፍ ላይ ሰክሷል ፤ ነገር ግን በፊደላት ፈንታ በርካታ የትዕግሥት
ምስሎች ነበሩ መጽሐፉ ውስጥ የሚነበቡለት ሳያስበው እርሳስ ከኪሱ አውጥቶ ስሌት ጀመረ ።

“ሦስት ወር ዐሥራ ሁለት ሳምንት ፥ ዘጠና ቀን ሁለት ሺህ አንድ መቶ ስድሳ ሰዓት አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ደቂቃ ፤ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ሴኮንዶች ... እንዴት በዚህ ሁሉ ጊዜ አንዲት ቃል እንኳ ሳልተነፍስላት እቆያለህ ? እንዴት ይህን ያህል ጊዜ በዐይን ፍቅር ብቻ እንገላታለሁ ? ! አንድ ወንድ እንዴት ይህን ያህል ጊዜ ልቡን ለሴት ልጅ ይሰጣል?” እያለ ሲያስብ
ድንገት ሳምሶን ጉልቤው ” የመኝታ ክፍሉን በር ከፍቶ ዘው አለ።

ከፀሐይ ላይ ስለ መጣ በስፖርት የዳበረው ጡንቻው ያብለጨልጭ ነበር አብዛኛውን ጊዜ በካኒቴራ ወይም
ጉርድ ሸሚዝ ነው የሚውለን ።

ተነሥ ደብዳቤ መጥቶልሃል ። ሰምህ ተለጥፎአል አለው አቤልን አስገምጋሚ ድምፅ አለው ። ልማድ ሆኖበት ረጋ ብሎ መናገር አይችልም ። ሳይቆጣም የተቆጣ
ይመስላል ። አቤልን ይወደዋል ። አቤል ግን ኣጸፋውን አይመልስለትም ሁሌ ዝምነው “ ይህንን ጸባዩንም ቢሆን ሳምሶን ጉልቤው የመኝታ ክፍል ጓደኛው እንደ መሆኑ መጠን ይረዳለታል ።

አቤልን ሁለት የዩኒቨርስቲዉ ወጣቶች በዐይን ፍቅረኝነቱ ሲያሙት ሰምቶ ካልተደባደብኩ ብሎ በግድ ነበር
የተገላገለው ። ፈጽሞ ጥቃቱን አይወድም

“ እውነትክን ነው ? ” አለው አቤል ፡ የደብዳቤውን መምጣት በመጠራጠር ። የደብዳቤ መምጣት ማንንም ስለሚያጓጓ ተማሪዎች አንዳንዱን ሳይመጣለት “ መጥቶልሃል ” እያሉ ልብ መስቀል የተለመደ ነበር ።

“ እውነቴን ነው ይልቅ የፖስታ ማደያው ቢሮ ሳይዘጋ ቶሎ ሒድ” አለውና ሳምሶን በአክብሮት ዘሎ አልጋው ላይ መጣ ። መኝታው ላይ በርጋታ ወጥቶ አያውቅም ።
የአልጋውን የጠርዝ ብረት ተመርኩዞ ሽቅብ ካልዘለለ አይሆንለትም ። ድብርትን ከሚያበሽቁት ነገሮች አንዱ
ሳምሶን መኝታው ላይ ሲወጣ የሚሰማው የአልጋው መንገጫገጭ ነው ።ተኝቶም ከሆነ ያባንነዋል ።

አቤል በነጠላ ጫማ በፍጥነት እርምጃ የመኝታ ቤቱን ደረጃ ወርዶ በሐሳቡ ማን ይሆን የጻፈልኝ ? ” እያለ በጉጉት ከደብዳቤ መቀበያው ቢሮ ደረሰ ።

“ የላኪው አድራሻ ” በሚለው በኩል የተጻፈው የእናቱ ስም ነበር ። የአራተኛ ዓመት ትምህርቱን ከጀመረ ከቤተሰቡ ደብዳቤ መጥቶለት አያውቅም ነበር እሱም ልኮ አያውቅም ደብዳቤውን
👍2
ለማንበብ ተቻኩሎ በመጣበት ፍጥነት ተመልሶ ገና ከምኝታ ክፍሉ በር ላይ ሲደርስ እሽጉን ቀደደው

“ እ ከየት ነው ? ” አለው ሳምሶን 'አ አልጋው ላይ እንደ ተንጋለለ።

“ ከቤተሰቦቼ ነው ”አለውና አቤል ከመኝታው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብሎ ያነብ ጀመር ።

“ እንደምን አለህ ልጄ ? ይህ ጽሑፍ የእኔ የናት። መሆኑን አትጠራጠር ” ይላል የደብዳቤው መግቢያ አቤል በእርግጥ የእናቱ ጽሕፈት መሆኑን ሊያምን አልቻ
ለም ። ነገር ግን ከቤተሰቡ ውስጥ እንደዚያ ዐይነት የእጅ ጽሑፍ ያለው ሌላ ሰው እንደሌለ ገመተ ። በቅርቡ ከማይምነት የተላቀቀ ጣት እንዳረፈበት በፊደል አጣጣሉ በመጫን የተጐዳው ወረቀት ያስታውቃል ።አቤል የሁለተኛ ዓመት ትምህርቱን እንደ ጨረሰ ወላጆቹን ሊጠይቃቸው ሔዶ በነበረበት ጊዜ ፥ እናቱ መሠረተ ትምህርት መጀመራቸውን
ነግረውት ነበር ። ሆኖም ይህን ያህል አርኪ ውጤት ያሳያሉ ብሎ አልገመተም ነበር ። ሕፃናት ማንበብና መጻፍ ቢችሉ
በዕድሜያቸው ምክንያት አያስደንቅም ። የወላጆቹ ከማይምነት መላቀቅ ግን ባህላችን ሆኖ ከደማችን እስኪዋሃድ
ድረስ ለጊዜው ያስደንቀናል ።

ተአምር ነው !” አለ አቤል በልቡ በዐይነ ሕሊናው በእጃቸው ብዕር ይዘው ከወረቀት ላይ ቃላት የሚያሰፍሩ
እናቱን እየተመለከተ ። መንፈሱ በደስታ ተወራጨ ። ጥሩ ነገር ማየት ጥሩ ሕልም ያሳልማል ። አቤልም ለአፍታ ያህል
በልቡ ትምህርቱን ጨርሶ ለኅብረተሰቡ ሊያበረክት የሚችለውን የተቀደሰ ተግባር አሰበ ። ለብልጽግናና ለተቀደሱ ግቦች ሀገሪቱ የምትጠብቀው የጋራ እጅ ብሐሳቡ ታየው ።እናም አንዳች የደስታና የተስፋ ስሜት ሰውነቱረን ወረረው
ነገር ግን ደብዳቤውን ዘልቆ ሊያነብ በቅጽበት ስሜቱ ተለዋወጠ ።

ቁትጽፍልን ይህን ያህል ለመቆየት እንደምን አስቻለህ ልጄ ? ደብዳቤም እኮ ተስፋ ነው ። አደራህን የምልህ ነገር ልጄ መመረቂያህ ቀን ሲደርስ እንድትነግረኝ
ነው ። እንዲያው እንደ ምንም ብዬ እመጣለሁ ። ቆብህን የምትጭንበትን ያንን ወርቅ ቀን አጠገብህ ሆኜ እልል
እያልኩ ማየት አለብኝ። አሁንማ ዓመቱን አጋምሰኸዋል፡ትንሽ ነው የቀረህ ። አባትህ ጤናም የለው ። ሁለቱንም አህዮች ሽጦአቸው ውሎው ከቤት ሆኗል መንቀሳቀስ አልቻለም ።በአሁኑ ጊዜ የእሱ ጓደኞች በጋራ ተደራጅተው ያርሳሉ ።
እንዴት የሞቀ ቤት አላቸው መሰለህ ! አርሶ ለባላባት መገበር ከቀረ ወዲህ የገበሬው ቤት ሙሉ ነው ። ምን ይሆናል !
አባትን ለዚህ አልታደለም ። ያ አስሙ በየጊዜው እየተነሳበት ያሠቃየዋል ። ቤተሰቡንደግፋ የያዘችው ያቺ አንድ
ላም ናት ። የሷንም ወተት ለተከራይዎቹ ማድረስ እንዴት ችግር መሰለህ ! ቤት ውስጥ የሚላክ ትንሽ ልጅ የለ ! እንዲያ መዋተት ነው ። ብቻ ግድ የለም ። ይኸው መውደቂያችኝ ላይ አምላክ አንተን አድርሶልናል ። እንግዲህ ምርኩዛችን
ነህ ። እጅህን እየጠበቅን ነው ልጄ !...

አቤል ደብዳቤውን ጨርሶ ማንበብ አልቻለም ። ደብዳቤው ላይ የሰፈሩት የሰቆቃው ጥሪ ፊደሎች እንባ ባቀረሩት
ዐይኖቹ ጎልተይን ብዥ ብዥና እያሉ ታዩት ወላጆቹ ዘንድሮ ይመረቅናል ብለው ማሰባቸውና በአንጻሩ እሱ በዚ ዓመት
ትምህርቱን እንደማይጨርስ አድርጎ መገመቱ ግላዊ የአእምሮ ግጭት ውስጥ ከተተው ። ነገሮች ተምታቱበት ድህነት ! ... ድህነት ! ... ድህነት ! ... ፍቅር ... የዐይን ፍቅር ! ...ትምህርት !... ትምህርት !

“ ድሀ ማፍቀር አይችልም ማለት ነውን ? ” ሲል ራሱን በራሱ ጠየቀ ። " አዎን አይችልም ፡ እንደምን ይችላል !
ከድህነቱ ለመፈወስ ይፍጨረጨራል ወይስ ፍቅሩን ያስታምማል ? ... እኔ ግን ድህነቴን የማላውቅ ዕውር ነኝ ። ለድህነቱ መፍትሔ ሳላገኝ ፍቅር ጀመርኩ እና አሁን የወላጆቼ የሰቆቃ ጥሪ በጠበጠኝ ። ... ግን ይታየኛል ።ለሁለቱም አልሆንም ። ከድህነቴም አልፈወስ ፥ ለፍቅርም አልበቃ ! . . . አዎ ! ለሁሉም አልሆንም ! ” እያለ በሐሳቡ ተወራጨ።

ድህኔትና የዐይን ፍቅር በእሱ የተነሣ ከፊት ለፊቱ ቆመው ፍልሚያ የገጠሙ መሰለው ። ድህነት የተበጣጠሰ ጥብቆ ለብሶ ተባዮች በሰውነቱ ላይ ፈልተው ፡ የተንጨባረረ ጸጉሩን እየፎከተ “ አድነኝ ” እያለ የተጠጋው መሰለው ። በአንጻሩ ደግሞ ፍቅር የተጐሳቆለና የከሳ ሰው
ነቱን አኮራምቶ የተራቡ ዐይኖቹን እያስለመለመ አስታመኝ ” ብሎ የተጠጋው መሰለው ።

ጥጋበኛ ድሀ ! ” ሲል አቤል ራሱን ሰደበ ። ዐይኑ ላይ የተራቀመው እንባ እስካሁን ጠብ አላለም ። ያሳለፈው ረዥም የድህነት ዘመን ታየው።

💥ይቀጥላል💥
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

#የመጨረሻው_መጨረሻ

ድንገት ስነቃ እራሴን አልጋ ላይ በጀርባዬ ተዘርሬ አገኘሁት፡፡ከፍተኛ ህመም ይሰማኛል፡፡ እራሴ አካባቢ፣ በቀኝ በኩል ሰውነቴን፣ፊቴን ይጠዘጥዘኛል፡፡ ዐይኖቼን ለመክፈት ሞከርኩ፡፡ የቀኝ ዐይኔን
ህመም ተሰማኝ፡፡ አልከፈት አለኝ፡፡ ዐይኔ ምን እንደሆነ ለመዳበስ፣ የቀኝ እጄን ለማንሳት ስሞክር፣ እ...ህ... ከፍተኛ ህመም፡፡ ማንቀሳቀስም፣ ማንሳትም አልቻልኩም፡፡ እጄስ ምን ሆኖ ነው...? ወደ እጄ ዞር ስል፣አንገቴ ከሆነ ነገር ጋር ታስሯል፡፡ ምን ሆኜ ነው..? የት ነው ያለሁት..? ማን ነው እዚህ ያመጣኝ...? በግራ እጄ ላይ የግልኮስ ገመድ
ተንጠልጥሎ አየሁ፡፡ ሆስፒታል ነው ያለሁት። የት ሆስፒታል ነው ያለሁት?፣ ምን ሆኜ ነው...? ለማስታወስ ሞከርኩ፡፡ ብዙ ጥያቄዎች በፍጥነት በጭንቅላቴ ተመላለሱብኝ፡፡ በበር በኩል፣ በርቀት አንድ ነጭ ገዋን የለበሰ ሰው ሲገባ አየሁ፡፡ እንዲስማኝ፣ አ...ብዬ አቃሰትኩ፡፡
እንደገመትኩት ድምፄን ሰምቶ ነው መሰል፣ በቀጥታ ወደ እኔ መጣ፡፡

“ኦ...ነቃህ?፣ በጣም ደስ ይላል፡፡ እንዴት ነህ?፣ ምን ይሰማሃል?” አለኝ፡፡

“ደህና ነኝ፡፡ ትንሽ እራሴ አካባቢ...” በደከመ ድምፅ፡፡

“ቆይ መጣሁ፡፡” ብሎኝ ሄደና፣ ብዙም ሳይቆይ የታካሚ ካርድ ይዞ ተመለሰ፡፡

የግራ እጄን ይዞ የልብ ምቴን ቆጠረ፡፡ በደም መለኪያ የደም ግፊቴን ለካ፡፡ ዐይኖቼን ከፍቶ አያቸው፡፡ ደረቴን በማዳመጫ አዳመጠ፡፡እግሮቼን አንቀሳቅስ እያለኝ፣ እግሮቼን በሹል ነገር እየወጋኝ፣ በሙሉ ስውነቴን መረመረኝ፡፡

“የት እንዳለህ አውቀሃል?” ጠየቀኝ፡፡

“ሆሰፒታል ነኝ መሰለኝ..."

“በጣም ጥሩ። እኔን ታውቀኛለህ?”

“አላውቅህም፡፡ ግን ዶክተር ትመስለኛለህ፡፡”

“እሺ፤ አሁን ስንት ሰዐት ይመስልሃል?”

“ሰዓቱን አላውቅም፡፡”

“በግምት፣ ጥዋት ከሰዓት ወይስ ምሽት ይመስልሃል?”

“መገመት ይከብደኛል።” አጠገቤ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጠና መፃፍ ጀመረ፡፡ ለደቂቃዎች ከፃፈ በኋላ፣ “አይዞህ፡፡ ትንሽ አደጋ ደርሶብህ ነው፡፡ አሁን ደህና ነህ፤
ተርፈሃል፡፡ እራስህና እጅህ አካባቢ ትንሽ ጉዳት ደርሶብሃል፡፡ ግን እድለኛ ነህ... ተረፈሃል ለህመምህ ማስታገሻ እንሰጥሃለን አይዞህ ብሎኝ ማስታገሻ መርፌ እንድወጋ አደረገ፡፡ ከብዙ ህመም ቦሃላ መልሶ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

ጥዋት ከእንቅልፌ ስነሳ፣ እረጅም እንቅልፍ እንደተኛው ተሰማኝ፡፡ ቀጣዮቹም ቀናት እጅግ በጣም ከባድ ነበሩ። ያለፈውን፣ የተፈጠረውን፣ መቀበልም መቋቋም አልቻልኩም፡፡ እራሴን በቁሜ
ቦርቡሬ፣ ገዝግዤ ጨርሼዋለሁ፡፡ ዳግመኛ እንዳልነሳ እንዳላንሰራራ
አድርጌ ቀብሬዋለሁ፡፡ አሁን ለኔ መኖር ከቀደመው የባሰ ሲኦል ነው፡፡ አሁን መሞት በጣም ያስፈልገኛል፡፡ ተሰምቶኝ ማያውቅ ጭንቀት እየተሰማኝ መጥቷል፡፡ . ትንሽ ድምፅ ይረብሸኛል። እንቅልፍ አይወስደኝም፡፡ ነገርግን፣ እንኳን እራሴን ላጠፋ፣ እራሴን ማንቀሳቀስ
ማልችል እንደሆንኩ ሳስብ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ ጭንቅላቴ
ሊፈነዳ ይደርሳል፡፡ በእንዲህ ባለ ሁኔታ ቀናቶች አለፉ፡፡ ዶክተሮች መጥተው ይከታተሉኛል፤ መድሀኒት ያዙልኛል። ጥዋት ጥዋት፣ የፊቴ ቁስል ይጠረግልኛል፡፡

አንድ ቀን እንደተለመደው ዶክተሮች ከጎበኙኝ ቦሃላ ሌላ እስፔሻሊስት ዶክተር መጥቶ እንደሚያየኝ ነግረውኝ ሄዱ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ሚከታተለኝ ወጣት ዶክተር እንደርሱ ነጭ ገዋን ከለበሰ ወጣት ጋር
ተመልሶ መጣ፡፡ አዲሱ ዶክተር ካርዴን ተቀብሎ አገላብጦ አነበበው፡፡

“ማን ነው እዚህ ያመጣው?” አዲሱ ዶክተር ጠየቀ፡፡

“አምስት ቀን ሆነው፡፡ ገዳም አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ናቸው አምጥተውት የሄዱት።”

ዝም አልኩኝ፡፡ በራሴ አፈርኩ፤ ዐይኔን ጨፈንኩ፡፡ አዲሱ ዶክተር፣ እኔን ሳያናግረኝ በእጁ ግራ እጄን እያሻሸ፣ ከስራ ባልደረባው ጋር ያወራል፡፡ በእጁ እንቅስቃሴ፣ ልስላሴና ሙቀት፣ በውስጡ እያዘነልኝ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡

“ዶ/ር ሄኖክ እባላለሁ፡፡ ሄኖክ ብለህ ልትጠራኝ ትችላለህ፡፡ የስነ-አዕምሮ ህክምና ክፍል፣ የመጨረሻ አመት የድህረ ምረቃ ሃኪም ነኝ፡፡አንተስ ስምህን ትነግረኛለህ?” ፊቱ፣ ድምፁ፣ ሁሉ ነገሩ ላይ ሃዘኔታና ርህራሄ የሚነበብ መሰለኝ፡፡

“ያቤዝ እባላለሁ፡፡”

“ያቤዝ ማን?”

“ያቤዝ አለማየሁ፡፡”

“እድሜ ?”

“ሠላሳ አራት፡፡”

“እራስህን ልታጠፋ ሞክረህ እንደነበር፣ ምታስታውሰው ነገር አለ?”

ዝም አልኩ፡፡ ጭንቅላቴ ይወቅረኝ ጀመር፡፡

“ደህና ነህ ያቤዝ?”

“ደህና ነኝ ዶክተር።”

“እሺ ያቤዝ፣ ለህክምናህ ስለሚረዳኝ የሆነውን ነገር ልትነግረኝ ትችላለህ?፡፡ ልትነግረኝ ምትፈልገውን፣ ግን ትክክለኛውን ብቻ ንገረኝ፡፡ እያንዳንዱ የምትነግረኝ መረጃ ካንተ ፍቃድ ውጪ፣ ለማንኛም ሶስተኛ ወገን በፍፁም አይደርስም፡፡ ለቤተሰብህም ቢሆን እንኳን፡፡ መናገር የማትፈልጋቸው ነገሮች ካሉ እለፋቸው፣ እንዳትዋሸኝ፡፡››
“እሺ!” አልኩት በደከመ ድምፅ፡፡ ውስጤ በጣም እየተረበሸ ነው፡፡ምን ብዬ ነው የምነግረው? ከየት ነው የምጀምረው? የተፈጠረውን ወደ ኋላ ሳስበው፣ እንባ እየተናነቀኝ መጣ፡፡

“ያቤዝ እየጠበኩህ ነው፡፡ የሆነውን፣ የተፈጠረውን ንገረኝ፡፡እራስህን ልታጠፋ ለምን ሞከርክ?”

ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡ ዶክተር ሊያባብለኝ ሞከረ፡፡ ውስጤ ጭራሽ ገነፈለ፡፡ “እኔ ከሞትኩ ቆይቻለሁ፡፡ በቁሜ የአርባና ሰማንያ ተዝካሬን አውጥቻለሁ፡፡ ሀብትና ንብረቴን ነፍስ ይማር ብዬ በትኜዋለሁ፡፡ለወራት ስንከራተት የከረምኩት፣ አስክሬኔን የምቀብርበት ምቹ ቦታ ፍለጋ ነበር እንጂ፣ ላለመሞት አልነበረም፡፡ እንዴት ተረፍኩኝ...? ለምን..? እኔ
መኖር አልፈልግም...!” እየጮኸኩ ተንሰቀሰኩ፡፡ ቢያባብሉኝም፣ ማቆም
አልቻልኩም፡፡ እንባዬ የፊቴን ቁስል እየለበለበኝ ይወርዳል፡፡ ዶክተሮቹ
ከወንበራቸው ሲነሱ፣ ኮቴ ሲበዛ፣ ግርግር ሲፈጠር፣ እጄ ላይ በተቀጠለው ግሉኮስ፣ መድሃኒት ሲስጠኝ ይሰማኛል፡፡ የማለቅስበት ሃይል እየከዳኝ፣ ሳላስበው እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

ከዛች ቀን ጀምሮ የዶክተር ሄኖክ ክትትል በጣም የተለየ ነበረ፡፡እንደቤተሰብ ብዙ ሰዓታት ከኔ ጋር ያሳልፋል። ጥሩ ተቀራርበናል፤የሚሰማኝን የህመም ስሜት እነግረዋለሁ፡፡ መድሃኒት ያዝልኛል፡፡
ያዘዘልኝ መድሃኒቶች፣ ጥሩ እንቅልፍ እንድተኛ እያገዙኝ ነው፡፡እኔ ሳልፈልጋቸው ወደ ጭንቅላቴ እንደፈለጉ ሚፈነጩብኝ፣ እነዛ ተላምጠው ማያልቁ አስጨናቂና ተስፋቢስ ሃሳቦች እንደ ሀምሌ ዝናብ
እኝኝ ማለታቸውን አየቀነሱልኝ ነው፡፡ ዶ/ር ሄኖክ በተለየ አቅርቦት ይንከባከበኛል፡፡ እንደታካሚው ሳይሆን፣ እንደታላቅ ወንድም፣ እንደቤተሰብ፣ በሁሉም ነገር እያገዘኝ ነው፡፡ ከሁሉም ታካሚዎች ቀድሞ እኔን ይጎበኘኛል የሚያስታምመኝ ቤተሰብ ስለሌለ ይሁን አዛኝ ተፈጥሮ
ኖሮት ባላውቅም፣ ካወቀኝ ጀምሮ ከኔ አልተለየም፡፡ የህክምና ወጪዬንም
እየሸፈነ እንደሆነ አውቂያለሁ፡፡ አልፎ አልፎ ምግብ ከውጪ ያስመጣልኛል፤ አብዛኛውን ግዜ ስራውን ሲጨርስ፣ በተለየ ርህራሄና ፍቅር ያጫውተኛል፤ ያበረታታኛል፡፡ ተስፋንና ጥንካሬን በውስጤ ይረጨል፡፡ ቀናቶች ሲያልፉ፣ እየተሻለኝ መጥቷል፡፡ የፊቴና የእጄ
ቁስሎች ለውጥ አላቸው፡፡ ህመሞቼ እየቀነሱ፣ ለውጥ እያመጣሁ፣ የሞተው፣ የተቀበረው ተስፋዬ ዳግም ያቆጠቁጥ ጀመር፡፡

እጄን ሁለት ጊዜ ራጅ ተነሳሁ፡፡የተሰበረው አጥንቴ ጥሩ ሆኖ ጠግኗል፡፡ የታሰረልኝ ጄሶ ሊፈታልኝ ቀጠሮ ተሰጠኝ፡፡ የፊቴ ቁስል ህመሙ ጠፍቷል፡፡ በእጆቼ ዳበስኩት፤ ይሻክራል፡፡ ፊቴ ላይ ትልቅ
የማይሽር
👍41
ጠባሳ ጥሎ እንደሚያልፍ ታወቀኝ፡፡ ሀኪሞች አሁን ብዙ አይጎበኙኝም፡፡ ግሉኮሱ ከተነቀለልኝ ቆየ፣ አሁን የምወጋው መርፌ የለም፡፡ የምውጣቸው ክኒኞችም፣ ዶ/ር ሄኖክ ያዘዘልኝ ናቸው:: በቅርብ ከሆስፒታል ውጣ መባሌ ማይቀር ነው፡፡ የት ነው ምሄደው? በምን ገንዘብ ነው ምሄደው? ለማን መደወል እችላለሁ? የማንም ስልክ
የለኝም፡፡ ዱካዬን ሳጠፋ፣ ስልኬን ሰባብሬ ቀፎውን ጥዬዋለሁ፡፡ በአካል ካልሄድኩኝ፣ ምንም የመገናኛ መንገድ የለኝም፡፡ ልሂድ ብልስ ማን ጋር ነው ምሄደው? ምንስ ብዬ ነው? እንዴትስ እንዲህ እንደሆንኩኝ ምን
ብዬ አስረዳለሁ...? ዶክተር ድንገት አጠገቤ ቁጭ ሲል ከሄድኩበት ሃሳብ
ተመለስኩ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ