አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

ሜሪ፣ ቆንጅዬ የማሂ ጓደኛና የመስሪያ ቤታችን ሰራተኛ ናት።በቁንጅና አይተናነሱም፡፡ ሜሪ ግን፣ በእድሜ ልጅ ነች። ገና እንቡጥ፡፡ልጅነቷ ተጨማሪ ውበት ሆኗታል። ማሂ አንዳንዴ፣ በአንድ ቤትማ ሁለት ንግስት አይኖርም እያለች ትቀልዳለች፡፡ እኔን ጨምሮ፣ ብዙ ወንዶች ዐይናችንን ሜሪ ላይ ጥለንባታል፡፡ አለቃዬን ግን በፍፁም አልጠረጠርኩም ነበር፡፡

“እሱን ማን ጠየቀሽ? አሁን አንቺን ነው ማግኘት የፈለኩት፡፡”አለቃዬ እንደመቆጣት አሉ፡፡

“ምነው አልሰጥም አለችህ እንዴ?” ብላ ክትክት ብላ ሳቀች፡፡

“ስነ ስርዐት! እንግዲህ አትጨማለቂ፡፡ ስንት ሰዓት ልምጣና ልውሰድሽ?”

“የአንተ መምጣት አያስፈልገኝም፡፡ በትራንስፖርት እመጣለሁ።ከመጣሁ እደውልልሃለው። ቻው።” መልስ ሳትጣብቅ ስልኩን ዘጋችው፡፡ፊቷ በደስታና በድል አድራጊነት በርቷል እኔ የምፈራቸውና ማከብራቸው አለቃዬን፣ ፀሃፊያቸው እንዴት እንዲህ ተዳፈረቻቸው...? ከስራ ውጪ ሌላ ግንኙነት አላቸው ማለት ነው? ስልኩን እንደዘጋች፣ ፋታ አልስጠኋትም፡፡ በጥያቄ አጣድፋት ጀመር፡፡
“አንቺ፣ ጋሽ ሃይሌን፣ አለቃችንን ነው እንዲህ እየተመናቀርሽ ምታዋሪያቸው..?” ዐይኗ ላይ አፍጥጬ ጠየኳት፡፡

“አዎ፡፡ ምን አጠፋሁ?”

ትንሽ እንኳ ክብር የለሽም...? አለቃሽ ናቸውኮ፡፡ ሌላው ቢቀር አባትሽ ይሆናሉ፡፡ እላያቸው ላይ እኮ ነው ስልኩን የዘጋችው። ሲጀመር እንዴት ደወሉልሽ፣ ትግባባላችሁ?”

“ታዲያ ባንግባባ ምን ያስደውለዋል?፡፡ የዛሬን አያድርገውና ከስራ አይጠፋም ነበር።”

“ምን ማለት ነው? እስቲ በደንብ አስረጂኝ፤ ምንድን ነው ማላውቀው ነገር?”

“ከኔ ስር አይጠፋም ነበራ...! ከኔ ጋር መሆን ኩራቱ ነበር።ከስራ ሲወጣ፣ ከተማውን ሚዞረው እኔን ይዞ ነበር :: ቅዳሜና እሁድ ደግሞ፣ ሶደሬ፣ ላንጋኖ፣”

“ትዳር የለውም እንዴ?” እኔም እንደሷ አንተ ማለት ጀመርኩ።

“ባለትዳር አይዝናናም?” እየሳቀች መልሳ ጠየቀችኝ፡፡ ይሄን አታውቅም ቂል ብላ፣ ምትስቅብኝ መሰለኝ፡፡

“አይ፣ በጣም ጀንትል ነው፣ እንደምታወሪው አይነት ሰው
አይመስልም፡፡”

“ኪ....ኪ...ኪ..!” እግሮቿን እያነሳች፣ በረጅሙ ሳቀችብኝ፡፡

“ምነው ሳቅሽ?”

“ሃይላን ነው፣ ጀንትል ያልከው፣ ሴት ካየ ሳይመርጥ ሚልከሰከስ፣ እዚህ ግቢ ያሉትን ሴቶች ሳያማርጥ ካልተኛሁሽ የሚል፣ስሜቱን መቆጣጠር ማይችል ዝርክርክ? እኔን ሚያናድዱኝና ሚያበሳጨኝ ሴቶቹ ናቸው። ጓደኛዋን እንደተኛት እያወቀች፣እግራቸውን ከፍተው አብራውት ሚተኙት፡፡”

“ማለት፣ ጋሽ ሃይሌ፣ ከስታፎች ጋር ይወጣል እያልሽኝ ነው?”

“እንዴ...፣ አገር ያወቀውን ፀሃይ የሞቀውን አንተ አላውቅም እያልከኝ ነው?”

“እውነቴን ነው፤ እኔ ምንም አላውቅም፡፡”

“ስም ልጥራልህ እንዴ...፣ ፌቨን፣ ሳራ፣ ቤቲ፣ አሁን ደግሞ ተረኛዋ ሜሪ ነች፡፡ አሁን ከእርሷ ጋር ከንፏል።” ብስጭት እያለች ነው፡፡

“ቆይ፣ ሚስቱን አይፈራም እንዴ?"

“ሚስትና ልጆቹ አዲስ አበባ ናቸው። ማን ያየኛል ብሉ እዚህ ይንዘላዘላል እንጂ፡፡”

“በስማም! ቢያንስ አይደብረውም...?”

“አይደብረውም አልከኝ...? አሁን ጭራሽ ሜሪን ሚስቴን ፈትቼ ካላገባሁሽ እያላት ነው፡፡ ደግሞ መጥታ ትነግረኛለች።”

“እና ሜሪ አመነችው...?”

“አዎና፡፡ የሆነች ጅል፣ ከርፋፋ፡፡ ቀላል አምናዋለች፡፡ ደሞ ድንግል ናት፡፡”

“እና ድንድልናዋን ሰጠችው...?

ወጣችለት...?” ምሰማው ሁሉ
ማመን አቅቶኛል፡፡

“እንጃባቷ...! ሰጥታው ነው ሚሆነው፡፡ የሆነች ነፈዝ፡፡” በጣም የልብ ጓደኛሞች ነበር ሚመስሉኝ፡፡ ከአነጋገሯ ግን ሌላ ነገር ተሰማኝ፡፡

“እኔ ምልሽ፣ አንችም ተነካክተሽ ነበር እንዴ? በጣም የቀናሽ ትመስያለሽኮ፡፡"

“ማ...? እኔ ማሂ ቆንጆ ከዚ ሼባ ጋር? በስማም አንተ!”

“አይ እንደምታወሪለት ከሆነ፣ ሰውየው የሆነ ያሰራው ነገርማ አለው፡፡”

“ብወደውማ፣ መጀመሪያውኑ እሷን አላሰተዋውቀውም ነበር፡፡”

“እሺ ግን እንዴት ከአንድ አንድ ከያቤዝ ጋር ነሽ' ብሎ ሊገምት ቻለ?”

“እኔንጃ፡፡ ምንአልባት፣ መጀመሪያ የመጣህ ሰሞን፣ “ለመጀመሪያ
ግዜ ደስ ሚል ወንድ ልጅ ቀጠራችሁ ብዬው ነበር መሰለኝ፡፡ አልፎ አልፎ፣ ያምራል ያልሽው ልጅ ተመቸሽ?' እያለ ይቀልድብኛል፡፡ ከዛ ተነስቶ ይመስለኛል።”

“አ.ሃ... ለዛ ነው? ሌላስ ምን ያውቃል? ሁሉንም ነገር ነግረሽዋላ?”

“ያምሃል እንዴ? ምን ብዬ ነው ምነግረው?” የተቆጣች ለመምሰል ሞከረች፡፡ ፊቷ ግን በፈገግታ እንደተሞላ ነው፡፡ ውስጤ በንዴት ሲጨስ እየተሰማኝ ነው፡፡ ቀልዳብኛለች! ሚስጥር ይሁን
ተባብለን ነበር፡፡ አሁን ምንድነው ሚሆነው? ምንድነው ማደርገው?
በሃሳብ ጭልጥ አልኩ፡፡

“ተጫወት እንጂ! በሃሳብ ነጎድክ።”

“ግን ቢያንስ ስለሰውየው ይሄን ሁሉ ነገር እንዴት አልነገርሺኝም...?” የሆነች ጨዋታ እንደተጫወተች እየተሰማኝ ነው፡፡
“ግቢው ውስጥ ሁሉም ሚያውቀው ስለሆነ፣ አንተም ምታውቅ መስሉኝ፡፡”

“እርግጠኛ ነሽ፣ ለዛ ብቻ ነው ያልነገርሺኝ?”

“እንዴ...! ሌላ ምን ምክንያት ይኖረኛል?”

“እሱንማ አንቺ ነሽ ምታውቂው፡፡”

ስልኬ መዝፈን ጀመረች፡፡ ከሱሪ ኪሴ ውስጥ አውጥቼ ተመለከትኩ፡፡ ሳምሶን ነው፡፡ ስልኩን አነሳሁት፡፡

“ጎረምሳው፣ ምነው በእሁዱ ድምፅህን አጠፍህ? ማታ ይዘህ . ነው እንዴ ያደርከው...?

“እንደውም ደብሮኝ ልደውልልህ ስል ነው የደወልከው፡፡”

“ምነው? ምን አጋጠመህ ወጣቱ...?”

“ዝም ብሎ ድብርት ቢጤ ነው፡፡ የት ነህ ልምጣ...?”

“እቤት ነኝ ና።”

“መጣሁ ጠብቀኝ፡፡” ስልኩን ዘጋሁት፡፡

“ምን መሆንህ ነው? ምን እያደረክ ነው?” አለችኝ ማሂ እንዳኮረፈች ሆና።

“መሄድ አለብኝ፡፡ የማላውቀው ነገር ውስጥ ገብቼ እየዋኘው እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ቢያንስ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ማወቅ አለብኝ፡፡

ተነሺ እንሂድ፡፡”

የጠጣነውን ጁስ ሂሳብ አየሁት፡፡ ሰማንያ ስምንት ብር፡፡ መቶ ብር አስቀምጬ፣ መልስ ሳልጠብቅ ተነሳሁ። ማሂም ተከትላኝ ተነሳች፡፡

ከግቢው በር ላይ ካለው መኪና ማቆሚያ ጋር ሄድን የቆመችው ቪትስ መኪናዬ ውስጥ ገባን፡፡

“የት ላድርስሽ?”

“አንተ የት ነው ምትሄደው?”

“ሳወራ እየሰማሽኝ አልነበር? ሳምሶን ጋር ነዋ፡፡” ተነጫነጭኩ፡፡

“እኔም አብሬህ እሄዳለሁ።”

“አይሆንም!” አምባረኩባት፡፡

“ለምን?”

“ብቻዬን ላናግረው ፈልጋለሁ፡፡”

“ቆይ ምንድነው እንዲህ የቀያየረህ? ምንድነው ይሄን ያክል ያናደደህ?”

“ከዚህ በላይ ምን ታደርጊኛለሽ? ምን አስበሽ ነው ይሄን ሁሉ ሚስጥር እስካሁን የደበቅሽኝ?” መኪናዬን አስነስቼ ከግቢ እየወጣሁ።

“ሆን ብዬ አልደበኩህም፡፡ ምታውቅ ስለመሰለኝ ነው አልኩህ እኮ!”

“ሃ...ሃ...ሃ...! እረ ባክሽ? አንቺ ወሬ ደግመሽ የምታወሪ ልጅ፣ገና ለገና ሰምቶ ይሆናል ብለሽ፣ ይሄን ሁሉ ወሬ ዝም አልሽ?!. ጥሩ ቀልደኛ ሆነሻል ባክሽ፡፡ አሁን የት ላድርስሽ?”

“በታክሲ መሄድ እችላለሁ፡፡ እዚህ ጋር አውርደኝ፡፡”

“እሺ!”

ንዴት በውስጤ እየፈላ ነው፡፡ ሳላንገራግር የመንገዱን ዳር ይዤ አቆምኩላት፡፡ ቦርሳዋን ከኋላ ወንበር አንስታ ተመናጭቃ ወረደች፡፡በቀጥታ ወደ ሳሚ ጋር ሄድኩና ተያይዘን ብቻችንን ስንሆን
የምናዘወትርበት ቤት ሄድን፡፡ ቢራ እየጠጣን ፑል መጫወት ጀመርን፡፡
ለወትሮው ስንጫወት በመበሻሸቅ እንሳሳቃለን፡፡ ዛሬ ቢቀልድብኝም
መልስ አልሰጠውም፡፡ ውስጤ ነገር ገብቷል፡፡ ማሂ የነገረችኝን ነገር
👍6
አኝካለሁ፡፡ ሶስት ጨዋታ እንደተጫወትን፣

“ምሳ እንብላ። እራበኝ፤” አልኩት፡፡

“ኦኬይ፤ ጨዋታው ብዙም አልጣመህም ነበር፡፡”

“እ.። ትንሽ ነገር ገብቶኝ እሱን እያመነዠኩ።”

“ምንድነው? ምን ተፈጠረ?”

“ምን ያልተፈጠረ ነገር አለ!” ብዬ ስለ አለቃችን ማሂ የነገረችኝን አወራሁለት፡፡ ምንም አዲስ ነገር እንዳልሰማ ዝም ብሎ አደመጠኝ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ስምንት ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) ሜሪ፣ ቆንጅዬ የማሂ ጓደኛና የመስሪያ ቤታችን ሰራተኛ ናት።በቁንጅና አይተናነሱም፡፡ ሜሪ ግን፣ በእድሜ ልጅ ነች። ገና እንቡጥ፡፡ልጅነቷ ተጨማሪ ውበት ሆኗታል። ማሂ አንዳንዴ፣ በአንድ ቤትማ ሁለት ንግስት አይኖርም እያለች ትቀልዳለች፡፡ እኔን ጨምሮ፣ ብዙ ወንዶች ዐይናችንን ሜሪ ላይ ጥለንባታል፡፡ አለቃዬን ግን በፍፁም አልጠረጠርኩም…»
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

አልደነቀውም፡፡ጭራሽ፣ወሬ ሊያስቀይረኝ ይሞክራል። እርሷ ጋር ደውሎ፣ በስልክ ስለኔ ያወሩትን ነገር ነገርኩት፡፡

"ጠብቄው ነበር!”

“ምኑን?”

“ይሄንን ነዋ፡፡ ልጅቷ ነገሯ አላማረኝም ነበር፡፡”

እንዴት?”

“በቃ አለባበሷ፣ ቢሮህ መመላለሷ፣ ብቻ ነግሬህ ነበር፡፡”

“ምን ብለህ?”

“ቀስ በል! አትቸኩል፡፡ የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል!' ብዬ ነግሬህ ነበር፡፡”

“እና ማሂ ያለችው እውነት ነው፡፡ ሰውዬው እንዲህ ያደርጋል?”

“ወንድሜ፣ ሰውየው በተወለደበት ቀዳዳ ተለክፏል፡፡ መሞቻውም እዛው እንደሚሆን ግልፅ ነው፡፡ ካ...ካ...ካ...፡፡ በዚህ እድሜ፣ሚስትና ልጆቹን አስቀምጦ ግቢ ውስጥ ያሉትን ሴቶች ሁሉ አትንኩብኝ ማለት...፣ እንደውም ደግ አደረክ! አንተ ወጣት ነህ፣ አላገበህም፣
መዝናናቱም፣ ሁሉም ባንተ ያምራል፡፡ እርሳው ባክህ፡፡ እንደውም ምሳችንን በልተን ሶደሬ እንሂድና ፈታ እንበል፡፡ ማሂንም ይዘናት እንሂድና ስትደጋግማት ታድራለህ፡፡ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም፡፡
ካ...ካ...ካ...”

“ትቀልዳለህ አንተ፡፡”

“የምሬን ነው፡፡” አሁን እኔም በአለቃዬ ድርጊት መናደድ ጀምሪያለሁ፡፡ እልህ እተሰማኝ ነው፡፡

“እሺ ደውልላት፡፡”

ለማሂ ደወለላት። አታነሳም፡፡ የኔን መኪና አቁመን በሱ መኪና ሶደሬ ሄድን፡፡ በፍልውሃ ታጠብን፣ እኔ ዋኘሁ፡፡ ሶደሬ ብቻችንን ስንመጣ እንደሚያደርገው፣ በሲጋራው ምትክ ሺሻ አጨስ፡፡ ወደ መዋኛው ገንዳ ተመልስን ዶሮ አሩስቶ አዘን በቢራ እያወራረድን በላን፡፡ ሰውዬው ለሰው ያለው ንቀትና ድርጊቶች አበሳጭተውኛል። የሳሚ አይዞህ
ሲጨመርበት፣ ውስጤ ተጋፈጠው ተጋፈጠው እያለኝ ነው፡፡ “ድርጅቱ
የቤተሰቡ ሀብት ቢሆን ሰራተኞቹንም የግል ንብረቱ አደረጋቸው እንዴ?፣
ቀጠራቸው እንጂ አላገባቸው...፣ ደግሞ አንዷ ብትበቃውስ፣ ሁሉን አትንኩብኝ፣ ጭራሽ የጣልኩትንም አታንሱ..? ቅሌታም! ደስ ያለኝን አማርጣለሁ፡፡ እንደውም፣ ማሂንም ጨምሬ እልሁን አስጨርሰዋለሁ።”ለራሴ አልኩኝ፡፡ ማታ እቤት ስገባ ምሽት ሶስት ሰአት አልፎ ነበር፡፡ደክሞኝ ስለነበር ወዲያው እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

የተፈጠረውን ነገር አዕምሮዬ ሊረሳው አልቻለም፡፡ የሆነ ድራማ እየተሰራብኝ እንደሆን አሰላስላለሁ፡፡ “የት ነሽ...? ከማን ጋር ነሽ...? ካልተገናኝን...?” ያለጥርጥር ከሰውየው ጋር ግንኙነት ነበራቸው፡፡ያለምክንያት እንደዛ አላንጓጠጠችውም፡፡ ሰውዬው ከእርሷ ጋር ከርሞ፣ እንደዘበት አሽቀንጥሮ በሜሪ ተክቶ አቃጥሏታል፡፡ ለዛ ነበረ ሜሪን ጅል፣
ነፈዝ እያለች ስታጣጥላት የነበረው፡፡ መጫወቻ ኳሷ አድርጋ፣ አለቃዬን
በኔ እያስቀናችና እያበሸቀችው ነበር፡፡ እኔ ጅሉ፣ እንደፈለገችው ተወንኩላት፡፡ ወይኔ ተኩቻው! አጠምዳታለሁ ብዬ ሄጄ፣ የእርሷ ወጥመድ ውስጥ ሰተት ብዬ ልግባላት? ፀባዩን የቀየረብኝ ይሄን አውቆ
ነበር ለካ..። ግን ቀንቶ ነው? ወይስ አሁንም ይፈልጋታል..? ወይኔ፣ ተኩቻው!! እቺ ብሽቅ እንዲህ ትጫወትብኝ፡፡

ስራ መሄድ ያስጠላኝ ጀምሯል። ግን እንደምንም እመላለሳለሁ፡፡ ተነሳሽነቴምና ትኩረቴም ከሞተ ቆይቷል። ከአለቃዬም ሆነ ከሌላ ሰራተኛ፣ ምንም ያየሁት አዲስ ነገር የለም፡፡ ውስጤ ግን እንደ ክረምት
ቀዝቅዟል፡፡ ተኮማትሯል፡፡ ሳሚ ቢሮ እየመጣ ሻይ እንድንጠጣ ይዞኝ
ይወጣል፡፡ እንደበፊቱ መሳቅ መጫወቴ ጠፍቷል። ውስጤ መጥፎና አስጨናቂ ሃሳቦችን እየመረጠ ያመነዥጋል፡፡ ስትስልልህ ነበር የከረመችው፤ ሰውየው ሊያጠቃህ አድፍጧል!' እያለ ጭንላቴ
ያስጨንቀኛል፡፡ አሁን፣ ለጨዋታዎች ስሜት አልባ ሆኛለሁ፡፡ ማሂም ማኩረፌን ስታይሉ ፣ ቢሮዬ ተመላልሳ፣ ይቅርታ ጠየቀችኝ፡፡ ሻይ እንድንጠጣ ጠየቀችኝ፡፡ አይሆንም አልኳዋት፡፡ እንደውም፣ ሁለተኛ
ቢሮዬ እንዳትመጣ፣ ላገኛት እንደማልፈልግ አምርሬ ነገርኳት፤ ቢሮዬ
መምጣት አቆመች፡፡

ከግዜ ወደግዜ ያለ በቂ ምክንያት መናደዴ፣ መበሳጨቴ እየተባባሰ መጣ፡፡ ስራ ስለመልቀቅ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ከዚህ በፊት ስራ በማቆሜ ምክንያት ያደረስኩትን ጉዳት በማስታወስ ውስጤን እንዲረጋጋ ታገልኩት። ስራዬ ግን እንደቀደመው አስደሳች አልሆን አለኝ፡፡ ከነ ሳሚ ጋር ወጥቼ መዝናናትን አቆምኩኝ፡፡ በምትኩ ደብረዘይት እየተመላለስኩ ጫት በመቃም ከድባቴዬ ለመሸሽ ሞክራለሁ፡፡ በተደጋጋሚ ምቅምበት ጫት ቤት አሌክስና ሃብታሙ ሚባሉ ጉደኛሞችን ተግባባሁ፡፡ አሌክስ
ሃብታሙን ዶክ እያለ ይጠራዋል። አሌክስ በጣም ፈጣን፣ ተጫዋችና ከሰው ጋር መግባባት ደስ ሚለው ሰው ነው፡፡ ቀልድ ሲያወራ አጠገቡ የተቀመጡ ሁሉ እንዲሰማው ጮክ ብሎ እንድናዳምጠው በዐይኑ እየጋበዘ ነው፡፡

“ትናንት ማታ የተዋወኳት ቺክ ውበት!፣ ወይኔ...!” ብሎ አሌክስ ለሁላችንም እንደሚያወራ በየተራ ተመለከተን፡፡

“ስንት ሰዓት? ትናንት እዚህ አብረን አልነበርን?” ሃብታሙ ጠየቀ፡፡

“ከዚህ እንደወጣን፣ ጨብሲ ሳንል ጥለኸኝ ላሽ አላልክም?”

“እ...፣ እሺ፡፡”

“የጨብሲ ስላልነበረኝ፣ በወክ ልሰብረው ብዬ ስዞር፣ የሆነች ልዕልት ምትመስል ቺክ አላገኝም፡፡ ወይኔ..፣ ወይኔ..፣ ወይኔ ዐይን! ስታያት በድንጋጤ ደንዝዘህ ትቀራለህ፡፡” ሲያወራ በመደነቅ ግንባሩን
ይዞ እያወዛወዘ ነው፡፡

“እሺ፡፡ ከዛስ ከምን አደረስካት ታዲያ?”

“በስማም ፣ ሞትኩባታ! ጭውቴው ደግሞ እንዴት ስክት ስክት እንዳለልኝ፡፡ ነገረ ስራዬ ለራሴ ገርሞኝ፣ እቤት ከገባሁ በኋላ ስስቅ ነበር።”

“ወሬ አታጣ ! ድሮስ ምላሳም አይደለህ? ምን ብለሃት ነው፣እንዲህ የተገረምከው?”

“ድንገት እጇ ላይ ተጠምጥሜ፣ 'የኔ ልዕልት መሳይ፣ በናትሽ ምሪኝ በናትሽ?” ብዬ ስለምናት፣ መጀመሪያ “ምን ሆንክ?” አለችኝ ደንግጣ፡፡ 'ይኼን ውብ ዐይንሽን ሳይ፣ የእኔ ዐይን አፍሮ ነው መሰል
አላይ አለኝ፣ ብዥ አለብኝ፡፡ ዐይኔን ልጨፍነውና፣ እባክሽን ምሪኝ?” ስላት በሳቅ ሞተች?!” ብሎ ሲስቅ፣ ሁላችንም በድርጊቱ አብረነው ሳቅን፡፡ አሳሳቁ ሰው ላይ ይጋባል፡፡ የዐይኖቹን ትንንሽነትና በራሱ ላይ መቀለዱ ደግሞ፣ የበለጠ እንድንስቅ አደረገን፡፡ ስግባባቸው፤ ሃብታሙ፣ የእንስሳት ሃኪም እንደሆነ አወኩ። አሌክስ ደግሞ የተገኘውን ተባራሪ ስራ ሚስራ አፈ ቀላጤ።

አንድ ቅዳሜ ምሽት፣ አሌክስ ወጥተን የጨብሲ አንድ ሁለት ካልጋበዝኩህ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ድርቅ አለብኝ፡፡ እሺ ብዬው አብረን ወጣን፡፡ እየጠጣን በአስቂኝ ጨዋታዎች የታጀበ ደስ ሚል ምሽት
አሳለፍኩ፡፡ እርሱ ልጋብዝህ ብሎ ይዞኝ ወጥቶ፣ ሂሳቡን ጓደኛው ሃብታሙ ከፈለ፡፡ ስልክ ተለዋወጥን፡፡ ጓደኛሞች ሆንን፡፡ አሌክስ በቀላሉ ጎትቶ ከነሱ ጋር ቀላቀለኝ፡ከነሱ ጋር ስሆን፣ ከአስጨናቂ ሃሳቦቼ
እረፍት ስለማገኝ እኔም ደስተኛ ሆንኩ፡፡ ቅዳሜና እሁድ ውሎና አዳሬ ቢሾፍቱ ሆነ፡፡ ገና ሰኞ ስራ ስገባ ቅዳሜ ትናፍቀኛለች፡፡ ከነማሂ ጋር ካሳለፍኩ፣ ስድስት ሳምንት አለፈኝ፡፡ ሳሚ በተደጋጋሚ በአካልም በስልክም ምነው ጠፋህ ሲለኝ፣ ቢሾፍቱ የራሴን ስራ ለመጀመር ስላሰብኩ፣ ቅዳሜና እሁድ ያን ለማመቻቸት እዛ እንደማሳልፍ ነገርኩት።
ምን ስራ ልትጀምር ነው?' ሲለኝ፣ ሲያልቅ ብታየው ይሻላል፤ አልኩት፡፡ እሺ ብሎ ተወኝ፡፡

ከእንቅልፌ ስነቃ ከንጋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ማታ ስጠጣ ያደርኩበት ጭንቅላቴን ይወቅረኛል፡፡ ከፍተኛ ድካምና ድባቴ እየተሰማኝ ነው፡፡ የሰውነቴ መዛል ከእንቅልፍ የተነሳሁ ሳይሆን፣ ሃያ አራት ሰዓት ካለረፍት ስስራ ያደርኩ ነው ሚመስለው፡፡ ስራ መሄድ እንዳለብኝ ሳስብ እንባዬ መጣ፡፡ የፈለገው ይምጣ ብዬ
👍41
ተመልሼ ተኛሁ፡፡እንቅልፍ ሊወስደኝ ግን አልቻለም፡፡ 'መቅረት አብዝተሃል፣ ለጠላቶችህ ማጥቂያ መሳሪያ እራስህ እያቀበልካቸው ነው፤'፣ እያለ ጭንቅላቴ
ጠዘጠዘኝ፡፡ ቀርቼም ስላም ከሌለኝ ብዬ ቅዳሜና እሁድ በለበስኩት ልብስ
ስራ አርፍጄ ገባሁ፡፡ ላለባበሴ ትኩረት መስጠት አቁሚያለሁ። ትንሽ እንደተቀመጥኩ ማሂ ቢሮዬ ገባች፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) አልደነቀውም፡፡ጭራሽ፣ወሬ ሊያስቀይረኝ ይሞክራል። እርሷ ጋር ደውሎ፣ በስልክ ስለኔ ያወሩትን ነገር ነገርኩት፡፡ "ጠብቄው ነበር!” “ምኑን?” “ይሄንን ነዋ፡፡ ልጅቷ ነገሯ አላማረኝም ነበር፡፡” እንዴት?” “በቃ አለባበሷ፣ ቢሮህ መመላለሷ፣ ብቻ ነግሬህ ነበር፡፡” “ምን ብለህ?” “ቀስ በል! አትቸኩል፡፡ የጅብ ችኩል…»
#ሰመመን


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


ከራሱ ጋር አወዳድሮት ነበር ያደንቀው አቤል ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ የሥራ ፍላጎቱ ላልቶ ፡ የወጣትነት ስሜቱ በሆነ ነገር በርዶ ፥ ሲራመድ እንኳ እንደ ጎታታ ሽማግሌ ቀስ ብሎ ነበር የሚሔደው የመሰላቸት ዐይነት !

በዚህ አረማመድ ወደ መጻሕፍት ቤት አመራ ። ዋናው መፅሐፍት ቤት ለመድረስ አጭር መንገድ እያለለት በጀርባ በኩል ለመዞር በዙሪያ ጥምጥም መንገድ ሔደ በዋርካው በኩል ለማለፍ ፈልጎ ነበር ።

ቀስ ብሎ የዋርካውን አካባቢ ማተረ ። ትዕግሥትና ማርታ እዛ ቦታ አልነበሩም ። ዋርካውን ባየ ቁጥር አንድ ነገር ትዝ
ይለዋል ። አሁንም በእግሩ ወደ ፊት እየተራመደ በሐሳቡ ብዙ አመት ወደ ኋላው ተጓዘ ...

በጎንደር ከተማ ወስጥ ነዋሪዎቹ እንደ ጣኦት የሚያመልኩት አንድ ግዙፍ ዋርካ ነበር ። እቤል የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ በነበረበት ጊዜ ከመኖሪያ ቤቱ የሚመላለሰው በዋርካው በኩል ነበር ። ማታ ከትምህርት ቤቱ፣ ሲመለስ አብዛኛውን ጊዜ ሁለት ወጣት ፍቅረኞች በዋርካው አካባቢ ይመለከት አበር። ሰዓት ጠብቀው ነው የሚገናኙት "
ብዙውን ጊዜ ወንድየው ቀድሞ ስለሚመጣ እየተንጎራደድ ይጠብቃታል ። መምጣቷን ገና ከሩቅ ሲመለከት፥ ፊቱ፡ በርቶ ጥርሶቹ ብልጭ ይላሉ ። እሷም አጠገቡ ስትደርስ የመቅለስለስ
ፈገግታ ታሳየዋለች ።

ደብተሯን ይቀበላትና ከንፈሯን ይስማታል ተቃቅፈው በቀስታ ርምጃ መራመድ ይቀጥላሉ ።

አቤል ያኔ ገና ልጅ ቢሆንም ሁኔታቸው ስለሚያስደስተው ሥራዬ ብሎ በደስታ ይከታተላቸው ነበር። ከትምህርት
ቤት ሲወጣ እንደ መክሰስ የሚናፍቀው እነሱን ማየት ነበር ።ምናልባት ዋርካው አካባቢ ቀድሞ ከደረሰ እንኳ እስኪመጡ
ድረስ ተደብቆ ይጠብቃቸዋል ። ቆዳው ሞኝ ቢመስልም ውስጡ ብልጣ ብልጥ ስለ ነበር ! እነሱን ለማየት እንደ
ሚከታተላቸው እንዳያውቁበት ይጠነቀቅ ነበር " በዝግታ በሚራመድበት ጊዜም ራቅ ብሎ የሚከተላቸው ራሱን እንደ
ተራ መንገደኛ ወይም በየመንገዱ እየተጫወተ እንደሚሔድ ልጅ አስመስሉ ነበር ። እየቆየ ሲመጣ ግን እነሱም ሳይነቁበት አልቀሩም ። ሆኖም አቤል ብቻ ሳይሆን በፍቅራቸው ሁኔታ የሚደነቁ ብዙ ተመልካቾች እንዳሏቸው ስለሚገምቱ
ደንታ አይሰጣቸውም ነበር ። ወንድየው ያማሩ ልብሶች እየለበሰ በተወሰነው ሰዓት ከዋርካው አካባቢ ከመምጣቱ በቀር ምን ሥራ እንዳለው አይታወቅም ። እሷ ግን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነበረች ።

ጨዋታቸው አለማለቁ ተመልካቻቸውን ሁሉ ያስገርመዋል ። ተገናኝተው ከተሳሳሙ በኋላ በፋሲል ግንብ በኩል
አድርገው በኤሊ አረማመድ ረዥም መንገድ ይጓዛሉ ፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ በየቀኑ ወሬ አያልቅባቸውም ። ጨዋታቸው ይብስ
የሚጐላው መለያያቸው ቦታ ሲደርሱ ነበር ። ከሦስት ጊዘ ያላነሰ ይሰነባበታሉ ። ጨዋታቸውን ደምድመው ለመለያየት ከተሳሳሙ በኋላ በመጨባበጥ ዐይነት እጅ ለእጅ ተያይዘዘው አዲስ ጨዋታይ ቀጥላሉ ። ደሞ እንደ ገና ይሳሳማሉ

“ እስኪ መታወቂያ ” የሚል የጥበቃ ጓድ ድምፅ አቤልን ከሐሳብ ጉዞው መለሰው ቤተ መጻሕፍቱ በር ላይ ደርሶ ነበር ። መታወቂያውን አውጥቶ አሳየና ወደ ወስጥ ግባ ።በቀጥታ የፍልስፍና መጻሕፍት ወደ ተደረደሩበት ረድፍ እያ
መራ “ የታደሉ ናቸው ”አለ በልቡ ፥ ሁለቱን ፍቅረኞች በማስታወስ " እሱ የሷን ሰውነት እሷም የሱን ሰውነት መዳሰስ በመቻላቸው ፡ የልባቸውን አውጥተው መጫወት በመቻላቸው ፡ የፍቅርን እስትንፋስ መተንፈስ በመቻላቸው
በእርግጥ የታደሉ ናቸው ።ሳይነጣጣሉ ሳይፈራሩ የፍቅርን ቃጠሎ በጋራ በመቀበላቸው የታደሉ ናቸው።

ዐይኖቹ መጻሕፍት መምረጣቸው አላቋረጠም « ነገር ግን ሐሳቡ ፈጽሞ መመለስ ስላልቻለ ትርጉም የለሽ ተራ
ፊደላት ነበር የሚመለከተው

“ ምን ይመስለው ?” አለ “ ወንድየው ምን ይመስለው ? ዐይኖቹ ተርበው ልቡ እየነጠረ መምጣቷን ሲጠበባቅ፡እሷም
መንገድ ርቆባት በልቧም በእግሯም ከንፋ ስትደርስለት :ዋርካው ሥር ሲገናኙ ፥ ዕቅፍ አድርጎ ሲስማት ምን ይመስለው ? ምን ይሰማው ? መታደል ነው ። መታደል ! ...

በደመ ነፍስ ከመደርደሪያው ላይ አንድ መጽሐፍ አውረደ ዐይኑን ስለሳበው ብቻ ነበር ዝም ብሎ እያገላበጠው ከራሱ ጋር ንትርኩን ቀጠለ

እኔስ ይህን ማድረግ የማልችለው ለምንድን ነው ? ”ሲል ራሱን ጠየቀ ትዕግሥትን አቅፎ መሳም " ከትዕግስት
ጋር የልቤን መጫወት ይህን ማድረግ የማልችለው ለምንድነው ? ...”

ትዕማግሥት በፈገግታ “ጉንጮቿን እየሰረጎዶች መጥታ ከፊቱ ቆማ ፈሪ ስለሆንክ ነዋ ! ጰርጳራ!” የምትለው መሰለው።

“ ታዲያ የምወዳትን ከፈራሀማ የልቤን ለማን ልናገር ነው?

የሥራ ክፍላቸው በር ሲንኳኳ ዬናታን ካቀረቀሩበት መፅሐፍ ቀና ብለው አቤት ይግቡ አሉ።

እስክንድር ማንደፍሮ ከልብ ያልሆነ ፈገግታ እያሳየ ገባ የበሩ ኳኳታ ከትኩስ ምርምር ላይ ቢያባንናቸውም ቅሉ የመጣው ሰው እስክንድር መሆኑን ባስታዋሉ ጊዜ ዬናታን ደስ አላቸው።

የማንበብያ መንጽራቸውን እያወለቁ ተቀመጥ እስክንድር ” በማለት መቀመጫውን አመለከቱት።

"እህሳ ? ጥናት እንዴት ይዞሃል?"
" እየታገልኩ ነው! »
"ምን አስብሃል ትምህርቱን ትቀልጥበታለህ ወይስ...

ለመጀመሪያ ዲግሪ የመጨረሻ ዓመት ተማሪ መሆኑን በሚመለከት ያቀረቡለት ጥያቄ።

"ገና አላሰብኩበትም » አለ እስክንድር ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይ ውጤቱ መሳኝነት ይኖረዋል።

“ አዎ አሉ ዮናታን ፥ ራሳቸውን እየነቀነቁ ።
«« በርትተህ ከሠራህ ጥሩ ውጤት ታመጣለህ ።

የእስክንድር መልስ ፈገግታ ነበር … ጥቂት ሰኮንዶች በዝምታ ከቆዩ በኋላ አቤል ጋደኛህ ነውን ? ” ሲሉ ጠየቁት።
ሌላው ሁሉ ዝብዝብ ዮናታን ለመንደርደሪያ ያህል ያቀረቡት ነበር እንጂ እስክንድርን ከክፍላቸው ድረስ ያስጠሩት ለዚህ አርእስት ጉዳይ ነበር ።

እስክንድር ወድያውኑ ጉዳዩ ገባው በመጀመርያ ዬናታን ያስጠሩት በእጃቸው ስላለው የጥናት ጽሑፍ ገዳይ ሊያነጋግሩት መስሎት ነበር አሁን ግን የተፈለገበትን ነገር ጠረጠረ።

"አዎ አንድ ክፍል ውስጥ ነው የምተኛው አብዛኛውን ጊዜም አብረን እናጠናለን" ሲል መለሰ።

“ አሃ ! ደህና ... እንዴት ነው ? በቅርቡ የምታውቀው የደረሰበት ችግር አለ?” ጥያቄው ቢገባውም " እስክንድር ሀሳባቸውን የተረዳላቸው ለመምሰል አልፈለገም ።

“ እንዴት ማለት? ” ሲል ጠየቃቸው ።

“ ማ...ማለቴ መንፈሱን የሚረብሽው ወይም የሚያበሳጨው በቅርብ የደረሰበት አጋጣሚ እንዳለ ? ”
“እኔ እንደገባኝ አንዲት ልጅ ያፈቀረ ይመስለኛል ” አላቸው ነገሩን ፍርጥርጥ አድርጎ ።
ዮናታን አንዳች ውጤት ያገኙ ይመስል መላ ሰውነታቸው ነቃ ፊታቸው ላይ ያልተንጸባረቀ ውስጣዊ ፈገግታ
ፈግማ አሉ።

“ እህ !እህ ! ” እያሉ ራሳቸውን ነቀነቁ ።

“ ግን ደግሞ እንደ ገመትኩት ” ሲል ቀጠለ እስክንድር ። « እኔ እንደ ገመትኩት ፍቅሩ ከዐይን አላለፈም

“ እንዴት ማለት?”

“ ከልጅቷ ጋር መነጋገር ቀርቶ ሰላምታ እንኳ ተሰጣጥተው አያውቁም « በግምት አስመስሎ አቀረበው እንጂ በትክክል የደረሰበትን ነበር የተናገረው። ከዐይኑ ወዲያ ምን ማስረጃ ያስፈልጋል ? ... እስክንድር ለአቤል የመኝታ ክፍል ጓደኛ እንደ መሆኑ መጠን የቀን ተቀን ተግባሩን
ተከታትሎ ማጥናት ለሱ ከባድ አልነበረም

ዮናታን ማንኛውንም መረጃ በእጃቸው ያገቡ ያህል ገፅታቸው በርቶ ወደ ኋላቸው ተለጥጠው ተቀመጡ እስክንድርን ያስጠሩት ለአቤል ችግር መጠነኛ መንደርደሪያ ይሰጠኛል ብለው ነበር ። ስለ አቤል
👍2
አበባ:
ል ከጠበቁት በላይ የሚያውቅ ሆኖ በማግኘታቸው ደስ አላቸው "

“ ታዲያ ስለ ሁኔታው ከአቤል ጋር ተወያይታችሁ ታውቃላችሁ ?

አዬዬ! አለ እስክንድር ፥ ራሱን እየነቀነቀ
“ እንኳን መወያየት ቀርቶ ገና የነገሩ ጫፍ ሲነካበት ፊቱ ይለዋወጣል ። ለማንም ስለዚህ ጉዳይ የሚያወራ አይመስለኝም ምክንያቱም በአካባቢው መቼም ከእኔ በላይ የሚቀርበው የለም ።

ዮናታን ዝም አሉ ፤ በልባቸው የዚህ ምክንያት ምን ሊሆን እንደሚችል እያብሰለሱ ነበር ። እስክንድር ቀጠለ

“እንዲያውም የጎዳው ጉዳዩን ለብቻው መያዙ ይመስለኛል ። ከፍተኛ ጭንቀት ነው ያተረፈው ። ከእኛ ከጓደኞቹ
ጋር ቢወያይበት ኖሮ ምናልባት ጭንቀቱ ይቀንስለት ነበር።” አለ የራሱን ግምት በመጨመር ።

እስክንድር ይህን ተናግሮ እንዳበቃ የዮናታንን ዐይን ተመለከተ ከርሳቸው ሐሳብ ወይም ጥያቄ ይጠብቅ ነበር ። ዮናታን ግን " በአካል እስክንድር አጠገብ ቢሆኑም ቅሉ በሐሳብ ርቀው ሔደው ነበር ። በእሳቸው አስተሳሰብ የዐይን ፍቅር ቀላል ጉዳይ አይደለም ። የዐይን ፍቅር ሲነሣ ምን ጊዜም ትዝ የሚላችው አሳዛኙ ካርል ነው ። ስለዚህ ሰው ታሪክ ያጫወተቻቸው ባለቤታቸው ሞኒካ ናት አሁንም እስክንድርን አጠገባቸው እንዳስቀመጡ በሐሳባቸው ከታሪኩ
ትውስት ውስጥ ሰምጠው ነበር ።

በዘመነ ፋሺዝም በጀርመን ኮንስንትሬሽን ካምፕ ታጉረው የሂትለርን በትር ከቀመሱት ሰዎች መሐል አንዱ የሞኒካ አባት ናቸው ። አባቷ ፥ ካርል ስለሚባል ወጣት ያወጓት ነገር ነበር ። እሳቸው ታሪኩን የሚያወሩት ምስኪኑ ካርል
እያሉ ነው ። ሞኒካም ይህንን ጨዋታ ለዮናታን አውርታላቸዋለች ።

ካርል፥ ከሞኒካ አባት ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ነበር የታጎረው ። በፀረ ፋሺዝም እንቅስቃሴው በጣም የታወቀ ወጣት
ነበር። በፋሽስቶች እጅ ያልቀመሰው ዐይነት ሥቃይ የለም።ከዚያ በላይ በአካዳሚክ ሕይወቱ በጣም የተደነቀ ነበር ።ነገሮችን በቀላሉ ይረዳል ። ሁኔታዎችን በማነጻጸር ረገድ...

💥ይቀጥላል💥
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

ስራ አርፍጄ ገባሁ፡፡ ላለባበሴ ትኩረት መስጠት አቁሚያለሁ።ትንሽ እንደተቀመጥኩ ማሂ ቢሮዬ ገባች፡፡

“እንዴት ነህ?”

“አለሁ፡፡ ምን ልታዘዝ?”

“ማወራህ ጉዳይ አለኝ፡፡ ሻይ ቤት መሄድ እንችላለን?”

“የሚያገናኘን የቢሮ ጉዳይ መሰለኝ፣ እዛ አልሄድም፡፡የምታወሪው ካለሽ፣ እዚሁ ማውራት ትችያለሽ፡፡”

“የቢሮ ጉዳይ አይደለም፡፡ የእኔና ያንተ የግል ጉዳይ ነው።”

“ማለት?"

“ግንኙነታችንን ማቆም ማንችልበት ነገር ተፈጥሯል፡፡ ላወራህ ፈልጋለሁ፡፡” ምን ለማለት እንደፈለገች ገመትኩ፡፡ አዞረኝ። ለቅፅበት በውስጤ ያሰብኩትን እውነት አታድርገው ብዬ ፀለይኩ፡፡ ደሜ ቀዝቅዞ
በድን ስሆን ተሰማኝ፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ፣ ቀስ ብዬ ተነስቼ እንዳለችኝ ሻይ ቤት ሄድን፡፡ ፈንጠር ያለ ቦታ መርጬ ተቀመጥኩና፣

አረገዝኩ ልትዪኝ ባልሆነ...!” አልኳት እንደተቀመጥን፡፡

“አዎ ልልህ ነው፡፡ የወር አበባዬ ከመጣ ወር አልፎታል፡፡ አርግዣለሁ፡፡”

“ስለዚህ ያንተ ነው ልትዪኝ ነው?” ዐይኔ ጨለመብኝ::

“እና ከማን ሊሆን ይችላል? ምን ማለት ፈልገህ ነው? ቆይ ግን አንተ እኔን እንዴት ነው ምታስበኝ?” ተንጨረጨረች፡፡

“ቀስ በይ አትጩሂ! ይኸውልሽ ማሂ፣ አሁን ከማን ነው ሚለውን እንርሳው፣ ያንተ ነው ካልሽኝ ግን፣ እኔ በዚህ ሰዓት አባት
ለመሆን በአቅምም በስነ ልቦናም ዝግጁ አይደለሁም፡፡”

“ስለዚህ?” ብላ አፍጥጣ ተመለከተችኝ፡፡
“ሌላው ቢቀር ያለ አባት ፍቅር ሚያድግ ልጅ ለመውለድ ባታስቢው ይሻላል። አንድ ነገር ብታደርጊ ጥሩ ነው፡፡”

“ምን?! አንተ ሰው መሳይ ሰይጣን ምን አልከኝ? አላደርገውም፡፡አላደርገውም...! የነገርኩህም ሰው መስለኸኝ ነው እሺ፡፡ እንደዚህ አይነት ጭራቅ መሆንህን አላውኩም ነበር፡፡ አባትነትህ እንጦሮጦስ መግባት ይችላል፡፡” ተስፈንጥራ ተነስታ በተቀመጥኩበት ጥላኝ ሄደች፡፡

ወደ ቢሮዬ ተመለስኩ፡፡ በህይወቴ ምን እየሆነ እንዳለ ግራ ገባኝ፡፡ በራሴ ዝርክርክነት፣ አጥምደው እየተጫወቱብኝ ነው። እራሴን ጠላሁት፡፡ እንደዛ በላዬ ላይ ስትጫወት ከርማ፣ አሁን ደግሞ እንዲህ
ትለኛለች፡፡ እውነቷንም ቢሆን፣ ወደዚህች ትርጉም አልባ፣ ጭለማ አለም ሌላ ህይወት ለማምጣት በጭራሽ ምክንያት መሆን አልፈልግም፡፡

ተሰምቶኝ ማያውቅ ጥልቅ ብስጭትና ሃዘን ወረሰኝ፡፡ ቢሮዬን ቆልፌ ወጣሁ።

ወደ ቤት ገብቼ ስልኬን አጥፍቼ፣ ለቀናት ተሸሸግሁ፡፡ ማንንም ማግኘት አልፈልግም፡፡ ወደ ስራ መሄድ ሳስብ አስፈሪ ጭንቀት ይሰማኝ ጀመር። አሁን የሚሰሙኝ ስሜቶች፣ ከዚህ በፊት ስራ ልለቅ ስል የሚሰሙኝ ስሜቶች ናቸው፡፡ መሸሽ፣ መደበቅ፣ መሸሸግ፡፡ ከዚህ ቀደም
ያጠፋሁትን ላለመድገም፣ ለራሴ የገባሁትን ቃል ለመጠበቅ፣ በመከራ
ያገኘሁት ስራ ላለመልቀቅ፣ ስራዬን እንደምንም ለመቀጠል፣ ለቀናት
ከውስጤ ጋር ታገልኩ፡፡ ግን፣ አልሆነም፡፡ አልቻልኩም፡፡ ለአራተኛ ግዜ ስራዬን መልቀቅ ግድ ሆነብኝ፡፡ ቢሮ ሄጄ፣ ቁልፍና ንብረት ለማስረከብ ምትሆን እንጥፍጣፊ ትዕግስት አልነበረኝም፡፡ መልቀቂያ እንኳን
ሳልወስድ፣ ድንገት በብስጭት እንደወጣሁ ቀረሁ፡፡ ለካ ውስጤ፣
ሳይታወቀኝ ሞልቶ ነበር፡፡ እየጠጣሁ እብሰከሰካለሁ። እብከነከናለሁ።
ሁሌም እንደዛ ነበር፡፡ “ለምድን ነው ሁሌም እኔ ላይ እንዲህ ሚሆነው?
ለምንድን ነው ነገር ሚደራረብብኝ፣ በአንዴ ሚጨልምብኝ? ምን ብረገም
ነው?”

ህይወቴን ወደኋላ መለስ ብዬ መመልከት ጀመርኩ፣ ሁሉም ጥቁርና አድካሚ ሆኖ ታየኝ፡፡ በመውጣትና በመውረድ፣ በስቃይ ብቻ የተሞላ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ህይወት በአንዴ ላይ ታወጣኝና መልሳ ከአፈር
ትደባልቀኛለች፡፡ እንደዚህ አይነት ህይወት ሰለቸኝ፡፡ ታከተኝ፡፡ ቢበቃኝ

ይሻለኛል ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡አዕምሮዬ “ከዚህ እስስት ከሆነ ኑሮ ሞት በስንት ጣዕሙ' አለኝ፡፡ ያስፈራል፡፡ ያስጨንቃል፡፡ እንደዛ ማሰብ አልፈልግም፡፡ ማሰቤን ግን ማስቆም አልቻልኩም፡፡ አዕምሮዬ ደጋግሞ በማስረጃ ይሞግተኛል፡፡ መሞት መፍትሄ እንደሆነ ይነግረኛል፡፡ እራሴን
ስለማጥፋት ደጋግሜ አስባለሁ፡፡ ለቀናት ምን ማድረግ እንዳለብኝ አሰብኩ። ከዚህ ከተማ መውጣት፣ መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩ፡፡ ቢሾፍቱን እወዳታለሁ፡፡ የነፍሴ እስትንፋስ ገመድ እዛ የተቋጠረች እስኪመስለኝ ድረስ፡፡ ሲከፋኝም፣ ስደስትም ወደሷ እበራለሁ፡፡ የሀይቆቿ የማይረበሽ፣ የማይናወጥ ውሃ፣ ተረጋግቶ ያረጋጋኛል፡፡ ለግዜውም ተረጋግቼ
ለማስብ፣ ከጥቂት አስፈላጊ ካልኳቸው እቃዎች በስተቀር ያለኝን የቤት እቃ ባገኘሁት ዋጋ ሸጬ፣ ወደ ቢሾፍቱ ለመጓዝ ተነሳሁ፡፡

ከአዳማ ከተማ ወጥቼ ትንሽ እንደተጓዝኩ፣ መንዳት አቃተኝ፡፡
በአይኔ የሞላው እንባ እይታዬን ጋረደኝ፡፡ መኪናዋን ጠርዝ አስይዤ፣ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡ አዳማን ብቻ ሳይሆን ህይወትን ተሰናብቼ እየወጣሁ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ በዚህ ሰዓት እንዲህ እየሆንኩ እንዳለ ሊገምት የሚችል አንድም እንኳ ሰው እንደሌለ ሳስብ፣ ሆድ እቃዬ
እስኪበጠበጥ አለቀስኩኝ፡፡ በቁሜ ለራሴ ለሞተ ሰው እንደሚለቀስ ተንሰቀሰኩ፣ በቀብሩ ማንም እንዳልተገኘ ብቸኛ ሰው ለራሴ አነባሁ፡፡ሲወጣልኝ ተነስቼ ወደ ቢሾፍቱ ሄድኩኝ፡፡ ነገሮችን እስክወስን፣ ቤት መከራየት አልፈለኩም፡፡ መለስተኛ ሆቴል አልጋ ይዤ መቆየትን መረጥኩ፡፡ ሁሉ ነገር፣ ሰልችቶኛል፡፡ አስጠልቶኛል፡፡ ቤተሰቦቼንም ጨምሮ፡፡ አሁን እነ አሌክስንም ማግኘት አልፈልግም፡፡ ስለዚህ ሌላ መዋያ ዱከም ፈልጌ አገኘሁ፡፡ ደብረዘይት ማደሪያዬ ብቻ ሆነች፡፡ ማታ ማታ አብዝቼ እጠጣለሁ፡፡ ስሰክር በለሊት ነድቼ አዲስ አበባ ሄጄ
አጨፍር አድራለሁ። ሲነጋ እንዴት እዛ እንደመጣሁ እንኳ ትዝ እስከማይለኝ፡፡ አንዳንዴም፣ እራሴን መኪና ውስጥ አድሬ አገኘዋለሁ፡፡

አንድ ቀን በመኪና አደጋ ልሞት እንደምችል አስባለሁ፡፡ እሱማ እድል
ነው፣ እንደዛማ ከሆነ እግዜር ይወደኛል እላለሁ፡፡ እራሱን አጠፋ ከምባል፣ በመኪና አደጋ ሞተ መባል በስንት ጣዕሙ ብዬ አስባለሁ፡፡ የመጠጡ ብዛት ጨጓራዬን ነካው፡፡ ስጠጣ ያስመልሰኛል፡፡ ከሚሰማኝ አስጨናቂ ስሜት ለመውጣት ከመጠጣት ውጪ አማራጭ የለኝም፡፡
አላቆምኩትም፡፡ የመጠጥ አይነት እየቀያየርኩ እጠጣለሁ፡፡በየቀኑ ዱከም እየተመላለስኩ እየቃምኩ መንገደኛ ሃሳቦችን ሳስብ እውላለሁ። በምመለከተው ነገር ድንገት በሚመጡ ሃሳቦች እነጉዳለሁ፡፡ ይመለከተኛል፤ ይጠቅመኛል፤ ሳይል አዕምሮዬ ያገኘውን
ያላምጣል። አንዱን አነሳለሁ፤ እጥላለሁ። ሲመሽ እጠጣለሁ። ካደለኝ ክፍሌ ገብቼ እተኛለሁ፡፡ መሽቶ ይነጋል፤ ሌላ ቀን፡፡ አንዳንዴ፣ ለመኖር በሚደረግ ጥረት የሚፈጠር ግርግር ለቅፅበት ቀልቤን ያዝ ያደርገኝና ስለ ኑሮ አስባለሁ፡፡ ሰዎች ለመኖር ይወጣሉ፤ ይገባሉ፤ ይጭናሉ፤
ያወርዳሉ፤ ይመጣሉ፤ ይሄዳሉ፡፡ ይህ ግርግር አንዳንዴ እንደሰመመን ይታየኛል፡፡ነገሮች ላይ ትኩረቴ በጣም ቀንሷል፡፡ እያሰብኩ የነበረውን ሁሉ ቶሎ እረሳለሁ፡፡ ጭንቅላቴ በፍጥነት ወደ ተለመደው፣ አስጨናቂ ሀሳቦች ይመልሰኛል፡፡

ዱከም ቤተኛ እየሆንኩ ነው፡፡ ባለቤቷ ጠፋህ፣ አረፈድክ ማለት ጀምራለች፡፡
ስራ ለቅቄ እዚህ ከመጣሁ ሶስት ሳምንት ሆነኝ፡፡ ማታ ስጠጣ፣ ከነ አሌክስ ጋር እንገናኝ ጀመር፡፡ ስንጠጣ ጨዋታቸው፣ ዘፈኑ፣ ጭፈራው፣ ጭጋጋማ ህይወቴን የብርሃን ጭላንጭል ይፈነጥቅልኛል፣
ቅንጥብጣቢ ደሰታ፡፡ ሲነጋ ግን፣ የተለመደው ከፍተኛ ድብርት፣ ባዶነት፣
ተስፋ ቢስነት ቦታቸውን ይረከባሉ፡፡ ቀኑን እንደምንም አሳልፈውና ማታ እነ አሌክስን እየፈለኩ ድብርቴን እዋጋው ጀመር፡፡ አሌክስ ጨዋታ አዋቂ
👍4
ልጅ ነው፡፡ ሲያወራ ጨዋታውን በሰውነት እንቅስቃሴው ማጀብ የተካነበት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎችን አስመስሎ ሲያወራ የሰውነት እንቅስቃሴን ጠልቆ የሚመለከትበትንና ደረጃና መልሶ ሚተውንበትን ችሎታ ሳይ፣ “አንተ መክሊትህ ትያትር ቤት ነበረች፡፡ እዚህ ቀልጠህ ቀርተህ ነው፤” እስክለው ያስደምመኛል፡፡

ሃብታሙም ቢሆን ሞቅ ሲለው ጥሩ ተጫዋች ነው፡፡ በተለይ በሙያው ላይ መቀለድ ይወዳል፡፡ ማታ ከጠጣን በኋላ፣ ልሸኝህ ስለው እሺ አይልም፡፡ ቀን ሳክማቸው የዋልኳቸው ውሾች ምን ሰርተው ይበላሉ፣ እየጮኹ አጅበውኝ ቤቴ ድረስ ይሸኙኛል፤” ይላል፡፡ አንድ
ምሽት እየጠጣን ስንጫወት፣
“ሃብትሽ መጀመሪያ የተዋወቅን ሰሞን፣ አሌክስ ዶክ ሲልህ ስምቼ፣ የሰው ሃኪም መስለኸኝ ነበር፤” አልኩት፡፡

“አንተ ብቻ አይደለኸም፡፡ ብዙ ሰው እንደዛ ይመስለዋል፡፡ እንደውም ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ የእንስሳት ዶክተር ጓደኛዬ
የገጠመውን ልንገራችሁ፤” አለን እየሳቀ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
አትሮኖስ pinned «#የታካሚው_ማስታወሻ ፡ ፡ #ክፍል_አስር ፡ ፡ #ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD) ስራ አርፍጄ ገባሁ፡፡ ላለባበሴ ትኩረት መስጠት አቁሚያለሁ።ትንሽ እንደተቀመጥኩ ማሂ ቢሮዬ ገባች፡፡ “እንዴት ነህ?” “አለሁ፡፡ ምን ልታዘዝ?” “ማወራህ ጉዳይ አለኝ፡፡ ሻይ ቤት መሄድ እንችላለን?” “የሚያገናኘን የቢሮ ጉዳይ መሰለኝ፣ እዛ አልሄድም፡፡የምታወሪው ካለሽ፣ እዚሁ ማውራት ትችያለሽ፡፡” “የቢሮ ጉዳይ አይደለም፡፡…»
#ታንቄ_እንዳልሞት

ታንቄ እንዳልሞት አጥሬ በስብሷል፡

ኮረንቲ እንዳልጨብጥ መብራት ደሞ ሄዷል፡

ከጎርፉ እንዳልገባ ዝናቡም አቁሟል ፡

እንግዲህ ልጠብቅ ልጠብቅ ይመጣል፤

ጠብቄ ጠብቄ ዝናቡም መጣልኝ፡

ጠብቄ ጠብቄ መብራቱም መጣልኝ፡

ግና ምን ያደርጋል ሰአቱ አለፈብኝ፡

እንዲያ ያስጨነቀኝ ንዴቴም ጠፋብኝ፤

ለካስ ሁሉም ያልፋል የጊዜ ጉዳይነው፡

ዛሬ ሲጨልምም ነገ ሌላ ቀን ነው ።
የሰው ልጅ ሞኝ ነው! ይገዛል መስታወት ኹሉን የሚያሳየው፣መሰንበት በሕይወት።
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“አንተ ብቻ አይደለኸም፡፡ ብዙ ሰው እንደዛ ይመስለዋል፡፡እንደውም ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ የእንስሳት ዶክተር ጓደኛዬ
የገጠመውን ልንገራችሁ፤” አለን እየሳቀ፡፡

“እሺ ንገረን፡፡”

“የንሰሃ አባቱ ዶክተር ሲባል፣ የሰው ሃኪም እንደሆነ ይመስላቸው፡፡”

“እሺ፡፡

“እና ንሰሃ ሊገባ እርሳቸው ጋር ይሄድና፣ አባቴ ሃጥያት ሰርቻለሁ፤ ይፍቱኝ ልሎት ነው የመጣሁት፤' ይላቸዋል፡፡ እሳቸውም
'ልጄ፣ ሰው ሆኖ ሃጥያት ማይሰራ ማን አለ? እግዚአብሄርስ ንሰሃን የሰራልን ይህን አውቆ አይደል? በል ንገረኝ ልጄ እፈታሃለው፤ ይሉታል።

አባቴ የኔስ ትንሽ ከበድ ያለ ነው፡፡ ይላል እየተቅለሰለሰ፡፡

አዬ ልጄ፣ ለሰው እንጂ ከብዶ ሚታየው፣ ለእርሱ ምን ይሳነዋል፣ አትፍራ ንገረኝ ልጄ፧' ይሉታል፡፡

“አባቴ ይፍቱኝ፣ ከታካሚዬ ጋር ወሲብ ፈፅሚያለሁ።

'አይ ልጄ፣ እንዳንተ ያሉ ዶክተሮች ሁሉ ሚወድቁበት፣ሚያጋጥም ነውኮ፡፡ አይዞህ ልጄ፣ ንሰሃ እሰጥሃለው፡፡ እግዚአብሄር
ይቅር ባይ ነው ፤ " ሲሉት፣

አባቴ እኔ ግን የእንስሳት ዶክተር ነኝ፣ ታካሚዎቼ... ብሎ ሳይጨርስ ደንግጠው፣

በስመአብ ወወልድ... እያሉ ሲደግሙ፣ እሱም ደንግጦ ወጥቶ ከንስሃ አባቱ በዛው ተቆራርጦ ቀረ፡፡” ካ....ካ... በጣም ሲያስቀን አመሸን፡፡

እነ ሃብትሽ በህይወቴ የቀሩኝ እንጥፍጣፊ ቅመሞች ሆነዋል፡፡ስለ ስራው ሲያወራ፣ የዶሮ እርባታ ስራ ጥሩ እንደሆነና ቢሾፍቱ ለዛ ስራ የተመቸች እንደሆነች ሲያወራ ሰማሁት። አስጨናቂ ሃሳቦቼ የተወሰነ ረገብ ብለውልኛል፡፡ ስልኬን ብዙ ግዜ ክፍት ማድረግ ጀመሪያለሁ፡፡ ሳሚና ማሂ አልፎ አልፎ ይደውላሉ፡፡ ማሂ በአቋሟ
ፀንታለች፡፡ እኔም እንደዛው፡፡ ሳሚ ስለማርገዟ ሰምቶ፣ አስረግዘህ ጠፋህ
አይደል?' እያለ ይቀልዳል፡፡ እስቅና ስለ ሜሪ እጠይቀዋለሁ፡፡ አሁንም ከሼባው ጋር እንደሆነች፣ ኤፍሬም ቦርኮ መንገድ ላይ እንደወጣና እንዳየው፣ በግቢው ያለውን አዲስ ነገር እየሳቀ ያወራኛል።

#እንጥፍጣፊ_መሻቶች...

ያለኝ ገንዘብ አየመነመነ ነው፡፡ አንድ ነገር ካላደረኩ፣ ከዚህ በኋላ ከአንድ ወር በላይ መንቀሳቀሻ ገንዘብ አይኖረኝም፡፡መኪናዬን ለመሽጥ በውስጤ ዝግጅት እያደረኩ ነው፡፡ ለመሸጥ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ ስጠጣ አምሽቼ ተኛሁ፡፡ ከእንቅልፌ ስነቃ የተለየ ስሜት
እየተሰማኝ ነው፡፡ ደስ ሚል ስሜት፣ የፈነደቀ፣ የበራ ውስጠት እየተሰማኝ ነው፡፡ ከአልጋዬ እንደተነሳሁ፤

“ኋት ኤ ብራይት ዴይ ኢዝ ቱዴይ...?”

“ቱዴይ ኢዝ ሳተርዴይ...”

“ኢት ኢዝ ማይ ብርዝ ዴይ...።” ብዬ ሳላስበው ቅኔ ተቀኘሁ፡፡

ወይኔ... ዛሬ ልደቴ ነው እንዴ? እኔኮ አንዳንዴ ሳላስበው በልሳን ምናገረው ነገር አለ፡፡ ልደቴን አላውቀውም። ግን ማን ያውቃል፣ዛሬ ሊሆን ይችላል እኮ..፡፡ ቢያንስ አንድ ሶስት መቶ ስልሳ አምስተኛ
ትክክል የመሆን እድል አለኝ፡፡ ማክበር አለብኝ፡፡

ሻወሬን ወሰድኩኝ፣ ጺሜን ተለጫጨሁ፣ አፍተር ሼቭ፣ ሽቶ ተቀባባሁ። ድንገት እብደቴ እየተነሳ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ ከወራት በኋላ፣ ለመጀመሪ ግዜ ከውስጤ ሳልጠጣ ደስ ሚል ስሜት እየተሰማኝ ነው:: ፈገግ ልል፣ ልስቅ ልጫወት ነው:: እብደቴን አውቀዋለሁ። እወደዋለሁ።
እሱ ይሻለኛል። ዝለል፣ ዝላል፣ ፈንጥዝ፣ ፈንጥዝ ይለኛል። ህይወት የፈካች አበባ፣ ብሩህ ሆና ትታየኛለች፡፡ ቀላልና አጓጊ ያደርግልኛል። ለባብሼ ስጨርስ፣ ምሳ ደርሷል። ወጥቼ ለራሴ ምርጥ ክትፎ ጋበዘኩት።ከምሳ በኋላ መኪናዬን አስነስቼ ዝም ብዬ ነዳሁኝ፡፡ ወዴት፣ ለምን፣
እንደምሄድ አላውቅም፡፡ ብቻ ደስ ብሎኛል። ፍንትው፣ ብርት፣ እንዳልኩ
ሳላስበው እዛው ዱከም ደንበኛዬ ጋር እራሴን አገኘሁት። መሄጃ የለኝም
ገባሁ። ያልተለመደ፣ሞቅ ያለ ስላምታ ሰጠኋቸው። ደስ ሲለኝ መደበቅ
አልችልም:: ፊቴ ያሳብቃል።

“እንዴት ነሽ...? ሰላም ነዉ...?” አልኳት ባለቤቷን፡፡

“አለን፡፡ እንዴት ነህ አንተ? ግባ!።” የቤቱ ባለቤት ወደ ተለመደዉ ቦታዬ እየጠቆመችኝ፡፡

“ዛሬ እምሮብሃል። ፍክት ብርት ብለሃል። ምን ተገኘ?”

“ልደቴ ነው። ዛሬ ከበር መልስ ግብዣ በኔ ነው::”

“እንኳን ተወለድክልን። ልደትህ ከሆነማ፣ እኛ ነን መጋበዝ ያለብን።”

“አመሰግናለሁ። ግን፣ የደስታዬ ቀን ስለሆነ፣ ግብዣው በኔ ነው። ብቻ ዛሬ
ልዩ እንክብካቤ ያስፈልገኛለ፤” ብዬ ጥጌን ይዤ ተቀመጥኩ ብዙም ሳትቆይ ሚያስፈልገኝን ሁሉ አምጥታ
አስቀመጠችልኝ፡፡ ቤተኛ ሆኛለሁ። ሚያስፈልገኝን፣ ልኬን፣ ሁሉን
አውቃለች፡፡ ዛሬ እንደ ከዚህ ቀደሙ፣ ስልኬ ላይ አልተደፋሁም: መሄጃ
ስላጣው እንጂ መቃም ሳይሆን ሰው ነው ያማረኝ፡፡ ለሳምንታት ሰው አስጠልቶኝ ከሰው እንዳልሽሽው፣ ዛሬ ከሰው ማውራት፣ መቀለድና መሳቅ አማረኝ፡፡ ከእነርሱ ጋር እየተጫወትኩ፣ እየቀነጣጠብኩ መቃም ጀመርኩ፡፡ ትንሽ እንደቃምኩ፣ አንድ ጥቁር በጥቁር የለበሰች ረጅም፣ ቁመናዋ የተስተካከለ፣ ቆንጅዬ ልጅ ገባች፡፡ እንዳየኋት ዐይኖቼን
ተክዬባት ቀረሁ፡፡

መጀመሪያ እዚህ ቤት መምጣት የጀመርኩ ሰሞን፣ ባለቤትየዋ እዚህ ከሚመጡ ደንበኞቼ ለየት ትላለህ፤' ያለችኝ ትዝ አለኝ፡፡ ልጅቷ ፅድት ያለች ናት:: ውብና ማራኪ! እኔም እስከዛሬ እዚህ ቤት ሲመጡ ካየኋዋቸው ሴቶች ተለየችብኝ፡፡ ሳሎኑን ተሻግራ፣ በመጋረጃው ጀርባ

ወደ ውስጥ ገባች። ከቤቱ ባለቤት ጋር እንደጓደኛ ሰላም ተባብለው እየተሳሳቁ ያወራሉ፡፡ ቤተኛ ነች፤ ይተዋወቃሉ ማለት ነው? ግን ሲታዩ፣ ፍፁም በተለያየ ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች ይመስላሉ፡፡ባለቤትየው፣ ሱስ ያጎሳቆላት ከሲታና የወየበች ናት፡፡ ይቺ ደግሞ፣ የቆዳዋ ጥራት፣ በታይቷ ውስጥ የሚታየው የተመቸው ሰውነት፣ ሱስ ባለፈበት አልፋ
ምታውቅ አትመስልም። እንዴት ተዋወቁ? ምን አገናኝቸው? ጓደኛማ በፍፁም ሊሆኑ አይችልም:: ከወደ ጓዳ ውስጥ የሚስማውን እንቅስቃሴ እያዳመጥኩ ግንኙነታቸውን ለመገመት እሞክራለሁ፡፡
ትንሽ ቆይታ ልጅቷ መጋረጃውን ከፍታ ወጣች:: በኔ ተቃራኒ ከመጋረጃው ጠርዝ መጅሊስ ላይ ተቀመጠች። ባለቤትየዋ ሺሻ አምጥታ ለኮሰችላት። አሁንም ያወራሉ። ሺሻውን ተቀብላ ማጨስ
ጀመረች፡፡ አትመስልም። በፍፁም ሱስ ባለፈበት ያለፈች አትመስልም።
እንደማያት አንድታውቅ ፈልጌያለሁ። ዐይኔን ተክዬ ቀረሁ:: እጅግ ውብ
ነች፡፡ ፀጉሯ ሉጫነቱ እርዝመቱ፣ ስስ ከንፈሮቿ ከተቀባችዉ ሊፒስቲክ
ጋር እንጆሪ ይመስላሉ። ጉመጣት ጉመጣት የሚል ስሜት ተሰማኝ።
ወተት እንደጠጣች ድመት፣ የራሴን ከንፈር በምላሴ ላስኩት፡፡ የቀይ
ዳማ ናት፡፡ ጥቁር አይኖቿን ሰማያዊ አይ ሻዶው ተቀብታቸዋለች። አማላይ የውበት እመቤት ትመስላለች፡፡

“ከእርሷ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት.
ላፈር አይደለም ወይ የተፈጠርኩት...” የተባለላት ትመስላለች፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍31
#ሰመመን


#ክፍል_አአምስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

ፈጣን ነው ። አንዴ ዲሰኩር ከጀመረ አድማጮቹን አፍ አስከፍቶ ይውላል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ አይናገርም በእምነቱ
ከብረት የጠነከረ ዲሲፕሊን ነበረው ።

ይህ ወጣት ታጋይ በኮንሰትራክሽን ካምፕ ቆይታው ጊዜ ድንገት አንዲት ሴት ይወዳል ። የሚያሳዝነው ይህች
የወደዳት ሴት የአንድ ፋሺስት ጀኔራል ሚስት መሆኗ ነው ።በሩቅ ከማየት በቀር ቀርቦ ለማነጋገር ዕድል አልነበረውም ።
ሴትዮዋ እዚያ ግቢ ውስጥ የምትመጣው የጄኔራሉ ሚስት በመሆኗ እስረኞቹን መጎብኘት እንደ መዝናኛዋ አድርጋ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ምሽት ሲቃረብ ወደ ካምፑ ብቅ ብላ « በሥቃይ የሚማቅቁ እስረኞችን በማየት ተዝናንታ
ትመለሳለች ። ምስኪኑ ካርል ዐይኑ ውስጥ የሴትዮዋ ውበት ገብቶ እንቅልፍ እየነሳው ይመጣል መምጫዋን ሰዓት
ጠብቆ ያያታል እሷ ግን ህልውናውንም ከታውቅለትም።

ሁኔታው እያደግ ይሔደና "ለካርል ድብቅ የውስጥ ሕመም ይሆንበታል ። ለማንም ሳይናገር ብቻዉን ወስጥ ውስጡን ይማቅቃል ። የሞኒካ አበት ለካርል ቅርቡ
ስለነበሩ ነገሩን በመከታተል ቀስ ብለው ደረሱበት ሴትዮዋን ያላየ ዕለት የሚሰማውን አሳዛኝ ስሜት አጠኑ ። ነገር ግን ምንም ሊረዱት አልቻሉም ከምስኪኑ ካርል አፍ የተገነዘቡት ነገር ቢኖር የሴት ውበት ሲማርከው የመጀመርያ የፍቅር ዐይኑ በማይሆን ቦታ መገለጡና በአጓጉል ሴት ላይ ማረፉ ነበር የሚያሳዝነው።

ቀስ በቀስ ነገሩ ተዛምቶ በቅርቡ የነበሩ እስረኘቀች ጆሮ ውስጥ ገባ። የፋሽስት ጀነራል ሚስት በመውደዱ ።እስረኞች ሁሉ ካርልን አክ እንትፍ አሉት ።። ይህ መገለል በምስኪኑ ካርል ላይ የባሰ ጭንቀትና ብቸኝነት አሳደረበት ። በመጨረሻም አንድ ሌሊት ራሱን ግድሎ ተገኘ . . .

እሺ ፥ ከዚያ . .አሉ ዮናታን በድንገት ከትውስታቸው እንደ ተመለሱ ።

እስክንድር ግር አለው። ከቀን ሕልማቸው ሲባንኑ እንዲያው የተነፈሱት ቃል ነው እንጂ እስክንድር መቀጠል ያለበት ምንም የተያያዘ ነገር አልነበረም ። እናም ከደካማ
ፈንግታ በቀር ምንም አልመለሰም።

እባክህ በዘዴ እየቀረብክ አጫውተው" አሉ የአባትነት ቃና ባለው አነጋገር አሁን ባለው ሁኔታ ላይ ብቸኝነት ከተጨመረበት መጥፎ ደረጃ ላይ ይደርሳል። እና እባክህ
ብኝነት እንዳይሰማው ለማድረግ ሞክር

“ እሺ ” ብሎ እስክንድር ከተቀመጠበት ተነሣ ክፍሉን ለቅቆ ሊወጣ ሲልም ዮናታን በባለ አደራናት ስሜት አጥብቀው ጨብጠው ነቀነቁት ።

የዐይን ፍቅር የዋዛ በሽታ አይደለም ” አሉ ዮናታን ራሳቸውን ለራሳቸው “አቤልን ከዚህን ሕመም ለማዳን ምን መደረግ አለበት የተለያየ የመፍትሔ ሐሳብ በጭንቅላታቸው ውስጥ መጣ ። ለጥቂት ደቂቃ ያህል ወደ ኋላቸው ተለጥጠው ተቀመጡ መነጽራቸውን መልሰው ዐይናቸው ላይ አደረጉ።

ወረቀቶቻቸው ጠረጴዛው ላይ እንደተበታተኑ ጥለዋቸወ ከክፍላቸው ወጡ። ወደ አቶ መዓምር ክፍል ነበር
የሄዱት ። አቶ መዓምር ለዮናታን ከሥራ ጓደኝነታቸውም ሌላ የቅርብ ጓደኛቸው ናቸው ።

ሰላምታ ተለዋውጠው እንደ ተቀመጡ «ዮናታን ያለምንም መንደርደሪያ በቀጥታ ወደ መጡበት ጉዳይ አመሩ ።

“ እባክህ አንድ ተማሪዬ ስለ ታመመ በምን መንገድ ልንረዳው እንደምንችል እንድታማክረኝ ነበር ?

“ ማ የሚባል ? ”

“ አቤል ! አቤል ፤ታስታውሰዋለህ ? ”

“ ኦ ! ኣዎ አስታውሰዋለሁ ፤ያ ጎበዙ ልጅ አይደለም ?” አሉ ኣቶ መዓምር ። ከአንድ ዓመት በፊት ሁለት ተከታታይ ኮርሶች አስተምረውት ነበር ። “አሁን ታዲያ ምን ነካው? በማለት ጠየቁ ።

“ አንዲት ልጅ በዐይኑ ወዷል የሚል መረጃ ነው ያገኘሁት” አሉ ዮናታን ፡ ከአቀማመጣቸው ለጠጥ ብለው

“ታዲያ ይሄ ሕመም ነው ወይስ ፍቅር ?” አቶ መዓምር ጉዳዩን ቀለል አድርገው በመመልከት ዐይነት ፈገግታ ፈገግ
አሉ። የዮናታን ግንባር ግን ፈጽሞ አልተፈታም ።

“ ሕመም ነው እንጂ!ከባድ ሕመም ። ”

“ ማለቴኮ ፡ ” አሉ አቶ መዓምር ፡ ከዮናታን ፊት ላይ ፈገግታ ባጡ ጊዜ ሽምቅቅ ብለው ነገሩን በማስተባበል ዓይነት ፡ “ ማለቴ " ይሄ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው ፤ ሁላችንም ብንሆን በዐይናችን ሳናፈቅር አላለፍንም ። እንዲያውም ከራሴ
ልምድ ብነሣ ተዋውቄ ካፈቀርኳቸው ይልቅ በዐይኔ ያፈቀርኳቸው በቁጥር ይበዛሉ ። ”

“ ለነገሩማ ፍቅር የሚጀምረው በዐይን ነው ” በማለት ዮናታንም ፈገግ አሉ ።

ታዲያስ አሁን እኮ ወደኔው መጡ አሉ አቶ
መዓምር ፥ የዮናታን ፈገግታ ለበለጠ ጨዋታ ጋብዟቸው ።“ ፍቅር ጤንነት ነው ። በኔ ግምት ሕመም ወይም በሽታ
የሚሆነው ጥላቻ ነው ። ዐይን ደግሞ ምን ጊዜም እንዲያፈቅር ያስፈልጋል ። ይህ ራሱ የሕይወት ቅመም ነው ። መጥፎ የሚሆነው ዐይን መጥላት ሲጀምር ነው ። ዐይን ተጨፍኖ
አይኬድ ነገር! ”

ዮናታን ውይይቱ ወደ ቀልድ እንዳዘነበለ ወይም ደግሞ መልኩን እንደ ለወጠ ተሰማቸው ። እሳቸው አክብደው
ያመጡት የአበል ጉዳይ ለአቶ ወዓምር ለምን ቀልሎ እንደ ታያቸው ዮናታን ሊገባቸው አልቻለም ። “ አቀራረቡ
ይሆን ?” ሲሉ በልባቸው አሰቡ ።

“ የአቢልን የዐይን ፍቅር ግን ፡ እንዲህ አቅልለን አናየውም ” አሉ እንደ ገና ኮስተር ብለው “ በደረጃ እኛ ከምንለው ብዙ ይለያል ። እንዳጠናሁት ከሆነ ትምህርቱን በሚገባ መከታተል አልቻለም ግድ የለሽነትን ስልቹነትን እያሳየ ነው ። አልፎ አልፎም ከገለጻ ክፍል ይቀራል ። ቀድም አቤልን የምታስታውሰው ከሆን ግን " እንዲህ ዐይነት ተማሪ አልነበረም ። እና መፍትሔ ካልተፈለገለት መጥፎ ሁኔታ
ላይ ነው የሚገኘው ” አሉና " የካርልን ታሪክ ሊያጫውቷቸው ምላሳቸው ላይ ካደረሱ በኋላ መለሱት

“ እንደ ምንም ይችን ዓመት ሊጨርስ አይችልም ማለት ነው? ” አሉ አቶ መዓምር ። በዩኒቨርስቲው ውስጥ
በታሪክ መምህርነት ብዙ ዓመት ስላገለገሉ ፥ የአቤል ዐይነት ችግር በተማሪዎች ዘንድ መከሠት ፥ ለእሳቸው አዲስ ነገር አልነበረም ። እንዲያውም ከጊዜ ብዛት እንዲሰለቹ አድርጓቸዋል ። ፈተና ሲደርስ መታመም ፥ ቅጠን ባጣ የጥናት ብዛት መቀወስ በጭንቀት ብዛት ማበድ ፥ በፍቅር ተጠምዶ ከትምህርት ተዘናግቶ መባረር ፡ ለዩኒቨርስቲው እንግዳ በመሆኔ የጎበዝ ተማሪዎች ተደናግሮ መውደቅ ፥ ይህንና ይህን የመሳሰሉት ሁኔታዎች በደረጃ ይለያዩ እንጂ በየዓመቱ፡ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ሳይከሠቱ አያልፉም ። አሁንም ዮናታንን እጅግያሳሰባቸ ጉዳይ {አቶ መዓምርን ምንም ያህል አልኮረኮራቸውም ።

መጨረሱንን ሊጨርስ ይችል ይሆናል ። ግን የሚያስፈልገው ጨርሶ መውጣቱ ብቻነው እንዴ?” አሉ ዮናታን።ጣ ባለ ድምፅ

“ ማለቴ ትምህርቱን ጨርሶ ሥራ ላይ ከዋለ፥ ራሱን በማዝናናት አሁን ካለበት ሁኔታ ነፃ ሊመጣ ይችላል ።”

“ እኔ ግን በዚህ መልክ አልመለከተውም ” አሉ ዮናታን አቤልን ዲግሪ አስይዘን ከዩኒቨርስቲ ማባረር ሳይሆን ታላቅ ምሁር የማድረግ ኃላፊነት አለብን ። ለዚህ ብቃት ያለው ልጅ ነው ። ደግሞም አሁን ባለበት ሁኔታ ትምህርቱንም ላይጨርስ ይችላል።

“እንግዲህ ለሥነ ልቡና ጥናት በሳል ለሆኑት እናማክራቸዋ ! ” አሉ አቶ መዓምር ነገሩን ለማሳጠር ያህል ።

“ለአካዳሚክ ኮሚሽኑም አስታውቀን አንድ መፍትሐ ይፈለግለት እንጂ ! ” አሉ ዮናታን ።

ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ይሆናል ። ማርታ ገና ከውጭ አልገባችም ። ትዕግሥትና ሁለት የመኝታ ክፍል
ጓደኞቿ አልጋቻው ላይ ጋደም ብለው ከመጀመሪያ ዓመት ኮርስ አንዱ የሆነውን የኢትዮጵያ ታሪክ እያጠኑ ይጠያየቃሉ።

የመኝታ ክፍላቸው በር ሳይንኳኳ “
ተከፈተ ።
👍3🥰1
ቤተልሔም አሰግድ አንገቷን ብቻ ወደ ውስጥ ብቅ አድርጋ ተመለከተች።

“ኦ ቤተልሔም ግቢ” አሏት ሦስቱም በአንድ ድምፅ ።ማርታ አልመጣችም ስትል ጠየቀች።

ግቢ ትመጣለች ” አሏት ደግመው ፡ ወደ ውስጥ ገብታ ትእ ሥት አልጋ ላይ ከግርጌ ተቀመጠች።

«« ምነው ቆየች ቶሎ እመጣለሁ ብላኝ ነበር ? "ካለች በኋላ ፥ ቤተልሔም ሰዓቷን አየችና ፥ “አንቺ ፡ ሦስት ሰዓት ከሩብ ሆኗልኮ ! ለመሆኑ ብትመልስ ዘበኞቹ ያስገቧታል ብለሽ ነው?” አለች ተስፋ በቆረጠ አነጋገር ።

ከመጣችስ ያስገቧታል ልጅትኮ ማርታ ነች አለች ትዕግሥት በቀልድ ዐይነት የማርታን ቅልጥፍና ለመግለጽ በርግጥም ማርታ አምሽታ በመጣች ቁጥር ጥብቅ ነን ”የሚሉትን የጥበቃ ጓዶች ጥርሷን አሳይታ ውሃ አድርጋቸው ነው የምትገባው።

ይልቅ አለች ትዕግሥት በመቀጠል ይልቅስ መምጣቷን ተጠራጠሪልኝ ” ለቤተልሔምም ጉዳዩ እንግዳ ነገር አይደለም ። ይልቁንም በተሳካ ጊዜ አብረው ነው ምሸቱን የሚወጡት ቤተልሔምን ከትእግስት ያስተዋወቀቻት
ማርታ ናት ። የእነሱ ጓደኝነት ግን ከውጭ ጀምሮ ነው ዓራት ዓመት ያህል አላቸው ። እንዲያውም ቤተልሔም ቀድማት ዩኒቨርስቲ በመግባቷ በመሐል ለተወሰነ ጊዜ ጓደኝነታቸው ላልቶ ነበር እንጂ መጀመሪያ ላይ በጣም ጥብቅ ጓደኞች ነበሩ " ቤተልሔም አሁን የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነች።

💥ይቀጥላል💥
👍1
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

መተዋወቅ አለብኝ፡፡ ውስጤ አሻፈረኝ ሲል ይታወቀኛል።አሁንም ፈዝዤ ዐይኔን እሷ ላይ እንደተከልኩት ነኝ፡፡ ዐይን ለዐይን እየተጋጨን ነው። እንዳሞራ ጆፌዬን እንደጣልኩባት ያወቀች
ይመስለኛል። በእጄ ነይ እዚህ ጋር ብዬ ምልክት ልሰጣት አሰብኩ፡፡ወዲያው ጭንቅላቴ መልሶ፣ አይ እንደዛማ አይሆንም፤ እንደዛ ድፍረት ይመስላል። እሷን መናቅ ይመስላል፡፡ ያቡ ሌላ ዘዴ መፈለግ አለብህ፡፡ምን ብላት ይሻላል..? አዎ!፣ ልደት...!፡፡ ልደቴ ጥሩ መግቢያ በር
ይፈጥርልኛል!፡፡ የልደት ካርዴን ስቤ በደንብ መጫወት አለብኝ..!

ባለቤቷን ጠራሁና፣ “በይ የልደቴን ግብዣ አንድ ብዬ ባንቺ ልጀምር። እስቲ አንድ ሙሉ ተጋበዥልኝ፡፡ልደቴን እንድታደምቅልኝ የጠራሻትን እዛጋር ለተቀመጠችው መላዕክ የመሰለች ቆንጆም ምትፈልገውን ጋብዢልኝ፡፡ ባለልደቱም እኔ እንደሆንኩ ንገሪያት:
ልታደምቅ መጥታ ጠፍቼባት እንዳይሆን ብቻዋን የተቀመጠችው፤ አልኳት፡፡

“ኪ...ኪ...ኪ... በጣም አመሰግናለሁ!፣ መልካም ልደት በድጋሚ...::”

“አደራ መላእክቷ ልደቴን ታድምቅልኝ...!”

“ጣጣ የለውም፤ ልደቱ እንዲደምቅ የተቻለንን እናደርጋለ፤”ፈገግ እንዳለች ሄደች:: ወደ ውስጥ ገብታ ጫት ይዛ ወጣችና ከቆንጅዬዋ ልጅ ጋር ቁጭ አለች። እየተሳሳቁ ያወራሉ። ልጅቷ ቀና እያለች ወደኔ ትመለከታለች፡፡ ያልኩትን እየነገረቻት መሆን አለበት። ቀና ስትል ጠብቄ በዐይኔ ያዝኳት:: ጎንበስ አለች። ለሁለተኛ ጊዜ ጠበኳት፤ አገኘኋት፤
እድሉን አላባከንኩትም፤ በግንባሬ ሰላምታ ሰጠኋት። አላሳፈረችኝም፣
ከፈገግታ ጋር አፀፋውን መለሰችልኝ፡፡ ትንሽ ቆይታ ልጅቷ፣ ቦርሳዋን ይዛ
ከአጠገቤ መጥታ ተቀመጠች፡፡ ባለቤትየዋ ሺሻዋን አምጥታ አጠገባችን አስቀመጠችና፣

“አደራ፣ ዘመዴ ልደቱ ነው፣ በደንብ ተንከባከቢልኝ፤” አለች እየሳቀች፡፡ ስትስቅ ፊቷ አጥንትና ቆዳ ብቻ እንደቀረው ያሳብቃል።

“ዘመድሽ ዘመዴ ነው አታስቢ፡፡” ልጅቱ ፈገግ ብላ መለሰች፡፡

“እሺ፣ ባለ ልደቱ እንዴት ነህ ...?” አለችኝ ወደኔ ዞራ፡፡

“አለሁ፡፡ እንዴት ነሽ ቆንጂት...?”

“ልደት እንዴት ነው ታዲያ...?”

“አጀማመሩ በጣም አሪፍ ይመስላል። እዚህ ብቻዬን ላከብር መጥቼ፣ አንችን መላዕክት የመስልች ቆንጅዬ እግዜሩ ላከልኝ::”

“ምነው ልደትን ሚያክል ነገር በብቸኝነት?”

“ያው ሰው እያለ ሰው ሲጠፍ ምን ይደረጋል? አንቺን መሳይ ቆንጆ በልደቴ ሊሰጠኝ ይሆናላ!”

“ኪ.ኪ.ኪ...ኧረ? ደግሞ ቆንጆ እያልክ አታሙቀኝ፡፡”

የምሬን እኮ ነው በጣም ታምሪያለሽ፡፡ ፀሎቴን ሰምቶ መሆን አለበት፣ በልደት ቀኔ አንቺን ውብ የላከልኝ፡፡ ይቅርታ ግን ሳንተዋወቅ ለፈለፍኩብሽ፣ ስምሽን ማወቅ ይቻላል...?”

“ምስጢር ምትጠብቅ ከሆነ...”

“ምስጢር በመጠበቅስ አልታማም፡፡ ችግሩ እኔ የምነግራቸው ሰዎች ምስጢር አይጠብቁም እንጂ...”

“ኪ...ኪ....ኪ..፣ ሞዛዛ ነገር ነህ ባክህ፡፡ እሺ ሃናን እባላለሁ።”

“እኔ ያቤዝ እባላለሁ።”

እሺ፡፡” ብላ ዝም አለች፡፡

“ተማሪ፣ ሰራተኛ..?” የማልወደው ጥያቄ ሳላስበው አመለጠኝ፡፡ዝም ላለማለት እንጂ፣ ምንም ብትሆን አይገደኝም፡፡

“ሁለቱንም አይደለሁም፡፡”

“ማለት ..?”

“ለግዜው ቦዘኔ ነኝ፡፡” ፈገግ አለች፡፡

“እንዴ! ምንም ሳይሰሩ መኖር ይቻላል እንዴ?”

“እንግዲህ እኔ እየኖርኩ ነኝ ባይ ነኝ፡፡”

“ሃ...ሃ... ከተቻለ፣ ለእኔም ንገሪኝና እንዳቺ አምሮብኝ ልቦዝን፡፡”

“ቀልደኛ ነህ፡፡ ስራን የመሰለ ምን ነገር አለና ነው፣ ልቦዝን ምትለው?”

“አንቺ ነሽ ቀልደኛ፡አንቺን የመሰለ ቆንጆ እንዴት ስራ ያጣል?”

“በቁንጅና ነዉ እንዴ ስራ ሚገኘው? ለነገሩ ለግዜው ነው ያልኩህ፡፡”

“እንደዛ አትዪም ታዲያ፤ እሺ ምን ነበር የምትሰሪው?”

“እንዴ... ምነው እንዲህ አጥብቀህ ጠየከኝ? ልትቀጥረኝ አሰበክ መሆን አለበት? ኪ.ኪ.ኪ...፣ እሺ ፊልም ነበር የምሞክረው።"

“ዋው! በጣም ደስ ይላል። አክትረስ ነሻ?”

“እንደዛ ነገር፣ ሙከራ...።”

“አንተስ ምንድነው የምትሰራው?”

“ዶሮ እርባታ ነገር እየሞከርኩ ነው::”

በቀደም ለሳሚ የነገረኩትን ውሽት ለእሷም ደገምኩላት፡፡ ተስፋ የቆረጠ ስራ ፈትን ማን ይፈልጋል፣ አይደለም እቺን የመሰለች ውብ፡፡ ለወራት የጠፋውን የፆታ
ፍላጎቴን፣ ኬት ጎትታ እንዳመጣችው ገረመኝ፡፡ በባሌም በቦሌም ብዬ መጥበስ አለብኝ፡፡” ብዬ አሰብኩኝ፡፡

“አሪፍ ነው፡፡ ጎበዝ፡፡”

“በደረቁ አደረኩሽ አይደል? ፈታ በይ የፈለግሽውን እዘዢ፡፡ ዛሬ የደስታዬ ቀን ነው፡፡” ሃናን ተግባቢና ቀለል ያለች የደብረ ዘይት ልጅ እንደሆነች ተረዳሁ፡፡ አጥብቆ ጠያቂነቴ ግን አልተመቻትም፡፡ባለቤቷን ጠርቼ ተጨማሪ ሺሻና ምትጠጣውን አዘዝኩላት፡፡ ተቀብላ ማጨስ ጀመረች፡፡ አጭሳ ከአፏ የምታወጣው ጭስ ብዛት ይገርማል፡፡ጭሱን በትኩረት እስከ መጨረሻው በዐይኗ ትከተዋለች፡፡ ጭሱን
አፍጥጣ ስትመለከተው፣ ከውስጡ አንድ የሆነ መልስ ወይም መፍትሄ ምትፈልግ ትመስላለች፡፡ እንደዛ ሆና ሳያት፣ በውብ መልኳና የተመቸው በሚመስለው ሰውነቷ የተጋረደ መከፋት ያየው መሰለኝ፡፡ ሳላስበው እቺን የመሰለች ልጅ ለምን እዚህ ጭስ ውስጥ መደበቅ ፈለገች የሚል ሃሳብ ውስጥ ተዘፈኩ፡፡

“እንካ አጭስ፡፡” ከሄድኩበት ሃሳብ መለሰችኝ፡፡

“እኔ አልወድም፡፡”

“ምንም አይልህም፡፡ ማጨሻ ፒፓ ይምጣልህ?”

“ከሆነማ ያንቺው ፒፓ ይሻለኛል፡፡በዛውም ቆንጆ ከንፈርሽን፣ከፒፓው ላይ እስመዋለሁ፡፡”

“ይሄን ያኸል...? ሞዛዛ፡፡” ብላ ሳቀች፡፡

“የምሬን ነው፣ ከንፈርሽ በጣም ውብ ነው ፤ እንጆሪ ነው ሚመስለው፡፡”

“አመሰግናለሁ!”

“አኔ ደግሞ እንጆሪ በጣም እወዳለሁ፡፡”
ኪ.ኪ.....፣ ደስ ምትል ቀልደኛ ነህ ባክህ፣ ታዲያ ምን ይሻልሃል?”

“ምን እንደሚሻለኝማ በደንብ ታውቂያለሽ የልደቴ ስጦታ ቢሆንልኝ ደስታዬን አልችለውም፤” ብዬ ጠቀስኳት፡፡

“ደረቅ...” ብላ ታፋዬን ቸብ አደረገችኝ፡፡ ሺሻውን ወደኔ ዘረጋችልኝ፡፡ ተቀበልኳትና ለማጨስ ሞከርኩ፡፡ ትን ብሎኝ ያስለኝ
ጀመር፡፡

“ኪ.ኪ.ኪ፣ እውነትም አጭሰህ አታውቅም፧” ብላ ተቀብላኝ ማጨሷን ቀጠለች፡፡ ሳቀርባት ሰተት ብላ እየቀረበችኝ ነው፡፡ ምፈልገው ድረስ ስቤ ብወስዳት ምትጎተትልኝ መስሎ ተሰማኝ፡፡ ለመሞከር ዝግጁ ሆንኩ፡፡ በደንብ ዘና ብላ መጫወት ጀምራለች፡፡ ባለ ቤትየዋ፣ በየመሃሉ እየመጣች፣ “ተጫወቱ፣ አሁንማ እኔን እረሳችሁኝ፤” ትለናለች፡፡ ከሆነ ሰዓት ጀምሮ ሳወራት፣ ታፋዋን እየነካካው፣ እጆቿን እያሻሸሁ ነው፡፡
ምንም ክልከላ አልገጠመኝም፡፡ ሰዓቴን አየሁና፣

“ስዓቱ እንዴት ሄደ?”

“ስንት ሰዓት ነው?”

“አስራ አንድ ሊሆን ነው፡፡”

“ወሬ ይዘን አልታወቀንም፡፡”

“ኢንስታይን፣ “ከቆንጆ ሴት ጋር ሲሆኑ ሰዓቱ እራሱ ይሮጣል፣ ምቀኛ ነው፧' ያለው እውነቱን ነው ለካ፡፡”

“ኪ.ኪ.ኪ.፣ መቼ ነው የነገረህ?”

“ሃሃሃ...፣ ኧረ የት አግኝቼው? አለ ሲባል ሰምቼ እንጂ፡፡ እዚህ ሃገር ሁሉ ነገር አሉ አይደል...”

እጆቼን ወደ ፈለኩት እየስደድኩ ነው፡፡ አሁንም ክልከላ የለም፡፡ሳማት፣ ሳማት የሚል ስሜት ከቅድም ጀምሮ ወጥሮ ይዞኛል።ልቆጣጠረው የምችለው ስሜት አይደለም፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብኝ
አሰብኩ፡፡ ደግነቱ ዛሬ፣ ብዙ ደምበኛ የለም፡፡ ነፃነት ተሰምቶኛል፡፡

“ተጫወት እንጂ! ዝም አልክ፡፡ ምን እያሰብክ ነው?” አለችኝ፡፡

“ያው ስላንቺ ነዋ፡፡ ውበትሽ ስሜታዊ ያደርጋል። ሳማት፤ሳማት
👍2
፤ ይለኛል፡፡ ደግሞ ምርጥ ልጅ ነሽ፡፡ በፍፁም ላስቀይምሽ የማልፈልጋት አይነት ቆንጆ ነሽ፡፡ እንደ ድፍረት ቆጥረሽብኝ
እንድታኮረፊኝ ደግሞ አልፈልግም፡፡ ምናባቴ ላድርግ ብዬ እያሰብኩ
ነበር፡፡” ከንፈሯን እያየሁ ደግሜ የራሴን ከንፈር በምላሴ ላስኩት፡፡

“አንተ እብድ. አታረገውም አይባልም እኮ፤” አለች ዐይኗን አፍጥጣ፡፡

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ሰመመን


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ


ቤተልሔም ቀድማት ዩኒቨርስቲ በመግባቷ በመሐል ለተወሰነ ጊዜ
ጓደኝነታቸው ላልቶ ነበር እንጂ መጀመሪያ ላይ በጣም ጥብቅ ጓደኞች ነበሩ ቤተልሔም አሁን የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነች።

ቤተልሔም የትዕግሥት አገላለጽ ስለ ገባት ሣቀችና መምጣትስ ትወጣለች እዛ ሠርጉ ቦታኮ ነው የሔደችው ቀን አብሬኣት ነበርኩ ። ስለ ሁኔታው ተነጋግረን ለነገ እንዳንደክም ዛሬ እዚሁ አድረን ጠዋት ለመሄድ ወስነናል አለቻት።

ትዕግሥት ትዝ አላት እሑድ የጓደኛዋ ሠርግ እንደሚኖር ማርታ ነግራት ነበር ።
አንቺም አብረሽን ትሕጃለሽ አይደለም ? አለች ቤተልሔም የትዕግሥትን ዐይን ዐይን እየተመለከተች እስቲ እግዜር ያውቃል ጥናቱኮ ተከምሮአል ? ” አለች ትዕግሥት በማመንታት ዐይነት ።

ከሪደሩ ውስጥ የታኮ ጫማ ድምፅ ስለ ተሰማቸው ጭውውታችውን ለአፍታ ያህል አቋረጡ ።

እንዳች ነገር በኋላሙ እንደሚያባርረው ሰው ማርታ በሩን ብርግድ አድርጋ ገባች ቤተልሔምን ከክፍሏ በማግኘቷ ደስ አላት ትንፋሿ እጥር እጥር እያለ “ሄይ ቤቴ! ቆየሁ እ! ምን ታረጊዋለሽ ! ” አለችና ሳመቻት ። ትዕግሥትንም ሳመቻት ከማዶ ያሉትን ሁለት ልጃገረዶች በፈገግታ
ብቻ ሰላምታ ተለዋዉጣቸው ከቤተልሔም ጎን ቁጭ አለች።

“ እንዴት ነው? ” አለኝና ቤተልሔምን ጠቀስ አረገቻት በሳመቻት ጊዜ ከንፈሯ እጅግ ለስልሶባት ነበር ።ለምስጢር ድርጊቶቻቸው ከንግግር የበለጠ በጥቅሻና ምልክት ይግባባሉ።

ምን ታረጊዋለሽ ? ” አለችና ማርታ ከነልብሷ መኝታዋ ላይ ወጥታ ጋደም አለች ።

ግን በርግጥ ሠርጉ ቦታ ነው ያመሸሽዉ? ” አለች ቤተልሔም ጥርጣሬ በተሞላበት አነጋገር

“ሙች እዚያው ነው ያመሸሁት ” አለች ማርታ ው ስንሠራራ አመሸንና ፥ የቅርብ የሆንነው ማታ ጓዳ ገብተን ራት ከበላን በኋላ ፥ አንድ ውስኪ ተከፈተልን ። ሌላ ነበር !አትሔጂም ብለውኝ በግድ ነው የመጣሁት ።”

“ ፓ! ግን ምንም የቀመስሽ አትመስዪም
“ሁለት መለኪያ ነችኮ የጠጣኋት ቤቴ ሙች "

እሺ ፥ ከዚያስ ? ማ ሸኘሽ ? ” አለቻት ። ከፊል ቅናት በተቀላቀለበት አነጋገር ።

“ አንዱ ባለ ቆርቆሮ ዋ ! ”

ትዕግሥት ነገሩ ስለ ገባት ሣቀች ከማዶ የተኙት ሁለት ልጃገረዶችም ከንፈራቸውን ከድነው ሣቁ ። በከፊል ቢያጠኑም በከፊል ጆሮአቸው እነ ማርታ ጨዋታ ላይ ነበር።

“ በሉ እንተኛ ” አለች ማርታ ሹራቧን እያወላለቀች “ ነገ'ኮ በጠዋት ተነሺዎች ነን ።”

“ አዎ !ኧረ ትላንትም አልተኛሁም ፡ ሁኔታታን ላረጋግጥ ብዬ ነው ኮ እንቺጋ የመጣሁት! ” አለችና ቤተልሔም ከተቀመጠችበት ተነሣች ።

“ ሁኔታው ሁሉ የተሟላ ነው። ጠዋት ተነሥተን መሔድ ብቻ ! ”

“ ደሞ ትዕግሥትን አንድ በያት ። እያመነታች ነው

“ ለምኑ ? ለመሔድ ? ” አለች ማርታ በቁርጠኝነት አነጋገር ። “ ወዳ በቀበሌ ተገዳ ! ” ልማዳዊ የአነጋገር ዘዴዋ ነው ።

“ ሆሆ ፈተናኮ እየተቃረበ ነው ”አለች ትዕግሥጋት በማመንታት ዐይነት ።
አብዛኛው ልቧ ግን በመሔድ ላይ
ያጋደለ ነበር ።

ታዲያ በአንድ ቀን ተአምር ልትፈጥሪ ነው?” ስትል ቤተልሔም ተነሣች ። ልትሔድ የነበረችዋ ሴትዮ ጭራሽ
ወገቧን ይዛ ማብራሪያ ትሰጥ ገባች ። የሁለተኛ ዓመት ተማሪ በመሆኗ፥ አገላለጿ አሁን የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሚጨነቁበትን ሁኔታ አርጌው አልፈኣለሁ ” በሚል የበላ
ይነት ስሜት ነው ።

“ አንድ ነገር ልንገርሻ ትዕግሥት” ስትል ጀመረች ።ይሄ ፍሬሽማን ላይ መረበሽ ፥ መጨነቅ ራስን ማሠቃየት ዝም ብሎ እየተለመደ የመጣ ነገር ነው ። እናም በኛ ጊዜ እንዲሁ ነበር ። ማጥናት ሳይሆን ፊደላትን መሰነጣጠቅ ነበር የተያዘው ። በዚያ ላይ ' ሁሉ ነገሩ የጭንቅ ግቢ ነበር
የሚመስለው ፤ ከፊሉ ዊዝድሮዋል ለማውጣት ሲሯሯጥ አንዳንዱም ሲቀልድ፥ አንዳንዱም ሌክቸረሮች በእጅዋ ናቸው እየተባለች ስትታማ አንዳንዱ ከአቅሙ በላይ ሌሊቱን ሙሉ ሲያጠና በተቀመጠበት እንቅልፍ ሲወስደው
ምኑ ቅጡ ግን መጨረሻው ምን ሆነ መሰለሽ ! ”

ከማዶ ያሉት ሁለት ልጃገረዶችም ፡ ጆሮአቸውን በጣም አስልተው ይሰማሉ ። ማርታ ብቻ እንደ ማሸለብ ስላረጋት በሰመመን ነበር የምታዳምጠው ።

ቤትልሔም ቀጠለች ፤ “ መጨረሻም ላይ ያው የገና ማዕበል መጣና ሁሉንም ለየ ። መውደቅ ያለበት ወደቁ ፤ማለፍ ያለበት አለፈ ።

“ ታዲያ ለእሱማ ነው “ ኮ ይሄ ሁሉ መፍጨርጨር ” አለች ትዕግሥት ባልተደነቀ ስሜት ።

“ ማለቴ ” አለች ቤተ ልሔም ልትል የፈለገችውን በቅጡ እንዳልተረዱላት በመገመት ። “ ታዲያ መውደቅ ወይም ማለፍ ፥ ከሁለት አንዱን መጋፈጥ የማይቀር ዕዳ ሆኖ ሳለ መጨነቁ ምን ይጠቅማል ? እንደኔ እንደኔ የሚያስፈል
ገው የተወሰነውን ነገር በፕሮግራም ማጥናት ነው ። ከዚያ ውጭ የራሱ ጉዳይ ! ግን የሚገርምሽ ደግሞ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አንድ የሚያስጠላው ነገር ፡ አንች እንደ ሌላው ጥናቱ ላይ ተደፍተሽበት ካላደርሽ ደኅና ውጤት ያመጣሽ እንደሆን ሐሜቱ መከራ ነው ። “ሌክቸረሩን አውርዳው ነው ሬጅስትራር ውስጥ ዘመድ አላት ፥ ፈተና ወጥቶላት ነው ሌክቸረሩን እግሩ ላይ ወድቃ ለምናው ነው ፥ ጉቦ ሰጥታ ነው? ኧረ ስንቱ ! ዩኒቨርስቲ የገባ ተማሪ በግድ መሠቃየት አለበት እንዴ? እንደኔ “ የአንደርስታንዲንግ ጕዳይ ይወስለኛል
አንዳንዱ ብዙም ሳይጨነቅ ቶሎ ይገባዋል አንዳንዱ ደግሞ ብዙ ሠርቶ ትንሽ የሚገባው" አለ ...ህእ!

በተዘዋዋሪም ቢሆን " ራሷን በፕሮግራም ከሚያጠኑትና በቀላሉ ከሚገባቸው መድባ ነበር የምታወራው ። እንዲህ
ብዙ እንድትናገር ያረጋት ቁስሏ ኔው ። አምና የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ሳለች ከላይ የጠቀሰቻቸውን ሁኔታዎች ታምታባቸዋለች እንዲያውም በጣም ደካማ በነበረችበት በኢትዮጵያ ጂኦግራፊ ኮርስ “B” ማምጣቷ ከአስተማሪው
ጋር በግልጽ እንድትጠረጠር አድርጓታል። እሷ ግን " “ እኔ የሴንትሜሪ ተማሪ ስለ ነበርኩና ጥሩ መሠረት ስለ ነበረኝ
የዩኒቨርስቲ ትምህርት በቀላሉ ነው የሚገባኝ ” ባይ ነች ።የማንኛወንም የትምህርት አይንት ገለጻ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ስለሚሰጥና እሷ ደግሞ እንግሊዝኛ ፍሎዌንት ነኝ”ስለምትል በቀላሉ ለመረዳቷ ይህም በከፊል ታማኝነት ያለው መከላከያዋ ነው ። በእርግጥም እንግሊዝኛ ስትናገር
ለሚሰማት ፥ ፕሮናውንሴሽን የሚሸጥ ቢሆን ኖሮ ብዙ ያወጣላት ነበር ።

“ እምልሽ ” ስትል ቀጠለች አንዳንዶቹ እንደ ሚሉት “ጭራሽ አላጠናም” ማለት እንኳ ዝም ብሎ ነው ማንኛውም ተማሪ ቢሆን ያጠናል ። የሚለያየው የአጠናን
ደረጃውና ስልቱ ብቻ ነው ። ግማሹ ለሊቱን ከቀን እያገናኘ ያጠናል ።ግማሹ ደግም በፕሮግራም አጭር ጊዜ ያጠናል
በሳይኮሎጂ እንደ ተማርነው ግን ጥሩው ዘዴ በየአንድና ሁለት ሰዓት ጥናት ውስጥ የተመሰነ ዕረፍት መውሰዱ ነው እንቅልፍ በደንብ መተኛትም አእምሮ ጥናትን በደንብ እንዲቀበል ይረዳል ። ”

የሳይኮሎጂ ነገር ስታነሣ ግልፍ አላት። ጥሩ አስተማሪ ደርሶአት ስለ ነበር በርግጥም ጥሩ ዕውቀት ገብይታበታለች።

የሳይኮሎጂ አስተማሪያችን ስለ ጥናት ዘዴ ሲያስተምር ምን አለን መሰለሽ ?“ከዩኒቨርስቲ ውስጥ እነዚህ ከመጠን በላይ እያጠኑ የሚያልፉ ተማሪዎች ።የመማር ኃይል (ፖቴንሺያል) የላቸውም ። ዩኒቨርስቲው ውስጥ የ ሚቆዩት በትግል ነው ። ስለዚህም ጨርሰው በሚመደቡበት ሥራ ላይ በቂ ግልጋሎት ሊሰጡ አይችሉም” ያለው ትዝ ይለኛል ። ችሎታው ካለሽ በቀላሉ ሊገባሽ ይችላል ። ችሎታው ከሌለሽ ግን ከንቱ
ትግል ነው ... ግን እኮ ሳይኰሎጂ
👍2
መሰጠት የነበረበት መጀመሪያ ዓመት ላይ ነው ። ከብዙ ጭንቀት ሊያድን ይችል
ነበር” ስትል የራሷን ግምት አከለችበት ።

ማርታ ከሰመመናዊ እንቅልፏ ባንና ተመለከተቻቸው፤ አይኗ ፍም መስሏል ።

“ አልተኛችሁም እንዴ? ” አለች ግንባሯን እንደቋጠረች ፥ ከእንቅልፍ መንፈስ ሳቢያ በሚመነጭ ቁጣ የተሞላበት አነጋገር ። “ አንቺ ቤቴ! ሒጂና ተኚ ፡ ጠዋት እኮ
ሐያጆች ነን ።”

ቀና ብላ ወደ ማዶ ደሞ ተመሰከተች ። ሁለት ልጃገረዶች ገና እያጠኑ ነበር ። መብራቱ ሊጠፋላት እንደማይችል ገባትና ብስጭት ብላ ተመልሳ ተኛች ።

💥ይቀጥላል💥
👍1