#የታካሚው_ማስታወሻ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሦስት
፡
፡
#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)
“ያው ስላንቺ ነዋ፡፡ ውበትሽ ስሜታዊ ያደርጋል። ሳማት፤ሳማት፤ ይለኛል፡፡ ደግሞ ምርጥ ልጅ ነሽ፡፡ በፍፁም ላስቀይምሽ የማልፈልጋት አይነት ቆንጆ ነሽ፡፡ እንደ ድፍረት ቆጥረሽብኝ እንድታኮረፊኝ ደግሞ አልፈልግም፡፡ ምናባቴ ላድርግ ብዬ እያሰብኩ
ነበር፡፡” ከንፈሯን እያየሁ ደግሜ የራሴን ከንፈር በምላሴ ላስኩት፡፡
“አንተ እብድ. አታረገውም አይባልም እኮ፤” አለች ዐይኗን አፍጥጣ፡፡
ዝም ብዬ አየኋት፡፡
«ባይዘዌ ግልፅነትህ በጣም ደስ ብሎኛል። ስሜትህን በግልፅነት
መንገርህ፣ ያንተንም ስልጡንነት ያሳያል፤” አለችኝ ::
ደስ ብለኸኛል...? አሁን መድፈር አለብኝ፡፡ ብስማት ምንም አትለኝም፡፡ ከዚ በላይ ምን እንድነው ምጠብቀው? በመጀመሪያ ቀን ልሳምሽ ስላት፣ አፏን አውጥታ እሺ እንድትለኝ ነው? ስሜቴ ከምቆጣጠረው በላይ ሆነ፡፡ አድርገው አድርገው ይለኛል፡፡ በዐይኔ የቤቱን እንቅስቃሴ እከታተላለው፡፡ አሁን ቤቱ ባዶ ሆኗል፡፡ ባለቤቷም ውጪ
ከወጣች ቆይታለች፡፡ ላድርገው? በድንገት ብትገባብንስ? ደግሜ ሰዓቴን አየሁ፡፡ ጋድ! አሁን ሂድልኝ ቢባልኮ እንዲህ አይሮጥም፡፡
“ስዐቱ በጣም ሄደ፡፡ ወደ አገርሽ ሄደን ደግሞ፣ ልደቴን በፈሳሽ ብናከብር ምን ይመስልሻል? እዚሁ አስራ ሁለት ሰዓት ሊሆንኮ ነው፡፡”
“እዛማ የማውቀው ሰው ሊያየኝ ይችላል። ባይሆን እዚህ ምታውቀው ቤት ካለ...?”
“ችግር የለም፡፡ መኪና ይዣለሁ፡፡ እዛው ሰው ማያየን ቦታ እወስድሻለሁ።” ዝም አለች፡፡ ዝምታ መስማማት ነው፡፡ ባለቤቷ
መጠባበቅ ጀመርኩ፡፡ ባለቤትየው ወዲያው እስክትመጣ አድፍጬ መጠባበቅ ጀመርኩ ባለቤትየዋ ወድያው
ብቅብላ፣
“ተጫወቱ! ዝም አላችሁ፡፡ ምን ይጨመር...?” አለችን፡፡
“ሂሳብ ስሪልን፤” አልኳት፡፡ እዚህ ተጨማሪ ሰዓት ማባከን አልፈፈለኩም፡፡
“እሺ!” ብላ ልትሰራልን ወጣች፡፡ ከሃናን ጋር እየተጠጋጋን ሳናስበው ተጣብቀናል፡፡ ሙቀቷ ይሰማኛል፡፡ ሂሳብ ከፈልኩና፣
ተነሽ እንውጣ!” አልኳት ልብሴን እያረጋገፍኩ፡፡
እሺ ግን፣ አብሬህ አልወጣም፣ አንተ ውጣና ውጪ ጠብቀኝ፡፡”
አላንገራገርኩም፡፡ የመኪናዬን አይነትና ያቆምኩበትን ቦታ ነግሪያት ወጣሁ፡፡ አላስጠበቀችኝም፤ ቶሎ መጣች፡፡ የዱከምን ከተማ ወደኋላ እየተውኩ፣ ወደ ደብረዘይት ነዳሁት። ልደቴን ደስ የሚልና ልዩ እንዳደረገችልኝ፣ ስለ ልዩ ውበቷ፣ ስለ ከንፈሯ ልዩነት እያወራሁ በፍጥነት እከንፋለሁ፡፡ በአንድ እጄ መሪ ይዤ በሌላው እጄ በስስ ታይት የተሸፈኑት ታፋዎቿ መሃል ገባሁ፣ ሙቀቷ ረመጧ ለበለበኝ፡፡ እጄን አወጣሁትና እጆቿን ያዝኳቸው፡፡ በላብ ረስርሰዋል፡፡ ጣቶቼን በጣቶቿ መካከል ሰገሰኳቸው፡፡ አጥብቄ ጨመኳቸው፡፡ ምንም አታወራም ዝም.
ብቻ፡፡ ሁሉም ተፈቅዷል፡፡
በስሜት ባህር ቀልጠን ሰምጠናል፡፡
ወደ ክፍሌ በፍጥነት እየነዳሁ ነው፡፡ ወዴት ነው እንኳ ሳትለኝ ትከተለኛለች፡፡ ልከመርባት ቸኩያለው፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ አምናኛለች፡፡ እንደበግ
እየተጎተተችልኝ ነው፡፡ የፈለኩትን ሁሉ ፈቅዳልኛለች፡፡ ከራሴ ሰውነት የሚወጣ ሙቀት በሸሚዜ አልፎ ፊቴን ይልፈኝ ጀመረ፡፡ ወደ ክፍሌ በሚወስደው የውስጥ መንገድ ታጠፍኩ፡፡ አሁንም ምንም አላለችም፡፡ ትንሽ እንደነዳሁ ከፊቴ ያለ ሚኒባስ አስፓልቱ ላይ መንገድ ዘግቶ ቆመ፡፡ ቸኩያለው፡፡ ደርቤ ላልፈው ስል፣ ከፊቴ ሌላ መኪና እየመጣ ነው፡፡
አክለፈለፈኝ፡፡ ወዲያው ሚኒባሱ ተንቀሳቀሰ፡፡ ጠጋ ስል፣ የተሰበሰቡ
ወጣቶች ተቆፍሮ የነበረውን መንገድ ያስተካከሉበት ገንዘብ እየጠየቁ
ነው፡፡ ግዜ የለኝም፣ እጄን ወደ ኪሴ ሰድጄ ያገኘሁትን ብር ሰጠኋቸው፡፡
“ያራዳ ልጅ...፣ ያራዳ ልጅ...
ይመችሽ...፡፡
መኪናሽን ሃመር ያርግልሽ፡፡”
በዜማ አዘል ምርቃት ሸኙኝ፡፡ ስንት ሰጥቻቸው ይሆን? ለነገሩ ስንትስ ብሰጣቸው፣ እኔ ይሄን የመሰለ መና ወርዶልኝ...፡፡ 'መኪናሽን ሃመር ያርግልሽ' ያሏት ምርቃት ከእዕምሮዬ ቀርታ በግድ ፈገግ አደረገችኝ፡፡ ቪትሴን ንቀዋት ነው? ለኔ ሃመሬ ናት፡፡
የክፍሉን በር፣ እንዴት ከፍቼ እንደዘጋሁት አላስታውስም፡፡ እንደቆምን በሩን አስደግፌ ተአምረኛውን ከንፈሯን መምጠጥ ጀመርኩ፡፡ በፍጥነት እራቁታችንን ሆንን፡፡ ረጅም ነች፡፡ በቁመት ብዙም አልበልጣትም፡፡ ልከኛ የተነፋፉ ጡቶቿን ለመዋጥ ዝቅ ስል፣ ራቁት
ገላዋን እታች ድረስ ሳየው፣ ከባድ ስሜት ተሰማኝና አልጋው ላይ በጀርባዋ አጋደምኳት፡፡ የገላዋ ልስላሴና የሰውነቷ ሙቀት ስሜቴን አላወሰው፡፡ ከውስጥ ሱሪዋ በስተቀር እራቁቷን ነች፡፡ እላዩዋ ላይ ተለጠፍኩባትና ተንጠራርቼ ከንፈሮቿን ጎረስኳቸው፡፡ በሁለት እጆቿ
ጆሮዎቼን ይዛ፣ ትስመኝ ጀመር፡፡ ትኩሳቴ ሲጨምር ይታወቀኛል፤ ስሜቴ ተንጠራራ፤ እየተሳሳምን እጄን ወደ ፓንቷ ላኩት፡፡ ፓንቷን ላወልቀው ስታገል ተረዳችኝ፡፡ ከንፈሯን ከከንፈሬ ሳታላቅቅ፣ ፓንቷን
እንዳወልቀው፣ እግሮቿን ወደላይ አጥፋ አመቻቸችልኝ፡፡
ስሜቴ በውስጤ ሲፈላ፣ ሲንተከተክ ይሰማኛል፡፡ ዋጣት፤ዋጣት፤ የሚል ስሜት ተሰማኝ፡፡ ልውጣት ከከንፈሮቿ ጀመርኩ።
ከንፈሮቿን ሳልጠግብ፣ አንገቷን፣ አንገቷን ሳልጠግብ፣ እየላስኳት ቁልቁል ወደ ጡቶቿ ወረድኩኝ፡፡ እልህ፣ ስግብግብነት፣ ውስጤን ወጥሮታል፡፡ የቱን ይዤ የቱን እንደምለቅ መምረጥ አቅቶኛል።
አንደኛውን ጡቷን እስከቻልኩት ያህል ዋጥኩት፡፡ ከወገቧ ወደላይ
ተንፈራገጠች፡፡ በስሜት ተቃጠልኩ፣ ጨስኩ፣ መትነን ጀመርኩ።መዋጥ አልሆንልህ ሲለኝ፣ እውስጧ መግባት፣ ገብቶ መሰንቀር አማረኝ፡፡ ታፋዎቿን ከፈትኳቸው፤ ያቃጥላሉ፡፡ ይፋጃሉ፡፡ በረጃጅም እግሮቿ፣ በለስላሳ ታፋዎቿ፣ መሀል ተንበረከኩኝ፣ ተርመሰመስኩላት::
በእግሮቿ ወገቤን አቅፋ ጎትታ ከራሱዋ
ጋር አጣበቀችኝ፡፡ እንደተመኘሁት ውስጧ ሰነቀረችኝ፡፡ በሙቀቷ ተቀቀልኩኝ፡፡ እራሳችንን እስክንስት፣ በስሜት ሰረገላ ተመነጠቅን፣ ከአለም ተነጠልን፡፡ ዳግም
የምንገናኝ እስከማይመስል ድረስ፣ ያበጠው ስሜቴ እስኪፈነዳና እስኪተነፍስ ድረስ፣ የቀረን እንጥፍጣፊ ሃይልና ጉልበት አልነበረንም፡፡ እንቅልፍ ወሰደን፡፡ ለእራት እንኳ መነሳት አቅቶን በዛው አደርን፡፡ የሆነ ሰዓት ላይ፣ እንደሰመመን እንደምታድር በስልክ ስታወራ ስማኋት፡፡
ለሊት ከእንቅልፌ ስባንን አጠገቤ ተኝታለች፡፡ ሳያት በጣም ደስ አለኝ፡፡ ህልም አይደለም፡፡ እውነት ነው፡፡ ፀጉሯ ተበታትኗል፣ ረጅምና ማራኪ ሰውነቷ ተበረጋግዷል፡፡ እርሷ ለጥ ብላ ተኝታለች፡፡ አልጋው ውስጥ ተገላብጬ ሰውነቷ ላይ ተለጠፍኩባት። ማታ የጠገብኳት
የመሰለኝ ደክሞኝ ነበር፡፡ ስሜቴ ዳግም ተላወሰ፡፡ አሁንም ውስጤ አልበረደም፡፡ እንድትነቃ አደረኳት፣ እንደ አዲስ እየተንገበገብኩ“እወድሻለሁ፣ በጣም ልዩ ነሽ፣ ስጦጠዬ ነሽ፡፡ እያልኩ እንደተላመደ
ሰው፣ የተለያየ አይነት የወሲብ ልፊያ እየቀያየርን በነፃነት ተላፍተን፣
ተመልሰን ተኛን፡፡ ጥዋት ስነሳ ሰዓቴ አራት ሰዓት ተኩል ይላል።ወላልቀን ስላደርን፣ መነሳት አቅቶን ስንንከባለል አምስት ሰዓት ተኩል ድረስ ቆየን፡፡ የረሃብ ስሜቱ ሲጠናብን ምግብ ፍለጋ ወጣን፡፡ ምግቡ
በጣም ይጣፍጣል፡፡ተርበን ነበር፡፡ ከበላን በኋላ ድካሙ የባዕ ተጫጫነን፡፡ከትናንት ጀምሮ እረስተነው ወደ ነበረው ወደየ ራሳችን የሃሳብ ዓለም ተመለስን፡፡
“ዛሬም ወደ ቤት አትሸኘኝም?” አለችኝ ሃናን፡፡
“እህ እ! እንዲህ ገድለሽኝ፣ በምን አቅሜ ነው የምሸኝሽ...?” አልኳት ፈገግ ብዬ፡፡
“ኪ.ኪ...ኪ...፣ ጭራሽ እኔ ገዳይ? አላስተረፍከኝም እኮ፣ አውሬ!” የድካም ሳቅ እየሳቀች፡፡

👍4
የምር ግን እንደ አውሬ አስፈራለሁ...?”
“ኧረ በጣም ደስ ትላለህ፡፡ ሞዛዛ!”
“ኦ፣ ሎርድ! አንቺምኮ ምርጥ እብድ ነሽ፡፡ በዛ ላይ ልዩና ጣፋጭ፡፡ በህይወቴ እንዲህ ደስተኛ ሆኜ አላውቅም፡፡ ወደፊትም አይመስለኝም፡፡”
“እሺ አሁን ምንድነው እቅድህ? እቤት ታደርሰኛለህ ወይስ ራሴው ልሂድ..?”
“እንዴት አባቴ ነው ማላደርስሽ፣ የኔ ንግስት? አንቺ በጣም ልዩ ነሽ! ምን ያህል እንዳከብርሽ እንዳደረግሽኝ አታውቂም፡፡ በተግባር እገልጥልሻለሁ፡፡››
“አንተ ትቀልዳለህ፣ እኔ ደክሞኛል፡፡ በዛ ላይ ውጪ ስላደርኩ እናቴ ታስባለች፡፡ ገና ስገባ ምን እንደምባል ጨንቆኛል፡፡ በናትህ ተነስ እንሂድ።"
ለመሸኘት ተነሳሁና፣ ፊቷን በጣቴ ቆንጠር አድርጌ ከንፈሯን ሳምኳት፡፡ መልሳ ሳመችኝ፡፡ እንደኔዉ እብድ ነች፡፡ ትናንት ሰው ያየናል እንዳላለች፣ አሁን አላስጨነቃትም፡፡ ሂሳባችን ከፍለን፣ ሰፈሯ ላደርሳት ወጣን፡፡ የእሳተ ጎሞራዋ ሀገር፣ የቢሾፍቱ፣ የሆራ፣ የባቡጋያ፣የኩሪፍቱ፣ የጨለለቃ ሀይቆች ሀገር፣ ውቢቷ ቢሾፍቱ፣ የምወዳትን ያህል በጣም በህይወቴ አስፈላጊዋን ውብ እየሰጠችኝ ነው፡፡ ይህች ልጅ የህይወቴ መጠማዘዣ፣ የመአዘን ድንጋዬ እንደሆነች እየተሰማኝ ነው፡፡ ሃኒን ከሸኘሁ በኋላ፣ እሁድ ከሰዓትን ከነ አሌክስ ጋር ቁጭ ብለን ስለ ትናንቱ ታሪካዊ ልደቴና ቅዱሱ አጋጣሚ እያወራን ስንስቅ አመሽን፡፡ በተለይ አሌክስ ተገረመ፡፡ እንደዚህ አይነት ፈጣን ሰው አትመስለኝም ነበር፤ አለኝ፡፡ ካላየሁ አላምንም ማለት ቀረው። ሃኒ በውስጤ አዲስ የመኖር ፍላጎትን ጭራብኛለች፡፡ በህይወቴ እንደዚህ አይነት ደስታ ሳላይ ልሞት ነበር፡፡ ለራሴ መሞት አለብኝ ሚለውን የጅል ወሬዬን ማቆም እንዳለብኝ ነገርኩት፡፡ መኖር መስራት አለብኝ፡፡
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍1
#ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
አቤል ገና ጎህ ሳይቀድ ነው ከእንቅልፉ የሚነቃው ።የዛሬን አያርገውና በርትቶ በሚሠራበት ጊዜ ፥ ለጥሩ ጥናት
የመረጣት ሰዓት ከሌሊቱ 11 እስከ 1: 30 ያለችውን ነበር ።በዚያው ለምዶበት አሁንም ወደ 12 ሰዓት አካባቢ ይነቃና፥
የቁርስ ሰዓት እስኪደርስ ድረስ ወዲያ ወዲህ ይንጎራደዳል ።ምንጊዜም ከመንጎራደድ ጋር የተያያዘች አንድ ተግባር አለችው ። ወደ ቁርስ ከመሔድ በፊት ከለል ያለ ቦታ ሆኖ ትዕግሥት ወደ ቁርስ ስትሔድ ማየት አለበት ። የዐይኑን
ፍቅር መሳለም አለበት ሌሊቱን እንዴት እንዳደረች ..
እንደ ወትሮው እሑድ ጠዋት ከመኝታ ክፍሉ ወጥቶ በኮሪዶሩ መስታወት በኩል ቁልቁል ይመለከታል ። አንዳንድ ልጃገረዶች ከመኝታ ክፍላቸው ወደ ቁርስ ክፍል መሔድ ጀምረዋል ጥቂት ቆይቶ የአቤል ዐይን የሚፈልጋት አጭር ጠይም ልጃገረድ ከሁለት ልጃገረዶች መሐል ሆና ብቅ አለች ። እንደ ሌላውኑ ጊዜ በነጠላ ጫማና በግዴለሽ አለባበስ አልነበረም የወጣችው ። ደምቃለች ፤የክት ልብሷን ለብሳለች ፤ከቁመቷም ከፍ ብላለች ። አቤል ቁልቁል ትክ ብሎ ተመለከታት። በዐይነ ሕሊናው ከመኝታ ክፍሏ ገብቶ ሻንጣዋን በረበረ ። ሳያያት ስለማይውል
ከቀን ብዛት ያሏትን ልብሶችና ጫማዎች ዓይነት ጠንቅቆ ያውቃል ። እንዲህ ዐይነት ጫማ ፈጽሞ አልነበራትም ፣ የተወሶ መሆኑን ገመተ።
“ ስፒል" ታኮ ያዋሰቻት ቤተልሔም ነበረች። ማርታና ቤተልሔም የጓደላትን መድመቂያ ሁሉ አሟልተው ፥ ኩል ቀብተው ሽቶ ረጭተው ፥ የከንፈር ቀለም ቀብተው ነበር ያወጧት ። ብቻ እንደነሱ በስሱ ቀይ የከንፈር ቀለም ላይ ቡና ዐይነት እንደርብልሽ ቢሏት ሳትስማማ ቀረችና ተዋት ቅንድቧንም አልላጭም ብላ አናደደቻቸው ። አረማመዷም
ያው ከደብረ ዘይት ይዛው የመጣችው ዐይነት ነበር ። በስፒል ታኮ መራመድ እምብዛም አልቻለችበትም ። ግን ብልህ
ስለ ሆነች ሚዛኗን እየጠበቀች ነበር እግሮቿን የምትወረውራቸው ። ማርታና ቤተልሔም አለባብሰዋት ከጨረሱ በኋላ
አንዳንድ ጉድለቶቿን አይተው “ ገና ይቀራታል ” በሚል መንፈስ እየተጠቃቀሱ ነበር የወጡት ። ለአቤል ግን በጣም
ደምቃበታለች ። “ የዛሬው ሌላ ነው የዋዛ አይደለም ” አለ በልቡ። ዐይኑ ቀስ በቀስ ደም እየመሰለ ሔደ ።። “የታባታቸው
ነው የሚወስዷት?” ሲል ለራሱ ተነፈሰ ። ሀለቱን ልጃገረዶች ደም ሥሩ ተገታትሮ ተመለከታቸው ። በተለይ ማርታን ...
ማርታ አቤልን ትወደዋለች ። የጓደኛዋ የዓይን ፍቅረኛ ስለሆነ በትምህርቱ ፡ ጎበዝ ነው ስለሚባል ፥ ወይም በሌላ
በየትኛው ምክንያት እንደሆን ራም አይገትባትም ። ግን ትወደዋለች ። ሳታየው መዋል አትፈልግም ።
አቤል ግን ማርታን አይወዳትም ሁልጊዜ ከትዕግሥት ስለማትለይ ታውቅብኛለች ብሎ ፈርቶ ፥ ከትዕግሥት ጋር ሆነው
ያሙኛል ። ይቦጭቁኛል ። ያሾፉብኛል ብሎ ጠርጥሮ ።ትዕግሥትን በደንብ እንዲያያትና እንዳይጠግባት የእሷ አብሮ
መሆን ያገደው መስሎት ! ትዕግሥትን ታባልግብኛለች ብሎ ፈርቶ ! ምክንያቱ በቅጡ አይገባውም ፤ ግን ለሁሉም ይጠላታል ። ሳያያት ቢውል ይመርጣል ።
አሁንም በልቡ ረገማት ። በቀሉት ዐይኖቹ ውስጥ እንባ የተቋጠረ መሰለውና ዐይኑን ጨመቀ ። ነገር ግን ውስጥ ውስጡን ከመቆጥቆጥ በቀር ጠብ ያለ ነገር አልነበረም።
ተከታትዬ መድረሻቸውን ማየት አለብኝ ! አለና ዛተ “ ተመስጦ ውስጥ ስለገባ አጠገባቸው ያለ ነበር የመሰለው። የሁለት ፎቅ ደረጃ መውረድ እንዳለበት የታየው ቁልቁል ጉዞ ሲጀምር ነው ።
በቅርብ ጊዜ እንዳመጣው ጸባይ እጁን ኪሱ ከቶ ተጀንኖ ሳይሆን ከሩጫ ባልተለየ ርምጃ ደረጃውን ወርዶ ወደ ውጭ ብቅ ሲል ከማርታና ትዕግሥት ጋር ዐይን ለዐይን ተገጣጠሙ ። ክው አለ ፤ እነሱም ክው አሉ ። ያጋጣሚ ጉዳይ ነው ። እሱ የገመተው ደረጃውን እስኪወርድ እነሱ
ብዙ አልፈው ይሔዳሉ ብሎ ከኋላቸው ሊከታተል ነበር ።ነገር ግን ቤተልሔም የሆነ ዕቃ ረስታ ወደ መኝታ ክፍል ስለ ተመለሰች ፥ ቆመው እየጠበቋት ነበር።
አቤል በድንጋጤ የሚሔድበት ጠፋው ። አይቶ እንዳላያቸው ቶሎ አለና ዐይኑን ሰበረ ። ከአካባቢው ለማምለጥ
ያህል ወደ ቀኙ ታጥፎ ባላሰበበት መንገድ ወደ ዋናው በር ተጓዘ ። ከአጥር ውጭ ቀድሞ መጠበቅ በድንገት የመጣለት ሃሳብ ነበር ፡፡
ምን እንዳው ይቺ ቤቲ ደሞ አይሞላላት ” አለች ማርታ ዐይኗን ወደ ሴቶች መኝታ ሕንጻ ወርውራ ።ትዕግሥትን ከሐሳባ ለማዘናጋት በድንገት የወረወረቻቸው
ቃላት ነበሩ ። አቤልን ካየችበት ሰዓት ጀምሮ የትዕግሥት ልብ ትርታ በድንጋጤም ይሁን በደስታ ምን ያህል ከፍ እንደሚል ማርታ ታውቃለች ።
ቤተልሔም ፊቷን ይቅርታ በሚጠይቅ ፈገግታ ሞልታ ፥ ቁና ቁና እየተነፈሰች መጣችላቸው ።
አዳር ነው እንዴ?” አለች ማርታ ፡ ከፊል ቀልድ ከፊል ንዴት በተቀላቀለበት አነጋገር ብዙ ስላቆየቻቸው በልቧ በሽቃለች።
ቤተልሔም ልማዷ ነው ። በጣም ስትደሰት ወይም ደንግጣ ስትረበሽ ጥቂት ትረሳለች ። ሽንቷ ደግሞ አሁንም አሁንም ይመጣል ግን ሽንት ቤት ትገባለች እንጂ ጥቂት ጭርር አርጋ ነው የምትወጣው ። በተለይ ወደ ፈተና ክፍል ልትገባ ስትል ፥ በግማሽ ሰዓት ውስጥ ሦስቴ ያህል ሽንት ቤት መድረስ አለባት ። አሁንም የሠርጉ
የደስታ ስሜት በውስጧ ስላለ ከመኝታ ክፍሏ የረሳችውን ዕቃ ከያዘች በኋላ ሽንት ቤቱን ለሁለተኛ ጊዜ ጎብኝታበት ነበር የመጣችው ። ተጠናቃ መውጣት ትፈልጋለች ፣ ግን የተጠናቀቀች አይመስላትም ።
“ በሉ እባካችሁ ይህን ግቢ ቶሎ እንልቀቅ ” አለች ማርታ ። “ ተማሪውኮ ወደ ቁርስ ቦታ መጉረፍ ጀምሮአል የተማሪዎቹን ትችት በመጠኑም ቢሆን ስለምትፈራ
እንዲህ ደምቃ በብዙ ተማሪ ፊት ማለፍ አልፈለገችም
ግቢውን ለቀው ሲወጡ፥ ትዕግሥት በዐይኗ ግራ ቀኙን እየማተረች ነበር አቤልን ፍለጋ ። ከደረጃ በወረደበት
ሰዓት በአጭር ጊዜ እይታም ቢሆን ስሜቱን በሚገባ ተረድታላች ። የቅናት የመጨስ ሁኔታ አይታበታለች ።እና
አሁን ተሸማቃ በዐይኗ ፈለገችው ፤ ብታየው እኔ ማርታን ከለላ አድርጋ የምትደብቀው ይመስል !
እሷ ልታየው አልቻለችም ።እሱ ግን ራቅ ካለ ቦታ ጥግ ይዞ እጁን በኪሱ አድርጎ ይመለከታቸው ነበር ። አስፋልቱን
ተሻገሩ ። በዐይኑ ተከተላቸው ። ቆመው ታክሲ ሲጠብቁ ትዕግሥት አቤልን ለማየት ፈለገች ። መጀመሪያ ማርታና
ቤተልሔም እንደማይነቁባት አረጋገጠች ከወደ መጡቡት አቅጣጫ ዘወር አለችና የሐውልቱን አካባቢ ቁስ ብላ መቃኘት ጀመረች ። እንዳጋጣሚ በእሷና በአቤል መካከል አንድ የምታውቀው ሰው ከፊት ለፊቷ ሲመጣ ተመለከተችና እጅዋን አውለበለበች ። አቤል ለሱ የተላከ መልእክት መሰለውና ከደስታ ብዛት እሚያደርገወ ነገር ጠፋው ። ከሰላምታው በተጨማሪ ሞቅ ያለ ፈዝግታ ሆን ብላ ለሱ ያሳየችው መሰለው ።
እንኳን በፈገግታ ጊዜ ይቅርና ገና ልትናገር ስትል ጉንጯ ምንኛ እንደሚሠረገድ ያውቃል ። መጀመሪያ ያያት ዕለት “ዲምፕሏ ታየ ! ሣቀች እኮ ! ሣቀች !” አለ በድንገት ፥ ድምፁን እንደ ማልጎምጎም ዐይነት አፈን አድርጎ ። ለአጭር ቁመቷ ተመጥኖ የሚያምረው እግሯ ለሱ ብቻ የተፈጠረ እሚመስለው ባቷና ተረከዟ በሐሳቡ ታየው ። ከፋይ
የሚመስለው ገጽታዋ እንደ ንጋት አድማስ እየፈካ የሳቂታ ዐይኖቹን ብርሃን ወደሱ ሲወረውር ታስበው ። እጆቹን ከኪሱ አወጣና አወራጫቸው ። ከዛ በኩራት መንፈስ ወገቡን ያዘ። “አዎን ልክ ነው ትሣቅ ! ትዕግሥት ብቻ ትሣቅ ያምርባታል ! ” አለ አሁንም አቤል ። ልክ እንዲህ ሲል ሳያስበው ራሱ መሣቅ ጀምሯል ። ከፊት

👍2
ለፊቱ ሕፃን ልጅ ያቀፈች ሴትዮ ታክሲ እየጠበቀች ነበር ። ታዲያ ባጋጣሚ ወደ አቤል ፊቷን ስትመልስ አቤል ያለ ምክንያት እያያት ሲሥቅ ደነገጠችና ፥ “በስማም” ብላ የሕፃኑን ፊት በነጠላዋ ለበስ አድርጋ ፥ በፈጣን እርምጃ ወደ ማዶ ተሻግረች ።
ትዕግሥት “ ሥቃ” ካበቃች ቆይታለች ። አቤል ግን አሁንም ችምችም ያለው ጥርሷና ስስ ከንፈሯ ይታየዋል •
“ ለምንድነው ግን ” አለ ለራሱ ። “ ለምንድነው ይሄን ውበት ለማንም የምታሳየው?! ” ደሞ ቅናቱ አገረሸበት ።
“ምን አስፈራህ አቤል ? ለምትወዳት ልጅ አንድ ቃል በመተንፈስ አቃተህ ! ምን መሰለችህ ? እርሷም ሰው ነችኮ ። ወጣት ነው ፤ ወጣት ነች። “ወደድኩሽ ማለት ምን ያስቸግራል ? “ደስ ትይኛለሽ” በላት ። እንቢ ብትልህኮ አትሞትም!. .
ልክ ይሄን ከማለቱ እነ ትዕግሥት ታክሲ አስቆሙና ገቡ ። መኪናው ተነሣ ። አቤል ኪሱን ዳበሰ ፤ ሠላሳ አምስት ሳንቲም ብቻ ነበረችበት ። በስሙኒዋ ሊፈርድባት አሰበ
ግን ወዴት?ራቅ ብሎ ስለ ነበር ። የት ብለው ታክሲውን እንዳስቆሙ መስማት አልቻለም ነበር ፤ በሸቀ ። ታክሲዋ ከዐይኑ እስክትርቅ ተከተላት። ቤተልሔምና ማርታ ከኋላ ወንበር ላይ ትዕግሥትን ከመሐከላቸው ነበር ያስቀመጧት ።
“ ሌቦች!” አላቸው በልቡ ንብረቱን ሠርቀውበት እንደ ሄዱ ሁሉ ።
ወደ ዩኒቨርስቲው ግቢ ተመልሶ መግባት አልፈለገም ።ግቢው አስጠላው። ቀጥታውን መንገድ ይዞ ሔደ ። የካቲት
12 ሆስፒታል ሲደርስ ለአፍታ ያህል ቆሞ ተመለከተ ፤እጁን በኪሱ አርጎ በመገረም ዐይነት እንቅስቃሴውን ቃኘ ።
ሆስፒታሉ በር ላይ ትርምስ ነው ። አዳሪ አስታማሚዎች በጋቢ ተጀቡነው በእንቅልፍ እጦት ተዳክመው አይናቸው ቀልቶ ይወጣሉ ፤ ጎብኝዎች ስንቅ ይዘው ወደ ውስጥ ይገባሉ ደፍ ደፍ እያሉ ፣ መግባት ያልተፈቀደላቸው ደግሞ
በሩ ላይ ተኮልኩለው ዘበኛውን ይለማመጣሉ ። ሆስፒታሉ በር አጠገብ ባለችው የፍራፍሬ መደብር መስኮት ላይ ብርቱካንና ሙዝ ገዥው ደርቷል ።
ቁርጡ ታዉቆለት “ሕመምተኛ” የተባለ ሰው የታደለ ነው ” ሲል አሰበ አቤል ። እንደዚህ ጎብኝዎች ይጎርፉለታል ። የሕመሙን ዐይነት ይጠይቁታል ፤ መድኃኒት ይፈልጉለታል ፤ ብቸኛ እንዳይሆን ወዳጅ ዘመዶቹ በፈረቃ
አጠገቡ ያድሩለታል ፣ ይውሉለታል ። ሕመሙ ያልታወቀለት ሰወ ግን ብቻውን ነው የሚሰቃየው ፤ የሚቃጠለው
የሚንገበገበው .. የትዕግሥትን ነገር ያለኔ ማን ያውቅልኛል ?. .
እስክንድር በድንገት ከኋላው መጥቶ ፥ “ ታዲያ ለምን ሕመምን አትነግረንም? ለምን መድኃኒቱን አንፈልግልህም
እኛ አንተን ለመርዳት አንሰን ነው?” የሚለው መሰለውና ከሐሳቡ ባነነ ። አጠገቡ ማንም ሰው አልነበረም ። ከራሱ ጋር እየተነታረከ ወደ አራት ኪሎ የሚወስደመውን ቀጥታ መንገድ
ይዞ ሄደ።
ለመሆኑ” ሲል ሐሳቡን ቀጠለ ። “ ለመሆኑ የሕመምተኝነት ምልክቱ ምንድን ነው ? አንድ ሰው ሕመምተኛ
ለመባል የግድ መቁሰል ፥ መንፈራገጥ ፡ ማቃሰት፡ መውደቅ መድማት ወይም አልጋ ላይ መቅረት አለበት እንዴ? ይህ
በግላጭ ካልታየ አይሆንም እንዴ በውስጥ መቁሰልም አለኮ ከውስጥ መድማትም አለኮ።
ሳያስበው እጁን አወራጨ ። አንዲት አሮጊት ብእጠገቡ ሲያልፉ አዩትና ወይ ልጄን ፥ እንደኔ ሐሳብ ገብቶታል ” አሉ
አልደነገጠም ። ቀና ብሎ አያቸውና ዝም ብሎአችሁ ሄደ።
አራት ኪሎ አደባባዩ ጋ ሲደርስ የትራፊክ መብራት እንደያዘው ሁሉ ቀጥ ብሎ ቆመ ቀጥታ መንግድ ቢሆን እግሩ እስካደረሰው ድረስ ዝም ብሎ ይቀጥል ነበር ። መስቀለኛ መንገድ ላይ መድረሱ ሐሳቡን ከፋፈለው ። ወዴት እንደሚሔድ ግራ ገባው ። ቁርስ ሳይቀምስ መውጣቱ ታወሰው ።እንዲያው ታወሰው እንጂ ሆዱ አልፈለገም ። “ምግብ ምን ያደርግልኛል ? ” እለ በሐሳቡ ፥ “ «ወስፋቴ ተከፍቶ አምሮኝ ካልበላሁ ምን ይጠቅመኛል ? እንዲያው ጥርሴንና
ጨጓራዬን ማድከም ነው ትርፉ ።
ወደ ፒያሳ የሚወስደውን መንገድ መርጦ ወደ ቀኙ ታጠፈ ። ጥቂት እንደ ተጓዘ። ከአንድ ቡና ቤት ወስጥ የሆነ ሙዚቃ ጆሮውን ጠለፈው ዘው ብሎ ገባ ጠዋት እንደ መሆኑ መጠን ያን ያህል ሰው አልነበረም ፤ የመልካሙ ተበጀ ዜማ በአዳራሹ ይንቆረቆራል
“ ኧረ መላ ምቱ ወዳጅ ዘመዶቼ
ዐይናአፋር ሆኛአለሁ ዐይን አፋር ኣይቼ
ሰላምታ አልሰጠኋት አላነጋገርኳት
በዐይን ብቻ እያየሁ አንድ ዓመት ወደድኳት ..
አሳላፊዋ በድንገት ከፊቱ ተገትራ፡ “ ምን ልታዘዝ ?” አለችው...
💥ይቀጥላል💥

#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)
አሁኑኑ መጀመር አለብኝ፤ እንደዋሸኋት ማወቅ የለባትም፡፡ ደስተኛ አድርጋኛለች፡፡ ላጣት ላስቀይማት አልፈልግም፡፡
“እኔ ምልህ ሃብትሽ...፣”
“ወዬ ያቤዝ፡፡”
“ባለፈው ስለ ዶሮ እርባታ ስራ አዋጭነት ስታወሩ ሰምቼ ነበር፡፡”
“አዎ፣ ምነው?”
“እኔም የራሴን ስራ መጀመር እያሰብኩ ነበር፡፡ አዋጭ ከሆነ አግዛችሁኝ እሱን ለምን አልጀምርም?”
“ጥሩ ሃሳብ ነው። ምን ችግር አለው ታዲያ? እናግዝሃለና፡፡ያውም በደስታ!”
ስራውን ለመጀመር ወሰንኩ፡፡ ቤት ኪራይ እንዲፈልጉልኝ ለነአሌክስ ነገርኳቸው፡፡፡ አዳሬ አድካሚ ስለነበር ሳላመሽ ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡ አልጋ ውስጥ ገብቼም የዶሮ እርባታውን ለመጀመር ሚያስፈልገኝን ገንዘብ በግምት አሰላለሁ፡፡ ስራው ገንዘብ ያስፈልገዋል
የቀረኝ ደግሞ ብዙም አያወላዳም፡፡ ከቤት ኪራይ ሌላ፣ እቃዎችን ጨምሮ
ሌላ ወጪዎች ይኖራሉ፡፡ ገንዘብ ያንሰኛል፡፡ ልበደረው የምችለው ሰው
ደግሞ የለም፡፡ መኪናዬን መሸጥ አለብኝ፡፡ ማሂ ቀድማኝ ደወለች፡፡ አንተ
በቃ ሰው ትዝም አይልህም?' ብላ ወቀሰችኝ፡፡ ለማስተባበል ሞከርኩ፡፡
የሰው ልጅ የህይወት ገመድ ግሩም ነው፣ እጅግም ውስብስብ፡፡ ህይወት ግን መኖር ሰልችቶኝ፣ ፍላጎቴ ጭላንጭል ብቻ ነበረች፡፡ እንደሚበራ ሻማ አይደለችም፡፡ ጭላንጭሉን በቀላሉ እፍ ብሎ ማጥፋት
አልተቻለኝም፡፡ ውስጤ ጨልሞ አስጨናቂና አስፈሪ ሃሳቦችን ብቻ
እንዳላመዠኩ፣ መኖር ከንቱ ልፋት ብሎ ጭንቅላቴ እየነዘነዘ ሰላም እንዳልነሳኝ፣ አሁን ደግሞ ይኸዉ፣ ቀኑንም ለሊቱን ከአንዲት ሴት ጋር የመኖርን አጓጊነት ያሳስበኛል፡፡ መኖርን ያጓጓኛል፡፡ የህይወቴን ገመድ ለመቀጠል ዶሮ እርባታ ስራ ለመጀመር እባዝናለሁ፡፡
ከሃኒ ጋር ጥሩ ተግባባን፡፡ በየቀኑ እንደዋወላለን፡፡ ባጋጣሚ ብንገናኝም፣ ሁለታችንም ሰው ተርበናል፡፡ ከነ አሌክስ ጋር አስተዋወኳት፡፡ እነሱም ወደዋታል። ቆንጅዬና ምርጥ ልጅ ናት፣አፍሰሃል ተባልኩ፡፡ በህይወቴ አዲስ እንደተወለደ ከእርሷ ጋር ማደርገው ሁሉ ብርቅና ልዩ ሆነብኝ፡፡ በየቀኑ በሚባል ሁኔታ እንገናኛለን፡፡ ስሜቴ እሷን ባየ ቁጥር ይለኮሳል፡፡ እናብዳለን፡፡ ዛሬ ግን፣ እንደከዚህ ቀደሙ ወደ አልጋ አልሮጥንም፡፡ ድሪም ላንድ ሪዞርት ሄደን ተቀመጥን፡፡ቢራችንን እየጠጣን፣ የረጋውን የቢሾፍቱን ሃይቅ ቁልቁል
እየተመከለከትን ከሃይቁ የሚነሳውን ገራም ንፋስ እየተቀበልን እንጨዋወታለን፡፡
“እኔ የምልህ ያቤዝ፣ ልነግርህ የምፈልገው ነገር አለኝ፡፡”
ስለኬ ጠራ፡፡ አሌክስ ነው፡፡ አነሳሁትና ሃኒ እንዳትሰማኝ ተነስቼ፣ ከእርሷ እራቅ ብዬ ማናገር ጀመርኩ፤ ለስራው ሚሆን ቤት
እንዳገኙልኝ፣ ኪራዩ በወር አራት ሺህ ብር እንደሆነ እና የስድስት ወር ቅድመ ክፍያ እንደሚፈልጉ፣ ከሃብትሽ ጋር ሄደው እንዳዩት፣ ፅድት ያለ ቤት እንደሆነና እንደወደዱት፣ ቶሎ ሄጄ እንዳየውና እንድከራየው ሲነግረኝ፣ ገንዘቡ በጣም ብዙ እንደሆነና ይህን ሚያህል ገንዘብ
እንደሌለኝ ነግሬው ስልኩን ዘጋሁት፡፡ ስመለስ፣
“ይቅርታ ስላቋረጥኩሽ ሃን፡፡”
“አይ ችግር የለውም፡፡ የሆነ ልነግርህ ምፈልገው ነገር ነበረኝ፤” በቀዘቀዘ ድምፅ፡፡
“ታዲያ ምንችግር አለው፣ ንገሪኛ፡፡”
“ስሜ ሃናን አይደለም፡፡ ማሂ ነው፤” ብላኝ አትኩራ ተመለከተችኝ፡፡
አልመለስኩላትም፡፡ የስም መመሳሰሉ አስደንግጦኝ ዝም አልኩኝ፡፡
“ስለዋሸሁህ በጣም ይቅርታ! ሌላም የዋሸሁህ ነገር አለ፡፡”
“ምንድን ነው?” ውስጤን ፍራት ወረረኝ፡፡ ማላቃትን ልጅ ነው እንዴ የወደድኩት ብዬ አሰብኩ፡፡ መጥፎ ነገር እንዳይሆን
ተመኘሁ፡፡
“ፊልም ነው ምሰራው ያልኩህ...”
“እና ምንድን ነው የምትሰሪው...?”
“አሜሪካ ነበርኩኝ፤ አሁን ትቼው መጥቼ ነው::”
“ለምንድን ነው ትተሽው የመጣሽው..?
“ከዚህ ስሄድም ሳልፈልገው፣ በድንገት ነው የሄድኩት፡፡ የአዋላጅ ነርስ ነኝ፤ እዚህ ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ውጪ ስለመሄድ አስቤም፣ ጓጉቼም አላውቅም፡፡ ፍቅረኛ ነበረኝ፡፡ እርሱ ደግሞ በተቃራኒው፣ ህልሙ አሜሪካ ነበረች፡፡ እዚህ እየኖረ ነበር ማለት ይከብዳል፡፡ ፌርማታ ጋር ቁጭ ብሎ ባስ እነደሚጠብቅ ሰው፣ አሜሪካ እስኪሄድ ሲጠባበቅ ነበር፡፡ አሜሪካ ለመሄድ ያልሞከረው ነገር የለም፡፡ አንድ ዓመት ላይ ዲቪ ሲከፈት፣
አብረን እንሙላ አለኝ፡፡ ሞልቼ አላውቅም፣ ትዝም አይለኝ ነበር፡፡ እንደባልና ሚስት ሞላን፣ ባጋጣሚ ደረስን፡፡ ብዙ ሰው እንድለኛ ነሽ አለኝ፡፡ እልል ተባለ። በተለይ ነርስ መሆኔ ብዙ እንደሚጠቅመኝ ነገሩኝ፡፡ፕሮሰሱን ጨርሰን አሜሪካ ገባን፡፡
እንደሄድን ከጓደኛዬ ቀድሜ እኔ ቶሎ ስራ አገኘሁ፡፡ ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል፡፡ ጓደኛዬም ብዙም አልቆየም፣ ሌላ ስቴት ላይ ስራ አገኘ፡፡ አንድ መጋዘን ውስጥ ተቆጣጣሪ ሆኖ ተቀጠረ፡፡ በመጀመሪያ ሁሉ ነገር ደስ ብሎኝ ነበር፡፡ የሆስፒታሉ ንፅህና፣
አደረጃጀት፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ክፍያው፣ ብቻ ሁሉም ነገር በጣም ደስ አለኝ፡፡ ከተወሰነ ግዜ በኋላ፣ እርሱም ቢዚ እየሆነ፣ መገናኘት እየከበደ፣ ይናፍቀኝ ጀመር፡፡ እርሱ፣ በትርፍ ሰዓቱ ሌላ ተጨማሪ ስራ መስራት ሲጀመር፣ የምንገናኝበት ጊዜ በጣም ቀነሰ፡፡ ከሳምንታት ወደ ወራት ረዘመ:: ሲደውልልኝም፣ ከድምፁ የምሰማው ናፈቆት ሳይሆን ድካምና መሰልቸት ሆነ፡፡ ለእኔ ቦታ እንደሌለው እየተሰማኝ መጣ፡፡ ብዙ እንጨቃጨቅ፤ እንጣላ ጀመርን፡፡ አትወደኝም እለዋለሁ፤ አትረጂኝም፤
ይለኛል። ሲኒማ እንኳ ከሰው ጋር መግባት ናፈቀኝ፡፡ ማውቃቸው ሰዎች ጋር ደውዬ ሲኒማ እንግባ ስላቸው፣ እስቲ ፕሮግራም ልይ ይሉና፣
(Next Month the last Sundayi am free, we can meet and do it)
የሚቀጥለው ወር የመጨረሻው እሁድ እረፍት ነኝ፣ መገናኝት እንችላለን
ይሉኛል፡፡
እኔ ደግሞ ሰው ነው የራበኝ፡፡ እረሃብ ደግሞ ግዜ አይሰጥም፡፡ሰው ስናፈቀኝ በሁለት ወር ሰው ማግኘት ሰለቸኝ፡፡ ስሜት አልባ በሆኑ፣ በቁሳዊ ነገሮች በሚደሰቱ ሰዎች ብቻ የተከበብኩ ያህል ተሰማኝ፡፡ ጓደኛዬ ከኔ ይልቅ፣ ፍቅር ያለውጠ ለዳላር ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ሁሉም machine
people, with machine brain and machine hearts መስለው ታዩኝ፡፡
የሰው ተፈጥሮ የሌላቸው በውስጣቸው፣ የሰው ፍቅር ርሀብ ማይሰማቸው፣ ዓለምን አስደናቂ፣ ግሩምና ሳቢ የሚደርጓት ቁሶች
ሳይሆኑ፣ ሰውና ተፈጥሮ እንደሆኑ ያልገባቸው ሮሆቦት ሆኑብኝ፡፡ በሰው
መሀል ሆኜ ሰው እራበኝ፡፡ ጥዬው መጣሁ፡፡”
በትካዜ ስሜት ውስጥ ሆና አወራችኝ፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች ዝም አለች፡፡ ደስተኛ ትመስለኝ ነበር፣ ንፁህ ያልደማ ልብ ያላት። ከትረካዋ እርሷም ቁስለኛ እንደሆነች ተረዳሁ፡፡ ላቋርጣት አልፈለኩም፡፡ይውጣላት፡፡ ትተንፍስ ብዬ፣ ዝም አልኳት፡፡ ቀጠለች፡፡
“ለእኔ ህይወት ቁስ አይደለም፣ ማፍቀር ነው! To live is love”! ከጓደኛዬ ተጣላን፡፡ የአሜሪካ ኑሮ በእኔ ዕይን፣ እድሜህን ለመቼ እንደሆነ ለማይታውቀው ነገ ቁስ እየሰበሰብክ፣ ዛሬህን የምታባክንበት ህይወት ነው፡፡ የእኔ ሀገር እዛ አይደለም! ወሰንኩ፡፡ ግን፣ ከባድ ውሳኔ፡፡ብነግራቸው፣ ባስረዳቸው ሚረዳኝ አጣሁ፡፡ ጭራሽ እንደ እብድ ቆጠሩኝ፡፡ጥዬው መጣሁ፡፡ ከመጣሁ አስር ወር አለፈኝ፡፡ እዚህ ስራ ለመጀመር
ወስኜ ነው የተመለስኩት፡፡ ውሳኔዬ ማንንም ደስተኛ አላደረገም፡፡ቤተሰብ፣ ጎሮቤት፣ ጓደኛ፡፡ ሁሉም በእራሳቸው ምኞት፣ ለክተው እያሰቡና እየመዘኑ ስህተት ነሽ ይሉኛል፡፡ ሊመክሩኝ፣ ሊያሳምኑኝ ይጨቀጭቁኛል

👍5
እዚህ ከእንደገና ስራ መጀመር እንዳሰብኩት ቀላል አልሆነም፡፡
የሙያ ፍቃድሽ መታደስ አለበት፤ ግዜው አልፏል አሉኝ፡፡ የማሳደሱ ሂደት እራሱ ከባድ ሆነ፡፡ ከተወሰነ ግዜ በኋላ፣ ስራ ፈትቼ መቀመጤን ተንተርሰው ያስጨንቁኝ ጀመር፡፡ ሰለቹኝ፡፡ ስራ እስክጀምር፣ ጊዜያዊ መደበቂያ አስፈለገኝ፡፡ አንዷ ጓደኛዬ ይህን ቤት አሳየችኝ፡፡ እንደ አጋጣሚ የተዋወቅን ቀን ለመጀመሪያ ግዜ ብቻዬን መጣሁ። አንተን ተዋወኩ፡፡
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
የሙያ ፍቃድሽ መታደስ አለበት፤ ግዜው አልፏል አሉኝ፡፡ የማሳደሱ ሂደት እራሱ ከባድ ሆነ፡፡ ከተወሰነ ግዜ በኋላ፣ ስራ ፈትቼ መቀመጤን ተንተርሰው ያስጨንቁኝ ጀመር፡፡ ሰለቹኝ፡፡ ስራ እስክጀምር፣ ጊዜያዊ መደበቂያ አስፈለገኝ፡፡ አንዷ ጓደኛዬ ይህን ቤት አሳየችኝ፡፡ እንደ አጋጣሚ የተዋወቅን ቀን ለመጀመሪያ ግዜ ብቻዬን መጣሁ። አንተን ተዋወኩ፡፡
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
#ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
“ ኧረ መላ ምቱ ወዳጅ ዘመዶቼ
ዐይናፋር ሆኛአለሁ ዐይን አፋር አይቼ
ሰላምታ አልሰጠኋት አላነጋገርኳት
በዐይን ብቻ እያየሁ አንድ ዓመት ወደድኳት ..
አሳላፊዋ በድንገት ከፊቱ ተገትራ፡ “ ምን ልታዘዝ ?”አለችው
“ ሻይ # ሻይ ! ” አላት አቤል በሙዚቃው ጣልቃ ስለ ገባችበት ከአጠገቡ እንድትሔድለት ተቻኩሎ
“ ..... ዐይኔ ተወርውሮ ዐይኗ ላይ ካረፈ
ድፍን ዓመታችን መጋቢት አለፈ
ሰላምታ አልሰጠኋት ኣላነጋግርኳት
በዐይኔ ብቻ እያየው አንድ ዓመት ወደድኳት
ኧረ መላ ምቱ ወዳጅ ዘመዶቼ
አይናፋር ሆኛአለሁ አይናፋር አይቼ ..
አሳላፊዋ ሻዩን ይዛ ስትመጣ የመልካሙ ጨዋታ አልቆ የመዝጊያው ዜማ ነበር የቀረው ። ሻዩን አጠገቡ ስታስቀምጥለት
አቤል ዐይን ዐይኗን በልመና አይነት እየተመለከተ
“ እባክሽ ይሄን ዘፈን ድገሙት ቢያቸው ” አላት ።
ከሬዲዮ እኮ ነወ የሚተላለፈው የእሁድ ጠዋት “ ፕሮግራም ” አለችው ።
ሽምቅቅ ብሎ በዝምታ ሻዩን እያማሰለ አሳላፌዋ ተመልሳ ልትሔድ ስትል ጠራትና
እሺ ክሩ እናንተጋ የለም ? ” ሲል ጠየቃት
“ እንጃ!” በማለት አይነት ትከሻዋን ነቅንቃ ከንፈሯን አጣማ ፡ በቂ መልስ ሳትሰጠው ሔደች ።
""ሸርሙጣ!” አላት በልቡ ፥ “ ይሄኔ ውስኪ ቢሆን ኖሮ የመልካውን ክር ቀርቶ ማጫወቻውን ከነነፍሱ አጠገቤ
ታመጣልኝ ነበር ሻይ የሚጠጣ ግን እንግዳ አይደለም !ደሃ ምንም ነገር መምረጥ አይችልም ማለት ነው?”
አሳላፊዋ ከመጠጥ መደርደሪያው አጠገብ ባንኮኒወሎን ተደግፋ እንደ ቆመች አቤል በክፉ ዐይኑ አያት። እሱ እንደዚህ የተናደደበትን ጉዳይ እሷ በአእምሮዋ ውስጥ ቦታም አልሰጠችው እምቢታዋ እሱን እንደ ጎዱ አልታመቃትም። ይልቅ የሚያያት ለሌላ ነገር ፈልጎአት መሰላትና እሷም ታየው ጀመር። ድርቅ ብላ ዐይኗን ሳትነቅል አየችው ። ይሄኔ አቤል እንደ መሸማቀቅ ብሎ ዐይኑን ሰበረ ። ጥቂት ቆይቶ
እንደ ገና ቀና ሲልም ዐይኗን ከሱ ላይ አላነሣችም ። ይኸኛውም አስተያየቷ ግን ፈገግታም ታክሎበት ነበር ።
አቤል የአሳላፊዋን የገበያ (ፍለጋ) ፈገግታ በሌላ ተረጎመው ። “ የዐይን ፍቅር” ዜማ እንዲደገምለት በመጠየቁ
የውስጥ ቁስሉን ዐውቃበት የምትሥቅበት መሰለውና አፈራት ። አሥራ አምስት ሳንቲሙን ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦላት ፈትለክ ብሎ ወጣ ።
ከኋላው ገረመመችው ። በዝግታ የመልካሙን ዜማ እያፏጨ ' በልቡ ግጥሙን እየደጋገመና ከራሱ ስሜት ጋር
እያያያዘ መንገዱን ቀጠለ ።
... ሰላምታ አልሰጠኋት ፥ አላነጋገርኳት
በአይኔ ብቻ እያየሁ ሁለት ወር ወደድኳት
ዐይኔ ተወርውሮ ዐይኗ ላይ ካረፈ
ድፍን ሁለት ወሬ ታኅሣሥ ፀለፈ”
አንድ ስሜት ከውስጡ ተሰማው ። የደስታ ወይም የሀዘን ብሎ መተርጎም ያዳግታል ብቻ የሚፈጥረው ስሜት ነው በሙዚቃ ኃይል የልብ ቁስል ሲፈነቀል እያመመ
እየወጋ እየቆረጠ ደስ የሚል ስሜት ይሰማል ።
“ ሙዚቃ የሕይወት ማዳበሪያ ነው” ሲል አሰበ ኤቤል ።“ሙዚቃ ምግብ ኔው ። ሙዚቃ የምስጢር ጓደኛ ነው፤ሙዚቃ
መዝናኛ ነው ። ሙዚቃ ሁሉንም ነው ። ”
የሁለተኛ ዓመት ተማሪ በነበረበት ጊዜ፡የሚያውቀው አንድ ሰው መንገዱ ላይ አገኘ ። ቀድሞውንም በዕድሜ በሰል
ያለ ሰው ነበር ። አሁን ደግሞ ይብስ በኑሮ የተጎሳቋቆለ ይመስላል
“ታዲያስ ጃል እንደምን አለህ ? ” አለ ሰውዬው የአቤልን እጅ አጥብቆ ጨብጦ ሁለቱም ስሞቻቸውኝ ተረሳስተዋል።
ደህና ነኝ ፣ መቼስ አለ አቤል ፥ በተሰላቸ አነጋግር። «ትምህርትስ እንዴት ነው?”
አቤል ይህን ጥያቄ ሲጠይቁት አይወድም ። ነገር ግን ከማንኛውም ሰው የሚቀርብለት የመጀመሪያ ጥያቄ ይሄው ነው። ሰዎች ለምን ይሄን እንደሚጠይቁ አይግባውም።
ትምህርት እያቅለሽለሽኝ እጅ ነው እባክህ ? ” አለ አቤል።ምን ያህል እንደ ተሰማው ለማሳየት ፊቱን ኮሶ አስመስሎ
“ እንዲህ አትበል እባክህ ” አለ ሰውዬው የውስጥ ስሜቱን በሚገልጽ አነጋገር ። “ የሥራ ዓለም እንዴት እንደሚያቅለሸልሽ ባየኸው ። እኔ ትምህርቴን አቋርጨ ሥራ
የገባሁበትን ቀን እየረገምኩ ነው ። የዛሬ ገንዘብ እንደሆን አንዱንም ቀዳዳ በቅጡ አይሽፍንልህ ። ትርፉ ስም ብቻ ነው ። ኧረ ተማሪነት በስንት ጣዕሙ ! ”
ሁሉም ያለበትን እንደ ረገመ ነው ” አለ አቤል በልቡ ተማሪው ሠራተኛ መሆን ይፈልጋል ፥ ሠራተኛው ደግሞ፥ ወደ ተማሪነት መመለስ ይሻል ፤ወጣቱ ያለዕድሜው እንደ አዛውንቱ መጀነንና መከበር ይፈልጋል ፤ ሽሜው ደግሞ "እንደ ወጣቶች ጉርድ ሸሚዝ ለብሶ መለወጥ ፥ መታደስ መሻሻል ይፈልጋል ። ለውጥ የሕይወት ቅመም ናት ይባል የለ ፤ አዲስ ነገርንና ለውጥን መመኘት መቼም የህልውና ምልክት ነው ። ግን የያዘውን ወዶ ባለበት የሚኮራና የሚመካ ሰው ማን ይሆን? ብርቱ ሰው ማለት እሱ ነው
ሰወዬው ከአቤል ጥያቄም ሆነ መልስ በማጣቱ በርታ እንግዲህ ምን አንተማ ግማሽ “ ሴሚስቴር” ነች የቀረችህ ። ተገላገልክ ” አለና ለመለያየት ጨበጠው
አቤል መርሳት የሚፈልገውን የሚሸሸውን የሚርቀውን የትምህርት አርዕስት ስላነሣበት ሰወዬውን ጠላው እስከሚለያዩ ተቻኩሎ ነበር ። እንደ ፈራውም አልቀረ ። የትምህርቱን ጉዳይ አንሥቶ የገዛ ሕሊናው ይሞግተው ጀመር
መጨረስ አለብህ ! በትዕግሥት ይህቺን ስድስት ወር መጨረስ አለብህ ፤ ደግሞም ትንሽ ነው የቀረህ ፤ ያልቃል።
“ አይመስለኝም ! መጨረስ የምትችል አይመስለኝም ።ቁም ነገሩ የጊዜው ወይም የኮርሱ ማነስና መብዛት አይደለም።ትንሽም ነገር ቢሆን ጨራሽ ይፈልጋል ። በራሱ ኃይል አያልቅም ። ፋብሪካ ውስጥ ኤሌክትሪክ ከጠፋ ምርቱ ትንሽ ትልቅ ሳይል መቆም አለበት እኔም በትምህርት ረገድ የአእምሮዬ ኤሌክትሪክ ጠፍቷል ። ”
አትቀልድ እባክህ ፥ በራስህ አትቀልድ ። ለማይረባ ጊዜያዊ ስሜትህ ተንበርክከህ አንተንም ወላጆችህንም አትጉዳ።
“አልቀለድኩም ። ለምን እቀልዳለሁ ? ከቶውንም በሕይወትና በፍቅር ቀልድ የለም ። ወላጆችም የራሳቸው ጉዳይ ነው።
የራሳቸው ጉዳይ አይደለም ። የአንተም ጉዳይ ነው ።እነሱ በደሃ አቅማቸው ለፍተው ጥረው ግረው እዚህ አድርሰዉሃል ። አሁን ሽምግለዋል ። የአንተኑ እጅ ጠባቂዎች ናቸው ። አስብ ፥ ካላንተ ማን አላቸው?”
“ እንጃ! አላውቅም !! እንጃ ! እንጃ ! እንጃ ! እንጃ !”« የማያውቅ ፡ የማያስብ አንጥሮ የሚመልስ ድንጋይ ብቻነው» ከሙሉ አእምሮ ጋር የተፈጠረ “ እንጃ” ማለት አይችልም ።
“ እንጃ አላውቅም ! እንጃ ! እሷ ትጠየቅ ! እሷ እሷ !”
ማነች እሷ ? ! ”
“ ጠይሟ አጭሯ ልጅ ስትሥቅ ጉንጮቿ የሚሠረትጉዱት ። ትዕግሥት ... ትዕግሥት ... ትዕግሥት ...
ትዕግሥት ስላንተ ምን አገባት ? ልታስብእት ፥ ልትጨነቅለት " ልታስታምመው የሚገባት እሷም የራሷ ሕይወት አላት እናም ስላንተ..
እንዴት አያገባትም ? እንዴት? ያ ይሄ ሁሉ ችግር በማን ተፈጠረና እኮ እንዴት አያገባትም ? ! ...”
።።።።
ዕድምተኞቹ ከወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ ! ሽር ጉድ ይላሉ ። ዘመድ አዝማድ የቤት ልሱን ለብሶ ውጭ ውጭውን ያያል ። ከበሮው ከምሽቱ ጀምሮ አልቆመም ሌሊቱን አድሮበት ቀኑንም ውሎበታል ። አውራጆቹ ግጥም ደርዳሪዎቹ ድማፃቸው ቢደክምም ። ቢጎረናም አላቋረጡም ።
የሙሽራ ቤት ደንብ ነው። ሙሽሪት ቤቱን ለቃ እስክትሔድ ወይም እስክትወሰድ ድረስ መድመቅ አለበት ። ከዚያ በኋላ
ጭር ይላል ። ዘመድ ኣዝማድ ብቻ ቀርቶ የተሰበረ ብርጭቆ ይቆጥራል ፤ ወጪና ገቢውን ያሰላል።ክምር ትራፊ እንጀራ
ከሰሃን

ሰሃን ያገላብጣል ። ቀኑ የትርምስና የደማቅ ትርኢት መድረክ ሆኖ ነው የዋለው ። ድንኳኑ አፉን ከፍቶ ሲያዛጋ
ያድራል ውሾች ያንዣብቡበታል ። ለሙሽሪትና ለሙሽራ ብቻ ተነጥፎ የዋለው የሥጋጃ ምንጣፍ የልጆች መቦ
ረቂያ ይሆናል ። እስከዚያው ግን ከበሮው እየተደለቀ ነው እንግዶቹ እየተንቻቹ ናቸው
“ ምን ዐይነቱ ባለጌ ነው ?” አለች ማርታ ሙሽራወይን በመተቸት ዐይነት ። “ ዘጠኝ ሰዓት ሊሞላኝ ኮ ነው " ።እንዴት እስካሁን አይመጣም? ! ” ዘመድም ባትሆን የሙሽሪት ጓደኛ በመሆኗ ተቆርቁራለች ።
“ እሷ ትሆናለቻ ያገባችው የዘንድሮ “ ባልኮ ችግር ነው ” አለች ቤተልሔም የሙሽራውን መዘግየት በኩራትና ንቀት ተርጉማው ጀልፋይ እንዴት እባክሽ ? ” አለች ማርታ በመቆርቆር ዐይነት « ለዘንድሮ ወንድ ? ይልቅ እንዲህ እያላችሁ የልብልብ አትስጡአቸው ።
ቤተልሔም ዝም አለች ።
“ ሆሆ ! እንግዶቹ” ኮ አንቃቃችሁ ” አለችና ማርታ በንዴት ራሷን ነቀነቀች «ሙሽራው ገና ስላልመጣ
ለእንግዶቹ መጠጥ እንጂ ምግብ አልቀረበም ነበር "
ትእግስት ይህ ሁሉ አላስጨነቃትም። ከነቤተልሔም ጋር ወደ አምስት ሰዓት አካባቢ ወጥሰሪዎች ቁርስ ስላቀመሱ
ብዙም አልራባትም ። ሁለቱ ጓደኞቹ ለመሽሪት ባላቸው ቅርበት የተነሣ አንዴ ጓዳ አንዴ ድንኳን፡ ሽር ጉድ እያሉ እሷን ብቸኛ ስላደረጓት ፥ ጥላቸው ወደ ዘፈኑ ከተቀላቀለች ቆይታለች። የሠርጉ ዘፈን ደስ ብሏታል ። አንዴ በሐሳብ መርከብ እያንሳፈፈ ወደኋላ መልሶ የደብረዘይትን ሙሽሮች ያስቆጥራታል ።አንዴ ደግሞ የራሷን የወደፊት የቀን ሕልም እያሳለመ ያስቦርቃታል ። በተለይ ዜማ የሚያወርዱት ጠና ያሉ ሴትዮ ሁኔታቸው አስገርሞአት ትክ ብላ ታያቸዋለች ።
ሁሎም ከወዲያ ወዲህ “ እትዬ ሙቀጫ” ይላቸዋል ። አጭር ሆነው ዶርፎጭ ስልሉ ነው መሰል ይህ ስም የወጣላቸው
በዘፈኑ ቦታ ኮከብ ናቸው ፤ከበሮውንም ሲይዙት ዜማውንም ሲያወርዱት ይደምቅላቸዋል ። እሳቸው ሲያወርዱ እጁን ሰበሰበ የሚቀመጥ ካዩ የፈረደበት ነው ። ሁሉም ባለ በሌለ ኃይል ያጨበጭባል ።
በዚህ ሁሉ ትርኢት መሐል የከበሮውን ድምፅ አሸንፎ የአውራጆቹን ዜማ ውጦ ዕድምተኞቹን በረጋግዶ በር ላይ የቆመውን የጥሪ ወረቀት ተመልካች ዘብ ጥሶ አቤል በትዕግሥት ሐሳብ ውስጥ ከተፍ አለ ።
ዐይኗን ቦዘዝ እንዳረገች ከሰርጉ ቦታ ወደ ካምፓስ “ተጓዘች ... ከጓደኞቿ ጋር ተቀምጣ የምታጠናበት ዋርካ ለምለም ሣር በሐሳቧ ታያት ። የአቤል ዐይን ፍቅር በየሔደችበት ሲነሣባት በመኝታ ክፍል ፣ የምግብ ኣዳራሽ አቤል ... አቤል አቤል ! በተለይ ማርታ ። ማርታ ያለሱ ወሬ የላትም ። “ እኔ እሱን ብሆን ኖሮ እንደሱ ጭንቅላት ቢረኝ ሜዲሲን ወይም ኢንጂነሪንግ » ነበር የማጠናው
ያለቻት ትዝ አላት ። ማርታ ግን ለምን እንዲህ አለች ። አቤልን ሁልጊዜ ማድነቅ ለምን ደስ ይላታል ? በልቧኮ ሳትወደው አትቀርም ... ትንሽ ትንሽም ቢሆን ሳይናፍቃት አይቀርም ። አለዚያ ለምን ደጋግማ ታነሣሰች ? ይገርማል !እንዲያው ነገሩን አልኩ እንጂ ፥ የሰው ሁናቴ ገርሞኝ ነው እንጂ " እኔማ ምን ጨነቀኝ ? ታዲያ አቤል ማርታን አይወዳትም ። ራሷው ናት ደሞ አይወደኝም እምትለው ። መቼም
እርግጠኛ ነኝ አፍ አውጥቶ አልወድሽም እላላትም ። እሱ ለራሱ መች ይናገርና....

#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ(MD)
ባለፈው ስናወራ፣ ሰው ሞልቶ፣ ሰው ሲጠፋ ምን ይደረግ ስትለኝ፣እንደኔው ሰው እንደራበህ ተሰማኝ፡፡ ሁሉም እንዲሆን በደስታ ፈቀድኩልህ፡፡ እንዲህ እንግባባለን ብዬ ስላልገመትኩ የውሸት ስምና ስራ ፈጥሬ ተዋወኩህ፡፡ ለዛ ነበር የዋሸሁህ፡፡” ዝም አልኳት፡፡
“በቃ ይሄው ነው፤” አለችኝ፡፡
“አንድ ነገር ልንገርሽ”
“እሺ ንገረኝ፡፡"
“ስለዋሸሽኝ አልተቀየምኩሽም፡፡ ግን እኔ ካሁን በኋላም ቢሆን፣ሃኒ ብዬ ነው ምጠራሽ፡፡ ማሂ ሚባል ስም ቆሌዬ አይወደውም፡፡”
“ኪ.ኪ.ኪ...፣ እሺ ባክህ፣ ባለ ቆሌ፣ አንተ ደስ እንዳለህ ጥራኝ፡፡” በአንዴ ፊቷ ከትካዜ ተላቀቀ፡፡ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳትና “ሃኒዬ፣ ያደረግሺው ሁላ፣ ትክክል ነው፡፡ ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰንሽው፡፡ ህይወት አንዴ ናት፡፡
አትደገምም፡፡ የአዕምሮ ደስታን፣የመንፈስ እርካታን የማይፈጥሩልሽን ቁሶች ስትሰበስቢ፣ ነብስሽ የምትሻውን ሳታገኚና ሳታጣጥሚ ለመሞት፣መኖር የለብሽም፡፡ ሚዛኑን መጠበቅ አስፈላጊ ነው!መኪና፣ ቤትና፣ሌሎች ቁሶች፣ ቋሚ ደስታ ሚፈጥሩ ሚመስሏቸው፣ እነርሱ ሳይገባቸው ሊያስረዱሽ የሚሞክሩ፣ ስላላዩት ሀገር የሚያወሩሽ፣ ሳይደርሱበት በርቀት እያዩ፣ በምኞት እረሀብ የሚቃጠሉና የሚቃዡ ናቸው፡፡ ተያቸው፡፡ ግራ ገብቷቸው ነው፣ ግራ ሚያጋቡሽ፡፡ እርሻቸው።” ፊቷ ላይ የደስታ ብርሃን
መፈንጠቅ ጀመረ፡፡
ጭምቅ አድርጋ አቀፈችኝ፡፡ “ያቡዬ ስለተረዳኸኝ በጣም አመሰግናለሁ!! አንተ ትክክል ነሽ፣ ያልከኝ የመጀመሪያው ሰው ነህ።እራሴን መጠራጠር ጀምሬ ነበር፡፡ ከረጅም ጊዜ በኋላ ትክክል እንደሆንኩ
እንዲሰማኝ አደረከኝ፡፡ ካገኘሁህ ቀን ጀምሮ ጥሩ እንዲስማኝ አድርገኸኛል። እወድሃለው፡፡”
ግንባሯን ሳምኳትና፣ “ደስተኛ እንደሆንሽ ስለነገርሽኝ፣አመሰግናለሁ፡፡ እኔም፣ በህይወቴ ተሰምቶኝ የማላውቀውን ደስታ
ሰጥተሽኛል፡፡ አንቺ በጣም ልዩ ሴት ነሽ፡፡ ስላንቺ በደንብ አስብያለሁ፡፡እንደዚህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም፣ የልቤ ንግስት አንጓነሽ፡፡ መቼም በምንም ምክንያት ላጣሽ አልፈልግም፡፡ ከአሁን በኋላ ሁሌም፣ በሁሉም ነገር አብሬሽ ነኝ፡፡ አንቺን ለማስደሰት ምንም አደርጋለሁ፡፡ ምንም!፡፡ አንቺ ለእኔ ልዩ ስጦታዬ ነሽ፡፡ ቀኑ ሲደርስ፣እኔም እንዳንቺ ሙሉ ታሪኬን እነግርሻለሁ። እስከዛው ግን እጅግ በጣም እወድሻለሁ፡፡” እንደዚህ የውስጥ ስሜታችንን ስናወራ አምሽተን ሸኘኋት፡፡
ከሃኒ ጋር በተደጋጋሚ እንገናኛለን፡፡ ሲከፋት፣ ሚረዳት ስታጣ እኔ ጋር ትደውላለች፡፡ የሙያ ፍቃዷ ስለተቃጠለ፣ ስራ መጀመር ከብዷታል፡፡ ቤተሰብ ደግሞ፣ በስራ መፍታቷ አመካኝቶ ያንገበግቧታል።ውሳኔዋ ስህተት እንደነበር እንድታምን በአሽሙር ይወጓታል፡፡ ተከፍታ መጥታ እኔ ጋር አምሽታ ሁሉን እረስታ ወደቤቷ ትመለሳለች። እኔም በእርሷ በጣም ደስተኛ ሆኛለሁ። የእኔ መኖር የሚጠቅመው፣ሚያስፈልገው ህይወት አገኘሁ፡፡ ተደስታ ስትሄድ ማላውቀው ደስታ ውስጤን ይሰማኛል። ስለሷ ማሰብ የህይወቴ ዋና ክፍል ሆኗል፡፡
ከእርሷ ጋር መኖርን ያጓጓኛል። አሁን መኖር አለብኝ፡፡ህይወቴን ሙሉ እርሷን ደስተኛ እያደረኩ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ የሃኒ
ተስፋዋ፣ መከታዋ እኔ ነኝ፡፡ በየቀኑ ከምትነግረኝ ብሶት ልገላግላት ምችለው እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ሆቴል ቁጭ ብዬ፣ ገቢ የሌለው ወጪ ብቻ የሆነ፣ ተስፋ የቆረጠ ሰው ንሮዬን አብቅቼ፣ ሰው ሆኜ ለእርሷም
ለመትረፍ በፍጥነት ስራ መጀመር አለብኝ፡፡ የዶሮ እርባታውን ስራ
ማፍጠን አለብኝ፡፡ መነሻ ስንት ብር ያስፈልገኝ ይሆን? አሌክስ ባለፈው
የነገረኝ የቤት ኪራይ ውድ ነው፡፡ ሌላስ የምን ወጪ አለ? ሃብታሙን ደውዬ ያለበት ቦታ ሄጄ አገኘሁት፡፡ ጭንቅላቴ ወር ሙሉ ሲያንቀላፋ ከርሞ፣ አሁን ያጣድፈኝ ጀመር፡፡ እንዳገኘሁት በቀጥታ ወደ ጉዳዩ
ገባሁ፡፡
“ሃብትሽ ያን ጉዳይ ዝም አላችሁኝ እኮ፡”
“የቱን ነው ያቤዝ?”
“የዶሮ ስራውን ነዋ፡፡ ጭራሽ በኛ ጣለው ብላችሁ ዝም አላችሁኝኮ፡፡”
“እ...፣ እሱንማ አንተው ነህ ዝም ያልከው፡፡ ባለፈው አሌክስ ቤት አገኘን ሲልህ፣ ሄደህ እንኳ አላይ ስትል የተውከው መሰለን፡፡”
“እሱኮ ውድ ሆኖብኝ ነው ሃብትሽዬ፡፡”
እሺ፣ ምን አይነት ዶሮ ነው ማርባት ምትፈልገው?”
“ማለት? ዶሮ ነዋ፡፡ ዶሮ ምን አይነት አለው?”
“አለው እንጂ ፤ የስጋ ዶሮ ነው፣ ወይስ የእንቁላል ማርባት ምትፈልገው?”
“እንደዛ ሚባል ነገርም አለ እንዴ? ሃብትሽዬ እኔ ምንም እውቀቱ የለኝም፡፡ ሚሻለውን እናተ ምረጡልኝ፡፡ ፕሊስ ሃብትሽ.”
“እኔ የእንቁላል ዶሮ ብትጀምር እመክርሃለው። ምክንያቱም፣ የእንቁላል ገበያ አመቱን ሙሉ አለ፡፡ ያ ደግሞ፣ አመቱን ሙሉ በወጥነት የሆነ ያህል ቢሆንም ገቢ አለህ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ፣ እንደቤት ኪራይና ሌሎች የወር ወጪዎችን ሊሸፍንልህ ይችላል፡፡ ያው ትንሽ በዛ ሚለው የምግብ ወጪያቸው ነው፣ እሱን ፈልጎ ከአቅራቢ መግዛት ነው፡፡ የስጋዎቹን ካረባህ፣ ምታገኘው ገቢ በአመት በተወሰነ ግዜ በአል ጠብቀህ
ብቻ ነው፡፡ ደግሞ ስንት ለፍተህ፣ በሽታ አንድ ነገር ቢያደርጋቸው፣እንዳትነሳ ሆነህ ትጎዳለህ፡፡” አለኝ፡፡
“እውነትህን ነው ሃብትሽ፤ የእንቁላል ይሻለኛል፡፡ አሌክስ ጋር ደውልለትና እረከስ ያለ ቤት ቶሎ ይፈልግልኝ፡፡ ምንም ስራ ሳልጀምር እጄ ላይ ያለው ብር ሊያልቅኮ ነው፡፡ በናትህ ሃብትሽ ቅበሩኝ፡፡” ተጣድፌ አጣደፍኩት፡፡
አሌክስን ደወለለትና፤ ይዤው ቤት ፍለጋ ከከተማው ጫፍ እስከ ጫፍ መዞር ጀመርን፡፡ በሁለት ቀን ከተማ ውስጥ ያሉትን ሰፈሮች አካለልናቸው፡፡ ቤት ውድ ነው፡፡ ለንግድ ሲሆን ደግሞ፣ ከስድስት ወር በታች ቅድመ ክፍያ አይቀበሉም፡፡ በመጨረሻም፣ በወር ሁለት ሺህ ብር
ለስድስት ወር አስራ ሁለት ሺህ ብር ከፍለን ተከራየን፡፡ ቤቱ ባለ ሶስት ክፍል ሲሆን፣ አንዱ እንደመጋዘን ሰፊና አራት መአዘን ነው፡፡ እሱን አናፂ ቀጥረን በስስ ሽቦ ወደ ስምንት የዶሮ መኖሪያ ክፍሎች ቀየርነው፡፡ተስፋ ቢስና ስልቹ የነበርኩት ልጅ፣ እነ ሃብትሽና አሌክስ እስኪሰለቹኝ፣
ጉዳዬን ሳልቋጭ ማይደክመኝ ተስፈኛ ሆንኩ፡፡ እንቁላል ጣይ ጫጩት በርካሽ ገዝቼ ከመጠበቅ አንድ መቶ እንቁላል ለመጣል የደረሱ ዶሮዎችን መርጬ ገዛሁና ስራ ጀመርኩ፡፡ ለአልጋ በየቀኑ የማወጣውን ወጪ ለመቆጠብ፣ አንዱን ክፍል ፍራሽና ብርድ ልብስ ገዝቼ መኖሪያዬ አደረኩት። ሃኒ ምግብ ማብሰያ እቃዎች ገዝታ፣ እቤት እየተመላለሰች
ታበስልልኝ ጀመር፡፡ በዛውም፣ እቤት ያስከፏትን ብሶቷን ስትነግረኝ አምሽታ እራት አብልታኝ ትሄዳለች፡፡
ከሁለተኛው ሳምንት በኋላ፣ እጄ ላይ ገንዘብ ጨረስኩኝ፡፡የዶሮዎቹን ምግብና የእኔን የቀን ወጪ መሸፈን አቃተኝ፡፡ ለሃብትሽ ሳማክረው፣ ስራው ጥሩ ትርፍ የሚኖረው፣ አምስት መቶና ከዛ በላይ
እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ሲኖር እንደሆነ ነገረኝ፡፡ እርሱ የነገረኝን ከማመንና ከመፈፀም፣ ወደ ፊት ከመሄድ ውጪ ምንም አማራጭ የለኝም፡፡ ያንን ለማድረግ ደግሞ መኪናዬን መሸጥ አለብኝ፡፡ ለመሸጥ ያላገባ ሳወጣ፣ እናቴ መኪና ልሽጥ እንደሆነ ጠርጥራ፤ 'ተው ልጄ ተው፣ ምን ሆንኩ ብለህ ነው ንብረት ምትሸጠው? ተው ንብረት ዝም ተብሎ አይሸጥም፡፡ ተው ልጄ፡፡" አለችኝ፡፡ ምክሯን ከቁብ ሳልቆጥረው፣ቆም ብዬ ሌላ አማራጭ እንኳ ለማየት ሳልሞክር መኪናዬን ሸጥኩኝ፡፡ተጨማሪ አራት መቶ እንቁላል መጣል የደረሱ ዶሮዎችንና ምግባቸውን በጅምላ ገዛሁ፡፡
አሁን በገንዘብ እጥረት ሚሰማኝ ስጋት ጠፋ፡፡ ኪሴ ወፍሯል፡፡ግን ገና ከቤት ለመውጣት ሳስብ፣ የታክሲ ጥበቃውና ፀሃዩን

አስብና መውጣት ይጨንቀኛል፡፡ ሳላውቀው የመኪና ጥገኛ ሆኛለሁ፡፡ መኪናም እንደሱስ፣ ጥገኛ ያደርጋል ለካ፡፡ መኪና ከሸጥኩ በኋላ፣ ውሎና አዳሬ
እቤት ሆነ፡፡ ሁለተኛው ሳምንት ላይ ይደብተኝ ጀመርኩ፡፡ ሃኒም ከቤተስብ ጭቅጭቅ ዞር እንድትል፣ እኔም መንፈሴን ለማደስ፣ ለአንድ ሳምንት አርባምንጭ
ለመሄድ ተስማማን፡፡ ቤቱንና ዶሮዎቹን
እስክንመጣ ሚጠብቅልን ሰው በነሃብትሽ በኩል አዘጋጀሁ፡፡ጉዞ ወደ አርባምንጭ፤
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
እቤት ሆነ፡፡ ሁለተኛው ሳምንት ላይ ይደብተኝ ጀመርኩ፡፡ ሃኒም ከቤተስብ ጭቅጭቅ ዞር እንድትል፣ እኔም መንፈሴን ለማደስ፣ ለአንድ ሳምንት አርባምንጭ
ለመሄድ ተስማማን፡፡ ቤቱንና ዶሮዎቹን
እስክንመጣ ሚጠብቅልን ሰው በነሃብትሽ በኩል አዘጋጀሁ፡፡ጉዞ ወደ አርባምንጭ፤
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ
❤1
#ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
ለራሱ መቼ ይናገርና ! እንዳይናገር የማለው ገና ሻንጣውን ይዞ እዚህ ግቢ ሲመጣ ነው ። ደሞ ማርታ የባጡን የቆጡን ስትለፈልፍ የሌሎቹ ማጋነን ፥ የሌሎቹ አብሮ ከበሮ መደለቅ ምን ይባላል ? ... “ ጥሩ ጭንቅላት አለው ... ሌክቸረሮቹን ቻሌንጅ ያደርጋል . . . ከአራት ጂ.ፒ.ኤ. ስለወረደ ሊሰቀል ነበር . ” ቅብጥርሴ ። ይሰቀላ ከፈለገ ! አለሱ
ጎበዝ ተማሪ የለም እንዴ ? ! ደሞስ በቀደም ዕለት 'አዜብና አሰገደች ፥ ማርታ ስታወራላቸው ግማሽ ሰዓት ሙሉ አፋች
ውን ከፍተው ከማዳመጥ ይልቅ ፡ አሳይሜንታቸውን አይሠሩም ነበር ? አሰገደች የማስረከቢያውን ቀን አሳልፋ ጋሼ ኤርምያስ አልቀበልም አላት ። እሱ ለራሱ ሴሪየስ ነው አዜብ ግን ተስፋ የላትም ። ከአባት ጦሮች ጋር ፀሐይ እየሞቀች ማን ያውራላት ? ማርታስ ብትሆን መቼ ከነሰ ትሻላለች?እሷ እምታውቀው አቤልን ማድነቅ ብቻ!ጎበዝ ተማሪ ማድነቅ ጎበዝ የሚያደርግ ይመስል ። ኦፍ ኮርስ ብራሊየንት
ነው ። እሱ የታወቀ ነው ... ግን ነገሩን ሲያስቡት ደሞ “አቤል ብሎ ሲኒየር፥ የመጽሐፍ ብሪሊያንት ! አቤል ብሎ
ወጣት ! ስሙ ራሱ ደስ አይልም !!...”
ትዕግሥት ወደሚዘፍኑት ሴቶች ተመለከተች፡፡ በሆዷ ለራሰ እምታወራውን የሰማት ይመስል-ግራና ቀኝ ወዳሉት
ሰዎች አማተረች ። አንዳንዶቹ ወዲያ ወዲህ ይላሉ ።አንዳንዶቹ እያጨበጨቡ ዘፈኑን ከሩቅ ያደምቃሉ ። ዐልፎ ዐልፎ እጅዋን ለኮፍ ማድረጓ ባይዘነጋትም፡እነማርታን ስታይ በወጉ ማጨብጨብ ጀመረች ። ቤተልሔምና ማርታ ጥቂት
ቆይተው ከሁለት ወንዶች ጋር ፈጠን ፈጠን እያሉ ሲያልፉ አየቻቸው ። ወደሷ ቀረብ ሲሉ ፥ ከማርታ ጋር እሚያወራው
ቀጠን ያለ ወጣት ላይ ዐይኗ ዐረፈ ። “ ማርታ ከሰው ጋር የመግባባት ችሎታ አላት ፥ በተለይ ከወንዶች ጋር ስትል
አሰበች ። ማርታ ፡ “ ወንድ ደስ እሚለኝ ቀጠን ሲል ነው ” እያለች ብዙ ጊዜ እምትናገረው ነገር በሐሳብዋ እየደጋገመ
ተሰማት ። ወዲያው በድንገት አቤል ከፊቷ ላይ ድቅን አለባት ። «መልኩ መስሎ በምናቧ መንቀሳቀስ ጀመረ ። አቤል ጠይም ነው ቀጠን ዘለግ ያለ ። ከሲታ ሳይሆን ፡ ሁሌ እሚለብሰው ጃኬቱ ጠባቃ ባያደርገው ፥ በአቋቋሙ ሚዛኑን የጠበቀ ነው ። አረማመዱ ኮራ ያለ ዐይነት ነው እሷን ሲያይ መርግጫውን እማያውቅ ከመምሰሉ በስተቀር ። አቤል ዐይኖቹ ተለቅ ተለቅ ያሉ ናቸው ። ሰልካካ አፍንጫው የተመጠነ አወራረድና ለግንባሩ ገጥታ ተስማሚ አቀማመጥ አለው ዞማ ጠጉሩ በደንብ ተበጥሮ እሚያውቅ አይመስልም ። ይሁን
እንጂ ለራስ ቅሉ እንደ ቆብ በልክ እንደ ተስፋ ሁሌ ክርክም ያለ ዐይነት ሆኖ ድምቀቱ ከጥቁር ከፋይ ይወዳደራል ! እስካሁን ጥርሶቹን በደንብ ለማየት አልቻለችም ። አቤል መች ይሥቃል ? ! እንዳይሥቅ ተገዝቶ ነው ካምፓስ የመጣው።እንዳውም እራት ዓመት ሙሉ በጭራሽ ሥቆ አያውቅም ።ጨፍጋጋ !ጨፍጋጋ ፊት ! እስቲ ምን ይባላል ፥ በጨፍጋጋ ሰው መታማት ? ! ቢሆንም ግን ላመል ፈገግ ሲል በጨረፍታ ኣ
አይታዋለች አንድ ቀን ከእስክንድር ጋር ቆሞ ሲያወራ ። ከዛም በፊት ሳታየው አትቀርም ፡ ማስታወሱ ይቸግራል እንጂ ። ስንቱ ነገር ይታወሳል ? አቤል ዝርዝር ያሉት ናቸው ጥርሶቹ በጠይም ፊቱ ላይ እንደ ወተት ነጭ መሆናቸው ነው ዐይን እሚስበው ። ድምፁ ግን ምን ዐይነት ነው
የአቤል? መቼም በዚህ ጥርስ አቀማመጥ በትንሿ ኮልተፍ ቢል ሳያምርበት አይቀርም ! ግን በየት በኩል ? እሱ ለራሱ ዲዳ ነው አይናገር አይጋገር ። ይቺ ማርታ ግን ዋና ናት
ጥርሰ ፍንጭት ነው እያለች ማውራቷ ። ቀድሞ ነገር የት ታውቀውና ያው እንደኔ ነው ከሩቅ የምታየዉ ..
ትዕግሥት ይሄን ስታስብ ቆይታ እስቲ በደንብ አየዋለሁ” አለች በልቧ ። ግን ደሞ ወዲያው ፥ እስክስታው ላይ ተተክሎ የነበረው ዐይኗ ቦዘዝ ብሎ ወደ ካምፓስ አዘገመ
ለምንድነው ጠዋት እንደዚያ የተቆጣው ? ” ስትል አሰበች ። አቤል ከደረጃ ወርዶ ፊት ለፊት በተገጣጠሙበት ሰዓት ከፊቱ ላይ ያየችው ቁጣ እንደ ገና ታያት ። የሱ መቆጣት ብቻ ሳይሆን ፥ የራሷም መሸማቀቅ ነበር ያስገረማት ።ንግግር የለ ! ሰላምታ መለዋወጥ የለ! ተቀራርቦ መጨዋወት የለ እንዲያውም እንደ ዲዳ እንደ ደንቆሮ በዐይን ብቻ መገናኘት ምንድነው ?
ዕንቆቅልሽ ሆነባት ። ዓይኗን ከድንኳኑ አሻግራ ወደ ማዶ ወረወረችው ፤እጅዋ ቀስ ቀስ እያለ ማጨብጨቡን አቋረጠ
ትምህርቷን መከታ አድርጋ ልትሽሽ የምትታገለው የዐይን ፍቅር እንደ ውሃ ጠብታ ቀስ ቀስ እያራሳት መሆኑ
ተሰማት መጨረሻዉ ናፍቋት ።
“ እሺ እንግዲህ መቼ ነው ታዲያ አፍ አውጥቶ የሚያናግረኝ ወይም አፍ አውጥቼ የማናግረው?” ስትል ሜሰቧን
ቀጠለች ። “ ዛሬ ያናግረኛል” ብላ ያሰበችበት የአንድ ቀኑ ጥሩ አጋጣሚ ታወሳት ።
የትምህርት ቀን ነበር። ነገር ግን ቀትር ሰዓት ላይ ስለሆነ የሚነቃነቅ ሰው አልነበረም ። አብዛኛው ምሳ በልቶ
በየክፍሉ ጋደም ብሎአል ። ጥቂቱ መጻሕፍት ቤት ገብቶ ያንኑ መጽሐፍ የሙጥኝ ብሏል ። ትዕግሥትን ከደብረ ዘይት የመጣ ዘመድ አስጠርቶአት ወደ ውጭው በር ስትሔድ አቤል ቡና ጠጥቶ ከውጭ ሲመጣ ተገጣጠሙ ። እሷ ፈጥና ነበር የምትራመደው። እሱም እሷን ባየ ጊዜ፥እጆቹን ከኪሱ አዉጥቶ ፈጠን አለ ። የተገጣጠሙበት መንገድ ወደ ግራም ወደ ቀኝም መታጠፊያ አልነበረውም ። ሊቀራረቡ ጥቂት
እርምጃ ሲቀራቸው የሁለቱም ልብ ትርታ ጨመረ ። ትዕግሥት ወደ ግራዋ ሰረቅ አርጋ አየችው ። እሱ መሬት መሬቱን
ነው የሚያየው።አጠገቡ ስትደርስ ገልመጥ አረገችው ፤ግልምጫዋ ለክፋት ያለችው አልነበረም ። ምናልባት አቤል
ለሰላምታ ጭንቅላቱን ሰብሮላት ፈገግ ብሎላት ወይም በግንባሩ ምልክት ሰጥቷት እንደሆን አጠፌታውን ልትመ
ልስለት ነበር ። አቤል ግን አጠገቧ ሲደርስ በልቡ እንዳልከጀላት ፈጽሞ እንዳልፈለጋት ፥ ጭራሽ እንደማያቃቃት
ፀይነት አንገቱን ደፍቶ ግንባሩን አኮማትሮ ቅርቅር አድርጓት አለፈ ።
ሁኔታው ትዕግሥትን ረበሻት ። በተለይ ችግሩን አስልታ ከትምህርቱ ጋር በተመለከተችው ጊዜ ዓይኗ እንባ
አቀረረ ። እንቅፋት ነው እንቅፋት!” ስትል ለራሷ ተነፈሰች ። ከዚያ ቀን በኋላ ከአቤል ዐይን ለመሸሽ ሞከረች
ግን ለማንም እላማከረችም ። በዕለቱ ከደብረ ዘይት ድረስ የመጣውን ዘመዷን እንኳ ፥ በቅጡ ሳታጫውተው ነበር የተለየችው .....
“ታዲያ ከዚያ ቀን የበለጠ አጋጣሚ ከየት ይገኛል? ”ብላ በሐሳብ ስትወራጭ የድንኳኑ ግርግር አባነናት ። ከውጭ ተከታታይ የመኪና ጥሩንባ ስለ ተሰማ ። በድንኳኑ የተሰበሰበው ተጋባዥ ሁሉ ሙሽራውን ለማየት የመቻኮል ስሜት ይታይበታል ። የቤተ ዘመድ ሽር ጉድ ማለትና መንጫጫት ግሏል ።
ማርታ ወደ ዘፋኞቹ ስትንደረደር መጥታ የትዬ ሙቀጫን ትከሻ ነካ ነካ አረገችና ። “ እትዬ ሙቀጫ ፥ ከበሮውን ይዛችሁ ውጡ እንጂ ! ሙሽራው እኮ መጥቷል ። ቶሎ በሉ እንጂ! ” አለቻቸው ።
ዘፋኞቹ ወደ በሩ ግልብጥ ብለው ሔደው ከበሮውን ሞቅ አድርገው እየመቱ ይዘፍኑ ጀመር ።
“አናስገባም በሩን ፡ ሰርገኛውን
በሩን ..
ሰርገኛውን ....
አናስገባም ሠርገኛ እደጅ ይተኛ
ሰርገኛ እደጅ ይተኛ ... ”
ማርታ ደስ አላት ። በሙሽራው ላይ እልኋን እንደ ተመጣች ሁሉ ፥ ብሽቀቷ በርዶላት ፊቷ ፈክቶ " ዳር ሆና ታጨበጭብ ጀመር።ሙሽራው ገብቶ ብፌ በሚዘረፍበት ሰዓት ቤተልሔም አንድ ሰው አየች።ለማ ካብትይመር ነበር።ከግርግሩ መሀል ለይታ እንድታየው ያስቻላት

👍3
ጸጉሩ ሸሽቶት የተጋለጠው ግንባሩ ነው ። ልክ እንዳየችው በደስታ ደነገጠች ። ብፌውን
ዘርፎ ወደ ቦታው ሔዶ እስኪቀመጥ ድረስ በዐይኗ ተከተለችው ። በሙሽሮቹ መደዳ ትንሽ ራቅ ብሎ ነበር የተቀመጠው።
አጃቢ ይሆን?” ስትል አሰበች ፥ “ እንዲያማ ቢሆን መታደል ነበር” አለች | የግንኙነት ጊዜው እንደሚረዝም በመገመት ።
ብዙም ሳትቆይ እሱ በተቀመጠበት አካባቢ ዐለፈች እንዲያያት ፈልጋ ነበር ። እሱ ግን ምግቡ ላይ አቀርቅሮ ስለ ነበረ ቀና ብሎ አላያትም ። እንዴት ሰላም እንደምትለው ግራ ገብቶታል ። የቀድሞ ግንኙነታቸው ያው የአሰተማሪና የተማሪ ስለሆነ ፥ ከአንገት ሰላምታ አላለፈም ። ስለሆነም አሁን ፊት ለፊት ሔዳ ሰላምታ መስጠት አልደፈረችም ።
ብሉ እስቲ ፥ ምን ጎደለ ? ” እያለች በሱ መደዳ ላሉት ሰዎች ፥ ድምጿን ከፍ አድርጋ ።
ለማ ቀና ሲል አያት ። ተማሪው መሆኗን አያት። እሷም በዝግታ ዐይኗን ቀልሳ አየችውና ሰላም የማለት ያህል ፈገግ
ብላ አንገቷን ሰበር አደረገች። ምላሹን ሰጣትና የሚጠጣውን ነገር ከጠርሙሱ ወደ ብርጭቆው ማንደቅደቅ ጀመረ ።
ቤተ ልሔም በልቧ እንደ መብሸቅ አለች።የሰላምታው ምላሽ የጠበቀችውን ያህል ሞቅታ ኣልነበረውም ።
ድርቅ ብላ ከፊቱ ቆመችና ፥ “ ምን ጎደለ ታዲያ? ምን ላምጣ ? ” አለችው ፡ ከአስተናጋጅነት ይልቅ ቅርብነት
በጎላበት ጣፋጭ አነጋገር ። በጎልማሳነት ክልል ውስጥ ቢሆንም ። ከዚህ በፊት ቀርባ አነጋግራው ስለማታውቅ። አንተ
ወይም አንቱ ለማለት ቸግሮአታል ። ነገር ግን ለማጥመድ ያሰበችውን ሰው አንተ ማለት የሚያስከትለውን ውጤት
ታውቃለች ። ኋላ አባትና ልጅ ወይም ወንድምና እኅት ሆኖ ቁጭ ነው ። እናም ደፍራ ኣንተ ለማለት ወሰነች ።
ሁሉም አለ። ግሩም ነው አላት ለማ ።
“እውነቴን ነው ፥ የምትመርጠውን ነገር ላምጣልህ ” አለችው ፡ በዐይኗ ከሰሐኑ ላይ የተቀመጠውን የምግብ ዐይነት እየፈለገች ። “ ጭኮዋን ወደሃታል አይደል?! እሷን ላምጣልህ” አለችውና ከእሱ መልስ ሳትጠብቅ ልታመጣለት
ሔደች ።
ለማ የዶሮ ወጡን እንቁላል እየፈረከሰ ቤተ ልሔምን ከኃላዋ ቃኛት ። ሰፋ ያሉ ጃፖኒ ቀሚስ ነበር የለበሰችው ። ውፍረቷ
ያንኑ መጠነኛ ቁመቷን ቢውጥባትም ለጊዜው በረዥም ታኮ ጫማ ተነሥታለች ስትራመድ ዳሌዋ ግራ ቀኝ ይረግጣል ።
የሚዛኗ አጠባበቅ ብዙ ልምምድ እንደ ተደረገበት ያስታውቃል ቤተልሔም የጭኮውን ሰሐን ብፌው ከተዘረጋበት ጠረጴዛ ላይ ስታነሣ ማርታ ተመለከተቻት እንደ ደንቡ ከሆነ ለድጋሚ ዙር የምግቡ ዐይነት ከተዘረጋበት ጠረጴን ተነሥቶ
በየገበታው የሚዞረው ተጋባዡ ሁሉ ብፌ ዘርፎ ከጨረሰ በኋላ ነው ። ቤተልሔም የጭኮውን ሰሐን ስታነሣ ግን ገና ብፌ ዘረፋው አልተጠናቀቀም ። ስለዚህም ማርታ ልቧ የሆነ ነገር ጠርጥሮ በዐይኗ ተከተለቻት ፤ ጭኮውን ወስዳ ለማ ሰሐን ላይ ስትዘረግፍለት በቅናት ስሜት ተመለከተቻት ።
“ኧረ በቃ!በቃ!” አለ ለማ የምትጨልፍበት እጅዋን ለማስጣል በግራ እጁ ይዞ
“ እሺ ፡ በል ያመጣሁልህን ብላ ” አለችና ዐይኗን አስለምልማ አየችው ። ሳያስበው የእሽታ ፈገግታ ሰጣት ።ፈገግታው ካመለጠው በኋላ በቅልጥፍናዋ ተደነቀ ።
እሷም እይታዋን አልደገመችውም ተቀባይ ልብ ላለው ሰው የአንዴው በቂ እንደሆን ታውቃለች ። በምላሽ ፈገግታው
ረክታ ነገሩን ለማድበስበስ ያህል በአቅራቢያው ላሉትም ብሉ እንጂ” እያለች ከጭቆው ጨመረችላቸው ።
ለማ ጸጉር በከዳው ግንባሩ በኩል ላብ ሲንቸረፈፍ ተሰማው ። ወንድነቱ “ ዘራፍ” እያለ መጣበት ። ምግቡ ላይ እንዳቀረቀረ ቤተልሔምን በልቡ ተመለከታት ጉሮሮ
ውን ምንም ነገር ሳይኮሰኩሰው ፡ ጣለ ፡ ለአፍታ ያህል ትንፋሹን አምቆ ቆየና በረዥሙ ተነፈሰ ። በድንገት የሚስተር
ራህማን ምስል ከፊቱ ተደቀነበት
ሚስተር ራህማን ለለማ የሥራ ባልደረባው ናቸው እሱ ተመርቆ ዩኒቨርስቲ ማስተማር ከጀመረ ገና አራተኛ
ዓመቱ ነው ። ሚስተር ራህማን ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ዩኒቨርስቲ ሲያስተምሩ ዘጠኝ ዓመት አላቸው ። ነገር ግን ሰማቸው። በዩኒቨርስቲው ውስጥ የዚያኑ ያህል ጠፍቷል በሴት ጉዳይ ተማሪው ብቻ ሳይሆን መምህራኑም ጭምር ያሟቸዋል ። የትም ይሁኑ የትም ዐይናቸው ከሴት ላይ አይነቀልም
ቆንጆ ልጅ ታክሲ ውስጥ ካጋጠመቻቸው ካልከፈልኩልሽ በማለት ብቻ አይመለሱም “ አይቲንክ አይ ኖው ዩ ሳምዌር ”ብለው ወሬ መክፈት ልማዳቸው ነው።

#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)
ጉዞ ወደ አርባምንጭ፤በጥዋት ተነስተን በሚኒ ባስ ተሳፍረን ጉዞ ጀመርን፡፡ሃኒ ከአዲስ አበባ ስንነሳ ጀምሮ መኪናው አልተመቻትም፤ ስትንቆራጠጥ ነው ሻሸመኔ ደረስን አደርን፡፡ ከሻሸመኔ ደግሞ ቅጥቅጥ አይሱዙ ተሳፍረን፣ በወላይታ
ሶዶ አድርገን፣ ጉዞ ወደ አርባ ምንጭ፡፡ መኪናው እላይ አድርሶ ያፈርጠናል፡፡ ደጋግሜ አይዞሽ እላታለሁ፡፡ በእርግጥ እንደዛ ከማለት ውጪ፣ ምንም ማድረግ ምችለው ነገርም የለም፡፡
“መዝናናት ሳይሆን መጉላላት ሆነብሽ?” አልኳት የሚሰማትን ማውቅ ፈልጌ፡፡
“ለምንድነው ግን፣ በቱር መኪና ያልመጣነው?” አለች፡፡
“አቅም ነዋ ሃኒዬ፣ አቅም..! በጣም ውድኮ ነው፡፡ በቀን ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር፣ አይከብድም...?”
“ኖ...! እንደሱ ሳይሆን፣ ኮስትር በጋራ ከሌላ ጎብኒዎች ጋር ሆነን ማለቴ ነው፡፡”
“እንደዛ አይነት ፓኬጅ ያለ አይመስለኝም፡፡ ሰምቼ አላውቅም፡፡
ሙሉ ኮስትር ግን ይባስ ውድ ነው፡፡”
“ለምን እንከራየዋለን? እንደኛ አርባ ምንጭን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጓዦችን አሰባስቦ የሚሄድ፣ የአስጎብኚ ድርጅቱ ጋር ሁለት ትኬት ገዝተን ብንሄድ ነው ምልህ፡፡ እንደውም፣ አስጎብኚ ስለሚኖር ብዙ ነገሮችን ማየት እንችላለን፡፡”
“እንደምትዪው አይነት ጉዞ ሰምቼ አላውቅም፡፡ በአስጎብኚዎች የሚዘጋጅ፣ የግሩፕ የጉብኝት ጉዞ እድል ያለው፣ ወደ እስራኤልና ሲሸል ለማስጎብኘት ሲሆን፣እንጂ ሀገራችን አልተለመደም፡፡ ሀገራችንን ለማየት፣ ያለን አማራጭ፣ በቀን ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር ከፍሎ፣ ላንድክሩዘር መከራየት ይጠይቃል ወይም
እንደዚህ በተለመደው የህዝብ ትራንስፖርት ተሳፍረሽ፣ ለመዝናናት
እየተጉላላሽ መሄድ ነው፡፡ የግሩፕ ጉዞ ቢኖር ኖሮማ፣ይሄኔ ሀገሬን ከሰሜን እስከደቡብ፣ ከምስራቅ እስከምዕራብ ማየት እችል ነበር፡፡”
“እንዴ ይኼ እኮ አሪፍ ቢዝነስ ነው፡፡ እና ወደ አርባ ምንጭም ሆነ፣ ወደተለያዩ የሀገራችን ተፈጥሯዊና ባህላዊ መስህብ ያላቸውን ቦታዎች በተደራጀ መልኩ፣ ቅስቀሳ አድርገው፣ በተመጣጣኝ ዋጋ
የማስጎብኘት ስራ የሚሰሩ ድርጀቶች የሉም እያልከኝ ነው?”
“በእርግጥ፣ ይሄ አካሄድ ገዳማትን ለማስጎብኘት በየታክሲው፣በከተማዋ ግድግዳዎችና የስልክ ቋሚዎች ላይ በሚለጠፉ ቅስቀሳዎች፣ፍላጎቱ ያላቸውን ሰዎችን አሰባስበው በማደራጀት በተመጣጣኝ ዋጋ ጉብኝቶችን ሲያዘጋጁ አይቻለሁ፡፡ ነገር ግን ይህን አካሄድ፣ በጥቂቱ አዘምነው፣ ሀይማኖታዊ ላልሆኑትም ለሌሎች የሀገሪቱ መስህቦችን ለማስጎብኘት ብንጠቀምበት፣ ማህበረሰቡን በተመጣጣኝ ዋጋ የተለዩ የሀገራችንን መስህቦች ለማስጎብኘት እድል ይሰጣል፡፡ በሂደቱም፣ ለብዙ ሰዎች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ፣ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ ነገርግን፣ ይህ የተለመደ ባለመሆኑ፣ ላሊበላን፣
አክሱምን፣ የጀጎል ግንብን፣ የባሌ ብሄራዊ ፓርክን፣ ነጭሳር ፓርክን
እና ሌሎች ልዩ እና ድንቅ የሆኑ የሀገራችን ውበቶችና ኩራቶች ከዜጎቻችን ይልቅ በውጪ ቱሪስቶች ይጎበኛሉ፡፡ ትውልዱም ሀገሩን የማወቅ እድል ስለሌለው፣ በሀገሩ መኩራት ሲገባው፣ ባለማወቁ ፀምክንያት ያፍርባታል፡፡”
“ይኸውልህ ያቡ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ ያለው ውጣ ውረድ አድካሚ እና የሚያጉላላ ከመሆኑም በተጨማሪ በየቦታው የሚገኙ መስህቦችን ቆም ብሎ ለማየት፣ ለማድነቅና ፎቶ ለማንሳት አይመችም፡፡በመሆኑም ጉብኝቱን የተሟላ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ እንደምትነግረኝ ከሆነ፣ የአስጎብኚ ድርጅቶች አደረጃጀት የውጪ ዜጎችንና ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን ሰዎች ብቻ ያማከለ ይመስላል፡፡ ይህም የመጎብኘት
ባህላችን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ጉብኝትን እንደቅንጦት እንዲቆጠር
ያደርጋል፡፡ እራስን አድሶ ለቀጣይ ስራ እራስን ከማዘጋጀትም በላይ፣
በመጎብኘት ውስጥ በጣም ብዙ አዲስ እውቀት፣ የፈጠራ ሀሳቦችና የልምድ ልውውጦች አሉ፡፡”
“ትክክል ብለሻል ሃኒዬ፡፡ እንደማህበረሰብ የመጎብኘት ባህላችን መሻሻል አለበት። እንዳልሺው መጎብኘት ከመዝናናት በዘለለ ብዙ ፋይዳዎች አሉት፡፡ አንዱ ማህበረሰብ ውስጥ ያየሽውን ባህልና እሴት ቀምረሽ፣ በህይወት ለሌሎች ችግሮችም እንደ መፍትሄ ልትጠቀሚበት
ትችያለሽ፡፡ ነገር ግን እንዳለ መታደል ሆኖ፣ በማህበረሰባችን መጎብኘትን
እንደቅንጦት፣ ለመጎብኘት የሚያወጣን ወጪ እንደ ማባከን የሚቆጥረው
ቁጥሩ ቀላል ሚባሉ አይደሉም፡፡”
እየተጫወትን ለመርሳት የመኪናውን እንግልት እንዲህ ሞከርን፡፡ ሲደክማት ጋደም እያለችብኝ፣ አስር ሰአት አርባ ምንጭ ከተማ ገባን፡፡ እንደደረስን ቱሪስት ሆቴል አልጋ ያዝን፡፡ ቢደክመንም፣ ሃኒ
ከተማውን ለማየት ካላት ጉጉት የተነሳ፣ ሳናርፍ ሻወር ወስደን ወጣን፡፡በቅርብ የተሰራ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ ለከተማዋ አዲስ ውበት ሰጥቷል፡፡ አርባ ምንጭ ግርግር ያልበዛበት ደርባባ ከተማ ነች፡፡ በባጃጅ ተዘዋውረን ከተማዋን ለማየት ሞከርን፡፡ ከተማዋ ሁለት ጫፎች አሏት፡፡የዩኒቨርስቲውን መስፋፋት ተከትሎ የተመሰረተውና የቀደመው መንደር ደረጃውን በጠበቀ የአስፓልት መንገድ በቅርብ እንደተገናኘ ያስታውቃል፡፡
አስፓልቱ ሳይሰራ ከተማዋን አሰብኳት፡፡ የአባይና ጫሞ ትልልቅ ሀይቆች ሀገር፣ የነጭ ሳር ፓርክ፤ የአዞ ገበያ፣ የሙዝና የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ የቱሪስት መናኸሪያ ሀገር፣ አርባ ምንጭ የረባ የአስፓልት
መንገድ ለዓመታት ብርቋ ነበር፡፡
ለዐይን ያዝ ሲያደርግ ወክ እያደረግን ወደ ቱሪስት ሆቴል ተመለስን፡፡ ወደ ሆቴሉ እንደገባን ረሃብ ስሜት ተሰማኝ፡፡ እራት
ለመብላት ዞርዞር ብለን ቦታ መፈለግ ጀመርን፡፡ አንድ ጥግ ላይ ክፍት ቦታ አገኘንና ተቀመጥን፡፡ አስተናጋጅ እየጠበቅን፣ ግቢውን ቃኘነው፡፡
“ግማሽ በግማሽ ፈረንጅ አይደል እንዴ?” አለች ሃኒ፡፡
“ያው ቱሪስት ሆቴል አይደል፡፡”
“ኪ.ኪ.ኪ..፣ እና ለዛ ነው?”
ማለቴ አርባ ምንጭ እኮ ምድራዊ ገነት ናት፡፡” አስተናጋጁ መጥቶ “ምን ልታዘዝ!” አለን፡፡
“ምን እንብላ ሃኒዬ?”
“እንዴ! አርባ ምንጭ መጥተንማ፣ ከአሳ ውጪ መብላት...”
“እሺ! አንድ ለብለብ አንድ ጉላሽ ይሁን?”
“እሺ፣አሪፍ ነው፡፡”
“የሚጠጣ ሁለት ጊዮርጊስ ቢራ፡፡”
አስተናጋጁ እየተዋከበ ከአጠገባችን ሄደ፡፡ ግቢውን በዐይኔ ቃኘሁት፡፡ በግቢው የመዝናናት መንፈስ ሰፍኗል፡፡ ሰው ይበላል፤ ይጠጣል፡፡ ይጫወታል፡፡ ከሃኒ ጀርባ የተቀመጡ ሁለት ነጭ ሴቶችን አየሁ፡፡ ከኔ ትይዩ ያለችው ፈረንጅ

ልከኛ ሰውነት ያላት ቆንጆ ነች። አብራት ያለችው፣ ጀርባዋ ብቻ ቢታየኝም፣ ግዝፍዝፍ ያለች ወፍራም እንደሆነች ታስታውቃለች።ቆንጅዬዋ ታወራለች። ወፍራሟ ታዳምጣለች፡፡ የአንድ አገር ሰው
አይመስሉም፡፡ የየት ሀገር ሰው ይሆኑ ብዬ አሰብኩ፡፡ በውስጤ ፀለመገመት እየሞከርኩ ነው፡፡
ነገ ምንድ ነው ፕሮግራማችን?” ብላ ሃኒ ከሄድኩበት ሃሳብ አወጣችኝ፡፡
“ነገማ አርባዎቹንም ምንጮች
እናያቸዋለና።”
“እንዴ! የምር አርባ ናቸው እንዴ?”
“ኧረ ስቀልድሽ ነው፡፡ ማን ቆጠራቸውና፡፡”
ከነጯ ጋር ደጋግመን ዐይን ለዐይን ተጋጨን፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ልተዋወቃት ፈልጊያለሁ፡፡ ወደ ሽንት ቤት ወይም እጇን ልትታጠብ ከተነሳች ተከትያት ለመሄድ ወስኛለሁ፡፡ በየመሃሉ በሃኒ ላይ አሻግሬ እመለከታታለሁ። ሃኒ ምን እንደማይ ለማየት፣ አንድ ሁለቴ
ዞራ ተመለከተች፡፡ ሃኒ ሌላ ደስ ሚል ባህሪዋ፣ ብዙ ጨቅጫቃ አየደለችም፡፡ አይታ እንዳላየ አለፈችኝ፡፡ የኛ ምግብ መጥቶ እየበላን እነሱ ታጥበው፣ ከፍለው እየወጡ ነው፡፡ በተቻለኝ መጠን ትኩረቴን
እንደሳበችኝ እንድታውቅ ደጋግሜ አየኋት። ሲወጡም፣ በዐይኔ ሸኘኋቸው፡፡
በሚቀጥለው ቀን የመንገዱ ድካም እስኪለቀን፣ ከተማዋን እያየን፣ እዛው ያሉ ሎጆችን እየጎበኝን ስንዝናና አመሸተን፣ ወደ ክፍላችን ስንገባ ትናንት እራት ላይ ያየናቸው ነጮች ወደ ክፍላቸው ሲገቡ በር ላይ ተገናኘን፡፡ እነሱም ቱሪስት ሆቴል ነው አልጋ የያዙት፡፡
ሳላስበው፤
ሄይ ሃው አር ዩ?” አልኳቸው፡፡ እነሱም ሰላምታ ሰጥተውን ተዋወቅን፡፡ ደስ ያለችኝ ኢቫ ትባላለች፡፡ የወፍራሟን ስም እዛው
እረሳሁት፡፡
“ሲ ዩ፡፡” ብለውን ገቡ፡፡ እኛም ወደ ክፍላችን ገባን፡፡ ሳላስበው ከነጮቹ ጋር ባደረኩት አፍሪያለሁ፡፡ ሃኒ ምን ተሰምቷት ይሆን? ግን ምን መሆኔ ነው? ፈረንጅ ብርቁ እንደሆነ ሰው፣ እንደዛ መሆን
አልነበረብኝም፡፡ በራሴ ተናደድኩ፡፡ ልንተኛ ልብስ እየቀየርን፤
“ነገስ የት ነው ምንሄደው?” አለችኝ ሃኒ፡፡ ምንም የመናደድ ምልክት አይታይባትም፡፡
“ነገ የት እንደምንሄድ አልወሰንኩም፤ እንዴት እንደምንሄድም አላውቅም፤ ግን የዶርዜ ሎጅን ብናይ ደስ ይለኛል፡፡”
“እንዴት ነው እዛ ሚኬደው?
ታውቀዋለኽ?”
“አይ፣ አላውቀውም፡፡ ጥዋት ስው እንጠይቃለን፡፡”
አልጋችን ውስጥ ገብተን ተኛን፡፡ እንቅልፍ ቶሎ አልወሰደኝም፡፡ከነጮቹ ጋር ያደረኩት ስሜታዊ ድርጊት ምን እንደሆነ ማስብ ጀመርኩ፡፡
እንዴት ማሂ እያለች እንደዚህ አይነት ስሜት ይሰማኛል? እንዴት ቢያንስ ማሂ ፊት ስሜቴን መደበቅ አቃተኝ? ከማሂ ጋር ተኝቼ ውስጤ ኢቫን ሰወሲባዊ ስሜት ያስባል፡፡ ምን አይነት እብደት ነው?፡፡ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ
.... " ቆንጆ ልጅ ታክሲ ውስጥ ካጋጠመቻቸው ካልከፈልኩልሽ በማለት ብቻ አይመለሱም “ አይቲንክ አይ ኖው ዩ ሳምዌር ” ብለው ወሬ መክፈት ልማዳቸው ነው።የመኖሪያ ቤታቸውን እቅጣጫ እየዘረዘሩ ቀጠሮ መለዋወጥ
ከጀመሩ ግን ፥ ከታክሲ ነጂው ጋር መጣላታቸው አይቀርም ።ሚስተር ራህማን በወሲብ ፍላጎታቸው ራሳቸውን መቆጣጠር አይችሉም ። ለምሳሌ ካምፓስ አካባቢ ከሴት ጋር ቆመው
ሲያወሩ ቢታዩ፥ ሠራተኛ ለመቅጠር እየተነጋገሩ ነው ማለት አይደለም። ወይም አማርኛ እየተለመማዱ ነው ብሎ እሚያስብ ተሳስቷል ። ሚስተር ራህማን በዚያን ሰዓት ያጠኗቸውንም ያላጠኗቸውንም ውበት ማድነቂያ ቃላት አንድ ባንድ እየቦረቦሩ በማዥጎድጎድ ላይ እንደሚሆኑ አይጠረጠርም እንዳውም በል ካላቸው የሴትዮዋን እጅ በጃቸው ጥርቅም አርገው እንደ ያዙ ፡ አደባባይ በመዞር ላይ ያሉ የሞላ ታክሲ
ወዲያውኑ ካላስቆምኩ ሊሉ ይችላሉ ።
የሚያወጧቸው ሴቶች አያወሩባቸውም ። “ A ” በእጃቸው እንደ ገባች አረጋግጠው ድምፃቸውን አጥፍተው ቁጭ ነው ።ነገር ግን የራህማንን ጥያቄ የማይቀበሉ ጥቂት
ጠንካራ ሴቶች ያጋጥማሉ።እኒህኞቹ ለቅርብ ጓደኞቻቸው ።አንቺዬ ይሄ ሽማግሌ ሕንድኮ ላውጣሽ እለኝ አያፍር
እንዴ በናትሽ ? ምን ቅሌታም ነው!” ሲሉ ይሰማል ። ወሬው እንዲህ እያለ ይራባል ወንዶች ይህን “ ዕድል” ባይታደ
ሉትም ፡ አንዳንዶቹ በአገናኝነት በማገልገል የበኩላቸውን ሚና ይጫወታሉ እየተባለ ይወራል ...
“ ከዚህ አድነኝ ! ” በማለት ዐይነት ለማ ግንባሩን ቋጥሮ ራሱን ነቀነቀ ። ከራሱ ጋር ቅራኔ ውስጥ ገባ ።
ቤተልሔም የጭኮውን ሰሐን ከጠረጴዛው ላይ መልሳ እየተፍነከነከች ሙሽራዋ ስትለባብስ ወደ ቆየችበት ክፍል ሔደች። ማርታም አይጥ እንዳየች ድመት በዐይኗ ስትከታተላት ቆይታ { ወደ ገባችበት ክፍል ዘው ብላ ገባች ።
«ዉይ ! ኮቴሽን ሳልሰማ ። እንዴት አስደነገጥሽ !አለች ቤተልሔም በደስታ የሚሥቁ ዐይኖቿን ማርታ ላይ ተክላ ። በቁም ሳጥኑ መስታወት እያየች ጸጉሯን ስታስተካክል ነበር የደረሰችባት ።
“ አለ ነገር ! ” አለች ማርታ ከፊል ቀልድ ከፊል ቅናት በተደባለቀበት ሞዛዛ አነጋገር “ ከግብዣ መሐል አስነሥቶ ጸጉር የሚያስበጥር ፡ አለ ነገር! አለ ነገር ! ”
“ መች አጣሽው ማርትዬ ፡ አለ እንጂ ጥብቅ ነገር ! ሠርግና ምላሽ መሐል ከመምህሬ ጋር ስገጣጠም ” አለች "
ዜማ ቀረሽ በሆነ ድምፅ ።
መምህርሽ ነው እንዴ?” ስትል በቁም ነገር ቃና ጠየቀቻት ።
“ አይተሽዋል እንዴ ? ” ስትል ፥ ቤተልሔም ጥያቄውን በጥያቄ መለሰች
አይቼዋለሁ ። ያ ራሰ በራሽን ሰመውዬ አይደለም? ”ጸጉሩ የሸሽው በዘር ሊሆን ይችላል እንጂ " እሱስ ገና ወጣት ነው
“ ማለቴ " ምልክቱን ነው እንጂ • ስለ ዕድሜው መግለጼ አይደለም ።
“ አዎ እሱ ነው ። ግን ከምኔው አየሽው ? አይ አንቺ !”አለችና በምስጢር ዐይነት ድምጿን ዝቅ አድርጋ “ አንድ ኮርስ ያስተምረኛል ” አለቻት ።
“ ታዲያ እንዴት ነው ? ” አለች ማርታ ከንፈሯን ነከስ አድርጋ ።
“ እንዴት ይመስልሻል ? ” አለችና ቤተልሔም የግራ ጎን ዳሌዋን በመስታወቱ ውስጥ እየተመለከተች ፡
ጠብ ነዋ ! ” አለቻት ።
ለማንኛውም ነገር ዕድልና አጋጣሚ ያስፈልጋል ? አለች ማርታ በልቧ ፥ “ አሁን ምናለበት ፈጣሪዬ አንዱን
መምህሬን ኣምጥቶ እዚህ ሰርግ ላይ ቢጥልልኝ !
ፊት ለፊት ቆማ ፥ በጎን በኩል ሆና ፥ ከኋላ በኩል አንግቷን አዙራ ፥ ባለችበት ራመድ ራመድ እያለች ቤተልሔም ራሷን መስታወት ውስጥ ተመለከተችና ፥ምን ይወጣልኛል ! ” በማለት ዐይነት በኩራት ፈገግ አለች።
ውፍረቷ አያስጠላባትም ። በአለባበስ ትሸፍነዋለች ።የትኛው ልብስ ከየትኛው ጫማና ሹራብ ጋር እንደሚሔድ
ጠንቅቃ ታውቀዋለች ። ሱሪ አታዘወትርም ከሰውነቷ ሁኔታ ጋር አዛምዳ ነው የምትለብሰው ። ገንጮቿ የተላጠ
ብርቱካን ነው የሚመስሉት ። ነገር ግን በምቾት አበጥ ስላሉ ጓደኞቿ “ ለጉንጮችሽ የጡት መያዣ ያስፈልጋቸዋል እያሉ ይቀልዱባታል ። ፎርሟን ለማስተካከልና ውፍረቷን
ለመቀንስ እንዳንድ ሰሞን ቁርስ መብላት ትተዋለች ። ነገር ግን ምሳ ላይ ደርሳ ነው የምትበላው ። የዩኒቨርስቲው ምሳ
አይስማማትም ። እንዲያው ነካ አድርጋ ነው የምትተወው ።ከዚያ በጓሮ በር የምትግባባቸው ቤቶች አሏት ። የሆድ ነገር ከሆነ የቅርብ ጓደኛዋንም አታስጠጋ ሹልክ ብላ ነው የምትሔደው ።
በቃሽ እንግዲህ ኤፍ ! ደሞ ለአስተማሪ ይህን ያህል ! ”አለች ማርታ በመሰላቸት አይነት ።
ቤተልሔም በልቧ " ባይሳካልሽ ነው” አለችና ሽቶ ከቦርሳዋ አውጥታ ጡቶቿ መሐል አርከፈከፈች ።ከነጋ አራተኛ ዜዊዋ መሆኑ ኔው ።
ተያይዘው ወደ ድንኳኑ ሲወጡ ቤተልሑም እንደ ልማዷ ወደ ሽንት ቤት ሔደች ። ማርታ አገሩ ገባትና ሣቅ አለች።
ከዚህ ሁሉ ትርኢት ርቃ ከዘፈኑ አካባቢ የቆየችው ትዕግሥት ፥ ማርታን ፈልጋት መጣችና ፤
“ አንቺ ማርታ " እረ እንሔድ ” አለቻት ። ።
“ የት ? ” አለች ማርታ ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር እንደ ጠየቀቻት ሁሉ ተደናግጣ ።
“ ወደ ካምፓስ ነዋ ! ምን ማለትሽ ነው? ” አለቻት ፥ የተከመረውን ጥናትና የተቃረበውን ፈተና በሚገልጽ ስሜት
ግንባሯን ኩምትር " ፊቷን ትክዝ አድርጋ ።
ትዕግሥት ሰርግ ቤት መቆየቱን አልጠላችም ። ብታድርም በወደደች ነበር ነገር ግን ሐሳቧ ተረጋግቶ መቀመጥ
አልቻለም ። እሷ ከዚህ ሙሽራ አጅባ ስታጨበጭብ ካምፓስ ውስጥ ተማሪው ጥናቱን ሲፈልጠው የታሪክ ትምህርቱን ሲለበልብው ። የፍልስፍና ትምህርቱን ሲሰነጣጥቀው የሒሳብ ትምህርቱን ሲያላምጠው በሐሳቧ ቁልጭ ብሎ እየታያት የመበለጥ ስሜት ተሰማት ። ከዚህ ሁሉ ደግሞ አቤል በምሳ ሰዓት ምግብ አዳራሽ ውስጥ በዐይኑ እንደሚፈልጋት ታውቃለች ከሄደችበት ተመልሳለች ወይስ አልተመለሰችም በሚል የቅናት ስሜት ። እና ወደ ካምፓስ መመለሷን እንዲያውቅ ራት ላይ እንኳን ልትታየው አሰበች ።
“ እሺ ቆይ ፥ ለማንኛውም ሙሽራ ይውጣ ” አለች ማርታ ። “ከዚያ መኪናም አይጠፋ ፤ካምፓስ ድረስ እንሸኝሻለን ።
ትዕግሥት እነሱ ወደ ካምፓስ እንድማይመለሱ ተረዱ ኧረ ግድየለም
እኔ በአውቶቡስ እሔዳለው አለቻት ።
“ እሺ ! ” አለች ማርታ ፡ ትዕግሥት የተናገረችውን ሳትሰማ ። ሐሳቧ ዐይኗን ተከትሎ ለማ ወደ ተቀመጠበት ሔዶ ነበር
ለማ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቤተልሔም ከዐይኑ ጠፍታበት አዳራሹን ግራ ቀኝ ሲማትር ፥ ድንገት ከጀርባው በኩል
“ ብሉ እስቲ ። ምን ጎደለ ? እዚህ አካባቢ ጠፋሁባችሁ አይደል? ” አለች ገና ከመድረሷ በሌላ መደዳ ስታልፍ የቆየች
ለማስመሰል
አብዛኛዎቹ መብላት አብቅተው ወደ መጠጡ አዘንብለው ነበር ። የተደጋገመው መስተንግዶ አስደንቆአቸው
እሷን በሙሉ ዐይናቸው ፡ እሱን ደግም በሰርቆት ተመልክተው ግብዣዋን በማመስገን ዐይነት እጅ ነሱ ።
የቤተልሔም የሙዚቃ መሳይ ድምፅ ጆሮውን ብቻ ሳይሆን ልቡን ጭምር ቢነካዉም ለማ ወደ ኋላው ዞር ብሎ
አልተመለከታትም ። መኩራቱ ሳይሆን መቆጠብ ነበር ።
ብርጭቆውን እንዳጎደለ ተመለከተችና እጅዋን በማጅራቱ በኩል አሳልፉ ከጠርሙሱ እየቀዳችለት
“ በጀርባህ በኩል በመቅዳቴ ይቅርታ ! ” አለችው ።
ምላስ እንደሌለው ሁሉ “ ምንም አይደለም በማለት ዐይነት ጭንቅላቱን ነቀነቀ ደረቷ ለአፍንጫው በጣም ሰለቀረበ የሽቶዋ መዓዛ ክፉኛ አወደው ። አሁንም ወንድነቱ የሽቶውን መዓዛ እየማገ ከእሱነቱ ውስጥ “ ዘራፍ ! ”ሲል ተሰማሁ
“ ምናባቷ

👍2🥰1
ትፈታተነኛለች ! ” አለ በልቡ ።
ብርጭቆው ቶሎ እንዳይሞላ ቀስ ብላ እየቀዳች ፡ “ ትቆያለ ወይስ ትሔዳለህ? ? ” ሰትል ሹክ አለችው ልቡ ክፉኛ ነጠረበት ለእሷ መልስ በመስጠት ፈንታ ቀስ ብሎ አጠገቡ የተቀመጠውትን ሰዎች ማትረ። እሷ ድምፅዋን ዝቅ አድርጋና ፈጥና ሌሎች እንዳይሰሙ አድርጋ ነበር የጠየቀችውኑ እሱ ቀና ሲል ከፊት ለፊቴ የተቀመጡት ሁልት ሴቶች አቀርቅረው ሲንሾካሾኩ ተመለከተ።
ምኗ ይሆን ? እንዴት ብትወደው ነው ? እያሉ ይሆናል የሚንሾካሾኩት ” ሲል አሰበ እጁ ሳይታዘዝ በራው ላይ ያቸፈቸፈውን ላብ ጠረገለት ሲያሳጣዉ ።
“ማለቴ” አለችው ቤተልሔም ፥ መልሱ ስለ ቆየባት።ጥያቄዋ ያደናገረው መስሏት ማማለቴ አጃቢ ሆነህ ነው የመጣኸው ወይስ ተጋብዘህ ? ”
ኧረ ተጋብዤ ነው አላት።
“ ቶሎ ሕያጅ ነሐ? ” ብላ መጠጡን ቀድታለት ጨርሳ ቀና ስትል ፊቷ ዕዝን ብሎ ነበር ። በዚያች ቅጽበት ዐይኗ
ውስጥ የሆነ ነገር አንብቦ “ በርታ ልቤ ! ” እያለ ግን ምን ዐይነት ዐይን ነው ያላት ! ” ሲል ተደነቀ ቤተልሔም ቆመችበት ተቁነጠነጠች ። ፊቷ ተለወጠ ። ለማ ቶሎ የሚሔድ ከሆነ የተጀመረው ነገር አሁኑኑ
ማለቅ አለበት ። ከአስተማሪነቱና ከተማሪነቱ መውጫ የሚገናኙበትን ቀጠሮ ማበጀት አለባቸው።ቤተልሔም ነገሩን በይደር መተወኑ አልፈለገችም ። ምናልባት ይህ አሁንበለማ ውስጥ ያበበው የሰሜት ተስፋ፡ ነገ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሐሜትን ፈርቶ ፥ ቁጥብነትን ፈልጎ ወይም በሌላ ምክንያት ሊጠወልግ ይችላል ። ይህ ከሆነ ደግሞ ወጥመዷ መክሸፉ ነው ። እና አሁኑኑ በአስቸኳይ ልቡ ሳያጋድል የስሜት እሳቱ ሳይበርድ ቀጠሮ ከአፉ ከወጣች ለመቼም ቢሆን ግድ የለም ። ቃሉን አጥፎ ወደ ኋላ እንደማይል ታውቃለች። ካወሩት እንዳደረጉት ይቆጠራል ። ነገሩ !እንደ ደስታዋና እንደ ድንጋጤዋ ጊዜ ሁሉ ፥ አሁንም ለጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ ለመስጠት ስሜቷ ስለ ተቁነጠነጠ ፥ ሽንቷ የመጣባት ፡ ውጥር አርጎ የያዛት መሰላትና እግሯን አኮራምታ ቆመች ።
የለማ ልብ ዐርፎ አልተቀመጠም ነበር ይንፈራንገጣል ። ከጥያቄዋና ከገጽታዋ ስሜቷን በሚገባ ተረድቷል ።አንዳች ሰይጣናዊ ስሜት ልቡን ገፋፋለትና እጅዋን ጎተት አርጎ ፡ ዝቅ ባለ ድምፅ
ልሔድ ስል አነጋግርሻለሁቻ ”አላት ።
“ እ ? ” ሳትሰማው ቀርታ ሳይሆን " ጆሮዋን ማመን አቅቷት ነበር ።
አልደገመላትም ።
ቶሎ የከፋው ልቧ ቶሉ ተደሰተ፤ እየተፍነከነከች ከሩጫ ባላነሰ እርምጃ ወደ ሽንት ቤት ሔደች ።
ጠረኗ ግን እዚያው ለማጋ ቀርቶ ነበር ። ወትዋች ህሊናው ደረቱን ገልብጦ ቡጢ ጨብጦ ግንባሩን አኮማትሮ የቤተልሔምን ጠረን ላለማሽተት አፍንጫውን ደፍኖ እሱነቱ ውስጥ ግትር ብሎ ቆሞ ተመለከተውኑ ሁለት ለማዎች!
ምንድን ነው ነውሩ ? ”መምህር የሚያስተምራትን ልጃ ገረድ ቢወድ ከሚወዳት ተማሪው ጋር ቢዳራ ምንድነው ነውሩ ?”
መውደድማ ባልከፋ ነበር ።ነገር ግን የወደደ ቸር ነው ። እና ማርክ አሰጣጥ ላይ , . . ደም የደደ ልብ ወዳጅ ሲወድቅ ዝም ብሎ አይመለከትም ።
እና ታዲያ?
እናማ ምርጫው ሁለት ነን !
"ኤጭ

#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ (MD)
አልጋችን ውስጥ ገብተን ተኛን፡፡ እንቅልፍ ቶሎ አልወሰደኝም፡፡ከነጮቹ ጋር ያደረኩት ስሜታዊ ድርጊት ምን እንደሆነ ማስብ ጀመርኩ፡፡እንዴት ማሂ እያለች እንደዚህ አይነት ስሜት ይሰማኛል? እንዴት
ቢያንስ ማሂ ፊት ስሜቴን መደበቅ አቃተኝ? ከማሂ ጋር ተኝቼ ውስጤ
ኢቫን በወሲባዊ ስሜት ያስባል፡፡ ምን አይነት እብደት ነው?፡፡ እንቅልፍ
ወሰደኝ፡፡
ጥዋት ተነስተን ተጣጠብንና ቁርስ በልተን ሁለት ሰዓት ላይ ወጣን፡፡ ባጃጅ ይዘን፣ አስጎብኚ ድርጅቶች ጋር ሄድን፡፡ የዶርዜ ሎጅ መጎብኘት እንደምንፈልግ ነገርነው፡፡
“ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ?”
“አዎ!”
“የሞላ መኪና አለ፡፡ ሂሳብ ክፈሉ።” የተጠየቅነውን ክፍያ ከፈልን፡፡ ባለድርጅቱ ከሌላ ልጅ ጋር አገናኘን፤
“ኑ፣ ፍጠኑ፡፡ እድለኛ ናችሁ፡፡”ተከተልነው።
“ከዚህ ይርቃል እንዴ?”
“ብዙም አይርቅም፡፡ ሰላሳ ኪ.ሜ. አካባቢ፡፡”
መኪናው ጋር አደረስን፡፡ እውነቱን ነበር፡፡ እንዳለው ሚኒባሱ ሞልቷል፡፡ ሁሉም በሚባል መልኩ፣ አብዛኛው ጎብኚ ፈረንጆች ናቸው።
ክፍት የነበረው የመጨረሻ ወንበር ላይ ሄደን ተቀመጥን፡፡ ወዲያው መኪናው ጉዞውን ጀመረ፡፡ የምናልፍበት ቦታ ሁሉ አረንጓዴ ነው።በየመንገዱ ማይሸጥ የፍራፍሬ አይነት የለም፡፡ ሙዝ፣ ሎሚ፣ አቡካዶ፣መንደሪንና የመሳሰሉት፡፡ የቦታው አረንጓዴነት፣ ከመሬቱ አቀማመጥ
ጋር እጅግ ውብ፣ መንፈስን የሚያድስ ነው፡፡
ሃኒ በምታየው ነገር ሁሉ፣ “ኦ... ሎርድ፣ እንዴት ያምራል!” ትላለች፡፡
“ምድራዊ ገነት ነች ያልኩሽ ዋሸሁ?”
“በፍፁም...!! እውነትም ምድራዊ ገነት፡፡ እንኳን እዚህ መጣን፡፡ሎርድ...ያቢዬ በናትህ ፎቶ ላንሳ ቦታ ቀይረኝ፤”
“እንዴ፣ እኔ አላነሳም እንዴ?”
ካሜራዬን አውጥቼ ማንሳት ጀመርኩ፡፡ ሃኒ “ዋው..፣ ይሄን ተራራ አንሳው፣ ሰማዩን አብረህ አስገባው፣ ዛፉን በከፊል...” ትላለች።
መልሳ ደግሞ፣ “ወይኔ ይሄኛው ሲያምር፣ እስቲ እኔም ላንሳ በናትህ፣” ተቁነጠነጠች፡፡ ቦታውን ቀየርኳት፤ ካሜራውን ሰጠኋት፤ ብዙ ፎቶዎችን
አነሳን፡፡ እያበላለጥን፣ እየተፎካከርን፣ እያደነቅን፣ ተደሰትን፡፡ እጅግ የሚገርም ብዙ ቅፅበታዊ ደስታዎች፡፡ በተፈጥሮ ተማርከን፤ ተዋጥን፣በደስታ ተንሳፈፍን፡፡ አስጎብኚያችን “አሁን ወደ ዶርዜ መንደር
ደርሰናል፤” ሲል ከሄድንበት የራሳችን የደስታ አለም ተመለስን፡፡አይተን፣ ተደስተን፣ አንስተን ግን፣ አልጠገብንም ነበር፡፡
ከመኪናው እንደወረድን፣ ሃኒ፣
“ዋ...ይ..!” ብላ ጮሃ ተጠምጥማብኝ፣ “እየው ያቡዬ” ትለኛለች፣ እጆቿን ወደ ፊታችን ቀስራ፡፡
“ኦ...፣ ማይ ጋድ! ምንድነው...? ሰው ነው?››
“ኖ ኖ...፣ እዚህ አሳ በብዛት ስላለ፣ አሳ ነው ሚሆነው::በአሳ ቅርፅ ነው የሰሩት፡፡ ሎርድ!”
“በጣም ግዙፍ እኮ ነው፡፡” ማንንም እየሰማን አይደለም፤ ቀስ ብለን እየተጠጋነው ነው፡፡ ምን አይነት ትልቅነት ነው? ምን አይነት ከፍታ ነው...?
“ጭንቅላት አለው፤ አፍንጫ አለው፤ አፍ አለው፤ ጆሮ አለው፤”ሃኒ በስሜት ሆና ትቆጥራለች፡፡
“ሃኒዬ ልንገርሽ? ይሄ የዝሆን ቅርፅ ነው፡፡”
“የስ..!፣ አሁን በትክክል ተመልሷል፡፡” ፈነጠዘች...!
“እስቲ ዝም ብለሽ እዪው:: ግዙፍነቱ፣ ወደ ላይ ያለው ከፍታ፣ኩንቢው፣ በረንዳው ነው:: አፉ በር ነው:: ጆሮዎቹ መስኮቶች ናቸው።
“... ፣ ሎርድ!፣ ምን አይነት ጥበብ ነው...! ምን አይነት እውቀት ነው...? ልቤ ልትቆም ሳግ ተናነቀኝ፡፡”
“ኧረ ፎቶ ሳንነሳ...!” ጮኸች ሃኒ፡፡
ውስጡ ገባን፤ እየዞርን አየነው፤ተሻሸነው፣ ታቀፍነው፣ እጅግ በጣም ብዙ ፎቶዎች ተነሳን፡፡ በተመለከትነው ኢትዮጲያዊ ድንቅ ጥበብ ነብሳችን ሃሴትን አደረገች፡፡ ፈረንጆቹ እንደ ተአምር ተደንቀው
ይመለከቱታል። ፎቶ ያነሱታል፡፡ የከተማ ህንፃዎች ለምን እንደዚህ አይነት የስነ ህንፃ ዲዛይን እንደማይጠቀሙ ገረመን፡፡ የምንችለውን ያክል ተዟዙረን አየነው:: በፎቶ ማስቀረት የቻልነውን ያክል አስቀረን፡፡ዶርዜዎች ለጥበብ የተፈጠሩ ህዝቦች ናቸው!፡፡ መመለስ ስላለብን
ተመለስን፡፡ ነብሳችን ግን እዛው ቀረች፤ አልተመለሰችም፡፡ ስላየነው ድንቅ ጥበብ ብቻ ስናወራ ተመልሰን አርባ ምንጭ ገባን፡፡ ደስታችን፣እርካታችን ቅጥ አጣ፡፡ እራት በላን፣ ከደስታችን የተነሳ የድካምም ስሜት አልተሰማንም፡፡ በየመጠጥ ቤቱና በየጭፈራ ቤቱ መዝናናት ጀመርን፡፡
እየጠጣን፣ ጨፈርን፣ ቤት እየቀያርን ተዝናናን፡፡ ደስ የሚል ልዩ ስሜት፡፡ እኩለ ለሊት እየሆነ ነው፡፡ የመጨረሻ አንድ ቤት እንይ ብለን የገባንበት ቤት፣ ደረጃውን የጠበቀና በቅርቡ እንደተከፈተ
የሚያስታውቅ፣ ሞቅ ያለ ጭፈራ ቤት ነው፡፡ ሙዚቃዉ ደርቷል፡፡በሚያምር የጭፈራ መብራቶች ታጅበው፣ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚጨፍሩ ሰዎች፣ አለባበሳቸውም ሆነ ውበታቸው አትለፉኝ፣
አትለፉኝ የሚሉ ቆነጃጂት ቤቱን ሞልተውታል፡፡ ከሃኒ ጋር እየተሽሎኮሎክን ወንበር ፈልገን ተቀመጥን፡፡ ሁለት ደብል ብላክ ሌብል አዝዘን፣ ሂሳብ በቅድሚያ ከፍለን እየጠጣን፣ ከቤቱ ጋር እስክንግባባ ወንበራችን ላይ ሆነን በቀስታ መደነስ ጀመርን፡፡ ስንገባም ሞቅ ስላለን፣ከቤቱ ጥሩ የሙዚቃ ምርጫ ጋር ተደምሮ የሞቀ ጭፈራ ጀመርን፡፡
ድንገት እነ ኢቫን ከበሩ በስተ ግራ በኩል ሆነው እንደ እብድ ሲደንሱ አየሁ፡፡ ከሃኒ ጋር እየጨፈርኩ፣ ልቤ ግን ኢቫ ጋር ሄዷል፡፡ ለምክንያት ሽንት ልሽናና ልምጣ ብዬ ወጣሁና ስመለስ ኢቫን አስደንሼያት
ተመለስኩ፡፡ ትንሽ ቆይቼ፣ ወደነሱ
ጋር ቦታ እንድንቀይርና እንድንቀላቀል አደረኩ፡፡ ደጋግሜ ኢቫን ወሲብ ቀስቃሽ ዳንስ አስደነስኳት፡፡ እያስደነስኳት እንደተማረኩባት ነገርኳት፡፡ እብደቱ
ብሶብኛል፡፡ ሃኒና ወፍራሟ ፈረንጅ ብዙ ሰዓት አብረው ይደንሳሉ፡፡ ከኢቫ
ጋር ተግባብተናል፡፡ አልጋ ይዜ ልምጣ አልኳት፡፡ አልተግደረደረችም፡፡
ይዤ መጣሁ፡፡
ውጪና ጠብቂኝ፡፡” በጆሮዋ አንሾካሾኩላት፡፡ በተራዋ ለጓደኛዋ
አንሾካሹካ ወጣች፡፡ ትንሽ ቆይቼ እኔም፣
“ሃኒዬ መጣሁ፣ ሽንት፡፡” ብያት ልወጣ ስል
“ያቡ ሰክረሀል ጠንቀቅ በል፧” አለችኝ፡፡
“ሃኒዬ፣ እኔን በዚች ሰክረሃል?”
“እሺ ለማንኛውም ጠንቀቅ በል፡፡”
“እሺ!” ብዬ ወጣሁ፡፡ እንደውጣሁ ኢቫን ወደ ያዝኩት ክፍል እያከነፍኩ ወሰድኳት፡፡ የተሰረቀ ነገር ሆኖብኝ አንገበገበኝ፡፡ በቁማችን ጀመርነው ልብሳችንን ተጋግዘን
አወልቀን፣ አልጋው ላይ ተወረወርንበት፡፡ ለዘመናት የተጠራቀም፣ የወሲብ አምሮት ያለብኝ እሰኪመስል፣ ሀይልና ስግብግብነት የተቀላቀለት ወሲብ ተዋሰብን፡፡ስንጨርስ ከውስጤ የወሲብ ሰንኮፍ ተነቅሎ የወጣ መስሎ ተሰማኝ፡፡
ስካሬ ለቀቀኝ፣ በምትኩ ሀፍረት ወረረኝ፡፡ ልብሴን በፍጥነት ለብሼ ቻው እንኳ ሳልላት ልወጣ፣ በሩን ሳብ ሳደርገው፣ አልተቆለፈም፡፡ ምን አይንት አብደት ነው፡፡ ሃኒን እንዴት ብዬ ነው ማያት፡፡ ቆይተን ይሆን? ትጠረጥረኝ ይሆን?፣ በፍጥነት ወደ ውስጥ ገባሁ፡፡
“ቆየሁ ሃኒዬ?”
“አይ ትንሽ፡፡ ደህና ነህ አይደል?”
“ደህና ነኝ፡፡ ሸንቼ ስመጣ ኢቫ ሲጋራ እያጨሰች አገኘኋት።
ንፋስ ለመውሰድ ትንሽ አወራኋት፡፡ የመጣልኝን ቀባጠርኩ፡፡
“አይ እንኳን ንፋስ ወሰድክ፡፡ አሁን ስካርህ የለቀቀህ ትመስላለህ፡፡” በአሽሙር እየተናገረችኝ መሰለኝ፡፡
“ሰከርክ ሰከርክ አትበይኝ እኔ ድሮም አልሰከርኩም፡፡” በእኔ ብሶ ኸኩኝ፡፡ ድካም ተሰምቶኛል፣ ፀፀት ተጨምሮበት እንደቅድሙ እየተጫወትኩኝ አደለም። አሁን የምፈልገው መውጣትና መሄድ ነው። ድንገት ቤቱ ውስጥ ትርምስና

❤1👍1
ጫጫታ ተፈጠረ። የብርጭቆ መሰበር ድምፅ ለመውጣት የሚደረግ ትርምስ ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልኩም "ኑ..ኑ...ውጡ ብዬ በሁለት እጆቼ ሶስቱንም እየገፈታተርኳቸው ወደ ውጨ ወጣን ግርግሩም ጫጫታውም ድንጋይ ውርወራውም ተከትሎን ውጪ ወጣ ከበሩ ፈቀቅ ብላ የቆመች ባጃጅ አየሁ ።
"ኑ ግቡ ኑ ግቡ ጮሁኩኝ።
ሾፌሩ የታል ሃኒ ጠየቀች። በአጠገባችን ምን የመመያክል ድንጋይ መሬት ነጥሮ አለፈ።እስካሁን አልተፈነከትንም።
ዝም ብላችሁ ግቡ ጮኽኩና ገፈታትሬ አስገባኋቸው እኔ ጋቢና ገባሁ ሹፌሩ አይቶን አልመጣም።ከአሁን አሁን ምን የሚያህል ድንጋይ አንዳችንን ሲተረክከን እየተሰማኝ ነው። ይሄ ሁሉ የኔ ሃጥያት ነው ዛሬ አይቀርልንም ብዬ አሰብኩኝ። በፍጥነት ከዚህ ቦታ መጥፋት አለብን። መሪው ላይ ቁልፍ መፈለግ ጀመርኩ። የለም ደንግጬለሁ። በፊልም ኤሌክትሪክ በጣጥሰው የቆመ መኪና አስነስተው ሚነዱት በአእምሮዬ ብልጭ አለብኝ። ጎንበስ ብዬ ገመድ መፈለግ ጀመርኩ። ከታች ብዙ ገመዶች አየሁ። የቱን ነው የምቆርጠው? ዝም ብዬ በደመነብስ ያገኘሁትን ገመድ እየጎተትኩኝ እታገላለሁ ቀና ስል ግርግሩ ቀንሷል።
“ምን እያደረክ ነው?” የሚል ድምፅ ሰምቼ ቀና ስል፣ ግዙፍ ቅልብ ጎረምሳ ፊትለፊቴ ቆሟል፡፡ ልቤ ፀጥ ልትልብኝ ነው፡፡

👍2❤1