#የታካሚው_ማስታወሻ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)
“አንተ ብቻ አይደለኸም፡፡ ብዙ ሰው እንደዛ ይመስለዋል፡፡እንደውም ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ የእንስሳት ዶክተር ጓደኛዬ
የገጠመውን ልንገራችሁ፤” አለን እየሳቀ፡፡
“እሺ ንገረን፡፡”
“የንሰሃ አባቱ ዶክተር ሲባል፣ የሰው ሃኪም እንደሆነ ይመስላቸው፡፡”
“እሺ፡፡
“እና ንሰሃ ሊገባ እርሳቸው ጋር ይሄድና፣ አባቴ ሃጥያት ሰርቻለሁ፤ ይፍቱኝ ልሎት ነው የመጣሁት፤' ይላቸዋል፡፡ እሳቸውም
'ልጄ፣ ሰው ሆኖ ሃጥያት ማይሰራ ማን አለ? እግዚአብሄርስ ንሰሃን የሰራልን ይህን አውቆ አይደል? በል ንገረኝ ልጄ እፈታሃለው፤ ይሉታል።
አባቴ የኔስ ትንሽ ከበድ ያለ ነው፡፡ ይላል እየተቅለሰለሰ፡፡
አዬ ልጄ፣ ለሰው እንጂ ከብዶ ሚታየው፣ ለእርሱ ምን ይሳነዋል፣ አትፍራ ንገረኝ ልጄ፧' ይሉታል፡፡
“አባቴ ይፍቱኝ፣ ከታካሚዬ ጋር ወሲብ ፈፅሚያለሁ።
'አይ ልጄ፣ እንዳንተ ያሉ ዶክተሮች ሁሉ ሚወድቁበት፣ሚያጋጥም ነውኮ፡፡ አይዞህ ልጄ፣ ንሰሃ እሰጥሃለው፡፡ እግዚአብሄር
ይቅር ባይ ነው ፤ " ሲሉት፣
አባቴ እኔ ግን የእንስሳት ዶክተር ነኝ፣ ታካሚዎቼ... ብሎ ሳይጨርስ ደንግጠው፣
በስመአብ ወወልድ... እያሉ ሲደግሙ፣ እሱም ደንግጦ ወጥቶ ከንስሃ አባቱ በዛው ተቆራርጦ ቀረ፡፡” ካ....ካ... በጣም ሲያስቀን አመሸን፡፡
እነ ሃብትሽ በህይወቴ የቀሩኝ እንጥፍጣፊ ቅመሞች ሆነዋል፡፡ስለ ስራው ሲያወራ፣ የዶሮ እርባታ ስራ ጥሩ እንደሆነና ቢሾፍቱ ለዛ ስራ የተመቸች እንደሆነች ሲያወራ ሰማሁት። አስጨናቂ ሃሳቦቼ የተወሰነ ረገብ ብለውልኛል፡፡ ስልኬን ብዙ ግዜ ክፍት ማድረግ ጀመሪያለሁ፡፡ ሳሚና ማሂ አልፎ አልፎ ይደውላሉ፡፡ ማሂ በአቋሟ
ፀንታለች፡፡ እኔም እንደዛው፡፡ ሳሚ ስለማርገዟ ሰምቶ፣ አስረግዘህ ጠፋህ
አይደል?' እያለ ይቀልዳል፡፡ እስቅና ስለ ሜሪ እጠይቀዋለሁ፡፡ አሁንም ከሼባው ጋር እንደሆነች፣ ኤፍሬም ቦርኮ መንገድ ላይ እንደወጣና እንዳየው፣ በግቢው ያለውን አዲስ ነገር እየሳቀ ያወራኛል።
#እንጥፍጣፊ_መሻቶች...
ያለኝ ገንዘብ አየመነመነ ነው፡፡ አንድ ነገር ካላደረኩ፣ ከዚህ በኋላ ከአንድ ወር በላይ መንቀሳቀሻ ገንዘብ አይኖረኝም፡፡መኪናዬን ለመሽጥ በውስጤ ዝግጅት እያደረኩ ነው፡፡ ለመሸጥ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ ስጠጣ አምሽቼ ተኛሁ፡፡ ከእንቅልፌ ስነቃ የተለየ ስሜት
እየተሰማኝ ነው፡፡ ደስ ሚል ስሜት፣ የፈነደቀ፣ የበራ ውስጠት እየተሰማኝ ነው፡፡ ከአልጋዬ እንደተነሳሁ፤
“ኋት ኤ ብራይት ዴይ ኢዝ ቱዴይ...?”
“ቱዴይ ኢዝ ሳተርዴይ...”
“ኢት ኢዝ ማይ ብርዝ ዴይ...።” ብዬ ሳላስበው ቅኔ ተቀኘሁ፡፡
ወይኔ... ዛሬ ልደቴ ነው እንዴ? እኔኮ አንዳንዴ ሳላስበው በልሳን ምናገረው ነገር አለ፡፡ ልደቴን አላውቀውም። ግን ማን ያውቃል፣ዛሬ ሊሆን ይችላል እኮ..፡፡ ቢያንስ አንድ ሶስት መቶ ስልሳ አምስተኛ
ትክክል የመሆን እድል አለኝ፡፡ ማክበር አለብኝ፡፡
ሻወሬን ወሰድኩኝ፣ ጺሜን ተለጫጨሁ፣ አፍተር ሼቭ፣ ሽቶ ተቀባባሁ። ድንገት እብደቴ እየተነሳ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ ከወራት በኋላ፣ ለመጀመሪ ግዜ ከውስጤ ሳልጠጣ ደስ ሚል ስሜት እየተሰማኝ ነው:: ፈገግ ልል፣ ልስቅ ልጫወት ነው:: እብደቴን አውቀዋለሁ። እወደዋለሁ።
እሱ ይሻለኛል። ዝለል፣ ዝላል፣ ፈንጥዝ፣ ፈንጥዝ ይለኛል። ህይወት የፈካች አበባ፣ ብሩህ ሆና ትታየኛለች፡፡ ቀላልና አጓጊ ያደርግልኛል። ለባብሼ ስጨርስ፣ ምሳ ደርሷል። ወጥቼ ለራሴ ምርጥ ክትፎ ጋበዘኩት።ከምሳ በኋላ መኪናዬን አስነስቼ ዝም ብዬ ነዳሁኝ፡፡ ወዴት፣ ለምን፣
እንደምሄድ አላውቅም፡፡ ብቻ ደስ ብሎኛል። ፍንትው፣ ብርት፣ እንዳልኩ
ሳላስበው እዛው ዱከም ደንበኛዬ ጋር እራሴን አገኘሁት። መሄጃ የለኝም
ገባሁ። ያልተለመደ፣ሞቅ ያለ ስላምታ ሰጠኋቸው። ደስ ሲለኝ መደበቅ
አልችልም:: ፊቴ ያሳብቃል።
“እንዴት ነሽ...? ሰላም ነዉ...?” አልኳት ባለቤቷን፡፡
“አለን፡፡ እንዴት ነህ አንተ? ግባ!።” የቤቱ ባለቤት ወደ ተለመደዉ ቦታዬ እየጠቆመችኝ፡፡
“ዛሬ እምሮብሃል። ፍክት ብርት ብለሃል። ምን ተገኘ?”
“ልደቴ ነው። ዛሬ ከበር መልስ ግብዣ በኔ ነው::”
“እንኳን ተወለድክልን። ልደትህ ከሆነማ፣ እኛ ነን መጋበዝ ያለብን።”
“አመሰግናለሁ። ግን፣ የደስታዬ ቀን ስለሆነ፣ ግብዣው በኔ ነው። ብቻ ዛሬ
ልዩ እንክብካቤ ያስፈልገኛለ፤” ብዬ ጥጌን ይዤ ተቀመጥኩ ብዙም ሳትቆይ ሚያስፈልገኝን ሁሉ አምጥታ
አስቀመጠችልኝ፡፡ ቤተኛ ሆኛለሁ። ሚያስፈልገኝን፣ ልኬን፣ ሁሉን
አውቃለች፡፡ ዛሬ እንደ ከዚህ ቀደሙ፣ ስልኬ ላይ አልተደፋሁም: መሄጃ
ስላጣው እንጂ መቃም ሳይሆን ሰው ነው ያማረኝ፡፡ ለሳምንታት ሰው አስጠልቶኝ ከሰው እንዳልሽሽው፣ ዛሬ ከሰው ማውራት፣ መቀለድና መሳቅ አማረኝ፡፡ ከእነርሱ ጋር እየተጫወትኩ፣ እየቀነጣጠብኩ መቃም ጀመርኩ፡፡ ትንሽ እንደቃምኩ፣ አንድ ጥቁር በጥቁር የለበሰች ረጅም፣ ቁመናዋ የተስተካከለ፣ ቆንጅዬ ልጅ ገባች፡፡ እንዳየኋት ዐይኖቼን
ተክዬባት ቀረሁ፡፡
መጀመሪያ እዚህ ቤት መምጣት የጀመርኩ ሰሞን፣ ባለቤትየዋ እዚህ ከሚመጡ ደንበኞቼ ለየት ትላለህ፤' ያለችኝ ትዝ አለኝ፡፡ ልጅቷ ፅድት ያለች ናት:: ውብና ማራኪ! እኔም እስከዛሬ እዚህ ቤት ሲመጡ ካየኋዋቸው ሴቶች ተለየችብኝ፡፡ ሳሎኑን ተሻግራ፣ በመጋረጃው ጀርባ
ወደ ውስጥ ገባች። ከቤቱ ባለቤት ጋር እንደጓደኛ ሰላም ተባብለው እየተሳሳቁ ያወራሉ፡፡ ቤተኛ ነች፤ ይተዋወቃሉ ማለት ነው? ግን ሲታዩ፣ ፍፁም በተለያየ ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች ይመስላሉ፡፡ባለቤትየው፣ ሱስ ያጎሳቆላት ከሲታና የወየበች ናት፡፡ ይቺ ደግሞ፣ የቆዳዋ ጥራት፣ በታይቷ ውስጥ የሚታየው የተመቸው ሰውነት፣ ሱስ ባለፈበት አልፋ
ምታውቅ አትመስልም። እንዴት ተዋወቁ? ምን አገናኝቸው? ጓደኛማ በፍፁም ሊሆኑ አይችልም:: ከወደ ጓዳ ውስጥ የሚስማውን እንቅስቃሴ እያዳመጥኩ ግንኙነታቸውን ለመገመት እሞክራለሁ፡፡
ትንሽ ቆይታ ልጅቷ መጋረጃውን ከፍታ ወጣች:: በኔ ተቃራኒ ከመጋረጃው ጠርዝ መጅሊስ ላይ ተቀመጠች። ባለቤትየዋ ሺሻ አምጥታ ለኮሰችላት። አሁንም ያወራሉ። ሺሻውን ተቀብላ ማጨስ
ጀመረች፡፡ አትመስልም። በፍፁም ሱስ ባለፈበት ያለፈች አትመስልም።
እንደማያት አንድታውቅ ፈልጌያለሁ። ዐይኔን ተክዬ ቀረሁ:: እጅግ ውብ
ነች፡፡ ፀጉሯ ሉጫነቱ እርዝመቱ፣ ስስ ከንፈሮቿ ከተቀባችዉ ሊፒስቲክ
ጋር እንጆሪ ይመስላሉ። ጉመጣት ጉመጣት የሚል ስሜት ተሰማኝ።
ወተት እንደጠጣች ድመት፣ የራሴን ከንፈር በምላሴ ላስኩት፡፡ የቀይ
ዳማ ናት፡፡ ጥቁር አይኖቿን ሰማያዊ አይ ሻዶው ተቀብታቸዋለች። አማላይ የውበት እመቤት ትመስላለች፡፡
“ከእርሷ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት.
ላፈር አይደለም ወይ የተፈጠርኩት...” የተባለላት ትመስላለች፡፡
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍3