#ሐኑን
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
በዝምታ ገባን፡፡ ገና እንደገባን ሔራን አቅፉ ከንፈሬን ሳመችኝ፡፡ ድንገተኛ ነበር፡፡ እናም "ይበቀሃል፡ አንዳንዴ ነገሮች ካልተውካቸው ዛሬን ማየት አትችልም ብላ ሳቀች።
ዓይኖቿን እያየሁ፣ “ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ!" አልኳት፡፡
በቃ እንደዚህ ነው የምታመሰግነው ወደራሴ ሳብኳት፡፡ ሰፊው አልጋ ላይ ተያይዘን ወደቅን ለዓመታት እንደ ሐውልት ውስጤ ገዝፎ የቆመ የሐኑን ፍቅር፣ ትዝታ እና መሻት ሁሉ አብሮ የወደቀ የተንኮታኮተ መሰለኝ፡፡ ከአንዲት ሴት ወደ ሌላ ሴት መሄድ መዳረሻዬ ሳይሆን መንገዴ መስሎ ተሰማኝ፡፡ ከአንዷ ወደ ሌላዋ ሲረማመዱ የመኖር ጅማሬ፤ ትንሽ ጸጸት ጋር፡፡ የሐኑን ነገር ግን የዚያን ቀን ፍጻሜው ሆነ አልኩ፡፡ ሔራን
አንገቴ ሥር ተሸጉጣ በሹክሹክታ የምታወራውን ብዙ ብዙ የፍቅር ቃል ወንድነቴ ያደመጠው፣ ለሞተው ፍቅሬ እንደሚነበብ የሕይወት ታሪክ ነበር፡፡ ዓይኖቼን ስከድናቸው የሒራን ጠይም ሰውነት የሐኑንን ቅላት ለብሶ ይታየኛል፡፡ማንን እንደምክድ እንጃ፤ የሆነ ክሕደት እየፈጸምኩ መስሎ ይሰማኛል ፡፡ ሔራንን በተለያየ ልብስ ላስባትና ሐሳቤን ልመልሰው በቁንጅናዋ እራሴን ላማልል እታገላለሁ፡፡ “ሔራንኮ ናት ከሥርህ
ያለችው፣ያቺ ምድረ ወንድ የሚያፈጥባት ጠይም ሳቂታ ሔራን ቆንጆዋ ሔራን
እለዋለሁ ለራሴ፡ ውብ ከንፈሮቿን፣ አንዳች ንዝረት የሚለቁ ዓይኖቿን፣ ማንንም ወንድ
የሚፈትኑ ጡቶቿን ባወጣ ባወርድ፣ በእጆቿ ፋይል ይዛ በጉርድ ቀሚስ ወዲያ ወዲህ ስትል ብቻ ነው የምትታየኝ፡፡ ከላያችን ላይ የደረብነውን አንሶላና ምናምን ብገልጠው፣ በግራና በቀኝ እጇ ፋይል እንደያዘች፡ ከነጉርድ ቀሚሷና ከተረከዘ ረጅም ጫማዋ፣ ከሥሬ የተኛች መስሎ ነበር የሚሰማኝ፡፡የሆነ ቢሯችን ውስጥ መሬት ለመሬት የሚሳብ
የኮምፒውተር ገመድ ጠልፎኝ እላይዋ ላይ የወደኩ ዓይነት፡፡
ከሔራን ጋር በአዲስ “ፍቅር መክነፍ ጀመርን፡፡ በተገናኘን ቁጥር የመጀመሪያ ሥራችን አልጋ ላይ መውደቅ ነበር፡፡ ለስሙ ፍቅረኞች ነን እንጂ በሳምንት ውስጥ የሚበዙት ቀኖች አዳሯ እኔ ጋር ነበር፡፡ ቅዳሜና እሁድ አብረን ነን፡፡ ቤቱን እየገዛች በምታመጣው እቃ ሞላችው፡፡ ከማብሰያ እስከመኝታ ቤት፡ የሔራን አሻራ ያላረፈበት እቃ የለም፡፡ቤቱ በወራት ውስጥ፣ አስር ዓመት በትዳር የቆዩ ባለትዳሮች ቤት መሰለ፡፡ ቁምሣጥኑን
ስከፍተው፣ ከእኔ ልብስ ይልቅ የሔራን ይበዛ ነበር፡፡ ወርቃማ የፀጉር ዘለላ የማይገኝበት የቤቱ ክፍል የለም፡፡ ከእሷ አልፎ እህቶቿ ቅዳሜና እሁድ እየመጡ፣ ቡና አፍልተው ሲያውካኩ ውለው ይሄዳሉ፡፡ ልክ ዛሬ እንደተወለደ ሰው፤ ነፍሳቸው ስለነገ ብቻ የሚጨነቅ፣ ወደኋላ የሚባል ነገር የማያውቁ ልጆች ናቸው፡፡ ሲመጡ ደስ ይለኛል፡፡አንዳንዴ እንዲያውም እራሴ እየደወልኩ “ምነው ጠፋችሁ?” እስከማለት ደርሼ ነበር፡፡
የሐኑን ነገር እየደበዘዘ ሄደ፣ ከአእምሮየ የጠፋ እስኪመስለኝ፣ የሐኑንን ጠረን በሔራን ጠረን የመለወጥ ትግል ላይ ነበርኩ፡፡ ወይም ሔራን እራሷ የነብሴ ጥጋጥግ የተገነባዉን የሐኑን መታሰቢያ ሁሉ እያፈራረሰች የራሷን አዲስ መንግሥት እየተከለች ነበር…እንጃ!
አንዴ ሜዳ ሁኛለሁ.…የፈለጉትን ሲተከሉ ሲነቅሉ ተው የሚል ወኔ አልነበረኝም፡፡
ሔራን ፈጣን ናት፡፡ ቆሜ ማሰብ እንኳን እስከሚያቅተኝ፣ ጥድፊያዋ ለጉድ ነበር፡፡ ምንም ነገር ትበለኝ አደርገዋለሁ፤ በራሴ አስቤ ግን አንድም ነገር አላደርግም፡፡ እንስፍስፍ ካለ ፍቅር ይልቅ፣ ራሴን እሷ ላይ ጥዬ ያደረገችኝን ታድርገኝ ወደሚል ስሜት ያዘነበለ ግንኙነት ነበር በመሃላችን የነበረው፡፡ “ከቤተሰቦችህ ጋር አሰተዋውቀኝ አለችኝ፣ ወስጄ
አስተዋወቅኋት፡፡ ወደዷት! አሁን ገና የምትሆንህን አገኘህ ተባለ፡፡ ከቤተሰቦቿ ጋር ወስዳ አስተዋወቀችኝ! የገደል ስባሪ የሚያካለዉ ወንድሟ ቀልቡ ወደደኝ፡፡ እውነቱን ለመናገር እኔም ወድጄው ነበር፡፡ የዓለም ቀልድ ሁሉ እሱጋ ነበር፡፡ ውሃ ቀጠነ ብሎ ከሰው ጋር ከመደባደብና ከመታሰር በተረፈው ጊዜ ሁሉ፣ መሳቅ ሥራው ነበር፡፡ በድፍን ከተማው
በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ስሜ በዋስትና ለመመዝገብ የበቃው፣ ይኼው ልጅ በታሰረ ቁጥር ለማስፈታት ስል ነበር፡፡ እሱም ታዲያ ለገላጋይ አስቸግሮ ዘራፍ ሲል፣ እኔ ከተናገርኩት ግን አደብ ይገዛ ነበር፡፡ እሰቲ ይሄንን ልጅ አንድ በለው፣ አንተን ነው መቼም የሚሰማው ትለኛለች ሔራን፡፡ የሆነ በቤተሰብ ድር የመተብተብ ሳላገባት በቤታቸው የምከበር ወሳኝ ሰው የሆንኩ መስሎ እንዲሰማኝ የማድረግ ጨዋታ፡፡ አልናገረው እንጂ በዙሪያየ የምታደራው ድር ነፍሴ ይገባታል፡፡ እጅ የሰጠን ሰው ለመማረክ የምትደክመው
ነገር ይገርመኛል፡፡
እንደሷው ፍጥን ካሉ ሁለት ቆንጆ እህቶቿ እና እናቷ ጋር ተዋወቅሁ፡፡እንደ አስከሬን
ለአራት ተሹመው ወደቀብሬ እያዳፉ የሚወስዱኝ እስኪመስለኝ ድረስ ወሬያቸው ሁሉ ሰርግና ጋብቻ ብቻ ነበር፡፡ በመጨረሻ ሔራን እራሷ እስከመቼ ነው እንዲህ የምንኖረው?ለምን አንጋባም!?” አለችኝ፡፡ ብንጋባ ከዚህ የተለየ ምን ይመጣል ብዬ ተስማማሁ፡፡ሔራንን ወድጃት ነበር፡፡ የማልወድበት ምንም ምክንያት አልነበረኝም፡፡ የማላገባባትም
እንደዚያው፡፡ እናም “ልክ ነሽ እንጋባ!” አልኳት፡፡ መውደድ ብቻ! ልክ እንደምወደው ምግብ፡ልክ እንደምወደው ፊልም፣ እንደምወደው ልብስ፣ እንድመወደው ምናም ሔራንን ወደድኳት እናም እንጋባ ስትለኝ እሽ አልኩ፡፡
“ጠይቀኛ ሽማግሌ ላክ፤ለምንድን ነው እኔ የሆነ ነገር እስከምል የምትጠብቀኝ?
ወደ ትዳር የሚወስደውን መንገድ እጄን ይዛ መራችኝ፡፡ ባለማመደችኝ ድገተኛ
አጠያየቅ፣ ሰው በተሰበሰበበት ታገቢኛለሽ ወይ? ብዬ ተንበርክኬ ጠየኳት፣ እስካሁን የሚገርመኝ ለምን እንዳለቀሰች ነው፡፡ ያዩን ሁሉ አጨበጨቡ፡፡ ወደቤተሰቦቿ ሽማግሌ
ላውሁ፡፡ ሽማግሌዎቹ ወደነ ሔራን ቤት ሲሔዱ ፣ሔራን እኔ እኔ ኤልጋችን ውስጥ
ነበርን፡፡ ሽማግሌዎቹ ደውለው እንኳን ደስ ያለህ ተሳክቷል” ሲሉኝ “ምኑ?” የሚል ቃል ሊያመልጠኝ ከከንፈሬ ጫፍ ነበር የመለስኩት፡፡ ሔራን ታዲያ ደረቴ ላይ እንደተለጠፈች
(የልብ ምቴን የምታዳምጥ ይመስል) ብዙም ደስ ያለህ አትመስልም” አለችኝ።
ቤተሰቦቻችን ደስታ አናታቸው ላይ ወጥቶ ሽር ጉድ ማለት ጀመሩ፡፡ እንደ ሰርግ
የሚያስጠላኝ ገር የለም፡፡ በሩቁም እፈራው ነበር፡፡ እየተጎተተ መጥቶ ቤቴ በር ላይ አንድ እግሩን አሳረፈ!!
አንድ ምሽት ከሔራን ጋር እራት እየበላን፣ ስለሚዜ ፡ ስለቬሎ፣ ስለኣዳራሽ፣ ስለ ጥሪ ካርድ ስለቀለስት ስናወራ (ስለ አንድ ነገር ሺህ ጊዜ ደጋግሞ ማውራት እንዴት
ይሰለቻል) ድንገት ስልኬ ጠራ፡፡ ዓይኔን እንደዋዛ ጠረጴዛው ላይ ድምፁን አጥፍቶ
ወደሚበራው ስልክ ላከሁ፤የልቤ ምት የቆመ ነበረ የመሰለኝ፡፡ሐኑን…! ስሟ አልነበረም፣ከስልኬ ላይ ካጠፋሁት ቆይቻለሁ፡፡ ቁጥሮቹ እነዚያ ስምንት ቁጥርን የትም ስመለከት፣ልቤ በኃይል እንዲመታ ያደረጉኝ ሦስት ስምንት ቁጥሮች ያሉበት ስልክ ቁጥሯ፡፡
ልጎርስ ያዘጋጀሁትን ጉርሻ ወደ ሰሃኑ መልሼ ተነስቼ ወጣሁና፣ አንድ ጥግ ላይ ቁሜ አነሳሁት፡፡
"ሄሎ"
ሄሎ" ያ በደም ሥሬ ውስጥ የሚፈስ የሚመስለኝ ድምፅ ከእግር ጥፍሬ እስከ እራስ ፀጉሬ ሲነዝረኝ ተሰማኝ፡፡ ሌላ ምንም ሳትተነፍስ አእምሮዬ ከተለያየንበት ቀን እስከዚያች
ቅጽበት ድረስ የነበረ ታሪኬን ሁሉ ሰርዞ ከቆመበት ማሰብ ጀመረ፡፡ መቸ ነው ከሐኑን ጋ የተለያየነው? ከትላንት ወዲያ?ትላንት? ቅድም? ወይንስ አልተለያየንም?
"ሐኑን!?
"አታውቀኝም ብዬ ፈርቼ ነበር” ድምፅዋን ስሰማ አለቀሰች፣ ሞተ፣ ያልኩት ትዝታዬ

👍2❤1
ሁሉ አፈሩን አራግፍ ሲነሳ ይሰማኝ ነበር፡፡ እያለቀሰች መሆኑ የገባኝ በኋላ ነው ፡፡
“ምን ሁነሻል? ሰላም ነሽ!”
"አባባ ሞተብኝ!" ደንግጨ ዝም አልኩ፡፡ ማጽናናትም ቃል ማውጣትም አልቻልኩም።ከረዥም ዝምታ በኋላ
"መቼ…?” አልኩ።
"አንድ ወር ሆነው፤ ትሰማለህ ብዬ ነበር፡፡”
“ማንም አልነገረኝም፡፡ ከማንም ጋር አልገናኝም እዛ ድሬዳዋ አልፎ አልፎ እንደዋወል ከነበሩ ጓደኞቼ ጋር ሁሉ ከተለያየን ቆየን፡፡
እኔም አልደውልልህም ነበር፣ ግራ ገብቶኝ ነው"
“ምነው ችግር አለ? ሐኑን ንገሪኝ…”
አባቷ ሞተው ገና በወሩ እነዚያ በጥላቻ ያበዱ ወንድሞቿ፣ ቤቱንም የሰውዬውንም
ንብረት ሁሉ መነጣጥቀው አስወጥተው ጥለዋት፣ መሄጃ ቸግሯት ነበር፡፡ ስባራ ሳንቲም እጇ ላይ አልነበረም፡፡ የምትይዘው የምትጨብጠው አጥታ ታለቅሳለች፡፡
አሁን የት ነው ያለሽው!”
“የአባባ ጓደኞች ሳይቀሩ በቤተሰብ ጉዳይ አንገባም እያሉ ሽሹኝ…ትምህርት ቤት
የማውቃት ልጅ ቤት ዓይኔን አፍጥጨ ሄድኩባት…እሷ ጋር ነኝ”
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍1
#አወይ_የኛ_ነገር!
አወይ የኛ ነገር!
ከለም ምድር መጥተን በቅለን ከጀግና ዘር”
አያልቅ ታሪካችን
ቢወሳ ቢነገር ቢጻፍ ቢዘረዘር
አወይ የኛ ነገር !...
ወራሪ ባዕዳንን መክተን መልሰን
ባላንጣን ጨርሰን ጀግነን ደምስሰን
ሁሉንም አዳርሰን ዳግም ተመልሰን
በጉጥ ተጉጥጉጠን በጉሳ ተጓጉሰን
እርስ በርሳችንም እንደጊንጥ ተናክሰን
ስንቱን አሳልፈን
ከዛም አልፈን ተርፈን
የሕብረታችንን ካብ በዘር አፈራርሰን
ያንድነትን መንፈስ አቅልለን አርክሰን
እንደ ድፎ ዳቦም ዳር ድንበርን ቆርሰን
ሰላም ተጠምተናል በሰላም ለግሰን፡፡
ከለም ምድር ወጥተን በቅለን ከጀግና ዘር
አያልቅ ታሪካችን
ቢወሳ ቢነገር ቢጻፍ ቢዘረዘር
አወይ የኛ ነገር !...
መግደል የወደድን መሞት የለመድን
እንደዕዳ ከብዶን ሰላምን ማውረድን
እየተበዳደልን
እየተገዳደልን
አቅቶን መታረቅ፣ .
እኛ እንዳለን አለን ዘመን ሲፈራረቅ፡፡
አለም ምድር ወጥተን በቅለን ከጀግና ዘር
አያልቅ ታሪካችን
ቢወሳ ቢነገር ቢጻፍ ቢዘረዘር
አወይ የኛ ነገር !
ዓለም ሳይሰለጥን ቆድመዓለም ሠልጥነን
ታሪክ ሠሪ ዘሮች እኛ ነን እኛ ነን፡፡
ዛሬ በዓለም ላይ
የደሃዎች ደሃ
የዓለም መጨረሻ ኋላ ቀሮች ሆነን
በስደተኝነት
በረሐብተኝነት
በዜና ቢስነት
የምንታወቀው ከዓለም በላይ ገነን
ታሪክ ሠሪ ዘሮች እኛ ነን እኛ ነን፡፡
ከለም ምድር ወጥተን በቅለን ከጀግና ዘር
አያልቅ ታሪካችን
ቢወሳ ቢነገር ቢጻፍ ቢዘረዘር
አወይ የኛ ነገር !...
እንደ ጥንቸል ፈጥነን ሩጠን ሲደክመን
እንቅልፍ ሲወስድን ለማረፍ ተጋድመን
እኛ ጉድ ሆነናል በኤሊ ተቀድመን፡፡
አያልቅ ታሪካችን
ቢተረክ ቢተረክ ቢተረት ቢተረት
አወይ የኛ ነገር .
ኤሊን ንቆ መተኛት ጥንቸል ሆኖ መቅረት።
አወይ የኛ ነገር!
ከለም ምድር መጥተን በቅለን ከጀግና ዘር”
አያልቅ ታሪካችን
ቢወሳ ቢነገር ቢጻፍ ቢዘረዘር
አወይ የኛ ነገር !...
ወራሪ ባዕዳንን መክተን መልሰን
ባላንጣን ጨርሰን ጀግነን ደምስሰን
ሁሉንም አዳርሰን ዳግም ተመልሰን
በጉጥ ተጉጥጉጠን በጉሳ ተጓጉሰን
እርስ በርሳችንም እንደጊንጥ ተናክሰን
ስንቱን አሳልፈን
ከዛም አልፈን ተርፈን
የሕብረታችንን ካብ በዘር አፈራርሰን
ያንድነትን መንፈስ አቅልለን አርክሰን
እንደ ድፎ ዳቦም ዳር ድንበርን ቆርሰን
ሰላም ተጠምተናል በሰላም ለግሰን፡፡
ከለም ምድር ወጥተን በቅለን ከጀግና ዘር
አያልቅ ታሪካችን
ቢወሳ ቢነገር ቢጻፍ ቢዘረዘር
አወይ የኛ ነገር !...
መግደል የወደድን መሞት የለመድን
እንደዕዳ ከብዶን ሰላምን ማውረድን
እየተበዳደልን
እየተገዳደልን
አቅቶን መታረቅ፣ .
እኛ እንዳለን አለን ዘመን ሲፈራረቅ፡፡
አለም ምድር ወጥተን በቅለን ከጀግና ዘር
አያልቅ ታሪካችን
ቢወሳ ቢነገር ቢጻፍ ቢዘረዘር
አወይ የኛ ነገር !
ዓለም ሳይሰለጥን ቆድመዓለም ሠልጥነን
ታሪክ ሠሪ ዘሮች እኛ ነን እኛ ነን፡፡
ዛሬ በዓለም ላይ
የደሃዎች ደሃ
የዓለም መጨረሻ ኋላ ቀሮች ሆነን
በስደተኝነት
በረሐብተኝነት
በዜና ቢስነት
የምንታወቀው ከዓለም በላይ ገነን
ታሪክ ሠሪ ዘሮች እኛ ነን እኛ ነን፡፡
ከለም ምድር ወጥተን በቅለን ከጀግና ዘር
አያልቅ ታሪካችን
ቢወሳ ቢነገር ቢጻፍ ቢዘረዘር
አወይ የኛ ነገር !...
እንደ ጥንቸል ፈጥነን ሩጠን ሲደክመን
እንቅልፍ ሲወስድን ለማረፍ ተጋድመን
እኛ ጉድ ሆነናል በኤሊ ተቀድመን፡፡
አያልቅ ታሪካችን
ቢተረክ ቢተረክ ቢተረት ቢተረት
አወይ የኛ ነገር .
ኤሊን ንቆ መተኛት ጥንቸል ሆኖ መቅረት።
#ጠርጥሪኝ
ጠልተሽኝ ስትሔጂ...
መጠላቴን ይዤ ፥ ተከትዬሽ መጣሁ
“አጣሁሽ” ባልልም
የትም እንዳገኝሽ ፥ ከሰውነት ወጣሁ፡፡
የትም ሁኚ የትም
ባለሽበት ቦታ ፥ እኔ አለሁ ጠርጥሪ
መስታወትሽ ሆኜ...
ቤትሽ እገባለሁ
ገላሽ ለማየት ፥ ልብስ ስትቀይሪ፡፡
በመንገድ ስታልፊ..
በመጥፎ አይነት ጠረን ፥ አፍንጫሽ ሲመታ
ከሰውነት ተራ
ወጥቼ የምኖር ፥ እኔ ነኝ ያ ሽታ።
ጠርጥሪኝ!
ገላሽ ፀሐይ ሲሞቅ ፥ እኔ ነይ ፀሐዩ
እንቅፋት ሲመታሽ ፥ እኔ ነኝ ድንጋዩ
ቀና ብለሽ ብታይ ፥ እኔ ነኝ ሰማዩ
በሔድሽበት እና
በቆምሽበት ቦታ
እኔ ነኝ መሬቱ ፥ እኔ ነኝ ድልድዩ ።
ድንገት ዝናብ ጥሎ
ገላሽን ከነካው ፥ ያ ዝናብ እኔ ነኝ
ጠርጥሪኝ!
ትንኝ ካይንሽ ውስጥ ፡ ገብቶ ሲያስለቅስሽ
በሻፋዳ ነፋስ ፥ ሲገለብ ቀሚስሽ
ጉንዳን ጭንሽ መሐል ፥ ቆንጥጦ ቢነክስሽ
ቆንጅተሽ ስትሔጂ...
ቅናተኛ አቧራ ፥ ተነስቶ ቢያለብስሽ
እኔ ነኝ ጠርጥሪኝ!
ነፋሱ ትንኙ ፥ ጉንዳኑም እድፉም
ኩል እና ጥላሸት
አለሁ ባለሽበት ፥ በደግም በክፉም፡፡
ፍፁም ፅዳትሽ ላይ..
ተባይ ብታገኚ ፥ ተጣብቆ ከገላሽ
ሰው ሆኜ ምትወጂኝ…
ከሰውነት ተራ ፥ ስወጣ ማስጠላሽ
ከሰውነት ተራ ፥ ወጥቼ ምበላሽ
ያ ተባይ እኔ ነኝ
ጠርጥሪኝ!
ጠልተሽኝ ስትሔጂ...
መጠላቴን ይዤ ፥ ተከትዬሽ መጣሁ
“አጣሁሽ” ባልልም...
የትም እንዳገኝሽ ፥ ከሰውነት ወጣሁ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ጠልተሽኝ ስትሔጂ...
መጠላቴን ይዤ ፥ ተከትዬሽ መጣሁ
“አጣሁሽ” ባልልም
የትም እንዳገኝሽ ፥ ከሰውነት ወጣሁ፡፡
የትም ሁኚ የትም
ባለሽበት ቦታ ፥ እኔ አለሁ ጠርጥሪ
መስታወትሽ ሆኜ...
ቤትሽ እገባለሁ
ገላሽ ለማየት ፥ ልብስ ስትቀይሪ፡፡
በመንገድ ስታልፊ..
በመጥፎ አይነት ጠረን ፥ አፍንጫሽ ሲመታ
ከሰውነት ተራ
ወጥቼ የምኖር ፥ እኔ ነኝ ያ ሽታ።
ጠርጥሪኝ!
ገላሽ ፀሐይ ሲሞቅ ፥ እኔ ነይ ፀሐዩ
እንቅፋት ሲመታሽ ፥ እኔ ነኝ ድንጋዩ
ቀና ብለሽ ብታይ ፥ እኔ ነኝ ሰማዩ
በሔድሽበት እና
በቆምሽበት ቦታ
እኔ ነኝ መሬቱ ፥ እኔ ነኝ ድልድዩ ።
ድንገት ዝናብ ጥሎ
ገላሽን ከነካው ፥ ያ ዝናብ እኔ ነኝ
ጠርጥሪኝ!
ትንኝ ካይንሽ ውስጥ ፡ ገብቶ ሲያስለቅስሽ
በሻፋዳ ነፋስ ፥ ሲገለብ ቀሚስሽ
ጉንዳን ጭንሽ መሐል ፥ ቆንጥጦ ቢነክስሽ
ቆንጅተሽ ስትሔጂ...
ቅናተኛ አቧራ ፥ ተነስቶ ቢያለብስሽ
እኔ ነኝ ጠርጥሪኝ!
ነፋሱ ትንኙ ፥ ጉንዳኑም እድፉም
ኩል እና ጥላሸት
አለሁ ባለሽበት ፥ በደግም በክፉም፡፡
ፍፁም ፅዳትሽ ላይ..
ተባይ ብታገኚ ፥ ተጣብቆ ከገላሽ
ሰው ሆኜ ምትወጂኝ…
ከሰውነት ተራ ፥ ስወጣ ማስጠላሽ
ከሰውነት ተራ ፥ ወጥቼ ምበላሽ
ያ ተባይ እኔ ነኝ
ጠርጥሪኝ!
ጠልተሽኝ ስትሔጂ...
መጠላቴን ይዤ ፥ ተከትዬሽ መጣሁ
“አጣሁሽ” ባልልም...
የትም እንዳገኝሽ ፥ ከሰውነት ወጣሁ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ሐኑን
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
"የአባባ ጓደኞች ሳይቀሩ በቤተሰብ ጉዳይ አንገባም እያሉ ሸኙኝ...ትምህርት አቤት የማውቃት ልጅ ቤት ዓይኔን አፍጥጬ ሄድኩባት እሷ ጋር ነኝ"
ትንሽ ቆይቼ እደውልልሻለሁ ጠብቂኝ' ብዬ ስልኩን ዘጋሁና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አሰብኩ፡፡ ነፍሴ ተጨነቀች ውስጤ ርብሽብኝ አለ። የምይዝ የምጨብጠውን አጣሁ ምን ማድረግ እንዳለብኝ፣ ምኑም አልመጣልኝ አለ፡፡ እናም በደመነፍስ መልሸ ደውዬ
በሕይወቴ ማድረግ የሌለብኝን የእብድ ሥራ ሠራሁ፣ “ሐኑን ምንም አትጨናነቂ፣ብር እልክልሻለሁ፣ ወደ አዲስ አበባ ትመጫለሽ .…እሺ?”
እሺ!" አለች።እሺታዋ ውስጥ እፎይታ፣ ከስጋት የማረፍ፣ ተስፋ ነበር፡፡ አንድ ቃል
አእምሮዬ ውስጥ ደጋግሞ ይጮህብኝ ነበር፡፡ ከዚያስ? ከመጣች በኋላስ…? ከዚያስ? ከዚያስ ? ከዚያስ …? ከዚያስ ? መልሼ ደግሞ እና ምን ማድረግ ነበረብኝ? ሀብትና ጥላቻ እንደ አሸዋ ሞልቶ ከተረፋቸው ወንድሞቿ ጋር ለምን ከአባቷ ቤት አባረራችኋት? ብየ ልፋለም? ወይስ በሌለኝ አቅምና ጊዜ ጠበቃ ቀጥሬ ልሟገት? ምንም ይሁን ምንም
በሕይወት ውስጥ ተገናኝተናል፣ እንዲሁ ከመገናኘት ያለፈ ታሪክ ያለን ሰዎች ነን፣ ሥራ አለኝ፤ ሥራ የላትም፡ ብር አለኝ፡ ብር የላትም፣ የማርፍበት ቦታ አለኝ፤ የምታርፍበት ቦታ የላትም ከአንዲት ግቢ ወጥታ የማታውቅ ሚስኪን ልጅ፣ ከአባቷ ቀጥሎ በዚህች ምድር ላይ ወደምትቀርበው አንድ ሰው አድነኝ ብላ ደወለች፤ ማዳኑ ቢቀር፣ ትድን ዘንድ ትንሽ
የማሪያም መንገድ መክፈት ከቻልኩ፣ ችግሩ ምንድነው…. ከእራሴ ጋር እየተሟገትኩ ወደ ሔራን ስመለስ ፊቴ ሁሉ ተቀያይሮ ነበር፡፡
“ስላም ነው?” አለችኝ፣ ወደ ስልኬ በአገጯ እየጠቆመች፡፡ ነፍሷ ንቁ ነው፡፡ ትክ ብዬ አየኋት፤ ልዋሻት አልፈለግም፡፡
ከድሬዳዋ ነው አልኳት፡፡ መብላቷን አቁማ ትክ ብላ አየችኝ፡፡ ፊቷ ላይ ስጋት ነበር፡፡
ከድሬዳዋ ማን?
ሐኑን?
ሹካዋን ሰሃኑ ላይ አስቀመጠችና በጉጉት ወሬዬን እንድቀጥል ጠበቀችኝ፡፡ አንድም ነገር ሳልደብቅ የተነጋገርነውን በሙሉ ነገርኳት፡፡ በመጨረሻም “ግራ ስለገባኝ የማይሆን ነገር ቀባጠርኩ፡፡ ብር እልከልሻለሁ ወደ አዲስ አበባ ነይ አልኳት፤ ይቅርታ ሳላማክርሽ …"
በረዥሙ ተንፍሳ እጇን ልካ እጄን ያዘችኝና “የምን መመካከር ነው፣ እኔም ብሆን
ይኼንኑ ነው የማደርገው፤ ልጅቱኮ ችግር ላይ ነች ምን ነካህ? …ማንም ሰው ላይ ሊደርስ የሚችል ነገር ነው!አትጨናነቅ፣ ትምጣ። ዕድሉን ከሰጠኸኝ እኔም እረዳታለሁ፡፡ ነገሮች እስኪስተካከሉ ዙፌ ጋር ታርፋለች” አለች: ዙፋን እህቷ ናት ፡፡
ኖ ይኼን ነገር ከእኔና ከአንች ውጭ ማንም መስማት የለበትም፤ ማንኛችንም ቤተሰብ ጋር እንዲደርስ አልፈልግም”
ኦኬ፡ የተሻለ ነገር ካለ ገረኝ?”
የምታውቂው ደላላ በዚህ ሳምንት አነስ ያለ ቤት እንዲፈልግልን ንገሪው፡፡
እስከዚያው ዋጋው አነስ ያለ ሆቴል ታርፋለች” ሔራን ወዲያው ስልኳን እንስታ ወደ ደላላው ደዎለች ድንገት ዘለን ከገባንበት አረንቃ ለመውጣት የማንጨብጠው ነገር የለ መቸስ ሐኑንን ነይ”የሚለው ቃሌ ምጽአት ከመጥራት እኩል ዓለሜን እንደሚገለባብጠው
የገባኝ ተናግሬ ሳልጨርሰው ነበር፡፡ ግን አሁን ራሱ ጊዜው ወደ ኋላ ተመልሶ ደግማ ብትደውል … እንደገና ልላት የምችለው ነገር ነይ!” ነው!
ሐኑን ከአውቶብስ ወርዳ ከሩቅ ሳያት፣ ውስጤ ሐዘን ይሁን ደስታ ባልገባኝ ስሜት ሲናወጥ ይሰማኝ ነበር፡፡ በግርግሩ ውስጥ ዓይኗን እያንከራተተች ስትፈልገኝ፣ ዝም ብዬ ለደቂቃዎች ከሩቅ አየኋት፡፡ እስቲ አሁን በምን አምናኝ እዚህ የማታውቀው ከተማ ድረስ መጣች!? ሐሳቤን ቀይሬ የራሷ ጉዳይ ብዬ ብተዋት የት ትሄዳለች? ኦህ! ከዚህ ሁሉ ችግር
በኋላም እጅግ ውብ ነበረች፡፡ሁሉን ነገር ድንገት አጥታ፣ ከዚያ ውብና ቅንጡ ኑሮ ተሰዳ የመጣች ምጻተኛ ፍቅር ተሰዶ የተንከራተተ መሰለኝ፣ ሰላም ተሰዶ የተንከራተተ መሰለኝ፣ እኔ ራሴ ውስጧ ተቀምጨ የተሰደድኩ መሰለኝ፡፡ ቀጥ ብዬ ወደ ቆመችበት ሄድኩ፤ ስታየኝ ተንደርድራ አቀፈችኝና ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ጠረኗ በቅጽበት የአእምሮዬን የተቆለፈ ስር በርግዶ፣ እያንዳንዷን ያሳለፍናትን ቅጽበት ልቤ ላይ
ዘረገፈው። የልብስ ሻንጣዋን ይዝለች፣ መኪና ወዳቆምኩበት ስወስዳት በግርግሩ ውስጥ እንዳልጠፋባት ክንዴን ጨምድዳ ይዛ ትከተለኝ ነበር፡፡ አያያዟ ፍርሐቷን ነግሮኛል፡፡
አያያዟ ጭው ካለ ገደል ጫፍ ላይ የተንጠለጠለ ሰው፣ ላለመውደቅ እንደያዘው ገመድ፣ የመጨረሻ አማራጭ እኔ መሆኔን ነግሮኛል፡፡ ቃል አላወጣችም፡ አያያዟ ነው ጩሆ ይችን ልጅ አደራ ያለኝ!! ያኔ ነው ለራሴ ብቻ በሚሰማ ድምፅ አይዞሽ!” ያልኩት፡፡ውስጤ የከበበኝን ስጋት ሁሉ ረስቶ በደስታ ይዘል ጀመር፡፡ ኑሮ ሁሉንም ነገር ያዘበራረቀባት ሐኑን መኪናዬ ውስጥ ገብታ እጎኔ ስትቀመጥ፣ ሲንቀዥቀዥ የኖረ ነፍሴ ሲረጋጋ ይታወቀኝ ነበር፡፡ ዙሪያዋን የማይታይ ሞግድ አለ፡፡ ስቀርባት ንዝረቱ በደም
ሥሬ የሚያልፍ፡፡
ወደያዝኲላት ሆቴል ስወስዳት፣ ምንም አልተነጋገርንም፡፡ አልፎ አልፎ እየዞርኩ
አያታለሁ፡፡ የዋህና ንጹህ ፈገግታዋ በሐዘን ደመና በተከበበ ፊቷ ላይ ብልጭ ብሎ ይጠፋል፡፡ ከመምጣቷ በፊት ስለ ማረፊያዋ ስለ ነገርኳት አልተደናገጠችም ወዲያው ስልኬ ጮኸ፡ ሔራን … “ሔራን የምትባል እጮኛ አለችኝ" አልኩ ለራሴ፡፡ ለምን እንደሆነ እንጃ፣ በመደወሏ ውስጤ ሲበሳጭ ይሰማኝ ነበር፡፡ ሐኑንን ከተቀበልኩ በኋላ፣ ቀለበት ለማየት እንሄዳለን ተባብለን ተቀጣጥረናል: ሐኑን እረፍ እንድትል ነግሪያት፣ የፈለገችውን ክፍሏ ውስጥ ሆና በስልክ እንድታዝ፣ እንዴት ማዘዝ እንዳለባት አሳይቻት፣
በዚያውም ምሳ አዝዤላት፣ ከቻልኩ ማታ፣ ካልሆነም ነገ እመለሳለሁ ብያት ልወጣ ስል እፊቴ ቁማ እጆቿን እርስ በእርስ እያፍተለተለቾ እነዚያን ዓይኖቿን እያንከባለለች እንደ ሕጻን ልጅ የምላትን ሁሉ እሺ! እሺ' ስትለኝ ውስጤ ተንሰፈሰፈ ድንገት ወደ ራሴ ስቤ አቀፍኳት፡፡ ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ፣ እንባዩን ለመቆጣጠር እየታገልኩ ነበር፡፡ ፊቴን ሳላዞር እዚያዉ በቆመችበት ትቻት ወጣሁ፡፡ ያረፈችበትን ሆቴል ሕንጻ ከውጭ ስመለከተው ፣ አንዳች ቤተመቅደስ ነገር መስለኝ፡፡ ድፍን ዓለም ቢታሰስ፣ በዚያች ሰዓት የልቤ መሻት ደስታዬ የተቀመጠበት ከዚህ የተሻለ ቦታ አይገኝም።
ከሆቴሉ እንደወጣሁ ወደ ፒያሳ ከነፍኩ፡፡ ሔራንን ከእህቷ ጋር አገኘኋት፡፡ ስለሐኑን
ብዘም ኤልጠየቀችኝም:እህቷ እንዳትሰማ ወደጆሮዬ ጠጋ ብላ ሰላም ገባች?” ብቻ
ብላኝ፣ ወደቀለበት መረጣችን ሄድን። ይኼን የሰርግ ጉዳይ እያንዳንዷን ጥቃቅን ቅጽበት በደንብ እየተዝናናችበት ነበር፡፡ በሚያምር ጣቷ ላይ ቀለበት ስትለካና ስታወልቅ እያየኋት፣ “ሕይወት እንዲህ ናት? እላለሁ፡፡ ጥቂቶች ብቻ ይመስሉኛል ትከከለኛው ጣት ላይ የቃል ኪዳን ቀለበታቸውን ለመሰካት የታደሉ፡፡ እንደ አገር ባይጮኽለትም፣ምክንያቱ ይለያይ እንጂ የሚበዛው ትዳር ቅኝ ግዛት ነው! “ማን አስገደደህ? ወደህ ነው የገባህበት” የሚለው ጀግና መሳይ ችቶት፣ ራሱ የፈሪ ዱላ ነው፡፡ ማንም ያስገድድህ፣ ያውልህ መውጫ መንገዱ፤ የሚል ጀግና ወዳጅ እምብዛም ነው፡፡
እንዴት ነው?” ትለኛለች ቀለበት በሰካች ቁጥር፤ ጣቷን እንደሹካ ፊቴ ላይ
እንጨፍርራ
“ጥሩ ነው” እላለሁ፡፡ በዚያ ሰዓት እንኳን ቀለበቷን ልመለኮት ይቅርና፣ የቀለበት ጣቷ ቦታው ላይ ባይኖር የማስተውል አይመስለኝም ሥጋ ነበር የሚንገላወደው ፤ ነብሴ አጠገቧ ኤልነበረም፡፡ የፖሊስ ካቴና እጇ ላይ አጥልቃ እንዴት ነው?

ብትለኝም “ጥሩ ነው ከማለት አልመለስም፡፡ እንደውም የሆነ ሰው አስገድዶ ከሔራን ጋር በአንድ ካቴና ያሰረኝ እስኪመስለኝ፣ የግድ ነበር እግሬን እየጎተትኩ ከአንዱ ሱቅ ወደ ሌላው ሰቅ የምከተላት። በዚህ ቅጽበት አንድ ተአምር ነፃ ነህ፤ ወደ ወደድክበት ብረር'” ቢለኝ መገኛዬ ሐኑን ጋር ነበር፡፡ነገሩ የወንድነት ስሜቴ አልነበረም፣ ፍቅርም አልነበረም፤ ሕይወት የሚባል መጥረቢያ፣ ግንዱን የሚከተከተውን ግዙፍ ዝግባዬን ጨርሶ ሳይወድቅ
የማዳን ፍላጎት እንጂ፡፡ ሁላችንም ነፍሳችን ውስጥ የአድባር ዛፍ አለን፤ ከስሩ ካልተጠለልን የትም ብንሄድ ምድረበዳ ነው፡፡ እያንዳንዱ ትዝታዋ እንደ ጃርት ላባ በመላ ሰውነቴ ላይ ተንጨፍርሮ፣ የተጠጋኝን ሰውም ይሁን ግድግዳ፣ ውጋው ውጋው! ይለኛል፡፡ - ልክ እንደሰው እጅ ከኋላየ ልብሴን አንቆ፣ ወደዚያ ሆቴል የሚጎትተኝ ነገር
አለ፡፡ መሄዱ እንኳን ቢቀር፣ ብቻዬን ተቀምጬ ከሐኑን ጋር አንድ ከተማ ውስጥ መሆናችንን ማሰብ እፈልጋለሁ፡፡ ቆይ ግን፣ ወንድሞቿ ምን ዓይነት ጋንጩር ቢሆኑ ነው?እያልኩ ሳስብ፣
ሔራን ፍቅር መሃሉ ላይ ፈርጥ ቢኖረውስ?” ትለኛለች አንዱን ቀለበት ስከታ የሚያፈርጥ ነገር …!
የዚያን ቀን ምሽት ወደ ሐኑን መሄድ አልቻልኩም፡፡ ሔራንን እና እህቷን እቤታቸዉ አድርሻቸው በሉ ደህና እደሩ ስል እህቷ ወርዳ ሔራን ቁጭ አለች፡፡ እናም ዛሬ ከአንተ ጋር ነው የማድረው …እንዴት እንደናፈከኝ አለችኝ” ምን ማድረግ እችላለሁ… ደግሞ ዘግይቶም ቢሆን ገብቶኛል ወደ ሐኑን ተመልሼ እንዳልሄድ ከዛች ቀን ጀምሮ በሰበብ አስባቡ ከጎኔ አትለይም ነበር፡፡ አብረን አደርን፡፡ እንደለመደችው ብትነካካኝም
“ደክሞኛል” ብዬ ጀርባዬን ሰጥቻት ተኛሁ፡፡ ሔራን ያዙኝ ልቀቁኝ የምትል ልጅ
እይደለችም፡፡ እንደ ፖለቲከኛ ምን ላይ መነጋገርና መቼ መነዛነዝ እንዳለባት ጠንቅቃ ታውቅ ነበር፡፡ እቤቴ ስታድር ልብሷን እስከታወልቅ እንኳን የማያስችለኝ እኔ፣ የቀድሞ ፍቅረኛዬ በመጣችበት ቀን ጀርባዬን መስጠቴ የትኛዋንም ሴት ለማበሳጨትና ለማጠራጠር በቂ ምክንያት ቢሆንም፣ ሔራን ግን ምንም እንዳልተፈጠረ አለፈችው አእምሮዋ በተወሳሰበ መንገድ ነገን እያሰላ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ግድ አልሰጠኝም።
በቀጣዩ ቀን ቅዳሜ፣ ደላላው አንዲት ባልቴት ግቢ ውስጥ ጠባብ ክፍል ቤት መገኘቱን ነገረን፡፡ ግቢው ንጹሕ፣ ጸጥ ያለና ሌላ ተከራይ የሌለበት ስለሆነ ወደድኩት፡፡ ሴትዮዋ ልጆቻቸው ውጭ አገር የሚኖሩ፣ እንዲሁ የሚያወራቸው ሰው የሚፈልጉ ወሬኛ ባልቴት ነበሩ፡፡ በእርግጥ ኪራዩ ትንሽ ወደድ ይል ነበር፡፡ እኔ ከምኖርበትም ሆነ ከሥራ
ቦታ ብዙም እይርቅም፡፡ በሳምንት ውስጥ እንደነገሩ ያስፈልጋል ያልኩትን እቃ ከሔራን ጓደኛ ሱቅ አምጥቼ አሟላሁ:: ሐኑንን በየቀኑ ብቅ እያልኩ አይቻት፣ ስለ ቤቱም አውርቻት እመለሳለሁ፡፡ “እስቸገርኩህ!” ነበር ምላሿ፡፡ ሔራን በዚህ ጊዜ፣ ለራሴም እስኪገርመኝ እየደወለች፣ ሄይ ተረጋግተህ ጨርስ… እንዳግዝህ ከፈለክ ጥራኝ… ደግሞ
ከባድ እቃ እንዳታነሳ…ምሳ በላህ” ከማለት ውጭ ምንም አይወጣትም ነበር፡፡ የቤቱን ጉዳይ እንደጨርስኩ ሐኑንን ሳምንት ከቆየችበት ሆቴል ወደቤቷ ወስጄ ከአከራይዋ ሴትዮ ጋር አስተዋወኳቸው፡፡የሚያስፈልጋትን አስቤዛ እራሷ እንድትገዛ ይዣት ወጣሁና፣ገዝተን እንደጨረስን አንድ ሬስቶራንት ወስጄ ምሳ ጋበዝኳት፡፡ እናም ስለሔራን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ በዝርዝር ነገርኳት፡ልንጋባ በዝግጅት ላይ እንደሆንም ጭምር፡፡ በቀጣዩ ቀን እንደማስተዋውቃት ነገርኳት፡፡
ሐኑን በዝምታ ስታዳምጠኝ ቆይታ “ጥሩ ልጅ ነህ፤ አላህ እንኳን እኩያህን ሰጠህ
አለችኝ፡፡ ከዛ በኋላ ግን የጀመረችውን ምግብ አልበላችም፡፡
“ሐኑን! አሁን ግንኙነታችን የእህትና የወንድም ነው፡፡ የሚያስፈልግሽን ሁሉ ሳትሳቀቂ እንደ ታላቅ ወንድም ጠይቂኝ፡፡ ቤተሰብ ነን! የቻልኩትን ሁሉ ባደርግልሽ ከልቤ ነው የምደሰተው፡፡ ሔራንም ሁሉንም ነገር ስለምታውቅ እህትሽ ማለት ናት፡፡ አሁን ከአንቺ የሚጠበቀው ጠንካራ መሆን ብቻ ነው፡፡ አብረን ማሰብ ያለብን ስለወደፊቱ ነው፤ ስለወደፊቱ ብቻ”
እንዳቀረቀረች እሺ” አለችኝ፡፡ እናም እንባዋ ድንገት ተዘረገፈ፡፡ አሁን ላገባ እየተዘጋጀሁ እንኳን ፡እሷ ልታገባ መሆኑን ብትነግረኝ እኔም የማለቅስ ነው የሚመስለኝ፡፡አልፈረድኩባትም፡፡ እንደውም አነጋገሬ ከሐኑን ይልቅ ራሴን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት
ነበር የሚመስለው፡፡

#ቀጥረሽኝ_ፈላስፋ_አደረግሽኝ
“ላገኝህ” ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፥ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፥ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬ'ት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፡ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በ'ላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፥ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
ሰዓቱ እስኪደርስ ፥ ሰዓት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፥ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን
እንዴት እንደምሔድ ፥ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፥ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዱ እግሬን ስጎትት ፥ አንዱ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፥ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፥ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፥ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው!
ሊስትሮ ጋር ሔድኩኝ ፥ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው ...
በወስፌ መንጠቆው ፥ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፥ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ !
“የህይወት ትንሽ ሽንቁር
ጊዜና ግመልን ፥ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፥ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
እየተጣደፍኩኝ….
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፥ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፥ “ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፥ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ…
“መፈለግ ነው” ብዬ ፥ የፍልስፍና አቅም፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፥ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፥ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፥ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፥ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፥ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ
ትቼው መጥቻለሁ ፥ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር
ላይጠግን ይሰፋል ፥ በወስፌ ተቀዶ።
እፈላሰፋለሁ !
ቀድሜ መጥቼ ፥ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ
እጅጉን ይሻላል ፥ አርፍዶ የመጣ፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ሰው የሚሉት ፍጡር..
ነፍስ ከስጋ ጋር ፥ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፥ ፍፁም የሚስተው፡፡
እፈላሰፋለሁ !
ቀድሜሽ መጥቼ ፥ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፥ ማይጠነቀቀው!!
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
“ላገኝህ” ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፥ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፥ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬ'ት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፡ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በ'ላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፥ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
ሰዓቱ እስኪደርስ ፥ ሰዓት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፥ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን
እንዴት እንደምሔድ ፥ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፥ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዱ እግሬን ስጎትት ፥ አንዱ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፥ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፥ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፥ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው!
ሊስትሮ ጋር ሔድኩኝ ፥ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው ...
በወስፌ መንጠቆው ፥ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፥ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ !
“የህይወት ትንሽ ሽንቁር
ጊዜና ግመልን ፥ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፥ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
እየተጣደፍኩኝ….
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፥ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፥ “ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፥ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ…
“መፈለግ ነው” ብዬ ፥ የፍልስፍና አቅም፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፥ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፥ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፥ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፥ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፥ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ
ትቼው መጥቻለሁ ፥ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር
ላይጠግን ይሰፋል ፥ በወስፌ ተቀዶ።
እፈላሰፋለሁ !
ቀድሜ መጥቼ ፥ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ
እጅጉን ይሻላል ፥ አርፍዶ የመጣ፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ሰው የሚሉት ፍጡር..
ነፍስ ከስጋ ጋር ፥ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፥ ፍፁም የሚስተው፡፡
እፈላሰፋለሁ !
ቀድሜሽ መጥቼ ፥ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፥ ማይጠነቀቀው!!
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1
#ሐኑን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ሔራን ሐኑንን ለመጀመሪያ ጊዜ ስትተዋወቃት፣ስሜቷን መደበቅ አልቻለችም ነበር፡፡ ስንመለስ ገና መኪና ውስጥ ከመግባታችን በጣም ቆንጆ ናት! እንደዚህ አልጠበኳትም ነበር አለች፡፡ ጠይም ፊቷ ማንም መንገደኛ በሚያነበው ቅናት ተሸፍኖ፣እጇ ሁሉ
በብስጭት እንደመንቀጥቀጥ ሲል አይቼው ነበር፡፡ “በጣም ልጅ ነች፣ ቆንጆ ነች ብታፈቅራት አይገርምም !እኔጃ እንደዚህ አልጠበኳትም ነበር ደገመችው የሆነ ነገር አንድላትና የምትጮኸበት ምክንያት እንዲፈጠር ፈልጋ እንደነበር ገብቶኝ ዝም ብዬ ቆየሁና “በአሁኑ ሰዓት በዚች ምድር ላይ የማውቃት ቆንጆ ሴት አንድ ብቻ ነች ያው ላገባት ነው!”
የእውነት ግን አንድ ነገር ልጠይቅህ፣ እሰቲ አቁመው…መኪናውን የሆነ ቦታ አቁመው “ፕሊስ አቁመው እንደ ዕብድ አድርጓት ነበር፡፡
እቤት እንሄዳለን፤ እቤት እናወራለን”
"ኖ ዛሬ ከአንተ ጋር መሄድ አልፈልግም፣ ወደ ቤቴ ነው የምሄደው፡፡ እዚሁ አቁመው
እንዳልሰማ ዝም ብዬ ወደቤቴ ወሰድኳት ገና እንደገባን… እንደ እንግዳ ሶፋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለች፡፡ የተቀመጠችበት ሄጄ ሳምኳት፡፡ ባላሰብኩት ፍጥነት ጥፊዋ ጉንጬ ላይ ሲያርፍ፣ ሰማይና ምድሩ ዞረብኝ፡፡
ንገረኝ! … ያረፈችበት ሆቴል ስትሄድ ምንም አላደረጋችሁም? እ?”
ወገቤን ይዤ ከፊቷ ለፊቷ ቆምኩ፤ እናም “ከፈለግሁ አሁንም አታቆሚኝምኮ!” ብዬ
አፈጠጥኩባት፡፡
ዘላ አቀፈችኝ እና ዓይኔን፣ ጆሮዬን፡ያገኘትውን ሁሉ እየሳመች ወደ አልጋው ስትገፋኝ ተያይዘን ወደቅን፡፡ ሸሚዜን ስትጎትተው አንዱ ቁልፍ ተበጥሶ በረረ፡፡ አነር ነበር የሆነቸው እንደ እብድ ልብሳችንን እያወለቅን ወረወርነው ተንጠራርታ መብራቱን አጠፋችውና፣ በጨለማዉ ውስጥ ድክም ባለ ድምፅ ሳያት ቀናሁ…! እንደ ዛሬ በሕይወቴ የበታችነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ የሆነ ኩትት ያልኩ ባልቴት የሆኑኩ
ነው የመሰለኝ ንገረኝ
“ምን ልንገርሽ? ሔር'
ቆንጆ ነሽ በለኝ - እወድሻለሁ በለኝ…ወንዶች ጋር ሳወራ እንደምትቀናብኝ ንገረኝ እንደምትፈልገኝ ንገረኝ የሆነ ነገር በል፣ በቃ የፈለከውን ጠንካራዋ ሔራን
ከተዋወቅን ጀምር ለመጀመሪያ ጊዜ እያለቀሰች ነበር፡፡
እንደዚያን ቀን ሁለታችንም በስሜት ጡዘን አናውቅም፡፡ ጨለማው ውስጥ በዚያ ሁሉ ላለመበለጥ በሚደረግ የሴትነት ትንቅንቅ ውስጥ፡በዘያ ሁሉ የአትርሳኝ ተማጽኖ መሃል፣
ጨለማው ላይ ገዝፎ የታየኝ የሐኑን መልክ ነበር። ልክፍት ነው! መብራቱን ድንገት ባበራው ከስሬ የምትንፋረቀው ሔራን፣ በሆነ ተአምር ሐኑን ሆና በቀይ ፊቷ ላይ እንባ ሲንኳለል የማገኛት እስኪመስለኝ፡፡ በሕይወት ውስጥ ግን፡ ማሸነፍ የሚባል ነገር የእውነት ይኖር ይሆን? ሔራን አሸንፋ እኔን ልታገባ ነው እኔ ተሸንፌ ሐኑንን ከነፍቅሯ ተነጥቂያለው ሐኑን በወንድሞቿ ተሸንፋ ሁሉንም ነገሯን ተነጥቃ እኔ እጅ ላይ ወድቃለች፡፡በኑሮ የተሸነፈችው ሐኑን ኑሮ እሹሩሩ የሚላትን ሙሽራ አሸንፍ እያስለቀሰች ነው፡፡እኔ ያቀፍኳት ሴት ጠይምነት በቀይ ቅዠት ተሸንፎ ያቀፍኩትና ያሰብኩት የሚምታታብኝ ደንጋራ ሁኛለሁ። ሁሉም አሸናፊ ከጭብጨባ ኋላ የሚያነሳው
የሽንፈት ዋንጫ አለ፡፡ ማሸነፍ የሚባል ነገር እዚያ መለኮታዊው ዓለም ላይ ካልሆነ በስተቀር ምድር የተሸናፊዎች ርስት ናት፡፡ ሁለታችንንም እንቅልፍ አሸንፎ ይዞን ጭልጥ አለ፡፡ ጧት ስንነሳ ሔራን ዓይኔን ማየት አፍራ ነበር፡፡
ቁርስ ልጋብዝሽ አልኳት ዝቅ ባለ ድምፅ፡፡
እሺ አለችኝ፡፡ ሰውን ሁሉ ምን ነካው? እሺ ብቻ! ቁርስ እየበላን ሰሃኗ ላይ አቀርቅራ
እንዲህ አለትኝ፣
ዓይኗ ከአንተ ላይ አይነቀልም፣እንስፍስፍ ብላ ነው የምታይህ፤ አውቃለሁ ሰው
ሲያፈቅር ምን እንደሚሆን፡፡በተለይ ሴት ስታፈቅር፣ ታፈቅርሃለች ማንም ሴት ብትሆን የእኔ ያለችው ወንድ በሌላ ሴት ተፈቅሮ ማየት፣ ግማሽ ስጋት ነው፡፡ ሳት ቢልህ ፣እምቢ የምትል ዓይነት አይደለችም” እናም የቀረበውን ቁርስ ንክች ሳታደርገው፣ ገፋ አደረገችው።
ሔራን የበላይነቷን ለማሳየት፣ በሐኑን ላይ የማታደርገው ነገር አልነበረም፡፡ የሚገባኝ እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ ሐኑን ራሷ “ይኼማ ወደር የሌለው በጎነት ነው” ልትለው የምትችለውን ድርጊት፣ ዓይኔን ጨፍኜ የሔራን ሰይጣናዊ ቅጣት እንደሆነ መናገር እችላለሁ፡፡እንደዓይኔ ብሌን ነበር ሐኑንን የምጠብቃት፡፡ አንድ ቀን ሰርጋችን ሲቃረብ፣ ሔራን ሐኑን ሥራ ታግዘን፣ ለዛውም ብቻዋን እንዳይደብራት እኛ ጋር ትሁን በሚል ሰበብ እቤታቸው ወሰደቻት የሔራን እህቶች፣ የእኔ ሁለት ጓደኞች (ለሚዜነት ሽር ጉድ የሚሉ) ቤቱን ሞልተን እናወራለን ሔራን ድንገት አንድ ጅንስ ሱሪ አንጠልጥላ ሐኑን ነይ ይሄን ለኪው እስኪ፣ ብዙም እለበስኩትም ጠቦኝ ነው፣ ልክሽ ከሆነ ትወስጅዋለሽ አለቻት። በሰው ፊት አሮጌ ሱሪዋን ለሐኑን በመመጽወት የበላይነቷን ለማሳየት
ያደረገችው መሆኑን በደንብ ነው የገባኝ። ምንም ነገር በፍቅር ቢያደርጉት ነውር
አይደለም፤ እንዲህ ዓይነት ጋጠወጥነት ግን ያቅለሸልሻል …ሐኑን ሻንጣ ተከፍቶ እጅ እንዳመጣ ቢላክ፣ሔራን እንደ ቅርስ የምትኮራበትን ዓይነት አስር ጅንስ ሱሪ የሚገዛ የቱርክ ቀሚስ ተመዞ ይወጣል፡፡ ነውረኛ!
እኔና ሔራን እንዲህ አይጥና ድመት ድብብቆሽ ላይ ሆነን ድል ባለ ሰርግ ተጋባን፡፡ እኔ ባልፈልግም፣ ሔራን ጠርታት ስለነበር ሐኑን ሰርጌ ላይ ተገኘት፡፡ ይኼም እንደ ቅስም መስበሪያ መሆኑ ነው፡፡ የሔራን አስቀያሚ ፖለቲካ፡፡ እንዲያውም እሁቶቿ ሆነ ብለው ሐኑንን ከሌሎች ወንዶች ጋር ለማቀራረብ ሲሞከሩ፣ ከሙሽራ ወንበሬ ላይ ሆኜ በጭፈራው መሃል እታዘብ ነበር፡፡ ከጎኔ በቬሎ ደምቃ ካሜራው ወደኛ በዞረ ቁጥር
ሠላሳ ሁለት ጥርሷን የምታሳየውን ሒራንን፣ ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብዬ “ሐኑንን ወደ ቤት እንዲሸኞት ንገሪያቸው አልኳት፡፡ ፈገግ እንዳለች “ምንድን ነው በሰርግህ ቀን እንኳን የዚች ልጅ ስም ከአፍህ የማይጠፋው? ተዋት ትጨዋት፣ ከሰዎችም ጋር ትቀላቀል፣ ባዶ
ቤት አፍነህ ምን ልታደርጋት ነው? ሆሆአለችኝ፡፡ ቁጣዬን መደበቅ አልቻልኩም ኮስተር ብዬ
ሔራን እንዲሸኟት ንገሪያቸው" አልኳት፤ እያንዳንዱን ፊደል ርግጥ አድርጌ:: መኮሳተሪ አስፈርቷት ይሁን፤ ሰርጓ እንዳይበላሽ ፈርታ፣ ፈገግ እንዳለች ሚዜዋን ጠርታ፣ ጆሮዋ የሆነ ነገር ነገረቻት፡፡ ሐኑንን ወዲያው ወደ ቤቷ ወስዷት። ማታ እልል እየተባለልን
የገባንስት ጫጉላ ቤት ውስጥ የመጀመሪያ ንግግራችን ወደንዝንዝ ያደላ ነበር፡፡ “ቆይ የፈለገችው ጋር ብታወራ አንተ ምን አስጨነቀህ…? ሕፃን ልጅ አይደለችም! የቤት ኪራይ ስለከፈልክላት ብቻ፣ ከማን ጋር ማውራት፣ ማንን አለማውራት እንዳለባት መወሰን
ትችላለህ ማለት አይደለምኮ!…ተዋት በቃ! ልጅቱን….ነፃነቷን ስጣት! ሌላ ነገር ውስጥህ ከሌለ በስተቀር ይኼን ያህል
“በቃ! ሲጀመር የአንቺ እህቶችም ሆኑ የኔ ቤተሰቦች ስለ ሐኑን ምንም እንዲያውቁ
አልፈልግም ብዬ ነግሬሻለሁ፡፡ አንቺ ግን ለእህቶችሽ ነግረሻቸዋል፡፡ እናም ገፋፍተው አንዱ ወንድ ላይ ስላጣበቋት፣ በአንቺ ሴት ትዳርሽ ከስጋት ነፃ ይሆናል! ደግሜ እነግርሻለሁ…ከሐኑን ጋር ምንም ጐዳይ የለኝም! ምንም! የዚህ ዓይነቱን ተንኮላችሁን አቁሙ፤አንቺም እህቶችሽም ለአንዲት ሚስኪን ይኼን ያህል ርብርብ ምንድነው?እኔ የሚያስፈልጋትን ከመስጠት ያለፈ ምንም አላደረኩም፤ ከሰው ጋር አታውሪም አላልኩም፡፡
አንቺ ነሽ ዙሪያዋን እየዞርሽ የማይረባ ድብብቆሽ የምትጫዎችው…በቃ ተያት!»
እንደተኮራረፍን ወደ አልጋችን አመራን፡፡
ሌላ ዓለም ነበር ይኼንኛው በለስላሳ እጆቿ ሰውነቴን

❤1
ስትነካካኝ፣ በዚህ ቁማር በሆነች ሕይወት ዉስጥ ሌላኛዉን ካርዷን እየመዘዘች እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ብትችል በተንኮሏ፣ ካልሆነም በሴትነቷ፣ ዛሬን ማረሳሳትና ለነገ በተሻለ ተንኮል መዘጋጀት ባህሪዋ ነው፡፡ ምንም ይሁን የሰርጌ ቀን ነው” በሚል ማጽናኛ
ጋር ዙሬ አቀፍኳት! ፕሊስ ሔራን፣ ይችን ልጅ አትጉጃት ከሚል ሹክሹክታ
ጋር…ዓረፍተ ነገሩን ሳልጨርሰው፣ ከንፈሯ ከንፈሬ ላይ አርፎ እጆቿ በአንገቴ እግሮቿም
በወገቤ ዙሪያ ሲጠመጠሙ ከሰውነቷ ልስላሴ ጋር ተዳምሮ ብዙ እግር ያላት ኦክቶፐስ” ነገር መሰለችኝ፡፡ የባሕር አውሬ ነገር፡፡
ከስርጋች በኋላ የሐኑን ጉዳይ የየቀን ግጭታችን መነሻ ሆነ፡፡ በተለይም ሔራን ካረገዘች በኋላ እንደ እብድ አደረጋት፡፡ ለቤተሰቦቼ ሳይቀር ነገሩን በዝርዝር ነገረቻቸው፡፡ “ይች ታዲያ ይኼን ሁሉ መቻሏ መላእክ ናት እንጂ ሰው ናት እንዴ? በዚህ ዘመን ቅምጥ? የነውር ነውርም” አለ አባባ፡፡ የሔራን እህቶች አኩርፈው በመጡ ቁጥር፣ በእራሴ ቤት ይመናጨራሉ። ግድ አልሰጠኝም፡፡ ጭራሽ ምንም ለማይመለከታቸው የሐኑን አከራይ ወሬው በየት እንደደረሰ እንጃ፤ ሐኑንን ልጠይቅ ስሄድ እፈልግሃለሁ ብለው፣ እቤታቸው አስገብተው፣ ደም የሚያፈላ፣ ምክር አይሉት ዘለፋ አወረዱብኝ
ቅምጥም ውሽማም ከጥንቱ ከአያት ቅድም አያት ያለኮነው እንኳን አንተ ተርታው በደሞዝ አዳሪ፣ ስንቱ ሀብታምና ንጉሥ የሚያደርገው ነገር ነው፤ ያንተ ችግሩ ምንድነው…? ትንሽ በግልጥ መሆኑ እዚሁ በዚሁ! አፍንጫ ሥር፤ ደስም እይል”
«ሐኑን፣ ውሽማዬም ቅምጤም አይደለችም እማማ… »
አፍንጫቸው ውስጥ ሰክተውት የነበረውን ነጭ ሽንኩርት ተነቅሎ እንዳይወድቅ፣
በጣታቸው እያሽከረከሩና እያጠበቁ፣
ሃድያሳ ምንህ ናት!? አገር ምድሩ አውርቶ የጠገበው ነገርኮ ነው። ልጅቱ እንደሆነች
ቤቷን ዘግታ ካላንተ ሰው አታናግር፡፡ እንኳን እንዲህ እየመጣህ ቤት ቆልፋችሁ
እየተቀመጣችሁ ቀርቶ ውበቷ ከመንገድ ድንገት ያያትን ጎትቶ የሚያስገባ አንዳች እሳት ነው አጉል ዕድሜ..."
"እማማ ለምን አይሰሙኝም? እንደሚያስቡትም እንደሚወራውም አይደለም፡፡ደግሞ ይኼ የግል ጉዳያችን ነው እርስዎን የሚያሳስብዎት ነገር አይደለም”
ዓንደው ነገሩን አልኩ እንጂ፤ እኔማ ምናሻኝ ! አንተም እሷም ድምፃችሁ የማይሰማ ጨዋ ናችሁ ውሃ አታፈሱ፣ ሰው አታንጋት! እኔ ውስጥ ለውስጥ ማማት ስለማልወድ ነው፣ ፊት ለፊት ነው ነገሬ …
✨ነገ እንጨርሰው መሰለኝ✨

#ከዚህ_የሚበልጥ
ዓለም ለእርሱ ተሰቅሎ
እርሱም ለአለም ተሰቀለ
ስለኛ በደል ሀጢአት በቀራኒዮ ዋለ
ሸክማችንን ተሸከመ
ቁስላችንንታመመ
በበደል በሀጢአት ሞተን
በፀጋው ሕይወት ሰጠን።
🔘ሰላም ዘውዴ🔘
ዓለም ለእርሱ ተሰቅሎ
እርሱም ለአለም ተሰቀለ
ስለኛ በደል ሀጢአት በቀራኒዮ ዋለ
ሸክማችንን ተሸከመ
ቁስላችንንታመመ
በበደል በሀጢአት ሞተን
በፀጋው ሕይወት ሰጠን።
🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ሐኑን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት(የመጨረሻ ክፍል)
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
እንደው ነገሩን አልኩ እንጂ፤ እኔማ ምናሻኝ! አንተም እሷም ድምፃችሁ የማይሰማ ጨዋ ናችሁ ውሃ አታፈሱ፣ሰው አታንጋትቱ! እኔ ውስጥ ለውስጥ ማማት ስለማልወድ ነው፣ፊት ለፊት ነው ነገሬ...
ሐኑን በጨንቃት ካፍቴሪያ ማስተናገድም ቢሆን እቀጠራለሁ አለች፡፡ ግራ ገባኝ::
ምን እንደማደርጋት ጨነቀኝ፡፡ ነገሮችን ትረዳለች የምላት እህቴ እንኳን፣ “ይኼኮ የአንተ ችግር አይደለም፣ በሕግም ይሁን በምን ወንድሞቿን ትጠይቅ የራሷ ወንድሞች። የጨከኑትን፣ እተ ምን ባይ ነህ ታዲያ? ለአንዲት ኖረችም አልኖረችም በሕይወትህ ውስጥ ምንም ለማታመጣ ሴት ብለህ፣ ትዳርህን ትበትናለህ? ምንድነው ዓላማህ በእውነት ደስ የማይል ነገር ነው፡፡ አፍ አለኝ ብለህ አታውራው፡፡ የአንተ ብር ማለት የሔራንም ነው፡፡ እያነሳህ ለአንዲት ሴት የቤት ኪራይና እስቤዛ ምን የሚሉት እብደት ነው...?!
በዙሪያዬ ያለው ቤተሰብ እና ጓደኛ፡ ልክ አንገት ላይ እንደገባ ሸምቀቆ አንቆ ትንፋሽ አሳጣኝ፡፡ የማውቃቸውን ጓደኞች ሁሉ የጽዳትም ሥራ ቢሆን ለሐኑን እንዳፈልጉላት ወጣሁ ወረድኩ፣ አልተገኘም፡፡ ቢጨንቀኝ ሔራንን እሺ እናስተምራት፣ የሆነ የአጭር ጊዜ ሥልጠና ነገርም ቢሆን ቢሆን ትማር የምግብ ዝግጅት ምናምን… ትንሽ ጊዜ ስጭኝ ብየ ተማጸንኳት፡፡ ይኼም ተአምር ሆኖ በመላ ቤተሰቡ ተወራ “እርፍ! ጭራሽ ላስተምር አለ? ያስነካችው ነገርማ አለ እየተባለ፡፡ በዚህ ጭንቀት ላይ እያለሁ ነበር የሔራን ወንድም ሐኑን ወደ ተከራየችበት ቤት ሄዶ ሐኑንንም አከራይዋንም ሴትዮ እንዳይሸጡ
እንዳይለወጡ አድርጎ ሰድቦና አስፈራርቶ መመለሱን የሰማሁት፡፡ አከራይዋን “ቤትሽ ውስጥ ባለትዳር የምታማግጥ ሴት አከራይተሽ ቆርቢያለሁ ትያለሽ! አንቺ ብሎ ቆራቢ አላቸው አሉ፡፡
ሐኑን፡ ደውላ፣ አከራይዋ ቤት ፈልጊ እንዷላት ነግራኝ፤ ለምን? ምን አደረገች? ብየ ስሄድ ነበር ይኼን ድንፋታውን የሰማሁት፡፡ እየተንቀጠቀጠች ነበር ሐኑን፡፡ “እንደገና ከመጣ ይገድለኛል የሚያስፈራራ ልጅ ነው አለችኝ፡፡ ለእኔ ግን እንደትቢያ እፍ ብለው የሚበትን ተራ ሰው ሁኖ ቀለለብኝ፡፡ እቤቱ ድረስ ሄጄ ኡኡ አልኩበት፡፡ ያ! የገደል ስባሪ የሚያክል
ሰው፣ ምንም ዱርየ ቢሆን ያደረኩለት ነገር ከብዶት ይሁን፡አልያም የእህቱ ባል መሆኔ ይሉኝታ አስይዞት ብቻ ጩኸቴንም ስድቤንም ጠጥቶ ዝም አለ፡፡ እኔ ግን እንደእብድ አድርጎኝ ነበር፡፡ ሔራንን ዓይኗን ማየት አስጠላኝ፡፡ እስስትነቷ አበሳጨኝ፡፡ ለሌሎች ያሳጣችብኝ መንገድ አንገበገበኝ፤ አዎ እውነት አላት፣ በአደባባይ ማንንም የሚያሳምን
እውነት አላት፡፡ ቀና ብዬ እንኳን ማስረዳት የማልችለው ውስብሰብ ታሪክ፣ ነገሬ
ለአደባባይ የሚሆን አይደለም.እንኳን የሰጡትን ሳያላምጥ የሚውጥ ማኅበረሰብ መሃል ለምን እና እንዴት የሚል ታዛቢም ቢመጣ፣ በእኔ ላይ መፍረዱ አይቀርም፡፡ ብቸኛ እውነቱን የምታውቀው ሔራን እወገር ዘንድ አሳልፋ በመስጠት ወገራውን ፈርቼ ከተራ
ስጋቷ ስሸሽ፣ በሽሽቴ ልትፈወስ አንድ አገር ወሬኛ አዝማች ሆና ከፊት ተሰለፈች።
በየሄድከብት ሽሙጥ፣ በየሄድኩበት አንገት ደፊ አገር አጥፊ” ተረት ከቦኝ የምኖር ሰው ሆንኩ፡፡ ባጠገባቸው ሳልፍ የሚሽቆጠቆጡ ባልደረቦቼ ሳይቀሩ፣ ከምር ሐሜትና ወሬ ላይ ቁመው ቁልቁል ሊመለከቱኝ ሲዳዳቸው እየተመለከትኩ እገረም ነበር፡፡ አንድ ሰው ከስንት ሺህ ሕዝብ ጋር ይከራከራል? ወይ ፊት ለፊት ደፍረው አያወሩ፣ አላስረዳቸው፡፡ በተለይ የወንዶቹ የሐሜተኝነት ሱስ ይሽከከኝ ነበር፡፡ ኮታቸውን እያርገበገቡ በየቡና
መጠጫው ስሜን ሲቦጭቁ፣ ይህው ሥልጣን ሆና ከእነሱ በአንድና በሁለት እርከን ከፍ ማለቱ፣ ህሊናቸው ላይ የለደፈባቸውን የበታችነት እድፍ፣ በጎደፈ የስም ውሃ የሚለቃለቁት ይመስላቸዋል፡፡ ደግሞም ሌላ የሚያማቸው ቁስልም ነበር፡፡ ለእነሱ በቁንጅናዋ እንደህልም የራቀች፣ በሙያዋ እንደተራራ የገዘፈች ሔራን፣ ለዓመታት ሲመኟት የኖሯት ሔራን፣ የእኔ ሚስት መሆኗ ሳያንስ እሷን ንቄ ሌላ ሴት ጋር መሄዴ በተወሳሰበ ሒሳብ “እሱ የናቃት እንኳን ማግኘት የማንችል ተራዎች ነን ወደሚል
አዘቅት ወርውሯቸው ነበር፡፡ እሱ ምን ስለሆነ ነው በሚል ማስታገሻ ራሳቸውን
እያስታመው ነበር፡፡ ፊት ለፊት እኔን መጋፈጥ ስለማይሆንላቸው ሔራንን በማጀገን በእሷ ግዳይ ላይ እንደጅብ ተረባርበው የድርሻቸውን ክብር ሊወሰዱ!
ሔራን በዘመድ አዝማድ ፊት ይቅርታ ተጠይቃ፣ ትንሽ እውነት ላይ የካበችውን የውሸት የበደል ታሪክ ተቀብየው እንድኖር ማድረግ ትፈልጋለች፡፡ ማንም የማይገባው ነገር፣ ከአንሶላችን ሥር የተናዘዘችው የዚህ ሁሉ ነገር መነሻ፣ የእኔ አለመታመን ሳይሆን የሐኑን ውበት ያንኮታኮተው የበታችነቷ ነበር፡፡ አሰብኩ፣ ብዙ አሰብኩ ሕዝብ በወሬ ተዛዝሎ የሚወድቅ ናዳ ነው፡፡ ከዚህ ናዳ የሚያድነው መሮጥ አይደለም፣ከዚህ ናዳ የሚያድነው
አብሮ መናድ አይደለም፣ ከዚህ ናዳ የሚያድነው ወገብ ይዞ መከራከር አይደለም፣ ይኼ ናዳ ሕዝብ ራሱን ብልህ ሲያደርግ፤ ለአንድ ሞኝ ገጸ ባህሪ ከተረተው ተረት፣ ከራሱ ከናዳው መሃል ነበር መፍትሔውን ያገኘሁት …
.
እንዱ ሞኝ ናዳ መጣብህ ሲሉ ተከናንቢያለሁ አለ አሉ ካሉት ተረት! ለእኔ
እንደዚህ “ሞኝ” እንደተባለ ሰው ብልህ ሆኖ ያገኘሁት ፍጥረት የለም፡፡ የሕይወት
ግብግብ ዓላማው፣ ከሞት መዳን አይደለም። ሰው ፈጠነም ዘገየም እንድ ቀን የሞት ዕጣ የሚወድቅበት ፍጡር ነው፡፡ በዚህ የማይቀር ዕጣ ከናዳ ያድነኛል ብለን የምንለብሰው ከንብንብ፣ ማኅበረሰቡ የብረት መዝጊያ፣ ቅብርጥስ የሚለው ትዳር አይደለም፣ ትምህርት
እይደለም፣ ሥልጣን ቤተሰብ አይደለም፤ ሳያድንም ያድነኛል የሚል እምነት ተከናንቦ ሞትን እንደመጠበቅ ውብ ነገር የለም ፡፡ ያ እምነት ፍቅር ይባላል … ! ሐኑንን ሃብታም ቤተሰብ ከሕይወት ናዳ አልታደጋትም፡፡ እኔን ድል ባለ ሰርግ የተመሠረተው ትዳር ከሐሜት ናዳ አልታደገኝም ያንን ኢዮብ የሚባል ቦዘኔ፡ የዓመታት የድብድብ ታሪኩና ጡንቻው ከእኔ የቁጣ ናጻ አላዳነውም፡፡ ብቸኛው ታዳጊ፣ እንደክንብንብ ስስ የሆነው
በልባችን ያለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ እናም ወሰንኩ፡፡ ለየትኛውም የማኅበረሰብ እንቶፈንቶ የይሉኝታ ሕግ አልኖርም፤ማን ለኔ ኖረ? ቀሪ ዘመኔን ከናዳው ባያተርፈኝም እንኳን፣ የፍቅር ከንብንቤ ውስጥ ብቻ አሳልፋለሁ! ያ ክንብንብ ደግሞ የት እንዳለ ጠንቅቄ አውቃለሁ እንዴት እንደምለብሰውም ጭምር !!
ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት ሄድኩና አለቃዬን እንዲህ አልኩት ቅያሬ እፈልጋለሁ፤ወደ ክፍለ ሐገር ወደ ባህር ዳር ፣ እባክህ ተባበረኝ..."
“ከአዲስ አበባ ወደባህር ዳር!"
“ማንም እንዲህ ዓይነት ዝውውር ጠይቆ አያውቅም፡፡ እዚያ ያሉት ይኼን ቢሰሙ እልል በቅምጤ ነው የሚሉት። በማንኛውም ሰዓት ይቀይሩሃል፡፡ ጠረጴዛዬን ያጣበበው ማመልከቻ ከከፍለ ሐገር ወደ አዲስ አበባ ቀይሩን የሚል ጥያቄ ነው፡፡ ከፈለግህ ብዙም ከባድ እይደለም ልንልክህ እንችላለን
ቀጥሎ አብሮኝ ወደ ተማረና የግል ቢሮ ወደከፈተ ጠበቃ ጓደኛዬ ጋ ሄድኩ፡፡ እናም
ፍቺ እፈልጋለሁ” አልኩት፡፡ …ሰርጌ ላይ ልቡ እስኪፈርስ የጨፈረ ነውና፣ ይሉኝታ
ይዞት የወጉን ምክር አደረሰ፡፡ ትንሽ ብትታገስ፣ ብትነጋገሩ፣ እንኳን ባልና ሚስት ምንትስ ይጋጫል …' እንደ ጠጠር የሚፈናጠሩ የምከር ናዳዎቹን እንደዝንብ ከፊቴ እሽ ብዬ የፍቺ ወረቀት አስጻፍኩ፡፡ ገና በቅጡ ሁለት ዓመት ያልሞላው በሽተኛ ትዳሬን፣
ሙሉ ዘመኔን እንደ ጋንግሪን ከመበከሉ በፊት፣ ቆርጨ ለመጣል ወሰንኩ፡፡ የፍቺ

ማመልከቻዬን ይዤ ሄድኩት ወደ ሐኑን ነበር…ወደ ከንብንቤ፡፡ ፊት ለፊቷ ተቀመጥኩና ውብ ፊቷን… ንጹሕ ዓይኖቿን ትክ ብዬ አየኋቸው፡፡ አፍራ አቀረቀረች: “ሐኑን እይኝ ቀና ብለሽ እይኝ
አፈቅርሻለሁ! መጀመሪያ ቡና ልታደርሽልኝ ወደቤቴ ከመጣሽበት ቀን ጀምሮ፣ እስካሁን ልቤ ላይ ያለሽው አንቺ ብቻ ነሽ፡፡ ከሔራን ጋር ተኝቼ የማስበው
አንቺን ነበር ሰርጌ ውብ ነበር፤ ብቸኛው ችግር ከጎኔ የነበረው ቪሎ ውስጥ አንቺ
አለመኖርሽ ብቻ ነበር፡፡ ሳገባ ከጎኔ ቬሎ የምትጎትተው ሴት ጥፋት፣ አንድ ብቻ ነበር፣አንቺን አለመሆኗ!
ሔራንን ለመፍታት ወስኛለሁ፡፡ቀሪ ዘመኔን ሁሉ አንቺ ጋር መኖር ነው ፍላጎቴ፡፡ይኼን
ከተማ እንለቃለን ባህር ዳር ወደሚባል ከተማ እንሄዳለን፡፡ እዚያ የዘንባባ ዛፎች አሉ፤ ባይኖሩም ግድ አይሰጠኝም፡፡ በዚያ ከዓመት እስከ ዓመት የማይነጥፍ ውሃ አለ፣ ባይኖርም ግድ አይሰጠኝም፡፡ በዚያ እንደ ናዳ ቁልቁል የሚወርድ ፏፏቴ አለ አብረን እንሄዳለን፣ አብረን እንኖራለን፡፡ ይኼ የማንንም ሠልጥኛለሁ ባይ የውሸት በራስ መተማመን፣ ከአፈር የቀላቀለ ውብ ፊትሽን በየቀኑ አያዋለሁ። ልክ እንደዚህ ዓይነት ውብ ፊት ያላቸው ልጆች እንወልዳለን፡፡ በዘንባባዎቹ ስር ድክ ድክ ይላሉ፣ በደፈረሰው ውሃ ይንቦራጨቃሉ… ስለወሰንኩ አትፍሪ፡፡ትዳር ብዩ ለገባሁበት ነገር መፍረስ፣ የአንቺ እጅ የለበትም። ካለበትም እንኳን ኖረበት፡፡ ካገባሁ በኋላ እንዳልነካሁሽ አንቺ ምስክር ነሽ፡፡
ለትዳሬም ታማኝ እንደነበርኩ፣ አንቺ ብቻ ምስክር ነሽ በእኔና አንቺ መኻል እውነት አለ።
ልታምኝኝ የምትችይ ሴት አንቺ ብቻ ነሽ ነፍሴ ከሚያምናት ልብ ሥር እንጅ
ከሚያስገድዳት ክንድ ሥር መንበርከክ አታውቅበትም! የሌለሽበትን አንችን ለመከላከል ሲፍገመገሙ፣ የራሳቸውን ሚዛን መጠበቅ አቅቷቸው ለወደቁ ሁሉ አንዳችም ጸጸት እንዳይሰማሽ፤ አፈቅርሻለሁ! ሰው መስለውኝ ይሄን እውነት ሰውቸላቸው ነበር፤
አይገባቸውም!!
ሐኑን እንባዋ በጉንጫ ላይ እየወረደ ዝም ብላ ስታዳምጠኝ ቆየችና ለመጨረሻ ጊዜ ስልክ ከዘጋሁብህ በኋላ ይኼን ሁሉ ጊዜ አንተን እያሰብኩ የታመምኩትን አላህ ነው የሚያውቀው፡፡አንተ ከወጣህ በኋላ ስንት ሌሊት በመስኮቴ ቆሜ፣ ባዶውን ወደ ተቀመጠዉ ቤትህ እንዳፈጠጥኩ አነጋሁ፡ እንደምወድህ ለማንም አልተናገርኩም፣ማንስ
ይሰማኛል? አባባ ሊሞት ሲያጣጥር ወደ ጆሮዎቹ ተጠግቼ እንደምወድህ ነገርኩት፡፡ ይስማኝ አይስማኝ እኔንጃ: አባባ አንድ ነገር ሲሆን፣ አንተን ፍለጋ የትም እንደምሄድ ነገርኩት፡፡አፉ በላኝ አልኩት ወንድሞቼ ባያባርሩኝም አተን ፍለጋ መምጣቴ አይቀርም ነበር፡፡ ልቤን እፈራው ነበር፣እንድ የስልክ ጥሪህ አባባን ጥየው እንድመጣ ሊያደርገኝ
ይችላል ብየ እፈራ ነበር ከድምፅህ ሸሸሁ! በዚህ ሁሉ አስቀያሚ ውጥንቅጥ ውስጥ እረጅና ተረጅ ሆነን የተቀመጥኩት እጅህን ከማየው በላይ፣ ዓይንህን በየቀኑ ለማየት ነው ትናፍቀኛለህ ፡አሁን እዚህ ተቀምጠህ እንካ ትናፍቀኛለህ…እወድሃለሁ"
አውቃለሁ ሁሉንም ነገር ቶሎ ጨርሼ እንሄዳለን፣ እንጋባለን”
“ኢንሻ አላህ!
ኢንሻ አላህ!
በተጠቀለለ የፍቺ ማመልከቻዬ፣ ታፋዩን እየተመተምኩ ወደ መኪናዬ ስሄድ ዞር ብዬ ተመለከትኩ ሐኑን፡ የእኔ ውብ መልዓክ በሩን ተደግፋ ከኋላዬ ትመለከተኛለች፡፡ዓይኖቿ ውስጥ ስስት አለ፡፡ ይሄን ስስት ከዚህ በፊት በዘመኔ ያየሁት እናቴ ዓይኖች ውስጥ ብቻ ነበር፡፡ ፈገግ አልኩላት ፈገግ አለች! ፈገግታዋ ውስጥ እርካታ ከነ ሙሉ ክብሩ ነግሷል፡፡ በብልጣብልጥነት አልታገለችም፤ ያደረገችው ብቸኛ ነገር ማፍቀር ነበር፡፡ ማፍቀርና ዝም ማለት፤ፍቅርና ዝምታ መለኮታዊ ኃይሎች ናቸዉ ፈጣሪን
የምንፈራዉ ከተከታዮቹ ብዙ ጩኸት ይልቅ በጥልቅ ዝምታዉ ሳይሆን አይቀርም…እናም በዝምታ ግርማ ሞገስ ዉስጥ ባለ እዉነተኛ ፍቅር፡፡ዝምታን የሚያሸንፍ ጩኸት፣ ፍቅርንም የሚያንበረከክ ብልጣ ብልጥነት የለም፡፡ በዝምታ አፈቀረችኝ፣ እናም መላው
ዩኒቨርስ ዝምታ ከጎኗ ቆመ፡፡ አሁን የፈለገው ናዳ ይውረድ ተከናንቢያለሁ!!
ተረታቸው ወደ ፊት ከሚያወርዱብኝ ናዳ ሥር ተከናንቤ ለምቆም እኔ'፣ የአሽሙር
ቀብድ ነው!!
💫አለቀ እኮ💫
በሌላ ድርሰት እንገናኛለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

❤4
#የድብልቅልቅ_ሰፈር_ሰዎች
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
ድብልቅልቅ ሰፈር ስያሜ የወጣላት በአያቴ ዘመን እንደሆነ አባቴ ነግሮኛል። እውነትም ድብልቅልቅ፡፡ ሁሉም እየተተራመሰ የሚኖርባት ሰፈር፡፡
ገና ከቤቴ ወጥቼ ግራና ቀኝ ተጠጋግተው በተሰሩ ቤቶች መካከል ሳቆራርጥ የቁመቴን መርዘም ሳልረግም አልወጣም፡፡ አጭር ብሆን ኖሮ የሰፈሩ ሁሉ ጣራ ገጭቶ ባልጨረሰኝ ነበር። ኮስመን ማለቴ ግን ከቤቶቹ መካከል ከመሽንቀር አድኖኛል።
ወደ ዋናው መንገድ ስዘልቅ መላወሻ መንገድ ቢኖርም የሚተራመስበት ህዝብ አይታጣም፡፡ ብዙ ጊዜ ከሰው
ጋር እጋጫለሁ፤ ምናልባት ጥቁር ስለሆንኩ ከሩቅ አልታይ ይሆን ብዬ
በመገመት ነጭ ልብስ እየለበስኩ መውጣት ከጀመርኩ ሰንበትበት
አልኩኝ፡፡
ዛሬም ማልጄ ወጥቻለሁ፡፡ ወንደላጤ ምን ሊያደርግ እቤቱ ያረፋፍዳል? የሳሩ ላይ ጤዛዎች ገና አልተነኑም፡፡ መንደሯ ለሃያ
አራት ሰዓት ትርምስ አይጠፋባትም፡፡ “እንደምን አደርክ አለማየሁ?”እያሉኝ የሚያልፉትን የሰፈሬን አዛውንቶች ከወትሮው በተለየ መልኩ በፍቅር ተመለከትኳቸው፡፡
በመወሰንና ባለመወሰን መካከል ስሟገት ስላደርኩ ነው መሰለኝ ከድካሜ የተነሳ ፊቴን እንኳን በወጉ የታጠብኩት
አልመሰለኝም።አቆራርጠን ስለምንሄድበት የስደት ጉዞ። ከጓዋደኞቼ ጋር ቀጠሮ ስለነበረኝና የኔን ውሳኔ በጉጉት ይጠብቁ ስለነበር ለመሄድ እንደ ወሰንኩኝ ስነግራቸው መቼም ደስታውን
አይችሉትም፡፡ የሰራሁበትን አጠራቅሜ እኔም ጓደኞቼ የደረሱበት ለመድረስ ስለ ወሰንኩ ማጨስ፣ መስከርና መቃም ካቆምኩ እረጅም ቀናቶች ተቆጠሩ። አዲስ ሰው የመሆን መንፈስ እየተሰማኝ ነው።ይህ የተፈጠረብኝ አዲስ ስሜት ደግሞ እራሴንም ሆነ አካባቢዬን
እንደ አዲስ ያሳየኝ መጀመሩ ገርሞኛል፡፡
ይህቺን ያደኩባትን የምንዱባኖች ሰፈር ትቼ መሄዱን ሳስበው ግን ሆዴን ባር ባር አለው። ለመጨረሻ ግዜ ግን ላጤናት
ትዝታዋን በአእምሮዬ ላስቀር በሰቀቀን ቃኘኋት፡፡
ሁሌም መንደሯ ላይ የማይጠፋው የአእምሮ በሽተኛው መሐሪ እየዛተብኝ አልፎኝ ሄደ። የውሃ ነጠብጣቦች አልፎ አልፎ ፊቴ ላይ እያረፉ ነው፡፡ ዝናብ በሌለበት ጊዜም በድብልቅልቅ ሰፈር
ሲታለፍ ውሃ ባናት ላይ ይንጠባጠባል። ዛሬም ወደ ላይ እያንጋጠጥኩና የፈሰሰብኝን እያባባሰኩ በመራመድ ላይ ነኝ፡፡
የሰፈሩ ሥልክ እንጨቶችና የመብራት ቋሚ እንጨቶች በድብልቅልቅ ሰፈር ድርብ ስራ አላቸው። ከግራና ከቀኝ ገመድ
ተወጥሮባቸው የሰፈሩን የታጠበ ልብስ በማድረቅ ያገለግላሉ፡፡የአንዱ ሲደርቅ የሌላው ስለሚተካ ዉሃው የሚንዠረዠር ጨርቅ አይጠፋም፤ የገመዶቹ ስራ ለደቂቃ ተቋርጦ አያውቅም፡፡
ሁለት ሴቶች ፊት ለፊቴ ካለው ገመድ አጠገብ ቆመው ጭቅጭቅ ጀምረዋል፡፡ አንደኛዋ አጭርና ወፍራም ሴት አብራት
ያለችውን ሴት ከገመዱ ላይ ያወረደችባትን ልብስ ከእጇ ላይ
መነጨቀችና ወደ ላይ ዘላ ልብሱን ገመዱ ላይ ወረወረችው፡፡ እላይዋ ላይ የተከማቸው ስጋ እላይዋ ላይ ተንደፋደፈ፡፡
“እኔ እኮ ደርቆልሻል ብዬ እንጂ...” ብላ እንዳቀረቀረች ተመለሰች፡፡
“ከየት የመጣሽ ወስፌ ነሽ ባክሽ? እርጥቡን እንዳስገባልሽ ፈለግሽ? በለሊት ወፍ ሳይንጫጫ ተነስቼ ማጠቤ እኮ ሰው
እንዳይቀድመኝና ልብሴ ቶሎ እንዲደርቅ ነው።” አለችና የተሰጡ ልብሶቿን እያገላበጠች ማስጣት ጀመረች፡፡
አዲሷ ልብስ አስጪ ሴትዮ እንግዳ መሆኗ በጀ እንጂ የዚሁ ሰፈር ሰው ብትሆን ኖሮ ቡጭሪያውና ጡጫው ይከተል ነበር፡፡
ሁልጊዜ በድብልቅልቅ ሰፈር ጩኸት አይታጣም፡፡ “ስጤ ላይ ውሃ ደፋሽ”፣ “ዶሮዬን መታሽብኝ”፣ “ደጃፌ ላይ አሰጣሽ”፣ “ድመትሽን ያዢልኝ...” የመሳሰሉት ነገሮች የዘወትር ጠብ
ማጫሪያዎች ናቸው፡፡ ይህን መንደር ለቅቄ መሄዴ ለምን እንዳስጨነቀኝ እራሴን ጠየኩት። ጥያቄዬን ለራሴ ሳልመልስ አንዲት ጸጉሯ የተንጨፈረረ ሴት በእጇ ምናምን ይዛ ወጥታ የያዘችውን
እንኳን በውል አይቼ ሳልጨርስ ፍሳሹን በላዬ ላይ ከለበሰችው፡፡መጸዳጃ ቤት መደፋት የነበረበት መሆኑን ያወኩት አፌን ጨው ጨው ሲለኝና አፍንጫዬን መጥፎ ሽታ ሲሰነፍጠው ነበር፡፡
“ድንባዣም!... ትደፊብኛለሽ?” ጮህኩ፡፡
ታዲያ አንተ እንደ ጅብራ ፊቴ ላይ ማን ተገተር አለህ!”
ሴትየዋ የተመለመለና የከሰለ እንጨት የመስሉ እግሮቿን እያማታች ወደ ቤቷ ገብታ የጣውላውን በር በኃይል ስትወረውረው ከበሩ መቃን ላይ የቀረው የጭቃ ልስን ረገፈ። “ባሏን ጎዳሁ ብላ..
የሚለው አባባል ትዝ እንደማለት አለኝና ቆሻሻዬን ከፊቴ ላይ እየጠራረኩኝ ለራሴ ያቀረብኩትን ጥያቄ መልስ ለማድመጥ
ተዘጋጀሁ፡፡
እነዚያን ጎስቋላ ቤተሰቦቼን አሰብኩኝ፡፡ የማይፋቅ ትዝታ ጥለውብኝ አልፈዋል። በሕይወት በነበሩ ሰዓት ስወጣ ስገባ “እባክህ ሰው ሁንልን?” የሚለው ንትርካቸው አስጨንቆኝ እየጣልኳቸው ውጭ አድር ነበር፡፡ እነሱን ሳጣ ግን
እክሳቸው ይመስል ከድብልቅልቅ መራቅ አቃተኝ፡፡ ይሄ የራሴ ለራሴ መልስ አሳማኝ ነበር፡፡
ሁልግዜም ጥንብዝ ብዬ ሰክሬ ወደቤቴ ስገባ እናቴ ቁጭ ብላ ትጠብቀኝ ወደ ነበረበት ቦታ አስተውላለሁ። “እናቴ
መጣሁልሽ!" ብዬ ስጮህ የምትቀመጥበት ድንጋይ አፍጦ ያየኛል።
ያን ቦታ ማየት ለኔ ሰቀቀን ነው። አሁን መስከሬን ሳቆም ግን የሙት መንፈሷ በፈገግታ የሚመለከተኝ ይመስለኝና ደስ ይለኛል።
አለፍ እንዳልኩ ሰክሬ የማጫውተው ልጅ መሰለኝ “አሌክስ” ብሎ ጠርቶኝ ተደበቀ፤ እሱን በዐይኔ ስፈልግ ቆፈን የያዛቸው
ህጻናት እጃቸውን እያሻሹ፣ እኔ አይደለሁም በሚል አስተያየት በፍርሀት እያዩኝ ቆመዋል። ከዚያው ዝቅ ብለው ደግሞ መስል ጓደኞቻቸው የወዳደቀ ነገር ይለቃቅማሉ።
እስቲ አሁን በለሊት ምን አስወጣቸው? አርፈው አይተኙም፤ ስራ እንዳለበት ሰው በጠዋት ተነስተው ከሚዳክሩ?
ተበሳጨሁ። ግን ምን ያድርጉ በድብልቅልቅ ሰፈር ምናልባት
መኝታቸውስ በተራ ቢሆን? ምስኪኖቹ አሳዘኑኝ፡፡
እነሱንአተኩሬ ሳይ አንድ ማዳበርያ ሙሉ ምናምን የተሸከመ ሰው ማዳበሪውን ጠርጎብኝ አለፈ። “ይበለኝ!” አልኩ።
እያየሁ መሄድ አለብኝ፤ የድብልቅልቅ ዕፈር ሰዎች “እባክህን፣ ይቅርታ”፣ “አሳልፈኝ” ለሚባሉ ቃላት ባእዳን ናቸው፡፡ ያገኙትን ሁሉ እየጨፈላለቁ ከመሄድ የሚከለክላቸው አንድም ነገር የለም፡፡
ሁልጊዜም በዚህ መንገድ ሳልፍ በልጅነቴ ሰኞ ማክሰኞ የተጫወትኩት ትዝ ይለኛል። ብዙ የሚዘለሉና የሚጨፈላለቁ
ነገሮች አሉ። እናም ጡብ፣ ጡብ እያልኩ እርምጃየን ቀጥያለሁ።
አንዲት አህያ ከመጠን በላይ በተጫነችው ሽክም እየተንገዳገደች ድንገት ፊቴ ድቅን በማለቷ በሌላ መንገድ ለመሻገር
አንድ ጥቁር ድንጋይ ላይ እንደመዝለል ስል ድንጋዩ አንሸራቶ ወደ ሰማይ ልኮ ለምድር አቀበለኝ፡፡ የጎድኔ አጥንቶችና የግራ እጄ ክንድ የደቀቁ መሰለኝ፡፡ ህመሜን ውጩና ትንፋሼን ተቆጣጥሬ ራሴን ገዛሁ፡፡ ወዲያው በአንድ ጎኔ ብድግ ብዬ እንደመነሳት ስል አገልግሎት የሰጡ ብዙ ኮንደሞች ከስሬ ተጎዝጉዘዋል። በእግሬ ስር ያለው ኮንደም ድንጋይ ላይ ተጣብቆ እንዳንሽራተተኝ ልብ አልኩ።
በአካባቢው አንድም በግቢ የታጠረ ቤት የለም፡፡ በራቸው ድንገት ከተከፈተ ገመናቸው ውጪ ይሰጣል። እልፍ ስል የመንጋ ጩኸት የመሰለ ነገር እየቀረበኝ መጣና ምልከታዬን ጩኸቱ ወዳለበት አዞርኩኝ፡፡
ቁጥራቸው ወደ ሃያ የሚጠጋ ውሾች እየተነካከሱ መንደሯን ድብልቅልቋን አወጧት፡፡ ድንገት ግር ብለው ወደኔ ሲመጡ ከውሾቹ ስሸሽ ተደነቃቅፌ ከመውደቅ ለመዳን ባደረግኩት መፍጨርጨር አንድ በር ላይ እጆቼ አረፉ፡፡
💫ነገ እንቀጥለው💫
አስተያየት አይረሳ @atronosebot ን ይጠቀሙ

👍2😁1
#አበው_እንዳላሉት
እምዬ ኢትዮጵያ
ታሪክሽ ተረትሽ ፥ በአበው ተከቦ
“አበው ይህን ሰርቶ ፥ አበው ይሄን ጠርቦ
አበው ጠላት ማርኮ ፥ አበው ተሰብስቦ
አበው ታሪክ ሰርተው
አበዎች ተርተው
አበው አንበርክከው ፥ አበዎች ፈንክተው
አበዎች ሰንዝረው ; አበዎች መክተው
አበው ይህን አርገው ፥ አበው ይህን ፅፈው
እያለ ቢያያወራም….
ትውልዱ በሙሉ ፥ የአበውን ገድል
አኔ ግን የራሴን ..
ታሪክ አወራለሁ ፥ ባገኘሁት እድል።
እናም ኢትዮጵያዬ .
ኢትዮጵያዊ መልኩን
ነብር መዥጎርጎሩን
“ቅዱስ መፅሐፉ” ፥ አይለወጥም ቢልም
ቢሻኝ ልርከስ እንጂ
የኢትዮጵያዊን መልክ
ከነብር ቆዳ ጋር ፥ አላመሳስልም።
እናልሽ ሀገሬ
አበው እንዳላሉት : እኔ እንደምለው
የኢትዮጵያዊ መልክ…
ከዝንጀሮ ቂጥ ነው ፥ የሚመሳሰለው።
እንዴት አልሽኝ አይደል?!
እንዴት ማለት ጥሩ ፥ ወደ መልስ ያመጣል
ልንገርሽ አድምጭኝ!
ኢትዮጵያዊ መሪ ፥ ብዙ ይቀመጣል
ከሥራ ቀን ይልቅ
የስብሰባ ቀኑ ፥ በድርብ ይበልጣል
ብዙ ተመሪ ህዝብ...
ተምሮ ተምሮ ፥ የሚሰራው ያጣል
የሚሰራው ያጣ
ብዙ ህዝብ ደሞ ፥ መጎለት ያመጣል
ኢትዮጵያዊ መልኩ
የዝንጀሮ ቂጥ ነው!
ከመቀመጥ ብዛት ፥ ቂጡ ይመለጣል።
እናም ኢትዮጵያዬ
ስለራሴ ላውራሽ!
ከቶ አያገባኝም
ሥለ አበው በማውራት ፥ ጊዜ ለሚገድሉት
“የ'ሳት ልጅ አመድ ነው” ፣ አበው እንደሚሉት!!!
እናም ኢትዮጵያዬ
ታሪክሽ ተረትሽ ፥ አበው ላይ ቢገኝም
እኔም ትውልድ ነኝ
አበው እንዳላሉት
አበው ካሉት ውጪ ፥ የምልሽ የለኝም ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
እምዬ ኢትዮጵያ
ታሪክሽ ተረትሽ ፥ በአበው ተከቦ
“አበው ይህን ሰርቶ ፥ አበው ይሄን ጠርቦ
አበው ጠላት ማርኮ ፥ አበው ተሰብስቦ
አበው ታሪክ ሰርተው
አበዎች ተርተው
አበው አንበርክከው ፥ አበዎች ፈንክተው
አበዎች ሰንዝረው ; አበዎች መክተው
አበው ይህን አርገው ፥ አበው ይህን ፅፈው
እያለ ቢያያወራም….
ትውልዱ በሙሉ ፥ የአበውን ገድል
አኔ ግን የራሴን ..
ታሪክ አወራለሁ ፥ ባገኘሁት እድል።
እናም ኢትዮጵያዬ .
ኢትዮጵያዊ መልኩን
ነብር መዥጎርጎሩን
“ቅዱስ መፅሐፉ” ፥ አይለወጥም ቢልም
ቢሻኝ ልርከስ እንጂ
የኢትዮጵያዊን መልክ
ከነብር ቆዳ ጋር ፥ አላመሳስልም።
እናልሽ ሀገሬ
አበው እንዳላሉት : እኔ እንደምለው
የኢትዮጵያዊ መልክ…
ከዝንጀሮ ቂጥ ነው ፥ የሚመሳሰለው።
እንዴት አልሽኝ አይደል?!
እንዴት ማለት ጥሩ ፥ ወደ መልስ ያመጣል
ልንገርሽ አድምጭኝ!
ኢትዮጵያዊ መሪ ፥ ብዙ ይቀመጣል
ከሥራ ቀን ይልቅ
የስብሰባ ቀኑ ፥ በድርብ ይበልጣል
ብዙ ተመሪ ህዝብ...
ተምሮ ተምሮ ፥ የሚሰራው ያጣል
የሚሰራው ያጣ
ብዙ ህዝብ ደሞ ፥ መጎለት ያመጣል
ኢትዮጵያዊ መልኩ
የዝንጀሮ ቂጥ ነው!
ከመቀመጥ ብዛት ፥ ቂጡ ይመለጣል።
እናም ኢትዮጵያዬ
ስለራሴ ላውራሽ!
ከቶ አያገባኝም
ሥለ አበው በማውራት ፥ ጊዜ ለሚገድሉት
“የ'ሳት ልጅ አመድ ነው” ፣ አበው እንደሚሉት!!!
እናም ኢትዮጵያዬ
ታሪክሽ ተረትሽ ፥ አበው ላይ ቢገኝም
እኔም ትውልድ ነኝ
አበው እንዳላሉት
አበው ካሉት ውጪ ፥ የምልሽ የለኝም ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1