#ማሙሼ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
“ኤድያ እኔን ብሎ ንግሥት! አሁን ምኑ ታይቷቸው ነው ንግሥት ያሉኝ? ባዶ ምኞት!" አለችና ከአንደኛው መኖሪያ ቤት
ተጠራቅሞ የወጣውን ቆሻሻ ወደ ያዘችው ማዳበሪያ ገለበጠችው።
“አሁን አንቺ ንግሥት ለመባል ምን ያንስሻል? ዘውዱን እንደሁ ጭነሽዋል።” አለቻት ጓደኛዋ ጸአዳ ንግሥት ለፀሐይ
መከላከያ ራሷ ላይ የጠቀለለችውን ጨርቅ እያመለከተቻት፡፡ድምጻቸውን ጮክ አድርገው በሳቅ አወካኩ፡፡
“ምን ያንቺ ብቻ የኔንስ ስም አላስተዋልሽውም? ጸአዳ! አየ ጉድ! እንዴት ጸድቻለሁ እቴ! ጉድ!” አለች ራሷን ከእግሯ ጀምራ ወደ ላይ እየቃኘች በማሽሟጠጥ፡፡
“ይገርማልኮ! “መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንደ ሚሉት፤ ምናልባት የአሁኑ እጣ ፋንታችን ታይቷቸው ይሆናል” አለች
ንግሥት፡፡
“አይ እቴ እንደሱስ አይደለም። እንዲያው ጥሩ ነገር መመኘታቸው ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው ይኸው የሰው ቤት ቆሻሻ ገልባጭ ሆነን አረፍንላቸው!” አለችና በመታከት ከውስጧ የታመቀ የሚመስል ትንፋሽ ተነፈሰች።
ጸአዳ ማዳበሪያዋን እንደማስቀመጥ አድርጋ፣
“እኔ የምለው ይህን ስራ በመስራትሽ እግዚሐርን እንደማመስገን ታማርሬያለሽ?” አለቻትና ወገቧ ላይ ያሰረችውን መቀነት አጠበቀች።
“እ... ታዲያሳ አንቺስ ቅድም ምን ስትይ ነበር? ስታማርሪ አልነበረም?” አለቻት እርሷም እንደመቆም ብላ።
“እኔማ ልማድ ሆኖብኝ እንጂ ስራዬን መች ጠላሁ፡፡ እንዲያውም ጸአዳዬ ከዚህ ደግሞ ሻል ያለ ስራ ከሰሞኑ ሳናገኝ
አንቀርም።”
“ኧረ! እውነትሽን ነው?” አለች ጸአዳ በአግራሞት አፏን ከፍታ።
“እውነቴን ነው። ትንሽ ፍንጭ ቢጤ
አለ፣” አለች ንግሥት።
“ኤድያ! ገና ለገና ብለሽ ነው የምታጓጊኝ? እኔ ሌላ ስራ እስከማገኝ ዎሼ ቀንድ ታበቅላለች።”
“እንቺ ደግሞ ተስፋ የሚሉት ነገር ከግንባርሽም አልተጻፈም!” አለች ንግሥት።
“ኤድያ! ተስፋ ቢጋግሩት እንጎቻ አይሆን!” ጸአዳ ንግግሯ መረር ብሏል።
“ኧረ የኔውስ ተስፋ እንኳን እንጀራ ሌላም ይሆናል፡፡ ታያለሽ ያባቴ አምላክ ባያደርገው!” አለች የጣለችውን ማዳበሪያ
አንስታና በግንባሯ ላይ ኮለል ብሎ የወረደውን ላቧን ጠርጋ የጸአዳ ጥላ እንዲጋርዳት በጎን እየዞረች፡፡
“እስቲ በይ ተጠለይ! እኔን ጌታ ረጅም ባያረግልሽ ኖሮ በየትኛው ዛፍ ትጠለይ ነበር?” አለች እንደመኩራት እያለች፡፡
“አቤት! በዚችው ቁመትሽ እንዲህ የተመጻደቅሽ ሌላ ነገር ቢኖርሽ አለቅን!” አለችና ጸአዳን ወደ ኋላ ትታ በፍጥነት
ተራመደች፡ ወደ ሌላኛው ብረት በር ሲደርሱ በሩን አንኳኩ፡፡ በሩን በፍጥነት የከፈተ የለም፡፡
“እንዲያው ያንን የማሙሼን ነገር እንዴት አደረጋችሁለት?” አለች ጸአዳ በበሩ ቀዳዳ ወደ ውስጥ አጮልቃ እያየች።
“ውይ እንዲያውም እነግርሻለሁ እያልኩ ጸአዳዬ... የማሙሼ ነገርማ እያለቀለት ነው፡፡ ሁላችንም ቃላችንን ሰጥተናል።”
“እንዲያው ምን ብላችሁ ይሆን የመሰከራችሁት?”
“እናቱንና አባቱን ማጣቱን ድፍን የሚካኤል ሰፈር ሰው ያውቃል፡፡ ያው እውነቱን ነዋ የምንመሰክረው... ለማተባችን ስንል!” አለች ንግሥት ማተቧ ውስጥ ሌባ ጣቷን ከትታ ወደፊት ጎተት
እያደረገች፡፡
“ታዲያ አምነው ተቀበሏችሁ?”
“እንዴ... ለምን አያምኑንም?”
“እኛ እራሳችን መጤዎችና በሰው ማድቤት ተጠላልለን የምንኖር ነን፡፡ እንዳው አብረን ስላልኖርን...”
“እንዲህ ብሎ ነገርማ የለም፡፡ ትንሽ ጊዜም ቢሆን እኮ ከናቱ ጋር አብረን መአድ ቆርሰናል። ምስክርነት ደግሞ አብረው በኖሩ አይደለም፡፡”
“ስለዚህ አሳዳጊዎቹ ሊረከቡ ነው ማለት ነው?”
“ታዲያስ! ከሰሞኑ ሳይወስዱት አይቀሩም።”
“እስቲ ይለፍለት የኔ ከርታታ ገና በልጅነቱ አሳሩን አየ” አለች ጸአዳ፡፡
“አየ እንጂ፣ የሱ አሳር ደግሞ ይነገራል! ይቅር ብቻ!”
አሁንማ ለይቶለታል፡፡ የሚያዝንለትም ሰው ለአንዴ ሆይ! ሆይ! ብሎ ዝም አለ፡፡”
“ለዚያ ነው የገንዳ ምግብ የጀመረው?”
“ታዲያ ምን ያድርግ እራብ እንደው ክፉ ነው፡፡”
“ገንዳውንስ የሚያስጥለው ነገር ቢመጣ ጥሩ ነበር፡፡”
“ታዲያ ከኛ የቀረበ ማን ይመጣል? እኛ የምንበላውን ብናካፍለው...”
“እ... አሁን አስር ዓመቱ ሳይሆን ይቀራል ብለሽ ነው?" አለች ንግሥት የቆሙበት በር ሲከፈት ወደ ውስጥ እያየች፡፡
አንዲት ልጅ በማዳበሪ ውስጥ የተሞላውን ቆሻሻ እየጎተተች ወጣች፡፡ በግምት አባቷ የሚሆን ጎልማሳ
በፍጥነት መጥቶ ከእጇ ላይ እየተቀበለ “እናትሽ ይሄን ቆሻሻ አትንኪ ብላ ስንቴ አስጠንቅቃሽ ነበር!” አለና የቆሻሻውን ላስቲክ ንግሥት እግር ስር ወርውሮ
ተመልሶ ገባ፡፡ ንግሥት እስከ ማዳበሪው ተቀብላ ቆሻሻ ማዳበሪያ ውስጥ ከተተችው፡፡ ጸአዳ የቸኮለች ይመስል ፊት ፊት ፈንጠር ብላ የንግሥትን እጅ ጎተት አድርጋት ስትሄድ ንግሥት የሆነ ነገር
ልትነግራት እንደሆነ ገብቷታል። በፍጥነት ከተል ብላ በጥያቄ አስተያየት አየቻት፡፡
“ይኸውልሽ ይሄ ሰውዬ ባለፈው የነገርኩሽ..”
“የቱ ነው?” ግንባሯን አኮሳትራ ወደ እርሷ አሰገገች።
“ባለፈው ሰርግ ሄጄ ስመለስ...”
“እንዴ! ያ እንኳን በመኪና ካላሳፈርኩሽ ብሎ ያደረሰሽ?”
ጸአዳ በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች፡፡
“አየሽ ልዩነታችንን! አየሽ! አሁን ሰላምታ እንኳን መች ሰጠን እግዚኦ ጌታዬ! የኛስ ነገር ምን ይሻለን ይሆን?” አለችና ወደ
ቀጣዩ በር እያመራች ንግግሯን ቀጠለች።
“አሁንማ ቆሻሻ መስዬ ቆሻሻ ለብሼ ስላገኘኝ ነው፡፡ የስርጉ እለት ደግሞ እግዚአብሄር ይስጣትና ዘመዴ ሰርጓ ላይ የምለብሰው እንዳላጣ ብላ ልባሽ ልብሶቿን እስከጫማዋ ሰታኝ ..”
“አቤት የፀጉርሽ ነገርማ አይነሳ! ጸዱ ሁልግዜ በቡቱቶ እየጠቀለልሽ ለካ እንደዛ አይነት ፀጉር ኖሮሻል? ኧረ ምነው አንዳንዴ ተሰሪው! የዛኔማ እንኳን እርሱን ለእኔስ ሌላ ሰው መስለሽኝ አልነበረም? አወይ ማማርሽ!” አለቻት ንግሥት ወደ ፀጉሯ እየተመለከተች።
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ

👍4
#ማሙሼ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት (የመጨረሻ ክፍል)
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
...
.
.
ጓደኛቸው ሐጎስ ሁልጊዜም
እንደሚያደርገው የሰበሰቡትን ቆሻሻ ወደ ጋሪው ገልብጦ ይዞላቸው ሄደ
ተረኛው በር ላይ እንደደረሱ የቆሙበትን
ያለማንኳኳታቸው ትዝ አላቸውና አንኳኩ አንዲት ሴትዮ አንድ ነገር ከፌስታል ውስጥ አውጥታ ከፊት ለፊታቸው ቁጭ አደረገች
ጸአዳ ጎንበስ ብላ አገላበጠችና፣ “በስመአብ ምንድነው?
ድመት! የሞተ ድመት! ምነው ይህንን
እንኳን ብትጥሉት.?”
በፍርሃት ገለጥ አድርጋ አየቻት ድመቷ ትተነፍሳለች
“ያውም እስከ ሕይወቷ! እኔ አልጥላትም፡፡ ራሳችሁ ጣሏት” መልሳ ከሴትየዋ እግር ስር አስቀመጠቻት
“ስራችሁ መሰለኝ እኮ!” ሴትየዋ በሁለት እጇ ወገቧን ይዛለች
“ይልቅስ ሌላ ነፍስ የሌለው ቆሻሻ የላችሁም?” አለች
ንግሥት ድመቷን በፍርኸት እያየች።”
ሴትየዋ ድመቷን እዚያው ጥላ በሩን በኃይል ዘግታ ገባች
“ዐይን የማያየው ነገር የለ! እንደው ይሄ ቆሻሻ ስንቱን ያሳየናል ንግሥቴ?”
“ጉድ ነዋ የሚያሳየን ከዚህ በፊት የሚገርመኝ ምን የመሰለውን ምግብ በፌስታል ጠቅልለው የሚጥሉት ነበሩ። ዛሬ ደግሞ.ይቅር በለን ጌታዬ!” ወደ ሰማይ አንጋጠጠች
“ምግብ የሚደፉት መቼም ባለቤቶች አይደሉም፡ ሠራተኞች የቀጣሪዎቻቸውን ትርፍራፊ መብላት ስለሚያስጠላቸው የተራረፈውን ምግብ ጠቅልለው ይጥሉና እነሱ እጅ ያልነካውን
ለመብላት ሲሉ ያንን ያደርጋሉ
“ወይ ጥጋብ! እግዚያብሄር የእጃቸውን ይስጣቸው ወይ እንጀራ ያስብላቸው ምነው ከሚጥሉት ለተራበ ቢሰጡት!”
“ግን ለደሃው በጅተዋል ለዚህ እኮ ነው እነማሙሼ ከገንዳ ላይ የማይጠፉት”
ከፊት ለፊታቸው የቤቱ በር ላይ የቆመ አንድ ልጅ ወደ ግቢው እየሮጠ ገብቶ ድምጹን ከፍ አድርጎ “ትርንጎ ትርንጎ ቆሻሾች መጡ” አለ ቆሻሻ የሚወስዱት የሚለውን አሳጥረው ለመናገር
ሲሞክሩ እንዲህ እንደሚሉ በመረዳት ንግሥትና ጸአዳ ተያዩና ፈገግ
አሉ ይህን ቋንቋ ለምደውታል
ትርንጎ የተባለችው ሴት የጠራትን ልጅ ወደ ውስጥ እንዲገባ ተቆጥታ ማዳበሪያዋን ይዛ ወደነሱ ቀረበች ከዚያም ወደ ግቢው ውስጥ እየተገላመጠች ከማዳበሪው ውስጥ አንድ ነገር ስባ አወጣችና
አየቻቸው፤ አዩዋት
“ይህንን ተጠቀሙበት” አለች የያዘችውን ወደነርሱ አቅርባ እያሳየቻቸው
“ኧረ! ... ምንድነው!” ጸአዳ በድንጋጤ ገፋ አደረገችው
“የሚያስፈራ ነገር አይደለም. ትንሽ ዱቄት ነው”
“እንዴ! እኛ እኮ ቆሻሻ ሰብሳቢዎች ነን!”
“ብትሆኑስ ታዲያ ይጠቅማችሁዋልኮ።” አለች ትርንጎ በሹክሹክታ
ይሔ እንደ ዝርፊያ ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ ቢቀርብን ይሻላል።” አለች ንግሥት ግንባሯን አኮሳትራ፡
“ሴትየዋ እኮ የለችም፡”
“የቷ ሴትዮ?” አለች ንግሥት ከቅድሙ የበለጠ ደንገጥ ብላ
“የቤቱ ባለቤት” ትርንጎ አንሾካሾከች፡፡
“ኧረ ወግጂልኝ እህቴ! ምኑን ክፉ ስራ አመጣሽብኝ እኛን የጠቀምሽ መስሎሽ ከሆነ በጣም ተሳስተሻል!”
ጸአዳ ምንም ሳትናገር ፊቷን አዙራ ወደ ቀጣዩ ቤት አመራች
ንግሥት ትርንጎን እንደቆመች ትታት ጸአዳን ተከተለቻት ትርንጎ ወደ ቤትም አልገባችም፡፡ አፏን ይዛ በሳቅ
ትንተከተካለች
ሲጠራት የነበረው ልጅ ወደ ውጪ ወጣና ላስቲኩን ተመለከተ
“እንዴ አልሸወድ አሉሽ እንዴ?” አለና ትርንጎን አያት ትርንጎ ሳቋን አላቋረጠችም
“ኧረ እነሱ ከኔ የበለጡ ቆቆች ናቸው፡፡”
“አይ አመድ አንሸከምም ስለምትሉ
በሲስተም ልታስወስዳችሁ ነበር፡” አለና አመዱን በእርግጫ ጠለዘው አመዱ
ወደላይ ተበትኖ ትርንጎ ዐይን ውስጥ ሲገባና ዐይኗን ስታሽ ንግሥትና ጸአዳ በብሽቀት ጸጥ ብለው ጋሪያቸውን እየገፉ የቆሻሻ አሰሳቸውን ቀጠሉ
“ስራ አይናቅም ቢሆንም አንዳንድ ነገሮች ሲታዩ ግን ይህንን ስራ መስራትም አያስመኝ ይህቺ ማሰብ የተሳናት
ቀለደችብን አይደል እንዴ?” አለች ጸአዳ፡
“እንግዲህ መታገስ ነው እናቴ አለበለዚያ አንድም እርምጃ መሄድ አይቻልም!” አለችና አንዲት ዛፍ ስር ቁጭ አለች ንግስት
“እንዲያው የቆሻሻውን ክርፋትና ግማት ለምደነዋል፤ሽቷችን ሆኗል፡፡ የሰውን አመል፣ ክርፋት.”
ንግሥት ጸአዳ አረፍተ ነገሩን እስክትቋጭ
አላስጨረሰቻትም በተናገረችው ንግግር በሳቅ ትንተከተክ ጀመር
“አንቺ ሳቂ !...ደግሞ ለምንድነው የተቀመጥሽው? ተነሽ ይልቅ ፀሐይ ሳይበረታ!” ጥላት ስትሔድ ተከተለቻት
ቆሻሽውን እየሠበሰቡ በየመንደሩ ከዞሩ በኋላ እነሱም የተቀረውን ለመዘርገፍ ወደ ቆሻሻ ገንዳ አመሩ
ከገንዳው ፊት ለፊት አስፋልት ዳር ላይ ሰዎች ይተራመሳሉ አንድ ልጅ እስከ ጉልበቱ የተተረተረውን ሱሪ እንደዳይጠልፈው ወደላይ ሰብስቦ እየሮጠ መጣ የንግሥት ጎረቤት
ልጅ ነው
“ምን አጋጠመህ አንተ?”
“እ .አ .ማሙሼ?” አለ መናገር አቅቶት በድካም እያለከለከ
“ማሙሼ ምን ሆነ?" አለች ጸአዳ በድንጋጤ
“እኔ እንጃ መሬት ላይ ወደቋል!...እ...እ...ሞቷል ሞቷል
መሰለኝ... እንጃ ብቻ ሰዎች ከበውት ያለቅሳሉ።”
“ወይኔ ልጄን ምን አገኘው ማሙሽዬን!”
“ምን እንዳገኝው አላቅም!” አለ የሚርገበገበው ድምጹ መለስ
ብሏል ንግሥትና ጸአዳ ወደተሰበሰበው ሰው እየሮጡ ሄደው እየተሽሎከሎኩ ማሙሼ ወዳለበት ተጠጉ
ማሙሼ እግሮቹንና እጆቹን ዘረጋግቷቸዋል በአፉ ዙሪያ
የሚታየው ነገር ቀደም ሲል አረፋ አስደፍቆት እንደነበር ያመለክታል ቀይ መልኩ ጠቁሯል አይኖቹ በከፊል ተከፍተዋል ንግሥት ሮጣ ልታነሳው ስትል ፖሊሶች ደርሰው የተዘረጋ
እጇን እንድትሰበስብ ወደ ኋላ ገፋ አደረጓት የማሙሼን ደረት ልብ
ብላ አየችው ትንፋሽ ያለው አይመስልም፡፡ የሷም ትንፋሽ ቀጥ
የሚል መሰላትና አምቃ የያዘችውን ትንፋሿን በረጅሙ ለቀቀችው፡እናቶች መቀነታቸውን በወገባቸው አስረው በለሆሳስ ያልጎመጉማሉ
ሮጦ የነገራቸው ልጅ የንግሥትን ልብስ ጎተት አደረገና፣ “አብረን እኮ ነበርን አሁን” አለ።
“ምን እያደረጋችሁ ነበር?” ጸአዳ ጠየቀች፡፡
“በአንድ እጁ ከላስቲክ ውስጥ እያወጣ ሲበላ አ
ገኘሁትና አላካፍልህም ብሎ ተጣላን፡፡ ከዚያ እሱን ተውኩና ወደ ገንዳው ሄጄ እኔም የተጣለ ነገር ስስበስብ ነበር፡፡ ትንሽ ቆያቶ እዚህ አፈር
ላይ መንከባለል ጀመረ፡፡”
“ውይ ልጄን አፈር ልብላልህ፡፡ ይህን የገንዳ ምግብ ተዉ ብንላቸው...”
“ታዲያ ሲርባቸው ምን ያድርጉ? እኛ እንደሁ አንዳንዴ ነው እንጂ ሁልግዜ አናስታውሳቸው፡፡ እነሱም እኮ የማያቁዋርጥ ሆድ አላቸው።”
ጸአዳ ንግግሯን ስትጨርስ ንግሥት መናገር አቅቷት በታፈነ ድምጽ እያልጎመጎመች እጥፍጥፍ ብላ ወደቀች።
ጸኣዳ “እህቴን!” ብላ ልታነሳት ጎንበስ አለች፡፡
ንግሥት ከአፏ አንድ ቃል ለማውጣት እየሞከረች ነው፡፡ ጸአዳ እየተርበተበተች “ኧረ ድረሱልኝ! ወይኔ እህቴን ምን አገኛት?” አለች።
ንግሥት መላ ሰውነቷ ቆፈን የወረደበት
ይመስል ይንቀጠቀጣል። ጥርሶቿ ይንገጫገጫሉ። እንደ ምንም አፏን በግድ አላቃ ጸአዳን እያየች “
ቀድሞ ከኛ በፊት... ሐጎስ የመጣውን
ሰውየው የጣለውን፣ ተጠንቀቁት ያለንን... የ..የአ........የአይጥ መርዝ...በልቶታል ማለት ነው።” ወዲያውኑ የጸአዳ ተደራራቢ ጩኸት አካባቢውን አናጋው።
✨አለቀ✨

👍2
#ልውውጥ
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
በአስፋልቱ ግራና ቀኝ ያሉ ዛፎች የፀሐይዋን ሙቀት ለማብረድ በሚነፍሰው ነፋስ እየተቃኙ በእንቅስቃሴ ሲያዜሙ ስዓታት የቆሙ ካህናትን ይመስላሉ። የተንጣለለው ስፊ የእርሻ
መሬት በአትኩሮት ሲመለከቱት ነፍስን በሐሴት ያፍነከንካል፡፡
ተፈጥሮን ሳደንቅ ውዬ ባድር አይሰለቸኝም፡፡ ለወትሮው ቤቴ ደርሼ መኪናዬን ካቆምኩ በኋላ ነበር ወጣ ብዬ በዚህ መንገድ ብቻዬን የምጓዘው፡፡ በዚያን እለት ግን ከቤቴም አላዳርስ አለኝ፡፡
መኪናዬን ወደ ዳር አቆምኳትና የለበስኩትን ሹራብ በወገቤ ዙሪያ
አገልድሜ መልካም አየሩን እየሳብኩ ወደ ዛፎች ጥላ አመራሁ፡፡ አልፎ አልፎ ከሚታዩ ሰዎች በስተቀር በአካባቢው ሰው በብዛት ሲንቀሳቀስ አይታይም፡፡ ምናልባት ዐይንን ወርወር ቢያደርጉ እረኛ
የሌላቸው ከብቶችን በተንጣለለው መስክ ላይ ማየት ይቻላል፡፡
ከፊት ለፊቴ በማሳው መሐል የተዘረጋች ቀጭን መንገድ ትታያለች፡፡ በዚህች ቀጭን መንገድ እኔ ወዳለሁበት የመኪና
መንገድ ቁልቁል የሚወርድ ሰው ታየኝ፡፡ ወደታች እየመጣ እንደገና ተመልሶ ወደ ላይ ሲወጣ ስመለከት ነው፡፡በሚያደርገው ተደጋጋሚ እንቅስቃሴ ግራ ተጋባሁ፡፡ በግምት አስር እርምጃ የሚሆን ወደ ፊት ተራምዶ እንደገና ይመለሳል፡፡
ለጥቂት ደቂቃዎች ይህንን ድርጊት ሲደጋግም ዓይኔን ሳልነቅል ተከታተልኩት፡፡ መቼም ጤነኛ ሰው ይህን ያህል ምልልስ ሊያደርግ አይችልም ብዬ አስብኩ ምልልሱን አቁሞ እኔ ወዳለሁበት ሲመጣ ፍርሃትና ግርምት በተቀላቀለበት ስሜት አየሁት፡፡ በአንድ እጁ ሌዘር ኮት በትከሻው አንጠልጥሎ፣ በሌላኛው-
እጁ ያለቀች ሲጋራ ይዟል፡፡ የለበሰው ጥቁር ሽሚዝ አዝራሮች ያለቦታቸው ተሰካክተዉ ፣ ኮሌታው ተዛንፏል።
የሚናገረው ባይሰማኝም አንዳች ነገር እንደ ሚናገር የከንፈሩ እንቅስቃሴ ያስታውቃል፡፡ እኔ ከተቀመጥኩበት ትይዩ ጀርባውን ሰጥቶኝ ተቀምጦ ወደ አንድ አቅጣጫ አተኩሮ አየ። እንደገና
ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደኔ ዞሮና ከወገቡ አጎንብሶ አንዳች ነገር ፈለገ
በፊት የጣላትን ሲጋራ አንስቶ ከተመለከታት በኋላ የቀረችውን ድጋሚ ለኮሰና እስኪበቃው ስቦ ወደኔ አቅጣጫ ወረወረው እኔ ወደቆምኩበት በቀስታ ሲጠጋ እንቅስቃሴውን መቃኘት አላቆምኩም፡ በግንባሩና በጉንጩ ላይ የተሰመሩ ጠባሳዎች ይታያሉ፤ ቁጭ ብዬ ስላየሁትም ይሁን እንጂ ስውየው እጅግ ገዝፎ ታየኝ፡፡ የሱሪው ቀበቶ በቦርጩ ተደብቋል። የቆዳው ቅላትና ወዝ
በምቾት ይኖር እንደነበር ጠቆመኝ፡፡ ድንገት ዐይኖቹን ዐይኖቼ ላይ
አሳረፋቸው፡፡ የዐይኑ ሽፋሽፍት የመርገብገብ ስራውን የቀነስና
በቁጣ የሚያይ ይመስላል፡፡
ዐይኔን ከእርሱ ላይ ነቅዬ ወደ መኪናዬ ለመግባት ስራመድ ረጅምና ግዙፍ ጥላው ሲከተለኝ አየሁና እጆቹን በአንገ ቴ ዙሪያ ሊያኖራቸው መስሎኝ ሽምቅቅ ብዬ ጭብጦ እንዳከልኩ ቀስ ብዬ ዞሬ
አየሁት። ፈገግ ለማለት ሙከራ ያደረገ ይመስላል። እኔም ግራ ገብቶኝ
ፈገግ፣ ኮስተር፣ ደግሞ ፊቴን ፈታ እያደረግሁ ተመለከትኩት፡፡ ባፈጠጠ ዐይኑ ወደታች ቁመናዬን ገረፍ አድርጎ
ቃኘኝና ዝም አለ፡፡ ወደመኪናዬ ልገባ አንድ እግሬን ሳነሳ፣
“ሃይ ዶክተር!” አለኝ፡፡ በድንጋጤ የሰላምታውን አጸፋ መለስኩና፣
“ይቅርታ እንተዋወቃለን?” አልኩት፡፡
“አንተ እንኳን አታውቀኝም፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን በቤታችሁ በር ላይ ስናልፍ ባለቤትህን ከውጪ በር ላይ አገኘናትና ወደቤት ገብተን ቡና እንድንጠጣ
ጋበዘችን፡፡እናቴ እንኳን ፈቃደኛ አልነበረችም
ለምን?”
“አለ አይደል...እ... ልጄ አብዷል ብላ ስለምታስብ..." አለና ምላሽ እንድሰጠው ይሁን አይሁን አልገባኝም ዝም ብሎ
ተመለከተኝ፡፡ የምመልስለት ግራ ቢገባኝም አሰብ አደረኩና “ታዲያ
እኔ በቤት ውስጥ ነበርኩኝ...እ የዚያን እለት ...እ...ከዚህ በፊት አይቼህ የማውቅ አልመሰለኝም?”
“በቤት ውስጥ እንኳን አልነበርክም፡፡ ግን ፎቶዎችህን እንዴት ግሩም አድርጌ አይቼያቸዋለሁ መሰለህ! በተለይ በዚህ
በለበስከው ኮት የተነሳኸው ፎቶ ፓ! እንዴት እንደሚያምር!"
“አንድ ቀን ያውም በፎቶ አይተኸኝ አለመርሳትህ ይገርማል!"
“ታዲያ አሁን እንዴት እብድ ልባል እችላለሁ?
አይገርምህም? እየሰማኋቸው 'የጽጌ ልጅ አብዶ መጣ! ይላሉ።
ምነው የሀገሬ ሰው እፍረቱንና ይሉኝታውን ወዴት አደረሰው? እ?
ንገረኝ! ወዴት አደረሰው?” በንዴት እየተወራጨ እጁን ወደኋላው
ሰደድ ሲያደርግ ልቤ በጉሮሮዬ የተሸነቀረች ይመስል ትንፋሽ
አጠረኝ እንደምንም ለመረጋጋት ሞከርኩና “እ...ግዴለም
እንዳልሰማህ ማለፍ ነው” አልኩት፡፡
“እንዴት እንዳልሰማ ይታለፋል? አየህ! እኔ የሀገሬ ሰው፣ መንደሬና ተስማሚ አየሩ ቢናፍቀኝ ሁሉንም ነገር ትቼ መጣሁ፡፡
ሰው ግን አልገባውም፡፡ የሚገርመው ነገር አንተን ማግኘት እንዴት እፈልግ እንደነበር…ተካልኝ እባላለሁ” ጨበጠኝ፡፡ እጄ በመዳፉ እቅፍ ውስጥ ሲገባ ጣቶቹ ተንቋቁ፡፡ ከዚያም በብስጭት እንደ መቁነጥነጥ ብሎ፣ ሰው ብቻውን ሲቀመጥ፣ ከራሱ ጋር ሲማከር እብድ ይባላል ወይኔ ተካልኝ!" አለ።
አፌን ለመናገር ከፍቻለሁ። ግን ቃል አልወጣኝም፡፡ እዚያው እንደቆመ አሻግሮ ወደ መንደሩ ተመለከተና
“መንደሬን እንዴት እወዳታለሁ መሰለህ አሁን ፊቱ ላይ ትንሽ ፈገግታ ብልጭ ሲል ታየኝ ።
“ስንት ግዜ ውጭ ሀገር ተቀመጥክ?” አልኩት፡፡
“ድፍን ሃያ አመት፡፡"
“ብዙ ቆይተኻል!”
“ምን ዋጋ አለው? ምንም አልሰራሁሰትም ፡፡ ታየዋለህ ያንን ቀይ ጥርያ ቆሮቆሮ ቤት ?"አለና ወደኔ ተመለከተ።በአወንታ መለስኩለት።
እናቴን ከዛ አላወጣኋትም።ድሮ አባቴ የሰራው ቤት ነው።ምንም ለውጥ አልተደረገበትም። ምንም!"
“እንግዲህ ምን ታደርገዋለህ? አንድ ግዜ ሆኗል።”
“አዎ! ምንም ላደርገው አልችልም! ምንም! ብዙዎች አሁን አንተ ያልከውን ነው የሚሉኝ፡፡ አባባሉ ተቀየረ እንጂ ያው
እንደነሱ!”
ዐይኖቹን ለመሸሽ ጥረት ባደርግም አላመለጥኩም፡፡
ዞርኩበት ዞሮ በኔ እይታ ፊት ለፊት ቆመና ወደኔ እየተጠጋ፣
“አንዴ ሆኗል! አንዴ ሆኗል! ለመሆኑ የሆነውን የመቀየር አሁንስ ጊዜ የለንም? የለንም ወይ?” ከፊት ለፊታችን ያለው ጋራ
አስፈሪ ድምጹን መልሶ አቀበለኝ፡፡ አምላክ የዛሬን እንዲያወጣኝ ደጋግሜ ተማጸንኩ፡፡
“ግን ለምን አበደ ይሉኛል? አሁን እኔ እብድ እመስላለሁ?"
የሚናገረው ሁሉ ያስጨንቀኝ ጀምሯል፡፡ ለጥቂት ደቂቃ ዝም አልኩ፡፡
“አሁን እኔ እብድ እመስላለሁ ወይ?”
“ኧረ አትመስልም፡፡ ምናልባት ቅድም እንዳልከው ብቻህን ስታወራ ያው እንደምታውቀው ብቻ ማውራት እብድ ያሰኛል።”
“እኔ ብቻ ነኝ ብቻዬን የማወራ? ድፍን የዓለም ህዝብ ብቻውን እያወራ እንደሚሄድ አታውቅም? አንተ ብቻህን
አታወራም? ቆይ አንተ እራስህ አሁን ለኔ ምን አይነት ስሜት ነው ያለህ? ሳትዋሽ ንገረኝ” አለኝ፡፡ ትንሽ ፈገግታ በፊቱ ላይ ብልጭ ያለ መሰለኝና እኔም ፈገግ ብዬ፣
“አንተን እብድ ነው የሚያስብል ምንም የተለየ ነገር አላየሁም” አልኩት፡፡
“ዋሽህ ዶክተር! ከውሸት ሁሉ የከፋው ደግሞ ምን አይነት ውሸት እንደሆነ ታውቃለህ?.. ራስን መዋሸት፡፡” አለና አሁንም አሻግሮ ማየት ጀመረ፡፡ ሁለተኛ በዚህ መንገድ ላለመምጣት በውስጤ
ማልኩ።
“አሁን ለምሳሌ ዋሸኸኝ አይደል?” አፈጠጠ፡፡
ፈራ ተባ እያልኩ፣
“በእርግጥ...” አልኩና ዝም አልኩ።
“በእርግጥ ምን?”
“እ..ብቻህን ስታወራ በማየቴ ትንሽ እንደመደንገጥ ብዬ ነበር፡፡ ግን ብቻ ማውራትህ ላንተ መልካም ከሆነ ጥሩ ነው። ግን በተቻለህ አቅም ከሰው ጋር ለመሆን ሞክር፡፡”
ለምን እንዲህ ብዬ እንደማወራ ግራ ገባኝ። የምናገረው አስቤበት ሳይሆን የሱ ስሜት

#ያንሰራራ_ነፍስ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
ግን ለምን? ለምን ባሌ...እኔን ማሰብ ተሳነው? አሁን አሁን እስከመኖሬም ማወቁን እጠራጠራለሁ። ለስሙ አብረን ውለን እናድራለን፡፡ ለወገን ለዘመድ የሚተርፍ ፍቅር አለው፡፡ ለኔ ያልሆነበት ምክንያት ምንድነው? ምን አደረኩት? ልጆቼን ለማሳደግ ስል የሰው ደሃ እንደሆንኩ ያውቃል፡፡ የራሱን ፍላጎትና እርካታ በማዳመጥ ፈንታ የኔን ስሜት አንድ ቀን እንኳን አዳምጦልኝ
አያውቅም፡፡ ታዲያ እኔ ፍቅርን ብናፍቅ ማን ይፈርድብኛል? ማን ይከሰኛል?' ከራሷ ጋር እየተሟገተችና ሰው እንዳያያት ወደኋላዋ እየተገላመጠች ከቀጠሮው ቦታ ደረሰች፡፡
በጻፈላት መልዕክት መሰረት የተከራየበትን ሆቴል ለማግኘት ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶባታል፡፡ በድካምና በፍርሃት የዛለ ሰውነቷን እየጎተተች የተከራየበት ሆቴል ስትደርስ እግሯ መንቀጥቀጥ ጀመረ።
ጆ ያረፈበትን ክፍል ስታይ ዛሬ የመጀመሪያ ቀኗ ነው፡፡ ስትገባ ጅቡቲያዊው ወጣት ሽርጡን እንዳሸረጠ
ከተቀመጠበት ምንጣፍ ላይ ተነሳ፡፡ “ኦ! ቢ ኦ! ቢ" እያለ ተጠጋት።
እሱ የሷን ፣ እሷ የሱን ስም መያዝ ስላልቻሉ ስማቸውን አሳጥረው በመጀመሪያው ፊደል ይጠራራሉ፡፡
ፍርሃት ያጠላበትን ፊቷን እንደምንም ደብቃ ፈገግ አለች፡፡እጆቹን በወገቧ ዙሪያ ጠምጥሞ አቀፋት። እንደገለባ ቀለላት፡፡
በእቅፏ የማይሞላ ደቃቃ ነገር ነው።
አጥንት እጆቹን ከላይዋ ላይ ሲያነሳ ተራ በተራ ቃኘቻቸው።በአካሉ ላይ ስጋ ያለው አይመስልም፡፡ በበለዘና በጠቆረ ቆዳ የተለበጠ እንጨት መሰላት፡፡ ከወገቡ በላይ እራቁቱን ነው።
ዐይኖቹን ስውነቷ ላይ እያንከባለለ በመጎምጀት አያት። ዛሬ እንደሌላው ሁሉ ቀን አልተሸፋፈነችም። የሰውነቷን ቅርጽ በውል ለይቶ የሚያሳይ ልብስ ለብሳለች። ፀጉሯንም ከተደበቀበት አውጥታ ነስንሳዋለች። ረጅም አንገቷንና ሰልካካ አፍንጫዋን ተራ በተራ ሳመና ጥርት ያለ ጠይም ቆዳዋን እየዳበስ ትላልቅ አይኖቿን በፍቅር ተመለከታቸው። “ኦ ቢ ቢዩቲፉል” አለ፡፡ በወገቧ ዙሪያ እጆቹን አቆላልፎ ቀጭን ወገቧን እየለካ።
ሹራብ፣ ሸሚዝ፣ ሱሪና ሌሎችም ልብሶች ተደበላልቀው በወንበር ላይ ተከምረዋል፡፡ አገልግሎታቸውን የጨረሱ የጁስ
ካርቶኖችና ቁርጥራጭ ቸኮሌቶች በአነስተኛ ጠረጴዛ ላይ ተበታትነዋል፡፡
ቢ እነዚህን ሁሉ ዝርክርኮች በተዝረከረከ መንፈሷ እየቃኘች ልትደብቀው ያልቻለችውን ፍርሐትና ድብርቷን ይዛ ከአልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠች፡፡
ጆ አጠገቧ ተቀመጠና ከንፈሮቿን እየተስገበገበ ጎረሳቸው፡፡
እፉ ውስጥ ያለው የጫት ድቃቂ ወደ አፏ ሲዘልቅ ምራቋን ልትተፋ ሞከረችና ይከፋዋል ብላ ስላሰበች በትግል እየተናነቃት ዋጠችው።
ከንፈሯን በማፈግፈግ ከከንፈሩ አላቃ ገፋ አደረገችው፡፡በአድናቆት ተመለከታት፡፡ “ኦ! ቢ ኦ! ቢ” ተመልሶ ወደ ከንፈሮቿ
ቀረበ።
በድጋሚ ገፋችውና “ኖ...እ... ዛሬ የመጣሁት ከአንተ ጋር ሻይ ለመጠጣት ነው እንጂ ለመቆየት አይደለም፡፡ አየህ መጀመሪያ መግባባት አለብን፡፡”
እጆቿን እያወራጨች ለማስረዳት ሞከረች፡፡ አልገባውም፡፡ትንሽ እንደመደናገር ብሎ፣
“አሌብን አለቢን?” አለና በመጨረሻ የተናገረችውን ቃል ደገመው፡፡ እንዳልገባው አወቀች፡፡ እንዴት እንደምታስረዳው ጨነቃት።
“ቺግር አለ? ቺግር አለ?” ካለ በኋላ ራሱን ነቀነቀና ወደ ኋላው አልጋ ላይ ተንጋለለ፡፡ አሻግራ ከፊት ለፊታቸው ያለውን ፎቅ
አየችና ሰዎች የሚመለከቷት ስለመሰላት ተነስታ መጋረጃውን ጋረደች፡፡
እዚያው መስኮቱ ጋር እንዳለች በእንግሊዝኛ በቀጣዩ ቀን እንደምትመጣ ነገረችው፡ በአዎንታ ራሱን ሲነቀንቅ ሀሳቧ የገባው መሰላት።
እተቀመጠችበት ትቷት ወደ መጸደጃ ቤት ገባ፡፡ የገላ መታጠቢያ ውሃ ሲለቀቅ አደመጠች፡፡ '
ተመስገን ሀሳቡን ቀይሯል፡፡ አለችና በፍርሐት የተሸማቀቀ ሰውነቷን ፈታ አደረገች፡፡
እየቆየች ስታስበው ለምን እንደመጣች ገረማት። ትናንት ጠዋት ገንዘብና ፍቅርን እለግስሻለሁ ነይ ብሎ በእንግሊዝኛ
በሞባይል መልእክት የጻፈላት ትዝ አላት፡፡ መልእክቱን የጻፈለት ሰው እንዳለ ተገንዝባለች፡፡ ምክንያቱም ከአረብኛና ከፈረንሳይኛ በስተቀር ለመግባቢያ የሚሆን ቋንቋ የለውም፡፡
ገንዘብና ፍቅር ባንድ ላይ የሚቸሩ ቁሶች ናቸው እንዴ?”እራሷን ጠየቀች፡፡ ግን ሁለቱንም ነገሮች ብትፈልጋቸውም
እንደፍቅር ግን የራባት ነገር የለም፡፡
የጆ ክፍል ምቾት የሚስጥ አይደለም፡፡ ሁለት ሻንጣዎች እዚህና እዚያ ወድቀዋል፡፡ የአልጋ ልብሱ መሬት ላይ ተዘርግቷል።እላዩ ላይ በአንድ ሳህን ላይ የተለነቀጠ ጎመን የሚመስል ነገር
ተቀምጧል። ምናልባት የታኘከ ጫት ይሆናል ብላ አሰበች፡፡
የክፍሉ ሽታ ከራሷ ሽቶ ጋር ተዳምሮ ውስጥን የሚያውክ ሽታ ፈጥሯል። “ጆ ትክክለኛ ፍቅር ይሰጠኛል?” ለሚለው ሀሳቧ እርግጠኛ አይደለችም፡፡
ግን በባሏ ተስፋ በቆረጠች አግኝታዋለች፡በተዋወቁበት ጥቂት ጊዜ ውስጥ እሷን ከማድነቅ የተቆጠበበት ደቂቃ አልነበረም፡፡
ከጆ የምትወድለት ነገር ቢኖር አድናቆቱን መግለጹና ለደቂቃ ከላይዋ ላይ የማይነሱ ዐይኖቹን ነው፡፡ ግን ፍቅር እንዳልያዛት
እርግጠኛ ነች፡፡የባሏን ቁመና አሰበች፡፡ ቆንጆ ነው! ቆንጆ! ታዲያ ምን ዋጋ
አለው? ግን ለምን ይሆን ስሜቴ የማይገባው? የምለብሰው፣
የምበላውና የምጠጣው፣ የማይገደው?”
“ቢ ካም! ቢ ካም!” አላት፡፡
በፍርሃት የመታጠቢያ ክፍሉን ከፍታ ጭንቅላቷን ወደ ውስጥ አስገብታ ተመለከተች፡፡ የተገመሱና የጠቆሩ ጥርሶቹን አሳያት፡፡ ደስ የሚልና ብሩህ ፈገግታ ከፊቱ ላይ አነበበች፡፡ እንደዚህ
አይነት አስደሳች ፈገግታ ከአስቀያሚ ጥርሶች መሐል ይፈጠራል ብላ አስባ አታውቅም፡፡
ካም! ካም!” አለና እጆቹን በገላው ላይ አሻሻቸው፡፡ ነይና እንታጠብ እንዳላት ገባትና ወደኋላ አፈግፍጋ ወደ ቀደመው ቦታ ተመልሳ ቁጭ አለች፡፡
ወጥታ ልትሄድ አሰኝቷት ወደ በሩ ተመለከተች፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባት እርግጠኛ አልሆነችም፡፡
“ምን ፈልጌ መጣሁ?...f ለምን? ... ግን አይፈረድብኝም፡፡ በፍቅር ዐይኑ እያየ የሚንከባከበኝ እፈልጋለሁ፡፡ አምላኬ መጥፊያዬ ደረሰ ማለት ነው? እኔ አልቻልኩም፡፡ አንተ ከቻልክ ግን ከዚህ ብልግና አውጣኝ?” ፈጣሪዋን ተማጸነችዉ።
“እውነት ይሄ ሰው እውነተኛ ፍቅር ይለግሰኛል? እስቲ ለማንኛውም ልሞክረው፡፡ እኔ የምፈልገው ፍቅር ምን አይነት ነው? ግዚያዊ ፍላጎቱን የሚያረካብኝን ወንድ ወይስ...?”
ራሷ ለራሷ ጥያቄ ሆነች፡፡ ወደ ራሷ ድምዳሜ የደረሰች ሲመስላት ደግሞ፣ አሁን የኔን ነፍስ የሚያስጨንቃት ፍቅር
የማጣት ጉዳይ ነው ብላ ለሚጮኸው ውስጧ መለሰችለት።
እሰራልሀለሁ! እንዳስጠላሁህ እጠላሀለሁ!፡፡ አለቅህም! አሁን
በእርግጥ የምትለኝን ሆኛለሁ። እንኳን
ደስ ያለህ! ምንም የማላውቀዋን ጨዋ “አመንዝራ! ብለህ ትሰድበኝ ነበር፡፡
እግዚአብሔር ይይልህ፣ አመነዘርኩልህ... እንዴት አይነት ደካማ ሰው ነኝ!”
ግድግዳውን ቃኘች፤ ቀለሙ በያለበት ተፋፍቋል፡፡ በተፋቀው ቀለም ውስጥ ዝብርቅርቅ ስእሎች ታዩዋት፡፡ በስእሎቹ ውስጥ እርሷ አለች፡፡ ከባሏ ሊነጥላት የእርሷን ቀሚስ የሚጎትት ኮስማና ሰው
ታያት። አሁን በስስት እያየ የሚያደንቃት ትፈልጋለች። “እኔ አድናቆት ፈላጊ ሴት ሆኜ ነው? አይ ማንኛዋም ሴት ከማንም ወንድ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የተቃራኒ ጾታ እንክብካቤ ትወዳለች።
እኔ ብቻ አይደለሁም፡፡ ጆ ሲያየኝ ውሎ ሲያየኝ ሲያድር አይጠግብም፡፡ በርከት ላለ ግዜ ያደንቀኛል። ጥሩ ፍቅር ሊለግሰኝ ፍቃደኛ እንደሆነ ነግሮኛል። ምን ዋጋ አለው? በየትኛው ቋንቋችን
እንግባባ? የጭንቀት ትንፋሽ በረጅሙ

#ክፍል_ሁለት(የመጨረሻ ክፍል)
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
ጆ በሐሳብ እርቃ የሄደችውን ቢ በዐይኗ የሞላውን እንባ አይቶ በርከክ አለና አገጯን ይዞ እየተመለከታት፡፡ “ቺግር አለ?” አለ።
“ችግር አለ” የሚለውን ቋንቋ ብቻ እንዴት እንደለመደው ደንቋታል። “ምናለ አማርኛ ቢስማና የልቤን በነገርኩት፡፡ ይሄኔ
አውቄ የምባልግ፣ በኃጢአት የወደኩ፣ አዳፋ አድርጎ ያየኝ ይሆናል፡፡
ምክንያቱም ባልና ልጆች እንዳሉኝ ነግሬዋለሁ። እሱንም ባስተርጓሚ።
ምን እንደምትፈልግ ግራ የገባው ይመስላል። ገፋ አድርጎ ወደ አልጋው አንጋለላት፤ እንደተኛች መላ አካሉን አየችው፡፡
ሀፍረተ ስጋው ከመላው አካሉ የሚበልጥ መሰላት። ደግሞ ከወደ ጫፉ ለምጽ የያዘዘው ይመስል ነጽቷል። ቀፈፋት፡፡ ዳበሳት፡፡ ዝም አለችው፡፡ እጇን ይዞ አካሉን እንድትዳብስለት በእጁ አስነካት።
እሷ ግን በተቃውሞ ወደ ነበረበት ቦት መለሰችው፡፡
ቀስ እያለ እላይዋ ላይ የተጋደመው ጆ አንዳች ኃይል የተመላ ይመስል ከብዶ ነፍስና ስጋዋን የሚለያይባት መሰላት፡፡
ያንን ሩህሩህና ኩሩ ባሏን በዐይነ ህሊናዋ አየችው። ሰፊና ግዙፍ ትከሻ ቢኖረውም ይህን ያክል አይከብዳትም፡ታከብረዋለች፣
ትወደዋለች ከሱ ሌላ ምንም አትፈልግም ነበር፡፡ እሱ ግን አንደ አንድ ግኡዝ ነገር መገልገያ አድርጓታል። እሱ ለብዙ ሰዎች ጉርስና ልብስ ነው፡፡ እሷ ግን በእርዛትና በጥማት ብትንገላታ ግድ የለውም፡፡
እኔ ገንዘብ ከሰው መጠበቅ የለብኝም፡፡ ምክንያቱም የመስራት አቅምና ችሎታ አለኝ፡፡ ስራ መስራት አለብኝ፡፡ ግፋ ቢል
ባሌን ላጣው እችላለሁ፡፡ ለገንዘብና ለፍቅር አሳልፌ ጨዋነቴን ልለውጠው አልፈልግም።ከነፍስና ስጋዋ ጋር ተሟገተች። ወዲያው ደግሞ ግን ደግሞ አይዞሽ እያለ የጎደለኝን እየፈለገ ሲከፋኝ እያባበለ ስሜቴን የሚያዳምጥ ወንድ እፈልጋለሁ፡፡ እኔ ለባሌ የማደርገውን
እሱም ለኔ ሊያደርግ ግድ ነው፡፡ አለበለዚያ ግን... አለች በትግሉ
መካከል እየተወራጨች።
ጆ ከንፈሯን የማላመጥ ያህል በአፉ ውስጥ ከቶ እያልመጠመጠ ነው። “ለምንድነው ከንፈሬን እንዲህ አድርጎ
የሚበላኝ?” አፏን ደም ደም አላት።
ከደረቱ ቀና ብሎ የለተቱና ከማስያዢያቸው ያመለጡ
ጡቶቿን ሊይዝ እጁን ሲስድ የጡት ማስያዢያ ስፖንጆች ውስጥ እጁ እያዋለለ የከሰሉ ደቃቃ ከንፈሮቹን አሞጥሙጦ ሊስማቸው ገሰገሰ፡፡
እጁን ከጡቷ ላይ መንጭቃ አወጣችው። መልሶ አስገባ፡፡ ይሄኔ እኮ ያጎጠጎጠ መስሎት ይሆናል፡፡ እንደ ለተተ ማን
በነገረው፡፡ ኮስተር ብላ እንደቀድሞ አፈጠጠች፡፡
“ቺግር አለ?” አለና በሚያሳዝንና በሚያባብል ዐይኑ አያት፡፡
“ችግር የለም!” አለች፡፡ እያቃተተች፡፡
“ኦ! ቢ ኦ! ቢ አይ ላቭ ዩ ሶ ማች፡፡” አለና ከላይዋ ላይ ተስፈንጥሮ ተነሳቶ አጠገቡ የተቀመጠች አነስተኛ እቃ ማስቀመጫ
ስር አጎነበሰ፡፡ ሰውነቱን ድጋሚ ተመለከተችው፡፡ ትንሽ፣ ደቃቃ
እራቁቱን ቁጢጥ ብሎ ብይ የሚጫወት መሰላት፡፡ እጆቹን ወደ ውስጥ ልኮ አንድ ነገር መዞ አወጣና ወደርሷ አመለከታት፡፡
የሚያመለክታትን ነገር አየችው። አውጥቶ አሳያትና አቀበላት፡፡ ተቀብላ አየችው፡፡ ኮንደም ነው፡፡
“እኔ ለዛሬ ዝግጁ አይደለሁም፡፡ በኮንደም እንጠቀም ማለትህ ጥሩ ነው” አለችው፡፡
“ቺግር አለ?” አላት፡፡
ችግር ያምጣብህ! ችግር አለ ከማለት በስተቀር የሚያቀው ንግግር የለም፡፡ አመዳም! አለች በውስጧ፡
ተነስቶ መሄድ እንደሚያዋጣት ገባትና ከመቀመጫዋ ስትነሳ በማባበል እያየ አስቀመጣትና ስልክ ደወለ፡፡
ሁለቱም በራሳቸው ሐሳብ ሲባዝኑ ከቆዩ በኋላ በር ተንኳኳ፡፡ ጆ ሽርጡን አገልድሞ ከፈተና በፈረንሳይኛ ድምጹን ከፍ
አድርጎ አንድ መልእክት አስተላለፈ።
አዲሱ ሰውዬ ወደ እርሷ እየተመለከተ፣
“ሀሳብሽ ምን እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋል። ምክንያቱም እርሱ በጣም ይወድሻል። ልትረጂው ይገባል እኔ አብሬው የምሰራ
ጓደኛው ነኝ፡፡ ላንቺ ሲል እንግሊዘኛና አማርኛ ሊማር ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ለብልግና ወይም ለጊዜያዊ ስሜት የሚፈልግሽ እንዳልሆነ ልትረጂ ይገባል።” አላት፡፡
ተመልሳ ተቀመጠች። ጆ አሁንም ፈገግ ለማለት ሞክሮ አስቀያሚ ጥርሶቹን አሳያት። አንዳች ነገር እንድትናገር በጥያቄ አስተያየት እያዩዋት ነው።
የመጣው ሰው ንግግሩን ቀጠለ፡፡
“በእርግጥ ምንም ባለመነጋገራችሁ ብዙ ነገሮች ላያግባቧችሁ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ለጊዜው ፍቅር ሊያግባባችሁ ይችላል፡፡ ወደፊት ግን በሚያደርገው ብርቱ ጥረት ቋንቋዉን ሊያዳብርና ልትግባቡ
ትችላላችሁ” አላት፡፡
ዛሬ እንደምትቸኩልና ለሌላ ጊዜ በረጅም ሰዓት በሰፊው እንደምታጫውተው ነገረችው። ጆ አስተርጓሚ ጓደኛውን
ቀና ብሎ አይቶ አመስግኖ ሸኘውና አጠገቧ ቁጭ ብሎ ጀርባዋን
እየደባበሰ በፍቅር ተመለከታት።
ቢ አሁን ከቅድሙ ፍርሃቷ እየለቀቃት ሲሄድ ተሰማት፡፡ ፈገግታውን አሳያትና ሽርጡን ከላዩ ላይ ወደ መሬት ጣለው::
ቅድም ካየችው የተለየ ነገር የለም፡፡
ጭንቀቷን ለመርሳት ስትሞክር የፍትወት ፍላጎት በመላ ሰውነቷ የናኘ መሰላት። እጆቿን እሱ እንደፈለገው በገላው
ልታዟዙር ሞከረች።
ጆ አንዴ ከንፈሯን ስሞ ከፊት ለፊቷ ቁጭ አለ፡፡ ልትዳራ ፈልጋ የውጭው ጨለማ እየጠነከረ ሲመጣ ቤቷን አሰበች። ይህኔ
ባሏ ከንፈሩን ጥሎና አገጩን አስረዝሞ ይጠብቃታል፡፡ ልጆቿ በተቀመጡበት ያንጎላጃሉ። በፍጥነት ተነሳች፡፡ ጆ ዘሎ እጁን ሲይዛት የሚያስገድዳት መሰላት፡፡ አንስታ በመስኮት ልትወረውረው እንደምትችል፣ ጠንካራ እንደሆነች፣ እንኳን ይህን ኮስማና ቀርቶ በትግል
እንደማያሸንፋት ታውቃለች።
ጆ ከተዝረከረኩ እቃዎቹ መኸከል ሱሪውን ስቦ ከኪሱ በርከት ያሉ አረንጓዴ ብሮች አውጥቶ ሰጣት። ቢ በፈገግታ ያለ
አንዳች መግደርደር ተቀበለችውና ከእጁ አፈትልካ ወደበሩ አመራች፡፡
ቺግር አለ?” አላት።
ችግር ያጣድፍህ!' አለች በውስጧ፡፡ ወደ ውጭ ወጥታ በሩን በላዩ ላይ ዘጋችው:: የሰጣትን ብር ጨምድዳ ቦርሳዋ ውስጥ
ከተተች፡፡
“ደግሜ እመጣ ይሆን ጌታ ሆይ? እኔ ለመምጣት እፈልጋለሁ። አንተ ግን ኃጢአት እንዳልሰራ እርዳኝ፡፡
ዞራ ተመለከተች፡፡ ከፊል እርቃኑን ከክፍሉ ውስጥ አውጥቶ ይመለከታታል። ቅን የሚያስመስሉትን ዐይኖቹን አይታ እጇን
አርገበገበችለት፡፡ ሙሉ በሙሉ ወጥቶ ተመለከታት።
ፈገግታ ከፊቱ አልጠፋም፡፡ “ምስኪን!” አለችና አካባቢዋን ሳትቃኝ እንዳቀረቀረች አጎንብሳ ወጣች፡፡
አምላኬ ሌብነት እንዴት ያሳቅቃል? ምንድን ነው የማደርገው? ኦ ጌታ ሆይ! አንተ ምን እንደማደርግ ታውቃለህ? ምን
እንደሆንኩም ጭምር፡፡ አሁን ኃጢአት እያደረግሁ ነው ማለት ነው? ግን ማንን ነው የምጎዳው? ማንንስ ነው የምጠቅመው? ይሄ በእጄ
ጨምቄ የያዝኩት ብር የኃጢአት ገንዘብ ነው?”
ቀስ በቀስ ወደ ራሷ ተመለሰች። “አይሆንም እኔ ጨዋ ነኝ፡፡ አሁን ያደረግሁትን ሁሉ አላደረግሁም፡፡ በፍጹም! ይሄም ገንዘብ የኔ አይደለም! ጆም ቢሆን ከንፈሬን አልሳመም! ጆንን አላውቀውም፡፡ የማንንም እርቃነ ስጋ ተመልክቼ አላውቅም፤ ከባሌ በስተቀር፡፡”
ከደቂቃዎች በፊት የሰራችውን እውነት ሽምጥጥ አድርጋ ክዳ፣ በሩጫ ወደ ጆ ክፍል ደርሳ በሩን ስትገፋው ተከፈተ፡፡
ጆ አልጋው ላይ ተኝቶ ያቃስታል። ይህን የሚያቃስት ሰው አታውቀውም። ከሔደች በኋላም እንደሚያስቃስተው
አልገባትም፡፡ ግን የእርሱ ገንዘብ በእጇ አለ። ብሮቹን አልጋው ላይ በተነቻቸው፡፡
ጆ በድንጋጤ ከተንጋለለበት ተነስቶ ብሮቹን አያቸው ሐሳቧን እንደቀየረች ገባው፡፡ የተበተነውን ብር ከላዩ ላይ አራግፎ ወደ በሩ እሮጠ፡ የለችም፡፡
ተመልሶ በመስኮቱ በኩል ወደ ውጭ ሲመለከት

👍4❤1🔥1
#ሸክም
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
“እናንተው ሰው የተፈጠረበትን ቀየ ትቶ ወዴት ይሰደዳል?” አለች ድምጿን አውጥታ ውስጥ ውስጧ የሚብላላውን ነገር ስታስታምም ቆይታ ልታጥብ ላወጣችው እንስራ ከቂጡ ስር የሳር
ጉዝጓዝ እያደረገችለት፡፡
አይኖቿን አጥብባ በርቀት እያየች አሰበች። ዛሬ ልንገራት?..ልንገራትና ምን እንደምትል ልስማ? እስከመቼ
እደብቀዋለሁ በዚያ ላይ ሰውየው እኔን ብቻ ሳይሆን የሰፈሩን ሴት ሁሉ ለማማገጥ ቆርጦ የተነሳ ነው የሚመስል...ወይ ልንገራትና የመጣው ይምጣ!” አጎንብሳ ማጠብ ጀመረች። ወዲያው ከነገረቻት በኋላ ልትል የምትችለውን አሰበች፡፡
“አይ እንዲህማ አይሆንም አንቺ ባልሽ የሞተ እንደሁ እኔም ባሌን ማጣት አለብኝ? እኔ እንደሆን ባሌን አምነዋለሁ፤ አንድ ማስረጃ ሳላገኝ ባሌን ልኮንን አልችልም' ትለኛለች ይቅርብኝ፡፡በእንስራ ውስጥ የከተተችውን ውሃና የግራዋ ቅጠል ደህና አድርጋ ስትደፍቀው አረፋው ተኩረፈረፈ፡፡ ወዲያው ከአንዳች ነገር ጋር
ትግል ስትገጥም የቆየች ይመስል በረጅሙ ተንፍሳ የምታጥበው እንስራ አጠገብ ተቀመጠችና በስንጥር ጥርሷን እየጎረጎረች ማሰብ ቀጠለች።
ከጎረቤቷ ከሸክም ጋራ ጥሩ ጓደኛሞች ናቸው፡፡ ሳይተያዩ። ውለው አያድሩም አሁን ግን የሸክም ባል እሷን ለማባለግ
በሚያደርገው ሙከራ በሀሳብ መብከንከን ከያዘች ዋል አደር አለች፡፡
ብዙ ጊዜ ውሃ ልትቀዳ ወደ ምንጭ ስትወርድ እየተከታተለ ጎነታትሏታል አመናጭቃ ገስጻዋለች። ቁጣዋ
ግን የገባው አይመስልም፡፡ በተደጋጋሚ ወደ ቤቷ ለመግባት ሙከራ ሲያደርግ
በር ዘግታ አባራዋለች። ጥሩሰው በር ላይ ብዙ ግዜ የታየው የሸክም ባል ጥሩሰውን በመንደሩ ሰው ጥርስ ውስጥ አድርጓታል ከሸክም ጋር ያላት ጥብቅ ፍቅር ደግም ይሄንን ለማስረዳት ድፍረት አልሰጣትም፡፡
ሐሳቧን ትሸሽው ይመስል የምታጥበውን እንስራ ትታ ከበረት ገብታ የተፈነቃቀሉ ድንጋዮችን ስታስተካክል ቆየች፡፡ የሸክም
ባለቤት እንደተለመደው ለጭቅጨቃ በር ድረስ መጥቷል። ሚስቱ ጥሩሰውን እየተጣራች ወደ ቤት ስትቀርብ ጥሩ ስው ከበረት መሆኗን አጢኖ በድንጋጤ ወደጥሩ ሰው ቤት ሰተት ብሎ ገባ፡፡
ሸክም እየቀረበች ስትመጣ ደመነፍሱን የጠላ እንስራዎች ወደሚቀመጡበት አነስተኛ ጨለማ ክፍል ውስጥ ከጋንና
ከእንስራዎች መኸከል ተዳበለ።
ሸክም በር ላይ ቆማ ስትጠራት ጥሩሰው እጇን በቀሚሷ እየጠራረገች ከበረት እንደወጣች ዐይኗ በበለዘው የሸክም ጉንጭ ላይ አረፈ።
“ከሳምንት አንድ ቀን የማይማታ ባል ምን ባል ይባላል?” አለች ሸክም የጠቆረ ፊቷ ጥሩሰውን እንዳስደነገጣት ልብ ብላ፡፡
“ኧረ ያንሳሽ ያባቴ አምላክ እቴ! ደሞ ብለሽ ብለሽ ዱላ ቀረብኝ ትይ አንቺ? ኧረ ይቦጭቅሽ! አህያ ይመስል ሰው ዱላ
ይወዳል እናንተዬ?”አለች ጥሩሰው የምታጥበውን እንስራ አቋርጣ፡፡
“ኤዲያ! በይማ ቁጣውን ትተሽ ከደጃፍ ላይ እንግባና ከሞላሽው አቅምሽኝ?” አለች። የያዘችውን ዋርማ እያቀበለቻት፡፡
“እና በጠዋት ባልሽን ወደ ስራ ትልኪያለሽ እንጂ የሚጠጣ
ጠላ በጠዋቱ...”
“ምን ላድርግ ብለሽ ነው? ይህችን ባይቀምስ አይደል ሰሞኑን ሸንቆጥ ሳያረገኝ የቀርቶ እናታለም፡፡”
“በይማ ቆይ፣ መቀነሻውን በወግ በወግ ሳላጥብ መተሺ...ኤዲያ... እንደው እኔስ በጠዋቱ ባትስጭው ነበር የምመርጥ?”
ሸክም የተኙትን የጥሩሰው ልጆች ከፊል እርቃን በነተበው ብርድ ልብስ ሸፈን እያደረገች ከመደቡ ላይ ቁጭ አለች፡፡ ልጆቹ የተኙበት ወዝ የጠገበ ቁርበት ተንሸራቶ ወደ መሬት ወድቋል፡፡
የወዳደቁ የበቆሎ ቆረቆንዳዎች በጥሩ ሰው እግር እየተነዱ በያሉበት
ይንገዋለላሉ።
ሸክም እጇን የሚልስ ነገር ተሰማት። ጥጃ እንደሆነ አላጣችውም፡፡ ጥጃውን ለማየት ዞር ከማለቷ አሻግራ በር የሌላትን ትንሽ ክፍል ተመለከተች። የሚላወስ ነገር የታያት መሰላት፡፡ እንደ መደንገጥ አለችና ለመጮህ አስባ፣ ምን አልባት ሰው ይሆን?' ብላ ጠረጠረች።
እፊያቸው ላይ የሽሮ ወጥ ነጠብጣቦች የደረቁባቸው የሸክላ ድስቶች በምድጃው ስር ተሰልፈዋል፡፡ ከበላይዋ ያለ መተኛ
የነበረ ቆጥ ላይ የሰፈሩ ዶሮዎች ያስካካሉ፡፡ “ብለሽ ብለሽ ይህንን
የዶሮ ማስፈሪያ አድርገሽው ታርፊ?...”
አለች ሸክም አንድ ዐይኗን ዝቅ አንድ ዐይኗን ከፍ አድርጋ አፏን ጠመም አድርጋ
በማሽሟጠጥ፡፡
“ኤዲያ ባሌን ከደፋ ወዲያ ወደ ላይ ወጥቼም አላውቅ፡፡ይኸው ደሮወችስ እርም ሆኖባቸው መች ጤና አላቸው?”
“እሱስ ልክ ነሽ፡፡” አለችና ያንን የሚንቀሳቀስ የመሰላትን ነገር አፍጣ አየች። አውጥታ ባትናገረውም አንዳች
ነገር ከንክኗታል። ወደ ጥሩስው እየተመለከተች፡
“እና ታቆይኛለሽ?” አለቻት። .
ኧረግ አንቺው! ምኒት ውጋት ሆንሽብኝ፤ መጥለቂያ እስካጥብ አጣደፈሽሳ! ይሄን ነገር ላንቺ ብለሽ ሳይሆን አይቀርም
አጅሪት...”
“ኧዲያ! ይልቅ ጥራሩ ውስጥ ብጣሽ ካለሽማ መች እጠላለሁ ብለሽ እንዲያው አንዳይደቃኝ?”
“ይኸው እኔስ መች አጣሁት? ለራስሽ ብላሽ ነው ስትክለፈለፈ የመተሸ ይኸው አያ ባንቲ መች ድምጹ ይሰማል?”
ሸክም አፏን በኩታዋ አፈን ኣድርጋ በሳቅ ተንተከተከች፡፡
“ኧግ ያፍርስሽ እቴ! ምንኛ ነው እንዲህ የሚያስገለፍጥሽ?”
አለች ከጥራር ውስጥ ብጣሽ እንጀራ ቆርሳ እያቀበለቻት፡፡ያሳቃትን ነገር ሳትገልጽ፣ “ማዋዢያም የለሽ?” አለች ሸክም ደርቆ እግሩን የሰቀለውን እንጀራ በንቀት እያስተዋለች።
“እኔሳ እንዳንቺ አይነቷን አላስጠጣ፤ አላስበላ የምትል የተረገመች ሴት ከአጠገቤ ከማይ...” ወገቧን ይዛ ሰትውረገረግ እንጀራው ተደፋ። ሁለቱም የጀመሩትን ሳቅ አቁመው የተደፋውን
እንጀራ አዩት።
“በይ እሱንም እንጀራ አንስቼ እበላለሁ ብለሽ እንዳንጣላ!”
አለች። ጥሩሰው ልታነሳ እየተንደረደረች። ሸክም አንስታ ግማሹን
ስጨርቅ አድርጋ ወደ አፏ ሰደደች፡፡
“ኧረግ እንደው ያንቺስ ተፈጥሮ ምን አይነት ይሆን አያ!
ቆሻሻውን ትበይው? ደግሞ እኮ ቅድም ደርሰህ ተቀምጦበት በሽንት
በምናምን አትረክርኮት ነበር፡፡ አሁን በስሚዛ ጠራርጌ ነው የመተሽ፡፡
ኧረግ ያባቴ አምላክ..!” ደጋግማ ስትጎርስ በንቀት እያስተዋለች፣
አሁንም እየበላሽ ነው...? እንደው ትንሽም አይቀፍሽ?” አለችና በመጸየፍ አየቻት፡፡
“ይልቅ ማባያ ካለሽ ስጪኝ ኤዲያ!” አለችና አካባቢዋን ቃኘች፡፡ ጥሩሰው ድጋሚ ስለማባያ በመጠየቋ ዐይኗን እንደ
ማጉረጥረጥ አድርጋ ወደ ስራዋ ተመለሰች። ሸክም አካባቢዋን ስትቃኝ ትላንት ከገበያ መልስ የገዙትን እቃ ቅንባ ውስጥ እንደሞላ አስተዋለች፡፡
“አንደኛሽን ሰንፈሽ የለ፡፡ የገዛነውን እቃ እንኳን ቦታ ማስያዝ ያቅትሽ፡፡ አፍሽ እኔ ላይ ብቻ ነው የሚበረታ።” እጇን ወደ ቅምባው ከርስ ሰዳ በላስቲክ የተጠቀለለች ነገር አወጣች። ምን እንደሆነ ትዝ አላት።
ጥሩ ሰው ጀርባዋን ለሷ ሰጥታ ጠላ እየቀዳች ነው፡፡ ሸክም የተጠቀለለውን የበርበሬ ቋጠሮ ፈትታ የምትበላው እንጀራ ላይ በተን አደረገችው። ትላንት የገዙት አንድ ስኒ በርበሬ ነበር፡፡ እንደነበር
ቋጠረችና መልሳ ወደ ቅምባው ወርወር አደረገችው፡፡
ሽክም ጠላውን ቀድታ አቀብላት ዞር ልትል ስትል እንጀራ ላይ የተነሰነሰውን በርበሬ ተመለከተች፡፡
“አንቺ ያቺነ በርበሬ መኖሯን ብታውቂ ነስነሺያት? ኧረ ተይ አንቺ አውደልድል! ኧረ ተይ!”
“እንግዲያ ምን ላድርግ የረሳሽውን ላስታውስሽ ብዪ እንጂ...”
“ምን እረሳዋለሁ! ሳለሁን ሆዱን አሞብኝ ሀሳቤ ሁሉ ልጄጋ እንጂ የገዛሁትም ትዝ አላለኝ፡፡” አለችና እቃዎቹን ቦታ ቦታ
ማስያዝ ጀመረች፡፡
ሸክም እንጀራውን ጨርሳ ጠላውን መጠጣት ጀምራለች።
“አወይ እድሌ ጠላውን

👍5👎1
#ሸክም
፡
፡
#ክፍል_ሁለት (የመጨረሻ ክፍል)
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
ጥሩሰውም አሻግራ ሸክም ወደምታይበት ተመለከተችና ዐይኗን ሳታቆይ መለሰችው ሰው ያለበት ጨለማ ቦታ አሁን ባዶ መሰላትና ሸክም አፍጥጣ ወደ ጨለማው ተመለከተች።
“የጥሩሰው ባል ከሞተ በኋላ አንድ ሰው በድብቅ ወደ ጥሩሰው ቤት ሲገባ በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡” የሚል ወሬ ስለነበር “ምናልባት በድንገት በመድረሴ በድንጋጤ ተደብቆ ይሆናል፡፡ ስትል
አሰበች፡፡ ደግሞ በዚህ ሀሳቧ እንዳትረጋ ያደረጋት ነገር የጥሩሰው መረጋጋትና ጨዋነት ነበር፡፡ እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ጥሩሰውም እንዲህ ተረጋግታ አትጫወትም።
አሁን ዐይኗን አፍጣ ወደ ጨለማው በድፍረት ተመለከተች።
ጥሩሰው “ምነውሳ ወደዚያ አፈጠጥሽ?” አለች፡፡
“አይ እንደው ሰው ያየሁ መስሎኝ ነበር፤ ዞር ስል ደግሞ የለም፡፡” አለች በፍርሃት እየተመለከተቻት።
“ቅዠትሽን ሳትጨርሺ በጠዋቱ ተነስተሸ እዚሁ መቃዠት ጀመርሽ? ለመሆኑ ምን አይነት ሰው ነው ያየሽው? ጋኔል ይሆን?”
አሾፈችባት፡፡
“አይ እንግዲህ ወደ ጓዳ ጎራ ያለ ሰው ሊኖር ይችላል።” ብላ ፈገግ አለች፡፡
ጥሩሰው ሸክምን እንደመገላመጥ አድርጋ በገበቴ ላይ ያለውን እቃ ማጠብ ጀመረች፡፡ ወዲያው ሳቂታና ገራገር ፊቷ
ጨለማ አጠላበትና ዝም አለች፡፡
ሸክም ጥሩሰው ጥሩ ስሜት ውስጥ እንዳልሆነች ቢገባትም ምንም እንዳልተፈጠረ ጨዋታዋን ልትቀጥል ፈለገችና ምን ማውራት እንዳለባት ስታስብ፣ ጥሩሰው ቀና ብላ አፍጥጣባት
ቀረች፡፡
“ምነው?”
“እንዴት?”
“አፈጠጥሽሳ?”
“እንዲያው ገርመሽኝ ነውይ፡፡ እንደው ደርሰሽ ሰው አየሁ ስትይ...”
“ምን ላርግ እናት አለም? ያየሁትን ማለፍ አልወድ. አንቺስ አመሌን ታውቂው የለ?”
“ምን ታደርጊ አንቺማ ሲያወሩ የሰማሽውን ነው፡፡”
“ምኑን?” አለች ሸክም ደንገጥ ብላና መስማቷ ግምባሯ ላይ የሚታይ ይመስል አንገቷን ቀብራ፡፡
“እስቲ ይሁን፣ የወደቀ እንጨት ምሳር ይበዛበታል አሉ።ይሁን ግዴለም፡፡ እውነቱን ግዜ ያወጣዋል።” አለች በዐይኗ ሙሉ የሞላው እምባ እንዳይወርድ ወደ ላይ እያንጋጠጠች፡፡
“እና ለሰው ወሬ ብለሽ ልታለቅሺ ነው እናት አለሜ? ራስሽን የምታውቂው ራስሽ እንጂ ሌላ ሰው አይደለም፣” አለች የጠጣችበትን ዋርማ ቦታ እያስያዘች።
“ይሁና እንግዲህ ምን አድርጋለሁ? ያሉትን ይበሉ። የባሌ ሐዘን ከሆዴ ሳይወጣ አፋቸውን አልቻልኩትም፡፡ በነሱ ቤት ማጽናናታቸው ይሆን?” ጥሩሰው በረጅሙ ተነፈሰችና፣
“ይኸውልሽ ባለፈው ሰንበት ያቺ ምህዶ አፍ ያለችኝ ከሆዴም አይጠፋ። ያንን ሸውራራ ዐይኗን ይበልጥ አንሽዋራና
ድምጿን ጮክ አድርጋ እኔ እንድሰማላት ጓደኛዋን አሻግራ እያየች
ስሚ! ባልሽን ጠበቅ አድርገሽ ያዢ! ዛሬ ባልሽን ገድሎ አብሮሽ የሚተኛ ጎረቤትሽ ነው!' አለች። ሰምተሻታል አይደል?”
“በእርግጥ ሰምቻለሁ። ግን ገና ለገና አሽሙር ተናገረች ብለሽ መገመትሽ ጥሩ አይደለም።”
“እስቲ ይሁን ግዴለም” ብላ እንዳቀረቀረች ወደ ጓዳ ገብታ
አነስ ያለችውን የእንጨት መስኮት ከፍታ ዞር ስትል ባየችው ነገር
በድንጋጤ ደርቃ ቀረች፡፡
ፊት ለፊቷ እንደ ጅብራ ግርግዳውን ተደግፎ የቆመው ሰው አፉን እየተመተመ ዝም እንድትል ለመናት፡፡ ዝም ማለት
አልቻለችም፡፡
“ኧረግ ያባቴ አምላክ!” አለች፡፡
ሸክም የጠረጠረችው ሰው እውነት እንደሆነ አውቃ ወደ ጓዳ
ዘው ብላ ገባች፡፡
የቆመው ሰው ሸክምን በድንጋጤ እያየ፣ “አንቺ ቅንዳሻም! መተሽ የምታወሪውን ልሰማ ጥሩስው በረት እያለች ነው ቀድሜሽ መጥቸ የተሸሽኩኝ፡፡ እንዲያው የባለጌ ጓደኛ ያደረገሽ ምን ይሆን
አያ? ሞተሽ ባረፍሽ! አጅሪት አንቺንም ላንዱ ጎረቤት እንድትድርሽ ነው?” ዐይኑን እያጉረጠረጠ ሽመሉን እየወዘወዘ ወጣ፡፡
ጥሩሰው፣ “የተደፈርኩት ባሌ ሲሞት ነው ወይኔ!” አለችና ተስፋ ቆርጣና የሚብረከረክ ጉልበቷን በእጇ ይዛ ዐይኖቿን በመዳፏ እንደሸፈነች ከመደቧ ላይ ቁጭ አለች።
ሸክም ባለችበት ቆማ ተምዘግዝጎ እየዋጣ ያለውን ባሏን ግቢዉን ለቆ እስኪወጣ ተመለከተችና ጥሩሰውን ዞራ አየቻት። ጥሩሰው፣ ሸክም ወደ እርሷ እየተመለከተች እንደሆነ ገብቷት ፊቷን
ሸክም ከቆመችበት በተቃራኒው አቅጣጫ እያየች የሚወርደውን
እንባዋን ደጋግማ ትጠርጋለች፡፡
“አሁን ለምን እንደምታለቅሺ ብቻ ንገሪኝ?” አለቻት ሸክም፡፡
ለጠየቀቻት ጥያቄ መልስ ባለመስጠቷ ወደጥሩ ሰው ሄዳ በአንድ ጉልበቷ በርከክ አለችና፣
“ፊትሽ ምን እንደመሰለ ባየሽ? አታልቅሽ በቃ! ማንን ይመቸው ብለሽ ነው የምታለቅሽው? አንቺንም አውቅሻለሁ፣
ባሌንም አውቀዋለሁ።” አለቻት፡፡
ጥሩ ሰው ሸክም የምትለው አልገባ ብሏት ዐይን ዐይኗን በፍርሃት ስታያት፣ “ከዚህ በፊት ባሌ ሲያናግርሽና ደጋግመሽ
ስታመናጭቂው አይቻለሁ። ያንን ባላይ እንኳን ጨዋይቱን ጓደኛየን አምንሻለሁ... እመዬ አይክፋሽ... ተይው እናቴነሽ... ተይው አታልቅሽ ይሄ ድራሸ ቢስ ሁለተኝ ቀና ብሎም አያይሽ።እንኳንም እጄ ላይ ጣለልሽ”
ጥሩሰው ከሃዘኗ መኸከል አምልጦ የወጣውን ፈገግታዋን ለሸክም እየለገሰች እጇን ይዛ ከተንበረከከችበት እነድትነሳ
አደረገችና እንድትቀመጥ መደቡ ላይ ያለውን አጎዛ አራገፈችላት፡፡
💫አለቀ💫

👍1👎1
#ስጦታ
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
ልጆቿን በግራና በቀኝ ክንዶቿ ላይ አቅፋ እንደተኛች የሰከረውን ባሏን ከአንገቷ ቀና ብላ አየችው፡፡ ባሏ በከፈተው በር
ሰተት ብሎ የገባው፥ ነፋስ ፊቷን ሲገርፋት፣
“ኧረ ልጆቼን ብርድ እንዳታስመታቸው?” ብላ ውርጩን በእጁ ትከላከል ይመስል ክንዷን መከተች።
“ምናለበት ልጆች ናቸው። ልጅና ፊት አይበርደውም ሲባል አልሰማሽም ድንበሬ?” አለ እንደ ሰንበሌጥ እየተወዛወዘ፡፡
“እላያችን ላይ እንዳትወድቅ!”
“ይልቅ ድ..ድንበርዬ ህእ... እራቴን ህእ ብ.ብትሰጭኝ...”
አላት ስርቅታ የሚቆራርጠውን ትንፋሹን እየታገለ፡፡
“የምን እራት?”
“እራት ነዋ! ህእ.የሚበላ ትንሽ... ትንሽ ቂ…ቂጣም ቢጤ
ሊሆን ይችላል
“ይቀጥቅጥህ አንዳች! እሱንስ የምታገኘው ሲኖር አይደል።ወገኛ”
“ህእ...በናትሽ አት...አትቀልጂ?” ፈገግ ለማለት ሞክሮ አልተሳካለትም፡፡
“ምነው ያገሬ ጅብ በበላህና በተገላገልኩ” እሱን ፊት ለፊት ላለማየት ጥረት አደረገች፡፡
ደረቱን በእጁ እየደቃ፣ ጭንቅላቱን በየአቅጣጫው እያወዛወዘ፣
“ምነው የኔ ሸጋ አጋርሽን! መ..መከታሽን!” አላት፡፡
“እ..ጉድ እቴ! እንዲህም አድርጎ አጋር የለ! አጋር ሳትሆን ችጋር ነህ አንተ?”
“እኔ ችጋር?.…እኔ?” ዐይኑን እያጉረጠረጠ
ግድግዳውን ደቃው፡፡
“ስነ-ስርአት! ይህን ያጎነበስ ግርግዳ እንዳትጥልብን!”
“ወድቆ ህእ... ባረፈና በተገላገልኩ፡፡ እንኳን እሱ እኔም እኔም ወ..ወድቄያለሁ”
“እሱ ቢወድቅ አገልግሎ ነው። አንተ ምን ስርተሃል?”
“ኧከከከከ! እንዴት ንቀሽኛል ባክሽ?”
“ኤድያ! እርባና ቢስ!” ቀስ ብላ ክንዶቿን ከልጇቿ ስር አነሳችና እዚያው ቁጭ አለች፡፡
“ገደልከኝ በቁሜ ቀበርከኝ” አለች በንቀት እያስተዋለችዉ።
“አሁን ስለቀብር የሚ..የሚወራበት ጊዜ ነው?"
“ጉድጓድ ያስገባህ ያባቴ አምላክ! የተረገምክ!” ከተቀመጠችበት
ተፈናጥራ ስትነሳ የረገበው ሽቦ አልጋ ሁለቱን ልጆች ወደ መካከል
አደባልቆ አስተኛቸው፡፡
ብቻ እንዳትመችኝ?” አለና እጁን እያወናጨፈና እየተንገዳገደ፣ በቤቱ ውስጥ ወዳለችው ብቸኛ ወንበር አመራ።
“አሁን ቁጭ ማለት` አያስፈልግም ፤ ተነስና ተኛ!” አለችው
ወዳልጋው እያመለከተች።
“አልተኛም! አልተኛም! እስቲ ምን ምን ይዋጥሽ?”
“ተገትረህ እደር! ግን ከአሁን በኋላ
አንድ ልፍለፋ እንዳልሰማ!”
“እሰይ! ይኸው ነው የቀረሽ አንደኛሽን አትትለጉሚኝም? እ...”
ወንበሩ ላይ ሲቀመጥ መቀመጫው ወደታች ወርዶ እሱን ወንበሩ
ውስጥ ቀረቀረው።
የተንጨፈረሩ እጆቹንና እግሮቹን በመጸየፍ እያየች፣
“ወንበሬን ታነክተው? አንድ ስው ማሳረፊያ ቢኖረኝ! አይ እንደው ፈጣሪዬ በምኑ በተረገመው ቀን ነው ከአንተ ጋር
የተገናኘሁት? አይይ...ይ!” እያማረረች ተፈቶ የተንዘላዘለውን ሻሿን ማሰር ጀመረች፡፡
ገስጥ ከተወተፈበት ወንበር ውስጥ ለመውጣት ተፍጨርጭሮ፣
የወንበሩን ማያያዣ እንጨቶች የእንቁላል ቅርፊት ሰብራ እንደምትወጣ ጫጩት ሰባብሮ ወለሉ ላይ ተንደባለለ።
ድንበሬ ዕይኗ እያየ ወንበሯ ሲበተን በንዴት የምትይዘውንና የምትጨብጠውን አጣች።
ስሚ! የሚበላ ብያለሁ የሚበላ! በኋላ ነገር እንዳ...እንዳትፈልጊኝ!”
“አየህ አይደል የሠራኸውን ብልግና? መስከሩንስ የራስህ ጉዳይ
ነው፣ አቅተኸኛል። የዚህን ቤት እቃ በሰከርክ ቁጥር ማውደምህ
ነው የሚያንገበግበኝ! እሺ ምን ቀረህ ንገረኝ? ምን ቀረህ?”
“አንቺ! አንቺ ብቻ ነሽ የቀረሽኝ፡፡”
“ወቸ ጉድ! አንተን በዱላ ወቅቶ ወቅቶ መጣል ነበር!”
ሂጅና ያባትሽን ጤፍ ውቂ! አላ..ላበዛችውም?” በፍርሃት
ድምጹን ቀነስ አድርጎ ተናገራት፡፡
“አቤት ንቀትህ? አቤት! ንግግርህ እንኳ ለከት የለው...”
“እንዴት አይነቷ ሞኝ ነሽ ባክሽ? ህእ ...ሰክሬ ለከት እንዲኖረኝ ትፈልጊያለሽ?”
“ድጋሚ እንኳን እንዳይሰራ አድርገህ እኮ ነው የለያየኸው።
ነፍስና ስጋህን እንደዚህ ይለያየው!” የተበታተኑትን እንጨቶች እያነሳች ተመለከተችና አንዱን የወንበር እግር አንስታ “በዚህ ነበር ወገብህን ማለት!” አለችው።
ገስጥ በንዴት ያፈጠጠችውን ሚስቱን በልምምጥ ዐይን ዐይኗን እየተመለከተ “አንቺ .....አንቺ አታረጊውም አይባልም፡፡ ሰክሬ በመጣሁ ቁጥር ያንቺ ዱላ ነው ያማረረኝ ደግሞስ እራሽው
በሰጠሽኝ ብር ነው የሰ...የሰከርኩት” አላት።
“ጨምረህ ጠጥተህ እንጂ እኔ የሰጠሁህ ብር ይህን ያህል የሚያሰክር አልነበረም፡፡ ደግሞ ለኔ ማዘን የጀመርክ መስሎኝ እንጂ እንደተጫወትክብኝ መች ገባኘ ነበር!” አለች የያዘችውን የወንበር
ስባሪ በቁጭት እያያች።
“በይ አሁን እሱን አስቀምጭና...”
“ያስቀምጥህ ያባቴ አምላክ!”
“ሲያስቀምጠኝም ጥሩ መቀመጫ ፈልጎ ነው፡፡ እንዳንቺ ወንበር ሲቀመጡበት የሚንቃቃ ....።”
“ተቅማጥ ያስቀምጥህ ነው ያልኩት ደግሞ ላንተ መቀመጫ ልመኝ እርጉም የተረገምክ !”
“እርግማኑ እንኳን አይጎዳኝም።”
“ታዲያ ወንበሬን አንክተህ የምለቅህ መስሎኻል?”
“እንደው በፈጣሪ ይዤሻለሁ! እሱ ወንበር ያንቺ ብቻ ነው?
ይልቅ አሁን ልጆች ከ...ከሚረበሹ...”
“ድንቄም! ለልጆችህ ትቆርቁረህ?”
“የኔ ቆ...ቆንጆ!” አለና ትንሽ ፈገግታ ብልጭ አደረገላት።
“ምን? የኔ ቆንጆ!? የኔ ቆንጆ!” እያሽሟጠጠች አየችው።
“ምነው? የኔ ቆንጆ ማለት በኔ አልተጀመረ...”
ገርሟት ከልቧ ሆዷን ደግፋ ሳቀች፡፡
“የኔ ቆንጆ መባል እንዲህ የሚያፍነከንክሽ መሆኑን ባውቅ ኖሮ
ያለእረፍት የኔ ሸጋ፣ የኔ ጠንበለል፣ የኔ ዛጎል ዐይን እልሽ ነበር፡፡”
“ግን ማነው አሰልጥኖ የላከህ? አሁን በስተርጅና ይሄ የሽንገላ
ቃል ያስደስታታል ብለህ ነው? የሰደብከኝ እንጂ ያሞገስከኝ እንዳይመስልህ።” የግንባሯ ላይ ደምስሮች ተገታተሩ።
“ወይ ጉድ! ድሮስ ሲያሞግሱሽ መች ትወጃለሽ?”
“ያንተን ሙገሳ ከስድብ እንጂ...”
የምትናገረውን ሳትጨርስ
“ያንችን ጭቅጭቅ ለማምለጥ ውጭ ወጥቼ ንፋስ መቀበል ይሻለኛል።" ብሏት ተመልሶ ወጣ፡፡ ድንበሬ ያዛሬው መስከሩ
ምክንያት እስዋው እንደሆነች ስታስበው በራሷ ተናደደች፡፡
ትላንትና ምሽት ሳይሰክር ገብቶ አስደስቷት ነበር።እንደዛሬው አልሰከረም፡፡ ገና እንደገባ፣
ይህንን ልብስ ለኪው።” አላት፡፡
“ምን?” የተናገረውን ቃል ማመን አቅቷታል፡፡
“ለኪው!” የያዘውን ፌስታል አቀብሏት አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለ፡፡
“ከየት አመጣኸው?” አለች ፌስታሉን ከዐይኗ ስር ራቅ አድርጋ እያየችው።
“ከየትም ይምጣ! ብቻ ለኪው።”
ከዚህ በፊት ልብስ ገዝቶላት ስለማያውቅ እየገረማት የተቋጠረውን ላስቲክ ለመፍታት መታገል ጀመረች። የፌስታሉ
ቋጠሮ አልፈታ ሲላት ቀዳ አወጣችው። አንድ ሙሉ ቀሚስና ሹራብ ነበር፡፡ በጣም ገርሟት ገስጥን አየችው፤ በሙሉ ፈገግታ እያያት በኩራት ተኮፍሷል፡፡
“እስቲ ንገረኝ በባትህ ሞት? እውነት ለኔ ገዝተኸው ነው?”
“አንቺ ደግሞ ብር ባይኖረኝ እንጂ... ላንቺ ሳላስብልሽ ቀርቼ ነው?”
ልብሱን አገላብጣ አየችው።
ሹራቡንም ልበሽው” አላት።
ለበሰችውና እንባ ባቆረ ዐይኗ አጨንቁራ አየችው፡፡ የደስታ እንባ በዐይኗ መሙላቱን ሲመለከት እሱም በደስታ ፈካ፡፡
“ስንጋባ አንድ ልብስ ብቻ ነበር የጣልክልኝ አሁን በስንት
ዓመትህ ጸደክብኝ?” አለችው፡፡
“እስይ የኔ ቆንጆ! አሁን ደስታው ይቆየን እርቦኛል፡፡” ሲላት ከልጆቿ የተረፈ ነገር ጠራርጋ ሰጠችውና ለሊቱን ደስ ብሏቸው
አደሩ፡፡
በነጋታው ስራ ለመሄድ ሲወጣ ከደስታዋ የተነሳ እጇ ላይ ያለውን ብር አንስታ አንድ ሁለት ብርሌ ጠጅ ጠጣበት ብላ
ሰጠችውና በቀራት ብር ለልጆቿ የሚበሉት ነገር ለመግዛት አዲስ ልብሷን ከእግር እስከ

👍2❤1
#የድብልቅልቅ_ሰፈር_ሰዎች
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
ድብልቅልቅ ሰፈር ስያሜ የወጣላት በአያቴ ዘመን እንደሆነ አባቴ ነግሮኛል። እውነትም ድብልቅልቅ፡፡ ሁሉም እየተተራመሰ የሚኖርባት ሰፈር፡፡
ገና ከቤቴ ወጥቼ ግራና ቀኝ ተጠጋግተው በተሰሩ ቤቶች መካከል ሳቆራርጥ የቁመቴን መርዘም ሳልረግም አልወጣም፡፡ አጭር ብሆን ኖሮ የሰፈሩ ሁሉ ጣራ ገጭቶ ባልጨረሰኝ ነበር። ኮስመን ማለቴ ግን ከቤቶቹ መካከል ከመሽንቀር አድኖኛል።
ወደ ዋናው መንገድ ስዘልቅ መላወሻ መንገድ ቢኖርም የሚተራመስበት ህዝብ አይታጣም፡፡ ብዙ ጊዜ ከሰው
ጋር እጋጫለሁ፤ ምናልባት ጥቁር ስለሆንኩ ከሩቅ አልታይ ይሆን ብዬ
በመገመት ነጭ ልብስ እየለበስኩ መውጣት ከጀመርኩ ሰንበትበት
አልኩኝ፡፡
ዛሬም ማልጄ ወጥቻለሁ፡፡ ወንደላጤ ምን ሊያደርግ እቤቱ ያረፋፍዳል? የሳሩ ላይ ጤዛዎች ገና አልተነኑም፡፡ መንደሯ ለሃያ
አራት ሰዓት ትርምስ አይጠፋባትም፡፡ “እንደምን አደርክ አለማየሁ?”እያሉኝ የሚያልፉትን የሰፈሬን አዛውንቶች ከወትሮው በተለየ መልኩ በፍቅር ተመለከትኳቸው፡፡
በመወሰንና ባለመወሰን መካከል ስሟገት ስላደርኩ ነው መሰለኝ ከድካሜ የተነሳ ፊቴን እንኳን በወጉ የታጠብኩት
አልመሰለኝም።አቆራርጠን ስለምንሄድበት የስደት ጉዞ። ከጓዋደኞቼ ጋር ቀጠሮ ስለነበረኝና የኔን ውሳኔ በጉጉት ይጠብቁ ስለነበር ለመሄድ እንደ ወሰንኩኝ ስነግራቸው መቼም ደስታውን
አይችሉትም፡፡ የሰራሁበትን አጠራቅሜ እኔም ጓደኞቼ የደረሱበት ለመድረስ ስለ ወሰንኩ ማጨስ፣ መስከርና መቃም ካቆምኩ እረጅም ቀናቶች ተቆጠሩ። አዲስ ሰው የመሆን መንፈስ እየተሰማኝ ነው።ይህ የተፈጠረብኝ አዲስ ስሜት ደግሞ እራሴንም ሆነ አካባቢዬን
እንደ አዲስ ያሳየኝ መጀመሩ ገርሞኛል፡፡
ይህቺን ያደኩባትን የምንዱባኖች ሰፈር ትቼ መሄዱን ሳስበው ግን ሆዴን ባር ባር አለው። ለመጨረሻ ግዜ ግን ላጤናት
ትዝታዋን በአእምሮዬ ላስቀር በሰቀቀን ቃኘኋት፡፡
ሁሌም መንደሯ ላይ የማይጠፋው የአእምሮ በሽተኛው መሐሪ እየዛተብኝ አልፎኝ ሄደ። የውሃ ነጠብጣቦች አልፎ አልፎ ፊቴ ላይ እያረፉ ነው፡፡ ዝናብ በሌለበት ጊዜም በድብልቅልቅ ሰፈር
ሲታለፍ ውሃ ባናት ላይ ይንጠባጠባል። ዛሬም ወደ ላይ እያንጋጠጥኩና የፈሰሰብኝን እያባባሰኩ በመራመድ ላይ ነኝ፡፡
የሰፈሩ ሥልክ እንጨቶችና የመብራት ቋሚ እንጨቶች በድብልቅልቅ ሰፈር ድርብ ስራ አላቸው። ከግራና ከቀኝ ገመድ
ተወጥሮባቸው የሰፈሩን የታጠበ ልብስ በማድረቅ ያገለግላሉ፡፡የአንዱ ሲደርቅ የሌላው ስለሚተካ ዉሃው የሚንዠረዠር ጨርቅ አይጠፋም፤ የገመዶቹ ስራ ለደቂቃ ተቋርጦ አያውቅም፡፡
ሁለት ሴቶች ፊት ለፊቴ ካለው ገመድ አጠገብ ቆመው ጭቅጭቅ ጀምረዋል፡፡ አንደኛዋ አጭርና ወፍራም ሴት አብራት
ያለችውን ሴት ከገመዱ ላይ ያወረደችባትን ልብስ ከእጇ ላይ
መነጨቀችና ወደ ላይ ዘላ ልብሱን ገመዱ ላይ ወረወረችው፡፡ እላይዋ ላይ የተከማቸው ስጋ እላይዋ ላይ ተንደፋደፈ፡፡
“እኔ እኮ ደርቆልሻል ብዬ እንጂ...” ብላ እንዳቀረቀረች ተመለሰች፡፡
“ከየት የመጣሽ ወስፌ ነሽ ባክሽ? እርጥቡን እንዳስገባልሽ ፈለግሽ? በለሊት ወፍ ሳይንጫጫ ተነስቼ ማጠቤ እኮ ሰው
እንዳይቀድመኝና ልብሴ ቶሎ እንዲደርቅ ነው።” አለችና የተሰጡ ልብሶቿን እያገላበጠች ማስጣት ጀመረች፡፡
አዲሷ ልብስ አስጪ ሴትዮ እንግዳ መሆኗ በጀ እንጂ የዚሁ ሰፈር ሰው ብትሆን ኖሮ ቡጭሪያውና ጡጫው ይከተል ነበር፡፡
ሁልጊዜ በድብልቅልቅ ሰፈር ጩኸት አይታጣም፡፡ “ስጤ ላይ ውሃ ደፋሽ”፣ “ዶሮዬን መታሽብኝ”፣ “ደጃፌ ላይ አሰጣሽ”፣ “ድመትሽን ያዢልኝ...” የመሳሰሉት ነገሮች የዘወትር ጠብ
ማጫሪያዎች ናቸው፡፡ ይህን መንደር ለቅቄ መሄዴ ለምን እንዳስጨነቀኝ እራሴን ጠየኩት። ጥያቄዬን ለራሴ ሳልመልስ አንዲት ጸጉሯ የተንጨፈረረ ሴት በእጇ ምናምን ይዛ ወጥታ የያዘችውን
እንኳን በውል አይቼ ሳልጨርስ ፍሳሹን በላዬ ላይ ከለበሰችው፡፡መጸዳጃ ቤት መደፋት የነበረበት መሆኑን ያወኩት አፌን ጨው ጨው ሲለኝና አፍንጫዬን መጥፎ ሽታ ሲሰነፍጠው ነበር፡፡
“ድንባዣም!... ትደፊብኛለሽ?” ጮህኩ፡፡
ታዲያ አንተ እንደ ጅብራ ፊቴ ላይ ማን ተገተር አለህ!”
ሴትየዋ የተመለመለና የከሰለ እንጨት የመስሉ እግሮቿን እያማታች ወደ ቤቷ ገብታ የጣውላውን በር በኃይል ስትወረውረው ከበሩ መቃን ላይ የቀረው የጭቃ ልስን ረገፈ። “ባሏን ጎዳሁ ብላ..
የሚለው አባባል ትዝ እንደማለት አለኝና ቆሻሻዬን ከፊቴ ላይ እየጠራረኩኝ ለራሴ ያቀረብኩትን ጥያቄ መልስ ለማድመጥ
ተዘጋጀሁ፡፡
እነዚያን ጎስቋላ ቤተሰቦቼን አሰብኩኝ፡፡ የማይፋቅ ትዝታ ጥለውብኝ አልፈዋል። በሕይወት በነበሩ ሰዓት ስወጣ ስገባ “እባክህ ሰው ሁንልን?” የሚለው ንትርካቸው አስጨንቆኝ እየጣልኳቸው ውጭ አድር ነበር፡፡ እነሱን ሳጣ ግን
እክሳቸው ይመስል ከድብልቅልቅ መራቅ አቃተኝ፡፡ ይሄ የራሴ ለራሴ መልስ አሳማኝ ነበር፡፡
ሁልግዜም ጥንብዝ ብዬ ሰክሬ ወደቤቴ ስገባ እናቴ ቁጭ ብላ ትጠብቀኝ ወደ ነበረበት ቦታ አስተውላለሁ። “እናቴ
መጣሁልሽ!" ብዬ ስጮህ የምትቀመጥበት ድንጋይ አፍጦ ያየኛል።
ያን ቦታ ማየት ለኔ ሰቀቀን ነው። አሁን መስከሬን ሳቆም ግን የሙት መንፈሷ በፈገግታ የሚመለከተኝ ይመስለኝና ደስ ይለኛል።
አለፍ እንዳልኩ ሰክሬ የማጫውተው ልጅ መሰለኝ “አሌክስ” ብሎ ጠርቶኝ ተደበቀ፤ እሱን በዐይኔ ስፈልግ ቆፈን የያዛቸው
ህጻናት እጃቸውን እያሻሹ፣ እኔ አይደለሁም በሚል አስተያየት በፍርሀት እያዩኝ ቆመዋል። ከዚያው ዝቅ ብለው ደግሞ መስል ጓደኞቻቸው የወዳደቀ ነገር ይለቃቅማሉ።
እስቲ አሁን በለሊት ምን አስወጣቸው? አርፈው አይተኙም፤ ስራ እንዳለበት ሰው በጠዋት ተነስተው ከሚዳክሩ?
ተበሳጨሁ። ግን ምን ያድርጉ በድብልቅልቅ ሰፈር ምናልባት
መኝታቸውስ በተራ ቢሆን? ምስኪኖቹ አሳዘኑኝ፡፡
እነሱንአተኩሬ ሳይ አንድ ማዳበርያ ሙሉ ምናምን የተሸከመ ሰው ማዳበሪውን ጠርጎብኝ አለፈ። “ይበለኝ!” አልኩ።
እያየሁ መሄድ አለብኝ፤ የድብልቅልቅ ዕፈር ሰዎች “እባክህን፣ ይቅርታ”፣ “አሳልፈኝ” ለሚባሉ ቃላት ባእዳን ናቸው፡፡ ያገኙትን ሁሉ እየጨፈላለቁ ከመሄድ የሚከለክላቸው አንድም ነገር የለም፡፡
ሁልጊዜም በዚህ መንገድ ሳልፍ በልጅነቴ ሰኞ ማክሰኞ የተጫወትኩት ትዝ ይለኛል። ብዙ የሚዘለሉና የሚጨፈላለቁ
ነገሮች አሉ። እናም ጡብ፣ ጡብ እያልኩ እርምጃየን ቀጥያለሁ።
አንዲት አህያ ከመጠን በላይ በተጫነችው ሽክም እየተንገዳገደች ድንገት ፊቴ ድቅን በማለቷ በሌላ መንገድ ለመሻገር
አንድ ጥቁር ድንጋይ ላይ እንደመዝለል ስል ድንጋዩ አንሸራቶ ወደ ሰማይ ልኮ ለምድር አቀበለኝ፡፡ የጎድኔ አጥንቶችና የግራ እጄ ክንድ የደቀቁ መሰለኝ፡፡ ህመሜን ውጩና ትንፋሼን ተቆጣጥሬ ራሴን ገዛሁ፡፡ ወዲያው በአንድ ጎኔ ብድግ ብዬ እንደመነሳት ስል አገልግሎት የሰጡ ብዙ ኮንደሞች ከስሬ ተጎዝጉዘዋል። በእግሬ ስር ያለው ኮንደም ድንጋይ ላይ ተጣብቆ እንዳንሽራተተኝ ልብ አልኩ።
በአካባቢው አንድም በግቢ የታጠረ ቤት የለም፡፡ በራቸው ድንገት ከተከፈተ ገመናቸው ውጪ ይሰጣል። እልፍ ስል የመንጋ ጩኸት የመሰለ ነገር እየቀረበኝ መጣና ምልከታዬን ጩኸቱ ወዳለበት አዞርኩኝ፡፡
ቁጥራቸው ወደ ሃያ የሚጠጋ ውሾች እየተነካከሱ መንደሯን ድብልቅልቋን አወጧት፡፡ ድንገት ግር ብለው ወደኔ ሲመጡ ከውሾቹ ስሸሽ ተደነቃቅፌ ከመውደቅ ለመዳን ባደረግኩት መፍጨርጨር አንድ በር ላይ እጆቼ አረፉ፡፡
💫ነገ እንቀጥለው💫
አስተያየት አይረሳ @atronosebot ን ይጠቀሙ

👍2😁1
#የድብልቅልቅ_ሰፈር_ሰዎች
፡
፡
#ክፍል_ሁለት(የመጨረሻ ክፍል)
፡
፡
#በእየሩስአሌም_ነጋ
ቁጥራቸው ወደ ሃያ የሚጠጋ ውሾች እየተነካከሱ መንደሯን ድብልቅልቋን አወጧት፡፡ ድንገት ግር ብለው ወደኔ ሲመጡ ከውሾቹ ስሸሽ ተደነቃቅፌ ከመውደቅ ለመዳን ባደረግኩት መፍጨርጨር አንድ በር ላይ እጆቼ አረፉ፡፡
በሩ ያለምንም ማንገራገር ተበርግዶ እኔን ይዞኝ እንደዘሉ የተነባበሩ ሰዎች ከተኙበት አልጋ ላይ ተዘረጋሁ፡፡ወደያው በድንጋጤ ለመነሳት ባደረኩት ጥረት የሰውየውን ወገብ በኃይል ስጫን ሴትየዋ ሁለት ጊዜ አቃስተች፡፡ ፊቱ ላይ ስጋ ያልተፈጠረበት
የሚመስል መጣጣ ጠይም ስውዬ በፍጥነት ከወገቡ ቀና አለ የሴትየዋን ደረት እየተጫነ፣
“እያለሁ? እስክወጣ እንኳ አላስችል አለህ?” የግንባሩ ላብ ተንጠባጠበ፡፡
“ደግሞ ያፈጣል እንዴ? ማን ጠራህና ነው የሰው በር በርግደህ የገባኸው?” በማለዳ ወፍራም ድምጿ አጉረመረመች።
በገባው ጥቂት ብርሃን ፍንጣቂ ጥርሷ ብቻ ሲብለጨለጭ ታየኝ፡፡
“አንቺ የቀጠርሺውን ምን ያድርግ? አስተዳዳሪ እስኪወጣ እንኳ አላስችል ብሎት...” ሌላ ነገር እንዲያስደምጡኝ እድል አልሰጠኋቸውም፤ ተመልሼ በመጣሁበት በር ወጣሁ።
ራመድ እንዳልኩ መለስ ብዬ የገባሁበትን ቤት ተመለከትኩ። በሩን ባለመዝጋቴ ምስጢራቸው ባደባባይ ተጋልጧል። በፍጥነት ተመልሼ ልዘጋ ስል ሴትየዋ ልትነሳ ትድበሰበሳለች፡፡ በድንጋጤ
እየተርበተበትኩ አልፌ ሄድኩ፡፡
ዐይኔን ወደጎን ሳዞር ሁለት ሰዎች በላስቲክ በተሰራ ዳስ ውስጥ ሻይ ይዘው ሲጠጡ አየሁ። ወደ ስደት ለመሄድ ካስብኩ ጀምሮ የምግብ ፍላጎቴ ሁሉ ተዘግቶ መብላት፣ የምጠላው አስተማሪ
የሚሰጠኝ ከባድ የቤት ስራ መስሎ ይታየኝ ከጀመረ ሰንብቷል።
ሕይወትን ለማራዘም ምግብ ግድ ስለሆነ ይህንን አስጨናቂ የቤት ስራ እሰራ ዘንድ ጎራ አልኩኝ፡፡
ሙሉ በሙሉ ተቀይሬ ሌላ ሰው እንደሆንኩ ተረዳሁ፡፡ምክንያቱም
በፊት የማሳያቸውን ቆሻሻ ነገሮች ዛሬ ማጤን ጀምሬያለሁ፡፡ በቤቱ ውስጥ የማያቸው ሁሉ ቆሻሻ መስለው ታዩኝ፡፡
በተስፋ መቁረጥ የተነሳ አለም በቃኝ ብዬ ክፉና ደጉን ማየት ተስኖኝ ነበር፡፡ የቀረበልኝን የሻይ ብርጭቆ ገና ወዳፌ ከማድረሴ ክርፋት ክርፋት ሸተተኝ፡፡ እንደማሽተት አድርጌ መልሼ አስቀመጥኩት፡፡
አስተናጋጇ ሌሊት የለበሰችውን ወፈር ያለ አብለጭላጭ ፒጃማ አልቀየረችም፡፡ የተበላባቸውን እቃዎች አነሳስታና ጀርባዋን ለኔ ስጥታ ጠረጴዛውን ትወለውላለች፡፡
ፒጃማዋ ላይ የፈሰሱ ቆሻሻዎች የፈጠሯቸውን ውስብስብ ካርታዎች አየሁ፡፡ የፈሰሰባት ነገር እጣ ፈንታችንን በጭላጭ ስኒ የሚተነብዩትን ጎረቤቴን አስታወሰኝ፡፡ “የኔም እጣ ፈንታ ከመቀመጫዋ ላይ ይነበብ ይሆን? ወይስ የምሄድበት መንገድ ካርታ ተስሎበት ይሆን?” አልኩና ብቻዬን ፈገግ አልኩ፡ ስትንቀሳቀስ መቀመጫዋ ዳንኪራ ይረግጣል።
ዐይኔን መግታት እንዳለብኝ ተሰምቶኛል። ዐይኔን ብቻ ሳይሆን ዐይነ ህሊናዬን ጭምር ማቀብ እንዳለብኝ ወስኛለሁ፡፡
የሩጫ ጊዜ፣ የዝላይ ጊዜ፣ የመቆሽሽ ጊዜ ማክተም አለበት፡፡
የበረደውን ሻይ አንስቼ ወደ አፌ ላንዶለዱለው ስል... ከኋላ ኪሴ ያስቀመጥኩት ሞባይል ንዝረት በመላ አካላቴ ፈሰሰ፡፡ አውጥቼ አየሁት፡፡ ለጉዞ መሰናዶ የሚሆነንን ነገር እንድንነጋገር
የቀጠርኳቸው ጓደኞቼ ነበሩ፡፡ “ዶሮ ማታ” እንደሚባል ልጅ እንደ ኮሶ እያንገሸገሸኝ የቀረበልኝን ሻይ ጠጥቼና ሂሳቤን ከፍዬ በፍጥነት ተነሳሁ።
ጥቂት ከተራመድኩ በኋላ አንድ ጋዜጠኛ የተለያዩ ሰዎችን እያፈራረቀ ሲጠይቅ አየሁ። ሰዎቹ የድብልቅልቅ ሰፈር ሰዎች
ናቸው፡፡
አንዱን ሰውዬ ጠጋ ብዬ ጠየኩት፡፡ የድብልቅልቅ ሰፈር ፈርሳ በአዲስ መልክ ልትገነባ እንደሆነና ሰዎቹ የተሰማቸውን ሀሳብ እየተናገሩ እንደሆነ አስረዳኝ፡፡ አብረን ልንለወጥ ቀጠሮ የነበረን
አንመስልም? አልኩና ማየቴንና ማዳመጤን ቀጠልኩ፡፡
ድብልቅልቅ ሰፈር ከፊል አካሏ እንደ ባቢሎን ፈራርሷል። ድህነትና ማይምነትም አብረው ሲፈራርሱ ታየኝና ፈገግ አልኩ፡፡ የድብልቅልቁ አሸባሪ እብዱ መሐሪ የጋዜጠኛውን መቅረጸ ድምጽ
ቀምቶ ዐይኑን እያጉረጠረጠ ጋዜጠኛውን ካስፈራራ በኋላ፣
ስማ እኔና አንተ ሳንለወጥ ሀገር ይለወጣል ብለህ አታስብ፡፡እስቲ እኔን እየኝ ፈርሼ በስብሼ እንደገና የምነሳ አይመስልህም?”ጋዜጠኛው ደንግጦ በፍርሃት ያየዋል።
“ይመስለሀል አይመስልህም? እኔ ደግሞ እራሴን ልክ እንደ ድብልቅልቅ ሰፈር ሳላፈራረስ ብቀር...ግን ቆሻሻ የፈጠሩ
ሰዎች ሳይፈራርሱ እንዴት ድብልቅልቅ ሰፈር ትነጻለች?
ድብልቅልቅን የፈጠሯት እኮ እነሱ እንጂ እርሷ ራሷ አይደለችም፡፡”
አንገቱን ወደ ሰማይ አቅንቶ ሳቀ፤ ወዲያው ደግሞ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ሳቁን ገታና ቀጠለ፡፡ ጋዜጠኛው መቅረጸ
ድምጹን ለመቀበል ሲሞክር ዐይኑን ሲያጉረጠርጥበት እንደ መፍራት ብሎ እጁን መለሰ።
ካንተ ይልቅ እኔ እውነት እናገራለሁ። ስለዚህ ድምጽ መቅረጫው ምን ያደርግልኸል?…እ?” ጋዜጠኛው ግራ በመጋባት ወደኃላው እንደ ማፈግፈግ ብሎ ተመልሶ ቆመ።
“ስማ ለመሆኑ ከራስህ ጋር ተጣልተህ እስከመቼ ነው?እስከመቼ? እንደኔ እውነት ለመዘገብ ማበድ አለብህ?...አለብህ
የለብህም? ንገረኝ! ምንድነህ አንተ አህያ ነህ? የጫኑህን የምትጫን፣በል ያሉህን የምትል። ጠይቅ ያሉህን የምትጠይቅ አንተ ለምን አትተወውም? ለምን አታብድም? እ..የዚያች ልጅ! አሁን በናንተ
ቤት አዲስ መንደር ልትሰሩ ነው አይደል? ዳግመኛዋ ድብልቅልቅ ሰፈር አትሏትም? ትሏታላችሁ አትሏትም?” ወዲያውኑ ጥቀርሻ በመሰለው የላስቲክ ቤቱ አጠገብ አንድ ሰው ቆሞ አየ።
“ቤቴን! ቤቴን!” ካለ በኋላ በድጋሚ ወደ ጋዜጠኛው ዞሮ
“ሆዳም! ለሆድህ ያደርክ! ህሊናህን የሸጥክ! እኔ እኮ እንዳንተ
ዋሽቶ መብላት አላቃተኝም! ግን ወገኔን አልበላም። ደሞ ሀቀኛ
ጋዜጠኞችን አታሰድብ እ...? አየህ? ቤቴን ሲያፈርሱት! አየህ?
አሁን ለኔ ኮንደሚኒየም ቤት ሊሰጡኝ? ነው? ይመስልሀል አይመስልህም? የዚያች ልጅ!” እንደገና ፊቱን ወደ ቤቱ መለሰ፡፡
“ቤቴን! ቤቴን! ከሙስና በጸዳ በንጹህ ገንዘቤ፣ በላቤ የሰራሁትን ቤቴን! አንድ ሰው እንዳያፈርስብኝ ቤቴን!” ድምጹን ከፍ
አድርጎ ጮኹ፡፡ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ቀረብ ብሎና ወደ ጋዜጠኛው ተጠግቶ፣ “ውሸት የጠጣች የድምጽ መቅረጫ ምን
ታድርግልኛለች? አየሃት እንዴት እንደከሳች... አየሃት እንዴት
እንደተጎሳቆለች?... አየህ! ውሸት በሽታ ነው፡፡ ሀገርህንም እንዲህ
ነው የምታከሳት! ገባህ? የዚያች ልጅ! ምን ይገባሀል አንደኛህን
ደንቁረህ! ብኩርናህን በጭብጥ ሽንብራ የሸጥክ!" መቅረጸ ድምጹን ጋዜጠኛው አፍንጫ ላይ ወርውሮ ሮጠ፡፡
ህንጻ ወደ ሆነው ወደ ራሴ ሰውነት አስተዋልኩ።በእርግጥም ድብልቅልቅ ሰፈርን የፈጠሩ ሰዎች እንደገና መፈጠር
አለባቸው።ለእውቀት ለእውነታ ለትጋት።ለውጡ ከራስ ይጀምራል፡፡
ያ የቆሸሸውና ሊፈራርስ የነበረው እኔነቴ ሊሰሩ እንደታሰቡት ህንጻዎች ሲደምቅ ታየኝ፡፡ እነዚያን የከብት መንጋ ይመስል
በየመንገዱ የሚርመሰመሱ ውሾች፣ ምርጊታቸው የፈራረስ ቤቶች፣ በሰው ላይ የሚደፉ ፍሳሾች፣ የሚጨፈላለቁ ነገሮች፣ የሚኮረኩመ ጣራያዎች፣
የሚገጩና የሚያጋጩ ሸክሞች፣
ቆሻሻዎችና ኮንደሞች... ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ በዐይነ ህሊናዬ
ተሰናበትኳቸው፡፡
በረጅሙ እግረ መንገዴ ውስጥ ከራሴ ጋር ያደረኩት ሙግት ቀላል አልነበርም፡፡ ወስኛለሁ ብዬ ከቤት መውጣቴና ለጓደኞቼ ልናገር ማሰቤ ልክ እንዳልነበረ ታወቀኝ፡፡ በተለይ የድብልቅልቅ
ሰፈር ፈርሶ እንደገና መሰራት የመሄዴን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንድለውጥ አድርጎኛል።በሃሳቤ

❤1