የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.36K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#መካነ_ኢየሱስ_ተፈራረመች
በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና በማስተር ቢውልደር ሴንተር መካከል የአጋርነት ፊርማ ተከናወነው።
የፊርማ ስነ ስረዓቱን በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በኩል የቤተክርሲትያኒቱ ፕሬዝደንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በማስተር ቢውልደር ሴነተር በኩል ደግሞ ቄስ ዶ/ር ጥላሁን መኮንን የአጋርነት ፊርማውን አኑረዋል።
ከማስተር ቢውልደር ሴነተር ጋር ቤተክርስቲያኒቱ ስትሰራ የመጀመሪያ እንዳልሆነ እና ብዙ ትብብር እና በሴንተሩ በኩልም ድጋፍ ሲደረግ እንደነበረ በፈርማው ስነ ስረዓት ወቅት የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ፕሬዝደንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ የገለጹ ሲሆን ይህ ነገር በአሁኑ ሰዓት ወደ ፊርማ እንዲሸጋገር አድርጎታል በልዋል።
በትንሹ የሚጀመር ነገር ነገ ላይ ለብዙዎች በረከት እና ለእግዚያብሄር ቤት አገልግሎት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
መቀመጫውን ሰሜን አሜሪካ ያደረገው እና ሰዎችን በኢኮኖሚካሊ፤ ማህበራዊ እና በተለያዩ ዘርፎ በተለይም በትምህርት እራሳቸውን ማሳደግ የሚፈልጉ አገልጋዮችን መደገፍ አላማው መደገፍ ማስተርስ ቢውልደር ሴነተር የተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚሰራ ተቋም ሲሆን በሀገራችን በስምምነት ደረጀ የኢትዮጵይኣ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ነች።
ተቋሙ 5 ራዕዮችን ይዞ የሚስራ እንደሆነም በፊርማው ስነ ስረዓት ላይ ቄስ ዶ/ር ጥላሁን መኮንን ተናግረዋል።
©The Christian News
#የኢትዮጵያ_ወንጌላዊት_ቤክ#መካነ_ኢየሱስ_የወንጌል_ተልዕኮና_ቲዮሎጂ_የስራ_ክፍል_የዳይሬክተሮች_የምክክር_ስብሰባ_በጉዲና_ቱምሳ_ሁለንተናዊ_የስልጠና_ማዕከል_ ተጀመረ።
በምክክር ስብሰባው የነባርና አዳዲስ ሲኖዶሶች የወ/ተ/ቲ የስራ ክፍል ሀላፊዎች በስራ ክፍሉ ተግባራት፣ አዳዲስ ጅማሮዎች፣ ስጋቶች እና ቀጣይ የስራ ክፍሉና የቤተክርስቲያኒቱ የወንጌል እንቅስቃሴዎች ላይ ይመክራል።
የስራ ሂደቱ ዳይሬክተር በዋና ቢሮ ቄስ ዶ/ር ሌሊሳ ዳንኤል እንደገለጹት፤ የምክክር መድረኩ በይዘቱ እስራቴጂያዊ (ስልታዊ) ሆኖ ለቤተክርስቲያኒቱ የስራ አስፈፃሚ ቦርድና ቀጥሎም ለዋናው ጉባዬ ለውሳኔ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ ይመከራል ብለዋል።
የቤተክርስቲያኒቱ የሴቶች እና የአስተዳደርና ፋይናንስ የዳይሬክተሮች በመክፈቻው ላይ ተገኝተዋል።
መረጃዉን ከቤ/ክ ማህበራዊ ትስስር ገፅ አገኘነዉ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/Evangelical MEDIA/Council
ዩትዩብ፦https://youtu.be/xRyLBBhqhUM
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#የአማራ_ክልል_ፋይናንስ_ቢሮ የኢትዮዽያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ_የልማት አገልግሎት ኮሚሽን_በልማትና_ማህበራዊ አገልግሎት ረገድ ከፍተኛ አንቅስቃሴ በማሳየትና በድንገተኛ ክስተቶች ወቅት ኮሚሽኑ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ላደረጋቸው የነብስ አድን ድጋፍና ስራዎች ብሎም ላመጣቸው ተጨባጭ ለውጦች #የእዉቅና_ሰርተፍኬት_ አበርክተዋል።መረጃዉን ከቤተክርስቲያኒቱ ማህበራዊ ትስስር ገፅ አገኘነዉ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፦ https://youtu.be/DAn9qGy1zZE
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#አስደሳች_ዜና
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ_የልማትና_ማህበራዊ_አገልግሎት ኮሚሽን በ(CCRDA) Christian Relief and Development Association በተደረገው የ2023 #የመልካም_ልምምድ ውድድር ላይ አሸናፊ ከሆኑ ድርጅቶች አንዱ በመሆን #ተሸለመ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/tXCAFcelpIg
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ #መካነ_ኢየሱስ የልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን #የአእምሮ_እድገት_ውስንነት_ያለባቸው_ልጆች_ማሰልጠኛ_ተቋም ለ2015 ዓ.ም ተመራቂዎች የሰርተፍኬትና #የምረቃት_ፕሮግራም_አካሂዷል
የምርቃት ስነ ስርዓቱ አርብ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች እንዲሁም የኮሚሽኑ አስተዳደሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡
መረጃው፤ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ የልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን ነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/cN28MNp_FVQ
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1
የኢትዮጲያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ_የስራ_አስፈፃሚ_ቦርድ_59ኛ መደበኛ ስብስባውን በጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና አካሄደ
* * * * ሐሙስ ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም ማለዳ በጌታ እራት አገልግሎት የተጀመረው የቦርዱ ስብሰባ ቀጥሎ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙን የመክፈቻ ንግግር አድምጧል። በእለቱም በቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ፀሐፊ ቄስ ተሾመ አመኑ የመወያያ አጀንዳዎች የቀረቡ ሲሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚደንት ንግግር እና በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ በዝርዝር ውይይቶች ተደርጓል።
የቦርዱ ውይይት በቀጣይ ቀን የቀጠለ ሲሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በሀገሪቱ ወቅታዊና ነባራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል። ተያይዞም ውሳኔዎችን አሳልፏል። 59ኛው የቦርዱ ስብሰባ ለያዝነው አመት የመጨረሻ ስብሰባ ሲሆን ቦርዱ አዲስ ለተመረጡና ቦርዱን ለተቀላቀሉ የአዳዲስ እና ነባር ሲኖዶስ ፕሬዚዳንቶች አቀባበል አድርጓል። ዜናውን ከቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ ድረገጽ አገኘነው።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/FzwAN1ZUrNI
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
1👍1
የኢትዮዽያ ወንጌላዊት ቤ/ክ #መካነ_ኢየሱስ ልማት ኮሚሽን #በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት #ለተፈናቀሉ_ወገኖች_የአልሚ_ምግቦች_ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ፤ ከbread for the World ጋር በጋራ በመሆን ነው አልሚ ምግቦችን በደርጅ አገን ቀበሌ እና እንደርታ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ያከፋፈለው፡፡
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍41
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ የልማት እና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን ከአጋሩ #ኪንደርኖትሂልፍ መንግስታዊ ያልሆነ የልማት ተቋም ጋር በጋራ በመሆን በተለያዩ የኢትዮጲያ አከባቢዎች #የተሰሩ_የልማት_ስራዎችን_የሚዘክር_50ኛ_አመት በዓል አከበረ።
አጋር ተቋሙ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በልጆች እና ወጣቶች ላይ የሚሰራ ሲሆን ባለፉት 50 አመታት ከቤተክርስቲያኒቱ ልማአ ኮምሽን ጋር በጋራ በመሆን ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ልጆችና ወጣቶች ሙሉ አቅማቸው ተጠቅመው ውጤታማና ምርታማ ዜጎች መሆን ይችሉ ዘንድ ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የትምህርት እድሎችን እና የሙያ ስልጠናዎችን ሲሰጥት ቆይቷል።
በዓሉም በጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል በተለያዩ ዝግጅቶች እና በኤግዚቢሽን አክብሯል። በመክፈቻ መርሀግብሩም ላይ የቤተክርስቲያኒቱና የልማት ተቋማቱ አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/sRiasuRa9cM
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🙏31
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ_አዲስ_አበባ_ሲኖዶስ_2ኛ_መደበኛ_ጉባኤውን ህዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም በእንጦጦ ማህበረ ምዕመናን አካሂዷል።
ጉባዮውም የቤተክርስቲያኒቱ ዓመራሮች፣ የተቀባይ ማህበረ ምዕመኗ እና የሲኖዶሷ አጋር ተቋማት ባቀረቡት ሰላም የጀመረ ሲሆን የሲኖዶሱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ኪሮስ ቀጥለው መራሄ ንግግር አድርገዋል። ባደረጉትም ሰፊ ንግግር ሲኖዶሷ ከተመሰረተችበት ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ዘጠኝ አመታት በመዲናዋ ውስጥ ሲኖዶሱ ስላከናወናቸው የወንጌል፣ የልማት እና የማህበራዊ አገልግሎቶች ያብራሩ ሲሆን ጨምረው ሲኖዶሱ እና በስሩ ያሉ ማህበራነ ምዕመናን ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች በዝርዝር አስቀምጠዋል።
አያያይዘውም ከተማዋ አህጉር ዓቀፍና ዓለም ዓቀፍ የዲፕሎማቲክ ግንኙነቶች እና ትላልቅ ተቋማት መቀመጫ ከመሆኗል የተነሳ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ቋንቋዎች ሊኖር ስለሚገባው ልዩ ወንጌል የማዳረስ አቀራረብ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል። መራኔ ንግግሩንም ተከትሎ ሲኖዶሱ የከተማዋን የስነ ሕዝብ አወቃቀር ባማከለ መልኩ ወንጌልን የማዳረስ ስራዎችን መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክሯል።
በማጠቃለያውም ጉባዬው ላለፉት ሁለት የአገልግሎት ዘመናት ሲኖዶሱን ሲመሩ የነበሩ አመራሮችን በታላቅ ምስጋና በማሰናበት ለቀጣይ አራት ዓመታት ሲኖዶሱን የሚመሩ መሪዎችን መርጧል።
የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ አዳዲስ የተመረጡ የሲኖዶስ መሪዎችን ቃለ-መሀላ ያስገቡ ሲሆን በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ቤተክርስቲያን ሴት የሲኖዶስ መሪ ያገኘችበት ታሪካዊ ቀን መሆኑን ጠቅሰዋል።
መረጃዉን ከቤተክርስቲያኒቱ ማህበራዊ ትስስር ገፅ አገኘነዉ።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/-p_1Zp50QVo
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
የኢትዮዽያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ_በደሴ ከተማ ሲሰጥ የቆየው #የማዕከላዊ_ሰሜን_ኢትዮጵያ_ክላስተር_የአገልጋዮች_የመሪነት_ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ።
የስልጠናዉ መሪ ሀሳብ “ለእግዚአብሔር ተልዕኮ ሲባል ለውጥን መምራት” የሚል ሲሆን ስልጠናውን አገልጋዮች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ተካፍለዋል።
ሰልጣኞችም በስልጠናው ማጠቃለያ ለለውጥ መነሳሳተቸውን ገልፀዋል።
ስልጠናውን የቤተክርስቲያኒቱ የወንጌል ተልዕኮና ቲኦሎጂ ዲፖርትመን ያዘጋጀው ሲሆን በያዝነው ዓመት የዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ስልጠና በሌሎች ሶስት ክላስተሮች በነቀምት፣ በጋምቤላ እና በአዲስ አበባ ከተሞች እንደተሰጠ ከቤተክርስቲያኒቱ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/b9c8xZ2OD28
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1
በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ_የምዕራብ_ጋምቤላ_ቤቴል_ሲኖዶስ ኒው ላንድ ማህበረ ምዕመናን ለቃሉና ለቅዱሳት ሚስጥራት አገልግሎት #52 አገልጋዮች #የቅስና_ሃላፊነት_ሰጠች
ጥር 19/2016 በተካሄደው በዚህ ስነስርዓት ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ለምዕመናን ቃለ እግዚአብሔር አስተምረው እጩ ቄሶቹን ቃለ መሃላ አስገብተው የቅስና ሃላፊነት ሰጥተዋል። በእለቱም የቀሰሱት እጩ ቄሶች በተለያየ ደረጃዎች ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ለአገልግሎቱ በሚረዳ መልኩ በመጋቢነት ሀላፊነት ዙሪያ በቤተክርስቲያኒቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ታሪኩ ቶሎሳ ከጥር 16-18/2016 ለሶስት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ወስደዋል።
በእለቱም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተንኳይ ጆክ በመገኘት ለምዕመናን ሰላምታ አቅርበዋል። ርዕሰ መስተዳደሩም በተመለከኩት ነገር የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ቤተክርስቲያን በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ብዙ ፍሬ ማፍራቷን እና አንዱም ፍሬ እራሳቸው አንደሆኑ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ይህንን ሥነ-ሥርዓት ለመታደም ጥሪ የተደረገላቸው የሚዮናውያን ልጆች፣ የአጋር ቤተ ክርስቲያናት ወተወካዮች፣ የእጩ ቄሶች ቤተሰቦች እና በርካታ የአከባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።
የምዕራብ ጋምቤላ ቤቴል ሲኖዶስ በሲኖዶስነት የተመሰረተው በ1984 ዓ.ም ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በስሩ 170 ማኀበራነ ምዕመናን እና 137,000 በላይ ምዕመናንን አቅፎ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲኖዶስ ነው።
ዜናውን ከቤተክርስቲያኒቱ የማህበራዊ ሚዲኦያ ገጽ አገኘነው።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/vbmLscuYvl0
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
👍3🙏2