የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.36K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ_አዲስ_አበባ_ሲኖዶስ_2ኛ_መደበኛ_ጉባኤውን ህዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም በእንጦጦ ማህበረ ምዕመናን አካሂዷል።
ጉባዮውም የቤተክርስቲያኒቱ ዓመራሮች፣ የተቀባይ ማህበረ ምዕመኗ እና የሲኖዶሷ አጋር ተቋማት ባቀረቡት ሰላም የጀመረ ሲሆን የሲኖዶሱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ኪሮስ ቀጥለው መራሄ ንግግር አድርገዋል። ባደረጉትም ሰፊ ንግግር ሲኖዶሷ ከተመሰረተችበት ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ዘጠኝ አመታት በመዲናዋ ውስጥ ሲኖዶሱ ስላከናወናቸው የወንጌል፣ የልማት እና የማህበራዊ አገልግሎቶች ያብራሩ ሲሆን ጨምረው ሲኖዶሱ እና በስሩ ያሉ ማህበራነ ምዕመናን ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች በዝርዝር አስቀምጠዋል።
አያያይዘውም ከተማዋ አህጉር ዓቀፍና ዓለም ዓቀፍ የዲፕሎማቲክ ግንኙነቶች እና ትላልቅ ተቋማት መቀመጫ ከመሆኗል የተነሳ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ቋንቋዎች ሊኖር ስለሚገባው ልዩ ወንጌል የማዳረስ አቀራረብ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል። መራኔ ንግግሩንም ተከትሎ ሲኖዶሱ የከተማዋን የስነ ሕዝብ አወቃቀር ባማከለ መልኩ ወንጌልን የማዳረስ ስራዎችን መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክሯል።
በማጠቃለያውም ጉባዬው ላለፉት ሁለት የአገልግሎት ዘመናት ሲኖዶሱን ሲመሩ የነበሩ አመራሮችን በታላቅ ምስጋና በማሰናበት ለቀጣይ አራት ዓመታት ሲኖዶሱን የሚመሩ መሪዎችን መርጧል።
የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ አዳዲስ የተመረጡ የሲኖዶስ መሪዎችን ቃለ-መሀላ ያስገቡ ሲሆን በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ቤተክርስቲያን ሴት የሲኖዶስ መሪ ያገኘችበት ታሪካዊ ቀን መሆኑን ጠቅሰዋል።
መረጃዉን ከቤተክርስቲያኒቱ ማህበራዊ ትስስር ገፅ አገኘነዉ።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/-p_1Zp50QVo
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!