የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.36K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ የልማት እና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን ከአጋሩ #ኪንደርኖትሂልፍ መንግስታዊ ያልሆነ የልማት ተቋም ጋር በጋራ በመሆን በተለያዩ የኢትዮጲያ አከባቢዎች #የተሰሩ_የልማት_ስራዎችን_የሚዘክር_50ኛ_አመት በዓል አከበረ።
አጋር ተቋሙ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በልጆች እና ወጣቶች ላይ የሚሰራ ሲሆን ባለፉት 50 አመታት ከቤተክርስቲያኒቱ ልማአ ኮምሽን ጋር በጋራ በመሆን ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ልጆችና ወጣቶች ሙሉ አቅማቸው ተጠቅመው ውጤታማና ምርታማ ዜጎች መሆን ይችሉ ዘንድ ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የትምህርት እድሎችን እና የሙያ ስልጠናዎችን ሲሰጥት ቆይቷል።
በዓሉም በጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል በተለያዩ ዝግጅቶች እና በኤግዚቢሽን አክብሯል። በመክፈቻ መርሀግብሩም ላይ የቤተክርስቲያኒቱና የልማት ተቋማቱ አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/sRiasuRa9cM
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🙏31