የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.36K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጲያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ_የስራ_አስፈፃሚ_ቦርድ_59ኛ መደበኛ ስብስባውን በጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና አካሄደ
* * * * ሐሙስ ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም ማለዳ በጌታ እራት አገልግሎት የተጀመረው የቦርዱ ስብሰባ ቀጥሎ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙን የመክፈቻ ንግግር አድምጧል። በእለቱም በቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ፀሐፊ ቄስ ተሾመ አመኑ የመወያያ አጀንዳዎች የቀረቡ ሲሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚደንት ንግግር እና በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ በዝርዝር ውይይቶች ተደርጓል።
የቦርዱ ውይይት በቀጣይ ቀን የቀጠለ ሲሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በሀገሪቱ ወቅታዊና ነባራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል። ተያይዞም ውሳኔዎችን አሳልፏል። 59ኛው የቦርዱ ስብሰባ ለያዝነው አመት የመጨረሻ ስብሰባ ሲሆን ቦርዱ አዲስ ለተመረጡና ቦርዱን ለተቀላቀሉ የአዳዲስ እና ነባር ሲኖዶስ ፕሬዚዳንቶች አቀባበል አድርጓል። ዜናውን ከቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ ድረገጽ አገኘነው።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/FzwAN1ZUrNI
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
1👍1