የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.4K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን #መካነ_ኢየሱስ_የምዕራብ_ጋምቤላ_ቤቴል_ሲኖዶስ ኒው ላንድ ማህበረ ምዕመናን ለቃሉና ለቅዱሳት ሚስጥራት አገልግሎት #52 አገልጋዮች #የቅስና_ሃላፊነት_ሰጠች
ጥር 19/2016 በተካሄደው በዚህ ስነስርዓት ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ለምዕመናን ቃለ እግዚአብሔር አስተምረው እጩ ቄሶቹን ቃለ መሃላ አስገብተው የቅስና ሃላፊነት ሰጥተዋል። በእለቱም የቀሰሱት እጩ ቄሶች በተለያየ ደረጃዎች ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ለአገልግሎቱ በሚረዳ መልኩ በመጋቢነት ሀላፊነት ዙሪያ በቤተክርስቲያኒቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ታሪኩ ቶሎሳ ከጥር 16-18/2016 ለሶስት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ወስደዋል።
በእለቱም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተንኳይ ጆክ በመገኘት ለምዕመናን ሰላምታ አቅርበዋል። ርዕሰ መስተዳደሩም በተመለከኩት ነገር የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ቤተክርስቲያን በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ብዙ ፍሬ ማፍራቷን እና አንዱም ፍሬ እራሳቸው አንደሆኑ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ይህንን ሥነ-ሥርዓት ለመታደም ጥሪ የተደረገላቸው የሚዮናውያን ልጆች፣ የአጋር ቤተ ክርስቲያናት ወተወካዮች፣ የእጩ ቄሶች ቤተሰቦች እና በርካታ የአከባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።
የምዕራብ ጋምቤላ ቤቴል ሲኖዶስ በሲኖዶስነት የተመሰረተው በ1984 ዓ.ም ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በስሩ 170 ማኀበራነ ምዕመናን እና 137,000 በላይ ምዕመናንን አቅፎ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲኖዶስ ነው።
ዜናውን ከቤተክርስቲያኒቱ የማህበራዊ ሚዲኦያ ገጽ አገኘነው።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/vbmLscuYvl0
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
👍3🙏2