#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎችን በቤጂንግ አግኝተው አወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቻይና ቤጂንግ እየተካሄደ ባለው የቻይና አፍሪካ ፎረም ጎን ለጎን ነው የተቋማቱን መሪዎች አጊንተው ተወያዩ።
በትናንትናው እለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በነበራቸው ቆይታም የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ለማስፋት እየሰራቸው ባላቸው ስራዎች እና በመን መልኩ መደግፍ ይቻላል የሚለው ላይ መክረዋል።
©Fbc
@YeneTube @Mycase27

#ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት የቡልቡላ ኢንተግሬትድ አግሮ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎበኙ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ የፓርኩ ግንባታ አሁን የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የቡልቡላ ኢንተግሬትድ አግሮ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በ26ዐ ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ጠቅላላ የፕሮጀክቱ ግንባታ 5 ዓመታትን ይወስዳል፡፡
በአሁኑ ወቅትም የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ 53 በመቶ ደርሷል፡፡ ግምባታው 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ይፈጃል ተብሏል፡፡
ፓርኩ ግንባታው ተጠናቆ ስራ ሲጀምር በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩና በአቅራቢያው ለሚገኙ አርሶ አደሮች የገበያ ትስስር እና ለወጣቶች ደግሞ የሥራ ዕድል የሚፈጥር ይሆናል፡፡
የፓርኩን ግንባታ የኦሮሚያ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ኮርፖሬሽን በባለቤትነት እየመራው ይገኛል፡፡
©ebc
@yenetube @mycase27

#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይና ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ ከሃገር መከላከያ የተለያየ ክፍለ ጦር የተውጣጡ የጦር ሰራዊት አባላትጋር ተወያዩ⬇️⬇️
የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሃገር መከላከያ የተለያየ ክፍለ ጦር የተውጣጡ #የጦር_ሰራዊት አባላት ጋር ተወያይተዋል።
አባላቱ ከተጣለባቸው ሃገራዊ ሃላፊነት እና ግዳጅ ጋር ተያያዥ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውንም ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያስታወቀው።
በውይይቱ የመከላከያ አባላት #እንደዜጋ ጥያቄያቸው #ሊደመጥ እና በተግባር መመለስ እንዳለበት አቶ ደመቀ ጠቁመዋል።
መንግስት እንደሃገር የጀመረው የሪፎርም ስራ በመከላከያ ዘርፉም በተመሳሳይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ተጨማሪ ውይይት በሚፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ መድረኮች የሚመቻቹ መሆኑን አቶ ደመቀ አስረድተው፥ በቀጣይም መንግስት በጀመረው የለውጥ ጉዞ ደረጃ በደረጃ እንደሚፈታ አረጋግጠዋል።
የመከላከያ አባለቱም በውይይቱ ለተነሱ የዘርፉ ችግሮች በሰከነ አግባብ እንዲፈታ እና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ዝግጁነታቸውን ማረጋገጣቸወን ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው።
(ፎቶ፦Office of Deputy Prime Minister)
©FBC
@YeneTube @Fikerassefa

▪️ስለሰላምና ስለበጎነት መስበክን ከጋሞ አባቶች መማር ይገባል▪️
#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
የጋሞ አባቶች የግጭት አፈታት በርካታ አመታትን በፖለቲካው ዓለም አሳልፈው ስለበጎነትና ስለፍቅር መስበክ ለሚቸገሩ ፖለቲከኞች ትምህርት እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንትና በአርባ ምንጭ ከተማ ከጋሞ አባቶች ባደረጉት ውይይት ላከናወኑት ተግባር #እውቅና ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት #የጋሞ አባቶች ባለፈው በከተማው የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም ያደረጉት አስተዋጽኦ የሚያስመሰግናቸው ነው።
ምንጭ ፦ ኢዜአ

#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በፕሬዚዳንቱ የመክፈቻ ንግግር ዙሪያ ዛሬ በምክር ቤቱ ቀርበው #የመንግስታቸውን አቋም ያብራራሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር #ሙላቱ ተሾመ ለህዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስብሰባ ባቀረቡት ንግግር ላይ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የመንግስታቸውን አቋም #ያብራራሉ።
ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ባለፈው ሳምንት በምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ ላይ የመንግስትን 2011 የትኩረት አቅጣጫዎች ያመላከተ #ንግግር ማቅረባቸው ይታወሳል።
ምክር ቤቱም በዛሬው እለት የፕሬዚዳንቱን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ምርጫም እንደሚከናወን የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።
ምክር ቤቱን ለላፉት ወራት #በአፈጉባኤነት ሲያገለግሉ የነበሩት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በዚህ ሳምንት ያቀረቡትን መልቀቂያ ምክር ቤቱ #መቀበሉን ተከትሎ፥ ወይዘሮ ሙፈሪያት አዲስ ለተቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መሾማቸው ይታወቃል።

#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ የመጀመሪያውን የአውሮፓ ጉብኝት በፈረንሳይና በጀርመን #ሊያደርጉ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የመጀመሪያውን የአውሮፓ ጉብኝት በፈረንሳይ እና በጀርመን ሊያደርጉ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪው ሳምንት መገባደጃ የሚያደርጉት ጉብኝት ከሁለቱ አገራት ጋር ያለን ዲፕሎማሲ ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከዚህ በተጨማሪ በፍራንክፈርት ከኢትዮጵያውያን ጋር በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡
25 ሺህ ኢትዮጵያውያን የሚመክሩበት ይህ መድረክ “አንድ ሆን እንነሳ ነገን እነገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ነው፡፡

#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጀርመን #ፍራንክፈርት ከተማ በአውሮፓ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ አባላት ጋር #ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ውይይት ያደርጋሉ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ #ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያደርጉት ጉብኝትና ውይይት “#አንድ_ሆነን_እንነሳ_ነገን_እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ሲሆን በውይይቱ ከ20 እስከ 25 ሺህ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጉብኝቱ ሁሉም #ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን በፍቅር እንዲገነቡ የሚያስችል በመሆኑ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል።
በአጠቃላይ #የሚደረገው ጉብኝትና ውይይት ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲና በውጭ ግንኙነት ላይ የሚሰራው ስራ አካል እንደሆነ ተገልጿል።
ቃል አቀባዩ ይህ ኢትዮጵያውያን እንደ አንድ ቤተሰብ በሚያገናኘው የፍራንክፈርት ውይይት ስኬታማ እንዲሆን በአገር ውስጥም ከአገር ውጪም አስፈላጊው #ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል።

#ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ነገ ወደ ፈረንሳይ #ያቀናሉ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአውሮፓ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉበኝት ነገ #ይጀምራሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን በፈረንሳይ የሚጀምሩ ሲሆን፥ በነገው እለትም ወደ #ፈረንሳይ እንደሚያቀኑ ተነግሯል።
በፈረንሳይ በሚኖራቸው ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
በመቀጠልም ወደ #ጀርመን የሚያቀኑ ሲሆን፥ በዚያም ከመራሂተ መንግስት #አንጌላ ሜርክል ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በጀርመን ቆይታቸውም ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ከሚውጣጡ 25 ሺህ ኢትዮጵያውያን ጋር በፍራንክፈርት ይወያያሉ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ጉብኝት “#አንድ_ሆነን_እንነሳ_ነገን_በጋራ_እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ መሆኑም ተነግሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን የሚያደርጉት #በሀገራቱ መሪዎች በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ነው።
ምንጭ ፦ኤፍ.ቢ.ሲ