YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጀርመን #ፍራንክፈርት ከተማ በአውሮፓ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ አባላት ጋር #ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ውይይት ያደርጋሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ #ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያደርጉት ጉብኝትና ውይይት “#አንድ_ሆነን_እንነሳ_ነገን_እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ሲሆን በውይይቱ ከ20 እስከ 25 ሺህ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉብኝቱ ሁሉም #ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን በፍቅር እንዲገነቡ የሚያስችል በመሆኑ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ #የሚደረገው ጉብኝትና ውይይት ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲና በውጭ ግንኙነት ላይ የሚሰራው ስራ አካል እንደሆነ ተገልጿል።

ቃል አቀባዩ ይህ ኢትዮጵያውያን እንደ አንድ ቤተሰብ በሚያገናኘው የፍራንክፈርት ውይይት ስኬታማ እንዲሆን በአገር ውስጥም ከአገር ውጪም አስፈላጊው #ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ምንጭ ፦ ኢዜአ
@yenetube @mycase27
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2012 የትምህርት ዘመን #በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት #አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ #ጥቅምት_01 ቀን እና #ጥቅምት_02 ቀን 2012 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ አሳውቋል፡፡

ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ፣
➡️ ብርድልብስና አንሶላ፣
➡️ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
➡️ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡
➡️ የስፖርት ትጥቅ

📌 በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡
📌 ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡
📌 ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲን ድረገጽ https://
portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን
📌 ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ጥቅምት 03 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡
📌 ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
📌 ተማሪዎች ከወላጆቻቸውና በአካባቢያቸው ከሚገኙ ወረዳዎች ጋር ውል ተፈራርመው የማረጋገጫ ወረቀት ካላመጡ ዩኒቨርስቲው የማይቀበል መሆኑን በጥብቅ ያሳስባል፡፡
📌 በተጨማሪም ባለፈው ስርዓተ ትምህርት መሠረት በመጀመሪያ ዓመት 1ኛ እና 2ኛ ሴሚስተር በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች ከዘድሮ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2012 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር መልሶ ቅበላ እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡እንዲሁም መደበኛ የድህረ ምረቃ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 06 2012 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Via አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa
ለኣክሱም ዩኒቨርሲቲ #አዲስ_መደበኛ የቅድመ-ምረቃና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ የ2012 የትምህርት ዘመን የመግቢያ ጊዜ #ጥቅምት 8-9 ቀን 2012 ዓ/ም መሆኑን እየገለፅን

📌 በቅድመ-ምረቃ በNatural Science የተመደባችሁ ወንድ ተማሪዎች የስማችሁ የመጀመርያው ፊደል ከA እስከ D እና ሴት ተማሪዎች ከA እስከ E የሆናችሁ በሽረ ካምፓስ እንዲሁም ሌሎች ሁሉም አዲስ ተማሪዎች በዋና ግቢ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን። በተጨማሪም በ2011 ዓ/ም የአንደኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የነበራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድረው ያደረጋችሁና የመልሶ ቅበላ መስፈርት የምታሟሉ ተማሪዎች የስርዓተ-ትምህርት ( ካሪክለም) ለውጥ የተደረገ በመሆኑ በተጠቀሰው ቀን ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ፡
ሁሉም የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ፡
📌 የ10ኛ ክፍል ሰርቴፊኬት፣ የመሰናዶ ትምህርት ትራንስክሪፕት እና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ሰርቴፊኬት ዋናውንና ፎቶኮፒ
📌 የፓስፖርት መጠን ያለው የቅርብ ጊዜ 8 ጉርድ ፎቶግራፍ
📌 የግል መጠቀሚያ አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ-ልብስ፣የስፖርት ትጥቅ
📌 የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ክብ ማህተም ያረፈበት የተማሪ፣ ወላጅ እና ዩኒቨርሲቲ ውል በመያዝ በግቢያችሁ እንድትገኙ እያሳሰብን
📌 የሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች የአንደኛ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕታችሁን ከተማራችሁበት ዩኒቨርሲቲ ቀድማችሁ እንድታስልኩ እናሳውቃለን።

-የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa