YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ነገ ወደ ፈረንሳይ #ያቀናሉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአውሮፓ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉበኝት ነገ #ይጀምራሉ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን በፈረንሳይ የሚጀምሩ ሲሆን፥ በነገው እለትም ወደ #ፈረንሳይ እንደሚያቀኑ ተነግሯል።

በፈረንሳይ በሚኖራቸው ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በመቀጠልም ወደ #ጀርመን የሚያቀኑ ሲሆን፥ በዚያም ከመራሂተ መንግስት #አንጌላ ሜርክል ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በጀርመን ቆይታቸውም ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ከሚውጣጡ 25 ሺህ ኢትዮጵያውያን ጋር በፍራንክፈርት ይወያያሉ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ጉብኝት “#አንድ_ሆነን_እንነሳ_ነገን_በጋራ_እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ መሆኑም ተነግሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን የሚያደርጉት #በሀገራቱ መሪዎች በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ነው።
ምንጭ ፦ኤፍ.ቢ.ሲ
@yenetube @mycase27
#ፈረንሳይ

በሀገረ ፈረንሳይ በ24 ሰዐት ሪፖርቷ 1,120 ሞት ሪፖርት ያደረገች ሲሆን ከነዚህ መካከል 532 የሚሆኑት በ(Nursing Home) የነበሩ ፣ ከዚህ በፊት ያልተቆጠሩትን ይጨምራል። እንዲሁም 5,233 ሰዎች በዛሬው ዕለት ብቻ በቫይረሱ ተይዘዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምር ቤት በትግራይ ክልል ግጭት ዙሪያ በዛሬው እለት ውይይት አድርጓል።

👉በውይይቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ የተገኙ ሲሆን፤ በጦርነቱ የተካፈሉ አካላት በሙሉ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም በማወጅ ከትግራይ ክልል ቢወጣም የህወሓት ሀይሎች ወደ ጎረቤት አፋር እና አማራ ክልሎች ጥቃት በመክፈታቸው አጠቃላይ የተኩስ አቁም ላይ መደረስ እንደልተቻለም ገልጸዋል።

👉#ፈረንሳይ እና #አየር_ላንድ ተወካዮች በበኩላቸው በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተፈጠሩ ነገሮች አሳሳቢ ናቸው ያሉ ሲሆን፤ የህወሓት ሀይሎች በአስቸኳይ ከወረሩት የአፋር እና የአማራ ክልል ለቀው እንዲወጡ፤ የአማራ ክልል ሀይሎች ከያዙት የትግራይ ክልል መሬት እንዲለቁ እንዲሁም ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል።

👉#አሜሪካ ተወካይ በበኩላቸው፤ በአፋጣኝ ተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ መስመር እንዲከፈት እና ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያካተተ ውይይት እንዲጀመር አሜሪካ ጥሪ አቅርባ ነበረ፤እስካን የተጀመረ ነገር የለም፤ በኢትዮጵያ መንግስተ በኩልም በጎ ምለሽ አላገኘንም ብለዋል።የህወሓት ሀይሎች ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ገብተው በከፈቱት ጥቃት በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናላቸውን በመጥቀስ፤ ይህ በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል ያሉ ሲሆን፤ “የኤርትራ ጦር በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ነው፤ አሁን ያለው የጦርነት እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ነው፤ ይህም አሜሪካን ያሳስባታል” ብለዋል።በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ ሚሊየኖች ለምግብ ችግር መጋለጣቸውን እና አሁን ባለው ሁኔታ በትግራይ ክልል ያሉ መጋዝኖች ውስጥ ክምችም ማለቁን በመጥቀስ፤ ለዚህም የኢትዮጵያን መንግስት ተወቃሽ አድርገዋል።

👉#ሩሲያ ተወካይ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ያወጀው የተናጥል የተኩስ አቁም በህወሓት ሀይሎች መጣሱ አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ የህወሓት ሀይሎች ከትግራይ ክልል ውጪ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ጥቃት መክፈታውን፤ የሀገር ውስጥ ፈናቃዮች ቁጥር በእጥፍ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።“የሰብአዊ ድጋፍ ጉዳይን ፖለቲካዊ ማድረግ ተገቢ አይደለም፣ በሚዲያ የሚካሄደው መርዛማ አካሄድ የመሳካጥትእድሉ አነስተኛ ነው” ያሉት የሩሲያ ተወካይ፤ ሰብአዊ ድጋች ሲቀርቡ ለትግራይ ብቻ ተብሎ ሳይሆን፤ ለአማራ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ኦሮሚያም ክልሎችም መሆን አለበት ሲሉም ተናግረዋል።“በኢትዮጵየ ፖለቲካው ውይይት እንደጀመር እንደግፋለን፤ ነገር ግን ውይይቱ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያውያን መሪነት ሊካሄድ ይገባል”ም ብለዋል።ለኢትዮጵያ የሚረጉ ድጋፎች የሀገሪቱን ሉአላዊነት እና አንድነት ባስጠበቀ መልኩ ሊካሄድ ይገባል ያሉ ሲሆን፤ በሰኔ ወር በተካሄደው ምርጫ ኢትዮጵያን የመረጡት መንግስት ሀገሪቱን ወደ ቀድሞ መስመር የመመለስ አቅም እንዳለውም የሩሲያ መንግስት ያምናል ሲሉም ተግረዋል።

👉#ቻይና ተወካይም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም አካላት በራሳቸውመ መንግድ በሚያድርጉት የፖለቲካ ውይይት ልዩነቶቻቸውን እንደሚፈቱ ቻይና ታምለች ብለዋል።በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ስራቸውን በሚሰሩበት ጊዜ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ባከበረ መልኩ መሆን ይገባል ያሉት ተወካዩ፤ ለኢትዮጵያ የሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።በሰብአዊ መብት እና በሰብዓዊ ድጋፍ ስም በኢትዮጵየ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶችን ቻይና አጥብቃ ትቃወማለችም ብለዋል።የኬንያ እና የህንድ ተወካዮችም የትግራይ ክልል ግጭት መፍትሄ በኢትዮጵየውያን መሪነት መምጣት አለበት የሚል ሀሳብ አንስተዋል።

Via @alainamharic
@YeneTube @FikerAssefa