YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት እድገት ውስጥ የቻይና ሚና #ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ቻይና ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት ያደረገችውን አስተዋጽኦም ኢትዮጵያ አትዘነጋውም ብለዋል #ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
©fbc
@yenetube @mycase27
ወደ ቻይና የሚሄዱ ዜጎች #ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ተነገረ።

ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ሰዎች በአደራ እንዲያደርሱላቸው የሚሰጣቸው የታሸገ ነገር ይዘው ከመሄድ #ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ቃለአቀባይ እንደተናገሩት አንድ አንድ አካላት በማርና መሰል በመሸፈንና በማሸግ አንደዛዥ እፆችን ለመላክ የሚንቀሳቀሱ በመኖራቸው ተጓዦች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲሁም
ምንነቱ ያልታወቀ #የታሸገ ነገር መቀበል የላቸውም። ቃለአቀባዩ አክለውም "ለትምህርት እድል ወደ ቻይና ሀገር እንልካለን" ከሚሉ ህገወጥ ሰዎች ህብረተሰቡ ራሱን መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል።

ምንጭ: ኢ.ፕ.ድ
@YENETUBE @FIKERASSEFA
📌ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ‼️

ዜጎች በሃገራቸው ውስጥ በነፃነት የመንቀሳቀስ እንዲሁም በመረጡት ኣከባቢ የመኖር እና ሃብት የማፍራት ህገ-መንግስታዊ መብታቸው መሆኑ ከተረጋገጠ ቆይቷል፡፡ የፌደራልና የክልል መንግስትም ይህ ህገ-መንግስታዊ የዜጎች መብት ሳይሸራረፍ ተግባራዊ ለማድረግ ኣስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉና ጥሰት ሲያጋጥም ደግሞ ኣስቸዃይ መፍትሔ በመስጠት በእንደዚህ ዓይነት የጥፋት ድርጊት ለሚሳተፉ ኣካላት ህግ ፊት ማቅረብ ደግሞ ህግ-መንግስታዊ ግዴታ ኣለባቸው፡፡

ይሁን እንጂ ባለፉት ጥቂት ኣመታት በተለያዩ የኣገራችን ክፍሎች የተለያዩ ብሄረሰብ ተወላጆች ማንነታቸውን መሰረት ያደረገ በህይወት እና ንብረታቸው ላይ የሚደርስ የጥቃት ዜና መስማት እየተለመደ መጥቷል፡፡ በትግራይ ተወላጆችም ተመሳሳይ #በደል መፈፀሙን የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይም በኣማራ ክልል ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የትግራይ ተወላጆች ህይወትና #ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድና በተደጋጋሚ ህገ-መንግስታዊ ጥሰት እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ የየኣከባቢው ህዝብ አደጋውን ለመቀነሰ ጥረት ባያደርግ ንሮ ከዚህ የከፋ ጥፋት ሊደርስ ይችል እንደነበረ ይታመናል፡፡ የተለያዩ ኣጀንዳዎች በመቅረፅ በትግራይ ህዝብ ሰላምና ድህንነት በማወክ ዙርያ የሚደረግ ዘመቻ ኣሁንም ሳያቋርጥ እንዲቀጥል እየተደረገ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ጉዳይ ላይ እጅን ከማስገባት በተጨማሪ ከትግራይ ጋር የሚያስተሳስሩ መንገዶች በመዝጋት እና የትግራይን #መሬት በሃይል #ለመውረር መፈለግ የመሳሰሉ #ያረጁና_ሃሏ_ቀር ኣስተሳሰቦችና ክፉ ተግባራትም እየታዩ ናቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኣሁንም ትላንት #በመተማና ሌሎች አከባቢዎች ተመሳሳይ ግፍ ተፈፅሟል፡፡ ችግር በተፈጠረባቸው ኣከባቢዎች ኣንዳንድ የኣማራ ክልል #ከፍተኛ_የስራ_ሃላፊዎች ኣስቀድመው በማንቀሳቀስ የደረሰውን ግፍ እንዲፈፀም ኣመራር የሰጡ መሆኑን ታውቆ _ባስቸኳይ_ወደ_ህግ ሊቀርቡ ይገባል፡፡

ሰዎች ለማህበራዊ ልማት ሊተጉ ሲገባ ለጥፋት እንቅልፍ ኣጥተው ሌተቀን ሲሰሩ ማየት ኣሳዛኝ ሲሆን ጥፋትን በጥፋት መመለሰ ግን ቀላል መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል፡፡

የትግራይ ህዝብና መንግስት ደግሞ ለጥፋት ሳይሆን ለጋራ ልማትና ሰላም የቆመ በመሆኑ የሁለቱን #ህዝብ ወንድማማችነት የሚያጠናክሩ እንጂ የሚያፈርሱ ስራዎች የማንሰራ መሆኑን አሁንም በድጋሜ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ #ይህ_ማለት_ግን በህዝባችን ላይ የሚፈፀሙ የጥፋት ተግባሮች ኣይተን እንዳላየን እንሆናለን ማለት ኣይደለም፡፡ በህዝባችን ንብረትና ህይወት ላይ ጉዳት ያደረሱ በሙሉ እንደ ክልል መንግስት በህግ እንዲጠየቁ ጥረት የምናደርግ ይሆናል፡፡ የኣማራ ክልል እና የፌደራል መንግስትም ህገ-መንግስቱን ያለ ማቋረጥ በተደጋጋሚ በሚጥሱ ኣካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል፡፡ ለዘመናት ኣብረው የነበሩና በብዙ መንገድ የተሳሰሩትን ህዝቦች ኣንድነታቸውና ወዳጅነታቸው ኣጠናክረው እንዲቀጥሉ ከማስቀጠል ይልቅ #ማንነት ላይ መሰረት ያደረገ ጥቃት ሲፈፀም ማየት የሚያሳዝን እና የሚሳፍር ድርጊት ነው፡፡ የኣማራ ክልል ህዝብና መንግስት እንዲሁም የፈደራል መንግስት ይህ ማንነት መሰረት ኣድርጎ እየተፈፀመ ያለውን በደል ኣጥብቆ በማወገዝ ኣስቸኳይ ምላሽ በመስጠት የዜጎችን ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የወደመ #ንብረታቸው እንዲተካና በተለያዩ ግዚያት በህዝብ ላይ ግፍ የሚያደርሱትን ወንጀለኞች በሙሉ እንዲሁም መንግስት በቅርብ በምህረት ለቋቸው ሲያበቃ በወንጀል ተግባር ላይ የተሰማርቱን ጨምሮ ወደ ህግ እንዲቀርቡ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በማንነታቸው ምክንያት ጥቃት እና ግፍ ለተፈፀመባቸው ሁሉ የተሰማውን ሓዘን በመግለፅ የዚህ ኣስነዋሪ ተግባር ሰለባ ለሆኑ ቤተሰብና ኣካላት በትግራይ ህዝብ እና መንግስት ስም #መፅናናትን ይመኛል፡፡

የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

መቐለ

ጥቅምት 27/2011 ዓ.ም
@YeneTube @Fikerassefa
#update
በምድር፣ በአየር፣ በባህር እና በህዋ ዝግጁ የሆነ የመከላከያ ሰራዊት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን የኢፌዲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #አብይ አህመድ አስታወቁ።

በመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው እየተደረገ የነበረው ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ላይ ጠ/ር ዶ/ር #አብይ አህመድ እንደተናገሩት፤ ዘመናዊ ዐውደ ውጊያ በሚጠይቃቸው አምስቱም ምህዳሮች ዝግጁ የሆነ #መከላከያ ሰራዊት የመገንባቱ ሂደት ተጀምሯል።

የአሰራር መመሪያዎች እንዲዳብሩና ዘመናዊ ሰራዊት ሊኖረው በሚገባው ደረጃ እንዲሆኑ #ከፍተኛ ጥረት መደረጉንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር የገለጹት።

መከላከያ የሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ቴክኖሎጂን የሚታጠቅ፣ #በራሱ አቅም መጠገን፣ ማሳደግ ብሎም መፍጠር የሚችል እንዲሆን በርካታ የአቅመ ግንባታ ስራዎች #እየተሰሩ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሰራዊቱ እነደሌሎች አገራት ከራሱም አልፎ ለሌሎች ዘርፎች ምንጭ መሆን የሚችል የቴክኖሎጂ ማዕከል እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል ሲሉም ነው የገለጹት።

ምንጭ ፦የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@yenetube @mycase27
መሪዎቹ ባሕር ዳር ገቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ አህመድ፣ፕሬዝዳንት #ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዝዳንት #ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ አሁን ባሕር ዳር ገብተዋል፡፡

📌በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል #የሀይማኖት አባቶች.#የሀገር ሽማግሌዎች እና #ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አደርገውላቸዋል፡፡
ፎቶ ፦ አብመድ
@yenetube @mycase27
"ለሼህ አላሙዲ #መፈታት የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር" አቶ ተካ


በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና የሳዑዲ ዜግነት ያላቸው ቢሊየነሩ ሼህ ሞሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ትናንት ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ከሪያድ ወደ ጅዳ በማቅናት ከቤተሰባቸው ጋር ተቀላቅለዋል።

የሳዑዲ መንግሥት ያካሄደውን የፀረ-ሙስና ዘመቻን ተከትሎ ከበርካታ ንጉሣዊ ቤተሰቦች እና ከበርቴዎች ጋር ተይዘው ከ14 ወራት በላይ በእስር ያሳለፉት አላሙዲ እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠበቃቸው አቶ ተካ አስፋው ለቢቢሲ ተናገረዋል።

አቶ ተካ ''ትናንት (እሁድ) በስልክ ተገናኝተናል። ጤናቸው በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተቀላቅለዋል'' ያሉ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ መቼ ሊመጡ ይችላሉ ተብለው ለተጠየቁት ''ወደ ኢትዮጵያ መምጣቸው አይቅርም፤ ነገር ግን መቼ እንደሚመጡ በእርግጠኝነት መናገር አልችልም'' ሲሉ የአላሙዲ ጠበቃ አቶ ተካ አስፋው ተናግረዋል።

ካለፈው ግንቦት 2009 ዓ.ም ጀምሮ አሊ-አላሙዲ ከእስር እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጥረቶችን ሲያደርጉ እንደቆዩ የሚናገሩት አቶ ተካ ''ጠቅላይ ሚንስትራችን ከአንዴም ሁለቴ ቦታው ድረስ ተገኝተው ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድረገዋል። ከዚያም በኋላ በነበራቸው ግንኙነት ከፍተኛ ጥረት እንዳደረጉ ነው የምናውቀው። ለመፈታታቸው የእሳቸው ጥረት እንዳለበት ነው የተረዳነው'' ብለዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት የፌስቡክ ገጽ የባላሃብቱን ከእስር መፈታት ይፋ ባደረገበት ጽሁፍ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ግንቦት 2010 ዓ.ም ሞሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ከእስር ለማስፈታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን እና በቅርቡም ወደ አገራቸው ይመለሳሉ በማለት በሚሊኒያም አደራሽ ያደረጉትን ንግግር አስታውሷል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ጨምሮም አሊ-አላሙዲ በሰላም እንዲመለሱ መልካም ምኞታችንን አንገልጻለን በማለት አስፍሯል።

ከ14 ወራት በፊት ከአላሙዲ ጋር በሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት መካከል ጥቂት የማይባሉ ከበርቴዎች መጠኑ በይፋ ያልተገለጸ ነገር ግን ካላቸው ሃብት ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ ለሳዑዲ መንግሥት ሰጥተው ከወራት በፊት ከእስር መውጣታቸው ይታወሳል።

ከዚህ አንጻር ሼህ አላሙዲንም ከእስር ለመፈታት #ከፍተኛ_ገንዘብ_ከፍለዋል ወይ ተብለው የተጠየቁት ጠበቃቸው አቶ ተካ ''ከፍለዋል ብዬ ለመናገር ይከብደኛል።

የተፈቱበትን አኳኋን ዝርዝር ሁኔታ ሰለማላውቅ ይሄ ነው ብዬ መናገር አልችልም። እኔ ግን ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለዋል ብዬ አላምንም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ግን ለመፈታታቸው የማይናቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል'' ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
#ሀዋሳ_ኮሮና_ቫይረስ_ዝግጅት_ሲፈተሽ

በሀዋሳ ከተማ አንድ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ አለ ተብሎ በተለይም ዋርካ አከባቢ ከፍተኛ መሸበረ እንዲሁም ግለሰብን የማግለል ሁኔታዎች ነበሩ በቦታው ተገኝተን ለመታዘብ የቻልነው እናካፍሎ።

( በፁሁፋችን መሀል ታማሚው - ኮሮና ቫይረስ ባይሆንም ግለሰብ ታሞ ስለ ነበር ታማሚ በሚል ተጠቅመናል )

ታማሚው ወደ 2:30 ሀዋሳ ዋርካ ሆቴል ወረድ ብሎ ባለ እንግዳ ማረፊያ ጋር ተጠግቶ ህመሙን ለአንድ ግለሰብ ያጋራዋል ከዚያ ያጋራው ግለሰብ #ከፍተኛ_የሳል : #አይን_መቅላት እንዲሁም #መተታጠፊያዬ ያመኛል ብሎ እንዳስረዳው በቀጥታ አቅራቢያው ወዳለ ጤና ጣቢያ ለመጦቀም አመራ ከዚያ የጤና ጣቢያው ባለሙያዎች በጉዳዩ ላይ እያፌዙ እንመጣለን ወይንም 6929 ደውል በማለት ልጁ ተመልሷል።

ታማሚው ልጅ ሳሉ በርትቶበታል ሰውም በቦታው ተስብስቧል ነገር ግን የጤና ጣቢያው ባለሙያዎች ቦታው ላይ አምቡላንስ የዘው ለመምጣት 3 ሰዐታት ፋጅቶባቸዋል።

ባለሙያዎች በአምቡላንስ መጡ የታማሚውን ሙቀት የለኩት በከፍተኛ ፍራቻ ነበር ( ይህ ስልጠና እንደሚጎላቸው ቦታው ላይ ተገኝተን ተመልክተናል) እንዲሁም ታማሚውን በአግባቡ አላስተናገዱትም ነበር።

ታማሚው የተቀመጠበት የነካቸውን ቦታዎች infected ሆነዋል ተብለው የሚገመቱ ቦታዎችን Disinfect ለማድረግ ከቀኑ 10:00 ላይ መተው ነው ርጭት ያደረጉት።

#ሀዋሳ_ከተማ_አስተዳደር_ዝግጅታችሁ_እንደገና_ፈትሹ

ፎቶ:- በቫይረሱ ተጠቅቶ ሊሆን ይችላል በሚል ቦታ ከቫይረሱ እያፅዱ
@Yenetube @Fikerassefa
በስፖርት ውርርድ /ቤቲንግ/ #ከፍተኛ_ልምድ ያላቸው ና ማሸነፍ ከፈለጉ ❓️
እንግዲያውስ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ቴሌግራም ቻናሉን አሁኑኑ ይቀላቀሉ 🙏
👇
https://tttttt.me/+QJxgPf4S329jZjBk
https://tttttt.me/+QJxgPf4S329jZjBk
በስፖርት ውርርድ /ቤቲንግ/ #ከፍተኛ_ልምድ ያላቸው ና ማሸነፍ ከፈለጉ ❓️
እንግዲያውስ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ቴሌግራም ቻናሉን አሁኑኑ ይቀላቀሉ 🙏
👇
https://tttttt.me/+QJxgPf4S329jZjBk
https://tttttt.me/+QJxgPf4S329jZjBk