YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በፕሬዚዳንቱ የመክፈቻ ንግግር ዙሪያ ዛሬ በምክር ቤቱ ቀርበው #የመንግስታቸውን አቋም ያብራራሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር #ሙላቱ ተሾመ ለህዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስብሰባ ባቀረቡት ንግግር ላይ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የመንግስታቸውን አቋም #ያብራራሉ

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ባለፈው ሳምንት በምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ ላይ የመንግስትን 2011 የትኩረት አቅጣጫዎች ያመላከተ #ንግግር ማቅረባቸው ይታወሳል።

ምክር ቤቱም በዛሬው እለት የፕሬዚዳንቱን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ምርጫም እንደሚከናወን የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

ምክር ቤቱን ለላፉት ወራት #በአፈጉባኤነት ሲያገለግሉ የነበሩት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በዚህ ሳምንት ያቀረቡትን መልቀቂያ ምክር ቤቱ #መቀበሉን ተከትሎ፥ ወይዘሮ ሙፈሪያት አዲስ ለተቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መሾማቸው ይታወቃል።
©FBC
@yenetube @mycase27
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት የጋራ መክፍቻ ስነ ስርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ሙላቱ ተሾመ ባደረጉት ንግግር ላይ ከምክር ቤቱ አባላት በመንግስት አሰራርና በሰራኛው ተጠቃነት ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ አህመድ ከደመወዝ ጭማሬና እና የመንግስት አሰራርን ለመቀየር ስተጠናውን የጂኤጂ /GAG/ ጥናት ትግበራ ካነሷቸው ሀሳቦች የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-⤵️⤵️

▪️ የመንግስት አሰራርን ለማዘመንና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በአዲስ መልክ ለማደራጀት የተጠና በመሆኑ ከደመወዝ ጭማሬ ጋር ግንኙነት የለውም፡፡

▪️ይሁን እንጂ አሰራሩን በሚመጥን ሁኔታ ተጠንቶ የቀረበው በጀት ከ30 ቢሊዮን እስከ 100 ቢሊዮን ብር የሚያስወጣ በመሆኑ አሁን ባለንበት ወቅት ተግባር ላይ ለማዋል አስቸግራል፡፡

▪️መንግስት በደመወዝ ጭማሬውም ሆነ የጂኤጅ ጥናቱን በሙሉ አቅም ለመተግበር የበጀት እጥረት ጫና፣ገቢ የመሰብሰብ አቅም ውስንነት፣ አንዳንድ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለማስጨረስ በተወሰደ እርምጃ ጫና መፈጠሩ፣ እንዲሁም የእዳ ጫና በአገሪቱ ላይ ሸክም በመሆኑ የሚፈለገውን ማሻሻያ መድረግ አላስቻለም፡፡

▪️የዋጋ ግሽበቱ እየቀነሰ መምጣቱ ኢኮኖሚያችን እያገገመ ለመሆኑ ተስፋ የሚሰጥ ነው፡፡

▪️በመሆኑም የሚደረገውን ጭማሬና ማሻሻያ የዋጋ ግሽበት እንዳይወስደው የማራጋገት ስራው መስመር ሲይዝ አሁን እያከፈልን ያለነው መስዕዋትነት ለአገር እንደሆነ ታስቦ መንግስትም ዝም አይልም፡፡

▪️ 1.5 ሚሊዮን የመንግስት ሰራተኛ ያለበት አገር በመሆኑ ለውጡና ማሻሻያው ለአገርም ለሰራኛውም ጠቃ በሆነ አግባብ መፈፀም ያስፈልጋል፡፡
ምንጭ ፦ ebc
@yenetube @mycase27
ምክር ቤቶቹ ነገ የፕሬዚዳንት ዶ/ር #ሙላቱን መልቀቂያ በመቀበል አዲስ የሪፐብሊኩን #ፕሬዚዳንት ይሾማሉ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ነገ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባቸውን ያካሂዳሉ።

ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመውም፥ ምክር ቤቶቹ በስብሰባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር #ሙላቱ ተሾመ የሚያቀርቡትን መልቀቂያ በመቀበል አዲስ ፕሬዚዳንት #ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቶቹ ነገ የፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱን #መልቀቂያ በመቀበል አዲስ የሪፐብሊኩን ፕሬዚዳንት ይሾማሉ
©FBC
@yenetube @mycase27
#update
ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ሙላቱ ተሾመ በፈቃዳቸው ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በራሳቸው ፍቃድ ከሀላፊነታቸው ለቀቁ።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የስራ መልቀቂያቸውን በዛሬው እለት በካሄደው 2ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ በማቅረብ ነው ሀላፊነታቸውን የለቀቁት።

የጋራ ምክር ቤቶቹም ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ያቀረቡትን የስራ መልቀቂያም ተቀብሏቸዋል።
ምንጭ ፦ኤፍ.ቢ.ሲ
@yenetube @mycase27
#ከስልጣን በፊትም ከስልጣን በሁዋላም #በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ህይወት እንዲህ #ይቀጥላል

☑️የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር #ነጋሶ ጊዳዳ
☑️የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት #ግርማ ወልደጊዮጊስ
☑️የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ሙላቱ ተሾመ
☑️የአሁኗ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ #ሳህለወርቅ ዘውዴ
@yenetube @mycase27