YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️
አቶ #ደመቀ_መኮንን የኢህአዴግ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይና ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ ከሃገር መከላከያ የተለያየ ክፍለ ጦር የተውጣጡ የጦር ሰራዊት አባላትጋር ተወያዩ⬇️⬇️

የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሃገር መከላከያ የተለያየ ክፍለ ጦር የተውጣጡ #የጦር_ሰራዊት አባላት ጋር ተወያይተዋል።

አባላቱ ከተጣለባቸው ሃገራዊ ሃላፊነት እና ግዳጅ ጋር ተያያዥ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውንም ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያስታወቀው።

በውይይቱ የመከላከያ አባላት #እንደዜጋ ጥያቄያቸው #ሊደመጥ እና በተግባር መመለስ እንዳለበት አቶ ደመቀ ጠቁመዋል።

መንግስት እንደሃገር የጀመረው የሪፎርም ስራ በመከላከያ ዘርፉም በተመሳሳይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ተጨማሪ ውይይት በሚፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ መድረኮች የሚመቻቹ መሆኑን አቶ ደመቀ አስረድተው፥ በቀጣይም መንግስት በጀመረው የለውጥ ጉዞ ደረጃ በደረጃ እንደሚፈታ አረጋግጠዋል።

የመከላከያ አባለቱም በውይይቱ ለተነሱ የዘርፉ ችግሮች በሰከነ አግባብ እንዲፈታ እና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ዝግጁነታቸውን ማረጋገጣቸወን ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው።

(ፎቶ፦Office of Deputy Prime Minister)
©FBC
@YeneTube @Fikerassefa
በኢፌዴሪ ምክትል  በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ #ደመቀ መኮንን ከፍተኛ የመንግስት የሚመራ ልዑክ ወደ ሳዑዲ' አረቢያ ሪያድ #አቀና

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ልዑክ ወደ ሳዑዲ ያቀናው   ከጥቅምት 13 እስከ 15 በሚካሄደው  የኢንቨስትመንት ፎረም ለማሰታፍ ነው ተብሏል።
@yenetube @mycase27
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ በሳዑዲዓረቢያ ቆይታ በሪያድ ከተማ የኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደት ዙሪያ #ከቦርድ አባላቱ ጋር ተወያይተዋል።
ምንጭ ፦AMMA
@YENETUBE @MYCASE27
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር #ደመቀ መኮንን ከሳዑዲ አልጋ ወራሽ #መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር ተነጋገሩ።

አቶ ደመቀ አለም በነፍስ አስገዳይነት አይኑን የጣለባቸውን #መሀመድ ቢን ሳልማንን ካነጋገሩት ጥቂት የሀገር መሪዎች #አንዱ ሆነዋል።

አልጋ ወራሹ ስደተኛ #ጋዜጠኛውን ከማል ኪጎሺን በደህንነት ሰራተኞቻቸው አስገድለዋል በሚል #እየተብጠለጠሉ ነው።

አንዳንድ ሀገራት በሳዑዲ በተካሄደው የንግድ ጉባዔ ላይ ላለመሳተፍ ወስነው ቀርተዋል፣ ሌሎች ደግሞ #ዝቅ ያሉ ባለስልጣናትን ልከዋል።

አቶ ደመቀ በሳዑዲና ኢትዮጵያ የጋራ የንግድ ፎረም ላይም ተካፍለዋል።
©wazema
@yenetube @mycase27
የሱማሊያው ፕሬዝዳንት #ሙሐመድ አብዱላሂ ጎንደር ገቡ

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ #አህመድና ምክትል ጠ/ሚኒስትር #ደመቀ መኮንን ጨምሮ ሌሎች የየክልሉ መሪዎች ለፕሬዝዳንቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
@yenetube @mycase27
♦️በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር #ደመቀ መኮንንና በአማራ ክልል ፕሬዝደንት ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ የአማራ ክልል የልዑካን ቡደን በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ጋር ለመወያየት ከሁለት ሳምንት በኅላ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ያቀናል

🔹የልዑካን ቡድኑ በዋሽንግተን ዲሲ (Dec 2, 4 & 5)፣ በዳላስ (Dec 8)፣ በሲያትል Dec 9) እና በሎስ አንጀለስ (Dec 15) ከተማዎች የውይይት
መርሃግብሮች ይኖሩታል።

ምንጫችን:- ELU
@YeneTube @Fikerassefa