YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ኢትዮጵያውያን ወደ ተለያዩ #የአረብ ሀገራት ሄደው መስራት የሚከለክለው እገዳ ሙሉ በሙሉ #መነሳቱን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

📌ከሰባት ወራት በፊት እገዳው መነሳቱ ቢገለፅም መንግስት አስፈላጊውን ዝግጅት ባለማድረጉ ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቷል።

📌 ከመስከረም ወር መጨረሻ ጀምሮ ግን ዜጎች ወደ መረጡት ሀገር በህጋዊ መንገድ በመጓዝ መስራት ይችላሉ።

📌 እገዳው የተጣለው ከአምስት አመት በፊት ነበር።
ምንጭ ፦ የሰ/ማ/ጉዳይ ሚኒስቴር
@yenetube @mycase27
#ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጀርመን #ፍራንክፈርት ከተማ በአውሮፓ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ አባላት ጋር #ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ውይይት ያደርጋሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ #ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያደርጉት ጉብኝትና ውይይት “#አንድ_ሆነን_እንነሳ_ነገን_እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ሲሆን በውይይቱ ከ20 እስከ 25 ሺህ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉብኝቱ ሁሉም #ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን በፍቅር እንዲገነቡ የሚያስችል በመሆኑ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ #የሚደረገው ጉብኝትና ውይይት ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲና በውጭ ግንኙነት ላይ የሚሰራው ስራ አካል እንደሆነ ተገልጿል።

ቃል አቀባዩ ይህ ኢትዮጵያውያን እንደ አንድ ቤተሰብ በሚያገናኘው የፍራንክፈርት ውይይት ስኬታማ እንዲሆን በአገር ውስጥም ከአገር ውጪም አስፈላጊው #ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ምንጭ ፦ ኢዜአ
@yenetube @mycase27
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት #ጀርመን በርሊን ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በርሊን ሲደርሱም የሀገሪቱ ባለስልጣናት እና በበርሊን የሚኖሩ #ኢትዮጵያውያን አቀባበል አድርገውላቸዋል
@yenetube @mycase27
#ግብፅ የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለእንግልት እና ለዘፈቀደ እስር እየተዳረጉ መሆኑን ገለጹ
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ውጥረት ተባብሶ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በግብፅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለዘፈቀደ እስርና እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ገለጹ።

በግብፅ የሚገኙ የማህበረሰብ መሪዎች እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለፁት እነዚህ ስደተኞቹ የገንዘብ ብዝበዛ፣ እንግልት፣ የዘፈቀደ እስራት እና ጥቃቶችን ጨምሮ ለበርካታ ችግሮች እየተዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም “በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ስደተኛ ተብለው እውቅና የተሰጣቸው እና እንደ ነጭ ካርድ፣ ቢጫ ካርድ እና የጥገኝነት ጠያቂዎች የመመዝገቢያ ካርድ ያሉ የተለያዩ መታወቂያ ካርዶችን የያዙ ስደተኞች ሳይቀሩ በግብፅ ለተለያዩ ፈተናዎችን መዳረጋቸው ቀጥሏል” ብለዋል።

አዲስ ስታንዳርድ
@Yenetube @Fikerassefa
👍26😭14
በደቡብ አፍሪካ 44 #ኢትዮጵያውያን አንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው መገኘታቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ

በደቡብ አፍሪካ #ጁሃንስበርግ 44 ኢትዮጵያውያን አንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው መገኘታቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ።

በጁሃንስበርግ በአንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ናቸው የተባሉት 44ቱ ኢትዮጵያውያኑ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ደቡብ አፍሪካ የገቡ ሳይሆኑ አልቀሩም ሲል ፖሊስ ገልጿል።

ትላንት ሚያዚያ 23 ቀን 2017 ሰባት ሰአት ተኩል አከባቢ በአንድ ቤት ግቢ ውስጥ አጠራጣሪ ድምጽ በመሰማቱ ፖሊስ ኦፐሬሽኑን ማካሄዱን የሀገሪቱ ጋዜጣ ኒውስ 24 ተመለከትኩት ያለውን የጆሃንስበርግ ፖሊስ ሪፖርት ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

የከተማዋ ፖሊሶች ወደ ቤቱ ቅጥር ግቡ በመግባት ፍተሻ ሲያደርጉ በሁለት ክፍል ውስጥ 44 ኢትዮጵያውያኑ ተቆልፎባቸው መገኘታቸውን ዘገባው አመላክቷል።

አንዱ ብቻ በተሰባበረ እንግሊዝኝ ከፖሊሶች ጋር ለመነጋገር መሞከሩን የጠቆመው ዘገባው ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለፖሊስ መግለጹን አስታውቋል።

በግቢው ውስጥ የነበረው ሁኔታ አስከፊ መሆኑን ፖሊስ በሪፖርቱ አመላክቷል ያለው ዘገባው ኢትዮጵያውያኑ በቂ ምግብ እንዳልቀረበላቸው፣ ከተቆለፈባቸው ክፍል እንዳይወጡ መደረጋቸውና የፀሃይ ብርሃን አይተው እንደማያውቁ እንዲሁም ደህና ልብስ እንኳ እንደሌላቸው አስታውቋል።

ባሳለፍነው አመት 2016 ዓ.ም ሐምሌ ወር ላይ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ “ኢ-ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ” ታጋተው የነበሩ ናቸው ያላቸው 90 ኢትዮጵያውያንን አስለቅቂያለሁ ሲል መግለጹን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።
@Yenetube @Fikerassefa
😭30👍245