YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ የጀመረውን ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ ሲባል ለጊዜው አገልግሎት እንዳይሰጡ ያገዳቸው ዘርፎችን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት የግል ኢንዱስትሪ አልሚዎች የመሬት ጥያቄ፣ የሰነድ አልባ እና አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ የተያዙ ይዞታዎች መስተንግዶ፣ መሬት ያልተረከቡ የመኖሪያ ቤት ማህበራት መስተንግዶ አገልግሎቶች የቅድመ ማጣራት ስራ እስኪጠናቀቅ ድረስ በአነዚህ ዘርፎች ላይ ማንኛውንም ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
#የአዲስ አበባ ድጋፍ ሠጪ ታክሲዎች ዛሬ ሥራ ማቆም አድማ አደረጉ፡፡

ከመንግስት የተሰጣቸው ስምሪት ፍትሐዊ ባለመሆኑ አድማውን ማድረጋቸውን ባለመኪናዎችና ሾፌሮች አስረድተዋል፤ አንዳንድ መስመሮች በሕገ ወጥ መንገድ ለተወሰኑ ግለሰቦች እንደሚለሰጥ፣ ለመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ተቆጣጣሪዎች የሚሰጡት ጉቦ እጅግ ስላስመረራቸው አድማ በማድረግ ተቃውሞ ለማሰማት መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች ለመንግስት ሚዲያዎች በሰጡት ማብራሪያ …በአንዳንድ ቦታ አድማ ቢደረግም የትራንስፖርት እጥረት እንዳላስከተለ፣ በሸገር ባስ ጉድለቱን መሸፈናቸውን ነው የተናገሩት።

@yenetube @mycase27
#የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ #ኢንጂነር ታከለ ኡማ በኦነግ አመራሮች አቀባበል #ስነ ስርዓት ላይ #ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች:-

▪️ አሁን አገራችን ውስጥ ለመጣው ለውጥ በርካታ ዜጎች መስዋዕትነት ከፍላውበታል፡፡

▪️ የኦሮሞ ቄሮዎች ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ወንድማዊነታቸውን እያሳዩ ነው

▪️ ጀግኖች አባቶቻችን ሞተው ያወረሱንን አገር ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ መረባረብ አለብን

▪️ አሁን ተባብረን፣ ተደማምጠን በጋራ የአገራን ግንባታ ላይ የምንረባረብበት ምዕራፍ ላይ ደርሰናል

▪️ በዚህ ከቀጠልን ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እናበረክታለን

▪️የገዳ ስርዓት ሁሉንም የሚያቅፍ ስርዓት ስለሆነ በጋራ ለአገር ግንባታ መስራት አለብን

▪️ የአዲስ አበባ ወጣቶች ለኦነግ አመራሮች አቀባበል ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ከልብ አመሰግናለሁ

▪️ አሁን ለመጣው ለውጥ ሁላችንም አሸናፊዎች ነን
©ebc
@yenetube @mycase27
#የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አማርኛና አፋን ኦሮሞን በመንግስት ትምህርት ቤቶች #አማራጭ የትምህርት መስጫ ቋንቋ አድርጎ ለመጠቀም መወሰኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር #ታቦር ገ/መድህን ገለጹ።
ምንጭ ፦የአ/አ/ት/ቢሮ
@yenetube @mycase27
#የአዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር  በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን #ማህበረሰቡ ጥቆማ በማደርግ  እንዲተባባር ጥያቄ #አቅርቧል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዘመናት የተከማቹ ብልሹ አሰራሮችን ለማረም ስራ መጀመሩን አስታውቋል።

መስተዳድሩ ባለፈዉ ሳምንትም በመዲናዋ ያለ ልማት ለብዙ  ዓመታት  ታጥረው የቆዩ 154 ቦታዎች 4 ሚሊየን በላይ ካሬ ሜትር መሬት የሊዝ ውላቸው ተቋርጦ ለህዝብ ጥቅም ተመላሽ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ከዚህ በመቀጠልም በህገወጥ መንገድ የተያዙ የጋራ በመኖሪያ ቤቶችን ኦዲት እንደሚያደርግ ያስታወቀዉ መስተዳድሩ ፥ሥራዉ የተሳካ እንዲሆንም ማህበረሰቡ ጥቆማ እንዲያቀርብ ጠይቋል።

በዚህ መሰረትም በስማቸዉ የመኖሪያ ቤት ኖሯቸዉ በህገ ወጥ መንገድ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የያዙ እና የወሰዱ አካላትን ነዋሪዎች እንዲያጋልጡ ተጠይቋል።
©fbc
@yenetube @mycase27
ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከመንገድ ላይና #ከተለያዩ ቦታዎች ተይዘው (ታፍሰው) በጦላይ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፕ የታሰሩ ከአንድ ሺሕ በላይ የሚሆኑ #የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ዜጎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲለቀቁ፣ ወይም የፈጸሙት ወንጀል በሕግ ዕውቅና ያለው ከሆነ ክስ እንዲመሠረትባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ፡፡ #AddisAbaba

የሪፓርተር ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ ⤵️
https://goo.gl/apTC7S
@YeneTube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወደነበረበት የሚመልስ ረቂቅ ዕቅድ ተዘጋጀ⤵️

ለመጀመርያ ጊዜ በአዲስ አበባ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ይቋቋማል

በግንቦት 1997 ዓ.ም. ከተካሄደው ምርጫ በኋላ በተፈጠረው ቀውስ ወደ ፌዴራል መንግሥት የተዘዋወረውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ወደ ከተማው አስተዳደር መመለስ የሚያስችል ረቂቅ ዕቅድ ተዘጋጀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረጃጀትና መዋቅር ጥናት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ባካሄደው ጥናት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የራሱ የሆነ አዲስ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እንዲመሠርት ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ባከናወነው ጥናት ላይ የመጀመርያ ዙር ውይይት ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ወቅት በቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ›› የተሰኘ አዲስ የካቢኔ አባል የሚሆን ተቋም እንዲመሠረት ሐሳብ ቀርቧል፡፡

ይህ አዲስ ተቋም ላለፉት 14 ዓመታትአስተዳደር በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሥር ሆኖ የቆየውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በድጋሚ ወደ ከተማው በመመለስ፣ የከተማውን ደንብ ማስከበር አገልግሎትና በክፍለ ከተማና በወረዳ የሚቋቋሙትን የፀጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶችን አቅፎ ይይዛል፡፡

#የአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታና ቢሮ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለከተማ #አስተዳደሩ ከንቲባ ይሆናል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረጃጀትና መዋቅር ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰይፈ ፍቃዱ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የተዘጋጀው ጥናት ለካቢኔ ቀርቦ ይሁንታ ካገኘ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቀርቦ ሲፀድቅ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

📌#በቀረበው ረቂቅ ጥናት ላይ #በሕገ_መንግሥቱ_አንቀጽ_49_ንዑስ_አንቀጽ_2_እና_በቻርተሩ_95_አንቀጽ_10_መሠረት፣ አዲስ አበባ ከተማ ራሱን የማስተዳደር #መብት አለው፡፡

📌‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ይኖረዋል፣ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፤›› ሲል ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ደንግጓል፡፡

ረቂቅ ጥናቱን ያቀረቡት የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ቤተ ማርያም መኮንን እንዳሉት፣ አዲስ አበባ ከተማ እስካሁን የራሱ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የለውም፡፡

‹‹ራሱን የቻለ የፀጥታ መዋቅር ባለመኖሩ የከተማውን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት ባደረገ መንገድ ባለመደራጀቱ፣ የፀጥታ ተቋማቱ በተለያየ መዋቅር እንዲመሩ ሆኗል፤›› በማለት የገለጹት አቶ ቤተ ማርያም፣ ‹‹አዲስ የፀጥታ አስተዳደር መዋቅር ተግባራዊ ሲሆን ይህ ችግር ይፈታል፤›› ብለዋል፡፡

በአዲሱ መዋቅር መሠረት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ የፀጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች፣ በማዕከል፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ ያሉ የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤቶች በቢሮው ሥር ይተዳደራሉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት የፍትሕ፣ የፀጥታ፣ የሰላም፣ የመልካም አስተዳደርና የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች መነሳታቸውን ያስታወሱት ደግሞ፣ የከተማው ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ኤፍሬም ግዛው ናቸው፡፡

ከነዋሪዎች የሚነሱትን እነዚህን ችግሮች ለመፍታት፣ የከተማውን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ አዲሱ መዋቅር ወሳኝ ድርሻ እንዳለው አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡

ይህ ጥናት እንዲካሄድ መመርያ የሰጠው የከተማ አስተዳደር ካቢኔ በመሆኑ፣ በሒደት ላይ ያሉ ሥራዎች ሲጠናቀቁ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
#የአዲስ አበባን የልማት እቅዶች ለማሳካት በየደረጃው ያለው ሰራተኛ ሃለፊነቱን መወጣት እንዳለበት የከተማዋ አስተዳደር #አሳሰበ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ ኡማ እንደገለጹት፥ አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ በኩል እየተደረገ ያለውን የልማት ሩጫ ለማሳካት በየደረጃው ያለውን ሰራተኛ ንቁ ተሳትፎ ይጠይቃል።

በ2011 በጀት አመት የቢሮና የሴክተር ተቋማት የሩብ አመት የስራ አፈፃፀም እቅድ ግምገማ ውይይት ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባው፥ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ውጤቶችን እውን ለማድረግ ከአመራሩ ብቻ ሳይሆን በየደረጃው ካለው ሰራተኛ ንቁ ተሳትፎ እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት።

ለዚህም የልማት እቅዶችን እስከታችኛው የመንግስት መዋቅር ድርስ በማውረድ በሰራተኛው ዘንድ በማስረጽና በመንግስትና በከተማ አስተዳደሩ በኩል እየተደረገ ያለውን የልማት ሩጫ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያለውን ሰራተኛ በንቃት በማሳተፍ ፍጥነቱን አስጠብቆ ማስኬድ እንደሚገባም አመልክተዋል።
©FBC
@yenetube @mycase27
#​የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ከአገልግሎት አሰጣጥና ህግና ደንብ ጥሰት ጋር በተያያዘ 18 ሰራተኞችን ከስራ #ማሰናበቱን ገለጸ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ #ሺሰማ ገብረስላሴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፥ ደንበኞችን የማያከብሩ፣ መድሎ የሚፈጽሙና የስነ ምግባር ችግር የታየባቸው 18 ሰራተኞች ከስራ ተሰናብተዋል፣ 102 ያህሉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል፣ 15 ያህሉ ከደረጃና ደሞዝ ዝቅ እንዲሉ #ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
©ኤፍ.ቢ.ሲ
@yenetube @mycase27
#update የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት #ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገለጸ

ከ42 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ቢሮ #አስታወቀ፡፡

ቢሮው በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱን ያራዘመው አዲስ ሶፍትዌር እየተዘጋጀ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኢንጅነር #ዘሪሁን አምደ ማሪያም ዕጣው ከዚህ ቀደም ጥቅምት 30 እንዲወጣ መርሃግብር መያዙን ጠቅሰው አሁን በሶፍትዌሩ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜያት መራዘሙን ገልጸዋል።

ከአሁን በፊት ዕጣው የሚወጣበት ሶፍትዌር ማሽን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ስር እንደነበረ የተነገረ ሲሆን ይህ ደግሞ የህጋዊነትና የፍትሃዊነት ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ ሶፍትዌር ማሽኑ ቤቱን መገንባትና ማስተዳደር በአዋጅ በተሰጠው የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ስር እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ #መወሰኑም ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም የ40/60 ቁጠባ ቤቶቹን ተረክቦ የማስተላለፍ ኃላፊነት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስረ የነበረ ሲሆን ይህ አሰራርም ተገቢ ባለመሆኑ ውሉ ተቋርጦ ቤቶቹን የሚገነባው #የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮ እንዲያስተላልፍ ተደርጓል በማለትም ኃላፊው ገልፀዋል።

ለዕጣው መዘግየትም እነዚህ ምክንያቶች ዋነኞቹ በመሆናቸው፥ በቅርብ ተስተካክሎ ባለ ዕድለኞች የቤት ባለቤት እንደሚሆኑ አሳስበዋል።

ቢሮው በበጀት ዓመቱ 132ሺ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ የያዘ ሲሆን በቅርብ ለባለ ዕድለኞች ይተላለፋሉ የተባሉት ከ42 ሺህ በላይ እንደሆኑም ኃላፊው አብራርተዋል።
ምንጭ ፦ኤፍ ቢ ሲ
@yenetube @mycase27
ሰልፉን አስመልክቶ‼️

# እሁድ ታህሳስ 7/4/2011ዓም ከጠዋቱ3 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ታህሳስ 14 ዞሯል፡፡

#የአዲስ አበባ ፖሊስ የፀጥታ ሃይል እጥረት ስላለብኝ አራዝሙት ባለው መሰረት ዛሬ ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሕዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል አስተዳደር አቶ ተስፉ ዋቅጅራ ጋር በመነጋገር ለታህሳስ 14 ለቀጣይ ሳምንት እንዲሆን የጋራ መግባባት ተደርሷል የፊታችን ሰኞ ለሚቀጥለው # ታህሳስ14 ሰላማዊ ሰልፍ የከተማው አስተዳደር ደብዳቤ ይሰጣል።

ምንጭ:- ስንታየሁ ቸኮል አስተባባሪ ኮሚቴው
@YeneTube @Fikerassefa
ዶ/ር ጌታቸው የካፕቴን ያሬድ (ትላንት የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ) አባት የልጁን ህይወት ማለፍ ዜና ሲሳሙ #ስትሮክ አጋጥሟቸው #ሆስፒታል መግባታቸውን #የአዲስ_ፎርቹን ጋዜጠኛ ዳዊት እንደሻው ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ #ግጭት ጉዳት ደረሰ። ግጭቱ የተፈጠረው የኦሮሞ ተማሪዎች #የአዲስ_አበባ ባለቤትነት እንዲሁም #ኦሮምኛ የፌድራል የስራ ቋንቋ እንዲሆን በመጠየቅ ተቃውሞ ማሰማት መጀራቸውን ተከትሎ ነው።

-ELU
@YeneTube @FikerAssefa