#በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ በደረሱ ጥቃቶች #44 ሰዎች መገደላቸውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት #አስታወቀ።
የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችልም ገልጿል።
በሁለቱ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢው አሁንም ጥቃት አለመቆሙን እና ቤቶች እየተቃጠሉ እንዳሉ ለDW እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ኃላፊ አቶ ዘላለም ጃለታ ለ«DW» እንደተናገሩት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ በደረሰ ጥቃት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ 16 ሰዎች ከኦሮሚያ ደግሞ 28 ሰዎች መገደላቸውን #ተናግረዋል።
ባለፈው ረቡዕ መስከረም 16 አራት የካማሺ ዞን አመራሮች መገደላቸውን ተከትሎ በአካባቢው በተቀሰቀሰ ግጭት ምክንያት በክልላቸው ብቻ 20 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በሰሞኑ ግጭት 70 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
ይህንን መረጃ መመልከታቸውን የተናገሩት አቶ ዘላለም ሰዎቹ የተፈናቀሉት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል #ብቻ ሳይሆን በወሰን አካባቢ ካሉ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ጭምር ነው ብለዋል።
በሰሞኑ ግጭት ቀያቸውን ለቅቀው “ወደ በረሃ መሸሻቸውን” የሚናገሩ አንድ ተፈናቃይ በአካባቢያቸው አሁንም ግጭቱ መቀጠሉን ለDW ተናግረዋል።
ከነቀምት ከተማ 42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለች አንገር በተሰኘች አነስተኛ መንደር ነዋሪ እንደሆኑ የተናገሩት አቶ ኤርሚያስ አበራ ከአምስት ቀን በፊት የተኩስ #ድምጽ ሲሰሙ እና ቤቶች መቃጠል ሲጀምሩ ህይወታቸውን ለማትረፍ መሸሻቸውን ገልጸዋል። በአካባቢያቸው ከስምንት እስከ 10 ሰው እንደሞተ መስማታቸውን እና ደብዛቸው እስካሁን ያልታወቀ እንዳለም ጠቁመዋል።
በመኖሪያ መንደራቸው ያለው ሁኔታ መሻሻሉን ለማየት ዛሬ ወደ ስፍራው የሄዱት አቶ አበራ ቤቶች ሲቃጠሉ እንደተመለከቱ የዓይን እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። ። በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊት ቢሰማራም ጥቃቱ አለመቆሙንም አስረድተዋል።
በአንገር እና አካባቢው ያለው ጥቃት አሁንም መቀጠሉን ያረጋገጡት አቶ ዘላለም ጉዳዩ ከክልሉ አቅም በላይ በመሆኑ ተጨማሪ የመከላከያ ኃይል ወደ ስፍራው እንዲገባ መጠየቁን #ገልጸዋል።
ምንጭ ፦ DW
@yenetube @mycase27

#update የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (#ኦብነግ) ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስለተደረሰው #ስምምነት የሰጠው አስተያየት የስምምነቱን መንፈስ የሚያንፀባርቅ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ መንግስት #አስታወቀ።
ድርድሩን በቅርበት የሚያውቁና ስማቸውን ይፋዊ መግለጫ እስኪሰጥ የሸሸጉ የመንግስት ተወካይ #ለዋዜማ እንደተናገሩት ስምምነቱ ኦብነግ ወደሰላማዊ ትግል እንዲመለስና ጥያቄዎቹን በጋራ በሚቋቋም ኮሚቴ እያቀረበ እንዲፈታ ከሚል ውጪ ትርጉም ያለው አልነበረም።
በኦብነግ በኩል የሚሰጠው አስተያየት ለፕሮፓጋንዳ #ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር የውይይቱን መንፈስ አያሳይም ብለዋል ባለስልጣኑ።
ኦብነግ መንግስት የእስከ መገንጠል መብታችንን በህዝበ ውሳኔ እንድናረጋግጥ ተስማምቷል ሲል ለቢቢሲ መግለጫ ሰጥቶ #ነበረ።
ቢቢሲ ዘግይቶ ባወጣው #ማረሚያ " ቀደም ሲል በወጣው ዘገባ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ጋር ካደረገው ተከታታይ ውይይት በኋላ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ተስማምቷል ተብሎ የተፃፈው #ስህተት ነው" ብሏል::
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ

#update የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት #ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገለጸ
ከ42 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ቢሮ #አስታወቀ፡፡
ቢሮው በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱን ያራዘመው አዲስ ሶፍትዌር እየተዘጋጀ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኢንጅነር #ዘሪሁን አምደ ማሪያም ዕጣው ከዚህ ቀደም ጥቅምት 30 እንዲወጣ መርሃግብር መያዙን ጠቅሰው አሁን በሶፍትዌሩ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜያት መራዘሙን ገልጸዋል።
ከአሁን በፊት ዕጣው የሚወጣበት ሶፍትዌር ማሽን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ስር እንደነበረ የተነገረ ሲሆን ይህ ደግሞ የህጋዊነትና የፍትሃዊነት ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ ሶፍትዌር ማሽኑ ቤቱን መገንባትና ማስተዳደር በአዋጅ በተሰጠው የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ስር እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ #መወሰኑም ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም የ40/60 ቁጠባ ቤቶቹን ተረክቦ የማስተላለፍ ኃላፊነት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስረ የነበረ ሲሆን ይህ አሰራርም ተገቢ ባለመሆኑ ውሉ ተቋርጦ ቤቶቹን የሚገነባው #የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮ እንዲያስተላልፍ ተደርጓል በማለትም ኃላፊው ገልፀዋል።
ለዕጣው መዘግየትም እነዚህ ምክንያቶች ዋነኞቹ በመሆናቸው፥ በቅርብ ተስተካክሎ ባለ ዕድለኞች የቤት ባለቤት እንደሚሆኑ አሳስበዋል።
ቢሮው በበጀት ዓመቱ 132ሺ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ የያዘ ሲሆን በቅርብ ለባለ ዕድለኞች ይተላለፋሉ የተባሉት ከ42 ሺህ በላይ እንደሆኑም ኃላፊው አብራርተዋል።
ምንጭ ፦ኤፍ ቢ ሲ