YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#​የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ከአገልግሎት አሰጣጥና ህግና ደንብ ጥሰት ጋር በተያያዘ 18 ሰራተኞችን ከስራ #ማሰናበቱን ገለጸ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ #ሺሰማ ገብረስላሴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፥ ደንበኞችን የማያከብሩ፣ መድሎ የሚፈጽሙና የስነ ምግባር ችግር የታየባቸው 18 ሰራተኞች ከስራ ተሰናብተዋል፣ 102 ያህሉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል፣ 15 ያህሉ ከደረጃና ደሞዝ ዝቅ እንዲሉ #ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።
©ኤፍ.ቢ.ሲ
@yenetube @mycase27
የ40/60 ክስ

ዛሬ የዋለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ፍ/ብሄር ችሎት የ40/60 እቤት እድለኞች(61ሰዎች) ባቀረቡት የጣልቃ መግባት አቤቱታ ላይ በከሳሽ ወገን ሆነው ጣልቃ እንግባ የሚል አቤቱታ ባቀረቡ ሰዎች አቤቱታ ላይና በ3ኛ ተከሳሽ (የአዲስ አበባ ከተማ የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ) የእግድ ይነሳልኝ (ወይም የኪሳራ ገንዘብ ከሳሾች ያስይዙልኝ) አቤቱታ ተመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

#ውሳኔ_1. በ98 ሰዎች (መቶ ፐርሰንት የከፈሉ ተመስጋቢዎች) ክስ የ2ኛ ዙር የ40/60 እድለኞች ላይ የተጣለው እግድ እንዲነሳ ተወስኗል። ነገር ግን በ98 ከሳሾች ልክ 98 ቤቶች ብቻ ታግደው እንዲቆዮ ተወስኗል።

#ውሳኔ_2. በ61 (የ2ኛ ዙር የ40/60 እድለኞች) በክሱ ጣልቃ የእንግባ ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል

#ውሳኔ_3. ሌሎች በከሳሽ ወገን የጣልቃ እንግባ ጥያቄን ውድቅ አድርጓል

#ውሳኔ_4. የከሳሽ ክስ የማሻሻል ጥያቄን ተቀብሏል

Via Housing in Addis Ababa
@YeneTube @FikerAssefa