YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ነገ በአዲስ አበባ የሚጠበቀው የኦነግ አቀባበል ካለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ በከተማ ደረጃ ምን ያህል በቂ ዝግጅት እንደተደረገ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር #ታከለ ኡማ ከሚመለከታቸው አከላት ጋር #እየተወያዩ ነው ።

ከ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን፣ ከፀጥታና ደህንነት፣ ከአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር እና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።
©ebc
@yenetube @mycase27
በምክትል ከንቲባነት የአዲስ አበባ ከተማን ማስተዳደር ከጀመሩ ሦስተኛ ወራቸው ላይ የሚገኙት #ታከለ (ኢንጂነር)፣ በቆይታቸው ወቅት ከመሬት ጋር በተያያዘ የገጠማቸውን የተከማቸ ዝርክርክነት ‹‹ጉድ ነው›› ሲሉ
ይገልጹታል፡፡

#addisababa #Ethiopia

የሪፓርተር ዘገባን ሙሉውን ያንብቡ
➡️ https://t.co/rqa4O8GY6s ⬅️
@YeneTube @Fikerassefa
​ም/ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ ኡማ ከ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወጣቶች ጋር እየተወያዩ ነው።

ምክትል ከንቲባው ከአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ጋር በመሆን በቂርቆስ ክፍለከተማ በመዲናዋ አስተዳደሩ በጀመራቸው የለውጥ እና የህዝብ ተሳትፎ ስራዎች ላይ ከወጣቶች ጋር ምክክር እያደረጉ ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚያደርጉት ይህ ውይይትም 4ኛው #መድረክ ነው።

የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ፣ፍትሀዊ ተጠቃሚነት፣የመልካም አስተዳደር ፣የመኖሪያ ቤት ችግር፣የወጣት ማእከላት እጥረት እንዲሁም ሌሎች በከተማዋ እየተከናወኑ ባሉ የለውጥ ስራዎች ዙሪያ ምክክር #እየተደረገ ነው።

ምንጭ፡- የአ/አ ከንቲባ ጽ/ቤት
@yenetube @mycase27
#የአዲስ አበባን የልማት እቅዶች ለማሳካት በየደረጃው ያለው ሰራተኛ ሃለፊነቱን መወጣት እንዳለበት የከተማዋ አስተዳደር #አሳሰበ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ ኡማ እንደገለጹት፥ አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ በኩል እየተደረገ ያለውን የልማት ሩጫ ለማሳካት በየደረጃው ያለውን ሰራተኛ ንቁ ተሳትፎ ይጠይቃል።

በ2011 በጀት አመት የቢሮና የሴክተር ተቋማት የሩብ አመት የስራ አፈፃፀም እቅድ ግምገማ ውይይት ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባው፥ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ውጤቶችን እውን ለማድረግ ከአመራሩ ብቻ ሳይሆን በየደረጃው ካለው ሰራተኛ ንቁ ተሳትፎ እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት።

ለዚህም የልማት እቅዶችን እስከታችኛው የመንግስት መዋቅር ድርስ በማውረድ በሰራተኛው ዘንድ በማስረጽና በመንግስትና በከተማ አስተዳደሩ በኩል እየተደረገ ያለውን የልማት ሩጫ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያለውን ሰራተኛ በንቃት በማሳተፍ ፍጥነቱን አስጠብቆ ማስኬድ እንደሚገባም አመልክተዋል።
©FBC
@yenetube @mycase27
​ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር #ታከለ ኡማ የእስራኤል አምባሳደር ራልፍ ማሮቭን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

በውይይታቸውም በቴክኖሎጂ #ሽግግር#በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፣ #በቱሪዝም እድገት ዙሪያ አብሮ ለመስራት #መክረዋል፡፡

አምባሰደር ራልፍ በናኖ ቴክኖሎጂና በጠብታ መስኖ ሀገራቸው ያላትን ልምድ ማካፈል እንደሚፈልጉ ለምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ ፦ ከንቲባ ጽ/ቤት
@yenetube @mycase27
News‼️ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች ዛሬ ከኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ባንቲ ጋር በኦዲቶሪየም አዳራሽ ሰብሰባ እንደሚያደርጉ መረጃዎች ጠቁመዋል።

የኔቲዩብ ከቦታው እየተከታተለሽ ታደርሳለች አብራችሁን ቆዩ!!
@YeneTube @Fikerassefa
#የሃሳብ_ልዩነት መጨረሻ #የሰከነ_ውይይት ሊሆን ይገባል‼️

ዛሬ ከአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ጋር ፍሬያማ የሆነ ውይይት አድርገናል። ባለፈው ካወጣሁት ፅሁፍ ጋር በተያያዘ ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ግልፅ የሆነ ውይይት አድርገናል። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሃሳብና አስተያየቴን በነፃነት መግለፄን በማድነቅ አበረታተውኛል።

በቀጣይም በከተማ መስተዳደሩ ሆነ በሌሎች የመንግስት አካላት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመንቀስና በመተቸት ትኩረት እንዲያገኙና ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የጀመርኩትን ጥረት አጠናክሬ እንድቀጥል መክረውኛል። እኔ በበኩሌ የከንቲባው የመኖሪያ ቤት ኪራይን ጨምሮ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚነሱ ጥያቄዎችን በማንሳት ጠቃሚ ውይይት አድርገናል። ለወደፊት ማንኛውም ዓይነት ጥያቄና አስተያየት ሲኖረኝ በስልክ ሆነ በአካል ተገኝቼ መረጃና ማብራሪያ መጠየቅ እንደምችል አረጋግጠውልኛል።

የሃሳብና አመለካከት ነፃነትን አክብሮ በቀናነት የመወያየት ልማድ በሁሉም ዘንድ ሊዘወተር የሚገባ ነገር ነው። የተለየ ሃሳብና አስተያየት በሰጠሁ ቁጥር በሰከነ መንገድ ከመወያየትና ሃሳብ ከመለዋወጥ ይልቅ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያዘንቡ ለሚውሉ ጭፍን ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ይሄ ጥሩ ማሳያ ነው። የሃሳብ ልዩነት መጨረሻ የሰከነ ውይይት እንጂ ዛቻና ማስፈራራት መሆን የለበትም።

ምንጭ:- ስዩም ተሾመ
@YeneTube @FikerAssefa
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ አባቶቼ፣ እናቶቼ፣ ወንድሞቼና እህቶቼ እንኳን ለተከበረው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ።
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ

ይህ ወር የመንፈሳዊነት ልእልናን የምትጎናፀፉበት፣ የበረከት፣ የእዝነትና የመጣብን መከራ የሚያልፍበት ወር እንዲሆን እመኛለሁ።

ታላቁ የረመዳን ወር የመረዳዳት፣የመተዛዘን እና የመተሳሰብ ወር ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወቅት ደግሞ መረዳዳት እጅግ የሚያስፈልግበት ወቅት በመሆኑ እንደዚህ ቀደሙ የረመዳን ወር የመረዳዳት ባህላችሁና ልምዳችሁ ከፍ ብሎ ይታይ ዘንድ አደራ እላለው፡፡

ውድ የሀገሬ ልጆች የመጣብንን መከራ እንድናልፍ ጥንቃቄ ሳይለየን፣ መመሪያዎችን ተግባራዊ እያደረግን ያለንን እያጋራን በአካላዊ መራራቅ ውስጥ የአብሮነትና ኣንድነት መንፈስን እያዳበርን እንድናሳልፈው ለማስታወስ እወዳለሁ።

መልካም የረመዳን ወር!
ፈጣሪ ሀገራችንና ህዝቦቿን ይባርክ!

Via:- ኢንጂነር ታከለ ኡማ
@Yenetube @Fikerassefa