#update የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት #ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገለጸ
ከ42 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ቢሮ #አስታወቀ፡፡
ቢሮው በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱን ያራዘመው አዲስ ሶፍትዌር እየተዘጋጀ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኢንጅነር #ዘሪሁን አምደ ማሪያም ዕጣው ከዚህ ቀደም ጥቅምት 30 እንዲወጣ መርሃግብር መያዙን ጠቅሰው አሁን በሶፍትዌሩ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜያት መራዘሙን ገልጸዋል።
ከአሁን በፊት ዕጣው የሚወጣበት ሶፍትዌር ማሽን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ስር እንደነበረ የተነገረ ሲሆን ይህ ደግሞ የህጋዊነትና የፍትሃዊነት ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ ሶፍትዌር ማሽኑ ቤቱን መገንባትና ማስተዳደር በአዋጅ በተሰጠው የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ስር እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ #መወሰኑም ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም የ40/60 ቁጠባ ቤቶቹን ተረክቦ የማስተላለፍ ኃላፊነት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስረ የነበረ ሲሆን ይህ አሰራርም ተገቢ ባለመሆኑ ውሉ ተቋርጦ ቤቶቹን የሚገነባው #የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮ እንዲያስተላልፍ ተደርጓል በማለትም ኃላፊው ገልፀዋል።
ለዕጣው መዘግየትም እነዚህ ምክንያቶች ዋነኞቹ በመሆናቸው፥ በቅርብ ተስተካክሎ ባለ ዕድለኞች የቤት ባለቤት እንደሚሆኑ አሳስበዋል።
ቢሮው በበጀት ዓመቱ 132ሺ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ የያዘ ሲሆን በቅርብ ለባለ ዕድለኞች ይተላለፋሉ የተባሉት ከ42 ሺህ በላይ እንደሆኑም ኃላፊው አብራርተዋል።
ምንጭ ፦ኤፍ ቢ ሲ
@yenetube @mycase27