YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የአዲስ አበባን የልማት እቅዶች ለማሳካት በየደረጃው ያለው ሰራተኛ ሃለፊነቱን መወጣት እንዳለበት የከተማዋ አስተዳደር #አሳሰበ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ ኡማ እንደገለጹት፥ አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ በኩል እየተደረገ ያለውን የልማት ሩጫ ለማሳካት በየደረጃው ያለውን ሰራተኛ ንቁ ተሳትፎ ይጠይቃል።

በ2011 በጀት አመት የቢሮና የሴክተር ተቋማት የሩብ አመት የስራ አፈፃፀም እቅድ ግምገማ ውይይት ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባው፥ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ውጤቶችን እውን ለማድረግ ከአመራሩ ብቻ ሳይሆን በየደረጃው ካለው ሰራተኛ ንቁ ተሳትፎ እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት።

ለዚህም የልማት እቅዶችን እስከታችኛው የመንግስት መዋቅር ድርስ በማውረድ በሰራተኛው ዘንድ በማስረጽና በመንግስትና በከተማ አስተዳደሩ በኩል እየተደረገ ያለውን የልማት ሩጫ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያለውን ሰራተኛ በንቃት በማሳተፍ ፍጥነቱን አስጠብቆ ማስኬድ እንደሚገባም አመልክተዋል።
©FBC
@yenetube @mycase27