YeneTube
120K subscribers
31.2K photos
480 videos
79 files
3.82K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአፍሪካ ኅብረት በህዳሴ ግድቡ የድርድር ውጤት ሪፖርት ላይ ነገ እንደሚመክር ይጠበቃል።

የአፍሪካ ኅብረት ጠቅላላ ጉባዔ ቢሮ በህዳሴ ግድቡ ድርድር ዙሪያ ሦስቱ ተደራዳሪ ወገኖች ስምምነት በደረሱባቸውና ባልተግባቡባቸው ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔውን ለማሳወቅ ነገ እንደሚሰበሰብ ይጠበቃል።

ይህ ስብሰባ በአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ እንደሚመራ የአፍሪካ ሕብረት በድረገጹ አስታውቋል።

በዚህ ስብሰባ ባሳለፍነው ሳምንት ያለ ስምምነት የተጠናቀቀው የህዳሴ ግድቡ የውኃ ሙሌትና አስተዳደር ድርድር አጠቃላይ ሪፖርትን እንደሚገመግም ተገልጿል።

የአፍሪካ ኅብረት ጠቅላላ ጉባዔ ቢሮ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ባካሄደው ስብሰባ ታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ግብፅና ሱዳን መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የአደራዳሪነት ሚናውን የአፍሪካ ኅብረት እንዲይዝ በወሰነው መሠረት፣ ሦስቱ አገሮች ለ11 ቀናት ሲደራደሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

በዚህ ድርድር ስምምነት የተደረሰባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም መሠረታዊ በሚባሉ ጥቂት ነጥቦች ላይ መቀራረብ ባለመቻላቸው ድርድሩ መቋረጡ አይዘነጋም።

በዚህም ምክንያት የድርድሩን አጠቃላይ ይዘትና የልዩነት ጭብጦችን ከእነ ምክንያቶቻቸውና የመፍትሔ ሐሳቦቻቸው፣ ሦስቱም አገሮች በተናጠል ለኅብረቱ ሪፖርት አቅርበዋል።

የአፍሪካ ኅብረትን በመወከል ድርድሩን የመሩት የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ተወካይና የኅብረቱ የባለሙያዎች ቡድን የጋራ ሪፖርትም፣ ለኅብረቱ ቀርበዋል።

የኅብረቱ ጠቅላላ ጉባዔም በነገው ስብሰባ የቀረቡትን ሪፖርቶች ገምግሞ፣ በቀጣይ አቅጣጫ ላይ ከሦስቱ አገሮች መሪዎች ጋር እንደሚወያይ ይጠበቃል።

#EthioFM

@YeneTube @FikerAssefa1
የኮሮና ቫይረስ ክትባት...

በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው የኮሮና ቫይረስ ክትባት በሰው ላይ ተሞክሮ መልካም ውጤት ማሳየቱ ተነገረ።

በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀው ይህ ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና የሰዎችን የበሽታ የመከላከል አቅም እንደሚያሻሽል መረጋገጡን ቢቢሲ ዘግቧል።

ክትባቱ ከፍ ባለ ሁኔታ ተስፋ ሰጭ ነው ያለው የቢቢሲ ዘገባ ቫይረሱን ለመከላከል በቂ መሆኑን ለማረጋገጥ ቀሪ ስራዎች እንዳሉ አስነብቧል፡፡

በመጀመሪያ ዙር በሰዎች ላይ በተካሄደው ሙከራ 1 ሺህ 77 ሰዎች ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡

መድሃኒቱ የሰዎችን የበሽታ ተከላካዩች (አንቲቦዲ) እና ነጭ የደም ህዋስ ማሳደጉ ተጠቁሟል።

ይህም ሰዎች የኮሮና ቫይረስን መከላከል እንዲችሉ ያደርጋል ነው የተባለው።

ብሪታኒያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራትም ChAdOx1 nCoV-19 የተሰኘው ክትባት እንዲቀርብላቸው ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ታውቋል።

#FBC

@YeneTube @FikerAssefa1
ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 56 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 304 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በቫይረሱ የተገኘባቸው ከአዲስ አበባ ከተማ 157፣ ከትግራይ ክልል 36፣ ከኦሮሚያ ክልል 46፣ ከጋምቤላ ክልል 26፣ ከአማራ ክልል 12፣ ከአፋር ክልል 17፣ ከሶማሌ ክልል 7፣ ከሐረሪ ክልል 2 እና ከደቡብ 1 ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ለ336 ሺህ 322 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 10 ሺህ 511 ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 173 ደርሷል፡፡

56 የኮሮና ቫይረስ ታካሚዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና መከታተያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉም ነው ያለው።

በተያያዘም 153 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም 5 ሺህ 290 ሰዎች በአጠቃላይ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኮቪድ 19...

በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ፍጥነት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ ህክምናዎች ዳይሬክተር ዶክተር ማይክ ረያን በሰጡት ማብራሪያ፥ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ስርጭት ፍጥነት እየጨመረ የመጣበት ጊዜ ላይ በመሆኑን በመጥቀስ ፤ ይህም እንደሚያሰጋቸው ነው ያስታወቁት።

እስከ ቅርብ ጊዜ በአፍሪካ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ጋር ሲነፃፀር እምብዛም እንዳልነበረ ነው የገለፁት።

በአፍሪካ እስካሁን 725 ሺህ ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፥ 15 ሺህ ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል፤ ይህም አፍሪካ በዓለም ላይ በቫይረሱ ዝቅተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ክፍለ አህጉሮች ከኦሽኒያ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።

ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የቫይረሱ ስርጭት አስጊ በሆነ ፍጥነት እየጨመረ የመጣ ሲሆን ፤ በተለይም በደቡብ አፍሪካ ያለው ስርጭትን እንደማሳያነት መነሳት ይችላል።

በደቡብ አፍሪካ ባሳለፍነው ቅዳሜ ብቻ በአንድ ቀን በ13 ሺህ 373 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይሰር የተገኘ ሲሆን፥ ይህም በዓለም ላይ በአንድ ቀን ከፍትኛ ቁጥር ካስመዘገቡ ሀገራት 4ኛ ደረጃን ያየዘ መሆኑ ተገልጿል።

በሀገሪቱ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ350 ሺህ የበለጠ ሲሆን ፤ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ5 ሺህ አልፏል ፤ ይህም በአፍሪካ ከፍተኛው ቁጥር መሆኑም ነው የተመላከተው።

በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም ባሳለፍነው ሳምንት በሀገሪቱ ያለው የስርጭት መጠን በ30 በመቶ ብቻ እንደጨመረም አመላክተዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት የቫይረሱ ስርጭት በኬንያ በ31 በመቶ፣ በማዳካስካር በ50 በመቶ፣ በዛምቢያ በ57 በመቶ እንዲሁም በናሚቢያ በ69 በመቶ መጨመሩንም አስታውቅዋል።

አሁን ላይ የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካ ምድር ላይ በከፍተኛ ፍጥነት የሚሰራጭበትን ጊዜ መመልከት እየጀመርን ነው ያሉት ዶክተር ማይክ ራያን፤ “ይህ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የማንቂያ ደውል ሊሆን ይገባል” ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።

#AlJazeera

@YeneTube @FikerAssefa1
የሸገር ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ በ400 ማከፋፈያዎች እየተሰራጨ እንደሚገኝ የፋብሪካዉ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሲሳይ ደበበ ገለፁ።

ፋብሪካው በዋነኛነት የዳቦ ዋጋን የህብረተሰቡን ገቢ ግንዛቤ ያስገባ እና አነስተኛ ዋጋ የማቅረብ አላማን ይዞ እንደመግባቱ ተደራሽነቱ ላይ በጥብቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በግብይት ሂደቱ ሰንሰለቱን በማሳጠር በመሀል የሚገባ ደላላን ለመከላከል በራሱ ተሽከርካሪዎች እያከፋፈለ ይገኛል ነው ያሉት ኢንጂነር ሲሳይ ደበበ።

በፋብሪካው የተመረተው ዳቦ በከተማዋ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በሆኑ በተመረጡ ቦታዎች በከተማ አስተዳደሩ በተደራጁ ወጣቶች አማካሽኝነት አቅርቦቱ ቀጥሏል ነው ያሉት።

የሸገር ዳቦ አሁን ላይ በቀን 600 መቶ ሺህ ዳቦ እያመረተ ለአዲስ አበባና አካባቢው ነዋሪዎች እያሰራጨ ሲሆን ፤ በቀጣይም በሙሉ አቅሙ ለማምረት እቅድ ስለመያዙ ገልጸዋል።

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ በቀጣይ እስከ 2 ሚሊየን ዳቦ በቀን የማምረት አቅሙን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑም ይታወቃል።

በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባውና በሰዓት 80 ሺህ ፤ በቀን እስከ 2 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርተው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ባሳለፍነው ሰኔ 18 2012 ዓ.ም በይፋ መመረቁ ይታወሳል።

#FBC

@YeneTube @FikerAssefa1
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በችግር ውስጥ የነበሩ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሽታው ከመከሰቱ ጊዜ አንስቶ በቤሩት በችግር ላይ የነበሩ 656፣ ከአቡዳቢ 72፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ 3 ሺህ 539፣ ከኩዌት 1 ሺህ 23 እንዲሁም በድንበር በኩል ደግሞ 24 ሺህ 797 ዜጎች በጠቅላላው 30 ሺህ 87 ዜጎች ወደ ሀገር ተመልሰዋል።

በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን በተመለተ በሀገሪቱ ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ያለውን የመረጃ እጥረት ለመፍታት እና ዜጎቻችን እርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት ኢትዮጵያ ከሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ጋር ንግግር መጀመሩን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው።

ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በሚገኙባቸው የተለያዩ የዓረብ ሀገራት መሰል ሥራዎች ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከኩዌት፣ ከተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች እና ከመሳሰሉት ሀገራት ጋር በትብብር መሰል ዜጎችን የመርዳት እና የማገዝ ሥራዎች በመሠራት ላይ እንደሚገኙም አክሏል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ተፅዕኖዎችን እያስከተለ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚገኙ ዜጎች ወረርሽኙን ተከትሎ እየደረሰባቸው ያሉ ችግሮች ተጠቃሽ ናቸው።

በዚህ ረገድ መንግሥት በተለያዩ የዓረብ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የመርዳት እና የማገዝ ሥራዎችን ኢትዮጵያዊያኑ ከሚገኙባቸው ሀገራት መንግሥታት፣ ቆንጽላ ጽ/ቤቶች፣ ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት እና ከረድኤት ድርጅቶች ጋር በተቀናጀ ሁኔታ እየሠራ ይገኛል።

በዋናነት በተለያዩ የዓረብ ሀገራት እና ጎረቤት ሀገራት በችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ቦታ መጠለያ፣ ምግብ፣ ሕክምና እና ሌሎች መሠረታዊ ግብዓቶች እንዲሟላላቸው ከማድረግ አንጻር ውጤታማ ሥራዎች መሠራታቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

የሊባኖስ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን ተከትሎ ከሥራ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን ለማገዝ በቤሩት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽ/ቤት፣ ከሀገሪቱ መንግሥት፣ ከኢትዮጵያዊን ኮሙዩኒቲ አባላት፣ ከዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ማለትም (IOM, ILO) ኢጋድ እንዲሁም ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማኅበር ጋር በጋራ በተሠሩ ሥራዎች በችግር ላይ ይገኙ የነበሩ ዜጎች እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ በአብነት ጠቅሷል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እስካሁን ለተገኙ ስኬቶች ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረጉ በተለያዩ ሀገርት ለሚገኙ የኮሙዩኒቲ አባላት፣ ኢትዮጵያዊያኑ ለሚገኙባቸው ሀገራት መንግሥታት፣ ለረድኤት ድርጅቶች፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየሠሩ ለሚገኙ የመንግሥት እና የግል ተቋማት እንዲሁም ለበጎ ፈቃደኞች ከፍተኛ ምስጋናውን አቅርቧል።

#EBC

@YeneTube @FikerAssefa1
ኮቪድ 19...

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 561 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ፣ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6 ሺህ 544 የላቦራቶሪ ምርመራ 561 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው እና የ7 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች በቦታ ሲለዩ፦
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 409፣
ከጋምቤላ ክልል 52፣
ከኦሮሚያ ክልል 25፣
ከትግራይ ክልል 16፣
ድሬደዋ 12፣
ደቡብ ክልል 11፣
ከሐረሪ ክልል 8
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 8
ሲዳማ ክልል 8
ከአማራ ክልል 6፣
ከሶማሌ ክልል 3 እና
ከአፋር ክልል 3 ናቸው።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 342 ሺህ 866 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 072 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ቁጥር 180 ደርሷል።

40 የኮሮና ቫይረስ ታካሚዎች ደግሞ በፅኑ ሕክምና መከታታያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለት 158 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 448 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የአፍሪቃ ህብረት ቢሮ አባል ሃገራት መሪዎች ኢትዮጵያና ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴ ግድብ ሰበብ የገጠሙትን ዉዝግብ ለማስወገድ የጀመሩትን ጥረት ዛሬ ቀጥለዉ ዉለዋል።

የቢሮዉ አባል ሃገራት መሪዎች የሦስቱ ሃገራት ባለስልጣናት ከአንድ ሳምንት በፊት በደረሱበት የዉይይት ዉጤት ላይ ዛሬ ሲነጋገሩ ነዉ የዋሉት።

የአፍሪቃ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪቃዉ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎዛ የሚመሩት ዉይይት በርቀት በቪዲዮ አማካኝነት ነዉ የተካሄደዉ።
የዉይይቱ ሂደትም ለጋዜጠኞች ለመገናኛ ዘዴዎች ዝግ ነዉ።

የአፍሪቃ ህብረት ቢሮ አባላት መሪዎች ከዚህ ቀደምም በአወዛጋቢዉ የህዳሴ ግድብ ላይ ለተከታታይ ቀናት ተወያይተዉ ነበር።

#DWAmharic

@YeneTube @FikerAssefa1
በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሲካሄድ የነበረው ድርድር በዓበይት ጉዳዮች ላይ በመስማማት መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ

በታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት እና ዓመታዊ የሥራ ክንውን ላይ ያተኮረውና ካለፈው የቀጠለው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ልዩ ስብሰባ ሐምሌ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የሚያደርጉትን ድርድር አጀንዳው ባደረገው ስብሰባ፣ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር በሆኑት ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ሰብሳቢነት መካሄዱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሦስቱ ሀገራት ልዩነቶቻቸውን አቻችለው ስምምነት ላይ ለመድረስ እንዲችሉ የአፍሪካ ኅብረት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን የማበጀት ሥራ አስቀድሞ በነበሩ ቀጣናዊ መፍትሔ ሰጪ አሠራሮች አማካኝነት መከወኑንም አድንቀዋል፡፡

በተጨማሪም፣ ግብጽ እና ሱዳንን ፈጽሞ በማይጎዳ መልኩ፣ የአባይን ውኃ ፍትሐዊነት በተሞላበት እና ለሁሉም ተደራሽ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ኢትዮጵያ ባላት ውሳኔ እንደምትጸና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

በቀጣናው የታየው ወቅታዊ የዝናብ እና የፈሰስ መጠን መጨመር ግድቡን ለመሙላት ሁኔታዎችን አመቺ አድርጓል ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ጸ/ቤት መግለጫ ፣የግድቡን የመጀመሪያ የውኃ ሙሌት እና ዓመታዊ የሥራ ክንውን አስመልክቶ፣ ኢትዮጵያ ሚዛናዊ እና ሦስቱም ሀገራት በፍትሐዊነት ከ ዓባይ ወንዝ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ድርድርን ለማካሄድ ባላት አቋም ትቀጥላለች ብሏል፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከተገኘው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የተነሣም፣ የግድቡ የመጀመሪያ ዓመት የውኃ ሙሌት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ውኃው በግንባታ ላይ ያለውን ግድብ አልፎ መፍሰስ መጀመሩን መግለጫው አመልክቷል፡፡

በሀገር መሪዎች እና ርዕሳነ መንግሥታት ደረጃ የተካሄደውን ስብሰባ፣ ሁሉም አካላት በዓበይት ጉዳዮች ላይ በመስማማት ያጠናቀቁ ሲሆን፣ ድርድሩ በስምምነት እንዲቋጭ መንገድ ጠርጓል።

በዚህም መሠረት፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የውኃ ሙሌቱን የተመለከቱ የቴክኒክ ውይይቶች በአፍሪካ ኅብረት በኩል በሚደረገው ሂደት እንዲቀጥሉ እና ወደ አጠቃላይ ስምምነት እንዲደረስ ተስማምተዋል።

#EBC

@YeneTube @FikerAssefa1
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት ተጠናቀቀ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የውሃ ሙሌቱ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ክረምቱ ገና ሳይገባደድ የመጀመሪያው ዙር ሙሌቱ በጥቂት ቀናት ሞልቶ መጠናቀቁና መፍሰስ መጀመሩ ለአገሪቱ ትልቅ የድል ምዕራፍ መክፈቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ላደረገው የኢትዮጵያ ህዝብና በድርድር ሂደት ሙያዊና የዜግነት ግዴታቸውን ለተወጡት ተደራዳሪዎች እንዲሁም ግድቡን አሁን ላለበት ደረጃ እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የአገሪቱ የቀድሞ መሪዎችም ጭምር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአሁኑ ሙሌት በሁለት ተርባይን ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ምዕራፍ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የግድቡ ግንባታ ዳር እንዲደርስ በድፕሎማሲውም ሆነ በግንባታው ሂደት ገና ብዙ ሂደት ይቀረዋል ብለዋል።

በመሆኑም ህዝብና መንግስት በተባበረ ጥረት ለአገራዊ ለውጥና ተጠቃሚነት በጋራ መስራታቸውን እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

የግድቡን ህልውና በዘላቂነት ለማረጋገጥም በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

#EBC

@YeneTube @FikerAssefa1
«ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ አንድ ቦይንግ 777 የእቃ ጫኝ አውሮፕላን ሻንጋይ፣ ቻይና በሚገኘው ፑዶንግ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በቆመበት ከፊል ቃጠሎ እንዳጋጠመው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል!»

«በጉዳዩ ዙርያ የአቪዬሽን ተንታኙ አሌክስ ማቻራም አረጋግጦ የፃፈ ሲሆን አየር መንገዱ ከደቂቃዎች በሁዋላ መግለጫ እንደሚሰጥ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።»

#EliasMeseret

@YeneTube @FikerAssefa1
#ተጨማሪ

⬆️ ዛሬ ቻይና ውስጥ በከፊል መቃጠል ስለደረሰበት አውሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰጠዉ ማብራሪያ

@YeneTube @FikerAssefa1
የWiFi አገልግሎት በአብዛኛዉ የኢትዮጵያ ክልሎች ጀመረ።

ላለፉት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት የአማራ እና የደቡብ ክልልን ጨምሮ በአዳማ፣ ድሬዳዋና ሀረር፣ እንዲሁም በአብዛኛዉ የሀገሪቱ ክፍሎች የWiFi አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኔቲዩብ ማረጋገጥ ችሏል።

ባለፉት ሳምንታት በአዲስ አበባ ፣ በተለያዩ የግልና የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተቋረጠዉ አገልግሎት መጀመሩ የሚታወስ ነዉ።

@YeneTube @FikerAssefa1
የክልል ታርጋ ያላቸው ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ ሲንቀሳቀሱ ካገኘ እንደሚወርስ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው ፍቃድ ከተሰጣቸው ሞተረኞች ውጪ የክልል ታርጋ ቢኖራቸው እንኳን ማንኛውም ሞተረኞች በመዲናዋ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ነው ቢሮው ያስታወቀው።በተጨማሪም በቢሮው ተደራጀተው አሁን ላይ እየሰሩ ከሚገኙት ሞተረኞች ውጪ የኮድ 2 ም ሆነ የኮድ 3 ሞተር ሳይክሎች ፍቃድ መስጠት መቆሙን ቢሮ አሳውቋል።የቢሮ ሀላፊው አቶ ስጦታ ጣሰው በ2011 የወጣውን የባለ ሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ የወጡ መመሪያ ቁጥር 2 እና ቀጥር 3 ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

መመሪያው በቢሮው ፍቃድ ከተሰጣቸው ውጪ በከተማዋ የክልል ታርጋ ለጥፈው የሚንቀሳቀሱ ሞተረኞች ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ ግልፅ ነገር እንዳልነበረው በዚህም የተነሳ ሞተረኞች የክልል ታርጋን አስመስለው በመስራት እንደ ባንክ ያሉ እና የተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ ትኩረት አድርገው ዝርፊያ ይፈፅሙ እንደነበር ተናግረዋል።ይህንን ክፍተት በመገምገምም የክልል ታርጋ ያላቸው ሞተረኞች በመዲናዋ ሲንቀሳቀሱ ከተገኙ ንብረታቸው እንዲወረስ እና ለፍርድ እንዲቀርቡ በመመሪያው በግልፅ መቀመጡን ቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በመዲናዋ የባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በከተማዋ ለደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ከፍተኛ አስተዋፆ ኖሮአቸው በመገኘቱ፣ የከተማዋን የትራፊክ እንስቃሴ በማወካቸው እንዲሁም ባለፊት 2 ዓመታት በሞትር ሳይክል ከቀላል ንጥቂያ እስከ ከባድ ወንጅል በመፈፀሙ መመሪያው 2011 ዓ.ም ላይ መውጣቱን አስታውሰዋል። በመመሪያው መሰረት በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ ሞተረኞች በማህበር እንዲደራጁ እና በግልፅ የሚታይ ታርጋ እንዲለጥፉ፣ ዩኒፎርም እንዲኖራቸው እና ለቁጥጥር ያመች ዘንድ ጂፒኤስ እንዲገጠምላቸው በማድረግ ከ3ሺ 600 በላይ አባላት ያሉት 56 የሞተረኞች ማህበራት ተደራጅተው በከተማዋ እንዲንቀሳቀሱ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa1
የፓስፖርት እድሳት አገልግሎትን እስከ ሁለት ወር ባለ ጊዜ ውስጥ በኢንተርኔት አማካይነት መስጠት እንደሚጀምር የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ገለፀ

በአንድ ወር ግፋ ቢል በሁለት ወር ውስጥ የፓስፖርት እድሳት አገልግሎትን በኢንተርኔት አማካይነት መስጠት እንደሚጀምር የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ለሸገር ተናግሯል፡፡ አንድ ሰው ፓስፖርት ለማሳደስ በኢንተርኔት ቅፅ መሙላትና በባንክ ክፍያ መፈፀም እንዳለበት የገለፁ ሲሆን የታደሰውን ፓስፖርት በአቅራቢያ ከሚገኝ የኤጀንሲው ቅርንጫፍ መውሰድ እንደሚቻል የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል ተናግረዋል፡፡በተመሳሳይ አዲስ ፓስፖርት ማውጣት የሚፈልጉም በኢንተርኔት ለዚሁ ዓላማ የተጋጀውን የኤጀንሲውን ቅፅ ሞልተው በቀጠሯቸው ቀን እንዲስተናገዱ ይደረጋል ሲሉም ገልፀዋል፡፡ የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የፓስፖርት እድሳትም ሆነ አዲስ የመስጠት አገልግሎት በሙሉ አቅሙ እያከናወነ እንዳልሆነ ይታወቃል።

Via Sheger FM/ Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 18 ቀን 2012 ዓ.ም (ቅዳሜ) በፊት ለፊትና በኦንላይን ያስተማራቸውን 5600 በላይ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ virtual የምረቃ ፕሮግራም የሚያስመርቅ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ያተላለፋል፡፡

#አአዩ_ፕሬዚዳንት_ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa1
ያስሚን ወሃብረቢ የገንዘብ ሚንስትር ደዔታ ሆነው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እንደተሾሙ ፎርቹን ዘግቧል፡፡አዲሷ ሚንስትር ደዔታ የሚንስቴሩን የውጭ ኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ይመራሉ፡፡ ያስሚን ላንድ ዐመት በሚንስቴሩ የዐለማቀፍ ፋይናንስ ድርጅቶች ትብብር ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል፡፡

Via Fortune/Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 452 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ፣ የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7 ሺህ 294 የላቦራቶሪ ምርመራ 452 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው እና የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች በቦታ ሲለዩ፦
• ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 301፣
• ከጋምቤላ ክልል 34፣
• ከኦሮሚያ ክልል 19፣
• ከትግራይ ክልል 32፣
• ድሬደዋ 0፣
• ደቡብ ክልል 17፣
• ከሐረሪ ክልል 2፣
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 0፣
• ሲዳማ ክልል 5፣
• ከአማራ ክልል 9፣
• ከሶማሌ ክልል 12 እና
• ከአፋር ክልል 21 ናቸው።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 350 ሺህ 160 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 524 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ቁጥር 188 ደርሷል።

38 የኮሮና ቫይረስ ታካሚዎች ደግሞ በፅኑ ሕክምና መከታታያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት 58 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 506 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

#EBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በኮሮና ስጋት ለብቻቸው እንዲታሰሩ ፍርድ ቤት የወሰነላቸውን ትዕዛዝ ፖሊስ ተፈጻሚ እንዳላረገ ጠበቃቸው ገለጹ።

እንጂነር ይልቃል ቀደም ሲል አብረዋቸው ታስረው የነበሩ ሁለት ሰዎች በኮሮና ተህዋሲ ተጠርጥረው ከተወሰዱ በኋላ ስጋት እንደገባቸው ለፍርድ ቤት አመልክተው እንደነበር እና ፍርድ ቤቱም ለብቻ እንዲወጡ ለፖሊስ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር ጠበቃቸው አቶ አዲሱ ጌታነህ ተናግረዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ዛሬ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተመልክተናል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa1