YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 15ኛ መደበኛ ጉባኤ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል፡፡ጉባኤው ሐምሌ 20 እና 21 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድም ታውቋል፡፡

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠሩት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀርበዋል!

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡በከሰአት በኋላ በነበረው ችሎትም የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በቡራዩና አዲስ አበባ በተፈጠረ አመጽና ሁከት በደረሰ የሰውና የንብረት ጉዳት የተጠረጠሩ 8 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።በጠዋቱ ችሎት በቀዳሚነት የቀረቡት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ላይ መርማሪ ፖሊስ የሰራውን የምርመራ ስራ ይፋ አድርጓል።በዚህም የምስክር ቃል መቀበሉን፣ ወንጀሉ የተፈጸመበት ስፍራን በቴክኒክ ማስረጃ ማረጋገጡን፣ ግብረ አበሮቻቸውን በቁጠጥር ስ ርአውሎ ምርመራ እየሰራ መሆኑን፣ አርቲስት ሃጫሉ የተገደለበትን ሽጉጥ ከተጠርጣሪዎች ቤት ከተቀበረበት ጓሮ ማውጣቱን እና በምርመራ ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ስልካቸውን ወደ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት መላኩን የአስከሬን ምርመራ ውጤት እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጾ ድርጊቱ የታቀደ መሆኑን በምርመራ ማረጋገጡን ተናግሯል።ከተጠርጣሪዎቹ በስተጀርባ ያለውን በጥንቃቄ እየመረመረ መሆኑን በመጥቀስም ከኢትዮ ቴሌኮም ያገኘውን በስልካቸው የተላከ ሰፊ መልዕክት እየተነተነ መሆኑን አስረድቷል። ለተጨማሪ ምርመራም 14 ቀን ጠይቋል።ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው የእስር አያያዛቸው ብርሃን የማያገኙበት መሆኑን አቤቱታ አስመዝግበዋል።ፍርድ ቤቱም አያያዛቸው እንዲስተካከል ለፖሊስ ትዛዝ በመስጠት ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀን በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለነሃሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷል።

በሌላ በኩል ከሰአት በነበረ የችሎት ውሎ የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በቡራዩና አዲስ አበባ በተፈጠረ አመጽና ሁከት በደረሰ የሰውና የንብረት ጉዳት የተጠረጠሩ በጃምባ ሁሴን መዝገብ የተካተቱ 8 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።መርማሪ ፖሊስ ባሳለፍነው ሃምሌ 7 ቀን 2012 ዓ.ም በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ የሰራውን ምርመራ አቅርቧል።በዚህም በ5ኛና 6ኛ ተጠርጣሪዎች ላይ የወንጀል ተሳትፎ መለየቱን 10 የተከሳሽ 20 ደግሞ የምስክር ቃል መቀበሉን ገልጿል። በአዲስ አባባ ገቢዎች ቢሮ፣ መንገዶች ባለስልጣን፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ የደረሰውን አጠቃይ ከ136 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት መድረሱን ማስረጃ ሰብስቤያለሁም ብሏል።

በቡራዩ በተነሳ ሁከት 4 ሰዎች መሞታቸውን እና አራት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል ጠቁሟል።
ከተለያዩ ተቋማት ማስረጃ ለመሰብሰብ ተጨማሪ ምርመራ ለማከናወን 14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀ ሲሆን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃም የተጠቀሰው ምክንያት ተጨማሪ ጊዜ የሚያሰጥ አይደለም ለማሰር ብቻ ነው ሲሉ ተቃውመዋል።ተጠርጣሪዎች ከቤተሰብ ጋር እንደማይገኛኙ በድጋሚ አቤቱታ አስመዝግበዋል።ፖሊስም ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን የአቶ በቀለ ገርባ ሁለት ልጆችን ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎችን ለቀናል እኛ ለማሰር ብቻ አደለም እየሰራን ያለነው ለምርመራ ነሲል ምላሽ ሰጥቷል።ፍርድ ቤቱም በድጋሚ አያያዛቸው እንዲስተካከል እና ከቤተሰብ ጋር በጥንቃቄ እንዲገናኙ ትዕዛዝ በመስጠት ለፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ሰባት ቀን ጊዜ ፈቅዷል።የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅም ለሃምሌ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ጠ/ ሚ ዐቢይ በኤሌክትሪክ ኃይል የምትሠራ መኪና በስጦታነት ተበረከተላቸው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤሌክትሪክ ኃይል የምትሠራ እና የሀዩንዳይ ኩባንያ አካል በሆነው ማራቶን ሞተርስ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመች የመጀመሪያ መኪና በስጦታነት ተበረከተላቸው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሀዩንዳይ ፕሬዚዳንት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን የመገጣጠም ሥራ ተጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሙሉ በሙሉ በባትሪ የሚሠራውን እና የካርበን ልቀት የማያስከትለውን መኪና በተቀበሉበት ወቅት፣ ይህን የመሳሰሉ መዋዕለ ነዋይ ፍሰት የሚያስገኙ ሥራዎች በሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለአረንጓዴ ልምላሜ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።መኪናውን የኃይል ማደያ ሳያስፈልግ በየትኛውም ቦታ ባትሪውን መሙላት እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የ2013 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚካሄድበት ጊዜ ተራዘመ!

ህዳር 6 ቀን ሊደረግ የነበረው የ2013 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተገልጿል።ድርጅቱ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ÷ የ2013 ዓ.ም ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በወረረሽኙ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉን ገልጿል።ወደ ፊት ምዝገባ የሚጀምርበትን እንዲሁም ሩጫው የሚደረግበትን ቀን በዝርዝር እንደሚያሣውቅም አስታውቋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአረፋ በዓልን ሲያከብር የኮቪድ19 መከላከያ መንገዶችን እና የተቀመጡ ክልከላዎችን በመተግበር ሊሆን ይገባል - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአረፋ በዓልን ሲያከብር በእምነቱ የተቀመጡ የወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጡ ክልከላዎችን ተግባራዊ በማድረግ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ። የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እንድሪስ በዓሉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡በመግለጫቸውም ሙስሊሙ ማህበረሰብም ይሁን ሌሎች የሀገሪቱ ዜጎች ኮሮናን በመከላከል ረገድ ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የዘንድሮውን የአረፋ በዓል የምናከብረው እንደ ቀደሙት አመታት በአንድ ላይ ተሰባስበን ሳይሆን ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን በመከወን መሆን ይገባዋልም ነው ያሉት፡፡ሙስሊሙ ማህበረሰብ በአረፋ በዓል ላይ የተቸገሩትን በመርዳትና የታመሙትን በመጠየቅ ሰብአዊ ተግባር እንዲፈጽምም ጥሪ አቅርበዋል፡፡በተጨማሪም ሰብአዊነትን በተግባር በማሳየት እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በያለበት ቦታ ሁሉ የዱዓ ፀሎት በማድረግ በአሉን እንዲያከብርም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡1 ሺህ 441ኛው የአረፋ በዓል ከነገ በስቲያ አርብ የሚከበር ይሆናል፡፡

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ 17ኛው የጉሙሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በአሶሳ ተከፈተ!

የኢፌዴሪ ጉሙሩክ ኮሚሽን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ የከፈተው የጉሙሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በይፋ ስታ ጀመረ።ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የገቢዎች ሚንስትር አቶ ላቀ አያሌው እችና የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በይፋ ሥራ አስጀምረዋል። በትናንትናው ዕለት በይፋ ሥራ የጀመረው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በኢትዮጵያ 17ኛው የጉሙሩክ ቅርንጫፍ ሆኖ መከፈቱ እንደተገለፀም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት መምህራንና ተመራማሪዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።

ዩኒቨርሲቲው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጠው ለፕሮፌሰር አሰፋ አባሁና እና ለፕሮፌሰር አማን ደቀቦ ነው።አሁን ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ምሁራን በረጅም ጊዜ ማስተማር፣ ጥናትና ምርምሮቻቸውን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች በማሳተምና በማህበረሰብ አገልግሎት አበርክቶዎቻቸው ማዕረጉ እንደተሰጣቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ ተናግረዋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በፍርድ ቤት ውሎ ዘገባ ህብረተሰቡ ተገቢና ሚዛናዊ መረጃ ሊቀርብለት እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ገለፁ።

የችሎት ዘገባ የሙያ ስነምግባርን እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ÷ የፍርድ ቤቶችን ነጻና ገለልተኛነት ያላማከለ፣ የተጠርጣሪዎችን ንጹህ ሆኖ የመገመት መብትን የሚጋፉ የችሎት ዘገባዎች በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ መሆኑን ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ሰለሞን አረጋ ተናግረዋል።ዛሬ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዘጋጅነት ከመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋር በተደረገ ውይይት÷ ከኢትዮጵያ ህግ አንጻር የሚገደቡና የማይገደቡ የችሎት ውሎ ዘገባዎች ምን መምሰል አለባቸው በሚለው ጉዳይ ላይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ አቶ ተስፋዬ ነዋይ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።

በዚህ ጥናታዊ ጽሁፋቸው ተጠርጣሪዎችን ወንጀል እንደፈጸሙ አድርገው የሚዘግቡ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን እንዳሉ አመላክተዋል።ይሁንና በሚዘገቡ የፍርድ ቤት ዘገባዎች ላይ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ እና መሰል ዘገባዎችን ከማስተላለፍ መቆጠብና በጥንቃቄ ሊዘገብ እንደሚገባ ተገልጿል።ከዚያም ባለፈ ዘገባዎች ፍሬ ነገርን የማያዛባ የዳኝነት አካሉን ተጽኖ ስር የማይከቱ ሊሆኑ እንደሚገባቸው ተጠቅሷል።ይሁንና በአንዳንዶች በኩል ተጠርጣሪዎች የሚናገሩትን ብቻ የሚዘግብ ሚዲያ ሚዛናዊነት የሚጎለው እንደሆነ የገለጹት አቶ ተስፋዬ በተቻለ መጠን የሁሉም አካል በሚዛናዊነት ሊካተት እንደሚገባ ጠቅሰዋል። በውይይቱ ላይ የተጠያቂነት ደረጃዎች እስከምን ድረስ የሚለውም የተነሳ ሲሆን÷በሚቀርቡ ሚዛናዊ ባልሆኑ ዘገባዎች ላይ ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባ ተጠቅሷል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።በአሁን ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከሉ ኡማ የ2012 ዓ.ም በጀት አፈፃፀምን ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ይገኛል።ምክትል ከንቲባው የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫን አቅርበው ውይይት እንደሚደረግበት ተጠቁሟል። በተጨማሪም የ2013 ዓ.ም የካፒታል በጀት እና መደበኛ በጀት ፣የ2012 የዋና ኦዲተር እና ፍርድ ቤቶች ሪፖርት እንዲሁም ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ አቶ አዲስአለም ገልጸዋል፡፡በዛሬው ዕለት የተጀመረው ጉባኤው ነገም እንደሚቀጥል ነው የተነገረው።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2013 በጀት ዓመት የሁሉንም መንግስት ሰራተኞች ሀብት ሊመዘግብ መሆኑን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከ2013 በጀት ዓመት ጀምሮ ቀደም ሲል ሲመዘግብ ከነበረው የተሿሚዎችና የህዝብ ተመራጮች በተጨማሪ የሁሉንም መንግስት ሰራተኞች ሀብት ለመመዝገብ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገልጿል።የምዝገባውን ሥርዓት የሚያስተባብረውና የሚያስፈጽመው ደግሞ በየተቋማቱ የተሰየሙዉ የሥነምግባር መኮንኑ ሲሆን÷ የእያንዳንዱ መንግስት ሰራተኛ ሀብት ምዝገባ የሚከናወነው ሰራተኛው በሚሰራበት ተቋም መሆኑም ነው የተገለጸው።ይህንንም ስራ ለማከናወን የሚያስችል ሥልጠናም ከሐምሌ 14 እስከ 18 ቀን 2012 ዓ.ም ለ213 የሥነምግባር መኮንኖች መሰጠቱ ተገልጿል።ኮሚሽኑ የሀብት ምዝገባ ሥራ ከጀመረበት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የ220 ሺህ ተሿሚዎች፣የህዝብ ተመራጮችና የተወሰኑ የመንግስት ሰራተኞችን ሀብት መመዝገቡ ታውቋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቶ ጃዋር መሀመድና እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ የቅደመ ምርመራ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጠ።

አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች በዛሬው እለት በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋርን ጨምሮ አጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች አቶ ጃዋር መሃመድ በሚል መዝገብ በመዝገብ ቁጥር 215585 ላይ የቅድመ ምርመራ መዝገብ የከፈተ ሲሆን፥ በዚህ መዝገብ ላይ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል የተጠረጠረ ጋዜጠኛም ተካቷል። አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 215585 የቀዳሚ ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠይቋል።

በተጨማሪም የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በዚህ መዝገብ ላይ በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ 15 ምስክሮች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን፤ እንዲሁም 5 ምስክሮች ደግሞ ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲል አቤቱታ አቅርቧል።በተጨማሪም በዝግ ችሎት ምስክሮቹ ቃላቸውን እንዲሰጡም ጠይቋል።የሁሉም ተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው አቃቤ ህግ ያቀረበው አቤቱታ ላይ መቃወሚያቸውን አቅርበዋል።በዚህም በዝግ ችሎት ተብሎ ለቀረበው አቤቱታ በግልፅ ችሎች ምስክሮቹ እንዲሰሙ እንደሚፈልጉ እና አቃቤ ህግ የሚያቀርባቸው ምስክሮች ጭብጥ ለመከላከል እንደሚያመች እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

እንዲሁም ምስክሮቹ ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃል መስጠት እንደሌለባቸው እና ስም ዝርዝራቸውም ተለይቶ ተሰጥቷቸው አውቀዋቸው የምስክርነት ቃላቸውን ሊሰጡ እንደሚገባም ገልፀዋል።ክሱ ስልጣን ባለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብ መሆኑን ተከትሎ የቀዳሚ ምርመራ የምስክር ቃልም ለክሱ መከላከል እንዲያስችላቸው አስቀድመው ሊያውቁት እንደሚገባም በመቃወሚያዎችን አንስተዋል።ተጠርጣሪ አቶ በቀለ ገርባ፥ “የማስመዘግበው አቤቱታ አለኝ፤ ሀሳቤን ፍርድ ቤቱ ይቀበለኝ” ያሉ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ “በጠበቆቻችሁ በኩል በቂ ሀሳብ ተነስቷል” ሲል አልተቀበላቸውም።የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ብይን ሰጥቷል።

በተለይም በስነ ስርዓት ህጉ መሰረት የቀረበው የቅድመ ምርመራ የአቃቤ ህግ ምስክሮች በዝግ ችሎት ቃላቸው እንደሚሰማ እና ይህም ክስ ከመመስረቱ በፊት የሚደረግ የቅድመ ምርመራ በዝግ ችሎት እንደሚሆን አብራርቷል። የምስክሮችን ዝርዝር እና ጭብጥ ጉዳይ ይሰጠን ተብሎ በቀረበ መቃወሚያ ላይም ለደህንነታቸው ታሳቢ ተደርጎ እንደማይሰጥና አምስቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮችም ከመጋረጃ በስተጀርባ ቃላቸውን እንዲሰጡ ብይን ሰጥቷል።የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በቅድመ ምርመራ መዝገቡ ላይ የምስክሮች ቃል እንዲሰማ ለነሃሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ጠ/ሚ ዐቢይ ከመደመር መፅሐፍ ሽያጭ የተሰበሰበውን ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለትምህርት ቤት ማሰሪያ እንዲውል አበረከቱ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመደመር መፅሐፍ ሽያጭ የተሰበሰበውን ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለትምህርት ቤት ማሰሪያ ይሆን ዘንድ ለቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት አስረክበዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መፅሐፍን ገቢ በመላው አገሪቱ ለትምህርት ቤቶች ማሰሪያ እንደሚውል ቃል በገቡት መሰረት ነው እስካሁን ከመፅሀፉ ሽያጭ የተሰበሰበውን ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት ዛሬ ያስረከቡት።በየክልሎቹ መደመር መፅሐፍ ተሸጦ የተሰበሰበው ገንዘብም ተመልሶ ለየክልሎቹ ትምህርት ቤት ግንባታ የሚውል እንደሆነም ተገልጿል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
የደቡብ ክልል ምክር ቤት 38 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2013 የክልሉ መንግስት በጀትን አጽድቋል።

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።የክልሉ ምክር ቤት በዛሬው ውሎውም የ2013 የየደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት በጀትን ተመልክቷል።ምክር ቤቱ ለ2013 በጀት ዓመት 38 ቢሊየን 21 ሚሊየን 970 ሺህ 828 ብር ሆኖ የቀረበለት የክልሉ መንግስት በጀት ላይም ተወያይቷል።በጀቱ ከፌደራል መንግስት ድጎማ፣ ከውስጥ ገቢና ከሌሎች የገቢ አማራጮች የሚገኝ እንደሆነ በጉባኤው ላይ መነሳቱን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዚህም ከአጠቃላይ በጀት ውስጥ 28 ቢሊየን ከፌደራል መንግስት የሚገኝ ድጎማ ሲሆን፥ 9 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የሚሆነው ደግሞ ከክልሉ ልዩ ልዩ ገቢዎች የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።

የክልሉ መንግስት የ2013 በጀት ዓምናው ማለትም ከ2012 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃር የ12 ነጥብ 24 በመቶ ብልጫ ያመው መሆኑም ተጠቁሟል።የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በበጀቱ ላይ በሰጡት ማብራሪያም፥ በ2013 በጀት በሁሉም ዘርፎች የበጀት አቅምን ባገናዘበ መልኩ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ እንደሚሰራ ገልፀዋል።የበጀት ክፍተት ከተገኘ ደግሞ አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶች በጥናት ላይ በመመርኮዝ እንደሚሰራም ነው አቶ ርስቱ ያብራሩት።የክልሉ ምክር ቤትም በቀረበለት የ2013 የክልሉ መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምጽና በአንድ ድምፀ ታቅቦ አጽድቆታል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በሀረሪ ክልል 35 ህገወጥ ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ጣሰው ቻለው÷በክልሉ ሶፊ ወረዳ የፀጥታ ሀይሉ ባደረገው ቅንጅታዊ ስራ 35 ሽጉጦችና 2 ክላሾችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፀዋል።ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን ይዘው የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ያህያ አብዱሰላም አስታውቀዋል።ሀላፊው አያይዘውም በክልሉ በተለያዩ ግዚያት ሲነሱ የነበሩ የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ሲባል በተያዘለት እቅድ መሰረት የመከላከያ ሰራዊት ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ፣ የፌደራልና የሀረሪ ፖሊስ በጋራ በመቀናጀት በሶፊ ወረዳ ባደረጉት የኦፕሬሽን ስራ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹና 1 ኮምፒዩተር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ በሀገር ውስጥ የልብ ህክምና ማእከል ህክምና እንዲያገኙ እንዲያደርግ ለፖሊስ ትዕዛዝ ቢሰጥም ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ!

ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ አያሌው በህክምና ምክንያት ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሲያደርግ፥ መርማሪ ፖሊስ ለመጨረሻ ጊዜ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የሰባት ቀን ጊዜ ፈቅዷል።በምስራቅ ሸዋ ዞን የቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ በቀረቡት አቶ ለደቱ አያሌው ላይ መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው ተጨማሪ 14 ቀናት  ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን የምርመራ ስራዎች ገልጿል።አቶ ልደቱ እጅ ላይ የተገኙ ሁለት ሽጉጦች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም የተላላኳቸውን የስልክ መልዕክቶች በፎረንሲክ  እያስመረመረ መሆኑን ተናግሯል።

በእጃቸው ላይ የኢትዮጵያ ህዳሴ እርቅና አንድነት የሽግግር መንግስት ማቋቋም የሚልና ሌሎች የፖለቲካ ሰነዶችን ማግኘቱን  የገለፀው መርማሪ ፖሊስ በሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ  ግድያን ተከትሎ መንግስት ለመገልበጥ እቅድ ይዘው ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር በቢሾፍቱ  ሁከትና አመፅ እንዲፈጠር ሲቀሰቅሱ ነበሩ ብሎ እንደጠረጠራቸውና ለዚህም የምስክሮችን ቃል መቀበሉን ገልጿል።ለጀመርኩት ምርመራ የፎረንሲክ ምርመራ ውጤት ለማምጣትና ተጨማሪ ሰነዶቸን ለማሰባሰብ 14 ቀን ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን  ጠይቋል።

አቶ ልደቱ ዛሬም በጠበቃ ያልተወከሉ  ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱ ለምን በጠበቃ እንዳልተወከሉ  ለጠየቃቸው ጥያቄ ሁለት ጠበቆች ፍቃደኛ  አለመሆናቸውን፤ አንድ ፍቃደኛ ቢያገኙም በዚሁ ሰዓት በሰበር ችሎት ቀጠሮ ስላለው እኔው ለዛሬ ልከራከር ሲሉ  ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ፍርድ ቤቱም ፈቅዶላቸዋል።በዚሁ መሰረት ፖሊስ ባቀረበው ምርመራ ላይ መቃወሚያ አሰምተዋል።ሽጉጡን በተመለከተ 1998 ዓመተ ምህረት ላይ መንግስት ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንደሰጣቸው አንደኛው ሽጉጥ ደግሞ ከአባታቸው በውርስ ያገኙት እና ፍቃድ ያለው መሆኑን አስረድተዋል።

በ1998 ዓመተ ምህረት ማስፈራሪያዎች ይደርስባቸው ስለነበር  በወቅቱ የነበረው መንግስት ችግሩ ሲያልፍ ትመልሳለህ ብሎ እንደሰጣቸው ነው ያስታወቁት።ሰነዶቹንም በተመለከተ የፖለቲካ ጉዳዮች ሆነው  በመገናኛ ብዙሃን እና በአደባባይ ሲገልጿቸው የነበሩ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልፀዋል።ከዚህ በፊት ከነበረኝ ቀጠሮ  ጋር ተመሳሳይ የሆነ መርመራ ነው የቀረበው፤ አዲስ አልቀረበም በማለት ተጨማሪ ጊዜ ለመርማሪ ፖሊስ ሊሰጥ አይገባም ሲሉ ተቃውመዋል።

በፈረንጆቹ ነሃሴ 6 የልብ ቀዶ ጥገና ምርመራ ለማድረግ እሁድ ወደ አሜሪካ ለመብረር ትኬት ቆርጠው አርብ እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀው፥ አሁንም የልብ ህክምና ያሰጋኛል  የፖሊስ ጣቢያው ውስጥም ማስክ ሳያደርጉ ከመንገድ ላይ የሚያዙ ሰዎች  ሳይመረመሩ እየገቡ ናቸው፤ ለኮሮናቫይረስ  ወረርሽኝ ተጋላጭ እንዳልሆን ስጋት አለኝ  ሲሉ አቤቱታ አስመዝግበዋል።ከዚህ በፊት የነበረው መንግስት አምስት ጊዜ አስሯቸው ነገር ግን ማስረጃ ስላልተገኘ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ የተናገሩት አቶ ልደቱ፥ አሁንም ማስረጃ ከተገኘብኝ ይጣራ  በውጭ ሆኜ ህክምናዬን እንድከታተል ፍርድ ቤቱ የጤናዬን ሁኔታ ከግምት  አስገብቶ በዋስ ይልቀቀኝ ሲሉ ጠይቀዋል።

ፖሊስ በበኩሉ ፖለቲካ ሳይሆን የወንጀል ጉዳይ ነው፤ እንደ ሀገር መንግስት ለመገልበጥ በተደረገ ሙከራ በቢሾፍቱ ወጣቶችን አደራጅተው አመፅና ሁከት በመቀስቀስ ነው የተጠረጠሩት፤ በመሆኑም ዋስትና ሊፈቀድ አይገባም ሲል ተቃውሟል።ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ከዛሬ ጀምሮ አቶ ልደቱ በሀገር ውስጥ የልብ ህክምና ማእከል ህክምና እንዲያገኙ እንዲያደርግ አዟል።የወረርሽኙን ሁኔታ በተቻለ መጠን  ጥንቃቄ እንዲደረግላቸው ያዘዘው ፍርድ ቤቱ፥ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የመጨረሻ ሰባት ቀን ጊዜ ፈቅዶለታል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ዳኛው ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ!

በእነ ጃዋር መሀመድ መዝገብ ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ማሰማት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም እነ አቶ ጃዋር ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ችሎቱ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በልደታ አዳራሽ መስማት ተጀምሮ ነበር።ይሁን እንጅ እነ አቶ ጃዋር ዳኛው ከመዝገባችን ላይ ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን ተመልክቶ ዳኛው መዝገቡ እንዲመረመርና በመዝገቡ ላይ ትዕዛዝ እስከሚሰጥበት ድረስ ተጠርጣሪዎቹ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲቆዩ እና መጥሪያ ሲደርሳቸው የሚመጡ ይሆናል በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡መዝገቡም ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ አዟል፡፡ከዚህ በፊት የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በዚህ መዝገብ ላይ በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ 5 ምስክሮች ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲል አቤቱታ ማቅረቡ ይታወሳል።ፍርድ ቤቱም አምስቱ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ከመጋረጃ በስተጀርባ ቃላቸውን እንዲሰጡ ብይን መስጠቱ የሚታወስ ነው።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በአርቲስት ሀጫሉ ግድያ የተጠረጠረው ከበደ ገመቹ ፍርድ ቤት ቀረበ!

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የግድያ ወንጀል የተጠረጠረውና ሸሽቶ በሃምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም አዳአ ድሬ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በቁጥጥር ስር የዋለው ከበደ ገመቹ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ።በዛሬው የችሎት ውሎም መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ በተጠርጣሪው ላይ የሰራውን ምርመራ ስራ ገልጿል።በዚህ ጊዜም ከተጠርጣሪው እጅ ላይ ከተገኘው ስልክ የድምጽ እና የመልዕክት ልውውጥ ከኢትዮ ቴሌኮም በማስመጣት በርካታ ማስረጃ ማሰባሰቡን ለችሎቱ አብራርቷል።በእጁ ላይ የተገኘው የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ለብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ለምርመራ መላኩን ያብራራው መርማሪ ፖሊስ፥ በዛሬው ችሎት መገለጽ የሌለባቸው ከበስተጀርባ ያሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምርመራዎች እየተደረጉ መሆናቸውን ገልጿል።

በዚህ መልኩ እየተከናወኑ ላሉ ስራዎች ተጨማሪ ምርመራዎች 14 ቀን እንዲሰጠውም ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።ተጠርጣሪው በአስተርጓሚ አስተያየት ካለው እንዲያቀርብ የተጠየቀ ቢሆንም፥ ምንም አይነት አስተያየት እንደሌለው ምላሽ ሰጥቷል።ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ለተጨማሪ መርመራ ለፖሊስ 14 ቀን በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለነሃሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።በተያያዘ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ቃለ መጠየቅ በማድረግ ፕሮግራሙን ቆርጦ በማቅረብ፤ እንዲሁም ሰኔ 22 እና 23 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ.ኤም.ኤን) አመጽና ብጥብጥ እንዲነሳ በመቀስቀስ የተጠረጠረው ጋዜጠኛ ጉዩ ዋርዮም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠርጣሪው ጋዜጠኛ ከላይ በተጠቀሰው ሚዲያ አመጽ እንዲነሳ ቅስቀሳ ማድረጉን የሚያስረዳ የሰነድ ማስረጃ ማሰባሰቡን እና ተጨማሪ የምስክር ቃል መቀበሉን ተናግሯል።በእጁ ላይ የተገኘ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ በፎረንሲክ እያስመረመረ መሆኑንም መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሰልጣን እና ከተለያዩ ተቋማት ማስረጃ ለማሰባሰብና ቀሪ ምርመራ ለመስራት ተጨማሪ 14 ቀን እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም የምርመራ መዝገቡን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነሃሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
አቶ ጃዋር መሐመድ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በልደታ አዳራሽ የአቶ ጃዋር መሃመድን ጉዳይ ተመልክቷል።አቶ ጃዋር መሃመድ ከዚህ ቀደም በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ መረሰት ነው በዛሬው እለት ከአንድ ጠበቃ ጋር ፍርድ ቤት የቀረቡት።መርማሪ ፖሊስ በአቶ ጃዋር መሃመድ ላይ የሚያደርገውን ምርመራ መዝገብ ማጠናቀቁን ገልጾ፤ አቃቤ ህግ በከፈተው ቅድመ መርመራ መዝገብ እንዲቀርቡልኝ ሲል በጽሁፍ አቤቱታ አቅርቧል።

የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቃ በበኩላቸው “መርማሪ ፖሊስ ምርመራዬን አጠናቅቄያለሁ ብሏል፤ የተጠርጣሪውን ዋስትና የሚያስከለክል ደረጃ ማስረጃ ስላላቀረበ ዋስትና ይፈቀድላቸው” ሲል ጠይቋል።ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤቱም ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ ቢቀርብ የሰው ህይወት ባለፈበት ወንጀል የተጠረጠሩ  መሆኑን ተከትሎ እስከ 15 ዓመት የሚያስቀጣ መሆኑን ካለው ድንጋጌ መረዳት ይቻላል ብሏል።በዚህም ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፥ መዝገቡም ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ አዟል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ዳኛ ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እነ አቶ ጃዋር ባቀረቡት አቤቱታ ላይ መርምሮ ብይን ሰጥቷል፡፡በዚህም አቤቱታው በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚል ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ይህን ተከትሎም ችሎቱ ከዚህ በፊት በነበረው ዳኛ የሚታይ ይሆናል ተብሏል፡፡በእነ አቶ ጃዋር መዝገብ 14 ሰዎች በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ዳዊት አብደታ የተባለው ተጠርጣሪ በኮቪድ19 ተጠርጥሮ ችሎት አልቀረበም፡፡እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ከትናንት በስቲያ ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ብልጽግና ፓርቲ ለተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጠ!

ብልጽግና ፓርቲ ለተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ሹመት መስጠቱን ፓርቲው በዛሬው እለት አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፡-
1. አቶ መለስ አለሙ- የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
2. አቶ ተስፋዬ በልጅጌ- በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ
3. ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ- በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የአለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ሆኖ ተመድበዋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa