ከፖለቲካ ጫና ነፃ የወጡት የመንግስት ሚዲያዎች ⬇️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (#ኢዘአ)፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ #ፕሬስ ድርጅት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ/#EBC) ተጠሪነታቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ፈርሶ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ስር እንዲጠቃለል ተደርጓል። በዚህ መሰረት ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በስልጣን ላይ ባለው የፖለቲካ ቡድን ቁጥጥር ስር ወድቀው የነበሩት የመንግስት ሚዲያ ተቋማት ከሞላ-ጎደል ነፃ ወጥተዋል። ከዚህ በኋላ የመንግስትን በውሸትና ግነት የታጨቀ ዘገባ እንዲያቀርቡ የሚገደዱበት አሰራር የለም። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስር እስከሆኑ ድረስ ተጠሪነታቸው ለህዝብና ለህግ ብቻ ይሆናል፡፡
©seyoum Teshome
@YeneTube @Fikerassefa

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EBC ተቋም የሚገነባው ፤ ሰላም የሚረጋገጠው ፣ ዴሞክራሲ የሚስፋፋው፣ ልማት የሚመጣው በመንግስት ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ፤ ለውጥ የህዝቦችን ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ የእነሱን ድርሻ፣ የእነሱን ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን አውቀው በጋራ ሲሳተፉ ብቻ ነው፡፡
ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከተለያዩ ክልሎች ከተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ካደረጉት ውይይት የተወሰደ።
@YeneTube @FikerAssefa
ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከተለያዩ ክልሎች ከተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ካደረጉት ውይይት የተወሰደ።
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አጋር ፓርቲዎች ከኢህአዴግ ጋር እኩል የሚሳተፉበት አንድ አገራዊ ፓርቲ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ገለፁ፡፡
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የፖለቲካ ጉዳዮች ፀሃፊና የህግ ባለሙያው አቶ ኪያ ፀጋዬ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
#EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የፖለቲካ ጉዳዮች ፀሃፊና የህግ ባለሙያው አቶ ኪያ ፀጋዬ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
#EBC
@YeneTube @FikerAssefa
Breaking News.........
በቻይና በእስር ላይ ለምትገኘው ናዝራዊት አበራ ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ እፅ ሰጥታለች በሚል ወንጀል የተጠረጠረችው ስምረት ካህሳይ ከጓደኛዋ ሰለሞን ፀጋዬ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡
#EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በቻይና በእስር ላይ ለምትገኘው ናዝራዊት አበራ ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ እፅ ሰጥታለች በሚል ወንጀል የተጠረጠረችው ስምረት ካህሳይ ከጓደኛዋ ሰለሞን ፀጋዬ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡
#EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ጦርና ተቃዋሚዎች ከስምምነት የደረሱበትን ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ በፊርማቸው አፀኑት።
ሁለቱ ወገኖች ከዚህ ቀደም የደረሱበትን ስምምነትን በፊርማቸው ማፅናታቸው የሽግግር መንግስቱን መመስረት እውን ለማድረግ በር የመክፈቻ ጅመሮ ተደርጎ ተወስዷል፡፡የተቃዋሚዎቹ መሪ አህመድ ራቤ እና የሱዳን ጦር ተወካይ ጀነራል ሀምዳን ዳግሎ ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡በስምምነቱ መሰረት ስድስት ሲቪሎችና አምስትር ጀነራሎች የሽግግር መንግስቱን በበላይነት ይመሩታል፡፡ለወራት የዘለቀውን የሱዳን ቀውስ ማብቂያ እንዲያገኝ የአፍሪካ ህብረትና የኢትዮጰያ ሸምጋይነት ቅቡልነት አግኝቶ የሽግግር መንግስት ለመመስረት ከስምምነት የደረሱት ባለፈው ቅዳሜ ነበር፡፡

ወጣቶችን ማስጨረስ ይብቃ!!
"ትላንትም ዛሬም ወደ ፊትም በውጊያ ኢትዮጵያ ውስጥ ማሸፍ የሚፈልጉ አካላት ተመሳሳይ ናቸው፡፡
ሌሎችን ማስጨረስ እንጂ እራሳቸው መሞት አይፈልጉም፡፡ እነዚህ እራሳቸው መሞት የማይፈልጉ ሀይሎች ወጣቶቻችንን እንዲያስጨርሱ ሊንፈቅድላቸው አይገባም፡፡" ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርትኳን ሚዴቅሳ የጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ በማቅረብ ላይ ናችው፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባው የ5ኛ አመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ እና 2ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤዎችን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ጨምሮ ሌሎች አምስት አጀንዳዎችን የሚመለከት ይሆናል።
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያፀድቃል፤ የቀጣይ የመፍትሄ ሃሳብ እንዲቀርብም ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎም ነው የሚጠበቀው።
#EBC
@Yenetube @FikerAssefa

ግብፅ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እንዳይዘግቡ እገዳ ጣለች!
የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ በሀገሪቱ ስላለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና ከሊቢያ ጋር አገሪቱ እያረገች ስላለው ጦርነት በተመለከተ ምንም ዓይነት ዘገባ እንዳይሰሩ የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኋን ካውንስል ማገዱን አስታውቋል። ካውንስሉ ባስተላለፈው እገዳ መሰረት የግብፅ መገናኛ ብዙኃን እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምንም ዓይነት ዘገባም ሆነ ውይይት አንዲሰሩ አይፈቀድላቸውም።በሀገሪቱ የህትመት ሚድያዎች ላይ የሚሰሩ መገናኛ ብዙኋን ይዘቶችን ከማሳተማቸው በፊት ለሚመለከተው የመንግስት አካል ማስገምገም እና በፅሁፍ ጥያቄ አቅርበው ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸውም ተገልጿል።ሀገሪቱ እርምጃውን የወሰደችው ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በሚል ሽፋን መሆኑንም የሚድል ኢስት አይ ኔት ዘገባ ያመለክታል።

እንሥራ" የሸክላ ስራ ማእከል የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በተገኙበት ተመረቀ።
የማእከሉ ግንባታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ እንደሆነም ተገልጿል።በማእከሉ 1000 በሸክላ ስራ ላይ የተሰማሩ እናቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ከተሟላ የማምረቻ ቦታ እና ከተሟላ ቁሳቁሶች ጋር እንደሚያገኙም ተገልጿል።የሸክላ ስራ የሙያውን ያህል ያልተከበረ የድካሙን ያህልም ጥቅም ያልተገኘበት ሆኖ ቆይቷል ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ይሄን ዘርፍ ባለሙያዎችን በሚያሳድግ ሀገርን በሚጠቅም መልኩ ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።የሸክላ ምርቶቹ ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ገበያ እንዲያገኝ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ንግግር እየተደረገ ነው ያሉት ኢ/ር ታከለ ዘርፉን የሚደግፉ የህግ ማሻሻያዎችም እየተዘጋጁ ነው ብለዋል።

በሰሞኑ የፀጥታ መደፍረስ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም 106 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ
ሰሞኑን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም 106 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ድጋፉ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 55.9 ሚሊዮን ብር፤ ለብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን 50 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የተሰጠ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰጠው ድጋፍም የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ አልባሳት፣ ዱቄት፣ ሩዝ፣ ፓስታና ምስርን የሚያጠቃልል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ድጋፉ የተሰበሰበውም ከሰራተኞች፣ የግብር ግዴታቸውን ካልተወጡ ድርጅቶችና በኮንትሮባንድ ከተያዙ ልዮ ልዮ እቃዎች መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
#EBC
@YeneTube @FikerAssefa1

የኮቪድ-19ን ክትባት ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል ከ150 በላይ አገራት ጥምረት ተመሠረተ
75 የበለጸጉ አገራት 90 ከሚደርሱ ድሀ አገራት ጋር በመተባበር ሕዝቡን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመታደግ በጋቪ ፕሮጀክት በኩል ኮቫክስ በተሰኘ መርሐ ግብር በኩል የቅድመ ግብይት ተነሣሽነት ገንዘብ ፈሰስ ሊያደርጉ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የፕሮጀክቱ ዓላማ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመግታት ሀብታም ወይም ድሀ ሳይባል ለሁሉም አገራት ፈጣን፣ ፍትሐዊ እና እኩል የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽ ማድረግ መቻል ነው።
በድምሩ 165 አገራት የተካተቱበት እና 60 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዓለማችንን ሕዝብ የያዙት መንግሥታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ፕሮጀክቱን ለሁሉም ለማድረስ ‘የተያዘው ዕቅድ እውን እንዲሆን ከፍተኛ በራስ መተማመን አሳይተዋል’ ተብሏል።
በዚህም ስብስብ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የቡድን 20 አባል አገራት መካተታቸው ተመልክቷል።
የዓለም አቀፉ የክትባት ትብብር ጋቪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሴዝ በርክሌይ፣ “ኮቫክስ ለኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እውነተኛው መፍትሔ ነው” ብለዋል።
አያይዘውም፣ “በራሳቸው ወጪ መግዛት ለሚችሉም ሆኑ ድጋፍ ለሚሹ ብዙዎቹ አገራት፣ እኩል ዕድል የሚሰጥ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
የኮቫክስ ቤተሰብ መሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት የማፋጠን ልማት፣ ምርት እና ፍትሐዊ የምርመራዎች፣ ሕክምናዎች እና ክትባቶች ተደራሽነት ቁልፍ አካል ነው ተብሏል።
ኮቫክስ በጋቪ፣ የዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ዝግጁነት ፈጠራ ማእከል እና በዓለም ጤና ድርጅት እንዲሁም ባደጉ እና በማደግ ላይ ባሉ አገራት ውስጥ በሚገኙ የክትባት አምራች ለኩባንያዎች ጥምረት የሚመራ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።

ከሰሞኑ ተከስቶ የነበረው የሰላም መደፍረስ እንቅስቃሴ በቁጥጥር ስር ውሎ መረጋጋት መፈጠሩን መንግስት አስታወቀ
በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ የሰላም መደፍረሱ ባጋጠማቸው አካባቢዎች የፀጥታ መዋቅሩ ከህብረተሰቡ ጋር በመናበብ ችግሩን ለመወጣት መስራታቸውን ገልጸዋል።
በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ወደ ፍትህ አደባባይ የሚወጡበት ስርዓት በአግባቡ እየተመራ መሆኑን እና ምርመራው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
የተፈጠረውን ግጭት የማረጋጋት፣ ዜጎችን የማቋቋምና የዕለት ደራሽ ምግብና ቁሳቁስ ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ ባለበት ሁኔታ እንደገና ብጥብጥና ረብሻ እንዲነሳ ጥሪ የሚያስተላለፉ አካላት እንደነበሩ አንስተዋል።
”ጥሪው ቢተላለፍም ህብረተሰቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመተባበር የአመጽ ጥሪዎቹ እንዲከሽፉ አድርጓል” ብለዋል።
”አሁን የምንገኝበት ምዕራፍ ብልጽግናን እውን ለማድረግ የምንረባረብበት ነው” ያሉት አቶ ንጉሱ፤ የብልጽግና ጉዞ አንዱ ቁልፍ አጀንዳ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሆኑን ገልፀዋል።
በግጭት ምክንያት የሚጠፋ ሀብትና ንብረት እንዳይኖር መንግስት ከልክ በላይ መታገሱን ህዝቡ እንደሚገነዘብ ያነሱት አቶ ንጉሱ፤ አሁን የህግ የበላይነትን ለማስከበር ቁርጠኝነት እንዳለ ገልጸዋል።
ሰሞኑን በደረሰው ጉዳት ከቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ የሚገኙ ዜጎችን መደገፍና መርዳት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።
#EBC
@Yenetube @FikerAssefa1

ሲዳማ ክልል...
“በሲዳማ ክልል የህዝቡን መሠረታዊ ጥያቄ የሚመለስ አደረጃጀት እየተዘረጋ ነዉ”
- ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ
ርዕሰ መስተዳድሩ አደረጃጀቱ በአሁኑ ወቅት በክልሉ የአዳዲስ ዞኖች መዋቅርና ነባር ወረዳዎችን መልሶ የሚያጠናከር ስራ እንደሆነ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጓዳኘም ክልሉ የሚመራበት ስትራቴጂና ዓመታዊ እቅድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተለይ የክልሉ አደረጃጀት በዋናነት የህብረተሰቡን ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበና ሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን ለማከናወን በሚያስችል መልኩ የሚዘረጋ መሆኑን አስታውቀዋል።
“አዲስ መዋቅር ለመዘርጋት ጥናት ተካሂዷል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ረገድ ዋና አካሄድ የሚገኘውን ሀብት በቁጠባ በመጠቀም ውጤት ለማስመዝገብና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት ማመቻቸት መሆኑን ገልጸዋል።
ያካሄዱት ጥናት ይህንን የሚደግፍ መሆኑን አመልክተው በዚህም የሲዳማ ክልል በዋናነት በአራት ዞኖች ይደራጃል ብለዋል።
የሚደራጁት ዞኖች ባህሪ ምክር ቤትና ብዛት ያላቸው መስሪያ ቤቶች የሚኖራቸው ሳይሆን 30 ወረዳዎችን በመፍጠርና የመረጃ ፍሰቱን በማቀላጠፍ በቅርበት ድጋፍ እንዲሰጡ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል።
በስድስት ካቢኔ ደረጃ የሚዋቀርና አስተባባሪ ያለው አንድ ዞን ከ50 የማይበልጥ የሰው ኃይል ያለው ሆኖ ዋና ተልዕኮው ክልልና ወረዳን ድልድይ ሆኖ ማገናኘት እንደሚሆን አስታውቀዋል።
ለጊዜው ተጨማሪ ወረዳን ለመክፈት ጥናቱ እንደማያሳይ ጠቁመው ወረዳን እያሰፉ መሄድ ወጪን ማብዛት እንጂ ህዝቡ የሚፈልጋቸውን መሠረታዊ የሆኑ የመንገድ ፣ውሃ፣ጤና፣ ትምህርትና ሌሎችንም አቅርቦት ለሟሟላት አያስችልም ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ “ክልል መሆን በራሱ ትልቅ ሃብት የሚያስገኝና የፈለጉትን ማድረግ የሚያስችል አድርጎ የሚያዩ ወገኖች አሉ፤ እኛ ግን ይህ እንዳልሆነ በፊትም እናውቃለን፣አሁንም በተጨባጭ እያየን ያለነው ይሄንኑ ነው ” ብለዋል።
ባለው ውስን ሀብት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ድህነትን መዋጋት፣መልካም አስተዳደርን ማስፈንና የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቅድሚያ በመስጠት ርብርብ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
እንደ አቶ ደስታ ገለፃ በሚቀጥሉት ዓመታት የትኩረት ማዕከል ሆኖ የሚቀጥለው ወጣቶችን የልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድርግ ነው።
በተመረጡ ዘርፎች ከ100 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማደራጀት በልማት ፕሮጀክቶች ግንባታና በሌሎችም ገበያ ተኮር በሆኑ የስራ መስኮች ለማሰማራት ጥረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በችግር ውስጥ የነበሩ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሽታው ከመከሰቱ ጊዜ አንስቶ በቤሩት በችግር ላይ የነበሩ 656፣ ከአቡዳቢ 72፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ 3 ሺህ 539፣ ከኩዌት 1 ሺህ 23 እንዲሁም በድንበር በኩል ደግሞ 24 ሺህ 797 ዜጎች በጠቅላላው 30 ሺህ 87 ዜጎች ወደ ሀገር ተመልሰዋል።
በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን በተመለተ በሀገሪቱ ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ያለውን የመረጃ እጥረት ለመፍታት እና ዜጎቻችን እርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት ኢትዮጵያ ከሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ጋር ንግግር መጀመሩን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው።
ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በሚገኙባቸው የተለያዩ የዓረብ ሀገራት መሰል ሥራዎች ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከኩዌት፣ ከተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች እና ከመሳሰሉት ሀገራት ጋር በትብብር መሰል ዜጎችን የመርዳት እና የማገዝ ሥራዎች በመሠራት ላይ እንደሚገኙም አክሏል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ተፅዕኖዎችን እያስከተለ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚገኙ ዜጎች ወረርሽኙን ተከትሎ እየደረሰባቸው ያሉ ችግሮች ተጠቃሽ ናቸው።
በዚህ ረገድ መንግሥት በተለያዩ የዓረብ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የመርዳት እና የማገዝ ሥራዎችን ኢትዮጵያዊያኑ ከሚገኙባቸው ሀገራት መንግሥታት፣ ቆንጽላ ጽ/ቤቶች፣ ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት እና ከረድኤት ድርጅቶች ጋር በተቀናጀ ሁኔታ እየሠራ ይገኛል።
በዋናነት በተለያዩ የዓረብ ሀገራት እና ጎረቤት ሀገራት በችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ቦታ መጠለያ፣ ምግብ፣ ሕክምና እና ሌሎች መሠረታዊ ግብዓቶች እንዲሟላላቸው ከማድረግ አንጻር ውጤታማ ሥራዎች መሠራታቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።
የሊባኖስ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን ተከትሎ ከሥራ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን ለማገዝ በቤሩት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽ/ቤት፣ ከሀገሪቱ መንግሥት፣ ከኢትዮጵያዊን ኮሙዩኒቲ አባላት፣ ከዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ማለትም (IOM, ILO) ኢጋድ እንዲሁም ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማኅበር ጋር በጋራ በተሠሩ ሥራዎች በችግር ላይ ይገኙ የነበሩ ዜጎች እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ በአብነት ጠቅሷል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እስካሁን ለተገኙ ስኬቶች ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረጉ በተለያዩ ሀገርት ለሚገኙ የኮሙዩኒቲ አባላት፣ ኢትዮጵያዊያኑ ለሚገኙባቸው ሀገራት መንግሥታት፣ ለረድኤት ድርጅቶች፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየሠሩ ለሚገኙ የመንግሥት እና የግል ተቋማት እንዲሁም ለበጎ ፈቃደኞች ከፍተኛ ምስጋናውን አቅርቧል።

በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሲካሄድ የነበረው ድርድር በዓበይት ጉዳዮች ላይ በመስማማት መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ
በታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት እና ዓመታዊ የሥራ ክንውን ላይ ያተኮረውና ካለፈው የቀጠለው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ልዩ ስብሰባ ሐምሌ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡
ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የሚያደርጉትን ድርድር አጀንዳው ባደረገው ስብሰባ፣ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር በሆኑት ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ሰብሳቢነት መካሄዱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሦስቱ ሀገራት ልዩነቶቻቸውን አቻችለው ስምምነት ላይ ለመድረስ እንዲችሉ የአፍሪካ ኅብረት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡
ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን የማበጀት ሥራ አስቀድሞ በነበሩ ቀጣናዊ መፍትሔ ሰጪ አሠራሮች አማካኝነት መከወኑንም አድንቀዋል፡፡
በተጨማሪም፣ ግብጽ እና ሱዳንን ፈጽሞ በማይጎዳ መልኩ፣ የአባይን ውኃ ፍትሐዊነት በተሞላበት እና ለሁሉም ተደራሽ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ኢትዮጵያ ባላት ውሳኔ እንደምትጸና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡
በቀጣናው የታየው ወቅታዊ የዝናብ እና የፈሰስ መጠን መጨመር ግድቡን ለመሙላት ሁኔታዎችን አመቺ አድርጓል ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ጸ/ቤት መግለጫ ፣የግድቡን የመጀመሪያ የውኃ ሙሌት እና ዓመታዊ የሥራ ክንውን አስመልክቶ፣ ኢትዮጵያ ሚዛናዊ እና ሦስቱም ሀገራት በፍትሐዊነት ከ ዓባይ ወንዝ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ድርድርን ለማካሄድ ባላት አቋም ትቀጥላለች ብሏል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከተገኘው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የተነሣም፣ የግድቡ የመጀመሪያ ዓመት የውኃ ሙሌት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ውኃው በግንባታ ላይ ያለውን ግድብ አልፎ መፍሰስ መጀመሩን መግለጫው አመልክቷል፡፡
በሀገር መሪዎች እና ርዕሳነ መንግሥታት ደረጃ የተካሄደውን ስብሰባ፣ ሁሉም አካላት በዓበይት ጉዳዮች ላይ በመስማማት ያጠናቀቁ ሲሆን፣ ድርድሩ በስምምነት እንዲቋጭ መንገድ ጠርጓል።
በዚህም መሠረት፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የውኃ ሙሌቱን የተመለከቱ የቴክኒክ ውይይቶች በአፍሪካ ኅብረት በኩል በሚደረገው ሂደት እንዲቀጥሉ እና ወደ አጠቃላይ ስምምነት እንዲደረስ ተስማምተዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት ተጠናቀቀ።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የውሃ ሙሌቱ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ክረምቱ ገና ሳይገባደድ የመጀመሪያው ዙር ሙሌቱ በጥቂት ቀናት ሞልቶ መጠናቀቁና መፍሰስ መጀመሩ ለአገሪቱ ትልቅ የድል ምዕራፍ መክፈቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ላደረገው የኢትዮጵያ ህዝብና በድርድር ሂደት ሙያዊና የዜግነት ግዴታቸውን ለተወጡት ተደራዳሪዎች እንዲሁም ግድቡን አሁን ላለበት ደረጃ እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የአገሪቱ የቀድሞ መሪዎችም ጭምር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአሁኑ ሙሌት በሁለት ተርባይን ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ምዕራፍ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የግድቡ ግንባታ ዳር እንዲደርስ በድፕሎማሲውም ሆነ በግንባታው ሂደት ገና ብዙ ሂደት ይቀረዋል ብለዋል።
በመሆኑም ህዝብና መንግስት በተባበረ ጥረት ለአገራዊ ለውጥና ተጠቃሚነት በጋራ መስራታቸውን እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
የግድቡን ህልውና በዘላቂነት ለማረጋገጥም በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 452 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ፣ የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7 ሺህ 294 የላቦራቶሪ ምርመራ 452 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው እና የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች በቦታ ሲለዩ፦
• ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 301፣
• ከጋምቤላ ክልል 34፣
• ከኦሮሚያ ክልል 19፣
• ከትግራይ ክልል 32፣
• ድሬደዋ 0፣
• ደቡብ ክልል 17፣
• ከሐረሪ ክልል 2፣
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 0፣
• ሲዳማ ክልል 5፣
• ከአማራ ክልል 9፣
• ከሶማሌ ክልል 12 እና
• ከአፋር ክልል 21 ናቸው።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 350 ሺህ 160 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 524 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ቁጥር 188 ደርሷል።
38 የኮሮና ቫይረስ ታካሚዎች ደግሞ በፅኑ ሕክምና መከታታያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለት 58 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 506 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።