YeneTube
120K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ከአራት ሚሊዮን በላይ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ተይዟል።

የፌደራል ፕላን እና ልማት ኮሚሽን የቀጣዮቹ 10 ዓመታት ብሔራዊ እቅድን ከተለያዩ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት እና ምሁራን ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በቀጣዮቹ 10 ዓመታት መንግስት ለዜጎች 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ማስቀመጡ ተገልጿል።

እንደ መንግስት እቅድ ከሆነ እነዚህ ቤቶች የሚገነቡት በአገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከተሞች ነው ተብሏል።

እነዚህ መኖሪያ ቤቶች የሚገነቡትም በመንግስት እና በግል ባለሃብቱ ትብብር እንደሚሆንም ተገልጿል።

በዚህ እቅድ መሰረት ከአስር ዓመት በኋላ ለሁሉም ዜጎች ንጹሁ መጠጥ ውሃ ለማቅረብም መታቀዱን ከኮሚሽኑ ሰምተናል።

#EthioFM

@YeneTube @FikerAssefa1
የአፍሪካ ኅብረት በህዳሴ ግድቡ የድርድር ውጤት ሪፖርት ላይ ነገ እንደሚመክር ይጠበቃል።

የአፍሪካ ኅብረት ጠቅላላ ጉባዔ ቢሮ በህዳሴ ግድቡ ድርድር ዙሪያ ሦስቱ ተደራዳሪ ወገኖች ስምምነት በደረሱባቸውና ባልተግባቡባቸው ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔውን ለማሳወቅ ነገ እንደሚሰበሰብ ይጠበቃል።

ይህ ስብሰባ በአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ እንደሚመራ የአፍሪካ ሕብረት በድረገጹ አስታውቋል።

በዚህ ስብሰባ ባሳለፍነው ሳምንት ያለ ስምምነት የተጠናቀቀው የህዳሴ ግድቡ የውኃ ሙሌትና አስተዳደር ድርድር አጠቃላይ ሪፖርትን እንደሚገመግም ተገልጿል።

የአፍሪካ ኅብረት ጠቅላላ ጉባዔ ቢሮ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ባካሄደው ስብሰባ ታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ግብፅና ሱዳን መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የአደራዳሪነት ሚናውን የአፍሪካ ኅብረት እንዲይዝ በወሰነው መሠረት፣ ሦስቱ አገሮች ለ11 ቀናት ሲደራደሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

በዚህ ድርድር ስምምነት የተደረሰባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም መሠረታዊ በሚባሉ ጥቂት ነጥቦች ላይ መቀራረብ ባለመቻላቸው ድርድሩ መቋረጡ አይዘነጋም።

በዚህም ምክንያት የድርድሩን አጠቃላይ ይዘትና የልዩነት ጭብጦችን ከእነ ምክንያቶቻቸውና የመፍትሔ ሐሳቦቻቸው፣ ሦስቱም አገሮች በተናጠል ለኅብረቱ ሪፖርት አቅርበዋል።

የአፍሪካ ኅብረትን በመወከል ድርድሩን የመሩት የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ተወካይና የኅብረቱ የባለሙያዎች ቡድን የጋራ ሪፖርትም፣ ለኅብረቱ ቀርበዋል።

የኅብረቱ ጠቅላላ ጉባዔም በነገው ስብሰባ የቀረቡትን ሪፖርቶች ገምግሞ፣ በቀጣይ አቅጣጫ ላይ ከሦስቱ አገሮች መሪዎች ጋር እንደሚወያይ ይጠበቃል።

#EthioFM

@YeneTube @FikerAssefa1