በጎንደር ከተማ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች በመኖሪያ ቤቱ ተገኝቶበታል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማው የሰላምና የህዝብ ደህንነት መምሪያ አስታወቀ፡፡የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ አንደበት ከበደ ለኢዜአ እንደተናገሩት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው በጎንደር ማራኪ ክፍለ ከተማ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የተደበቀ የጦር መሳሪያዎች ተገኝቶበት ነው።
ከግለሰቡ መኖሪያ ቤት ከተገኙት የጦር መሳሪያዎች መካከል አምስት ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች እና ሁለት ሽጉጦች ይገኙበታል፡፡የከተማው የጸጥታ ኃይል ከህብረተሰቡ በደረሳቸው ጥቆማ ሐምሌ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ማግኘት መቻሉን አቶ አንደበት ተናግረዋል፡፡በተጠርጣሪነት በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን አስታውቃዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በከተማው ቀበሌ 18 ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በድብቅ በተሽከርካሪ ሲንቀሳቀስ የነበረ 7 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ በቀጥጥር ስር መዋሉን የመምሪያው ምክትል ኃላፊ ጨምረው ገልጸዋል።ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያውን ሲያጓጉዝ የተገኘው ተሸከርካሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ሾፌሩ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑንም አመልክተዋል።
Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa1

የትምህርትና ስልጠና መስኩን ከኮቪድ 19 በኃላ ለማስጀመር በሚከናወኑ ቅድመ ዝግጅቶች ላይ ከዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡
#MoSHE
@YeneTube @FikerAssefa1
#MoSHE
@YeneTube @FikerAssefa1
በአማራ ክልል ውስጥ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ተልእኮ ተቀብለው ወደ ክልሉ ሰርገው የገቡ 85 "የጥፋት ሃይሎች" በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ፡፡
ርእሰ መስተዳድሩ በማእከላዊና በሰሜን ጎንደር ዞኖች የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን ትናንት በመረቁበት ወቅት እንደተናገሩት የጥፋት ሃይሎቹ የክልሉን ሰላም በማደፍረስ ክልሉን የግጭት ቀጠና ለማድረግ ተልእኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው፡፡እነዚህ ጸረ-ሰላም ሃይሎች በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ሰርገው የገቡት ጸበልተኛ፣ መነኩሴና የአዕምሮ ህሙማን በመምሰል እንደሆነ የጠቆሙት ርእሰ መስተዳድሩ እኩይ አላማቸውን ሳያሳኩ በህብረተሰቡ ትብብርና ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡የጥፋት ተልእኮ በመቀበል ወደ ክልሉ ገብተው የነበሩት እነዚህ ጸጉረ ልውጥ ግለሰቦች ታዋቂ ሰዎችንና ከፍተኛ አመራሮችን የመግደል፤ በሃይማኖት ተቋማትና በታሪካዊ ቅርሶች ላይ ጉዳት ለማድረስ እቅድ ይዘው የገቡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
#ENA

ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ አንድ መንደር በሙሉ ኳራንቲን ተደረገ!
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ 24 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የኮሮና ቫይረስ ከሌሎች አካባቢዎች በላቀ ሁኔታ በስፋት በመታየቱ አንድ መንደር በሙሉ ተለይቶ ኳራንቲን መደረጉ ታወቀ።አዲስ ማለዳ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ስፍራው ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ኦክስፋም ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ‹‹አስቤስቶስ›› የተባለ መኖሪያ መንደር ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን አረጋግጠዋል። ከሐምሌ 15 /2012 ጀምሮ ከመኖሪያ መንደሩ መውጣት እና ወደ መንደሩ መግባት እንደማይቻል ለማወቅ ተችሏል።
በአሁኑ ሰዓት በተዘጋው መንደር ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደተናገሩት የኮቪድ ምርመራ እየተካሔደ እንደሆነ እና ናሙና እየተወሰደ እንደሆነ ታውቋል። ከመንደሩ መዘጋት ጋር ተያይዞም ከቀናት በፊት በመንደሩ ውስጥ ከሰባ በላይ ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በመታመኑ እንደሆነም ነዋሪዎች ተናግረዋል።ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ አንድ መኖሪያ መንደር ቫይረሱ በስፋት ተሰራጭቷል በሚል በመንግስት ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ እና እንቅስቃሴ እንዳይኖር መደረጉ የሚታወስ ነው።
Via Addis Maleda

የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤትን ለጉብኚዎች ክፍት ለማድረግ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።መኖሪያ ቤቱ ከኅዳር 2013 በኋላ የእድሳትና ጥገና ሥራ ተጠናቅቆ ለጉብኝት ክፍት እንደሚሆን ኢዜአ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
ሀይሌ ሪዞርት በዝዋይ እና በሻሸመኔ ከተሞች ለወደመበት ኢንቨስትመንት መንግስት ድጋፍ ካደረገ ወደ ስራው እንደሚመለስ አስታውቋል።
የድርጅቱ ባለቤት አትሌት ሃይሌገብረስላሴ አንዳለው የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞትን ተከትሎ በዝዋይ እና ሻሸመኔ ከተሞች በስራ ላይ የነበሩት ሆቴሎች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል። አትሌት ሃይሌ ከዚህ በፊት በነዚህ ከተሞች የነበረውን ኢንቨስትመንት ማቋረጡን ያስታወቀ ቢሆንም አሁን ግን መንግስት ለወደመበት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንት ድጋፍ ካደረገለት ወደ ስራ እንደሚመለስ ገልጿል።
የዝዋዩን ሪዞርት ወደ ስራ ለመመለስ ከአንድ ዓመት በላይ የጥገና ጊዜ የሚፈጅ ሲሆን የሻሸመኔው ሀይሌ ሪዞርት ቅርንጫፍ ግን የግድ እንደ አዲስ መገንባት ስለሚጠይቅ ወደ ስራ ለመመለስ በትንሹ ሶስት አመታትን እንሚፈጅ አትሌት ሀይሌ ተናግሯል።የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከዚህ በፊት በነበሩ ሁከቶች ምክንያት ለወደሙ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በባለሙያ በማስጠናት ካሳ መክፈሉ ይታወሳል። የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ቢሮ ባሳለፍነው ሳምንት ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት በኋላ በተፈጠሩ ሁከቶች በክልሉ ለወደሙ ኢንቨስትመንቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ መናገሩ አይዘነጋም።
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa

የፌዴራል ስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን 3 ሚሊየን የስራ እድሎችን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መፍጠሩን ተናገረ፡፡
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ደግሞ 330 ሺ ስራዎች ከስመዋል ብሏል፡፡ባለፈው ዓመት ከተፈጠሩት የስራ እድሎች 62 በመቶዎቹ ቋሚ ሲሆኑ 38 በመቶዎቹ ጊዜያዊ ናቸው ተብሏል፡፡ከተፈጠሩት የስራ ዕድሎች ውስጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ 1.1 ሚሊየን የስራ ዕድሎችን በአነስተኛና ግዙፍ ማኒፋክቸሪ ዘርፍ በመፍጠር ከፍተኛውን ደረጃ ይዟል፡፡ግብርና ደግሞ በአነስተኛ መስኖ በሚመረቱ የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ 900 ሺህ የስራ ዕድሎችን በመፍጠር ተከታዩን ደረጃ ይዟል፡፡በስራ እድል ተጠቃሚነት ደረጃ ባለፈው ዓመት የሴቶች ተጠቃሚነት ዝቅተኛ እንደነበር ኮሚሽኑ ዛሬ ከሰጠው መግለጫ ሰምተናል፡፡የኢፌድሪ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን በቀጣይ 5 ዓመታት 14 ሚሊየን የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ውጥን መያዙን ተናግሯል፡፡
#Sheger

በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ የተቀሰቀሰዉ ግጭት እየተባባሰነዉ ተባለ!
በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌያት ከባለፈው እሁድ ጀምሮ የተነሳው ግጭት እየተባባሰ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ እንዳሉት በአዋሳኝ ቀበሌያቱ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ከቀናት በፊት በተነሳው ግጭት አሁንም ሰዎች እየሞቱ ፣መኖሪያ ቤቶችም እየተቃጠሉ ይገኛሉ። የኮንሶ ክላስተር በተባለ ስፍራ ነዋሪ ነኝ ያሉ አንድ የዓይን እማኝ ቦርቆራ ቀበሌ ከለንጎ በተባለ መንደር ሰዎች ሲገደሉና ቤቶች ሲቃጠሉ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
የከለንጎ መንደርን ጨምሮ በእነኝሁ አካባቢዎች እስከአሁን አስራ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን እንደሚያውቁ የዓይን እማኙ ለዶቼ ቨለ በስልክ ገልጸዋል።የኮንሶ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ሃሰን ወላሎ በሁለቱ የማህበረሰብ አባላት መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ ሌሎች ቀበሌያት በመስፋቱ በቀላሉ ለመቆጣጠር መቸገራቸውን ገልጸዋል። ሃላፊው እስከትናነት ደርሶኛል ባሉት መረጃ አስራ አንድ ሰዎች መገደላቸውንና በሁለት መንደሮች ውስጥ የነበሩ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ተናግረዋል።
ከባለፈው እሁድ አንስቶ በአካባቢው የተከሰተው ግጭት ከዚህ በፊት ከታዩት የከፋ መሆኑን የጠቀሱት የመምሪያው ሃላፊ በአሁኑ ወቅት የክልሉ የጸጥታ አባላት ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ሁኔታውን ለመቆጣጠር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌያት በተከሰተው ግጭት ዙሪያ የደቡብ ክልል መስተዳድርም ሆነ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ እስከአሁን በጉዳዩ ላይ ያሉ ነገር የለም።
#DW

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት 409 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ9 ሰዎች ሕይወት አልፏል!
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 898 የላብራቶሪ ምርመራ 409 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 933 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በትዊተር ገፃቸው ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።
ከዚህ ባለፈ የ9 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 197 መድረሱንም አመላክተዋል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 139 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 645 መድረሱም ተገልጿል።

በሻሸመኔ ከተማና በምእራብ አርሲ በ10 ወረዳዎች በሁከትና አመጽ ወንጀል የተጠርጣሩ 1 ሺህ 523 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ፍርድ ቤት የቀረቡት 1 ሺህ 523 ግለሰቦች የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ÷ በሻሸመኔ ከተማ እና በምእራብ አርሲ 10 ወረዳዎች በተፈጠረ ሁከትና አመጽ፣ በሰው ህይወት ላይ ለደረሰው ጥፋት ፣በንብረት ላይ ለደረሰው ውድመትና በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው።በሻሸመኔ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና በምዕራብ አርሲ 10 ወረዳዎች በሚገኙ ፍርድ ቤቶች በቀረቡ ተጠርጣሪዎች ላይ መርማሪ ፖሊስ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ድርጊት ገልጿል።
የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል የጥምረት መርማሪ ፖሊሶች በሻሸመኔ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአጠቃላይ 553 ተጠርጣሪዎችን ያቀረቡ ሲሆን ÷ከዚህ ውስጥ 97ቱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።በሌላ በኩል በምእራብ አርሲ ዞን በ10 ወረዳ ፍርድ ቤቶች 970 ተጠርጣሪዎች የቀረቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 54ቱ ሴቶች ናቸው ተብሏል።ተጠርጣሪዎቹ በተጠቀሱት አካባቢዎች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ÷ በሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ለደረሰ የሰው ህይወት መጥፋት ፣ የግልና የመንግስት ንብረት ፣ መውደም እና ዘረፋ ተጠርጥረው ምርመራ እየተከናወነባቸው መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።
የአስከሬን ምርመራ እና የወደመው ንብረትን በባለሙያ ለማስገመት እየሰራ መሆኑን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ የሰውና የተጠርጣሪ ቃል መቀበሉን ተናግሯል።ከዚያም ባለፈ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለመሰብሰብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ሲል ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው በዋስ እንዲፈቱ የጠየቁ ሲሆን÷ የሻሸመኔ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የምዕራብ አርሲ ወረዳ ፍርድ ቤቶች የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜን ፈቅደዋል።የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅ ከሃምሌ 28 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
#FBC

በአራዳ ክፍለ ከተማ በህንፃ ግንባታ ላይ በደረሰው የመደርመስ አደጋ የ1 ሰው ህይወት ሲያልፍ በ3 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ!
በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚደረግ የማስፋፊያ ግንባታ ስራ ላይ በተሰማሩ ሰራተኞች ጉርጓድ በመደርመሱ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በሁለት ሰራተኞች ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡የአራዳ ቅ/ጽ/ቤት ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር መስፍን እሽቱ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ዛሬ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ገደማ ነው፡፡በዕለቱ በግንባታ ስራ ላይ ከተሰማሩት 16 ሰራተኞች ውስጥ ሶስቱ ጉርጓድ ቁፋሮ ላይ ተሰማርተው በስራ ሂደት ላይ እንደነበሩ የመደርመስ አደጋው እንደደረሰባቸው ኮማንደር መስፍን ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ፖሊስና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች 7 ሰዓታትን በፈጀው የህይወት አድን ስራ ሁለት ሰራተኞችን በህይወት ማግኘት የተቻለ ሲሆን ወደ አቤት ሆስፒታል ለህክምና መወሰዳቸውን ኮማንደር መስፍን ተናግረዋል፡፡አንድ ሰራተኛ ግን ህይወቱ ማለፉን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደ ተደረመሰው ህንጻ ገብተው የህወት አድን ስራውን ለመስራት መግቢያ መንገድ አለመኖሩ የህይወት አድን ስራውን አደጋች እንዳደረገውም አመልክተዋል፡፡
#ETV

የቀድሞ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ምካፓ አረፉ!
ታንዛኒያን ከ1995-2005 እአአ ለአስር አመታት የመሯት ምካፓ በተወለዱ በ81 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። የወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ከሰዓታት በፊት እንዳሳወቁት በዳሬሳላም በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ሌሊት ለዛሬ አጥቢያ ማረፋቸውን አልጃዚራ ዘግቧል።

ኦነግ አመራሮቹ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና የት እንደታሰሩ እንደማያውቅ ገለፀ!
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ ከፍተኛ አመራሮቹና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ ከታሰሩ አሥራ አምስት ቀናት ቢያልፉም ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።ግለሰቦቹ ስለሚገኙበት ሁኔታ ፓርቲው ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቻቸውም ጭምር እንደማያውቁ ተናግረዋል።
የኦሮምያ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጂብሪል መሐመድ በበኩላቸው ግለሰቦቹ የት እንደሚገኙ እንደሚታወቅ ገልፀዋል። “ታስሮ ፍርድ ቤት ያልቀረበ፣ወይንም የምርመራ ውጤቱ ያልተጀመረ፣ ወይንም ተመርምሮ መዝገብ ያልተደራጀበት ሰው የለም” ብለዋል።ግለሰቦቹ የታሰሩት ኢትዮጵያ ውስጥ በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋት፣ አካል መጉደል እና ንብረት መውደም ተጠርጥረው እንጂ ከፖለቲካ ፓርቲ ሥራቸው ጋር በተያያዘ እንዳልሆነም ተናግረዋል።
#VOA

ኢትዮጵያ እና ጃፓን የ490 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ተፈራርመውታል፡፡ገንዘቡ በኢትዮጵያ ኪቪድ19ኝን ጨምሮ በጤናው ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግና ለህክምና ቁሳቁስ መግዣ የሚውል ነው ተብሏል፡፡ሁለቱን የከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በማቅረብ የጤና ስርአቱን ለማዘመን ለሚደረገው ጥረት ይውላልም ነው የተባለው፡፡በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ድጋፉ በኢትዮጵያ ኮቪድ19ኝን ጨምሮ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት እንደሚውል ተናግረዋል፡፡

ከሰኔ 15 የአማራ ክልል መሪዎች ግድያ ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ለሐምሌ 24 ተቀጠሩ፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰኔ 15 የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ግድያ የተጠረጠሩ ሰዎችን የእምነት ክህደት ቃል ተቀብሎ በማጠናቀቁ ማን ለማን ያስረዳል የሚለውን ዝርዝር በቁጥር እንዲያቀርብ ለዐቃቢ ሕግ ትዕዛዝ በመስጠት ለሐምሌ 24 ቀጠረ፡፡የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ረፋዱን ባስቻለው ችሎት በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ግድያ የተጠረጠሩትን በእነ ሻምበል መማር ጌትነት መዝገብ የተከሰሱ 49 በማረሚያ ቤት የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ከዚህ በፊት ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል፤ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱን መፈጸም አለመፈጸማቸውን የዕምነት ክህደት ቃል በመቀበልም ዛሬ አጠናቅቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በከፊል ሥራ እንዲሠራ በወሰነው መሠረት 49 ተከሳሾችን በአንድ አድርጎ ጉዳያቸውን ማየት የኮሮናቫይረስን በማስፋፋት የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በመረዳት እና ጉዳዩ ደግሞ መታየት አለበት የሚል ውሳኔ ላይ በመድረሱ በአንድ ጊዜ 6 ተከሳሾችን ችሎት እንዲቀርቡ በማድረግ የ49 ተከሳሾችን የዕምነት ክህደት ቃል ተቀብሏል፡፡ ሁሉም ተከሳሾች ድርጊቱን አልፈጸምንም በሚል ክደው ተከራክረዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪዎችን ድርጊቱን አልፈጸምንም በሚል ክዶ መከራከር መሠረት በማድረግ ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸው 167 ምስክሮች ወደ መስማት የሚሄድ በመሆኑ ሁሉንም ምስክሮች በአንድ ጊዜ ለመስማት ከወረርሽኙ አንጻር ስለማይቻል የትኛው ምስክር ማን ለማን ያስረዳል የሚለውን ለይቶ እንዲያመጣ ፍርድ ቤቱ ለዐቃቤ ሕግ ትዕዛዝ ሰትቷል፡፡ በዚህም መሠረት ዐቃቤ ሕግ ፍርድ ቤቱ ባዘዘው መሠረት ባለማምጣቱ ማን ለማን ያስረዳል የሚለውን ዝርዝር በቁጥር እንዲያቀርብ ለዐቃቤ ሕግ ትዕዛዝ በመስጠት ችሎቱ ለሐምሌ 24 ቀን 2012ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ምንጭ፡-የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/AMMA

አቶ ልደቱ አያሌው በቁጥጥር ስር ዋሉ!
ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ዛሬ ሐምሌ 17/2012 ረፋድ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያዊያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ።የፓርቲው ፕሬዘዳንት አዳነ ታደሰ በፓርቲው ፌስ ቡክ ገጽ ላይ እንዳሰፈሩት መጥሪያ የያዙ ፖሊሶች ልደቱን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት በስልክ ደውለው እንደነገራቸው እና በመጥሪያውም ላይ በቢሾፍቱ ከተማ የተቀሰቀሰውን ቀውስ አስተባብረሀ፣ በገንዘብ ደግፈሀል በሚል ጥርጣሬ እንደሆነ አስታውቋል።
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa1
ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ዛሬ ሐምሌ 17/2012 ረፋድ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያዊያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ።የፓርቲው ፕሬዘዳንት አዳነ ታደሰ በፓርቲው ፌስ ቡክ ገጽ ላይ እንዳሰፈሩት መጥሪያ የያዙ ፖሊሶች ልደቱን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት በስልክ ደውለው እንደነገራቸው እና በመጥሪያውም ላይ በቢሾፍቱ ከተማ የተቀሰቀሰውን ቀውስ አስተባብረሀ፣ በገንዘብ ደግፈሀል በሚል ጥርጣሬ እንደሆነ አስታውቋል።
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa1
YeneTube
አቶ ልደቱ አያሌው በቁጥጥር ስር ዋሉ! ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ዛሬ ሐምሌ 17/2012 ረፋድ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያዊያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ።የፓርቲው ፕሬዘዳንት አዳነ ታደሰ በፓርቲው ፌስ ቡክ ገጽ ላይ እንዳሰፈሩት መጥሪያ የያዙ ፖሊሶች ልደቱን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት በስልክ ደውለው እንደነገራቸው እና በመጥሪያውም ላይ በቢሾፍቱ ከተማ የተቀሰቀሰውን…
አቶ ልደቱ አያሌውን ሸገር ኤፍ ኤም በስልክ እንዳገኛቸው ዘግቧል፡፡
አቶ ልደቱም ስልካቸውን አንስተው የኦሮሚያ ፖሊስ ባቀረበው መጥሪያ መሰረት የፌዴራል ፖሊስ ለእነሱ አስረክቦኛል ብለዋል፡፡
“አሁን ከኦሮሚያ ፖሊሶች ጋር ወደ ቢሾፍቱ እየሄድኩኝ ነው” ያሉት አቶ ልደቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አረጋግጠዋል፡፡
አቶ ልደቱ የኦሮሚያ ፖሊስ በቢሾፍቱ ከተቀሰቀሰው ሁከት ጋር በተያያዘ ክስ ሊመሰርትባቸው በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው የነገራቸው መሆኑን ለሸገር ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 15ኛ መደበኛ ጉባኤ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል፡፡ጉባኤው ሐምሌ 20 እና 21 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድም ታውቋል፡፡
#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ በመኸር እርሻ 7 ነጥብ 75 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ!
በዚህ ዓመት በመኸር እርሻ 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማረስ የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ እስከ አሁን 7 ነጥብ 75 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።
#ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በዚህ ዓመት በመኸር እርሻ 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማረስ የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ እስከ አሁን 7 ነጥብ 75 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።
#ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ፣ 5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን ጉባዔውን ሐምሌ 18 እና 19 እንደሚያካሂድ የጨፌው አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ሎሚ በዶ አስታወቁ።
አፈ-ጉባዔዋ በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ጨፌው በሁለት ቀን ውሎው የ2012 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም እንደሚገመግም እና የ2013 በጀት እንደሚያፀድቅ ጠቁመዋል። በተጨማሪም የሕግ ማርቀቅ እና በተጓደሉ አመራች ቦታ ሹመት ማፅደቅ ሥራ የሚሠራ መሆኑን አብራርተዋል።