YeneTube
120K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኮቪድ 19...

በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ፍጥነት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ ህክምናዎች ዳይሬክተር ዶክተር ማይክ ረያን በሰጡት ማብራሪያ፥ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ስርጭት ፍጥነት እየጨመረ የመጣበት ጊዜ ላይ በመሆኑን በመጥቀስ ፤ ይህም እንደሚያሰጋቸው ነው ያስታወቁት።

እስከ ቅርብ ጊዜ በአፍሪካ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ጋር ሲነፃፀር እምብዛም እንዳልነበረ ነው የገለፁት።

በአፍሪካ እስካሁን 725 ሺህ ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፥ 15 ሺህ ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል፤ ይህም አፍሪካ በዓለም ላይ በቫይረሱ ዝቅተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ክፍለ አህጉሮች ከኦሽኒያ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።

ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የቫይረሱ ስርጭት አስጊ በሆነ ፍጥነት እየጨመረ የመጣ ሲሆን ፤ በተለይም በደቡብ አፍሪካ ያለው ስርጭትን እንደማሳያነት መነሳት ይችላል።

በደቡብ አፍሪካ ባሳለፍነው ቅዳሜ ብቻ በአንድ ቀን በ13 ሺህ 373 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይሰር የተገኘ ሲሆን፥ ይህም በዓለም ላይ በአንድ ቀን ከፍትኛ ቁጥር ካስመዘገቡ ሀገራት 4ኛ ደረጃን ያየዘ መሆኑ ተገልጿል።

በሀገሪቱ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ350 ሺህ የበለጠ ሲሆን ፤ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ5 ሺህ አልፏል ፤ ይህም በአፍሪካ ከፍተኛው ቁጥር መሆኑም ነው የተመላከተው።

በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም ባሳለፍነው ሳምንት በሀገሪቱ ያለው የስርጭት መጠን በ30 በመቶ ብቻ እንደጨመረም አመላክተዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት የቫይረሱ ስርጭት በኬንያ በ31 በመቶ፣ በማዳካስካር በ50 በመቶ፣ በዛምቢያ በ57 በመቶ እንዲሁም በናሚቢያ በ69 በመቶ መጨመሩንም አስታውቅዋል።

አሁን ላይ የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካ ምድር ላይ በከፍተኛ ፍጥነት የሚሰራጭበትን ጊዜ መመልከት እየጀመርን ነው ያሉት ዶክተር ማይክ ራያን፤ “ይህ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የማንቂያ ደውል ሊሆን ይገባል” ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።

#AlJazeera

@YeneTube @FikerAssefa1