በደቡብ ጎንደር ዞን የላይ ጋይንት ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ታረቀኝ ዮሴፍ፣ በላይ ጋይንት ወረዳ የደሮ ቀበሌ በስራ ላይ እንዳሉ ለጊዜዉ ማንነታቸዉ ባልታወቁ ሀይሎች በጥይት መገደላቸውን የወረዳው ኮምኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ከዚህ አለም በሞት ተለየ!
ታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ ዘፋኝና፣ የዘፈን ግጥም ደራሲ የሆነው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ በገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በጥይት የተመታ ሲሆን፣ ወደ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ማዳን ሳይቻል ቀርቷል። R.I.P!
ምንጭ: አዲስ ስታንዳርድ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ለኢቢሲ እንደተናሩት፥ የከተማዋ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ግድያውን በመፈፀም የተጠረጠሩ የተወሰኑ ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በወንጀሉ ምርመራ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ነው ያመለከቱት።አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በከተማዋ ሰላማዊና የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን ያመለከቱት ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ አሳስበዋል።
Via EBC/FBC
@YeneTube @FikerAssefan

የአርቲስት ሃጫሉ ሽኝት ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ወደ ትውልድ ስፍራው አምቦ!
በሺዎች የሚቆጠሩ የአርቲስቱ አድናቂዎች አሸኛኘት እያደረጉለት ይገኛሉ።
#OMN
@YeneTube @FikerAssefa
በሺዎች የሚቆጠሩ የአርቲስቱ አድናቂዎች አሸኛኘት እያደረጉለት ይገኛሉ።
#OMN
@YeneTube @FikerAssefa
ኮቪድ 19
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5 ሺህ 186 የላብራቶሪ ምርመራ 294 ሠዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው እና የ2 ሠዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በቫይረሱ የተያዙ ሠዎች 209 ከአዲስ አበባ ፣ 31 ከትግራይ ፣ 20 ከጋምቤላ ፣ 13 ከኦሮሚያ፣ 4 ከድሬደዋ ፣ 9 ከአማራ፣ 6 ከአፋር ፣ 2 ከሶማሌ ክልል ናቸው፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሠዎች ቁጥር 8,475 የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፉ ቁጥር ደግሞ 148 ደርሷል፡፡
በዛሬው እለትም ሃምሳ አንድ (51) ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4768 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa1

የኮሮና ወረርሽኝ ባየለበት ወቅት የኩፍኝ፣ የመንጋጋ ቆልፍ እና ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ ክትባቶች በአሳሳቢ ኹኔታ በመቀነሱ በሚሊዮንኖች የሚቆጠሩ ሕፃናት ሕይወት አደጋ ላይ መውደቁን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች አስጠነቀቁ።
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ከተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ጋር በመተባበር በሰጡት መግለጫ "ሕፃናት ከዚህ ቀደም ይሰጡ የነበሩ ክትባቶችን በማጣታቸው የሚፈጠረው ሥቃይ እና ሞት በራሱ በኮሮና ከሚከሰተው የላቀ ነው" ብለዋል። ሁለቱ ተቋማት ይፋ ባደረጉት ጥናት እስካለፈው ግንቦት ከ82 አገሮች አንድ ሶስተኛው በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ከዚህ ቀደም የነበሯቸው የክትባት መርሐ ግብሮች ችግር እንደገጠማቸው ይፋ አድርጓል።
በክትባት መርሐ ግብሮች የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ለመከላከል የሚያስፈልጓቸው ግብዓቶች እጦት፣ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ገቢራዊ የተደረጉ የጉዞ ክልከላዎች እና የጤና ተቋማት ያሉባቸው የባለሙያዎች እጥረት ዋንኛ እንቅፋቶች ናቸው። እነዚህ ችግሮች የክትባት መርሐ ግብሮች እንዲቋረጡ ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ አስገድደዋል ተብሏል።
ቢያንስ 30 የኩፍኝ ክትባት መርሐ ግብሮች በመቋረጣቸው አሊያም የመቋረጥ እጣ ፈንታ ስለተጋረጠባቸው የኩፍኝ ወረርሽኝ እንደገና ሊቀሰቀስ እንደሚችል ተቋማቱ ይፋ ያደረጉት ጥናት ይጠቁማል።
በጎርጎሮሳዊው 2019 ብቻ 14 ሚሊዮን ሕፃናት የነፍስ አድን ክትባቶች አምልጧቸዋል። ከእነዚህ አብዛኞቹ አፍሪካውያን ናቸው። እንደ የዓለም የጤና ድርጅት ከሆነ ከኮሮናም በፊት የክትባት ዘመቻዎች መስተጓጎል ቢገጥማቸውም ወረርሽኙ ችግሩን የከፋ አድርጎታል።
© dwamharic

የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት የግድቡን ተፈጥሯዊ የግንባታ ሂደት በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ ነው – ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ
©FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
©FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
" የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ላይ እጁ የለበትም " ሲል የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ( 'ኦነግ ሸኔ ' ) መሪ ጃል መሮ ( ኩምሳ ድሪባ ) የመንግስትን ክስ አስተባበለ ።
#VOAamharic
@YeneTube @FikerAssefa1
#VOAamharic
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ከአራት ሚሊዮን በላይ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ተይዟል።
የፌደራል ፕላን እና ልማት ኮሚሽን የቀጣዮቹ 10 ዓመታት ብሔራዊ እቅድን ከተለያዩ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት እና ምሁራን ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።
በዚህም መሰረት በቀጣዮቹ 10 ዓመታት መንግስት ለዜጎች 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ማስቀመጡ ተገልጿል።
እንደ መንግስት እቅድ ከሆነ እነዚህ ቤቶች የሚገነቡት በአገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከተሞች ነው ተብሏል።
እነዚህ መኖሪያ ቤቶች የሚገነቡትም በመንግስት እና በግል ባለሃብቱ ትብብር እንደሚሆንም ተገልጿል።
በዚህ እቅድ መሰረት ከአስር ዓመት በኋላ ለሁሉም ዜጎች ንጹሁ መጠጥ ውሃ ለማቅረብም መታቀዱን ከኮሚሽኑ ሰምተናል።
#EthioFM

የኦፌኮ አመራራር አቶ በቀለ ገርባና አቶ ጃዋር መሃመድ ፍርድ ቤት ቀረቡ
የአርቲስት ሀጫሉ ግድያን ተከትሎ አስክሬን በመቀማት እና ሁከት በመፍጠር ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎችም ተጠርጣሪዎች በዛሬው እለት ነው ልደታ ምድብ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እና አራዳ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት።
ከእነ አቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራዳ ተረኛ ወንጀል ችሎት ባሳለፍነው ሰኞ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊሰጥ ይገባል አይገባም በሚለው ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ሐምሌ 9 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ በሰጠው መሰረት ነው ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት።
ባሳለፍነው ሰኞ ሐምሌ 6 2012 ዓ.ም ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር በተያያዘ መርማሪ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት በኦሮሚያ ክልል ወደ ተለያዩ አካበቢዎች ስልክ በመደወል ሁከት እንዲቀሰቀስና ነዋሪዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የመንግስት ደጋፊዎች ላይም ጥቃት እንዲፈጸም ትዕዛዝ ያስተላለፉበት የስልክ ልውውጥ በማስረጃ መልክ ማግኘቱን አስታውቋል።
ከዛም ባለፈ በአቶ በቀለ ገርባ ቤት ባደረገው ብረበራ ሁለት ሽጉጦች መገኘታቸውን እና ፍቃድ ይኑራቸው አይኑራቸው ገና እያጣራ መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ማስታወቁም ይታወሳል።
አቶ በቀለ ገርባ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የለኝም ለቅሶ ለመድረስ በአሸዋ ሜዳ ስሄድ መንገድ በመዘጋቱ ነው የተመለስኩት እና ወደ ኦሮሞ ባህል ማዕከል ያቀናሁት ቢሉም፤ መርማሪ ፖሊስ ግን አስክሬን በሃይል ቀምተው መስቀል አደባባይ ለ10 ቀናት አቆይተው ህዝብን በማስለቀስና ብጥብጥ ለመፍጠር አቅደው የፈጸሙት መሆኑን በምላሹ ጠቅሷል።
ከአቶ በቀለ ገርባ ሁለት ልጆች ጋር በተያያዘ መርማሪ ፖሊስ የአባታቸውን ትዕዛዝ ተቀብለው ሁከት ሲያነሳሱ ነው በቁጥጥር ስር ያዋልኳቸው ያለ ሲሆን፥ ጠበቆቻቸው ደግሞ ልጆቹ ለቅሶ ለመድረስ ከአባታቸው ጋር አብረው ስለተገኙ ብቻ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት ብሏል።
በኤግዚቢትነት ከተያዙት እቃዎች ውስጥ ወደማስረጃነት የሚቀየሩ ጉዳዮችን ለመመርመር ጊዜ እንደሚያስፈልገው ፖሊስ አስታውቋል።
ሰባት መርማሪዎች በተለያዩ የአሮሚያ ክልል አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸው የሰውና የንብረት ጉዳት መጠንን ለመመርመርና ማስረጃ ለመሰብሰብ በማቅናታቸው እነርሱ ይዘው የሚመለሱትንና ሌሎች ማስረጃዎችን ለማሰባሰበ 14 ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል መርማሪ ፖሊስ መጠየቁም ይታወሳል።
ጉዳዮን የተመለከተው ችሎትም የተጠርጣሪዎችን መቃወሚያ አድምጦ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊሰጥ ይገባል አይገባም በሚለው ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ለሐምሌ 9 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ አይዘነጋም።
#FBC

በሰሞኑ የፀጥታ መደፍረስ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም 106 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ
ሰሞኑን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም 106 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ድጋፉ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 55.9 ሚሊዮን ብር፤ ለብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን 50 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የተሰጠ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰጠው ድጋፍም የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ አልባሳት፣ ዱቄት፣ ሩዝ፣ ፓስታና ምስርን የሚያጠቃልል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ድጋፉ የተሰበሰበውም ከሰራተኞች፣ የግብር ግዴታቸውን ካልተወጡ ድርጅቶችና በኮንትሮባንድ ከተያዙ ልዮ ልዮ እቃዎች መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
#EBC

የኮቪድ-19ን ክትባት ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል ከ150 በላይ አገራት ጥምረት ተመሠረተ
75 የበለጸጉ አገራት 90 ከሚደርሱ ድሀ አገራት ጋር በመተባበር ሕዝቡን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመታደግ በጋቪ ፕሮጀክት በኩል ኮቫክስ በተሰኘ መርሐ ግብር በኩል የቅድመ ግብይት ተነሣሽነት ገንዘብ ፈሰስ ሊያደርጉ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የፕሮጀክቱ ዓላማ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመግታት ሀብታም ወይም ድሀ ሳይባል ለሁሉም አገራት ፈጣን፣ ፍትሐዊ እና እኩል የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽ ማድረግ መቻል ነው።
በድምሩ 165 አገራት የተካተቱበት እና 60 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዓለማችንን ሕዝብ የያዙት መንግሥታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ፕሮጀክቱን ለሁሉም ለማድረስ ‘የተያዘው ዕቅድ እውን እንዲሆን ከፍተኛ በራስ መተማመን አሳይተዋል’ ተብሏል።
በዚህም ስብስብ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የቡድን 20 አባል አገራት መካተታቸው ተመልክቷል።
የዓለም አቀፉ የክትባት ትብብር ጋቪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሴዝ በርክሌይ፣ “ኮቫክስ ለኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እውነተኛው መፍትሔ ነው” ብለዋል።
አያይዘውም፣ “በራሳቸው ወጪ መግዛት ለሚችሉም ሆኑ ድጋፍ ለሚሹ ብዙዎቹ አገራት፣ እኩል ዕድል የሚሰጥ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
የኮቫክስ ቤተሰብ መሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት የማፋጠን ልማት፣ ምርት እና ፍትሐዊ የምርመራዎች፣ ሕክምናዎች እና ክትባቶች ተደራሽነት ቁልፍ አካል ነው ተብሏል።
ኮቫክስ በጋቪ፣ የዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ዝግጁነት ፈጠራ ማእከል እና በዓለም ጤና ድርጅት እንዲሁም ባደጉ እና በማደግ ላይ ባሉ አገራት ውስጥ በሚገኙ የክትባት አምራች ለኩባንያዎች ጥምረት የሚመራ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 356 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6 ሺህ 886 የላብራቶሪ ምርመራ 356 ሠዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው እና የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በቫይረሱ ከተያዙ ሠዎች መካከል ከአዲስ አበባ 255 ፣ ከትግራይ 48፣ ከአፋር 1፣ ከሀረሪ 5፣ ከድሬደዋ 11፣ ከአማራ 5፣ ከሲዳማ 4፣ ከሶማሌ 11፣ ከኦሮሚያ 14 ከደቡብ 2 ናቸው፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 323 ሺህ 932 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በቫይረሱ የተያዙ ሠዎች ቁጥር 9 ሺህ 503 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፉ ቁጥር 167 ደርሷል፡፡
በዛሬው እለትም 41 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፡፡
በዚህም በአጠቃላይ በቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4941 መድረሱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
@yenetube @fikerassefa1

ከሰሞኑ ተከስቶ የነበረው የሰላም መደፍረስ እንቅስቃሴ በቁጥጥር ስር ውሎ መረጋጋት መፈጠሩን መንግስት አስታወቀ
በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ የሰላም መደፍረሱ ባጋጠማቸው አካባቢዎች የፀጥታ መዋቅሩ ከህብረተሰቡ ጋር በመናበብ ችግሩን ለመወጣት መስራታቸውን ገልጸዋል።
በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ወደ ፍትህ አደባባይ የሚወጡበት ስርዓት በአግባቡ እየተመራ መሆኑን እና ምርመራው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
የተፈጠረውን ግጭት የማረጋጋት፣ ዜጎችን የማቋቋምና የዕለት ደራሽ ምግብና ቁሳቁስ ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ ባለበት ሁኔታ እንደገና ብጥብጥና ረብሻ እንዲነሳ ጥሪ የሚያስተላለፉ አካላት እንደነበሩ አንስተዋል።
”ጥሪው ቢተላለፍም ህብረተሰቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመተባበር የአመጽ ጥሪዎቹ እንዲከሽፉ አድርጓል” ብለዋል።
”አሁን የምንገኝበት ምዕራፍ ብልጽግናን እውን ለማድረግ የምንረባረብበት ነው” ያሉት አቶ ንጉሱ፤ የብልጽግና ጉዞ አንዱ ቁልፍ አጀንዳ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሆኑን ገልፀዋል።
በግጭት ምክንያት የሚጠፋ ሀብትና ንብረት እንዳይኖር መንግስት ከልክ በላይ መታገሱን ህዝቡ እንደሚገነዘብ ያነሱት አቶ ንጉሱ፤ አሁን የህግ የበላይነትን ለማስከበር ቁርጠኝነት እንዳለ ገልጸዋል።
ሰሞኑን በደረሰው ጉዳት ከቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ የሚገኙ ዜጎችን መደገፍና መርዳት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።
#EBC
@Yenetube @FikerAssefa1

በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ቀን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰወች ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ መመዝገቡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
በ24 ሰዓታት ውስጥ አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰወች ቁጥር 260ሺህ ማለፉን ድርጀቱ ጠቅሶ ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ቀን የተመዘገበ ትልቅ ጭማሪ መሆኑን ነው የተናገረው፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት መረጃ በአንድ ቀን ከሩብ ሚሊዮን ያለፉ ሰወች በወርርሽኙ ሲያዙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነውም ብሏል፡፡
ትልቁ ጭማሪ በአሜሪካ ፣ ብራዚል ፣ ህንድ እና ደቡብ አፍሪካ ሲሆን በአለም ዙሪያ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፉ ሰወች ቁጥርም በአንድ ቀን 7ሺህ 360 ሆኗል፡፡
ከዚህ በፊት በአንድ ቀን በወረርሽኙ የተያዙ ሰወች ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ የተመዘገበው ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ መሠረት በአለም ዙሪያ በቫይረሱ የተያዙ ሰወች ቁጥር በትናንትናው ዕለት ከ14 ሚሊዮን ማለፉ የሚታወስ ነው፡፡

ሲዳማ ክልል...
“በሲዳማ ክልል የህዝቡን መሠረታዊ ጥያቄ የሚመለስ አደረጃጀት እየተዘረጋ ነዉ”
- ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ
ርዕሰ መስተዳድሩ አደረጃጀቱ በአሁኑ ወቅት በክልሉ የአዳዲስ ዞኖች መዋቅርና ነባር ወረዳዎችን መልሶ የሚያጠናከር ስራ እንደሆነ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጓዳኘም ክልሉ የሚመራበት ስትራቴጂና ዓመታዊ እቅድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተለይ የክልሉ አደረጃጀት በዋናነት የህብረተሰቡን ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበና ሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን ለማከናወን በሚያስችል መልኩ የሚዘረጋ መሆኑን አስታውቀዋል።
“አዲስ መዋቅር ለመዘርጋት ጥናት ተካሂዷል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ረገድ ዋና አካሄድ የሚገኘውን ሀብት በቁጠባ በመጠቀም ውጤት ለማስመዝገብና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት ማመቻቸት መሆኑን ገልጸዋል።
ያካሄዱት ጥናት ይህንን የሚደግፍ መሆኑን አመልክተው በዚህም የሲዳማ ክልል በዋናነት በአራት ዞኖች ይደራጃል ብለዋል።
የሚደራጁት ዞኖች ባህሪ ምክር ቤትና ብዛት ያላቸው መስሪያ ቤቶች የሚኖራቸው ሳይሆን 30 ወረዳዎችን በመፍጠርና የመረጃ ፍሰቱን በማቀላጠፍ በቅርበት ድጋፍ እንዲሰጡ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል።
በስድስት ካቢኔ ደረጃ የሚዋቀርና አስተባባሪ ያለው አንድ ዞን ከ50 የማይበልጥ የሰው ኃይል ያለው ሆኖ ዋና ተልዕኮው ክልልና ወረዳን ድልድይ ሆኖ ማገናኘት እንደሚሆን አስታውቀዋል።
ለጊዜው ተጨማሪ ወረዳን ለመክፈት ጥናቱ እንደማያሳይ ጠቁመው ወረዳን እያሰፉ መሄድ ወጪን ማብዛት እንጂ ህዝቡ የሚፈልጋቸውን መሠረታዊ የሆኑ የመንገድ ፣ውሃ፣ጤና፣ ትምህርትና ሌሎችንም አቅርቦት ለሟሟላት አያስችልም ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ “ክልል መሆን በራሱ ትልቅ ሃብት የሚያስገኝና የፈለጉትን ማድረግ የሚያስችል አድርጎ የሚያዩ ወገኖች አሉ፤ እኛ ግን ይህ እንዳልሆነ በፊትም እናውቃለን፣አሁንም በተጨባጭ እያየን ያለነው ይሄንኑ ነው ” ብለዋል።
ባለው ውስን ሀብት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ድህነትን መዋጋት፣መልካም አስተዳደርን ማስፈንና የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቅድሚያ በመስጠት ርብርብ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
እንደ አቶ ደስታ ገለፃ በሚቀጥሉት ዓመታት የትኩረት ማዕከል ሆኖ የሚቀጥለው ወጣቶችን የልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድርግ ነው።
በተመረጡ ዘርፎች ከ100 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማደራጀት በልማት ፕሮጀክቶች ግንባታና በሌሎችም ገበያ ተኮር በሆኑ የስራ መስኮች ለማሰማራት ጥረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ኮቪድ 19...
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 7 ሺህ 334 የላብራቶሪ ምርመራ 704 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም ከፍተኛው ቁጥር መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 207 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 551 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 39 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 30 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣26 ከጋምቤላ ክልል ፣ 3 ሰው አፋር ክልል፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 10 ሰዎች ከድሬ ደዋ አስተዳደር፣ 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 21 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 11 ሰዎች ከሲዳማ ክልል እንዲሁም 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ናቸው።
ከዚህ ባለፈ የ3 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ቁጥር 170 መድረሱንም ነው ሚኒስቴሩ በእለታዊ ሪፖርት ያመላከተው።
በዛሬው ዕለት 196 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5137 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 331 ሺህ 266 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 207 ደርሷል።

በከፊል ዝግ የነበረው የፌደራል ፍርድ ቤቶች የችሎት ስራ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል።
በዚህም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረሰ በሁሉም ፍርድ ቤቶች የመልስ መልስ፣ አስተያየቶች፣ የትዕዛዝ ውጤቶችን ለመቀበል የተቀጠሩ እንዲሁም እልባት ለመስጠት ጥቂት ሂደት የቀራቸው ጉዳዮች እና እስረኛ ያላቸው መዛግብት በየቀጠሮ ቀናቸው የማስተናገድ ስራ ይሰራል።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ቃለ አቀባይ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ነዋይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የሚታዩ ጉዳዮች አስቸኳይነት በዳኛው፣ በፍርድ ቤቱ እንዲሁም በየደረጃው በሚገኝ አመራር አሳማኝነቱ ካልታመነበት ለቀጣዩ አመት የሚቀጠር ይሆናል፡፡
በተጨማሪም ፍርድ ቤቶቹ አዳዲስ መዝገቦችን ማለትም የቀጥታ ክስ፣ ይግባኝ እና አፈጻጸም መዝገቦችን ደግሞ ከነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ማየት ይጀምራሉ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ባለጉዳዮች የሚቀርቡ አቤቱታዎች ይስተናገዳሉም ብለዋል፡፡
ከክልል የሚመጡ የሰበር ጉዳዮች ግን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል ተለዋጭ የስራ አቅጣጫ እስከሚሰጥ አይስተናገዱም።