YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አዲስ አበባ ጉለሌ በሚገኘው ጽ/ቤቱ እየተደረገ ያለው ስብሰባ ከግንባሩ መሪም ሆነ ከግንባሩ ጉባዔ እውቅና ውጭ መሆኑን አንድ የግንባሩ አመራር አባል ገለጹ።

የዛሬው የጉለሌ ስብሰባ በግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራ እና ከአርባ የጉሚ ሰባ የኮሚቴ አባላት አስራ አንዱን እንዲሁም ከጉሚ ሸኔ አባላት ደግሞ አምስቱን ብቻ በማሳተፍ አስራ ስድስት ሰዎች ብቻ እየተሳተፉበት መሆኑንንም የግንባሩ የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በቴ ዑርጌሳ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።በግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር እየተመራ ነው የተባለው ይኸው ቡድን የግንባሩን ሊቀመንበር ጨምሮ ዋነኞቹ የግንባሩ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በሌሉበት የሚያደርገው ውይይት እና የሚወስናቸው ውሳኔዎች በእስር ላይ የሚገኙትን የግንባሩን አመራሮች የከእስር የሚያስለቅቅ እስካልሆነ እና አመራር ለመቀየር የሚደረግ ጥረት ከሆነ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።የቡድኑ አባላት ስብሰባውን ለማካሄድ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ታግዘው ወደ ጽህፈት ቤቱ መምጣታቸው መንግስት ግንባሩን ለመቆጣጠር በሚያመቸው መንገድ እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

«የፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች ከበቀደም ጀምረው ያንን አካባቢ ከበው ነበር። ዛሬ ደግሞ የጽ/ቤት ጠባቂያችንን በግዴታ አስከፍተው ከመንግሥት ነው የተላክነው እዚህ ስብሰባ እንድናደርግ ተፈቅዶልናል።በሰላም ጉዳይ ላይም አብረን እንሰራለን ከፍታችሁ አስገቧቸው ብለው ጠባቂዎቻችንን አስገድደው አስገብተዋቸው አሁንስብሰባ እያደረጉ ነው።»የግንባሩ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖርያ ቤታቸው እንዳይወጡ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጥብቅ ጥበቃ ስር መውደቃቸውንም አቶ በቴ ተናግረዋል።ቀደም ሲል የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎም ሆነ ከዚያ በፊት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ያዋሏቸው የግንባሩ የስራ አስፈጻሚም ሆነ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የት እንደታሰሩ እና በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ እንማይታወቅ አቶ በቴ አስረድተዋል።

«እነዚህ አመራሮች ታሰሩ እንጂ የታሰሩበት ቦታ ፣ ለምን እንደታሰሩ ፣ፍርድ ቤት መቼ እንደሚቀርቡ የሚታወቅ ነገር የለም። ቤተሰቦቻቸውም ሊጠይቋቸው አልቻሉም። በዚህም እኛም እንደ ድርጅት እነዚህን ሰዎች ስናፈላልግ ነበር። ለምን ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎችን ስናስስ ነበር። የፌዴራል፣ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ፖሊስን ብንጠይቅም ልናገናቸው አልቻልንም። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አጠቃላይ ጉባዔውን ሊያካሂድ ከአራት እስከ አምስት ወራት ቀርተውት ነበር ያሉት አቶ በቴ አሁን በጥቂት ሰዎች አማካኝነት የሚካሔደው ስብሰባ አላማው እና ግቡ እንደማይታወቅም ገልጸዋል።የግንባሩን ቀጣይ አቅጣጫ ለመናገር ግን ከስብሰባው በኋላ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ይወስናሉ ሲሉም አቶ በቴ ዑርጌሳ ተናግረዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ያለ ግንባሩ ሊቀመንበር ያካሄደው ስብሰባ ዛሬ መጠናቀቁን አስታወቀ።

ስብሰባው ከሳምንት በፊት በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ የአባላቱ መታሰርና የግንባሩ የወደ ፊት ስራዎች ላይ ለመምከር የተጠራ መሆኑን የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።አቶ ቀጀላ የኦነግ ሊ/መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከ10 ቀናት አንስቶ በመንግስት የፀጥታ አካላት ሲጠበቁ ስለነበር አስቀድሞም እንደማይሳተፉ የተገመተ በመሆኑ ስብሰባው በምክትል ሊቀመንበሩ መካሄዱን ገልጸዋል።ስብሰባው የተካሄደው ሊቀመንበሩን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ «ከእውነት የራቀ» ሲሉ አስተባብለዋል።አቶ ቀጄላ አሁን የአመራር ለውጥ ለማድረግ ፓርቲው ምንም እቅድ እንደሌለውም ገልጸዋል።አቶ ዳውድ ያሉበትን ሁኔታ ማየት አልቻልንም ያሉት የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ስልካቸውም ከባለፈው አርብ ጀምሮ መዘጋቱን አረጋግጠዋል፡፡

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
የትግራይ ክልል የምርጫ ኮምሽን ምዝገባ ጀመረ!

በቅርቡ በትግራይ ክልል ምክር ቤት በአዋጅ የተቋቋመው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምርጫ ኮምሽን የተባለው ተቋም ዘንድሮ ሊያካሂደው ባቀደው ምርጫ ተሳታፊ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎችን መመዝገብ ጀመረ፡፡የኮምሽኑ አመራሮች ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ ፓርቲዎችን ዳግም በኮምሽኑ መመዝገብ ያስፈለገው የምርጫው ተወዳዳሪ ፓርቲዎችን ለመለየት፣ ሀሳባቸው ለመቀበልና ለመደገፍ ታቅዶ መሆኑ አስታውቀዋል፡፡

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
ቻይና እና የአፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ የሚገነባውን የአፍሪካ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና መሥሪያ ቤት የመጀመሪያ ምዕራፍ ለመጀመር ሥምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱን የፈረሙት የቻይና የንግድ ምክትል ምኒስትር ኪያን ኬሚንግ እና የአፍሪካ ኅብረት ማኅበራዊ ጉዳዮች ኮሚሽነር አሚራ ኤልፋዲል ናቸው።መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና መሥሪያ ቤት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 23 ሺሕ 244 ስኩዌር ሜትር ይሸፍናል። ዋና መሥሪያ ቤቱ ሁለት የቢሮ ሕንፃዎች፣ ሁለት የቤተ ሙከራ ሕንፃዎች፣ የድንገተኛ ማዕከል፣ የመረጃ ማዕከል እና ላብራቶሪ ይኖረዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 90,000 ስኩዌር ሜትር ቦታ ለዋና መሥሪያ ቤት ግንባታው አቅርቧል። የኅብረቱ መረጃ እንደሚጠቁመው የሕንፃ ግንባታው 40,000 ስኩዌር ሜትር ላይ ይከናወናል።ግንባታውን ለማስጀመር ስምምነቱ ሲፈረም የአፍሪካ ኅብረት የማኅበራዊ ጉዳዮች ኮሚሽነር አሚራ ኤልፋዲል የአፍሪካ ኅብረት ፕሮጀክቱን በፍጥነት ለማስጨረስ ከቻይና ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በተከተለው አመጽና ሁከት ተጠርጥረው የታሰሩት አቶ እስክንድር ነጋ ከመንግሥትና ለመንግሥት ቅርበት ካላቸው መገናኛ ብዙሀን ውጭ ሌሎች ጋዜጠኞች ችሎት እንዳይገቡ መከልከሉ ተገቢ እንዳይደለ ዛሬ ላቀረቡት አቤቱታ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ የቀጠሮ ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ ችሎቱ ለመገናኛ ብዙሀን ክፍት እንደሆነ በመግለጽ ፖሊስ እንዳይከለክል ማዘዙን የእስክንድር ጠበቃ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።ችሎቱ ፣ ፖሊስ በአቶ እስክንድር ጉዳይ ላይ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ አድርጎ 9 ቀናት ፈቅዷል።ለነሐሴ አንድ 2012 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

#DW
@YeneTube @FFikerAssefa1
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድባቲ እና ቡለን ወረዳዎች ዉስጥ ሠላም ለማወክ ሞክረዋል ወይም ከሰላም አዋኪዎች ጋር ተባብረዋል የተባሉ 20 ሰዎች ታሰሩ።

የታሳሪ ቤተሰቦች እና የሁለቱ ወረዳዎች ነዋሪዎች እንደሚሉት ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት የኦነግ ሸኔ ከተባለዉ አማፂ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸዉ በሚል ነዉ። ከታሰሩት ሰዎች መካከል በመተከል ዞን የሚኖሩ አባገዳዎች ሰብሳቢ ደበሎ ሒካን፣ የሆቴል ባለቤቶችና ነጋዴዎች ይገኙበታል።ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸዉ፣ የመተከል ዞን አስተዳዳሪ አትንኩት ሽታዉ እንዳሉት ሰዎቹ የታሰሩት በአካባቢዉ ለሸመቁ ደፈጣ ተዋጊዎች የጦር መሳሪ፣ ስንቅና ከለላ ሰጥተዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ ናቸዉ።የታሰሩትን ሰዎች ብዛት ግን አስተዳዳሪዉ «ጥቂት» ከማለት በስተቀር ትክክለኛ ቁጥራቸዉን መናገር አልፈቀዱም።በመተከል ዞን የጎሳ ልዩነትን መሠረት ያደረገ በሚመስል ተደጋጋሚ ጥቃት በየጊዜዉ ሰላማዊ ሰዎች ይገደላሉ።በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ብቻ ጉባ በተባለዉ ወረዳ ታጣቂዎች በትንሽ ግምት 13 ሰላማዊ ነዋሪዎች መግደላቸዉ ተዘግቧል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በድጋሚ በጸጥታ ኃይሎች ወደ ቤታቸው መወሰዳቸውን ግንባሩ አስታወቀ።

አቶ ዳውድ በጸጥታ ኃይሎች ተገደው ወደ ቤት እንዲመለሱ የተደረጉት «ለደህንነታቸው ሲባል ነው» የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን የግንባሩ ቃል አቃባይ ቀጄላ መርዳሳ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።የግንባሩ ሊቀመንበር በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጥብቅ ቁጥጥር ስር መሆናቸው በዕለት ተዕለት ስራቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም አቶ ቀጄላ ተናግረዋል። «ባለፈው ጊዜም እንደተነገረው  ከእርሳቸውም አንደበትም የሰማነው ለደህንነታቸው ተብሎ ነው። ነገር ግን ይሄ ጉዳይ በስራቸው ላይ ቢሮአቸው ለመሄድ ተጽዕኖ አለው»ቀደም ሲል የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ባልተገኙበት በተወሰኑ የስራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አማካኝነት ተከናውኖ የነበረው ስብሰባ ዓላማውን ባልተረዱ ሰዎች የስም ማጥፋት ዘመቻ ተካሂዶበት በግንባሩ ላይ ብርቱ ጉዳት ማስከተሉን አቶ ቀጄላ ተናግረዋል።«አሁን ከስብሰባው ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ውዥንብር ብዙ ጥፋት ተከስቷል።መጠነ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሲከፈት ነበር። በስብሰባው ላይ የተሳተፉትን ሁሉ በጠላትነት የመፈረጅ ስራዎች ሀገር ባሉ በግንባሩ አባላት እና ደጋፊዎች ሲከናወን ቆይቷል። «አንዳንድ ሰዎች የሚጽፉትን እያየን ነው በጣም አጥፊ ተግባር ነው » በግንባሩ ውስጥ ተፈጠረ ችግርም አቶ ዳውድ ኢብሳ  ወደ መደበኛ ስራቸው ሲመለሱ ሁሉም ነገር በንግግር ይፈታልም ብለዋል አቶ ቀጄላ ።አያይዘውም  አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ ወደ መኖርያ ቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ከግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር አራርሶ ቢቂላ ጋር መወያየታቸውን ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
በትግራይ ክልል ከተሞች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አስገዳጅ ድንጋጌ ተግባራዊ ሆኗል። በተለይም የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ይታይባታል በተባለችው መቐለ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ መንቀሳቀስ ቅጣት ያስከትላል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
በድሬዳዋ 21 የጤና ባለሙያዎች በሥራቸው ላይ ሳሉ በኮሮና መያዛቸውን አስተዳደሩ አስታወቀ!

በድሬዳዋ 21 የጤና ባለሙያዎች በሥራቸው ላይ ሳሉ በኮሮና መያዛቸውን የከተማ አስተዳደሩ የጤና ቢሮ አስታወቀ። በድሬዳዋ በኮሮና ከተያዙ መካከል 23 ታራሚዎች እና 24 የጸጥታ አስከባሪዎች ይገኙበታል። የዘጠኝ አመት አዳጊን ጨምሮ ለስደት ወደ ጅቡቲ የተጓዙ ኢትዮጵያውያን በተሕዋሲው መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል። የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ይዘሮ ለምለም በዛብህ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በህብረተሰቡ ዘንድ እየታየ ባለው መዘናጋት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱንና ድሬደዋ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ከፍተኛ ስጋት ያለባት ከተማ ሆናለች።በአስተዳደሩ አቅም በፈቀደ መልኩ እየተካሄደ ባለው የኮቪድ ምርመራ ቫይረሱ እየተገኘባቸው ካሉ የህብረተሰቡ ክፍሎች አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸውን ኃላፊዋ አስረድተዋል። 

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እስካሁን 200 ያህል አባላቶቼ ታሰረቡኝ ሲል አማረረ።

በኦሮምያ ክልል የሚንቀሳቀሱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በአንዳንድ ዞኖች ጽ/ቤታቸዉ በመዘጋቱ የፓርቲያቸዉ ሕልዉና አደጋ ላይ መዉደቁን አስታዉቀዋል። የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና የፓርቲ አባላት እስራት ከአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በፊትም ነበረ ሲሉ ተናግረዋል።በተለይ በወረዳ የሚገኙ ጽ/ቤቶቻችን ተዘግተዉብናል ያሉት ዶ/ር መረራ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የታሰሩ አባላቶቻችን ጉዳይ ይጣራልን ብለን ደብዳቤ አስገብተናል ብለዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃለ አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው የኦነግ ዘጠኝ የሥራ አስፈፃሚ አባልት በመታሰራቸዉ፤ ፓርቲዉ በሙሉ አቅሙ እየተንቀሳቀሰ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ከዚህ በፊት በታዩ ጥቃቶች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ሙሉ በመሉ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ከሁሉም በላይ ያለምንም ስጋት መንቀሳቀስ እንዲቻል የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ ያስፈልጋል ተብሎአል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበት ወደ 22.3 በመቶ አሻቅቧል።

የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያሳየው የምግብ ዋጋ ግሽበት 24.9 በመቶ ሲደርስ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት 18.9 በመቶ ደርሷል።የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በሐምሌ ወር "አብዛኛዎቹ የእህል ዓይነቶች እና አትክልት ጭማሪ ያሳዩ ሲሆን ለምግብ ዋጋ ግሽበት መጨመር ከፍተኛ አሰተዋጽዖ አላቸው" ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ሊያሳድር የሚችለውን ማሕበራዊ እና ምጣኔ ሐብታዊ ጫና በተነተነበት እና ባለፈው ግንቦት ይፋ ባደረገው ጥናት ግን በተለይ የምግብ ዋጋ ግሽበት በሚቀጥሉት አምስት ወራት ሊጨምር እንደሚችል ጥቆማ ሰጥቷል።የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቢሮ ትንታኔ ኮሮና በአገሪቱ ሊስፋፋ የሚችልበትን ፍጥነት፤ ወረርሽኙን ለመቋቋም ገቢራዊ የሚደረጉ ክልከላዎችን ክብደት፤ የበረሐ አንበጣ መንጋ እና የውጭ ምንዛሪ ተመን የሚደርስበትን ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት በሶስት ሁኔታዎች የተከፋፈለ ነው።

በትናንታኔው መሠረት ኮሮና በኢትዮጵያ እጅግ ከከፋ እና ወረርሽኙን ለመከላከል ተግባራዊ የሚደረጉ እርምጃዎች ከጠነከሩ የምግብ ዋጋ ግሽበት እስከ 40 በመቶ ሊያሻቅብ ይችላል።ይኼ ሶስተኛው እና አስከፊው ኹኔታ ሊከሰት የሚችለው በወር በኮሮና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሺሕ በላይ ካሻቀበ እና በመላ አገሪቱ ጠበቅ ያሉ ገደቦች ሥራ ላይ ከዋሉ ነው።የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው አቶ አብዱልመናን መሐመድ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የባሰ ገጥሟት ቢያውቅም የዋጋ ግሽበቱ የተባበሩት መንግሥታት ሰነድ ባለው መጠን ከጨመረ ፈታኝ መሆኑ አይቀርም።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
ከትናንት በስትያ ምሽት መዲና ቤይሩትን ባናወጠዉ ሁለት ከፍተኛ ፍንዳታ እስካሁን 10 ኢትዮጵያዉያን መሞታቸዉ መታወቁ ተነገረ።

በቤይሩት ነዋሪ የሆነችዉ ኢትዮጵያዊትዋ ትዕግስት ለዶቼ ቬለ በስልክ እንዳረጋገጠችዉ የአገሪቱ መንግሥት እስካሁን አስር ኢትዮጵያዉያን መሞታቸዉን አረጋግጦአል።በቤይሩት ነዋሪ የሆነችዉ ይህች ኢትዮጵያዊት መዲና ቤይሩት አሁንም በፍርስራሽ ስር የተቀበሩ አስክሪንን እያወጣች መሆኑን ተናግራለች። በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀኔራል ተመስገን ዑመር ትናንት ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት በሊባኖስ ከ 250 እስከ 300 ሺህ ኢትዮጵያዉያን ይኖራሉ ፤ አብዛኞቹ ደግሞ ደግሞ የሚገኙት ቤይሩት ከተማ ዉስጥ ነዉ።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ይችላል ተባለ!

በሃገሪቱ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትሉ የሚችሉ የዝናብ ሁኔታዎች ስለሚኖሩ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሜትርዎሎጂ ኤጄንሲ አስጠነቀቀ። ኤጄንሲው እንዳለው በሃገሪቱ በተከታታይ እየጣለ የክረምቱ ዝናብ ድንገተኛ ጎርፍ አስከትሎ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ብርቱ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ብርቱ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ሲል አሳስቧል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ  የአዋሽ ወንዝ  ከተፈጥሮ ፍሰቱ ሰብሮ በመውጣት በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች  በሰብል እና የግጦሽ መሬቶች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 13 ሰዎች ሲሞቱ በ8 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በጭነት ተሽከርካሪ ላይ ሰዎችን በመጫን በሚከናወነው አገልግሎት የሚደርሰው ጥፋት ከፍተኛ እንዲሆን ምክንያት ነው ተብሏል።የዞኑ ፖሊስ መመሪያ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ተጠባባቂ ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ለዶቼ ቬለ በስልክ በሰጡት መረጃ አደጋው የደረሰው ከወረዳው በሬዳ ገጠር ቀበሌ ወደ ሐረዋጫ ከተማ 21 ሰዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-09576 አ/አ አይሱዙ የጭነት መኪና ሙሉኢሳ ገጠር ቀበሌ ላይ በመገልበጡ መሆኑን አመልክተዋል።ትናንት ምሽት ደረሰ በተባለው በዚህ አደጋ 13 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ስምንት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንም ተናግረዋል። እሳቸው እንደገለጹት ጉዳት ከደረሰባቸው አብዛኞቹ ለንግድ ሥራ ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሱ ናቸው።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደደር ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን እና የሟቾች አስክሬን ቤተሰቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው እየወሰዱ እንደሚገኙም አስረድተዋል።የአደጋው መንስኤ በአካባቢው የነበረው ዝናብና ጉም ተሽከርካሪው ወደኋላ እንዲሸራተት በማድረጉ መሆኑን የጠቆሙት ኢንስፔክተር ቶሎሳ ትክክለኛውን መንስኤ ለማወቅ ለጊዜው የተሰወረውን አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ በክትትል ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በአካባቢው ለሕዝብ የመጓጓዣ አገልግሎት የሚውል ተሽከርካሪ ባለመኖሩ ኅብረተሰቡ በጭነት መኪና እንደሚጠቀም ጠቅሰው ይህም በየጊዜው በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ከፍተኛ እያደረገው መሆኑንም አመልክተዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ማሻሻያዉን ተቃወመ!

የትግራይ ክልል ምክርቤት ያደረገው የምርጫ ስርዓት ለውጥ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተቃውሞና ድጋፍ አስተያየት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህና ሌሎች ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ መግለጫ የሰጠው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በምክርቤቱ የተደረገው ማሻሻያ ተቃውሟል፡፡

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
👍1
ፈረንሳይና ተመድ በቤይሩቱ ፍንዳታ ለደረሰው ውድመት ለመታደግ እርዳታ ሊያሰባስቡ ነው!

በሊባኖስ መዲና ቤይሩት በተከሰተው ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ የደረሰውን ከፍተኛ ውድመት ለመታደግ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመሆን የእርዳታ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ማዘጋጀታቸውን ፈረንሳይ አስታወቀች። መርሃ ግብሩ ነገ እሁድ ከእኩለ ቀን ጀምሮ በቪዲዮ በሚደረግ የቃል መግባት ስነስረዓት እንደሚካሄድ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ዛሬ አስታውቋል።የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው በመርሃ ግብሩ ላይ እንደምትሳተፍ ከወዲሁ አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የመርሃ ግብሩ መ,ዘጋጀቱን እንደሰሙ በሰጡት መግለጫቸው ከፕሬዚዳንት ማክሮን ፣ ከሊባኖስ መሪዎች እና ከተቀረው የዓለምአቀፉ ማሕበረሰብ ጋር ሊባኖስ መረዳት በምትችልበት አግባብ እንመክራለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን» ብለዋል። «ሊባኖስ የደረሰባትን ድንገተኛ አደጋ ሁሉም ማገዝ ይፈልጋል» ሲሉ ትራምፕ አክለዋል።ባለፈው ማክሰኞ በቤይሩት ወደብ ያለጥንቃቄ ለአመታት ተከማችቶ የነበረ አሞንየም ናይትሬት የተባለ የኬሚካል ፈንድቶ ከ150 በላይ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቶ ከ6,000 ሺ በላይ ሰዎችን ለአካል ጉዳት ዳርጎ ከፊሉን የከተማዋን ክፍል እንዳልነበር አድርጓል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
ሰበር ዜና!

የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት ሰዎችን አገደ!

የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሦስት የፓርቲዉ የስራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዱን ገለፀ።ፓርቲዉ የሁለት ቀናት ዝግ ስብሰባዉን ዛሬ ምሽት ሲያጠናቅቅ የተለያዩ ዉሳኔዉች ላይ በመድረስ ነዉ።የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሁለት ቀናት ዝግ ጉባዔዉን ሲያጠናቅቅ በሰጠዉ መግለጫ አቶ ለማ መገርሳን፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋን እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንን ከፓርቲዉ ማገዱን አስታዉቋል። የኦሮምያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ስብሰባዉ እንደተጠናቀቀ ለክልሉ የመንግሥት ቴሌቭዥን «OBN» ዛሬ ምሽት ላይ በሰጡት መግለጫ አቶ ለማ መገርሳ፤ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በፓርቲ ዉስጥ ካላቸዉ ኃላፊነት ተነስተዋል፤ እገዳዉ ኃላፊነታችሁን በአግባብነት አልተወጣችሁም በሚል መሆኑም ታዉቋል። እነዚህ የታገዱት ሦስት ግለሰቦች በነበራቸዉ ኃላፊነት ልክ ለመስራት ዝግጁ ሲሆኑ በማንኛዉም ሰዓት መመለስ አንደሚችሉ ፓርቲዉ መወሰኑን አቶ ፈቃዱ በመግለጫቸዉ ተናግረዋል።አቶ ለማ መገርሳና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን የፓርቲዉ ስራ አስፈጻሚ አባለት የነበሩ ሲሆን ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ ደግሞ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥራቸውን ለቀቁ።

በሀገሪቱ በተቀጣጠለው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ ጠንካራ ትችት የተሰነዘረባቸው የፖሊስ አዛዥ ጃፌት ኮሜ በዛሬው ዕለት የስንብት ደብዳቤ አስገብተዋል።

የኬንያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤትም የኮሜን የስንብት ደብዳቤ ፕሬዝደንት ዊልያል ሩቶ መቀበላቸውን አረጋግጧል።

ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በቦታቸው ምክትል የኬንያ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ዳግላስ ካንጃ መተካታቸውን አስታውቋል።

በሀገሪቱ ላይ የተካሄደውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ያደራጀው ጀነሬሽን Z በአጭሩ ጄን Z የተሰኘው የኬንያ ወጣቶች ስብስብ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል ያሉት የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥልጣናቸውን እንዲቀቁ ግፊት ሲያደርግ ነበር።

ሕዝባዊ ተቃውሞ የበረታባቸው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ትላንት ካቢኒያቸውን መበተናቸው ይታወሳል።

#DW
@Yenetube @Fikerassefa
👍27👏102
የዳኞች አድማ በትግራይ

በትግራይ ክልል የዳኞች የሥራ ማቆም አድማ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። ዳኞቹ ከዚህ በፊትም ከሥራቸው ጋር በተገያያዘ የደኅንነት ስጋት እየተፈጠረ መሆኑን ሲገልጹ ነበር። ትናንት ታዲያ በመቀለ የሚገኙ የሰባቱ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤቶች እንዲሁም የመቀለ ከተማ መካከኛ ፍርድ ቤት ሥራቸውን አቁመው ውለዋል። የሥራ ማቆሙ እርምጃ ዛሬም ቀጥሏል።

ዳኞቹ በዋነኝነት ሥራቸውን ለማቆም ያስገደዳቸውን ሲገልጹም «በዳኞች ላይ የደኅንነት ስጋት ተፈጥሯል፤ በዚህም ምክንያት ሥራችንን ማከናወን አልቻልም ነው» ያሉት። የትግራይ ዳኞች ማኅበር ከቀናት በፊት በተለያዩ ጫናዎች ምክንያት በርካታ ዳኞች ሥራቸውን እየለቀቁ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል። በተለይም ከጾታ ጥቃት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በሚዳኙ ዳኞች ላይ ጫናዎችና ማስፈራሪያ እንደሚደርስም አመልክቷል። እየደረሱባቸው ባለ እንዲህ ያሉ ጫናዎች ምክንያትም ከ138 በላይ ዳኞች ሥራ መልቀቃቸውን የማኅበሩ ፕሬዝደንት አቶ ዳዊት ኃይለ ሥላሴ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
በትናንትናው ዕለት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባለወጣው መግለጫ በፍርድ ቤቶች እና ዳኞች ላይ የሚደርስ ስጋት የሚፈጥር ሁኔታን እንደማይታገስና ፈጣን እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል።

Via:- #DW
@Yenetube @Fikerassefa
👍19😁1