YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ተጨማሪ⬆️

ጥረት ኮርፖሬት ዳሽን ቢራን፣ አምባሰል የንግድ ስራዎች ድርጅትን፣ ጥቁር አባይ ትራንስፖርትን ጨምሮ ከ30 ያላነሱ ድርጅቶችን በስሩ ያስተዳድራል።

@yenetube @mycase27
#ተጨማሪ በአገሪቱ የኤሌክትሪክ ሀይል ስርጭት በፈረቃ ሊደረግ ነው። ሰሞኑን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በግድቦች በቂ ውሀ ባለመኖሩ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ የኢፌዴሪ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የኃይል መቆራረጡ የተከሰተው በተለይ በጊቤ 3 የሀይል ማመንጫ ግድብ በተከሰተው የዝናብ እጥረት ምክንያት የግድቡ ውሀ በመቀነሱ መሆኑን ነው የገለፀው፡፡

በአሁኑ ሰአት በአገሪቱ የ476 ሜጋ ዋት የሀይል እጥረት መከሰቱን የኢፌዴሪ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለሱዳን እና ጅቡቲ ትልክ የነበረውን የኤሌክትሪክ ሀይል እነደምታቋርጥም ተገልጿል፡፡

አገሪቱ ከሀይል ሽያጩ ታገኝ የነበረው 180 ሚዮን ዶላር እንደነበርም ተገልጿል፡፡

በእጥረቱ ምክንያትም የኤሌክትሪክ ሀይል በመላ አገሪቱ በፈረቃ እንደሚሆን ሚንስትሩ ያስታወቁ ሲሆን ከፍተኛ ሀይል የሚጠቀሙ ድርጅቶችም የፈረቃው አካል ይሆናሉ ተብሏል፡፡

በመላ አገሪቱ የኃይል ስርጭቱ በ3 ፈረቃ የተከፋፈለ ሲሆን

ፈረቃ 1 ፡- ከማለዳ 11 ሰአት እስከ ረፋዱ 5 ሰአት

ፈረቃ 2፡- ከረፋዱ 5 ሰአት እስከ ቀኑ 10 ሰአት

ፈረቃ 3፡- ከቀኑ 10 ሰአት እስከ ምሽቱ 4 ሰአት

በፈረቃው መሰረት ሁሉም ተገልጋይ ቢያንስ ባንዱ ፈረቃ የኤሌክትሪክ ሀይል እንደሚያገኝ ተገልጿል፡፡

የፈረቃ የሀይል ስርጭቱ እስከ ሰኔ 30/ 2011 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በቅርቡ በቂ ዝናብ የሚጥል ከሆነ ችግሩ ሊቃለል እንደሚችልም በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

Via EtV
@YeneTube @FikerAssefa
ዶ/ር ዓብይ ለኦነግ ይሠሩ ነበር!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በትናንትናው ዕለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ዶ/ር ዓብይ አሕመድ ለኦነግ መረጃ ያቀብሉ እንደነበር ይፋ አድርጓል።እንደ ኦነግ መግለጫ ዶ/ር ዓብይ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ሠራተኛ በነበሩበት ወቅት ካቀበሉት መረጃ አንዱ፤ በምዕራብ ኦሮሚያ ይንቀሳቀስ በነበረው የግንባሩ አመራር ለገሰ ወጊ ላይ ግድያ ለመፈጸም ልዩ ዝግጅት መደረጉ እንደነበር ተጠቅሷል።

#ተጨማሪ የግል ማስታወሻ
በእስር ቆይታዬ ወቅት፤ ለገሰ ወጊን በቅርበት የሚያውቁ እና አብረውትም በትግል ሜዳ የነበሩ ወጣቶች አጋጥመውኝ ነበር። ስለእሱ ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፦

"የሚደንቅ ባሕሪ የነበረው ጀግና ነበር። ምርጥ ወታደራዊ አሰልጣኝ፣ የሚታገለው ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት ቢሆንም ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ አክብሮትና ፍቅር የነበረው፣ በጣም የተረጋጋ እና ሰው አማኝ ነበር። ይህ አብዝቶ ሰው ማመኑም በ'ወዳጅ' እጅ በተኛበት ለአሰቃቂ ግድያ አበቃው።" ከላይ በተጠቀሰው መግለጫ መሰረት ያ ግድያ ከመፈጸሙ በፊት የዶ/ር አብይ መልዕክት ለድርጅቱ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ታጋዩ ሃላፊነቱን በመውሰዱ ባልተጠበቀ መንገድ የተፈጸመውን አደጋ ማስቀረት አልተቻለም።

https://www.bbc.com/afaanoromoo/oduu-50272740?ocid=socialflow_facebook

Via Woubshet Taye
@YeneTube @FikerAssefa
#ተጨማሪ_ሁለት_መቶ_ሺ_ሊትር ይከፋፈላሉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከነማ ፋርማሲዎች በምርት ላይ ያሉ ተጨማሪ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮችን እንደሚከፋፈል አስታወቀ።

በቀጣይ ቀናት ለከነማ ፋርማሲዎች የሚከፋፈለው ሳኒታይዘር ባለፈው የከተማ አስተዳደሩ ካቀረበው 200 ሺህ ሊትር ተጨማሪ እንደሆነ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ አስታውቀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ማህበራዊ ድህረ ገጽን ለበጎ አገልግሎት ማዋል

በማህበራዊ ድህረገጽን ለበጎ አገልግሎት እናውል! በሚል የሚተዋወቁ ጓደኞች በከፈቱት የቴሌግራም እና የሜሰንጀር ግርፑ ጓደኞችን በማስተባበር

#ለመኮድና #ለፈለገ ህይወት ሆስፒታል አጠቃላይ ግምቱ 158ሺብር የሚጠጋ መከላከያ ቁሳቁሶች አስረክበዋል።

የብክለት መከላከያ 440 N95 ማስክ : 400 ሰርጅካል ማስክ : 96 የፕላስቲክ ጫማዎች : 10 ሱት ጓወን : 60 መከላከያ መነፅሮች አስረክበዋል።

#ተጨማሪ :-
- 3ቴርሞ ሜትር ለደጀን ከተማ የተሰጠ
- 3ቴርሞ ሜትር ለቤንሻንጉል ክልል ለተመረጡ ለሶስት ቀቤሌዎች የተሰጠ

ለመተከል ዞን እና በምስራቅ ጎጃም ለደጀን ከተማ 49000ብር የሚያወጣ 6 ቴርሞ ሜትር(የሙቀት መለኪያ) ተለግሷል።

በኤቫሾው የቴሌግራም ግሩፕና በአምሀራ ኢኮኖሚ ዲስኮርስ የሜሰንጀር ግሩፕ አስተባባሪነት እና ገንዘብ በማዋጣት የተሰበሰበውን ሐብት ገቢ አድርገናል።
@Yenetube @Fikerassefa
#ተጨማሪ

⬆️ ዛሬ ቻይና ውስጥ በከፊል መቃጠል ስለደረሰበት አውሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰጠዉ ማብራሪያ

@YeneTube @FikerAssefa1