ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ኢየሱስ አምላክ መሆኑን የሚያረጋግጡ ጥቅሶች

አምላክ ተብሏል፡፡
ዮሐ. 1:1፣14፣18፣ 10:30፣ 20:28 2ተሰ. 1:12፣ ሮሜ 9:5 ቲቶ 2:13፣ ቆላ. 2:9 ዕብ. 1:3

እግዚአብሔርን አባቱ ብሎ በመጥራት “ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል አድርጓል፡፡”
ዮሐ. 5፡18

ከሰማይ የመጣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ሲጠመቅ ማቴ. 3:16-17፣ ማር. 1:10-11፣ ሉቃ 3:21-22; ዮሐ. 1:32-34

በተራራው ክብር ወቅት፡ ማቴ. 17:5፣ ማር. 9:7፣ ሉቃ 9:35; 2ጴጥ. 1:17

ኢየሱስ ከብሉይ ኪዳኑ ያሕዌ ጋር አንድ ነው፡፡
ሉቃ 1:76 ከሚል. 3:1

ሮሜ 10:13 ከኢዩ. 2:32

ሮሜ 14:9-11 ከኢሳ. 45:23-25 ጋር አነፃፅሩ፡፡

ኢየሱስ መለኮታዊ ባሕርያት ሁሉ አሉት፡፡ እነዚህ ባሕርያት የፈጣሪ ብቻ ናቸው፡፡
ዘላለማዊ፡ ኢሳ. 9:6፣ ዮሐ. 1:1-2፣ 8:58፣ 17:5፣ ዕብ 1:8፣ ራዕ 1:8

በሁሉም ቦታ የሚገኝ፡ ማቴ. 18:20፣ 28:20፣ ዮሐ. 3:13፣ ኤፌ. 1:23

ሁሉን አዋቂ 9:4፣ ዮሐ. 2:24-25፣ 6:64፣ 16:30፣ 21:17፣ ቆላ 2:3

ሁሉን ቻይ፡ ኢሳ. 9:6፣ ማቴ. 28:18፣ ፊል. 3:21፣ ራዕ. 1:8

ራሱን በራሱ የሚያኖር፡ ዕብ. 1:10-12፣ 13:8

ኢየሱስ አምላክ ብቻ የሚሠራቸውን ሥራዎች ሠርቷል፡፡
መፍጠር፡ ዮሐ. 1:3-10፣ ቆላ. 1:16-17፣ ዕብ. 1:2፣3፣10

መግቦት፡ ሉቃ. 10:22፣ ዮሐ. 3:35፣ 17:2፣ ኤፌ. 1:22፣ ቆላ. 1:17

ኃጢአትን ይቅር ማለት፡ ማቴ. 9:27፣ ማር. 2:5-10፣ ቆላ. 3:13

ሙታንን በማስነሳት ፍርድ መስጠት፡ ማቴ. 25:31-32፣ ዮሐ. 5:19-30፣ ሐዋ. 10:42፣ 17:31፣ ፊል. 3:21፣ 2ጢሞ. 4:1

ጸሎትና አምልኮን ተቀብሏል፡ ሉቃ. 24:51-52፣ ዮሐ. 5:23 14:14፣ ሐዋ. 7:59፣ 16:31፣ ፊል. 2:10፣11፣ ዕብ. 1:6

ለበለጠ ንባብ 👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/who-is-god/01-3/
👍2
"ሁለቱ ማንነቶች"
ክፋል ፮
👉 አላህ በ48፥9 ላይ ሙሐመድ ክብር እሚገባው እንደሆነና ይህንንም ዘወትር እንድናውጅ ያዘናል። ነገሩ በዚ አያበቃም አላህ መመስከር ብቻም ሳይሆን እራሱ ያዘዘውን ለሙሐመድ #ገቢ ሲያደርግ በምዕራፍ 33፥56-57 ላይ ይስተዋላል። አሁንም እንደ ቅድሙ በብዙ ትርጉሞች ላይ በተሰራው ማሻሻያ ይህን እውነት ለመደበቅ ቢሞከርም አልተሳካም።
إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسْلِيمًا
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ 33:56
በዚህ አያ ላይ "የአክብሮትን እዝነት" በማለት የተተረጎመችው የአረብኛ ቃል መሰረቷ "#ሰላ" ስትሆን በመዝገበ ቃላት ትርጉሟም
صَلُّو sallu, #yusalli#;
Pray, comfort, console, entertain, allivate, amuse, solace, relieve, divert ...ማለት ነው።
💡ባጭሩ ይሰግዳሉ አልያም ይፀልያሉ ነው። መልካም ይህ ከሆነ ዘንዳ እኛም እንዲህ እንበል፦ ይሰግዳሉ ከሆነ አላህ እንኳ የሚሰግድለት ማነው እርሱ ወገኖቼ?😱
🙏ይፀልያሉ በሚለው እንኳ ብንስማማ፤ አላህ ወደማ ይፀልያል ወገኖች?😱 አላህስ የሚፀልይ ከሆነ አላህ ፈጣሪ አደለም ማለት ነው በእስልምና(በእስልምና አላህ ነጠላ አንድነት ስላለው ማለት ነው)
"ሰላ" ማለት "ባርኮት" ማለት ከሆነ ደግሞ(ማስረጃ ያስፈልገዋል!) መላዕክት እንዴት አላህ በሚያወርደው ልክ ባርኮትን መስጠት ይችላሉ? ባርኮትስ የሚሰጥ አንድ ፈጣሪ ብቻ አይደለም ወይ? 🤔
*ይህ ጥያቄ "የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ" ለሚለውም ትርጉምም ይሆናል ምክንያቱም መላእክት አላህ "ሰላም ይስጥህ!" ይባርክህ አሉት እንኳ ብንል፤ አላህ ከማ? እንዴትና ወደማ? ይህንን አብሮ ይላል? 🤔 (ልብ አድርጉ "አላህና መላዕክቱ" ካለ "#ይሰሉና" ለሁለቱም አንድና ተመሳሳይ ሙያና ተግባር እንደሚሰጥ፤ ስለዚ የቃሉ ትርጉም ሁለቱንም የሚጠቃልል መሆን አለበት።) ...አንድ ፍጡር ሌላን ባረከ ሲባል "ፈጣሪ ይባርክህ!" አለ ማለት ነው፤ ፈጣሪ ባረከ ስንል ግን እራሱ በእሱነቱ ሁሉን አድራጊ ስለሆነ ባለቤትነቱ ራሱ ላይ ያርፋል። ስለዚ በየትኛውም ማሻሻያ ትርጉም አያስኬድም
👉 በዋነኝነት ግን በሰማይም ቢሆን #የአምልኮትና የባርኮት #ማዕከሉ አላህ ሳይሆን #ሙሐመድ መሆኑን እንመለከታለን።
📚 ተፍሲር ኢብኑ ካቲር ለዚህ ቃል ባሰባሰበው ትርጉም " '#የአላህ "#ሰላ" ባርኮቱ ነው #የመላእክት ግን ፀሎታቸውና #ልመናቸው ነው' አቡ አል አሊያህ እንዳሉት።" ብሎ ዘግቦአል። "አት ተርሚዝም '#የመላእክት "#ሰላ" #የይቅርታ ፀሎታቸውና #ልመናቸው ነው' ብሏል።" በማለት ዘግቧል(መላዕክት ይቅርታን ለዛውም #ከሙሐመድ እንደሚጠይቁ ልብ በሉ)። እንግዲ አላህ ባርኮትን ወደ ሙሐመድ ልኳል እንኳ ቢባል እንዴት ነው መላእክት ፀሎታቸውንና የይቅርታ ልመናቸውን ወደ ሙሐመድ የሚልኩት? ይህ ሙሐመድን አምላክ አያደርገውምን? 🤔 መልሱ አለምንም ጥያቄ ያደርገዋል ነው።
🔎 ይህን በይበልጥ የምንረዳው እውነትም ፀሎት ወደ አላህ ብቻ ሳይሆን ወደ ሙሐመድም እንደሚደረግና ሙሐመድም ይህንን እንዳረጋገጠ 📚በጃሚ አት ተርሚዝ ቅፅ 6 ሐዲዝ ቁጥር 3578 ላይ የተዘገበውን #ሳሂህ ሐዲዝ ስናይ ነው።
በዚ ክፍል ላይ አንድ አይነ ስውር ሰው ወደ ሙሐመድ ይቀርብና "ወደ አላህ ፀልየህ ፈውሰኝ::" ብሎ ሲለምነው እናያለን። ሙሐመድም #ራስህ ፀልይ ከማለት ይልቅ አንተ ከፈለግህ #አደርገዋለሁ ብቻ ታገስ ብሎ ሲመልስለት እናያለን። በመቀጠልም ሙሐመድ እንዲህ ብሎ ሰውዬው እንዲፀልይ ያዘዋል..." ኦ አላህ እኔ ወደ አንተ በነብይህ ሙሐመድ በምህረት ነብይ በኩል እመጣለሁ። በርግጥም ወደ ጌታዬ ቀረብሁ፤ #ባንተ(በነብዩ) በኩል ይህን ችግሬን በተመለከተ #መፍትሄን አገኝ ዘንድ። እናም አላህ የነብዮን ምልጃ ተቀበል።" ብለህ ፀልይ ሲለው እንመለከታለን።
በዚህ ፀሎት ውስጥ እየተለመነ ያለው አላህ ብቻ አይደለም መሐመድም እንጂ "#ባንተ በኩል ወደ ጌታዬ መፍትሄን አገኝ ዘንድ እመጣለሁ።" ማለቱ ሙሐመድም የፀሎቱ #ተደራሲ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። በርግጥ ሰውዬው አላህን የሙሐመድን ምልጃ እንዲቀበል የጠየቀ ቢሆንም ግን ችግሩ ያለው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሙሐመድ የፀሎቱ ተደራሲ አካል መሆኑ ነው። "በእርሱ በኩል" ብሎ እንጀመረ ቢቀጥል ኖሮ "#ምልጃ!" እንለው ይሆናል "#ባንተ_በኩል" ካለና #ከመነሾውም ሙሐመድን የፀሎትና ልመና #ተደራሲ አድርጎ መምጣቱ ሙሐመድም ይህንን ሳያርም ጨምሮ ማበረታታቱ ይህ ሐዲዝ ሙሐመድም የልመናው ድልድይ ብቻም ሳይሆን #ከፈፃሚውም_አካል_ተርታ እንደሚሰለፍ ያሳያል። ስለዚ ፀሎት ወደ ሙሐመድ እንደሚደረግ ሌላ ማስረጃ ነው ማለት ነው
👉 እንግዲህ አንድ አካል ልመናን ተቀበለ ወይም ፀሎት ወደ እርሱ ተፀለየ ማለት ተመለከ ማለት ነው ብዬ እሞግታለሁ። ይህንም ለአብነት ያህል 📚በሱናን ኢብን ማጃህ ቅፅ 5 ሐዲዝ ቁጥር 3828 ላይ "...በእርግጥም ልመና(ፀሎት) አምልኮት ነው።" ብለው የአላህ መልእክተኛ ተናገሩ" ተብሎ ተዘግቧል። ይህንንም በዚሁ መፅሐፍ ገፅ 95-96 ላይ ተብራርቶ እናገኘዋለን።
እናም ሙሐመድ በአላህ አማኝ ሁሉ ክብርን #ይሰጠውና ሌት ቀን ያውጅለት ዘንድ ዘንድ ትእዛዝ ወጥቶለታል(48፥9)፤ አላህና መላእክቱ እራሱ #ሲሰግዱለት የአምልኮትም #መዐከል ሆኖ ሲቀርብ ይነበባል(33፥56)፤ የፀሎትም ተደራሽ በመሆን ከአምልኮት ሁሉ #የጠራውን_አምልኮት_ሲቀበል እንመለከታለን(3፥55፣ በጃሚ አት ተርሚዝ ቅፅ 6 ሐዲዝ ቁጥር 3578፣ በሱናን ኢብን ማጃህ ቅፅ 5 ሐዲዝ ቁጥር 3828 ወዘተ መሰረት)።
ስንቋጨው ይህና የመሳሰሉ ንባባትና ድርጊቶች ናቸው እንግዲ "ሰው ብቻ ነኝ" ያለውን 👳ሙሐመድን በዛው መፅሐፍ #አምላክ አድርገው የሚያቀርቡልን። በእስልምና ሙሐመድ ሰውም ብቻ ነኝ እያለ እየተመለከም ነው። #ሁለቱ_የመሐመድ_ማንነቶች እስቲ ደግሞ በቀጣይ መፅሕፍቱና መዛግብቱ ጨምረው ሙሐመድ እንዲህም እንዲያም ነው የሚሉንን እግዚአብሄር ቢፈቅድና ብንኖር እናያለን።
.................//................
" እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:32)
🙏አርነት በእውነት ይሆንላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው!🙏🙏🙏
"ሁለቱ ማንነቶች"
✍️ ክፍል ፯
👉እስልምናን ደርሶና ቀልሶ እንካችሁ ያለው ሙሐመድ ባስተላለፈው ቁርአኑ፣ ሐዲዛቱና ሱናው እራሱን ከሰው በላይ አለፍ ሲልም አምላክ አድርጎ ማቅረቡን በእስካሁኑ "የሁለቱ ማንነቶች" ምንባብ ቃኝተናል። ዛሬ ደግሞ ይህንን በይበልጥ የሚያስረዳልንን ወንድሞችን አንፆ ያፀናውን ሙግት እናያለን።

በእስልምና #ተውሂድ ማለት አሕዳዊ አሐድነትን የሚሰብክና ይህም አንዳንዶች እንደሚሉት በሶስት የሚገለጥ ነው(ግራም ነፈሰ ቀኝ በሦስትም ከፈልነው በሌላ ዋናው የአላህና ለአላህ ብቻ የተባለውን የነካ ተውሒድን ነክቷል)። እነዚህም #ተውሂድ_አር_ሩቡቢያህ#ተውሂድ_አል_አሉህያ እና #ተውሂድ_አል_አስማ_ዋ_አል_ሲፍት የሚባሉት ምድቦች ናቸው። ተውሂድ አል አሉህያህ ማለት አላህ ብቻውን አምልኮ የሚገባውም የሚቀርብለትም አካል እንደሆነ የሚገልፅ ሲሆን ይህን የተውሂድ አንጓ ከበፊት በነበሩት ክፍሎች ሙሐመድ አምልኩኝ እንዳለ አንደተመለከም በማሳየት እንዴት ይህ የእስልምና አምድ በራሱ በእስልምና አፈር ድሜ እንደበላ ሞግቻለሁ። ተውሂድ አል አስማ ዋ ሲፍት ስለ የአላህ ስሞችና አላህ ብቻ ስለሚገለጥባቸው ባህሪዎች የሚያትት ሲሆን ይህንንም እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር በሚቀጥሉት ክፍሎች እንዳስሳቸዋለን።

እንግዲህ ከእነዚህ የመጀመርያው ተውሂድ አር ሩቡቢያህ የሚሰኘው ሲሆን ይህም አላህ ብቸኛ ሉዐላዊ የሆነ #ጌታነትና #ፈራጅነት #መጋቢነትንም የሚተነተንበት ነው። በተጨማሪም አላህ ብቸኛ #ሊጠቅምም #ሊጎዳም የሚችል ሐይል ያለው እሱ ብቻ እንደሆነ ያትታል።
በቁርዐኑ ምዕራፍ 17:79 ላይ
وَمِنَ ٱلَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِۦ نَافِلَةًۭ لَّكَ عَسَىٰٓ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًۭا مَّحْمُودًۭا
"ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ (በቁርኣን) ስገድ፡፡ ጌታህ #ምስጉን_በኾነ_ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል፡፡" 17:79

👉በዚህ አንቀፅ ላይ አላህ ሙሐመድን ምስጉን በኾነ ስፍራ እንደሚያስቀምጠው ይናገራል። ይህ ምስጉን የሆነ ስፍራም ብዙ ሙፈሲሮች በመጨረሻ ቀን አላህ #የማማለድን_የላቀን ቦታ ይሰጠዋል ማለት እንደሆነ ይናገራሉ። ይህ ከሁሉም የላቀ የማማለድ ስፍራን እንዴት አድርጎ አላህ እንደሚያጎናፅፈው ግን የሚነግረን አል ታባሪ በታሪኩ በቅፅ 1 ገፅ 149-151 ላይ ባሰፈረው ከፊል የ17:79 ተፍሲ ር ትርጉም በተሰኘው ክፍል ላይ ነው።(The history of Al-Tabari- General introduction and from creation to flood, translated by Franz Rosenthal[state university of New York press(SUNY), Albany 1989]
✍️ በዘገባው ላይ የ #maqaman_mahmudan ትክክለኛ ትርጓሜ #አላህ_ሙሐመድን_በዙፍኑ_ላይ(በራሱ ዙፋን ላይ) ያስቀምጠዋል የሚል ነው። ይህን ትርጓሜ ለክርክር እንኳ የማይቀርብ ትክክል የሆነ መሆኑን እራሱ ያስረግጥልናል። ስለዚ በለተ ትንሳኤ ሙሐመድ #ማማለዱን የሚተገብረው አላህ ዙፋን ላይ ተቀምጦ 😮 እንደሆነ ምንም አያጠያይቅም። ጥያቄው ሙሐመድ አብሮ ከአላህ ጋር ይቀመጣል ወይስ አይቀመጥም የሚል ይሆናል። ይህንን ነው አል ታብሪ አከራካሪ እንደሆነና እንዲህ ነው እንዲያ የሚሉ #ሶስት አመለካከቶችም አሉበት የሚለው። እኛ ወደዚህ ሐተታ እንኳ ሳንገባ በቀላሉ(በራሱ ብዙ ጥያቄዎችን ያስነሳል) ምን ማለት እንደሆነ ብናይ ይበቃናል።
አላህ በምዕራፍ #17:79 ሙሐመድን ምስጉን በሆነ ስፍራ ማለትም በራሱ ዙፋን ላይ የማስቀመጡ ብሂል እንዲሁ የሚታለፍ አደለም። ይህንን ለማስረዳት በትንሹ የአላህንና የዙፋኑን ምንነት እንይ፦
👉 የአላህ #ኩርሲው(ዙፋኑ) በ2:255 መሰረት በሰማያትና በምድር ሁሉ ላይ የተዘረጋ #የልቀቱ_የከፍተኛነቱ_ምልክት ነው። አላህ ዙፋኑ ወይም #ዐርሹ ማለት በ10:3 መሰረት ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀን ፈጥሮ ሁሉን #የሚያስተናብርበት ይህ ማለት በኢብን አባስ ተፍሲር እንደተቀመጠው #ፍጥረታቱን_የሚመራበት የሚቆጣጠርበት መገለጥንም ቢሆን የሚልክበት ማለት ነው። ሌሎችንም ጥቅሶች መጨመር ይቻላል ባጠቃላይ ግን ዐርሹ ዙፋኑ ኩርሲው የአላህ ከፍጥረቱ ጋር የፈጠረው፣ #ሉዐላዊነቱን፣ ብቸኛ መሪነቱን፣ #ፈራጅቱን ብቻውን የሚከውንበት የመለኮታዊ ስልጣኑን ምልክት መሆኑን እንረዳለን።

🤔ጥያቄ፦ ፩,አላህ ይህንን ሁሉ የሚያደርግበትን የሚከውንበትን ዙፋኑን ለሌላ "ፍጡር" #እንዲቀመጥበትና እንዲወስንበት መፍቀዱ ሉዐላዊነቱንና ብቸኛ ፈራጅነቱን #የሚያጋራ፤ ሙሐመድንም የዚህ ተካፋይ አምላክም የሚያደርግ አይሆንም ወይ? አይሆንም ከተባለ ማስረጃ?
፪, ሌላስ ከነብያት ወይንም ከሰዎች፤ #ከፍጥረታት ይህንን #የተጎነጨ አለን? ከሌለና ሙሐመድ ብቻ ከሆነ #አንድምታው ምንድነው?🤔

✍️ሙግት፦ ከላይ ባነሳሁት መንደርደርያ ሐሳብ መሰረት አላህ ሙሐመድን ተጋሪው አድርጎ አቅርቦታል‼️ ይህንን የማጠነክርበትም በዙፋኑ ላይ መቀመጥ #መቀመጥ_ብቻ እንዳልሆነ በማሳየትና አላህ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ የሚከውነውን ሙሐመድም #መከወኑን በማስረገጥ ነው።
በቁርአኑ ምዕራፍ #17:111 ላይ አላህ ሉአላዊ የሆነና #ለንግስናው ምንም #ተጋሪ የሌለው መሆኑን፤ #18:26 ላይ #ፍርዱንም ለማንም #እንደማያጋራ ተቀምጧል። ስለዚህ አንድ አካል ልክ እንደ አላህ ዙፋኑ ላይ #ከተቀመጠ ከዛም ፍርድን ካስቀለበሰና የማይገባቸውን ካሰጠ ከፍርዱም ከንግስናውም #ተጋራ ማለት ነው። ይህንን አላህ ራሱ ፈቅዶ ካደረገው ደግሞ #አያጋራም እያለ #አጋርቷልና ቁርአኑ እርስ በእርሱ #ተጋጭቷል‼️
📚ኢብን ካቲር በ17:79 ተፍሲሩ ላይ ሙሐመድ ምስጉን በሆነ ስፍራ ላይ ተቀምጦ #እንደሚያማልድ ይነግረናል። ይህም ማማለድ በአይነቱ #ልዮ የሆነና እንደዚህም ያለ ማንም እንዳላደረገ እንደማያደርግም ያትታል። ሲለጥቅም እንዲህ ይላል፦

"... #እርሱ_ስራቸው_ገነት_ለማያስገባቸው ወደ ሲኦልም ይወርዱ ዘንድ ለታዘዘባቸውን ሰዎች ያማልዳል, እነርሱም ተመልሰው #ይመጣሉ።...በገነት ከሁሉም በላጭ የሆነችዋን #አል_ዋሲላህ የተባለችውን ስፍራ የሚደርስባትም እርሱ ነው።..." ተፍሲር ኢብን ካቲር 17:79

👉ይህ ማለት የተፈረደባቸውን እንኳ ሳይቀሩ፤ ስራቸው ገነትን የማያስወፍቃቸው እንኳ ሳይቀሩ እርሱ በአላህ ዙፋን ላይ ተቀምጦ በሚያደርገው ምልጃ ገነት ይገባሉ። ሙሐመድ የአላህ ኩርሲ ላይ መቀመጡና ይህን መሰል ድርጊት መፈፀሙ #ተውሂድ_አር_ሩቡቢያህን የአላህን ብቸኛ ሉዐላዊ ፈራጅነት ዳኝነት ፍጥረትን አስተናባሪነት #የሚጥስና የራሳቸውን ተውሂድንም #የሚንድ ቁርአናዊ አስተምሮት ነው። መቼም አንድ አካል በፈጣሪ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ፈጣሪ የሚያደርገውን ካደረገ፤ የተፈረደን ፍርድ እንኳ አስቀይሮ የማይገባቸውን ገነት ካገባ ይህ ራሱ አምላክ እንጂ፤ የፈጣሪ ተጋሪ እንጂ ሌላ ምንድነው ጎበዝ!
.................//................
" እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:32)
🙏አርነት በእውነት ይሆንላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው!🙏🙏🙏.
አስገራሚ የእስልምና እውነታዎች

ክፍል አንድ
መሀመድ የሚሸናው እንደ ሴት ነበር፡፡  መሀመድ አንደ ወንድ ቆሞ ሸንቶ አያውቅም፡፡ 

ጃሚ አት ቲርሚዲ ምዕራፍ 8 ቁጥር 12 አይሻ እንደተናገረችው መሀመድ ቆሞ ሽንቱን ይሸናል፡፡ ብሎ የነገረህን ሰው እንዳታምነው፡፡ መሀመድ ሁል ጊዜ የሚሸናው ቁጢጥ ብሎ ነበር፡፡ ማለቷን ዘግቦታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 2ኛው ከሊፋ የነበረው ኡመር እንደተናገረው እስልምናን ከተቀበልኩ ጊዜ አንስቶ ቆሜ ሽንቴን ሸንቼ አላውቅም፡፡ ማለቱን በዚሁ ሀዲስ ተዘግቧል፡፡

አስገራሚ የእስልምና እውነታዎች

ክፍል 2

ሰይጣን ጆሮህ ላይ ይሸናብሃል

አቡ ሁሬይራ መሀመድ አብዛኞቹ የመቃብር ላይ ስቃዮች የሚመጡት በሽንት ነው ማለቱን ዘግቦታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰይጣን ሰው ጆሮ ላይ መጥቶ እንደሚሸና መሀመድ ይነግረናል፡፡

ሳሂህ አል ቡኻሪ 1144 አብደላህ እንደተነተነው አንድ ሰው ስሙ ከመሀመድ ፊት ተነሳ፡፡ ሰውየው ለፈጅር ሶላት ከእንቅልፉ ተነስቶ አልመምጣቱ ለመሀመድ ተነገረው፡፡ መሀመድም ሰይጣን ጆሮው ላይ ሸንቶበት ነው፡፡ በማለት መለሰላቸው ሲል ዘግቦታል፡፡

ስለዚህ አንድ ሙስሊም እንቅልፍ ይዞት የሌሊት ሶላት ካመለጠው ደክሞት ወይም ሰንፎ ሳይሆን ሰይጣን ጆሮው ላይ ሸንቶበት ነው ማለት ነው፡፡ ወደ እስልምና እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡

አስገራሚ የእስልምና እውነታዎች

ክፍል 3

የግመል ሽንት ለሆድ ህመም ፍቱን ነው

ሆዳቸውን ለሚያማቸው የግመል ወተትና ሽንት ፍቱን መድሀኒት እንደሆነ መሀመድ ይነግረናል፡፡

ሱናን አነሳይ ቁጥር 307 አናስ ቢን ማሊክ እንደተናገረው ከኡሬይናህ የመጡ የበደዊን ሰዎች ወደ መሀመድ ቀርበው እስልምናን ተቀበሉ፡፡ ነገር ግን የመዲና አየር ንብረት ስላልተስማማቸው ቆዳቸው ወደ ቢጫነት ተቀየረ፡፡ ሆዳቸውም ማበጥ ጀመረ፡፡ መሀመድም የእርጉዝ ግመሎች ወተትና ሽንት ቀላቅለው እስኪሻላቸው እንዲጠጡ ከጠባቂዎቹ ጋር ላካቸው፡፡ ከዛ በኋላ ሰዎቹ የግመሎችን ጠባቂዎች ገደሉ፡፡ ግመሎቹንም አባረሩ፡፡ መሀመድ ሰዎቹን አሲይዞ አስመጣቸው፡፡ እጅና እግራቸው ተቆራረጦ አይናቸው በጋለ ምስማር ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ የሙዕሚኖች የጦር አዛዥ አብዱል መሊክ ለአናስ እንደነገረው እነዘህ ሰዎች የተቀጡት በሀጢያታቸው ሳይሆን እስልምናን ስለከዱ ነበር፡፡ በማለት ዘግቦታል፡፡

ይህ ታሪክ በሳሂህ አል ቡኻሪ ሀዲስም ይገኛል፡፡ በዚህ ሀዲስ የግመሎቹን ሽንትና ወተት ከጠጡ በኋላ አንደተሻላቸው ተዘግቧል፡፡ እኛ ግን አንድ ጥያቄ ልናነሳ ወደድን፡፡ እነዚህ የበደዊን ሰዎች ሽንቱንና ወተቱን ቀላቅለው ከጠጡ በኋላ ከተሻላቸው የግመል ጠባቂዎቹን መግደልና እስልምናን መክዳት ምን አስፈላጋቸው፡፡ መልሱ ግልጽ ያለ ነው፡፡ መሀመድ እንዲወስዱ የነገራቸው መድሃኒት ምንም ሊያሽላቸው የሚያስችል ባለመሆኑና ሀይማኖቱ የውሸት እንደሆነ ስላወቁ ብቻ ነው፡፡ እንኳን ወደ እስልምና በደህና መጣችሁ፡፡
አስገራሚ የእስልምና እውነታዎች

ክፍል 4

ሰይጣን ሰው አፍንጫ ላይ ተኝቶ ያድራል

ሳሂህ አል ቡኻሪ 3295 አቡ ሁሬይራ አንደተናገረው መሀመድ እያንዳንዳችሁ ጧት ከመኝታችሁ ስትነሱ አፍንጫችሁን በውሃ ማጽዳት አለባችሁ፡፡ ስታጸዱም 3 ጊዜ ውሃ የአፍንጫ ቀዳዳዎቻችሁ ውስጥ እያስገባችሁ መልሳችሁ ማውጣት ይኖርባችኋል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣን ሌሊቱን ሙሉ በአፍንጫችሁ ላይኛው ክፍል ተኝቶ ስለሚያድር ነው ብሏል፡፡ በማለት ዘግቦታል፡፡ ይገርማል ሰይጣን አፍንጫ ውስጥ ገብቶ ማደሩ ሳያንስ እንደሚወገድ ቁስ አካል በውሃ ታጥቦ የሚወገድ መሆኑ መስማት በጣም ያስቃል፡፡ ሁላችንም እንደምናወቀው ሰይጣን መንፈስ ነው አይታይም አይዳሰስም፡፡ መሀመድ ግን የሚታይ በውሃ የሚጠረግ ብናኝ አቧራ እንደሆነ ነው የሚነግረን፡፡ በአለም ላይ በቢሊዮን የሚቆጠሩ አፍንጫዎች አሉ፡፡ ሰይጣን በአንድ ጊዜ እነዚህ አፍንጫዎች ላይ ማደር ከቻለ አምላክ ነው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በአንድ ጊዜ መገኘት የአምላክነት ባህሪ በመሆኑ፡፡

አስገራሚ የእስልምና እውነታዎች

ክፍል 5

አዛን ሲደረግ ሰይጣን ፈሱን ይፈሳል፡፡

ሳሂህ አል ቡኻሪ 1231 አቡ ሁሬይራ እንደተነተነው መሀመድ “አዛን ሲደረግ ሙዕሚኖች እንዳይሰሙት ሰይጣን ወደ ኮረብታ ከወጣ በኋላ ፈሱን መፍሳት ይጀምራል፡፡ አዛኑ ሲያልቅ ወደ ነበረበት ይመለሳል፡፡ ብሎ መናገሩን ዘግቦታል፡፡

ይህ ታሪክ በሱናን አነሳይ 671 ላይም ተዘግቧል፡፡ በዚህ ሀዲስ ሰይጣን እስከበላና እስከጠጣ ድረስ መፍሳቱ የማይቀር መሆኑን ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡ ከዚህ የምንረዳው እስልምናን የመሰረተው የ40 አመት ጎልማሳ ሳይሆን የ5 አመት ህጻን እንደሆነ ነው፡፡

አስገራሚ የእስልምና እውነታዎች

ክፍል 6

የመሀመድ የወሲብ ሱስ

መሀመድ የወሲብ ሱስ የተጠናወተው ሰው እንደሆነ ከብዙ የሀዲስ ጽሆፎች እናነባለን፡፡

ሳሂህ አል ቡኻሪ 5068 አናስ እንደዘገበው መሀመድ በየቀኑ በአንድ ሌሊት ዘጠኝ ሚስቶቹን ያዳርስ (በወሲብ) ነበር፡፡ በማለት ተዘግቧል፡፡

በዚሁ ሀዲስ ቁጥር 268 ላይ ቃታዳ ከአናስ ቢን ማሊክ ሰምቶ እንደተነተነው አናስ መሀመድ ከ11 ሚስቶቹ ጋር በየቀኑ ቀንና ሌሊት ወሲብ ይፈጽም ነበር አለኝ፡፡ እኔም በየቀኑ ወሲብ የሚፈጽምበት አቅም አለው ወይ ብየ ጠየኩት፡፡ እሱም ሁል ጊዜ መሀመድ የ30 ወንዶች የወሲብ አቅም ተሰጥቶታል እያልን እናወራ ነበር፡፡ በማለት መለሰልኝ፡፡ በማለት ተዘግቧል፡፡ ሰይድ በቃታዳ ትንተና ላይ አናስ የነገረው 9 ሚስቶች እንጂ 11 አልነበረም ማለቱን ዘግቧል፡፡

ስለሆነም መሀመድ ባሁኑ ዘመን ቢኖር ኖሮ ዝነኛ የወሲብ ሞዴል ከሆኑ ወንዶች ተርታ ይመደብ ነበር፡፡
አስገራሚ እውነታዎቹ ይቀጥላሉ...
አስገራሚ የእስልምና እውነታዎች

ክፍል 7

የዝንብ ክንፍ ለበሽታ መድሃኒትነት

ዝንብ፣ ቆሻሻ ስፍራዎች ላይ በማረፍ የተለያዩ የበሽታ አምጪ ህዋሳትን በማጓጓዝ ለኮሌራ፣ ሳልሞኔላ፣ ለተቅማጥና ለሌሎች በሽታዎች መንስኤ እንደሆነች ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የ7ኛው ክፍለ ዘመኑ ግለሰብ፣ መሀመድ ኢብን አብደላ የዝንብ ክንፍ ለብዙ በሽታዎች መድኀኒት እንደሆነ ለተከታዮቹ ያስተምር ነበር፡፡

ሳሂህ አል ቡኻሪ 3320 አቡ ሁሬይራ እንደተነተነው እየጠጣችሁ እያለ የምትጠጡት ፈሳሽ ዝንብ ከገባች ወደ ውስጥ ካስገባችኋት በኋላ ጠጡ፡፡ ምክንያቱም አንድ ክንፏ በሽታ ሲሆን አንድ ክንፏ ደግሞ መድኀኒት ነው፡፡ በማለት መሀመድ መናገሩን ዘግቦታል    

አስገራሚ የእስልምና እውነታዎች

ክፍል 8

የመሀመድን ደም መጠጣት-->ለጀነት

የእሱን ደም የጠጣ ሰው ከገሀነም እሳት እንደሚተርፍ ራሱ መሀመድ ይነግረናል፡፡

በአልዲ አያት አሺፋህ ገጽ 23 ላይ አንድ ጊዜ መሊክ ኢብን ሲናን በኡሁድ ጦርነት የመሀመድን ደም መላስ ጀመረ፡፡ መሀመድም ፈቀደለትና እንዲህ አለው፡፡ እሳቱ አይነካህም፡፡ የሚል ታሪክ ተጽፏል፡፡ በተመሳሳይ አብደላህ ኢብን ዙቤይር ከተበጣ ወይም ከጎደጎደ የመሀመድ ሰውነት የፈሰሰውን ደም ጠጣ፡፡ መሀመድም ወዮላችሁ ህዝቦች ይህ ሰው (አብደላህ) ይህን በማድረጉ አልተጸጸተም በማለት መለሰ፡፡ የሚል ታሪክ አለ፡፡ ስለሆነም መሊክና አብደላህ የመሀመደን ደም በመጠጣታቸው የገሀነም እሳት አይነካቸውም ማለት ነው፡፡ በጣም አሪፍ አስቂኝ ተረት ነው፡፡

በሌላ መልኩ ሰዒድ ኢብን መንሱር ከኡመር ኢብን አል ሳኢብ ሰምቶ በዘገበው ሀዲስ መሀመድ በጦርነት እየተዋጋ እያለ ቆሰለ፡፡ መሊክ የአቡ ሰይድ አል ኩድሪ አባት የቆሰለውን የመሀመድ አካል በአፉ ልሶ ነጩ ሰውነቱ እስኪታይ ድረስ አጸዳው፡፡ ከዛ በኋላ እንዲተፋው ተነገረው፡፡ እሱ ግን በአላህ ይሁንብኝ አልተፋውም በማለት ወደ ጦርነቱ ተቀላቀለ፡፡ መሀመድም በጀነት ያሉ ሰዎችን ለመገናኘት የሚፈልግ ሰው ካለ ይህንን ሰው መመልከት ያስፈልጋል በማለት ነገራቸው፡፡ በመጨረሻ መሊክ በጦርነቱ ተሰዋ፡፡ በማለት ዘግቦታል፡፡
አስገራሚ የእስልምና እውነታዎች

ክፍል 9

የመሀመድ የዘር ፈሳሽ

አይሻ መሀመድን የዘር ፈሳሹ (semen) የነካ ልብሱን ሁል ጊዜ ታጥብለት እንደነበር ትነግረናለች፡፡

ሳሂህ አል ቡኻሪ 232 አይሻ እንደተነተነችው ሁልጊዜ መሀመድን የዘር ፈሳሹ የነካ ልብሱን አጥብለት ነበር፡፡ ነገርግን ታጥቦለትም እንኳን የዘር ፈሳሹ ነጠብጣቦች ይታዩ ነበር ማለቷን ዘግቦታል፡፡

ሳሂህ ሙስሊም 669 አይሻ የዘር ፈሳሽን አስመልክቶ እንደተነተነችው ሁል ጊዜ መሀመድን የዘር ፈሳሹ የነካበትን ልብስ አስለቀቅለት ነበር፡፡ ማለቷን ዘግቦታል፡፡

ሱናን ኢብን ማጃህ 537 አይሻ እንደተነተነችው ሁልጊዜ መሀመድን የዘር ፈሳሹ የነካ ልብሱን በእጄ ፈትጌ አስለቅቅለት ነበር፡፡ ማለቷን ዘግቦታል፡፡ ዘገባው ተዓማኒ ነው፡፡

አይሻ ሁል ጊዜ መሀመድ ወደ ሶላት ከመሄዱ በፊት በዘር ፈሳሹ የተበከለ ልብሱን በውሃ ከፈተገችለት በኋላ ወደ ሶላት ይሄድ እንደነበርም ትነገረናለች፡፡

ሳሂህ አል ቡኻሪ 230 ሱልይማን ቢን ያሳር እንደተነተነው አይሻን በዘር ፈሳሽ ስለተበከሉ ልብሶች ጠየኳት፡፡ እሷም ሁል ጊዜ መሀመድ በዘር ፈሳሹ የተበከሉ ልበሶቹን በውሃ ፈትጌ ካስለቀኩለት በኋላ ወደ ሶላቱ ይሄድ ነበር፡፡ ነገር ግን በውሃ ከፈተጓቸውም በኋላ ልብሱ ላይ ያሉት የዘር ፈሳሽ ነጥብጣቦች ይታዩ ነበርብላ መለሰችልኝ፡፡ ማለቱን ዘግቦታል፡፡
የዮሓኒስ ወንጌል 1:1፦ክፍል 1

በዘመናችን ያሉ እውቀት አልባ ሙስሊሞች ልክ ባዶ እቃ ሲመታ እንደሙዚቃ መሳሪያ እንደሚጮህ ሁሉ አንድ አንድ አስተማሪ ነን ባይ ኡስታዝ ተብዬዎች የተናገሩትን የወረደ "ማብራሪያ" ከጫፍ እስከጫፍ ተቀባብለው ሲያዜሙት እንታደማለን። በጣም የሚገርመው ነገር  ካልጠፋ ጥቅስ የዮሓኒስ ወንጌል 1:1ን ለራሳቸው እንደሚመች አድርገው ግሪኩን በ 1ኛ ክፍል የግሪክ ቋንቋ ያውም በጆሮ ጠገብ እንጂ በ እውቀት ባልሆነ ትርጉማቸው ሲተረጓግሙት ሰምተናል። "Little knowledge is dangerous" የተባለውም ለዚህ መሆኑ ግልጽ በሆነ መንገድ ተረድተናል።

ክፍሉን እስኪ አንድ በ አንድ እንመልከት

ዮሓኒስ 1:1-2
Ἐν ἀρχῇ ἦν ὁ Λόγος, καὶ ὁ Λόγος ἦν πρὸς τὸν Θεόν, καὶ Θεὸς ἦν ὁ Λόγος.
Οὗτος ἦν ἐν ἀρχῇ πρὸς τὸν Θεόν.

(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
1፤ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

2፤ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።

#Ἐν_ἀρχῇ_(En_arche)_'በመጀመሪያ'

ዮሓኒስ ይህንን ክፍል ሲጽፍ የተጠቀመባቸውን ቃላት በጥንቃቄ እየመረጠ ነው።  በዚህ ክፍል፣ #Ἐν "En-' የምትለው ቃል መጀመሪያን ለመግለፅ እንደሆነ ይታወቃል። መጠየቅ ያለብን ጥያቄ፣ " መጀመሪያ ማለት ምን ማለት ነው?" ወይም "የትኛው መጀመሪያ" የሚል ሲሆን፣ ለዚህ መልስ የሚሰጠን ከላይ ያነበብነው Ἐν_ἀρχῇ የሚለው ቃል ነው። ይሄን ቃል የምንጠቀመው፣ "መጀመሪያ_የሌለው_'መጀመሪያ'" "timeless_beginning' ለመግለፅ ነው። ይሄ ማለት፣ አንድ ሰው መጀመሪያ ብሎ የሚያስበውን "ጊዜ" እንደፈለግ በ ቢሊየን በሚቆጠሩ ዘመናትን ወደ ኋላ ገፍቶ "ይሄ መጀመሪያ" ነው ብሎ ቢያስብ፣ ያኔ እየሱስ (ሎጎስ)  #ነበር ማለት ነው። ሌላም ሰው መጀመሪያ የሚለውን ጊዜ ወደ ኋላ ጨምሮ ቢገፋው ያኔም እየሱስ ነበር ማለት ነው። በ አጭር ቃል " ዘላለማዊ" ማለት ነው። ዮሓኒስ ይህንን ቃል የተጠቀመውም እኛ ሰዎች በ ጊዜ እና ስፔስ (Time and Space) ተገድበን ስላለን ነው። ግን በዚህ አላበቃም። በዚህ "መጀመሪያ" ተብሎ በተጠቀሰው ጊዜ በተመሳሳይ ጊዜ ቃሉ"ሎጎስ" #ከእግዘብሔር_ጋር_ነበር ይላል። ይሄ ማለት አንድ ሰው 'መጀመሪያ ብሎ የሚያስበውን ጊዜ (specific time) የፈለገ ያህል ወደ ኋላ ቢገፋው already በዛ ጊዜ እየሱስ (ቃሉ ወይም #ሎጎስ) ከ እግዚያብሔር(አብ) ጋር በሕብረት ነበር ማለት ነው( Logos eternally co-existed with the Father)። በ አጭር ቋንቋ ይሄ #ሎጎስ  ከዘላለም ጀምሮ ነበር ማለት ነው።

ልብ በሉ፣ ዮሓኒስ ሲፅፍ፣ "በ መጀመሪያ ቃል ተገኘ" ወይም ሎጎስ የ እግዚያብሔር አብ #የይሁን_ቃል ነው #አላለም። 'ይህ ሎጎስ፣ የሆነ ጊዜ ላይ ተገኘ' ማለት ቢፈልግ ኖሮ " en arche" የሚለውን ቃል ሳይሆን "egeneto" የሚል ቃል በተጠቀመ ነበር።  አሁን ግን አልተጠቀመም።

ታላቁ የ ግሪክ ቋንቋ ምሁር  አርኪባልድ ቶማስ ሮበርትሰን፣ 'Word Pictures in the New Testament, vol 5' በተሰኘው መፅሓፋቸው ውስጥ ሲጽፉ እንዲህ ብሏል፤ " ዮሓኒስ በዚህች አረፍተ ነገር ውስጥ 3 ጊዜ 'En' የምትለውን ቃል ተጠቅሟል። ይሄም የሚያሳየው "እግዚያብሔርም(እግዚያብሔር አብም)"  "ሎጎስም(ወልድም)" መጀመሪያ እንደሌላቸው ወይም ደግሞ ዘላለማዊነታቸውን "Continous Existence" የሚያሳይ ነው።"

'Ev' "En" የሚለው ቃል የ "εἰμί" (Eimi) imperfect ቃል ሲሆን ዘላለማዊነትን (timeless existence) የሚያሳይ ነው። ይህንን ቃል እየሱስ በ ዮሓኒስ 8:58 ላይ ተጠቅሞ እናገኛለን።
εἶπεν αὐτοῖς Ἰησοῦς Ἀμὴν ἀμὴν λέγω ὑμῖν, πρὶν Ἀβραὰμ γενέσθαι #ἐγὼ_εἰμί.
" ኢየሱስም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ #እኔ_አለሁ አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:58)
ይሄም የሚያሳየው እየሲስ ዘላለማዊ መሆኑንን እንደሆነ ትላልቅ የ ግሪክ ምሁራን (ሮበርትሰንን ጨምሮ) አረጋግጧል።


#ታዲያ_ሎጎስ_Λόγος_ምንድነው?

Λόγος ሎጎስ ወይም "ቃል" እኛ በ 21ኛው ም.አ ውስጥ ሆነን እንደምናስበው ዝም ብሎ የንግግር ቃል አይደለም። LOGOS ገና ዮሓኒስ ወንጌሉን ሳይፅፍ በቢዙ ግሪክ ፊሎሶፊና እምነቶች ውስጥ ጥቅም ላይ ነበር። ትርጉሙም ሰፊ ነው።

1. ሔራቅሊጦስ (Heraclitus) 535 B.C-475 B.C ከ ሶቅራጦስ በፊት የነበረ በ ኤፌሶንም ይኖር የነበረ የግሪክ ፊሎሶፈር ነው። እሱም ሎጎስ 'Logos'  የሚለውን ቃል "The principle which controls the Universe"(ጠፈሮችን የሚቆጣጠር ፕሪንሲፕል" ብሎ ያስተምር ነበር።

2. #እስቶይክስ የሚባሉ የፊሎሶፊ ግንዶች ደግሞ #ሎጎስን "Anima Mundi" ብለው ይጠቀሙ ነበር። ይህ ማለት "የአለማችን ሕይወት ወይም የ ሕይወት ምንጭ" (Soul of the World) ማለት ነው።

3. ማርቆስ አውራሊየስ (Marcus Aurelius) ከ121 A.D-180 A.D ይኖር የነበረ የሮም ገዢ እንዲውም ፊሎሶፈር ነበር። Spermatikos Logos የሚል ፕሪንሲፕል ይጠቀም ነበር። ይህም "ሎጎስ" የ አለማችንን የመፍጠርና የመራባትን ሕግ የሚቆጣጠር (Generative principle of the Universe)፣ በ ሌላ ቋንቋ ወይም ፍልስፍና ባልሆነ ቋንቋ ሲታይ "አምላክን" የሚወክል ማለት ነው።

4. በ ኢብራይስጥ ቋንቋ "Memra" "ሜምራ" ማለት ሲሆን ኢብራውያን ለ "አምላክ" ተጠቅመውበታል። ለምሳሌ በ ታርጉማቸው ውስጥ ስለ ኦሪት ዘዳግም 26:17-18 ሲፅፉ " Ye have appointed The MEMRA (logos) a king over you this day, that #he may be YOUR #GOD" (ሎጎስን በራስህ ላይ ንጉስ አድርገህ ሹመኃል፤ ይህም #አምላክ እንዲሆንህ ነው።)

#ታድያ_ሎጎስ_የሚለውን_ቃል_ለምን_መረጠ?

ዮሓኒስ ይህንን ወንጌል ሲፅፍ "GNOSTICS" ኖስቲክስ የሚባሉ ግሩፖች  እንዲዩም "Dicipline of Valentinus' (ዲሲፕሊን ኦፍ ቫሌንቲነስ) የተሰኘ አስተምህሮ ተነስቶ ነበር። እነኚህ ማህበረሰብ "ሎጎስ የሚባል አካል "Aeions" ከሚባሉ የመጀመሪያ ፍጡሮች አንዱ ሲሆን "ዞዪ"(Zoe) ከምትባል ሌላ "ኤዎን" ጋር በመሆን ሌሎች ፍጡሮችን ማስገኘት እንደጀመረ ይናገራሉ። እንኚህ ግሩፖች የመፅሓፍ ቅዱስን አስተምህሮ በማዛባትና ከነሱ በፊት የነበረውን የሎጎስ ትርጉሞች ተጠቅመው የራሳቸውን ሓሰተኛ ወንጌል መስበክ በጀመሩ ጊዜ ነው ዮሓኒስ መፃፍ የጀመረው። ታዲያ ዮሓኒስ "የሎጎስን" ፍልስፍና በሚያውቅ ሕብረተሰብ ውስጥ ነው ይህንን ስያሜ ለእየሱስ የተጠቀመው። ይህን ቃል ሲጠቀም ግን የነሱ ትርጉም ትክክል ነው ብሎ እንደወረደ አልተጠቀመም። ይልቁንስ ሎጎስ የተፈጠረ አምላክ ሳይሆን እራሱ ዘላለማዊና ፈጣሪ መሆኑን ለማሳየት En Arche ብሎ ጀመረው። ከዛም "ቃሉም በመጀመሪያ ከ እግዚያብሔር ጋር ነበር" በማለት "ተፈጠረ" የሚለውን ቃል አፈረሰ፣ውድቅ አርገ እንጂ።
#ይቀጥላል...
Ref.
1.Barnes note on John 1:1
2.Iraneus Against Heresies Bk 1,Ch 1
@Jesuscrucified
የሃይማኖት ግጭት በባሌ ጎባ ከተማ። ሰዎች እየተገደሉ ነው። http://www.ewnetlehulu.org/am/news/goba_religious_conflict/
ዮሓኒስ 1:1 ክፍል ሁለት

ዮሓኒስ 1፣ ክፍል 1 ስር "ሎጎስ" ማለት ምን ማለት እንደሆነና ዮሓኒስ ለምን እንደተጠቀመው አይተናል።  አሁን ደግሞ፣ የ ዓረፍተ ነገሩ አወቃቀር እንዴት እየሱስ እና አብ ሁለት የተለያዩ አካል ግን አንድ መሎኮት እንደሆኑ የሚያስተምረን ክፍል የምናይ ይሆናል።

ዮሓኒስ 1:1
Ἐν ἀρχῇ ἦν ὁ Λόγος, καὶ ὁ Λόγος ἦν πρὸς τὸν Θεόν, καὶ Θεὸς ἦν ὁ Λόγος.
(En arche en ho logos, kai ho logos en pros ton theon, Kai theos en ho logos)

ሙግታችን የሚሆነው የመጨረሻዋ ዓ.ነገር ላይ ነው " #Kai_theos_en_ho_logos"። በዚህ አረፍተ ነገር ላይ "ho" የምትለው ግሪክ አርቲክል (በ ኢንግሊዘኛ 'The') የገባቺው ከ "logos" ፊትለፊት ብቻ ነው። "Theos" ፊትለፊት አልገባችም። ይህ ነገር ደግሞ በ ግሪክ ሰዋሰው ውስጥ ትልቅ ትርጉም አለው። ምን ማለት እንደሆነ የታላቁን የግሪክ ስኮላር የሮበርትሰንን ማብራሪያ ልስጣቹ።

Robertson Grammar pp 766-768
"ዮሓኒስ፣ kai theos en ho logos(#The word was God) ብሎ ሲፅፍ በምክኒያት ነው። ምክኒያቱም 'theos' ከሚለው ቃል ፊትለፊትም "'ho' አስገብቶ ቢሆን ኖሮ (ወይም kai HO theos en Ho logos)(The word was The God) ብሎ ቢፅፍ ኖሮ፣ "ሳቤሊያኒዝም"(Sabellianism) የተሰኙ መናፍቃንን ይደግፍ ነበር። ምክኒያቱም 'ho' ከሁለቱም ፊትለፊት ከገባች፣ ሁለቱ (theos እና logos) የተለያዩ አካል አይደሉም ማለት ነው። ይሄ ማለት "አብም" "ወልድም"  አንድ አካል ናቸው፣ ሁለት ስም ተሰጥቶት ነው እንጂ እንደማለት ነው። በሌላ ቋንቋ፣ "ቃልም እግዚያብሔር ነበር" የሚለውን ቦታ አቀያይረን "እግዚያብሔርም ቃሉ ነበር" ማለት በተቻለ ነበር። ይሄ ደግሞ እየሱስና አብ የሚባሉ ሁለት አካል የሉም እንደማለት ነው።  ነገር ግን፣ ዮሓኒስ ይሄን ትርጉም እንዳንሰጥ "ho" የሚለውን አርቲክል ከ 'ሎጎስ' ፊትለፊት ብቻ አስገባ። ይሄ ማለት ቦታ አቀያይሮ " እግዚያብሔርም ቃሉ ነበር" "ወይም ደግሞ "ቃሉ የ እግዚያብሔር የ ይሁን ቃል ነው" ማለት #በፍፁም_አይቻልም ማለት ነው።  ይህ ማለትም "ሎጎስ እራሱ ከ ዘላለም ጀምሮ እግዚያብሔር ነበር" ማለት ነው። በምሳሌ እንይ:
1. John 4:24- God is Spirit "እግዚያብሔር መንፈስ ነው" "#Pneuma_ho_theos
በዚህ ክፍል ላይ "ho" የገባቺው ከ "theos" ፊትለፊት ብቻ ነው። ስለዚህ፣ ቦታ አቀያይሮ "መንፈስ እግዚያብሔር ነው" ማለት አይቻልም።
2.  1 john 4:16- ho theos agape estin ( እግዚያብሔር ፍቅር ነው)። እዚህም ላይ ቦታ አቀያይሮ " ፍቅር እግዚያብሔር ነው" ማለት አይቻልም።

ስለዚህ፣ ዮሓኒስ በግልፅ እንዳሳየን ከሆነ "ሎጎስ"(እየሱስ) ከ እግዚያብሔር አብ የተለየ አንድ personality (ህልውና ወይም አካል) እንደሆነና ይህ አካል (ሎጎስ ) ከ "አብ" ጋር ዘላለማዊ የሆነ አንድ "መሎኮት" እንደሆኑ ( ምክኒያቱም አብም ወልድም እዚህ ክፍል ላይ "Theos" "እግዚያብሔር" ተብሏል። ነገር ግን እግዚያብሔሮች ወይም 'ሁለተኛው እግዚያብሔር' አልተባሉም። መሎኮት አንድ ነውና።)
ልብ በሉ፣ ዮሓኒስ ሲፅፍ "logos en ho theos" ብሎ ከ "theos" ፊትለፊት ብቻ ho አስገብቶ ቢሆን ኖሮ፣ ትርጉሙ " እግዚያብሔር ቃል ነበር" ይሆን ነበር። ሙስሊሞቹንም ደግፎ " እየሱስ በ አካል የተለየ አምላክ አይደለም" ተብሎ ይሰበክ ነበር። አሁን ግን ዮሓኒስ በ አረፍተ ነገር እወቃቀሩ የሙስሊሞችንም ሆነ የሌሎች የክርስቶስ ተቃዋሚ ተቋሞችን ተስፋ አጨልሞባቸዋል።

ክፍል ሶስት ይቀጥላል...
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
@JESUS_ALHAQ
@JESUS_ALHAQ
ሌላ የ አፖሎጄቲክስ ቻነል ነው። join!
ብዙ ሚስት በባይብል??

"፤ የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ የጌታህንም #ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።"
(መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 12: 8)

አንዳንድ ንቀን የተውናቸው ሙሓመዳውያን ስናፍጭ በምታክለው ጭንቅላታቸው መፅሓፍ ቅዱስን ወደ እራሳቸው የወረደ ደረጃ ሲጎትቱና በየ ቻነሎቻቸው የወደቀ ትርጉም ሲፈላሰፉለት እያየን ነው። ከላይ ያነበብነውን የመፅሓፍ ቅዱስ ክፍል፣አንዱ እንዲህ ብሎ ትርጉም ሰጥቶታል። እስኪ የሱን ትርጉም ላስነብባቹ፤

"........አንዳንድ ክርስቲያን ወገኖች የዳዊትና የልጁ ሰለሞንን ከመጠን ያለፈ የሚስት ብዛት ለማስተባበል የሚጠቀሙት ቃል "እግዚአብሄር ሳያዛቸው በፍቃዳቸው የሰሩት ነው በዚህም ተወቅሰዋል" የሚል ነው። በመጀመሪያ ነገር በሚስት ማብዛታቸው ምክንያት ተቀጡ የሚል የለም። ሲቀጥል መጀመሪያውኑ እግዚአብሄር አይደል እንዴ በጅምላ እንዲያገቡ ያመቻቸው?...." ብሎ 2ሳሙኤል 12:8 ጠቅሷል።እስኪ ክፍሉን እናጥናው፤

1. #የጌታህንም_ሚስቶች your master's wives

ለዳዊት ጌታው(master) የነበረው #ሳኦል ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ሳኦል ብዙ ሚስት አለው የሚል መፅሓፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ሳኦል #አንድ_ሚስት(1ሳም 14:49-50) እና "ሪጽፋን" የምትባል አንድ #ቁባት(concubine)(2ሳም 3:6-7)ብቻ ነበረው። "ሚስቶች" የተባለውም እሷን ጨምሮ ነው።በ ኢስራኤልም ሆነ በ ድሮ ምስራቃዉያን አለም፣ የ አንድ ንጉስ ሚስትም ሆነ ቁባት፣ ንጉሱ ከሞተ፣ የቀጣዩ ንጉስ ይሆናሉ። ንጉሱ ሊያገባትም ላያገባትም ይችላል። ብቻ እጣ ፈንታቸውን የሚወስነው ቀጣዩ ንጉስ ነው ማለት ነው።  የሚገርመው ነገር፣ መፅሓፍ ቅዱስን ከ ጫፍ እስከ ጫፍ ብታነብ፣ ዳዊት የሳኦልን ሚስት እንዳገባ የሚናገር #አንድም_ማስረጃ_የለም። ሌላው አስገራሚው ነገር ደግሞ፣ የሳኦልን ቁባት የወሰደው ዳዊት ሳይሆን #አበኔርም የሚባል ሰው ነው(2ሳም 3:7)። የቀረችው አንድ የሳኦል ሚስት ናት፤እሷንም ዳዊት እንዳገባት የሚናገር ጥቅሥም ማስረጃም የለም። ታዲያ ሙስሊሞች የሚሉት 'የትኞቹን የሳኦል ሚስቶች ናቸው ዳዊት ያገባው??'
ይልቁንስ ክፍሉ ላይ '... የጌታህንም #ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፤..' ለሚለው  ተቀባይነት ያለው ትርጉም "በራሱ በሳኦል ሚስቶች ላይ መብት ሰጠሁ፤" ይሄ ማለት የፈለገውን ማግባት ይችላል ነው እንጂ 'ሁሉንም ማግባት ይችላል'  ማለተም አይደለም። ለዳዊት ይሄ መብት ተሰቶታል ማለት ግን "አግብቷል" ማለት #አይደለም። ማስረጃም የለም። ስለዚህ በ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 'እግዚያብሔር  ወንዶች ብዙ ሚስቶችን እንዲያገቡ ፈቅዷል' የሚል ሙግት ውድቅ ይሆናል ማለት ነው።

2. "..ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር.."

ሙሓመዳውያን በዚህኛው ደግሞ እጅግ የሚያስቅ ሙግት ሰርቷል። ሙግታቸውም "..ለዳዊት አንሶት ቢሆን ኖሮ እግዚያብሔር ለዳዊት ብዙ ሚስቶችንም ይጨምርለት ነበር.." የሚል ነው። አንድ ፊደል የቆጠረ ሰው ይሄንን ክፍል መረዳት ያቅተዋል ብዬ አላስብም ነበር( apparently i was wrong 😂)።

በዚህ ክፍል ላይ፣እግዚያብሔር ለዳዊት የሰጠውን ነገር በዝርዝር እያስቀመጠ ነው ያለው፤ እንመልከት
1. የጌታህንም ቤት..
2. የጌታህንም ሚስቶች..
3.የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት..
 ሰጠሁህ፤
..ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።"
ስለዚህ፣ እግዚያብሔር "እጨምራለው" እያለ ያለው፣ ዝርዝሩን (e.g 4.ብር፣ 5.ወርቅ ወ ዘ ተ) እንጂ  #ሚስቶችን ወይም የተጠቀሱ ነገሮችን 'በብዛት' እጨምራለው' ማለት አይደለም።

ይልቁንስ፣ ቀጥለን በምናነበው ክፍል ላይ እግዚያብሔር በግልጽ #የትኛውም የእስራኤል ንጉስ ብዙ ሚስት እንዳያገባ ከልክሎ እናገኛለን። ስለዚህ ዳዊትም ሆነ ሶሎሞን ብዙ ሚስት ቢያገቡም እግዚያብሔር ፈቅዷል ማለት አይደለም።



(ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 17)
----------
15፤ አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን በላይህ ታነግሣለህ፤ ከወንድሞችህ መካከል የሆነውን በአንተ ላይ ንጉሥ ታነግሣለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ከሌላ ወገን ሰው በላይህ ንጉሥ ታደርግ ዘንድ አይገባህም።

16፤ ነገር ግን ለእርሱ ፈረሶችን አያበዛም፤ እግዚአብሔር። በዚያ መንገድ ደግማችሁ አትመለሱም ብሎአችኋልና ፈረሶችን ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስም።

17፤ ልቡም እንዳይስት #ሚስቶችን_ለእርሱ_አያበዛም፤ ወርቅና ብርም ለእርሱ እጅግ አያበዛም።

"17 Neither shall he multiply wives to himself, that his heart turn not away: neither shall he greatly multiply to himself silver and gold."

የኢስልምና አፖሎጂስቶችን ሎጂክ እናስተምር እንዴ?
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
የእስልምና ቀልድ ጥግ!!

መሬትን የተሸከመው ዓሠ-አነባሪ(whale)

እስልምና፣ ሙሓመዳውያን እንደሚሰብኩት ከሳይንስ ጋራ የተጣጣመ ትምህርት ሳይሆን ጭራሽ ሳይንስን R.I.P (rest in peace) "#ነፍስ_ይማር" በሚያስብሉ ትምህርቶች እንደተሞላ ጥቂት ምሳሌዎችን አንስተን ከዚህ በፊት አይተናል። ለመሆኑ፣ እስልምና ስለመሬት አፈጣጣር(earth) ሲያስተምር፣ 'መሬት 1 ብቻ ሳትሆን 7 መሬቶች እንደ ሳንድዊች ተደራርቦ እንዳሉና ሰባቱም ከስር ትልቅ ዓሳ-አንባሪ ላይ እንደተቀመጡ፣ ይህ ዓሳ-አንባሪም ስልሚንቀሳቀስ የመሬትን ባላንስ ለመጠበቅ አላህ ተራሮችን ችካል አድርጎ እንደተከላቸው' እንደሚያስተምር ያውቃሉ?? 😂


ሱራ 68:1: نٓ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ
ነ. (ኑን)፤ (1) በብርዕ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት።
Nun. By the pen and what they inscribe,

ሙስሊሞች ይሄን ክፍል ሲተሮግሙት" نٓ" "noon" የምትለውን የአዕረብኛ ቃል ትርጉም ሳይሰጡት "ኑን" ብሎ አልፈዋል። እውነታው ግን፣ ትላልቅ የእስልምና ሙፋሲሮች፤ #ኢብን ከሢር፣ #አ_ጠበሪ#አል_ቁርጡቢ፦ "ኑን" ማለት "አሳ አንባሪ" እንደሆነ በተፍሲራቸው ጽፏል።
ስለዚህ ይህ ክፍል(68:1) ትርጉም ቢሰጠው፤
   "በ ዓሳ አንባሪ (ኑን) እና( و)በ ብርዕ( ٱلْقَلَمِ)እምላለው     በሚጽፉት.." ይሆናል።

ማስረጃዎቻችንን አንድ በ አንድ እንመልከት።
#ዓሳ_አንባሪ በ አረብኛ ምን ይባላል
   1. አል-ኑን  نٓ (noon)
   2. አል-ሁት الحوت (al-hoot)

ሀ. ከቁርዓን

ቁርአን 21:87፦ የዐሣውንም(ٱلنُّونِ al-noon)ባለቤት(man of the fish) ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፤ እርሱም ላይ ፍጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ፤ (ዐሳም ዋጠው)፤ በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ ፦ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ጥራት ይገባህ፤ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ።
   እዚህ ጋር "አል-ኑን"  ሲተረጎም "#ዓሣ" ተብሏል።

ለ. የተፍሲሮች ትርጉም

1. አረቢኛው ተፍሲር ኢብኑ ከሢር ሱራ 68:1

እንዲህ ይላል፦ " نۤ حوت عظيم"። ትርጉሙም  " 'ኑን' 'ن'ۤ  #ትልቅ #አሳ_አንባሪ ነው" ' noon is a big whale'
፦በኢንጊልዘኛው ላይ አልተሮጎሙትም

2. ተፍሢር አል ጠበሪ፦ሱራ 68:1
هو الحوت الذي عليه الأرَضُون

"መሬት(መሬቶቹ, الأرَضُون)  ትልቅ ዓሳ-አንባሪ( الحوت, አል-ሁት) ላይ ነች/ናቸው።"

3. ተፍሢር አል ቁርጡቢ

'نۤ' الحوت الذي تحت الأرض السابعة
'Nun'- the whale (الحوت), which is (الذي) under (تحت) the Earth (الأرض) the seventh (السابعة).
'ኑን' 'ዓሳ አንባሪዋ' ከሰባተኛው መሬት ስር ያለችው..

4. ኢብኑ አባስ በተፍሲር ኢብኑ ከሢር (አረቢኛው)
በ ሱራ 68:1 ላይ

ابن عباس قال: أول ما خلق الله القلم قال: اكتب، قال: وماذا أكتب؟ قال: اكتب القدر، فجرى بما يكون من ذلك اليوم إلى قيام الساعة، ثم خلق النون، ورفع بخار الماء، ففتقت منه السماء، وبسطت الأرض على ظهر النون، فاضطرب النون، فمادت الأرض، فأثبتت بالجبال؛

"እብኑ አባስ እንደዘገበው: "በመጀመሪያ አላህ ብርዕ (pen)(القلم) ፈጠረ። እንዲፅፍም አዘዘው፣ከዚያም ብዕሩ እንዲህ አለ: ምን ልፃፍ፤ እሱም መልሶ፣ 'ሰለ ሰዎች እጣ-ፈንታ (القدر)' አለው። ብዕሩም ከፍጥረት እስከ ትንሳኤ ድረስ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ፃፈ። ከዚያም #አል_ኑንን (النون) ፈጠረ። ከዚያም ውሓ እና ሰማያትን ፈጠረ፣ ምድርንም በ 'ኑን'(አሳ) ጀርባ( ظهر) ላይ( على)
ሰራት።መሬትም በጀርባው ላይ ስትንቀሳቀስ በ ተራሮች እንደ ጭካል (እንዳትንቀሳቀስ) አፀናት።"  ልብ በሉ፣ ሓዲሡ ኢብኑ አባስ የዘገበው ሓዲሥ ሲሆን፣ይሄ ሓዲሥ ሳሂህ(sahih, ታማኝ, authentic)ነው። ኦንላይን በዚህ ገብታቹ ማየት ይቻላል።
(http://hdith.com/?s=ثم+خلق+النون+فوق+الماء،+ثم+كبس+الأرض+عليه)

የጋራዎችንም "ችካል" መሆን ቁርዓን ያስተምራል

ሱራ 78:7
"ጋራዎችንም #ችካሎች አላደረግንምን"

ትናንት የተወለዱት የዘመናችን ኡስታዝ ተብዬዎች "ከነ እብኑ ከሢርና አል-ጠበሪ እንበልጣለን" ይሉን ይሆን?? ከ ኢብኑ አባስስ??

እኛ እንዘግባለን፣ፍርዱን ለአንባቢው!!
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
የነፍሴ ጥያቄዎች.pdf
616.7 KB
ሙሓመድ የማን መልዕክተኛ ነው??
ሳሂህ ኢማን
🔥1