ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
"ሰላ" ማለት "ባርኮት" ማለት ከሆነ ደግሞ(ማስረጃ ያስፈልገዋል!) መላዕክት እንዴት አላህ በሚያወርደው ልክ ባርኮትን መስጠት ይችላሉ? ባርኮትስ የሚሰጥ አንድ ፈጣሪ ብቻ አይደለም ወይ? 🤔
*ይህ ጥያቄ "የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ" ለሚለውም ትርጉምም ይሆናል ምክንያቱም መላእክት አላህ "ሰላም ይስጥህ!" ይባርክህ አሉት እንኳ ብንል፤ አላህ ከማ? እንዴትና ወደማ? ይህንን አብሮ ይላል? 🤔 (ልብ አድርጉ "አላህና መላዕክቱ" ካለ "#ይሰሉና" ለሁለቱም አንድና ተመሳሳይ ሙያና ተግባር እንደሚሰጥ፤ ስለዚ የቃሉ ትርጉም ሁለቱንም የሚጠቃልል መሆን አለበት።) ...አንድ ፍጡር ሌላን ባረከ ሲባል "ፈጣሪ ይባርክህ!" አለ ማለት ነው፤ ፈጣሪ ባረከ ስንል ግን እራሱ በእሱነቱ ሁሉን አድራጊ ስለሆነ ባለቤትነቱ ራሱ ላይ ያርፋል። ስለዚ በየትኛውም ማሻሻያ ትርጉም አያስኬድም
👉 በዋነኝነት ግን በሰማይም ቢሆን #የአምልኮትና የባርኮት #ማዕከሉ አላህ ሳይሆን #ሙሐመድ መሆኑን እንመለከታለን።
📚 ተፍሲር ኢብኑ ካቲር ለዚህ ቃል ባሰባሰበው ትርጉም " '#የአላህ "#ሰላ" ባርኮቱ ነው #የመላእክት ግን ፀሎታቸውና #ልመናቸው ነው' አቡ አል አሊያህ እንዳሉት።" ብሎ ዘግቦአል። "አት ተርሚዝም '#የመላእክት "#ሰላ" #የይቅርታ ፀሎታቸውና #ልመናቸው ነው' ብሏል።" በማለት ዘግቧል(መላዕክት ይቅርታን ለዛውም #ከሙሐመድ እንደሚጠይቁ ልብ በሉ)። እንግዲ አላህ ባርኮትን ወደ ሙሐመድ ልኳል እንኳ ቢባል እንዴት ነው መላእክት ፀሎታቸውንና የይቅርታ ልመናቸውን ወደ ሙሐመድ የሚልኩት? ይህ ሙሐመድን አምላክ አያደርገውምን? 🤔 መልሱ አለምንም ጥያቄ ያደርገዋል ነው።
🔎 ይህን በይበልጥ የምንረዳው እውነትም ፀሎት ወደ አላህ ብቻ ሳይሆን ወደ ሙሐመድም እንደሚደረግና ሙሐመድም ይህንን እንዳረጋገጠ 📚በጃሚ አት ተርሚዝ ቅፅ 6 ሐዲዝ ቁጥር 3578 ላይ የተዘገበውን #ሳሂህ ሐዲዝ ስናይ ነው።