ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ዮሓኒስ 1:1 ክፍል ሁለት

ዮሓኒስ 1፣ ክፍል 1 ስር "ሎጎስ" ማለት ምን ማለት እንደሆነና ዮሓኒስ ለምን እንደተጠቀመው አይተናል።  አሁን ደግሞ፣ የ ዓረፍተ ነገሩ አወቃቀር እንዴት እየሱስ እና አብ ሁለት የተለያዩ አካል ግን አንድ መሎኮት እንደሆኑ የሚያስተምረን ክፍል የምናይ ይሆናል።

ዮሓኒስ 1:1
Ἐν ἀρχῇ ἦν ὁ Λόγος, καὶ ὁ Λόγος ἦν πρὸς τὸν Θεόν, καὶ Θεὸς ἦν ὁ Λόγος.
(En arche en ho logos, kai ho logos en pros ton theon, Kai theos en ho logos)

ሙግታችን የሚሆነው የመጨረሻዋ ዓ.ነገር ላይ ነው " #Kai_theos_en_ho_logos"። በዚህ አረፍተ ነገር ላይ "ho" የምትለው ግሪክ አርቲክል (በ ኢንግሊዘኛ 'The') የገባቺው ከ "logos" ፊትለፊት ብቻ ነው። "Theos" ፊትለፊት አልገባችም። ይህ ነገር ደግሞ በ ግሪክ ሰዋሰው ውስጥ ትልቅ ትርጉም አለው። ምን ማለት እንደሆነ የታላቁን የግሪክ ስኮላር የሮበርትሰንን ማብራሪያ ልስጣቹ።

Robertson Grammar pp 766-768
"ዮሓኒስ፣ kai theos en ho logos(#The word was God) ብሎ ሲፅፍ በምክኒያት ነው። ምክኒያቱም 'theos' ከሚለው ቃል ፊትለፊትም "'ho' አስገብቶ ቢሆን ኖሮ (ወይም kai HO theos en Ho logos)(The word was The God) ብሎ ቢፅፍ ኖሮ፣ "ሳቤሊያኒዝም"(Sabellianism) የተሰኙ መናፍቃንን ይደግፍ ነበር። ምክኒያቱም 'ho' ከሁለቱም ፊትለፊት ከገባች፣ ሁለቱ (theos እና logos) የተለያዩ አካል አይደሉም ማለት ነው። ይሄ ማለት "አብም" "ወልድም"  አንድ አካል ናቸው፣ ሁለት ስም ተሰጥቶት ነው እንጂ እንደማለት ነው። በሌላ ቋንቋ፣ "ቃልም እግዚያብሔር ነበር" የሚለውን ቦታ አቀያይረን "እግዚያብሔርም ቃሉ ነበር" ማለት በተቻለ ነበር። ይሄ ደግሞ እየሱስና አብ የሚባሉ ሁለት አካል የሉም እንደማለት ነው።  ነገር ግን፣ ዮሓኒስ ይሄን ትርጉም እንዳንሰጥ "ho" የሚለውን አርቲክል ከ 'ሎጎስ' ፊትለፊት ብቻ አስገባ። ይሄ ማለት ቦታ አቀያይሮ " እግዚያብሔርም ቃሉ ነበር" "ወይም ደግሞ "ቃሉ የ እግዚያብሔር የ ይሁን ቃል ነው" ማለት #በፍፁም_አይቻልም ማለት ነው።  ይህ ማለትም "ሎጎስ እራሱ ከ ዘላለም ጀምሮ እግዚያብሔር ነበር" ማለት ነው። በምሳሌ እንይ:
1. John 4:24- God is Spirit "እግዚያብሔር መንፈስ ነው" "#Pneuma_ho_theos
በዚህ ክፍል ላይ "ho" የገባቺው ከ "theos" ፊትለፊት ብቻ ነው። ስለዚህ፣ ቦታ አቀያይሮ "መንፈስ እግዚያብሔር ነው" ማለት አይቻልም።
2.  1 john 4:16- ho theos agape estin ( እግዚያብሔር ፍቅር ነው)። እዚህም ላይ ቦታ አቀያይሮ " ፍቅር እግዚያብሔር ነው" ማለት አይቻልም።

ስለዚህ፣ ዮሓኒስ በግልፅ እንዳሳየን ከሆነ "ሎጎስ"(እየሱስ) ከ እግዚያብሔር አብ የተለየ አንድ personality (ህልውና ወይም አካል) እንደሆነና ይህ አካል (ሎጎስ ) ከ "አብ" ጋር ዘላለማዊ የሆነ አንድ "መሎኮት" እንደሆኑ ( ምክኒያቱም አብም ወልድም እዚህ ክፍል ላይ "Theos" "እግዚያብሔር" ተብሏል። ነገር ግን እግዚያብሔሮች ወይም 'ሁለተኛው እግዚያብሔር' አልተባሉም። መሎኮት አንድ ነውና።)
ልብ በሉ፣ ዮሓኒስ ሲፅፍ "logos en ho theos" ብሎ ከ "theos" ፊትለፊት ብቻ ho አስገብቶ ቢሆን ኖሮ፣ ትርጉሙ " እግዚያብሔር ቃል ነበር" ይሆን ነበር። ሙስሊሞቹንም ደግፎ " እየሱስ በ አካል የተለየ አምላክ አይደለም" ተብሎ ይሰበክ ነበር። አሁን ግን ዮሓኒስ በ አረፍተ ነገር እወቃቀሩ የሙስሊሞችንም ሆነ የሌሎች የክርስቶስ ተቃዋሚ ተቋሞችን ተስፋ አጨልሞባቸዋል።

ክፍል ሶስት ይቀጥላል...
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified