ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
በዚ ክፍል ላይ አንድ አይነ ስውር ሰው ወደ ሙሐመድ ይቀርብና "ወደ አላህ ፀልየህ ፈውሰኝ::" ብሎ ሲለምነው እናያለን። ሙሐመድም #ራስህ ፀልይ ከማለት ይልቅ አንተ ከፈለግህ #አደርገዋለሁ ብቻ ታገስ ብሎ ሲመልስለት እናያለን። በመቀጠልም ሙሐመድ እንዲህ ብሎ ሰውዬው እንዲፀልይ ያዘዋል..." ኦ አላህ እኔ ወደ አንተ በነብይህ ሙሐመድ በምህረት ነብይ በኩል እመጣለሁ። በርግጥም ወደ ጌታዬ ቀረብሁ፤ #ባንተ(በነብዩ) በኩል ይህን ችግሬን በተመለከተ #መፍትሄን አገኝ ዘንድ። እናም አላህ የነብዮን ምልጃ ተቀበል።" ብለህ ፀልይ ሲለው እንመለከታለን።
በዚህ ፀሎት ውስጥ እየተለመነ ያለው አላህ ብቻ አይደለም መሐመድም እንጂ "#ባንተ በኩል ወደ ጌታዬ መፍትሄን አገኝ ዘንድ እመጣለሁ።" ማለቱ ሙሐመድም የፀሎቱ #ተደራሲ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። በርግጥ ሰውዬው አላህን የሙሐመድን ምልጃ እንዲቀበል የጠየቀ ቢሆንም ግን ችግሩ ያለው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሙሐመድ የፀሎቱ ተደራሲ አካል መሆኑ ነው። "በእርሱ በኩል" ብሎ እንጀመረ ቢቀጥል ኖሮ "#ምልጃ!" እንለው ይሆናል "#ባንተ_በኩል" ካለና #ከመነሾውም ሙሐመድን የፀሎትና ልመና #ተደራሲ አድርጎ መምጣቱ ሙሐመድም ይህንን ሳያርም ጨምሮ ማበረታታቱ ይህ ሐዲዝ ሙሐመድም የልመናው ድልድይ ብቻም ሳይሆን #ከፈፃሚውም_አካል_ተርታ እንደሚሰለፍ ያሳያል። ስለዚ ፀሎት ወደ ሙሐመድ እንደሚደረግ ሌላ ማስረጃ ነው ማለት ነው
👉 እንግዲህ አንድ አካል ልመናን ተቀበለ ወይም ፀሎት ወደ እርሱ ተፀለየ ማለት ተመለከ ማለት ነው ብዬ እሞግታለሁ። ይህንም ለአብነት ያህል 📚በሱናን ኢብን ማጃህ ቅፅ 5 ሐዲዝ ቁጥር 3828 ላይ "...በእርግጥም ልመና(ፀሎት) አምልኮት ነው።" ብለው የአላህ መልእክተኛ ተናገሩ" ተብሎ ተዘግቧል። ይህንንም በዚሁ መፅሐፍ ገፅ 95-96 ላይ ተብራርቶ እናገኘዋለን።
እናም ሙሐመድ በአላህ አማኝ ሁሉ ክብርን #ይሰጠውና ሌት ቀን ያውጅለት ዘንድ ዘንድ ትእዛዝ ወጥቶለታል(48፥9)፤ አላህና መላእክቱ እራሱ #ሲሰግዱለት የአምልኮትም #መዐከል ሆኖ ሲቀርብ ይነበባል(33፥56)፤ የፀሎትም ተደራሽ በመሆን ከአምልኮት ሁሉ #የጠራውን_አምልኮት_ሲቀበል እንመለከታለን(3፥55፣ በጃሚ አት ተርሚዝ ቅፅ 6 ሐዲዝ ቁጥር 3578፣ በሱናን ኢብን ማጃህ ቅፅ 5 ሐዲዝ ቁጥር 3828 ወዘተ መሰረት)።
ስንቋጨው ይህና የመሳሰሉ ንባባትና ድርጊቶች ናቸው እንግዲ "ሰው ብቻ ነኝ" ያለውን 👳ሙሐመድን በዛው መፅሐፍ #አምላክ አድርገው የሚያቀርቡልን። በእስልምና ሙሐመድ ሰውም ብቻ ነኝ እያለ እየተመለከም ነው። #ሁለቱ_የመሐመድ_ማንነቶች እስቲ ደግሞ በቀጣይ መፅሕፍቱና መዛግብቱ ጨምረው ሙሐመድ እንዲህም እንዲያም ነው የሚሉንን እግዚአብሄር ቢፈቅድና ብንኖር እናያለን።
.................//................
" እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:32)
🙏አርነት በእውነት ይሆንላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው!🙏🙏🙏